ቀጥታ፡

የዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ሂደት እና ‘የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ’ ኢኒሼቲቭ ትግበራ ተጠናክሮ ይቀጥላል-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ሂደት እና ‘የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ’ ኢኒሼቲቭ ትግበራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ዛሬ ስብሰባውን ማድረጉን ገልጸዋል።


 

ምክር ቤቱ በአመቱ ውስጥ እንዲፈፀሙ ያስቀመጣቸውን ተግባራት አፈፃፀም በጥልቀት በማየት አቅጣጫ ማስቀመጡን አመልክተዋል።

የብሔራዊ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤቱ አጠቃላይ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የስራ ክንውን፣ የዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ሂደት እንዲሁም ‘የ5 ሚሊየን የኢትዮጵያ ኮደርስ’ ኢኒሼቲቭ ትግበራ አፈጻጸምን ገምግሞ በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ መደረሱን ጠቁመዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢትዮጵያ በመከናወን ላይ የሚገኙ አዳዲስ የዲጂታል ስራዎች ከዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ ጋር ያላቸውን ተጣጣሚነትን በውይይታችን ተመልክተናል ሲሉ ተናግረዋል።

የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታችን በእመርታ የሚያድግበት ዘመን ላይ እንደመሆኑ፤ ምክር ቤቱም ለዚሁ ዕድገት ተገቢውን ሚና ለመወጣት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም