ቀጥታ፡

አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ ተምሳሌታዊ ሒደት ነው

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/ 2028 (ኢዜአ) ፦አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር አንድነትን ለማጠናከር ትልቅ ተምሳሌታዊ ሒደት ነው ሲሉ የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ገለጹ።

የሃገራዊ ምክክሩ ተመካካሪዎች ዛሬ በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮች ችግኞችን የመትከል መርሃ-ግብር ተሳትፈዋል።

በዚህ ወቅት ዋና ኮሚሽነሩ እንደተናገሩት አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከችግኞች መትከል ያለፈ ተግባር ነው።

በምክክሩ መነጋገርንና መደማመጥን እያሰፋን ሃሳቦችን እየተከልን ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብርም ሃሳብን ለመትከል ለአንድነትና የጋራ ሃገር ለመገንባት ተምሳሌት እንደሚሆን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም