ቀጥታ፡

የሀገር ሉዓላዊነትንና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ ዘመናዊ ሰራዊት ለማደራጀት ቴክኖሎጂ ወሳኝ ነው-ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018(ኢዜአ)፦የሀገር ሉዓላዊነትንና ብሔራዊ ጥቅምን የሚያስጠብቅ ዘመናዊ ሰራዊት ለማደራጀት ቴክኖሎጂ ወሳኝ ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ፡፡

የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሰራዊት እና የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በሰው ሠራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ የተደራጀ ዘመናዊ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለመገንባት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በስምምነቱ ወቅት እንደገለጹት፥ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩቱ መቋቋም ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡

የሀገርን ሉዓላዊነት እና ብሔራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ በሚያስችል መልኩ ዘመናዊ ሠራዊት ለማደራጀት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መታገዝ ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል።

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) በበኩላቸው፥ የኤ.አይ ቴክኖሎጂ ለመከላከያ ኃይል በተለይም በአየር፣በምድር እና በሳይበር አቅም ግንባታ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተናግረዋል።

የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ም የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ለመደገፍ ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጸዋል።

ሁለቱ ተቋማት በሎጂስቲክስ፣ በስልጠና፣ በሳይበር ደህንነት፣ በመከላከያ ሰራዊት ጤና አጠባበቅ፣እንዲሁም በአየር ኃይል እና በኤሌክትሮኒክስ ዋርፌር ዘርፎች በኤ.አይ በመታገዝ የሠራዊቱን አቅም ማሳደግ የሚያስችሉ አበይት ጉዳዮችን ላይ መወያየታቸውን ከአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም