የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ያስችላል - ኢዜአ አማርኛ
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ለማስረከብ ያስችላል
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 27/2018 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር ማስረከብ የሚያስችል መሆኑን ኢዜአ የነጋገራቸው የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
"ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሐሳብ ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ሲካሄድ የዋለው በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከ805 ሚሊዬን በላይ ችግኞችን በመትከል ተጠናቅቋል፡፡
ኢዜአ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለየዩ የችግኝ መትከያ ቦታዎች ቅኝት አድርጎ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንዳሉት አረንጓዴ ዐሻራ ለመጭው ትውልድ የተሻለች ሀገርን ማስረከብ ያስችላል ብለዋል፡፡
ከአስተያየት ሰጭዎች መካከል በክብካብ አስፋው፤ የአረንጓዴ ዐሻራችንን በማኖራችን ለቀጣዩ ትውልድ የለመለመች ኢትዮጵያን ማስተላለፍ ያስችላል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ሌላው በመርሃ ግብሩ ሲሳተፉ ያገኘናቸው መክብብ አበበ በበኩላቸው፤ በአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን መንከባከብ ይገባል ብለዋል፡፡
በመርሀ ግብሩ ተሳታፊ መሆን የሚያስደስት መሆኑን የገለጹት ሌላው አስተያየት ሰጭ ነጋሽ ወሌ፤ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የጎላ አበርክቶ እንዳለው አንስተዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ የተግባር እርምጃ መሆኑን የገለጹት ደግሞ አቶ ካሳሁን አህመድ ናቸው።