ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
በተለያዩ ሀገራት በኢ-መደበኛ ፍልሰት ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እየተደረገ ነው - አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
Aug 12, 2026 98
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በተለያዩ ሀገራት በኢ-መደበኛ ፍልሰት ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ገለጹ። የሳዑዲ ዓረቢያ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብትና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ቤተሰቦቻቸው የማቀላቀሉ ሥራ በተቀናጀ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል ጋር በመተባበር ከስደት ተመላሾችን መልሶ ማቋቋም የሚያስችል የድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል። በስምምነቱ ወቅትም ከሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል የተበረከቱ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች የድጋፍ ርክክብ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ ረጅም ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው። የሀገራቱ ታሪካዊ ግንኙነትም በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የትብብር መስኮች ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት እየተሸጋገረ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለአብነትም ከሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት ባሻገር በሕጋዊ የሥራ ስምሪትን በመከተል በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሙያ መስኮች በሳዑዲ ዓረቢያ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በኢ-መደበኛ ፍልሰት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ተጉዘው በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ ትብብር ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። የሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል ከስደት ተመላሽ ዜጎች ሰብዓዊ መብትና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ላበረከተው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። በማዕከሉ የተበረከተው የዕለት ደራሽና የማጓጓዣ ቁሳቁስ ድጋፍም የሀገራቱን የረጅም ዘመናት ወዳጅነትና ትብብር የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር አብዱላህ ሀሰን አልዛህራኒ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያና የሳዑዲ ዓረቢያ ታሪካዊ አጋርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። የተደረገው ድጋፍ ለኢትዮጵያውያን ስደት ተመላሾች ለሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚውል ሲሆን፣ የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ወዳጅነትና የሰብዓዊ ትብብር እሴት የሚያጎለብት መሆኑን ጠቅሰዋል። የሳዑዲ ዓረቢያ የኢ-መደበኛ ስደት ተመላሽ ጎራየ ጌትነት፤ በኢ-መደበኛ ስደት ያሳለፉትን አስከፊ ውጣ ውረድ አስታውሷል። የሳዑዲ ዓረቢያ የኢ-መደበኛ ስደት ተመላሽ ገብረ ሃዋሪያ ሐጎስ፤ ከነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ ሀገራቸው በመመለሳቸው የተደረገላቸውን አቀባበልና እንክብካቤ አመስግነዋል። የሳዑዲ ዓረቢያ የኢ-መደበኛ ስደት ተመላሽ ከማል መሐመድ፤ ያሳለፉትን አስቸጋሪ የሕይወት ውጣ ውረድ በማስታወስ በቀጣይ በሀገሬ ሰርቼ ለመለወጥ እተጋለሁ፤ ኢ-መደበኛ ስደትም አስከፊ ነው ብለዋል።  
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አቀፍ የጥናትና ምርምር አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ውጤት እያስገኘ ነው
Aug 12, 2026 133
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አቀፍ የጥናትና ምርምር አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ፕሬዝዳንት ተመስገን ደበሎ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂደዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተመስገን ደበሎ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው በሀገር በቀል እውቀቶች፣ በማዕድን፣ በግብርና፣ በእንስሳት ሀብትና በጤና ዘርፎች የጥናትና ምርምር ላይ ውጤታማ ሥራ እየሰራ ነው ብለዋል። የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አቀፍ የጥናትና ምርምር አገልግሎትም የበርካታ ዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እመርታዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን የምርምርና የልማት ሥራዎች ለህዝብ በተሻለ ሁኔታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትም የዩኒቨርሲቲውን ሥራዎች ለህዝብ በማስተዋወቅና የሀገርን ገጽታ በመገንባት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተፈራ በቀለ በበኩላቸው፣ ኢዜአ የህዝብን አንድነትና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያጎለብቱ የዜናና ዜና ነክ ተግባራትን ለህዝብ እያዳረሰ ይገኛል ብለዋል። የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አቀፍ የልማት ሥራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የማይተካ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። በዚህም የኢዜአን የተደራሽነት አድማስ የበለጠ በማጠናከር የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሚያፈልቃቸውን የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በቀጣይም የአካባቢውን እምቅ አቅሞችና ሀገር በቀል እውቀቶች ለማስተዋወቅ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የትብብር ስምምነት ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። በትብብር ስምምነት መሰረት ዩኒቨርሲቲው በምርምርና በሀገር በቀል እውቀቶች ዙሪያ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ለህዝብ በተሻለ ሁኔታ ለማድረስ ጠቃሚ መደላድል ይፈጥራል።
የምክክር ጉባኤው በዜጎቿ መካከል ሀገራዊ መግባባት የሰፈነባት ጠንካራ ኢትዮጵያን በመገንባት ታሪካዊ ድርሻ እንደሚኖረው እምነት አለን - ተመካካሪዎች
Aug 12, 2026 133
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በዜጎቿ መካከል ሀገራዊ መግባባት የሰፈነባት ጠንካራ ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ታሪካዊ ድርሻ እንደሚኖረው እምነት አለን ሲሉ ተመካካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ የሕዝብ ወኪሎችም በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ። በዚህ ታሪካዊ መድረክ የተሳተፉ ተመካካሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ምክክሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እኩል በማሳተፍ ሀገራዊ አንድነት በሚያጎለብት መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። ይህ የምክክር መድረክ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ አብሮነት እና ሕብረብሔራዊ አንድነትን እንደሚያጠናክር ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል። ከተመካካሪዎች መካከል ዳዊት ሙራ እንዳሉት፣ ምክክሩ በሀገሪቱ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ሂደቶች ውስጥ ሁሉም ዜጋ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ለማመቻቸት መሠረት እንደሚጥል አንስተዋል። ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶች እና ችግሮች በምክክር በመፍታት ለሀገራችን ብሩህ መጻኢ ዘመን ጠንካራ መሠረት የሚጣልበት ነው ብለዋል። ሌላኛዋ ተመካካሪ ለምለም ጎበና በበኩላቸው፣ የምክክር መድረኩ እያንዳንዱ ተመካካሪ ሐሳቡን በስፋትና በጥልቀት ማቅረብ በሚችልበት መልኩ መካሄዱ የሚደነቅ ነው ብለዋል። በምክክሩ የሚነሱ ሐሳቦች በሙሉ በተገቢው መንገድ የሚደመጡ በመሆኑ ለጋራ ሀገራዊ ግንባታ ጠንካራ ግብዓት ሆነው እንደሚያገለግሉ አንስተዋል። ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚገኙበት መድረክ መሆኑ ደግሞ የምክክሩን አካታችነት እና አሳታፊነት በግልጽ የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክሩ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነጻነት ሀሳቡን የሚያንሸራሽርበትና ድምፁ የሚሰማበትን እድል ፈጥሯል ያሉት ደግሞ ተመካካሪ ደፋለ መንሱር ናቸው። ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እርስ በእርስ የመደማመጥና የመከባበር ባህልን በማጠናከር፣ ታላቋን ኢትዮጵያ በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባትና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ እንደሚያስችል ተናግረዋል።            
የምክክር ጉባኤው የወጣቶችን ተስፋ የሚያለመልም የመግባባት ምክረ ሀሳብ የሚፈልቅበት የጋራ መድረክ እንደሚሆን እንጠብቃለን - የአዲስ አበባ ወጣቶች
Aug 12, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የወጣቶችን ተስፋ የሚያለመልም ሀገራዊ የመግባባት ምክረ ሀሳብ የሚፈልቅበት የጋራ መድረክ እንደሚሆን እንጠብቃለን ሲሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሰፊ ተሳትፎና በጥልቅ ምክክር መካሄዱን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልናና በምርጫ ሥርዓት፣ በሙስናና በመልካም አስተዳደር፣ በሃይማኖት ጉዳዮችና በሰላም ግንባታ ዙሪያ በተካሄዱ ምክክሮች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦች ላይ መግባባት መደረሱን ይፋ አድርጓል። ይህ ሂደት በተለይ ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ ተስፋን የሚያለመልም መሆኑን በአዲስ አበባ ኢዜአ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልጸዋል። እንደ ወጣቶቹ አስተያየት ምክክርና መደማመጥን የሚያስቀድሙ ሀገራዊ መድረክ ዘላቂ ሰላምን፣ ሀገራዊ መግባባትንና የጋራ የልማት ርዕይን ለመገንባት ጠንካራ መሠረት ይጥላል። የአዲስ አበባ ነዋሪዋ ወጣት ልዩወርቅ ሙሉጌታ እንደገለጸችው፤ ምክክርን በማስቀደም ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት ጥረቶች የወጣቱን ተስፋ የሚያለመልሙ ናቸው። ሀገር ስትመክር የተሻለች ኢትዮጵያን እንድናይ ያስችለናል ያለችው ወጣቷ፤ በምክክር የምትገነባ ሀገርም የዜጎቿን ዕድገትና ብልፅግና ለማሳለጥ ጠንካራ መደላድል መፍጠር እንደምትችል ገልጻለች። የምክክር ጉባኤው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት፣ በሰላም ግንባታና በልማት ሂደት ያላቸውን ተሳትፎ በማጠናከር ለቀጣዩ ትውልድ ተስፋ የሚሰጥ የጋራ መድረክ መሆኑንም ተናግራለች። ከጉባኤው የሚፈልቁ የጋራ መግባባት ምክረ ሀሳቦችም ሰላምና አንድነቷን ጠብቃ ወደ ዘላቂ ዕድገትና ብልፅግና የምትራመድ ኢትዮጵያን ለመገንባት አጋዥ ሚና እንደሚኖራቸው ሀሳቧን አንስታለች። ሌላው የመዲናዋ ወጣት ንጉሥ አይጋበዝ በበኩሉ፤ የምክክር ጉባኤው ቀጣዩ ትውልድ መደማመጥንና ምክክርን የአስተሳሰብና የኑሮ ባህል እንዲያደርግ ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን ተናግሯል። በሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች መካከል የሚፈጠረው መግባባትና የሚቀርቡት ምክረ ሀሳቦችም በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም በመገንባት ሰላምን፣ አንድነትንና የጋራ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስከበር ወሳኝ አበርክቶ እንደሚኖራቸው ገልጿል። ሀገራዊ መግባባትን በመገንባት የወጣቶችን በሀሳብ የበላይነት፣ በሰላም የተመሠረተና የብልፅግና ርዕይ ያለው ሀገር መሻት ምላሽ ለመስጠት ጉባኤው ጠቃሚ መሆኑን ደግሞ ነብያት ስብሀቱ ተናግራለች። ኢትዮጵያ እየመከረች ነው ያለችው ወጣቷ፤ የጉባኤውን ሂደትም በሚገባ በመከታተል የጋራ መግባባት ውጤቶችን በጉጉት እየተጠባበቀች መሆኑን ገልጻለች። ሌላኛው የአዲስ አበባ ወጣት አብነት ንጉሴ በበኩሉ፤ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የትውልድን የመመካከርና የመደማመጥ የአስተሳሰብ ባህል የሚያጎለብት የጋራ መድረክ ነው ብሏል። በመደማመጥና በመመካከር ለዘመናት የቆዩ አለመግባባቶችንና ቁርሾዎችን በሰለጠነና ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጉባኤው የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል።
የአፍሪካ አቪዬሽን አርማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋማዊ ልህቀት በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዓይን
Aug 12, 2026 137
በሙሴ መለሰ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የአንድን ሀገር ኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ የቱሪዝም ዕድገት እና የጂኦፖለቲካዊ ተፅዕኖ የመወሰን ከፍተኛ አቅም ያለው ስትራቴጂካዊ ዘርፍ ነው። በአፍሪካ አህጉር በርካታ ሀገራት ብሔራዊ አየር መንገዶቻቸውን በትክክለኛ የንግድ መስመርና ጠንካራ ተቋማዊ መዋቅር ለመገንባት በሚታገሉበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሳየው ዘላቂ ዕድገትና ስኬት በመላው ዓለም ትልቅ አድናቆትንና ትኩረትን የሳበ አጋጣሚ ሆኗል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሠረተበትን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት፣ ከትራንስፖርት ተቋም ከመሆን አልፎ የአፍሪካ አቪዬሽን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መሪ በመሆን ቁልፍ ሚናውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ተቋሙ በተከተለው የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ፣ በሙያዊ አስተዳደር እና ባደራጀው ዘመናዊ የአቪዬሽን ማዕከል አማካኝነት ሀገሪቱን የአህጉሪቱ ዋነኛ አገናኝ ድልድይ እና የትራንዚት መዳረሻ ሆኗል። ይህን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የላቀ ደረጃ የበለጠ ለማጠናከር እና የወደፊቱን የዓለም አቪዬሽን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት፣ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ግዙፍ መሠረተ ልማት ነው። ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ሜጋ ኤርፖርት፣ የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድን የጭነትና የመንገደኞች ጫና በመቀነስ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ አልሞ የተነሳ ነው። ይህም ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ግዙፉ የአቪዬሽን ማዕከል በመሆን የቀጣናውን የቱሪዝም፣ የንግድና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያነቃቃው ይጠበቃል። ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በሰሞኑ ዘገባቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስኬት እና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ላይ ትኩረታቸውን አድርገዋል። የዩናይትድ ኪንግደሙ ዕለታዊ ጋዜጣ ዴይሊ ኤክስፕረስ (Daily Express) በዘገባው እንደጠቀሰው፣ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በዓለም አቀፉ የዛሃ ሀዲድ አርክቴክቶች ዲዛይን የተደረገ ግዙፍ ፕሮጀክት እንደሆነ አመልክቷል። አየር ማረፊያው እ.አ.አ. በ2030 በሚጠናቀቀው የመጀመሪያው ምዕራፍ 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ይህም በዓመት 28 ሚሊዮን የሚያስተናግደውን የደቡብ አፍሪካውን ኦሊቨር ታምቦ እና 26 ሚሊዮን የሚያስተናግደውን የግብፁን ካይሮ ኤርፖርቶች በከፍተኛ ልዩነት በመብለጥ በአህጉሪቱ የመሪነቱን ቦታ እንደሚይዝ ገልጿል። ፕሮጀክቱ አራት የመሬት ላይ የአውሮፕላን መነሻና ማረፊያ መንገዶችን፣ የ38 ኪሎ ሜትር ፈጣን የባቡር መስመር፣ የሆቴልና የንግድ ማዕከላትን ያካተተ በመሆኑ፣ የዓለም ኃያላን አገራትን፣ አሜሪካንና ቻይናን ጨምሮ፣ የዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችን ትኩረት መሳቡን ዘገባው አመልክቷል። ሌላኛው የዩናይትድ ኪንግደም ዕለታዊ ጋዜጣ ዴይሊ ሚረር (Daily Mirror) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬት በኤርፖርት መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ በተቋማዊ የአመራር ዘዴው ለአህጉሪቱና ለሌሎች ሀገራት ትልቅ ተሞክሮ እንደሆነ ገልጿል። ዲፕሎማት ካና ካናናታን በጋዜጣው ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ፣ አየር መንገዱ በመንግሥት ሥር ሆኖ ሳለ እ.አ.አ. በ2025/26 በጀት ዓመት 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱ፣ 20.7 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙ እና በ174 አውሮፕላኖች ወደ 150 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች መብረሩ “የመንግሥት ባለቤትነት የኪሳራ መንስኤ ነው” የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት ያፈረሰ መሆኑን አመልክቷል። እንደ ስሪላንካ ያሉ ሀገራት በየዓመቱ ብሔራዊ አየር መንገዶቻቸውን ከመንግሥት ግምጃ ቤት ለመደጎም ሲታገሉ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ የንግድ ስትራቴጂ መመራቱ የስኬቱ ምሥጢር መሆኑ ተመላክቷል። የኢትዮጵያ የአቪዬሽን አመራር ልህቀት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያደገ መምጣቱ በጽሑፉ ላይ ሰፍሯል። በተመሳሳይ መልኩ ዘ ኢስት አፍሪካን (The East African) ላይ በቻርልስ ኦንያንጎ-ኦቦ የቀረበው ጽሑፍ እንደሚያስረዳው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበላይነት የመጣው በጠንካራ የቴክኒክ ሥልጠና፣ በአውሮፕላን ጥገና ልህቀት፣ በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ፣ በተቋማዊ አሠራር እና በጠንካራ ዲሲፕሊን የሚመራ በመሆኑ ነው። አየር መንገዱ የራሱን ስኬት ከማስመዝገብ ባለፈ፣ የቀድሞና የአሁኑ አመራሮቹን እንደ ASKY፣ Malawi Airlines፣ Air Congo፣ Zambia Airways፣ Uganda Airlines እና RwandAir ባሉ በርካታ የአፍሪካ አየር መንገዶች ውስጥ በቁልፍ የካፒቴንነትና የአመራር ቦታዎች ላይ በመመደብ የመላው አፍሪካ አቪዬሽን አቅም እንዲገነባ መሠረት መሆኑን ጽሑፉ አመልክቷል። ታይምስ ኩዌት (The Times Kuwait) ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እ.አ.አ. 1945 የተመሠረተው ይህ አየር መንገድ የ80 ዓመታት የልህቀት ጉዞውን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት በስካይትራክስ (SKYTRAX) ዘንድ ለስምንት ተከታታይ ዓመታት “የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ” በመባል መመረጡን ገልጿል። አየር መንገዱ አዲስ አበባን የትራንዚት ማዕከል በማድረግ መንገደኞች በቆይታቸው እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ ወንጪ ሐይቅ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ላሊበላን እና የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ ሌሎች የመስብ ቦታዎችን እንዲጎበኙ በማስቻል የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ እያነቃቃ እንደሚገኝ ጠቅሷል። በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬት የአንድ ሀገር ተቋም ጥንካሬ ማሳያ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ በሙያዊ አመራርና በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ከተመራ ምን ያህል ስኬታማ መሆን እንደሚችል ያሳየ ትልቅ ተሞክሮ ነው። በቢሾፍቱ እየተገነባ የሚገኘው አየር ማረፊያ ሲጠናቀቅ የመንገደኞችን የማስተናገድ ጫና በመቀነስ፣ የአህጉሪቱን የንግድ፣ የሎጂስቲክስና የቱሪዝም ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል። ይህ የራዕይና የተቋማዊ ጥንካሬ ቅንጅት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ካርታ ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ይበልጥ የሚያጠናክረው ይሆናል።
የሚታይ
በምክክሩ ኢትዮጵያን የሚገነቡ ጠንካራ ሀሳቦች እየተንጸባረቁ ነው- ተመካካሪዎች
Aug 12, 2026 217
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ) ፦በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያን የሚገነቡ እና ወደፊት የሚያራምዱ ጠንካራ ሀሳቦች እየተንጸባረቁ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ። ዋናው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ይገኛል። በምክክሩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የወከሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ይገኛሉ። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ለዘመናት ለዘለቁ አለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሔ በማበጀት ሰላም እና መግባባት የሰፈነባትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ መሠረት እንደሚጥል ይታመናል። በመድረኩ የተሳተፉ ተመካካሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፣ ይህ ስልጡን አካሄድ ኢትዮጵያውያንን ይበልጥ በማቀራረብ ጠንካራ የዴሞክራሲ እና የምክክር ባህልን እንደሚያጎለብት ተናግረዋል። የ6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባል መብራቱ ዓለሙ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በምክክሩ ኢትዮጵያን ወደፊት የሚያራምዱ እና የቆዩ ችግሮቻችንን ሊፈቱ የሚችሉ ምክረ ሀሳቦች እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ምክክሩ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ እና እንደ ሀገር የሚያስማሙንን ጉዳዮች የጋራ እያደረግን ለመቀጠል ትልቅ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በሂደቱ ተሳታፊ መሆናቸው ሀገራዊ የፖለቲካ ባህላችን ምክክርን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑን ገልጸዋል። የታሪክና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንዲሁም ተመካካሪው አልአዛር ዓባይነህ በበኩላቸው፤ ለዘመናት በዘለቁ አለመግባባቶች ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ስትፈተን መቆየቷን አስታውሰው፤ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከምክክር ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ገልጸዋል።   የምክክር ጉባኤው በሀገራዊ መግባባት የጸናች ኢትዮጵያን ለመገንባትና ለመጪው ትውልድ ብሩህ መሠረት ለመጣል ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑንም ጠቁመዋል። በምክክሩ ለሀገር የሚጠቅም ሐሳብ በማበርከት የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ አካል በመሆናቸው ኩራት እንደሚሰማቸውም ገልጸዋል። ይህ ወቅት በሀገሬ ያለኝ ተስፋ እጅግ የለመለመበት ወቅት ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛው ተመካካሪ እና የሕግ ባለሙያ ወንድሙ ግዛው ናቸው።   ፍትሕ እና እኩልነት የሰፈነባትን የተሻለች ኢትዮጵያ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም ተመካካሪ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን መመልከታቸውንም አንስተዋል።    
ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርንና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በማፋጠን ለአፍሪካ የጋራ ብልፅግና ጠንካራ መሠረት እየጣለች ነው - አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ
Aug 12, 2026 331
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርንና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በማፋጠን ለአፍሪካ የጋራ ብልፅግና ጠንካራ መሠረት እየጣለች መሆኗን በኢትዮጵያ የዛምቢያ አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ ገለጹ። ዛምቢያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ የንግድ፣ ኢንቨስትመንትና ብዝኅ ዘርፍ የዲፕሎማሲ ትብብር በአዳዲስ መስኮች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗንም አረጋግጠዋል። አምባሳደር አልበርት ሙቻንጋ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በዛምቢያና በኢትዮጵያ መካከል ያለው የዲፕሎማሲ ወዳጅነት በንግድና የኢንቨስትመንት ትብብር ዘርፍ እየተጠናከረ ነው። ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትስስርንና አህጉራዊ የኢኮኖሚ ውህደትን በማፋጠን በአርአያነት የሚጠቀስና ለአፍሪካ የጋራ ብልፅግና አስደናቂና ጠንካራ መሠረት እየጣለች መሆኗንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናዊ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ በመሠረተ ልማት ትስስር፣ በንግድና ኢንቨስትመንት የትብብር መስኮች የፈጠረችው የልማት አቅም ተምሳሌታዊ መሆኑን አብራርተዋል። በኢትዮጵያና ዛምቢያ መካከል የተቋቋመው የጋራ ትብብር ኮሚሽንም ቀጣይ ስብሰባውን በኢትዮጵያ በማካሄድ የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያስገኙ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር እንደሚሰራ ጠቅሰዋል። ስብሰባውም በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች እየተካሄዱ ያሉ የትብብር ሥራዎችን ለመገምገምና ወደፊት የሚወሰዱ አዳዲስ የትብብር አቅጣጫዎችን ለመወሰን ወሳኝ እንደሚሆን አመልክተዋል። በተለይም በንግድ፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ሥልጠናና በአቪዬሽን ዘርፍ የትብብር ዕድሎችን በመለየት የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ተጨባጭ የጋራ ጥቅም ለመቀየር የሚያስችል ዕቅድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ጠቁመዋል። ዛምቢያና ኢትዮጵያ በምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ከሁለቱ ሀገራት ጥቅም ባሻገር የአፍሪካን የጋራ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ለማጠናከር እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የኢትዮጵያና ዛምቢያ ግንኙነት ከታሪካዊ የዲፕሎማሲ ትብብር የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያጎለብት ሁለንተናዊ አጋርነት እየተሸጋገረ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የደን መልሶ ማልማትን በማጠናከር ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታና ለዘላቂ ልማት በቁርጠኝነት እየሠራች መሆኗን አስረድተዋል። አረንጓዴ ዐሻራ በደን፣ በውሃና በአካባቢ ጥበቃን የሚያጠናክር የሥነ-ምህዳር ደኅንነት ሚዛንን ለማስጠበቅ ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ የደን ሽፋንን በማሳደግ እያስመዘገበች የምትገኘው የልማት ስኬትም ወሰን ተሻጋሪ ዓለም አቀፍ የልማት ግብ መሆኑን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በትክክለኛ የዕድገት አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰች ነው ያሉት አምባሳደር ሙቻንጋ፤ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት ግንባታ እመርታዎቿም ለሌሎች የዓለም ሀገራት ጭምር አርአያ ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ በአህጉራዊ ትስስርና በአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የመሪነት ሚና እየተወጣች መሆኑን ጠቁመዋል። በዚህም በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና በምሥራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) በንቃት እየተሳተፈች እንደምትገኝም አንስተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ማዕቀፍ የንግድ ልውውጥን ለማቀላጠፍ እየሠራች መሆኑንም አስረድተዋል።    
የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ የለውጥ ዋነኛ ሞተር ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Aug 12, 2026 247
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለፁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዓለም አቀፍ ወጣቶች ቀንን በማስመልከት በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም ብለዋል። የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው ሲሉም አክለዋል። ‎የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወጣቱ የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል ብለዋል። የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። ‎‎ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ሲሉም ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም መሸፈን የሚያስችል አቅም ገንብቷል
Aug 11, 2026 421
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አደረጃጀትና አቅም መገንባቱን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ገለፀ። የቋሚ ኮሚቴው አባላት የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ጎብኝተዋል፡፡   ቋሚ ኮሚቴው ባለፉት አምስት ዓመታት ኮሚሽኑ የተሰጠውን ኃላፊነት እንዲወጣ ላደረገው ድጋፍና ክትትል የምስጋና መርሃ-ግብር ተካሂዷል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኮሚሽኑ ባለፉት አምስት ዓመታት በርካታ ለውጦችን አስመዝግቧል። የኮሚሽኑን ሪፖርት ከመገምገም ባለፈም ቋሚ ኮሚቴው የመስክ ምልከታ በማድረግ ያልተቋረጠ ድጋፍና ክትትል ሲያደርግ መቆየቱን ተናግረዋል። የአደጋ ስጋት አመራር ፖሊሲን ከመከለስ ባለፈ የአዋጅ ማሻሻያ መደረጉን አንስተው፤ የተለያዩ ደንቦችም ተዘጋጅተዋል ብለዋል፡፡   ዜጎች ከተረጂነት አስተሳሰብ ተላቀው ወደ አምራችነት እንዲሸጋገሩ የሚያስችሉ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑን በአዳዲስ አሰራሮችና በአዋጅ እንዲደራጅ በማድረግ በኢትዮጵያ ሊደርስ የሚችልን አደጋ አስቀድሞ መከላከልና ሲደርስ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም እንዲገነባ ተደርጓል ብለዋል፡፡   የቋሚ ኮሚቴው አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ራዕዩን ማሳካት የሚያስችሉ ተስፋ ሰጭ ጥረቶችን እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ኮሚሽኑ ራስን በምግብ በመቻል የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት አከናውኗል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኮሚሽኑ ባለፉት አምስት ዓመታት ተጨባጭ ለውጦችን ማስመዝገቡን ገልጸዋል፡፡ ከለውጡ በኋላ በአዳዲስ አሰራሮችና ህጎችን በማሻሻል ሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን በራስ አቅም ማረጋገጥ የሚያስችል ውጤት አምጥቷል ብለዋል፡፡
የጋራ መግባባትን ለማጠናከር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የታሪክ ድልድይ - ሀገራዊ ምክክር
Aug 11, 2026 454
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ) ፦ በመካሄድ ላይ ያለው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የጋራ መግባባትን ለማጠናከር እና የተሻለች ሀገርን ለመገንባት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት የታሪክ ድልድይ ነው። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ 4 ሺህ የሕዝብ ወኪሎችም በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ። የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በስፋት የተሳተፉበት ይህ መድረክ፤ የዜጎችን ሀሳብ በማቀናጀት የሀገሪቱን ዘላቂ ሰላም፣ አብሮነት እና የጋራ መግባባትን ለማጠናከር ትልቅ ተስፋ የተጣለበት ወሳኝ ምዕራፍም ነው። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ተመካካሪዎች እንደሚሉት፤ ምክክሩ የጋራ መግባባትን በማጎልበት ልዩነቶችን በሰላማዊ ውይይት ለመፍታት ሰፊ ዕድል ከፍቷል። የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የፕሬዝደንት ጽህፈት ቤት ሀላፊ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ሀገራዊ ምክክሩ ትልቅ የሆነ ታሪካዊ ማካፈያ ስርዓት ነው ብለዋል። ምክክሩ በኢትዮጵያ ቀደም ሲል መግባባት ባልተደረሰባቸው ጉዳዮች ላይ በመምከር ወደ መፍትሄ ለመቅረብ የሚያስችል ትልቅ ስርአት ነው ብለዋል። ይህ ታላቅ ሁነት ባሳለፍነው የጦርነት ታሪክና አለመግባባትን በምክክር በመፍታት ሰላሟ የተረጋገጠና የልማት ጎዳና ላይ ባለችው ኢትዮጵያ መሃከል ያለ ልዩ የታሪክ ድልድይ ነው ብለዋል። ምክክሩ ከተለያየ አስተሳሰብ እና የአኗኗር ዘዬ የመጣውን ማህበረሰብ እርስ በእርስ የመተዋወቅ እድልን አስፍቷል ብለዋል።   ሌላኛዋ ተመካካሪ ሜሪ ደስታ በበኩላቸው፤ በምክክሩ ተመካካሪዎች ሀሳባቸውን በነፃነት ለመግለጽ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ገልጸው፤ የሀሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም በሚያግባቡን ጉዳዩች ላይ በማተኮር እየተመካከርን ነው ብለዋል። ምክክሩ ለትውልዱ አንድነቷ የተጠናከረና የበለጸገች ሀገር የምናሻግርበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲሉም ተናግረዋል።   ምክክሩ ከአጀንዳ አሰባሰብ ጀምሮ አሁን እስካለበት ሂደት ድረስ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍሎች አካታችና አሳታፊ ያደረገ እንደነበር የገለጹት ደግሞ ሌላኛው ተመካካሪ አብርሀም ሀይሌ ናቸው።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የምክክር ጉባኤው በዜጎቿ መካከል ሀገራዊ መግባባት የሰፈነባት ጠንካራ ኢትዮጵያን በመገንባት ታሪካዊ ድርሻ እንደሚኖረው እምነት አለን - ተመካካሪዎች
Aug 12, 2026 133
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በዜጎቿ መካከል ሀገራዊ መግባባት የሰፈነባት ጠንካራ ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ታሪካዊ ድርሻ እንደሚኖረው እምነት አለን ሲሉ ተመካካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ የሕዝብ ወኪሎችም በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ። በዚህ ታሪካዊ መድረክ የተሳተፉ ተመካካሪዎች ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ሀገራዊ ምክክሩ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን እኩል በማሳተፍ ሀገራዊ አንድነት በሚያጎለብት መልኩ እየተካሄደ ይገኛል። ይህ የምክክር መድረክ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ አብሮነት እና ሕብረብሔራዊ አንድነትን እንደሚያጠናክር ያላቸውን ጽኑ እምነት ገልጸዋል። ከተመካካሪዎች መካከል ዳዊት ሙራ እንዳሉት፣ ምክክሩ በሀገሪቱ ማኅበራዊ፣ ምጣኔ ሀብታዊ እና ፖለቲካዊ ሂደቶች ውስጥ ሁሉም ዜጋ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚሆንበትን መንገድ ለማመቻቸት መሠረት እንደሚጥል አንስተዋል። ለዘመናት የዘለቁ አለመግባባቶች እና ችግሮች በምክክር በመፍታት ለሀገራችን ብሩህ መጻኢ ዘመን ጠንካራ መሠረት የሚጣልበት ነው ብለዋል። ሌላኛዋ ተመካካሪ ለምለም ጎበና በበኩላቸው፣ የምክክር መድረኩ እያንዳንዱ ተመካካሪ ሐሳቡን በስፋትና በጥልቀት ማቅረብ በሚችልበት መልኩ መካሄዱ የሚደነቅ ነው ብለዋል። በምክክሩ የሚነሱ ሐሳቦች በሙሉ በተገቢው መንገድ የሚደመጡ በመሆኑ ለጋራ ሀገራዊ ግንባታ ጠንካራ ግብዓት ሆነው እንደሚያገለግሉ አንስተዋል። ሴቶች፣ ወጣቶች፣ አካል ጉዳተኞች እና ሌሎችም የኅብረተሰብ ክፍሎች የሚገኙበት መድረክ መሆኑ ደግሞ የምክክሩን አካታችነት እና አሳታፊነት በግልጽ የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክሩ የሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነጻነት ሀሳቡን የሚያንሸራሽርበትና ድምፁ የሚሰማበትን እድል ፈጥሯል ያሉት ደግሞ ተመካካሪ ደፋለ መንሱር ናቸው። ይህ ሀገራዊ የምክክር መድረክ እርስ በእርስ የመደማመጥና የመከባበር ባህልን በማጠናከር፣ ታላቋን ኢትዮጵያ በጠንካራ መሰረት ላይ ለመገንባትና ለቀጣይ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ እንደሚያስችል ተናግረዋል።            
የምክክር ጉባኤው የወጣቶችን ተስፋ የሚያለመልም የመግባባት ምክረ ሀሳብ የሚፈልቅበት የጋራ መድረክ እንደሚሆን እንጠብቃለን - የአዲስ አበባ ወጣቶች
Aug 12, 2026 122
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የወጣቶችን ተስፋ የሚያለመልም ሀገራዊ የመግባባት ምክረ ሀሳብ የሚፈልቅበት የጋራ መድረክ እንደሚሆን እንጠብቃለን ሲሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በሰፊ ተሳትፎና በጥልቅ ምክክር መካሄዱን ቀጥሏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽንም በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልናና በምርጫ ሥርዓት፣ በሙስናና በመልካም አስተዳደር፣ በሃይማኖት ጉዳዮችና በሰላም ግንባታ ዙሪያ በተካሄዱ ምክክሮች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦች ላይ መግባባት መደረሱን ይፋ አድርጓል። ይህ ሂደት በተለይ ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ ተስፋን የሚያለመልም መሆኑን በአዲስ አበባ ኢዜአ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ገልጸዋል። እንደ ወጣቶቹ አስተያየት ምክክርና መደማመጥን የሚያስቀድሙ ሀገራዊ መድረክ ዘላቂ ሰላምን፣ ሀገራዊ መግባባትንና የጋራ የልማት ርዕይን ለመገንባት ጠንካራ መሠረት ይጥላል። የአዲስ አበባ ነዋሪዋ ወጣት ልዩወርቅ ሙሉጌታ እንደገለጸችው፤ ምክክርን በማስቀደም ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚደረጉ ማንኛውም ዓይነት ጥረቶች የወጣቱን ተስፋ የሚያለመልሙ ናቸው። ሀገር ስትመክር የተሻለች ኢትዮጵያን እንድናይ ያስችለናል ያለችው ወጣቷ፤ በምክክር የምትገነባ ሀገርም የዜጎቿን ዕድገትና ብልፅግና ለማሳለጥ ጠንካራ መደላድል መፍጠር እንደምትችል ገልጻለች። የምክክር ጉባኤው የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት፣ በሰላም ግንባታና በልማት ሂደት ያላቸውን ተሳትፎ በማጠናከር ለቀጣዩ ትውልድ ተስፋ የሚሰጥ የጋራ መድረክ መሆኑንም ተናግራለች። ከጉባኤው የሚፈልቁ የጋራ መግባባት ምክረ ሀሳቦችም ሰላምና አንድነቷን ጠብቃ ወደ ዘላቂ ዕድገትና ብልፅግና የምትራመድ ኢትዮጵያን ለመገንባት አጋዥ ሚና እንደሚኖራቸው ሀሳቧን አንስታለች። ሌላው የመዲናዋ ወጣት ንጉሥ አይጋበዝ በበኩሉ፤ የምክክር ጉባኤው ቀጣዩ ትውልድ መደማመጥንና ምክክርን የአስተሳሰብና የኑሮ ባህል እንዲያደርግ ትልቅ መሠረት የሚጥል መሆኑን ተናግሯል። በሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች መካከል የሚፈጠረው መግባባትና የሚቀርቡት ምክረ ሀሳቦችም በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ አቋም በመገንባት ሰላምን፣ አንድነትንና የጋራ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስከበር ወሳኝ አበርክቶ እንደሚኖራቸው ገልጿል። ሀገራዊ መግባባትን በመገንባት የወጣቶችን በሀሳብ የበላይነት፣ በሰላም የተመሠረተና የብልፅግና ርዕይ ያለው ሀገር መሻት ምላሽ ለመስጠት ጉባኤው ጠቃሚ መሆኑን ደግሞ ነብያት ስብሀቱ ተናግራለች። ኢትዮጵያ እየመከረች ነው ያለችው ወጣቷ፤ የጉባኤውን ሂደትም በሚገባ በመከታተል የጋራ መግባባት ውጤቶችን በጉጉት እየተጠባበቀች መሆኑን ገልጻለች። ሌላኛው የአዲስ አበባ ወጣት አብነት ንጉሴ በበኩሉ፤ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የትውልድን የመመካከርና የመደማመጥ የአስተሳሰብ ባህል የሚያጎለብት የጋራ መድረክ ነው ብሏል። በመደማመጥና በመመካከር ለዘመናት የቆዩ አለመግባባቶችንና ቁርሾዎችን በሰለጠነና ሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ጉባኤው የሚያበረክተው ሚና ከፍተኛ መሆኑንም ገልጿል።
ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል እንዲዳብር መሠረት ይጥላል
Aug 12, 2026 164
ወላይታ ሶዶ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፡-ሀገራዊ ምክክሩ ለቆዩ አለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሄ ከመስጠት ባለፈ ችግሮችን በውይይት የመፍታት ባህል እንዲዳብር መሰረት ይጥላል ሲሉ የወላይታ ዞን የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ለዘመናት የዘለቁ ችግሮችን በመፍታት ሀገራዊ አንድነትን እንደሚያጠናክር የታመነበት ሀገራዊ ምክክር የተለያዩ ሂደቶችን አልፎ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ የማጠቃለያ ጉባኤ በመካሄድ ላይ ነው። ምክክሩ ሰላምና ልማትን በዘላቂነት በማስፈን ለሁሉም የምትመች ሀገር በመገንባት ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ ምክክሩን አስመልክቶ ኢዜአ በወላይታ ዞን ያነጋገራቸው የሀገር ሽማግሌዎች እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያዊያን ከጥንት ጀምሮ የነበራቸውን የመመካከርና አብሮ የመኖር እሴት በማስቀጠል ልዩነቶችን በዘላቂነት ለመፍታት ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ከሀገር ሽማግሌዎች መካከል አቶ ጌታቸው መና፤ ምክክሩ እኔ አውቅልሃለሁ እሳቤን አስቀርቶ በተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች ያሉ ዜጎችን በማካተት መካሄዱ ለኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ትልቅ ዕድል መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያውያን መካከል ለዘመናት መተማመንን ያሳጡ አለመግባባቶችና ቁርሾዎችን በመፍታት ሀገራዊ አንድነትን የማጠናከር አቅሙ የጎላ በመሆኑ ለትውልድ የተሻለች ሀገር መፍጠር ያስችላል ብለዋል። በሀገሪቱ ለቅራኔ ምንጭ የነበሩ የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከማስቻሉ ባለፈ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት ባህል እንዲዳብር መሰረት ይጥላል ብለዋል። በተለያዩ ምክንያቶች እየተሸረሸረ የመጣው አብሮነትና የሰላም እጦት ችግርን በዘላቂነት ለመፍታት ሁሉን ያሳተፈ ምክክር ማድረግ ሚናው የጎላ ነው ያሉት ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የሀገር ሽማግሌ አቶ ኢያሱ ጋጃቦ ናቸው። ወደማጠቃለያ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክርም ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሆነ ገልጸው፣ በጉባኤው ውይይት እየተደረገባቸው ያሉ ስምንት አጀንዳዎች የህዝብ ሀሳቦች መሆናቸውን ተናግረዋል። በአጀንዳዎቹ ላይ ከተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ተመካካሪዎች ጥልቅ ውይይቶችን በማድረግ በቀጣይ ለሀገርና ለህዝብ ይጠቅማል የሚል ምክረ ሀሳቦችን ያስቀምጣሉ የሚል ጽኑ እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል። ተወካዮቻቸውም በምክክሩ በመሳተፍ ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረው፣ በጋራ መክሮ የሚሰራ ሥራ ውጤቱ ይሰምራል ብለዋል። የዘመናት ችግሮች በውይይት እንዲፈቱ በሀገራዊ ምክክር እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ለሀገር ሰላምን ከማጽናት ባለፈ ከሀይል ይልቅ ችግሮችን በውይይት መፍታትን ባህሉ ያደረገ ትውልድ ለመፍጠር ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል "ሁላችንም ከኢትዮጵያ ውጭ ሌላ ሀገር የለንም" ያሉት አቶ ኢያሱ ምክክር ስር የሰደዱ ችግሮቻችንን በመፍታት ለሁላችንም የምትመች ሀገር ለመገንባት ስለሚያስችል ይህን ታሪካዊ እድል ልንጠቀምበት ይገባል ብለዋል። አቶ ፒኖ ማኖ የተባሉ ሌላኛው ሀገር ሽማግሌ በበኩላቸው አለመግባባቶችን ለመፍታት ጠረጴዛ ዙሪያ መሰባሰብ የመመካከር ባህልን የሚያሳድግና የተሻለች ሀገር ለትውልድ ለማቆየት ያስችላል፡፡ በሀገራዊ ምክክሩ ሁሉም በወኪሎቹ አማካይነት እየተሳተፈ መሆኑን ገልጸው፣ ይህም ለዘመናት ላለመተማመንና ለልዩነት ምንጭ በሆኑ ችግሮች ላይ በጋራ መክሮ መፍትሄ ለመስጠት ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል። ጠንካራ ሀገራዊ መግባባት ለመፍጠርና ቂምና ቁርሾዎችን በማስቀረት አንድነቷ የጸና ሀገር ለመገንባት ወሳኝ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ የምክክር ሂደቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክተው በሰጡት መግለጫ የምክክር ሂደቱ እየተጠናከረና ወደ ማጠቃለያ ምዕራፍ እየተሸጋገረ እንደሚገኝ መናገራቸው ይታወሳል።
በምክክሩ ኢትዮጵያን የሚገነቡ ጠንካራ ሀሳቦች እየተንጸባረቁ ነው- ተመካካሪዎች
Aug 12, 2026 217
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ) ፦በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ኢትዮጵያን የሚገነቡ እና ወደፊት የሚያራምዱ ጠንካራ ሀሳቦች እየተንጸባረቁ መሆኑን ተመካካሪዎች ገለጹ። ዋናው የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ በሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል በመካሄድ ላይ ይገኛል። በምክክሩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የወከሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ እየመከሩ ይገኛሉ። ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው ለዘመናት ለዘለቁ አለመግባባቶች ዘላቂ መፍትሔ በማበጀት ሰላም እና መግባባት የሰፈነባትን ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ መሠረት እንደሚጥል ይታመናል። በመድረኩ የተሳተፉ ተመካካሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፣ ይህ ስልጡን አካሄድ ኢትዮጵያውያንን ይበልጥ በማቀራረብ ጠንካራ የዴሞክራሲ እና የምክክር ባህልን እንደሚያጎለብት ተናግረዋል። የ6ኛው ዙር የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል እና የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አማካሪ ኮሚቴ አባል መብራቱ ዓለሙ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በምክክሩ ኢትዮጵያን ወደፊት የሚያራምዱ እና የቆዩ ችግሮቻችንን ሊፈቱ የሚችሉ ምክረ ሀሳቦች እየተንጸባረቁ ይገኛሉ። ምክክሩ የተሻለች ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ ለማስረከብ እና እንደ ሀገር የሚያስማሙንን ጉዳዮች የጋራ እያደረግን ለመቀጠል ትልቅ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በሂደቱ ተሳታፊ መሆናቸው ሀገራዊ የፖለቲካ ባህላችን ምክክርን መሠረት ያደረገ እንዲሆን ትልቅ ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑን ገልጸዋል። የታሪክና የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንዲሁም ተመካካሪው አልአዛር ዓባይነህ በበኩላቸው፤ ለዘመናት በዘለቁ አለመግባባቶች ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ስትፈተን መቆየቷን አስታውሰው፤ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከምክክር ውጭ ሌላ አማራጭ እንደሌለ ገልጸዋል።   የምክክር ጉባኤው በሀገራዊ መግባባት የጸናች ኢትዮጵያን ለመገንባትና ለመጪው ትውልድ ብሩህ መሠረት ለመጣል ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑንም ጠቁመዋል። በምክክሩ ለሀገር የሚጠቅም ሐሳብ በማበርከት የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ አካል በመሆናቸው ኩራት እንደሚሰማቸውም ገልጸዋል። ይህ ወቅት በሀገሬ ያለኝ ተስፋ እጅግ የለመለመበት ወቅት ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛው ተመካካሪ እና የሕግ ባለሙያ ወንድሙ ግዛው ናቸው።   ፍትሕ እና እኩልነት የሰፈነባትን የተሻለች ኢትዮጵያ ለትውልድ ለማስተላለፍ ሁሉም ተመካካሪ ሀገራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑን መመልከታቸውንም አንስተዋል።    
የምክክር ጉባኤው በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ መግባባትን በመገንባት የጋራ አሸናፊነትን የሚያቀዳጅ አካታች መድረክ ነው
Aug 12, 2026 178
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ የዘመናት ልዩነትና አለመግባባትን በሰለጠነ የመደማመጥ ምክክር ወደ የጋራ መግባባትና የጋራ አሸናፊነት የሚያቀዳጅ አካታች መድረክ መሆኑን ተመካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። በጉባኤው በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በስምንት ዐበይት ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ። በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልናና በምርጫ ሥርዓት፣ በሙስናና በመልካም አስተዳደር፣ በሃይማኖት ጉዳዮችና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦች መግባባት ላይ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይፋ አድርጓል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ተመካካሪዎች እንዳሉት፣ ሀገራዊ ምክክሩ መደማመጥና መከባበርን መሠረት በማድረግ እየተካሄደ በመሆኑ የጋራ መግባባትን ለመገንባት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ተመካካሪና የጉምዝ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ ሊቀ መንበር ግራኝ ጉደታ እንደገለጹት፣ የምክክር ጉባኤው የጋራ መግባባትን በሚገነቡ አካታችና አሳታፊ ሃሳቦች እየተንጸባረቁበት ነው። ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ወኪል ተመካካሪዎች ለሀገር የሚጠቅሙ የተለያዩ ሀሳቦችን በነጻነትበማቅረብ የጋራ ምክክር እየተካሄደባቸው መሆኑን ገልጸዋል። የምክክር ሂደቱ ለረጅም ዓመታት የቆዩ ችግሮችን ለመፍታትና ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር ምቹ ሁኔታ እየፈጠረ እንደሚገኝ ተናግረዋል።   ሌላው ተመካካሪና የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ህብረት ሊቀመንበር ገብሩ በርሔ በበኩላቸው፣ የሀገራዊ ምክክር ሂደቱ በውይይት የሚያምን ትውልድና ማኅበረሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል። ምክክር ለትውልድ የተሻለች ሀገርን ለማሸጋገር የሚያግዝ የጋራ መድረክ ነው ያሉት አቶ ገብሩ፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤም መግባባትን የሚገነባ ምክክር እያደረገ ነው ብለዋል። ተመካካሪ ነስሩ ዑዳ በበኩላቸው፣ በጉባኤው የምንመክርባቸው ዐበይት አጀንዳዎች የምንፈልጋትን ኢትዮጵያ ለመገንባት የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።   በ10፣ በ50፣ በ250 እና በ500 የምክክር ቡድኖች ደረጃ እየተካሄደ የሚገኘው የምክክር መድረክ የጋራ መግባባትን የሚገነቡ ሃሳቦች እየቀረቡበት መሆኑን ገልጸዋል። በምክክሩ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የተወከሉ ተመካካሪዎች ሰፊ ምክክር እያደረጉ እንደሚገኙም ጠቁመዋል። የምክክር ሂደቱ አካታችና አሳታፊ ነው ያሉት ተመካካሪዋ፤ ተመካካሪዎች የተለያዩ ሀሳቦችን በመከባበርና በመደማመጥ በማንሳት የጋራ መግባባት የሚገነባ ምክክር እየተደረገባቸው መሆኑን ተናግረዋል። በሀገራዊ ምክክሩ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ለመጪው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማስረከብ ምቹ ሁኔታ መፈጠሩንም ገልጸዋል።  
ሀገራዊ ምክክሩ መግባባት የሰፈነባት እና ብሩህ ተስፋ ያላትን ሀገር እንደሚፈጥር ጽኑ እምነት አለን
Aug 12, 2026 186
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የዘለቁ ችግሮችን በሰለጠነ ምክክር የፈታች፣ መግባባት የሰፈነባት እና ብሩህ ተስፋ ያላትን ሀገር እንደሚፈጥር ጽኑ እምነት እንዳላቸው ተመካካሪዎች ገለጹ። ከመላው ኢትዮጵያ የተውጣጡ ተወካዮች የተሳተፉበት፣ በስምንት ዋና ዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ የሚያተኩረው እና ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም የተጀመረው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። ምክክሩ ኢትዮጵያዊያን በባለቤትነት መንፈስ የሀገራቸውን የነገ ብሩህ ዕጣ ፈንታ እንዲወስኑ እና ሀገራዊ መግባባት የሰፈነባትን ሀገር መገንባት የሚያስችል ታሪካዊ ዓላማን ሰንቋል። በሂደቱ እየታየ ያለው ሰፊ አካታችነት፣ አሳታፊነትና የዜጎች ተነሳሽነትም ችግሮችን በሰለጠነ የምክክር አግባብ ለመፍታት በህዝብ ዘንድ ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ ሆኗል። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡት የተለያዩ የሲቪል ማህበረሰብ ተወካይ ተመካካሪዎች፣ ሀገራዊ ምክክሩ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማት መሠረት የሚጥሉ እና የጋራ መግባባትን የሚያጠናክሩ የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦች የሚፈልቁበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በሂደቱ የሚደረሱት ስምምነቶችም ሕብረብሔራዊ አንድነትን ይበልጥ ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንደሚኖረው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ተመካካሪው ዮሐንስ በንቲ( ዶ/ር)፤ ምክክሩ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች፣ የሙያ ማኅበራት፣የሃይማኖት ተቋማት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ነው ብለዋል። ተመካካሪዎች በቡድኖች ተደራጅተው ውይይት ማካሄዳቸው ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲገልጹና አሳታፊ የውይይት ምህዳር እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጸዋል ። ሂደቱ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ልማት እና አብሮነት መሠረት የሚጥሉ የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦች የሚፈልቁበት መሆኑንም ነው የተናገሩት። የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ቦርድ አባል ተመካካሪው ኢንጂነር አለማየሁ ንጋቱ በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የዘለቁ ችግሮችን በሰለጠነ ምክክር የፈታች፣ መግባባት የሰፈነባት እና ብሩህ ተስፋ ያላትን ሀገር እንደሚፈጥር ጽኑ እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ህዝብ ለልማት በጋራ የሚነሳበት አውድ በመፍጠርም የተረጋጋች እና ዘላቂ ሰላም ያላት ሀገር ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሀገር ሽማግሌዎች መማክርት የቦርድ አባል ተመካካሪው ሀጂ ሙፍቲ ዑመር ፤ እስካሁን የነበረው የምክክር ሂደት እጅግ አሳታፊ እና ለጠንካራ ሀገር ግንባታ ወሳኝ ሚና የሚጫወት ነው ብለዋል። ምክክሩ የተሳካ ውጤት እንደሚያመጣ ያላቸውን እምነት ገልጸው፤ የኢትዮጵያዊያንን አብሮነት ይበልጥ የሚያጠናክር እና የሚያስተሳስር መሆኑን ተናግረዋል፡።        
የምክክር ጉባኤው የዘመናት ቅሬታና ስብራትን በመጠገን ሀገርን የሚያሻግር የተስፋ መድረክ ነው
Aug 12, 2026 215
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የዘመናት ሀገራዊ ቅሬታና ስብራትን በሰለጠነ ምክክር በመጠገን ወደ መግባባት የሚያሻግር የተስፋ መድረክ መሆኑን ምሁራን ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። ኢዜአ ያነጋገራቸው ምሁራን እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው አሳታፊና አካታችነት ሁሉም ዜጋ አለኝ የሚለውን ጉዳይ በግልጽ የሚያንጸባርቅበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም የጋራ መግባባትን መገንባት የሚያስችል ምክክር በማካሄድ አንዱ የአንዱን ሀሳብ የሚገነዘብበትን ዕድል በመፍጠር ሀገር የሚያሻግር ምክረ ሀሳብ ለማፍለቅ እንደሚያግዝ ገልጸዋል። በምክክር ሂደት የሀገር ሽማግሌና የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር አሕመድ ዘከሪያ እንዳሉትም፤ ኢትዮጵያ በሰለጠነ የምክክር መድረክ የጋራ መግባባት የሚሹ በርካታ የታሪክ ስብራቶች ያሉባት ሀገር ናት ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤም በመሠረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ምክክር በማካሄድ የሁሉንም አሸናፊነት የሚያቀዳጅ የጋራ መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። የምክክር ጉባኤውም ከታችኛው የማኅበረሰብ ክፍል ጀምሮ በአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ የቅድመ ምክክር ጉባኤ ወቅት አካታችና አሳታፊ እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህም በዋናው የምክክር ጉባኤ ላይ የ130 ሚሊዮን ህዝብ ወኪል የሆኑ አራት ሺህ የኢትዮጵያውያን ተመካካሪዎች ግልጽ፣ አሳታፊና አካታች ምክክር እያደረጉ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በምክክር ለትውልድ የሚበጅ የጋራ መግባባትን መገንባት ያስፈልጋል ያሉት ፕሮፌሰር አሕመድ፤ በዚህም ሀገራችንን ወደተሻለ የመግባባት ምዕራፍ ለማሸጋገር ጠቃሚ ምክክር እያደረግን ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤ ውጤትም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጭምር የሚበጁ ምክረ ሀሳቦች እንደሚፈልቁበት እምነት እንዳላቸው አንስተዋል። የካናዳ ዲያስፖራ ማኅበረሰብ ወኪል ተመካካሪና የሕግ ባለሙያ ዳንኤል ወርዶፋ በበኩላቸው፤ የምክክር ባህል የሀሳብ የበላይነትን ለማስረጽ የሚያስችል የጋራ አሸናፊነት መድረክ ነው ብለዋል።   የኢትዮጵያ የምክክር ጉባኤም በሀገር ውስጥና በውጭ ዓለማት የሚኖሩ ዜጎችን ሁለንተናዊ የተቃና የመግባባት መስተጋብር ለመገንባት መሠረት እየጣለ መሆኑን ገልጸዋል። ሁሉም የሕዝብ ወኪል አሉኝ የሚሏቸውን ሀሳቦች በማንጸባረቅ የጋራ መፍትሔ፣ መደማመጥ፣ መግባባትና መቀራረብ ባህልን በማጎልበት ሀገርን ያስቀደመ ምክክር እየጎለበተ መምጣቱን ተናግረዋል። በተመካካሪዎች መካከል እየተፈጠረ ያለው የመግባባት መንፈስም ውስብስብና መሠረታዊ በሆኑ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መፍትሔ በመስጠት ሀገርን ወደተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር እንደሚያስችል አንስተዋል። ምክክሩ ችግሮችን ለመካድ ሳይሆን ውስብስብ ችግሮችን አውቆና ቆርጦ በመነሳት ሀገሪቱን ወደ የተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚያስችል ገልጸዋል። የምክክር ጉባኤው ተመካካሪዎች ያለምንም ገደብና ከልካይ ሀሳባችንን በሙሉ ነጻነት የምናንጸባርቅበት የጋራ መግባቢያ መድረክ ነው ያሉት ደግሞ ሌላኛው ተመካካሪ መምህር ዘላለም ገላው ናቸው።   በሀገሪቱ በርካታ ችግሮች ቢኖሩም፤ በተመሳሳይ መልኩ ለችግሮቹ የሚሆኑ በርካታ የመፍትሔ ሀሳቦች መኖራቸውን በምክክር ግንዛቤ እንደተወሰደ መሆኑን ገልጸዋል። በ50፣ በ250 እና በ500 የምክክር ቡድኖች ደረጃ የተካሄደው ምክክርም ችግሩን ከታችኛው መዋቅር ጀምሮ ለመተንተንና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት ወሳኝ መሆኑንም ጠቁመዋል። በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ፣ የፖለቲካ ሥርዓት፣ የፖለቲካ ውክልናና የምርጫ ስርዓት፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር ጉዳዮች፣ የሃይማኖት ጉዳዮችና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሃሳቦቻቸው መግባባት ላይ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ይፋ አድርጓ።
ሀገራዊ ምክክሩ ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር አርአያ የሚሆን ነው
Aug 12, 2026 205
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር አርአያ የሚሆን ነው ሲሉ ተመካካሪዎች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። በሀገር ውስጥና በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን የሚወክሉ አራት ሺህ የሕዝብ ወኪሎች በስምንት ዐበይት አጀንዳዎች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር ጥልቅና አሳታፊ ምክክር እያካሄዱ ይገኛሉ። በምክክር መድረኩ እየተነሱ ያሉት ሐሳቦች ሀገራዊ ሰላምን፣ ዴሞክራሲን እና አብሮነትን ለማጠናከር ጠንካራ መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን ተመካካሪዎች ለኢዜአ ተናግረዋል። ከተመካካሪዎች መካከል ወጣት ዳንኤል ሲሳይ፣ የሀገራዊ ምክክር የእስካሁን ሂደት በጥሩ ሁኔታ ላይ የሚገኝ እና ትልቅ ሀገራዊ ተስፋ የሚታይበት ነው ብሏል። ሂደቱ ሀገራዊ የትውልድ ዕጣ ፈንታን በባለቤትነት በመቅረጽ ረገድ ታሪካዊ ፋይዳ እንዳለው በመገንዘብ የሚካሄድ በመሆኑ በተለይም ለመጪው ትውልድ፣ ታዳጊዎች እና ለወጣቶች ብሩህ ተስፋን የፈነጠቀ ነው ብሏል። አቶ ጸድቻ ሌሌ በበኩላቸው፣ መድረኩ አካታች፣ መከባበር የተሞላበት፣ ሁሉም ሰው በነፃነት ሀሳቡን የሚያንሸራሽርበት እና ጠንካራ ህብረት የታየበት መሆኑን ተናግረዋል። እያንዳንዱ ተመካካሪ ችግሮችን በምክክር መፍታት እንደሚቻል በማመንም፣ ስሜቱንና ሀሳቡን በግልጽ ያንጸባረቀበት መድረክ መሆኑንም አብራርተዋል። አቶ ፋራህ ወርሰመ እየተካሄደ ያለው የሀገራዊ ምክክር ሂደት ሁሉንም ያሳተፈ እና የኢትዮጵያን ችግሮች ለመፍታት ሰፊ ዕድል የሚከፍት መሆኑን ገልጸዋል። ሁሉም ኢትዮጵያውያን በምክክር ችግሮቻቸውን ለመፍታት በአንድነት የተሰበሰቡበት ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ በመሆኑ ከጉባኤው የሚጠበቀው ውጤትም አዎንታዊ እንዲሆን ከፍተኛ እምነት እንደሚጣልበት ተናግረዋል። ይህ አሳታፊ የምክክር ሂደት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራትም ጭምር የገጠሟቸውን ተግዳሮቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንደ መልካም ተሞክሮ እና ሞዴል ሊወሰድ የሚችል ነው ብለዋል። በጉባኤው የተገኙት ገንቢ ውይይቶችና የተደረሱ ስምምነቶችም ለቀጣይ ሰላም፣ ዕድገት እና አብሮነትን ለማጠናከር ታላቅ ምዕራፍ የሚከፍቱ መሆኑን ተናግረዋል።

ማህበራዊ
በተለያዩ ሀገራት በኢ-መደበኛ ፍልሰት ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እየተደረገ ነው - አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር)
Aug 12, 2026 98
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በተለያዩ ሀገራት በኢ-መደበኛ ፍልሰት ምክንያት በአስቸጋሪ ሁኔታ የነበሩ ዜጎች ወደ ሀገር ቤት ተመልሰው ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲቀላቀሉ እየተደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) ገለጹ። የሳዑዲ ዓረቢያ ስደት ተመላሽ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ መብትና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ቤተሰቦቻቸው የማቀላቀሉ ሥራ በተቀናጀ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል ጋር በመተባበር ከስደት ተመላሾችን መልሶ ማቋቋም የሚያስችል የድጋፍ ስምምነት ተፈራርሟል። በስምምነቱ ወቅትም ከሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል የተበረከቱ ተሽከርካሪዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች የድጋፍ ርክክብ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅት ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም (ዶ/ር) እንዳሉት፤ ኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ ረጅም ዘመናትን የተሻገረ ታሪካዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው። የሀገራቱ ታሪካዊ ግንኙነትም በማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ የትብብር መስኮች ወደ ስትራቴጂክ አጋርነት እየተሸጋገረ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ለአብነትም ከሀገራቱ የንግድና ኢንቨስትመንት አጋርነት ባሻገር በሕጋዊ የሥራ ስምሪትን በመከተል በርካታ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሙያ መስኮች በሳዑዲ ዓረቢያ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። በኢ-መደበኛ ፍልሰት ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ተጉዘው በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንም በዜጋ ተኮር የዲፕሎማሲ ትብብር ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑን አንስተዋል። የሳዑዲ ዓረቢያው ንጉሥ ሳልማን የሰብዓዊ እርዳታ ማዕከል ከስደት ተመላሽ ዜጎች ሰብዓዊ መብትና ክብራቸው ተጠብቆ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲቀላቀሉ ላበረከተው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። በማዕከሉ የተበረከተው የዕለት ደራሽና የማጓጓዣ ቁሳቁስ ድጋፍም የሀገራቱን የረጅም ዘመናት ወዳጅነትና ትብብር የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን አስረድተዋል። በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር አብዱላህ ሀሰን አልዛህራኒ በበኩላቸው፣ የኢትዮጵያና የሳዑዲ ዓረቢያ ታሪካዊ አጋርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። የተደረገው ድጋፍ ለኢትዮጵያውያን ስደት ተመላሾች ለሚደረገው የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ የሚውል ሲሆን፣ የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ ወዳጅነትና የሰብዓዊ ትብብር እሴት የሚያጎለብት መሆኑን ጠቅሰዋል። የሳዑዲ ዓረቢያ የኢ-መደበኛ ስደት ተመላሽ ጎራየ ጌትነት፤ በኢ-መደበኛ ስደት ያሳለፉትን አስከፊ ውጣ ውረድ አስታውሷል። የሳዑዲ ዓረቢያ የኢ-መደበኛ ስደት ተመላሽ ገብረ ሃዋሪያ ሐጎስ፤ ከነበሩበት አስቸጋሪ ሁኔታ ወደ ሀገራቸው በመመለሳቸው የተደረገላቸውን አቀባበልና እንክብካቤ አመስግነዋል። የሳዑዲ ዓረቢያ የኢ-መደበኛ ስደት ተመላሽ ከማል መሐመድ፤ ያሳለፉትን አስቸጋሪ የሕይወት ውጣ ውረድ በማስታወስ በቀጣይ በሀገሬ ሰርቼ ለመለወጥ እተጋለሁ፤ ኢ-መደበኛ ስደትም አስከፊ ነው ብለዋል።  
የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አቀፍ የጥናትና ምርምር አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ውጤት እያስገኘ ነው
Aug 12, 2026 133
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አቀፍ የጥናትና ምርምር አገልግሎቶች የአካባቢውን ህብረተሰብ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ፕሬዝዳንት ተመስገን ደበሎ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ በጋራ መስራት በሚያስችላቸው የትብብር መስኮች ዙሪያ የምክክር መድረክ አካሂደዋል። የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተመስገን ደበሎ (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው በሀገር በቀል እውቀቶች፣ በማዕድን፣ በግብርና፣ በእንስሳት ሀብትና በጤና ዘርፎች የጥናትና ምርምር ላይ ውጤታማ ሥራ እየሰራ ነው ብለዋል። የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አቀፍ የጥናትና ምርምር አገልግሎትም የበርካታ ዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ እመርታዊ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው የሚያከናውናቸውን የምርምርና የልማት ሥራዎች ለህዝብ በተሻለ ሁኔታ ለማድረስ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ጋር በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትም የዩኒቨርሲቲውን ሥራዎች ለህዝብ በማስተዋወቅና የሀገርን ገጽታ በመገንባት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተፈራ በቀለ በበኩላቸው፣ ኢዜአ የህዝብን አንድነትና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያጎለብቱ የዜናና ዜና ነክ ተግባራትን ለህዝብ እያዳረሰ ይገኛል ብለዋል። የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የጥናትና ምርምር ማህበረሰብ አቀፍ የልማት ሥራዎች የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የማይተካ ጠቀሜታ እንዳለው ገልጸዋል። በዚህም የኢዜአን የተደራሽነት አድማስ የበለጠ በማጠናከር የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የሚያፈልቃቸውን የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለህዝብ ተደራሽ በማድረግ በትብብር እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። በቀጣይም የአካባቢውን እምቅ አቅሞችና ሀገር በቀል እውቀቶች ለማስተዋወቅ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የበኩሉን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የትብብር ስምምነት ሐምሌ 9 ቀን 2018 ዓ.ም በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን የትብብር ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። በትብብር ስምምነት መሰረት ዩኒቨርሲቲው በምርምርና በሀገር በቀል እውቀቶች ዙሪያ የሚያከናውናቸውን ሥራዎች ለህዝብ በተሻለ ሁኔታ ለማድረስ ጠቃሚ መደላድል ይፈጥራል።
የወጣቶችን አቅምና እውቀት በማስተባበር ሁለገብ ልማትን ማፋጠን አለብን
Aug 12, 2026 97
ገንዳ ውኃ፣ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፡-የወጣቶችን አቅምና እውቀት በማስተባበር የአካባቢውን ሁለገብ ልማት ማፋጠንና ህዝባዊ አንድነትን ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ እያሱ ይላቅ ገለጹ። "ብዙኃን የወጣቶች እውቀት ለጋራ ትልም" በሚል መሪ ቃል ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በምዕራብ ጎንደር ዞን ገንዳ ውኃ ከተማ ተከብሯል።   ዕለቱ በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶችና በተለያዩ ሁነቶች በድምቀት የተከበረ ሲሆን፣ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችና የመሠረተ ልማት አውታሮች ተጎብኝተዋል። በበዓሉ ላይ የተገኙት የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እንዳሉት፤ ወጣቶች በአካባቢው የሚከናወኑ የልማት ሥራዎችን በማፋጠን፣ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን በማጠናከርና ዘላቂ ሰላምን በማረጋገጥ ረገድ የጎላ ሚና አላቸው። በተለይም የሀገር ህልውና፣ የልማትና የለውጥ ዋና ኃይል በመሆናቸው፤ እውቀታቸውን፣ ጉልበታቸውንና ፈጠራቸውን በማስተባበር ለአካባቢው ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገት በግንባር ቀደምነት ሊሰለፉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የምዕራብ ጎንደር ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለው ማሩ በበኩላቸው፤ ወጣቶችን በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና በማኅበራዊ ዘርፎች የነቃ ተሳታፊና ተጠቃሚ ለማድረግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ወጣቶች በመልካም ሥነ-ምግባር ታንጸው ሀገራዊ አንድነትን እንዲገነቡና ከአሉታዊ አስተሳሰቦች ርቀው የልማት አርበኛ እንዲሆኑ ከአጋር አካላት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል። በበጎ ፈቃድ ሥራው የተሳተፈው ወጣት ያለው ተረፈ፤ "ያለብንን የዜግነት ግዴታ በመወጣት ለአካባቢያችን ልማትና አንድነት በቁርጠኝነት መሥራታችንን እንቀጥላለን" ብሏል። አክሎም ወጣቱ የሀገር ተረካቢ እንደመሆኑ መጠን ከአሉታዊ እንቅስቃሴዎች በመውጣት አቅሙንና እውቀቱን ለአካባቢው ሰላም፣ ልማት፣ የሥራ ዕድል ፈጠራና የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ማዋል እንዳለበት አስገንዝቧል። ሌላዋ አስተያየት ሰጪ ወጣት አክማዝ ገብሬ በበኩሏ፤ "አንድነታችንን በማጠናከርና እርስ በእርስ በመደጋገፍ ለአካባቢያችን ሁለገብ እድገት መሥራት ይጠበቅብናል" ስትል ተናግራለች። በተለይም በበጎ ፈቃድ አገልግሎትና በማኅበራዊ ሥራዎች ላይ የሚደረገውን ርብርብ በማጠናከር ሕብረተሰቡን ለመደገፍና የዞኑን መልካም ገጽታ ለመገንባት እንደሚሠሩ አስረድታለች።  
የወጣቶች ወርቃማ የስነ-ህዝብ ዕድል፦ ለአዲስ ታሪክ ግንባታና ለሀገራዊ ብልጽግና
Aug 12, 2026 158
በሙሴ መለሰ የዓለም የወጣቶች ቀን መነሻ ታሪኩ የሚጀምረው እ.ኤ.አ. በ1991 (በኢትዮጵያ 1983 ዓ.ም) በኦስትሪያ ቪዬና በተካሄደው የመጀመሪያው የዓለም የወጣቶች ፎረም ላይ ነው። በወቅቱ የተሰበሰቡት ወጣት ተወካዮች በዓለም አቀፍ ደረጃ የወጣቶች ድምፅ የሚሰማበትና ትኩረት የሚያገኝ ልዩ ቀን እንዲኖር ሀሳብ አቀረቡ። ይህ ሀሳብ ዳብሮ እ.ኤ.አ. በ1998 በሊዝበን ፖርቱጋል በተካሄደው የዓለም የወጣቶች ጉዳይ ሚኒስቴሮች ጉባኤ ላይ ውሳኔ ሆኖ ቀርቧል። ይህን ተከትሎም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እ.አ.አ በ1999 ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት በየዓመቱ ኦገስት 12 (ነሐሴ 6) ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ሆኖ እንዲከበር ተወስኗል። የመጀመሪያውም እ.አ.አ በ2000 ተከበረ። የቀኑ ዋና ዓላማ ወጣቶች የሚያጋጥሟቸውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮች በመዳሰስ፣ ለዓለም ሰላምና ዘላቂ ልማት የሚያበረክቱትን የፈጠራና የልማት አቅም እውቅና መስጠት ነው። ዘንድሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ “ብዝሃ የወጣቶች እውቀት፤ ለጋራ ትልም!” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ ለ27ኛ ጊዜ እየተከበረ ይገኛል። መሪ ሀሳቡ በዓለም ዙሪያ የሚገኘው ወጣት የተለያየ ባህል፣ አካባቢና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ቢኖረውም፣ የተሻለ ወደፊት የመገንባት፣ የትምህርት፣ የስራ እና የሰላም የጋራ ፍላጎት እንዳለው የሚያሳይ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት መረጃ ያመለክታል። በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስተባባሪነት “ብዝሃ የወጣቶች እውቀት፤ ለጋራ ትልም!” በሚል ሀገራዊ ጭብጥ ለ23ኛ ጊዜ እየተከበረ ሲሆን፣ ይህም የሀገሪቱን ወጣቶች ልዩ ልዩ እውቀት፣ ክህሎትና አቅም በማስተባበር ለጋራ ሀገራዊ ዕድገት ማዋል እንደሚገባ ጥሪ የሚያቀርብ ነው። ይህ ዕለት ለኢትዮጵያ ልዩና ታሪካዊ ትርጉም አለው፤ ምክንያቱም ከኢትዮጵያ ህዝብ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው ዕድሜው ከ35 ዓመት በታች በመሆኑ ኢትዮጵያ እጅግ ግዙፍ የሆነ ወርቃማ የስነ-ህዝብ ዕድል (Demographic Dividend) ባለቤት ናት። ይህን አቅም በተገባ መንገድ በመጠቀም ወጣቱን በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን፣ በማክሮ-ኢኮኖሚ ግንባታ፣ በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጎ አድራጎት እና በፈጠራ ስራዎች ላይ ማሰማራት የሀገሪቱ የብልጽግና ዋና ምሰሶ ያደርገዋል። በመሆኑም ወጣቱን በችግር ጊዜ ብቻ ትኩረት የሚሰጠው አካል ሳይሆን፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ዛሬ ላይ ቆሞ በጋራ የሚቀርጽ ግንባር ቀደም ኃይል የማድረግ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልጋል። ይህንን ሀገራዊ እውነታ እና የወጣቱን ቁልፍ ሚና አስመልክተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት መልእክት ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም ሲሉ ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተር እና የሀገራችን ሉዓላዊነት ጽኑ ማገር ነው። የአሁኑ ወጣት ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶችን በመራቅ በልማት ላይ አተኩሯል፤ ድህነትንም ተጠይፎ የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል። ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግም ሁሉም በንቃት እየተጋ በፍቅር እንዲመላለስ ጥሪ በማቅረብ፣ ወጣቱ በሀገሪቱ የወደፊት ጉዞ ላይ ያለውን የማይተካ ድርሻ በአፅንኦት አጉልተዋል። በአጠቃላይ፣ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ለኢትዮጵያ ወጣቶች ቀኑን አስታውሰው የሚያልፉበት ብቻ ሳይሆን፣ የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት የሚያስታውሱበት እና አቅማቸውን የሚያድሱበት መልካም አጋጣሚ ነው። የኢትዮጵያ የወደፊት ብልጽግና እና ዘላቂ ሰላም እውን የሚሆነው የወጣቶችን እውቀት፣ ጉልበት እና የፈጠራ አቅም በአንድነት አስተባብሮ መጠቀም ሲቻል ብቻ ነው። በዲጂታል ፈጠራ፣ በአረንጓዴ ልማት እና በማህበራዊ አገልግሎቶች ላይ የወጣቱ ንቁ ተሳትፎ መቀጠል የነገዋን የበለፀገች ኢትዮጵያ በጋራ የመገንባቱን ሂደት ያፋጥነዋል።
ኢኮኖሚ
የአፍሪካ አቪዬሽን አርማ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተቋማዊ ልህቀት በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ዓይን
Aug 12, 2026 137
በሙሴ መለሰ የአቪዬሽን ኢንዱስትሪ የአንድን ሀገር ኢኮኖሚያዊ ትስስር፣ የቱሪዝም ዕድገት እና የጂኦፖለቲካዊ ተፅዕኖ የመወሰን ከፍተኛ አቅም ያለው ስትራቴጂካዊ ዘርፍ ነው። በአፍሪካ አህጉር በርካታ ሀገራት ብሔራዊ አየር መንገዶቻቸውን በትክክለኛ የንግድ መስመርና ጠንካራ ተቋማዊ መዋቅር ለመገንባት በሚታገሉበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያሳየው ዘላቂ ዕድገትና ስኬት በመላው ዓለም ትልቅ አድናቆትንና ትኩረትን የሳበ አጋጣሚ ሆኗል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተመሠረተበትን 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት፣ ከትራንስፖርት ተቋም ከመሆን አልፎ የአፍሪካ አቪዬሽን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መሪ በመሆን ቁልፍ ሚናውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ተቋሙ በተከተለው የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ፣ በሙያዊ አስተዳደር እና ባደራጀው ዘመናዊ የአቪዬሽን ማዕከል አማካኝነት ሀገሪቱን የአህጉሪቱ ዋነኛ አገናኝ ድልድይ እና የትራንዚት መዳረሻ ሆኗል። ይህን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የላቀ ደረጃ የበለጠ ለማጠናከር እና የወደፊቱን የዓለም አቪዬሽን ፍላጎት ታሳቢ ያደረገው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት፣ ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን የመሪነት ሚና ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ግዙፍ መሠረተ ልማት ነው። ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ እየተገነባ የሚገኘው ይህ ሜጋ ኤርፖርት፣ የቦሌ ዓለም አቀፍ አየር መንገድን የጭነትና የመንገደኞች ጫና በመቀነስ በዓመት እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን ለማስተናገድ አልሞ የተነሳ ነው። ይህም ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ በአፍሪካ ግዙፉ የአቪዬሽን ማዕከል በመሆን የቀጣናውን የቱሪዝም፣ የንግድና የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ እንደሚያነቃቃው ይጠበቃል። ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በሰሞኑ ዘገባቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ስኬት እና የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ፕሮጀክት ግንባታ ላይ ትኩረታቸውን አድርገዋል። የዩናይትድ ኪንግደሙ ዕለታዊ ጋዜጣ ዴይሊ ኤክስፕረስ (Daily Express) በዘገባው እንደጠቀሰው፣ ከአዲስ አበባ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገነባው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በዓለም አቀፉ የዛሃ ሀዲድ አርክቴክቶች ዲዛይን የተደረገ ግዙፍ ፕሮጀክት እንደሆነ አመልክቷል። አየር ማረፊያው እ.አ.አ. በ2030 በሚጠናቀቀው የመጀመሪያው ምዕራፍ 60 ሚሊዮን መንገደኞችን የማስተናገድ አቅም የሚኖረው ሲሆን፣ ይህም በዓመት 28 ሚሊዮን የሚያስተናግደውን የደቡብ አፍሪካውን ኦሊቨር ታምቦ እና 26 ሚሊዮን የሚያስተናግደውን የግብፁን ካይሮ ኤርፖርቶች በከፍተኛ ልዩነት በመብለጥ በአህጉሪቱ የመሪነቱን ቦታ እንደሚይዝ ገልጿል። ፕሮጀክቱ አራት የመሬት ላይ የአውሮፕላን መነሻና ማረፊያ መንገዶችን፣ የ38 ኪሎ ሜትር ፈጣን የባቡር መስመር፣ የሆቴልና የንግድ ማዕከላትን ያካተተ በመሆኑ፣ የዓለም ኃያላን አገራትን፣ አሜሪካንና ቻይናን ጨምሮ፣ የዓለም አቀፍ ኢንቨስተሮችን ትኩረት መሳቡን ዘገባው አመልክቷል። ሌላኛው የዩናይትድ ኪንግደም ዕለታዊ ጋዜጣ ዴይሊ ሚረር (Daily Mirror) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬት በኤርፖርት መሠረተ ልማት ግንባታ ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን፣ በተቋማዊ የአመራር ዘዴው ለአህጉሪቱና ለሌሎች ሀገራት ትልቅ ተሞክሮ እንደሆነ ገልጿል። ዲፕሎማት ካና ካናናታን በጋዜጣው ላይ ባሰፈረው ጽሑፍ፣ አየር መንገዱ በመንግሥት ሥር ሆኖ ሳለ እ.አ.አ. በ2025/26 በጀት ዓመት 9.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማስገኘቱ፣ 20.7 ሚሊዮን መንገደኞችን ማጓጓዙ እና በ174 አውሮፕላኖች ወደ 150 ዓለም አቀፍ መዳረሻዎች መብረሩ “የመንግሥት ባለቤትነት የኪሳራ መንስኤ ነው” የሚለውን የተሳሳተ አመለካከት ያፈረሰ መሆኑን አመልክቷል። እንደ ስሪላንካ ያሉ ሀገራት በየዓመቱ ብሔራዊ አየር መንገዶቻቸውን ከመንግሥት ግምጃ ቤት ለመደጎም ሲታገሉ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ከፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ነፃ በሆነ የንግድ ስትራቴጂ መመራቱ የስኬቱ ምሥጢር መሆኑ ተመላክቷል። የኢትዮጵያ የአቪዬሽን አመራር ልህቀት ዓለም አቀፍ ተቀባይነት እያደገ መምጣቱ በጽሑፉ ላይ ሰፍሯል። በተመሳሳይ መልኩ ዘ ኢስት አፍሪካን (The East African) ላይ በቻርልስ ኦንያንጎ-ኦቦ የቀረበው ጽሑፍ እንደሚያስረዳው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበላይነት የመጣው በጠንካራ የቴክኒክ ሥልጠና፣ በአውሮፕላን ጥገና ልህቀት፣ በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ፣ በተቋማዊ አሠራር እና በጠንካራ ዲሲፕሊን የሚመራ በመሆኑ ነው። አየር መንገዱ የራሱን ስኬት ከማስመዝገብ ባለፈ፣ የቀድሞና የአሁኑ አመራሮቹን እንደ ASKY፣ Malawi Airlines፣ Air Congo፣ Zambia Airways፣ Uganda Airlines እና RwandAir ባሉ በርካታ የአፍሪካ አየር መንገዶች ውስጥ በቁልፍ የካፒቴንነትና የአመራር ቦታዎች ላይ በመመደብ የመላው አፍሪካ አቪዬሽን አቅም እንዲገነባ መሠረት መሆኑን ጽሑፉ አመልክቷል። ታይምስ ኩዌት (The Times Kuwait) ባወጣው መረጃ መሠረት፣ እ.አ.አ. 1945 የተመሠረተው ይህ አየር መንገድ የ80 ዓመታት የልህቀት ጉዞውን በሚያከብርበት በዚህ ወቅት በስካይትራክስ (SKYTRAX) ዘንድ ለስምንት ተከታታይ ዓመታት “የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ” በመባል መመረጡን ገልጿል። አየር መንገዱ አዲስ አበባን የትራንዚት ማዕከል በማድረግ መንገደኞች በቆይታቸው እንደ እንጦጦ ፓርክ፣ አንድነት ፓርክ፣ ወንጪ ሐይቅ፣ ጨበራ ጩርጩራ፣ ላሊበላን እና የሰሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ጨምሮ ሌሎች የመስብ ቦታዎችን እንዲጎበኙ በማስቻል የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ እያነቃቃ እንደሚገኝ ጠቅሷል። በአጠቃላይ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬት የአንድ ሀገር ተቋም ጥንካሬ ማሳያ ብቻ ሳይሆን፣ የአፍሪካ አቪዬሽን ኢንዱስትሪ በሙያዊ አመራርና በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ከተመራ ምን ያህል ስኬታማ መሆን እንደሚችል ያሳየ ትልቅ ተሞክሮ ነው። በቢሾፍቱ እየተገነባ የሚገኘው አየር ማረፊያ ሲጠናቀቅ የመንገደኞችን የማስተናገድ ጫና በመቀነስ፣ የአህጉሪቱን የንግድ፣ የሎጂስቲክስና የቱሪዝም ትስስር ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋግረዋል። ይህ የራዕይና የተቋማዊ ጥንካሬ ቅንጅት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ካርታ ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት ይበልጥ የሚያጠናክረው ይሆናል።
በሸገር ከተማ በምግብ ራስን ለመቻል የሚያስችሉ የግብርና ስራዎች በመከናወን ላይ ናቸው
Aug 12, 2026 102
ሸገር ፤ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፡– በሸገር ከተማ ተረጂነትን ለማስወገድ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ የተያዘውን በምግብ እህል ራስን የመቻል ዕቅድ ለማሳካት የሚያስችሉ የግብርና ስራዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን የከተማዋ አስተዳደር አስታወቀ። ኢትዮጵያ በምግብ እህል ራስን ለመቻል እና የስንዴ ምርትን ከውጭ ማስገባትን ለማስቆም ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በስፋት እየተገበረችው የሚገኘው የኩታገጠም እርሻ ውጤት እያስገኘ ነው። የሸገር ከተማ አስተዳደርም በከተማ ዙሪያ የሚገኙ የእርሻ መሬቶችን በዘመናዊ አሰራር በማልማት ተረጂነትን ለማስወገድ እና የከተማዋን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። በከተማዋ ኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ በ340 ሄክታር መሬት ላይ በኩታገጠም አሰራር ለምርጥ የስንዴ ዘር ብዜት የሚሆን የዘር መዝራት ስራ ዛሬ ተከናውኗል። ይህን ዓላማ ለማሳካት ዋናው ማነቆ የሆነውን የምርጥ ዘር እጥረት ለመቅረፍ፣ ዛሬ በኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ የተካሄደው የ340 ሄክታር መሬት ኩታገጠም ዘመቻ ጥራት ያለው የስንዴ ዘር በማባዛት ለአካባቢውና ለሌሎች አራሾች ለማቅረብ ያለመ ነው።   በስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የሸገር ከተማ የግብርና እና ልማት ክላስተር አስተባባሪ አቶ ግርማ ሀይሉ እንደገለጹት፤ በከተማዋ ምርታማነትን በማሳደግ በግብርናው ዘርፍ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችሉ ተግባራት በሰፊው በመከናወን ላይ ይገኛሉ። በተለይም በከተማዋ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ የውጭ ኤክስፖርትን ማሳደግ እና ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የመተካት ዕቅዶችን ለማሳካት በትኩረት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል። በዚህም ለከተማዋ አርሶ አደሮች የክህሎት ሥልጠና በመስጠት የሥራ ባህልን መለወጥ ተችሏል ብለዋል። ዛሬ የተካሄደው ስንዴን በኩታ ገጠም ማሳን በዘር የመሸፈን ዘመቻም የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን ጠቁመዋል። የዛሬው ስንዴን የመዝራት ዘመቻ የግብርና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በሙሉ በመጠቀም የተከናወነ መሆኑን አብራርተዋል። በዚሁ መሠረት በከተማዋ በዘንድሮው የመኸር እርሻ ወቅት 70 ሺህ ሄክታር መሬት በኩታገጠም ለማልማት ታቅዶ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።   የሸገር ከተማ ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደጀኔ በቀለ በበኩላቸው፤ በከተማዋ የምርት እና የምርታማነት መጠንን ለማሳደግ ዘንድሮ እየተከናወነ ካለው የግብርና ሥራ ውስጥ እስካሁን 55 በመቶ የሚሆነው ሙሉ የግብርና ፓኬጅ በመጠቀም እንዲለማ መደረጉን ገልጸዋል። በከተማዋ የኩራ ጂዳ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ ተማም ሁሴን፤ በክፍለ ከተማው እየለማ ካለው አጠቃላይ መሬት ውስጥ ስንዴ በኩታገጠም የማልማቱ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል። የኩታገጠም እርሻ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ ከማስቻሉም በላይ ምርትና ምርታማነታቸውን እንዳሳደገላቸው የተናገሩት ደግሞ በዘር ብዜቱ ተሳታፊ አርሶ አደሮች ናቸው።      
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በድሬዳዋ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ ነው
Aug 12, 2026 120
ድሬደዋ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ እያደረገ መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ገለጹ። በድሬዳዋ አስተዳደር በከፊል ወደ ስራ የተሸጋገሩ ስምንት አምራች ኢንዱስትሪዎች ተጎብኝተዋል ።   ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ በወቅቱ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ውጤታማ ለማድረግ የተደረጉ የተቀናጁ ድጋፎችና ክትትሎች ውጤት እያመጡ ነው። የመሬት፣ የኤሌክትሪክ፣ የፋይናንስ፣ የመሠረተ ልማት እና ሌሎች ጥያቄዎች በአፋጣኝ እንዲመለሱ በማድረግ ኢንዱስትሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ አስችሏል ብለዋል። በዚህም በተጠናቀቀው በጀት አመት ብቻ 11 ከፍተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ በመግባት ከ1ሺ 400 በላይ የቋሚ የስራ ዕድል መፍጠራቸውን አንስተዋል ። ኢንዱስትሪዎቹ ተኪ ምርቶች ከማምረት በተጨማሪ የወጪ ምርቶችን በማምረት ወደ ውጭ ሀገራት በመላክ ምንዛሬ እያስገኙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። የዛሬው ጉብኝትም እየተደረገ የሚገኘውን የድጋፍና የክትትል ስራ በማጠናከር በከፊል ማምረት የጀመሩትን አምራች ኢንዱስትሪዎች በሶስት ወራት ውስጥ ወደ ሙሉ አገልግሎት እንዲገቡ ለማስቻል መሆኑን አመላክተዋል።   ጉብኝት ከተደረገባቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች መካከል የሳሙና ፣ የጭማቂ፣ የውሃ፣ የሮቶ፣ የካርቶንና፣ የእርሻ መሳሪያ ማምረቻዎች እንዲሁም የቡና ማቀነባበሪያዎች እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። ከተማ አስተዳደሩ ኢንደስትሪዎችን ምርታማ ለማድረግ የሚያደርገው ድጋፍና ክትትል ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉን ያነሱት ደግሞ የኤስ ስቲል አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤት አቶ ሰለሞን ተስፋዬ ናቸው። ኤም ኮፊ ቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ጀማል አብዱረህማን በበኩላቸው ለቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካቸው የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄ በአንድ ወር ውስጥ ምላሽ ማግኘታቸው ስራቸውን ለማሳካት እንዳገዛቸው ጠቁመዋል። የቡና ምርቶች ላይ እሴት በመጨመር ወደ አውሮፓ፣ አሜሪካ፣ መካከለኛ እና ሩቅ ምስራቅ ገበያ በመላክ ተወዳዳሪ እንዳደረጋቸው ገልጸዋል።
በአማራ ክልል ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ተሰጠ
Aug 12, 2026 109
ደሴ፤ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ173 ሺህ ለሚበልጡ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መሰጠቱን የክልሉ መሬት ቢሮ አስታወቀ። በደሴ ከተማ አስተዳደር የገጠር ቀበሌ አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል።   በሥነ- ሥርዓቱ ላይ የአማራ ክልል መሬት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሲሳይ ዳምጤ እንደገለጹት፤ የክልሉን መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም በማዘመን የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ማሳደግ ተችሏል። በክልሉ ባለፉት ዓመታት የአርሶ አደሮችን ዘላቂ የመሬት ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተደረገው ጥረት ተጨባጭ ውጤት እንዳስገኘ ተናግረዋል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ብቻ ከ488 ሺህ በላይ የመሬት ይዞታዎች ላይ የሁለተኛ ደረጃ ማረጋገጫ ደብተር መስጠት መቻሉን ገልጸዋል። የይዞታ ደብተሩ የአርሶ አደሩን ይዞታ በዘመናዊ መንገድ በመለካትና ማረጋገጫ በመስጠት የብድርና ሌሎች አገልግሎቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም አመልክተዋል። እንዲሁም ቀደም ሲል በመሬት ወሰንና ድንበር አካባቢ የሚፈጠሩ ግጭቶችን፣ አለመግባባቶችንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ከማስቀረቱ ባለፈ ትክክለኛ ግብር መክፈል እንዲቻል የሚያደርግ መሆኑን አስረድተዋል። በበጀት ዓመቱ ከ43 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተራቸውን ዋስትና በማስያዝ ከ3 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር መውሰዳቸውን ገልጸዋል።   በዛሬው ዕለትም በደሴ ከተማ አስተዳደር ለ996 አርሶ አደሮች የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር መስጠት መቻሉን ገልጸው፣ በአዲሱ በጀት ዓመትም ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል። የደሴ ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ በበኩላቸው፤ በከተማው የገጠር መሬት አያያዝና አጠቃቀምን በማዘመን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። መሬቱን በሳይንሳዊ መንገድ በመለካት ትክክለኛ መገኛውን፣ ድንበሩን፣ ወሰኑንና መጠኑን በማስቀመጥ ለአርሶ አደሩ የሁለተኛ ደረጃ የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተር እየተሰጠ መሆኑን አመልክተዋል።   ይህም ሕገ-ወጥ መሬት ወረራንና ግንባታን በማስቀረት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን እያቃለለ መሆኑን አስገንዝበዋል። በደሴ ከተማ የዋሊዶ ገጠር ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር አሊ ሁሴን እና ወይዘሮ ደመቁ ሁሴን፤ የይዞታ ማረጋገጫ ደብተር ማግኘታችን መሬቱን በተሻለ መንገድ ለማልማትና ተጨማሪ ሀብት ለማፍራት ያስችለናል ነው ያሉት። የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ ደብተሩ ወሰንና ልኬትን በትክክል ያስቀመጠ በመሆኑ የመሬታችንን ዘላቂ ዋስትና እና ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ነው ብለዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የክልልና የከተማ አመራሮችን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።    
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የሀገር ሉዓላዊነትንና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ ዘመናዊ ሰራዊት ለማደራጀት ቴክኖሎጂ ወሳኝ ነው-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ
Aug 12, 2026 99
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፦የሀገር ሉዓላዊነትንና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ ዘመናዊ ሰራዊት ለማደራጀት ቴክኖሎጂ ወሳኝ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተደራጀ ዘመናዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት፥ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱ መቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡ የሀገርን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ ዘመናዊ ሠራዊት ለማደራጀት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመከላከያ ኃይል በተለይም በአየር፣በምድር እና በሳይበር አቅም ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል። የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል። ሁለቱ ተቋማት በሎጂስቲክስ፣ በስልጠና፣ በሳይበር ደህንነት፣ በመከላከያ ሰራዊት ጤና አጠባበቅ፣እንዲሁም በአየር ኃይል እና በኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር ዘርፎች በኤ.አይ በመታገዝ የሠራዊቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ አበይት ጉዳዮችን ላይ መወያየታቸውን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዞ አንዱ መገለጫ -መሶብ
Aug 12, 2026 142
(በሙሴ መለሰ) የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች መመላለስ፣ የወረቀት ክምርና ረጅም ሰልፍ የኢትዮጵያውያን የቆየ የዕለት ተዕለት ፈተና ነበር። ይህንን የዜጎች እንግልት በዘላቂነት ለመቅረፍ እና አሰራርን ለማዘመን ታስቦ የተመሠረተው መሶብ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። የተቀናጀው የ"አዲስ መሶብ" ሱፐር አፕ (Super App) ዲጂታል መድረክ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ወደ ሙሉ ሥራ መግባቱ ይታወሳል። የመሶብ ዋና ዓላማ ተበታትነው የነበሩ ልዩ ልዩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጋዥነት በአንድ ጣሪያ ስር ማገናኘት ነው። ዜጎች ጊዜና ገንዘባቸውን ሳይባክኑ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣ የሰዎችን ቀጥተኛ ንክኪ በመቀነስ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት፣ እንዲሁም ግልጽነትን ማስፈን የተቋሙ መሠረታዊ ምሰሶዎች ናቸው። በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ደግሞ እያንዳንዱ ዜጋ በብሔራዊ የፋይዳ (Fayda) መታወቂያው ብቻ በመጠቀም ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ አካውንት እንዲያገኝ ማድረግ እና ሥርዓቱን ለአፍሪካ ሀገራት እንደ መሪ ተሞክሮ ማቅረብን ያለመ ነው። ይህ የዲጂታል መድረክ እና አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሀገር በቀል እውቀት የበለጸገ ሲሆን፣ ጥቅም ላይ የዋሉት የሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች ለሁሉም ክፍት የሆነ (Open-source) መሆናቸው ተቋሙን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ አድኖታል። በማዕከላቱ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች ጥብቅ የሆነ የምልመላ ፈተና እና ልዩ ስልጠናዎችን አልፈው የሚገቡ በመሆናቸው የአገልግሎት ጥራቱ ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን አስችሏል። መጀመሪያ ላይ በ12 ተቋማትና በ41 አገልግሎቶች ብቻ የተጀመረው ይህ ዘመናዊ አሰራር፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያሳየ ባለው ፈጣን እድገት በአሁኑ ወቅት የትስስር አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችሏል። አሁን ባለው ተጨባጭ ቁመና መሶብ 27 ዋና ዋና የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መስመር ማገናኘት የቻለ ሲሆን፣ እነዚህ ተቋማት በአንድ ላይ በመቀናጀት ከ288 በላይ የተለያዩ ዲጂታል አገልግሎቶችን በጥራትና በፍጥነት እያቀረቡ ይገኛሉ። ተገልጋዮች እንደ ፓስፖርት፣ ውክልና፣ የንግድ ፈቃድ እና የሰነዶች ማረጋገጫ ያሉ ወሳኝ ጉዳዮቻቸውን በአንድ ማዕከል ወይም በሞባይል መተግበሪያቸው ማከናወን ይችላሉ። ይህንን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ማዕከላት የተቋቋሙ ሲሆን፣ እስካሁንም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በማስተናገድ የአገልግሎት እርካታውን በፌዴራል ደረጃ ወደ ከ98 በመቶ በላይ ማድረስ ተችሏል። በቅርብ ቀናት ውስጥ የወጡ አዳዲስ ወቅታዊ መረጃዎች ደግሞ ተቋሙ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እና ተለዋዋጭ እያደረገው መሆኑን ያሳያሉ። በቀን የሥራ ሰዓት መስተናገድ ለማይችሉ ሠራተኞችና ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ከተለመደው የሥራ ሰዓት ውጭ የምሽት አገልግሎት (Night Service) በይፋ ተጀምሯል። ከዚህ በተጨማሪ ወደ ማህበረሰቡ በቀጥታ በመሄድ አገልግሎት የሚሰጡት እና የራሳቸውን ኃይል በከፊል ከፀሐይ ብርሃን የሚያመነጩት ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ አውቶቡሶች (Mobile Mesob Bus) በተለይ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች የቤት ለቤት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። የጤናው ዘርፍ አገልግሎቶችንም ለማካተት ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ጋር አዲስ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ ወደ ሀገር ለሚገቡ ባለሃብቶችና ዳያስፖራዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በቦሌ ዓለም አቀፍ አየውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ማዕከል እየተገነባ ይገኛል። በአዲስ አበባ ከተማም ከ480 በላይ የአገልግሎት መስኮቶች የሚኖሩት አንድ ግዙፍ ማዕከላዊ የኮምፕሌክስ ሕንፃ ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ ነው። “ዩኒፋይድ መሶብ” የተሰኘው የኦንላይን መድረክ ዜጎች በሞባይል ስልካቸው የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓትም ተግባራዊ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት መሶብ ከሀገር ውስጥ አልፎ ዓለም አቀፍ ትኩረትን እየሳበ ይገኛል። ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና የቤኒን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ማዕከሉን በይፋ የጎበኙ ሲሆን፣ መሶብ ለአፍሪካ ሀገራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ለመገንባት እንደ ትልቅ የምርጥ ተሞክሮ ማሳያ እየተወሰደ ነው። በቀጣይም ከጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ጋር በዲጂታል አገልግሎት ዙሪያ የጋራ ትስስር በመፍጠር የአህጉር አቀፍ የዲጂታል ሥርዓት የመገንባት ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሰራ ይገኛል። በአጠቃላይ መሶብ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን እና የሕዝብን እንግልት በመቀነስ ረገድ ውጤታማነቱን በተግባር ያረጋገጠ ስኬታማ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማሳያ ነው።
ማእከሉ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠትና ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት እያገዘ ነው
Aug 12, 2026 118
ባህር ዳር ፤ነሀሴ 6/2018 (ኢዜአ)፡ -የባህር ዳር መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት ባለፈ ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የባህር ዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። መንግስት መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎትን በማስፋፋት ዜጎች ቀልጣፋና ዘመናዊ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋለውን የመልካም አስተዳደር ችግር እየፈታ ይገኛል።   እንዲሁም ዜጎች በአንድ ቦታ የተቀናጀ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ከአላስፈላጊ ወጭና እንግልት ከመታደግ ባለፈ ብልሹ አሰራርን እያስቀረም ይገኛል። ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች መሶብ የአንድ ማእከል አገልግሎት ግልጽና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የረዳቸው መሆኑን ተናግረዋል ። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ አብርሃም ያረጋል እንደገለጹት፣ የባህር ዳር መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ከተማዋን የሚመጥን አግልግሎት እየሰጠ ነው።   መንጃ ፈቃድ ለማደስ ወደ ማእከሉ መምጣታቸውን ጠቁመው ቀደም ሲል ከሁለት ቀን በላይ ይወስድ የነበረው እድሳቱ በማእከሉ ከ30 ደቂቃ ባነሰ ጊዜ ውስጥ አገልግሎቱን ማግኘታቸውን ተናግረዋል ። የሰራተኞቹም መልካም መስተንግዶ እንዲሁም ግልጽነትና ፍትሃዊነት የሰፈነበት አሰራር አስደሳች መሆኑን ጠቁመው በዚህ ረገድ ብልሹ አሰራር እንዲወገድ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ጠቁመዋል። ሌላዋ የከተማው ነዋሪ ውባየሁ ጥጋቡ በበኩላቸው የወሳኝ ኩነት መረጃዎችን ለማስፈጸም ከዚህ ቀደም ሁለት ቦታ መሄድ ይጠይቅ እንደነበር አስታውሰው በማእከሉ በሚሰጠው የተቀናጀ አገልግሎት ችግሩ መፈታቱን ተናግረዋል ። በማእከሉ ምንም አይነት መጉላላት ሳይገጥማቸው ፈጣንና ባጭር ጊዜ ውስጥ የተሳለጠ አገልግሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል።   የባህር ዳር መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት አስተባባሪ አቶ ማስረሻ ፈንታ በማእከሉ 14 ተቋማት አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል። በተቋማቱ 91 የተለያዩ አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑን አመልክተዋል። በማእከሉ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ በሚሰጠው አገልግሎት በየቀኑ እስከ 400 የሚደርሱ ደንበኞችን የማስተናገድ አቅም መፈጠሩን ተናግረዋል። ማእከሉ ስራ ከጀመረበት ከመስከረም 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁን ከ75 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ተገልጋዮች አገልግሎት መስጠቱ ተመላክቷል ።    
አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ምህዳር ለመገንባት ወሳኝ የሆነውን ብቁ የሰው ሃይል የማፍራት ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል
Aug 11, 2026 390
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 5/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ አስተማማኝ የሳይበር ደህንነት ምህዳር ለመገንባት ወሳኝ የሆነውን ብቁ የሰው ሃይል የማፍራት ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሂሚድ ገለጹ። 5ተኛው ዙር ብሄራዊ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ የታዳጊዎች የስልጠና መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መካሄድ ጀምሯል።   መርሃ ግብሩ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የሚያዘጋጀው ሲሆን በሳይበር ደህንነትና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ዝንባሌ ያላቸውን ታዳጊዎችና ወጣቶች ለማፍራት ያለመ ነው። የሳይበር ደህንነት፣ሶፍትዌር ልማት፣ኮዲንግ፣ አቪዬሽን፣የኤሮስፔስ ቴክኖሎጂ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፎች በመርሃ ግብሩ ተካተዋል። የሀርድ ዌር እና ሴኪዩሪቲ ዲዛይኖችን ማዘጋጀት የስልጠና መርሀ ግብር ሌላው የትኩረት ማዕከል ነው። የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤የኢትዮጵያን ዲጂታል ሽግግር ውጤታማ ለማድረግ የሳይበር ደህንነትን ማረጋገጥ ወሳኝ ነው። ለዚህ ደግሞ በቁ የሰው ሃይል አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፤አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሰው ሃይል የማፍራቱን ተግባር አጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል። የሰመር ካምፕ የስልጠና መርሃ ግብር የዚሁ አካል መሆኑን ጠቁመው፤ መርሃ ግብሩ የነገ የኢትዮጵያ ተስፋ የሆኑ ተተኪ ትውልድ በማፍራት ረገድ ትልቅ ድርሻ ያለው መሆኑን ተናግረዋል። የስልጠና መርሃ ግብሩ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ መጀመሩን አስታውሰው ፤ በአሁኑ ወቅት ስልጠናው በባህር ዳር፣ጅማ ፣ወላይታ ሶዶ፣ሀረማያ ዩንቨርስቲዎችን ጨምሮ በአስተዳደሩ ግቢ ውስጥ እየተሰጠ መሆኑን ጠቁመዋል።   የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) በበኩላቸው፤የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግናን እውን ለማድረግ የቴክኖሎጂ አቅሙ የተገነባ ሀገር ተረካቢ ትውልድ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህ ረገድ ኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የጀመረው ተተኪ ትውልድ የማፍራት ስራ የሚያስመሰግን ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለመርሃ ግብሩ ስኬት ዩንቨርሲቲው የሚጠበቅበትን ድርሻ እንደሚወጣ አረጋግጠዋል። ሰልጣኞችም ኢትዮጵያን የማገልገል አደራ አለባቸሁ፤ለዚህ ደግሞ ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትላችሁ ተገቢውን ክህሎት ልትጨብጡ ይገባል ብለዋል።
ስፖርት
ፒኤስጂ ከአስቶንቪላ፤ የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ፍልሚያ
Aug 12, 2026 130
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ መርሐ ግብር ዛሬ በፒኤስጂ እና አስቶንቪላ መካከል ይደረጋል። ጨዋታው ምሽት አራት ሰዓት ላይ ኦስትሪያ በሚገኘው ሬድ ቡል አሬና ይካሄዳል። የፈረንሳዩ ፒኤስጂ ለዚህ ጨዋታ የበቃው በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻሜ ላይ አርሰናልን በመለያ ምት አሸንፎ ዋንጫውን በማንሳቱ ነው። በሉሲስ ኤነሪኬ የሚመራው ፒኤስጂ ባለፈው የውድድር ዓመትም ላይ ቶተንሃምን በተመሳሳይ በመለያ ምት አሸንፎ የዋንጫው ባለቤት እንደነበር የሚታወስ ነው። በሌላ በኩል አስቶን ቪላ በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ መሪነት በዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ የጀርመኑን ፍራይበርግ 3 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ለዛሬው ጨዋታ በቅቷል። በታሪክ አስቶን ቪላ እ.ኤ.አ በ1982 ባርሴሎናን አሸንፎ ዋንጫውን አንዴ ጊዜ አንስቷል። ፒኤስጂ እና አስቶን ቪላ ከዚህ ቀደም በአውሮፓ መድረክ የተገናኙት እ.አ.አ 2024/25 የሻምፒዮንስ ሊግ ሩብ ፍጻሜ ላይ ብቻ ነበር። በወቅቱ ፒኤስጂ በሜዳው 3 ለ 1 ሲያሸንፍ፥ አስቶን ቪላ በቪላ ፓርክ የ3 ለ 2 ድል አስመዝግቧል። በድምር ውጤት ፒኤስጂ 5 ለ 4 በማሸነፍ ለግማሽ ፍጻሜ ያለፈ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የውድድሩ አሸናፊ መሆን ችሏል። ይህንን ጨዋታ ይበልጥ ልዩ የሚያደርገው በዳኝነት ረገድ የሚመዘገበው አዲስ ታሪክ ነው።   የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (ዩኤፋ) ጨዋታውን በዋና ዳኝነት እንዲመሩ የ34 ዓመቱን ሶማሊያዊ ዳኛ ኦማር አርታንን መርጧል። ይህም በውድድሩ የ51 ዓመታት ታሪክ ውስጥ የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታን የመሩ የመጀመሪያው የአውሮፓ ዜግነት የሌላቸው ዳኛ ያደርጋቸዋል። የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የክለቦች ውድድር አሸናፊዎችን የሚያገናኝ የዓመቱ ማጠቃለያና አዲስ የውድድር ዘመን መክፈቻ መርሐ ግብር ነው። ጨዋታው መደበኛው 90 ደቂቃ በአቻ ውጤት ከተጠናቀቀ፥ ወደ ተጨማሪ 30 ደቂቃ ሳይሄድ በቀጥታ ወደ መለያ ምት ያመራል። የጨዋታው አሸናፊው ቡድን የአምስት ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ሽልማት ሲያገኝ፥ ተሸናፊው ደግሞ አራት ሚሊዮን ዩሮ ወደ ካዝናው ያስገባል። የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ሪያል ማድሪድ ሲሆን ስድስት ጊዜ ዋንጫውን አንስቷል። ባርሴሎና እና ኤሲ ሚላን በተመሳሳይ በአምስት ዋንጫዎች ይከተላሉ።
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር አባል ሆነች
Aug 10, 2026 728
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 4 /2018(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር (World Boxing) ባወጣው መረጃ መሰረት የማህበሩ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ ኢትዮጵያን ጨምሮ የስድስት አገራትን የአባልነት ጥያቄ ማፅደቁን አሳውቋል። ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ቦክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ እያሱ ወሰን ባስተላለፉት መልዕክት፣ ኢትዮጵያ ማህበሩን በመቀላቀሏ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። አክለውም፣ ይህ ለኢትዮጵያ የኩራት ጊዜ ብቻ ሳይሆን፣ እንደ አንድ የአፍሪካ የቦክስ ቤተሰብ ለሁላችንም የደስታና የክብር ወቅት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ፕሬዚዳንቱ አያይዘውም በአፍሪካ ስፖርቱን የሚያጠናክር እያንዳንዱ እርምጃ ለሁሉም ድል መሆኑን ጠቅሰዋል። ለዚህ ታሪካዊ ምዕራፍ መሳካት አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ሁሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ፕሬዝዳንቱ አዲሱ ምዕራፍ ለአፍሪካ ቦክስ ታላላቅ እድሎችንና ስኬቶችን ይዞ እንደሚመጣም ያላቸውን ምኞት መግለጻቸውን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ቻድ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ላይቤሪያ፣ የመን እና ኩዌት ሌሎች የዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር አባል የሆኑ ሀገራት ናቸው። የዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር (World Boxing) የተቋቋመው እ.ኤ.አ. አፕሪል 2023 ነው። ማህበሩ በአዲስ መልክ የተቋቋመው የቀድሞው ዓለም አቀፍ የቦክስ ማህበር (IBA) የአሰራር እና የሙስና ችግሮች ስለነበሩበት፣ ቦክስ በኦሊምፒክ ስፖርትነት የመቀጠል እድሉን ለማስጠበቅ በሚል ዓላማ ነው። ዋና መስሪያ ቤቱን በስዊዘርላንድ ያደረገው የዓለም አቀፉ የቦክስ ማህበር (World Boxing) ዛሬ አባልነታቸው ተቀባይነት ያገኙትን ጨምሮ 168 አባል ሀገራት በስሩ ይዟል።
አካባቢ ጥበቃ
ዩኒቨርሲቲው በብዝሃ ህይወት እና ዘላቂ የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ረገድ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች በምርምር እንዲፈቱ እያገዘ ነው
Aug 11, 2026 268
ሮቤ፤ ነሐሴ 5/2018(ኢዜአ)፡- የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በብዝሃ ህይወት እና ዘላቂ የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃና እንክብካቤ ረገድ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶች በምርምር ተለይተው እንዲፈቱ የበኩሉን ድርሻ እየተወጣ መሆኑን ገለጸ። የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት የጎባ ቅርንጫፍ ጋር በመቀናጀት "ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሀሳብ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ዛሬ አካሄደዋል።   የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት በዛብህ ወንድሙ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው ለአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬት በየጊዜው ከሚያደርገው ተሳትፎ በተጓዳኝ በዘላቂ የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ረገድ ሳይንሳዊ ምርምር እያካሄደ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው በተለይም በባሌ አካባቢ የሚከናወነው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን በሳይንሳዊ ምርምር የማገዝ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾዋል። በዩኒቨርሲቲው የሚካሄዱት ምርምሮች፣ ከችግኝ ተከላ ጋር ተያይዘው በአየር ንብረትና በአካባቢ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን በጥናት ለመለየትና መፍትሔ ለመስጠት ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ገልጸዋል።   በኢትዮጵያ ብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት የጎባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በንቲ ኦፍገሃ በበኩላቸው፣ ኢንስቲትዩቱ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ከዩኒቨርሲቲው ጋር በተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ዙሪያ ባለፉት ሦስት ዓመታት የተሰሩት ሥራዎች የዚሁ ጥረት አካል መሆናቸውን ገልጸው፤ በተለይም የተራቆቱ መሬቶች መልሰው እንዲያገግሙ በመደረጋቸው ጠፍተው የነበሩ የዱር እንስሳትና ምንጮች እየጎለበቱ መምጣታቸውን ጠቁመዋል።   በችግኝ ተከላው ከተሳተፉ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት መካከል መምህር ኡመር መሐመድኑር፣ በአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ እንደ ዜጋ በየዓመቱ ከመሳተፍ ባሻገር ችግኞቹ ፀድቀው ለውጤት እንዲበቁም የበኩላቸውን እንደሚወጡ ተናግረዋል። የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ሥራው የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋም ለኢኮኖሚ ዕድገት መፍትሄ በሚሆን አግባብ መከናወን እንደሚገባውም እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በጎባ ክፍለ ከተማ ''ስራክ ጥብቅ ደን'' አካባቢ በተካሄደው መርሐ ግብር የደን፣ የመጠለያ፣ የእንስሳት መኖና ሌሎች ችግኞች መተከላቸውን ለማወቅ ተችሏል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተከላ፣ክትትልና የፅድቀት መጠን በጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ እየተረጋገጠ ነው
Aug 10, 2026 245
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 4/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተከላ፣ ክትትልና የፅድቀት መጠን በጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ እየተረጋገጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት አስታወቀ። በኢንስቲትዩቱ የካርታ ስራ መሪ ስራ አስፈፃሚ ቴዎድሮስ ካሳሁን ለኢዜአ እንደገለጹት፥ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በሳይንሳዊ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ፣በጂፒኤስ (GPS) ልኬትና በሳተላይት ምስል ትንተና መደገፍ መጀመሩ በመረጃዎች ጥራትና በውጤታማነት በኩል ከፍተኛ ለውጥ አምጥቷል። የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂ በዋናነት የመረጃዎችን የት፣እንዴት እና መቼ የሚሉ ሶስት መሰረታዊ ጥያቄዎች በትክክል መመለስ እንደሚረዳ ተናግረዋል። እንደ አቶ ቴዎድሮስ ማብራሪያ፣በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ችግኝ የሚተከልባቸው ቦታዎች በጂፒኤስ ንባብ አማካኝነት መጋጠሚያቸው ተለይቶ የተመዘገቡና ያልተመዘገቡ ተብለው ይከፈላሉ። በቅርቡ በተካሄደው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ብቻ ከ291 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ሙሉ በሙሉ በጂፒኤስ ተለክቶና የቦታ ስፋቱ ተሰልቶ መደራጀቱን ጠቁመዋል። ይህ አሰራር ቀደም ሲል ይስተዋሉ የነበሩ የመረጃ መደጋገሞችንና የመረጃዎች መሳሳትን ሙሉ በሙሉ ማስቀረቱን ገልፀዋል። አሁን ተግባራዊ በተደረገው አሰራር መረጃው ቢሮ እንደደረሰ በሳተላይት ምስል እንደሚረጋገጥ ጠቁመው፤ በተመረጡ ቦታዎች ላይ ባለሙያዎች በአካል በመገኘት የማረጋገጥ ስራ እንዲሰሩ ተደርጓል ብለዋል። ችግኝ መትከል ብቻውን ግብ አለመሆኑን በመግለጽ፣የተተከሉ ችግኞች ማደጋቸውንና የአካባቢውን አረንጓዴነት መለወጣቸውን ለመከታተል የርቀት ቴክኖሎጂ (Remote Sensing) ትንተና ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል። ባለሙያዎች የደረቅ ወቅት የሳተላይት ምስሎችን በመጠቀም የመሬት ሽፋኑን (የከተማ፣ የእርሻ፣ የወንዝ እና የደን) የሪፍሌክታንስ (Reflectance) ዋጋ በመተንተን ትክክለኛውን የደን ሽፋን እንዲለዩ ይደረጋል ብለዋል። በዚህ ሳይንሳዊ መንገድ በተካሄደው ዳሰሳና በመስክ ማረጋገጫ ስራ፣ ቀደም ሲል 17 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን በአሁኑ ወቅት ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደጉ መረጋገጡን ገልጸዋል። ይህ ትልቅ ስኬት የተገኘው ህብረተሰቡ ባለፉት ስምንት ዓመታት ባደረገው ያልተቋረጠ ጥረትና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በተከናወኑ ስራዎች መሆኑንም አመላክተዋል። በአሁኑ ወቅት ኢንስቲትዩቱ ያዘጋጃቸውን የደን፣ የሰብልና የከተማ መረጃ ክትትልን ጨምሮ 10 ማዕከላትን በመጠቀም መረጃዎችን ለውሳኔ ሰጪዎችና ለግብርና ሚኒስቴር ተደራሽ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሮች ምቹ አካባቢን በመፍጠር የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ አስችለዋል
Aug 8, 2026 237
ጂግጂጋ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሮች ምቹ አካባቢን በመፍጠር የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ አስችለዋል። 3ኛው ዙር የአካባቢ ብክለት መከላከል ክልል አቀፍ ንቅናቄ ''ፅዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' በሚል መሪ ሐሳብ በጂግጂጋ ተካሄዷል። በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኢብራሂም ኡስማን እንደገለጹት፣ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሮች ምቹ አካባቢን በመፍጠር የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ አስችለዋል። ጽዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግም የፕላስቲክ ነክ ተረፈ ምርቶችን፣ የደረቅና ፈሳሽ ቆሻሻ ብክለትን በመከላከል በውሃ እና አፈር ላይ እየተፈጠረ ያለውን ተጽዕኖ ለመቀነስ የወጡ ህጎችና መመሪያዎችን ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ አክለውም የቆሻሻ ማስወገጃ ዘላቂ ሥርዓቶችን በመገንባት ከተሞች ምቹና ጽዱ እንዲሆኑ በትኩረት እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። የአከባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ በበኩላቸው፣ መርሃ ግብሩ ባለፉት ሁለት ዙሮች የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከርና፣ በማስፋት፣ ጤናማና ንጹህ አካባቢን የመፍጠር ተግባሩን ለማጠናከር ያለመ መሆኑን አመልከተዋል። ''እንዲሁም አካባቢያችንን ለመጠበቅ እና ለመጪው ትውልድ ፅዱ ኢትዮጵያን ለማውረስ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ለማረጋገጥም ጭምር ነው'' ብለዋል። 3ኛው ዙር የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በቀጣዮቹ ሶስት ወራት የሚተገበርና በዋናነት የፕላስቲክ ብክለትን በመከላከል፣ አደገኛ ኬሚካሎችንና ቆሻሻዎች አያያዝን፣ እንዲሁም የድምፅ ብክለትን የመከላከል ተግባራት እንደሚከናወንም አክለዋል። እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ ገለጻ፤ ፅዱ ኢትዮጵያ በመንግስት ብቻ የሚከወን ባለመሆኑ በየቤታችን፣ በየትምህርት ቤቱ፣ በየመሥሪያ ቤቱና በፋብሪካዎች የምንፈጽማቸው በጎ ተግባራት ተደምረው ትልቅ ሀገራዊ ለውጥ ያመጣሉ። በዚህም ሁሉም የመንግስት ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪል ማህበረሰብ፣ የሚዲያ ተቋማት፣ የሴቶችና የወጣቶች ማህበራት እንዲሁም እያንዳንዱ ዜጋ የዚህ ሀገራዊ ንቅናቄ ባለቤት በመሆን በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል። የሶማሌ ክልል የአካባቢ ጥበቃና ገጠር መሬት አስተዳድር ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ሙህየዲን አብዲ በበኩላቸው በክልሉ ባለፉት ዓመታት በጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄዎች በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ጽዱ አካባቢ ለመፍጠር እየተከናወኑ የሚገኙ በርካታ ተግባራትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የቢሮ ኃላፊው አረጋግጠዋል። በመርሃ ግብሩም በክልሉ ፕላስቲክን በመከላከል፣ መመሪያዎችን በመተግበርና ቆሻሻን በአግባቡ በማስወገድ ውጤታማ የሆኑ ከተሞች የእውቅና መስጠት ሥነ-ሥርዓት ተካሄዷል።
አረንጓዴ አሻራ ለትውልድ የሚተላለፍ ጠንካራ የአካባቢ ጥበቃ ባህል ነው
Aug 8, 2026 246
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 2/2018 (ኢዜአ) ፦አረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያውያን ለትውልድ የሚያስተላልፉት ጠንካራ የአካባቢ ጥበቃ ባህል ነው ሲሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮርፖሬት አገልግሎት ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ ገለጹ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች፣ ’’ተስፋን እንትከል’’ በሚል መሪ ቃል በእንጦጦ ሸገር ፓርክ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ አከናውነዋል።   የባንኩ የኮርፖሬት አገልግሎት ኤክስኪዩቲቭ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ኤፍሬም መኩሪያ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ አረንጓዴ አሻራ ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮችን መቋቋም ያስችላል። በኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ ስራዎች የታዩ ተጨባጭ ለውጦች መኖራቸውን አንስተው፣ በተለይም ለአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። የተፈጥሮ ስነ ምህዳሯ የተጠበቀና አረንጓዴ አገርን ለቀጣይ ትውልድ ለማስረከብ ችግኝ መትከልና መንከባከብ ወሳኝ ሀገራዊ ሀላፊነት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ባንኩ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከ250 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል ማቀዱን ገልጸው፤አረንጓዴ አሻራ ለቀጣይ ትውልድ ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ጠንካራ የኢትዮጵያዊያን የአካባቢ ጥበቃ ባህል መሆኑን ተናግረዋል። የባንኩ አመራሮች እና ሰራተኞችም በዚህ ታላቅ ሀገራዊ መርሀግብር የሚያደርጉትን ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 560
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 566
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች።   ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 847
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 1340
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
ለብዙዎች ብርሃን የፈነጠቀው የገጠር ሞዴል መንደር!
Aug 9, 2026 557
ለብዙዎች ብርሃን የፈነጠቀው የገጠር ሞዴል መንደር! በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን ) የገጠሩ ማህበረሰብ የጨለማ ኑሮ የተፈረደበት ይመስል ኑሮውን ማሻሻል ሳይችል እልፍ ዓመታት ተቆጥረዋል፤ ለዘመናት መብራትና ውኃ ለማግኘትና ከቴክኖሎጂ ጋር ተቀራርቦ ለመኖር ወደ ከተማ መሰደድ ብቸኛው አማራጭም ነበር። የከተሜው ዋልታ የሀገር ኢኮኖሚ መሠረት የሚወሰንበት የአራሹ ገበሬ የኑሮ ደረጃ ባህላዊውን የአኗኗር ዘዬ ባለመልቀቁ ደስተኛ ጊዜ የሚያሳልፍበት ሂደት አድካሚ እንደሚሆን ግልጽ ነው። የገጠሬው የተበታተነ የአኗኗር ሥርዓትም ለገጠሬው አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን ለማሟላት አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል፤ የእዚህን የህብረተሰብ ክፍል ምርቱን እንጂ ኑሮውን የጠየቀ አልነበረም ቢባል ግነት አይሆንም።   ቀደም ሲል በነበሩ መንግስታት ከተማን እንጂ ገጠርን ማዘመን የሚያስብ ስለመኖሩ ያጠራጥራል፤ ይህም በሀገሪቱ ለኢፍትሐዊ ዕድገት የራሱን ተጽዕኖ ሲያሳደር ቆይቷል። የመደመር መንግሥት ግን ይህን ቀይሮታል። ሀገር የመምራት ኃላፊነት ከተረከበበት ጊዜ አንስቶ በከተማና በገጠር ሁለንተናዊ ብልጽግናን በማረጋገጥ በዜጎች የኑሮ ሥርዓት ላይ ለውጥ ማምጣትን ግብ አድርጎ እየሰራ ነው ከተሜነት ብቻውን አድጎ የገጠሩ ማኅበረሰብ በቀድሞ የኑሮ ደረጃ ላይ ከሆነ የተሟላ ዕድገት ማምጣት አይቻልም የሚል ጽኑ እምነት አለው። በእዚህም ከተማና ገጠርን ለማቀራረብ በገጠር ትራንስፎርሜሽንን የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን ቀርጾ መተግበር ከጀመረ ከራርሟል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን አንዱ አካል የሆነው የገጠር ሞዴል መንደር በአርሶ አደሮች ዘንድ የሚጨበጥ ተስፋን ይዘው ከመጡ ኢኒሼቲቮች በግንባር ቀደምነት የሚጠቀስ ነው። ከተስፋ ተሻግረው በዚህ ሞዴል መንደር የነዋሪነት ዕድልን ያገኙት ደግሞ ብርሃን አይተዋል፤ የትናት አኗኗራቸውን የቀየረ አዲስ ዛሬን በእጃቸው አድርገዋል፤ ነገን አልቀው መመልከት የግብርና ተግባራቸው አንዱ አካል ሆኗል። በአዲሱ መንደራቸው ዛሬ የሚያፈስ ቤት የለም፣ የእንስሳት ቆሻሻ ሽታ በአፍንጫቸው አይገባም፣ በሚቆረቁር እንጨት ወይም መደብ ላይ አይቀመጡም፤ የከተሜው መዘነጫ ሶፋ በሳሎናቸው ተከስቷል። ጓሮዎቻቸው ሁሉ ሙሉ እንደሆኑ አፍ አውጥተው የሚያወሩ ናቸው። በዚህ ቆስጣ፤ በዛ በኩል ጎመንና ቀይስር፤ ዘውር ሲሉ ደግሞ ከአስር የሚልቁ ዘመናዊ የንብ ቀፎዎች፤ በአንድ ክፍል ደግሞ እናት ላም ከጥጃዋ ጋራ፣ የእንቁላል ዶሮ ከሥጋ ዶሮ ጋር ሁሉንም በአንድ ጊቢ ውስጥ ያገኛሉ። ምን ይሄ ብቻ አቮካዶ እና ፓፓያ፣ ሙዝና እንሰት፣ በርበሬና ሽንኩርት ሳይቀር ለተትረፈረፈ የአርሶ አደር ማዕድና ገበያ ራሳቸውን አዘጋጅተዋል።   አርሶ አደር ኃይሉ ሞትንሞስ በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ የጌሊት ሞዴል መንደር ነዋሪ ናቸው። እርሳቸው "መንግስት ጨለማችንን ገፎ ብርሃን አሳየን" ሲሉ በጠንካራ ቃላት የገጠር ሞዴል መንደር ፕሮጀክት ያመጣላቸውን በጎ ነገር ይገልጻሉ። እውነት ነው ያላዩትን ብዙ ነገር አሳይቷቸዋል። ያም ብርሃን ቤት ውስጥ የሚበራ ብቻ ሳይሆን በሕይወታቸው፣ በነገ ተስፋቸውና በኢኮኖሚያቸው ላይ የፈነጠቀ ብርሃን ነው። ዛሬ ያሉበትን ህይወትም "ለእኔ አዲስ ነገር ነው። አይቼው አላውቅም፤ መቼም በራሴ ሀሳብ አላደርገውም ነበር።" ሲሉ ይገልጻሉ። መንግስት አበራልኝ ያልኩት በእጄ ያለኝን ያላየሁትን ዕድል ስላሳየኝ ነው በማለትም ሀሳባቸውን ይቀጥላሉ። እኛ ሀብት አለን፤ ሀብታችንን የምንጠቀምበት መንገድ ግን ትክክል አይደለም። ይልቁንም የምናባክነው ይበዛል በማለትም የቀደመ ሕይወታቸውን እያሰቡ ይቆጫሉ። አሁን ግን ብዙ ተገነዘብኩ የሚያስብል የመደመር መንግስት በመኖሩ አዲስ ሕይወት በአዲስ ተስፋ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። እርግጥ ነው የገጠር ሞዴል መንደር ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያለው ነው። ለአብነትም የማኅበራዊ አገልግሎት መስጫ መሠረተ ልማት ዝርጋታን ማንሳት ይቻላል። የተሠሩ ሞዴል መንደሮች በመጀመሪያ የመንገድ መሠረተ ልማት ተጠቃሚ የመሆን ዕድል ገጥሟቸዋል። በመቀጠል ንጽሕናው ያልተረጋገጠ የመጠጥ ውኃ ወንዝ ወርዶ ከመቅዳት ተቆጥበው በመንደራቸው የተገነባውን የከረሰ ምንድር ውሃ ከቧንቧ ቀድተው መጠጣት አስችሏቸዋል። በእሳት እና ኩራዝ ጭስ ሲሰቃዩ የነበሩ ዓይኖቻቸው ዛሬ ከሶላር ቴክኖሎጂ የመነጨ ብርሃን ማየት ጀምረዋል። ብርሃን ብቻ አይደለም ለወትሮ ለገበያ ወደ ከተማ ብቻ ሲወጡ ይመለከቱ የነበረውን ቴሌቪዥን ዛሬ በቤታቸው አስገብተው የመረጃና የመዝናኛ ዓለምን ተቀላቅለዋል። አርሶ አደሮቹ ቴሌቭዥንን ከመዝናኛነት ይበልጥ ለመረጃ እንደሚጠቀሙት ያነሳሉ። ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታን በዜና ተከታትሎ መረዳት፣ የገበያ ሁኔታን ማወቅ፣ የግብርና ሥራ ተሞክሮን መቅሰምና የአየር ንብረት ሁኔታን ጨምሮ ለሕይወታቸው ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎችን የሚያገኙት ከቴሎቪዥን መስኮት እንደሆነ ይናገራሉ።   በጓሯቸው የተትረፈረፈ የሌማት ትሩፋት ምርት መሰብሰብ የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታ ደግሞ የምግብ ዋስትናቸውን ለማረጋገጥ የጎላ ጠቀሜታ አለው። በተለይ መንግስት በጓሯቸው ጥምር እርሻ እንዲያከናውኑ ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ የነገ ኢኮኖሚያቸውን በአስተማማኝ መሠረት ላይ የሚያስቀምጥ ነው። ከተማን መናፈቅን ያስቀረው የገጠር ሞዴል መንደር ያኔ ከጅምሩ አመኔታን አላገኘም። የቦታና የአካባቢ ቁሳቁስ ለማቅረብ ዝግጁ እስካለመሆን የደረሱ አርሶ አደሮችም ነበሩ። በወቅቱ ጉዳዩን እንደፌዝ አዩት። ዛሬ ግን ውጤቱን በአግራሞት በዐይናቸው ተመለከቱ። የተናገረውን የሚከውን፤ የጀመረውን የሚጨርስ የመደመር መንግሥትን ተጨባጭ ስራዎች በማረጋገጥ እንደ ትንግርት ቆጠሩ። ዛሬ በየአካባቢው ያሉ አርሶ አደሮች በቁጭት ተሞልተው መንደራቸውን ወደዚህ የሞዴል መንደር እሳቤ ለመቀየር ተነሳስተዋል። የጌሊት ቀበሌ አርሶ አደሮቹ መኮንን አርዶ እና ነጻነት ተስፋሁን ለዚህ ተጠቃሾች ናቸው። ያዩትን ተሞክሮ በራስ አቅም በመንደራቸው ለማስፋፋት ማቀዳቸውን ተናግረዋል። ከተማ ሄደን የምናወጣውን ወጪና የምናባክነውን ጊዜና ጉልበት በማስቀረት እዚሁ መዝናናት የምንችልበትን ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል።   "ይህ ዕድል ለእኛ ለአርሶ አደሮች በታሪክ የሚነገር ትልቅ አጋጣሚ ነውም" ይላሉ። በጤዛ እየራስን እንጓዝበት የነበረው መንገዳችን ዛሬ ሰፍቷል። ተሽከርካሪ በደጃችን ስለሚያልፍም ምቹ ዕድልን ይዞልን መጥቷል። ይህን ጅምር ተግባር ወደ ላቀ ውጤት ማሸጋገር የእኛ ድርሻ ነውና ጠንክረን እንሠራለንም ብለዋል።   ይህን ዕድል ወደ ትልቅ አቅም ለመቀየር መዘጋጀታቸውን የገለጹት ደግሞ በቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ የሸሸቃ ሞዴል መንደር ተጠቃሚ አርሶ አደር አልዓዛር ዘርክናንስ ናቸው። የዶሮና የከበት እርባታን እንዲሁም ዘመናዊ የንብ ማነብ ሥራን ከመደበኛው የእርሻ ሥራ ጋር አስተሳስረው በመሥራት ከቤተሰብ ፍጆታ ተርፎ ለገበያ የሚበቃ ምርት ለማምረት እየተዘጋጁ ነው።   ይህም የገቢ አቅማቸውን ከማሳደግ ባለፈ ልጆቻቸው ወተትና የወተት ተዋጽኦ በቤታቸው እንዲያገኙ ያደርጋል። ማር፣ እንቁላል እና ሥጋ እንዳያምራቸው የሚያደርግ ትልቅ ኢኒሼቲቭም ነው። አንዱ ቢጎድል በሌላው እየሞሉ የሚኖሩበትን የሥራ መስክ አጠናክረው ለውጤት አብቅተው ለተሻለ ለውጥ እንደሚሠሩ አክለዋል። የአርሶ አደር እናቶች ዘምቢል ይዘው አትክልትና ፍራፍሬ ሸመታ ወደ ገበያ ማቅናት የለባቸውም። ይልቁንም ከጎሮቸው ወደ ገበያ ይዞ መውጣት የኑሮ ዘዬያቸው ወግ ነው። ወይዘሮ መሠረት ማሞ በሸካ ዞን የኪ ወረዳ የበቆ ሞዴል መንደር ነዋሪ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም ያልለመዱትን አዲስ ሕይወት ከአዲስ ተስፋ ጋር መጀመራቸውን ከሚናገሩት መካከል ናቸው።   ትናንት ኩሽናቸው፣ መኝታቸው እንዲሁም የከብትና የዶሮ ማደሪያ በአንድ ቤት ወስጥ የተወሰነ እንደነበር ያስታውሳሉ። ዛሬ ግን ሽንት ቤትና መታጠቢያ ቤት ሳይቀር ለየብቻ የራሱ የሆነ ቤት ተገንብቶ ጽዳቱ የተጠበቀ ኑሮ መኖር ጀምረዋል። ቤታቸው ሲገቡና ሲወጡ ለዓይን ማራኪ፤ ለመቀመጥ ምቹ፤ ለመተኛትም ንጹህና ወገብ የሚያሳርፍ ሆኖ አግኝተዋል። እናም በዚህ እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ይናገራሉ። "መንግስት እንደ አባት ጎዶሏችንን ሞልቷል" ሲሉም ተደምጠዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያስጀመሩት ይህ የአርሶ አደሮችን ሕይወት ብሩህ ያደረገው የገጠር ሞዴል መንደር ኢኒሼቲቭ በመላው ሀገሪቱ በመስፋፋት ላይ ነው። ባለፉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ብቻ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል 16 ሞዴል መንደሮች በ16 ወረዳዎች ተገንብተዋል።   የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ፍቅሬ አማን እንደገለፁት ኢኒሺዬቲቩ የአርሶ አደር ኑሮ ዘዬን ከማሻሻል ባለፈ ከኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነቱ ጋር ለማቆራኘት ያስቻለ ነው። የተሻለ መኖሪያ ቤት ኖሮት በጓሮው የሚበላ ነገር ካጣ ሕይወቱ ትርጉም ያለው ለውጥ አያመጣም። ይህም በመሆኑ ቤቶቹን ከእያንዳንዱ የግብርና ልማት ዘርፎች ጋር በማጣመር እንዲገነቡ የተደረገው። ይህም የአርሶ አደሩን የአኗኗር ዘይቤ ከመቀየር ባለፈ በምግብ ራስን የመቻል ሀገራዊ ስትራቴጂን የሚያጠናክርና ገበያን የማረጋጋት ዓላማን የያዘ ጭምር ነው። በገጠር ሞዴል መንደር ግንባታ የተገኘው መልካም ውጤት በቀጣይ በሁሉም ወረዳዎች የሚስፋፋ ሲሆን በዞን እና ወረዳ መዋቅሮች ድጋፍና ክትትል በቀበሌ ደረጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጠል አንስተዋል። ይህ ኢኒሼቲቭ የሀገራዊ ብልጽግና ጉዞ አንዱ አቅም ነው። የተደመረ የማኅበረሰብ ብልጽግና ሀገርን ከፍ ያለ የዕድገት ማማ ላይ ያስቀምጣታል። እነሆ የክልሉ አርሶ አደሮች የአካባቢያቸውን ጸጋ ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚ የሚቀይሩበት መስክ በሞዴል መንደር ምክንያት እጃቸው ላይ ደርሷል። አርሶ አደሮቹ እንዳሉትም በብዙ መንገድ ጨለማ የከበበው የገጠሩ ማኅበረሰብ ሕይወት ዛሬ ብርሃን ማየት ጀምሯል። ይህ የብርሃን ፋና እየተቀጣጠለ ወደ ብዙኃኑ ሊደርስ የሁሉንም ፍላጎት አነሳስቷል። ሥሩ ከማለት ይልቅ ሠርቶ ማሳየትን የሚያስቀድመው የመደመር መንግስት የፈጠራቸው የገጠር ሞዴል መንደሮች ዛሬን ብቻ ሳይሆን ነገን በዘላቂነት የሚያሳምሩ ናቸው። ሰላም እንሰንብት!  
ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የአፍሪካ ኃያል ሀገር እየሆነች ነው-ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ፈርስት ፖስት
Aug 7, 2026 499
አዲስ አበባ፤ነሐሴ 1/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት የመጪው ዘመን የአፍሪካ ኃያል ሀገር ወደመሆን እየተሸጋገረች ነው ሲል ታዋቂው የህንድ ሚዲያ ፈርስት ፖስት ዘግቧል። ፈርስት ፖስት ሚዲያ ኢትዮጵያን በተመለከተ በሠራው ትንታኔው የሰው ዘር መገኛ፣የጥንታዊ መንግስታት ምድር፣የንግድ መስመሮች እና ከፍ ያለ የአፍሪካ ታሪካዊ መሰረት ያላት ሀገር መሆኗን አውስቷል። ሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ወደ ስልጣን ከመጡ ወዲህ ከቀድሞ ገናና ታሪኳ እኩል ታላቅ የሆነ አዲስ ምዕራፍ ለመገንባት በትጋት ላይ መሆኗን አንስቷል። በጠቅላይ ሚኒስትሩ መሪነት በቀጣናው እና የአፍሪካ ኃያል ሀገር መሆን የሚያስችላትን እንዲሁም የአህጉሪቱን የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚበይንና የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት እየሠራች መሆኗንም እንዲሁ። ለረጅም ዓመታት ዓለም ኢትዮጵያን የሚያውቃት በጦርነት፣በድርቅ እና በፖለቲካዊ አለመረጋጋት እንደነበር በማስታወስ፥ዛሬ ግን ሀገሪቱ ይህንን የተዛባ ትርክት በኢነርጂ መሠረተ ልማት፣ በአቪየሽን፣ በማዕድን እና በዲጂታል ኢኮኖሚ አስደማሚ ለውጦች ለመቀየር እየሠራች ነው ብሏል። ኢትዮጵያ ፈተናዎችን ተሻግራ እንዴት በአፍሪካ ፈጣን ዕድገት ካላቸው ኢኮኖሚዎች ቀዳሚዋ ሆና ልትቀጥል ቻለች? የሚለውን ጥያቄ በማንሳትም በዝርዝር መልሶቹን ያብራራል። የዚህ ዋና ጥያቄ ዝርዝር ምላሽ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት እየተተገበሩ የሚገኙ የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስኑ ግዙፍ ፕሮጀክቶች ላይ ነው ያለው ሲል አንስቷል።   • የመጀመሪያው የኢነርጂ አብዮት እና ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነው። በዚህ የኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ጎልቶ የሚነሳው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሲሆን፣ ከ5 ሺህ ሜጋዋት በላይ የማመንጨት አቅም ያለው የአፍሪካ ትልቁ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ፕሮጀክት መሆኑን ፈርስት ፖስት በዘገባው ጠቅሷል። ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ መሻቶች መሰረት፣የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የውጭ ምንዛሬ እና የቀጣናዊ ተጽዕኖ መፍጠሪያ አቅም መሆኑንም አብራርቷል። የሕዳሴ ግድብ ልዩ የሚያደርገው የኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ከዓለም ባንክ ወይም ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም አንድ ሳንቲም ሳይበደር በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደም፣ ላብና ገንዘብ የተገነባ አፍሪካውያን በራሳቸው ህልማቸውን ማሳካት እንደሚችሉ ያሳየነው ብሏል። ለኢትዮጵያውያን ግድቡ ከኮንክሪት እና ከተርባይን በላይ ትርጉም አለው ያለው ይህ የፈርስት ፖስት ዘገባ፥ እጅግ የላቀ እራስን የመቻል እና የኢኮኖሚ ነፃነት ማሳያ ሐውልት መሆኑንም ተንትኗል። ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ለኬንያ፣ ለጂቡቲ እና ለሱዳን በመሸጥ ኤሌክትሪክን ወደ ከፍተኛ ገቢ ማመንጫነት እየቀየረች ከመሆኑም በላይ የመላው ምስራቅ አፍሪካ ቀጣናዊ የትስስር ማዕከል ሆናለች ነው ያለው። • የኢትዮጵያ የዕድገት ምሰሶ አቪዬሽን እና ቀጣናዊ ትስስር ኢነርጂ ብቻውን ኢኮኖሚያዊ አቅምን አይገነባም፤ ይልቁንም ኢነርጂ ኢንዱስትሪን ያነቃቃል፣ ትስስር ዓለም አቀፍ ንግድን ይመግባል ያለው ፈርስት ፖስት፥የአፍሪካ ግዙፉ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ለላቀ የዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት ጉዞ መጀመሩን አንስቷል። በ12 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ግንባታው እየተፋጠነ የሚገኘው የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በየዓመቱ እስከ 110 ሚሊዮን ተጓዦችን እና ወደ 4 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ የዕቃ ጭነት ማስተናገድ አቅም አለው። ሙሉ በሙሉ ግንባታው ሲጠናቀቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከታላላቅ የአቪዬሽን ማዕከላት አንዱ ይሆናል ብሏል።   ይህ ፕሮጀክት የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ የዲፕሎማሲ መናኸሪያ የሆነችውን አዲስ አበባንና አፍሪካን፣ከሌሎች የዓለም ክፍሎች የሚያስተሳስር ዋና የመተላለፊያ ማዕከል እንደሚሆንም ተገልጿል። ስለዚህ አዲሱ የቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ለንግድ፣ ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም፣ ለዓለም የዲፕሎሲ ትብብር ጉልህ ሚና እንዲያበረክት ታስቦ እየተገነባ ነው ብሏል። • የማዕድን ኢንቨስትመንትና በምግብ ራስን መቻል በሌላ በኩል ከኢትዮጵያ መሬት በታች ላለው የማዕድን ሀብቷ ትኩረት በመስጠት የልማት አብዮት እያካሄደች ስለመሆኑም ተንትኗል። ሀገሪቱ የወርቅና ሌሎች ማዕድናት ማውጫ ሜጋ ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት አዳዲስ የውጭ ምንዛሬ ምንጮችን እያፈራች የማዕድን ኢንዱስትሪዋን እያሳደገች ነው። ወርቅ በፍጥነት ከኢትዮጵያ ቀዳሚ የወጪ ንግድ ምርቶች አንዱ በመሆን ለረጅም ጊዜ በግብርና ላይ ብቻ ጥገኛ ሆኖ የቆየውን ኢኮኖሚ ወደ ብዝኃ ዘርፍ እያሸጋገረ ይገኛል። በሌላ በኩል በምግብ ራስን ከመቻል ውጭ የትኛውም ኢኮኖሚያዊ ለውጥ የተሟላ ሊሆን አይችልም ያለው የፈረስት ፖስት ዘገባ፥ ግብርና የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት መሆኑን ጠቅሷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሚመራው መንግሥት ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን እንድትችል በጀመረው የለውጥ ጉዞ አስደማሚ ውጤት እያመጣ ነው ብሏል። ከዚሁ ጋር በተያያዘም ከጉባ ብስራቶች አንዱ የሆነውና በሶማሌ ክልል እየተገነባ የሚገኘው የማዳበሪያ ፋብሪካ ፕሮጀክት በየዓመቱ 3 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ዩሪያ ማዳበሪያ ማምረት የሚችል ነው። ይህም ከውጭ የሚገባውን ማዳበሪያ ጥገኝነት በመቀነስ የኢትዮጵያን የግብርና ምርታማነት ለማሳደግ እንደሚያስችል አብራርቷል። "የምግብ ዋስትና የእኛ ስትራቴጂካዊ ጣልቃ ገብነት ነው።ያንን ግብ እውን ለማድረግ ግብአቶች ላይ መስራት አለብን።በግብአት ላይ መስራት ካልተቻለ የምግብ ዋስትናን እውን ለማድረግ መንገድ የለውም" የሚለውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ በማካተት ዘገባው ሰፊ ሽፋን ሰጥቷል። ዲጂታላይዜሽን እና የኢንቨትመንትና የገበያ ማሻሻያዎች በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ለውጥ ወደ ዲጂታልም እየተሸጋገረ ነው።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እንደተናገሩት የ5 ሚሊዮን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ከዕቅዱ ቀድም ከመሳካቱም በላይ በርካታ ወጣቶች የዲጂታል እውቀት ባለቤት አድርጓል።   በተመሳሳይ የዲጂታል ትስስር እየሰፋ ሲሆን የ4ጂ እና 5ጂ አገልግሎቶች በበርካታ ከተሞች ተደራሽ ሆኗል። ኢትዮጵያ ለበርካታ አስርት ዓመታት ተዘግተው የቆዩ እንደ ቴሌኮሙኒኬሽን፣ ባንክ እና የካፒታል ገበያዎች ያሉ ዘርፎችን ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ማድረጓንም አድንቋል። የካፒታል ገበያን መጀመሯም የግል ካፒታል ልውውጥን በማጎልበት ለኢኮኖሚ ዕድገት ትልቅ ሚና እንደሚጫወት ተንትኗል። እነዚህ ማሻሻያዎች በአጠቃላይ በመንግስት ቁጥጥር ስር ከነበረው የኢኮኖሚ ወደ ግል ዘርፍ ኢንቨስትመንት እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚ መሰረታዊ ለውጥን እየተገነባ መሆኑን ያሳያሉ ነው ያለው። ኢትዮጵያ ካላት የጂኦ ፖለቲካ ስትራቴጂካዊ አቀማመጥ አኳያ እድልና ፈተናዎች ከፊቷ መሆናቸውን በማንሳት፥ አዲሱን የዓለም አቀፍ የትብብር ጥምረት ብሪክስ አባል መሆኗን አውስቷል። ከቻይና፣ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት፣ ከምዕራባውያን አጋሮችና ከአፍሪካ ኢንቨስተሮች ኢንቨስትመንትን እየሳበች እንደምትገኝም እንዲሁ። ኢትዮጵያ ጎራ ሳትለይ ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር ትብብሯን እያጠናከረች ነው ብሏል። ዓለም ኢትዮጵያን የምታስታውሰው በጦርነት ቢሆንም፥ኢትዮጵያ ዓለም በአዲሱ የለውጥና የስኬት ጉዞዋ እንዲያስታውሳት እየሠራች ነው። ለዚህም በመላው ሀገሪቱ በሁሉም ዘርፍ ግዙፍ የኢኮኖሚ ሽግግር እየተካሄደ ሲሆን፥ ይህ የኢትዮጵያ ጉዞ ለቀጣዮቹ ዓመታት የቀጣናውንና የአፍሪካን ኢኮኖሚያዊና አጠቃላይ ገጽታ በአዲስ መልኩ የሚቀርጽ ነው ሲል ፈርስት ፖስት ዘገባውን አብራርቷል።
ያቀደችውን በተግባር የምታሳካ ታላቅ ሀገር
Aug 3, 2026 808
የአንድ ሀገር ታላቅነት ከሚለካባቸው ጉዳዮች አንዱ የተያዙ ሀገራዊ እቅዶችን በተግባር የመለወጥ አቅም ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያም በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው አዲስ ታሪካዊ ስኬት፣ ሀገሪቱ ያቀደችውን በተግባር ማሳየት የምትችልና ትልልቅ ህልሞችን የመተርጎም አቅም ያላት ታላቅ ሀገር መሆኗን ለመላው ዓለም በተግባር ያስመሰከረ ነው። ይህ በአንድ ጀምበር የተከናወነ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በርካታ ጥልቅ ትርጉሞችን የያዘ ነው፡ በአንድ ጀንበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል ግዙፍ የሎጂስቲክስ፣ የዝግጅትና የህዝብ ንቅናቄ ስራን ይጠይቃል።   ይህ ስኬት ሀገሪቱ ማንኛውንም ታላቅ አገራዊ እቅድ አቅዳ እስከ መጨረሻው የትግበራ ምዕራፍ ድረስ በብቃት የመምራትና የማስተባበር ተቋማዊና ህዝባዊ አቅም እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ዕድሜ፣ ጾታ፣ ወይም ልዩነት ሳይለያያቸው በአንድ ቀን ለተመሳሳይ አገራዊ ዓላማ መቆማቸው፣ ኢትዮጵያውያን ለጋራ እድገታቸውና ለሀገራቸው የወደፊት ተስፋ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎትና አንድነት አሳይቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት ዋና ስጋት በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ እርምጃ ለችግሩ መፍትሔ በመስጠት ረገድ የዓለም አቀፍ መሪነቷን ያስመሰከረችበት አጋጣሚም ጭምር ነው። ይህ ስኬት ሀገሪቱ የገጠሟትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች ተሻግራ፣ አቅሟን አስተባብራ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደምትችል ለዜጎቿም ሆነ ለውጭው ዓለም የሰጠችው ትልቅ የራስ መተማመንና የተስፋ መልእክት ነው። በአጠቃላይ፣ በአንድ ጀምበር የተከናወነው ይህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ አርቆ የማሰብና የማቀድ ችሎታዋን ብቻ ሳይሆን፣ ያቀደችውንም በአንድነትና በቁርጠኝነት ወደ መሬት በማውረድ በተግባር የምታሳይ ታላቅ ሀገር መሆኗን በግልጽ ያረጋገጠ አኩሪ ተግባር ነው።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ ትንሳኤ ብስራት!!
Aug 2, 2026 614
በሐዊ አጫሉ መግቢያ፡- የኢንዱስትሪ ዘርፍ የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬን ከሚወስኑ ዋነኛ የብልፅግና ማረጋገጫ ምሰሶዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ዘርፉ ምርትን ከማሳደግ ባሻገር የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን የሚያፋጥን የልማት ሞተር ነው። ኢትዮጵያም ከግብርና መሠረት የተነሳ ኢኮኖሚዋን ወደ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪና ሁሉን አቀፍ የምርት ሥርዓት ለማሸጋገር ከምታደርገው ጥረት መካከል ኢንዱስትሪውን በቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶነት በማካተት እየሰራችበት ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ቴክኖሎጂ አምስት ዐበይት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ምሰሶዎች ተመሥርቶ እየተመራ ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ ኢንዱስትሪው የምርት አቅምን በማሳደግ የግብርና ምርቶችን ወደ ተጨማሪ እሴት በመቀየርና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ ፋይዳ እያስገኘ ነው። ይህንን ሽግግር እውን ለማድረግ የምርት አቅምን ማሳደግ፣ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን እና የሰው ኃይል ልማት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ የቀድሞ ገጽታ፤ ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ለውጥ መንገድ!! በቀደሙት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተለያዩ ዕድሎችንና ፈተናዎችን በማስተናገድ በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል። ሀገሪቱን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር በተደረጉ ጥረቶች የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተዋል። እነዚህ ፓርኮችም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በግብርና ምርት ማቀነባበር ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተሞከረበት ወሳኝ ምዕራፍ እንደነበር ይታወሳል። ይሁን እንጂ ይህ ጉዞ በበቂ መሠረተ ልማት፣ በተሟላ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና በተቀናጀ የምርት ሰንሰለት እጥረት ምክንያት በበርካታ ፈተናዎች ለመውደቅ ተገዶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ውስንነት፣ ዕውቅትና ክህሎትን የተሰላበሰ የሰው ኃይል አለመኖር፣ የፋይናንስ እጥረት፣ ውስብስብና አስቸጋሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትና የገበያ ትስስር እጥረት የዘርፉን እድገት ገድበው የነበሩ ሁነኛ ተግዳሮቶች ናቸው። ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ምርታማነት፤ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ የለውጥ ፍኖት!! ባለፉት ዓመታት በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተስተዋሉ መዋቅራዊ ችግሮችን ለመፍታትና የሀገሪቱን የማምረት አቅም ለማሳደግ አዳዲስ የለውጥ አቅጣጫዎች ተነድፈው ተተግበረዋል። በተለይም ኢንዱስትሪን ከተለመደው የምርት ሥርዓት በማሻገር ወደ ተወዳዳሪ ዘመናዊና ውጤታማ የማምረቻ ማዕከል ለመቀየር የተለያዩ የፖሊሲማሻሻያዎች ተደርገዋል። የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን ማስፋት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን፣ የሰው ኃይል አቅምን ማሳደግና የግብርና-ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር በዘርፉ የተወሰዱ ሁነኛ የለውጥ እርምጃዎች ናቸው። በዚህም የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት በማጎልበት ከሀገር ውስጥ ገበያ እስከ ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ድረስ ውጤት እያስገኘ ነው። የግል ባለሃብቱ ሚና፤ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሞተር!! የኢንዱስትሪ ልማት በመንግሥት ጥረት ብቻ የሚሳካ አይደለም። የግል ዘርፉ በካፒታል፣ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂና በአስተዳደር ብቃት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ለዘርፉ ዕድገት የማይተካ ሚና አለው። በዚህ ረገድ የግል ባለሃብቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዋና አጋር እንዲሆን የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተሻሽለው እየተሰራባቸው ይገኛል። ይህም የግሉን ዘርፍ የኢንቨስትመንት በማሻሻል፣ የንግድ ሥራ ሂደቶችን በማቀላጠፍ፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋትና የምርት አቅምን በማሳደግ የግሉን ዘርፉ የምርታማነት አቅም እያጎለበተ ነው። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ የትንሳኤ ብስራት!! በሀገራችን የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውስጥ የምርትና አገልግሎት አሰጣጥን በማቀናጀት አዲስ ምዕራፍ ከከፈቱ ዐበይት ሀገራዊ መርሃ-ግብሮች መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጠቃሽ ነው። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ የማምረት ባህልን በማሳደግ ዘርፉ ወደ አዲስ የልማት ምዕራፍ የሚሸጋገርበት ሁነኛ ዕድልን ፈጥሯል። ንቅናቄው የማምረት አቅምን በማሳደግ ሥራ ያቆሙ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ መመለስ፣ የአምራቾችን ችግሮች በፍጥነት መፍታትና አዳዲስ ባለሃብቶችን ወደ ዘርፉ በመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ እያበረከተም ይገኛል። በዚህ ሂደት በፋይናንስ፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በውጭ ምንዛሬና በተቋማዊ ቅንጅት ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎች የአምራች ዘርፉን የምርታማነት አቅም በማጎልበት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲያንሰራራ በማድረግ የምርታማነት አብዮት እንዲቀጣጠል እያደረገ ይገኛል። የንቅናቄው ዋና ዓላማ በአምራች ዘርፉ የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት የኢትዮጵያን የማምረት አቅም ማሳደግ ነው። ይህም ሥራ ያቆሙ ወይም በአቅማቸው ልክ ያልሠሩ ፋብሪካዎችን ወደ ሙሉ ምርት በመመለስ የአምራቾችን ችግር በተቀናጀ መንገድ መፍታት፣ የፋይናንስና የግብዓት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጓል። በዚህ ሂደት የማምረቻ ዘርፉ በአዲስ የሥራ ባህል፣ በተቋማዊ ቅንጅትና በፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ እየተመራ መሆኑ የለውጡን ፍጥነት እያሳደገው ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ተደራሽነትን ማሻሻልና የምርት ጥራትን ማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ትንሳኤ ዋና ማሳያዎች ናቸው። ለአብነትም፡- የፋይናንስ አቅምና የብድር አቅርቦት ማሻሻል፡- የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ በተደረገው ርብርብ፣ የብድር አቅም ቀደም ሲል ከነበረበት 40 ቢሊዮን ብር ወደ 115 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል በማድረግ ለአምራቾች ሰፊ የካፒታል አቅም መፍጠር ተችሏል። የውጭ ምንዛሬ ግኝትና የግብዓት ድጋፍ ማደግ፡- ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ይቀርብ የነበረው የውጭ ምንዛሬ መጠን አሁን ላይ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንዲደርስ ተደርጓል። ይህም ፋብሪካዎች ከአቅማቸው በታች እንዲሠሩ ያስገድድ የነበረውን የምርት ውስንነት በከፍተኛ ደረጃ አቃሎታል። የምርት ዕድገት፣ ተኪ ምርትና የኤክስፖርት አፈጻጸም፡- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ረገድ ከነበረበት 348 ሚሊዮን ዶላር ወደ 5.9 ቢሊዮን ዶላር በማደግ ግዙፍ ሀገራዊ ድል ተመዝግቧል። እንዲሁም በኤክስፖርት ገበያ የሚገኘው ገቢ ከ385 ሚሊዮን ዶላር ወደ 607 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ማለት ችሏል። ተቋማዊ ቅንጅትና አዲስ የሥራ ባህል ማዳበር፡- በክልሎችና በፌዴራል ተቋማት መካከል የነበረውን የቢሮክራሲ ጫና በመቀነስ ፈጣን ውሳኔዎች እንዲሰጡ መደረጉ፤ እንዲሁም ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርትን በኩራት የመጠቀም እና የሀገር ፍቅር ስሜትን ከአምራችነት ጋር የማስተሳሰር ትልቅ ማህበራዊ ንቃተ-ህሊና መገንባት ተችሏል። የወደፊት ተስፋ፤ ኢትዮጵያ አዲሲቷ አፍሪካዊት የኢንዱስትሪ ምርታማነት ተምሳሌት ሀገር!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ በቀጣይ ዓመታት ከተለመደው ማምረት ወደ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የምርት ሥርዓት እንዲሸጋገር ይጠበቃል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና የፈጠራ ሥርዓቶችን ወደ ማምረቻ ዘርፉ ማስገባት የወደፊቱ ትኩረት ይሆናል። በተመሳሳይም ጠንካራ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስር፣ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአህጉራዊ ገበያ ተደራሽነት የሀገሪቱ ቀጣይ የኢንዱስትሪ ግቦች ናቸው። የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) የሚፈጥረውን ሰፊ የገበያ ዕድል በመጠቀም ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችል መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ማጠቃለያ፡- ማምረት፤ የኢትዮጵያ የብልፅግና ቁልፍ መሳሪያ!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ ከፈተና ወደ ዕድል፣ ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል፣ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ተጨማሪ እሴት ያለው ምርት አቅራቢነት በማምራት እመርታዊ ውጤቶችን እያስገኘ ነው። የኢንዱስትሪውን አቅም ማሳደግ ማለት ፋብሪካዎችን ብቻ ማስፋፋት ሳይሆን የሀገርን ምርታማነት፣ የወጣቶችን ዕድል፣ የኢኮኖሚ ነፃነትንና የልማት ዘላቂነትን ማረጋገጥ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን የዛሬ ልማት ብቻ ሳይሆን የነገውን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚገነባ ሀገራዊ ራዕይ ነው።  
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ጉዞ አንዱ መገለጫ -መሶብ
Aug 12, 2026 142
(በሙሴ መለሰ) የመንግሥት አገልግሎቶችን ለማግኘት በተለያዩ መሥሪያ ቤቶች መመላለስ፣ የወረቀት ክምርና ረጅም ሰልፍ የኢትዮጵያውያን የቆየ የዕለት ተዕለት ፈተና ነበር። ይህንን የዜጎች እንግልት በዘላቂነት ለመቅረፍ እና አሰራርን ለማዘመን ታስቦ የተመሠረተው መሶብ የተቀናጀ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል። የተቀናጀው የ"አዲስ መሶብ" ሱፐር አፕ (Super App) ዲጂታል መድረክ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ሚያዝያ ወር 2017 ዓ.ም በይፋ ተመርቆ ወደ ሙሉ ሥራ መግባቱ ይታወሳል። የመሶብ ዋና ዓላማ ተበታትነው የነበሩ ልዩ ልዩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ አጋዥነት በአንድ ጣሪያ ስር ማገናኘት ነው። ዜጎች ጊዜና ገንዘባቸውን ሳይባክኑ ፈጣን አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ፣ የሰዎችን ቀጥተኛ ንክኪ በመቀነስ ሙስናና ብልሹ አሰራርን መዋጋት፣ እንዲሁም ግልጽነትን ማስፈን የተቋሙ መሠረታዊ ምሰሶዎች ናቸው። በረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ዕቅዱ ደግሞ እያንዳንዱ ዜጋ በብሔራዊ የፋይዳ (Fayda) መታወቂያው ብቻ በመጠቀም ሁሉንም የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ አካውንት እንዲያገኝ ማድረግ እና ሥርዓቱን ለአፍሪካ ሀገራት እንደ መሪ ተሞክሮ ማቅረብን ያለመ ነው። ይህ የዲጂታል መድረክ እና አጠቃላይ የቴክኖሎጂ ሥርዓቱ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች ሀገር በቀል እውቀት የበለጸገ ሲሆን፣ ጥቅም ላይ የዋሉት የሶፍትዌር ቴክኖሎጂዎች ለሁሉም ክፍት የሆነ (Open-source) መሆናቸው ተቋሙን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ አድኖታል። በማዕከላቱ ውስጥ የሚሰሩ ባለሙያዎች ጥብቅ የሆነ የምልመላ ፈተና እና ልዩ ስልጠናዎችን አልፈው የሚገቡ በመሆናቸው የአገልግሎት ጥራቱ ከብልሹ አሰራር የፀዳ እንዲሆን አስችሏል። መጀመሪያ ላይ በ12 ተቋማትና በ41 አገልግሎቶች ብቻ የተጀመረው ይህ ዘመናዊ አሰራር፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያሳየ ባለው ፈጣን እድገት በአሁኑ ወቅት የትስስር አቅሙን በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ ችሏል። አሁን ባለው ተጨባጭ ቁመና መሶብ 27 ዋና ዋና የመንግሥት ተቋማትን ሙሉ በሙሉ በዲጂታል መስመር ማገናኘት የቻለ ሲሆን፣ እነዚህ ተቋማት በአንድ ላይ በመቀናጀት ከ288 በላይ የተለያዩ ዲጂታል አገልግሎቶችን በጥራትና በፍጥነት እያቀረቡ ይገኛሉ። ተገልጋዮች እንደ ፓስፖርት፣ ውክልና፣ የንግድ ፈቃድ እና የሰነዶች ማረጋገጫ ያሉ ወሳኝ ጉዳዮቻቸውን በአንድ ማዕከል ወይም በሞባይል መተግበሪያቸው ማከናወን ይችላሉ። ይህንን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ100 በላይ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ማዕከላት የተቋቋሙ ሲሆን፣ እስካሁንም ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በማስተናገድ የአገልግሎት እርካታውን በፌዴራል ደረጃ ወደ ከ98 በመቶ በላይ ማድረስ ተችሏል። በቅርብ ቀናት ውስጥ የወጡ አዳዲስ ወቅታዊ መረጃዎች ደግሞ ተቋሙ አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እና ተለዋዋጭ እያደረገው መሆኑን ያሳያሉ። በቀን የሥራ ሰዓት መስተናገድ ለማይችሉ ሠራተኞችና ነጋዴዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ከተለመደው የሥራ ሰዓት ውጭ የምሽት አገልግሎት (Night Service) በይፋ ተጀምሯል። ከዚህ በተጨማሪ ወደ ማህበረሰቡ በቀጥታ በመሄድ አገልግሎት የሚሰጡት እና የራሳቸውን ኃይል በከፊል ከፀሐይ ብርሃን የሚያመነጩት ዘመናዊ ተንቀሳቃሽ አውቶቡሶች (Mobile Mesob Bus) በተለይ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች የቤት ለቤት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። የጤናው ዘርፍ አገልግሎቶችንም ለማካተት ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል ጋር አዲስ ስምምነት የተፈራረመ ሲሆን፣ ወደ ሀገር ለሚገቡ ባለሃብቶችና ዳያስፖራዎች ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር በቦሌ ዓለም አቀፍ አየውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ማዕከል እየተገነባ ይገኛል። በአዲስ አበባ ከተማም ከ480 በላይ የአገልግሎት መስኮቶች የሚኖሩት አንድ ግዙፍ ማዕከላዊ የኮምፕሌክስ ሕንፃ ግንባታ በፍጥነት እየተከናወነ ነው። “ዩኒፋይድ መሶብ” የተሰኘው የኦንላይን መድረክ ዜጎች በሞባይል ስልካቸው የመንግሥት አገልግሎቶችን በቀላሉ እንዲያገኙ የሚያስችል ሥርዓትም ተግባራዊ ሆኗል። በአሁኑ ወቅት መሶብ ከሀገር ውስጥ አልፎ ዓለም አቀፍ ትኩረትን እየሳበ ይገኛል። ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ያደረጉ የአፍሪካ ሀገራት አምባሳደሮች እና የቤኒን ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሚኒስትር ማሁና አክፕሎጋን ማዕከሉን በይፋ የጎበኙ ሲሆን፣ መሶብ ለአፍሪካ ሀገራት በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመንግሥት አገልግሎት ሥርዓት ለመገንባት እንደ ትልቅ የምርጥ ተሞክሮ ማሳያ እየተወሰደ ነው። በቀጣይም ከጅቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኬንያ ጋር በዲጂታል አገልግሎት ዙሪያ የጋራ ትስስር በመፍጠር የአህጉር አቀፍ የዲጂታል ሥርዓት የመገንባት ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሰራ ይገኛል። በአጠቃላይ መሶብ ሀገር በቀል ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን እና የሕዝብን እንግልት በመቀነስ ረገድ ውጤታማነቱን በተግባር ያረጋገጠ ስኬታማ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማሳያ ነው።
ወዳጅነት ፓርክ ፦ የመደመር እሴት ማሳያ
Aug 11, 2026 169
በሙሴ መለሰ በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ ነው። ይህ ፕሮጀክት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረውና 56 ኪሎ ሜትር ርዝማኔ ባለው የ“ሸገርን የማስዋብ ፕሮጀክት” (Beautifying Sheger Project) ስር የተከናወነ ነው። ፕሮጀክቱ በሁለት ዋና ዋና ምዕራፎች ተከፍሎ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተገንብቶ ሊጠናቀቅ ችሏል። ኢትዮጵያ የጀመረችው ይህ የከተማ ውበትና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ የውበት ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ሀብት ፈጣሪ መሆኑንም በተግባር ያረጋገጠ ህያው ማሳያ ነው። የወዳጅነት አደባባይ የምዕራፍ አንድ የግንባታ ሂደት በ2011 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን፣ ቀደም ሲል የቆሻሻ ማጠራቀሚያና ክፍት ቦታ የነበረውን ስፍራ ወደ ዘመናዊ አረንጓዴ ሥነ-ምህዳር ለመቀየር ያለመ ነበር። ግንባታው በ11 ወራት ብቻ የተጠናቀቀ ሲሆን፣ በጳጉሜ 2012 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በቀድሞዋ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ተመርቆ ለሕዝብ ክፍት ሆኗል። ይህ ክፍል 32 ሄክታር መሬት በማልማት፣ አሳ እና ዳክዬዎች የሚቀዝፉበት ሰው ሠራሽ ሐይቅ፣ ትልቅ አደባባይ (Square)፣ እና 1 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የወንዝ ዳርቻን መልሶ ማቋቋምን ያካተተ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ለምሽት መዝናኛ የሚሆን ማራኪ የፏፏቴ ላይ የብርሃን ትርኢት (Dancing Fountain)፣ ከ16 በላይ የውጪ ላይ ስብሰባ ማካሄጃ ቦታዎች (Event Venues)፣ የሰርግ አፀዶች፣ ካፌዎች፣ የፎቶ ስቱዲዮዎች እና ጠዋት ጠዋት የአካል ብቃት እንቅስቃሴና ሩጫ ለማድረግ ምቹ የሆኑ የተከለሉ መንገዶችን ይዟል። ምዕራፍ አንድ ከተመረቀ በኋላ ወዲያውኑ የሁለተኛው ምዕራፍ (Friendship Park 2) የዲዛይንና የዝግጅት ሥራዎች ተጀምረዋል። በግንባታው ወቅት ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም፣ ከሌላ ቦታ የተሰባሰቡ ከ4ሺህ በላይ አገር በቀል ትልልቅ ዛፎች (Indigenous trees) መጥተው በቦታው ላይ በተሳካ ሁኔታ እንዲተከሉ ተደርጓል። ግንባታው በጥቅምት 2015 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቋል። 16 ሄክታር መሬት የሸፈነው ይህ ክፍል ከአብርሆት ቤተ-መጽሐፍት ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን፣ ሙሉ በሙሉ ለሕፃናት፣ ለታዳጊዎችና ለቤተሰብ ስፖርታዊ መስተጋብር ተለይቶ የተገነባ ነው። በውስጡም እጅግ ዘመናዊና ሰፊ የሕፃናት መጫወቻ ስፍራዎችን (Playgrounds)፣ ታዳጊዎች እየተጫወቱ ሳይንስና ቴክኖሎጂን የሚለማመዱበትን የሳይንስ ማዕከል፣ ትንንሽ የእግር ኳስ (Mini-football) እና የቅርጫት ኳስ (Basketball) ሜዳዎችን፣ የሩጫ ትራኮችን፣ ለወጣቶች ንባብ የሚሆኑ ቦታዎችን (Reading nooks) እና ከጎኑ ያለውን የሳይንስ ሙዚየም ግንባታን ያካተተ ሰፊ ይዘት አለው። የወዳጅነት ፓርክ ከብሔራዊ ቤተመንግሥት እስከ መስቀል አደባባይባለው አካባቢ የሚዘልቅ ዘመናዊ የሕዝብ መገልገያና መዝናኛ ማዕከል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ ይህ ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ማስገኘት ችሏል። ይህም የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች ራሳቸውን ችለው ከፍተኛ ገቢ ማመንጨት ከመቻል ባለፈ፣ በቱሪዝም ዘርፉ፣ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እና በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ዘንድ ለበርካታ ዜጎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሰፊ የሥራ ዕድል እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እየፈጠረ ይገኛል። ከዚህ ኢኮኖሚያዊ እሴቱ ባሻገር፣ ፕሮጀክቱ የከተማ ነዋሪዎችን ማኅበራዊ ትስስር በከፍተኛ ደረጃ ያጠናክራል፤ የዜጎችን የኑሮ ጥራት፣ የጤና ሁናቴ እና ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤ (Life style) ከማሻሻል አንጻርም የመደመር እሴት በተግባር መሬት ማወረዱንና የዜጎችን አገራዊ የባለቤትነት ስሜት በጽኑ የሚያሳድግ ትልቅ ማሳያ ነው። ፓርኩ ለጤና፣ ለአካል ብቃት፣ ለመዝናኛና ለንባብ ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ወጣቶች ጊዜያቸውንና ጉልበታቸውን በስፖርት፣ በዕውቀት ቀሰማና በሌሎች በጎ ነገሮች ላይ እንዲያሳልፉ ምቹ ከባቢ ፈጥሯል። በተጨማሪም ቦታው ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎችና ጎብኝዎች በየቀኑ በስፋት የሚገናኙበት ማዕከል መሆን ችሏል። በስፍራው ከቤተሰቦችና ሕፃናት፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከሠርግ ተካፋዮች ጀምሮ እስከ ዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች፣ እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በከፍተኛ ቁጥር ይገኙበታል። ይህም ለሀገር ውስጥ ይዘት ፈጣሪዎች (Content Creators) ምቹ ከባቢ በመፍጠር፣ የአዲስ አበባን ዘመናዊና ማራኪ ገጽታ በማኅበራዊ ትስስር ገጾች ላይ በስፋት እንዲያስተዋውቁና የከተማዋን በጎ ስም ለዓለም እንዲያደርሱ ትልቅ ዕድል ከፍቷል። ይህ ፓርክ አዲስ አበባን ለሌሎች የክልል ከተሞች በአረንጓዴ ልማት፣ በጽዳትና በዘመናዊ የሕዝብ መገልገያዎች በሞዴልነት የሚጠቀስ ሲሆን፣ የከተማዋን የዲፕሎማሲያዊ መዲናነት ገጽታ ይበልጥ በማደስ ለውጭ ሀገር ጎብኚዎች፣ ለዲፕሎማቶችና ለዓለም አቀፍ እንግዶች በጣም ሳቢና ተመራጭ መዳረሻ አድርጓታል። ፓርኩ በከተማዋ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ውስጥ እየተገነቡ ላሉ ተመሳሳይ የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ቀዳሚ ማሳያ ሲሆን፣ እነዚህ አዳዲስ ቦታዎች እሴት የሚፈጥሩ፣ ዕድሎችን የሚያመቻቹ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያውያንን ባለቤትነት የሚያረጋግጡ ማዕከላት መሆናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መልዕክት ያረጋግጣል።
የኮደሮች ኢኒሼቲቭ፡ የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታና የወጣቶች ብሩህ መፃኢ ዕድል
Aug 10, 2026 189
በሙሴ መለሰ ኢትዮጵያ በዲጂታሉ ዓለም ያላትን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እና የወጣቶችን ክህሎት ለማልማት ያለመው የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል። ይህ ኢኒሼቲቭ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች መካከል በተደረገ ትብብር የተዘጋጀ ሀገራዊ የዲጂታል ክህሎት ማሳደጊያ ፕሮጀክት ነው። ዋና ዓላማውም ወጣቶች በዲጂታሉ ዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆኑና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚፈለጉ የቴክኖሎጂ ክህሎቶችን እንዲጨብጡ ማስቻል ነው። የስልጠናው መርሃ ግብር በኦንላይን ”Udacity” በተሰኘ ዓለም የትምህርት መድረክ በኩል የሚሰጥ ሲሆን፣ በዌብ ዲቨሎፕመንት፣ በዳታ አናሊቲክስ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዋና ዋና ዘርፎች የተከፈለ ነው። ከእነዚህም ጎን ለጎን የንግድና ሥራ ፈጠራ እንዲሁም የመሪነት ክህሎት አጫጭር ስልጠናዎች ተካተዋል። እያንዳንዱ ኮርስ በግል ፍጥነት የሚወሰድ ሆኖ በአማካይ ከ6 እስከ 7 ሳምንታት የሚወስድ ሲሆን፣ ስልጠናውን በጥሩ ሁኔታ ላጠናቀቁ ሰልጣኞች ሙሉ በሙሉ በነፃ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው የ’Udacity’ እና የኢኒሼቲቩ ይፋዊ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ይሰጣል። በዚህ ፕሮግራም ላይ ዕድሜው ከ13 ዓመት በላይ የሆነ ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የቀደመ የኮዲንግ እውቀት ሳይጠይቀው መመዝገብ ይችላል። ለመማር የሚያስፈልጉት ነገሮች የኢንተርኔት ግንኙነት ያለው ኮምፒውተር ወይም ስማርትፎን ብቻ ሲሆኑ፣ ምዝገባውም በይፋዊው 5millioncoders.gov.et ድህረ ገጽ በኩል ይከናወናል። የኢኒሼቲቩ የመጨረሻ ግቦች ሀገሪቱን በምስራቅ አፍሪካ እና በመላው አህጉር ውስጥ የቴክኖሎጂ ማዕከል ማድረግ እና የዲጂታል ስትራቴጂዎችን ማሳካት ናቸው። በተጨማሪም ሰልጣኞች በሀገር ውስጥና በውጭ ድርጅቶች እንዲቀጠሩ፣ ከቤት ሳይወጡ በዶላር የሚከፍሉ የርቀት ስራዎችን እንዲሰሩ እና የራሳቸውን የቴክኖሎጂ ስታርታፕ እንዲመሰርቱ መንገድ ይከፍታል። በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚታየውን የክህሎት እጥረት በመሙላትና ለሀገር የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማስገኘት የወጣቶችን ተወዳዳሪነትና በራስ የመተማመን አቅም ያሳድጋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባስተላለፉት ሀገራዊ ጥሪ፣ ይህ ክረምት በከንቱ እንዲያልፍ ሳይፈቀድ ወጣቶች በነጻ የሚሰጠውንና ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለውን ትምህርት እንዲወስዱ አሳስበዋል። አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ቀድመው የወሰኑ በመሆናቸው፣ ሌሎችም ይህንን እድል በመጠቀም የክረምቱ ወቅት ከመጠናቀቁ በፊት የተሳታፊዎችን ቁጥር ወደ ሰባት ሚሊዮን ለማድረስ የቀረበውን ጥሪ እንዲቀላቀሉ ጥሪ አቅርበዋል። ይህንን ሀገራዊ ጥሪ ተከትሎ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስተናጋጅነት የልምድ ልውውጥ መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል። ዝግጅቱ የዘርፉን መሪዎች፣ ፖሊሲ አውጭዎችን፣ የምስክር ወረቀት ያላቸውን የኢኒሼቲቩን ተመራቂዎች እና ወጣት ባለሙያዎችን በአንድነት ያገናኘ ሲሆን፣ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ላይ ባተኮረ የኤግዚቢሽን ጉብኝት ተጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ሥዩም የመክፈቻ ንግግር ቀጥሏል። ኃላፊዋ የወጣቶች የቴክኒክና የዲጂታል ክህሎት ብቃት ወሳኝ ሀገራዊ ሀብት መሆኑን ገልጸው፣ የኮደሮችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የቀረበውን ጥሪ ተግባራዊነት አረጋግጠዋል። ቀጥሎ በተካሄደው የፓናል ውይይት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ዶ/ር አብዮት ባዩ፣ የጊሮ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ቤተልሔም ደሴ፣ እንዲሁም የኢኒሼቲቩ ምሩቃን የሆኑት አዝመራው ታደሰ እና የቴክኖሎጂ ሥራ ፈጣሪዋ ማኅሌት ሥዩም ልምዳቸውንና እይታቸውን አካፍለዋል። ፓናሊስቶቹ ወጣቶች ክህሎታቸውን ያለማቋረጥ እንዲያሳድጉ እና በኢትዮጵያ የዲጂታል ሥነ-ምህዳር ዕድገት ውስጥ የድርሻቸውን እንዲወጡ ያበረታቱ ሲሆን፣ መርሃ ግብሩም የኢኒሼቲቩን ከፍተኛ ሀገራዊ ሚና በድጋሚ ያረጋገጠ ሆኖ ማለፉን ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የ5 ሚሊዮን ኮደሮች ኢኒሼቲቭ ኢትዮጵያ በዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ ያላትን ራዕይ ለማሳካት የተጣለ ትልቅ መሰረት ነው። ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚጨብጡት ዕውቀት የራሳቸውን የፈጠራ መንገድ ከመክፈቱም በላይ፣ ሀገሪቱ በምስራቅ አፍሪካና በአህጉሪቱ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሆና እንድትወጣ ያስችላታል። በመሆኑም ይህን አጋጣሚ በአግባቡ መጠቀም ለሀገሪቱ ዘላቂ እድገትና ለወጣቱ ብሩህ ተስፋ ወሳኝ እርምጃ ነው።
የአፍሪካ የውሃ ማማ ኢትዮጵያ ሳትሆን ግብፅ ናት!
Aug 10, 2026 388
ግብጽ ራሷን የምትስልበት የውሃ እጥረት ትረካ ከነባራዊ ሁኔታም በእጅጉ የተቃረነ ነው። የአፍሪካን የታሪክ፣ የኢኮኖሚና ጂኦ-ፖለቲካ በከፍተኛ ሁኔታ ከሚቃኙት ተፈጥሯዊ ሃብቶች መካከል ውሃ ግንባር ቀደሙን ስፍራ ይይዛል። አፍሪካውያን የውሃ ሀብታቸውን በጋራ አልምቶ የመጠቀም ፍላጎታቸውና ጥረታቸው የአህጉሪቱን የወደፊት የልማትና የሰላም አቅጣጫ የሚወስን ወሳኝ ጉዳይ ቢሆንም ይህ አህጉራዊ የትብብርና የጋራ እድገት መንፈስ እውን ሊሆን የሚችለው የተፋሰሱ ሀገራት ያላቸውን እውነተኛ የውሃ ሀብት መጠንና ፍላጎት በሳይንሳዊ እውነታዎችና በግልጽኝነት ላይ ተመስረተው ሲተገብሩት ብቻ ነው። በዚህ አህጉራዊ የተፋሰስ ትብብር ውስጥ ትልቁን ስፍራ የሚይዘው የታላቁ ዓባይ ወንዝ ተፋሰስ ነው። ሆኖም ለዘመናት የዘለቀውና አሁንም ድረስ በዲፕሎማሲው መድረክ የሚንጸባረቀው ዋነኛው ማነቆ ግብፅ እራሷን "ለከፍተኛ የውሃ እጥረት የተጋለጠችና ፍጹም የዓባይ ጥገኛ የሆነች ብቸኛ ሀገር" አድርጋ የምታቀርብበት ትርክት ነው። ይህ ትረካ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብን ሲያደናግር ቆይቷል። ነገር ግን የጂኦግራፊ፣ የሃይድሮሎጂና የዘመናዊ ቴክኖሎጂ መረጃዎችን በጥልቀት ስንመረምር ግብፅ እራሷን የምትስልበት የውሃ እጥረት ትረካ ከእውነተኛው ነባራዊ ሁኔታ ጋር በእጅጉ የሚቃረን ሆኖ እንገኘዋለን። ግብፅ በውስጧ የያዘቻቸውን ግዙፍና ያልተነኩ ድብቅ ሀብቶች፣ የቴክኖሎጂ አቅሞችን እና በበረሃ ውስጥ የምታከናውናቸውን ሰፋፊ የውሃ ማዞር ፕሮጀክቶች ስንመለከት ሀገሪቱ እውነተኛ የውሃ እጥረት ሳይሆን ከፍተኛ የውሃ ሀብት ያላት መሆኗን በግልጽ ያሳያል። ይህንን እውነታ በግልጽ የሚያስረዱትንና የግብፅን እውነተኛ የውሃ ማማነት የሚያረጋግጡትን ዋና ዋና ሳይንሳዊና ተግባራዊ ማስረጃዎች እንደሚከተለው ቀርበዋል፦ የከርሰ ምድር ውሃ ከገፀ-ምድር ውሃ ባሻገር በግብፅ፣ ሊቢያ፣ ሱዳን እና ቻድ ስር የሚገኘው የኑቢያ አሸዋማ ድንጋይ የከርሰ-ምድር ውሃ ስርዓት (Nubian Sandstone Aquifer System) በዓለም ላይ ካሉ የከርሰ-ምድር ውሃዎች ትልቁ ነው። አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያመላክቱት በግብፅ ግዛት ስር ብቻ የሚገኘው የዚህ ውሃ መጠን ከ5 ትሪሊዮን እስከ 10 ትሪሊዮን ኪዩቢክ ሜትር እንደሆነ ይገመታል። ይህ ግዙፍ ሀብት የዓባይ ወንዝን የአምስት ክፍለ-ዘመናት (500 ዓመታት) አጠቃላይ የውሃ ፍሰት የሚበልጥ ድብቅ ሃብት ነው። ግብፅ ይህንን ሀብቷን በዘመናዊ መንገድ አውጥታ ብትጠቀም ለበርካታ አስርት ዓመታት ያለ ምንም የገፀ-ምድር ውሃ ስጋት መኖር የሚያስችላት ስትራቴጂካዊ ክማቸት አላት ማለት ነው። የአስዋን ከፍተኛ ግድብና የናስር ኃይቅ የግብፅ የውሃ መከላከያ ማዕከል የሆነውና በአስዋን ከፍተኛ ግድብ የተገደበው ናስር ሀይቅ እስከ 169 ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ውሃ የመያዝ አቅም አለው። ይህም ማለት በናስር ሃይቅ የተከማቸው ውሃ ብቻ የግብፅን የዓመታት ሙሉ የውሃ ፍላጎት ያለ ምንም ተጨማሪ የወንዝ ፍሰት መሸፈን የሚያስችል ግዙፍ ስትራቴጂካዊ መያዣ (Buffer) ሆኖ ያገለግላል። የባሕር ውሃ ማጣራት አቅምና የግብጽ 2050 ማስተር ፕላን ግብፅ በሜዲትራኒያን እና በቀይ ባህር ረጅም የባህር ዳርቻዎች ያሏት በመሆኑ በጨዋማ ውሃ ማጣሪያ ቴክኖሎጂ ትልቅ እርምጃ እየወሰደች ትገኛለች። በአሁኑ ወቅት በቀን ከ1 ነጥብ 5 እስከ 2 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር የተጣራ ውሃ እያመረተች ሲሆን፤ በግልና በሕዝብ ፣ በካርቦን ቅነሳ ድጋፎች እና በባህር ዳርቻ ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች አማካኝነት የማጣራት አቅሟን በጥሬው በእጥፍ ለማሳደግ የሚያስችል እስከ 2050 የሚዘልቅ ስትራቴጂካዊ ማስተርፕላን አዘጋጅታለች። ግዙፍ የውሃ ማዞር ፕሮጀክቶች ግብጽ በቶሽካ ፕሮጀክት አማካኝነት ከናስር ሀይቅ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ኩቢክ ሜትር ውሃዎችን ወደ ምዕራብ በረሃ በመቀየር ሰው ሰራሽ ሀይቆች እና ክፍት የመስኖ ቦዮች እንዲፈጠሩ አድርጋለች ። በሌላ በኩል በኒው ዴልታ እና ጂሪያን በሚሊዮን ሄክታር መሬት ለማልማት እና አዳዲስ ከተሞችን ለመገንባት የተፈጥሮ የአባይ ወንዝን አቅጣጫ በመቀየር ቢሊዮን ኩቢክ ሜትር ውሃ በመመደብ ላይ ትገኛለች።እነዚህ ፕሮጀክቶች ግብፅ ለትልልቅ የበረሃ ልማቶች የሚተርፍ ትርፍ ውሃ እንዳላት በተግባር የሚያሳዩ ናቸው። ውሃን መልሶ የመጠቀም አቅም ግብፅ ውሃን መልሶ በማጣራት ጥቅም ላይ ለማዋል ትልልቅ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያዎችን ለምሳሌ በህር ኤል ባቃር (Bahr El-Baqar plant) ገንብታለች። ሀገሪቱ በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ኩቢክ ሜትር ፍሳሽ ውሃዎችን መልሳ በመጠቀም ለግብርና በማዋል የምትጠቀመውን እያንዳንዱን የውሃ ጠብታ የማባዛት ከፍተኛ ቴክኖሎጂያዊ አቅም እንዳላት አስመስክራለች። መደምደሚያ አፍሪካውያን የውሃ ሀብታቸውን በጋራ አልምተው ለመጠቀም የሚያደርጉት ጉዞ እውን ሊሆን የሚችለው ግብጽ የምታራምደውን አይነት የተሳሳቱ ትርክቶችን በሳይንሳዊ እውነታዎች መተካት ሲቻል ብቻ ነው። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብም ይህን በሚገባ ሊገነዘብ ይገባል። ግብፅ ግዙፍ የከርሰ-ምድር ውሃ፣ ዘመናዊ የውሃ ማጣሪያ ጣቢያዎች፣ ከፍተኛ የውሃ መልሶ መጠቀም አቅም እና በበረሃ ውስጥ ውሃ እስከ ማዞር የሚያስችል ሀብት ያላት ሀገር ናት። ይህም ግብፅ የውሃ እጥረት ያለባት ሀገር ሳትሆን፣ የአፍሪካ የውሃ ማማ መሆኗን በተግባር የሚያሳይ ነው።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 11710
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 21534
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 14560
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20311
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 104012
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 78942
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 57465
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 55047
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 39442
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 39248
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 38727
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 37370
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 104012
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 78942
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 57465
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 55047
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
በምክክር እንጂ በመሳሪያ ድምጽ ሀገር አይገነባም
Aug 8, 2026 415
ኢትዮጵያ የዛሬ ማንነቷና ሉዓላዊ ክብሯ ተጠብቆ እዚህ እንድትደርስ በርካታ ውጣውረዶችን አልፋለች። በቀደመ ታሪኳም ዜጎች በራሳቸው የውስጥ ጉዳይ መስማማት ባለመቻል እርስ በእርስ ካደረጓቸው ግጭቶች ባለፈ የውጭ ሃይሎችም የራሳቸውን አሉታዊ ጫና ሲፈጥሩ ቆይተዋል፤ አሁንም ይህንኑ ለማስቀጠል ተላላኪዎቻቸውን ለመጠቀም ሲሞክሩ ይታያል። በአንድ ሃገር ውስጥ የማያግባቡ ጉዳዮች በየትኛውም አጋጣሚና የታሪክ ምዕራፍ ሊያጋጥሙ ይችላሉ። እነዚህን ችግሮች በሃይል ለመፍታት የሚደረገው የመሳሪያ ትንቅንቅ ግን አክሳሪና ዘመን እያለፈበትም ነው። ይሁን እንጂ የኢትዮጵያን ሰላማዊ የእድገት ጉዞ ለማወክ የህዝቦቿን አንድነት ለመበጥበጥ ከቅርብም ሆነ ከሩቅ የሚመጡ ጠላቶች ጠፍተው አያውቁም። በየዘመናቱ የተሻገርናቸው የታሪክ ስብራቶችን ፣ የመብት ጥያቄዎችንና ሌሎችንም መነሻ በማድረግ በውስጥ ባንዳዎች እና በውጭ ባዳዎች አማካኝነት የማያቋርጥ ጦርነት ውስጥ ለመክተት፣ የብልጽግና ጉዞዋን ለማደናቀፍ የሚደረጉ ሴራዎች ዛሬም ላይ ቀጥለዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላት ተሰሚነትና ተጽዕኖ የሚያሳምማቸው ለዜጎቿን እኩል ተጠቃሚነትና ብልጽግና መረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚያስጨንቃቸው እነዚህ ሃይሎች በመብት ፣ በነጻነት፣ በዴሞክራሲ፣ በማንነትና በሌሎችም የሃሰት ትርክቶች መነሻነት በሩቅ ቢያቅታቸው በቅርብ የውስጥ ተላላኪ ባንዳዎችን እያደራጁ በጀት መድበው የጦር መሳሪያ አቅርበው ሀገር የማፍረስ ሙከራቸውን አላቋረጡም። በመደመር እሳቤ ሁሉንም በአንድ ላይ በማቀራረብና የጋራ ትርክቶችን በመገንባት ከልዩነት ይልቅ የሚያቀራርቡ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ዘላቂ ልማቷን መፃኢ ብሩህ ተስፋዋን ለማለምለም በሁሉም ዘርፍ ኢትዮጵያ በዜጎቿ ተሳትፎ እየሰራች መሆኗም ምቾት ነስቷቸዋል። በሀገራችን ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሔደ ያለውና ወርቃማው እድል ሃገራዊ ምክክር ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት ፣ የሚያስችሉ ወሳኝ ምዕራፎች ላይ ደርሷል ። በዚህ የምክክር ሒደት በሀገሪቱ የትኛውም ጥግ ያለ ዜጋ እንዲሁም በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የተወከሉበት ፣ የብሔር፣ የፖለቲካ አመለካከትና የሃይማኖት ልዩነት የማያደናቅፉት ሁሉንም ያሳተፈ ምክክር እየተካሔደ ይገኛል። ጥያቄያችንን በጠብመንጃ አፈሙዝ እንፈታለን ያሉ ታጣቂዎችም ብረት በማስቀመጥ አጀንዳዎቻቸውን ይዘው ወደ ጠረጴዛው ቀርበዋል። ልክ ናቸው ሀገር ከሁሉም ነገር ትበልጣለችና ይሄንን ወርቃማ እድል ለመጠቀም ማሰብ ትክክለኛው ውሳኔ ነው። በትጥቅ ትግል ጥያቄያችንን እንመልሳለን በሚል ሽፋን የሌሎችን አጀንዳ ለማሳካት የሚደረግ ጥረት የሃገርና የትውልድ ጠባሳ ከማስቀመጥና የታሪክ ተወቃሽ ከመሆን የዘለለ ፋይዳ እንደማይኖረው መገንዘብ ብልህነት ነው። የዚህ ምክክር ተሳታፊ/ተመካካሪ ከሆኑት የቀድሞ ታጣቂዎች መካከል የአማራ ፋኖ ህዝባዊ ድርጅት(አፋሕድ) አመራር ካፒቴን ማስረሻ ሰጤ በዚህ ይስማማሉ ። ሀገራዊ ምክክር ትልቅ ተስፋ የጣልንበት፣ በንግግር፣ በምክክር ሀገራችንን የምናስቀጥልበት፣ ሁሉም ተነጋግሮ ተመካክሮ የወደፊቷን ኢትዮጵያ ከችግሮች ነፃ የሚያደርግበት ነው ይላሉ። ምክክሩ ሁሉም ኢትዮጵያዊ የሚነጋገርበት፣ የሚመካከርበት እና በሃሳብ የበላይነት ጠንካራ ሃገር የሚፈጠርበት መልካም የታሪክ አጋጣሚ መሆኑንም ይናገራሉ። በምክክር፣ በድርድር የሕዝብን ጥያቄ በመመለስ ሀገርን የምናስቀጥልበትና የውጭ ኃይሎችን ጣልቃ ገብነት የምናስወግድበት በመሆኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ነው ብለዋል። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር የቀድሞ ታጣቂ ጃል ሰኚም ይሄንኑ ሃሳብ ይጋራሉ። በኢትዮጵያ ውስጥ ለዓመታት የቆዩ ልዩነቶችን ለመፍታት ሀገራዊ ምክክር መዘጋጀቱ ትልቅ እርምጃ እንደመሆኑ እሳቸውም ያላቸውን ሀሳብ በማንጸባረቅ እየመከሩ ይገኛሉ። እርሳቸውና ቡድናቸው ከዚህ ቀደም የትጥቅ ትግልን በመምረጥ ጫካ ገብተው እንደነበር አስታውሰው፤ ችግሮችን በመሳሪያ ከመፍታት ይልቅ በሰላማዊ የምክክር መድረክ መፍታት ጥሩ አማራጭ መሆኑን አምነው ወደ ሰላም መንገድ መምጣታቸውንም ተናግረዋል። ችግሮቻቸውን በምክክር የፈቱ ሀገራት በሁሉም ዘርፍ ዕድገታቸውን የሚያስቀጥሉ ሲሆኑ ወደ ትጥቅ ትግል ያመሩና ግጭት ውስጥ የገቡት ደግሞ በፖለቲካዊ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ውድቀት ለከፋ ድህነት መዳረጋቸውን ጠቅሰዋል። የጦር መሣሪያ በመነቅነቅና ደም አፋሳሽ ጦርነት ውስጥ በመግባት የሚፈታ ችግር እንደሌለ የሚናገሩት ደግሞ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ(አብን) አመራሩ ተመካካሪ ጣሒር መሀመድ ናቸው። ጫካ ባለውና እዚህ ባለው ሰው መካከል ምንም ዐይነት የዜግነት ልዩነት እንደሌለ ገልጸው ከትጥቅ ትግል ይልቅ በሃሳብ ለመታገል ልዩነቱን ለማቅረብ የፈለገ ሁሉም ዜጋ በምክክሩ የመሳተፍ ነጻነት እንዳለው ገልጸዋል። በሃገራዊ ምክክሩ ከትጥቅ ትግል ይልቅ በሰላማዊ መድረክ መወያየት የተመረጠበት ዋና ምክንያት ዘላቂ ሰላም፣ አገራዊ መግባባት እና የፖለቲካ ባህል ለውጥ ለማምጣት ነው:: የትጥቅ ትግል የዜጎችን ህይወት ያጠፋል፣ መሰረተ ልማቶችን ያወድማል፤ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውድቀትንም ያመጣል: ፤ ሰላማዊ መድረክ ግን ያለምንም ደም መፋሰስ ሃሳብን በሃሳብ ለመሞገት እድል ይሰጣል:: በኃይል የሚመጣ ለውጥ ብዙውን ጊዜ አሸናፊና ተሸናፊን ስለሚፈጥር የቁስል እና የቂም ዑደትን ያስቀጥላል:: በሰላማዊ ውይይት የሚገኝ መፍትሄ ግን የሁሉንም ወገን ስጋት እና ፍላጎት ያገናዘበ በመሆኑ ዘላቂነት ይኖረዋል:: ሃገራዊ ምክክሩ የታጠቁ አካላትም ጭምር መሳሪያቸውን አስቀምጠው በሃሳብ እንዲፎካከሩ መንገድ ከፍቷል። ይህ ታሪካዊና ወርቃማ እድል ኢትዮጵያዊንን አግባብቶ ወደተረጋጋችና የበለጸገች ሃገር የሚመራ በመሆኑ ስኬታማነቱ አያጠራጥርም። ለእድለኛው ትውልድ ያጋጠመው ወርቃማው ስጦታ ሃገራዊ ምክክር የተቋቋመለትን ዓላማ ያሳካል።
ከካይሮ ሴራ ጀርባ፤ የCNN ዘገባ የገለጠው የኢትዮጵያ እውነት
Aug 4, 2026 1294
ግብፅ በታሪኳ የዓባይን ወንዝ በብቸኝነት ለመጠቀም የተከተለችው ዋና ስልት "ጠንካራና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለካይሮ ስጋት ናት" የሚል ቀመርን ነው። በመሆኑም በየዘመናቱ የተነሱ የካይሮ መንግስታት ኢትዮጵያ ተረጋግታ ሀብቷን እንዳታለማ ለማድረግ ረዥም ርቀት ተጉዘዋል። በታሪክ አጋጣሚ የዓባይን መነሻ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር በርካታ የወረራ ሙከራዎችን ያደረገችው ግብጽ፣ በጉንደት (1875) እና በጉራዕ (1876) በተደረጉ ታሪካዊ ውጊያዎች በኢትዮጵያውያን ጠንካራ ክንድ መራራ ሽንፈትን አስተናግዳለች። ከቀጥታ ጦርነት ከተመለሰች በኋላ ካይሮ ስልቷን ወደ "ውስጥ ለውስጥ ማበጣበጥ" ቀይራለች። ይህም የኢትዮጵያን መንግስት ትኩረትና የፋይናንስ አቅም ከልማት ፕሮጀክቶች (በተለይም ከታላቁ ህዳሴ ግድብ እና መሰረተ ልማቶች) ወደ ጸጥታ ማስከበር እንዲዞር ለማድረግና ሀገሪቱን ወደማያልቅ የውስጥ ብጥብጥ ለመክተት በርካታ ሴራዎችን ስታከናውን ቆይታለች። ይህ አልሳካ ሲላት ደግሞ የሀሰት መረጃዎችን ማሰራጨትን እንደ አማራጭ መንገድ ስትጠቀም ቆይታለች፤ እየተጠቀመችም ትገኛለች። የግብፅ የፖለቲካ ምሁራንና ዲፕሎማቶች የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ “ግድቡ በታችኞቹ የተፋሰሱ ሀገራት ላይ የከፋ ጉዳት ያደርሳል” በሚል የሐሰት ትረካቸውን ሲያሰራጩና ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ ሲያሳስቱ ቆይተዋል። ሆኖም ግን፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥበብ የተሞላበት አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ የውጭ ተፅዕኖዎችንና የውስጥ ፈተናዎችን በመሻገር ይህንን ግዙፍ ፕሮጀክት ከፍፃሜ ማድረስ ችላለች። ይህም የመደመር እሳቤ የሆነው ፈተናን ወደ እድል የመቀየር ትልቁ ማሳያ ነው። የግድቡን እውን መሆን ተከትሎም የካይሮ ተደጋጋሚ የሀሰት ቅሬታና የተዛባ ፕሮፓጋንዳም ዘግይቶም ቢሆን እውነቱ በዓለም ፊት እየተገለጠ ይገኛል።በCNN “Connecting Africa” ወርሃዊ ፕሮግራም ላይ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ ያቀረበችው ዘገባ የዚሁ እውነት ማሳያ ነው። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2020 የቢቢሲ የኮምላ ዱሞር ሽልማት አሸናፊ የሆነችው ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩባዲሪ፣ የኢትዮጵያ ታላቁ ህዳሴ ግድብ በሚገኝበት ጉባ ተገኝታ ባከናወነችው ዘገባ የካይሮን ምናባዊ ቅዥት የሚያፈርሱ ተግባራዊ እውነቶችን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይፋ አድርጋለች። የምህንድስና ልህቀት እና የጋራ ልማት ማሳያ፦ CNN በዘገባው ስለ ሕዳሴ ግድብ ለዓመታት ሲነገር የቆየውን የሀሰት ሴራ ሳይሆን፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የምህንድስናና የግንባታ ባለሙያ ኢትዮጵያዊያን ጥረትን እውን ያደረገ የኢንጂነሪንግ ልህቀት አብነት መሆኑን አጉልቶ አሳይቷል። የግብፅ መንግስት ግድቡን “የስጋት ምንጭ” አድርጎ ለማሳየት ቢጥርም፣ የCNN ዘገባ ግን ግድቡ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአጠቃላይ ቀጣናው የተዘረጋ የጋራ እድገት መድረክ መሆኑን አብራርቷል። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር መስከረም 2025 በይፋ የተመረቀው ይህ ግዙፍ ፕሮጀክት፣ የሀገሪቱን የኃይል አቅርቦት በማሳደግ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት እያበራ መሆኑን በማሳየትም፤ ግድቡ ኢትዮጵያ ከድህነት ለመውጣት የምታደርገው ጥረት አካል መሆኑን በተግባር ገልጧል። የጋዜጠኛ ሩባዲሪ ዘገባ የግብፅን ተደጋጋሚ ቅሬታና ሴራ በሶስት ዋና ዋና ነጥቦች ውድቅ ያደርጋል። የጋራ ተጠቃሚነት መርህ ፦ ግድቡ የታችኞቹን የተፋሰሱ ሀገራት የማይጎዳ፣ ይልቁንም የውሃ ፍሰትን በማስተካከልና ደለልን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ሚና የሚጫወት፣ በጋራ ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተ ፕሮጀክት መሆኑን የግድቡ ግንባታ ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ ሃሳብን በማካተት ጭምር አሳይታለች። ቀጣናዊ የመደመር እሳቤ ማሳያ ፦ ግድቡ ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ በመሸጥ ገቢ ከማግኘቷም ባለፈ፣ የቀጣናውን ሀገራት በኃይልና በኢኮኖሚ የሚያስተሳስር ነው። ይህ ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግስት እሳቤ ማለትም “በጋራ ማደግ እና እርስ በእርስ መደጋገፍ” የሚለውን ቀጣናዊ ራዕይ በተግባር የሚያረጋግጥ እንጂ ግብፅ እንደምትለው ቀጣናውን ወደ አለመረጋጋት የሚከት አለመሆኑን ያመላክታል። ሰው ተኮር የኢኮኖሚ ሽግግር፦ በCNN ዘገባ የተካተቱት የኢንተርናሽናል ግሮውዝ ሴንተር (IGC) የኢትዮጵያ ኃላፊ ቴዎድሮስ መኮንን በግልጽ እንዳስቀመጡት፤ 70 በመቶው ህዝቧ ከ30 ዓመት በታች የሆነችው ኢትዮጵያ፣ ከ15 ዓመታት በፊት ከነበረችበት ከአማካይ በታች የነበረ የነፍስ ወከፍ ገቢ አሁን በአፍሪካ ከሚገኙ ግዙፍ ኢኮኖሚ ካላቸው ሀገራት አንዷ መሆን ችላለች። ግድቡም ይህንን ወጣት ኃይል ወደ ዘላቂ ምርታማነት ለመቀየር የሚደረገው ጥረት አካል ነው። መደምደሚያ፦ በአጠቃላይ ግብፅ ግድቡን መሰረት በማድረግ የምታካሂደው የዲፕሎማሲና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ የፖለቲካ ቁማር እንጂ ከሳይንሳዊና መሬት ላይ ካለው እውነት ጋር እንደማይገናኝ የCNN ዘገባ በግልጽ አሳይቷል። በሀገር ውስጥ አቅም እና በጥበብ በተሞላ ሀገራዊ አመራር እውን የሆነው የታላቁ ህዳሴ ግድብ፣ የኢትዮጵያን መጻኢ የኢኮኖሚ ጊዜ የሚቀርጽ፣ የአፍሪካ ቀጣናን በኃይልና በንግድ የሚያስተሳስር የልማት ማማ እንጂ የትኛውንም ሀገር የሚጎዳ ስጋት አይደለም። የመደመር እሳቤ ያጎናፀፈው ይህ የታሪካዊ ድል ብርሃንም መላውን ቀጣና ማብራቱን ቀጥሏል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም