ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ማምሻውን በአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሩዋንዳዊው ፓትሪክ ሲቦማና በ16ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ጎል ኢትዮ ኤሌክትሪክ መሪ ሆኗል።

አስቻለው ታመነ በ63ኛው ደቂቃ በፍጹም ቅጣት ምት ድሬዳዋ ከተማን አቻ ያደረገውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ46 ነጥብ ከነበረበት ስድስተኛ ደረጃ ወደ አራተኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ድሬዳዋ ከተማ በ35 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሰባት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።

ዛሬ ቀን ላይ በተደረጉ የ33ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ኢትዮጵያ ቡና ፋሲል ከነማን 2 ለ 1 ሲረታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሃዋሳ ከተማን፣ መቀሌ 70 እንደርታ ሸገር ከተማን በተመሳሳይ 1 ለ 0 አሸንፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም