ቀጥታ፡

የርገን ክሎፕ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የጀርመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የርገን ክሎፕን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል።

የ59 ዓመቱ ጀርመናዊ የአራት ዓመት ውል የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱ አሰልጣኙን እስከ 2030 የዓለም ዋንጫ መጨረሻ ድረስ የሚያቆያቸው ነው።

ክሎፕ በቦታው የተኩት በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጀርመን በ32ቱ ዙር በፓራጓይ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ከሆነች በኋላ ከኃላፊነታቸው የለቀቁትን ጁሊያን ናጌልስማንን በመተካት ነው።




ከሊቨርፑል የዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ የሬድ ቡል ሳልስበርግ የዓለም እግር ኳስ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ክሎፕ፣ የጀርመን እግር ኳስን እንደገና ወደ ቀደመ ገናናነቱ የመመለስ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

ክሎፕ ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም. በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ (Uefa Nations League) ከኔዘርላንድስ ጋር ያደርጋሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም