ቀጥታ፡

በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት

‎አዲስ አበባ፣ነሐሴ 6/ 2018 (ኢዜአ)፦በአሜሪካ ኦሪገን በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን አቀባበል ተደረገለት፡፡

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው 2 ወርቅ፣ 3 ብር እና 1 ነሐስ በድምሩ 6 ሜዳልያዎችን በማግኘት ውድድሯን አጠናቃለች።

የዘንድሮውን ውድድር አዘጋጇ አሜሪካ 24 ሜዳልያዎችን በመሰብሰብ በበላይነት አጠናቃለች።

ኬንያ በ11 ሜዳልያ 2ኛ ሆናለች ፤ ኢትዮጵያ ከዓለም 5ኛ ከአፍሪካ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሯን አጠናቃለች።

ከሁለት ዓመት በፊት በፔሩ ሊማ በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ኢትዮጵያ 6 የወርቅ ጨምሮ በአጠቃላይ 10 ሜዳልያ በማግኘት ማጠናቀቋ ይታወሳል።

ሻምፒዮናው በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት ዩጂን ከተማ ሄይዋርድ ፊልድ ከሐምሌ 29 ቀን እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ተካሂዷል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም