ቀጥታ፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ያሻሻለበትን ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 33ኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ብሩክ አለማየሁ በስምንተኛው ደቂቃ ግቡን ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

በሊጉ 11ኛ ድሉን ያገኘው ቅዱስ ጊዮርጊስ በ43 ነጥብ ደረጃውን ከ14ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሃዋሳ ከተማ በ45 ነጥብ ከነበረበት አምስተኛ ደረጃ ወደ ስድስተኛ ዝቅ ብሏል።

ባለፉት 10 የሊግ ጨዋታዎች ከድል የራቀው ሃዋሳ ከተማ የውጤት ማጣት ቀውስ ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም