ቀጥታ፡

በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በመሳተፍ የልማት አርበኝነታችንን እያሳየን ነው

ደብረ ብርሃን ፤ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የሀገር ሰላምና የህዝቡን ደህንነት ከማስጠበቅ ጎን ለጎን በአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በመሳተፍ የልማት አርበኝነታቸውን እያሳዩ መሆኑን የፌዴራል ፖሊስ አባላት ገለጹ።

የአረንጓዴ አሻራ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር “ተስፋን እንትከል“ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ነው።

በፌደራል ፖሊስ ሰሜን ምስራቅ ቀጠና 7ኛ ሬጅመንት አዛዥ ዋና ሳጅን ናስር መሐመድ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ የፖሊስ አባላቱ በተሰማሩበት አካባቢ ሁሉ በኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ የልማት ስራዎች በመሳተፍ ላይ ናቸው።


 

በዚህም አገራቸውንና ህዝባቸውን እያገለገሉ መሆኑን  ገልጸዋል።

የፌዴራል ፖሊስ አባላቱ በተለያዩ አካባቢዎች  ሰላም ለማስፈን የተሰጣቸውን ተልእኮ ከመወጣት ጎን ለጎን በአንድ ጀንበር የአረንጓዴ  አሻራ መርሃ ግብር በቁርጠኝነት ተሳትፈናል ነው ያሉት።

በቀጣይም የተከሏቸውን ችግኞች በመንከባከብ ጸድቀው ለታለመላቸው ዓላማ እንዲውሉ ተከታታይ ስራ እንደሚሰራም አረጋግጠዋል። 

በዋናነትም የህዝብ ደህንነትን ከማስጠበቅ ባሻገር በዛሬው እለት በአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመሳተፍ የልማት አርበኝነቱን አረጋግጧል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም