ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ከማጠናከር ባሻገር ትልቅ የልማት አቅም እየሆነ መጥቷል
Jul 27, 2026 9
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ከማጠናከር ባሻገር ትልቅ የልማት አቅም እየሆነ መምጣቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ። የ2018 ዓ.ም የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል። ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ ሀገራዊ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ወጣቶች ከራሳቸው አካባቢ በመውጣት ሌሎች ማህበረሰቦችን እንዲያውቁ፣ የጋራ ሀገራዊ ስሜትን እንዲያጎለብቱና የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን እንዲያጠናክሩ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። ለሶስት ሳምንታት በቆየው መርሃ ግብር ወጣት በጎ ፈቃደኞች በአራቱም አቅጣጫዎች በመንቀሳቀስ የተለያዩ ሀገራዊ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን አከናውነዋል። በዚህም የአካባቢ ጥበቃ፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የማህበረሰብ ድጋፍና ሌሎች ማህበራዊ ተግባራትን በማከናወን ለህዝብ ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ወጣቶቹ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ድልድዮች በመሆን በተለያዩ አካባቢዎች የመረዳዳትና የመተሳሰብ መንፈስን ማጠናከራቸውን ገልጸዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የወጣቶችን ጉልበት፣ እውቀትና ችሎታ በመጠቀም በመንግስትና በማህበረሰብ ያልተሸፈኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያግዝ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በሀገራዊ ምክክርና በጋራ መግባባት ሂደት ላይ በምትገኝበት ወቅት የወጣቶች ተሳትፎ የሰላምና የአንድነት ግንባታን ለማጠናከር ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል። ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ከማጠናከር ባሻገር ትልቅ የልማት አቅም እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው፤ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ ሀገራቸውን በተሻለ ለማወቅና የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎችን እውነተኛ ገጽታ ለመረዳት ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። በተለይም ለአረጋውያን፣ ለአቅመ ደካሞችና ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ያበረከቷቸው አገልግሎቶች ትልቅ እፎይታ እንዲሰማቸው እንዳደረጋቸው ጠቁመዋል። በመድረኩ ለወጣት በጎ ፈቃደኞች፣ ለክልል አመራር አባላት፣ ለጤና ቡድኖች፣ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ለመርሃ ግብሩ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ቀርቧል።
በኢትዮጵያ ዋናው የምክክር ጉባኤ ለወጣቶች የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት እየተመካከርን ነው
Jul 27, 2026 29
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋናው የምክክር ጉባኤ ለወጣቶች የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት እየተመካከሩ መሆናቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተመካካሪ ወጣቶች ገለጹ። ተመካካሪዎቹ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ከጠቅላላ መድረኮች እስከ ንዑሳን የምክክር ቡድኖች ድረስ የተካሄዱት ውይይቶች ሁሉም ተሳታፊዎች በሚገባቸው ቋንቋ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲያቀርቡ ዕድል ፈጥሯ። ይህም በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባትን ለማጠናከር ወሳኝ ዕድል የፈጠረ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል። ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጣው ተመካካሪ ወጣት አደም ሳሌ እንደገለጸው፤ የምክክሩ ሂደት ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና ሌሎች የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በስፋት ያሳተፈ አካታች መድረክ ነው። በምክክሩ የተለያዩ አስተያየቶችና ሃሳቦች ቢቀርቡም፣ በአብዛኛዎቹ የሀገር ግንባታ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እየተፈጠረ እንደሚገኝ ገልጿል። ይህም ለረጅም ዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ ሀገራዊ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግሯል። ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመጣችው ተመካካሪ ወጣት ሊዲያ ኬሮ በበኩሏ፣ ምክክሩ አካታች በሆነ መልኩ በማሳተፍ ልዩነቶችን ወደ መግባባት እየቀየረ መሆኑን ገልጻለች። የአሁኑ ትውልድ በምክክሩ ያሳየው ተሳትፎና መስዋዕትነት ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለችና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ የሚጥል ታሪካዊ እርምጃ ነው ብላለች። ከጋምቤላ ክልል የመጣው ተመካካሪ ወጣት ቾል ፑግ በበኩሉ፣ የምክክሩ ሂደት ከመጀመሪያው ጀምሮ በተደራጀና በአካታች መልኩ መካሄዱንና፣ የተሳታፊዎች የጋራ ውይይት ለሀገር ግንባታ የጋራ ኃላፊነትን ለማጎልበት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጿል። ችግሮችን በመወያየትና የጋራ መፍትሔ በማፈላለግ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እንደሚቻልም ነው የተናገረው። ከድሬዳዋ የመጣው ተመካካሪ ወጣት አሕመድ ሁሴን በበኩሉ፣ በሀገራዊ ምክክሩ መሳተፉ የሀገሪቱን ችግሮች በጋራ ለይቶ በመወያየት ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ በሚደረገው ታሪካዊ ጥረት አካል ነው ብሏል። ችግሮቻችንን በጋራ ለይተን በመወያየት ተግባራዊ መፍትሔ የሚያስቀምጥ ውጤታማ ምክክር እየተደረገ በመሆኑ ጥሩ ውጤት ይመጣል ሲል ገልጿል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የቆዩ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት፣ የጋራ ራዕይ ለመገንባት፣ የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ለማጠናከርና ለቀጣይ ትውልድ የተረጋጋች፣ የተባበረችና ሰላማዊት ኢትዮጵያን ለማሸጋገር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስተያየት የሰጡት ተመካካሪች ገልጸዋል።
ቱሪዝም - የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ በኢትዮጵያ!!
Jul 27, 2026 66
በቤተልሔም ባህሩ መግቢያ፡- ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ሥልጣኔ መነሻ፣ የታሪክ መዝገብና የቱባ ባህል ሀብት ካስማ ምድር መሆኗ የአደባባይ ሃቅ ነው። የሺህ ዓመታት ታሪኮች፣ በዘመናት የተገነቡ ዕድሜ ጠገብ የሕንፃ አሻራዎች፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ ባህላዊ እሴቶችና በዓላት ኢትዮጵያን በዓለም የቱሪዝም ካርታ ላይ ልዩ ስፍራ የሚያስይዙ መለያ ምልከቶቿ ናቸው። እንደ የአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የአልነጃሺ መስጂድ፣ የሐረር ጀጎል እና የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ያሉ ታሪካዊ ቅርሶች የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የሃይማኖታዊ ትውፊትና የአርክቴክቸር ብልጽግና ሕያው ምስክሮች ናቸው። በተጨማሪም መስቀል፣ ጥምቀት፣ የገዳ ሥርዓት፣ አሸንዳ/አሸንድዬ፣ ኢሬቻ፣ ፊቼ ጨምበላላ እና ጊፋታ የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላትም ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳቡ የማይዳሰሱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች የሚያንጸባርቁ የኢትዮጵያ ውድ ሃብቶች ናቸው። እነኝህ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶች በዓለም አቀፍ ዕውቅናም የተቸራቸው ናቸው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 16 የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ማስመዝገብ ችላለች። በቅርቡ የተመዘገቡት የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የሐረር ሸዋል ኢድ ኢትዮጵያ ለዓለም ህዝብ ያበረከተቻቸው አዳዲስ የመስህብ ትሩፋቶች ናቸው። እነዚህ ቅርሶች የኢትዮጵያን ገጽታ በዓለም ላይ ከማጉላት ባሻገር በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን በመሳብ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በብዝኅ ተፈጥሮ፣ ታሪክና ባህል የታደለች ሀገር ብትሆንም ለረጅም ጊዜ እነዚህን ዕምቅ ሃብቶች በዘመናዊ የቱሪዝም አቀራረብ ለማልማት፣ ለዓለም አቀፍ ገበያ በብቃት ለማስተዋወቅና ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመቀየር የሚገባውን ያህል ትኩረት ሳይሰጣቸው ቆይቷል። በመሆኑም የቱሪዝም ዘርፍ የሀገሪቱን እውነተኛ አቅም በሚመጥን ደረጃ መጠቀም ሳይቻል ቆይቷል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በኢትዮጵያ በተተገበረው ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ አምድ እንዲሆን በመደረጉ ልዩ ትኩረት አግኝቷል። ይህም ዘርፉ ከተለምዷዊ አካሄድ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ልማት፣ ወደ ከፍተኛ ተወዳዳሪነትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚሸጋገርበትን መሰረት ጥሏል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተተገበሩት "የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ለውጥ ወሳኝ ምዕራፍ ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች በተፈጥሮ፣ በታሪክና በባህል የታደሉ ስፍራዎችን በዘመናዊ መንገድ በማልማት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ማራኪ መዳረሻዎችን መፍጠር ችለዋል። በዚህም የጎብኚዎች ፍሰት ጨምሯል፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት አድጓል፣ የየአካባቢዎቹ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተነቃቅተዋል፣ የኢትዮጵያም የቱሪዝም ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ መልክ እያገኘ መጥቷል። ዛሬ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጫ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ምንጭ፣ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ ዋና ሞተር በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ኢትዮጵያ፤ በአፍሪካ ቀዳሚ የዓለም ቅርሶች ማዕከል ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከ16 በላይ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ያስመዘገበች በአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናት። ከሚዳሰሱት ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የፋሲል ግቢና የጎንደር ቤተ መንግስት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የታችኛው ኦሞና የአዋሽ ሸለቆዎች፣ የሐረር ጁገል ግንብ እንዲሁም የባሌና የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮች ይገኙበታል። ከማይዳሰሱት ቅርሶች ደግሞ የመስቀል ደመራ በዓል፣ የጥምቀት በዓል፣ የፊቼ ጨምበላላና የገዳ ሥርዓት ተጠቃሽ ናቸው። ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት እነዚህን ዓለም አቀፍ ቅርሶች በተሻለ ሁኔታ የመጠበቅና የማደስ ሥራዎች የሚሰሩበትን ዕድል ፈጥሯል። በተመሳሳይም አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት ኢትዮጵያን ይበልጥ ተወዳዳሪና ማራኪ የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ የሚያስችል ሰፊ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። ሶስቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ገበታ ለሸገር - የአዲስ አበባን ገጽታ የቀየረ የለውጥ ጥንስስ!! የገበታ ለሸገር መርሃ ግብር የአዲስ አበባን የከተማ ገጽታ በመቀየር የቱሪዝም ስበት ማዕከልነቷን ያጎለበተ የለውጥ ምዕራፍ ነው። በመርሃ ግብሩ የተገነቡት የእንጦጦ፣ የአንድነትና የወዳጅነት ፓርኮች፣ የሳይንስ ሙዚየምና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከተማዋን ከዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ ባሻገር ዓለምአቀፍ የኮንፍረንስ ቱሪዝምና የመዝናኛ ጉብኝት ማዕከል እንድትሆን መሠረት ጥለዋል። ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ የተተገበሩት የከተማ ኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ለበርካታ ዓመታት ችላ የተባሉ ስፍራዎችን ወደ አረንጓዴ፣ ዘመናዊ እና ለሁሉም ተደራሽ የመዝናኛ ከባቢነት ቀይረዋል። ይህም ከተማዋን ለጎብኚዎች ይበልጥ ማራኪ ከማድረጉ በተጨማሪ ለነዋሪዎች ጤናማ፣ ንጹህና ምቹ የከተማ ምኅዳር መፍጠር አስችሏል። ገበታ ለሸገር የአዲስ አበባን የከተማ ውበት በማሳደግ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትና የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን በማበራከት የቱሪዝም ዕድገትን ያፋጠነ ብቻ ሳይሆን፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ያሻሻለና የዘመናዊ ከተማ ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስኬታማ ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር - ከገበታ ለሸገር የተቀዳ የሀገር በረከት!! ገበታ ለሀገር መርሃ ግብር በገበታ ለሸገር የተጀመረውን የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ወደ መላው ሀገር በማስፋት፣ በየክልሉ የሚገኙ ዕምቅ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶችን ወደ ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎች የቀየረ ትልቅ የልማት ፕሮጀክት ነው። በዚህ ማዕቀፍ የወንጪ ኢኮ ቱሪዝም፣ የጎርጎራ፣ የኮይሻና ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶች በመገንባታቸው የክልሎችን የቱሪዝም አቅም በእጅጉ በማሳደግ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች አዳዲስና ማራኪ የጉብኝት መዳረሻዎችን ፈጥረዋል። በተመሳሳይም ፕሮጀክቶቹ በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ሥርጭት እንዲፈጠር በማድረግ፣ የመንገድ፣ የመስተንግዶ፣ የመዝናኛና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች በስፋት እንዲገነቡ አስችለዋል። ይህም የቱሪዝም ጥቅም በተወሰኑ ከተሞች ብቻ እንዳይገደብ በማድረግ፣ የአካባቢ ኢኮኖሚን በማነቃቃት፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና የክልሎችን የልማት ተጠቃሚነት በማሳደግ የቱሪዝም ዕድገትን ወደ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ የቀየረ ውጤታማ ፕሮጀክት ሆኗል። ገበታ ለትውልድ - የቱሪዝም ልማትን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ያሸጋገረ የአገልግሎት ዘርፍ እመርታ!! ገበታ ለትውልድ መርሃ ግብር በገበታ ለሸገርና ገበታ ለሀገር የተጀመረውን የቱሪዝም ልማት በማስቀጠል፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት ከመጠበቅ ጋር በማጣጣም ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት ያስቻለ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። መርሃ ግብሩ የቱሪዝም ልማትን ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር ለትውልድ የሚተርፍ ሃብት የመጠበቅ እሳቤ ጋር አሰናስሎታል። በዚህ ማዕቀፍ በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርትን ጨምሮ፣ የሸበሌ፣ የሎጎ ሐይቅ ሪዞርቶችና የሀሮ ደንዲ ኢኮ ሎጅ ተጠናቀው ወደ ሥራ ገብተዋል። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገነቡና እየተገነቡ የሚገኙ ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ የልማት ሥራዎችም ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ አቅም ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች በማስፋፋት፣ አገልግሎትን ወደ ዓለምአቀፍ ደረጃ በማሳደግና የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም በኩል ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው። በተመሳሳይም ለአካባቢያዊ የኢኮኖሚ መነቃቃት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ በማሳለጥም ገንቢ ሚና እየተወጡ ይገኛል። የኮሪደር ልማትና አዳዲስ የቱሪዝም ትስስሮች በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ተጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እየተስፋፋ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበት እያፈካ ይገኛል። በዚህም የከተሞችን መሠረተ ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራን፣ የመዝናኛና የእግረኛ መንገዶችን በስፋት በማልማት ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ የከተማ ምኅዳር ፈጥሯል። ይህ ልማት የከተሞችን ውበት ከማሳደግ ባለፈ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማትን በማጠናከር፣ የጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘምና የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ዘርፉን ወደ ከፍተኛ የዕድገት ምዕራፍ አሸጋግሯል። የኮንፍረንስ ቱሪዝም (MICE) የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ውብ፣ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ከተማ በማድረግ፣ የአፍሪካ ኅብረትና የበርካታ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን ከተማ ወደ ቀዳሚ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ቀይሯታል። አዲስ ዓለም ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የሳይንስ ሙዚየምና ሌሎች ዘመናዊ መዳረሻዎች በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ተቋማትን በማፍራት ከተማዋን ለሀገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች፣ ኤግዚቢሽኖችና ትላልቅ የንግድ መድረኮች ተመራጭ አድርጓታል። ለአብነትም የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ፣ የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) እና መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮችን በብቃት ማስተናገድ ተችሏል። በተለይም የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም እንዲያስተዋውቁ ምቹ መድረክ ፈጥሯል። ይህም የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ገጽታ ከማጎልበት ባለፈ የቱሪዝም ማስተዋወቅን በዲጂታል ዘመን ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግሮታል። የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም መርሃ ግብርም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም በአዲስ አበባ የሚያልፉ ትራንዚት መንገደኞችን ከመሸጋገሪያነት ብቻ ወደ ጎብኚነት ለመቀየር አስፈላጊ ዕድል ፈጥሯል። በዚህም መዲናዋን ከቱሪስት መሸጋገሪያነት ወደ ቱሪዝም ማዕከልነት ቀይሯታል። በከተማዋ የተከናወነው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማትም ውብና ማራኪ የከተሜነት ገጽታን በመፍጠር፣ መንገደኞች በቆይታቸው የተለያዩ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ዘመናዊ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ አስችሏል። ይህም የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ከማራዘም ባለፈ፣ የመስተንግዶ፣ የትራንስፖርት፣ የባህልና የንግድ አገልግሎቶችን በማነቃቃት ለሀገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲፈጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶች በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል። በዚህም ከታሪካዊ ቅርሶች ባሻገር የባህል፣ የተፈጥሮ፣ የኢኮ ቱሪዝምና የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋፋት፣ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በተሻለ ሁኔታ እንድትጠቀም መንገድ ከፍተዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎች መስፋፋት የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር ከማሳደጉ ባለፈ የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲጠናከር በማድረግ ዜጎች የሀገራቸውን ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሯዊ ጸጋዎች እንዲያውቁና እንዲጎበኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ይህም የቱሪዝም ገቢን በማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ምንጭን በማስፋፋትና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጨምረውን አስተዋጽኦ ከፍ አድርጎታል። በተጨማሪም ዘርፉ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አበርክቶ እያስገኘ ነው። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በኢኮ ቱሪዝም፣ በባህል ውጤቶች ንግድና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች በመሳተፍ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል ፈጥሯል። በመሆኑም ቱሪዝም ከመዝናኛ ዘርፍ ባሻገር የልማት፣ የሥራ ዕድልና የኢኮኖሚ ለውጥ ማስፈንጠሪያ ምሰሶ እየሆነ መጥቷል። ማጠቃለያ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ሃብቶቿን ከዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ጋር በማስተሳሰር፣ በኮሪደር ልማት፣ በተሻሻለ የአገልግሎትና በዓለም አቀፍ የማስተዋወቅ ስራዎች በቱሪዝም ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እየጻፈች ትገኛለች። የተቀናጀው የልማት አቅጣጫ ሀገሪቱ ለዘመናት የያዘቻቸውን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም፣ የሥራ ዕድልና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ እየቀየረ ይገኛል። ዛሬ ቱሪዝም የኢኮኖሚ አንድ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል፣ የባህልና ታሪክ መዳረሻ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ሀገር ለማድረግ የሚያግዝ ስትራቴጂያዊ አቅም ሆኗል። ይህም ለሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ገጽታ፣ የባህል ትስስርና የዓለም አቀፍ ተሳትፎ አዲስ ዕድል ፈጥሯል። በተለይም የዲጂታል ዘመን የቱሪዝም ዘርፉን ለማስተዋወቅ ዕድሎችን የሚያሰፋ በመሆነኑ ይህንኑ በመጠቀም፣ እንደ አይሾ ስፒድና ዲላን ፔጅ ያሉ ዓለም አቀፍ ተከታይ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን ውብ ተፈጥሮ፣ ባህልና ታሪክ ለዓለም በማስተዋወቅ የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ትኩረት እያሳደጉ ናቸው። በመሆኑም ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ከጉብኝት ዘርፍ ባሻገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሀገር ገጽታ ግንባታና የዓለም አቀፍ ትስስር መሣሪያ በማድረግ ወደ አዲስ የቱሪዝም ዘመን እየተሸጋገረች ትገኛለች። ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ፤ የኢትዮጵያ አዲሱ የብልፅግና ዘመን የኢኮኖሚ መሰሶነቱን በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል።
በክልሉ የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ለማጠናከር በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል
Jul 27, 2026 82
ሆሳዕና ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላም እሴቶችን በመጠቀም የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ለማጠናከር በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው "ብዝሀነትና የሰላም እሴታችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ሀሳብ ከሀይማኖት ተቋማት መሪዎችና የባህል ሽማግሌዎች ጋር የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል። የቢሮው ምክትልና የሰላም ግንባታና ብዝሃነት አያያዝ ዘርፍ ሀላፊ አቶ እንዳለ ወልደአማኑኤል በመድረኩ እንደገለጹት፤ የክልሉን ሰላም አስጠብቆ ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው፡፡ ለዘመናት የዳበሩ ቱባ ዕሴቶች የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ለማጠናከርና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ለዚህም ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓትን በጥናት ላይ በተደገፈ መልኩ የማጠናከር ጨምሮ ሰላምን ጠብቀው የሚያስቀጥሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል ። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የየም ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ገብረ ሚካኤል መንግስቴ፤ የህዝቦች አብሮነት መጠናከር ለአካባቢው ፈጣን እድገት መረጋገጥ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። ለዚህም አብሮነትን በሚያጠናክሩና ለዘላቂ ሰላም ግንባታው መሰረት የሚጥሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙና ተግባሩን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ገልጸዋል። በክልሉ የተጀመሩ ትልልቅ የልማት ስራዎች እንዲሳለጡና እንዲጠናከሩ ሰላምን ማስጠበቅና አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባ ያነሱት ደግሞ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ኡስታዝ ሼህ በኸጃ አብድልጀሊል ናቸው። ምክር ቤቱ የክልሉን ህዝቦች አብሮነትን በማጠናከር ለጋራ ተጠቃሚነት መረጋገጥ አበክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል። ሰላምን ማስጠበቅ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አይተኬ ሚና እንደሚጫወት የተናገሩት ደግሞ የሀድያ ባህል ሽማግሌ ዳኛ ብርሃኑ ጡሞሮ ናቸው። ባህላዊ እሴቶችን በመጠቀም ሰላምን ጠብቆ በማስቀጠልና የህዝቦችን አብሮነት በማጎልበት የልማት ስራዎችን ለማጠናከር በሚከናወኑ ተግባራት ሚናቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለችው አስተዋፅኦ የሚደነቅ ነው
Jul 27, 2026 125
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጀነራል ዳግቪን አንደርሰን ኢትዮጵያ ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት እያበረከተች ያለችውን አስተዋፅኦ አደነቁ። የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጀነራል ዳግቪን አንደርሰን የተመራውን የአፍሪኮም ልዑክ በቢሯቸው ተቀብለው ተወያይተዋል። በውይይታቸው ላይም በአፍሪካ የአሜሪካ ዕዝ (አፍሪኮም) አዛዥ ጀነራል ዳግቪን አንደርሰን ከኢትዮጵያ ጋር ያለው የመከላከያ ትብብር በተለያዩ ዘርፎች እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል። ይህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ የመከላከያ አጋርነትና የጋራ ቁርጠኝነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን አስታውቀዋል። የትብብር መስኮችን ማስፋት፣ በሶማሊያ አልሸባብንና አይኤስ አይኤስን ጨምሮ በሽብርተኝነት ላይ የሚደረገውን ትግል ማጠናከር እንዲሁም ወደፊት ያሉ የትብብር ዕድሎችን መለየት ዋና የውይይቱ አጀንዳዎች እንደነበሩም ጀነራል ዳግቪን አንደርሰን ገልጸዋል። ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ኢትዮጵያ እያበረከተች ያለችውን አስተዋፅኦ ያደነቁት ጀነራል መኮንኑ፣ ከኢትዮጵያ ጋር በጋራ የአፍሪካ የሎጂስቲክስና የኮሙኒዩኬሽን ሲምፖዚየምን ማዘጋጀት መቻላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የመከላከያ ትብብር የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ መሆኑን ጠቁመዋል። የሁለቱ ወዳጅ ሀገራት ግንኙነት ከጋራ ወታደራዊ ተልዕኮዎች ባሻገር ዘላቂና ዘመናዊ የመከላከያ አቅምን በመገንባት ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ በአህጉሪቱ ያሉ የደህንነት ተግዳሮቶችን በጋራ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነትም እንደሚያሳይ ጠቁመዋል። የጉብኝታቸው ዋና ዓላማ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ መከላከያ ሠራዊት ጋር በመተባበር የአፍሪካ የሎጂስቲክስና የኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየምን ማካሄድ መሆኑን ገልጸዋል። ሲምፖዚየሙ ልምድ ለመለዋወጥ፣ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ለማስተዋወቅ፣ ከንግድ ዘርፉ ጋር ትብብርን ለማሳደግና የአፍሪካ የመከላከያ ተቋማትን አቅም ለማጠናከር ጠቃሚ መድረክ መሆኑንም አስታውቀዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ የአህጉሪቱን ሀገራት በአንድ መድረክ በማሰባሰብ የጋራ የደህንነት ችግሮችን ለመፍታት ያላትን የአመራር ሚና እያሳየች መሆኑን ገልጸዋል። የመከላከያ የውጭ ግንኙነትና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክትሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ተሾመ ገመቹ በበኩላቸው፣ ውይይቱ ፍሬያማና በኢትዮጵያና በአሜሪካ መካከል ያለውን የረጅም ጊዜ ወዳጅነትና የመከላከያ ትብብር የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። በውይይቱ ላይ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን ጨምሮ የሁለቱ አገራት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች መሳተፋቸውን ከመከላከያ ኦንላይን ሚዲያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ።
ፖለቲካ

በሶማሌ ክልል በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት ተከናውነዋል
Jul 27, 2026 101
ጅግጅጋ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦በሶማሌ ክልል በተጠናቀቀው በጀት አመት በሰላም፣ በልማትና በመልካም አስተዳደር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ተግባራት መከናወናቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ አስታወቁ። የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ አመት 11ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ የክልሉ መንግሥትን የ2018 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ ርዕሰ መስተዳድሩ ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት እንደገለጹት፤ በክልሉ በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፎች ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል ። በተለይም በሰላምና በልማት እንዲሁም በመልካም አስተዳደር ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል ። በክልሉ በማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች በድህነት ቅንሳ፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንዲሁም በተፈጥሮና በሰው ሠራሽ የሚመጡ አደጋዎች ቅነሳ ከፍተኛ ሥራዎች መከናወናቸውን አንስተዋል። በክልሉ የህግ የበላይነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት አበረታች መሆናቸውን ጠቁመው የፍትህ አካላትን አቅም ለመገንባት በተደረገ ጥረት የፍትህ ሂደቱ የተሳለጠ እንዲሆን አስችሏል ሲሉ አመልክተዋል።
ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትብብርን በማጠናከር ለአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ገንቢ ሚናዋን እየተወጣች ነው
Jul 27, 2026 123
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ትብብርን በማጠናከር ለአፍሪካ ሰላምና ደህንነት ገንቢ ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን ሩዋንዳዊያን መኮንኖች ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ ያሰለጠናቸውን 71ኛ ዙር መተማ ኮርስ ዕጩ መኮንኖችን አስመርቋል። አካዳሚው ከኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት የመጡ አፍሪካውያን ዕጩ መኮንኖችንም አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል ሩዋንዳዊቷ ምክትል መቶ አለቃ ኔገና ሉሲ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በአካዳሚው የንድፈ-ሐሳብና የተግባር ትምህርትና ስልጠና አግኝተዋል። ኢትዮጵያ በኮሪያ ጦርነት፣ በሩዋንዳ እና በሌሎች አፍሪካ ሀገራት በነበራት የሰላም ማስከበር ተልዕኮ ደማቅ ታሪክ ማስመዝገቧን ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ መከላከያ ትምህርትና ስልጠና የላቀ ብቃት ባላቸው ባለሙያዎች የሚሰጥ መሆኑን በማንሳት፤ ለአፍሪካ ቀንድና ለአህጉራዊ ቀጣናዎች ሰላምና ደህንነት ገንቢ ሚና እየተወጣች መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሌላኛው ሩዋንዳዊ ምክትል መቶ አለቃ ፍሬሞትዋ ሂርዋ፤ በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ በብቃት መወጣት የሚያስችል የንድፈ ሃሳብና የተግባር ስልጠና ማግኘታቸውን ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመከላከል ለዓለም ሰላምና ደህንነት እየሰራች መሆኑን ገልጸው፤ ለአፍሪካ ሰላምና መረጋጋት ግንባር ቀደም ተሰላፊ መሆኗንም ተናግረዋል፡፡ ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ የሀገራት ትብብር ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ በኢትዮጵያ ወታደራዊ አካዳሚ መሰልጠናቸው ሀገሪቱ ለቀጣናዊ ሰላምና ደህንነት የምታደርገውን ትብብር ያሳያል ብለዋል፡፡
ሀገራዊ ምክክሩ የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ማሳለጫና የጋራ አሸናፊነት ማብሰሪያ ነው
Jul 27, 2026 149
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-ሀገራዊ ምክክሩ የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ማሳለጫና የጋራ አሸናፊነት ማብሰሪያ መሆኑን የምክክር ጉባኤው ተመካካሪ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገር ውስጥና በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያንን በማወያየት ምክክር የሚደረግባቸው ስምንት አጀንዳዎችን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል። በዚህም አራት ሺህ ተመካካሪዎች በአዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል ምክክር እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት አቶ አሕመድ ሁሴን ለኢዜአ እንዳሉት፤ ምክክሩ አንዱ የሌላውን ፍላጎት እና አተያይ በአግባቡ እንዲረዳ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ምክክሩ ዜጎች ፍላጎታቸው ማስረዳት የሌሎችን ሀሳብ መስማት የሚችሉበትን የጋራ መድረክ ፈጥሯል ብለዋል። ጉባኤው ለሀገር ግንባታ ገንቢና ጠቃሚ ሀሳቦች የሚነሱበት በኢትዮጵያ አዲስ ባህል እና ልምምድ መሆኑንም ገልጸዋል። በዜጎች መካከል መተማመንን መፍጠር የሚያስችል አሳታፊ እና አካታች ጉባኤ በመሆኑ ለሀገረ መንግስት ግንባታ የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል ብለዋል። የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ኅብረት ዳይሬክተር አቶ መስዑድ ገበየሁ፤ የሀገራዊ ምክክር ጉባዜ ለዘመናት የቆዩ ስር የሰደዱ ችግሮችን ለመምታት ትልቅ እርምጃና ስኬት መሆኑን ገልጸዋል። ኅብረቱ ከአስር በላይ ታዛቢዎችን በማሰማራት በጉባኤው የብዙሃን ማኅበረሰብ ተወካዮች በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ በንቃት ሀሳብ ሲያንሸራሽሩ መታዘቡን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከመላው ኢትዮጵያ የተወከሉ ተመካካሪዎች ሀሳባቸውን በቋንቋቸው በነጻነት መግለጽና ማዳመጥ የሚችሉበት አስተርጓሚዎችን ማሰማራቱን ገልጸዋል። የተመካካሪዎች ንቁ ተሳትፎ በአጀንዳዎቹ ላይ የጋራ ፖለቲካዊ መግባባት በመፍጠር ተቋማዊ መፍትሔ ለማመንጨት የጎላ ሚና ይኖረዋልም ብለዋል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ፌደሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ ወጣት ዮሴፍ አበራ በበኩሉ፤ በምክክር ጉባኤው ተሳትፎው የተለያዩ ልምድና ተሞክሮ ማግኘቱን ገልጿል። በምክክር ጉባኤው የኢትዮጵያን ከፍታ የሚያረጋግጡ ሀሳቦች እየመነጩ መሆኑን በመግለጽ፤ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ማሸጋገር የሚያስችል ስኬት እንደሚመዘገብ ተስፋ አለኝ ብሏል።
በዲፕሎማሲ ዘርፍ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ ወጣቶችን ማፍራት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ነው
Jul 27, 2026 199
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-በዲፕሎማሲ ዘርፍ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስጠብቁ ወጣቶችን ማፍራት የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ገለጸ። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ሁለተኛ ዙር የአንድ ወር የክረምት የዲፕሎማሲ ሥልጠና (Summer Camp) የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት እንዳስታወቀው፣ በፍጥነት እየተለዋወጠና እየተወሳሰበ በመጣው ዓለም ውስጥ የዲፕሎማሲ ብቃትና ክህሎት ያለው የሰው ኃይል ማፍራት አስፈላጊ ነው። በኢንስቲትዩቱ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ዋና ዳይሬክተርና የዋና ዳይሬክተሩ ጽሕፈት ቤት ጊዜያዊ ኃላፊ ግዛቸው አስራት (ዶ/ር)፤ ሥልጠናው ወጣቶች በፍጥነት እየተሳሰረና እየተወሳሰበ በመጣው ዓለም በራስ መተማመን እንዲሳተፉ፣ ወሳኝ የትንተና አስተሳሰብ፣ የባህል ተሻጋሪ የመግባቢያ ክህሎት፣የአመራር ብቃትና የችግር ፈቺ ክህሎት እንዲያገኙ ለማብቃት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው አስገንዝበዋል። ኢንስቲትዩቱ በወጣቶች ላይ በቀጣይነት ኢንቨስት በማድረግ፣በሀገራዊ፣ በቀጣናዊና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ትርጉም ያለው አስተዋጽኦ የሚያበረክት አዲስ ትውልድ ለማፍራት በቁርጠኝነት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። በቀጣይም ወጣት ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማቶች በሀገራዊ፣በአህጉራዊና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የሚያስችሉ መድረኮችን የመፍጠር ሥራ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ሥልጠናው የዕውቀትና የአመራር ክህሎትን ለማጎልበት፣በመረጃ ላይ የተመሠረተ ተሳትፎን ለማበረታታትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን የሚመጥን ትውልድ ለመገንባት እንደሚያግዝም ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት የተካሄደው የመጀመሪያ ዙር የክረምት ሥልጠና፣ ተሳታፊዎች ሙያዊ ትስስር እንዲፈጥሩና ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ስላላት ሚና ሰፊ ግንዛቤ እንዲያገኙ ዕድል መፍጠሩንም አስታውሰዋል። በዘንድሮው ሥልጠና የፖሊሲ ውይይቶች፣ የድርድር ልምምዶች፣ ከታዋቂ ዲፕሎማቶች፣ ምሁራንና የፖሊሲ አውጪዎች ጋር የሚደረጉ ውይይቶች ከሥልጠናው ዋና ዋና ተግባራት መካከል እንደሚገኙም ጠቅሰዋል። በኢንስቲትዩቱ የባለድርሻ አካላት ሥልጠናና አማካሪ አገልግሎት ጊዜያዊ ዋና ዳይሬክተር መላኩ ሙሉዓለም፤ ኢንስቲትዩቱ በጥልቅ ምርምር፣ በስትራቴጂያዊ ትንበያና የዲፕሎማሲ አቅምን በማጎልበት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም ለማገልገል እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል። በሁለተኛው ዙር የክረምት ሥልጠና፣ ከዓለም አቀፍ ግንኙነትና ከውጭ ፖሊሲ ጋር የተያያዙ ከ10 በላይ የሥልጠና ርዕሶች መካተታቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ማዕከል እንደመሆኗ፣ ይህ ለአንድ ወር የሚቆይ ሥልጠና ወጣቶች ስለ ዲፕሎማሲ ያላቸውን ዕውቀት በተግባር የሚያጎለብት መሆኑን ገልጸዋል። ከሥልጠናው በኋላም ወጣቶች ከኢንስቲትዩቱ ጋር በተለያዩ መርሃ ግብሮች የሚሳተፉባቸው ዕድሎች እንደሚኖሩ አክለዋል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በቀጣናዊና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ያላት ሚና እየጎለበተ በመምጣቱ፣ የኢንስቲትዩቱም ኃላፊነትና ሚና እያደገ መምጣቱን ገልጸዋል። በዚህ ዓመት ሥልጠናውን የሚቀላቀሉት ሠልጣኞችም፣ የኢትዮጵያን የውጭ ፖሊሲ ስትራቴጂያዊ አስተሳሰብ በመቅረጽ ከፍተኛ ኃላፊነት የተጣለበት ተቋም አካል እንደሚሆኑ አስገንዝበዋል።
አሜሪካ አጋርነትን በማጠናከር በአፍሪካ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ ናት
Jul 27, 2026 185
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦አሜሪካ አጋርነትን በማጠናከር በአፍሪካ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ጉዳዮች ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኗን በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገለጹ። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) ጋር በመተባበር ያዘጋጀችውና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የተሳተፉበት የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 25 ቀን በሚካሄደው ሲምፖዚየም፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂንና የሎጂስቲክስ አቅምን በማሳደግ የአህጉሪቱን የጸጥታ ተግዳሮቶች በጋራ መቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጓል። በሲምፖዚየሙ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን፣ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናንት ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል፣ የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖችና የአፍሪካ ሀገራት የጦር መሪዎች ታድመዋል። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካን የፀጥታና ደኅንነት ተግዳሮቶች ለመግታት በአህጉሪቷና በዓለም አቀፍ አጋሮች መካከል ጠንካራ ትብብርን መገንባት ያስፈልጋል። ሲምፖዚየሙም በአፍሪካና በአሜሪካ መካከል ዘላቂ አጋርነትን በመገንባት ተቋማትን ለማጠናከር፣ ወታደራዊ ትምህርትን ለማስፋፋትና ዘላቂ የመከላከያ ኢኮኖሚን ለማበረታታት እንደሚያስችል ገልጸዋል። አሜሪካም ለአፍሪካ ሀገራት የምታደርገውን የመከላከያ ድጋፍ በማጠናከር ዘላቂ ወታደራዊ ዝግጁነትን ለማጎልበት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል። የአፍሪካ ወታደራዊ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን መጎልበትም የዜጎችን ሁለንተናዊ ደኅንነት በማስጠበቅ አህጉራዊ ንግድና ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል። በዚሁ መሰረትም ጠንካራ ወታደራዊ ዝግጁነትና ትብብርን በማጎልበት ሽብርተኝነትን፣ ሕገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የሳይበር ጥቃትንና ግጭቶችን በጋራ መመከት እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል። የሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም በመንግሥትና በወታደራዊ ተቋማት፣ በሀገራትና በመንግሥታት፣ እንዲሁም በመንግሥትና በግሉ ዘርፍ መካከል ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክር ጠቁመዋል። ተሳታፊዎችም ውይይቶችን ወደ ተጨባጭ አቅም የሚቀይር ምክክር እንዲያደርጉ ጥሪ በማቅረብ፤ ሲምፖዚየሙ እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የአፍሪካን የፀጥታና ደኅንነት ተግዳሮቶች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ወታደራዊ ዝግጁነትን የሚያጠናክር ጠንካራ የሎጂስቲክስና ተናባቢ የኮሚዩኒኬሽን አቅም መገንባት ያስፈልጋል
Jul 27, 2026 166
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካን የፀጥታና ደኅንነት ተግዳሮቶች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ወታደራዊ ዝግጁነትን የሚያጠናክር ጠንካራ የሎጂስቲክስና ተናባቢ የኮሚዩኒኬሽን አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገለጹ። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) ጋር በመተባበር ያዘጋጀችውና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የተሳተፉበት የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 25 ቀን በሚካሄደው ሲምፖዚየም ዘመናዊ ቴክኖሎጂንና የሎጂስቲክስ አቅምን በማሳደግ የአህጉሪቱን የጸጥታ ተግዳሮቶች በጋራ መቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጓል። በሲምፖዚየሙ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፤ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን፣ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናንት ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል፣ የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖችና የአፍሪካ ሀገራት የጦር መሪዎች ታድመዋል። የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያ መድረኩን ለማስተናገድ መመረጧ ለአህጉራዊ ሰላምና መረጋጋት ያላትን ገንቢ ሚና የሚያስመሰክር ነው። የ2026 የአፍሪካ የሎጂስቲክስና የኮሚዩኒኬሽን ሲምፖዚየም ማካሄዱም የኢትዮጵያና አሜሪካን ስትራቴጂክ አጋርነት የሚያንጸባርቅ መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባን የልማት ውጤቶች ከማስገንዘብ ባሻገር መዲናዋ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉባኤዎችን በብቃት የማስተናገድ አቅም እንዳላት በተግባር የሚያረጋግጥ ጭምር መሆኑንም ተናግረዋል። የአፍሪካን የፀጥታና ደኅንነት ተግዳሮቶች አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠትም ወታደራዊ ዝግጁነትን የሚያጠናክር ጠንካራ የሎጂስቲክስና ተናባቢ የኮሙዩኒኬሽን አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። የሲምፖዚየሙ የቴክኒካዊ ውይይቶችም አህጉራዊ ትብብርን በማጠናከር፣ ልምድና ተሞክሮ በመለዋወጥ የደኅንነት ተግዳሮቶችን መመከት የሚያስችሉ ተቋማትን ለመገንባት ወሳኝ ናቸው ብለዋል። በትብብርና በፈጠራ ወታደራዊ ዝግጁነትን ማሳደግ፣በሰራዊቶች መካከል ያለውን ተናባቢነት ማጠናከር የሲምፖዚየሙ ዓላማ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሲምፖዚየሙ ለአህጉሪቱ ሰላም፣ ደኅንነትና ዘላቂ ልማት የጋራ አቅም የሚፈጥር መሆኑን በመጠቆም፤ተሳታፊዎችም የወደፊቱን የደኅንነት ፍላጎቶች ታሳቢ ያደረገ ፍሬያማ ውይይት እንዲያካሂዱ ጥሪ አቅርበዋል።
የአፍሪካን ደኅንነትና መረጋጋት ለማረጋገጥ ወታደራዊ ሎጂስቲክስና የኮሙኒኬሽን አቅም መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው
Jul 27, 2026 216
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-የአፍሪካን ደኅንነትና መረጋጋት ለማረጋገጥ ወታደራዊ ሎጂስቲክስና የኮሙኒኬሽን አቅም መሰረታዊ ጉዳዮች መሆናቸውን የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን ገለጹ። ኢትዮጵያ ከአሜሪካ አፍሪካ ዕዝ (AFRICOM) ጋር በመተባበር ያዘጋጀችውና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የተሳተፉበት የአፍሪካ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ሲምፖዚየም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሐምሌ 25 ቀን የሚቀጥለው ሲምፖዚየም ዘመናዊ የቴክኖሎጂና የሎጂስቲክስ አቅምን በማሳደግ የአህጉሪቱን የጸጥታ ተግዳሮቶች በጋራ መቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ትኩረት ያደረገ ነው። በሲምፖዚየሙ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ፣ የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን፣ የመከላከያ ሎጂስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጄኔራል አብዱራህማን እስማኤል፣ የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖችና የአፍሪካ ሀገራት የጦር መሪዎች ታድመዋል። የአሜሪካ የአፍሪካ ዕዝ አዛዥ ጄኔራል ዳግቪን አር ኤም አንደርሰን በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ማንኛውንም ወታደራዊ ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት ወሳኝ ነው ብለዋል። የሎጂስቲክስና ኮሙኒኬሽን ኢንቨስትመንት ዘመናዊ የመከላከያ ቴክኖሎጂ ውጤታማነትን ለማጎልበት ጎልህ ፋይዳ እንዳለውም ገልጸዋል። በአፍሪካ የሽብርተኝነት፣ሕገ-ወጥ ዓሣ ማጥመድ፣ ማዕድን ማውጣት፣ የሰዎችና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውር እየጨመረ መምጣቱን አስረድተዋል። የአህጉሪቷን መሰል ተግዳሮቶች ለመቋቋም በጠንካራ ትብብር ላይ የተመሰረተ ውጤታማ የኮሙኒኬሽንና የሎጂስቲክስ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። አፍሪካ ለዓለም ደኅንነትና መረጋጋት ከፍተኛ አቅም አላት ያሉት ጄኔራል መኮንኑ፤ በቀጣይም ውስን ሃብትን በተሻለ ሁኔታ ለመጠቀም አዳዲስ ቴክኖሎጂና ፈጠራን ማስፋፋት ይገባል ብለዋል። የሰው አልባ ተዋጊ ድሮኖች፣ ዘመናዊ የዲጂታል ኮሙኒኬሽንና ሳተላይት ቴክኖሎጂ የዓለምን የጦርነት ባህሪ በመቀየር አዲስ የጦርነት ምዕራፍ እየፈጠሩ መሆናቸውን አንስተዋል። በዚህም የአፍሪካ ሀገራት ዘመናዊ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎችን በማላመድ ራሳቸውን ከዓለም የለውጥ ሁኔታና ባህሪ ጋር አብረው ማስኬድ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል። በሲምፖዚየሙ ላይ 26 የመከላከያና የኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ምርትና አገልግሎታቸውን ማቅረባቸውም አጋርነትን ለማጠናከር ከፍተኛ ዕድል እንደሚፈጥር አመላክተዋል። የሕክምና ድጋፍም ከሎጂስቲክስ ጋር የተሳሰረ ነው ያሉት መኮንኑ፤ ወታደሮችን በውጤታማነት ለመደገፍ የሕክምና አቅምና የአቅርቦት ስርዓት በተቀናጀ መልኩ መገንባት እንደሚገባ ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት በሎጂስቲክስ፣ በኮሙኒኬሽንና በቴክኖሎጂ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር በማጠናከር የጋራ የደኅንነት ተግዳሮቶችን በተሻለ ሁኔታ መመከት እንደሚኖርባቸውም አስገንዝበዋል።

ማህበራዊ
ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ከማጠናከር ባሻገር ትልቅ የልማት አቅም እየሆነ መጥቷል
Jul 27, 2026 9
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦ ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ከማጠናከር ባሻገር ትልቅ የልማት አቅም እየሆነ መምጣቱን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ገለጹ። የ2018 ዓ.ም የወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማጠቃለያ የእውቅናና ምስጋና መርሃ ግብር ተካሂዷል። ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ ሀገራዊ የበጎ ፈቃድ ንቅናቄ ወጣቶች ከራሳቸው አካባቢ በመውጣት ሌሎች ማህበረሰቦችን እንዲያውቁ፣ የጋራ ሀገራዊ ስሜትን እንዲያጎለብቱና የኢትዮጵያዊነት እሴቶችን እንዲያጠናክሩ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። ለሶስት ሳምንታት በቆየው መርሃ ግብር ወጣት በጎ ፈቃደኞች በአራቱም አቅጣጫዎች በመንቀሳቀስ የተለያዩ ሀገራዊ የበጎ ፈቃድ ሥራዎችን አከናውነዋል። በዚህም የአካባቢ ጥበቃ፣ የአረንጓዴ ልማት፣ የማህበረሰብ ድጋፍና ሌሎች ማህበራዊ ተግባራትን በማከናወን ለህዝብ ተጠቃሚነት አስተዋጽኦ አበርክተዋል። ወጣቶቹ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ድልድዮች በመሆን በተለያዩ አካባቢዎች የመረዳዳትና የመተሳሰብ መንፈስን ማጠናከራቸውን ገልጸዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ የወጣቶችን ጉልበት፣ እውቀትና ችሎታ በመጠቀም በመንግስትና በማህበረሰብ ያልተሸፈኑ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ክፍተቶችን ለመሙላት የሚያግዝ ሀገራዊ ንቅናቄ መሆኑንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በሀገራዊ ምክክርና በጋራ መግባባት ሂደት ላይ በምትገኝበት ወቅት የወጣቶች ተሳትፎ የሰላምና የአንድነት ግንባታን ለማጠናከር ወሳኝ መሆናቸውን ገልጸዋል። ወሰን ተሻጋሪ የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት የህዝብ ለህዝብ ትስስርን ይበልጥ ከማጠናከር ባሻገር ትልቅ የልማት አቅም እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል። ተሳታፊ ወጣቶች በበኩላቸው፤ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብሩ ሀገራቸውን በተሻለ ለማወቅና የተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎችን እውነተኛ ገጽታ ለመረዳት ትልቅ ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል። በተለይም ለአረጋውያን፣ ለአቅመ ደካሞችና ድጋፍ ለሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ያበረከቷቸው አገልግሎቶች ትልቅ እፎይታ እንዲሰማቸው እንዳደረጋቸው ጠቁመዋል። በመድረኩ ለወጣት በጎ ፈቃደኞች፣ ለክልል አመራር አባላት፣ ለጤና ቡድኖች፣ ለመገናኛ ብዙኃን ተቋማትና ለመርሃ ግብሩ ስኬት ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና ቀርቧል።
በኢትዮጵያ ዋናው የምክክር ጉባኤ ለወጣቶች የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት እየተመካከርን ነው
Jul 27, 2026 29
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዋናው የምክክር ጉባኤ ለወጣቶች የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት እየተመካከሩ መሆናቸውን ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ተመካካሪ ወጣቶች ገለጹ። ተመካካሪዎቹ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ ከጠቅላላ መድረኮች እስከ ንዑሳን የምክክር ቡድኖች ድረስ የተካሄዱት ውይይቶች ሁሉም ተሳታፊዎች በሚገባቸው ቋንቋ ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲያቀርቡ ዕድል ፈጥሯ። ይህም በሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የጋራ መግባባትን ለማጠናከር ወሳኝ ዕድል የፈጠረ ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ብለዋል። ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የመጣው ተመካካሪ ወጣት አደም ሳሌ እንደገለጸው፤ የምክክሩ ሂደት ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ የመንግሥት ሠራተኞችን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና ሌሎች የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎችን በስፋት ያሳተፈ አካታች መድረክ ነው። በምክክሩ የተለያዩ አስተያየቶችና ሃሳቦች ቢቀርቡም፣ በአብዛኛዎቹ የሀገር ግንባታ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እየተፈጠረ እንደሚገኝ ገልጿል። ይህም ለረጅም ዓመታት ሳይፈቱ የቆዩ ሀገራዊ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትና ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግሯል። ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመጣችው ተመካካሪ ወጣት ሊዲያ ኬሮ በበኩሏ፣ ምክክሩ አካታች በሆነ መልኩ በማሳተፍ ልዩነቶችን ወደ መግባባት እየቀየረ መሆኑን ገልጻለች። የአሁኑ ትውልድ በምክክሩ ያሳየው ተሳትፎና መስዋዕትነት ለሚቀጥለው ትውልድ የተሻለችና የተረጋጋች ኢትዮጵያ ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ የሚጥል ታሪካዊ እርምጃ ነው ብላለች። ከጋምቤላ ክልል የመጣው ተመካካሪ ወጣት ቾል ፑግ በበኩሉ፣ የምክክሩ ሂደት ከመጀመሪያው ጀምሮ በተደራጀና በአካታች መልኩ መካሄዱንና፣ የተሳታፊዎች የጋራ ውይይት ለሀገር ግንባታ የጋራ ኃላፊነትን ለማጎልበት ጉልህ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጿል። ችግሮችን በመወያየትና የጋራ መፍትሔ በማፈላለግ ዘላቂ ሰላምን ማስፈን እንደሚቻልም ነው የተናገረው። ከድሬዳዋ የመጣው ተመካካሪ ወጣት አሕመድ ሁሴን በበኩሉ፣ በሀገራዊ ምክክሩ መሳተፉ የሀገሪቱን ችግሮች በጋራ ለይቶ በመወያየት ዘላቂ መፍትሔ ለማስቀመጥ በሚደረገው ታሪካዊ ጥረት አካል ነው ብሏል። ችግሮቻችንን በጋራ ለይተን በመወያየት ተግባራዊ መፍትሔ የሚያስቀምጥ ውጤታማ ምክክር እየተደረገ በመሆኑ ጥሩ ውጤት ይመጣል ሲል ገልጿል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር የቆዩ ልዩነቶችን በውይይት ለመፍታት፣ የጋራ ራዕይ ለመገንባት፣ የኢትዮጵያዊነት ስሜትን ለማጠናከርና ለቀጣይ ትውልድ የተረጋጋች፣ የተባበረችና ሰላማዊት ኢትዮጵያን ለማሸጋገር ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አስተያየት የሰጡት ተመካካሪች ገልጸዋል።
በክልሉ የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ለማጠናከር በተከናወኑ ተግባራት ውጤት ተመዝግቧል
Jul 27, 2026 82
ሆሳዕና ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሰላም እሴቶችን በመጠቀም የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ለማጠናከር በተከናወኑ ተግባራት ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው "ብዝሀነትና የሰላም እሴታችን ለዘላቂ ሰላማችን" በሚል መሪ ሀሳብ ከሀይማኖት ተቋማት መሪዎችና የባህል ሽማግሌዎች ጋር የምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ አካሂዷል። የቢሮው ምክትልና የሰላም ግንባታና ብዝሃነት አያያዝ ዘርፍ ሀላፊ አቶ እንዳለ ወልደአማኑኤል በመድረኩ እንደገለጹት፤ የክልሉን ሰላም አስጠብቆ ለማስቀጠል ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው፡፡ ለዘመናት የዳበሩ ቱባ ዕሴቶች የህዝቦችን አብሮነትና አንድነት ለማጠናከርና ለዘላቂ ሰላም ግንባታ ወሳኝ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ለዚህም ባህላዊ የግጭት አፈታት ስርዓትን በጥናት ላይ በተደገፈ መልኩ የማጠናከር ጨምሮ ሰላምን ጠብቀው የሚያስቀጥሉ ተግባራት በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል ። ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የየም ሀገረ ስብከት ስራ አስኪያጅ ሊቀ ጉባኤ አባ ገብረ ሚካኤል መንግስቴ፤ የህዝቦች አብሮነት መጠናከር ለአካባቢው ፈጣን እድገት መረጋገጥ ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል። ለዚህም አብሮነትን በሚያጠናክሩና ለዘላቂ ሰላም ግንባታው መሰረት የሚጥሉ ስራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኙና ተግባሩን አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉ ገልጸዋል። በክልሉ የተጀመሩ ትልልቅ የልማት ስራዎች እንዲሳለጡና እንዲጠናከሩ ሰላምን ማስጠበቅና አብሮነትን ማጠናከር እንደሚገባ ያነሱት ደግሞ የክልሉ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ኡስታዝ ሼህ በኸጃ አብድልጀሊል ናቸው። ምክር ቤቱ የክልሉን ህዝቦች አብሮነትን በማጠናከር ለጋራ ተጠቃሚነት መረጋገጥ አበክሮ እንደሚሰራ ገልጸዋል። ሰላምን ማስጠበቅ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አይተኬ ሚና እንደሚጫወት የተናገሩት ደግሞ የሀድያ ባህል ሽማግሌ ዳኛ ብርሃኑ ጡሞሮ ናቸው። ባህላዊ እሴቶችን በመጠቀም ሰላምን ጠብቆ በማስቀጠልና የህዝቦችን አብሮነት በማጎልበት የልማት ስራዎችን ለማጠናከር በሚከናወኑ ተግባራት ሚናቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ትልቅ ዓላማ ያለው በመሆኑ ተሳትፏችን ተጠናክሮ ይቀጥላል
Jul 27, 2026 107
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2018(ኢዜአ)፦ የደም ልገሳ መርሃ ግብሩ ትልቅ ዓላማ ያለው በመሆኑ ተሳትፏቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (POA) ሚዲያ አመራርና ሠራተኞች ገለጹ። የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና የፐልስ ኦፍ አፍሪካ (POA) ሚዲያ አመራርና ሠራተኞች ለ17ኛ ጊዜ ዛሬ ደም ለግሰዋል። መርሐ ግብሩ በየሦስት ወሩ በቋሚነት የሚከናወነው የማኅበራዊ ኃላፊነት አካል ሲሆን፣ የዘንድሮው ደግሞ ከክረምት የበጎ ፈቃድ ተግባራት ጋር ተያይዞ መከናወኑ ተገልጿል። ደም ልገሳ በትራፊክ አደጋ፣ በወሊድ እና በተለያዩ ጉዳቶች ምክንያት ደም የሚያስፈልጋቸውን ወገኖች ከሞት ለማዳን እጅግ ወሳኝ መሆኑም ተመላክቷል። በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሕግ፣ የሥነ-ምግባርና ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክተርና የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ ታደለች ቦጋለ፤ የደም ልገሳው በተቋሙ ሠራተኞች በጎ ፈቃደኝነትና ተነሳሽነት በየሦስት ወሩ በቋሚነት እየተከናወነ የሚገኝ ነው ብለዋል። የሚለገሰው ደም በወሊድ ወቅት ደም ለሚያስፈልጋቸው እናቶች እና በሆስፒታሎች በደም እጥረት የሚቸገሩ ወገኖችን ጤና እና ሕይወት ለመታደግ የሚያስችል በመሆኑ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ገልጸዋል። የደም ልገሳው ለ17ኛ ጊዜ የተደረገ ሲሆን፣ የአሁኑ ከክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራ ጋር ተያይዞ መከናወኑ ልዩ እንደሚያደርገው አስታውቀዋል። የኢዜአ እና የፒኢኤ የኮሙኒኬሽን ቡድን መሪ ዮሐንስ ወንድይራድ፣ ኢዜአ መረጃን ለሕዝብ ተደራሽ የማድረግ ዋና ተልዕኮውን ከመወጣት ጎን ለጎን እንደ አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ እና ደም ልገሳ ባሉ ማኅበራዊ አገልግሎቶች ላይ በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል። የኢዜአ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተር ተከታይ ደለለኝ በበኩላቸው፣ ለበርካታ ጊዜ ደም መለገሳቸውን አስታውሰው፤ ደም መለገስ ለሌላ ሰው መትረፍ በመሆኑ እጅግ ደስተኛ ሆኜ ነው የምለግሰው ብለዋል። በተቋሙ የፋይናንስ ባለሙያ ትግስት ብርሃኑ በደም እጥረት የሚሰቃዩ ወገኖችን የምንታደግበት በጎ ተግባር በመሆኑ ከፍተኛ የመንፈስ እርካታ ፈጥሮብኛል ብላለች። ደም መለገስ ከሰብአዊ ተግባር ባለፈ የሌሎችን ሕይወት መታደግ ጭምር በመሆኑ በጎ ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የተናገረው ደግሞ የአፋን ኦሮሞ ዲጂታል ዘርፍ ጋዜጠኛ ቶሌራ ኢዶሳ ነው። በተቋሙ የአረብኛ ሥራ ክፍል ጋዜጠኛ ቢንያም ተስፋዬ በበኩሉ የምለግሰው ደም የሰዎችን ሕይወት ስለሚታደግ በቀጣይም ይህን በጎ ተግባር አጠናክሬ እቀጥላለሁ ብሏል። በኢትዮጵያ ደም እና ሕብረ ህዋስ ባንክ አገልግሎት ተንቀሳቃሽ ቡድን ነርስ የሆኑት ፍሥሐ ለወየሁ በበኩላቸው፣ በየጊዜው በወሊድ ምክንያት ለሚቸገሩ እናቶችና በተለያዩ ህመሞች የደም እጥረት የሚገጥማቸው ወገኖችን ሕይወት ለመታደግ ደም መለገስ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ተናግረዋል። በተጨማሪም የደም ልገሳ ከሚሰጠው መንፈሳዊ እርካታ ባሻገር ለለጋሹም ቢሆን አዳዲስ የደም ሴሎች እንዲተኩ በማድረግ በኩል ከፍተኛ የጤና ጥቅም እንዳለው ገልጸዋል። ባለሙያው አቅም በሚፈቅደው ልክ ሰዎችን ለመርዳት ከሚደረጉ በጎ ተግባራት አንዱ ደም መለገስ በመሆኑ፣ ይህንን ባህል አድርጎ መቀጠል እንደሚገባ መክረዋል።
ኢኮኖሚ
ቱሪዝም - የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ በኢትዮጵያ!!
Jul 27, 2026 66
በቤተልሔም ባህሩ መግቢያ፡- ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ሥልጣኔ መነሻ፣ የታሪክ መዝገብና የቱባ ባህል ሀብት ካስማ ምድር መሆኗ የአደባባይ ሃቅ ነው። የሺህ ዓመታት ታሪኮች፣ በዘመናት የተገነቡ ዕድሜ ጠገብ የሕንፃ አሻራዎች፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ ባህላዊ እሴቶችና በዓላት ኢትዮጵያን በዓለም የቱሪዝም ካርታ ላይ ልዩ ስፍራ የሚያስይዙ መለያ ምልከቶቿ ናቸው። እንደ የአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የአልነጃሺ መስጂድ፣ የሐረር ጀጎል እና የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ያሉ ታሪካዊ ቅርሶች የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የሃይማኖታዊ ትውፊትና የአርክቴክቸር ብልጽግና ሕያው ምስክሮች ናቸው። በተጨማሪም መስቀል፣ ጥምቀት፣ የገዳ ሥርዓት፣ አሸንዳ/አሸንድዬ፣ ኢሬቻ፣ ፊቼ ጨምበላላ እና ጊፋታ የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላትም ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳቡ የማይዳሰሱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች የሚያንጸባርቁ የኢትዮጵያ ውድ ሃብቶች ናቸው። እነኝህ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶች በዓለም አቀፍ ዕውቅናም የተቸራቸው ናቸው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 16 የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ማስመዝገብ ችላለች። በቅርቡ የተመዘገቡት የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የሐረር ሸዋል ኢድ ኢትዮጵያ ለዓለም ህዝብ ያበረከተቻቸው አዳዲስ የመስህብ ትሩፋቶች ናቸው። እነዚህ ቅርሶች የኢትዮጵያን ገጽታ በዓለም ላይ ከማጉላት ባሻገር በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን በመሳብ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በብዝኅ ተፈጥሮ፣ ታሪክና ባህል የታደለች ሀገር ብትሆንም ለረጅም ጊዜ እነዚህን ዕምቅ ሃብቶች በዘመናዊ የቱሪዝም አቀራረብ ለማልማት፣ ለዓለም አቀፍ ገበያ በብቃት ለማስተዋወቅና ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመቀየር የሚገባውን ያህል ትኩረት ሳይሰጣቸው ቆይቷል። በመሆኑም የቱሪዝም ዘርፍ የሀገሪቱን እውነተኛ አቅም በሚመጥን ደረጃ መጠቀም ሳይቻል ቆይቷል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በኢትዮጵያ በተተገበረው ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ አምድ እንዲሆን በመደረጉ ልዩ ትኩረት አግኝቷል። ይህም ዘርፉ ከተለምዷዊ አካሄድ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ልማት፣ ወደ ከፍተኛ ተወዳዳሪነትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚሸጋገርበትን መሰረት ጥሏል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተተገበሩት "የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ለውጥ ወሳኝ ምዕራፍ ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች በተፈጥሮ፣ በታሪክና በባህል የታደሉ ስፍራዎችን በዘመናዊ መንገድ በማልማት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ማራኪ መዳረሻዎችን መፍጠር ችለዋል። በዚህም የጎብኚዎች ፍሰት ጨምሯል፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት አድጓል፣ የየአካባቢዎቹ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተነቃቅተዋል፣ የኢትዮጵያም የቱሪዝም ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ መልክ እያገኘ መጥቷል። ዛሬ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጫ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ምንጭ፣ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ ዋና ሞተር በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ኢትዮጵያ፤ በአፍሪካ ቀዳሚ የዓለም ቅርሶች ማዕከል ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከ16 በላይ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ያስመዘገበች በአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናት። ከሚዳሰሱት ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የፋሲል ግቢና የጎንደር ቤተ መንግስት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የታችኛው ኦሞና የአዋሽ ሸለቆዎች፣ የሐረር ጁገል ግንብ እንዲሁም የባሌና የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮች ይገኙበታል። ከማይዳሰሱት ቅርሶች ደግሞ የመስቀል ደመራ በዓል፣ የጥምቀት በዓል፣ የፊቼ ጨምበላላና የገዳ ሥርዓት ተጠቃሽ ናቸው። ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት እነዚህን ዓለም አቀፍ ቅርሶች በተሻለ ሁኔታ የመጠበቅና የማደስ ሥራዎች የሚሰሩበትን ዕድል ፈጥሯል። በተመሳሳይም አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት ኢትዮጵያን ይበልጥ ተወዳዳሪና ማራኪ የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ የሚያስችል ሰፊ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። ሶስቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ገበታ ለሸገር - የአዲስ አበባን ገጽታ የቀየረ የለውጥ ጥንስስ!! የገበታ ለሸገር መርሃ ግብር የአዲስ አበባን የከተማ ገጽታ በመቀየር የቱሪዝም ስበት ማዕከልነቷን ያጎለበተ የለውጥ ምዕራፍ ነው። በመርሃ ግብሩ የተገነቡት የእንጦጦ፣ የአንድነትና የወዳጅነት ፓርኮች፣ የሳይንስ ሙዚየምና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከተማዋን ከዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ ባሻገር ዓለምአቀፍ የኮንፍረንስ ቱሪዝምና የመዝናኛ ጉብኝት ማዕከል እንድትሆን መሠረት ጥለዋል። ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ የተተገበሩት የከተማ ኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ለበርካታ ዓመታት ችላ የተባሉ ስፍራዎችን ወደ አረንጓዴ፣ ዘመናዊ እና ለሁሉም ተደራሽ የመዝናኛ ከባቢነት ቀይረዋል። ይህም ከተማዋን ለጎብኚዎች ይበልጥ ማራኪ ከማድረጉ በተጨማሪ ለነዋሪዎች ጤናማ፣ ንጹህና ምቹ የከተማ ምኅዳር መፍጠር አስችሏል። ገበታ ለሸገር የአዲስ አበባን የከተማ ውበት በማሳደግ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትና የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን በማበራከት የቱሪዝም ዕድገትን ያፋጠነ ብቻ ሳይሆን፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ያሻሻለና የዘመናዊ ከተማ ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስኬታማ ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር - ከገበታ ለሸገር የተቀዳ የሀገር በረከት!! ገበታ ለሀገር መርሃ ግብር በገበታ ለሸገር የተጀመረውን የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ወደ መላው ሀገር በማስፋት፣ በየክልሉ የሚገኙ ዕምቅ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶችን ወደ ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎች የቀየረ ትልቅ የልማት ፕሮጀክት ነው። በዚህ ማዕቀፍ የወንጪ ኢኮ ቱሪዝም፣ የጎርጎራ፣ የኮይሻና ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶች በመገንባታቸው የክልሎችን የቱሪዝም አቅም በእጅጉ በማሳደግ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች አዳዲስና ማራኪ የጉብኝት መዳረሻዎችን ፈጥረዋል። በተመሳሳይም ፕሮጀክቶቹ በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ሥርጭት እንዲፈጠር በማድረግ፣ የመንገድ፣ የመስተንግዶ፣ የመዝናኛና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች በስፋት እንዲገነቡ አስችለዋል። ይህም የቱሪዝም ጥቅም በተወሰኑ ከተሞች ብቻ እንዳይገደብ በማድረግ፣ የአካባቢ ኢኮኖሚን በማነቃቃት፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና የክልሎችን የልማት ተጠቃሚነት በማሳደግ የቱሪዝም ዕድገትን ወደ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ የቀየረ ውጤታማ ፕሮጀክት ሆኗል። ገበታ ለትውልድ - የቱሪዝም ልማትን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ያሸጋገረ የአገልግሎት ዘርፍ እመርታ!! ገበታ ለትውልድ መርሃ ግብር በገበታ ለሸገርና ገበታ ለሀገር የተጀመረውን የቱሪዝም ልማት በማስቀጠል፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት ከመጠበቅ ጋር በማጣጣም ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት ያስቻለ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። መርሃ ግብሩ የቱሪዝም ልማትን ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር ለትውልድ የሚተርፍ ሃብት የመጠበቅ እሳቤ ጋር አሰናስሎታል። በዚህ ማዕቀፍ በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርትን ጨምሮ፣ የሸበሌ፣ የሎጎ ሐይቅ ሪዞርቶችና የሀሮ ደንዲ ኢኮ ሎጅ ተጠናቀው ወደ ሥራ ገብተዋል። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገነቡና እየተገነቡ የሚገኙ ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ የልማት ሥራዎችም ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ አቅም ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች በማስፋፋት፣ አገልግሎትን ወደ ዓለምአቀፍ ደረጃ በማሳደግና የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም በኩል ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው። በተመሳሳይም ለአካባቢያዊ የኢኮኖሚ መነቃቃት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ በማሳለጥም ገንቢ ሚና እየተወጡ ይገኛል። የኮሪደር ልማትና አዳዲስ የቱሪዝም ትስስሮች በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ተጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እየተስፋፋ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበት እያፈካ ይገኛል። በዚህም የከተሞችን መሠረተ ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራን፣ የመዝናኛና የእግረኛ መንገዶችን በስፋት በማልማት ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ የከተማ ምኅዳር ፈጥሯል። ይህ ልማት የከተሞችን ውበት ከማሳደግ ባለፈ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማትን በማጠናከር፣ የጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘምና የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ዘርፉን ወደ ከፍተኛ የዕድገት ምዕራፍ አሸጋግሯል። የኮንፍረንስ ቱሪዝም (MICE) የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ውብ፣ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ከተማ በማድረግ፣ የአፍሪካ ኅብረትና የበርካታ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን ከተማ ወደ ቀዳሚ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ቀይሯታል። አዲስ ዓለም ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የሳይንስ ሙዚየምና ሌሎች ዘመናዊ መዳረሻዎች በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ተቋማትን በማፍራት ከተማዋን ለሀገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች፣ ኤግዚቢሽኖችና ትላልቅ የንግድ መድረኮች ተመራጭ አድርጓታል። ለአብነትም የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ፣ የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) እና መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮችን በብቃት ማስተናገድ ተችሏል። በተለይም የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም እንዲያስተዋውቁ ምቹ መድረክ ፈጥሯል። ይህም የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ገጽታ ከማጎልበት ባለፈ የቱሪዝም ማስተዋወቅን በዲጂታል ዘመን ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግሮታል። የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም መርሃ ግብርም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም በአዲስ አበባ የሚያልፉ ትራንዚት መንገደኞችን ከመሸጋገሪያነት ብቻ ወደ ጎብኚነት ለመቀየር አስፈላጊ ዕድል ፈጥሯል። በዚህም መዲናዋን ከቱሪስት መሸጋገሪያነት ወደ ቱሪዝም ማዕከልነት ቀይሯታል። በከተማዋ የተከናወነው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማትም ውብና ማራኪ የከተሜነት ገጽታን በመፍጠር፣ መንገደኞች በቆይታቸው የተለያዩ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ዘመናዊ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ አስችሏል። ይህም የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ከማራዘም ባለፈ፣ የመስተንግዶ፣ የትራንስፖርት፣ የባህልና የንግድ አገልግሎቶችን በማነቃቃት ለሀገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲፈጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶች በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል። በዚህም ከታሪካዊ ቅርሶች ባሻገር የባህል፣ የተፈጥሮ፣ የኢኮ ቱሪዝምና የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋፋት፣ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በተሻለ ሁኔታ እንድትጠቀም መንገድ ከፍተዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎች መስፋፋት የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር ከማሳደጉ ባለፈ የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲጠናከር በማድረግ ዜጎች የሀገራቸውን ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሯዊ ጸጋዎች እንዲያውቁና እንዲጎበኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ይህም የቱሪዝም ገቢን በማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ምንጭን በማስፋፋትና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጨምረውን አስተዋጽኦ ከፍ አድርጎታል። በተጨማሪም ዘርፉ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አበርክቶ እያስገኘ ነው። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በኢኮ ቱሪዝም፣ በባህል ውጤቶች ንግድና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች በመሳተፍ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል ፈጥሯል። በመሆኑም ቱሪዝም ከመዝናኛ ዘርፍ ባሻገር የልማት፣ የሥራ ዕድልና የኢኮኖሚ ለውጥ ማስፈንጠሪያ ምሰሶ እየሆነ መጥቷል። ማጠቃለያ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ሃብቶቿን ከዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ጋር በማስተሳሰር፣ በኮሪደር ልማት፣ በተሻሻለ የአገልግሎትና በዓለም አቀፍ የማስተዋወቅ ስራዎች በቱሪዝም ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እየጻፈች ትገኛለች። የተቀናጀው የልማት አቅጣጫ ሀገሪቱ ለዘመናት የያዘቻቸውን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም፣ የሥራ ዕድልና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ እየቀየረ ይገኛል። ዛሬ ቱሪዝም የኢኮኖሚ አንድ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል፣ የባህልና ታሪክ መዳረሻ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ሀገር ለማድረግ የሚያግዝ ስትራቴጂያዊ አቅም ሆኗል። ይህም ለሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ገጽታ፣ የባህል ትስስርና የዓለም አቀፍ ተሳትፎ አዲስ ዕድል ፈጥሯል። በተለይም የዲጂታል ዘመን የቱሪዝም ዘርፉን ለማስተዋወቅ ዕድሎችን የሚያሰፋ በመሆነኑ ይህንኑ በመጠቀም፣ እንደ አይሾ ስፒድና ዲላን ፔጅ ያሉ ዓለም አቀፍ ተከታይ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን ውብ ተፈጥሮ፣ ባህልና ታሪክ ለዓለም በማስተዋወቅ የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ትኩረት እያሳደጉ ናቸው። በመሆኑም ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ከጉብኝት ዘርፍ ባሻገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሀገር ገጽታ ግንባታና የዓለም አቀፍ ትስስር መሣሪያ በማድረግ ወደ አዲስ የቱሪዝም ዘመን እየተሸጋገረች ትገኛለች። ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ፤ የኢትዮጵያ አዲሱ የብልፅግና ዘመን የኢኮኖሚ መሰሶነቱን በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል።
በምዕራብ ሸዋ ዞን ጤፍን በኩታ ገጠም በማልማት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ተችሏል
Jul 27, 2026 235
አምቦ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦በምዕራብ ሸዋ ዞን ጤፍን በኩታገጠም በማልማት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ማሳደግ እንደተቻለ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ ገለፁ። በዞኑ ኤጀርሳ ለፎ ወረዳ በመኸር አዝመራው በ4 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የጤፍ ሰብልን በኩታ ገጠም የመዝራት መርሃ ግብር ተካሂዷል። የምዕራብ ሸዋ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዲዳ ጉደታ በመርሃ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት፤ በዞኑ በተያዘው የመኸር ወቅት ምርትና ምርታማነትን በመጨመር በምግብ ራስን ለመቻል የተጣለውን ግብ ለማሳካት እየተሰራ ይገኛል። ከለውጡ ዓመታት ወዲህ ለግብርናው ዘርፍ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረትና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በአግባቡ ለመጠቀም በመቻሉ ምርትና ምርታማነትን ለተከታታይ ጊዜያት ማሳደግ መቻሉን ተናግረዋል። የምዕራብ ሸዋ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተረፈ አራርሳ በበኩለቸው እንዳሉት፤ በዞኑ የጤፍ ልማቱን በተሻለ መንገድ ስኬታማ ለማድረግና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየቱን እና በዚህም የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን አክለዋል። በዞኑ በምርት ዘመኑ 84 ሺህ ሄክታር መሬት በጤፍ ዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን አንስተው፣ እስካሁን በተደረገው እንቅስቃሴ 58 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ገልፀዋል። የኤጄርሳ ለፎ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ከበደ ለሊሳ በበኩላቸው ፤በተያዘው የመኸር ወቅት ከ25 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በተለያዩ ሰብሎች ለመሸፈን በማቀድ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል። ከዚህ ውስጥም ከ12 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ በጤፍ ሰብል ለማልማት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በዞኑ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እንዲቻልም የአፈር ማዳበሪያ እና ምርጥ ዘር በተሻለ ሁኔታ መቅረቡን ጠቁመው አርሶ አደሩ የግብርና ፓኬጆችን ሙሉ በሙሉ እንዲተገብርም ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በልማቱ እየተሳተፉ ካሉት የወረዳው አርሶ አደሮች መካከል አቶ ከበደ ፊጣ እና ዲዳ ጉታ፤ ባለፉት አራት ዓመታት ከአካባቢው አርሶ አደሮች ጋር በመሆን በኩታ ገጠም ጤፍ በማልማት ውጤታማ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም ከወረዳው ግብርና ጽህፈት ቤት የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችን አግኝተው የእርሻ ስራዎችን በወቅቱ መጀመራቸውን ተናግረዋል። በተያዘው የምርት ዘመንም ጠንክረውና ተቀናጅተው በመስራት ከአንድ ሄክታር እስከ 21 ኩንታል የጤፍ ምርት ለማግኘት አቅደው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
ወልቂጤ ከተማን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል
Jul 27, 2026 110
ወልቂጤ ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦ የወልቂጤ ከተማን የኮሪደር ልማት በተያዘለት ጊዜ በማጠናቀቅ ከተማዋን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን የከተማው አስተዳደር አስታወቀ። የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር ለኢዜአ እንደገለፁት፤ በከተማዋ በሁለተኛው ዙር እየተገነባ ያለውን የ6 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር የኮሪደር ልማት በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ርብርብ እየተደረገ ነው፡፡ በዚህም ከተማዋን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን ጠቅሰው የኮሪደር ልማቱ ፋውንቴይን ፣ የተሽከርካሪ ማቆሚያ፣ የእግረኛ መንገድ ፣ የልጆች መጫወቻን ጨምሮ ፕላዛዎችን አካቶ እየተገነባ ነው ብለዋል፡፡ ከመጀመሪያው ዙር ልምድ የተወሰደበት ሁለተኛው ዙር የኮሪደር ልማት በመንገድ ዳርቻ ያሉ የንግድ ተቋማትንም በአዲስ መልክ በመገንባት የከተማዋን ገጽታ እየቀየረ ሲሆን በለሙ ቦታዎችም የጥላ ዛፎች እየተተከሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከ70 በመቶ በላይ የተጠናቀቀው የኮሪደር ልማት ከ220 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተያዘለት ሲሆን እስከ ፊታችን ነሃሴ መጨረሻ ለማጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከወልቂጤ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ሻምበል በደዊ መሃመድና አቶ ሃብታሙ እሸቱ እንደተናገሩት፤ የኮሪደር ልማቱ የከተማዋን ገፅታ በመቀየር ለነዋሪዎቿ ምቹ እንድትሆን እያደረጋት ነው። በተለይም ከዚህ ቀደም የነበረውን የመንገድ ጥበት በመቅረፍ ከተማዋን ለኢንቨስትመንት ተመራጭና ተወዳዳሪ እያደረጋት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በኮሪደር ልማቱ የስራ እድል ከተፈጠረላቸው ዜጎች መካከል ሲራክ ተመስገን በሰጠው አስተያየት፤ ልማቱ ሙያዊ አቅሙን ከማሻሻልና የስራ ባህልን ከመቀየር ባለፈ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዳደረገው ተናግሯል፡፡
በክልሉ የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠው ትኩረት ውጤት ተመዝግቧል
Jul 27, 2026 102
ታርጫ ፤ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ)፦በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተሰጠ ትኩረት ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ገለጹ። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት 10ኛ መደበኛ ጉባኤውን በታርጫ ከተማ እያካሄደ ነዉ። ርዕሰ መስተዳድሩ የክልሉን መንግስት የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ክንውን ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት እንዳመላከቱት፤ የክልሉ ዋነኛ የኢኮኖሚ አቅም ለሆነው የግብርና ዘርፍ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በበጀት አመቱ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ ሜካናይዜሽን እና የክላስተር እርሻን በማስፋት ዘርፉን ለማዘመን የተሰራው ስራም መሻሻል ማሳየቱን ተናግረዋል። በመኸርና በልግ ወቅት እንዲሁም፣ በበጋ መስኖ በዋና ዋና ሰብሎች ከ801 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በዘር በመሸፈን ከ23 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰብ መቻሉን ገልፀዋል። በተመሳሳይ በስራስር፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንሰት ከ80 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መገኘቱን ጠቅሰዋል። በቡና፣ በሻይና ቅመማ ቅመም ልማትም ምርትን ለማሳደግ የተሰራው ስራ ፍሬያማ እንደነበር ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። በበጀት ዓመቱ ከ61 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ የተሻለ ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰዋል። ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ከሚያስችሉ ግብዓቶች መካከል አንዱ የሆነውን ምርጥ ዘር በራስ አቅም ለማባዛት በተሰጠው ትኩረትም ውጤት መመዝገቡን አንስተዋል። በሌማት ትሩፋት ዘርፍ በዶሮ፣ በማር፣ በወተትና በዓሳ መንደሮችን ማደራጀትና የተደራጀቱን በማጠናከር ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ሰፊ ጥረት መደረጉንም አንስተዋል። ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የመጠባበቂያ እህል እና መጠባባቂያ ፈንድ የማሰባሰብ ስራ በትኩረት መሰራቱንም ተናግረዋል። በሌላ በኩል የክልሉን የገቢ አቅም በማሳደግ የታቀዱ የልማት ግቦችን ለማሳካት በተደረገ ጥረት ከ18 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ተችሏል ብለዋል። ከስራ እድል ፈጠራ አንፃርም በበጀት ዓመቱ ለ78 ሺህ በላይ ወጣቶችን በገጠርና በከተማ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አንስተዉ፣ ለወጣቶቹ የመስሪያና መሸጫ ቦታዎችን የማመቻቸት እንዲሁም የብድር አቅርቦት ስራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳይ ነው
Jul 26, 2026 215
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ መሸጋገሩን የሚያሳይ ነው ሲሉ የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ ገለጹ። የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባውን የማሰልጠኛ እና የምርምር ዘመናዊ የላቀ ላብራቶሪ ስራ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ፤የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ብርጋዴር ጀነራል ከበደ ረጋሳ፣የመከላከያ ሰራዊት ጀነራል መኮንኖች፣የተባበሩት አረብ ኢመሬትስ ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። ላቦራቶሪው በ20 ሺህ 850 ካሬ ሜትር መሬት ላይ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ለስልጠና እና ምርምር የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑ ተገልጿል። ላቦራቶሪው በውስጡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ የሳይበር፣ የኤሌክትሪክ ሀይል፣የአውቶሜሽን፣የኮሙኒኬሽን እና ኤሌክትሮኒክስ፣የነርሲንግ ሲሙሌሽን ላብራቶሪዎች በውስጡ ማካተቱ ተመላክቷል። በተጨማሪም ላቦራቶሪው ዘመናዊ የሶላር ስርዓት እና ዘመናዊ መሳሪያዎች የተገጠሙለት መሆኑ ተመላክቷል። የመከላከያ ሚኒስትሯ ኢንጅነር አይሻ መሀመድ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ በላቦራቶሪው መሰረተ ልማቱ የረቀቁ ቴክኖሎጂዎችን ጥቅም ላይ ማዋል ብቻውን በቂ አይደለም ብለዋል። ይልቁንም እውቀትን ወደ ሙያዊ ብቃት፣ምርምርን ወደ ፈጠራ እንዲሁም ፈጠራን ለሀገራችን አገልግሎት ወደሚውሉ ተግባራዊ መፍትሄዎች የሚቀይር አዲስ የትምህርት የሳይንስ እና ተቋማዊ አቅም የተከፈተበት ታላቅ አጋጣሚ መሆኑን ገልጸዋል። የዚህ የልህቀት ምእራፍ መሰረት በኢትዮጵያ እና በተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች መካከል ዘመናትን የተሻገረ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት መሆኑን ገልጸዋል። ይህ ታሪካዊ ወዳጅነት ቀደም ሲል ከነበሩት ዲፕሎማሲያዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር አሁን ላይ የሁለቱን ሀገራት ሀገራዊ ደህንነት፣ቴክኖሎጂያዊ ሽግግርና የተቋማትን ዘመናዊነት ወደሚያጎለብት የላቀ ምእራፍ መሸጋገሩን ጠቁመዋል። የላቦራቶሪ ማእከሉ በቁሳቁስ ድጋፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በእውቀት ሽግግር ፣በሳይንሳዊ ምርምር እና በሀገር በቀል የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ትውልድን የሚቀርጽ መሆኑን ጠቁመዋል። ላቦራቶሪው የመከላከያ ሰራዊቱን ሁለንተናዊ የዘመናዊነት ጉዞ የሚያፋጥን የተቋሙን የቴክኖሎጂና ምርምር መሰረት የሚያጎለብት እና የወደፊት ሀገራዊ ደህንነት በጽኑ መሰረት ላይ የሚጥል ታላቅ እርምጃ መሆኑን አመላክተዋል፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱን ዘላቂ ወዳጅነት የሚያሳይ ታሪካዊ ምልክት ነው
Jul 26, 2026 206
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባው ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ የሀገራቱን ዘላቂ ወዳጅነት እና ስትራቴጂያዊ አጋርነትን የሚያሳይ ታሪካዊ ምልክት መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ ገለጹ። የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባውን የማሰልጠኛ እና የምርምር ዘመናዊ የላቀ ላቦራቶሪ ስራ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሀግብሩ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሀመድ፣ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣የመከላከያ ሰራዊት ጄኔራል መኮንኖች፣የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። ላቦራቶሪው በ20 ሺህ 850 ካሬ ሜትር ላይ የተገነባ ሲሆን በውስጡ ለስልጠና እና ምርምር የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች የተሟሉለት መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ብርጋዴር ጄኔራል ከበደ ረጋሳ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ፕሮጀክቱ በእውቀት፣ በፈጠራና በሰው ኃብት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት ለዘላቂ ልማትና ለብሔራዊ ደህንነት መሠረት መሆኑን የሚያንጸባርቅ ነው ብለዋል። ለፕሮጀክቱ ስኬት አስተዋጽኦ ላበረከቱት የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች መንግሥት ላሳየው ድጋፍና ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል። ይህም በሁለቱ ወንድማማች ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ ግንኙነትና የጋራ የልማት ራዕይ የሚያሳይ ተጨማሪ ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። ላቦራቶሪው የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የሳይበር ደህንነት፣ የመገናኛ ምህንድስና፣ የአውቶሜሽንና የቁጥጥር ሥርዓቶች፣ የኃይል ምህንድስና፣ የ3ዲ ዲዛይን፣ የፕሮቶታይፕ ልማት እና የነርሲንግ ሲሙሌሽን ዘርፎችን የሚያካትቱ ዓለም አቀፍ ደረጃ ያላቸው መገልገያዎችን መያዙን ተናግረዋል። ይህም ለከፍተኛ ትምህርት፣ ለሳይንሳዊ ምርምር፣ ለቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ ለምርት ልማት፣ ለምህንድስና መፍትሔዎችና ለቴክኖሎጂ ሽግግር የተቀናጀ መድረክ እንደሚፈጥር አንስተዋል። በተጨማሪም ማዕከሉ በዩኒቨርሲቲዎች፣ በኢንዱስትሪ፣በመንግሥት ተቋማትና በዓለም አቀፍ አጋሮች መካከል የምርምርና የፈጠራ ትብብርን የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመዋል። የማዕከሉ ስኬት በተገጠሙ መሣሪያዎች ሳይሆን በሚያፈራቸው ብቁ ባለሙያዎች፣ በሚያመነጨው ምርምር፣ በሚፈጥረው ፈጠራና ለሀገር የሚያበረክተው ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንደሚለካ ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የማሰልጠኛ እና የምርምር የላቀ ላቦራቶሪ በይፋ ስራ ጀመረ
Jul 26, 2026 173
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች (UAE) መንግስት ጋር በመተባበር ያስገነባውን ዘመናዊ የማሰልጠኛ እና የምርምር የላቀ ላቦራቶሪ በይፋ ስራ አስጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ መሐመድ፣ የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ብርጋዴር ጀነራል ከበደ ረጋሳ፣ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ጀነራል መኮንኖች፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ተወካዮች እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎች ተገኝተዋል። ላቦራቶሪው በ20 ሺህ 850 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን፣ ለላቀ ስልጠና እና ምርምር የሚያስፈልጉ ዘመናዊ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ የተሟሉለት ነው። በውስጡ የሰው ሰራሽ አስተውሎት፣የሳይበር፣የኤሌክትሪክ ኃይል፣የአውቶሜሽን፣ የኮሙኒኬሽን እና ኤሌክትሮኒክስ እንዲሁም የነርሲንግ ሲሙሌሽን ላቦራቶሪዎችን አካቷል። ህንፃዎች በተለየ መልኩ ዘመናዊ የሶላር የኃይል ስርዓትና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የተገጠሙለት ነው። ማዕከሉ የተለያዩ የሳይንስ፣ የቴክኖሎጂ እና የመከላከያ ምርምር ዘርፎችን በአንድ ላይ የሚያገናኝ ዘመናዊ የእውቀት ማዕከል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ለዩኒቨርሲቲው ወደ ተግባራዊ ምርምርና ፈጠራ ይበልጥ ለመሸጋገር ትልቅ እምርታን የሚፈጥር ነው ተብሏል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ማዕከሉ ለመከላከያ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ለሀገሪቱ አጠቃላይ የቴክኖሎጂ፣ የኢንዱስትሪ፣የጤና እና የሳይንስ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተመላክቷል።
በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን የሚያፋጥን የሰው ኃይል እየተገነባ ነው
Jul 25, 2026 418
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 18/2018(ኢዜአ)፦ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ የዲጂታል ሽግግርን የሚያፋጥን የሰው ኃይል እየተገነባ መሆኑን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በተገኙበት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ለመጀመሪያ ጊዜ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የሰለጠኑ ስታርት አፖችን አስመርቋል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ዲጂታል ሽግግር ጠንካራ የሰው ኃይል አቅም እንዲሁም አስተማማኝ መሠረተ ልማቶችን ይጠይቃል። ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ሀገሪቱን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን ተናግረዋል። በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሰው ሠራሽ አስተውሎት ፖሊሲና ስትራቴጂ መቀረጹን፣ ችግር ፈቺ ውጤቶች መመረታቸውን፣ ለአለም ገበያ ብቁ የሆኑ ዲጂታል ባለሙያዎችን ማፍራት መቻሉን፣ የሰው ሠራሽ አስተውሎት መሠረተ ልማት ዝርጋታና ሌሎች ውጤቶች መገኘታቸውን ጠቅሰዋል። በሁሉም ዘርፎች በተለይም ቅድሚያ በሚሰጣቸው የፍትህና አስተዳደር፣ ስማርት ኮርት (ዘመናዊ ፍርድ ቤት)ና ስማርት ፖሊስ ጣቢያ፣ ጤና፣ የሕዝብ አገልግሎትና በሌሎች ዘርፎች በAI የታገዙ ቴክኖሎጂዎች በስፋት ሥራ ላይ መዋላቸውን ገልጸዋል። በዘርፉ ለተገኘው ስኬት በስታርታፕ፣ ሰመር ካምፕ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና በሌሎች ተቋማት የሰው ኃይል ልማት ጠንካራ የአቅም ግንባታ ሥራዎች በመከናወኑ ነው ብለዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሰለጠኑት ተመራቂዎች የዲጂታል ኢኮኖሚውን ለማንቀሳቀስ ዝግጁ የሆኑ፣ የተፈተሹ፣ ሥራ ላይ የዋሉና በገበያው ሊስፋፉ የሚችሉ ውጤቶች ማቅረባቸውን ገልጸዋል። እነዚህ ውጤቶች የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ወደ ተግባር መሸጋገሩን እንደሚያሳዩ ተናግረዋል። በዕለቱ በተዘጋጀው አውደ-ርዕይ ሰልጣኞቹ በጤና፣ በትምህርት፣ በትራንስፖርት፣ በቋንቋ ቴክኖሎጂ፣ በስማርት ሲቲ፣ በፋይናንስ እና በሰብዓዊ ልማት ዘርፎች የሠሯቸውን ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዕይታ አቅርበዋል።
ስፖርት
ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በስፖርት መሰረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ መስራት ይገባል
Jul 26, 2026 173
ሀዋሳ፤ሐምሌ 19/2018(ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ እግር ኳስ ተወዳዳሪና ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በስፖርት መሠረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ የሚሰሩ ስራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ ተጠቆመ። እ.አ.አ. በ1957 የተመሰረተው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መስራች ከነበሩ ሀገራት አንዷ የሆነችው ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዕድገት ትልቅ አሻራ አሳርፋለች። የአፍሪካ እግር ኳስ በዓለም መድረክ የሚገባውን ቦታ እንዲይዝ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉት የካፍ ፕሬዝዳንት የነበሩት የይድነቃቸው ተሰማ ሀገር ኢትዮጵያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የእግር ኳስ አፍቃሪያን ያሉባትም ናት። ኢትዮጵያ ለአፍሪካ እግር ኳስ ዕድገት ያኖረችውን አሻራና የቀደመ ገናና ታሪክ በማንሳት የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቧም ይታወቃል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የሲዳማ ቡና እግር ኳስ ክለብ ዋና አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እና የክለቡ ተጫዋች ሁሴን ጠሃ፤ በኢትዮጵያ ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት በመሰረተ ልማትና ታዳጊዎች ላይ ሊሰራ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ በእግር ኳሱ የላቀ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች እንዳሏት አንስተው ተወዳዳሪ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ዕድሎችን ለመጠቀም ብዙ ልንሰራ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። የ2018ቱ የሲቢኢ ፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ቡድን አሰልጣኝ ያሬድ ገመቹ እንደገለጸው፤ ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን ለመገንባት ሌላው ዓለም የሚሰራውን መስራት መቻል አለብን ። የስፖርት መሰረተ ልማትና የታዳጊ ስልጠና ማዕከላትን ማጠናከር፤ የምልመላ ስርዓትና የውድድር ዕድሎችን ማስፋት ቀዳሚዎች መሆናቸውን አንስቷል። ዕምቅ ችሎታ ያላቸው ተጫዋቾች የሚፈሩባቸው ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ የሚደረጉ ስልጠናዎችና ውድድሮች ላይ ማተኮር እንደሚገባም አክሏል። አሰልጣኞችን ልምድ ባላቸው ሀገራት ማስተማር፣ ወጥ የሆነ የስልጠና ማኑዋል ማዘጋጀትና ሳይንሳዊ የሆነ የምልመላ ስርዓት መዘርጋት ሌላው ሊተኮርበት የሚገባ ጉዳይ መሆኑን አንስቷል። መንግስት የ2029 የአፍሪካ ዋንጫን ለማስተናገድ ጥያቄ ማቅረቡ በስፖርቱ ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ መነሳሳትን እንደሚፈጥር የጠቀሰው አሰልጣኝ ያሬድ ዕድሉን መጠቀም ይገባናል ሲል ገልጿል። ለዋናው ብሔራዊ ቡድን የመጫወት ህልም ይዞ እየሰራ ያለው የክለቡ ከ20 ዓመት በታች የግራ መስመር አጥቂ ሁሴን ጠሃ በበኩሉ፤ ተፎካካሪ ብሔራዊ ቡድን ለመፍጠር ታዳጊዎችና የስልጠና ሜዳዎች ሊጠናከሩ ይገባል ነው ያለው።
የርገን ክሎፕ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ
Jul 24, 2026 253
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 17/2018 (ኢዜአ)፦ የጀርመን እግር ኳስ ፌዴሬሽን የርገን ክሎፕን የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መሾሙን ዛሬ ይፋ አድርጓል። የ59 ዓመቱ ጀርመናዊ የአራት ዓመት ውል የተፈራረሙ ሲሆን ስምምነቱ አሰልጣኙን እስከ 2030 የዓለም ዋንጫ መጨረሻ ድረስ የሚያቆያቸው ነው። ክሎፕ በቦታው የተኩት በ23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ጀርመን በ32ቱ ዙር በፓራጓይ ተሸንፋ ከውድድሩ ውጪ ከሆነች በኋላ ከኃላፊነታቸው የለቀቁትን ጁሊያን ናጌልስማንን በመተካት ነው። ከሊቨርፑል የዘጠኝ ዓመታት ቆይታ በኋላ የሬድ ቡል ሳልስበርግ የዓለም እግር ኳስ ኃላፊ ሆነው ሲሰሩ የቆዩት ክሎፕ፣ የጀርመን እግር ኳስን እንደገና ወደ ቀደመ ገናናነቱ የመመለስ ትልቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ክሎፕ ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን ጋር የመጀመሪያ ጨዋታቸውን በመስከረም ወር 2019 ዓ.ም. በዩኤፋ ኔሽንስ ሊግ (Uefa Nations League) ከኔዘርላንድስ ጋር ያደርጋሉ።
የዓለም አትሌቲክስ የአትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን አፀደቀ
Jul 23, 2026 267
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 16/2018 (ኢዜአ)፦ የዓለም አትሌቲክስ የኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ የሴቶች ብቻ (women’s only) የማራቶን የዓለም ክብረ ወሰንን ዛሬ ማፅደቁን ይፋ አድርጓል። አትሌት ትዕግስት እ.አ.አ አፕሪል 26 / 2026 በለንደን ማራቶን 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ በመግባት እ.አ.አ በ2025 በራሷ ተይዞ የነበረውን ክብረ ወሰን በዘጠኝ ሴኮንድ በማሻሻል አሸንፋለች። የዓለም አትሌቲክስ የአትሌቷን የሴቶች ብቻ የዓለም ክብረ ወሰን ዛሬ ማፅደቁን አስታውቋል። የሴቶች ብቻ (women’s only) የዓለም ክብረ ወሰን ሴቶች ብቻ በሮጡበት ውድድር ብቻ የተመዘገበ የዓለም ፈጣን ሰዓት ማለት ነው። የዚህ የዓለም ክብረ ወሰን አመዘጋገብ በሴቶች ውድድር ላይ የወንድ አሯሯጮች ወይም ወንዶች ተቀላቅለው ሲሮጡ (አጠቃላይ ሩጫ) ከሚመዘገበው የዓለም ክብረ ወሰን ጋር የሚለያይ ነው። ወንዶች በሴቶች ውድድር ላይ መኖራቸው የውድድሩን አዝማሚያ እና ሴቶች የሚያስመዘግቡት ሰዓት ላይ ተጽእኖ እንደሚያሳድር የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል። ሴት እና ወንድ ተደባልቀው በሚሮጡበት አጠቃላይ የሴቶች ማራቶን ውድድር የዓለም ክብረ ወሰንን (Overall women's world record) የያዘችው ኬንያዊቷ አትሌት ሩት ቼፕጌቲች ናት። ሩት እ.አ.አ በ2024 በቺካጎ ማራቶን 2 ሰዓት ከ9 ደቂቃ ከ56 ሴኮንድ በመግባት ክብረ ወሰኑን ጨብጣለች። የዓለም አትሌቲክስ ከአትሌት ትዕግስት በተጨማሪ ሰባት የዓለም ክብረ ወሰኖችን ማጽደቁን አስታውቋል። እውቅናና ፈቃድ በተሰጣቸው ውድድሮች ላይ ማሸነፍ፣ የውድድር ሜዳዎቹ የሚፈለገውን መስፈርት ያሟሉ መሆንና አትሌቶች በአበረታች ቅመም ምርምራ ውጤት ጤነኛ መሆናቸው መረጋገጥ አትሌቶች የዓለም ክብረ-ወሰን ባለቤት የሚሆኑባቸው ዋነኛ ቅደመ-ሁኔታዎች ናቸው።
የስፔኑ ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
Jul 20, 2026 693
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 12/2018 (ኢዜአ)፦ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ ጣምራ አዘጋጅነት ሲካሄድ የቆየው 23ኛው የፊፋ የዓለም ዋንጫ ዛሬ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ተጠናቋል። በኒው ዮርክ ኒው ጀርዚ ስታዲየም በተካሄደው የፍጻሜ ጨዋታ ስፔን አርጀንቲናን 1 ለ 0 በማሸነፍ ለሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን አንስታለች። ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ የኮከብ ተጫዋቾች ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል። በዚሁ መሰረት የስፔኑ አምበል ሮድሪ የዓለም ዋንጫው ኮከብ ተጫዋች በመባል ተመርጧል። የስፔኑ ተከላካይ ፓዎ ኩባርሲ የወጣት ኮከብ ተጫዋች ሽልማትን አግኝቷል። ኡናይ ሲሞን (ስፔን ) የውድድሩ ኮከብ ግብ ጠባቂ ሆኗል። ፈረንሳዊው ኪሊያን እምባፔ 10 ግቦች በማስቆጠር የኮከብ ግብ አግቢነቱን ሽልማት ወስዷል።
አካባቢ ጥበቃ
የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታዎች ከተፈጥሮ ሀብት ጋር ተጣጥመው እየተከናወኑ ነው
Jul 27, 2026 92
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 20/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ተፈጥሯዊ አደጋዎችን ለመከላከል የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጋር አጣጥሞ እያከናወነ መሆኑን ገለጸ። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር 75ኛ ዓመት የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓሉን በማስመልከት የተቋሙ አመራሮችና ባለሙያዎች "75 ዓመታት ኢትዮጵያን በመንገድ ያስተሳሰረ ጉዞ" በሚል መሪ ሀሳብ የአረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የአስተዳደሩ የመንገድ ሀብት ማኔጅመንት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አለማየሁ አየለ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት፤ አስተዳደሩ ባለፉት 75 ዓመታት ኢትዮጵያን በመንገድ መሰረተ ልማት እያስተሳሰረ መጥቷል ብለዋል። የሚከናወኑ የመንገድ ግንባታዎች የተፈጥሮ አካባቢውን በማይጎዳ መልኩ እንዲገነቡ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። የአየር ንብረት ለውጥ የሚያስከትላቸውን እንደ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተትና የናዳ አደጋዎችን ለመከላከል መሰረተ ልማቶችን ከተፈጥሮ ጥበቃ ጋር አጣጥሞ መስራት የጉዳት መከላከያ ስትራቴጂ መሆኑን ጠቅሰዋል። በመሆኑም የመንገድ ግንባታዎች ተፈጥሮን በማይጎዳ መንገድ እንዲሰሩ ከመደረጉ በላይ፣ በመንገድ ኮሪደሮች ላይ ዛፎችን የመትከልና የተፈጥሮ ሀብትን የመንከባከብ ስራዎች ከዲዛይን አሰራር ጀምሮ ታሳቢ ተደርገው እየተከናወኑ ነው ብለዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ተግባራዊ መሆን ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ የመንገድ መሰረተ ልማት ግንባታዎች ከተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጋር ተጣጥመው እንዲሄዱ መደረጉን አንስተዋል። በአስተዳደሩ የግንባታ ፕሮጀክቶች ማኔጅመንት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ብርሃኑ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ አስተዳደሩ ባለፉት 75 ዓመታት ከ180 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ መንገዶችን ገንብቷል ብለዋል። በግንባታ ሂደት የተጎዱ መሬቶች ወደነበሩበት ተፈጥሯዊ ይዘት እንዲመለሱ መደረጉንም ጨምረው ተናግረዋል። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ለአካባቢ ጥበቃ ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን ጠቁመው፤ ችግኞችን ከመትከል ባለፈ እንዲጸድቁ የመንከባከብ ስራ ትኩረት እንደተሰጠው ገልጸዋል። በደን ሀብት አካባቢዎች የሚሰሩ መንገዶች በተፈጥሮ ላይ የሚያደርሱትን ጉዳት ለመቀነስ በአቅጣጫ እየተሰራ መሆኑን አመላክተዋል። የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በግንባታ ወቅት የሚጎዱ የተፈጥሮ አካባቢዎችን መልሶ የመተካት ሀገራዊ ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የአካባቢ፣ ማህበራዊ፣ የስራ ቦታ ጤናና ደህንነት አስተዳደር ዳይሬክተር ኢንጂነር ነጻነት ወርቁ ናቸው።
ሰራዊቱ ለሀገሩ በጀግንነት ከመቆም ባለፈ በልማት ተግባራት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው-ሜጀር ጄነራል ተስፋዬ ረጋሳ
Jul 27, 2026 102
ባህርዳር፤ ሃምሌ 20/2018(ኢዜአ)፡- መከላከያ ሰራዊት ለሀገሩ ክብርና ሉአላዊነት በጀግንነት ከመቆም ባለፈ በልማትና በጎ ተግባራት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን በምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ ገለጹ። የምስራቅና ሰሜን ምእራብ እዞች ስታፍ አመራሮችና አባላት በባህር ዳር መኮድ ካምፕ የአረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። በዚሁ መርሃ ግብር ከተሳተፉት መካከል የምስራቅ እዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ ረጋሳ፤ ሰራዊቱ በተሰማራበት ግዳጅ ሁሉ አደራውን በላቀ ብቃትና ጀግንነት እየፈጸመ ይገኛል ብለዋል። ሰራዊቱ ኢትዮጵያን ከውጭ ጠላትና ከውስጥ ተላላኪ ባንዳዎች የጥፋት ተልእኮ በመጠበቅ የሀገሩን ክብርና ሉአላዊነት ማስከበሩን አንስተው በልማትና በጎ ተግባራት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። በዛሬው እለትም የምስራቅና የሰሜን ምእራብ እዞች አመራሮችና አባላት በጋራ በመሆን የአረንጓዴ አሻራቸውን በማኖር የልማት አለኝታነታቸውን ማረጋገጣቸውን ጠቅሰዋል። ሰራዊቱ ችግኝ ሲተክል ሰላምን በማወጅ የአገር ልማትን ለማረጋገጥ፣ የለመለመ አካባቢ ለመፍጠርና የቀጣዩ ትውልድ መጻኢ እድልና ተስፋ ብሩህ መሆኑን ለማብሰር ያለመ መሆኑን አስረድተዋል። "ሰራዊቱ ሁል ጊዜም የሰላምና ልማት ተልእኮውን ለመወጣት ዝግጁ ነው" ያሉት ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ በቀጣይም ከሰላም ማስጠበቅ ጎን ለጎን የሚያከናወናቸው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በሰሜን ምእራብ እዝ የደረጃ-3 ሆስፒታል አዛዥ ኮሎኔል ዶክተር ታደገ አበራ በበኩላቸው፤ ዛሬ የተተከሉት ችግኞች የአየር ንብረት ለውጥ እየደረሰ ያለውን ተጽእኖ ለመቋቋም የሚያስችሉ ናቸው። እንደ ኮሎኔል ዶክተር ታደሰ ገለጻ ሰራዊቱ ሁልጊዜም አገርና ህዝብ የሚጥቅሙ የልማት ተግባራት ላይ ግንባር ቀደም ሚና የሚጫወት የአገር አለኝታ መሆኑን አስገንዝበዋል። ሀገሪቱ ከድህነት እንድትላቀቅም በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በንቃት በመሳተፍ ሰራዊቱ እያበረከተ ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል። ከሰሜን ምእራብ እዝ 10 አለቃ አስናቀች በላቸው እንደገለጹት፤ የተተከሉት ችግኞች ፀድቀው ለታለመለት አላማ አንዲውሉ የእንክብካቤ ስራ ለመስራት ማቀዳቸውንም ነው የተናገሩት። ከምስራቅ እዝ የኮማንዶ አባል ምክትል 10 አለቃ መሃመድ ታደሰ በበኩላቸው ዛሬ የተተከሉት ችግኞች ለመጭው ትውልድ ሰላሟ የተጠበቀ፣ አረንጓዴና የለመለመች አገር ለማስረከብ ያለንን ፍላጎት የሚያሳይ ነው ብለዋል። ምስራቅና የሰሜን ምእራብ እዞች በተሰማሩበት የግዳጅ ቀጠና ሁሉ ባጠቃላይ ሁለት ነጥብ አራት ሚሊየን ችግኞችን የመትከል ግብ ይዘው እየሰሩ መሆኑን ከእዞቹ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
አረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ተጨባጭ ውጤቶች እያመጣ ነው
Jul 27, 2026 105
አዲስ አበባ፣ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):-አረንጓዴ ዐሻራ የምግብ ዋስትና እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ተጨባጭ ውጤቶች እያመጣ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ ገለጹ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣የቤተ መንግሥት አስተደደር እና የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አመራር እና ሰራተኞች በቆቃ ቤተ መንግሥት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዓለምፀሀይ ጳውሎስ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ አረንጓዴ ዐሻራ የተጎዱ በርካታ አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው። ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አዎንታዊ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸው፤የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት እንዲሳካ መደላደል መፍጠሩን ተናግረዋል። አረንጓዴ ዐሻራ የደን ሽፋን እንዲጨምር እያደረገ ነው ያሉት ሚኒስትር ዓለምፀሀይ፤ የአየር ንብረት ለውጥን በመከላከል ረገድ ዓለም አቀፋዊ ፋይዳው ከፍ ያለ መሆኑን ተናግረዋል። በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአቮካዶ እና ቡና ችግኞች ተተክለው ለውጤት መብቃታቸውን አስታውሰው፤ይህም የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲጨምር አስችሏል ብለዋል። የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በበኩላቸው፤ አረንጓዴ ዐሻራ የኢትዮጵያን ገጽታ እየገነባ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያዊያን በጋራ ሲሰሩ ምን ዓይነት ስኬት ሊመጣ እንደሚችል አረንጓዴ ዐሻራ ህያው ማሳያ መሆኑን ጠቁመው፤ሌሎች ሀገራትም በተሞክሮነት እየወሰዱት መሆኑ የመርሃ ግብሩን አርአያነት በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን አስረድተዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ቀጣይነት ያለው በመሆኑ ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን ለማውረስ ዛሬ ችግኝ የመትከል እና መንከባከብ ስራዎችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የቤተ መንግሥት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ምትኩ ደሬሳ በበኩላቸው፤ በቤተ መንግሥቱ ይዞታዎች ላይ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በሰፊው እየተከናወነ ነው ብለዋል። በቆቃ ቤተ መንግሥት ባዶ የነበሩ ቦታዎች ላይ የፍራፍሬ ተክሎችን ጨምሮ ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ዓይነተኛ ሚና የሚጫወቱ ተክሎች በሰፊው እየተተከለ መሆኑን አብራርተዋል። በዛሬው ዕለትም በ12 ሄክታር መሬት ላይ የአቮካዶና ማንጎ ችግኞች መተከላቸውን ጠቅሰው፤ ችግኞቹ የነገ ኢንቨስትመንት የገቢ ምንጭም ጭምር ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሚሊዮን ኃይለሚካኤል በበኩላቸው፤ለትውልዱ የተሻለ ሀገር ለማስረከብ በተወጠነው ሀገራዊ ሁነት ላይ የበኩሌን አሻራ በማኖሬ ደስተኛ ነኝ ብለዋል። እንደ ተቋምም በአረንጓዴ ዐሻራ ያለንን ተሳትፎ አጠናክሮ ለማስቀጠል በቁርጠኝነት እንሰራለን ሲሉም ተናግረዋል። ችግኝ መትከል ብቻ ሳይሆን ተንከባክቦ ለውጤት ማብቃት ግባችን ሊሆን ይገባል ያሉት ደግሞ ከብሄራዊ ቤተ መንግሥት ሙዚየም የመጡት ኮለኔል ተስፋዬ በቀለ ናቸው።
በኦሮሚያ ክልል እስካሁን በ733 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተተክለዋል
Jul 27, 2026 114
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 20/2018 (ኢዜአ):- በኦሮሚያ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን በ733 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መተከላቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ ግብርና ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ እንዳሻው ጀማነህ ለኢዜአ እንደገለጹት በክልሉ በተያዘው ክረምት አንድ ነጥብ አንድ ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ የተለያዩ የችግኝ ዓይነቶች ለመትከል ታቅዶ ወደ ሥራ ተገብቷል። ከታቀደው መሬት ውስጥ እስካሁን ከ733 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ላይ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። ችግኞቹ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ዞኖች እየተተከሉ መሆናቸውን ተናግረው በዋናነት ለደን ሽፋን፣ ለእንስሳት መኖ፣ ቀርከሃ፣ ለውበትና ለምግብነት የሚውሉ ሁሉገብ ጠቀሜታ ያላቸው መሆናቸውን ጠቅሰዋል። ችግኞቹ በመንግሥት፣ በማኅበራትና በግለሰቦች ችግኝ ጣቢያዎች የተዘጋጁ መሆናቸውን ጠቁመው፤ በልማቱም እስካሁን በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ዳይሬክተሩ አክለውም፣ ችግኝ መትከል ብቻውን ግብ እንደማይመታ በመጠቆም፣ ማኅበረሰቡ በተከላው ላይ በንቃት እንደተሳተፈ ሁሉ ለእንክብካቤውም በጋራ መረባረብ ተገቢ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት አለብን-መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
May 25, 2026 20462
አዲስ አበባ፤ግንቦት 17/2018 (ኢዜአ)፦የአፍሪካን አንድነት የበለጠ በማጎልበት የበለፀገች አህጉር መገንባት እንደሚያስፈልግ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። 63ኛው የአፍሪካ ቀን ''የ63 ዓመታትን ዓመታት አንድነት፣ ትስስርና ልማት፤ አብረን እናክብር” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ቅጥር ግቢ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ጨምሮ የሕብረቱ አባል ሀገራት ዲፕሎማቶችና ተጋባዥ እንግዶች ታድመዋል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ አፍሪካ በዓለም መድረክ ያላት ሚና በየ ጊዜው እየታደሰ መምጣቱን ገልጸዋል። የአህጉሪቷ የሕዝብ ቁጥርና የኢኮኖሚ ዕድገትም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የአፍሪካን ጥቅል የሀገር ውስጥ ዕድገት ምጣኔ 10 ትሪሊዮን ዶላር ያደርሰዋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል። የአፍሪካ ወጣቶችም ሌሎች አህጉራት ጭምር የሚመኟቸው የአህጉሪቷ ዕድገትና ብልፅግና አቅም መሆናቸውን አንስተዋል። በቀጣይም የአፍሪካዊያንን የአንድነት ኃይል የበለጠ በማጎልበት የአህጉሪቱን ዕምቅ ፀጋዎች ለሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና መቀየር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ በበኩላቸው፥የአፍሪካዊያን ባህልና ዕሴት ለአህጉሪቷ መፃኢ ዕድል፣ ዕድገትና ብልፅግና የሚተርፍ የጥንካሬ ምንጭ ነው ብለዋል። የአፍሪካን የትብብር አቅም በማጎልበት የአህጉሪቷ ዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥና የራስን የተሻለ ዕድል መቅረፅ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል። ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የአፍሪካን የኢኮኖሚ ዕድገት በማስፋት የአህጉሪቱን ዕምቅ የልማት ፀጋ ወደ ዘላቂ ብልፅግና መቀየር እንደሚገባ ተናግረዋል። በአህጉሪቷ ላይ የደረሱ በደሎች ፍትሕ እንዲያገኙ ከማድረግ ባሻገርም ለአጀንዳ 2063 ስኬት በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት እጣ ፋንታ መወሰን እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በየዓመቱ የአፍሪካ ቀን መከበር የጀመረው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁን የአፍሪካ ህብረት እ.ኤ.አ በ1963 መመስረቱን እንደሆነ ይታወቃል። የዘንድሮው የአፍሪካ ቀንም የህብረቱ ኮሚሽን ከህብረቱ ሰራተኞች ማኅበር፣ አባል ሀገራት፣ ከህብረቱ አደረጃጀቶችና ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ተዘጋጅቷል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 13288
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 12081
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 11980
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
ሐተታዎች
የባሕር በር ፣ የኢትዮጵያውያን የልማትና የሕልውና ጥያቄ
Jul 26, 2026 225
የባሕር በር ፣ የኢትዮጵያውያን የልማትና የሕልውና ጥያቄ በዜናው ፈንቴ እንደ መግቢያ፡- የባሕር በር የአንድ ሀገር የውኃ ዳርቻ ባለቤትነት መገለጫ ብቻ አይደለም፤ የንግድ ደም ስር፣ የኢኮኖሚ አምድ፣ ፍኖተ ስልጣኔ፣ የባህል መስተጋብርና የጂኦፖለቲካ ኃይል እንጂ። የዓለም ታላላቅ የሥልጣኔ መሰረት የሆኑ ከተሞች የውኃማ አካላትን ጠርዝ ተንተርሰው የተቆረቆሩ ናቸው። ባሕር የውሃ ስፋት ብቻ አይደለም፤ ይልቁንስ የንግድ ማሳለጫ፣ የደህንነት ዋስትና የሉዓላዊነት ማረጋገጫ ነው። የዓለም 80 በመቶ የንግድ ልውውጥ በባህር ላይ ይከወናል፤ በዓመቱ በአማካኝ እስከ 12 ቢሊዮን ቶን ጭነት ይጓጓዛል፤ የባሕር በር ያላቸው ሀገራት በፈጣን ዕድገት፣ በወጭ ንግድ፣ በኢንዱስትሪ መስፋፋትና በቀጣናዊ ተፅዕኖ የተሻለ አቅም መገንባት ይችላሉ፤ የባሕር በር የሌላቸው ሀገራት ደግሞ ለከፍተኛ የሎጂስቲክስ ወጪ፣ ለንግድ መጓተትና ለውጭ ጥገኝነትን ይጋለጣሉ፡፡ ለዚህም ነው የባሕር በር የአንድ ሀገርና ዜጎች የህልውና ጉዳይ ነው የሚባለው። ይህ እውነታ በኢትዮጵያ በግልጽ ይንጸባረቃል፤ በአፍሪካ ከ130 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ያላት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም፣ በኃይል ልማትና በዲጂታል ኢኮኖሚ እየተለወጠች ነገር ግን የባሕር በር የሌላት ሀገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት። ተለዋዋጭ በሆነው የምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ትልቅ የሕዝብ ቁጥርና በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ ለምትመራው ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባሕር በር ማግኘት የህልውና ፍትሕ እንጂ ቅንጦት አይደለም፡፡ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላምና ልማትም ዋስትና። ቀይ ባሕር አውሮፓን፣ ኤዥያና አፍሪካን የሚያገናኝ፤ የስዌዝ ቦይን ከሕንድ ውቅያኖስ ጋር የሚያስተሳስር፣ የዓለምን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ የሚያሳልጥ የዓለም ወሳኝ የባሕር መስመር ነው። በዚህ ወሳኝ ጂኦ ስትራቴጂክ ቀጣና የሚገኝ ሀገር አስተማማኝ የባሕር በር ያስፈልገዋል። ኢትዮጵያም ይገባታል፤ የታሪክ፣ የጂኦግራፊ፣ ነባራዊ ሁኔታና የተፈጥሮ ሚዛን ወደ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ያጋደለ ነው። የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ለሺህ ዘመናት የተሻገረ በአክሱም ስልጣኔ ዓለምን የናኘ ዓለም አቀፍ የንግድ እንቅስቃሴ እንደነበራት የአደባባይ ሐቅ ነው። የአዱሊስ ወደብም አፍ አውጥቶ ይናገራል፤ ከመካከለኛው ዘመን እስከ ቅርቡ አሰብ ወደብ ኢትዮጵያና የባሕር በር የማይነጣጠሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ሆነው ቆይተዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሲቪልና የአካባቢ ምህንድስና ትምህርት ክፍል መምህር በለጠ ብርሃኑ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከዓባይና የቀይ ባሕር ውሃዎች ጋር የተቆራኘ መሆኑን ያስታውሳሉ፡፡ የባሕር በር የሀገር ብሔራዊ ጥቅም አንጓ ሆኖ እያለ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር የተገለለችበት መንገድ የሚያስቆጭና በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የተፈፀመ በደል ነው ይላሉ። የኢትዮጵያ የወቅቱ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄም ሕጋዊ፣ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና መልክዓ-ምድራዊ ማስረጃዎች እንዳሉት ያብራራሉ። ከሦስት አስርት ዓመታት በፊት ተመራጭ መንግሥትና ሕጋዊ የሕዝብ ውክልና ያልተሰጠው የሽፍታ ስብስብ ኤርትራን በማስገንጠል ኢትዮጵያን የባሕር በር አልባ አድርጓታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ይህንን ሕገ ወጥና በሀገር ላይ የተፈጸመ ክህደት ሲያብራሩ "ኢትዮጵያ የባሕር በር ያጣችበትን ውሳኔ ማን ወሰነው?" ሲሉ ይጠይቃሉ። ሲቀጥሉም "ካቢኔው ይሆናል ብለን የካቢኔውን ዶክመንት ብናነብ የለም፣ ካቢኔው አያውቅም። አይ የለም ምክር ቤት ይሆናል የወሰነው ብለን ብንወስድ ምክር ቤትም አልነበረም፣ ምክር ቤቱም አላወቀም። የለም የኢትዮጵያ ህዝብ በሪፈረንደም ወስኖ ይሆናል እንዳይባል አልወሰነም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ያልወሰነውን፣ ተወካዮቹ ያላዩትን፣ ቢያንስ ቢያንስ አስፈጻሚው ካቢኔ ያላየውን ውሳኔ ማን ወሰነው? ማጣትን የሚያክል ነገር ያጣንበት መንገድ ሕጋዊነት ችግር እንዳለው የሚያሳየው፣ ተቋሞች አልገቡበትም" በማለት ውሳኔው ሕዝባዊና ተቋማዊ ውክልና ባልነበረው ስብስብ የተወሰነ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ የሀገር ውስጥ ባንዳና ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር በፈጠሩት ጥምረት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ኢ-ፍትሐዊ በደል ፈፅመዋል። ይህም ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት፣ በፍጥነት እያደገች ያለች ኢኮኖሚ ያላትና በቀጣናው የሰላምና የደኅንነት ዋና ተዋናይ የሆነችውን ኢትዮጵያ ያላቋረጠ የጂኦፖለቲካ ፈተና ውስጥ አስገብቷታል። በዚህ አውድ ውስጥ የቀረበው የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የሌላ ሀገርን ግዛት ለመውሰድ ወይም ሉዓላዊነትን ለመጋፋት የቀረበ ጥያቄ አይደለም። ይልቁንም በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ጥቅም፣ በቀጣናዊ ትብብር እና በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች መሠረት ሁሉንም ወገኖች የሚጠቅም ዘላቂ መፍትሔ ለማስገኘት የቀረበ የልማትና የሕልውና አጀንዳ ነው። የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ከኢኮኖሚ ጥቅም በላይ የሀገር ዘላቂ ዕድገት፣ የቀጣናው ትስስር እና የብሔራዊ ሕልውና ጉዳይ ነው። ስለዚህም ጥያቄው ታሪካዊ እውነታን፣ ሕጋዊ መሠረትን፣ ጂኦግራፊያዊ እውነታን እና የጋራ ቀጣናዊ ጥቅምን በሚያጣምር መንገድ መታየት ያለበት ስትራቴጂካዊ ጉዳይ እንጂ የግጭት ወይም የመስፋፋት የፖለቲካ መገለጫ ተደርጎ የሚወሰድ አይደለም። 👉ባሕር፤ የታሪካችን አካል፣ የወደፊታችንም መሠረት የኢትዮጵያ ከባሕር ጋር ያላት ትስስር ከዛሬ የተጀመረ ሳይሆን ከሥልጣኔዋ መነሻ ጋር የተቆራኘ የአደባባይ ሐቅ ነው። የአክሱም ሥልጣኔ በአዱሊስ ወደብ በኩል ከሮማ፣ ከግብፅ፣ ከሕንድ፣ ከዓረቡ ዓለምና ከሩቅ ምሥራቅ ጋር የንግድና የሥልጣኔ ትስስር መፍጠሩ በታሪክ የተመዘገበ እውነታ ነው። በዚህ ወደብ አማካኝነት ወርቅ፣ የዝሆን ጥርስ፣ ቅመማ ቅመሞችና ሌሎች የንግድ ሸቀጦች ወደ ዓለም ገበያ ይደርሱ እንደነበርም ታሪክ ያስረዳል። በዚህ ረገድ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኃይድሮ ፖለቲክስ ተመራማሪና ዓለም አቀፍ የውሃ ተደራዳሪ ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፣ የባሕር በር ጉዳይ በኢትዮጵያ ታሪክ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው የብሔራዊ ጥቅም ማጠንጠኛ ነው። ከዚህ አንጻር ኢትዮጵያ ከባሕር ጋር የነበራት ታሪካዊ ትስስር በተለያዩ የፖለቲካ ለውጦች ቢቋረጥም፣ በሕዝብ የልብ ማህደረ ውስጥ ያለው ስፍራ አልተሸረሸረም። ኢትዮጵያ በታሪኳ አሰብን፣ ምጽዋንና ሌሎች ወደቦችን ተጠቅማ ከቀጣናውና ከዓለም ጋር ሰፊ የንግድ ትስስር የፈጠረች ሀገር ናት። ስለዚህ የባሕር በር ጉዳይ አዲስ ፍላጎት ወይም አዲስ ፖለቲካዊ አጀንዳ ሳይሆን ከሀገሪቱ ታሪክ፣ ኢኮኖሚና ጂኦግራፊያዊ እውነታ ጋር የተቆራኘ ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው። ዛሬ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝም፣ በአቪዬሽን፣ በዲጂታል ኢኮኖሚና በኃይል ልማት ዘርፎች ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበች ትገኛለች። ይሁን እንጂ ይህ የኢኮኖሚ መስፋፋት ውጤታማ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና የተረጋጋ የባሕር በር ተደራሽነት ካልተደገፈ ሙሉ አቅሙን ማሳየት አይችልም። በዚህ ምክንያት የባሕር በር ጉዳይ የታሪክ ትውስታ ብቻ ሳይሆን፣ የዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልጽግና መሠረት ሆኗል። በመሆኑም የባሕር በር ጉዳይ የትናንትን ታሪክ ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ የነገዋን ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለማጠናከር፣ የንግድ ወጪዎችን ለመቀነስ፣ የቀጣናዊ ትብብርን ለማስፋትና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የሚያገለግል ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው። ከዚህ አንጻር በቀይ ባሕር አካባቢ በቅርብ ርቀት የምትገኘው ኢትዮጵያ ከባሕር ተደራሽነት ውጭ መሆኗ በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገትና በቀጣናዊ ተወዳዳሪነት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ በተረጋጋ የውይይትና የትብብር መንገዶች መፍትሔ የሚሻ ስትራቴጂክ ጉዳይ መሆኑን ያሳያል። 👉የባሕር በር፤ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ የልማትና የሕልውና ጥያቄ በ21ኛው ክፍለ ዘመን የአንድ ሀገር ጥንካሬ በወታደራዊ ኃይል ብቻ ሳይሆን፣ በኢኮኖሚ ተወዳዳሪነት፣ በንግድ ትስስር፣ በሎጂስቲክስ ቅልጥፍናና ዓለም አቀፍ ገበያ ተደራሽነት ይለካል። በዚህ መለኪያ የባሕር በር ለኢትዮጵያ የቅንጦት ሳይሆን የልማት መሠረታዊ መስፈርት ሆኖ ይታያል። በዚህ አውድ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ታሪካዊ እውነታን፣ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጥንና ዓለም አቀፍ የሕግ መርሆዎችን ያጣመረ የልማት ጉዳይ መሆኑን ምሁራን ያስረዳሉ። ኢትዮጵያ ለዚህ ጥያቄ መፍትሔ ለማግኘት የምታደርገው ጥረትም በሰላማዊ ውይይት፣ በዲፕሎማሲ፣ በጋራ ጥቅምና በቀጣናዊ ትብብር ላይ የተመሠረተ ነው። ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት፣ በአፍሪካ በፍጥነት እያደገች ያለች፣ በአቪዬሽን፣ በግብርና፣ በኢንዱስትሪ፣ በማዕድን፣ በኃይልና በዲጂታል ኢኮኖሚ መሠረት እየገነባች ያለች ኢትዮጵያ፣ ይህን የልማት እመርታ በተቀላጠፈ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና በተረጋጋ የባሕር በር ተደራሽነት ካልደገፈች ሙሉ አቅሟን ማሳካት አትችልም። በዚህ ምክንያት የባሕር በር ጉዳይ የአንድ ወደብ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን፣ የንግድ ተወዳዳሪነት፣ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልፅግና ጉዳይ ነው። እንደዚሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ደጋግመው እንደገለጹት፣ የኢትዮጵያ ጥያቄ የጦርነት ወይም የመስፋፋት ሳይሆን፣ በሰላማዊ ውይይት፣ በጋራ ጥቅምና በቀጣናዊ ትብብር መሠረት መፍትሔ የሚፈልግ የልማትና የሕልውና ጉዳይ ነው። 👉የኢኮኖሚ እመርታና የባሕር በር ትስስር በሀገራዊ ለውጡ ማግስት ኢትዮጵያ በብዝኅ ኢኮኖሚ ሥርዓት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ኢኮኖሚ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን አስመዝግባለች። የግብርና ምርት ጨምሯል፣ የኢንዱስትሪ ማምረት አቅም ጎልብቷል፣ የማዕድን ሀብቶች ወደ ውጭ ገበያ እየቀረቡ ሲሆን፣ የቱሪዝምና የዲጂታል ኢኮኖሚ መስፋፋትም አዲስ የዕድገት ምዕራፍ ከፍቷል። ይሁን እንጂ ይህ እመርታ ተወዳዳሪና ዘላቂ ሊሆን የሚችለው ከተቀላጠፈ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና ከአስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነት ጋር ሲተሳሰር ነው። የግብርና ምርቶች፣ የኢንዱስትሪ ውጤቶች፣ የማዕድን ሀብቶችና ሌሎች ወደ ዓለም ገበያ በፍጥነትና በወጪ ቆጣቢነት እንዲደርሱ የባሕር በር ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት፣ የኢትዮጵያና የቀይ ባሕር ትስስር ከሀገረ መንግሥቷ ታሪክ ጋር የተቆራኘ ሲሆን፣ የባሕር በር ጉዳይም የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የብሔራዊ ጥቅም ቁልፍ አጀንዳ ነው። በተለይም ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለወደብና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት ብቻ ከ1.5 እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጓ፣ የባሕር በር ጉዳዩ ከኢኮኖሚ ጋር ያለውን ቀጥተኛ ትስስር ያሳያል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያዎችም እንደሚጠቁሙት፣ አስተማማኝ የባሕር በርና አማራጭ የወደብ አገልግሎት ለኢትዮጵያ ቅንጦት ሳይሆን የፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማስቀጠል የሚያስፈልግ መሠረታዊ ፍላጎት ነው። ስለዚህ የባሕር በር ጉዳይ የአንድ ዘርፍ ፍላጎት ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትን፣ የንግድ መስፋፋትንና የዘላቂ ብልጽግና ጉዞን የሚወስን ስትራቴጂካዊ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው። 👉ከታሪካዊ መብት ወደ የጋራ ብልፅግና፤ ምላሽ የሚሻው የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ!! የኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ የትናንትን ታሪክ ለማስታወስ ብቻ የቀረበ አይደለም፤ የነገውን የቀጣናው ኢኮኖሚ፣ የንግድ ትስስርና የጋራ ብልፅግና የሚወስን ስትራቴጂካዊ ጉዳይ ነው። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ሀገራት ፉክክርን ሳይሆን ትብብርን ከመረጡ፣ ወደቦች የአንድ ሀገር ብቻ ሳይሆኑ የቀጣናውን የጋራ ዕድገት ማስፈንጠሪያ መድረኮች ይሆናሉ። በዚህ እሳቤም የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለቀይ ባሕር ቀጣና፣ ለአፍሪካ ቀንድ እና ለቀጣናዊ ሰላምና ኢኮኖሚያዊ ትስስር አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት የሚያስችል ዕድል ነው። የምጣኔ ሀብት ምሁር ጀማል መሐመድ (ዶ/ር) እንደሚገልጹትም፣ የኢትዮጵያ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት አስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነትን ይሻል፤ ይህ አለመኖሩ ግን የንግድ ተወዳዳሪነትን በመገደብ በሀገሪቱ ኢኮኖሚና በዜጎች ተጠቃሚነት ላይ ቀጥተኛ ጫና ያሳድራል። ስለዚህ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ የግዛት መስፋፋት ሳይሆን፣ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሀገር ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማረጋገጥ፣ የንግድ ተወዳዳሪነቷን ለማሳደግና የቀጣናዊ የጋራ ብልፅግናን ለማጠናከር የሚቀርብ የልማትና የሕልውና ጥያቄ ነው። 👉የቀይ ባሕር ጂኦፖለቲካ፤ የዓለም ትኩረት ለምን በቀጣናው ላይ ነው? የቀይ ባሕር ከውሃ አካልነቱ ባሻገር የዓለም ኢኮኖሚና የጂኦፖለቲካ ወሳኝ ማዕከል ነው። ከሕንድ ውቅያኖስ እስከ ሜዲትራኒያን የሚዘረጋው ይህ የባሕር መስመር የእስያን፣ የአፍሪካንና የአውሮፓን ኢኮኖሚዎች የሚያገናኝ ዋነኛ የዓለም የንግድ መተላለፊያ ነው። በዚህ ቀጣና የሚያልፉ መርከቦች ሸቀጦችን ብቻ ሳይሆን የኃይል አቅርቦትን፣ የምግብ ዋስትናንና የዓለም ኢኮኖሚ ቀጣይነትንም ይሸከማሉ። ስለዚህም የቀይ ባሕር ደህንነት የአንድ ቀጣና ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ ጉዳይ ሆኗል። በቀጣናው የሚፈጠር ማንኛውም መስተጓጎል የነዳጅና የምግብ ዋጋ፣ የመጓጓዣ ወጪ እንዲሁም የዓለም የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ ያሳድራል፤ ስለዚህ ዓለም የቀይ ባሕርን በልዩ ትኩረት ትከታተላለች። 👉ኢትዮጵያ፤ የቀጣናው ተፈጥሯዊ ማዕከል ኢትዮጵያ ለሦስት አስርት ዓመታት ከቀይ ባሕር ዳርቻ ተገልላ ብትቆይም፣ የቀጣናው ትልቁ ኢኮኖሚ፣ ገበያና የሰው ኃይል ማዕከል ሆና ቀጥላለች። ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ በፍጥነት እያደገ ያለ ኢኮኖሚ፣ ጠንካራ የአየር መጓጓዣ ትስስር፣ ትልልቅ የኃይል ፕሮጀክቶችና እየሰፋ ያለ የማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ያላት ሀገር፣ በቀይ ባሕር ጂኦ-ኢኮኖሚ ውስጥ ማዕከላዊ ሚና እንዳይኖራት ማሰብ አይቻልም። በመሆኑም የኢትዮጵያ ፍላጎት ወደ ባሕር መድረስ ብቻ ሳይሆን፣ ለቀጣናው ዘላቂ የኢኮኖሚ ትስስርና የጋራ ብልፅግና የሚያገለግል አስተማማኝና ተመጣጣኝ የባሕር በር ተደራሽነት ማረጋገጥ ነው። ይህም ለጎረቤት ሀገራት የንግድ፣ የኢንቨስትመንት፣ የሥራ ዕድልና የመሠረተ ልማት መስፋፋትን በማፋጠን የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጠናክር እድል ይፈጥራል። 👉ከታሪክ ወደ የጋራ ጥቅም የቀይ ባሕር ቀጣና በታሪክ ዘመናት የሥልጣኔ፣ የንግድና የባህል መገናኛ ሆኖ ቆይቷል። ከአክሱም ጀምሮ እስከ ዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ድረስ የባሕር በር ከሀገሪቱ ኢኮኖሚና ታሪክ ጋር የተሳሰረ ተፈጥሯዊ አካል ነው። ይህን ታሪክ ማስታወስም ያለፉ ግጭቶችን ለመቀስቀስ ሳይሆን፣ የዛሬውን ጉዳይ በትክክለኛ ታሪካዊ እና ስትራቴጂያዊ አውድ ለመረዳት ነው። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ከታሪካዊ መብት ባሻገር፣ ከኢኮኖሚ ዕድገት፣ ከሕዝብ ብዛት፣ ከቀጣናዊ ትስስርና ከጋራ ብልፅግና አንፃር ሊታይ ይገባል። ዘላቂ መፍትሔም በዓለም አቀፍ ሕግ፣ በጋራ ጥቅም፣ በኢኮኖሚ ትብብርና በተቋማዊ ውይይት ላይ የተመሠረተ ሲሆን፣ ለኢትዮጵያም ሆነ ለመላው የቀይ ባሕር ቀጣና የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ሊሆን ይገባል። 👉የወደፊቷ ኢትዮጵያ፤ ከብሉ ኢኮኖሚ ጋር የተሳሰረ ርዕይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ፣ ከዚያም ወደ እሴት ጨማሪ ምርትና ዲጂታል ኢኮኖሚ እየተሸጋገረ ነው። ይህ ሽግግር ዘላቂ እንዲሆን ግን ውጤታማ የሎጂስቲክስ ሥርዓትና አስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነት ወሳኝ ነው። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ የባሕር በር አጀንዳ የፖለቲካ ክርክር ሳይሆን የትውልድ የልማት ራዕይ ነው። በሕግ፣ በዲፕሎማሲና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ኢትዮጵያን ከዓለም ገበያ በተሻለ ሁኔታ ያገናኛል፤ ለቀጣናውም መረጋጋትና የጋራ ብልፅግና መሠረት ይሆናል። ስለዚህ የባሕር በር ጉዳይ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ዕድገትና የብሉ ኢኮኖሚ የወደፊት ራዕይ አካል ነው። 👉መደምደሚያ፡ የባሕር በር ጉዳይ፤ የግጭት ሳይሆን የጋራ ብልፅግና መንገድ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጉዳይ ያለፈውን ታሪክ ለመመለስ ብቻ የቀረበ ጥያቄ ሳይሆን፣ የወደፊቱን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የቀጣናዊ ትስስርና የጋራ ብልፅግና የሚወስን ስትራቴጂያዊ አጀንዳ ነው። የባሕር በር ተደራሽነት የሌላ ሀገር ጥቅምን በመጉዳት ሳይሆን፣ በጋራ ጥቅም፣ በኢኮኖሚ ትብብርና በቀጣናዊ ልማት ላይ የተመሠረተ የዕድገት መንገድ ነው። በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሀገራት ብልፅግና በመገፋፋት ሳይሆን በመተባበርና በጋራ ዕድገት ይገነባል። ስለዚህ የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ ለቀጣናው የኢኮኖሚ ትስስር፣ ለንግድ መስፋፋትና ለዘላቂ ሰላም አዲስ ዕድል የሚከፍት ነው። ከአክሱም ሥልጣኔ ጀምሮ ከቀይ ባሕር ጋር የቆየው ታሪካዊ ትስስር ከዘመኑ የሕዝብ ብዛት፣ ከኢኮኖሚ ዕድገትና ከቀጣናዊ ሚና ጋር ተያይዞ አዲስ ስትራቴጂያዊ አስፈላጊነት አግኝቷል። ስለሆነም አስተማማኝ የባሕር በር ተደራሽነት ማረጋገጥ የዛሬው ትውልድ የልማት ራዕይና የጋራ ኃላፊነት ነው። ይህም በጽኑ ሀገራዊ አንድነት፣ በበሰለ ዲፕሎማሲ፣ በውይይትና በጋራ ጥቅም መርህ ሊመራ ይገባል። በመጨረሻም የባሕር በር የትናንት ትዝታ ብቻ ሳይሆን፣ የኢትዮጵያ የነገ ብልፅግና፣ የቀጣናው የጋራ ልማትና የአፍሪካ ተስፋ መንገድ ነው። የባሕር በር የኢትዮጵያ የነገ ብልፅግና መንገድ እንጂ የትናንት ትዝታ ብቻ አይደለም!!
ምግቤን ከደጄ፤ የከተማ ግብርና አዲሱ የምግብ ዋስትና መሰረት
Jul 25, 2026 280
በመቅደስ ወልዴ መግቢያ፡- ዛሬ ዓለም በፈጣን የከተሜነት ሽግግር ውስጥ ትገኛለች። በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከገጠር ወደ ከተማ በመፍለስ፣ ከተሞችን የኢኮኖሚ፣ የኢንቨስትመንትና የኑሮ ማዕከላት እያደረጓቸው ነው። ይህ ሽግግር አዳዲስ የልማት ዕድሎችን ቢፈጥርም፣ ከምግብ አቅርቦት እስከ የኑሮ ውድነት፣ ከአካባቢ ጥበቃ እስከ የሥራ ፈጠራ ድረስ ያሉ አዳዲስ ፈተናዎችንም አስከትሏል። በተለይም በታዳጊ ሀገራት የከተሞች መስፋፋት የምግብ ዋስትናን ከልማት ፖሊሲዎች ማዕከል ላይ አስቀምጦታል። በ2050 ከዓለም ሕዝብ ሁለት ሦስተኛው በከተሞች እንደሚኖር የሚጠበቀው እውነታ፣ ከተሞች ምግባቸውን ለማረጋገጥ አዳዲስና ዘላቂ መፍትሔዎችን እንዲፈልጉ አስገድዷቸዋል። ኢትዮጵያም ከዚህ ዓለም አቀፋዊ ሽግግር ውጭ አይደለችም። የከተማ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ ሲሄድ፣ የምግብ አቅርቦት፣ የገበያ መረጋጋትና የኑሮ ውድነት አዳዲስ የፖሊሲ ጉዳዮች ሆነው ተነስተዋል። በዚህ ዐውድ ውስጥ የከተማ ግብርና ባዶ ቦታን ወደ ምርት፣ ቆሻሻን ወደ ማዳበሪያ፣ ሸማቹን ወደ አምራች የሚቀይር ዘመናዊና ዘላቂ የልማት መንገድ ሆኖ እየጎለበተ ነው። የከተማ ግብርና፤ ምንነቱና ጠቀሜታው የከተማ ግብርና በከተማ ውስጥ በሚገኙ አነስተኛ ቦታዎች፣ በመኖሪያ ግቢዎች፣ በሕንፃ ጣሪያዎችና በበረንዳ ስፍራዎች ላይ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችንና ቀላል የምርት ዘዴዎችን በመጠቀም አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ እንስሳት፣ ዓሳና ሌሎች የግብርና ውጤቶችን የማምረት ሥርዓት ነው። ቀደም ሲል ግብርና የገጠር ብቻ ተደርጎ ይታሰብ የነበረው አመለካከት ዛሬ በእጅጉ ተለውጧል። በከተሞች የሚገኙ ጠባብ ስፍራዎች እንኳን ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የልማት መስኮች ሆነዋል። በቤት ዙሪያ ይደረግ የነበረው ቀላል የጓሮ አትክልት ልማትም ዛሬ ለሺዎች የሥራ ዕድል የፈጠረ፣ ገበያን የሚያረጋጋና የሀገር ኢኮኖሚን የሚደግፍ ዘርፍ ሆኗል። ከተሞችን ውብና አረንጓዴ ከማድረጉ ባሻገር፣ ነዋሪዎች በራሳቸው ምርት የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ፣ ተጨማሪ ገቢ እንዲያገኙና ለአካባቢ ጥበቃ ተጨባጭ አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ አስችሏቸዋል። እንዲሁም የዶሮ እርባታ፣ የንብ ማነብና ሌሎች አነስተኛ የግብርና ሥራዎች የቤተሰብን ምግብ ከማሟላት ባለፈ ገበያውን በማረጋጋት ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። የከተማ ግብርና ለምን አስፈለገ? የግብርና ልማት ዛሬ በገጠር አርሶ አደሮች ጥረት ብቻ የሚገደብ አይደለም። የከተሞችን እምቅ ሀብት በመጠቀምና ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በማቀናጀት የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት የሚቻልበት ውጤታማ መንገድ መሆኑ በተግባር ተረጋግጧል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ተሞክሮዎችም የከተማ ግብርና የከተሞችን ገበያ በማረጋጋት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር፣ የከተማ ቆሻሻን ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ በመቀየርና የከተሞችን አረንጓዴነት በማጎልበት ያለውን ጉልህ አስተዋጽኦ በተግባር አሳይተዋል። የከተማ ግብርና፤ ከጓሮ ልማት ወደ ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ቀደም ሲል በቤት ጓሮ የሚከናወን ቀላል የአትክልት ልማት ተደርጎ ይታይ የነበረው የከተማ ግብርና፣ ዛሬ የምግብ ዋስትናን፣ የገበያ መረጋጋትን፣ የሥራ ፈጠራንና የአረንጓዴ ኢኮኖሚን የሚያጠናክር ሀገራዊ የልማት ስትራቴጂ ሆኖ ተቀይሯል። በአነስተኛ ቦታዎች፣ በቤት ግቢዎች፣ በሕንፃ ጣሪያዎችና በባዶ መሬቶች ላይ የአትክልት፣ የፍራፍሬ፣ የዶሮ እርባታ፣ የወተት ሀብት፣ የንብ እርባታና ሌሎች የግብርና ሥራዎች በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ። "ምግቤን ከደጄ" የሚለው ሀገራዊ ንቅናቄም የከተማ ነዋሪዎች በራሳቸው ምርት የምግብ ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ አዲስ ዕድል ፈጥሯል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ እስከ የገበያ መረጋጋት የከተማ ግብርና ከሚያስገኛቸው ትልልቅ ጥቅሞች መካከል ዋነኛው የምግብ ምርትን ለተጠቃሚው በአጭር ጊዜ፣ በአነስተኛ ወጪና በተሻለ ጥራት ማድረስ መቻሉ ነው። በከተማ ውስጥ የሚመረቱ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ እንቁላልና ወተት ረጅም ርቀት ሳይጓዙ በቀጥታ ለገበያ ስለሚቀርቡ ትኩስነታቸውን ይጠብቃሉ፤ የመጓጓዣ ወጪንም በእጅጉ ይቀንሳሉ። በሌላ በኩል ቤተሰቦች በጓሯቸው የሚያመርቱት ምርት የዕለት ተዕለት የምግብ ወጪያቸውን በመቀነስ የምግብ ዋስትናቸውን ያጠናክራል። ከቤተሰብ ፍጆታ በላይ የሚተርፈው ምርት ደግሞ ወደ ገበያ በመግባት የምግብ አቅርቦትን ያሳድጋል፤ በዚህም የዋጋ ንረትን በመቀነስ የገበያ መረጋጋትን ለማስፈን የጎላ አስተዋፅኦ ያደርጋል። የአረንጓዴ ኢኮኖሚ አዲስ ምዕራፍ የከተማ ግብርና የምግብ ምርትን ከማሳደግ ባለፈ፣ አዳዲስ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር የከተማ ኢኮኖሚን የሚያነቃቃና የአረንጓዴ ኢኮኖሚ መሠረትን የሚያጠናክር ዘርፍ ሆኗል። በአዲስ አበባን ጨምሮ በበርካታ የኢትዮጵያ ከተሞች በአትክልት፣ በፍራፍሬ፣ በዶሮ እርባታ፣ በወተት ሀብትና በንብ ማነብ የተሰማሩ በርካታ ወጣቶችና ሴቶች ቋሚ የገቢ ምንጭ እያገኙ ይገኛሉ። ይህም የከተማ ግብርና የቤተሰብ የምግብ ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር የሥራ አጥነትን ለመቀነስና የከተማ ኢኮኖሚን ለማጠናከር እያበረከተ ያለውን ጉልህ አስተዋፅኦ ያሳያል። አካባቢን ከመጠበቅ እስከ የከተሞችን ውበት የከተማ ግብርና የሥነ-ምህዳር ጠቀሜታውም ከፍተኛ ነው። ከቤት የሚወጡ ኦርጋኒክ ቆሻሻዎችን ወደ ተፈጥሯዊ ማዳበሪያ በመቀየር የአፈር ለምነትን ያሻሽላል፤ በተመሳሳይ ጊዜም የከተማ ጽዳትን ያጠናክራል። ከዚህ በተጨማሪ የአረንጓዴ ስፍራዎች መስፋፋት የከተሞችን የሙቀት መጠን በመቀነስ፣ የአየር ጥራትን በማሻሻልና ለነዋሪዎች ጤናማና ምቹ የኑሮ አካባቢ በመፍጠር ለከተማ ዘላቂነት የጎላ አስተዋፅኦ ያደርጋል። ማጠቃለያ የከተማ ግብርና የኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት የልማት አቅጣጫ መሆኑን በተግባር አረጋግጧል። የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ጀምሮ የኑሮ ውድነትን መቀነስ፣ የሥራ ፈጠራን ማስፋፋት፣ የከተሞችን ውበት ማጎልበትና የአረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ድረስ ያለው ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎላ ነው። ስለሆነም ለከተማ ግብርና የሚስማሙ ቴክኖሎጂዎችን ማስፋፋት፣ ለወጣቶችና ለሴቶች የፋይናንስና የቴክኒክ ድጋፍን ማጠናከር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻልና በከተማ ፕላን ውስጥ ለግብርና ተስማሚ ቦታዎችን በቋሚነት መመደብ ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ናቸው። ከተሞች የምግብ ፍጆታቸውን በራሳቸው የማምረት አቅም እያዳበሩ ሲሄዱ፤ የኢትዮጵያ ዘላቂ የምግብ ዋስትና፣ ጠንካራ አረንጓዴ ኢኮኖሚና ተወዳዳሪ የከተማ ልማት ስኬታማ ትልም ይበልጥ ይፋጠናል። ከደጃችን የሚጀምረው ምርት፤ ለሀገር ዕድገት የሚሆን ትልቅ አቅም ነው።
የአረንጓዴ ዐሻራ፤ ከሥነ-ምኅዳር ዘብ እስከ ዓለም የልማት ተምሳሌት
Jul 23, 2026 497
በመጽሔት አንለይ በወሳኝ ሀገራዊ የልማት ውይይቶች ላይ ከ48 ቢሊየን በላይ ችግኞች መተከላቸው፣ በዚህም በርካታ ሚሊየን ሄክታር መሬት መታደሱ እንዲሁም የተመዘገበ የደን ሽፋን በአበይት ጉዳይነት ይነሳሉ። ኢትዮጵያ እየተገበረችው ባለው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የአርሶ አደሩ ምርታማነት ማደግ፣ የወጣቱ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ መሆን፣ የእናቶች የኑሮ መሻሻልና የተፈጥሮ ሃብት መጠበቅ መቻሉ እንዲሁም የአየር ንብረት መዛባትን ማስተካከልና የደን ሽፋንን ማሳደጉ ለመርሃ ግብሩ ውጤታማነት በአብነትነት ይጠቀሳሉ። በዚህ አተያይ የኢትዮጵያ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ከተራ የችግኝ ተከላ ዘመቻ ባሻገር በአካባቢ ጥበቃ፣ በግብርና፣ በምግብ ዋስትና፣ በኢኮኖሚና በማኅበራዊ ልማት ዘርፎች መዋቅራዊ ለውጥ በማምጣት አንጸባራቂ ውጤት እያሰገኘ ነው። የዓለም አየር ንብረት ጉዳይ ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ ባለበት ወቅት፣ አፍሪካ የችግሩ ተጠቂ ብቻ ሳትሆን ለመፍትሄውም የራሷን ልምድና አቅም ማበርከት እንደምትችል እያሳየች ይገኛል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ሀገራዊ ንቅናቄም ለአፍሪካ የአካባቢ ጥበቃ ጥረት አዲስ የተግባር ልምድ እየሆነ መጥቷል። የአረንጓዴ ዐሻራው ልዩነት በተተከሉ ችግኞች ቁጥር ብቻ አይለካም። በተራቆቱ መሬቶች ላይ የተመለሰው ሕይወት፣ በገጠር የተፈጠሩ የኢኮኖሚ ዕድሎች፣ የተጠበቁ የውሃ ሀብቶችና ለወደፊት ትውልድ የተገነባው የአካባቢ መሠረት ዋናው ውጤቱ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ፤ ከርዕይ ወደ ተግባር!! የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በሀገራዊ ለውጥ ማግስት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በሕዝባዊ ተሳትፎ የተጀመረ ሲሆን፤ እስካሁን ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞች ተተክለዋል። ከዚህ በፊት የነበረው የተፈጥሮ ሃብት መራቆት በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ብቻ ሳይሆን በዜጎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ላይም ከፍተኛ ጫና ፈጥሮ ነበር። የአፈር መሸርሸር፣ የደን መጥፋትና የድርቅ ተጋላጭነቶችም የገጠር ሥነ-ምኅዳራዊ ሕይወትን ሲፈታተኑ ቆይተዋል። ይህን ምላሽ ለመስጠትም የአረንጓዴ ዐሻራ የተራቆቱ መሬቶችን መልሶ በማልማትና የደን ሽፋንን ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ በማሳደግ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የአረንጓዴ አሻራ የኢኮኖሚ ዐሻራ፡- የአረንጓዴ ዐሻራ ትርጉም በአካባቢ ጥበቃ ብቻ አይወሰንም። በኢኮኖሚውም ውስጥ አዲስ የልማት መንገድ እየፈጠረ ይገኛል። በጥምር ግብርና (Agroforestry) አማካኝነት ቡና፣ ፍራፍሬና ሌሎች የኢኮኖሚ ዋጋ ያላቸው ምርቶች ከደን ልማት ጋር እንዲሰናሰሉ አድርጓል። ይህም የገቢ ምንጭን ከማስፋት ባሻገር የውጭ ምንዛሬ ግኝትን ለማሳደግ አስተዋፅዖ አድርጓል። በተለይ የቡና ዘርፍ ከሚሊዮን ወደ ቢሊዮን ዶላር ደረጃ መሻገሩ የዚህ ጥምረት ውጤት አንዱ ማሳያ ነው። የአቮካዶ ምርት ለወጪ ንግድ የፈጠረው ዕድልም አንዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ውጤታማነት አብነት ሆኗል። በሌሎች የፍራፍሬ ምርቶች ላይ የመጣው ዕድገት ኢትዮጵያን በዓለም ገበያ የተሻለ ተወዳዳሪ የምትሆንበትን ዕድል ፈጥሯል። ከአፈር ጥበቃ እስከ ምግብ ዋስትና፡- የአረንጓዴ ዐሻራ በአፈር ጤናማነት ላይ ያመጣው ለውጥ የግብርና ምርታማነትን ከፍ አድርጓል። የአፈር ኦርጋኒክ ካርቦን መጨመር፣ የውሃ ማቆየት አቅም መሻሻልና የተፋሰስ ልማት በኢትዮጵያ የመስኖ ልማትና የምግብ ምርት ዕድገት መሠረት ጥለዋል። የስንዴ ምርታማነት ዕድገት እና የቤተሰብ ብልፅግናን የሚያረጋግጥ ስኬታማ ጉዞም የአረንጓዴ ዐሻራ ተጠቃሽ ውጤቶች ናቸው። የተፈጥሮ ጋሻነት፡- ኢትዮጵያ ለድርቅ፣ ለጎርፍና ለመሬት መንሸራተት ተጋላጭ ከሆኑ ሀገራት መካከል ተጠቃሽ ናት። ዛፎችና ስሮቻቸው አፈርን በመያዝ መሸርሸርን ይቀንሳሉ፤ የውሃ ሃብቶችን ጠብቆ በማቆየትና በማሻሻል የድርቅ ተጋላጭነትን የመቋቋም አቅም እየገነባ ነው። በተለይም በርካታ የኃይል ማመንጫ ግድቦችንና የውሃ ሃብቶችን ከደለል አደጋ ለመጠበቅ የደን ልማት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ እሙን ነው። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም የተፈጥሮ አደጋዎችን በመቀልበስ የተፈጥሮ ጋሻነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። የትውልድ ሐውልትና የልማት ውርስ የሆነው አረንጓዴ ዐሻራ!! የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የመንግሥትና የሕዝብ የጋራ ተሳትፎ ውጤት መሆኑን የግብርና ሚኒስትሩ አቶ አዲሱ አረጋ በአንድ ወቅት ገልጸዋል። እንደ እርሳቸው ገለጻም፣ ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው ዘመቻ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ተሳትፈውበታል። ይህም ኢትዮጵያዊያን የጋራ ታሪክ በመፃፍ በልማት መስክ አስደናቂ የትብብር መንፈስ እንዲገነቡ አስችሏል። የመርሃ ግብሩ ብሔራዊ የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ አረንጓዴ ዐሻራ የደን ውድመትን በመከላከል የተፈጥሮ ሃብትን ለመጠበቅ፣ የድርቅና የበረሃማነት ተጋላጭነትን ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ፋይዳ እያስገኘ ነው። የኢትዮጵያ የአየር ንብረት ተፅዕኖ መቋቋም አዲስ የዲፕሎማሲ ሚና!! በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረክ የአፍሪካ ዋና ጥያቄ የአየር ንብረት ፍትሐዊነት ነው። አህጉሪቱ በአነስተኛ የካርቦን ልቀት ላይ ብትገኝም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ከባድ ጫናን እየተጋፈጠች ይገኛል። በዚህ አውድ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ዐሻራን እንደ ሀገራዊ ፕሮጀክት በመውሰድ ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር የሚጋራ ተሞክሮ ፈጥራለች። የአፍሪካ አህጉራዊ የአየር ንብረት ጉባኤ በአዲስ አበባ መካሄዱም ኢትዮጵያ በዚህ ዘርፍ ያላትን ተሳትፎና አመራር ያሳየ ክስተት ነው። ይህ ጉባኤ ኢትዮጵያን የአፍሪካ የአየር ንብረት ውይይት ማዕከል እንድትሆን ከማገዙም በላይ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረኮችን ለማስተናገድ ያላትን አቅም በተግባር አሳይቷል። ማጠቃለያ፡- የተተከለ ችግኝ፣ የተገነባ ተስፋ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የዘንድሮውን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በቢሾፍቱ ሆራ አርሰዲ ሐይቅ ዳርቻ ''ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ሃሳብ በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፤ በዚህ ዓመት ስምንት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ግብ ተቀምቷል። በዚሁ ወቅትም ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን ወደ 65 ቢሊዮን ችግኞች ግብ የመድረስ ትልማችንን ለማሳካት በፅናት እየገሰገስን እንገኛለን ብለዋል፡፡ ዘንድሮም የተያዘውን የስምንት ቢሊዮን ችግኞችን የመትከል ግብ ለማሳካት በሚደረገው ብሔራዊ የንቅናቄ ስራ ላይ በሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለተግባራዊነቱ እንዲረባረቡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል። አረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ መትከል ብቻ አይደለም። የኢትዮጵያ የወደፊት የዕድገትና ብልፅግና ማሳኪያ የልማት ትልም እንጂ። የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብርም ከአንድ ችግኝ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት መድረክ የደረሰ የሀገር ተሞክሮ ነው። የተተከሉት ችግኞች ዛሬ የአካባቢ ጥበቃ ዘብ ሲሆኑ፣ ነገ ደግሞ የኢኮኖሚ ዕድል፣ የምግብ ዋስትና፣ የኃይል ዘላቂነትና የትውልድ ተስፋ ይሆናሉ። የተተከለው ችግኝ ነገ የሚሆነው ዛፍ ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር የኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ የተፈጥሮ ጥበቃ ጋሻና ለመጪው ትውልድ የሚተላለፍ ሕያው ቅርስ ነው። አረንጓዴ ዐሻራ ዛሬ የሚተከል ተስፋ፣ ነገ የሚሰበሰብ ብልፅግና ነው፤ ተስፋን እንትከል!!!
የሌማት ትሩፋት፡ የኢትዮጵያ ግብርና በአዲስ ምዕራፍ
Jul 22, 2026 430
በሳባ ስለሺ መግቢያ ኢትዮጵያ ለዘመናት የነበራትን የግብርና እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ የምግብ ዋስትና ለመቀየር ተግዳሮት ሆኖባት የቆየ ቢሆንም፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት በመንግስት በተጀመረው ዘርፈ-ብዙ የሪፎርም ጉዞ የዘርፉ ታሪክ በተጨባጭ እየተቀየረ ነው። የዚህ ለውጥ አብይ ማሳያ የሆነውና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም በአርባ ምንጭ ከተማ ይፋ የሆነው "የሌማት ትሩፋት" መርሃ ግብር አንዱ ነው። ይህ ሀገራዊ ንቅናቄ የሀገሪቱን የግብርና እና የእንስሳት ሀብት ልማት ጉዞ በአዲስ ምዕራፍ የቃኘ ነው። የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር ሁሉን አቀፍ የግብርና ልማት ሲሆን፣ በዋናነት በእንስሳት ሀብት እና ተያያዥ ዘርፎች ላይ ያተኩራል።በእንስሳት ሀብት ልማት ረገድ የወተት ላሞችን፣ የዶሮ (ሥጋ እና እንቁላል)፣ የንብ ማነብ (ማር) እና የዓሣ እርባታን በስፋት የሚያካትት ነው።የመርሃ ግብሩ ዋና ዓላማ ኢትዮጵያን ከምግብ ሸማችነት ወደ አምራችነት በማሸጋገር የምግብ ሉዓላዊነትን ማረጋገጥ ነው። በተለይም በቤተሰብ ደረጃ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ፣ የኑሮ ውድነትን በማቃለል፣ የአርሶና አርብቶ አደሩን ገቢ በማሳደግ እንዲሁም ለሀገሪቱ የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት የምግብ ሉዓላዊነትን እውን ለማድረግ ያለመ ነው። የሌማት ትሩፋት ለምን አስፈለገ? ፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ ኢትዮጵያ ያላትን እምቅ የተፈጥሮ ሀብትና የሰው ኃይል በመጠቀም፣ ለዘመናት የዘለቀውን የምግብና ሥነ-ምግብ ዋስትና ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የተነደፈ ነው። መንግስት ለዚህ መርሃ ግብር ከፍተኛ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት የሚገኘውም፣ ሀገሪቱ ያላትን ከፍተኛ የእንስሳት ሀብት በቴክኖሎጂ በመደገፍ ወደ ተጨባጭ እሴትና የሀገር ውስጥ ተጠቃሚነት ለመቀየር እንዲሁም የዘርፉን ምርታማነት በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ነው። ባለፉት አራት ዓመታት ምን ተከናወነ?፡- ባለፉት አራት ዓመታት በተተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የወተት፣ የእንቁላል፣ የሥጋ፣ የዓሣ እና የማር ምርቶችን ምርታማነት በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ ተከናውኗል። ለዚህ ስኬት በቂና ጥራት ያለው የእንስሳት ተዋጽኦ ለማቅረብ የሚያስችሉ ሰፊ የእንስሳት ዝርያ ማሻሻልና የማዳቀል ሥራዎች የተከናወኑ ሲሆን፤ የአዳቃይ ቴክኒሻኖችን አቅም መገንባት፣ የፈሳሽ ናይትሮጂን አቅርቦትና ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ለዘርፉ ተዋናዮች ማስተላለፍ ተችሏል። እንዲሁም የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና ተደራሽነትን በማስፋፋት፣ የእንስሳት እርባታ ደህንነታቸውን በጠበቀ መልኩ እንዲከናወን በማድረግ እና አስፈላጊውን መሰረተ ልማት በማሟላት ረገድ ላለፉት አራት ዓመታት ቅድሚያ ተሰጥቶ ሲሰራ ቆይቷል። በመስኩ ምን ተጨባጭ ውጤት ተገኘ ?፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የሀገሪቱን የምግብና ስነ-ምግብ ደህንነት ከማረጋገጥ ባለፈ፣ በዜጎች ዘንድ የቆየውን አመለካከት በመቀየር ረገድ ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግቧል። በተለይም በገጠሪቱ የሀገሪቱ ክፍል ብቻ ተወስኖ የነበረውን የግብርና እንቅስቃሴ ወደ ከተሞች በማስፋት፣ ህጻናት፣ እናቶች እና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ከእንስሳት ተዋጽኦ ማግኘት የሚገባቸውን አስፈላጊ ንጥረ ነገሮች እንዲያገኙ አስችሏል። ይህ ተነሳሽነት የከተማ ግብርናን በማስተዋወቅ ዜጎች በቤታቸው እንስሳትን በማርባት ከራስ ፍጆታ ባለፈ ምርቶቻቸውን ለገበያ በማቅረብ የኢኮኖሚ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። በመሆኑም፣ ባለፉት ዓመታት በመስኩ የተመዘገቡት ስኬቶች እንደሚያሳዩት፣ መርሃ ግብሩ ዜጎች በተቋማት ተቀጥረው ከመስራት ይልቅ በዘርፉ ተሰማርተው የራሳቸው ስራ ኖሯቸው ለሌሎችም የስራ እድል እንዲፈጥሩ አድርጓል። ይህ የመንግስት ያላሰለሰ ጥረት፣ የዜጎችን የስነ-ምግብ ፍላጎት ከማሟላት አልፎ፣ ጤናማ እና ሁለንተናዊ ብቃት ያለው ትውልድ በመገንባት ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በአሀዛዊ መረጃ የተደገፉ የዘርፉ ስኬቶች ፡- የግብርና ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው አኃዛዊ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር በተጀመረ በአራት ዓመታት (2014 ዓ.ም -2018 ዓ.ም) ውስጥ በእንስሳት ምርታማነት አስደናቂ ለውጥ ተመዝግቧል። በወተት ምርት፦ መርሃ ግብሩ ሲጀመር የነበረው 7 ነጥብ 1 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም፣ በአሁኑ ወቅት ወደ 15 ነጥብ 7 ቢሊዮን ሊትር አድጓል። በእንቁላል ምርት፦ ከነበረበት 3 ነጥብ 2 ቢሊዮን በከፍተኛ ሁኔታ በማደግ፣ ወደ 11 ነጥብ 7 ቢሊዮን ከፍ ብሏል። በዶሮ ሥጋ ምርት፦ በ2014 ዓ.ም 90 ሺህ ቶን የነበረው የማምረት አቅም፣ በ2018 ዓ.ም ወደ 253 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። በማር ምርት፦ በ2014 ዓ.ም 146 ነጥብ 7 ሺህ ቶን የነበረው የማምረት አቅም፣ በ2018 ዓ.ም ወደ 428 ሺህ ቶን ከፍ ብሏል። በአሳ ምርት፦ የውሃ አካላትንና ሰው ሰራሽ ኩሬዎችን በአግባቡ በመጠቀም የተከናወነው የአሳ ጫጩት ስርጭት፣ ከ300 ሺህ ወደ 16 ነጥብ 5 ሚሊዮን አድጓል። ይህ ውጤት ሀገሪቱ በእንስሳት ተዋጽኦ ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም በጥቂት ዓመታት ውስጥ እንዴት ማጎልበት እንደተቻለ በግልጽ ያሳያል። ዘርፉ ለውጭ ምንዛሪ ግኝት ምን አበረከተ?፡- የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የሀገር ውስጥ የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ኢትዮጵያ ከእንስሳት ተዋፅኦ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሬ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ አስቻይ ሁኔታዎችን ፈጥሯል። በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ብቻ 24 ነጥብ 2 ሺህ ቶን የተቀነባበረ የእንስሳት ተዋጽኦ ምርቶችን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ 128 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ማግኘት ተችሏል። ማጠቃለያ፦ በዘርፉ የተመዘገበውን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ አርብቶ አደር እና አርሶ አደሩ ከተለመደው ባህላዊ የእንስሳት አረባብ ዘዴ ለማላቀቅ የተጀመሩ ስራዎችን ማስቀጠል፣ የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና ጤና አገልግሎትን የማዘመን፣ እንዲሁም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የማስተዋወቅና የማምረት አቅም ግንባታ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው። በተጨማሪም የመንግስት፣ የግሉ ዘርፍ እና የማህበረሰቡን ቅንጅት ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አሰራር መዘርጋት፣ የቴክኖሎጂ ድጋፍ ያለው የገበያ ትስስር መፍጠርና የደላሎችን ጣልቃ ገብነት ማስወገድ እንዲሁም አምራቹና ሸማቹን በቀጥታ በማገናኘት ለተጀመረው የብልጽግና ጉዞ ጠንካራ መሰረት ማኖር ይቻላል። በአጠቃላይ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር የኢትዮጵያን የግብርና እምቅ ሀብት ወደ ተጨባጭ ሀገራዊ ብልፅግና ለመቀየር የተጀመረ ውጤታማ መንገድ መሆኑን ባለፉት አራት ዓመታት አሳይቷል። ይህ ከተጠናከረ ሀገሪቱ የምግብ ሉአላዊነቷን ለማረጋገጥ ያለመችውን ትልም ከማሳካት የሚያስቆማት ነገር እንደማይኖር አመላካች ነው።
ትንታኔዎች
የኢትዮጵያዊያን ምክክር፤ የጋራ ነገን የሚያሻግር የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ድልድይ
Jul 22, 2026 450
በሚኪያስ ጎቡ መግቢያ፡- ሀገራት ከጦርነት በላይ የሚፈትናቸው ጠላት አለ፤ እርሱም በአንድ ሀገር ልጆች መካከል የሚፈጠረው የመተማመን መሰናክል ነው። መሣሪያ የፈጠረውን ጉዳት እንደገና መገንባት ይቻላል። የተሰበረ ልብና የጠፋ መተማመን ግን በጉልበት አይመለስም። ለዚህም ነው ብዙ ሀገራት ከግጭት በኋላ ወደ ምክክር የሚመለሱት። ብሔራዊ ምክክር የአንድ መንግሥት ፕሮጀክት ወይም የፖለቲካ ውድድር አይደለም። የአንድ ትውልድ ለቀጣዩ ትውልድ የሚያስተላልፈው የሰላም ውርስ ነው። የሚጋጩ ሃሳቦች በጠመንጃ ሳይሆን በቃል ሲገናኙ፣ የተለያዩ ትርክቶች በመደማመጥ ሲቀራረቡ፣ ልዩነቶችም የጥላቻ ምንጭ ሳይሆኑ የመግባባት መነሻ ሲሆኑ ነው እውነተኛ ሀገራዊ ምክክር የሚፈጸመው። የዓለም ተሞክሮ እንደሚያሳየው ብሔራዊ ምክክር አንድ ዓይነት ቀመር የለውም። እያንዳንዱ ሀገር በታሪኩ፣ በባህሉ፣ በፖለቲካዊ እውነታውና በማኅበራዊ መዋቅሩ መሰረት የራሱን መንገድ ይመርጣል። ነገር ግን የሁሉም ግብ አንድ ነው፤ ግጭትን በመግባባት፣ ጥላቻን በመተማመን፣ ፍርሃትን በተስፋ መተካት። በአውሮፓ ከኮሙኒዝም ውድቀት በኋላ፣ በአፍሪካ ከአምባገነናዊ አስተዳደሮች ሽግግር ወቅት፣ በደቡብ አሜሪካ የሕገ-መንግሥት ማሻሻያ ሂደቶችና በዓረቡ ዓለም ከፖለቲካ አብዮቶች በኋላ የተካሄዱ ምክክሮች አንድ ትልቅ ትምህርት ይሰጣሉ። ምክክር ሲታመን ሀገር ያድናል፤ ለፖለቲካ ጥቅም ሲውል ግን ቀውስን ያባብሳል። ይህ የኢትዮጵያም ትልቁ ፈተና ነው። ሀገራዊ ምክክር የአንድ ተቋም ወይም የአንድ ወገን ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነት ነው። የምንናገረው ቃል፣ የምንጽፈው ሐሳብ፣ የምናዳምጠው አቋምና የምንቀበለው ልዩነት የነገዋን ኢትዮጵያ ይቀርጻሉ። ምክክር የሚጀምረው በአዳራሽ ሳይሆን በሰዎች ልብ ውስጥ ነው፤ የሚሳካውም ከመናገር በላይ በመደማመጥ ሲቻል ነው። ስለዚህ የዛሬው ጥያቄ "ምክክር ይካሄድ ወይ?" የሚል አይደለም። "ምክክሩን ለሀገር የሚበጅ፣ ለትውልድ የሚተርፍ፣ ለታሪክ የሚያስከብር እንዴት እናድርገው?" የሚለው ነው። መልሱም በአካታችነት፣ በእውነት፣ በመከባበርና በሀገርን ከግል ጥቅም በላይ በማስቀደም ውስጥ ይገኛል። ምክክር፤ የሀገር መድኃኒት ወይስ የትውልድ ፈተና? ምክክር ለምን ያስፈልጋል?፡- ማንኛውም ሀገር የሚያድገው በሰማይ ጠቀስ ሕንፃ ግንባታ ብቻ አይደለም። በሕዝቦቿ መካከል በሚኖረው መተማመን ጭምር እንጂ። መንገድ፣ ድልድይና ፋብሪካ መገንባት ይቻላል፤ ነገር ግን የተሰበረ ማኅበራዊ ትስስር ካልተጠገነ የልማቱ መሠረት ይናወጣል። ስለዚህ ብሔራዊ ምክክር የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን የሀገር የወደፊት ዕጣ ፋንታ የሚወሰንበት የጋራ አስተሳሰብ ሂደት ነው። የምክክሩ ዋና ዓላማ አሸናፊና ተሸናፊ መፍጠር አይደለም። ይልቁንም ሁሉም ወገኖች የራሳቸውን እውነት እየገለጹ፣ የሌላውንም እውነት በማዳመጥ የጋራ መግባባት የሚፈጥሩበት ሂደት ነው። እውነተኛ የምክክር ድል የሚለካውም የማን ሃሳብ አሸነፈ ሳይሆን ለሀገር ምን ያህል ሰላምና መተማመን ፈጠረ በሚለው ነው። የዓለም ተሞክሮ የሚያስተምረን፡- የታሪክ ገጾች እንደሚያሳዩት ሀገራት የብሔራዊ ምክክርን መንገድ የመረጡት ሌሎች አማራጮች ሲያቅቷቸው ነው። አንዳንዶቹ የረዥም ጊዜ የፖለቲካ ቀውስ ነበራቸው፤ ሌሎቹ ደግሞ በዘር፣ በሃይማኖት ወይም በሥልጣን ሽኩቻ ተከፋፍለው ሲራኮቶ የሰነባበቱ ናቸው። ነገር ግን የተሳካላቸው ሀገራት አንድ የጋራ መርህ ነበራቸው፤ የሀገርን ጥቅም ከፓርቲ፣ ከቡድንና ከግል ጥቅም በላይ አስቀድመዋል። ደቡብ አፍሪካ ከአፓርታይድ ወደ ዴሞክራሲ የተሸጋገረችው በበቀል ሳይሆን በሰለጠነ ምክክር ነው። ፖላንድና ሀንጋሪ የፖለቲካ ሽግግራቸውን በየጠረጴዛ ዙሪያ ምክክር አሳልፈዋል። ላይቤሪያና ሊባኖስ የጦርነት ቁስላቸውን ለማዳን የመደማመጥን መንገድ መርጠዋል። በተቃራኒው ግን ምክክርን ለፖለቲካ ሕጋዊነት ማግኛ፣ ለሥልጣን ማራዘሚያ ወይም ለውጭ ጫና ማስታገሻ ብቻ ያደረጉ ሀገራት የበለጠ ቀውስ ውስጥ ገብተዋል። ይህም አንድ ግልጽ ትምህርት ይሰጠናል፤ የምክክር ስኬት የሚወሰነው በመድረኩ ሳይሆን በተመካካሪዎች ቅንነት መሆኑን ያስረዳናል። ምክክር የሚጠይቀው ከባድ ኃላፊነት፡- ሀገራዊ ምክክር የኮሚሽን ወይም የመንግሥት ሥራ ብቻ አይደለም። የሁሉም ዜጎች የጋራ ኃላፊነትን የሚጠይቅ የጋራ ነገ አሻጋሪ ድልድይና የብሩህ ዘመን ማብሰሪያ ነው። ፖለቲከኛው የሀገርን ጥቅም ማስቀደም፣ የሚዲያው እውነትን በሚዛናዊነት ማቅረብ፣ የሲቪክ ማኅበራት የተገለሉ ድምፆችን ማሰማት፣ የኃይማኖት ተቋማት ይቅርታና መቻቻልን ማስፋፋት፣ ወጣቱ ከጥላቻ ይልቅ ውይይትን መምረጥና ምሁራን በማስረጃ የተደገፈ ሃሳብ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። ማንም ወገን የራሱን አቋም ብቻ ለማስገደድ ከሞከረ፣ ምክክሩ ወደ ክርክር ይቀየራል። ሁሉም ለመረዳት እንጂ ለማሸነፍ ካልመጡ ደግሞ የምክክሩ መንፈስ ይጠፋል። የሀገራዊ ምክክር ትልቁ ድል የሌላውን አቋም መለወጥ ሳይሆን፣ የሌላውን ህመም መረዳት ነው። ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር፤ ልዩነታቸው ምንድን ነው?፡- ብዙ ጊዜ ምክክር፣ ውይይት፣ ድርድርና ክርክር የሚሉት ቃላት በአንድ ትርጉም ይጠቀሳሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊና በማኅበራዊ ሂደቶች እያንዳንዳቸው የተለየ ዓላማና ባህሪ አላቸው። ይህንን ልዩነት አለማወቅ ሀገራዊ ምክክርን ከመጀመሪያው ሊያዛባው ይችላል። ውይይት የሐሳብ ልውውጥ ነው። ሰዎች ስለ አንድ ጉዳይ አመለካከታቸውን ይገልጻሉ፣ ይደማመጣሉ። ሁልጊዜ ውሳኔ ላይ ላይደርስ ይችላል። ክርክር የሚያተኩረው የማን ሃሳብ ትክክል እንደሆነ ላይ ነው። የራስን አቋም በማስረጃ ለማስረዳት ይደረጋል፤ አንድ አሸናፊና አንድ ተሸናፊ ሊኖር ይችላል። ድርድር ደግሞ የጥቅም ግጭትን በመካከለኛ መፍትሔ ለመፍታት የሚደረግ ሂደት ነው። እያንዳንዱ ወገን ከአቋሙ በመቀነስ የጋራ መፍትሔ ለማግኘት ይሞክራል። ሀገራዊ ምክክር ግን ከእነዚህ ሁሉ የላቀ ሂደት ነው። ዓላማው ማንንም ማሸነፍ ወይም ማስሸነፍ ሳይሆን የሀገር የወደፊት አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር ነው። በምክክር ውስጥ የሚሸነፍ ሰው የለም፤ የሚያሸንፈው ሀገር ነው። የኢትዮጵያ ልዩ እውነታ፡- ኢትዮጵያ ሦስት ሺህ ዘመናትን የተሻገረ በሕብር ያሸበረቀ ታሪክ፣ ብሔር፣ ብሔረሰብ፣ ሕዝብ፣ ቋንቋ፣ ባህልና ኃይማኖት ያላት ሀገር ናት። ይህ በሕብር ያሸበረቀ ልዩነት የኢትዮጵያ ጥንካሬ መሆን ሲገባው በተለያዩ ወቅቶች የፖለቲካ አለመግባባቶችና የታሪክ ትርክቶች የመከፋፈል መሣሪያ ሆነው ቆይተዋል። የሀገራዊ ምክክሩ ዋና ፈተናም ይህ ነው። ሁሉም የራሳቸውን ታሪክ ይዘው ወደ ጠረጴዛው ይመጣሉ፤ ነገር ግን ከጠረጴዛው የሚወጡት አንድ የጋራ የወደፊት ርዕይ ይዘው መሆን አለባቸው። ይህ ቀላል አይደለም። ስለዚህ ምክክሩ ከቃላት በላይ በተግባር የሚገለጥ ቅንነትን ይፈልጋል። የዋናው ምክክር ጉባኤ የህዝብ ወኪል ተመካካሪዎችም ሀገርን የማስቀደም ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ስኬታማ ምክክር የሚመሰረትባቸው አምስት ምሰሶዎች፡- ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዲሆን ቢያንስ አምስት መሠረታዊ ምሰሶዎች ሊኖሩት ይገባል። እነሱም መተማመን፣ አካታችነት፣ እውነት፣ ፍትሕና የጋራ ርዕይ ናቸው። ከሁሉም ክልሎች፣ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እና በውጭ ከሚኖሩ የዲያስፖራ ማህበራሰብ የሕዝብ ወኪል 4 ሺ ተመካካሪ ኢትዮጵያዊያንም በሀገር ግንባታ ጉዳይ፣ የመንግስት አደረጃጃትና ስርአት ጉዳይ፣ የፌዴራል ከተሞች አዲስ አበባ እና ድሬድዋ ከተሞች ጉዳይ፣ የሃይማኖት ጉዳዮች፣ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነትና ሰብዓዊ መብቶች ጉዳይ፣ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ ሙስናና የመልካም አስተዳዳር ጉዳዮች፣ የሰላም ግንባታ ጉዳዮች በአዲስ አበባ አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽ ማዕከል እየመከሩ ይገኛል። ሀገራዊ ምክክር ያለፈውን ለመቁጠር ሳይሆን፣ የወደፊቱን ለመገንባት የሚደረግ የጋራ ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ መንገድም የልዩነት ግድግዳን የሚያፈርስ የትውልድ አደራና የብሔራዊ መግባባት ማሰሪያ ጥበብና ትልም ሆኖ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር፤ የተገኙ ዕድሎች፣ ዋና ፈተናዎች እና የወደፊት አቅጣጫ በታሪክ ጉዞዋ ውስጥ ኢትዮጵያ ብዙ የፈተና ዘመናትን አልፋለች። አንዳንዶቹ ፈተናዎች ከውጭ ጥቃት የመጡ ቢሆኑም፣ አብዛኞቹ ግን ከውስጣዊ አለመግባባቶች፣ ከተለያዩ የታሪክ ትርክቶች፣ ከፖለቲካ ፉክክርና ከመተማመን እጥረት የተፈጠሩ ናቸው። ስለዚህ የዋናው ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ሂደት የዛሬን ችግር ለመፍታት ብቻ ሳይሆን፣ የትውልድ ዕዳን ለማቃለል የተጀመረ ታሪካዊ ሂደት ነው። ይህ ሂደት ቀላል አይደለም። በርካታ ዓመታት የተከማቹ ቅሬታዎች፣ የተለያዩ እውነታዎች፣ የተቃራኒ ትርክቶችና የተለያዩ የፖለቲካ ፍላጎቶች በአንድ ጠረጴዛ ዙሪያ መገናኘታቸው በራሱ ትልቅ ፈተና ነው። ነገር ግን ከዚህ በላይ ትልቁ ፈተና ልዩነትን ወደ መግባባት መቀየር ነው። ዕድሎች፤ ሊጠቀሙባቸው የሚገቡ ወሳኝ መስኮቶች፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት ኢትዮጵያ ለብዙ ዓመታት ያልተመለሱ ጥያቄዎችን በሰላማዊ መንገድ የምታነሳበት ትልቅ አጋጣሚ ነው። የታሪክ አተረጓጎም፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የሥልጣን ክፍፍል፣ የሀብት አጠቃቀም፣ የፍትሕ ጉዳዮችና የአብሮነት ዕሴቶች በጦርነት ሳይሆን በሐሳብ የሚፈቱበት ዕድል ይፈጥራል። ከዚህም በላይ ምክክሩ የፖለቲካ ባህልን ለመቀየር የሚያስችል ዕድል ነው። ለብዙ ዓመታት "አሸናፊና ተሸናፊ" በሚለው አስተሳሰብ የተመራውን ፖለቲካ ወደ "አብሮ ማሸነፍ" የሚሸጋግር ከሆነ እውነትም የኢትጵያ የዴሞክራሲ ጉዞ ጠንካራ መሠረት ያገኛል። በሂደቱ ፊት የሚቆሙ ፈተናዎች፡- ማንኛውም ሀገራዊ ምክክር ከፍተኛ ተስፋ እንደሚፈጥር ሁሉ ከባድ ፈተናዎችንም ይዞ ይመጣል። የመጀመሪያው ፈተና የመተማመን እጥረት ነው። ለብዙ ዓመታት የተገነባ ጥርጣሬ በጥቂት ወራት አይጠፋም። ስለዚህ የምክክሩ ተዓማኒነት በእያንዳንዱ እርምጃ ሊገነባ ይገባል። ሁለተኛው ፈተና የተለያዩ የታሪክ ትርክቶች ናቸው። አንድ ክስተት በአንዱ ወገን የድል ታሪክ ሲሆን፣ በሌላው ወገን የመከራ ታሪክ ሊሆን ይችላል። ይህን ልዩነት በክብር መቀበል እንጂ መግፋት አይቻልም። በሌላ መልኩም የጥላቻ ንግግርና የሐሰት መረጃ ስርጭት ነው። በዲጂታል ዘመን አንድ ያልተረጋገጠ መረጃ በጥቂት ደቂቃዎች ሺዎችን ሊደርስ ይችላል። ስለዚህ የሚዲያ ተቋማትና የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የሚወስዱት ኃላፊነት ከመቼውም በላይ ወሳኝ ይሆናል። የምሁራንና የመገናኛ ብዙኅን ሚና፡- በብሔራዊ ምክክር ሂደት ውስጥ ምሁራን ስሜትን ሳይሆን ማስረጃን ማቅረብ አለባቸው። የማኅበረሰብ ችግሮችን በሳይንሳዊ ጥናት መተንተን፣ ከሌሎች ሀገራት ልምድ መማርና አማራጭ መፍትሔዎችን ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል። መገናኛ ብዙኅንም በዚህ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸው። መገናኛ ብዙኅን ወሬን ከማባዛት ይልቅ እውነትን ማጣራት፣ ልዩነትን ከማባባስ ይልቅ መግባባትን ማጎልበት፣ ስሜትን ከማቀጣጠል ይልቅ እውነታን ማቅረብ አለበት። ምክክሩን የሚያጠናክር የመገናኛ አውታር ታሪክ ይሠራል፤ የሚያደናቅፍ ደግሞ በታሪክ ይጠየቃል። ሀገራዊ ምክክር በአንድ ቀን የሚጠናቀቅ ክስተት አይደለም። ምክክር በትውልድ የሚገነባ የፖለቲካ ባህል ነው። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሥራውን ሊጨርስ ይችላል፤ ነገር ግን የመደማመጥ ባህል በሕዝብ ውስጥ ካልሰረጸ የምክክሩ እውነተኛ ዓላማ አይሳካም። የዛሬ ውሳኔ፤ የነገ ኢትዮጵያ፡- አንዳንድ የታሪክ ወቅቶች በየቀኑ አይመጡም። አንዳንድ ውሳኔዎችም የአንድ መንግሥት ዘመንን ብቻ ሳይሆን የትውልዶችን ዕጣ ፈንታ ይወስናሉ። ሀገራዊ ምክክር የእነዚህ ታሪካዊ ውሳኔዎች አንዱ ነው። ዛሬ በምንመርጠው የምክክር ባህል፣ በምንገነባው መተማመንና በምናሳየው የፖለቲካ ብስለት ላይ የነገዋን የጠንካራ ሀገረ መንግሥት ተምሳሌት ኢትዮጵያ ያንፃል። ምክክር ሁሉንም ችግር በአንድ ጊዜ የሚፈታ አስማታዊ መፍትሔ አይደለም። ነገር ግን ጦርነትን ከውይይት፣ ጥላቻን ከመቻቻል፣ መከፋፈልን ከመተባበር የሚተካ ብልህ መንገድ ነው። የሚያደርገውም ልዩነቶችን ማጥፋት ሳይሆን ልዩነቶችን በአንድ ሀገር ጣሪያ ስር እንዴት እንደሚኖሩ የጋራ ሕግና ሥርዓት መፍጠር ነው። በእርግጥ ኢትዮጵያ ከባድ ፈተናዎችን አሳልፋለች። የፖለቲካ አለመተማመን፣ የማንነት ጥያቄዎች፣ የፀጥታ ችግሮች፣ የኢኮኖሚ ጫናዎችና የማኅበራዊ ስብራቶች በቀላሉ የሚያልፉ አይደሉም። ይሁን እንጂ እነዚህን ችግሮች በጥይት ከመፍታት ይልቅ በምክክር ለመፍታት መሞከር በራሱ የታሪክ ለውጥ ነው። ይህ ጉዞ ግን የአንድ ተቋም ብቻ አይደለም። የመንግሥት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማኅበራት፣ የኃይማኖት ተቋማት፣ የመገናኛ ብዙኅን ተቋማት፣ የምሁራን፣ የወጣቶች፣ የሴቶችና የእያንዳንዱ ዜጋ የጋራ ኃላፊነት ነው። የሀገር ዕጣ ፋንታ ለአንድ ቡድን ብቻ የሚተው አይደለም፤ በጋራ የሚገነባ እንጂ። ከምክክር ወደ ባህል፡- ምክክሩ ተጠናቀቀ ማለት የሀገሪቱ ችግሮች ተፈቱ ማለት አይደለም። እውነተኛው ስኬት የሚለካው የመደማመጥ ባህል በማኅበረሰቡ ውስጥ ሲሰርጽ ነው። በትምህርት ቤቶች፣ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ በመገናኛ ብዙኅን፣ በፖለቲካ ተቋማትና በየቤቱ የመነጋገር ባህል ካልጠነከረ፣ ምክክሩ የሰነድ ውጤት ብቻ ሆኖ ይቀራል። የእውነተኛ ዴሞክራሲ መሠረት ተመሳሳይ አስተሳሰብ መኖር አይደለም፤ የተለያዩ አስተሳሰቦችን በሰላም የመቀበል ባህል መኖር ነው። ልዩነት የችግር ምንጭ ሳይሆን የጥንካሬ ምንጭ ሲሆን ነው አንድ ሀገር ዘላቂ ሰላም የምታገኘው። የማጠቃለያ፡- የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚያስፈልገው ብልህ አመራር ብቻ አይደለም፤ ታጋሽ ዜጎችንም ይፈልጋል። ሀገር የምትገነባው በግንብ ሳይሆን በመተማመን ነው። ሰላም የሚጸናውም በፍርሃት ሳይሆን በፍትሕ ነው። ዛሬ የምንመርጠው የምክክር መንገድ ነገ ለልጆቻችን የምንተወው ታሪክ ይሆናል። ስለዚህ በኢትዮጵያን ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ተደራጅተው የሚመከርባቸው ስምንት ዐበይት አጀንዳዎች የዛሬ አጀንዳ ብቻ አይደሉም፤ የነገዋን ኢትዮጵያ የሚቀርጽ የትውልድ አደራ እንጂ። የዋናው ምክክር ጉባኤ ተመካካሪ የሕዝብ ወኪሎችም ከግልና ቡድን ፍላጎት ይልቅ የቀጣዩን ትውልድና ሀገርን ማስቀደም ይጠበቅባቸውል። ምክክር የቃላት ልውውጥ ብቻ አይደለም፤ የተሰበረ መተማመንን የሚጠግን፣ የተከፋፈለ ማኅበረሰብን የሚያቀራርብ፣ የትውልድ ታሪክን በአዲስ ተስፋ የሚጽፍ ሀገራዊ ጥበብ ነው። የምንወስነው ዛሬ የምንወርሰውን ነገ ይበይናል። ምክክር የሀገር መድኅን ነው፤ ኢትዮጵያም እየመከረች ነው።
ፈተናዎችን ወደ ዕድል የቀየረው የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪው ዘርፍ እመርታ
Jul 21, 2026 608
በሙሴ መለሰ ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የተከናወኑ ሁለንተናዊ የፖሊሲና የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች በኢንዱስትሪው ዘርፍ ላይ አዲስ መነቃቃትንና ተጨባጭ ስኬቶችን አስመዝግበዋል።መንግስት የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳን ቀርፆ ወደ ተግባር በመግባት፣ የግል ዘርፉን በማበረታታት እና የአምራች ኢንዱስትሪውን በማዘመን ረገድ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። ይህ መዋቅራዊ ሽግግር የሀገሪቱን የገቢና ወጪ ንግድ ከማመጣጠን ባለፈ፣ በሁሉም ንዑሳን የኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ተስፋ እንዲፈነጥቅ አድርጓል። የለውጡ ዓመታት የኢንዱስትሪ ስኬቶች መካከል በዋንኛነት የሚጠቀሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ ወር 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ “ኢትዮጵያ ታምርት” ሀገራዊ ንቅናቄ ነው። ይህ ንቅናቄ በፋይናንስ፣ በግብዓት እና በኃይል አቅርቦት እጥረት ምክንያት ተዘግተው የነበሩ አምራች ኢንዱስትሪዎችና ፋብሪካዎችን ዳግም ወደ ሙሉ ማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ አድርጓል። ንቅናቄው በተጀመረባቸው የመጀመሪያዎቹ ተከታታይ ዓመታት ብቻ የአገር ውስጥ ምርትን በማሳደግ በርካታ የውጭ ምንዛሬ የሚያስወጡ የውጭ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለመተካት የተቻለ ሲሆን፣በተለይም በጨርቃ ጨርቅ፣በቆዳና የቆዳ ውጤቶች፣ እንዲሁም በምግብና መጠጥ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ የምርት ዕድገት ተመዝግቧል። ይህም የሀገሪቱን የአምራች ኢንዱስትሪ አማካይ የማምረት አቅም በከፍተኛ ሁኔታ ማሳደጉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከኢቢሲ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፣ኢትዮጵያ ያጋጠሟትን እንደ ኮሮና ወረርሽኝና የአጎዋ (AGOA) ስረዛ ያሉ ዓለም አቀፋዊ ጫናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር በዘርፉ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችላለች። የኢንዱስትሪ መሪነቱን ከመንግሥት ወደ ግሉ ዘርፍ የማሸጋገር ሥራን ጨምሮ በተቀረጹ ስትራቴጂካዊ ምሰሶዎች አማካኝነት፣ ቀደም ሲል 8 ሺህ ገደማ የነበሩት አነስተኛና መካከለኛ ኢንዱስትሪዎች በአሁኑ ወቅት ከ26 ሺህ በላይ መድረሳቸውን አመልክተዋል። በተጨማሪም በተለያዩ ማነቆዎች ሥራ አቁመው የነበሩ 800 ገደማ ፋብሪካዎች አስፈላጊው ድጋፍ ተደርጎላቸው ወደ ማምረት መመለሳቸውንና ይህም የኢንዱስትሪዎችን አማካይ የማምረት አቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ ማድረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል። ተኪ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በማምረት ሂደትም እስካሁን ለውጭ ምርት ይወጣ የነበረውን 3.6 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያን የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል ለማድረግ በሎጂስቲክስና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ታላላቅ ፕሮጀክቶች እየተከናወኑ መሆኑን በወቅቱ ገልጸው ነበር። የኢትዮጵያን ግብርና ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር የተከናወኑት ተግባራት ሌላኛው የለውጡ ማሳያ ነው። በይርጋለም፣ቡሬ እና ቡልቡላ የሚገኙ የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ወደ ሙሉ ስራ መግባት አርሶ አደሩ ምርቱን በቀጥታ ለፋብሪካዎች እንዲያቀርብና እሴት የተጨመረበት ምርት ለውጭ ገበያ እንዲቀርብ መንገድ ከፍቷል። ይህ ስትራቴጂ የገጠር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማሳደጉም በላይ የኢንዱስትሪዎቹን የጥሬ ዕቃ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት ትልቅ እገዛ አድርጓል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በኬሚካል፣ በፋርማሲዩቲካል እና በሕክምና መገልገያ ቁሳቁሶች ማምረቻ ዘርፍ የታየው ስኬት ለሀገሪቱ የጤና ዋስትና ትልቅ ምሰሶ ሆኗል። ከዚህ ቀደም አብዛኛው የመድኃኒት ፍላጎት በከፍተኛ ወጪ ከውጭ የሚገባ ሲሆን፣ በለውጡ ዓመታት ግን የአገር ውስጥ መድኃኒት አምራቾች አቅም እንዲጎለብትና አዳዲስ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የፋርማሲዩቲካል ፋብሪካዎች ወደ ማምረት እንዲገቡ ተደርጓል። ይህም ለአገር ውስጥ ገበያ ጥራት ያላቸው መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ አስችሏል። በሌላ በኩል፣በኮንስትራክሽን እና ማዕድን ኢንዱስትሪ ላይ የታየው መነቃቃት የሀገሪቱን የመሠረተ ልማት ፍላጎት በራስ አቅም ለመደገፍ አስችሏል። አዳዲስ የሲሚንቶ እና የብረት ፋብሪካዎች ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉ እና ነባሮቹ አቅማቸውን እንዲያሳድጉ መደገፉ፣ በሀገሪቱ ለሚታዩት ሰፊ የኮሪደር ልማት እና የዘመናዊ ከተሞች ግንባታ ፕሮጀክቶች የአገር ውስጥ ግብዓትን በበቂ ሁኔታ ለመጠቀም አስችሏል። ማዕድናትን በተመለከተም፣ ጥሬ ግብአት ከመላክ ይልቅ እሴት ጨምሮ የመላክ ፖሊሲ በመተግበሩ የዘርፉን የሀገር ውስጥ ገቢ ድርሻ በከፍተኛ ሁኔታ አሳድጎታል። ለኢንዱስትሪው ዘርፍ መፋጠን ሌላው ዋነኛ አስደጋፊ የሆነው የኢነርጂ እና ታዳሽ ኃይል ልማት ዘርፍ ነው። የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች የውሃ፣ የንፋስ እና የፀሐይ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ መጠናቀቅና ወደ ሥራ መግባት አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያገኙትን የኃይል አቅርቦት እንዲያድግ አስችሏል። ይህ የአረንጓዴ የኃይል አቅርቦት የፋብሪካዎችን የማምረት አቅም ከማሳደጉም በላይ፣ የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ (Eco-friendly) እንዲሆኑ አድርጓል። ከነዚህ ዘርፎች ባሻገር፣ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ የምታደርገውን ሽግግር ተከትሎ በቴክኖሎጂው እና በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪ አበረታች ስኬቶች ተመዝግበዋል። በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የሞባይል ስልኮች እና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁሶች የመገጣጠም ስራ በስፋት እየተከናወነ ይገኛል።በተለይም ደግሞ ለአካባቢ ጥበቃና ለነዳጅ ወጪ ቅነሳ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያላቸው የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች (EVs) በአገር ውስጥ በስፋት መገጣጠም መጀመራቸው ሀገሪቱ በቴክኖሎጂ ራሷን እንድትችል እና ለሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ዘላቂ የስራ ዕድል እንዲፈጠር መሰረት የጣለ እርምጃ ሆኗል። በአጠቃላይ፣ የለውጡ ዓመታት በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ውስጥ መዋቅራዊ ሽግግር የተደረገባቸው ነበሩ ሊባል ይችላል። ከፖሊሲ ማሻሻያ ጀምሮ እስከ መሬት ወርደው የተተገበሩ ሀገራዊ ንቅናቄዎች ድረስ የተከናወኑት ተግባራት ሀገሪቱ በምርት ራሷን እንድትችል እና የውጭ ምርት ጥገኝነትን እንድትቀንስ አግዘዋታል። እነዚህ የተመዘገቡ ስኬቶች የኢትዮጵያን የነገ ብልጽግና የሚያረጋግጡ ጠንካራ መሰረቶች ናቸው።
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ
Jul 3, 2026 4593
ምክክር-ለኢትዮጵያ ብሩህ ነገ (በቀደሰ ተክሌ ከኢዜአ-ሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥቃቅን ችግሮች እያደጉ ሔደው ሀገር የማፍረስ አደጋን ከመደቀናቸው በፊት ከሥር መሠረቱ ማስተካከያ ማድረግ ብቸኛው መንገድ ሁሉን አካታች ሀገራዊ ምክክርን ማካሔድ ነው። በዚህም ራሳቸውን ከመጥፋት ታድገው ሀገር በሚል ስያሜ ሕልውናቸውን ያቆዩ ሀገራት አሉ። ከእነዚህም መካከል በአካታች ምክክር ከግጭት ወደ ዘላቂ ሰላምና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የተሸጋገሩትን ማንሳት ይቻላል። ለአብነት የቱኒዚያ ሀገራዊ ምክክር በዓለም ላይ ካሉ የቅርብ ጊዜ ስኬታማ ተሞክሮዎች ቀዳሚው ነው። እ.አ.አ በ2011 የ"አረብ አብዮት" መነሻ የነበረችው ቱኒዚያ፣ የፖለቲካ መሪዎች መገዳደል እና ከፍተኛ አለመረጋጋት ገጥሟት ነበር። አራት የሲቪክ ማህበራት (የሰራተኞች ማህበር፣ የጠበቆች ማህበር፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እና የነጋዴዎች ማህበር) በጋራ በመሆን "የቱኒዚያ ብሔራዊ ምክክር ኳርትት አቋቋሙ። ፖለቲከኞችን አስገድደው በጠረጴዛ ዙሪያ እንዲቀመጡ አደረጉ። በዚህም ሳቢያ ሀገሪቱ አዲስ እና ሁሉን አቀፍ ህገ-መንግስት ቀረጸች፤ ሰላማዊ ምርጫ ተካሄደ፤ ሀገሪቱ ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከመግባት ዳነች። ይህንን ምክክር የመሩት አራት ድርጅቶችም እ.አ.አ በ2015 የኖቤል የሰላም ሽልማትን አግኝተዋል። ደቡብ አፍሪካም ለዘመናት የዘለቀውን የዘረኝነት እና የአፓርታይድ ስርዓት ያቆመችው በጦርነት ሳይሆን በሁሉን አካታች ብሔራዊ ምክክር ነው። በኔልሰን ማንዴላ የሚመራው ኤ.ኤን.ሲ እና የነጮች ገዥ ፓርቲ በጥላቻ ፋንታ "ለነገዋ ሀገር" በሚል ይቅርታን እና ድርድርን አስቀደሙ። በምክክሩ ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሃይማኖት መሪዎች እና የነገዶች ተወካዮች በሙሉ ተሳትፈዋል። ያለምንም ደም መፋሰስ የስልጣን ሽግግር ተደረገ፤ በአለም ላይ እጅግ ተራማጅ የሚባል አዲስ ህገ-መንግስት ተቀረጸ፤ "የእውነትና የእርቅ ኮሚሽን" በማቋቋም ያለፈው ቁስል እንዲሻር ተደረገ። የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሁዋን ማኑኤል ሳንቶስን የኖቤል ተሸላሚነት ያበቃው ምክክር የተካሄደው በኮሎምቢያ መንግስት እና በኤፍ.ኤ.አር.ሲ አማፂያን መካከል ለአምስት አስርት ዓመታት የዘለቀው እና ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች ላለቁበት ጦርነት እልባትን ሰጥቷል። ምክክሩ ከሀገር ውጭ (በኩባ እና ኖርዌይ) በተደረጉ ድርድሮች የተደገፈ ሲሆን፣ ዋናው ትኩረቱ ግን የአርሶ አደሩን የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ፣ የፖለቲካ ተሳትፎ እና የአደንዛዥ ዕፅ ንግድን ማቆም ላይ ያተኮረ ነበር አማፂያኑ ሙሉ በሙሉ ጦርነቱን አቁመው ነፍጣቸውን አስረክበው፤ ወደ ሰላማዊ የፖለቲካ ፓርቲነት በመቀየር ሰላማዊ ትግላቸውን እንዲቀጥሉ ያስቻለ ነው። ኢትዮጵያም ዛሬ ለዘመናት ሲንከባለል የመጣን ዕዳ በጫንቃዋ ላይ ተሸክማ ቆማ ያንን አሳራፊ መድኃኒት ሽታለች። በዘመነኛው ዓለም ውስጥ ሆና በትላንት በሽታ ትታመማለች። የቀደሙት የጣሉት የስህተት እርሾ ዛሬም ከሊጥ ጋር እየተቦካ የኮመጠጠ የአኗኗር ሥርዓትን ትውልዱ እንዲጋፈጥ ምክንያት መሆን ከጀመረ ከራርሟል። ይህም የማይነጋ ሌሊት መስሎ ታይቶ ብዙዎችን ለቀቢጸ-ተስፋ ዳርጓል። የሰላም በር ዘግቶ ሰላም መፈለግ፣ መክፈቻ ቁልፍ በእጅ ይዞ ወደ ሌላ ማማተር ሆነና ነገሩ፤ ችግሩ ከነግሳንግሱ እያደገ ጥቁር ደመናን በሀገሬ ሰማይ ላይ ለመጋረድ አቅሙን ተጠቀመ። ሆኖም እንደተባለው የማይነጋ ሌሊት፣ የማይፈታ ሕልም የለም። "ፈጣሪም ሀገርን ያለ አንዳች አይተውም" ነውና ቃሉ፤ የተስፋ ብርሃን በኢትዮጵያ ሰማይ ሥር ፈነጠቀ። ወደ ውስጥ የሚመለከት፣ የራስ ማንነትን በኢትዮጵያዊ ቀለም የሚፈትሽ፣ ችግርን ሳይሆን መፍትሔን አነፍንፎ ገሃድ የሚያወጣ፣ ሀገር በቀል ዕውቀትን ያከበረና መልካም የሆኑ ነባር እሴቶችን ለችግሮቻችን ወጌሻ ያደረገ የለውጥ ተስፋ ከተፍ አለ። የመጋቢት ብስራት ኢትዮጵያን ወደ ፍካት ለመለወጥ በሀገር ፍቅር ስሜት አዳዲስ የሰላም መንገዶችን መክፈት ጀምሯል። ከመገፋፋት ይልቅ መደመርን፣ ከመካሰስም ይቅርታን የሚያስቀድመው የመደመር መንግሥት ሁሉንም ወገን አሸናፊ የሚያደርግ ሀሳብ ይዞ የምክክር ኮሚሽንን በማቋቋሙ አንድ እርምጃ ወደፊት የሚያስብል ተግባር በኢትዮጵያ ተወጠነ። በፖለቲካ እሳቤም ሆነ በሐሰት ትርክት አልያም የማያግባባ የትኛውንም ጉዳይ በመምዘዝ አኩርፎ ነፍጥ ማንገብን ልምድ ያደረገ የፖለቲካ ሥርዓት ባለበት፤ በአንጻሩ አቅም ኖሮት ሥልጣን የጨበጠ በሀሳብ የተቃረነውን በሚኮንንበትና ቀፍድዶ በወህኒ ቤት በሚያሰቃይባት ምድር በጠረጴዛ ዙሪያ ተቀምጦ መመካከር ትልቅ ትርጉም አለው። ይህ በደማቅ የታሪክ ቀለም የሚመዘገብ ክስተትም ነው። ምክክር በባህላችን አብሮን የኖረ የማንነታችን አካል የሆነ እሴታችን ቢሆንም ለፖለቲካው ሜዳ ግን እንግዳ ነገር ነውና። ጠላቶቻችን የኢትዮጵያን ሰላምና ዕድገት ማየት አይሹምና ሂደቱን ለማደናቀፍ ጥረዋል። በዚህም የመለወጥ መንገዳችንን ለመዝጋት ብዙ ጉድጓዶችን ምሰዋል። ጉድጓድ ለማዘጋጀት ከሩቅ ያመጡት ቁሳቁስ የለም፤ ከራሳችን ጋር አብሮ ባደገው የዘርኝነት፣ የጽንፈኝነትና አክራሪነት ገሶ (ትልቅ የጉድጓድ መቆፈሪያ) ነው እንጂ። በተለይ የኢትዮጵያ ጌጥ የሆነው ብዝኃ-ብሔር እና ሃይማኖት ብዙ ሳይደክሙ ያጠመዷቸው ፈጣን ውጤት የሚያስገኙላቸው ወጥመዶች ነበሩ። የወል ትርክት በሐሰተኛ ትረካ ተሞልቶ ለብዙዎች ሕይወት መጥፋት መንስኤ ሆነ። ጠንካራዋ ሀገር ኢትዮጵያ ግን መሠረቶቿ ዓለት ላይ ስለሆኑ ይህ ሁሉ የጥፋት ጎርፍና ነፋስ ሊያነቃንቃት አልቻለም። ይልቁንም በጽናት ቆማ ወጀብ ማዕበሉን ጸጥ የሚያደርግ ሀገርኛ መሣሪያ ታጥቃለች - የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን! በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ አማረ ፈንታው (ዶ/ር) እንደሚሉት፤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን መቋቋምና በአግባቡ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናቆ አጀንዳ መለየት መቻሉ የኢትዮጵያውያንን የሥነ-ልቦና እና የሞራል ከፍታ ማሳያ ነው። ለዚህም አመክንዮ ሲያስቀምጡ፤ ኢትዮጵያ በታሪኳ ለችግር መፍቻ ወደ ጠረጴዛ ሳይሆን ወደ ጫካ የሚሮጥ የፖለቲካ ሥርዓትን ነው ስታስተናግድ የቆየችው ብለዋል። ዛሬ ላይ ግን ያ ልክ አለመሆኑን የተረዳ ትውልድ በስብዕና ሞራል ላይ አዎንታዊ ተጽዕኖን አሳድሮ በጥይት ሳይሆን በሀሳብ ለማሸነፍ ራሱን አዘጋጅቷል። በጦር ግንባር ሳይሆን በጠረጴዛ ዙሪያ መፍትሔ ሊያገኝ ከራሱ ጋር ተስማምቷል። ይህ የመማርና የማደግ ውጤት ነው። የትናንት አካሔድ ሞትና ችግርን እንጂ ብልጽግናን አላተረፈም። መመካከር በእጃችን የነበረ አውጥተን ያልተጠቀምንበት ሀብታችን ነው። እንደ ተፈጥሮው ሁሉ እሴታችን የተሸፈነበት አቧራ በምክክር ተራግፎ በአብሮነት እና ዘላቂ ሰላም የምንደምቅባትን ጀንበር ልናይ ንጋት ላይ ተቃርበናል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በታሪኩ ትልቅ ተስፋ የጣለበት ጉዳይና ውጤቱን አጥብቆ የሻተበት አጀንዳ ምን ይሆን ተብሎ ቢጠና፤ "የምክክር ኮሚሽን ወደ ተግባር መግባት" ከሚለው በላይ ሌላ አጀንዳ ይኖራል ብሎ በልበ-ሙሉነት መግለጽ አይቻልም። ያለ ልዩነት ሁሉም ደግፎ በብርቱ ናፈቀው። የጥንት የአያት ቅድመ-አያቱ ወግ ነባርና አዲስ ሳይሆንበት በብርሃን ፍጥነት ዓላማውን ተረዳ። ተረድቶም ሳይቀር ተስፋውን ወደ ሚጨበጥ ውጤት ለመቀየር ባለው አቅም ሁሉ ለመደገፍ ተረባረበ። ዕድል የገጠመውም በቁርጠኝነት ሂደቱ ላይ ተሳተፈ። የዚህ ድምር ውጤት የምክክር ኮሚሽኑ ለኢትዮጵያ የነበሩ አለመግባባቶች ቁልፍ መፍቻዎች ናቸው ያላቸውን 8 ዋና ዋና የምክክር አጀንዳዎችን በስኬት ለመለየት አበቃው። የምክክሩ አጀንዳ ልየታ ሥርዓት ከአጀንዳ መለየት ያለፈ ትርጉም ያለው ነው። ስኬታማ የተቋም ግንባታ አንጸባራቂ ክስተት ጭምር እንጂ። አካታችነትን ባረጋገጠ መልኩ የሁሉንም አካባቢ ወግ፣ ባህልና ሥርዓት ተገንዝቦ ለሀገር የሚሆን አጀንዳ በስኬት መሰብሰብ የተቋማዊ ብቃት ማሳያ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ማድረግ የምትችል መሆኗን ገላጭ ሌላኛው የድል ገጽ ቢባል ግነት አይሆንም። አጀንዳዎቹ የኢትዮጵያን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት የሚያስችሉ ናቸው። ኃይል የተሞላበት የፖለቲካ ሥርዓትን በመገርሰስ ወደ ዴሞክራሲያዊ እና የተሟላ የሰላም ደሴት የሚያሸጋግር አጋጣሚ እንደሚሆንም ዶ/ር አማረ ይገልጻሉ። ምክክሩ ለኢትዮጵያ የለውጥ ጉዞ ወሳኝ ምዕራፍ ሲሆን በታሪክ ድርሳን የምናስቀምጠውና ወደፊት መጪው ትውልድ የሚያወሳው ኩነት ነው ብለዋል። መምህር ቢመርቅ በርሁን በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር ናቸው። እርሳቸው የምክክር ኮሚሽንን ተግባር ለኢትዮጵያ ያለውን መልካም ዕድልነት ሲገልጡ፤ ስር የሰደዱ ችግሮችን ከሥር የሚነቅል መሣሪያ ብለውታል። ከግለሰቦች የፖለቲካ ትርክት ተላቆ ወደ ተቋማዊ አሠራር መሸጋገሪያ ድልድይም እንደሆነ እንዲሁ። ኢትዮጵያ በበርካታ ነጠላ ትርክቶች ለሰላም እጦት ተዳርጋለች፣ በግለሰቦች ግላዊ ፍላጎት ብዙዎች ሕይወታቸውን ገብረዋል። ይህ የመጠፋፋት ሰንሰለት ይበጠስ ዘንድ ምክክሩ አስፈላጊ ነው። ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተግባራት ስኬት አካታችነት ትልቅ አቅም እንደሆነውም መምህር ቢመርቅ ያነሳሉ። በኮሚሽኑ የተሠራው የአጀንዳ ማሰባሰብና ልየታ እንዲሁም የምክክሩ ተሳታፊ መረጣ ሂደት በተማሩ ኃይሎች አልያም በፖለቲካ ልሂቃን ላይ ብቻ መሠረት ያደረገ አይደለም። በታችኛውም እርከን ወርዶ አርሶ አደሩን፣ አካል ጉዳተኛውንና ሌሎችንም ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው የኅብረተሰብ ክፍሎችን የጉዳዩ ባለቤቶች ናችሁ ብሎ ማሳተፉ በጎ ውጤት አመልካች ቅድመ-ሂደት ነበር ነው ያሉት። የአካታችነቱ ወሰን መስፋት ሰፊውን የማኅበረሰብ ጥያቄ ይዞ ለመነሳት አስችሎታል። የሁሉም ጥያቄ በስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ማለትም፦ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት አደረጃጀትና ቅርጽ እንዲሁም በፖለቲካ ሥርዓት፣ በፖለቲካ ውክልና እና በምርጫ ሥርዓት፣ በፌዴራል ከተሞች (የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና የድሬዳዋ አስተዳደር) ጉዳይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች፣ በተቋማት ግንባታ፣ በሕግ የበላይነት እና በሰብዓዊ መብቶች፣ በማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ጉዳዮች፣ በሙስና እና መልካም አስተዳደር እንዲሁም በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ሥር ተጠልሏል። እነዚህ አጀንዳዎች በአንድም በሌላም የመከፋፈል፣ በጎሪጥ የመተያየትና የጥርጣሬ መንፈስን በመንዛት ዜጎች እርስ በእርስ ከመተማመንና በአብሮነት ከመቀጠል ይልቅ "የኔ" የሚል አጥር ውስጥ እንዲገቡ ያደረጉ ናቸው። በሌላ በኩል "ተበደልኩ"ን ወልደው ኩርፊያን አስፍተዋል። ይህም በአንድ ወገን ሳይሆን ከሰሜን እስከ ደቡብ፣ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ በተለያየ መጠን የሚንጸባረቅ ችግር ነው። አሁን የመጣ ሳይሆን ትናንት የነበረ፣ ለዛሬ የተዘራና እንክርዳድ እያበቀለ ያለ የግጭት ዘር ነው። ሀገራዊ የሆኑ የፖለቲካ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን የአስተዳደር ሥርዓት ፈትሾ እውነትን እና ለነገ የሚበጀውን የወል ትርክት በሕዝብ ይሁንታ ሊያጸና ቀጠሮ የያዘው ኮሚሽኑ፤ በሁሉም ዜጎች ትብብር ሀገራዊ ድልን ያጎናጽፋል። ሰላምና ስኬት ለኢትዮጵያችን! አበቃሁ!!
በመደመር የተቃኘ ኢትዮጵያን የሚመጥን የከተሜነት ጉዞ
Jul 3, 2026 3746
በዮሐንስ ደርበው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ጥቅምት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተገኙ ጊዜ፤ የኮሪደር ልማት ዓላማ ኢትዮጵያን የሚመጥን ከተማ መገንባት መሆኑን ገልጸዋል። ከተማ ሲለማ ደግሞ ለነዋሪም ሆነ ለጎብኚ፤ ለዐይንም፣ ለጤናም ለእንቅስቃሴም ውበትና ምቾት ማላበሱ አይካድም። ትናንትን ከዛሬና ከነገ ጋር ማስተሣሠር የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ ወደ መግባባት መሸጋገሪያው ድልድይ! የኮሪደር ልማት ጽዱ ከተሞችን ይሠራል፤ከትራንስፖርት፣ ከትራፊክ ምልክቶች፣ ከብስክሌትና እግረኛ መንገድ ደኅንነት ጋርም ተጣጥሞ ተሠርቷል። በዚህ ዐውድ የኮሪደር ልማት ውበትም ምቾትም ነው። መሠረተ-ልማት ተጠብቆ ለረጅም ጊዜ እንዲጠቅምም የኮሪደር ልማት ሚና የላቀ ነው። ኢትዮጵያ በከተሞቿ እና ገጠራማ አካባቢዎቿ የኮሪደር ልማት እያከናወነች ነው። ይህ በኢትዮጵያ ከውበት በላይ ነው። · ማኅበራዊ መሥተጋብርን በመጠገን፡- ኢትዮጵያውያን ከሚታወቁባቸው አንዱ በየዐውዱ የሚገለጠው ጥብቅ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸው ነው። በጋራ መንቀሳቀስ፣ መጫወት፣ ከቤት ወጣ ብለው መመካከር የኑሯቸው አካል ነው። ይሁን እንጂ በተለይም ከተሜው ከወዳጅ ጋር በኅብረት በእግር ወይም በብስክሌት ለመንቀሳቀስ፣ አረፍ ብሎ የሚያወጋበት በቂ አረንጓዴ ስፍራና ፓርኮች ባለመኖራቸው ማኅበራዊ መሥተጋብሩ እየላላ የመጣ ይመስላል። አሁን የኮሪደር ልማት በደረሰባቸው ከተሞች፤ሰዎች ሲያሻቸው በእግር አሊያም በብስክሌት ከወዳጆቻቸው ጋር የልባቸውን እያወጉ ለመንቀሳቀስ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ሰዎች በእንቅስቃሴያቸው መሐል ዐረፍ ማለት ቢሹም ችግር የለም፤ አሁን እንደ ድሮ አይደለምና። አረንጓዴ መናፈሻ ስፍራ ፍለጋ ከከተማ መውጣት አያሻም። በሌላ በኩል ወጣቶች እና ሕጻናት ኳስ የሚጫወቱበት ስፍራ መመቻቸቱ ጤናን ከመጠበቅ ባሻገር፤ ማኅበራዊ መሥተጋብራቸውን ያጠናክራል። · ጤናማ አከባቢን በመፍጠር፡- የኮሪደር ልማት ለሰው ልጆች ከቸራቸው ጥቅሞች አንዱ፤ ጤናማ ከባቢን መፍጠር ነው። በተለይም በደካማ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ለሚታሙ ከተሞች የኮሪደር ልማት ሁነኛ መፍትሔ ሆኗል። ይህ ደግሞ በቀጥታ ከነዋሪዎች ጤና ጋር ይገናኛል። ደግሞም በንጹህ አካባቢ የመኖር መብትን ማስጠበቅ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በኮሪደር ልማት ሰፋፊ መንገድ ከመሥራት ባለፈ ታዳጊዎች እግር ኳስ የሚጫወቱባቸው የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እና የእግረኛ መንገዶች ተሠርተዋል ያሉትም ለዚሁ ነው። · በሥራ ዕድል ፈጠራ፡- የኮሪደር ልማት የዘመቻ ሥራ አይደለም።በትንሹ በአንድ ከተማ ወይም አካባቢ ተጀምሮ እየሰፋ ይቀጥላል። በዚህ ሂደት የሚፈጠረውን የሥራ ዕድል ማሰብ አያዳግትም። እንዲሁም የኮሪደር ልማት ሥራዎች ሲከናወኑ፤ ለሥራ ዕድል ፈጠራ የሚያገለግሉ የመኪና ማቆሚያ፣ ሱቆች እና መሰል ለንግድ ተግባራት እንዲበጁ ተደርገው ነው። የኮሪደር ልማት ከከተሜነት ዕድገት ጋር የተሣሠረ ልማት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መናገራቸው ይታወሳል። · በገጽታ ግንባታ ረገድ፡- ከተሞች ሲጸዱና ምቹ ሲሆኑ በዓለም ዘንድ መታወቂያ ይሆናሉ። ነዋሪም በኩራት ስለአካባቢው በየሄደበት አምባሳደር ሆኖ ይመሠክራል። ቱሪስቶችንም ይስባሉ። የቆይታ ጊዜያቸውንም ለማራዘም ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያበረክታሉ። ዓለም አቀፍ፣ አኅጉር አቀፍ እና ሀገር አቀፍ ጉባዔዎች እንዲካሄድባቸውም እንዲመረጡ ያስችላል። በከተሞች ከሚሠራው የኮሪደር ልማት ባሻገር፤ የገጠር ኮሪደር ልማት በውጤታማነት እየተሠራ ነው። ይህም ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ ፍትሐዊ መሰረተ-ልማት ለዜጎች መቅረቡን ያሳያል። ኮሪደር ልማት ኢትዮጵያውያን የተሻለ ኑሮ ይገባቸዋል በሚል የተጀመረ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ተናግረዋል። የተሟላ ብልጽግና የምናረጋግጠው በዚሁ መንገድ ነውም ብለዋል። የተሻለ ኑሮ ፍለጋ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረገውን ፍልሰት በመቀነስ የተመጣጠነ ዕድገት በሁሉም አካባቢ ለማምጣት የገጠር ኮሪደር ልማት መጠናከር ጠቀሜታው የጎላ ነው። የገጠር ኮሪደር ልማት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ሥነ-ምኅዳራዊ ፋይዳን ጨምሮ ብዙ ጥቅም አለው፤ ይህም ዘላቂ ልማትና የተረጋጋ ኅብረተሰብ ለመፍጠር ከፍተኛ ሚና ይጫወታል። የከተሞች መዋብና ምቹ መሆን ለነዋሪው ነው፤ በቀጥታ ተጠቃሚውም ሕዝቡ። ስለዚህ መንግሥት ከሚያከናውናቸው በተጨማሪ ባለሃብቱ፣የመንግሥትም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ኅብረተሰቡ የኮሪደር ልማትን በተነሳሽነት ለማስፋፋት መትጋት ይጠበቅበታል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 10799
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 20959
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 13990
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 19746
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ቱሪዝም - የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ በኢትዮጵያ!!
Jul 27, 2026 66
በቤተልሔም ባህሩ መግቢያ፡- ኢትዮጵያ የሰው ልጅ ሥልጣኔ መነሻ፣ የታሪክ መዝገብና የቱባ ባህል ሀብት ካስማ ምድር መሆኗ የአደባባይ ሃቅ ነው። የሺህ ዓመታት ታሪኮች፣ በዘመናት የተገነቡ ዕድሜ ጠገብ የሕንፃ አሻራዎች፣ ከትውልድ ወደ ትውልድ የተላለፉ ባህላዊ እሴቶችና በዓላት ኢትዮጵያን በዓለም የቱሪዝም ካርታ ላይ ልዩ ስፍራ የሚያስይዙ መለያ ምልከቶቿ ናቸው። እንደ የአፄ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የአልነጃሺ መስጂድ፣ የሐረር ጀጎል እና የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግሥት ያሉ ታሪካዊ ቅርሶች የጥንታዊ ሥልጣኔ፣ የሃይማኖታዊ ትውፊትና የአርክቴክቸር ብልጽግና ሕያው ምስክሮች ናቸው። በተጨማሪም መስቀል፣ ጥምቀት፣ የገዳ ሥርዓት፣ አሸንዳ/አሸንድዬ፣ ኢሬቻ፣ ፊቼ ጨምበላላ እና ጊፋታ የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላትም ዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳቡ የማይዳሰሱ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች የሚያንጸባርቁ የኢትዮጵያ ውድ ሃብቶች ናቸው። እነኝህ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶች በዓለም አቀፍ ዕውቅናም የተቸራቸው ናቸው። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት 16 የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቿን በዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ዝርዝር ማስመዝገብ ችላለች። በቅርቡ የተመዘገቡት የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የሐረር ሸዋል ኢድ ኢትዮጵያ ለዓለም ህዝብ ያበረከተቻቸው አዳዲስ የመስህብ ትሩፋቶች ናቸው። እነዚህ ቅርሶች የኢትዮጵያን ገጽታ በዓለም ላይ ከማጉላት ባሻገር በየዓመቱ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ጎብኚዎችን በመሳብ ለውጭ ምንዛሬ ግኝት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለኢኮኖሚ እንቅስቃሴ መነቃቃት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛል። ይሁን እንጂ ኢትዮጵያ በብዝኅ ተፈጥሮ፣ ታሪክና ባህል የታደለች ሀገር ብትሆንም ለረጅም ጊዜ እነዚህን ዕምቅ ሃብቶች በዘመናዊ የቱሪዝም አቀራረብ ለማልማት፣ ለዓለም አቀፍ ገበያ በብቃት ለማስተዋወቅና ወደ ዘላቂ የኢኮኖሚ ጥቅም ለመቀየር የሚገባውን ያህል ትኩረት ሳይሰጣቸው ቆይቷል። በመሆኑም የቱሪዝም ዘርፍ የሀገሪቱን እውነተኛ አቅም በሚመጥን ደረጃ መጠቀም ሳይቻል ቆይቷል። በሀገራዊ ለውጡ ማግስት በኢትዮጵያ በተተገበረው ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ አምድ እንዲሆን በመደረጉ ልዩ ትኩረት አግኝቷል። ይህም ዘርፉ ከተለምዷዊ አካሄድ ወጥቶ ወደ ዘመናዊ ልማት፣ ወደ ከፍተኛ ተወዳዳሪነትና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚሸጋገርበትን መሰረት ጥሏል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተተገበሩት "የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች ለቱሪዝም ዘርፉ ለውጥ ወሳኝ ምዕራፍ ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች በተፈጥሮ፣ በታሪክና በባህል የታደሉ ስፍራዎችን በዘመናዊ መንገድ በማልማት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች ማራኪ መዳረሻዎችን መፍጠር ችለዋል። በዚህም የጎብኚዎች ፍሰት ጨምሯል፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት አድጓል፣ የየአካባቢዎቹ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎች ተነቃቅተዋል፣ የኢትዮጵያም የቱሪዝም ገጽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ አዲስ መልክ እያገኘ መጥቷል። ዛሬ ቱሪዝም ለኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ መሣሪያ ብቻ ሳይሆን፣ የኢኮኖሚ ዕድገት ማረጋገጫ፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት ምንጭ፣ የሥራ ዕድል መፍጠሪያ እና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ ዋና ሞተር በመሆን እያገለገለ ይገኛል። ኢትዮጵያ፤ በአፍሪካ ቀዳሚ የዓለም ቅርሶች ማዕከል ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከ16 በላይ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን ያስመዘገበች በአፍሪካ ቀዳሚ ሀገር ናት። ከሚዳሰሱት ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የፋሲል ግቢና የጎንደር ቤተ መንግስት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የጢያ ትክል ድንጋዮች፣ የታችኛው ኦሞና የአዋሽ ሸለቆዎች፣ የሐረር ጁገል ግንብ እንዲሁም የባሌና የስሜን ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮች ይገኙበታል። ከማይዳሰሱት ቅርሶች ደግሞ የመስቀል ደመራ በዓል፣ የጥምቀት በዓል፣ የፊቼ ጨምበላላና የገዳ ሥርዓት ተጠቃሽ ናቸው። ለቱሪዝም ዘርፍ በተሰጠው ትኩረት እነዚህን ዓለም አቀፍ ቅርሶች በተሻለ ሁኔታ የመጠበቅና የማደስ ሥራዎች የሚሰሩበትን ዕድል ፈጥሯል። በተመሳሳይም አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት ኢትዮጵያን ይበልጥ ተወዳዳሪና ማራኪ የቱሪዝም መዳረሻ ማድረግ የሚያስችል ሰፊ ሥራ እየተከናወነ ይገኛል። ሶስቱ ሜጋ ፕሮጀክቶች ገበታ ለሸገር - የአዲስ አበባን ገጽታ የቀየረ የለውጥ ጥንስስ!! የገበታ ለሸገር መርሃ ግብር የአዲስ አበባን የከተማ ገጽታ በመቀየር የቱሪዝም ስበት ማዕከልነቷን ያጎለበተ የለውጥ ምዕራፍ ነው። በመርሃ ግብሩ የተገነቡት የእንጦጦ፣ የአንድነትና የወዳጅነት ፓርኮች፣ የሳይንስ ሙዚየምና የዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም ከተማዋን ከዲፕሎማሲ ማዕከልነቷ ባሻገር ዓለምአቀፍ የኮንፍረንስ ቱሪዝምና የመዝናኛ ጉብኝት ማዕከል እንድትሆን መሠረት ጥለዋል። ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ የተተገበሩት የከተማ ኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎች ለበርካታ ዓመታት ችላ የተባሉ ስፍራዎችን ወደ አረንጓዴ፣ ዘመናዊ እና ለሁሉም ተደራሽ የመዝናኛ ከባቢነት ቀይረዋል። ይህም ከተማዋን ለጎብኚዎች ይበልጥ ማራኪ ከማድረጉ በተጨማሪ ለነዋሪዎች ጤናማ፣ ንጹህና ምቹ የከተማ ምኅዳር መፍጠር አስችሏል። ገበታ ለሸገር የአዲስ አበባን የከተማ ውበት በማሳደግ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋትና የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችን በማበራከት የቱሪዝም ዕድገትን ያፋጠነ ብቻ ሳይሆን፣ የነዋሪዎችን የኑሮ ጥራት ያሻሻለና የዘመናዊ ከተማ ግንባታ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ ስኬታማ ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር - ከገበታ ለሸገር የተቀዳ የሀገር በረከት!! ገበታ ለሀገር መርሃ ግብር በገበታ ለሸገር የተጀመረውን የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ወደ መላው ሀገር በማስፋት፣ በየክልሉ የሚገኙ ዕምቅ ተፈጥሯዊ፣ ታሪካዊና ባህላዊ ሃብቶችን ወደ ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎች የቀየረ ትልቅ የልማት ፕሮጀክት ነው። በዚህ ማዕቀፍ የወንጪ ኢኮ ቱሪዝም፣ የጎርጎራ፣ የኮይሻና ሌሎች መሰል ፕሮጀክቶች በመገንባታቸው የክልሎችን የቱሪዝም አቅም በእጅጉ በማሳደግ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ጎብኚዎች አዳዲስና ማራኪ የጉብኝት መዳረሻዎችን ፈጥረዋል። በተመሳሳይም ፕሮጀክቶቹ በክልሎች መካከል ፍትሐዊ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ሥርጭት እንዲፈጠር በማድረግ፣ የመንገድ፣ የመስተንግዶ፣ የመዝናኛና ሌሎች ዘመናዊ አገልግሎቶችን የሚሰጡ መሰረተ ልማቶች በስፋት እንዲገነቡ አስችለዋል። ይህም የቱሪዝም ጥቅም በተወሰኑ ከተሞች ብቻ እንዳይገደብ በማድረግ፣ የአካባቢ ኢኮኖሚን በማነቃቃት፣ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠርና የክልሎችን የልማት ተጠቃሚነት በማሳደግ የቱሪዝም ዕድገትን ወደ ሀገራዊ የኢኮኖሚ ለውጥ የቀየረ ውጤታማ ፕሮጀክት ሆኗል። ገበታ ለትውልድ - የቱሪዝም ልማትን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ያሸጋገረ የአገልግሎት ዘርፍ እመርታ!! ገበታ ለትውልድ መርሃ ግብር በገበታ ለሸገርና ገበታ ለሀገር የተጀመረውን የቱሪዝም ልማት በማስቀጠል፣ የተፈጥሮ ሀብቶችን በዘላቂነት ከመጠበቅ ጋር በማጣጣም ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ማልማት ያስቻለ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። መርሃ ግብሩ የቱሪዝም ልማትን ከኢኮኖሚ ዕድገት ባሻገር ለትውልድ የሚተርፍ ሃብት የመጠበቅ እሳቤ ጋር አሰናስሎታል። በዚህ ማዕቀፍ በቅርቡ የተመረቀው የአርባ ምንጭ ኮንፍረንስ ሪዞርትን ጨምሮ፣ የሸበሌ፣ የሎጎ ሐይቅ ሪዞርቶችና የሀሮ ደንዲ ኢኮ ሎጅ ተጠናቀው ወደ ሥራ ገብተዋል። በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተገነቡና እየተገነቡ የሚገኙ ሌሎች የቱሪስት መዳረሻ የልማት ሥራዎችም ዘርፉን በማነቃቃት ከፍተኛ አቅም ፈጥረዋል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም መዳረሻዎች በማስፋፋት፣ አገልግሎትን ወደ ዓለምአቀፍ ደረጃ በማሳደግና የሀገር ውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘም በኩል ጉልህ ሚና እየተጫወቱ ነው። በተመሳሳይም ለአካባቢያዊ የኢኮኖሚ መነቃቃት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለውጭ ምንዛሬ ግኝት እንዲሁም ኢትዮጵያን በአፍሪካ ተመራጭ የቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ በማሳለጥም ገንቢ ሚና እየተወጡ ይገኛል። የኮሪደር ልማትና አዳዲስ የቱሪዝም ትስስሮች በኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ተጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች እየተስፋፋ የሚገኘው የኮሪደር ልማት የከተሞችን ውበት እያፈካ ይገኛል። በዚህም የከተሞችን መሠረተ ልማት፣ የአረንጓዴ ስፍራን፣ የመዝናኛና የእግረኛ መንገዶችን በስፋት በማልማት ለነዋሪዎችም ሆነ ለጎብኚዎች ምቹና ማራኪ የከተማ ምኅዳር ፈጥሯል። ይህ ልማት የከተሞችን ውበት ከማሳደግ ባለፈ፣ የቱሪዝም መሠረተ ልማትን በማጠናከር፣ የጎብኚዎችን ቆይታ በማራዘምና የአካባቢውን ኢኮኖሚ በማነቃቃት ዘርፉን ወደ ከፍተኛ የዕድገት ምዕራፍ አሸጋግሯል። የኮንፍረንስ ቱሪዝም (MICE) የኮሪደር ልማቱ አዲስ አበባን ውብ፣ ዘመናዊና ዓለም አቀፍ ከተማ በማድረግ፣ የአፍሪካ ኅብረትና የበርካታ ዓለም አቀፍ የዲፕሎማቲክ ተቋማት መቀመጫ የሆነችውን ከተማ ወደ ቀዳሚ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል ቀይሯታል። አዲስ ዓለም ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የሳይንስ ሙዚየምና ሌሎች ዘመናዊ መዳረሻዎች በአንድ ጊዜ በሺዎች የሚቆጠሩ ተሳታፊዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ተቋማትን በማፍራት ከተማዋን ለሀገራዊ፣ ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች፣ ኤግዚቢሽኖችና ትላልቅ የንግድ መድረኮች ተመራጭ አድርጓታል። ለአብነትም የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ፣ የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) እና መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮችን በብቃት ማስተናገድ ተችሏል። በተለይም የአፍሪካ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ተከታዮች ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ሀብቶች ለዓለም እንዲያስተዋውቁ ምቹ መድረክ ፈጥሯል። ይህም የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ገጽታ ከማጎልበት ባለፈ የቱሪዝም ማስተዋወቅን በዲጂታል ዘመን ከፍ ወዳለ ደረጃ አሸጋግሮታል። የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም የስቶፕ ኦቨር ቱሪዝም መርሃ ግብርም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በመጠቀም በአዲስ አበባ የሚያልፉ ትራንዚት መንገደኞችን ከመሸጋገሪያነት ብቻ ወደ ጎብኚነት ለመቀየር አስፈላጊ ዕድል ፈጥሯል። በዚህም መዲናዋን ከቱሪስት መሸጋገሪያነት ወደ ቱሪዝም ማዕከልነት ቀይሯታል። በከተማዋ የተከናወነው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማትም ውብና ማራኪ የከተሜነት ገጽታን በመፍጠር፣ መንገደኞች በቆይታቸው የተለያዩ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ዘመናዊ መዳረሻዎችን እንዲጎበኙ አስችሏል። ይህም የቱሪስቶችን የቆይታ ጊዜ ከማራዘም ባለፈ፣ የመስተንግዶ፣ የትራንስፖርት፣ የባህልና የንግድ አገልግሎቶችን በማነቃቃት ለሀገሪቱ ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲፈጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። የተመዘገቡ ተጨባጭ ውጤቶች በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል። በዚህም ከታሪካዊ ቅርሶች ባሻገር የባህል፣ የተፈጥሮ፣ የኢኮ ቱሪዝምና የኮንፍረንስ ቱሪዝም መዳረሻዎችን በማስፋፋት፣ ኢትዮጵያ ያላትን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በተሻለ ሁኔታ እንድትጠቀም መንገድ ከፍተዋል። የቱሪዝም መዳረሻዎች መስፋፋት የውጭ ጎብኚዎችን ቁጥር ከማሳደጉ ባለፈ የሀገር ውስጥ ቱሪዝም እንዲጠናከር በማድረግ ዜጎች የሀገራቸውን ታሪክ፣ ባህልና ተፈጥሯዊ ጸጋዎች እንዲያውቁና እንዲጎበኙ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል። ይህም የቱሪዝም ገቢን በማሳደግ፣ የውጭ ምንዛሬ ምንጭን በማስፋፋትና ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚጨምረውን አስተዋጽኦ ከፍ አድርጎታል። በተጨማሪም ዘርፉ ለሥራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አበርክቶ እያስገኘ ነው። በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በኢኮ ቱሪዝም፣ በባህል ውጤቶች ንግድና በተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች በመሳተፍ በኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድል ፈጥሯል። በመሆኑም ቱሪዝም ከመዝናኛ ዘርፍ ባሻገር የልማት፣ የሥራ ዕድልና የኢኮኖሚ ለውጥ ማስፈንጠሪያ ምሰሶ እየሆነ መጥቷል። ማጠቃለያ ኢትዮጵያ ጥንታዊ የታሪክ፣ የባህልና የተፈጥሮ ሃብቶቿን ከዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ጋር በማስተሳሰር፣ በኮሪደር ልማት፣ በተሻሻለ የአገልግሎትና በዓለም አቀፍ የማስተዋወቅ ስራዎች በቱሪዝም ዘርፍ አዲስ ምዕራፍ እየጻፈች ትገኛለች። የተቀናጀው የልማት አቅጣጫ ሀገሪቱ ለዘመናት የያዘቻቸውን ዕምቅ የቱሪዝም ሀብቶች ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ጥቅም፣ የሥራ ዕድልና የሀገር ገጽታ ግንባታ ማጎልበቻ እየቀየረ ይገኛል። ዛሬ ቱሪዝም የኢኮኖሚ አንድ ዘርፍ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኮንፍረንስ ቱሪዝም ማዕከል፣ የባህልና ታሪክ መዳረሻ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ ሀገር ለማድረግ የሚያግዝ ስትራቴጂያዊ አቅም ሆኗል። ይህም ለሀገሪቱ የዲፕሎማሲ ገጽታ፣ የባህል ትስስርና የዓለም አቀፍ ተሳትፎ አዲስ ዕድል ፈጥሯል። በተለይም የዲጂታል ዘመን የቱሪዝም ዘርፉን ለማስተዋወቅ ዕድሎችን የሚያሰፋ በመሆነኑ ይህንኑ በመጠቀም፣ እንደ አይሾ ስፒድና ዲላን ፔጅ ያሉ ዓለም አቀፍ ተከታይ ያላቸው የማኅበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የኢትዮጵያን ውብ ተፈጥሮ፣ ባህልና ታሪክ ለዓለም በማስተዋወቅ የሀገሪቱን ዓለምአቀፍ ትኩረት እያሳደጉ ናቸው። በመሆኑም ኢትዮጵያ ቱሪዝምን ከጉብኝት ዘርፍ ባሻገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የሀገር ገጽታ ግንባታና የዓለም አቀፍ ትስስር መሣሪያ በማድረግ ወደ አዲስ የቱሪዝም ዘመን እየተሸጋገረች ትገኛለች። ጭስ አልባው ኢንዱስትሪ፤ የኢትዮጵያ አዲሱ የብልፅግና ዘመን የኢኮኖሚ መሰሶነቱን በተግባር እያስመሰከረ ይገኛል።
ቱሪዝም- የኢትዮጵያ የማከናወን ዐቅም ማሳያ
Jun 29, 2026 7156
በዮሐንስ ደርበው “ሀገራችን ከቱሪዝም ልታገኛቸው የምትችላቸውን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ሁሉ ከቀረው ዓለም ጋር ተወዳድራ እንድታገኝ፣ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ጎብኚ ወደ ሀገራችን መሳብ አለብን። ለዚህም የተለያዩ ስልታዊ መላዎች ነድፈን እየተንቀሳቀስን እንገኛለን (የመደመር መንግሥት 273)። የቱሪዝም ኢንዱስትሪ የለውጡ መንግሥት እመርታዎችን ካስመዘገበባቸው ዘርፎች አንዱ ነው። መንግሥት ከአምሥቱ የትኩረት መስኮች አንዱ አንድርጎም በጥናት፣ አካባቢያዊ ፀጋን ዐውቆና ለይቶ በተደመረ ዐቅም ባከናወናቸው ሥራዎች በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገር፣ በገበታ ለትውልድ፣ በኮሪደር ልማት፣ በወንዝ እና የወንዝ ዳርቻዎች ልማት እሠየው ያሰኙ ተግባራት አከናውኗል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በገበታ ለሸገር የተገለጠው የተደመረ ዐቅም - ለኢትዮጵያ ስኬቶች እንደማሳያ የመልከ መልካሟ ብዙ መልኮች ለአስም በሽታ አጋላጭ ምክንያቶችና ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተመረቀው ከእንጦጦ - ቀበና የተከናወነው የወንዝና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትም ለጎብኚም ለነዋሪም ምቹ ከባቢን በመፍጠር ረገድ እየተደረገ ያለውን ትጋት ያስረዳል። ምረቃውን ተከትሎ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባጋራው መረጃ፤ “መቆሸሽ እኛ አይገባንም፣ መጠልሸት እኛ አይገባንም፣ ማነስ እኛ አይገባንም! ሠርተን እንደምንችል ማሳየት ያስፈልጋል” ሲል የሥራውን ማራኪነትና ውበት ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትሩም በዚሁ ወቅት፤ የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን ሲሉ በቀጣይ ካለፈው የበለጠ እንደሚሠራ አመላክተዋል። ገንዘብን፣ ዕውቀትን፣ ጉልበትን፣ ሐሳብን፣ የአመራር ብቃትን ስንደምር የሚከሰተው ነገር እንደዚህ ያለው ውበት ይሆናል ሲሉም አስገንዝበዋል። በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው (ገጽ 256) ላይም፤ “የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ሀገራት በዘመናቸው ሁሉ የሠሩትንና ተፈጥሮ ያደለቻቸውን መልካም ገጽታ በኩራት ለዓለም የሚያስተዋውቁበት፣ ‘ሀገሬ ይሄንን ትመስላለች’ የሚሉበት መድረክ ነው። ሀገርን በሚያኮራና ለሌሎች ለመጋበዝ በማያሳፍር መልኩ መገንባት፣ ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ መሠረቱ ነው።” ያሉትም የበለጸገች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ በቁጭት መነሳታቸውን ይገልጻል። ነገን ዛሬ እየሠራች ያለችው ኢትዮጵያ ካላት ላይ ሳትነፍግ የገንዘብም ሆነ የሰው ኃብቷን ቱሪዝም ላይ ስታውል፤ አንድም የኢንዱስትሪውን ዐዋጭነት ብሎም የዜጎቿን በየዘርፉ ዘላቂ ተጠቃሚነት በመገንዘብ ነው። እዚህ ላይ ለሀገር ገቢ በማስገኘት እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ዘርፉ የሚያበረክተውን ጥቅም ማጤን ይገባል። በአዲስ አበባ ከተከናወኑ ቁልፍ የቱሪዝም ልማቶች መከካከል፤ የመስቀል ዐደባባይ ቅርስን ማንበርና ማዘመን፣ ከአዲስ አበባ ልማት ጋር ተሣሥሮ የተገነባው የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ በአዲስ መልክ የታደሠው ብሔራዊ ቤተ-መንግሥት፣ የአምሥቱ ዕውቀት ተኮር ማዕከላት (አብርኾት ቤተ-መጻሕፍት፣ ሳይንስ ሙዝየም፣ የሀገር በቀል ዕጽዋት ማሳያ፣ የአንድነት ቤተ-መዛግብት እና የማዕድን ሙዝየም) ግንባታ፣ የአዲስ አበባ ኮንቬንሽን ማዕከል እና ሌሎችም ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ ጎብኚዎች የሚያርፉበት ሎጂና ሆቴሎች ግንባታም በስፋት እየተከናወነ ይገኛል። ገበታ ለሸገር ብሎ ከአዲስ አበባ የተነሳው የቱሪዝም ልማት በገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ ወደ ክልሎች ተስፋፍቶ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጂዎች እንዲገነቡ አስችሏል። የተገነቡት ሎጂዎች ደግሞ ለጎብኚዎቹ ምቾትን የሚያስጠብቁ መሠረተ-ልማቶችን ስበዋል። በርካታ ጎብኚ መሳብና ገቢን ማሳደግ፣ በጎ ገጽታን መሸጥ፣ ለዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር፣ የበለጸገች ኢትዮጵያ ዕውን ማድረግ እየተከናወኑ ላሉ ተግባራት ሁሉ ግቦች ናቸው። መንግሥት ዕምቅ የጎብኚዎች መስኅብ ዐቅም የሆኑና አቧራ ለብሰው የተደበቁትን ፀጋዎች ውበታቸውን ገላልጦ እያሳዬ ያለውም ለዚህ ነው። ቱሪዝም በቀጥታ ዜጎች (ሰዎች) የሚጠቀሙበት ኢንዱስትሪ ነው። ለዚህ ደግሞ ሰዎች ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርና መጠበቅ ይኖርባቸዋል።መሠረተ-ልማቶችን በመጠበቅ እንዲሁም ከመንግሥት ጎን በመሆን በሚፈለጉበት ሁሉ ንቁ ተሳትፎ ማድረግም ይጠበቅባቸዋል። ዜጎች ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ቁርጠኝነታቸውን ያረጋገጡበት ጠቅላላ ምርጫ ምክክር - ወደ መግባባት መሻጋገሪያው ድልድይ! ያልተቋረጠ የስኬት ጉዞ #የኢትዮጵያ_ዜና_አገልግሎት #Ethiopian_News_Agency #ቱሪዝም #PMOEthiopia #በኢዜአ_ዐይን #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers