ቀጥታ፡

ለዋልያዎቹ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ዝግጅት ለ39 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 4 /2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ለ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎች ለ39 ተጫዋቾች ዛሬ ጥሪ አድርገዋል።

ጥሪ ከተደረገላቸው ተጫዋቾች መካከል ከ20 ዓመት በታች ናሽናል ካምፕ ላይ የሚገኙ ስድስት ተጫዋቾች ይገኙበታል።

ተጫዋቾቹ አርብ ነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በመሰባሰብ ዝግጅት ማድረግ እንዲጀምሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጥሪ አቅርቧል።

36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ በ2027 በኬንያ፣ ዩጋንዳ እና ታንዛንያ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል።

በውድድሩ ላይ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ።

48 ሀገራት በ12 ምድብ ተከፍለው ለአፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ይጫወታሉ።

ኢትዮጵያ በምድብ 10 ከሴኔጋል፣ ሞዛምቢክ እና ሱዳን ጋር ተደልድላለች።

የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዎች በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም ይደረጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም