በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች በቀሰሙት እውቀት ህዝብን ለማገልገል መትጋት አለባቸው - ኢዜአ አማርኛ
በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች በቀሰሙት እውቀት ህዝብን ለማገልገል መትጋት አለባቸው
አምቦ፤ሐምሌ 26/2018(ኢዜአ)፡- በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች በቀሰሙት እውቀት ህዝብን ለማገልገል ሊተጉ እንደሚገባ የኦሮሚያ ክልል የሥራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ገለጸ።
የአምቦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በመደበኛ በተለያዩ መርሃ ግብሮች ሙያ ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 590 ተማሪዎችን አስመርቋል፡፡
በምርቃት መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል የሥራ እድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሀብታሙ ካሳ፤ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የሚመረቁ ወጣቶች በቀሰሙት እውቀት ህዝብን በማገልገል የድርሻቸውን እንዲወጡ አስገንዝበዋል።
የመማርና መሰልጠን የመጨረሻ ግቡ ችግር ፈች እና መፍትሄ አመላካች በመሆን ዜጎችን ማገልገልና ለሀገር አስተዋጽኦ ማድረግ መሆኑን አንስተው የዛሬ ተመራቂዎችም ይህንኑ ተግባር ለመፈፀም መዘጋጀት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
የአምቦ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን ሙሉነህ ተፈራ፤ ተመራቂዎች በትምህርት ቆይታቸው የተሻለ እውቀትና ክህሎት ያካበቱ መሆኑን ተናግረዋል።
በመሆኑም በቀጣይ በሚሰማሩባቸው የስራ መስኮች ሁሉ ህዝባቸውን በታማኝነት በማገልገል በኢትዮጵያ እድገትና ብልጽግና ሂደት አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ መክረዋል።
የኮሌጁ ተመራቂዎችም በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ በቅነትና በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።