ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Aug 3, 2026 210
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡ አገልግሎቱ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው። መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል። ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ ባለቤትነት ተቀብለው ለስኬቱ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም በዛሬው ዕለት 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን ግብ ከዕቅድ በላይ አሳክተውታል። ይህ መንግሥትና ሕዘብ ሲተባበሩ ምን ማድረግ አንደሚችሉ የሚያሳይ፣ ማንም በዓለም ላይ ያለ ሀገር በቀላሉ ሊያሳካው የማይችል ድንቅ ስኬት ነው። ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና የመንግሥት ስትራቴጂካዊ አቋም በአንድ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ነው። በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው መሬት ሲያለምዱ ውለዋል፤ በዚሁ ጽኑ እንቅስቃሴም የዘንድሮው ክረምት ከገባ ጀምሮ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ኢትዮጵያ በልጆቿ ኮርታለች፤ መንግሥትም የሕዝቡን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ባየበት በዚህ ታሪካዊ ክስተት ከፍተኛ ኩራትና ክብር ተሰምቶታል። ይህም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሕዝብ በበለጠ ኃላፊነትና ታማኝነት የማገልገል ጽኑ አቋሙን እንዲያጠናክር ተጨማሪ ብርታት ሆኖታል። ክቡራን ኢትዮያውያን፣ ክቡራን የኢትዮጵያ ወዳጆችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አካላት፤ ዛሬ ይኸንን አገራዊ ራዕይ በጋራ እውን ማድረግ እንድንችል ስላደረጋችሁት ከፍተኛ ርብርብ መንግሥት በኢትዮጵያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። የክረምቱን አጠቃላይ የ8 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረው አገራዊ ተሳትፎና ጽኑ አቋም ተጠናክሮ ይቀጠጥላል። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የተከልነው ችግኝ የነገ ተስፋችንን የሚያለመልም ነው- በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
Aug 3, 2026 132
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 27/2018(ኢዜአ)፡- የተከልነው ችግኝ የነገ ተስፋችንን የሚያለመልም ነው ሲሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ተናገሩ። በሀዋሳ ከተማ 15ኛ ዙር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰልጠናን እየተከታተሉ ያሉ ወጣቶች በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተሳትፈው አሻራቸውን አሳርፈዋል። ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መካከል ወጣት መስከረም አበራ፤ሙሉጌታ ሀይሌ እና ወጣት ተመስገን አሼቦ እንዳሉት ዛሬ የተከልናቸው ችግኞች የነገ ተስፋዎቻችን በመሆናቸው ከተከላው ባሻገር የእንክብካቤው ስራ ላይ እንሳተፋለን። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እያስገኝ ካለው ጠቀሜታ ባሻገር ለቀጣዩ ትውልድ የለማች ሀገር ለማስተላለፍ ወሳኝ ምእራፍ መሆኑን ተናግረዋል።   የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የህዝቦች አንድነትና ትስስር እያጠናከረ መምጣቱን አመልክተው ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፎም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ ከተጀመረ ወዲህ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚሰማሩበት አካባቢ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ነው ያረጋገጡት። የስልጠውና አስተባባሪ ወይዘሮ አበባ ተገኝ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ መላው ህዝብ እየተከለ ያለው ችግኝ የቀጣዩን ትውልድ ተስፋን የሚያለመልም የጋራ ሀብት ነው ብለዋል። ባለፉት ጊዜያት በሀገሪቱ የተተከሉ ችግኞች የአፈር መሸርሸርን በማስቀረትና ለምነትን በማሳደግ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ያደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የድርቅና የጎርፍ አደጋዎችን በመከላከል ውጤት አስገኝቷል
Aug 3, 2026 203
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የድርቅና የጎርፍ አደጋዎችን በመከላከል ውጤት ማስገኘቱን የተለያዩ ክልሎች የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሮች አመለከቱ ። የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል ኮሚሽነሮች፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሀዋሳ ከተማ በተካሔደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተሳትፈዋል።   የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በየአመቱ ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥ በመዋጋት ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች። እየተካሔደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ችግር መፍትሔ በመሆን ልምድ የሚወሰድባት ሀገር እንድትሆን እያደረጋት ነው ብለዋል።   ችግኞችን መትከል በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ እንዲሳካ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር አብዱሰላም ሙሴ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የጎርፍ ስጋት ከመቀነስ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አስችሏል ብለዋል። በዛሬው እለት የተካሔደው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መላውን ማህበረሰብ ያለ ልዩነት በማሰለፍ መጻኢ ልምላሜና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ነው የጠቀሱት።   የሶማሌ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ የአደጋ ምላሽ ፈንድ ዳይሬክተር አቶ በሽር አረብ ፤ የችግኝ ተከላው በደን ሽፋን መቀነስ ሳቢያ የሚከሰቱ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ለመከላከል መፍትሔ መሆኑን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት በክልሉ የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች የአፈር ለምነት ከመጨመር ባለፈ ጎርፍና ሌሎች ችግሮችን ለመቀነስ እንዳስቻለም ነው ያነሱት። በፌዴራል ፖሊስ 6ኛ ሬጂመንት 2ኛ ሻምበል አመራር ዋና ሳጂን አይጎታ አላ በበኩላቸው፤ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ ሁለንተናዊ ልማቷ እንዲጠናከር በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ አሻራ ተሳትፎ መደረጉን ነው የጠቀሱት።
አረንጓዴ ዐሻራ ለመጪው ትውልድ ጽዱና አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን የማስረከብ ትውልድ ተሻጋሪ ተግባር ነው
Aug 3, 2026 142
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ ለመጪው ትውልድ ሚዛኗን የጠበቀች፣ ለኑሮ ተስማሚ፣ ጽዱና አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን የማስረከብ ትውልድ ተሻጋሪ ተግባር መሆኑን የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገለጹ። የዘንድሮው "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል።   የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አዳማ ፈጣን መንገድ ዳርቻ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ አረንጓዴ ዐሻራ ሚዛኗ የተጠበቀች፣ ፅዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ የምናወርስበት የታሪካችን አንድ አካል ነው። መርሃ ግብሩም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ የሚያስተላልፍ የልማት ውርስ መሆኑን አንስተዋል። የአረንጓዴ ዐሻራም የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት አቅም እየፈጠረ የሚገኝ ውጤታማ የልማት ትልም መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች ሁለንተናዊ ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶና የአርብቶ አደሮችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉና የሚተከሉ ችግኞችም የአካባቢን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር ለምግብ ዋስትና የሚረዱ የፍራፍሬ እና ለአካባቢ ጥበቃ ጠቀሜታ ያላቸው እንደሆኑም ጠቁመዋል። በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞችን ተከታትሎ ማሳደግ፣ መንከባከብና የፅድቀት መጠናቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።   የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንገ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመቋቋም ከምትሰራቸው ስራዎች አረንጓዴ አሻራ ስራ ዋነኛው መሆኑን ገልፀው በዚህም አበረታች ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል። መርሃ ግብሩ የደን ሽፋን ከመጨመር በላይ የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ በሚሰራው ስራ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።   የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአፈር መሸርሸር፣ ለውሃ ሀብት ጥበቃና ለግብርና ምርታማነት ትርጉም ያለው ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ የገለፁት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ምክትል ስራ አስፈፃሚ መልእክተ ሳህሉ ናቸው።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ያስችላል
Aug 3, 2026 129
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ የሚያስችል መሆኑን ኢዜአ የነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ሲካሄድ የዋለው በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ805 ሚሊዬን በላይ ችግኞችን በመትከል ተጠናቅቋል፡፡ ኢዜአ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለየዩ የችግኝ መትከያ ቦታዎች ቅኝት አድርጎ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት አረንጓዴ ዐሻራ ለመጭው ትውልድ የተሻለች ሀገርን ማስረከብ ያስችላል ብለዋል፡፡ ከአስተያየት ሰጭዎች መካከል በክብካብ አስፋው፤ የአረንጓዴ ዐሻራችንን በማኖራችን ለቀጣዩ ትውልድ የለመለመች ኢትዮጵያን ማስተላለፍ ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ሌላው በመርሃ ግብሩ ሲሳተፉ ያገኘናቸው መክብብ አበበ በበኩላቸው፤ በአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ ይገባል ብለዋል፡፡ በመርሀ ግብሩ ተሳታፊ መሆን የሚያስደስት መሆኑን የገለጹት ሌላው አስተያየት ሰጭ ነጋሽ ወሌ፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የጎላ አበርክቶ እንዳለው አንስተዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ የተግባር እርምጃ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ካሳሁን አህመድ ናቸው።
የሚታይ
ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Aug 3, 2026 210
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡ አገልግሎቱ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው። መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል። ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ ባለቤትነት ተቀብለው ለስኬቱ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም በዛሬው ዕለት 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን ግብ ከዕቅድ በላይ አሳክተውታል። ይህ መንግሥትና ሕዘብ ሲተባበሩ ምን ማድረግ አንደሚችሉ የሚያሳይ፣ ማንም በዓለም ላይ ያለ ሀገር በቀላሉ ሊያሳካው የማይችል ድንቅ ስኬት ነው። ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና የመንግሥት ስትራቴጂካዊ አቋም በአንድ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ነው። በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው መሬት ሲያለምዱ ውለዋል፤ በዚሁ ጽኑ እንቅስቃሴም የዘንድሮው ክረምት ከገባ ጀምሮ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ኢትዮጵያ በልጆቿ ኮርታለች፤ መንግሥትም የሕዝቡን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ባየበት በዚህ ታሪካዊ ክስተት ከፍተኛ ኩራትና ክብር ተሰምቶታል። ይህም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሕዝብ በበለጠ ኃላፊነትና ታማኝነት የማገልገል ጽኑ አቋሙን እንዲያጠናክር ተጨማሪ ብርታት ሆኖታል። ክቡራን ኢትዮያውያን፣ ክቡራን የኢትዮጵያ ወዳጆችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አካላት፤ ዛሬ ይኸንን አገራዊ ራዕይ በጋራ እውን ማድረግ እንድንችል ስላደረጋችሁት ከፍተኛ ርብርብ መንግሥት በኢትዮጵያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። የክረምቱን አጠቃላይ የ8 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረው አገራዊ ተሳትፎና ጽኑ አቋም ተጠናክሮ ይቀጠጥላል። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
ኢትዮጵያውያን ለልጆቻቸው መሰረት መጣል ሲወስኑ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለዓለም ህዝብ አሳይተዋል
Aug 3, 2026 160
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን ለነገ ለልጆቻቸው መሰረት መጣል ሲወስኑ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለዓለም ህዝብ ያሳዩበት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ሲካሄድ የዋለው በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ805 ሚሊዬን በላይ ችግኞችን በመትከል ተጠናቅቋል፡፡   ኢትዮጵያ ዛሬ ያሳካችው ድል በብዙ ሀገራት ሊታሰብ ይችላል ነገር ግን በቀላሉ ሊሳካ እንደማይችል የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንን ታላቅ ተግባር የፈጸመው የኢትዮጵያ ህዝብ በታላቅ ክብር አመሰግናለሁ ብለዋል፡፡   የኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት ክፍያ ሳይከፈላቸው ሙሉ ቀን ያውም በዝናብ ችግኝ ሲተክል መዋል በዋዛ ፈዛዛ የሚታይ አይደለም ብለዋል፡፡ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ለዚህ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያውያን ምንም ማድረግ እንደሚችሉ በተግባር ማሳየታቸውን ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያውያን ተደምረን ተስፋን በመትከልና መሰረት በመጣል የነገዋን ኢትዮጵያ የምትበለጽግ፣ የማትለምን፣ ለተቸገሩት የምትደርስ መሆኗን ለአፍሪካም ለዓለምም ማሳየት አለብን ብለዋል፡፡ በመሆኑም በሌሎች ሥራዎቻችን አብሮ በመቆም፣ በመተባበርና በቀና እሳቤ ተስፋን ለልጆቻችን መዝራት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡   ዛሬ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ወጥቶ መትከሉ ብቻ ሳይሆን ተቋሞቻችን ያላቸውን ብቃት በተግባር አይተንበታል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያውያን ለነገ ለልጆቻቸው መሰረት መጣል ሲወስኑ ምን ማድረግ እንደሚችሉ ለዓለም ህዝብ አሳይተዋል ብለዋል፡፡ በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ተስፋን እንተክላለን ብለን ከጀምረንበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 6 ነጥብ 5 ቢሊዬን ችግኝ መትከል ችለናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ቀሪው 1 ነጥብ 5 ቢሊዬን ችግኝ በቀጣይ ወራት እንደሚተከል ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአንድ ቀን ከ805 ሚሊዬን በላይ ችግኝ በመትከል ሪከርድ መስበሯንና ማድረግ እንደምትችል ደጋግማ ያሳየችበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ኢዜአ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ህብረተሰቡን ከማንቃት ባለፈ በተግባርም አርአያነቱን እያሳየ ይገኛል
Aug 3, 2026 179
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት(ኢዜአ) በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የህብረተሰቡን ተሳትፎ ለማጠናከር የማንቃትና የመቀስቀስ ሚናውን ከመወጣት ባሻገር በተግባርም አርአያነቱን እያሳየ እንደሚገኝ የተቋሙ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ ገለጹ። "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄደው የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ተካሄዷል።   ኢዜአ ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ እና ከወረዳ 6 አመራሮች ጋር በመሆን በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ አከናውኗል። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሰይፈ ደርቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ተቋሙ በ2018 የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለሶስተኛ ጊዜ የችግኝ ተከላ አካሂዷል።   ዛሬ በተካሄደው የችግኝ የመትከል መርሃ ግብርም የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች መሳተፋቸውን ተናግረው፤ በቀጣይም የተተከሉትን ችግኞች የመንከባከብ ስራ እንደሚያከናውን ተናግረዋል።   ኢዜአ ለአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስኬት ህብረተሰቡን የማንቃትና የመቀስቀስ ሚናውን ከመወጣት ባሻገር በተግባርም አርአያነቱን እያሳየ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 ዋና ስራ አስፈጻሚ አለማየሁ መርጋ በበኩላቸው፤ የወረዳው ነዋሪ ከለሊት ጀምሮ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በንቃት ሲሳተፍ መቆየቱን ገልጸዋል።   የወረዳው ነዋሪዎች በየጊዜው በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሚያደርጉት ተሳትፎ እያደገ መምጣቱን ያነሱት አቶ አለማየሁ፤ በቀጣይም ይህንኑ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።   በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በከፍተኛ ንቅናቄ ተጀምሮ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በነቂስ ወጥቶ ሲተክል መዋሉን የተናገሩት ደግሞ የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ ቅድስት ንጋቱ ናቸው።
ያቀደችውን በተግባር የምታሳካ ታላቅ ሀገር
Aug 3, 2026 265
የአንድ ሀገር ታላቅነት ከሚለካባቸው ጉዳዮች አንዱ የተያዙ ሀገራዊ እቅዶችን በተግባር የመለወጥ አቅም ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያም በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው አዲስ ታሪካዊ ስኬት፣ ሀገሪቱ ያቀደችውን በተግባር ማሳየት የምትችልና ትልልቅ ህልሞችን የመተርጎም አቅም ያላት ታላቅ ሀገር መሆኗን ለመላው ዓለም በተግባር ያስመሰከረ ነው። ይህ በአንድ ጀምበር የተከናወነ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በርካታ ጥልቅ ትርጉሞችን የያዘ ነው፡ በአንድ ጀንበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል ግዙፍ የሎጂስቲክስ፣ የዝግጅትና የህዝብ ንቅናቄ ስራን ይጠይቃል።   ይህ ስኬት ሀገሪቱ ማንኛውንም ታላቅ አገራዊ እቅድ አቅዳ እስከ መጨረሻው የትግበራ ምዕራፍ ድረስ በብቃት የመምራትና የማስተባበር ተቋማዊና ህዝባዊ አቅም እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ዕድሜ፣ ጾታ፣ ወይም ልዩነት ሳይለያያቸው በአንድ ቀን ለተመሳሳይ አገራዊ ዓላማ መቆማቸው፣ ኢትዮጵያውያን ለጋራ እድገታቸውና ለሀገራቸው የወደፊት ተስፋ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎትና አንድነት አሳይቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት ዋና ስጋት በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ እርምጃ ለችግሩ መፍትሔ በመስጠት ረገድ የዓለም አቀፍ መሪነቷን ያስመሰከረችበት አጋጣሚም ጭምር ነው። ይህ ስኬት ሀገሪቱ የገጠሟትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች ተሻግራ፣ አቅሟን አስተባብራ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደምትችል ለዜጎቿም ሆነ ለውጭው ዓለም የሰጠችው ትልቅ የራስ መተማመንና የተስፋ መልእክት ነው። በአጠቃላይ፣ በአንድ ጀምበር የተከናወነው ይህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ አርቆ የማሰብና የማቀድ ችሎታዋን ብቻ ሳይሆን፣ ያቀደችውንም በአንድነትና በቁርጠኝነት ወደ መሬት በማውረድ በተግባር የምታሳይ ታላቅ ሀገር መሆኗን በግልጽ ያረጋገጠ አኩሪ ተግባር ነው።
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማሳደግ የዜጎች የሀገራዊ ልማት ባህል እየሆነ ነው
Aug 3, 2026 205
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማሳደግ የዜጎች የሀገራዊ ልማት ባህል እየሆነ መምጣቱን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የዘንድሮው "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተካሄዷል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አዳማ ፈጣን መንገድ ዳርቻ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋምና የአፈርና የውሃ ሀብት ጥበቃን በማጠናከር ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ፋይዳ እያስገኘ ነው።   ይህም የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ለደለል ተጋላጭነት ከመቀነስ ባለፈ የኤሌክትሪክ ኃይልን ዘላቂነትና የምግብ ዋስትናን የሚያጠናክር አቅም እየፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን መትከላቸውን ገልጸዋል። መርሃ ግብሩም የኢትዮጵያን የአቮካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ምርቶች ወጪ ንግድ ምርታማነትን በማሳደግ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።   የዜጎችን የይቻላል መንፈስ በማጎልበትም ኢትዮጵያ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እያተረፈች መሆኗን ገልጸዋል። የሕዝቡ ከፍተኛ ተሳትፎም አብሮነትና አንድነትን በማጠናከር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሀገራዊ የልማት ባህል እንዲሆን እያስቻለ መሆኑን አንስተዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማሳደግ የዜጎች የሀገራዊ ልማት ባህል እየሆነ መምጣቱንም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጀሚላ መሀመድ በበኩላቸው፤ በዛሬው ዕለት በሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ የተተከሉት የፍራፍሬ ችግኞች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።   ህብረተሰቡ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለታቀደው ግብ ስኬት ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
የአዲስ አበባ ፖሊስ የመዲናዋን ሰላምና ደኅንነት በማጽናትና የጸረ ሰላም ኃይሎችን ከንቱ ዓላማ በማምከን የሚያኮራ ተግባር እየፈጸመ ነው - ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ
Aug 2, 2026 583
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 26/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ፖሊስ የመዲናዋን ሰላምና ደኅንነት በማጽናትና የጸረ ሰላም ኃይሎችን ከንቱ ዓላማ በማምከን የሚያኮራ ተግባር እየፈጸመ መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጄኔራል መላኩ ፋንታ ገለጹ። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ የሥራ ክፍሎች፣ አመራሮች፣ አባላትና ባለድርሻ አካላት የእውቅናና የምስጋና መርሃ ግብር አካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ፣ የፖሊስ አመራሮች፣ አባላትና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ በዚሁ ወቅት፤ አዲስ አበባ በተከናወኑ ልማቶች ዜጎችን ተጠቃሚ ከማድረግ ባለፈ በአፍሪካ ተጠቃሽ ከተማ እየሆነች መምጣቷን ገልጸዋል። ይህ እውን እንዲሆን የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የጸጥታ ተቋማት ጋር በቅንጅት በመስራት የከተማዋን ሰላምና ጸጥታ በማስጠበቅ የጎላ ሚና መጫወቱንም አድንቀዋል። መንግሥት ዜጎችን በልማት ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመራቸውን ጥረቶች ለማሰናከል የሚንቀሳቀሱ የጸረ ሰላም ኃይሎች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመተባበር እየሰሩ መሆናቸውን ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ በተቀናጀ የአሰራር ሥርዓት የመዲናዋን ሰላምና ደኅንነት በማጽናትና የጸረ ሰላም ኃይሎችን ከንቱ ዓላማ በማምከን ያስመዘገበው ውጤት የሚያኮራ ነው ብለዋል። በመሆኑም መላው የአዲስ አበባ ፖሊስ አመራርና አባላት የጸረ ሰላም ኃይሎችን ተልዕኮ በማክሸፍ የተገኘውን ስኬት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። በተጨማሪም ወንጀልን አስቀድሞ በመከላከል እና ወንጀል ሲፈጸም ፈጣንና ውጤታማ ምላሽ በመስጠት ረገድ የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።
ከህብረተሰቡ እና ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል - የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ
Aug 2, 2026 454
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 26/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ከህብረተሰቡ እና ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን ማከናወኑን አስታወቀ። ዋና ጠቅላይ መምሪያው በ2018 ዓ.ም የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ የስራ ክፍሎች አመራርና እና አባላት እንዲሁም ተቋሙ ስኬታማ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር እያካሄደ ነው። በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ባለው መርሀ ግብር ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ፣ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ ሊዲያ ግርማ፣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ፣ የፖሊስ አመራር እና አባላትን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ሌተናል ጀነራል አስራት ዴኔሮ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ጠቅላይ መምሪያው ከህዝቡ እና ሌሎች ፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራት አከናውኗል። ዓመቱ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫን ጨምሮ ትላልቅ አህጉራዊ ኹነቶች የተካሄዱበት መሆኑን አስታውሰው፤ ኹነቶቹ በስኬት እንዲካሄዱ የከተማው ፖሊስ ከተለያዩ የጸጥታ ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን አመርቂ ስራ መሰራቱንም ጠቅሰዋል። በማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገለግሎት ህዝቡን ተሳታፊ በማድረግ ስኬታማ ስራ መከናወኑን ገልጸው፤ በዚህም የመዲናዋን ሰላም በማጽናት ረገድም ተጠቃሽ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል። ዋና ጠቅላይ መምሪያው የፖሊስ አባላቱን ውጤታማነት ይበልጥ የሚያልቁ አሰራሮችን እየተገበረ መሆኑን አስታውቀዋል። ለፖሊስ አባላት መኖሪያ የሚሆን ባለ 15 ወለል ህንጻዎች ግንባታ መጀመሩን አስታውሰው፤ የዋና መምሪያው ቢሮ ዕድሳትም በቅርቡ ይጠናቀቃል ብለዋል። የዛሬው የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር በቀጣይም የሚከወኑ ስራዎች በላቀ ተነሳሽነት እንዲሰሩ ለማድረግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
የምክክር ጉባኤው የጋራ መግባባትን የሚገነባ ለአፍሪካም ተምሳሌት የሚሆን ታሪካዊ ሂደት ነው
Aug 2, 2026 466
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 26/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ጠንካራ ሀገረ መንግሥትና የጋራ መግባባትን የሚገነባ ለአፍሪካም ጭምር ተምሳሌት የሚሆን ታሪካዊ ሂደት መሆኑን ፖለቲከኞች ገለጹ። ዋናው የምክክር ጉባኤ በ4 ሺህ የሀገር ውስጥና የውጭ ዜጎች የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች መካከል ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መካሄዱን ቀጥሏል። ፖለቲከኛው አበራ በቀለ ለኢዜአ እንዳሉት፤የምክክር ጉባኤው ለዘመናት ሲቆዩ በነበሩ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ መሠረታዊ ሀገራዊ አለመግባባቶች ላይ የጋራ መግባባት ለመፍጠር የተከፈተ ታሪካዊ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል። በጉባኤው የሕዝብ ውክልና የተሰጣቸው ተመካካሪዎችም ለዘመናት ሲጠበቅ የነበረውን ታሪካዊ ዕድል በአግባቡ በመጠቀም የጋራ መግባባትን ለመፍጠር መድረኩን ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የምክክር ሂደቱ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅምና በምክክር መፍታት እንደሚችሉ የሚያሳይ በመሆኑ ለአፍሪካም ጠቃሚ ተሞክሮና ትምህርት እንደሚሰጥ ጠቁመዋል። የኢትዮጵያን ችግሮች በራሷ መንገድ በጋራ መግባባት መፍትሔ የምትሰጥ ሀገር ስትሆን ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎቷን የምታስጠብቅ ጠንካራ ሀገር መገንባት እንደሚያስችል ተናግረዋል።   የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና ፖለቲከኛ አብርሃም በርታ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ የምክክር ጉባኤው ሀገራዊ መግባባትን በማጠናከር ሰላምን፣ ብሔራዊ ደህንነትንና ልማትን ለማፋጠን ከፍተኛ ፋይዳ አለው። አሁን እየተካሄደ ያለው የምክክር ሂደት የይስሙላ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ የቆዩ መሠረታዊ ሀገራዊ ችግሮችን በተጨባጭ ለመፍታት የታለመ መሆኑን አስረድተዋል። የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች አካታችና አሳታፊነትም ሁሉም ዜጋ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎችና ችግሮች በማንጸባረቅ የጋራ ሀገራዊ መግባባትና አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ፖለቲከኞቹ እንደገለጹት፤ የሀገራዊ ምክክር ጉባኤው የኢትዮጵያን ችግሮች በዜጎቿ ምክክርና መግባባት ለመፍታት የሚያስችል ታሪካዊ ዕድል ከመሆኑም በላይ የፓን አፍሪካኒዝምን እሳቤ በተግባር የሚያንጸባርቅ ሂደት መሆኑን አመልክተዋል። ይህም አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው አቅምና ችሎታ መፍታት እንደሚችሉ ጠንካራ መልዕክት የሚያስተላልፍ መሆኑን ጠቅሰዋል። የምክክሩ ውጤትም ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀጣናውና ለመላው አፍሪካ በሰላም ግንባታ፣ በልማትና በጋራ መግባባት ረገድ ጠቃሚ ተሞክሮ እንደሚሆን ገልጸዋል። በተጨማሪም ልዩነቶችን በኃይል ሳይሆን በውይይትና በሃሳብ የበላይነት የመፍታት የሰላም ባህልን በማጠናከር፣ ለቀጣዩ ትውልድ ተምሳሌት የሚሆን ጠቃሚ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል።
ሀገራዊ ምክክር ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሀገራዊ መግባባት ወርቃማ ዕድል ነው
Aug 2, 2026 494
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 26/2018(ኢዜአ)፦ሀገራዊ የምክክር መድረክ ለኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እና የጋራ መግባባት ወርቃማ ዕድል መሆኑን ተመካካሪ ሌተናል ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ሐምሌ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መጀመሩ ይታወቃል። በጉባኤው ላይ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በመሳተፍ በአሁኑ ወቅት በዓበይት ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ጥልቅ ምክክር በማድረግ ላይ ይገኛሉ። ይህ ሀገራዊ የምክክር ሂደት ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም፣ አብሮነት እና የጋራ መግባባት መረጋገጥ እጅግ ታላቅ ተስፋ የተጣለበት መድረክ ሆኗል። ተመካካሪ ሌተናል ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል፣ በምክክር ሂደቱ በከፍተኛ ደስታና አክብሮት እየተሳተፉበት እንደሚገኙ ገልጸዋል። አራት ሺህ ተመካካሪዎች ለሀገሪቱ ሰላም እና የጋራ መግባባት የሀሳብ ፊት አውራሪ ሆነው እንደሚወጡ ትልቅ እምነት እንዳላቸው አንስተዋል። በመድረኩ ተመካካሪዎች ሀሳባቸውን በግልጽ በማንጸባረቅ ላይ መሆናቸውን ጠቁመው፣ ከዚህ አሳታፊ ሂደት ትልቅ ትምህርት እና ልምድ መቅሰም እንደሚቻል አስገንዝበዋል። መድረኩ የመሸናነፍ ሳይሆን ሀገራዊ መግባባት የሚገነባበት ነው ያሉት ሌተናል ጄኔራል ዮሃንስ ገብረመስቀል፣ በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን ታሪካዊ የምክክር ሂደት ተስፋ የጣሉበት መሆኑን አንስተዋል። ሰላማዊ የመፍትሔ ማዕድ በሆነው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ተሰባስቦ መመካከር የተሻለ እና የሰለጠነ አካሄድ መሆኑንም ተናግረዋል። የየትኛውም አካባቢ ችግር የሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ፣ በጋራ መግባባት እና በአብሮነት መንፈስ የጋራ መፍትሔ ማበጀት እንደሚቻልም አስረድተዋል። ይህ ሀገራዊ የምክክር ሂደት በተለይም ልሂቃን በዘመናቸው ያካበቱትን ልምድ፣ ያነበቡትን እና ያወቁትን ወደ መሬት አውርደው ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚኖራቸውን አዎንታዊ ሚና የሚያበረክቱበት ወርቃማ ዕድል ነው ብለዋል። በመሆኑም ያላቸውን ሀሳብ ሰብሰብ አድርገው ለሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምና አብሮነት አስተማማኝ መሠረት እንዲጥሉ የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።  
የምክክር ጉባኤው ለኢትዮጵያ አዲስ የምክክር ልምምድን የከፈተ ታሪካዊ ዕድል ነው
Aug 2, 2026 598
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለኢትዮጵያ አዲስ የምክክር ልምምድን የከፈተ ታሪካዊ ዕድል መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲዎች ገለጹ። የፖለቲካ ፓርቲ ተወካይ ተመካካሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ በጉባኤው የግልና የቡድን ፍላጎቶችን በማጥበብ ሀገራዊ ጥቅምን በማስቀደም፣ በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ ነፃና አሳታፊ ምክክር እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለኢትዮጵያ አዲስ የምክክር ልምምድን የከፈተ ታሪካዊ ዕድል መሆኑንም የፖለቲካ ፓርቲ ተወካይ ተመካካሪዎች ገልጸዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) ተወካይና ተመካካሪ ጣሂር መሐመድ እንዳሉት፤ በምክክር ጉባኤው ሀገርን ወደ ተሻለ ምዕራፍ የሚያሸጋግር ምክክር እየተደረገ ነው። በዋናው የምክክር ጉባኤ የሚመከርባቸው ዐበይትና ንዑሳን አጀንዳዎችም በተመካካሪዎች መካከል በነፃነትና አካታችነት እየተመከረባቸው መሆኑን ገልጸዋል። የምክክር ጉባኤው የኢትዮጵያን መሠረታዊና መዋቅራዊ ችግሮች በሃሳብ የበላይነት ላይ የተመሠረተ መግባባት በመፍጠር መፍትሔ የሚሰጥ ጉልህ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል።   የትግራይ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ትዴፓ) ሊቀመንበርና ተመካካሪ አረጋዊ በርሔ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤው የመደማመጥና የመግባባት ባህልን በማጠናከር በተሻለ አሳታፊነት እየተካሄደ ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ከአጀንዳ ማሰባሰብና ከተሳታፊዎች ልየታ ሂደት ጀምሮ አሳታፊነትንና አካታችነትን በተግባር በማረጋገጥ ውጤታማ ሥራ መሠራቱንም አስታውሰዋል። ከአራቱም የሀገሪቱ ማዕዘናት ሕዝብን የወከሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በዋናው የምክክር ጉባኤ ላይ ሃሳባቸውን በነፃነት በማንሸራሸርና በግልጽ ተሳትፎ ተስፋ ሰጪ ምክክር እያካሄዱ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሀገራዊ ችግሮችን በሰለጠነ ምክክር ለመፍታት፣ በጋራ ጉዳዮች ላይ ለመምከርና ዘላቂ የሆነ መግባባት ለመፍጠር የተገኘ ታሪካዊ ዕድል መሆኑን ጠቁመዋል።   የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) አባልና የጉባኤው ተመካካሪ ሙሐሙድ መሐመድ ሀሰን ለኢዜአ እንዳሉት፤ የምክክር ጉባኤው አራት ሺህ የሕዝብ ወኪል ተመካካሪዎች የኢትዮጵያን ብዝኅነት፣ ሕብረ-ብሔራዊ እሴቶችና የጋራ ሀገራዊ ጥቅሞችን በሚያንጸባርቁ ሃሳቦች ላይ እንዲመክሩ ዕድል ፈጥሯል። ሀገራዊ አለመግባባቶችን በጦር መሣሪያ በታገዘ ግጭትና በኃይል ለመፍታት መሞከር ዘላቂ መፍትሔ የማያማጣና አዋጭ ያልሆነ አካሄድ መሆኑን አስገንዝበዋል። በዚህም የጋራ ሀገርን በመገንባት አዲስ የምክክር ታሪክ እየጻፍን ነው ያሉት አቶ ሙሐሙድ፤ የጉባኤው አጀንዳዎች ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የመግባባት ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።   የቁጫ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንትና ተመካካሪ ገነነ ገረቡ በበኩላቸው፤ በምክክር ጉባኤው አንዱ የሌላውን ሃሳብ መረዳት በሚያስችል መልኩ ማንኛውም የሕዝብ አጀንዳ በነፃነት እየተንጸባረቀ ነው ብለዋል። የምክክር ጉባኤውም ለዘመናት የቆዩ የአለመግባባቶችን ለቀጣዩ ትውልድ እንዳይተላለፉ ለማድረግ ስልጡን ምክክር እያደረግን ነው ብለዋል። በተመካካሪዎች መካከልም በአርአያነት የሚወሰድ ነፃ ምክክር እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል።  
ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት ነው
Aug 2, 2026 563
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለውን ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠበት ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር ቆይታ አድርገዋል።   በቆይታቸውም ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ50 ሺህ በላይ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የተካሄደ ሕዝቡም ያለ አንዳች መሰላቸት ረጅም ሰዓት ተሰልፎ ድምጹን የሰጠበት ነው ብለዋል፡፡ ምርጫ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገለጫ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ምርጫ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መንግሥትን ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት የሚገልጽበት መንገድ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡ ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በምርጫ ሂደቱ መሳተፋቸው ብዙ ነገሮችን እንድንማር አድርጎናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሰላማችንን እንድንፈትሽ፣ ተቋሞቻችንን እንድንፈትሽና የሕዝቡን ስሜት ይበልጥ እንድንገናዘብ አድርጎናል ብለዋል፡፡ ከእንግዲህ በኋላ በኢትዮጵያ ከምርጫ ውጭ ሌላ የስልጣን ማግኛ መንገድ አለመኖሩንም ጠቅሰዋል፡፡ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ስልጣንን በሰላማዊ መንገድና በሕዝብ ይሁንታ ብቻ ማግኘት እንደሚቻል ያሳየ መሆኑን አንስተው፤ ምርጫው ከፍተኛ ትርጉም ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ማንቂያም ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ዜጎች የተኩስ ድምፅ ሳያቆማቸው፣ ዝናብ፣ ብርድና ቁር ሳያቆማቸው ዋጋ ከፍለው ድምጻቸውን ለመስጠት የሄዱበት መንገድ የሚደነቅ ነው ብለዋል፡፡ ምርጫው ኢትዮጵያውያን በሀገረ መንግሥት ግንባታ ላይ አሉታዊ ሃሳቦችን ለመስማት ዝግጁ አለመሆናቸውን በተግባር ያሳየ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ የሀገረ መንግሥት ግንባታና የመንግሥት መኖር ጥቅሙ ምን እንደሆነ ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የዛሬይቱ ኢትዮጵያ በህልውናዋ የሚገዳደራትን ማንኛውንም ስጋት መመከት የሚያስችል አቅም አላት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Aug 1, 2026 781
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 25/2018 (ኢዜአ)፦ የዛሬይቱ ኢትዮጵያ በህልውናዋ የሚገዳደራትን ማንኛውንም ስጋት መመከት የሚያስችል አቅም እና ዝግጁነት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር ቆይታ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል እና ኦሮሚያ ክልል ጫካ የገቡ ኃይሎች በዋናነት “ለህዝብ ጥቅም እንቆማለን እና ለህልውናው እንታገላለን” ቢሆኑም በተግባር ግን እየታየ ያለው በተቃራኒው መሆኑን አንስተዋል። እነዚሁ ሃይሎች ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር የጀመሩት ያልተቀደሰ ጋብቻ በየትኛውም መንገድ ከጥፋት በስተቀር ልማት ሊያመጣ እንደማይችል ተናግረዋል። ከታሪካዊ ጠላቶች የማበር እና የኢትዮጵያን ጥቅም የማሳጣት ጉዳይ በታሪክ ውስጥ የነበረ መሆኑን አውስተዋል። የውስጥ እንክርዳዶችና ሃይሎች ከውጭ ጠላቶች ጋር ያልተቀደሰ ጋብቻ በመፍጠር ኢትዮጵያ የቀይ ባህር እንድታጣ በማድረግ የጂኦግራፊ እስረኛ እንድትሆን ማድረጋቸውን አመልክተዋል። በዚህም ምክንያት በርካታ ትውልዶችን ተጎጂ ያደረገ ታሪካዊ ጥፋት መፈጸሙንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል። እነዚህ ያልተቀደሱ ጋብቻዎች በኢትዮጵያ ላይ ጥቁር ጠበሳ ጥለው ማለፋቸውን ጠቅሰው ያለፈውን ታሪክ ለሚያውቅ ሰው አሁን ላይ ያለውን ነገር በግልጽ መረዳት ይችላለ ብለዋል። አሁን ያለው ያልተቀደሰ ጋብቻ ሽርጉድ ከዚህ ቀደም ከነበሩ መሰል ጥፋቶች ውጪ ለኢትዮጵያውያን ጥቅም እንደማያመጣ አስገንዝበዋል። የዛሬይቱ የኢትዮጵያ የያኔው ኢትዮጵያ አይደለችም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገሪቱ ከዛ ጊዜ መማሯንና የዛን ጊዜ ጥፋቶችና ስብራቶች አውቃ ተዘጋጅታለች ብለዋል። ኢትዮጵያ አሁን ላይ ባላት ህልውና የሚገዳደራት ከመንገዷ የሚያወጣት እንቅስቃሴ ትናንት በነበረው ደረጃ ስጋት እና ጥፋት እንደማያመጣባት ተናግረዋል። እነዚህ ሃይሎች ከትናንትናው ጉዳይ ሊማሩ እንደሚገባም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያውያን የውስጥ ሃይሎች አዲስ ያልተቀደሰ ጋብቻ ለመፍጠር እያደረጉትን ያለውን እንቅስቃሴ በሰከነ መንገድ እንዲያስተውለውም አስገንዝበዋል። የውስጥ ልዩነቶች፣ ችግሮች አለመግባባቶች ኢትዮጵያ ባላት የካበተ የእርቅና ሽምግልና ስርዓት መፍታት እንደሚቻል ገልጸው ከዛ ውጪ የውጭ ሃይሎችን ማስገባት ከጥፋት ውጪ የተለየ ነገር እንደማያመጣ ገልጸዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA
የፕሪቶሪያው ስምምነት የአማራ ክልልን ጨምሮ የመላው ኢትዮጵያውያንን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ነው - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
Aug 1, 2026 661
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 25/2018 (ኢዜአ)፦ የፕሪቶሪያው ስምምነት የአማራ ክልልን ጨምሮ የመላው ኢትዮጵያውያን ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ ማስቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ጋር ቆይታ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፕሪቶሪያ ስምምነትን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ስምምነቱ የጥይት ድምጽን በማስቆም ወደ ልማት ትኩረት እንዲደረግ ማስቻሉን ገልጸዋል። ስምምነቱ የአማራ፣ ትግራይ እና አፋር ክልልሎች አልፎም መላው ኢትዮጵያን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በአማራ ክልል አብዛኞቹ የልማት ስራዎች የተከናወኑት ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ መሆኑ ክልሉን ተጠቃሚ ያደረገ እንደሆነ ዋነኛ ማሳያ መሆኑን አመልክተዋል። የፕሪቶሪያ ስምምነት ላይ በብልጽግና ፓርቲ እና በመንግስት ደረጃ በነበሩ ውይይቶች ላይ የአማራ ክልል ውሳኔ አሻራ መኖሩን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል። በስምምነቱ የተካተቱ ነጥቦች ተግባራዊ መደረጋቸው የአማራ ክልልN የሚጠቅሙ እንጂ በፍጹም የሚጎዱ አይደሉም ብለዋል። የፖለቲካ ቁማርተኞች የአማራ ክልል በፕሪቶሪያው ስምምነት ተሳትፎ አላደረገምና ተጠቃሚ አልሆነም እያሉ የሚያሰራጩት መረጃ ሀሰተኛና የተዛባ መሆኑንም ተናግረዋል። ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ አንጻራዊ ሰላም፣ የተሻለ ልማት እና እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ደረጃ መታየቱንና በዚህም የአማራ ክልል ተጠቃሚ መሆኑን አመልክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #ENA

ማህበራዊ
በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በመሳተፍ የልማት አርበኝነታችንን እያሳየን ነው
Aug 3, 2026 113
ደብረ ብርሃን ፤ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የሀገር ሰላምና የህዝቡን ደህንነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በመሳተፍ የልማት አርበኝነታቸውን እያሳዩ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ አባላት ገለጹ። የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር “ተስፋን እንትከል“ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው። በፌደራል ፖሊስ ሰሜን ምስራቅ ቀጠና 7ኛ ሬጅመንት አዛዥ ዋና ሳጅን ናስር መሐመድ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የፖሊስ አባላቱ በተሰማሩበት አካባቢ ሁሉ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስራዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።   በዚህም አገራቸውንና ህዝባቸውን እያገለገሉ መሆኑን ገልጸዋል። የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ በተለያዩ አካባቢዎች ሰላም ለማስፈን የተሰጣቸውን ተልእኮ ከመወጣት ጎን ለጎን በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በቁርጠኝነት ተሳትፈናል ነው ያሉት። በቀጣይም የተከሏቸውን ችግኞች በመንከባከብ ጸድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ተከታታይ ስራ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። በዋናነትም የህዝብ ደህንነትን ከማስጠበቅ ባሻገር በዛሬው እለት በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመሳተፍ የልማት አርበኝነቱን አረጋግጧል ነው ያሉት።
መከላከያ ሰራዊቱ  ሀገራዊ ግዳጁን  ከመወጣት ባሻገር  የልማት ስራዎች ላይ መሳተፉን ይቀጥላል
Aug 3, 2026 114
ሐረር፤ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ መከላከያ ሰራዊቱ ሀገራዊ ግዳጁን ከመወጣት ባሻገር የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ የህዝብ አለኝታነቱን በተግባር እያረጋገጠ ይቀጥላል ሲሉ የምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ጸጋዬ ተናገሩ። የሰራዊቱ አባላት ከሐረሪ ክልል ማህበረሰብ ጋር በመሆን የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አከናውነዋል።   በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ሜጀር ጀነራል ፍቃዱ ጸጋዬ እንዳሉት፤ሰራዊቱ የሀገርን ሉአላዊነት ከማስጠበቅ ባሻገር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በመሳተፍ የበኩሉን አስተዋጽኦ እያደረገ ነው። ባለፉት ሰባት ዓመታትም የአረንጓዴ አሻራውን ከማኖር ባሻገር ማሕበረሰቡን ተጠቃሚ በሚያደርጉ የልማት ስራዎች ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። በአሁኑ ወቅትም ሰራዊቱ በግብርናው ዘርፍም ተሳትፎ ከማድረግ ባለፈ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ላይ በመሳተፍ የአካባቢውን ህዝብ ተጠቃሚ በማድረግ ስራ ላይ የሕዝብ ወገንተኝነቱን እያሳየ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በየአመቱም በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር እየተሳተፉ መሆኑን የተናገሩት ደግሞ ሌላው የምስራቅ እዝ አባል ኮሎኔል ስሜነህ ብርሃኑ ናቸው።   የሰራዊቱ አባላትም ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ እንዲጸድቁ በማድረግ እየሰሩና የምርቱም ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።   ሻለቃ ሃይሉ ታሪኩ በበኩላቸው፤ ሰራዊቱ ከተሰጠው ግዳጅ ጎን ለጎን የችግኝ ተከላና የአረንጓዴ ልማት ስራዎች ላይ በትኩረት እየተሳተፈ ይገኛል ብለዋል።
በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች በቀሰሙት እውቀት ህዝብን ለማገልገል መትጋት አለባቸው
Aug 2, 2026 321
አምቦ፤ሐምሌ 26/2018(ኢዜአ)፡- በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች በቀሰሙት እውቀት ህዝብን ለማገልገል ሊተጉ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል የሥራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ። የአምቦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሙያ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 590 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡   በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል የሥራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሀብታሙ ካሳ፤ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች በቀሰሙት እውቀት ህዝብን በማገልገል የድርሻቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል። የመማርና መሰልጠን የመጨረሻ ግቡ ችግር ፈች እና መፍትሄ አመላካች በመሆን ዜጎችን ማገልገልና ለሀገር አስተዋጽኦ ማድረግ መሆኑን አንስተው የዛሬ ተመራቂዎችም ይህንኑ ተግባር ለመፈፀም መዘጋጀት እንዳለባቸው ገልጸዋል።   የአምቦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ሙሉነህ ተፈራ፤ ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው የተሻለ እውቀትና ክህሎት ያካበቱ መሆኑን ተናግረዋል። በመሆኑም በቀጣይ በሚሰማሩባቸው የስራ መስኮች ሁሉ ህዝባቸውን በታማኝነት በማገልገል በኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና ሂደት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መክረዋል። የኮሌጁ ተመራቂዎችም በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ በቅነትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
ኢኮኖሚ
አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማሳደግ የዜጎች የሀገራዊ ልማት ባህል እየሆነ ነው
Aug 3, 2026 205
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማሳደግ የዜጎች የሀገራዊ ልማት ባህል እየሆነ መምጣቱን የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ገለጹ። የዘንድሮው "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ ተካሄዷል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አዳማ ፈጣን መንገድ ዳርቻ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፣ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን በመቋቋምና የአፈርና የውሃ ሀብት ጥበቃን በማጠናከር ዘርፈ ብዙ የኢኮኖሚ ፋይዳ እያስገኘ ነው።   ይህም የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ለደለል ተጋላጭነት ከመቀነስ ባለፈ የኤሌክትሪክ ኃይልን ዘላቂነትና የምግብ ዋስትናን የሚያጠናክር አቅም እየፈጠረ መሆኑን አብራርተዋል። በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም የሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማት አመራርና ሠራተኞች ለምግብነት የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን መትከላቸውን ገልጸዋል። መርሃ ግብሩም የኢትዮጵያን የአቮካዶና ሌሎች የፍራፍሬ ምርቶች ወጪ ንግድ ምርታማነትን በማሳደግ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል።   የዜጎችን የይቻላል መንፈስ በማጎልበትም ኢትዮጵያ በአፍሪካና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና እያተረፈች መሆኗን ገልጸዋል። የሕዝቡ ከፍተኛ ተሳትፎም አብሮነትና አንድነትን በማጠናከር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሀገራዊ የልማት ባህል እንዲሆን እያስቻለ መሆኑን አንስተዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የኢትዮጵያን አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅና በማሳደግ የዜጎች የሀገራዊ ልማት ባህል እየሆነ መምጣቱንም አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ጀሚላ መሀመድ በበኩላቸው፤ በዛሬው ዕለት በሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ የተተከሉት የፍራፍሬ ችግኞች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል።   ህብረተሰቡ በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ለታቀደው ግብ ስኬት ችግኞችን በመትከልና በመንከባከብ የበኩሉን ሚና እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው
Aug 3, 2026 203
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ለኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ዕድገትና ለካርበን ልቀት መቀነስ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታዎች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ቱሪዝም ሚኒስቴርና የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አሻራቸውን አኑረዋል፡፡ የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ችግኝ መትከል ለቱሪዝም ዘርፍ ዕድገት መሠረት መጣል ነው፡፡   በዱር እንስሳት ጥበቃ ስፍራዎችና በብሔራዊ ፓርኮች ውስጥ ያለውን የደን ሽፋን እንዲጨምር በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል፡፡ መርሃ ግብሩ የዱር እንስሳትን ስደት ከመቀነስ ባሻገር የፓርኮችን የቱሪስት መስህብነት በከፍተኛ ደረጃ በማሳደግ ጎብኚዎች ከተፈጥሮ ጋር የሚገናኙበትን፣ ንጹህ አየርና አረንጓዴ አካባቢን የሚመርጡበትን የዘላቂ ቱሪዝም ዕድል ያሰፋል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ የምታሳየው የተግባር ምላሽ ዓለም አቀፍ ገጽታዋን በበጎ በመቀየር በዘላቂና በአረንጓዴ ቱሪዝም አርአያ እንድትሆን ማስቻሉን ገልጸዋል፡፡ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሀሰን መሀመድ በበኩላቸው፤ መርሃ ግብሩ የኢትዮጵያውያንን አንድነት በተግባር ያሳየበት ታሪካዊ ክስተት ነው ብለዋል፡፡   በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው ይህ ንቅናቄ ኢትዮጵያን በአየር ንብረት ጥበቃ አርዓያ እና የዓለም አቀፍ የችግሮች መፍትሄ አካል ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የካርበን ልቀትን መቀነስ ቀዳሚ ግቡ መሆኑን በማንሳት፤ አረንጓዴ ዐሻራ በአንድ በኩል የምድርን ጸጋ መጠበቅ በሌላ በኩል ደግሞ የአየር ብክለትን የመከላከል ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡ ባለፉት ዓመታት የተተከሉ የቡና፣ አቮካዶ እና የፍራፍሬ ችግኞች ለቤተሰብ የገቢ ምንጭ፣ ለሀገር ደግሞ የውጭ ምንዛሬ መሳቢያ መሆን ጀምረዋል ብለዋል፡፡ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል፣ የበረሃማነት መስፋፋት በመግታትና እና ለውሃ እጥረት ምላሽ በመስጠት ለነገው ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብም እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እያነጸ ይገኛል 
Aug 3, 2026 141
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ በጽኑ መሠረት ላይ እያነጸ እንደሚገኝ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሀገራዊ ግብ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በይፋ እየተካሄደ ይገኛል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አመራሮች እና ሠራተኞች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ፈጣን መንገድ ላይ ችግኞችን ተክለዋል።   በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ መርሃ ግብሩ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና በሀገሪቱ የተዘረጋውን የአረንጓዴ ትራንስፖርት ስትራቴጂ ለማገዝ ከፍተኛ ሚና አለው። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የአፈር መሸርሸርን ለመከላከል፣ የውሃ ሀብትን ለመጠበቅ እና ለተተኪው ትውልድ የሚተርፍ የተፈጥሮ ፀጋን ለማስረከብ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር የተተከሉ ችግኞች የደን ሽፋን ከመጨመር ባሻገር የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ በሚደረጉ ሥራዎች ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ አውስተዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በከተሞች አካባቢ ደንን ማስፋፋት የከተሞችን ሙቀት በመቀነስ ሰዎች በእግር ወይም በብስክሌት በቀላሉ እንዲንቀሳቀሱ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር አብራርተዋል። ኢትዮጵያ ወደ ኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች የምታደርገውን ሽግግር በዋናነት የምትደግፈው በኤሌክትሪክ ኃይል በመሆኑ፣ የአረንጓዴ አሻራ እንቅስቃሴ የዝናብ ዑደትንና የግድቦችን ደህንነት በመጠበቅ አስተማማኝ ንጹህ ኃይል እንዲኖር እንደሚያስችል ገልጸዋል፡፡ መርሃ-ግብሩ ሀገሪቱ የያዘችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚጥል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍራኦል ጣፋ ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለችው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን ለመቋቋምና ምርታማነትን ለማሳደግ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልፀዋል።   ባለሥልጣኑ ከዚህ ቀደም የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከብ የተሻለ የጽድቀት ምጣኔ እንዲኖር ሲሰራ መቆየቱንና ይህንን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።   የኢትዮጵያ ሲቪል አቬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ዮሐንስ አበራ በበኩላቸው ዓለም በካርበን ልቀት ምክንያት እየተፈተነች እንደምትገኝ ገልፀው አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ይህንን ለመከላከል አይነተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ተናግረዋል።   የፐብሊክ ሰርቪስ ትራንስፖርት ዋና ዳይሬክተር አስካለ ተክሌ በበኩላቸው፤ በትራንስፖርት ዘርፉ የበካይ ጋዝ ልቀትን ለመከላከል በመርሃ ግብሩ ተሳታፊ በመሆን ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተከታትሎ የመንከባከብ ስራም እያከናወንን እንገኛለን ብለዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ ፅዱና ማራኪ ከተሞችን በመፍጠር ለነዋሪዎች ምቹ የከተሜነት ምህዳር እየገነባ ነው
Aug 3, 2026 160
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ፅዱና ማራኪ ከተሞችን በመፍጠር ለነዋሪዎች ምቹ የከተሜነት ምህዳር እየገነባ መሆኑን የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡ "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ የሚካሄደው የአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ሀገራዊ መርሃ ግብር ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማትም በዚሁ ሀገራዊ መርሃ ግብር በመሳተፍ የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ አካሂደዋል። የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ በዚሁ ወቅት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአብሮነትን መንፈስ በማጠናከር፣ ሀገረ መንግሥትን በመገንባትና የዜጎችን የኑሮ ደረጃ በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።   መንግሥት የሕዝብን ተሳትፎ በማሳደግ የሚተከሉ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ በአግባቡ በመንከባከብ እስከ ፍሬ እንዲደርሱ በትኩረት እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል። የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራምም የከተማ ግብርናን በማስፋፋት፣ የአካባቢ ጥበቃና ውበትን በማጎልበት፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል በመፍጠርና የኑሮ ደረጃቸውን በማሻሻል ጉልህ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝ ጠቁመዋል። ከተሞች የመኖሪያ ስፍራ ብቻ ሳይሆኑ የምርት ማዕከላት እንዲሆኑ ታስቦ የተነደፈው ፕሮግራም የተተከሉ ችግኞችን ከመንከባከብ ጀምሮ ለምርት እስኪደርሱ ድረስ ክትትል የሚደረግበት መሆኑንም አብራርተዋል። አረንጓዴ ልማቶች የዜጎችን ተጨማሪ ገቢ ከማሳደግ ባለፈ፣ ከተሞችን ምቹ፣ ንጹሕና አረንጓዴ በማድረግ ለቀጣይ ትውልድ ተስማሚ የኑሮ አካባቢ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙ አስረድተዋል።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የተጀመረው የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ በቴክኖሎጂ፣ በፍጥነት፣ በፈጠራ፣ በጥራትና በታማኝነት ማስፋፋቱ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jul 30, 2026 727
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018(ኢዜአ)፦‎ የተጀመረው የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ በቴክኖሎጂ፣ በፍጥነት፣ በፈጠራ፣ በጥራትና በታማኝነት ማስፋፋቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ አስገነዘቡ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዛሬ ሀገር በቀል ሆኖ በሰባት አምዶች ተደራጅቶ የተቀረጸውን የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር አፈጻጸም ሪፖርት ለሪፎርም ምክር ቤቱ ቀርቦ በዝርዝር ተገምግሟል ብለዋል። አምዶቹም ዘመኑን የዋጀና በተዋረድ የተናበበ አደረጃጀት፣ ብቃት ያለው የሰው ኃይል ስምሪት፣ ብዝሃነት፣ ዲጂታላይዜሽ፣ የለውጥ አመራር እና የአገልግሎት ማሻሻያን የያዘ መሆኑን ገልጸዋል።   አፈጻጸሙም ፍጥነትን፣ ፈጠራን፣ ፈጻሚዎቹን ባለቤት ማድረግንና ዘላቂ ሥርዓት ግንባታን መሠረት ተደርጎ በጥብቅ ዲስፕሊንና በእውቀት ውጤታማ እና ተስፋ በሚሰጥ ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑንም አይተናል ነው ያሉት በመልዕክታቸው። በሪፖርቱ ሰው ተኮር በሆነ ሁኔታ የመሶብ አገልግሎትን በማስፋፋት ሂደት ጉልህ የሚባል መሻሻል በየከተሞቹ ታይቷል ሲሉም አስታውቀዋል። በመልዕክታቸው አክለውም በአገልግሎት ማሻሻያ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የምንችል መሆኑንና በዜጎች በኩል የነበረውን እሮሮ መፍታት መጀመራችን በተግባር የታየበትም ጉዳይ ነው ብለዋል። የተጀመረው የመንግስት አገልግሎት ማሻሻያ በቴክኖሎጂ፣ በፍጥነት፣ በፈጠራ፣ በጥራትና በታማኝነት ማስፋፋቱ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋለ። ለዚህም ሥራ የጠራ መረጃ ማደራጀት፣ ቴክኖሎጂን ማበልጸግና የሰራተኞችን ብቃት ማጠናከር የቀጣይ ትኩረት እንዲሆን በምክር ቤቱ አቅጣጫ መቀመጡንም ገልጸዋል።
የዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ሂደት እና ‘የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ’ ኢኒሼቲቭ ትግበራ ተጠናክሮ ይቀጥላል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Jul 30, 2026 534
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ሂደት እና ‘የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ’ ኢኒሼቲቭ ትግበራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባውን ማድረጉን ገልጸዋል።   ምክር ቤቱ በአመቱ ውስጥ እንዲፈፀሙ ያስቀመጣቸውን ተግባራት አፈፃፀም በጥልቀት በማየት አቅጣጫ ማስቀመጡን አመልክተዋል። የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤቱ አጠቃላይ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የስራ ክንውን፣ የዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ሂደት እንዲሁም ‘የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ’ ኢኒሼቲቭ ትግበራ አፈጻጸምን ገምግሞ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል። ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ የሚገኙ አዳዲስ የዲጂታል ስራዎች ከዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ጋር ያላቸውን ተጣጣሚነትን በውይይታችን ተመልክተናል ሲሉ ተናግረዋል። የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ የሚያድግበት ዘመን ላይ እንደመሆኑ፤ ምክር ቤቱም ለዚሁ ዕድገት ተገቢውን ሚና ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።
በክልሉ የመንግስት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር የተገልጋይን እንግልት ለመቀነስ አስችሏል
Jul 30, 2026 337
ወራቤ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ) ፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመንግስት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር የተገልጋይን እንግልት ለመቀነስ ማስቻሉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር፣ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አንተነህ ፈቃዱ ገለፁ። የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሚመክር መድረክ በወራቤ ከተማ እያካሄደ ይገኛል።   በዚህ ወቅት አቶ አንተነህ እንዳሉት፤ በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመንግስት አገልግሎትን ዲጂታላይዝ የማድረጉ ተግባር የተገልጋይን እንግልት ለመቀነስ አስችሏል። ለዚህም በተቋማት ግንባታና በሰው ኃይል ማብቃት ላይ በመሥራት ሰባት የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል። በዚህም በመንግሥት የሚሰጡ አገልግሎቶች ላይ ይስተዋሉ የነበሩ ብልሹ አሠራሮችን ከመቅረፍ በተጨማሪ የማኅበረሰቡን እርካታ እያሳደገ መምጣቱን ገልጸዋል። የክልሉ ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሰላሙ አማዶ በበኩላቸው፤ በክልሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራን ለማሳካት በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የሰው ኃይል ልማት ላይ እየተሠራ መሆኑን ተናግረዋል።   በዚህም በበጀት ዓመቱ ከ235 ሺህ በላይ ዜጎች ስልጠናውን መውሰዳቸውንና ከእነዚህም ውስጥ ከ185 ሺህ በላይ የሚሆኑት የእውቅና ሰርተፊኬት ማግኘታቸውን አስረድተዋል። ስልጠናውን ወስደው እውቅና ያገኙትንም የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል። በዞኑ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ትግበራ ዘርፈ-ብዙ ውጤቶች እየተመዘገቡ መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሙበራ ከማል ናቸው።   በዞኑ የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን የማስፋፋቱ ስራ የመንግሥት አገልግሎትን ለማዘመንና ለወጣቶች የሥራ ዕድልን ለመፍጠር እየዋለ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ይህም የተገልጋዩን ማኅበረሰብ ጊዜ፣ ጉልበትና እንግልት በማስቀረት ረገድ ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበበት እንደሚገኝ ገልጸዋል። በወራቤ ከተማ ተግባራዊ የተደረገውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ወደ ሌሎች የዞኑ መዋቅሮች የማስፋፋት ሥራ ስለመጀመሩም አክለው ገልጸዋል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ቀልጣፋ የመንግስት አሰራር እንዲሰፍን እያደረገ ነው 
Jul 29, 2026 435
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ) :-መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ብልሹ አሰራሮችን በማስወገድ ቀልጣፋ የመንግስት አሰራር እንዲሰፍን እያደረገ ነው ሲሉ ምሁራን ገለጹ። በፌዴራል ደረጃ በአዲስ አበባ የተጀመረው የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትም በሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በማስፋት ዘመናዊ አገልግሎት እየተፈጠረ ነው። በዚህም አገልግሎቱ በተጀመረ አንድ ዓመት ባልበለጠ ጊዜ 102 ማዕከላት፣ ሦስት ተንቀሳቃሽና አንድ የተቀናጀ መተግበሪያ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ሥራ ገብተዋል፡፡ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ አማራጮችም 953 ተቋማትን በማስገባት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች አገልግሎት አግኝተዋል፡፡ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥትን አገልግሎት ጥራት በማሻሻል የተገልጋዮችን እርካታ በማሳደግ የመልካም አስተዳደር ሥርዓትን እያሰፈነም ይገኛል፡፡ ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራን ፤ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት በሀገር ደረጃ ትልቅ የለውጥ እርምጃ እንዲሁም የመልካም አስተዳደርና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጫ መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደርና አመራር ትምህርት ክፍል መምህር ኡጁሉ ኡኮክ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ማዕከሉ ህዝቡ ለአንድ አገልግሎት ወደተለያዩ መሥሪያ ቤቶች መመላለስ ሳይጠበቅበት ጊዜውንና ገንዘቡን በአግባቡ እንዲጠቀም የሚያስችል ትልቅ ማሻሻያ ነው። አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ከብልሹ አሠራር የጸዳ ሥርዓት በመፍጠር ግልጽነትና ተጠያቂነትን እንደሚያሰፍን ገልጸዋል። ይህ አሰራር ብልሹ አሰራርን በማስቀረት፣ ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥንና መልካም አስተዳደር ለማረጋገጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዚሁ ዩኒቨርሲቲ የልማታዊ ተግባቦትና የሚዲያ ጥናት መምህርና ተመራማሪ ዘለቀ ተሾመ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓቱ ህብረተሰቡ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ላነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ መሆኑን አንስተዋል። መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ከዚህ ቀደም የነበረን መጉላላት በማስቀረት የተቀላጠፈ፣ ምቹና ዘመኑን የዋጀ አገልግሎት ለማግኘት ማስቻሉ ለዜጎች ትልቅ እፎይታን የፈጠረ ነው ብለዋል፡፡ አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ማደራጀት የተገልጋዩን ጊዜና ወጪ በመቀነስ የመንግስትን የአሰራር ቅልጥፍናና ከህዝብ ጋር ያለውን ግንኙነት የሚያጠናክር ትልቅ እርምጃ መሆኑን አስታውቀዋል። አሰራሩ በአፍሪካ ደረጃም በጥሩ አርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑን አክለዋል፡፡
ስፖርት
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ወደ አሜሪካ አመራ
Aug 3, 2026 197
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 26/2018 (ኢዜአ)፦ በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት፣ ዩጂን ከተማ በሚካሄደው 21ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ምሽቱን ወደ ውድድሩ ስፍራ አቅንቷል። ሻምፒዮናው በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ታሪካዊ መድረክ በሆነው በሄይዋርድ ፊልድ ስታዲየም የሚካሄድ ሲሆን፣ ከዓለም ዙሪያ የተውጣጡ ወጣት አትሌቶች ይሳተፋሉ። ሻምፒዮናው ከሐምሌ 29 እስከ ነሐሴ 3 ቀን 2018 ዓ.ም ይካሄዳል። በዘንድሮው ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ5000 ሜትር፣ 3000 ሜትር፣ 1500 ሜትር፣ 800 ሜትር (በሁለቱም ፆታዎች)፣ 3000 ሜትር መሰናክል (በሴቶች)፣ 400 ሜትር (በሴቶች) እንዲሁም በርምጃ ውድድር (በሁለቱም ፆታዎች) ትሳተፋለች። የኢትዮጵያ አትሌቶች በሻምፒዮናው ላይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅታቸውን አድርገዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን፣ የፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አመንሲሳ ከበደ (ዶ/ር) እና የፌዴሬሽኑ የስልጠና፣ ጥናትና ምርምር ዳይሬክተር አሰፋ በቀለ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ልዑክ ቡድኑን መሸኘታቸውን የፌዴሬሽኑ መረጃ ያመለክታል። በዘንድሮው ሻምፒዮና ላይ ከ147 ሀገራት የተውጣጡ ከ1800 በላይ አትሌቶች ይሳተፋሉ። እ.አ.አ በ2024 በፔሩ ሊማ በተካሄደው 20ኛው የዓለም ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 6 የወርቅ፣ 1 የብር እና 2 የነሐስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ በመሆን ማጠናቀቋ የሚታወስ ነው።
ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በስፖርት መሰረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ መስራት ይገባል
Jul 26, 2026 534
ሀዋሳ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተወዳዳሪና ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በስፖርት መሠረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ተጠቆመ። እ.አ.አ. በ1957 የተመሰረተው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስራች ከነበሩ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዕድገት ትልቅ አሻራ አሳርፋለች። የአፍሪካ እግር ኳስ በዓለም መድረክ የሚገባውን ቦታ እንዲይዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉት የካፍ ፕሬዝዳንት የነበሩት የይድነቃቸው ተሰማ ሀገር ኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ያሉባትም ናት። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዕድገት ያኖረችውን አሻራና የቀደመ ገናና ታሪክ በማንሳት የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቧም ይታወቃል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እና የክለቡ ተጫዋች ሁሴን ጠሃ፤ በኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በመሰረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ በእግር ኳሱ የላቀ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች እንዳሏት አንስተው ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ዕድሎችን ለመጠቀም ብዙ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የ2018ቱ የሲቢኢ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ቡድን አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እንደገለጸው፤ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ሌላው ዓለም የሚሰራውን መስራት መቻል አለብን ። የስፖርት መሰረተ ልማትና የታዳጊ ስልጠና ማዕከላትን ማጠናከር፤ የምልመላ ስርዓትና የውድድር ዕድሎችን ማስፋት ቀዳሚዎች መሆናቸውን አንስቷል። ዕምቅ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች የሚፈሩባቸው ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የሚደረጉ ስልጠናዎችና ውድድሮች ላይ ማተኮር እንደሚገባም አክሏል። አሰልጣኞችን ልምድ ባላቸው ሀገራት ማስተማር፣ ወጥ የሆነ የስልጠና ማኑዋል ማዘጋጀትና ሳይንሳዊ የሆነ የምልመላ ስርዓት መዘርጋት ሌላው ሊተኮርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስቷል። መንግስት የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቡ በስፖርቱ ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ መነሳሳትን እንደሚፈጥር የጠቀሰው አሰልጣኝ ያሬድ ዕድሉን መጠቀም ይገባናል ሲል ገልጿል። ለዋናው ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ህልም ይዞ እየሰራ ያለው የክለቡ ከ20 ዓመት በታች የግራ መስመር አጥቂ ሁሴን ጠሃ በበኩሉ፤ ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድን ለመፍጠር ታዳጊዎችና የስልጠና ሜዳዎች ሊጠናከሩ ይገባል ነው ያለው።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Aug 3, 2026 210
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው ሲል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡ አገልግሎቱ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በስኬት መጠናቀቁን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት መልዕክት ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ቀርቧል፡- ስንትባበር ምን ማድረግ እንደምንችል ደጋግመን ለዓለም ያሳየንበት የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ዛሬም በድል ተጠናቋል። ኢትዮጵያ የሚለው ስም በጋራ የመቻልና የጽኑ አቋም ተምሳሌት ነው። መንግሥት የሀገሪቱን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ የሚያስፈልጉ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎችን ሲያስቀምጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ሀገራዊ ፍላጎቱን በጋራ ተነሣሽነት እውን የማድረግ የዘመናት ልምምድ አለው። በተለይም መንግሥት ለአረንጓዴ ልማትና ሀገራዊ ከፍታ ለሚያቀርበው ጥሪ ሕዝቡ በላቀ ተሳትፎ ምላሽ የመስጠት ቁርጠኝነቱ ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ አብነት የሚሆን ነው። መንግሥት በኢትዮጵያ የተራቆቱ አካባቢዎች በልጆቿ ብርቱ እጆች እንዲታከሙ፣ እየተስፋፋ የመጣው ድርቅና በረሃማነት በዘላቂነት እንዲገታ እና በአስተማማኝ መሠረት ላይ የተገነባ አረንጓዴ ኢኮኖሚ እውን እንዲሆን ግልጽና ጽኑ አቋም በመያዝ ጥሪ ሲያቀርብ ቆይቷል። በዚህም በላቀ የሕዝብ ተሳትፎና በመንግሥት መሪነት ታላቁን የሕዳሴ ግድብ እውን ማድረግ ተችሏል፤ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ ላይ ምድራቸውን አረንጓዴ ማልበስ ባህላቸው አድረገውታል ፤ባለፉት ሰባት ዓመታት ብቻ በአረንጓዴ ዐሻራ ንቅናቄ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለው ኢትዮጵያ አረንጓዴ ሸማ ለብሳለች። ዘንድሮም በንቅናቄው 8ኛው ዓመት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን፣ በክረምቱ ደግሞ በአጠቃላይ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል መንግሥት ቁርጠኛ አቋሙን በይፋ አሳውቋል። ለመንግሥት ሀገራዊ ጥሪ ቀናኢ የሆኑ ውድ የኢትዮጵያ ልጆችም ይህንን ጥሪ በሙሉ ባለቤትነት ተቀብለው ለስኬቱ ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። በዚህም በዛሬው ዕለት 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በአንድ ጀምበር ከ805.3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል የተቀመጠውን ግብ ከዕቅድ በላይ አሳክተውታል። ይህ መንግሥትና ሕዘብ ሲተባበሩ ምን ማድረግ አንደሚችሉ የሚያሳይ፣ ማንም በዓለም ላይ ያለ ሀገር በቀላሉ ሊያሳካው የማይችል ድንቅ ስኬት ነው። ይህ ውጤት የኢትዮጵያ ሕዝብ ፍላጎትና የመንግሥት ስትራቴጂካዊ አቋም በአንድ አቅጣጫ ላይ እንደሚገኙ ማረጋገጫ ነው። በዛሬው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር 26 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ብርድ፣ ዝናብና ፀሐይ ሳይበግራቸው መሬት ሲያለምዱ ውለዋል፤ በዚሁ ጽኑ እንቅስቃሴም የዘንድሮው ክረምት ከገባ ጀምሮ 6 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞች ተተክለዋል። ኢትዮጵያ በልጆቿ ኮርታለች፤ መንግሥትም የሕዝቡን ከፍተኛ ቁርጠኝነትና ባለቤትነት ባየበት በዚህ ታሪካዊ ክስተት ከፍተኛ ኩራትና ክብር ተሰምቶታል። ይህም መንግሥት ይህንን ታላቅ ሕዝብ በበለጠ ኃላፊነትና ታማኝነት የማገልገል ጽኑ አቋሙን እንዲያጠናክር ተጨማሪ ብርታት ሆኖታል። ክቡራን ኢትዮያውያን፣ ክቡራን የኢትዮጵያ ወዳጆችና የዲፕሎማቲክ ማኅበረሰብ አካላት፤ ዛሬ ይኸንን አገራዊ ራዕይ በጋራ እውን ማድረግ እንድንችል ስላደረጋችሁት ከፍተኛ ርብርብ መንግሥት በኢትዮጵያ ስም ላቅ ያለ ምስጋና ያቀርባል። የክረምቱን አጠቃላይ የ8 ቢሊዮን ችግኞች ተከላ ዕቅድ ሙሉ በሙሉ ለማሳካት የተጀመረው አገራዊ ተሳትፎና ጽኑ አቋም ተጠናክሮ ይቀጠጥላል። ሐምሌ 27 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ የኢፌዴሪ መንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
የተከልነው ችግኝ የነገ ተስፋችንን የሚያለመልም ነው- በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች
Aug 3, 2026 132
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 27/2018(ኢዜአ)፡- የተከልነው ችግኝ የነገ ተስፋችንን የሚያለመልም ነው ሲሉ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተሳታፊ ወጣቶች ተናገሩ። በሀዋሳ ከተማ 15ኛ ዙር ብሔራዊ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሰልጠናን እየተከታተሉ ያሉ ወጣቶች በአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተሳትፈው አሻራቸውን አሳርፈዋል። ከበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች መካከል ወጣት መስከረም አበራ፤ሙሉጌታ ሀይሌ እና ወጣት ተመስገን አሼቦ እንዳሉት ዛሬ የተከልናቸው ችግኞች የነገ ተስፋዎቻችን በመሆናቸው ከተከላው ባሻገር የእንክብካቤው ስራ ላይ እንሳተፋለን። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እያስገኝ ካለው ጠቀሜታ ባሻገር ለቀጣዩ ትውልድ የለማች ሀገር ለማስተላለፍ ወሳኝ ምእራፍ መሆኑን ተናግረዋል።   የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የህዝቦች አንድነትና ትስስር እያጠናከረ መምጣቱን አመልክተው ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ተሳትፎም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ ከተጀመረ ወዲህ በግብርና፣ ኢንዱስትሪና በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች የህዝብን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል። ይህም ተጠናክሮ እንዲቀጥል በሚሰማሩበት አካባቢ የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡ ነው ያረጋገጡት። የስልጠውና አስተባባሪ ወይዘሮ አበባ ተገኝ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ መላው ህዝብ እየተከለ ያለው ችግኝ የቀጣዩን ትውልድ ተስፋን የሚያለመልም የጋራ ሀብት ነው ብለዋል። ባለፉት ጊዜያት በሀገሪቱ የተተከሉ ችግኞች የአፈር መሸርሸርን በማስቀረትና ለምነትን በማሳደግ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ያደረገ መሆኑን ነው የተናገሩት።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የድርቅና የጎርፍ አደጋዎችን በመከላከል ውጤት አስገኝቷል
Aug 3, 2026 203
ሀዋሳ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የድርቅና የጎርፍ አደጋዎችን በመከላከል ውጤት ማስገኘቱን የተለያዩ ክልሎች የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነሮች አመለከቱ ። የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር)ን ጨምሮ የክልል ኮሚሽነሮች፣ ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና የፌዴራል ፖሊስ አባላት በሀዋሳ ከተማ በተካሔደው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተሳትፈዋል።   የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተክለማርያም(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ በየአመቱ ችግኞችን በመትከል የአየር ንብረት ለውጥ በመዋጋት ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች። እየተካሔደ የሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ኢትዮጵያ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ችግር መፍትሔ በመሆን ልምድ የሚወሰድባት ሀገር እንድትሆን እያደረጋት ነው ብለዋል።   ችግኞችን መትከል በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ እንዲሳካ የሚያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል። የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክትል ኮሚሽነር አብዱሰላም ሙሴ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት የተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የጎርፍ ስጋት ከመቀነስ ባለፈ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አስችሏል ብለዋል። በዛሬው እለት የተካሔደው የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር መላውን ማህበረሰብ ያለ ልዩነት በማሰለፍ መጻኢ ልምላሜና የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እንደሚረዳ ነው የጠቀሱት።   የሶማሌ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ቢሮ የአደጋ ምላሽ ፈንድ ዳይሬክተር አቶ በሽር አረብ ፤ የችግኝ ተከላው በደን ሽፋን መቀነስ ሳቢያ የሚከሰቱ የአየር ንብረት ለውጥና ሌሎች ተያያዥ ችግሮችን ለመከላከል መፍትሔ መሆኑን ጠቁመዋል። ባለፉት ዓመታት በክልሉ የተከናወኑ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች የአፈር ለምነት ከመጨመር ባለፈ ጎርፍና ሌሎች ችግሮችን ለመቀነስ እንዳስቻለም ነው ያነሱት። በፌዴራል ፖሊስ 6ኛ ሬጂመንት 2ኛ ሻምበል አመራር ዋና ሳጂን አይጎታ አላ በበኩላቸው፤ የሀገርን ሰላምና ደህንነት ከመጠበቅ ባለፈ ሁለንተናዊ ልማቷ እንዲጠናከር በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ አሻራ ተሳትፎ መደረጉን ነው የጠቀሱት።
አረንጓዴ ዐሻራ ለመጪው ትውልድ ጽዱና አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን የማስረከብ ትውልድ ተሻጋሪ ተግባር ነው
Aug 3, 2026 142
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የአረንጓዴ ዐሻራ ለመጪው ትውልድ ሚዛኗን የጠበቀች፣ ለኑሮ ተስማሚ፣ ጽዱና አረንጓዴ የሆነች ኢትዮጵያን የማስረከብ ትውልድ ተሻጋሪ ተግባር መሆኑን የሰላም ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ገለጹ። የዘንድሮው "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ የሚካሄደው የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ዛሬ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ይገኛል።   የሰላም ሚኒስቴር አመራርና ሠራተኞች እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በአዲስ አዳማ ፈጣን መንገድ ዳርቻ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት፣ አረንጓዴ ዐሻራ ሚዛኗ የተጠበቀች፣ ፅዱና አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ የምናወርስበት የታሪካችን አንድ አካል ነው። መርሃ ግብሩም በአረንጓዴ ኢኮኖሚ የበለፀገች ኢትዮጵያን ለትውልድ የሚያስተላልፍ የልማት ውርስ መሆኑን አንስተዋል። የአረንጓዴ ዐሻራም የኢትዮጵያን የደን ሽፋን በማሳደግ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የግብርና ምርታማነት አቅም እየፈጠረ የሚገኝ ውጤታማ የልማት ትልም መሆኑን ገልጸዋል። ባለፉት ሰባት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተተከሉ ችግኞች ሁለንተናዊ ምርታማነትን በማሳደግ የአርሶና የአርብቶ አደሮችን ተጠቃሚነት በማሳደግ ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉና የሚተከሉ ችግኞችም የአካባቢን ገጽታ ከመቀየር ባሻገር ለምግብ ዋስትና የሚረዱ የፍራፍሬ እና ለአካባቢ ጥበቃ ጠቀሜታ ያላቸው እንደሆኑም ጠቁመዋል። በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የሚተከሉ ችግኞችን ተከታትሎ ማሳደግ፣ መንከባከብና የፅድቀት መጠናቸውን ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።   የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንገ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመቋቋም ከምትሰራቸው ስራዎች አረንጓዴ አሻራ ስራ ዋነኛው መሆኑን ገልፀው በዚህም አበረታች ውጤት እያስመዘገበች ትገኛለች ብለዋል። መርሃ ግብሩ የደን ሽፋን ከመጨመር በላይ የምግብ ሉአላዊነት ለማረጋገጥ በሚሰራው ስራ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ተናግረዋል።   የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለአፈር መሸርሸር፣ ለውሃ ሀብት ጥበቃና ለግብርና ምርታማነት ትርጉም ያለው ለውጥ እያመጣ እንደሚገኝ የገለፁት ደግሞ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ምክትል ስራ አስፈፃሚ መልእክተ ሳህሉ ናቸው።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 479
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 944
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ተጠናቀቀ
Jul 29, 2026 972
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ ሲካሄድ የቆየው 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን አዘጋጅነት የተካሄደው የሁለት ቀናት ስብሰባ ላይ የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ተሳትፈዋል። ሚኒስትሮቹ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ቁልፍ አጀንዳዎችና የአፍሪካን አህጉራዊ ትስስር ማፋጠን በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። በስብሰባው ሚኒስትሮቹ የአጀንዳ 2063 አፈፃፀም የሚከታተለውን ኮሚቴ ሪፖርት እንዲሁም የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት እና በአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ወቅት ያሉ ስምምነቶችና የአሰራር ማዕቀፎች ያሉበትን የትግበራ ደረጃ ገምግመዋል። በተጨማሪም የ2026ቱን የህብረቱን የዓመቱ መሪ ሀሳብ የእስካአሁን የአፈጻጸም ሂደት ላይም መክረዋል። ስብሰባው እ.አ.አ. በ2017 በህብረቱ አባል ሀገራትና መንግስታት መሪዎች የፀደቀውን ተቋማዊ ማሻሻያ መነሻ ያደረገ ነው። ከስብሰባው የተገኙ ውጤቶች አህጉራዊ ዘላቂ ልማትን፣ ትስስርና ብልፅግናን እውን ለማድረግ የተቀረፀውን የአፍሪካ ህብረት የረጅም ጊዜ መሪ እቅድ (አጀንዳ 2063) ስኬታማ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖራቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።
አፍሪካ ከውጭ የፋይናንስ ጥገኝነት በመላቀቅ የውስጥ የገቢ አቅሟን በአግባቡ መጠቀም ይጠበቅባታል 
Jul 28, 2026 509
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 21/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ዘላቂ ልማቷን ለማረጋገጥ ከውጭ የፋይናንስ ጥገኝነት ተላቃ የውስጥ የገቢ አቅሟን በአግባቡ መጠቀም እንዳለባት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ክሌቨር ጋቴቴ ገለጹ። 49ኛው የአፍሪካ ህብረት የሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ በህብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ይከናወናል። የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ ኤድዋርድ ቢዚማና፣ የአባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች እንግዶች በስብሰባው መክፈቻ ላይ ተገኝተዋል።   የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሀፊ ክሌቨር ጋቴቴ እንደገለጹት፤ በአሁኑ ወቅት የጂኦፖለቲካ ውጥረቶች፣ የግጭቶች መበራከት፣ የብድር ክፍያ ጫና እና የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት በአህጉሪቷ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እያሳደሩ ይገኛሉ። እነዚህን ፈተናዎች ለመወጣት የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን አባል ሀገራት የታክስ ስርዓታቸውን እንዲያዘምኑ ጠቁመው፤ ኮሚሽኑ የሀገር ውስጥ ካፒታል ገበያዎችን እንዲያጠናክሩ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል። አህጉሪቷ በየዓመቱ በሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር ሳቢያ በርካታ ገንዘብ እንደምታጣና የታክስ መሰብሰብ አቅሟም ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርቷ 16 በመቶ ብቻ መሆኑን አመልክተው፤ ይህ አሰራር በአስቸኳይ መለወጥ እንዳለበትም ተናግረዋል። በግብርና፣ በኃይል፣ በኢንዱስትሪ እና በአየር ንብረት መከላከል የተቀናጀ ፖሊሲና አሰራር መከተል እንደሚገባ ገልጸዋል። የሀገር ውስጥ ቁጠባና ኢንቨስትመንትን ለአህጉሪቱ ልማት ማዋል እና ሕገ-ወጥ የገንዘብ ማሸሽን መግታት እንደሚገባ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት የአፍሪካ እርስ በርስ ንግድ 17 በመቶ ብቻ ሲሆን፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ሙሉ በሙሉ ሲተገበር በ2045 የውስጥ ንግድን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል። የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም፣ የመረጃ ስርዓቶችን ለማዘመንና ዲጂታል መሠረተ-ልማቶችን ለማስፋፋት መዋዕለ-ነዋይ ማፍሰስ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ሐተታዎች
ያቀደችውን በተግባር የምታሳካ ታላቅ ሀገር
Aug 3, 2026 265
የአንድ ሀገር ታላቅነት ከሚለካባቸው ጉዳዮች አንዱ የተያዙ ሀገራዊ እቅዶችን በተግባር የመለወጥ አቅም ዋነኛው ነው። ኢትዮጵያም በዛሬው እለት በአንድ ጀምበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን ችግኞችን በመትከል ያስመዘገበችው አዲስ ታሪካዊ ስኬት፣ ሀገሪቱ ያቀደችውን በተግባር ማሳየት የምትችልና ትልልቅ ህልሞችን የመተርጎም አቅም ያላት ታላቅ ሀገር መሆኗን ለመላው ዓለም በተግባር ያስመሰከረ ነው። ይህ በአንድ ጀምበር የተከናወነ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር በርካታ ጥልቅ ትርጉሞችን የያዘ ነው፡ በአንድ ጀንበር ከ805 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል ግዙፍ የሎጂስቲክስ፣ የዝግጅትና የህዝብ ንቅናቄ ስራን ይጠይቃል።   ይህ ስኬት ሀገሪቱ ማንኛውንም ታላቅ አገራዊ እቅድ አቅዳ እስከ መጨረሻው የትግበራ ምዕራፍ ድረስ በብቃት የመምራትና የማስተባበር ተቋማዊና ህዝባዊ አቅም እንዳላት ማረጋገጫ ነው። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ዕድሜ፣ ጾታ፣ ወይም ልዩነት ሳይለያያቸው በአንድ ቀን ለተመሳሳይ አገራዊ ዓላማ መቆማቸው፣ ኢትዮጵያውያን ለጋራ እድገታቸውና ለሀገራቸው የወደፊት ተስፋ ያላቸውን ጽኑ ፍላጎትና አንድነት አሳይቷል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት ዋና ስጋት በሆነበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በንግግር ብቻ ሳይሆን በተግባራዊ እርምጃ ለችግሩ መፍትሔ በመስጠት ረገድ የዓለም አቀፍ መሪነቷን ያስመሰከረችበት አጋጣሚም ጭምር ነው። ይህ ስኬት ሀገሪቱ የገጠሟትን ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ፈተናዎች ተሻግራ፣ አቅሟን አስተባብራ ታላላቅ ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደምትችል ለዜጎቿም ሆነ ለውጭው ዓለም የሰጠችው ትልቅ የራስ መተማመንና የተስፋ መልእክት ነው። በአጠቃላይ፣ በአንድ ጀምበር የተከናወነው ይህ ታሪካዊ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር ኢትዮጵያ አርቆ የማሰብና የማቀድ ችሎታዋን ብቻ ሳይሆን፣ ያቀደችውንም በአንድነትና በቁርጠኝነት ወደ መሬት በማውረድ በተግባር የምታሳይ ታላቅ ሀገር መሆኗን በግልጽ ያረጋገጠ አኩሪ ተግባር ነው።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ ትንሳኤ ብስራት!!
Aug 2, 2026 286
በሐዊ አጫሉ መግቢያ፡- የኢንዱስትሪ ዘርፍ የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬን ከሚወስኑ ዋነኛ የብልፅግና ማረጋገጫ ምሰሶዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ዘርፉ ምርትን ከማሳደግ ባሻገር የሥራ ዕድል ፈጠራን፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝትን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን እና የሀገር ውስጥ ምርታማነትን የሚያፋጥን የልማት ሞተር ነው። ኢትዮጵያም ከግብርና መሠረት የተነሳ ኢኮኖሚዋን ወደ ዘመናዊ፣ ተወዳዳሪና ሁሉን አቀፍ የምርት ሥርዓት ለማሸጋገር ከምታደርገው ጥረት መካከል ኢንዱስትሪውን በቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶነት በማካተት እየሰራችበት ይገኛል። በአሁኑ ወቅት ግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ቱሪዝም፣ ማዕድን እና ቴክኖሎጂ አምስት ዐበይት የብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት ምሰሶዎች ተመሥርቶ እየተመራ ይገኛል። ከእነዚህ ውስጥ ኢንዱስትሪው የምርት አቅምን በማሳደግ የግብርና ምርቶችን ወደ ተጨማሪ እሴት በመቀየርና ለዜጎች ሰፊ የሥራ ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ ፋይዳ እያስገኘ ነው። ይህንን ሽግግር እውን ለማድረግ የምርት አቅምን ማሳደግ፣ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን እና የሰው ኃይል ልማት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል። የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ የቀድሞ ገጽታ፤ ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ለውጥ መንገድ!! በቀደሙት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተለያዩ ዕድሎችንና ፈተናዎችን በማስተናገድ በርካታ ውጣ ውረዶችን አሳልፏል። ሀገሪቱን ከግብርና መር ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለማሸጋገር በተደረጉ ጥረቶች የተለያዩ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ተገንብተዋል። እነዚህ ፓርኮችም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ በቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በግብርና ምርት ማቀነባበር ዘርፎች ላይ ትኩረት በማድረግ የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ የተሞከረበት ወሳኝ ምዕራፍ እንደነበር ይታወሳል። ይሁን እንጂ ይህ ጉዞ በበቂ መሠረተ ልማት፣ በተሟላ የጥሬ ዕቃ አቅርቦትና በተቀናጀ የምርት ሰንሰለት እጥረት ምክንያት በበርካታ ፈተናዎች ለመውደቅ ተገዶ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። የውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ የጥሬ ዕቃ አቅርቦት ውስንነት፣ ዕውቅትና ክህሎትን የተሰላበሰ የሰው ኃይል አለመኖር፣ የፋይናንስ እጥረት፣ ውስብስብና አስቸጋሪ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓትና የገበያ ትስስር እጥረት የዘርፉን እድገት ገድበው የነበሩ ሁነኛ ተግዳሮቶች ናቸው። ከመዋቅራዊ ተግዳሮት ወደ ምርታማነት፤ የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ የለውጥ ፍኖት!! ባለፉት ዓመታት በኢንዱስትሪ ዘርፉ የተስተዋሉ መዋቅራዊ ችግሮችን ለመፍታትና የሀገሪቱን የማምረት አቅም ለማሳደግ አዳዲስ የለውጥ አቅጣጫዎች ተነድፈው ተተግበረዋል። በተለይም ኢንዱስትሪን ከተለመደው የምርት ሥርዓት በማሻገር ወደ ተወዳዳሪ ዘመናዊና ውጤታማ የማምረቻ ማዕከል ለመቀየር የተለያዩ የፖሊሲማሻሻያዎች ተደርገዋል። የግል ባለሀብቱን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን ማስፋት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ማፋጠን፣ የሰው ኃይል አቅምን ማሳደግና የግብርና-ኢንዱስትሪ ትስስርን ማጠናከር በዘርፉ የተወሰዱ ሁነኛ የለውጥ እርምጃዎች ናቸው። በዚህም የኢትዮጵያን አምራች ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት በማጎልበት ከሀገር ውስጥ ገበያ እስከ ዓለም አቀፍ የንግድ ሥርዓት ድረስ ውጤት እያስገኘ ነው። የግል ባለሃብቱ ሚና፤ የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሞተር!! የኢንዱስትሪ ልማት በመንግሥት ጥረት ብቻ የሚሳካ አይደለም። የግል ዘርፉ በካፒታል፣ በፈጠራ፣ በቴክኖሎጂና በአስተዳደር ብቃት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ለዘርፉ ዕድገት የማይተካ ሚና አለው። በዚህ ረገድ የግል ባለሃብቱ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ዋና አጋር እንዲሆን የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተሻሽለው እየተሰራባቸው ይገኛል። ይህም የግሉን ዘርፍ የኢንቨስትመንት በማሻሻል፣ የንግድ ሥራ ሂደቶችን በማቀላጠፍ፣ የፋይናንስ ተደራሽነትን ማስፋትና የምርት አቅምን በማሳደግ የግሉን ዘርፉ የምርታማነት አቅም እያጎለበተ ነው። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ፤ የአምራች ኢንዱስትሪ የትንሳኤ ብስራት!! በሀገራችን የኢኮኖሚ አቅጣጫ ውስጥ የምርትና አገልግሎት አሰጣጥን በማቀናጀት አዲስ ምዕራፍ ከከፈቱ ዐበይት ሀገራዊ መርሃ-ግብሮች መካከል በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አነሳሽነት የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ተጠቃሽ ነው። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ዘርፍ የማምረት ባህልን በማሳደግ ዘርፉ ወደ አዲስ የልማት ምዕራፍ የሚሸጋገርበት ሁነኛ ዕድልን ፈጥሯል። ንቅናቄው የማምረት አቅምን በማሳደግ ሥራ ያቆሙ ፋብሪካዎችን ወደ ሥራ መመለስ፣ የአምራቾችን ችግሮች በፍጥነት መፍታትና አዳዲስ ባለሃብቶችን ወደ ዘርፉ በመሳብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል፤ እያበረከተም ይገኛል። በዚህ ሂደት በፋይናንስ፣ በግብዓት አቅርቦት፣ በውጭ ምንዛሬና በተቋማዊ ቅንጅት ረገድ የተወሰዱ እርምጃዎች የአምራች ዘርፉን የምርታማነት አቅም በማጎልበት ጉልህ ሚና ተጫውቷል። የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄም የኢንዱስትሪ ዘርፍ እንዲያንሰራራ በማድረግ የምርታማነት አብዮት እንዲቀጣጠል እያደረገ ይገኛል። የንቅናቄው ዋና ዓላማ በአምራች ዘርፉ የነበሩ ማነቆዎችን በመፍታት የኢትዮጵያን የማምረት አቅም ማሳደግ ነው። ይህም ሥራ ያቆሙ ወይም በአቅማቸው ልክ ያልሠሩ ፋብሪካዎችን ወደ ሙሉ ምርት በመመለስ የአምራቾችን ችግር በተቀናጀ መንገድ መፍታት፣ የፋይናንስና የግብዓት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ትኩረት አድርጓል። በዚህ ሂደት የማምረቻ ዘርፉ በአዲስ የሥራ ባህል፣ በተቋማዊ ቅንጅትና በፈጣን ውሳኔ አሰጣጥ እየተመራ መሆኑ የለውጡን ፍጥነት እያሳደገው ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ የፋይናንስ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ተደራሽነትን ማሻሻልና የምርት ጥራትን ማረጋገጥ የኢንዱስትሪው ትንሳኤ ዋና ማሳያዎች ናቸው። ለአብነትም፡- የፋይናንስ አቅምና የብድር አቅርቦት ማሻሻል፡- የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ ዋነኛ እንቅፋት የሆነውን የፋይናንስ እጥረት ለመቅረፍ በተደረገው ርብርብ፣ የብድር አቅም ቀደም ሲል ከነበረበት 40 ቢሊዮን ብር ወደ 115 ቢሊዮን ብር ከፍ እንዲል በማድረግ ለአምራቾች ሰፊ የካፒታል አቅም መፍጠር ተችሏል። የውጭ ምንዛሬ ግኝትና የግብዓት ድጋፍ ማደግ፡- ንቅናቄው ከመጀመሩ በፊት ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ይቀርብ የነበረው የውጭ ምንዛሬ መጠን አሁን ላይ ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ እንዲደርስ ተደርጓል። ይህም ፋብሪካዎች ከአቅማቸው በታች እንዲሠሩ ያስገድድ የነበረውን የምርት ውስንነት በከፍተኛ ደረጃ አቃሎታል። የምርት ዕድገት፣ ተኪ ምርትና የኤክስፖርት አፈጻጸም፡- ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካት ረገድ ከነበረበት 348 ሚሊዮን ዶላር ወደ 5.9 ቢሊዮን ዶላር በማደግ ግዙፍ ሀገራዊ ድል ተመዝግቧል። እንዲሁም በኤክስፖርት ገበያ የሚገኘው ገቢ ከ385 ሚሊዮን ዶላር ወደ 607 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ማለት ችሏል። ተቋማዊ ቅንጅትና አዲስ የሥራ ባህል ማዳበር፡- በክልሎችና በፌዴራል ተቋማት መካከል የነበረውን የቢሮክራሲ ጫና በመቀነስ ፈጣን ውሳኔዎች እንዲሰጡ መደረጉ፤ እንዲሁም ህብረተሰቡ የሀገር ውስጥ ምርትን በኩራት የመጠቀም እና የሀገር ፍቅር ስሜትን ከአምራችነት ጋር የማስተሳሰር ትልቅ ማህበራዊ ንቃተ-ህሊና መገንባት ተችሏል። የወደፊት ተስፋ፤ ኢትዮጵያ አዲሲቷ አፍሪካዊት የኢንዱስትሪ ምርታማነት ተምሳሌት ሀገር!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ በቀጣይ ዓመታት ከተለመደው ማምረት ወደ ዘመናዊ እና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የምርት ሥርዓት እንዲሸጋገር ይጠበቃል። የዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ አውቶሜሽን፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና የፈጠራ ሥርዓቶችን ወደ ማምረቻ ዘርፉ ማስገባት የወደፊቱ ትኩረት ይሆናል። በተመሳሳይም ጠንካራ የግብርናና ኢንዱስትሪ ትስስር፣ አረንጓዴ ኢንዱስትሪ ልማት፣ ዘላቂ የሥራ ዕድል ፈጠራ እና የአህጉራዊ ገበያ ተደራሽነት የሀገሪቱ ቀጣይ የኢንዱስትሪ ግቦች ናቸው። የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) የሚፈጥረውን ሰፊ የገበያ ዕድል በመጠቀም ኢትዮጵያ የምሥራቅ አፍሪካ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችል መሠረት እየጣለች ትገኛለች። ማጠቃለያ፡- ማምረት፤ የኢትዮጵያ የብልፅግና ቁልፍ መሳሪያ!! የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ጉዞ ከፈተና ወደ ዕድል፣ ከጥገኝነት ወደ ራስን መቻል፣ ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ ተጨማሪ እሴት ያለው ምርት አቅራቢነት በማምራት እመርታዊ ውጤቶችን እያስገኘ ነው። የኢንዱስትሪውን አቅም ማሳደግ ማለት ፋብሪካዎችን ብቻ ማስፋፋት ሳይሆን የሀገርን ምርታማነት፣ የወጣቶችን ዕድል፣ የኢኮኖሚ ነፃነትንና የልማት ዘላቂነትን ማረጋገጥ ነው። በመሆኑም የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትራንስፎርሜሽን የዛሬ ልማት ብቻ ሳይሆን የነገውን ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚገነባ ሀገራዊ ራዕይ ነው።  
የክልሎች ቅኝት - በወፍ በረር
Aug 2, 2026 175
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 26/2018 (ኢዜአ) የክልሎች ቅኝት - በወፍ በረር በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የግብርናውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ አበርክተዋል። በክልሉ ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5 ዓመት 3ኛ የሥራ ዘመን 5ኛ መደበኛ ጉባኤው ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፤ የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም በክልሉ የግብርናውን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ ድርሻ ማበርከቱን አንስተዋል። የሜካናይዜሽን እርሻም ተግባራዊ በመደረጉ ከ55 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱንም ጠቅሰዋል። ከማዕድን ዘርፍም በበጀት ዓመቱ ከ 8 ሺህ 900 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ ማቅረብ መቻሉን ገልጸዋል። ኦሮሚያ ክልል በኦሮሚያ ክልል የመንግስት የአገልግሎት አሰጣጥን ግልጽ እና ተጠያቂነት ያለበት በማድረግ የሙስና እና የብልሹ አሰራር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ሪፎርም እየተተገበረ ይገኛል። ለዚህም የመንግስት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ይፋ የማድረጊያ መርሃ ግብር ''የአገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ለሁለንተናዊ ብልጽግና'' በሚል መሪ ሀሳብ በቢሾፍቱ ከተማ ተካሂዷል።   የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንት አወሉ አብዲ፤ የመንግስትን አገልግሎት አሰጣጥን የተሳለጠ ለማድረግ የሚያስችል እስከ ቀበሌ የደረሰ አሰራር መዘርጋቱን በወቅቱ አንስተዋል። አልግሎቶችን በዲጂታል ስርዓት በመደገፍ የህዝቡን እንግልት፣ ጊዜና ወጪ በመቆጠብ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ ነው ብለዋል። ይህም በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ሲዳማ ክልል የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ፤ በክልሉ የ2019 የትምህርት ዘመን የትምህርት ንቅናቄ መድረክ ላይ በመገኘት ባደረጉት ንግግር በክልሉ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ሥራ ምቹ ማድረግና በግብአት ለማሟላት በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን አንስተዋል።   ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ስራ ምቹ በማድረግ በትምህርት ጥራት ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲታይ መደረጉንም አስረድተዋል። ጋምቤላ ክልል ‎የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ''ተስፋን እንትከል'' በሚል መሪ ሀሳብ የ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በማጃንግ ዞን በመንገሺ ወረዳ ያስጀመሩትም በዚሁ ሳምንት ነው። በክልሉ የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትን ለማረጋገጥ የአረንጓዴ አሻራ ልማት ስራዎች በህዝብ ተሳትፎ እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል ።   ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት የአረንጓዴ አሻራ ልማት የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲያገግሙ ከማድረጋቸው ባለፈ የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ማስቻሉንም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልፀዋል። ‎አማራ ክልል በአማራ ክልል የግብርናን ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለኢንዱስትሪዎች ግብአት ማምረት ተችሏል። የዚሁ አካል የሆነው በክልሉ በሰሜን ሸዋ ዞን በሞረትና ጅሩ ወረዳ 837 አርሶ አደሮች በማህበር በመደረጃት “የጅሩ-አግሮ ቢዝነስ“ ኩባንያን መስርተዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የአማራ ክልል ገጠር ክላስተር አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት ኩባንያው የአርሶ አደሮችን ምርት በማቀነባበር ለገበያ የሚያቀርብ ነው። የአግሮ-ቢዝነስ ኩባንያውም ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ የሚደረገውን የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ይህም አርሶ አደሩ ከጥሬ ግብአት አቅራቢነት ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስተርነት በማደግ ላይ መሆኑን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል። ደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር)፤ በኮንታ ዞን አመያ ከተማ አስተዳዳር ዙሪያ ጨታ ቀበሌ የተገነባውን የባቾ ገጠር ሞዴል መንደር መርቀው ለነዋሪዎች አስረክበዋል። በወቅቱም የሞዴል የገጠር መንደሩ መገንባት የሌማት ትሩፋት ስራዎችን ውጤታማ በማድረግ የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ አቅም ለማሳደግ ብሎም ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።   በሌላ በኩል በክልሉ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት ገንብቶ በማጠናቀቅ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራም ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል። በተለይም የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን በመገንባት የወረዳና ቀበሌዎች ማህበራዊ ትስስር እንዲጠናከርና የግብይት ሰንሰለትም እንዲቀላጠፍ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። ለአብነትም በክልሉ ኮንታ ዞን በአመያ ዙሪያ ወረዳ በኡማ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናት ችግር ያቃለለና ለመሰረተ ልማት ጥያቄያቸው ምላሽ የሰጠ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ማስተዋወቂያ መድረክ ላይ በመገኘት ንግግር አድርገዋል።   በመልእክታቸውም በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተገኘ ስለመሆኑ ተናግረዋል። በ2019 በጀት ዓመትም በክልሉ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ 48 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ግብር ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ለዚህም በህግና የአሠራር ስርአት በመታገዝ የገቢ አቅምን በማስፋት የክልሉን ዕድገት ዘላቂነት በማረጋገጥ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ገቢዎች ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 ዕቅድ ላይ ያተኮረ የምክክር ጉባኤ በአርባ ምንጭ ከተማ አካሂዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ፤ በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በአግባቡ በመሰብሰብ የህዝቡን የልማት ፍላጎት ለማሟላት እየተደረገ ባለው ጥረት ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል ። በ2019 በጀት አመትም የክልሉን የገቢ አቅም ለይቶ በተደራጀ ህዝባዊ ንቅናቄ የግብር እቅድን ለማሳካት እንደሚሰራ ተናግረዋል። በዚህም በበጀት አመቱ 48 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። ገቢውን ለማሳካትም የህግና የአሠራር ስርአት በመዘርጋት የክልሉ ዕድገት በዘላቂነት በትኩረት እንደሚሠራ አስታውቀዋል። አፋር ክልል በአፋር ክልል የእንሰሳትና ዓሳ ሀብትን በማልማት ለወጣቶች የስራ እድልን ለማስፋት የተሰሩ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን የክልሉ የእንሰሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኀላፊ አቶ ኢብራሂም መሐመድ ገልጸዋል። ለዚህም ስምንት የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ሐይቆች ላይ ወጣቶችን አደራጅቶ ወደ አሳ ልማት ስራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል። ለአብነትም በአፋምቦ ሐይቅ ላይ 200 ወጣቶች በዓሳ ሀብት ልማት ላይ በመሰማራት ተጠቃሚ የሚሆኑበት አሰራር መዘርጋቱን አስረድተዋል። በዓሳ ሀብት ልማቱ ተደራጅተው ወደ ስራ የገቡ ወጣቶች እንዳሉት የአሳ ሀብትን አልምተው ተጠቃሚ ለመሆን በማህበር ተደራጅተው በመስራት ላይ ናቸው። ስራውንም ለማሳካት ክልሉ እያደረገ ያለው የሙያ ስልጠናና ድጋፍ የማይተካ ድርሻ አለው ብለዋል። ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል "ሁሉ አቀፍ እመርታ ፣ ለሁለንተናዊ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ የ2018 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ስራ አፈፃፀምና የ2019 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የከፍተኛ አመራሮች የውይይት መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል።   ርዕስ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በወቅቱ እንዳሉት በክልሉ በሰላም፣ በልማትና መልካም አስተዳደር የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ስራዎች ተከናውነዋል። የህዝቦችን አብሮነት በማጠናከር ክልሉን የህብረ ብሄራዊነት ተምሳሌት ለማድረግ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገቡን አመልክተዋል። በበጀት ዓመቱ የተገኙ ስኬቶችን ማጠናከርና የተስተዋሉ ጉድለቶችን በማረም ቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ የመድረኩ ዋና ዓላማ ስለመሆኑም ገልጸዋል። ሐረሪ ክልል የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ሃላፊ ሮዛ ኡመር እንደገለፀት፤ በክልሉ ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት የመውጣት ስራ በገጠር ወረዳዎች የመስኖ ልማት በስፋት ተከናውነዋል። ተግባሩን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ የ2018 የግብርና ልማት እቅድ አፈጻጸምና የ2019 የግብርና ልማት መሪ እቅድ ላይ የውይይት መድረክ ተካሂዷል።   በሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር የእንስሳት ተዋጽኦና የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት ትልቅ እመርታ የተገኘበት ነው ብለዋል። የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብርም ከተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ባሻገር የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ ተወጥቷል ብለዋል። ሶማሌ ክልል የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 11ኛ መደበኛ ጉባዔውን ሲያካሂድ ርእሰ መስተዳድሩ ሙስጠፌ ሙሀመድ፤ የተጠናቀቀውን በጀት ዓመት ሪፖርት አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም በክልሉ የሰላምና የልማት እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ስራዎችና የመጡ ውጤቶችን አብራርተዋል።   የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው፤ የፍትህ አካላትን አቅም ለመገንባት በተደረገ ጥረት የፍትህ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን መቻሉንም አንስተዋል። በክልሉ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በድህነት ቅንሳ፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ የሚመጡ አደጋዎች ቅነሳም ከፍተኛ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል።      
ከሀገር አቀፍ ንቅናቄ እስከ ዓለም አቀፍ እውቅና፦የአረንጓዴ አሻራ ውጤታማ አበርክቶ
Jul 30, 2026 503
በታዋቂ ዓለም አቀፍ የሳይንስ መጽሔቶች ላይ የታተሙ ተከታታይ ጥናቶች የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በደን መልሶ ማልማት፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተዕፅኖን በመከላከል ፣ የካርበን ክምችት በማሳደግ እና በማህበረሰብ ተሳትፎ ረገድ ተጨባጭ ውጤቶችን እያመጣ መሆኑን አረጋገጡ። የጥናቱ ግኝቶች ከስምንት ዓመታት በፊት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመረው የአረጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር፣ በአፍሪካ ግዙፍ እና እጅግ ውጤታማ ወደሆነ የመሬት ገጽታ መልሶ ማልማት ፕሮግራም ማደጉን የሚያሳይ ጠንካራ ሳይንሳዊ ማስረጃ አቅርበዋል። ኔቸር ፖርትፎሊዮ (Nature Portfolio)፣ ኤልሴቪየር (Elsevier) እና ስፕሪንገር (Springer)ን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው አሳታሚዎች እ.ኤ.አ. በ2026 የወጡ አምስት ጥናቶች፤ የሳተላይት ምስሎችን፣ የመስክ የዳሰሳ ጥናቶችን፣ የጂኦስፓሻል ቴክኖሎጂዎችን እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም የመርሐ-ግብሩን አካባቢያዊ ፋይዳ ገምግመዋል። ከፍተኛ የችግኝ ጽድቀት ምጣኔ - የውጤታማ መልሶ ማልማት ማሳያ በኤልሴቪየር 'ትሪስ፣ ፎረስስ ኤንድ ፒፕል' (Trees, Forests and People) መጽሔት ላይ የታተመ ጥናት (አሰፋ እና ሌሎች፣ 2026) እንዳመለከተው፣ በደቡብ ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የተተከሉ የዛፍ ችግኞች 80 በመቶ የሚገመት የጽድቀት ምጣኔ አስመዝግበዋል፤ ይህም ከሌሎች በርካታ ሰፊ የደን ልማት ፕሮግራሞች ልቆ የተገኘ ነው። ተመራማሪዎቹ ለዚህ ስኬት በዋነኛነት የጠቀሷቸው የተሻሻሉ የመልሶ ማልማት ልምዶችን ሲሆን፣ ከነዚህም መካከል በዋናው የክረምት ወቅት መትከል፣ ጥንቃቄ የተሞላበት የቦታ ምርጫ፣ እንዲሁም በቴክኒክ ስልጠና የታገዘ ጠንካራ ማህበረሰብ አቀፍ እንክብካቤ ይገኙበታል። የጥናቱ መሪ ዶ/ር ታደሰ አሰፋ እንደገለጹት፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ከሳይንሳዊ የደን አያያዝ ጋር ማቀናጀት አዳዲስ ተከላ የተካሄደባቸው አካባቢዎች ጊዜያዊ የችግኝ መትከያ ቦታዎች ብቻ ሆነው ከመቅረት ይልቅ ዘላቂ ወደሆነ ደንነት እንዲያድጉ አስችሏል።   የማህበረሰብ ተሳትፎ ለስኬቱ ሞተር ነው በስፕሪንገር 'ዲስከቨር ኢንቫይሮመንት' (Discover Environment) ላይ የታተመ ሌላ ጥናት ደግሞ ሰፊው የማህበረሰብ ተሳትፎ የመርሐ-ግብሩ ታላቅ ጥንካሬ መሆኑን አመልክቷል። የጥናቱ መሪ ዶ/ር አብዱረዛቅ ሀጂ እንዳስገነዘቡት፣ እያደገ የመጣው የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ እና በጎ ፈቃድ ላይ የተመሰረተ የህዝብ ተነሳሽነት፣ አባወራዎች ችግኝ መትከልን የአካባቢን የመቋቋም አቅም ለመገንባት፣ ለዘላቂ ግብርና እና ለወደፊት የኑሮ መሰረት እንደተደረገ ኢንቨስትመንት እንዲመለከቱት አድርጓል። የህዝብ ተሳትፎ የመርሐ-ግብሩ የረጅም ጊዜ ስኬት የማዕዘን ድንጋይ መሆኑን ጥናቱ በማጠቃለያው አስቀምጧል። የደን ሽፋን ማደግ የአካባቢን አየር ንብረት ያሻሽላል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ ቡኖ በደሌ ዞን የተካሄደ ጥናት በስድስት ዓመታት ውስጥ የደን ሽፋን በከፍተኛ ሁኔታ ማደጉን፣ ማለትምከ27.64 በመቶ ወደ 38.24 በመቶ ከፍ ማለቱን አስመዝግቧል። ጥናቱ የመሬት ገጽ የሙቀት መጠን እስከ 1.16 ዲግሪ ሴልሺየስ መቀነሱን ያረጋገጠ ሲሆን፣ ይህም የደን ሽፋን መስፋፋትየአካባቢውን አየር ንብረት እያሻሻለ እና የአየር ንብረት ለውጥን የመቋቋም አቅምን እያጠናከረ መሆኑንያሳያል። እነዚህ ለውጦች የስነ-ምህዳር አገልግሎቶችን እንደሚያሳድጉ እና የግብርና ምርታማነትን እንደሚደግፉ ይጠበቃል ሲሉ ተመራማሪዎቹተናግረዋል። ጥናቶች ከፍተኛ የካርበን ክምችት አቅም መኖሩን አጉልተዋልበኔቸር ፖርትፎሊዮ (Nature Portfolio) ሥር በ'ሳይንቲፊክ ሪፖርትስ' መጽሔት ላይየወጣ ሌላ ጥናት፣ የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የዛፍ ዝርያዎች እና የግብርና-ደን ሥርዓቶች ከፍተኛ መጠንያለው የካርበን ዳይኦክሳይድ ክምችት የመያዝ አቅም እንዳላቸው አረጋግጧል። አንዳንድ መልመው ያገገሙ መሬቶች በሄክታር ወደ 500 ሜጋግራም የሚጠጋ የካርበን ዳይኦክሳይድ መጠን የያዙ መሆናቸው የተረጋገጠሲሆን፣ ይህም መርሐ-ግብሩ የአየር ንብረት ለውጥን በማቃለል ረገድ ያለውን ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያሳያል። የደን መልሶ ማልማት ስራውን ማስፋፋት የኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት እርምጃ ተሳትፎ የበለጠ እንደሚያጠናክርናበማደግ ላይ ባለው የዓለም አቀፍ የካርበን ገበያ ላይ ዕድሎችን እንደሚፈጥር ተመራማሪዎቹ ገልጸዋል።   አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የደን ዕድገቱ እንደሚቀጥል ተንብዮአል ማሽን ለርኒንግ፣ የሳተላይት ምስሎች እና የጂኦስፓሻል ትንታኔዎችን በመጠቀም በስፕሪንገር 'ኢንቫይሮመንታል ሞኒተሪንግ ኤንድአሴስመንት' (Environmental Monitoring and Assessment) መጽሔት ላይ የታተመ ሌላ ጥናት እንዳመላከተው፣አሁን ያለው የመልሶ ማልማት ጥረት ከተቀጠለ የኢትዮጵያ የደን ሽፋን ቢያንስ እስከ 2035 ድረስ መስፋፋቱን እንደሚቀጥልተንብዮአል። በመሬት ገጽታ መልሶ ማልማት ላይ የሚደረገው ተከታታይ ኢንቨስትመንት የደን ሽፋንን የበለጠ እንደሚያሳድግ፣ የካርበን ክምችትንእንደሚያጠናክር እንዲሁም የኢትዮጵያን የአየር ንብረት እና የዘላቂ ልማት ግቦችን እንደሚደግፍ ጥናቱ ያሳያል።   ዓለም አቀፍ ሳይንሳዊ እውቅና በአጠቃላይ ሲታይ፣ አምስቱ ገለልተኛ ጥናቶች የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር ሁለንተናዊ ሳይንሳዊ ግምገማ በማቅረብ፤በደን መልሶ ማልማት፣ በካርበን ክምችት፣ በአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም እና በህዝብ ተሳትፎ ረገድ የሚለኩና ተጨባጭ ውጤቶችንማምጣቱን ደምድመዋል። እነዚህ ግኝቶች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የሰፊ ሥነ-ምህዳር መልሶ ማልማት ቀዳሚ ሞዴል በማድረግ ያስቀመጡትሲሆን፤ ዘላቂ የፖለቲካ ቁርጠኝነት፣ ሳይንሳዊ ዕቅድ እና አገር አቀፍ የህዝብ ንቅናቄ እንዴት ተጨባጭ የአካባቢ ጥበቃ ውጤቶችንማምጣት እንደሚችሉና፣ ለዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥ እና የመሬት መራቆትን ለመከላከል ለሚደረጉ ጥረቶች ከፍተኛ አስተዋጽዖእንደሚያበረክቱ በጉልህ አሳይተዋል።
ትንታኔዎች
በተቃርኖ የተሞላው ሕገ ወጡ ሕወሓት የጥፋት ጉዞ
Jul 30, 2026 433
የሕገ ወጡ የሕወሓት ቡድን የፖለቲካ ጉዞ በበርካታ መሠረታዊ ተቃርኖዎችና የፖለቲካ ስህተቶች የተሞላ ነው። ቡድኑ በትግል ጊዜም ይሁን ሀገርን በመምራት ባደረገው የፖለቲካ ተሳትፎ ታሪክ ይቅር የማይላቸው ስህተቶችን ፈጽሟል። ከሁሉም በላይ የትግራይን ሕዝብ ለዘመን ተሻጋሪ መከራና ስቃይ ዳርጓል። የወጣቶችን ተስፋ እና ሕልም አጨልሟል። የሕገ ወጡ ቡድን በተቃርኖ የተሞላ ጉዞ በጨረፍታ እንመልከት። ተቃርኖ አንድ፦ የሀገር ገዥነት እና የነጻ አውጪነት መንፈስ ሕገ ወጡ ሕወሓት ከሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ግንባር ፈጥሮ ሀገር በመራበት ዘመንም ጉዞው በተቃርኖ የተሞላ ነበር። በዚህ የሥልጣን ዘመኑ ኢትዮጵያ ውስጥ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን፤ ከኅብረት ይልቅ መነጠልን ሥር እንዲሰድ አድርጓል። በስም ደረጃ ሕብረ ብሔራዊ የፌዴራል ሥርዓት እንደሚያራምድ ቢናገርም ለኢትዮጵያውያን የተለያየ የዳቦ ስም በመስጠት እርስ በእርስ እንዲጠራጠሩ በማድረግ የጥላቻ ፖለቲካን አንግሷል። የሕግ የበላይነት እና የሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት በአንዱ ቡድን ላይ የማይተገበር ሌላው ላይ ግን ተግባራዊ እንዲሆን አድርጓል። ከቡድኑ ጋር የጥቅም ትስስር ያላቸው ቡድኖች ለሕግ የማይገዙ፣ ከኮንትሮባንድ እስከ ዓለም አቀፍ ወንጀሎች ውስጥ የሚሳተፉ ነበሩ። ሌላው ጽንፈኛ፣ አክራሪ እና ተስፋፊ ተደርጎ በሽብር እየተወነጀለ በየማረሚያ ቤቱ እንዲንገላታ ተደርጓል። በጥቅሉ ሕገ-መንግሥት እና የፌዴራል ሥርዓትን ለራሱ በሚያመች መልኩ ሲጠቀምበት ቆይቷል። ከዚህም ባለፈ ሕገ ወጡ ቡድን ሀገርን እየመራ እንደ አንድ የክልል ነጻ አውጪ ድርጅት በብሔሮች መካከል ጥርጣሬና ልዩነት እንዲሰፋ የሚያደርጉ የከፋፍለህ ግዛ ፖለቲካዎችንም አንግሷል። ‘እኛ እና እነሱ’ የሚል ፖለቲካን ከማካሄድ ባለፈ ‘ልዩ ኃይል’ በሚል ወታደራዊ አደረጃጀት ፈጥሮ መንግሥት መስሎ ሀገርን የማፍረስ እና የማዳከም ተግባር ውስጥ ተሳትፏል። ተቃርኖ ሁለት፦ ሰሜን እዝን ባጠቃበት ጊዜ ሕገ ወጡ ቡድን ራሱ ያደራጀውን እና ሲያሞካሸው የቆየውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 2013 ዓ.ም. በማጥቃት የተቃርኖ ጉዞውን መቀጠሉን አረጋግጧል። በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ የትግራይ ሕዝብ ጋሻና መከታ፣ የችግር ጊዜ ደራሽ እና ከሻዕቢያ ተከላካይ ሆኖ ላቡንና ደሙን ገብሯል። ሕገ ወጡ ቡድን የሀገር ሉዓላዊነትና የሕገ-መንግሥት ጠባቂ ነኝ ሲል ቆይቶ፣ ለ20 ዓመታት በትግራይ ሕዝብ ደህንነት ጥበቃ ላይ የነበረውን እና የትግራይ ተወላጆችንም በሠራዊቱ ውስጥ ያቀፈውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት አጥቅቷል። ሴረኛው እና በተቃርኖ የተሞላው ቡድን የማይመርዝና የማይለውጠው መሆኑን ያረጋገጠበትን ድርጊት ፈጽሞ የሀገር ጋሻና መከታን አዋርዷል። ይህ ድርጊት በኢትዮጵያ ዘመናዊ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳፋሪ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። የተቃርኖው ውጤት ግን መላውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልተጠበቀ ሁኔታ አንድ ላይ አስተሳሰረ፤ ለሉዓላዊነትና ለግዛት አንድነት የአባቶቹን ታሪክ እንዲደግም ዕድል ፈጠረ። ተቃርኖ ሦስት፦ የሰላም ውል እና የውስጥ ክፍፍል ሕገ ወጡ ቡድን የሥልጣን ጥመኝነቱን ለማርካት ስፍር ቁጥር የሌላቸው የትግራይ ክልል ተስፋ የሆኑ ወጣቶችን በጦርነት ከማገደ በኋላ የሰላም ስምምነት ተፈረመ። በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተፈረመው የሰላም ስምምነት ጦርነቱን ለማስቆም የተደረገ ወሳኝ እርምጃ ነበረ። ነገር ግን ከስምምነቱ በኋላ አሁንም ከስህተቱ የማይማረው ይህ ቡድን የተቃርኖ ጉዞውን መቀጠሉን ያረጋገጠበት ጥፋት ፈጸመ። ሕገ ወጡ ቡድን ስምምነቱን በይፋ ከተቀበለው በኋላ ስምምነቱን የሚጥሱ ድርጊቶችን መፈጸም ቀጠለ። መሣሪያ ለማስረከብ ተስማምቶ በስምምነቱ መሠረት መሄድ አቃተው፣ እንቅፋት ፈጠረ። በትጥቅ ውስጥ የቆዩ ወጣቶች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ማድረግ ነበረበት፣ አላደረገም። ይልቅስ ለሌላ ጥፋት ውስጥ ለውስጥ መዘጋጀቱን ተያያዘው። ጊዜያዊ አስተዳደር ለመመስረት ተስማምቶ ወደ ተግባር ከተገባ በኋላ የጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮችን አልቀበልም በማለት ሕገ ወጥነቱን ቀጥሎ ለትግራይ ሕዝብ ሰላም እና እፎይታ የሰጠውን የሰላም ስምምነት አፈረሰ። ከጦርነቱ ማብቃት በኋላ ትኩረት መደረግ የነበረበት የወደሙ አካባቢዎችን መገንባት፣ የተፈናቀሉትን መመለስ እና ሰብዓዊ እርዳታ ማፋጠን ላይ መሆን ሲገባው፣ ሕገ ወጡ ቡድን ወደ ውጭ ይፋ በወጣ የሥልጣን ሽኩቻና የእርስ በእርስ ውንጀላ ውስጥ መዘፈቁ ለሕዝቡ ያለው ግድየለሽነት ማሳያ ሆኖ ተወሰደ። ለጥፋት ተልዕኮው ስኬት በፍጹም የዓላማም ይሁን የትግል አንድነት የለኝም ሲላቸው ከነበሩ የጥፋት ቡድኖች ጋር አበረ። ይህ ብቻ ሳይሆን ከኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በመመሳጠር ሉዓላዊነትን ለማስደፈር እና ሀገር ለማፍረስ በሙሉ አቅሙ መንቀሳቀስ ጀመረ። ልብ ማለት የሚገባን ባህር በርን የሚያክል ጉዳይ እንደ ተራ ሸቀጥ ያየው ቡድን እንዴት ስለ ብሔራዊ ክብር እና ሉዓላዊነት ሊያስብ ይችላል? ሊሆን አይችልም። ተቃርኖ አራት፦ የሕገ ወጡ ቡድን የመጨረሻው የጥፋት ጉዞ ዓለምና የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ ቢቀየርም፣ ሕገ ወጡ ሕወሓት ግን አሁንም በ1960ዎቹ እና 70ዎቹ የትግል ስልት ተከተሏል። ቡድኑ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶች ከሆኑት ባዕዳን ተልዕኮ ተቀብሎ ከሀገር ውስጥ ባንዳዎች ጋር አብሯል። ‘ጽምዶ’ ከተባለው የጥፋት ስብስብ ፊት አውራሪ በመሆን የለመደውን የተቃርኖ ጉዞ ለመቀጠል ተቅበዝብዟል። የወጣቱን የሥራ፣ የዲሞክራሲ፣ የኢኮኖሚና የዘመናዊነት ጥያቄ በትክክለኛ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ወደ ሥልጣን ለመመለስ ለሚያደርገው የቀቢጸ ተስፋ ሙከራ እያደረገ ነው። ከምርጫ ቦርድ ጋር ያለው ሕጋዊ ሰውነት የማጣት አለመግባባት እና በሕጋዊ መንገድ ራሱን ለማደስ ፈቃደኛ አለመሆኑ ቡድኑን በሕግ ፊትም ሆነ በፖለቲካዊ ምህዳሩ ውስጥ ወደ መጨረሻው የመገለልና የውድቀት ምዕራፍ መርቶታል። ዛሬ ግን ትናንት አይደለም። ኢትዮጵያ ዘመኑን በዋጀ አመራር እየተመራች ትገኛለች። ዘመኑን ሙሉ የተቃርኖ ጉዞ ያደረገው ሕገ ወጡ ቡድን ወደ መጨረሻው የፖለቲካ ውድቀት እያመራ ነው። የሕገ ወጡ ቡድን የተቃርኖ ጉዞም የበቃል።
የኢትዮጵያዊያን ምክክር፤ የጋራ ነገን የሚያሻግር የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ድልድይ
Jul 22, 2026 822
በሚኪያስ ጎቡ መግቢያ፡- ሀገራት ከጦርነት በላይ የሚፈትናቸው ጠላት አለ፤ እርሱም በአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚፈጠረው የመተማመን መሰናክል ነው። መሣሪያ የፈጠረውን ጉዳት እንደገና መገንባት ይቻላል። የተሰበረ ልብና የጠፋ መተማመን ግን በጉልበት አይመለስም። ለዚህም ነው ብዙ ሀገራት ከግጭት በኋላ ወደ ምክክር የሚመለሱት። ብሔራዊ ምክክር የአንድ መንግሥት ፕሮጀክት ወይም የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአንድ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው የሰላም ውርስ ነው። የሚጋጩ ሃሳቦች በጠመንጃ ሳይሆን በቃል ሲገናኙ፣ የተለያዩ ትርክቶች በመደማመጥ ሲቀራረቡ፣ ልዩነቶችም የጥላቻ ምንጭ ሳይሆኑ የመግባባት መነሻ ሲሆኑ ነው እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚፈጸመው። የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ብሔራዊ ምክክር አንድ ዓይነት ቀመር የለውም። እያንዳንዱ ሀገር በታሪኩ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካዊ እውነታውና በማኅበራዊ መዋቅሩ መሰረት የራሱን መንገድ ይመርጣል። ነገር ግን የሁሉም ግብ አንድ ነው፤ ግጭትን በመግባባት፣ ጥላቻን በመተማመን፣ ፍርሃትን በተስፋ መተካት። በአውሮፓ ከኮሙኒዝም ውድቀት በኋላ፣ በአፍሪካ ከአምባገነናዊ አስተዳደሮች ሽግግር ወቅት፣ በደቡብ አሜሪካ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሂደቶችና በዓረቡ ዓለም ከፖለቲካ አብዮቶች በኋላ የተካሄዱ ምክክሮች አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ። ምክክር ሲታመን ሀገር ያድናል፤ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውል ግን ቀውስን ያባብሳል። ይህ የኢትዮጵያም ትልቁ ፈተና ነው። ሀገራዊ ምክክር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው። የምንናገረው ቃል፣ የምንጽፈው ሐሳብ፣ የምናዳምጠው አቋምና የምንቀበለው ልዩነት የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርጻሉ። ምክክር የሚጀምረው በአዳራሽ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፤ የሚሳካውም ከመናገር በላይ በመደማመጥ ሲቻል ነው። ስለዚህ የዛሬው ጥያቄ "ምክክር ይካሄድ ወይ?" የሚል አይደለም። "ምክክሩን ለሀገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለታሪክ የሚያስከብር እንዴት እናድርገው?" የሚለው ነው። መልሱም በአካታችነት፣ በእውነት፣ በመከባበርና በሀገርን ከግል ጥቅም በላይ በማስቀደም ውስጥ ይገኛል። ምክክር፤ የሀገር መድኃኒት ወይስ የትውልድ ፈተና? ምክክር ለምን ያስፈልጋል?፡- ማንኛውም ሀገር የሚያድገው በሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ብቻ አይደለም። በሕዝቦቿ መካከል በሚኖረው መተማመን ጭምር እንጂ። መንገድ፣ ድልድይና ፋብሪካ መገንባት ይቻላል፤ ነገር ግን የተሰበረ ማኅበራዊ ትስስር ካልተጠገነ የልማቱ መሠረት ይናወጣል። ስለዚህ ብሔራዊ ምክክር የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የሀገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወሰንበት የጋራ አስተሳሰብ ሂደት ነው። የምክክሩ ዋና ዓላማ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ወገኖች የራሳቸውን እውነት እየገለጹ፣ የሌላውንም እውነት በማዳመጥ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው። እውነተኛ የምክክር ድል የሚለካውም የማን ሃሳብ አሸነፈ ሳይሆን ለሀገር ምን ያህል ሰላምና መተማመን ፈጠረ በሚለው ነው። የዓለም ተሞክሮ የሚያስተምረን፡- የታሪክ ገጾች እንደሚያሳዩት ሀገራት የብሔራዊ ምክክርን መንገድ የመረጡት ሌሎች አማራጮች ሲያቅቷቸው ነው። አንዳንዶቹ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ቀውስ ነበራቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በሥልጣን ሽኩቻ ተከፋፍለው ሲራኮቶ የሰነባበቱ ናቸው። ነገር ግን የተሳካላቸው ሀገራት አንድ የጋራ መርህ ነበራቸው፤ የሀገርን ጥቅም ከፓርቲ፣ ከቡድንና ከግል ጥቅም በላይ አስቀድመዋል። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገረችው በበቀል ሳይሆን በሰለጠነ ምክክር ነው። ፖላንድና ሀንጋሪ የፖለቲካ ሽግግራቸውን በየጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር አሳልፈዋል። ላይቤሪያና ሊባኖስ የጦርነት ቁስላቸውን ለማዳን የመደማመጥን መንገድ መርጠዋል። በተቃራኒው ግን ምክክርን ለፖለቲካ ሕጋዊነት ማግኛ፣ ለሥልጣን ማራዘሚያ ወይም ለውጭ ጫና ማስታገሻ ብቻ ያደረጉ ሀገራት የበለጠ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። ይህም አንድ ግልጽ ትምህርት ይሰጠናል፤ የምክክር ስኬት የሚወሰነው በመድረኩ ሳይሆን በተመካካሪዎች ቅንነት መሆኑን ያስረዳናል። ምክክር የሚጠይቀው ከባድ ኃላፊነት፡- ሀገራዊ ምክክር የኮሚሽን ወይም የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም። የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የጋራ ነገ አሻጋሪ ድልድይና የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ነው። ፖለቲከኛው የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ የሚዲያው እውነትን በሚዛናዊነት ማቅረብ፣ የሲቪክ ማኅበራት የተገለሉ ድምፆችን ማሰማት፣ የኃይማኖት ተቋማት ይቅርታና መቻቻልን ማስፋፋት፣ ወጣቱ ከጥላቻ ይልቅ ውይይትን መምረጥና ምሁራን በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ማንም ወገን የራሱን አቋም ብቻ ለማስገደድ ከሞከረ፣ ምክክሩ ወደ ክርክር ይቀየራል። ሁሉም ለመረዳት እንጂ ለማሸነፍ ካልመጡ ደግሞ የምክክሩ መንፈስ ይጠፋል። የሀገራዊ ምክክር ትልቁ ድል የሌላውን አቋም መለወጥ ሳይሆን፣ የሌላውን ህመም መረዳት ነው። ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር፤ ልዩነታቸው ምንድን ነው?፡- ብዙ ጊዜ ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር የሚሉት ቃላት በአንድ ትርጉም ይጠቀሳሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ሂደቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ዓላማና ባህሪ አላቸው። ይህንን ልዩነት አለማወቅ ሀገራዊ ምክክርን ከመጀመሪያው ሊያዛባው ይችላል። ውይይት የሐሳብ ልውውጥ ነው። ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ይደማመጣሉ። ሁልጊዜ ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችላል። ክርክር የሚያተኩረው የማን ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ላይ ነው። የራስን አቋም በማስረጃ ለማስረዳት ይደረጋል፤ አንድ አሸናፊና አንድ ተሸናፊ ሊኖር ይችላል። ድርድር ደግሞ የጥቅም ግጭትን በመካከለኛ መፍትሔ ለመፍታት የሚደረግ ሂደት ነው። እያንዳንዱ ወገን ከአቋሙ በመቀነስ የጋራ መፍትሔ ለማግኘት ይሞክራል። ሀገራዊ ምክክር ግን ከእነዚህ ሁሉ የላቀ ሂደት ነው። ዓላማው ማንንም ማሸነፍ ወይም ማስሸነፍ ሳይሆን የሀገር የወደፊት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። በምክክር ውስጥ የሚሸነፍ ሰው የለም፤ የሚያሸንፈው ሀገር ነው። የኢትዮጵያ ልዩ እውነታ፡- ኢትዮጵያ ሦስት ሺህ ዘመናትን የተሻገረ በሕብር ያሸበረቀ ታሪክ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ኃይማኖት ያላት ሀገር ናት። ይህ በሕብር ያሸበረቀ ልዩነት የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆን ሲገባው በተለያዩ ወቅቶች የፖለቲካ አለመግባባቶችና የታሪክ ትርክቶች የመከፋፈል መሣሪያ ሆነው ቆይተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ፈተናም ይህ ነው። ሁሉም የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ወደ ጠረጴዛው ይመጣሉ፤ ነገር ግን ከጠረጴዛው የሚወጡት አንድ የጋራ የወደፊት ርዕይ ይዘው መሆን አለባቸው። ይህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ምክክሩ ከቃላት በላይ በተግባር የሚገለጥ ቅንነትን ይፈልጋል። የዋናው ምክክር ጉባኤ የህዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም ሀገርን የማስቀደም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስኬታማ ምክክር የሚመሰረትባቸው አምስት ምሰሶዎች፡- ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ቢያንስ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ሊኖሩት ይገባል። እነሱም መተማመን፣ አካታችነት፣ እውነት፣ ፍትሕና የጋራ ርዕይ ናቸው። ከሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበራሰብ የሕዝብ ወኪል 4 ሺ ተመካካሪ ኢትዮጵያዊያንም በሀገር ግንባታ ጉዳይ፣ የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽ ማዕከል እየመከሩ ይገኛል። ሀገራዊ ምክክር ያለፈውን ለመቁጠር ሳይሆን፣ የወደፊቱን ለመገንባት የሚደረግ የጋራ ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ መንገድም የልዩነት ግድግዳን የሚያፈርስ የትውልድ አደራና የብሔራዊ መግባባት ማሰሪያ ጥበብና ትልም ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፤ የተገኙ ዕድሎች፣ ዋና ፈተናዎች እና የወደፊት አቅጣጫ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ ኢትዮጵያ ብዙ የፈተና ዘመናትን አልፋለች። አንዳንዶቹ ፈተናዎች ከውጭ ጥቃት የመጡ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ከውስጣዊ አለመግባባቶች፣ ከተለያዩ የታሪክ ትርክቶች፣ ከፖለቲካ ፉክክርና ከመተማመን እጥረት የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የትውልድ ዕዳን ለማቃለል የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው። ይህ ሂደት ቀላል አይደለም። በርካታ ዓመታት የተከማቹ ቅሬታዎች፣ የተለያዩ እውነታዎች፣ የተቃራኒ ትርክቶችና የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መገናኘታቸው በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ነገር ግን ከዚህ በላይ ትልቁ ፈተና ልዩነትን ወደ መግባባት መቀየር ነው። ዕድሎች፤ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ወሳኝ መስኮቶች፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምታነሳበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። የታሪክ አተረጓጎም፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የፍትሕ ጉዳዮችና የአብሮነት ዕሴቶች በጦርነት ሳይሆን በሐሳብ የሚፈቱበት ዕድል ይፈጥራል። ከዚህም በላይ ምክክሩ የፖለቲካ ባህልን ለመቀየር የሚያስችል ዕድል ነው። ለብዙ ዓመታት "አሸናፊና ተሸናፊ" በሚለው አስተሳሰብ የተመራውን ፖለቲካ ወደ "አብሮ ማሸነፍ" የሚሸጋግር ከሆነ እውነትም የኢትጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ያገኛል። በሂደቱ ፊት የሚቆሙ ፈተናዎች፡- ማንኛውም ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ ተስፋ እንደሚፈጥር ሁሉ ከባድ ፈተናዎችንም ይዞ ይመጣል። የመጀመሪያው ፈተና የመተማመን እጥረት ነው። ለብዙ ዓመታት የተገነባ ጥርጣሬ በጥቂት ወራት አይጠፋም። ስለዚህ የምክክሩ ተዓማኒነት በእያንዳንዱ እርምጃ ሊገነባ ይገባል። ሁለተኛው ፈተና የተለያዩ የታሪክ ትርክቶች ናቸው። አንድ ክስተት በአንዱ ወገን የድል ታሪክ ሲሆን፣ በሌላው ወገን የመከራ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይህን ልዩነት በክብር መቀበል እንጂ መግፋት አይቻልም። በሌላ መልኩም የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭት ነው። በዲጂታል ዘመን አንድ ያልተረጋገጠ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ሺዎችን ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማትና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚወስዱት ኃላፊነት ከመቼውም በላይ ወሳኝ ይሆናል። የምሁራንና የመገናኛ ብዙኅን ሚና፡- በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ምሁራን ስሜትን ሳይሆን ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው። የማኅበረሰብ ችግሮችን በሳይንሳዊ ጥናት መተንተን፣ ከሌሎች ሀገራት ልምድ መማርና አማራጭ መፍትሔዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መገናኛ ብዙኅንም በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙኅን ወሬን ከማባዛት ይልቅ እውነትን ማጣራት፣ ልዩነትን ከማባባስ ይልቅ መግባባትን ማጎልበት፣ ስሜትን ከማቀጣጠል ይልቅ እውነታን ማቅረብ አለበት። ምክክሩን የሚያጠናክር የመገናኛ አውታር ታሪክ ይሠራል፤ የሚያደናቅፍ ደግሞ በታሪክ ይጠየቃል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ክስተት አይደለም። ምክክር በትውልድ የሚገነባ የፖለቲካ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ሊጨርስ ይችላል፤ ነገር ግን የመደማመጥ ባህል በሕዝብ ውስጥ ካልሰረጸ የምክክሩ እውነተኛ ዓላማ አይሳካም። የዛሬ ውሳኔ፤ የነገ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ የታሪክ ወቅቶች በየቀኑ አይመጡም። አንዳንድ ውሳኔዎችም የአንድ መንግሥት ዘመንን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሀገራዊ ምክክር የእነዚህ ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ዛሬ በምንመርጠው የምክክር ባህል፣ በምንገነባው መተማመንና በምናሳየው የፖለቲካ ብስለት ላይ የነገዋን የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያንፃል። ምክክር ሁሉንም ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ አስማታዊ መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ጦርነትን ከውይይት፣ ጥላቻን ከመቻቻል፣ መከፋፈልን ከመተባበር የሚተካ ብልህ መንገድ ነው። የሚያደርገውም ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን በአንድ ሀገር ጣሪያ ስር እንዴት እንደሚኖሩ የጋራ ሕግና ሥርዓት መፍጠር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ ከባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች። የፖለቲካ አለመተማመን፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችና የማኅበራዊ ስብራቶች በቀላሉ የሚያልፉ አይደሉም። ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በጥይት ከመፍታት ይልቅ በምክክር ለመፍታት መሞከር በራሱ የታሪክ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ ግን የአንድ ተቋም ብቻ አይደለም። የመንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው። የሀገር ዕጣ ፋንታ ለአንድ ቡድን ብቻ የሚተው አይደለም፤ በጋራ የሚገነባ እንጂ። ከምክክር ወደ ባህል፡- ምክክሩ ተጠናቀቀ ማለት የሀገሪቱ ችግሮች ተፈቱ ማለት አይደለም። እውነተኛው ስኬት የሚለካው የመደማመጥ ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲሰርጽ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በፖለቲካ ተቋማትና በየቤቱ የመነጋገር ባህል ካልጠነከረ፣ ምክክሩ የሰነድ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። የእውነተኛ ዴሞክራሲ መሠረት ተመሳሳይ አስተሳሰብ መኖር አይደለም፤ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በሰላም የመቀበል ባህል መኖር ነው። ልዩነት የችግር ምንጭ ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ ሲሆን ነው አንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም የምታገኘው። የማጠቃለያ፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚያስፈልገው ብልህ አመራር ብቻ አይደለም፤ ታጋሽ ዜጎችንም ይፈልጋል። ሀገር የምትገነባው በግንብ ሳይሆን በመተማመን ነው። ሰላም የሚጸናውም በፍርሃት ሳይሆን በፍትሕ ነው። ዛሬ የምንመርጠው የምክክር መንገድ ነገ ለልጆቻችን የምንተወው ታሪክ ይሆናል። ስለዚህ በኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተደራጅተው የሚመከርባቸው ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የዛሬ አጀንዳ ብቻ አይደሉም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጽ የትውልድ አደራ እንጂ። የዋናው ምክክር ጉባኤ ተመካካሪ የሕዝብ ወኪሎችም ከግልና ቡድን ፍላጎት ይልቅ የቀጣዩን ትውልድና ሀገርን ማስቀደም ይጠበቅባቸውል። ምክክር የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የተሰበረ መተማመንን የሚጠግን፣ የተከፋፈለ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ፣ የትውልድ ታሪክን በአዲስ ተስፋ የሚጽፍ ሀገራዊ ጥበብ ነው። የምንወስነው ዛሬ የምንወርሰውን ነገ ይበይናል። ምክክር የሀገር መድኅን ነው፤ ኢትዮጵያም እየመከረች ነው።      
ፈተናዎችን ወደ ዕድል የቀየረው የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪው ዘርፍ እመርታ
Jul 21, 2026 924
በሙሴ መለሰ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ አዲስ መነቃቃትንና ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት፣ የግል ዘርፉን በማበረታታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማመጣጠን ባለፈ፣ በሁሉም ንዑሳን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ተስፋ እንዲፈነጥቅ አድርጓል። የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪ ስኬቶች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በፋይናንስ፣ በግብዓት እና በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሙሉ ማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ንቅናቄው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዓመታት ብቻ የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የተቻለ ሲሆን፣በተለይም በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። ይህም የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ አማካይ የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን እንደ ኮሮና ወረርሽኝና የአጎዋ (AGOA) ስረዛ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችላለች። የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራን ጨምሮ በተቀረጹ ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አማካኝነት፣ ቀደም ሲል 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውንና ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ሂደትም እስካሁን ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያን ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑት ተግባራት ሌላኛው የለውጡ ማሳያ ነው። በይርጋለም፣ቡሬ እና ቡልቡላ የሚገኙ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ ስራ መግባት አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ለፋብሪካዎች እንዲያቀርብና እሴት የተጨመረበት ምርት ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መንገድ ከፍቷል። ይህ ስትራቴጂ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደጉም በላይ የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ ዕቃ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ እገዛ አድርጓል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ማምረቻ ዘርፍ የታየው ስኬት ለሀገሪቱ የጤና ዋስትና ትልቅ ምሰሶ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ በለውጡ ዓመታት ግን የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም ለአገር ውስጥ ገበያ ጥራት ያላቸው መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አስችሏል። በሌላ በኩል፣በኮንስትራክሽን እና ማዕድን ኢንዱስትሪ ላይ የታየው መነቃቃት የሀገሪቱን የመሠረተ ልማት ፍላጎት በራስ አቅም ለመደገፍ አስችሏል። አዳዲስ የሲሚንቶ እና የብረት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ እና ነባሮቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ መደገፉ፣ በሀገሪቱ ለሚታዩት ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የዘመናዊ ከተሞች ግንባታ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ግብዓትን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም አስችሏል። ማዕድናትን በተመለከተም፣ ጥሬ ግብአት ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ የመላክ ፖሊሲ በመተግበሩ የዘርፉን የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። ለኢንዱስትሪው ዘርፍ መፋጠን ሌላው ዋነኛ አስደጋፊ የሆነው የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውሃ፣ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቅና ወደ ሥራ መግባት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ አስችሏል። ይህ የአረንጓዴ የኃይል አቅርቦት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) እንዲሆኑ አድርጓል። ከነዚህ ዘርፎች ባሻገር፣ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ተከትሎ በቴክኖሎጂው እና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ስልኮች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የመገጣጠም ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።በተለይም ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ለነዳጅ ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) በአገር ውስጥ በስፋት መገጣጠም መጀመራቸው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ራሷን እንድትችል እና ለሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር መሰረት የጣለ እርምጃ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ የለውጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ውስጥ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገባቸው ነበሩ ሊባል ይችላል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ እስከ መሬት ወርደው የተተገበሩ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ሀገሪቱ በምርት ራሷን እንድትችል እና የውጭ ምርት ጥገኝነትን እንድትቀንስ አግዘዋታል። እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ጠንካራ መሰረቶች ናቸው።
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 4889
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!  
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና 
Jun 17, 2026 11286
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል።   የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል።   የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ? 
Oct 13, 2025 21240
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 14269
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል።   በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20020
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 103291
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 78318
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 56996
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 54568
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 39150
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 38891
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 38375
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 37118
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 103291
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 78318
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 56996
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 54568
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ዓይነ ስውሩ የቧንቧ ሰራተኛ 
Jul 31, 2026 995
ዋግ ኽምራ፤ሐምሌ 24/2018 (ኢዜአ) ፦"ዓይኖቼ ማየት ባይችሉም እጆቼ ተዓምር ይሰራሉ'' -ዓይነ ስውሩ የቧንቧ ሰራተኛ በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መለስ ጌታነህ የ62 ዓመት የእድሜ ባለጸጋ አዛውንት ናቸው፤ ከጊዜ በኋላ በመጣ ችግር የሁለት ዓይኖቻቸውን ብርሃን ያጡ ቢሆንም በአካባቢው ስመ ጥር የቧንቧ ሠራተኛ ናቸው። ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ ገና በወጣትነት ዕድሜያቸው የቧንቧ ሥራ ሙያን ቀስመው፣ በዋግ ኽምራ በሚገኙ ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ለንጹሕ መጠጥ ውሃ ተደራሽነት አሻራቸውን እያሳረፉ ያሉ ትጉህ ባለሙያ ናቸው። ቆላ በመውረድ፣ ደጋ በመውጣት፣ ተራራና ሸንተረሩን ሳይበግራቸው የውሃ መስመር በመዘርጋት ህብረተሰቡን የመጠጥ ውሃ እንዲደርሰው እያደረጉ ያሉ አዛውንት ናቸው። ለዚህም በተደጋጋሚ የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። በ1991 ዓ.ም የተፈራ ኃይሉ መታሰቢያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ ሲጀምር እሳቸው በቧንቧ ባለሙያነት በቋሚነት በመቀጠር፣ የውሃ መስመር በመዘርጋትና በመጠገን የሕክምና ክፍሎች ያልተቋረጠ ውሃ እንዲያገኙ ማድረግ ችለዋል። ይሁን እንጂ ከዕለታት በአንድ ቀን ሥራቸውን እያከናወኑ ባሉበት ወቅት ባላወቁት ምክንያት የሁለት ዓይኖቻቸውን ብርሃን ያጡበት አጋጣሚ በመከሰቱ ከቤት ለመዋል መገደዳቸውን ያወሳሉ። እንደ አቶ መለስ ገለጻ፡ “ዓይኔ ማየት ባለመቻሉ ራሴን ችዬ መንቀሳቀስ፣ እንደልቤ ሜትር ዘርግቼ ለክቼ መቁረጥና ገደል ላይ ተንጠልጥዬ የቧንቧ መስመር መዘርጋት አልችልም የሚል የተሸናፊነት ስሜት አድሮብኝ ተስፋ ቆርጬ ተቀምጬ ነበር” ይላሉ። በዚህ ወቅት ትጋታቸውንና ብርታታቸውን የሚያውቁ የሆስፒታሉ ዳይሬክተር የነበሩት ዶክተር ዓለማየሁ ትኩ፣ ወደ ሆስፒታሉ በመውሰድና በመምከር ሥራቸውን እንዲቀጥሉ እንዳገዟቸው አውስተዋል። ቀስ በቀስም አቶ መለስ ሜትር በመዘርጋትና መጋዝ በመጨበጥ ልኬታን አስተካክለው፣ መገጣጠሚያ ቦታዎችን በዳበሳ ለይተው የቧንቧ ሙያ ሥራቸውን እንደገና “ሀ” ብለው ማስቀጠላቸውን አመልክተዋል። ምንም እንኳን ከወረዳ ወረዳ ተንቀሳቅሶ መሥራት ባይችሉም፣ በግለሰብ ቤቶችና ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱ የቧንቧ ጥገና ሥራቸውን በብቃት እያከናወኑ ያሉ ብቁ ባለሙያ ሆነው ቀጥለዋል። በሆስፒታሉም ከአገልግሎት ውጭ የነበሩ የውሃ መስመሮችን በመለየትና በአግባቡ በመጠገን፣ ለሐኪሞችና ለሕመምተኞች ወጥ የሆነ የንጹሕ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እንዲኖር በማድረግ “አንቱ” የተባሉ ባለሙያ ሆነዋል። አቶ መለስ በቧንቧ ሥራ ሳይገደቡ፣ በራዲዮ በሚቀርቡ የቴክኖሎጂ ፕሮግራሞች ባገኙት እውቀት ከአገልግሎት ውጭ የነበረውን የሆስፒታሉን የላውንድሪ (ልብስ ማጠቢያ) ማሽን በዳበሳ ጠግነው ወደ አገልግሎት በመመለስ ሆስፒታሉን ከወጪ ታድገዋል። “ብርሃን ከዓይን ብቻ ሳይሆን ከልብና ከመዳፋችንም ይገኛል” የሚሉት አቶ መለስ፣ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ምጣዶችን በመጠገንና ሌሎችንም የቴክኒክ ሥራዎች በመሥራት ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን የሚያስተዳድሩ ጠንካራ የዕድሜ ባለፀጋ ናቸው። "የዓይን ብርሃኔን አጣሁ ብዬ አንድም ቀን አስቤ አላውቅም” የሚሉት አቶ መለስ፣ አሁን ላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች (ኮንዶሚኒየም) ጣራ ላይ በመውጣት ጭምር ቧንቧ ጠግነው የሚወርዱ ባለሙያ ሆነዋል። “እኔ ሥራ ሳልሠራ ስውል ያመኛል” የሚሉት አቶ መለስ፣ ወጣቱ ሥራን ሳይንቅ ከሰራ ከትንሽ ነገር ተነስቶ ጊዜውን በአግባቡ በመጠቀም ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ እንደሚችል ምክራቸውን ለግሰዋል። ስለ ጉዳዩ ኢዜአ ያነጋገራቸው የተፈራ ኃይሉ ጠቅላላ ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ አቶ ታምሩ ቢምረው እንዳሉት፡ ጋሽ መለስ የዓይን ብርሃናቸውን ቢያጡም በሙያቸው የትጋትና የ“ይቻላል” ተምሳሌት የሆኑ አዛውንት ናቸው። አዛውንቱ በሙያቸው የሆስፒታሉ የውሃ አቅርቦት እንዳይቋረጥ በማድረግ ለሕክምና ሥራ መቀላጠፍ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልጸው ለሌሎች ባለሙያዎች በታታሪነት፣ በሥራ ፍቅር እና በጥንካሬ አርዓያ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
የአካባቢ ፀጋን በማወቅ የተገኘ ስኬት-የምህንድስና ምሩቁ ሞዴል አርሶአደር
Jul 30, 2026 403
የምህንድስና ምሩቁ ሞዴል አርሶአደር (በቀደሰ ተክሌ- ሚዛን አማን) እውቀት በቅድሚያ ራስን ለመለወጥ ከዚያም አልፎ ለሀገር ሲተርፍ ይበልጥ ትርጉም ይሰጣል። ማወቅ ከተማርነው ትምህርት የዘለለ መረዳት እንዲኖረን በማድረግ ለነገሮች ያለንን የእይታ አድማስ ያሰፋል። የ"ለምን?" ጥያቄዎችን በማንሳት በምላሹ መፍትሔ ለመስጠት ይሞክራል። በዚህም ረገድ ከተማሩበት ትምህርት ባሻገር ሌላ ዓለም እንዳለ በማሳየት በኩል ተምሳሌት የሚሆኑ አሉ። የዚህ ፅሁፍ ባለታሪክም ከምህንድስና ትምህርቱ ባሻገር ያለውን ፀጋ በእርጋታ ተመልክቶ ውጤታማ መሆን እንዴት እንደሚቻል ለሌሎች ምሳሌ የሆነ ወጣት ነው። ወጣቱ ኢንጂነር ይንገሥ ጌታቸው ይባላል። በሸካ ዞን የኪ ወረዳ የአላሞ ቀበሌ ነዋሪ ነው። በአካባቢው ባከናወነው ውጤታማ የግብርና ሥራ ሞዴል አርሶ አደር የሚል ሌላ የማዕረግ ስያሜን አግኝቷል። ይንገስ አስተዳደጉ በግብርና ስራ ከተሰማሩ ቤተሰቦቹ የእርሻ ማሳ ጋር የተያያዘ ነው። ዕድሜው ለትምህርት ሲደርስ ከትምህርት ቤት መልስ ቤተሰቦቹን በግብርና ስራ ያግዛል። ይህም የእርሻ ሥራን በአግባቡ እንዲረዳ አድርጎታል። ቤተሰቦቹን የሚያግዝበት እጁ የሻከረ ጉልበቱ የበረታ ነበር።   ከዚያ አለፍ ሲልም በትምህርቱ ጎበዝ ስለነበርም እስከ ዩኒቨርሲቲ ዘለቀ። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ትምህርቱን አጠናቆ ተመረቀ። ወደ ቀዬው ሲመለስም ስራ ከመፈለግ ይልቅ ከልጅነቱ ጀምሮ በሚያውቀው የግብርና ስራ ላይ ለመሰማራት በመወሰን በአጭር ታጥቆ ወደ ስራ ገባ። ለዘመናት ውጤታማ ሳይሆን የቆየውን የእርሻ ስራ ወደ የተሻለ ደረጃ ላይ የማድረስ ራዕይን ሰንቆ እጁን ከጭቃ ጋር አገናኘ። ወጣት ይንገስ ወደ እርሻ ስራ ለምን እንደመጣ ሲናገር "ቤተሰቦቼ ዕድሜያቸውን ሙሉ በግብርና ሥራ ነው የቆዩት፤ ነገር ግን ለውጥ የሚባል ነገር የለም።" ይህ ቁጭት ነው እንግዲህ "ለምን?" የሚል የመብሰልሰል ጥያቄን ሊያጭርበት የቻለው። የዘልማድ አሰራር፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የግብዓት አጠቃቀም፣ በዕውቀት ያለመመራትና ሌሎች ምክንያቶች የእርሻ ስራውን ውጤታማ እንዳይሆን እንዳደረጉት ተገነዘበ። ለዚህም ክፍተትን ማየት፣ መንስኤ መለየት፣ ከዛም ለውጥን አልሞ ወደ ውጤት መቀየር መፍትሔ ሊሆን እንደሚችል ተረዳ። በትናንቱ መንገድ ባለመጓዝ የዘመነና ገበያው የሚፈልገውን ምርት ለማምረት ለራሱ ቃል ገባ፤ ከራሱ ጋር ተስማማ።   ወጣቱ አካባቢው ለቅመማ ቅመም ምርት የተመቸ ፀጋን የታደለ መሆኑን ስለሚያውቅ ይህን ዕድል ለመጠቀም በማሰብ ውድ የሆኑ የቅመማ ቅመም ምርቶችን በማምረት ለገበያ ለማቅረብ ወጠነ። ወጥኖም አልቀረም ወደ ተግባር ለመቀየር ተንቀሳቀሰ። ይህን ጊዜ ነው የሕይወቱ አዲስ ምዕራፍ የተከፈተው። ከአላሞ ተነስቶ ወደ ቴፒ የግብርና ምርምር ማዕከል አቀና። ማዕከሉ በብሔራዊ ደረጃ በቅመማ ቅመም ላይ ትኩረት በማድረግ የምርምር ስራዎችን ይሰራል። የምርምር ማዕከሉ ከሚያወጣቸው ዝርያዎች መካከል ቫኒላ አንዱ ነው። ቫኒላ ደግሞ በዓለማችን ውዱ ቅመም ነው። ወጣቱ ይንገስም ፍላጎቱ ተሳክቶ ዝርያውን ከማዕከሉ በመውሰድ ማሳው ላይ ተክሎ መንከባከብ ጀመረ። የቫኒላ የአመራረት ሂደት ትዕግሥትን የሚጠይቅ ነው። በተለይ ፍሬ እንዲሰጥ እርስ በእርስ የማዳቀሉ ተግባር ጥብቅ ክትትልና ትጋትን የሚጠይቅ ነው። ሂደቱን ተሻግሮ ምርት እስከሚሰጥ ድረስ ወጣቱ ከባለሙያዎች ድጋፍን ከመጠየቅ ባሻገር ድረ-ገፅን በመጠቀም በዓለም አቀፍ ደረጃ የቫኒላ አመራረት ያለበትን ደረጃ እስከ መከታተል የደረሱ ጥረቶችን ያደርጋል። በዚህም ብዙዎች ተስፋ የቆረጡበትን የቫኒላ ቅመም ምርት እርሱ በአግባቡ አልምቶ ውጤታማ እንዲሆን አድርጎታል። እነሆ አሁን ላይ ወጣቱ ካፒታሉን በማሳደግ በየዓመቱ ሚሊዮን ብሮችን ወደ ካዝናው የሚያስገባ ባለሃብት ሆኗል። በተጨማሪም ወጣቱ የቤተሰቡን ማሳ በአዲስ የቡና ዝርያ ለመሸፈን በሳይንስ የተደገፈ የማሳ ዝግጅት አድርጎ ቡና መትከል ጀመረ። እነሆ ዛሬ 5 ሄክታር በምርምር የተገኘ ምርጥ የቡና ዝርያ ለምቶ ፍሬ መስጠት ጀምሯል። ይህ የቡና ውጤታማነት ዝቅተኛ መልክዓ-ምድር ባላት የአላሞ ቀበሌ ከዚህ ቀደም የማይታሰብ አዲስ ብሥራት ነው። ከዚህ ቀደም የነበሩ የቡና ዝርያዎች ለቆላማ አካባቢ ተስማሚ ስላልነበሩ አርሶአደሮች ቡና አልምተው ብዙም ተጠቃሚ አይሆኑም ነበር። ወጣቱ የቴፒ ግብርና ምርምር ያወጣቸውን እንደ "K-1፣ K-2 እና I-3" በሚል ስያሜ የሚታወቁ የቡና ዝርያዎችን በመውሰድ በማሳው ላይ በመሞከር ውጤት አምጥቶለት ችግኞቹ በ9 ወር አብበው የምሥራች ፍሬ ሊሰጡ ችለዋል። ዝርያዎቹ በሙሉ አቅም ምርት ሲሰጡ በሄክታር ከ20 ኩንታል በላይ ምርት ይሰበሰብባቸዋል። ኢንጂነሩ ሞዴል አርሶ አደር በቫኒላ እና በቡና ልማት ላይ ብቻም ራሱን አልገታም። በአቮካዶ፣ በሙዝ፣ በአናናስ፣ በፓፓያና በሌሎች የፍራፍሬ ዓይነቶችን ጨምሮ በካካዎ እና በቁንዶ በርበሬ ቅመማ ቅመም ምርቶች ላይ በመሰማራትም ተጠቃሚ መሆን ችሏል። የካካዎን ምርት ለኢንዱስትሪ ግብዓት እንዲውል በማድረግ የውጭ ምንዛሬን የማዳን ዓላማን ይዞ ወደ ምርት መግባቱን ይናገራል። ካካዎ ቾኮሌት ለሚያመርት ፋብሪካ በግብዓትነቱ ተጠቃሽ ነው።   ወጣት ይንገስ በተለያዩ ምርቶች ላይ ከመሰማራት ባሻገር የተሻሻሉ የዘር ችግኞችን እያባዛ ለአካባቢው አርሶ አደሮችም እያቀረበ ይገኛል። በዚህም በዓመት በሚሊዮን የሚቆጠር ገቢ በማግኘት ራሱን እና ቤተሰቡን የተሻለ የኑሮ ደረጃ ላይ አድርሷል። የሸካ ምድር ፍሬ ለመስጠት የምርት ዓይነት አይመርጥም። የሰጡትን ያበቅላል፤ ይህ ደግሞ በተፈጥሮ የተቸረ ጸጋ ነው። የወጣት ይንገሥ ማሳ አንድ ምርት ብቻን የማልማት ዕድልን ማን ይሰጠዋል። በጥምር የእርሻ ስነ-ዘዴ እርስ በእርስ ተመጋጋቢ የሆኑ የተለያዩ ምርቶች በአንድ ላይ ይመረታሉ። ለአብነትም አቮካዶ፣ ፓፓያና ሙዝ በአንድ ላይ ይመረታሉ። ይህም ውጤታማ የመሬት አጠቃቀም ሥርዓትን ፈጥሯል። ለአካባቢው ሥነ-ምህዳር ጥበቃ፣ ለጥላና የእንጨት ሥራ ውጤቶች ግብዓት የሚሆነው የግራቪላ ዛፍ ለቁንዶ በርበሬ ልማት መሠረት ሆኖ ያገለግላል። መንግሥት "ምግቤን ከጓሮዬ" በሚል ያስጀመረው ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ ማሳያ ከሆኑ ማሳዎች ውስጥ የሚመደበው የወጣቱ ማሳ ከፋብሪካ ውጤቶች በቀር ይህ ጎደለ የሚባልለት አይደለም። ከወተት እስከ ማር፣ ከአትክልት እስከ አዝርዕት ሁሉም በመጠኑ ይመረታል። ውጤታማ የግብርና ሥራ መሬትን አርሶ ከዘር ጋር ከማገናኘት ያለፈ ትርጉም የሚፈልግ መሆኑን ከኢንጂነሩ ሞዴል አርሶ አደር ይንገሥ የሥራ ተሞክሮ መማር ይቻላል። በቴክኖሎጂ ዘመን ከቴክኖሎጂ ርቆ ማልማት ድካም ከማብዛት ውጭ ውጤቱ አርኪ አይደለም። የግብርና ምርቶችን በከፊል ማቀነባበር የሚችሉ ማሽኖችን በመትከል ምርቶቹን በጥራት ለዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ አቅዶ እየሠራ መሆኑን ጠቅሷል። ከወጣት ይንገሥ የሥራ ውጤታማነት በኋላ ብዙዎች የአካባቢው ወጣቶች ተነቃቅተዋል። ብዙ ዓመት ሰፊ ማሳ አልምተው ጥቂት ምርት ይሰበስቡ የነበሩ አርሶ አደሮችም ወደ ይንገሥ ማሳ ጎራ ብለው ተሞክሮ በመቅሰም ለትግበራው ወደ ማሳቸው አቅንተዋል። ተሞክሮውን ፈጥነው ወደ ውጤት ከቀየሩ ወጣቶች መካከል ወጣት ብርሃኑ ጌታቸው አንዱ ነው። እርሱም ዛሬ ሁለተኛ ዓመቱን የያዘ የ5 ሄክታር ቡና ማሳ ባለቤት ሆኗል። ቡናን ከመትከል በተጨማሪ ዘር በማፍሰስ ችግኝ የማዘጋጀት ተግባር እንደሚያከናውን ገልጿል።   አርሶ አደር ታደሰ እጅጉ፤ ላለፉት በርካታ ዓመታት በእርሻ ሥራ ቢቆዩም ውጤታማውን መንገድ ሳይከተሉ መቆየታቸውን ይናገራሉ። አሁን ላይ ወጣቶቹ ሠርተው ባመጡት ውጤት ተደስተው አሠራሩን በማሳቸው ለመተግበር መነሳሳታቸውን ገልጸዋል። ያላቸውን 10 ሄክታር የእርሻ ማሳ ከልጆቻቸው ጋር በማልማት በአዳዲስ የቡና፣ የቅመማ ቅመም እና የፍራፍሬ ልማት ለመሸፈን ማቀዳቸውን ጠቅሰዋል። አቶ ተስፋዬ ግዛው የየኪ ወረዳ ቡና፣ ሻይና ቅመማ ቅመም ጽሕፈት ቤት ባለሙያ ናቸው። በወጣት ይንገሥ ጌታቸው የተከናወነው ውጤታማ ሥራ የወረዳውን የግብርና ሥራ ያነቃቃ መሆኑን ተናግረዋል። በቡና ምርታማነት ላይ የታየው ተሞክሮ ወደ ሌሎች ቀበሌዎች እንዲስፋፋ እያደረግን ነው ብለዋል።   በተለይ በጥምር እርሻ አመራረት ሥነ-ዘዴ የታየው የቅመማ ቅመም እና ፍራፍሬ ማሳ ውጤት በጠባብ ማሳ ብዙ የምርት መጠን መሰብሰብ የሚቻልበትን መንገድ በተግባር ያሳየ መሆኑን ገልጸዋል። የኢንጂነሪንግ ምሩቁ ወጣት ተሞክሮ የአካባቢን ፀጋ ባለመመልከት በሥራ ፍለጋ ጊዜያቸውን ለሚያባክኑ ወጣቶች የሚያስተምረው ዘርፈ ብዙ ትምህርት አለ ብለዋል። የሰው ልጅ ሕይወት የሚቀየረው በሥራ ዓይነት ሳይሆን በጠንካራ የሥራ ባህል ነው። በእጅ ያለን ወርቅ እንደ መዳብ ቆጥሮ የሩቅ ከመሻት ይልቅ በአጠገብ ያለን ጸጋ አይቶ ወደ ውጤት መቀየር ነገን በተሻለ ደረጃ አሻግረን እንድናይ ያስችለናል። ለዚህ ደግሞ የኢንጂነሪንግ ምሩቁ ሞዴል አርሶ አደር ይንገሥ ጌታቸው ተግባር ሕያው ምስክር ነው። ሰላም!
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም