ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 የውድድር ዓመት ኮከቦች ሽልማት ሊያበረክት ነው
Sep 2, 2026 40
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 ዓ.ም የውድድር ዓመት ምርጦች ዕውቅና የመስጠት መርሐ ግብር ጳጉሜን 3 እንደሚያካሂድ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ፣ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሊግ አንድ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ፣ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እንዲሁም ምስጉን ዳኛ እና ረዳት ዳኞች ሽልማት ይበረከታል። የሽልማት ስነ ሥርዓቱ የሚካሄድበት ቦታ በቀጣይ እንደሚገለጽ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
ዲፕሎማሲ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላም ግንባታ ያለው ፋይዳ ላይ ያተኮረው የአሰፋ አብዩ (ዶ/ር) መጽሐፍ ተመረቀ
Sep 2, 2026 104
አዲስ አበባ፣ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አሰፋ አብዩ(ዶ/ር) የዲፕሎማሲ ሥራ በአፍሪካ ቀንድ ለሚካሄደው የሰላም ግንባታ ሂደት ያለውን ቁልፍ ሚና አስመልክቶ የጻፉት አዲስ መጽሐፍ ተመርቋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ መኮንን አዳራሽ በተካሄደው የመጽሐፉ ምረቃ ስነ ስርዓት ላይ ማኅበረሰብ፣የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት እንዲሁም ምሁራን ተገኝተዋል። ዲፕሎማሲ ለሰላም ግንባታ ስትራቴጂ በአፍሪካ ቀንድ ያለው ተሞክሮና ፈተናዎቹ (Diplomacy As A Peace Building Strategy:-Approaches and challenges in the Horn Africa) የተመረቀው መጽሐፍ ርዕስ ነው። የመጽሐፉን ዳሰሳ ያቀረቡት የብሔራዊ ደኅንነት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንደገለጹት፤ የመጽሐፉ ዋነኛ ዓላማ ዲፕሎማሲ ለሰላም ግንባታ ያለውን ፋይዳ አጉልቶ ማሳየት ነው፡፡ ፀሐፊው በዳበረ ሙያዊ ልምድ፣ የአመራርነት ክህሎት፣ በትምህርት ባገኙት እውቀትና ጥልቅ ጥናት ታግዘው ያዘጋጁት መጽሐፍ መሆኑን ከንባባቸው መገንዘባቸውን የገለጹት ፕሬዚዳንቱ፤ ዲፕሎማሲ ከሰላም ግንባታ ባሻገር ብሔራዊ ጥቅምና ደኀንነትን ለማረጋገጥ ቁልፍ ማሣሪያ መሆኑ በትኩረት እንደተተነተነ ጠቁመዋል፡፡ ዲፕሎማሲያዊ መንገድ በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ግጭቶችንና ጦርነቶችን መፍታት ብቻ ሳይሆን፤ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ቁልፍ መሣሪያ መሆኑ በመጽሐፉ በሚገባ መብራራቱ የጥንካሬው ማሳያ ነው ብለዋል። ሌላኛው የመጽሐፍ ዳሰሳ አቅራቢ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም-አቀፍ ግንኙነት መምህር ባዩልኝ ዘመድአገኘሁ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መጽሐፉ የአፍሪካ ቀንድ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን አጉልቶ ማሳየቱ ጠንካራ ጎኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሰላም ጉዳዮችንና የዲፕሎማሲ ፅንሰ-ሐሳቦችን አስተሳስሮ በማንሳት መፍትሔ እንደሚጠቁም አብራርተዋል። መጽሐፉ ወቅታዊ የሆኑ አህጉራዊና ዓለም-አቀፋዊ ክስተቶችና ግጭቶችን በማጣቀስ በአፍሪካ ቀንድ የሚስተዋሉ ችግሮች በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ እንዲፈቱ ለተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ፖሊሲ አውጪዎች 21 ምክረ-ሐሳቦችን በግብዓትነት ማቅረቡ የይዘት ጥንካሬውን አጉልቶ እንደሚያሳይ ዶክተር ባዩልኝ አመልክተዋል። ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዳሰሳ ያቀረቡት አምባሳደር ሽብሩ ማሞ፤ መጽሐፉ ሰላም፣ዲፕሎማሲና ደኀንነት ከድንበር ግጭት ጋር ያላቸውን ትስስር በሚገባ የሚያነሳ መሆኑን ጠቁመዋል። የሀገራችን ዲፕሎማቶች፣የፀጥታና ደኀንነት አባላት፣ ጥናትና ምርምር ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ግንባታ ጥረቶች ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲጨብጡ እንደሚያደርግ ጠቅሰዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኀንነት አማካሪ ቀነአ ያደታ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ መጽሐፉ ወሳኝ የሆኑ የሰላም፣ ግጭትና ዲፕሎማሲ ጽንሰ-ሐሳቦችን በሚገባ እንዳነሳ ጠቅሰዋል፡፡ በአፍሪካ በተለያዩ ሀገራት የሚታዩ የድንበር ወሰን ችግሮች የፀጥታና ደኅንነት ስጋት እንደሚፈጥሩ በመግለጽ፤ መጽሐፉ ለባለድርሻ አካለት ግብዓት እንደሚሆን አመልክተዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ድንበሮች ጥናት ግብረ-ኃይል አስተባባሪ አምባሳደር ኢብራሂም አድሪስ በበኩላቸው፤ መጽሐፉ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት ክፍተት በሆኑት የድንበር ግጭት ፣ ሰላምና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር መሆኑ ጠቅሰው፤ በዲፕሎማሲ ፣ፀጥታና ደኀንነት ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎችና አመራሮች ጠቃሚ ግብዓቶችን ያካተተ መሆኑን ጠቁመዋል። በቀጣይ በዲፕሎማሲና የሰላም ግንባታ ዘርፎች የካበተ ሥራ ልምድና ተሞክሮ ያላቸው ባለሙያዎችም መጽሐፍ ለመጻፍ እንዲነሳሱ የሚያበረታታ መሆኑን ገልጸዋል። የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል አሰፋ አብዩ (ዶ/ር) በፀጥታና ደኅንነት ተቋማት እንዲሁም በዲፕሎማሲ የተልዕኮ ሥምሪት ያገኙት ልምድና ተሞክሮ እንዲሁም የፒኤችዲ ድግሪ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ያዘጋጁት ጥናታዊ ጽሑፍ መጽሐፉን ለማዘጋጀት መነሻ እንደሆናቸው ጠቁመዋል። ከዝግጅት እስከ ሕትመት ባለው ሂደት ተሳትፎ ላደረጉት አካላት በሙሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ከመጽሐፉ ሽያጭ ከሚገኝ ገቢ 100 ሺህ ብር ለኢትዮጵያ ሰላምና ደኅንነት መስዕዋትነት ለሚከፍለው ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት እንዲሁም 100 ሺህ ብር ደግሞ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በስምሪት ላይ እያሉ ጉዳት ለደረሰባቸው የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አባላት እንደሚያበረክቱ በመድረኩ ላይ ማረጋገጣቸውን ኢዜአ ከአገልግሎቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በአማራ ክልል ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የተጀመረው የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል
Sep 2, 2026 118
ባሀርዳር፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር የተጀመረው የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) ገለፁ። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የጤና ስርአት ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ አካሂዷል። ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት መንግስት የጤና ዘርፉን ለማሻሻል መከላከልና አክሞ ማዳን ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። በዚህም ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን በተከናወኑ ጤና ተቋማትን የመገንባት፣ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን የማሟላትና አገልግሎትን የማሻሻል ስራዎች ለውጥ ማምጣታቸውን ገልጸዋል። በህገ-ወጥ መንገድ በሚገቡ መድሃኒቶች፣ ምግቦችና ደረጃቸውን ባልጠበቁ የህክምና መሳሪያዎች ላይ የሚደረግ የቁጥጥር ስራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል። ይህም ጥራት ያለው፣ ፈጣንና ፍትሃዊ የህክምና አገልግሎት በመስጠት በህብረተሰቡ ዘንድ የበለጠ መተማመንን ለመገንባት ያስችላል ሲሉ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃለፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በበኩላቸው በጤናው ዘርፍ የሚካሄዱ ተግባራትን በቅንጅት ለመምራት በተከናወነ ስራ አበረታች ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል። በተለይም ህገ ወጥ መድሃኒቶችን፣ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦችን እንዲሁም ከደረጃ በታች የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ለመቆጣጠር የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ አሰተዳደር አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን በዲጂታል በማዘመን አገልግሎቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Sep 2, 2026 87
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን በዲጂታል በማዘመን አገልግሎቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ እንደሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመደመር መንግስት የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲመራ ይፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። ከዓመታት በፊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የህዝብ ቅሬታ ከሚስተዋልባቸው ተቋማት ውስጥ አንዱ ነበር። አሁን ግን ታሪክ ተቀይሯል ነው ያሉት። በዓመት የማይስተናገድ ዜጋ ጉዳዩን በቀን ውስጥ ፈፅሞ የሚመለስበት ተቋም ሆኗል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን በዲጂታል በማዘመን አገልግሎቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ግብኝት ማድረጋቸውን ጠቅሰው ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተቋማዊ ሪፎርምና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ሥራዎች የተቋሙን ስምና የሥራ ባህል በአዲስ መልክ እየቀየሩ ነው ብለዋል። በተለይም አገልግሎቶቹን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ማሸጋገሩ ተገልጋዮች ፈጣን፣ ግልጽና እንግልትን የቀነሰ አገልግሎት እንዲያገኙና እርካታቸውም እንዲጨምር እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል። አገልግሎቱ በብቁ የሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ራሱን በማደራጀት የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት፣ የቪዛ፣ የጉዞ ሰነዶች፣ ለውጭ ዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን እንዲሁም የአየርና የመሬት ድንበር ቁጥጥርን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን በውጤታማነት እያከናወነ እንደሚገኝም ነው ያብራሩት። እያንዳንዱ ሪፎርም የሚለካው ዜጎች በሚያገኙት የአገልግሎት ጥራት፣ በሚቆጥቡት ጊዜና በሚያገኙት እርካታ ነው። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋማዊ ለውጥም መንግሥት ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ተጠያቂና ዜጋ-ተኮር የሆነ የአገልግሎት ሥርዓት ለመገንባት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በቀጣይም የተቋሙን የዲጂታል ሽግግር በማፋጠን፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ጥራትን በማሳደግ፣ ተቋማዊ ዐቅሙን በማጠናከር እና የተገልጋዮችን እርካታ በተጨባጭ በማረጋገጥ ላይ መትጋት እንደሚገባም አሳስበዋል። የተገልጋዮችን ሐሳብና ቅሬታ ራስን ለማሻሻል መነሻ አድርጎ መቁጠር ከተቻለ ከዚህም በላይ መለወጥ እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።
የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ ነው
Sep 2, 2026 95
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ መሆኑ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ኩመዳን ገለጹ። ከመላው የሀገሪቱ የተውጣጣ የወጣቶች ቡድን በሦስት የአፍሪካ ሀገራት ነገ የሚጓዝ ይሆናል። የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ የሚጓዙት ጋና፣ ዚምባብዌና ናይጄሪያ ነው። በዚህ የጉዞ መረሃ ግብር ሀያ አራት ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ልምድ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል። መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ በፓኪስታን የችግኝ ተከላ ማካሔዳቸውን ገልጸዋል። የልዑካኑ ጉዞ የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል። በቀጣይም ወጣቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ የማካፈል ተግባርን ያጠናክራል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በስኬታማነት እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ ዓመት ብቻ ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መተከላቸው ይታወሳል። ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትም ተሞክሮውን እየወሰዱት ይገኛሉ።
ፖለቲካ

የህዳሴ ግድብ ግንባታን ያሳካ ታሪካዊ ትውልድ የባህር በር ጥያቄንም ያሳካል
Sep 2, 2026 157
ደሴ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የህዳሴ ግድብ ግንባታን በማሳካት ታሪክ የሰራው ይህ ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትንም እውን በማድረግ ለሌላ ታሪክ መትጋት አለበት ሲሉ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ገለጹ። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለረጅም ዘመናት የቀይ ባህር ዳርቻዎችና ወደቦች ባለቤት ሆና የቆየች ቢሆንም፣ በየጊዜው በነበሩ የታሪክ አጋጣሚዎችና ጂኦፖለቲካዊ ሁነቶች ምክንያት የባህር በር አልባ እንድትሆን መደረጓ ይታወቃል። ይሁን እንጂ የሀገሪቱ የህዝብ ብዛት፣ እያደገ የመጣው ኢኮኖሚ እና የመልክዐ ምድራዊ አካባቢዋ ተፈጥሯዊ ቁርኝት ተፈጥሯዊና ታሪካዊ የባህር በር መብቷን እንደገና እንድታስከብር የሚያስገድድ መሆኑም ይታወቃል። የአርበኞች ማህበር አባላት፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የቀድሞ የሰራዊት አባላት፣ ለሀገር ተቆርቋሪ ምሁራንና ሌሎችም ይህ ታሪካዊና ህጋዊ እውነት በትውልዶች መካከል ሳይደበዝዝ እንዲቀጥል የነበራቸውን ድርሻ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የደቡብ ወሎ ዞን የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ጽህፈት ቤት አባላት፤ በቀይ ባህር ቅርብ እርቀት ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ የባህር በር ማጣቷ የሚያስቆጭ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ መደረጉ በሴራ የተፈፀመ የባንዳነት ተግባር መሆኑን ያነሱት አርበኞቹ አሁን ላይ ይህንን የቆየ ስብራት ለመጠገን በመደመር መንግስትና በህዝቡ የተጀመረው ጥረት የሚደነቅ ነው ብለዋል። የጽሕፈት ቤቱ ፀሐፊ ተተኪ አርበኛ አየለ ወልደ ጊዮርጊስ፤ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር እንድትርቅ የተደረገበት ምክንያት እስካሁን ለማንም ግልጽ ያልሆነና የምንቆጭበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። በመሆኑም የህዳሴ ግድብ ግንባታን በማሳካት ታሪክ የሰራው ይህ ትውልድ የባህር በር ባለቤትነትንም እውን በማድረግ ለሌላ ታሪክ መትጋት እንዳለበት አንስተዋል። በዚህ ረገድ የተጀመሩ ጥረቶች የሚደነቁ መሆናቸውን ገልጸው ለስኬቱም የሁላችንም ሀገራዊ አደራ እና ሃላፊነት አለብን ብለዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተዘግቶባት መዝለቅ የማትችልና የህልውናዋ ጉዳይ በመሆኑ ጥያቄው መልስ ሊያገኝ እንደሚገባም ገልጸዋል። የማህበሩ አባል አቶ ማሞ አያሌው እና ሃምሳ አለቃ አለማየሁ አበበ፤ ለኢትዮጵያ የባህር በር ቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ መሆኑን የትውልዱ መረዳት አስደናቂነት አንስተው ለተግባራዊነቱ በጋራ መትጋት ይጠበቅብናል ብለዋል። የኢትዮጵያ እና የቀይ ባህር መልክዓ ምድራዊ ቁርኝት ከጥንት ጀምሮ ዘመናትን የተሻገረ መሆኑን አንስተው በዚህ ዘመን የባህር በር የምትነፈግበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያና ቀይ ባህርን ለመነጠል የተሄደበት ርቀት የሴራ ፖለቲካ ውጤት መሆኑን ያነሱት ሌላኛው የማህበሩ አባል ሃምሳ አለቃ ባለሟል መለሰ፤ ኢትዮጵያ ታሪኳን አድሳ የባህር በር ባለቤት የምትሆንበት ጊዜ ብዙም እሩቅ ሊሆን አይችልም ብለዋል። በወቅቱ የነበሩ ፖለቲከኞች የሰሩት ታሪካዊ ስህተት ኢትዮጵያን አሁን ላይ ብዙ ዋጋ እያስከፈላት መሆኑን የሚናገሩት ሃምሳ አለቃ ባለሟል መለሰ፤ የባህር በር ባለቤትነቷ እውን እንዲሆን በመስራት ታራካችንን የምናድስበት ጊዜ እየተቃረበ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ በታሪክ፣ በመልክዐ ምድርና በዓለም አቀፍ ህግ መሰረት ምላሽ ሊሰጠው የሚገባ ተገቢ ጥያቄ መሆኑም ተናግረዋል።
በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ጊዜ ሳያባክኑ እድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል
Sep 2, 2026 281
ጎንደር ፤ ነሐሴ 27/2018(ኢዜአ) ፦ በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል ጊዜ ሳያባክኑ እድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል ሲሉ በአማራ ክልል ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የቀድሞ ታጣቂዎች ተናገሩ። በጽንፈኛ ቡድኖች የህዝብ ትግል እየተባለ የሚነሳውም ዓላማው ዘረፋና ሃብት የማካበት ጉዳይ መሆኑን ሁሉም ሊገነዘበው ይገባልም ብለዋል። በአማራ ክልል በተሳሳተ መንገድ ትጥቅ በማንሳት ጫካ ገብተው የነበሩ ወገኖች የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በይቅርታ ወደ ህዝባቸው ገብተዋል፤ እየገቡም ይገኛሉ። በጎንደርና አካባቢው በጫካ ሲንቀሳቀሱ የነበሩና የተሃድሶ ስልጠና ወስደው ወደ ልማት ከገቡ የቀድሞ ታጣቂዎች መካከል አቶ አበበ ሽፈራው፤ ለህዝብ እንታገላለን የሚል ሽፋን በመያዝ የሚደረግ እንቅስቃሴ ዓላማው ዘረፋ መሆኑን ተረድተናል ብለዋል። በመሆኑም እራሳቸውና በእርሳቸው ስር የነበሩ ከ50 በላይ የቀድሞ ታጣቂዎችን በመያዝ የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ሰላምን መርጠው መምጣታቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያ አሁን ላይ የትኛውም የፖለቲካ ጥያቄ በንግግርና በመግባባት እንደሚፈታ እናምናለን፤ ለዚህም ምቹ እድሎች አሉ የሚሉት አቶ አበበ፤ የትኛውም ታጣቂ ጊዜውን በጫካ ሳያባክን የሰላም እድሉን በአግባቡ ሊጠቀም ይገባዋል ብለዋል። የአማራ ክልል ህዝብ ከለውጡ በፊት ሆን ተብሎ ብዙ በደሎች ይፈፀሙበት እንደነበር አስታውሰው የመደመር መንግስት ግን የጋራ እሳቤዎችን በመሰነቅ ለሀገር ልማትና ለህዝብ ተጠቃሚነት እየሰራ መሆኑን ቆይተንም ቢሆን ተገንዝበናል ሲሉ ተናግረዋል። ሌላኛው የቀድሞ ታጣቂ አቶ ተረፈ እንየው፤ በኢትዮጵያ አሁን ላይ የትኛውም የትጥቅ ትግል አማራጭ መፍትሄ የማያመጣና የተሳሳተ ስሌት ስለመሆኑ ተናግረዋል። በጦርነት የሚፈታ የፖለቲካ ጥያቄም ሆነ የሚገነባ ሀገር እንደሌለ ገልጸው በተሳሳተ ቅስቀሳ ወደ ጫካ የገቡ ወገኖቻችን ዛሬ ነገ ሳይሉ የሰላምን አማራጭ በመቀበል ወደ ልማታቸው ሊመለሱ ይገባል ሲሉ መክረዋል። በኢትዮጵያ የጠመንጃ ጊዜ አብቅቶ የምክክር ጊዜ እውን መሆኑን በተግባር አይተናል ያሉት የቀድሞ ታጣቂው ከቅራኔ እና ግጭት በመውጣት በልማት ሀገራችንን ለመገንባት መትጋት አለብን ብለዋል። ሌላኛው የቀድሞ ታጣቂ አቶ ዮሐንስ አዲስ፤ የትጥቅ ትግል ልማትን ከማደናቀፍና ዜጎችን ከማጎሳቆል በስተቀር ሌላ አላማ የሌለውና ውጤት የማያመጣ መሆኑን በትክክል መናገር እችላለሁ ሲሉ ተናግረዋል። በአማራ ክልል ባለፉት ሶስት ዓመታት የተመለከትነው የባእዳንን ተልእኮ ለማሳካት በባንዳነት በመሰለፍ የህዝብን ሃብት መዝረፍና ማውደም ነው ብለዋል ። በመሆኑም በጫካ የሚገኙ ታጣቂዎች ሁሉ በጥፋታቸው በመጸጸት የመንግስትን የሰላም ጥሪ በመቀበል መጥተው ማህበረሰባቸውን መቀላቀልና ወደ ልማት መግባት እንዳለባቸው የቀድሞ ታጣቂዎቹ መክረዋል።
ብልፅግና ፓርቲ የሚመራበት የመደመር እሳቤ በኢትዮጵያ ለሚታዩት ለውጦች ዋነኛ መሠረት ናቸው
Sep 1, 2026 453
አዲስ አበ ፤ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ) :-ብልፅግና ፓርቲ የሚመራበት የመደመር እሳቤና የፓርቲው ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ለሚታዩት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች ዋነኛ መሠረት መሆናቸውን በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ነብዩ ስሑል ገልጸዋል። በብልፅግና ፓርቲ ዋና ፅ/ቤት የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ የውጭ ግንኙነት ዳይሬክተር ጄኔራል አቶ ነብዩ ስሑል የተመራ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ልዑክ በቻይና ጉብኝት እያደረገ ይገኛል። ልዑኩ በቤጂንግ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአፍሪካ ጉዳዮች ኮሚቴ ጋር የፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነትን በተመለከተ ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ ላይ አቶ ነብዩ ስሑል፣ ብልፅግና ፓርቲ የሚመራበት የመደመር እሳቤና የፓርቲው ፕሮግራሞች በኢትዮጵያ ለሚታዩት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ለውጦች ዋነኛ መሠረት መሆናቸውን ገልጸዋል። የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ፖሊሲው ውጤታማነት፣ የከተማና የገጠር ልማትን በተቀናጀ መልኩ ማከናወን፣ ሕዝብን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚከናወኑ የልማት ሥራዎች እና የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ የፓርቲውን የእሳቤ ጥራትና የማስፈጸም አቅም የሚያሳዩ ዋነኛ ተግባራት መሆናቸውንም አቶ ነብዩ ጠቁመዋል። የአረንጓዴ አሻራ ንቅናቄ ከሀገር ውስጥ የልማት ሥራ ባሻገር፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ አቅም እያጠናከረ ያለ ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል። በፖለቲካው መስክ እየተመዘገቡ ያሉ አበረታች ለውጦችን በመጥቀስ፣ ኢትዮጵያ በ2026 የአፍሪካ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጉባኤን በአዲስ አበባ ለማስተናገድ መመረጧንና ለጉባኤው ዝግጅት እያደረገች መሆኗን አስረድተዋል። የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል ሪኦ ዩሃ ብልፅግና ፓርቲ “ጠንካራ ፓርቲ ለጠንካራ መንግሥት፤ ጠንካራ መንግሥት ለጠንካራ ሀገር” በሚል እሳቤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እያስመዘገበ ያለውን ለውጥ ፓርቲያቸውና መንግሥታቸው በከፍተኛ አድናቆት እንደሚከታተሉ ገልጸዋል። የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲና ብልፅግና ፓርቲ በፓርቲ ለፓርቲ ግንኙነት የሚያደርጉትን ትብብር እና የጋራ ጥቅሞችን በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ቅንጅት በቀጣይ ለማጠናከር ፓርቲያቸው ጠንካራ አቋም እንዳለው አረጋግጠዋል። የብልፅግና ፓርቲ ልዑክ በቤጂንግ በነበረው የመጀመሪያ ቀን ውሎ፣ ከሁለትዮሽ ውይይቱ በተጨማሪ የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲን ታሪክ፣ ልምድ፣ ድሎችና ተግዳሮቶች የሚያሳየውን የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ሙዚየም መጎብኘቱን ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላምና ዕድገት መሠረት ይጥላል
Sep 1, 2026 431
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ህብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት የሚጥል መሆኑን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፕሬዝዳንቶች ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባዔ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች፣ አደረጃጀቶች፣ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተወከሉ አራት ሺህ ተመካካሪዎች በስምንት አጀንዳዎች በመምከር ችግሮችን በንግግር መፍታት የሚቻልበትን አዲስ የታሪክ አሻራ አስቀምጦ ተጠናቋል። ኢትዮጵያ ያካሄደችው አካታችና አሳታፊ ሀገራዊ የምክክር ጉባዔ የሕዝቦችን አብሮነት የሚያጠናክር፣ ሀገራዊ መነሳትና የዕድገት ዘመንን የሚያበስር ታሪካዊ ክስተት ነው። የጅማ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ደረጄ እንግዳ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንዳሉት፣ የምክክር ጉባዔው በኢትዮጵያ ልዩነቶችን በንግግር የመፍታት የሰለጠነ ማኅበረሰብ ባህልን ያንጸባረቀ ነው። በኢትዮጵያ በሕዝቦች መካከል ለዘመናት የተዘራውን የጥላቻ ትርክት በማረቅ፣ ሕብረ ብሔራዊ አንድነትንና የእኩልነት እሴቶችን ማጠናከር ያስችላል ብለዋል። እንደ ዓድዋ ድል ሁሉ በታሪክ ሲወሳ የሚኖር አኩሪ የትውልዱ አሻራ ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ የሀሳብ ልዩነቶችን በማጥበብ አሰባሳቢ ትርክት ለመገንባት ምክክር ብቸኛ አማራጭ መሆኑን ገልጸዋል። የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር)፣ ኢትዮጵያውያን የምክክር ጉባዔውን ተጠቅመው ለሀገራቸው በሚበጁ ጉዳዮች ላይ ተመካክረው የጋራ አቅጣጫ አስቀምጠዋል ብለዋል። ኢትዮጵያ የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በማየት ያካሄደችው ስኬታማ የምክክር ጉባዔ ልዩነቶችን በማጥበብ ለዘላቂ ሰላምና ሁለንተናዊ ብልጽግና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። ሀገራዊ ምክክር ጉባዔው ሕብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላምና ለሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት ይጥላል ብለዋል። የሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፈየራ ዲንሳ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ በኢትዮጵያ ለዘመናት የቆዩ ተጻራሪ ትርክቶችን በምክክር ወደ የጋራ አሸናፊነት ማምጣት የተቻለበት መድረክ መሆኑን ገልጸዋል። ለሀገራዊ ምክክር የተሻለ ዋጋ የሰጡ ሀገራት ወደ ተሻለ ሰላምና ዕድገት መምጣታቸውን ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ያሳያሉ ብለዋል። ኢትዮጵያውያን እንደ ምክክር ጉባዔው፣ ሕዳሴ ግድብና ዓድዋ ያሉ አኩሪ ድሎችን ጠብቆ ለቀጣዩ ትውልድ ማውረስ እንዳለባቸው አሳስበዋል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ኡባህ አደም (ዶ/ር)፣ የሀገራዊ የምክክር ጉባዔው በኢትዮጵያውያን መካከል መግባባት በመፍጠር ለሀገር ግንባታና ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት መጎልበት ታሪካዊ ሚና ተጫውቷል ብለዋል። በሂደቱ የተለያዩ ስሜቶችና የሀሳብ ልዩነቶች ቢንጸባረቁም፣ በመደማመጥና በመከባበር መግባባት ላይ መድረስ እንደሚቻል በተግባር ማሳየቱን ገልጸዋል። የብሔር፣ የሃይማኖትና የቋንቋ ልዩነቶች የሕብረ ብሔራዊነት ጌጥ እንጂ የጥላቻ ምንጭ እንዳልሆኑ የገለጠ መድረክ ነው ብለዋል።
ፓርቲው የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት ይሰራል-አቶ ጌቱ ወዬሳ
Sep 1, 2026 369
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 ( ኢዜአ)፦ብልፅግና ፓርቲ የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በትጋት እንደሚሰራ በብልፅግና ፓርቲ የሀረሪ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌቱ ወዬሳ ገለፁ። የጽህፈት ቤቱ ኃላፊው አቶ ጌቱ ወዬሳ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በክልሉ በብልፅግና ፓርቲ መሪነት በተለያዩ ዘርፎች በተከናወኑ ተግባራት በርካታ ስኬቶች ተመዝግበዋል። የፓርቲውን እሳቤዎች በተግባር በመተርጎም በየዘርፉ የተመዘገቡ ድሎችን አጠናክሮ ማስቀጠል ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። በያዝነው አዲሱ የበጀት ዓመትም ፓርቲው ለህዝብ የገባውን ቃል አልቆ የሚፈፅምበትና እንደሀገርና ክልል አዲስ ታሪካዊ ምዕራፍ የሚከፈትበት እንዲሆን በትኩረት ይሰራል ብለዋል። የብልፅግና ፓርቲ እሳቤዎች እና የፖለቲካ ፕሮግራሞች ወደ ተግባር በመቀየር የህዝባችንን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ነው ያነሱት። እነኚህ ድሎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም በተለይ በአገልግሎት አሰጣጥ የህዝብን እርካታ ማሳደግ እንዲሁም ብልሹ አሰራሮችን ከማስወገድ አንፃር በልዩ ትኩረት መንቀሳቀስ አስፈላጊ ነው ብለዋሎል። በፓርቲና በመንግሥት የተቀናጀ አመራር የስራ ዕድል ፈጠራን ለማስፋት፣ገበያን የማረጋጋትና የኑሮ ውድነትን ለመቀነስ የጀመራቸው ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል። የፓርቲ አደረጃጀቶችና አባላት በዘርፉ ግንባር ቀደም ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባ በማሳሰብ፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰሩ ያሉ ስራዎች መቀጠል እንዳለበት አመልክተዋል። የሴቶችና ወጣቶች ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንዲሁም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት የሚያሳድጉ ስራዎችን በማላቅ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እና ልመናንና ተረጂነትን ለመቀነስ ይሰራል ሲሉ አብራርተዋል። "አዲሱ በጀት ዓመት ህዝባችንን ይበልጥ የምናገለግልበት፣ ክልሉን የብልፅግና ተምሳሌት የማድረግ ጉዟችንን የምናረጋግጥበት እንዲሆን ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል''። የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዶች በተሻለ አፈጻጸም እንዲተገበሩ ሁሉም የፓርቲ መዋቅሮችና የመንግሥት ተቋማት በቅንጅት፣ በተጠያቂነትና በውጤት ተኮር አሰራር ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባም ጠቁመዋል። የታቀዱ ግቦችን ለማሳካት በየደረጃው የሚገኘው አመራር በቁርጠኝነትና በከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት መስራት እንደሚገባውም አጽንኦት ሰጥተዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመመካከር ለመፍታት አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል
Sep 1, 2026 425
ሰመራ፣ነሀሴ 26/2018(ኢዜአ) :-ሀገራዊ ምክክሩ የቆዩ ችግሮችን በሰለጠነ መንገድ በመመካከር ለመፍታት አዲስ ምዕራፍ መክፈቱን በአፋር ክልል የዱብቲና የሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ ። የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር መድረክ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን በየደረጃው ማሳተፍ የቻለና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት በመምከር ውጤት ማምጣት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው። ምክክሩ አሻጋሪ ጉዳዮች የተነሱበትና ኢትዮጵያ ያሸነፈችበት ታሪካዊ መድረክ መሆኑም ተመላክቷል። ኢዜአ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው በአፋር ክልል በአውሲ ረሱ ዞን የዱብቲ ከተማ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ መድረኩ በሀገሪቱ የቆዩ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ትልቅ ተስፋ የፈነጠቀ ነው። ከከተማው ነዋሪዎች መካከል አቶ ሙሉጌታ ወርቁ እንዳሉት ሀገራዊ ምክክሩ ኢትዮጵያውያን በመመካከር ችግሮችን የመፍታት ባህልን ለማዳበር ጠንካራ መሰረት የጣሉበት ነው። ይህ ሂደት ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማስቀጠል እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል። ለልዩነቶች መነሻ የሆኑ ጉዳዮችን ወደ መሐል አምጥቶ ለመፍታት መመካከር ብቸኛውና ወሳኙ መንገድ መሆኑን በተግባር ማረጋገጡንም አክለዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ መምህር ሸዋታጠቅ አደመ በበኩላቸው፤ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ተመካክረው ጠንካራ ሀገር ለመገንባት የሚያስችላቸውን አዲስ ምዕራፍ መክፈት የቻሉበት ተግባር መሆኑን ገልጸዋል። የምክክር መድረኩ ለዘመናት የቆዩ ችግሮች እልባት እንዲያገኙ የሚያስችልና መጪው ጊዜ ለሀገሪቱ ብሩህ ተስፋ የሰነቀ መሆኑን ያሳየ ነው ብለዋል። የምክክር መድረኩ የቆዩ ባህላዊ የሰላም እሴቶችን እና የግጭት አፈታት ሥርዓቶችን በዘመናዊ መንገድ ለመተግበርና ጥቅም ላይ ለማዋል ትልቅ ዕድል የፈጠረ መሆኑንም አመልክተዋል። የሎጊያ ከተማ ነዋሪ አቶ አብዱ መሐመድ በበኩላቸው እንዳሉት የምክክር መድረኩ ለሁሉም የምትመች ኢትዮጵያን ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያውያን የተሻለች ሀገር ለመገንባት ይበጃል ያሉትን ሀሳቦች ያዋጡበትና ሀገር ያሸነፈችበት መሆኑንም ጠቁመዋል። ምክክሩ ችግሮችን በስክነት የመፍታት ባህል እንዲጎለብትና ዴሞክራሲያዊ ስርአት ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን ያነሱት ደግሞ ሌላኛው የሎጊያ ከተማ ነዋሪ አወል ኡመር ናቸው። ምክክሩ የልዩነት ሀሳቦችን ለመፍታት የሐይል አማራጮች ስፍራ እንደሌላቸው ያረጋገጠ መሆኑን አስታውቀዋል።
የወርሀ ሐምሌ እና ነሐሴ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቁልፍ ተግባራት ቅኝት
Sep 1, 2026 425
የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር፦ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ስምንተኛ ዓመቱን በያዘበት በዚህ ዓመት፤ የኮፕ32 (COP32) ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኮፕ32 ብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በተገኙበት ዓመታዊውንና የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን መርተዋል። ዘመቻው በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በአንድ ቀን ውስጥ 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ታላቅ ግብን የሰነቀ ሲሆን በዚህም ከተቀመጠው እቅድ በላይ ማሳካት የቻለ ዘመቻ ነበር። ይህ ጥረት በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተከናወነ ሲሆን፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩም ተሳታፊዎች የታሪክ፣ የአንድነት እና የጽናት ድል ያስመዘገቡ መሆናቸውን በመግለጽ ለሁሉም ምስጋና አቅርበዋል። ፕሮጀክቶች ጉብኝት እና ምረቃ፦ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባሕር ዳር የሚገኘውን የደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ ተርሚናል መርቀው ከፍተዋል። ይህ ፕሮጀክት ለኢትዮጵያ ቁልፍ ከሆኑ መግቢያ በሮች አንዱ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ከተማዋ በቅርቡ ባጋጠሟት ፈተናዎች ሳትበገር የጽናት፣ የማገገም እና የቀጣይ ኢንቨስትመንት ማዕከልነት ማረጋገጫ መሆኑን አስገንዝበዋል። አዲሱ ተርሚናል ዘመናዊ የአውሮፕላን ማረፊያ መሠረተ ልማቶችን፣ የተሻሻሉ የመዳረሻ መንገዶችን እና ሰፊ አገልግሎቶችን በማካተት የአውሮፕላን ማረፊያውን አቅም የሚያሰፋና የመንገደኞችን ምቾት የሚያሻሽል ሲሆን፤ ይህም ከከተማዋ ሰፊ የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ ባሕር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ማዕከል ያደርጋታል። ማኅበራዊ ጉዳይ፦ በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ (OBN) ጋር ቃለ መጠይቅ ያደረጉ ሲሆን በቆይታቸውም ከሀገራዊ ጥቅም ይልቅ ግላዊ ጥቅምን ያስበለጡ በኦሮሚያ፣ በአማራ እና በትግራይ የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች መንግሥትን ለብቻቸው ማሸነፍ እንደማይችሉ ከተገነዘቡ በኋላ ህብረት መፍጠራቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም ጊዜው ባለፈበት የፖለቲካ አስተሳሰብ እና የአመራር ዘይቤ እነዚህ ቡድኖች ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ለመበታተን ለሚፈልጉ ታሪካዊ የውጭ ጠላቶች እንደ መጠቀሚያ መሣሪያ እያገለገሉ የመሆናቸውን ታሪካዊ ግድፈት አብራርተዋል። አክለውም እውነተኛ ዲሞክራሲ ከተራ የፖለቲካ ግልጽነት ባለፈ የሕግ የበላይነትን ወደሚያረጋግጥ እውነተኛ ብሔራዊ ውይይት መሸጋገር እንዳለበት አፅንዖት ሰጥተዋል። #PMOEthiopia #EthiopiaDelivers

ማህበራዊ
በአማራ ክልል ጤናማና አምራች ዜጋን ለመፍጠር የተጀመረው የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል
Sep 2, 2026 118
ባሀርዳር፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በአማራ ክልል ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር የተጀመረው የተቀናጀ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) ገለፁ። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የጤና ስርአት ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ በባህር ዳር ከተማ አካሂዷል። ሙሉነሽ ደሴ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት መንግስት የጤና ዘርፉን ለማሻሻል መከላከልና አክሞ ማዳን ላይ የተመሰረተ ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። በዚህም ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርአት በመዘርጋት ጤናማና አምራች ዜጋ ለመፍጠር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን በተከናወኑ ጤና ተቋማትን የመገንባት፣ ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን የማሟላትና አገልግሎትን የማሻሻል ስራዎች ለውጥ ማምጣታቸውን ገልጸዋል። በህገ-ወጥ መንገድ በሚገቡ መድሃኒቶች፣ ምግቦችና ደረጃቸውን ባልጠበቁ የህክምና መሳሪያዎች ላይ የሚደረግ የቁጥጥር ስራ በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል። ይህም ጥራት ያለው፣ ፈጣንና ፍትሃዊ የህክምና አገልግሎት በመስጠት በህብረተሰቡ ዘንድ የበለጠ መተማመንን ለመገንባት ያስችላል ሲሉ አስታውቀዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ሃለፊ አቶ አብዱልከሪም መንግስቱ በበኩላቸው በጤናው ዘርፍ የሚካሄዱ ተግባራትን በቅንጅት ለመምራት በተከናወነ ስራ አበረታች ውጤት እየተገኘ ነው ብለዋል። በተለይም ህገ ወጥ መድሃኒቶችን፣ የታሸጉ ምግቦችና መጠጦችን እንዲሁም ከደረጃ በታች የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ለመቆጣጠር የተጀመረው ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በመድረኩ ላይ የክልሉ ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ የክልል፣ የዞንና የከተማ አሰተዳደር አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን በዲጂታል በማዘመን አገልግሎቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ ነው- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Sep 2, 2026 87
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን በዲጂታል በማዘመን አገልግሎቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ እንደሚገኝ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የመደመር መንግስት የተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ የህዝብን ፍላጎት ማዕከል ባደረገ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ግልጽ በሆነ መንገድ እንዲመራ ይፈልጋል ሲሉ ተናግረዋል። ከዓመታት በፊት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በሚሰጣቸው አገልግሎቶች የህዝብ ቅሬታ ከሚስተዋልባቸው ተቋማት ውስጥ አንዱ ነበር። አሁን ግን ታሪክ ተቀይሯል ነው ያሉት። በዓመት የማይስተናገድ ዜጋ ጉዳዩን በቀን ውስጥ ፈፅሞ የሚመለስበት ተቋም ሆኗል። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት አሠራሩን በዲጂታል በማዘመን አገልግሎቱን ወደ አዲስ ምዕራፍ እያሸጋገረ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በአገልግሎቱ ዋና መሥሪያ ቤት ግብኝት ማድረጋቸውን ጠቅሰው ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ የተቋማዊ ሪፎርምና የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ሥራዎች የተቋሙን ስምና የሥራ ባህል በአዲስ መልክ እየቀየሩ ነው ብለዋል። በተለይም አገልግሎቶቹን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል ማሸጋገሩ ተገልጋዮች ፈጣን፣ ግልጽና እንግልትን የቀነሰ አገልግሎት እንዲያገኙና እርካታቸውም እንዲጨምር እያደረገ መሆኑን አመልክተዋል። አገልግሎቱ በብቁ የሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ራሱን በማደራጀት የኤሌክትሮኒክ ፓስፖርት፣ የቪዛ፣ የጉዞ ሰነዶች፣ ለውጭ ዜጎች የሚሰጡ አገልግሎቶችን እንዲሁም የአየርና የመሬት ድንበር ቁጥጥርን ጨምሮ በርካታ ተግባራትን በውጤታማነት እያከናወነ እንደሚገኝም ነው ያብራሩት። እያንዳንዱ ሪፎርም የሚለካው ዜጎች በሚያገኙት የአገልግሎት ጥራት፣ በሚቆጥቡት ጊዜና በሚያገኙት እርካታ ነው። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ተቋማዊ ለውጥም መንግሥት ቀልጣፋ፣ ግልጽ፣ ተጠያቂና ዜጋ-ተኮር የሆነ የአገልግሎት ሥርዓት ለመገንባት ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። በቀጣይም የተቋሙን የዲጂታል ሽግግር በማፋጠን፣ የአገልግሎት ቅልጥፍናንና ጥራትን በማሳደግ፣ ተቋማዊ ዐቅሙን በማጠናከር እና የተገልጋዮችን እርካታ በተጨባጭ በማረጋገጥ ላይ መትጋት እንደሚገባም አሳስበዋል። የተገልጋዮችን ሐሳብና ቅሬታ ራስን ለማሻሻል መነሻ አድርጎ መቁጠር ከተቻለ ከዚህም በላይ መለወጥ እንደሚቻልም አስገንዝበዋል።
በቅርሶች ምዝገባ፣ እድሳትና ልማት ላይ የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት የቱሪስት ፍሰቱ እንዲያንሰራራ አድርገዋል
Sep 2, 2026 110
ባህር ዳር ነሐሴ 27/2018(ኢዜአ)፡-በቅርሶች ምዝገባ፣ እድሳትና ልማት ላይ የተከናወኑ ስኬታማ ተግባራት የቱሪስት ፍሰቱ እንዲያንሰራራ እያደረጉ መሆኑን የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ገለጸ። የአማራ ክልል ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረኩን በባህር ዳር ከተማ ማካሄድ ጀምሯል። በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቢሮው ኃላፊ አቶ መልካሙ ፀጋዬ እንደገለጹት፤ በመንግስት ኢኒሼቲቭ የተገነቡትን የጎርጎራና ሎጎ ሃይቅ ሪዞርቶች ከነባር የመስህብ ሀብቶች ጋር በማስተሳሰር ዘርፉን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል። በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክልሉ ያሉ ባህላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶችን በማስተዋወቅ ቱሪስቶችን ለመሳብ የተደረገው ጥረት አበረታች ውጤት ማስገኘቱንም ገልጸዋል። በተለይም ቱሪዝሙ በሚቀዛቀዝበት የክረምት ወቅት እንደ ሻደይ፣ አሸንድዬ፣ ሶለል፣ ቡሄና እንግጫ ነቀላ ያሉ ባህላዊ እሴቶችን በማስተዋወቅ የጎብኝዎች ቁጥር እንዲጨምር ማድረግ መቻሉን ጠቁመዋል። ይህም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኝዎች በስፋት ወደ ክልሉ እንዲመጡ በማድረግ፣ የክልሉን ኢኮኖሚ ከማነቃቃት ባለፈ ህብረተሰቡን ከዘርፉ ተጠቃሚ ማድረግ እንዳስቻለም ነው የጠቀሱት። በመጪው አዲስ ዓመት፣ በመስቀልና በሌሎች በዓላትም ወደ ክልሉ የሚመጡ ጎብኝዎችን ቁጥርን በተሻለ መልኩ ለማሳደግ ዞኖችና የከተማ አስተዳደሮች ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል። የቢሮው የዕቅድ፣ በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክተር አቶ መላኩ ብርሃኔ በበኩላቸው ፤በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 121 ቅርሶችን በመጠገን፣ 5 ሺህ 766 ተንቀሳቃሽና 190 ቋሚ ቅርሶችን በመመዝገብ ለቱሪዝም ልማት ማዋል ተችሏል ብለዋል። በተፈጠረው ምቹ ሁኔታም በበጀት ዓመቱ ከ18 ሚሊዮን በላይ የሀገር ውስጥ ፤ ከ58 ሺህ 300 በላይ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች የክልሉን የመስህብ ሀብቶች በመጎብኝታቸው ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን አስታውቀዋል። በምክክር መድረኩ ላይ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር የዘርፉ አመራሮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
በጅግጅጋ ከተማ የመማር ማስተማሩ ስራ ስኬታማ እንዲሆን የቅድመ ዝግጀት ሥራ ተከናውኗል
Sep 2, 2026 96
ጅግጅጋ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የ2019 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ስራ ስኬታማ እንዲሆን ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን ገለጹ። በከተማው የ2019 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ምዝገባ በሁሉም ትምህርት ቤቶች እየተካሄደ ነው። በጅግጅጋ ከተማ ኢዜአ ያነጋገራቸው ትምህርት ቤቶች ለ2019 የትምህርት ዘመን ለመማር ማስተማሩ ስራ ስኬታማነት ዝግጅት ማድረጋቸውን ተናግረዋል። የጅግጅጋ ካህ አንድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ከድር ረሺድ እንደገለጹት፣ በመጪው የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማሩ ስራ ውጤታማ እንዲሆንና ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ከወዲሁ እየተሰራ ነው ። በትምህርት ቤቱ የመማሪያ ክፍሎች ዝግጁ የማድረግ ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚገቡ ከ1 ሺህ 300 በላይ ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተማር የተማሪዎች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል። የጅግጅጋ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር ሰኢድ ንጋቱ በበኩላቸው በትምህርት ዘመኑ ለተማሪዎች ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት የመማሪያ ክፍሎች እድሳት፣ የቤተ-ሙከራ፣ የቤተ መጻህፍትና የአይሲቲ አገልግሎቶችን የማደራጀትና ዝግጁ የማድረግ ስራ ተከናውኗል ። ትምህርት ቤቱ በትምህርት ዘመኑ ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በቂ ዝግጅ አድርጓል ብለዋል። በትምህርት ቤቱ የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር ገልጸው በአዲሱ የትምህርት ዘመንም ከመደበኛ የትምህርት አገልግሎት ባለፈ የተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት እንደሚሰጥ ተናግረዋል። የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ኑር መሀሙድ እንደገለጹት በጅግጅጋ ከተማ ከቅድመ መደበኛ እስከ 2ኛ ደረጃ የሚያስተምሩ 238 የግልና የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ይገኛሉ ። በሁሉም ትምህርት ቤቶች በ2019 የትምህርት ዘመን ከ120 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑን ተናግረዋል ። በትምህርት ዘመኑ ለመማር ማስተማሩ ስራ ስኬታማነት የመማሪያ ክፍሎችን የማስተካከልና የቤተ ሙከራና የቤተ መጻህፍት አገልግሎቶችን የማደራጀት ዝግጅቶች በቅንጅት መከናወናቸውን አስታውቀዋል ።
ኢኮኖሚ
ብራዚል ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ለማስፋት የሚያስችላትን ቋሚ ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ ከፈተች
Sep 2, 2026 193
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018(ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ያለውን የኢኮኖሚ፣ የንግድ እና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር የብራዚል ንግድ እና ኢንቨስትመንት ማስተዋወቂያ ኤጀንሲ (አፔክስብራዚል) ቋሚ ጽሕፈት ቤቱን በአዲስ አበባ ከፍቷል። በመክፈቻው መርሃ ግብር ከፍተኛ የኢትዮጵያ እና የብራዚል የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የንግድ ማህበረሰብ ተወካዮችና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደተናገሩት፤ ቋሚ ጽህፈት ቤቱ በአዲስ አበባ መክፈቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ተጨባጭ ስትራቴጂካዊ ቅንጅት መጀመሩን የሚያበስር መሆኑን ገልፀዋል። አፔክስብራዚል ለኢንቨስተሮች የመረጃ እጥረቶችን በማስወገድ፣ አካባቢያዊ የገበያ መረጃ በመስጠት እና የንግድ ትስስርን በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል። የብራዚልን የላቀ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የግብርና ልምድ ከኢትዮጵያ ሰፊና ለም መሬት ጋር በማጣመር በቡና፣ በምርጥ ዘር ፣ በእንስሳት ሀብት እና ዘመናዊ አግሮ-ቢዝነስ ላይ መስራት ያስችለዋል ሲሉ ገልፀዋል። ኮሚሽኑ ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ለሚገቡ የብራዚል ኩባንያዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል። በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ክዣንዲር ፈሬራ ዶስ ሳንቶስ እንደተናገሩት፤ አፔክስብራዚል በአዲስ አበባ ቋሚ ጽሕፈት ቤት መክፈቱ በሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ግንኙነት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው። በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት ማደጉን የሚያሳይ እና ወደፊት ለመድረስ ያለውን ታላቅ ምኞት የሚያንጸባርቅም ነው ብለዋል። ጽሕፈት ቤቱ የብራዚል ኩባንያዎች የኢትዮጵያን ገበያ አማራጮችን እንዲገነዘቡ፣ አጋሮችን እንዲያገኙ እና የገበያ መረጃዎችን እንዲያገኙ የሚያስችል እንደሆነ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ባለሀብቶችም በዓለም ትልልቅ ኢኮኖሚዎች በአንዱ በሆነችው ብራዚል ውስጥ ያሉ እድሎችን እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል ብለዋል። አዲስ አበባ የአፍሪካ ዲፕሎማሲያዊ መዲና በመሆኗ አፔክስብራዚል ከኢትዮጵያ ባለፈ በምስራቅ አፍሪካ እና በሰፊው የአፍሪካ ገበያ እንደ ግብርና፣ አቪዬሽን፣ መድኃኒት ማምረት፣ መሠረተ ልማት እና ታዳሽ ኃይል ባሉ ዘርፎች ያሉ እድሎችን እንድትጠቀም ያደርጋታል ሲሉ ገልፀዋል። በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄኔራል አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) በበኩላቸው አፔክስብራዚል በአዲስ አበባ ቋሚ ጽሕፈት ቤት መክፈቱ በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ባለው የኢኮኖሚ አጋርነት ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው ብለዋል። የአፔክስ ጽሕፈት ቤት የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትስስርን የበለጠ ለማሳደግ፣ የንግድ አጋርነትን ለማመቻቸት እና በኢትዮጵያ እና በብራዚል ባለሀብቶች መካከል ትርጉም ያለው እና ተጨባጭ ትስስርን ለማስፋፋት የሚያገለግል መድረክ እንደሚሆንም ተናግረዋል።
ከምስራቅ ቦረና ዞን ቆላማ ወረዳዎች ከዘንድሮ የበልግ አዝመራ ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቧል
Sep 2, 2026 90
ነገሌ ቦረና፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን ከዘንድሮው የበልግ አዝመራ ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የዞኑ ግብርና ጽህፈት ቤት ገለጸ፡፡ በምስራቅ ቦረና ዞን ግብርና ጽህፈት ቤት የአዝርእት ልማትና ጥበቃ ባለሙያ አቶ ቦነያ ሁቃ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በዞኑ ከ176 ሺህ 20 ሄክታር በላይ መሬት በበልግ አዝመራው በተለያዩ ሰብሎች መልማቱን አስታውሰዋል፡፡ በልማቱ ከተሳተፉት 143 ሺህ 288 ከፊል አርብቶ አደሮች መካከል 23 ሺህ 614 ሴቶች እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ በዞኑ ቆላማ ወረዳዎች ከለማው ከዚሁ መሬት 2 ሚሊዮን 126 ሺህ ኩንታል የሚጠጋ አጠቃላይ ምርት መሰብሰቡን አስታውቀዋል፡፡ በዞኑ የበልግ አዝመራ ከተመረቱት የሰብል አይነቶች መካከል ስንዴ፣ ጤፍ፣ በቆሎ፣ ቦለቄ፣ ማሽላና ሰሊጥ ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑ ጠቁመዋል፡፡ ዘንድሮ ከዞኑ ሁሉም ወረዳዎች ከበልግ አዝመራ የተሰበሰበው አጠቃላይ ምርት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ብልጫ ያለው ነው ብለዋል፡፡ በበልግ አዝመራው ልማት ከተሳተፉት የዞኑ ነዋሪዎች መካከል የነገሌ ቦረና ከተማ ዙሪያ ወረዳ ነዋሪ አቶ አበራ ሞገስ ከበልግ አዝመራ ካለፉት አመታት ሁሉ የተሻለ ምርት መሰብሰባቸውን ገልጸዋል፡፡ የተሻሻለ የግብርና አሰራር፣ የምርት ማሳደጊያ አጠቃቀምና የተስተካከለ የዝናብ ስርጭት መኖሩ ውጤት ማስገኘቱን ጠቅሰዋል፡፡ የኩታ ገጠም አስተራረስ፣ በመስመር መዝራትና ሜካናይዜሽን አጠቃቀም ከተሻሸሉ የግብርና አሰራሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንደሆኑም ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡ በምስራቅ ቦረና ዞን ከመጋቢት አጋማሽ እስከ ሚያዝያ ወር የዝናብና የዘር፣ ከሐምሌ እስከ ነሔሴ ወር ደግሞ የምርት መሰብሰቢያ ወቅት እንደሆነ ይታወቃል፡፡
የከተማ ግብርና ዘርፍ የገቢ አቅማችንን ለማሳደግ አግዞናል- በሸገር ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ
Sep 2, 2026 86
ሱሉልታ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡- በከተማ ግብርና በመሰማራታቸው የገቢ አቅማቸው ማደጉን በሸገር ከተማ በዘርፉ የተሰማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ፡፡ የሸገር ከተማ አርሶ አደሮች ቀን «ዘመናዊ ገበሬና ዘመናዊ ግብርና ለአጠቃላይ ብልፅግና» በሚል መሪ ቃል በከተማው ሱሉልታ ክፍለ ከተማ በተለያዩ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል። አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግም የባዛር እና ኤግዚቢሽን ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን፣ የግብርና ምርቶች፣ ማሽነሪዎች፣ የምርት ማሳደጊያ ግብዓቶችና ሌሎችም በበዛሩና ኤግዚቢሽኑ ላይ ለእይታና ሽያጭ ቀርበዋል። የአርሶ አደሮቹ ቀን አከባበር ዋነኛ ዓላማም በከተሞች በከተማ ግብርና ዘርፍ በስፋት በመሰማራት በምግብ ራስን ከመቻል ባሻገር፣ ትኩስ የግብርና ምርቶችን በበቂ መጠንና በፍትሐዊ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ የኑሮ ውድነትን መቀነስ እና ገበያውን ማረጋጋት እንደሆነም ተገልጿል። የመርሃ ግብሩ ተሳታፊ አርሶ አደሮች ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት፣ አስተዳደሩ የከተማ ግብርናን በማስፋፋትና ዘመናዊና ዘላቂነት ያለው የምግብ ዋስትና ማረጋገጫ ስራዎችን በማከናወን ረገድ እየደገፋቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል። አርሶ አደሮቹ የመንግስትን ድጋፍ መነሻ በማድረግ ምርታማነታቸውን ማሳደጋቸውን ጠቅሰው፣ የተፈጠረላቸውን የገበያ ዕድል በመጠቀምም የግብርና ምርቶቻቸውን በማቅረብ ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል። በተለይም በእንስሳት እርባታ ላይ በመሰማራት ጥሩ ገቢ እያገኙ መሆናቸውን የገለፁት አርሶ አደሮቹ፣ የእንስሳት እርባታን በማዘመን ረገድ ትልቅ ስራ እየሰሩ እንደሚገኙ ጠቁመዋል። ከአርሶ አደሮቹ መካከል በንብ እርባታና ማር ምርት ላይ የተሰማሩት አቶ አበራ ሰቦቃ እንደተናገሩት፣ እየሰሩት ባለው ስራ ተጠቃሚነታቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ምርታቸውን ለገበያ በማቅረብ ገቢያቸውን እያሳደጉ ነው። ወደፊትም ሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ ከማቅረብ ሳይወሰን ወደ ውጭ የሚላከውን ምርት በማሳደግ ረገድ ድርሻችንን እንወጣለን ብለዋል። በተመሳሳይ ወይዘሮ አሰገደች ስሜ በእንስሳት ተዋጽኦ አቅርቦት ላይ በማህበር ተደራጅተው እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። በተፈጠረው የገበያ ትስስር ተጠቃሚ መሆናቸውን የጠቆሙት አርሶ አደሯ፤ ከባለሙያዎችና ከመንግስት ጋር በቅንጅት እየሰሩ እንደሚገኙና በቀጣይም ስራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል። የሸገር ከተማ ግብርና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ደጃኔ በቀለ በበኩላቸው፤ ከተማዋ ቀደም ሲል ምርት ሳታመርት ከውጭ የምትገዛ እንደነበረች አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን በዘመናዊ ግብርና በማምረት ለገበያ ማቅረብ መጀመሯን ገልጸዋል። በከተማ ደረጃ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ በመፍጠርና ከቴክኖሎጂ ጋር ከማስተዋወቅ አንጻር በተከናወኑት ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
በጋምቤላ ክልል የእንስሳት ጤና አጠባበቅና ዝርያን በማሻሻል ምርታማነትን የማሳደግ ተግባር ውጤት አስገኝቷል
Sep 2, 2026 113
ጋምቤላ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፡-በጋምቤላ ክልል የእንስሳት ጤናን በመጠበቅና ዝርያን በማሻሻል ምርታማነትን ለማሳደግ የተከናወኑ ተግባራት ውጤት ማስገኘታቸውን የክልሉ ዓሣና እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። በክልሉ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ25 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር በላይ የወተት ምርት መገኘቱን ቢሮው ገልጿል። የክልሉ እንስሳትና ዓሣ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ክርሚስ ሌሮ ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በጋምቤላ ክልል ያለውን የእንስሳት ሀብት ምርታማነት ለማሳደግ የተሻሻሉ ዝርያዎችን የማስራጨትና የእንስሳት ጤና ላይ እየተሰራ ነው። ይህም ውጤት ማስገኘቱን ገልጸው፣ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የእንስሳት ሀብት ልማቱን ከሌማት ቱሩፋት መርሃ ግብር ጋር በማስተሳሰር የተሰራው ሥራም ለውጤቱ አስተዋጾ ማድረጉን ተናግረዋል። ለእዚህም በ2018 በጀት ዓመት 25 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር ወተት፣ ከ12 ሚሊዮን በላይ እንቁላል እና ሌሎች የእንስሳት ተዋጾ ምርት መገኘቱን ጠቅሰዋል። ቢሮው የእንስሳትን ጤና ለማስጠበቅም ዘመናዊ ላቦራቶሪ የማደራጀትና የእንስሳት ጤና ኬላዎችን ተደራሽ የማድረግ ሥራ መሰራቱን ገልጸዋል። በተለይም በማጃንግ ዞን ጎደሬ ወረዳ በሰው ሰራሽ ማዳቀል የተጀመሩትን የወተት ላሞች ዝርያ የማሻሻል ሥራዎች በአዲሱ በጀት ዓመትም ወደ ሌሎች ወረዳዎች የማስፋት እንቅስቃሴ መጀመሩን ተናግረዋል። የተሻሻሉ የእንቁላልና የሥጋ ዶሮዎችን በዘርፉ ልማት ለተሰማሩ አርቢዎች ተደራሽ በማድረግ ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። የእንስሳት ሀብት ልማቱን ከሌማት ቱሩፋት ኢንሼቲቩ ጋር ማስተሳሰር ከተጀመረ ወዲህ የባለሃብቱ፣ የአርሶ እና የአርብቶ አደሩ የዘርፉ ተጠቃሚነት ማደጉን ጠቅሰዋል። ይህም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ከማሳደጉ ባለፈ በከተሞች የዋጋ ንረትን ለማርገብ እያገዘ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ማጃንግ ዞን ጎዴሬ ወረዳ በተሻሻሉ የወተት ላሞች እርባታ ሥራ የተሰማረው አቶ ቢተውልኝ ግርማ እንዳሉት የተሻሻሉ የወተት ላሞችን በማርባት ወተትና የወተት ተዋጾን ለገበያ በማቅረብ ገቢያቸውን እያሳደጉ ናቸው። በአሁኑ ወቅት ሥራውን በማስፋት በቀን ከ60 ሊትር በላይ ወተት ለህብረተሰቡ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸዋል። በዶሮ እርባታ ሥራ በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን የገለጹት ደግሞ የክንድዬና ጓድኞቹ የዶሮ እርባታ ማህበር ተወካይ አቶ ክንድዬ ጥጋቡ ናቸው። ማህበሩ የእንቁላልና የሥጋ ደሮዎችን በማርባት በጋምቤላ ከተማና አካባቢው ላሉ ነዋሪዎች በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል
Sep 2, 2026 233
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ በተመለከተ ለኢዜአ መግለጫ ልኳል። በመግለጫውም ነሀሴ ወር የክረምት የመጨረሻ ወቅት በመሆኑ በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የዝናብ መጠን እንደሚቀንስ በማመላከት ለረጅም ጊዜ ደረቅ ሆነው የሰነበቱት ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን እንደሚያስተናግዱ ጠቁሟል። በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በመካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚቀነስ ነገር ግን በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስርጭትም በመጠንም የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ በመግለጫው ተመላክቷል። በሚቀጥሉት አስር ቀናትም ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ማኅበረሰቡም ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ የሚኖረውን የእርጥበት ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የግብርና ስራቹን እንዲያከናውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ከሚያስተናግዱ ቦታዎች መካከል ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር የምዕራብ ፣መካከለኛ ፣ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ካማሺ፣ መተከል፣ አሶሳ ዞኖች እንደሚገኙበት ከመግለጫው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ሁሉም ሸዋ ዞኖች፣ አኝዋክ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጉራጌ ፣አዲስ አበባ ፣ድሬዳዋ፣ የምዕራብ ፣የሰሜን ምዕራብ ፣መካከለኛው፣ ምሥራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ፣የሲዳማ አብዛኛው የክልሉ ዞኖች ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ከሚያስተናግዱ አካባቢዎች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ቀላል፣መካከለኛ እና ከባድ እርጥበትን የሚያስተናግዱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ፣ የመኸር ሰብል አብቃይ ፣ አርብቶ አድርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይህን የአየር ሁኔታ ለግብርና ስራዎቻቸው እንዲያውሉ አስገንዝቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መካከለኛ እና ከባድ የዝናብ መጠን የሚያስተናግዱ አካባቢዎች ተደፋታማ ማሳዎች ላይ የተዘጉ የማፋሰሻና የማንጣፈፊያ ቦዮች ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብል በሽታን አረምን አስቀድሞ መከላከል ፣የአፈር መሸርሸር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን፣ እና አርሶ አደሮችም የማሳ ጉብኝት በየጊዜው በማድረግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል። ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ ቦታዎች ደግሞ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የዝናብ ውሀን በማሰባሰብ በደረቅ ወቅቶች መጠቀም ፣የአፈር ውስጥ ትነትን መጠንን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ፣የእንስሳት ግጦሽ ሳርን በአግባቡ መያዝ ተገቢ ነውም ተብሏል። ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆየው አየር ፀባይ ሁኔታም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
በምዕራብ ጎንደር ዞን በሰብል ዝርያዎች ምርምርና በመነሻ ዘር ብዜት በትኩረት እየተሰራ ነው
Sep 2, 2026 134
መተማ፣ ነሐሴ27/2018 (ኢዜአ):- በምዕራብ ጎንደር ዞን የግብርና ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ በሰብል ዝርያዎች ምርምርና በመነሻ ዘር ብዜት ተግባራት ላይ በማተኮር እየተሰራ እንደሚገኝ የጎንደር ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ። ማዕከሉ እያካሔደ ባለው የዘር ብዜትና ማላመድ ስራ ላይ ያተኮረ የጉብኝት መርሃ ግብር ዛሬ ተካሂዷል። በማዕከሉ የቅባትና ጭረት ሰብሎች ምርምር ባለሙያ አቶ እንዳልካቸው አክሊሉ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ማዕከሉ የደጋ፣ ወይና ደጋና ቆላማ አካባቢዎች የሰብል ምርታማነት ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል። የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለማውጣት፣ ለማላመድ ፣ ለሰብል አያያዝና ጥበቃ ላይ ያተኮሩ የምርምር ስራዎችን በማከናወን ምርታማነትን በማሳደግ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በዚህም በያዝነው ክረምት በምዕራብ ጎንደር ቆላማ አካባቢዎች በ100 ሄክታር መሬት ላይ 17 የሰብል አይነቶች የዘር ብዜት እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። ከሁለት ሺህ ኩንታል በላይ ዘር ለዘር አባዥ አርሶ አደሮችና ተቋማት በመስጠት የዘር ብዜትና የማላመድ ተግባሩን በስፋት እያከናወነ እንደሚገኝ አስረድተዋል። በዚህም በቅርቡ ምርታማነታቸው ተረጋግጦ ይፋ የተደረጉትን "መልካም" የማሽላ፣ "ጠረፍ ወርቅ" የአኩሪ አተር፣ "ማርዘነብ" የሰሊጥና "ጃንተከል" የጥጥ ዝርያን ወደ አርሶ አደሩ ለማድረስ እየተሰራ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በማዕከሉ የማሽላ፣ ሰሊጥ ፣ አኩሪ አተር፣ የፈረንጅ ሱፍ ፣ ለውዝ ፣ ጤፍና በቆሎ የመነሻ ዘር ብዜት ስራዎች እያካሄደ መሆኑን ጠቁመው፤ ጉብኝቱም የጀመረውን ተግባር ለማስፋት የሚያስችል ነው። በማዕከሉ የሩዝ ሰብል ምርምር ባለሙያ አቶ አሳየ ብርሃኑ እንዳሉት፤ የሩዝ ሰብልን ከፎገራና አካባቢው ባሻገር በምዕራብ ጎንደር ያለውን እምቅ የተፈጥሮ ስጦታ በመጠቀም ለማስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት ምርታማነታቸው የተሻሻሉ "ሚሪካ4" እና "አዝመራ" የተሰኙ የሰሊጥ ዝርያዎችን ማቅረባቸውን ጠቁመው፤ አሁን በሄክታር እስከ 60 ኩንታል የሚሰጥ "ፎገራ1" የተሰኘ ዘር እያባዙ መሆኑን ተናግረዋል። የዛሬው ጉብኝትም በዞኑ በሰፋፊ እርሻ ቦታዎች ሩዝን ለማልማት የሚያስችል እየተደረገ ያለውን ጥረት አመራሩና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገንዝበው እንዲደግፉ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል። የመተማ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት ፈቃዱ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ ባለፉት ሰባት ዓመታት በምርጥ ዘር ብዜትና አዳዲስ ዝርያዎችን በማስተዋወቅ ምርታማነት ለማሳደግ ጥረት አድርጓል ነው ያሉት። በተለይም በምርምር የተገኘውን "መልካም" የተሰኘ የማሽላ ምርጥ ዘር በማቅረብ ቀደም ሲል በሄክታር ከ16 ኩንታል የነበረውን ምርታማነት ወደ 40 ኩንታል እንዲያድግ ማስቻሉን አውስተዋል። ወረዳውም ማዕከሉ የምርምር ስራውን ለማስፋፋት እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ ለወጭ ንግድና ለኢንዱስትሪ ግብአት የሚሆን ምርት ለማምረት የተያዘውን ግብ ለማሳካት እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በመስክ ጉብኝቱ የተሳተፉት አቶ መስፍን አበራ በበኩላቸው፤ የምርምር ማዕከሉ እያደረገ ያለው የዘር ብዜትና የማላመድ ተግባር በዘርፉ የተሰማሩ አርሶ አደሮችና ባለሃብቶችን ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። "በማዕከሉ ድጋፍ እየተባዛ ያለው ሰብል ቁመና እጅግ አስደሳች ነው" ያሉት አቶ መስፍን፤ ይህም የምርምር ስራው ውጤታማነትን ያረጋገጠ መሆኑን መመልከታቸውን አስረድተዋል።
ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን እያሳደገ የሚገኘው ኮደርስ
Sep 2, 2026 93
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኮደርስ ስልጠና ከዘመኑ ቴክኖሎጂ ጋር ለመራመድና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገላቸው መሆኑን ስልጠናውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ገለፁ። የ''አምስት ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ’’ ስልጠና ሐምሌ 2016 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋ መደረጉ ይታወሳል። መርሃ ግብሩ በቀጣዮቹ ሦስት ዓመታት 5 ሚሊየን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲጨብጡ ለማስቻል ያለመ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተያዘው ክረምት ወቅት የ5 ሚሊየን የኮደርስ መርሐ ግብር ወደ 7 ሚሊየን ከፍ ለማድረግ ጥሪ ማቅረባቸውም ይታወሳል። የኮደርስ ስልጠናን የተከታተሉ ሰልጣኞች ለኢዜአ እንዳሉት ስልጠናው ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ መሆኑን ተናግረዋል። በኮተቤ ሳይንስ ሼርድ ካምፓስ የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ዕፁብ የወንድወሰን ስልጠናን በተመቸ ጊዜ መውሰድ የሚቻልና ከክፍያ ነፃ የሆነ ዕድል መሆኑን ተናግራለች። ስልጠናው ከዘመኑ ጋር ለመራመድ የሚያስችል ራስን ማብቂያ መንገድ ነውም ብላለች። በሳውዝ ዌስት አካዳሚ የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ነቢዩ ዳዊት፣ ከትምህርት ሰዓቱ ጋር በማጣጣም በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል ስልጠናውን በመከታተል ማጠናቀቁን ገልጿል። ሌሎችም ወጣቶች የኮደርስን ስልጠናን በመውሰድ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን ማሳደግ እንዳለባቸው ጠቁሟል። የአዲስ አበባ ከተማ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ቱሉ ጥላሁን (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት እንደ ሀገር የኮደሮችን ቁጥር ወደ 7 ሚሊየን ለማድረስ የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት እየተሰራ ነው። ቀደም ሲል በአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ እቅድ ለአዲስ አበባ የተመደበው 809 ሺህ ለማሰልጠን እንደነበርና ሀገራዊ እድቀዱ ወደ ሰባት ሚሊዮን ማደጉን ተከትሎ ወደ 1 ነጥብ 1 ሚሊዮን ከፍ ማለቱን አንስተዋል። እስካሁን ባለው ለመመዝገብ ከታቀደው ውስጥ ወደ 985 ሺህ ዜጎች መመዝገባቸውንና ከእነዚህ ውስጥም 871 ሺህ ስልጠናቸውን አጠናቅቀው የምስክር ወረቀት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ቢሮው የተለያዩ መድረኮችን በመጠቀም የግንዛቤ ስራዎችን በማከናወንና ከተቋማት ጋር በመቀናጀት ዕቅዱን ለማሳካት እየሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል። በቀሪ ጊዜያትም የተማሪዎች ላብራቶሪዎችን፣ የወጣቶች ማዕከላትን፣ ቤተ መጻሕፍትን እና የተለያዩ የማህበረሰብ መድረኮችን በመጠቀም ዕቅዱን ለማሳካት ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ትግበራ በብዙ ዘርፎች ለመጣው እድገት የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል- ምሁራን
Sep 1, 2026 231
ዲላ ፤ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፡- የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ትግበራ በብዙ ዘርፎች ለመጣው እድገትና ለተመዘገበው ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ። ኢትዮጵያ የዲጅታል 2025 ስትራቴጂክ ትግበራ በስኬት በማጠናቀቅ ወደ ሌላ ምእራፍ በመሸጋገር የዲጅታል 2030 ትግበራ በማከናወን ላይ ትገኛለች። የስትራቴጂክ ትግበራው በዘርፉ በብዙ መልኩ የሚገለፅ እመርታ የተመዘገበ ሲሆን ለተለያዩ ሴክተሮችም የዲጅታል ትግበራና ማንሰራራት ወሳኝ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የዘርፉ ምሁራን የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ ትግበራ በብዙ ዘርፎች ለመጣው እድገትና ለተመዘገበው ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸዋል። የዘርፉ ልማት ከተለያዩ ሴክተሮች ተግባራዊ እንቅስቃሴ ጋር በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ የሚገናኝ መሆኑን ያነሱት ምሁራኑ በተለይም ትምህርት እና ጤናን ጨምሮ የተለያዩ የአገልግሎት ዘርፎች የሚጨበጥ ውጤት ማምጣት አስችሏል ብለዋል። በዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አዲሱ ፍርንጆ (ዶ/ር)፤ የዲጂታል መሰረተ ልማት ከግንባታ ጀምሮ እሰከ ትግበራ ድረስ በጥቂት አመታት በመንግስት የተከናወነው ስራ እና የመጣው ውጤት አስደናቂ መሆኑን አንስተዋል። የፋይዳ መታወቂያ፣ የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትና ሌሎችም ተያያዥ ተግባራዊ እንቅስቃሴዎች ለዜጎች ፈጣን አገልግሎትና ብልሹ አሰራርን ለመከላከል ማሳቻሉን አንስተዋል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናም በተለይም ወጣቶች በዘርፉ የካበተ እውቀት እንዲኖራቸውና ብቁ ተወዳዳሪ ሆነው የስራ እድል እንዲፈጠርላቸው ያደረገ መሆኑን አንስተዋል። የዘርፉ ልማት ለብዙ ሴክተሮች እድገትና ማንሰራራት መሰረት መሆኑን አንስተው በዲጅታል ዘርፍ በጥቂት አመታት የታየው ስኬት የኢትዮጵያን መፃኢ እድል በግልጽ የሚያመላክት መሆኑን አስረድተዋል። የዩኒቨርሲቲው በርካታ አገልግሎቶች በዲጂታል እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው በዘርፉ የወጣቶችን የፈጠራ አቅም ለማሳደግ በሰው ስራሽ አስተውሎትና በሮቦትክስ ዘርፍ ስልጠና እየተሰጠ ስለመሆኑም ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የኮምፒዮተር ሳይንስ መምህርና ተመራማሪ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት ዲጂታላይዜሽንና የውጭ ፕሮጀክት ዘርፍ ሃላፊ ሰናይት ሞቲ፤ የዲጂታል ኢትዮጵያ ትግበራ በፋይናንስ ስርዓት፣ በአገልግሎትና ሌሎችም ዘርፎች የፈጠረው አቅም ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል። የዲጂታል ሥርዓት የአገልግሎት አሰጣጥና የአኗኗር ዘይቤ እየሆነ መምጣቱን አንስተው መልዕክት ከመለዋወጥ ጀምሮ የትኛውንም አገልግሎት ለመስጠትና ለማግኘት ከወረቀት ንክኪ ነጻ የማድረግ ስራ እየተስፋፋ ይገኛል ብለዋል። የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም የዲጅታል ትግበራ ማዕከል በመሆን በዘርፉ የማህበረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ የዲጂታል 2030 እውን ለማድረግ እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና አስተዳደራዊ ዘርፎች ላይ መሰረታዊ እመርታዊ ለውጥ ማምጣቱ ይታወቃል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 የውድድር ዓመት ኮከቦች ሽልማት ሊያበረክት ነው
Sep 2, 2026 40
አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለ2018 ዓ.ም የውድድር ዓመት ምርጦች ዕውቅና የመስጠት መርሐ ግብር ጳጉሜን 3 እንደሚያካሂድ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ፣ የወንዶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሴቶች ከፍተኛ ሊግ፣ የሊግ አንድ እና ከ20 ዓመት በታች ፕሪምየር ሊግ የ2018 የውድድር ዘመን ኮከብ ተጫዋች፣ ኮከብ አሰልጣኝ፣ ኮከብ ግብ ጠባቂ፣ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ እንዲሁም ምስጉን ዳኛ እና ረዳት ዳኞች ሽልማት ይበረከታል። የሽልማት ስነ ሥርዓቱ የሚካሄድበት ቦታ በቀጣይ እንደሚገለጽ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።
ማንችስተር ሲቲ የቼልሲውን ኤንዞ ፈርናንዴዝን ለማስፈረም ተስማማ
Sep 1, 2026 223
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ ማንችስተር ሲቲ በዝውውር መስኮቱ ማብቂያ ቀን የቼልሲውን አማካይ ኤንዞ ፈርናንዴዝን በ125 ሚሊዮን ፓውንድ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ ደርሷል። የ25 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አማካይ ከቤንፊካ በ107 ሚሊዮን ፓውንድ ወደ ቼልሲ የተቀላቀለው እ.አ.አ በ2023 ነበር። ተጫዋቹ ቼልሲ ከፉልሃም ጋር ባደረገው የመጀመሪያ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ተሰልፎ የነበረ ቢሆንም፣ ከሉተን ጋር በካራባኦ ካፕ እንዲሁም ከብራይተን ጋር በተደረገው የሊጉ መርሐ ግብር አልተጫወተም። ይህ ዝውውር ሊቨርፑል ባለፈው ዓመት በክረምቱ የዝውውር መስኮት ማጠናቀቂያ ቀን የኒውካስትል ዩናይትዱን አጥቂ አሌክሳንደር ኢሳክ ለማስፈረም ከከፈለው የእንግሊዝ ክብረ ወሰን ክፍያ እኩል መሆኑን ስካይ ስፖርትስ ዘግቧል። ፈርናንዴዝ ወደ ማንችስተር ሲቲ ማምራት እንደሚፈልግ ያሳወቀ ሲሆን፣ በኢትሃድ ከቀድሞው የቼልሲ አሰልጣኙ ኤንዞ ማሬስካ ጋር እንደገና ይገናኛል። ተጫዋቹ በቀጣይ ሰዓታት ውስጥ የሕክምና ምርመራዎችን አድርጎ ዝውውሩን ሙሉ በሙሉ ያጠናቅቃል ተብሎ ይጠበቃል። ቼልሲ አርጀንቲናውን አማካይ የሚተካ ሌላ ተጫዋች ለማስፈረም እየሰሩ ይገኛሉ። ክለቡ የሮማውን ማኑ ኮኔ እና የሞናኮውን ላሚን ካማራን ለመግዛት እየተንቀሳቀሰ ሲሆን በፕሪሚየር ሊጉ የሚገኙ ሌሎች አማካዮችንም እየተመለከተ ይገኛል።
አርሰናል ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ
Sep 1, 2026 271
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አርሰናል አስቶንቪላ 1 ለ ዐ አሸንፏል። ማምሻውን በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቡካዮ ሳካ በ59ኛው ደቂቃ ግቧን አስቆጥሯል። የ24 ዓመቱ የክንፍ መስመር ተጫዋች በውድድር ዓመቱ ሁለተኛ ግቡን ከመረብ ላይ አሳርፏል። እምብዛም ግልጽ የግብ እድሎች ባልተፈጠሩበት ጨዋታ አርሰናል ያገኘውን የግብ እድል በሚገባ ተጠቅሟል። አስቶንቪላ ወደ አርሰናል የግብ ክልል በተደጋጋሚ ጊዜ ቢደርስም ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ ተስኖታል። በ75 ሚሊዮን ፓውንድ ከኒውካስትል ዩናይትድ ወደ አርሰናል የተዘዋወረው ብሩኖ ጉማራይሽ ተቀይሮ በመግባት የመጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል። የወቅቱ የሊጉ ሻምፒዮን አርሰናል ተከታታይ ድሉን አግኝቷል። በአንጻሩ በክረምቱ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት በርካታ ቁልፍ ተጫዋቾቹን ያጣው አስቶንቪላ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል። አስቶንቪላ በሁለቱ የሊግ ጨዋታዎች ኢላማውን የጠበቀ ሙከራ ማድረግ አልቻለም። በሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር አስቶንቪላ ከአዲስ አዳጊው ሁል ሲቲ ጋር ይጫወታል። በለንደን ደርቢ አርሰናል ከቼልሲ የሚያደርገው ጨዋታ ከወዲሁ ተጠባቂ ነው። የሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነሐሴ 29 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ይካሄዳሉ።
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሴካፋ ማጣሪያ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቀቀ
Aug 31, 2026 263
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 25/2018 (ኢዜአ)፦ በካፍ የሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ የደረጃ ጨዋታ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የደቡብ ሱዳኑን ዬ ጆይንት ስታርስን 6 ለ 1 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ እፀገነት ግርማ፣ ብዙአየሁ ታደሰ፣ ማህሌት ምትኩ፣ እሙሽ ዳንኤል፣ ምህረት አየለ እና ረድኤት አስረሳኸኝ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ማውሪን ናንኪንጋ በፍጹም ቅጣት ምት የዬ ጆይንት ስታርስን የማስተዛዘኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፋለች። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በማጣሪያው ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል። ንግድ ባንክ በግማሽ ፍጻሜው በዩጋንዳው ካዌምፔ ሙስሊም ሌዲስ መሸነፉን ተከትሎ በካፍ ሴቶች ሻምፒዮንስ ሊግ የመሳተፍ ህልሙ ማክተሙ ይታወቃል።
አካባቢ ጥበቃ
የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ ነው
Sep 2, 2026 95
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ልምድ ለማካፈል ወጣቶች ወደተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ሊያቀኑ መሆኑ የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽህፈት ቤት ሀላፊ አባንግ ኩመዳን ገለጹ። ከመላው የሀገሪቱ የተውጣጣ የወጣቶች ቡድን በሦስት የአፍሪካ ሀገራት ነገ የሚጓዝ ይሆናል። የብልፅግና ፓርቲ ወጣቶች ክንፍ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አባንግ ኩመዳን እንደገለጹት፤ ወጣቶቹ የሚጓዙት ጋና፣ ዚምባብዌና ናይጄሪያ ነው። በዚህ የጉዞ መረሃ ግብር ሀያ አራት ወጣቶች የሚሳተፉ ሲሆን፤ የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ችግኞችን በመትከል ልምድ እንደሚያካፍሉም አስታውቀዋል። መርሃ ግብሩ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄድ መሆኑን ገልጸው፤ ከዚህ ቀደም የብልጽግና ወጣት ክንፍ በፓኪስታን የችግኝ ተከላ ማካሔዳቸውን ገልጸዋል። የልዑካኑ ጉዞ የልምድ ልውውጥ ከማድረግ በተጨማሪ ወንድማማችነትን ለማጠናከር የሚያግዙ ተግባራትን እንደሚያከናውን አስታውቀዋል። በቀጣይም ወጣቶች ወደ ተለያዩ ሀገራት በመሄድ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማከናወን የኢትዮጵያን ልምድ የማካፈል ተግባርን ያጠናክራል ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በስኬታማነት እየተከናወነ ይገኛል። በዚህ ዓመት ብቻ ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኞች በአንድ ጀምበር መተከላቸው ይታወሳል። ይህ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ዓለም አቀፍ እውቅና እያገኘ ሲሆን የተለያዩ ሀገራትም ተሞክሮውን እየወሰዱት ይገኛሉ።
በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ ይኖራቸዋል
Sep 2, 2026 233
አዲስ አበባ ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ) ፦ በሚቀጥሉት አስር ቀናት ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው የኢትዮጵያ የሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ከነሃሴ 26 ቀን ጀምሮ እስከ ጳጉሜን አምስት ቀን 2018ዓ.ም ድረስ በኢትዮጵያ የሚኖረውን የአየር ፀባይ ሁኔታ በተመለከተ ለኢዜአ መግለጫ ልኳል። በመግለጫውም ነሀሴ ወር የክረምት የመጨረሻ ወቅት በመሆኑ በሰሜን ምሥራቅ የሀገሪቱ ክፍሎች የዝናብ መጠን እንደሚቀንስ በማመላከት ለረጅም ጊዜ ደረቅ ሆነው የሰነበቱት ደቡብና ደቡብ ምሥራቅ አካባቢዎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸውን እንደሚያስተናግዱ ጠቁሟል። በምሥራቅ፣ በሰሜን ምሥራቅና በመካከለኛው ኢትዮጵያ አካባቢዎች የዝናብ መጠንና ስርጭት እንደሚቀነስ ነገር ግን በደቡብና ደቡብ ምሥራቅ የሀገሪቱ አካባቢዎች በስርጭትም በመጠንም የተሻለ ዝናብ እንደሚያገኙ በመግለጫው ተመላክቷል። በሚቀጥሉት አስር ቀናትም ምዕራብ፣ሰሜን ምዕራብ፣ደቡብ ምዕራብ እና መካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው ዝናብ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል። ማኅበረሰቡም ከላይ በተጠቀሱት ቦታዎች ላይ የሚኖረውን የእርጥበት ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የግብርና ስራቹን እንዲያከናውን ኢንስቲትዩቱ አስታውቋል። ከመካከለኛ እስከ ከባድ መጠን ያለው እርጥበት ከሚያስተናግዱ ቦታዎች መካከል ቄለም ወለጋ፣ ኢሉባቦር የምዕራብ ፣መካከለኛ ፣ደቡብ እና ሰሜን ጎንደር፣ የሰሜን፣ የምዕራብ እና ምሥራቅ ጎጃም ዞኖች፣ ካማሺ፣ መተከል፣ አሶሳ ዞኖች እንደሚገኙበት ከመግለጫው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ሁሉም ሸዋ ዞኖች፣ አኝዋክ፣ ከፋ፣ ምዕራብ ኦሞ፣ ጉራጌ ፣አዲስ አበባ ፣ድሬዳዋ፣ የምዕራብ ፣የሰሜን ምዕራብ ፣መካከለኛው፣ ምሥራቅ እና ደቡብ ትግራይ ዞኖች ፣የሲዳማ አብዛኛው የክልሉ ዞኖች ደግሞ ከቀላል እስከ መካከለኛ መጠን ያለው ዝናብ ከሚያስተናግዱ አካባቢዎች መካከል መሆናቸው ተጠቁሟል። ኢንስቲትዩቱ ቀላል፣መካከለኛ እና ከባድ እርጥበትን የሚያስተናግዱ የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ፣ የመኸር ሰብል አብቃይ ፣ አርብቶ አድርና ከፊል አርብቶ አደር አካባቢዎች የሚገኙ የማኅበረሰብ ክፍሎች ይህን የአየር ሁኔታ ለግብርና ስራዎቻቸው እንዲያውሉ አስገንዝቧል። ይህ በእንዲህ እንዳለ መካከለኛ እና ከባድ የዝናብ መጠን የሚያስተናግዱ አካባቢዎች ተደፋታማ ማሳዎች ላይ የተዘጉ የማፋሰሻና የማንጣፈፊያ ቦዮች ክፍት እንዲሆኑ ማድረግ፣ የሰብል በሽታን አረምን አስቀድሞ መከላከል ፣የአፈር መሸርሸር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ማከናወን፣ እና አርሶ አደሮችም የማሳ ጉብኝት በየጊዜው በማድረግ አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባም አሳስቧል። ከቀላል እስከ መካከለኛ እርጥበት የሚያገኙ ቦታዎች ደግሞ የሚገኘውን እርጥበት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል፣ የዝናብ ውሀን በማሰባሰብ በደረቅ ወቅቶች መጠቀም ፣የአፈር ውስጥ ትነትን መጠንን ለመቀነስ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን ፣የእንስሳት ግጦሽ ሳርን በአግባቡ መያዝ ተገቢ ነውም ተብሏል። ለተከታታይ አስር ቀናት የሚቆየው አየር ፀባይ ሁኔታም የክረምት ዝናብ ተጠቃሚ በሆኑ የሀገሪቱ ተፋሰሶች ላይ ከዝቅተኛ እስከ ከፍተኛ መጠን ያለው የገፀ ምድር የውሃ ፍሰት እንደሚኖራቸው ኢንስቲትዩቱ ገልጿል።
በአፍሪካ አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል
Sep 2, 2026 289
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ)፦በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትንና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረተ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ገቢራዊ ማድረግ እንደሚገባ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓም ተገልጿል። የአፍሪካ ቀጣና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም ፎረም በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን መካሄድ ጀምሯል። የቅድመ ማስጠንቀቂያ ለሁሉም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2022 ይፋ የተደረገ ሲሆን እስከ 2027 እያንዳንዱን ሰው በአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና በተፈጥሮ አደጋዎች መጠበቅ የሚያስችል ኢንሼቲቭ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ከተመድ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ቢሮና ሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር የአፍሪካ የተቀናጀ አይነተ ብዙ አደጋ ቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ እርምጃ ሥርዓት ተግባራዊ አድርጓል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሀና አበበ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ፎረም ወቅታዊና ተገቢ ነው። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ መዛባት ድርቅ፣ ጎርፍ እና ሌሎችን አደጋዎችን በተደጋጋሚ እያስተናገደች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ሴቶችና ህፃናት ጨምሮ በርካታ የማህበረሰብ ክፍሎች የአደጋው ገፈት ቀማሽ እየሆኑ ነው ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የውስጥ የፋይናንስ አቅምን ማጎልበትና ተቋማዊ አንድነት ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የአየር ንብረት መዛባትና መሰል አደጋዎችን ለመቋቋም በቴክኖሎጂ የተደገፈና በትብብር ላይ የተመሰረት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን የብሔራዊ የልማት ዕቅዷ አካል ማድረጓን ጠቅሰው፤ በሰው ሰራሽ አስተውሎት፣ በቴሌኮሙኒኬሽን፣ በፋይናንስና ሌሎችም ተቋማት መካከል ጠንካራ ትብብር መፍጠር እንደሚገባ ተናግረዋል። ማንም ሀገር ብቻውን የአደጋ ስጋት ቅነሳ ስትራቴጂን ውጤታማ ማድረግ እንደማይችል ገልጸው፤ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራትና የተለያዩ አጋር አካላት ጋር በአይነተ ብዙ የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። በአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን የዘላቂ አካባቢና ብሉ ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሀርሰን ኒያምቤ፤ በአፍሪካ ቀጣይነት ያለው የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ማህበረሰቡን አደጋን የመቋቋም አቅም መገንባትና ከአደጋ መጠበቅ ይገባል ብለዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት እንደ አውሮፓውያን ዘመን አቆጣጠር በ2027 እያንዳንዱን ሰው ከአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል አደጋዎች መጠበቅ የሚለውን ግብ ለማሳካት ውይይቱ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ጎርፍና የተራዘመ ደርቅ፣ በማህበረ-ኢኮኖሚ፣ እና በሌሎች አደጋዎች ተጋላጭነት ተባብሶ መቀጠሉን በመግለጽ፤ አፍሪካውያን ውስጣዊ ትብብራቸውን ማጠናከር አለባቸው ብለዋል። አደጋ ድንበር የለውም ያሉት ዳይሬክተሩ፤ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን በአይነቱ ብዙ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአባል ሀገራቱን አቅም ለመገንባት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ቢሮ ዳይሬክተር ኤግነስ ኪጃዚ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት የአመራር ቁርጠኝነት እያደገ በመምጣቱ መሻሻል እያመጣ መሆኑን ተናግረዋል። ይሁን እንጂ አፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትና መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች በፍጥነትና በተወሳሰበ ሁኔታ ተባብሰው ቀጥለዋል ብለዋል። በመሆኑም ችግሩን ለመቆጣጠር የቅደመ ማስጠንቀቂያ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንስና በሀገራት የተቀናጀ አሰራር መምራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት የ2027 ግብ ጠቃሚ መሰረት መሆኑን በመግለፅ፤ በአፍሪካ የፋይናንስ ተቋማት ለቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓት ግንባታ ዘላቂና እምነት የሚጣልባቸው መሆን አለባቸው ብለዋል። በአፍሪካውያን መካከል ቀጣናዊ ትብብርን ማጠናከር የሚያስችሉ ተቋማትን መገንባት እንደሚገባ በመጥቀስ፤ የዓለም ሚቲዎሮሎጂ ድርጅት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል።
የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ይካሄዳል - የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት
Sep 1, 2026 166
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 26/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና ዘላቂ የኢንቨስትመንት እድል የሚያሰፋ የመጀመሪያው የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት አስታውቀ። የምክር ቤቱ ምክትል ዋና ጸሐፊ ካሳሁን ማሞ፤ ምክር ቤቱ ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀውን የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም፤ የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የኢትዮጵያን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካትና ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር ለማፋጠን ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ገልጸዋል። ፎረምና ኤግዚቢሽኑም ፖሊሲ አውጪዎች፣ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮችና የአረንጓዴ ቢዝነስ ኩባንያዎችና አልሚዎች በተሳተፉበት ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ አስታውቀዋል። የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ በማላቅ ዘላቂ ሥነ-ምህዳራዊ ዕይታን ያማከለ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት እንዲጎለብት ከአጋር አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም ረገድ ከጀርመን ዓለም አቀፍ የትብብር ድርጅት እና ከኔዘርላንድ የልማት ድርጅት ጋር በመተባበር የአረንጓዴ ልማትና ዘላቂነት ማዕከል ማቋቋሙን አመልክተዋል። የአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ፎረምና ኤግዚቢሽንም ጤናማ ሥነ-ምኅዳርን የተከተለ የታዳሽ ኃይልና አረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታን በማጠናከር የዘርፉ ተዋናዮች ምርትና አገልግሎታቸውን እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል። መድረኩም በአረንጓዴ ኢንቨስትመንት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትንና ሥራ ፈጣሪዎችን በማገናኘት አዳዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግር በማፋጠን ዘላቂ ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋትና የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ለማላቅም ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት አስገንዝበዋል። በኔዘርላንድ የልማት ድርጅት የሊዌይ የፕሮግራም ማኔጀር ሔለን ጌታው በበኩላቸው፤ መድረኩ ከአዲስ አበባ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው ብለዋል። ፎረሙም በአረንጓዴ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ አልሚዎችን የፋይናንስ፣ የገበያ፣ የቴክኖሎጂና የመረጃ ተግዳሮቶች በመለየት መፍትሔ የሚመላከትበት ጠቃሚ መድረክ እንደሚሆንም ገልጸዋል። በተጨማሪም ባለድርሻ አካላትን በማገናኘት የገበያ ትስስርና የድጋፍ ዕድሎችን ለመፍጠር እንደሚያስችል አክለዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 1509
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች ነው- ሲኤንኤን
Aug 4, 2026 1189
የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ በኢትዮጵያ ላይ በሚያተኩረው ዘገባዋ በሀገሪቱ ኮረብቶች ያለውን ወርቅ ጨምሮ ከፍተኛ የብረት ማዕድናት አምራች ለመሆን እያደረገች ያለውን ጥረት መመልከቷን ተናግራለች። በዘገባዋ ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ከፍተኛ የሃይል ሚዛን መሆን እንደምትፈልግ ገልጻ፤በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኘው ኩርሙክ የወርቅ ፕሮጀክት በኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንቶች ውስጥ በዋናነት የሚጠቅስ መሆኑን ተናግራለች። በምዕራብ ኢትዮጵያ አረንጓዴ ከለበሱት ከፍተኛ የኮረብታ ስፍራዎች ላይ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን የሚያስገኙ ከፍተኛ የወርቅ ሀብቶች እንዳሉ እና አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ብቅ እያሉ መሆኑን ትናገራለች። በሺዎች የሚቆጠሩ የግንባታ ባለሙያዎች እና ማዕድን አውጪዎች በኢትዮጵያ ግዙፍ የሆነውን የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ ግንባታ እያከናወኑ እንደሚገኝ ገልጻለች። በስፍራው የሚገኙ የማዕድን እና ጂኦሎጂ ባለሙያዎች የወርቅ ማዕድኑን የማጣራት ስራ እያከናወኑ መሆኑን ገልጻለች። ጋዜጠኛዋ የወርቅ ማጣራት እና ምርት ሂደቱን በተመለከተ ከባለሙያዎች ማብራሪያ ማግኘቷንም አመልክታለች። ወርቁን የማግኘት ሂደቱ እጅጉን ፈታኝ እና አድካሚ እንደሆነ ገልጻ፥ይሁንና ልፋቱ ትልቅ ጠቀሜታ የሚያስገኝ መሆኑን ተናግራለች። የወርቁን ግብአት ውጪ ሀገር ልኮ ከማጣራት ይልቅ በኩርሙክ የወርቅ ማዕድን ፋብሪካ የራሱ ማጣሪያ ፕላንት እንዳለው በጉብኝቷ ወቅት መረዳቷን አመልክታለች። የሲኤንኤኗ ጋዜጠኛ ቪክቶሪያ ሩቢዳሪ ወርቅ የሀገሪቷ ዋና የወጪ ንግድ ገቢ ምንጭ እየሆነ መምጣቱን ገልጻለች። ባለፈው ዓመት በወርቅ የተገኘው የወጪ ንግድ ገቢ ከፍተኛ መሆኑን ተናግራለች። ይህም የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ውጥኖች በግልጽ የሚያሳይና ኢትዮጵያ የማዕድን ሀብቷን ቀጣዩ የኢኮኖሚዋ ምሰሶ እያደረገች እንደምትገኝ ሲኤንኤን በዘገባው አስረድቷል።
የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር ይገባል
Jul 30, 2026 1463
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 23/2018 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተትን ለመቋቋም አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ ተመለከተ፡፡ የአፍሪካ ህብረት በፓሲፊክ ውቅያኖስ ሙቀት የሚፈጠር የአየር ንብረት መዛባት (ኤልኒኖ) አስመልክቶ አስቸኳይ ስብስባውን ዛሬ በአዲስ አበባ እያካሄደ ይገኛል። በህብረቱ የግብርና፣ ገጠር ልማት፣ ውሃ እና ከባቢ አየር (ADREE) ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ የተዘጋጀው ስብሰባ እ.አ.አ በ2026 ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኤልኒኖ አየር ንብረት ክስተት ለመቋቋም እና አህጉራዊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። ከፍተኛ የምክክር መድረኩ "የአፍሪካን ቅድመ ዝግጅት፣ የመቋቋም አቅም እና የአየር ንብረት እርምጃዎችን ማጠናከር" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። በስብሰባው ላይ በአካል ከተገኙት ተሳታፊዎች በተጨማሪ በበይነ መረብ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በሁነቱ ላይ ታድመዋል። የስብሰባው ዋና ትኩረት አፍሪካ ለኤልኒኖ የተቀናጀ ምላሽ እንድትሰጥ የጋራ ትብብርን መፍጠር ነው። በተጨማሪም በ31ኛው እና በ32ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎች (COP31) እና (COP32) ላይ የአፍሪካን ሚና ማሳደግ እና የአህሪቷን አጀንዳዎች ጎልተው እንዲታዩ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይም ይመክራል። ለአንድ ቀን የሚቆየው ስብስባ በባለሙያዎች እና በሚኒስትሮች ደረጃ ተከፍሎ ይካሄዳል። የአፍሪካ የሜቲዎሮሎጂ ትግበራዎች ልማት ማዕከል (ACMAD) የኤልኒኖ ክስተትን ትንበያ እና በአህጉሪቱ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ተፅዕኖ በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀርባል። በተጨማሪም በአየር ንብረት ለውጥ የአፍሪካ ተደራዳሪዎች ቡድን መሪነት አህጉሪቱ በመጪዎቹ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች የምታደርገው ተሳትፎ እና ለዓለም አቀፉ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ጉባኤ የሚደረጉ ዝግጅቶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል። የአፍሪካ የውሃ ሚኒስትሮች ምክር ቤትም (AMCOW) ከ 2026 የአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ሀሳብ ጋር የተያያዘ ሪፖርት ያቀርባል። የአባል ሀገራት ሚኒስትሮችም ስለ ኤልኒኖ ተፅዕኖ እና አህጉራዊ ምላሽ መግለጫዎችን ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። ስብሰባው በኤልኒኖ ዙሪያ የተዘጋጀውን የድርጊት መርሃ ግብር፣ የባለሙያዎች ሪፖርት እና የጋራ የአቋም መግለጫ እንደሚያፀድቅም ተመላክቷል። በስብሰባው ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተጨማሪ የተለያዩ አጋር አካላት ተገኝተዋል። ኤልኒኖ (El Nino) በፓሲፊክ ውቅያኖስ የውሃ ሙቀት ከመደበኛው በላይ በመጨመሩ ምክንያት የሚከሰት ዓለም አቀፋዊ የከባቢ አየርና የአየር ንብረት መዛባት ክስተት ነው። የኤልኒኖ ተጽእኖ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያልተለመደ የከፋ ድርቅን፣ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋንና የሙቀት መጠን መጨመርን በማስከተል በግብርና እና በሰዎች ሕይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል።
ሀገራት የአፍሪካ ህብረትን የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ ማድረግ ይገባቸዋል - አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና
Jul 29, 2026 2058
አዲስ አበባ ፤ሐምሌ 22/2018(ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የአፍሪካ ህብረት የፋይናንስ ነጻነት ለማረጋገጥ የተጠናከረ ድጋፍ እንዲያደርጉ የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ጥሪ አቀረቡ። በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው እና የህብረት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሳተፉበት 49ኛው የአፍሪካ ህብረት ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ዛሬ ተጠናቋል። የምክር ቤቱ ስብሰባ “ ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚለው የ2026 የህብረቱ ዓመታዊ መሪ ሀሳብ አማካኝነት ተከናውኗል። የብሩንዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የአፍሪካ ህብረት የስራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ሰብሳቢ አምባሳደር ኤድዋርድ ቢዚማና ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ምክር ቤቱ አጀንዳ 2063 እና የህብረቱ መሪ ሀሳብን ጨምሮ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ መምከራቸውን ገልጸዋል። የአፍሪካ ሀገራት አጀንዳ 2063 ለማሳካት እና የእርስ በእርስ ትብብራቸውን ለማጠናከር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን አመልክተዋል። በፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ያሳዩት ፍላጎት አበረታች መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ኬንያ ለአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ በበጎ ፈቃደኝነት ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ይፋ ማድረጋቸው የፋይናንስ ነጻነትን ማረጋገጥ የሚያስችል እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል። ሌሎች የህብረቱ አባል ሀገራት የኢትዮጵያንና የኬንያን ፈለግ በመከተል ተመሳሳይ እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል። ሀገራት የገቧቸውን ቃል ኪዳኖችና ስምምነት የደረሱባቸውን ጉዳዮች በሚገባ መተግበር እንዳለባቸውም ነው ያስገነዘቡት። ኢትዮጵያ የምክር ቤቱ ስብሰባ በስኬት እንዲጠናቀቅ እንዲሁም ለሚኒስትሮችና ሌሎች ልዑካን ላደረገችው አቀባበልም አመስግነዋል።
ሐተታዎች
የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች
Aug 28, 2026 257
አዲስ አበባ ነሀሴ 22/2018 (ኢዜአ) የስኬት መገለጫና የውጤት ማሳያዎች በኢትዮጵያ ባለፉት አምስት ዓመታት ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (Homegrown Economic Reform) እቅዶችን በመተግበር በበርካታ ዘርፎች መሠረታዊ ለውጦችን እና ስኬቶችን ማስመዝገብ ተችሏል። በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል (አይሲቲ)፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች የሀገሪቱን ምጣኔ ሀብታዊ አቅም ከማሳደግ ባሻገር የወደፊት ዘላቂ እድገት መሠረት ያኖሩ መሆኑን መናገር ይቻላል። በመሆኑም በአምስቱ ዋና ዋና ሴክተሮች የመጡ ውጤቶችና የተመዘገቡ ስኬቶችን በወፍ በረር እንቃኛለን። 1. በግብርና ዘርፍ የስንዴ ምርትና የውጭ ኤክስፖርት: የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት መስፋፋት ኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናዋን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሰረት አስቀምጧል። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ ሀገር መላክ የቻለችበትን እመርታዊ ስኬትም አሳይቶናል። የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቭን በመተግበር በወተት፣ በእንቁላል፣ በዶሮና የማር ምርት እንዲሁም በአትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሩዝና ሻይ ልማትም ባለፉት አምስት አመታት እመርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል። አርሶ አደሩ የመሬትና የውሃ ሀብቶችን አቃፊ በሆነ መንገድ በመጠቀም በዓመት ሁለትና ሶስት ጊዜ ማምረት የሚችልበት አሰራር ተዘርግቷል። በዚህም የቤተሰብ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ሁነኛ የገቢ ምንጭ የሆነበትን እድል ፈጥሯል። ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን የመቻል አቅም በመገንባት ላይ ይገኛል። በተለይም ደግሞ የቡና ምርታማነትና ጥራት በማደጉ ምክንያት በኤክስፖርት ዘርፍ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ማገኘት ተችሏል። በዘርፉ በቀጣይም የግብርናውን ዘርፍ ይበልጥ በዘመናዊ ቴክኖሎጂና በሜካናይዜሽን በማስደገፍ ምርታማነትን የማሳደግ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የመስኖ መሠረተ ልማቶችን በማስፋፋት የዝናብ ጥገኝነትን ለመቀነስ መጣር እንዲሁም የግብርና ምርቶችን ጥራት በማሻሻልና በማቀነባበር ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ዋጋ ማሳደግ ተገቢ ይሆናል። 2. የኢንዱስትሪ ዘርፍ ሀገራዊ የአምራች ኢንዱስትሪ ንቅናቄ በመፍጠር ቀደም ሲል ተቆልፈው የነበሩና በዝቅተኛ አቅምያመርቱ የነበሩ ፋብሪካዎች ወደ ሙሉ የማምረት አቅማቸው እንዲመለሱ ተደርጓል። የሀገር ውስጥ የምርት ፍላጎትን በመሸፈን ለውጭ ሀገር ምርቶች ይወጣ የነበረውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪም መቀነስ አስችሏል። ለሀገር ውስጥና ለውጭ ባለሀብቶች ምቹ የህግና የአሰራር ሁኔታዎችን በመፍጠር በርካታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል። ከተገነቡት የተቀናጁ የግብርና ማቀነባበሪያ ፓርኮች (IAIPs) ጋር አርሶ አደሩን በማስሳሰር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲጠናከር ተደርጓል። የአምራች ዘርፉ መስፋፋት ለብዙ ሺህ ዜጎች፣ በተለይም ለወጣቶች የሥራ እድል መፍጠር የታቸለበት ሆኗል። በቀጣይም የኢንዱስትሪ ፓርኮችን በኃይል፣ በሎጂስቲክስና በግብአት አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በመደገፍ ኤክስፖርትን ማሳደግ። የአምራች ኢንዱስትሪዎች 80% እና ከዚያ በላይ የሀገር ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት፣ በህዝብና በግል አጋርነት (PPP) አማካኝነት በትልልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶች ላይ የግሉን ዘርፍ አሳትፎ ማስፋፋት ትኩረት የሚደረግበት ይሆናል። 3. የዲጂታል (አይሲቲ) ዘርፍ የ"ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" ስልት ስኬቶችን በማስቀጠል ወደ "ዲጂታል 2030" እቅድ መሸጋገር ተችሏል። በ"መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በሌሎች ፖርታሎች አማካኝነት ህዝባዊ አገልግሎቶችን በበይነ-መረብ (Online) የመስጠት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የዜጎችን መረጃ ማዕከላዊ የሚያደርግና ለፋይናንስ እንዲሁም ለሌሎች አገልግሎቶች መሠረት የሆነውን የፋይዳ መታወቂያ ፕሮጀክት በላቀ መልኩ ማሳካት ተችሏል። የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን የኮደር ስልጠናም የዜጎችን የዲጂታል ክህሎት ለማሳደግ ታላቅ ሀገራዊ የስልጠና መርሃ ግብር ተዘርግቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።የዲጂታል አገልግሎቶች መዘርጋታቸው የፊት ለፊት ግንኙነትን በመቀነስ ሌብነትንና ብልሹ አሰራርን በመከላከል የኢንቨስትመንት ምህዳሩን አሳልጧል። የቴሌኮም ዘርፍ ውድድር: የቴሌኮም ዘርፉን ክፍት ማድረግን ተከትሎ የኢንተርኔትና የኔትወርክ ተዳራሽነትንና ጥራትን በየገጠሩ የማስፋት ስራ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የዲጂታል ክፍያ ሥርዓቶችን እና የባንክ አገልግሎቶችን ይበልጥ ዘመናዊና የተቀናጁ ማድረግም አስፈላጊ ይሆናል። የሀገሪቱን የዲጂታል መሠረተ ልማት ከሳይበር ጥቃቶች የመጠበቅ አቅምን ማጠናከር። 4. የማዕድን ዘርፍ በዘርፉ ይስተዋል የነበረውን ኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ ንግድ በመግታት ህጋዊ አሰራርና ቁጥጥር እንዲሰፍን ተደርጓል። የህግና መመሪያዎች ማሻሻያ በማድረግ የማዕድን ዘርፉን ለውጭና ሀገር ውስጥ ኢንቨስትመንት ማራኪ የሚያደርጉ የፖሊሲ ማሻሻያዎች ተደርገዋል። የወርቅ፣ የከሰል ድንጋይ፣ የሲሚንቶ ግብአቶችና የከበሩ ድንጋዮች ምርትን በማሳደግ ዘርፉ የሀገሪቱ ዋነኛ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ እንዲሆን ተሰርቷል። በተለይም የከሰል ድንጋይ ምርትን በሀገር ውስጥ አምርቶ በመተካት ለፋብሪካዎች ግብአት ማቅረብ ተችሏል። 5. የቱሪዝም ዘርፍ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ( ዶ/ር)አነሳሽነት የተጀመሩት "ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች በመላ ሀገሪቱ በርካታ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መገንባት ተችሏል። በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የተከናወኑ የኮሪደር ልማቶች የከተሞችን ውበትና ለኑሮ ምቹነት ከመጨመራቸው ባሻገር ለከተማ ቱሪዝም ትልቅ እድል ፈጥረዋል። አዲስ አበባ በርካታ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ኮንፈረንሶችን ባካሄደችበት የዲፕሎማሲና የኮንፈረንስ ማዕከልነቷን አጠናክራለች። የሀገሪቱን ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች የመጠበቅ፣ የማደስና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ ስራዎች በስፋት ተከናውነዋል። በድምሩ ባለፉት አምስት ዓመታት በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል፣ በማዕድን እና በቱሪዝም ዘርፎች የተመዘገቡት ስኬቶች ሀገሪቷን ወደ ተሻለ የኢኮኖሚ ምዕራፍ ማሸጋገር አስችለዋል። በመሆኑም እነዚህን ስኬቶች አጠናክሮ ለማስቀጠል የታቀዱትን የወደፊት ስትራቴጂካዊ አቅጣጫዎች በተቀናጀ መልኩ መተግበር፣ የህግ የበላይነትን ማረጋገጥ እና የግሉን ዘርፍ አሳታፊነት ማሳደግ በቀጣይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት ዋነኛ የቤት ስራ ይሆናል።
የአረንጓዴ አሻራ ስኬት፦ኢትዮጵያን የአየር ንብረት ጥበቃ ሞዴል ያደረገ ኢኒሼቲቭ
Aug 23, 2026 483
የኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በይፋ የተጀመረው በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት ነው። በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እስከ አሁን ከ54 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉ ሲሆን፣ 32ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 32) እ.አ.አ በ2027 በኢትዮጵያ በሚካሄድበት ወቅት የተተከሉ ችግኞችን ብዛት 65 ቢሊዮን የማድረስ እቅድ ተይዞ እየተሠራ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታዎች ያሉት ነው።ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የምግብ ምርታማነትን በማሳደግ፣ የደን ሽፋንን በመጨመር፣ የተራቆተ መሬትን ወደ ነባር ይዞታው እንዲመለስ በማድረግ እና አይበገሬ የአረንጓዴ ኢኮኖሚን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። በዚህም በ2011 ዓ.ም 17.2 በመቶ የነበረው የኢትዮጵያ የደን ሽፋን፣ ባለፉት ተከታታይ ዓመታት በተከናወነው ሥራ ወደ 23.6 በመቶ ማደግ ችሏል። ይህ ሀገራዊ እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅና አግኝቷል።በሁለተኛው የዓለም የምግብ ሥርዓት ጉባኤ እንዲሁም በአዲስ አበባ በተካሄደው ሁለተኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ሥራዋን ያስተዋወቀች ሲሆን፣ የአፍሪካ ሀገራትም ለአህጉሪቱ ትልቅ ተምሳሌት የሚሆን ኢኒሼቲቭ ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ኮፕ 32ን እንድታዘጋጅ መመረጧ በአየር ንብረት ለውጥ መከላከል እያከናወነች ላለው ጥረት ዓለም አቀፍ እውቅና የተሰጠበት እና የሀገሪቱን የአረንጓዴ ዲፕሎማሲ ውጤት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ለጎረቤት ሀገራት ችግኞችን በመለገስ የአካባቢ ጥበቃ የጋራ አጀንዳ መሆኑን በተግባር አሳይታለች።ይህም አረንጓዴ ዲፕሎማሲ በሀገራት መካከል በጎ ግንኙነትንና አዎንታዊ የቀጣናዊ ትስስር ድልድይን እየገነባ ይገኛል። የድንበር ተሻጋሪ የወንዝ ተፋሰሶችን በመንከባከብ፣ የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለጎረቤት ሀገራት በማዳረስ እና በጋራ ድንበሮች አካባቢ የደን ሽፋንን በማሳደግ ረገድ እያከናወነችው ያለው ሥራ አህጉራዊ ሰላምና ትብብርን የሚያጎለብት አዲስ የዲፕሎማሲ መንገድ ከፍቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ በአፍሪካ ህብረት እና በተለያዩ ዓለም አቀፍ መድረኮች የአህጉሪቱን ፍላጎትና ጥቅም ለማስከበር ግንባር ቀደም ተሟጋች ሆናለች። ለአየር ንብረት ለውጥ አነስተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ነገር ግን ለጉዳቱ በከፍተኛ ሁኔታ የተጋለጡ የአፍሪካ ሀገራት ፍትሃዊ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንዲያገኙ ድምፅ በመሆን አህጉራዊ መሪነቷን አስመስክራለች። ይህም አፍሪካውያን በራሳቸው ሀገር በቀል መፍትሔዎች የአየር ንብረት ጥበቃን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ማረጋገጫ ሆኗል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና አምባሳደሮች የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት እንቅስቃሴ ለአካባቢ ጥበቃ አርአያ የሚሆን ዓለም አቀፍ ሞዴል ሲሉ አድንቀውታል። ኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይልን ከመጠቀም፣የካርቦን ልቀትን ከመቀነስ እና ከኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች መስፋፋት ጋር አጣጥማ የምታካሂደው እንቅስቃሴ በዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ጉባኤዎች ላይ እውቅና እንድታገኝ አስችሏታል።
ረብጣ ገንዘብ ከወጣባቸው ዝውውሮች እስከ አነጋጋሪ የህግ ለውጦች ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲሱ የውድድር ዓመት ምን ይዞ መጣ?
Aug 21, 2026 480
በሙሴ መለሰ የዓለም እግር ኳስ አፍቃሪያን በጉጉት የሚጠብቀው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ዛሬ በይፋ ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር ዘመን በሰኔ እና ሐምሌ ወራት የተካሄደውን የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ ተከትሎ፣ ለተጫዋቾች በቂ የእረፍት ጊዜ ለመስጠት ሲባል ከተለመደው አንድ ሳምንት ዘግይቶ እንዲጀምር ተደርጓል። የመክፈቻው ጨዋታ በኢምሬትስ ስታዲየም የባለፈው የውድድር ዘመን ሻምፒዮን አርሰናል እና ከ25 ዓመታት በኋላ ወደ ሊጉ በተመለሰው ኮቨንትሪ ሲቲ መካከል ምሽት አራት ሰዓት ላይ በኤምሬትስ ስታዲየም ይካሄዳል። ይህ አዲስ የውድድር ዘመን ከመጀመሩ በፊት በክረምቱ የተጫዋቾች ዝውውር መስኮት ላይ የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች ከፍተኛ ተሳትፎ አድርገዋል። እስካሁን ባለው መረጃ መሠረት፣ የሊጉ ክለቦች ለተጫዋቾች ዝውውር ብቻ ከ2.14 ቢሊዮን ፓውንድ በላይ ወጪ አድርገዋል። ይህ የወጪ መጠን የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ከሌሎች የአውሮፓ አራት ታላላቅ ሊጎች (ስፔን፣ ጣልያን ጀርመንና ፈረንሳይ) በጥምረት ካወጡት የገንዘብ መጠን በላይ ሆኗል። ሞርጋን ሮጀርስ ከአስቶን ቪላ ወደ ቼልሲ በ117 ሚሊዮን ፓውንድ በመዘዋወር የክረምቱ ውዱ ተጫዋች መሆን ችሏል። ኤሊዮት አንደርሰን ከኖቲንግሃም ፎረስት ወደ ማንቸስተር ሲቲ በ116 ሚሊዮን ፓውንድ አምርቷል። በተጨማሪም ሳንድሮ ቶናሊ ከኒውካስል ወደ ቶተንሃም በ100 ሚሊዮን ፓውንድ፣ እንዲሁም ብሩኖ ጉማሬሽ ከኒውካስል ዩናይትድ ወደ አርሰናል በ75 ሚሊዮን ፓውንድ መዘዋወራቸው የክረምቱን የዝውውር ገበያ ከሚጠቀሱ ዝውውሮች መካከል ዋና ዋናዎቹ ናቸው። ከዝውውር ወጪው ባሻገር፣ የዘንድሮው የውድድር ዘመን በአዳዲስ አሰልጣኞች የታጀበ ሆኗል። በሊጉ ታሪክ ከፍተኛው በተባለ ደረጃ ዘጠኝ ክለቦች ውድድሩን በአዲስ አሰልጣኞች ይጀምራሉ። ፔፕ ጋርዲዮላ ማንቸስተር ሲቲን በገዛ ፈቃዱ መልቀቁን ተከትሎ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ አሁን ላይ በሊጉ ረጅም ጊዜ (ሰባት ዓመታት) የቆየው አሰልጣኝ ሆኗል። የቼልሲው ዣቢ አሎንሶ፣ የማንቸስተር ሲቲው ኤንዞ ማሬስካ እና የሊቨርፑሉ አንዶኒ ኢራኦላ ከአዳዲሶቹ አሰልጣኞች መካከል ይጠቀሳሉ። ማይክል ካሪክ በማንቸስተር ዩናይትድ እንዲሁም ሮቤርቶ ዴ ዜርቢ በቶተንሃም ሆትስፐርስ የመጀመሪያ ሙሉ የውድድር ዓመታቸውን ይጀምራሉ። የሊጉ የተሳታፊዎች ስብጥርን በተመለከተ፣ ኮቨንትሪ ሲቲ ከ25 ዓመታት በኋላ ከሃል ሲቲ እና ኢፕስዊች ታውን ጋር በመሆን ከታችኛው ሊግ አድገው ሊጉን ተቀላቅለዋል። በተቃራኒው ዌስትሃም ዩናይትድ፣ በርንሌይ እና ዎልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ባለፈው የውድድር ዘመን መውረዳቸው የሚታወስ ነው። በተጨማሪም የእንግሊዝ ክለቦች ባለፈው ዓመት በአውሮፓ ባሳዩት አስደናቂ ብቃት ምክንያት፣ በዚህ የውድድር ዘመን ክብረ ወሰን የሆነ ዘጠኝ የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በአውሮፓ ውድድሮች ላይ ይሳተፋሉ። አርሰናል፣ አስቶንቪላ፣ ሊቨርፑል፣ ማንቸስተር ሲቲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ በሻምፒዮንስ ሊግ የሚወዳደሩ ሲሆን፣ በርንማውዝ፣ ሰንደርላንድ እና ክሪስታል ፓላስ በዩሮፓ ሊግ እንዲሁም ብራይተን በኮንፈረንስ ሊግ አገራቸውን ይወክላሉ። የሊጉ አስተዳደር የክለቦችን የፋይናንስ ወጪ የሚቆጣጠር አዲስ የወጪ ገደብ (Squad Cost Ratio) መመሪያን ተግባራዊ አድርጓል። በዚህም መሠረት ክለቦች ለተጫዋቾች ደሞዝ እና ለዝውውር የሚያወጡት ጠቅላላ ወጪ ከገቢያቸው 85 በመቶ እንዳይበልጥ ተወስኗል። ህጉን የሚጥሱ ክለቦችም የነጥብ ቅነሳ ቅጣት ይገጥማቸዋል። የጨዋታ ፍጥነትን ለመጨመርና ሰዓት ማባከንን ለመግታት በርካታ አዳዲስ የዳኝነት ህጎች በይፋ ስራ ላይ ይውላሉ። በእጅ ውርወራ (Throw-in) እና በመልስ ምት (Goal-kick) ላይ ሰዓት ለሚያባክኑ ተጫዋቾች ዳኛው አምስት ሴኮንድ የሚቆጥር ሲሆን፣ ጊዜ ካለፈ እጅ ውርወራው ለተቃራኒ ቡድን ይሰጣል፤ የመልስ ምት ላይ ከሆነ ደግሞ የተቃራኒ ቡድን የማዕዘን ምት ያገኛል። ሌላው ሰዓት ማባከንን ለመቆጣጠር የወጣው ህግ ተጫዋቾች ታክመው ከወጡ በኋላ ወደ ሜዳ ለመመለስ ቢያንስ አንድ ደቂቃ ውጭ እንዲጠብቁ የሚያስገድደው ደንብ ነው። በተጨማሪም ተጫዋቾች በሚቀየሩበት ወቅት ከሜዳ ለመውጣት የ10 ሴከንድ ገደብ የተጣለባቸው ሲሆን፣ ይሁንና ጊዜው ካለፈ ተቀያሪው መግባት የሚችለው ጨዋታው በሚቀጥለው ጊዜ ሲቆም ብቻ ይሆናል። በዚህ የውድድር ዘመን የቪዲዮ ረዳት ዳኛ (VAR) ውሳኔዎችን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ ትልቅ ማሻሻያ ተደርጓል። አንድ ተጫዋች በሁለተኛ ቢጫ ካርድ ከሜዳ ሲሰናበት አጠራጣሪ ከሆነ ቫር ጣልቃ የመግባት ስልጣን ተሰጥቶታል፤ እንዲሁም በጨዋታ ወቅት በቫር እና በሜዳ ላይ ዳኛው መካከል የሚደረጉ የድምፅ ውይይቶች በሊጉ የጨዋታ ማዕከል በኩል ለደጋፊዎች በቀጥታ ይፋ ይደረጋሉ። በአጠቃላይ፣ የዘንድሮው የ2026/27 የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመን ከአዳዲስ የህግ ለውጦች፣ ከከፍተኛ የዝውውር ወጪዎች እና አዳዲስ የአሰልጣኞች ሹመት ጋር ተያይዞ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረትን ስቧል። አርሰናል የዋንጫ ክብሩን ለማስጠበቅ፣ ማንቸስተር ሲቲ ያለ ፔፕ ጋርዲዮላ አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር፣ እንዲሁም አዳዲስ አሰልጣኞችና ክለቦች ህልማቸውን ለማሳካት የሚያደርጉት ፍልሚያ የእግር ኳስ አፍቃሪያን እስከ ግንቦት ወር መጨረሻ ድረስ የሚዘልቅ አስደሳች እና አጓጊ የእግር ኳስ ጊዜን እንደሚያሳልፉ አያጠራጥርም።
ቡሄ እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ምስረታ ታሪካዊ ቁርኝት
Aug 19, 2026 680
በሙሴ መለሰ ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን የቡሄ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ባለበት በዚህ ዕለት፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አጀማመሩንና ምስረታውን ከዚህ በዓል ጋር ያለውን የጠበቀ ትስስር ወደ ኋላ መለስ ብሎ የሚታወስበት ነው። የክለቡ ምስረታና የቡሄ በዓል (የሆያ ሆዬ ጨዋታ) ቀጥተኛና የማይነጠል ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን፣ ክለቡ በመስረታው ወቅት የነበረበትን የፋይናንስ እጥረት ቀርፎ የመጀመሪያውን ማሊያ ለመግዛት የበቃው በዚህ ዕለት በተሰበሰበ የሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ነበር። የቅዱስ ጊዮርጊስ እግር ኳስ ቡድን መጀመሪያ ሲጠነሰስ በጆርጅ ዱካስና በአየለ አትናሽ አማካኝነት የነበረ ቢሆንም፣ ክለቡን በይፋ አደራጅቶ ለማቋቋም ግን የግድ የፋይናንስ አቅም ወይም ገንዘብ ያስፈልግ ነበር። ሆኖም ግን በሃገር ፍቅር ስሜት የተነሱት ዘጠኙ ወጣቶች ማለትም አየለ አትናሽ፣ ጆርጅ ዱካስ፣ ዮሐንስ ጥላሁን፣ ገብረመድህን ተፈሪ፣ ተፈራ ገብረእግዚአብሔር፣ ዓለማየሁ እጅጉ፣ መኮንን ደምሴ፣ አስፋው ያዕቆብ እና ክልቱ አያኖ ክለቡን በሚመሰርቱበት ወቅት ቤሳ ቤስቲን እንኳ ኪሳቸው ውስጥ ስላልነበራቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ተሰብስበው በሰፊው ተወያዩ። በዚህ የውይይት ወቅት ነው ገንዘብ ለማግኘትና የክለቡን መመስረት እውን ለማድረግ የቡሄ ቀን እጅግ መልካምና ትልቅ አጋጣሚ መሆኑን የተረዱት። ዘጠኙ ወጣቶች በአንድ ድምፅ ተስማምተው በታሪካዊው የቡሄ ዕለት ማለትም ነሐሴ 13 ቀን 1927 ዓ.ም. በጋራ በመሆን ቡሄ ጨፍረው (ሆያ ሆዬ ብለው) በሚያገኙት ማናቸውም ነገር የክለቡን የመጀመሪያ ማሊያ ለመግዛት ቁርጥ የሆነ ውሳኔ ላይ ደረሱ። በዚያን ጊዜ የነበረው የባህል ልማድ አሁን ካለው የተለየ በመሆኑ፣ ቡሄ ሲጨፈር የሚሰጠው ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን ሙልሙል ዳቦ ነበር። በመሆኑም ዘጠኙ ተጫዋቾችና መስራቾች ቀደም ሲል ከሚጨፍሩበትና ለምደውት ከነበረው አካባቢ ራቅ ብለው በመንቀሳቀስ በየቤቱ በር እያንኳኩ በደመቀ ሁኔታ ጨፈሩ፤ በዚህም ጥረታቸው በርካታ ቁጥር ያለው የሙልሙል ዳቦ በአንድነት ማሰባሰብ ቻሉ ታሪካዊውን ስራ ሰሩ። ይሁን እንጂ የተሰበሰበውን ይህንን በርካታ ዳቦ ወደ ጥሬ ገንዘብ ለመቀየር አዲስ አበባ ውስጥ ወደሚገኘው ሰራተኛ ሰፈር ለሚገኙ ወዛደሮች ለመሸጥ ዳቦውን በከረጢት ይዘው ጉዟቸውን ጀመሩ። በዚህ የጉዞ መስመር ላይ ሳሉ ግን ያልተጠበቀ ፈተና ገጠማቸው፤ በመንገድ ላይ ያገኟቸው “ዱርዬዎች” ከተሰበሰበው ዳቦ ላይ የተወሰነውን ነጠቋቸው። ወጣቶቹ ተስፋ ሳይቆርጡ ጉዟቸውን በመቀጠል የተረፈውን ዳቦ ለሰራተኛ ሰፈሩ ወዛደሮች በመሸጥ ማሊያ መግዣ የሚሆን ጥሬ ገንዘብ በእጃቸው አስገቡ። ከዳቦው ሽያጭ የተገኘችው ጠቅላላ የገንዘብ መጠን በወቅቱ መገበያያ በትክክል ሁለት ጠገራ ብር ነበረች። የክለባችው የመጀመሪያ መለያ ቡናና ነጭ ነበር። ቡናና ነጭ መሊያን የገዙት ግን ፈልገው አልነበረም በቂ ገንዘብ ስላልነበራቸው በሁለት ጠገራ ብር ከፒያሳ «ግሪካዊ አውግስታስ ዱስ» ከተባለ ሱቅ በርካሽ ስላገኙት ነበር። ይህ በቡሄ ዕለት የተጀመረው ታሪካዊ የማሊያ ግዢ በኋላ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በታህሣሥ ወር 1928 ዓ.ም. በይፋ ተመሠረተ። ክለቡ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ክለብ በመሆን ታሪካዊ ማዕረግንና ቀዳሚነትን ተቀዳጀ። በ1928 ዓ.ም. በይፋ የተመሰረተው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ በታሪኩ የመጀመሪያውን የሜዳ ጨዋታ ያደረገው ከ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ነበር። በዚሁ ታሪካዊ የመጀመሪያ ጨዋታው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተጋጣሚውን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል። በዕለቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጠንካራ ተፎካካሪ ከነበረው የ"አራራት አርመን" ቡድን ጋር ለመጫወት ወደ ሜዳ ሲያመራ፣ አስቀድመው ከተመረጡትና ቡድኑን ካደራጁት ተጫዋቾች መካከል አንዱ ባልታወቀ ምክንያት ሳይመጣ ቀረ። በዚህ ድንገተኛ መቅረት ምክንያት ቡድኑ በሰው ጎደሎ ለመጫወት በተገደደበት ወሳኝ ሰዓት፣ መስራቾቹ በሜዳው አቅራቢያ መንገድ ላይ ሲጫወት ያገኙትን አንድ ታዳጊ ወጣት ተመለከቱ። ይህ ታዳጊ በወቅቱ ገና የ14 ዓመት ዕድሜ የነበረውና በኋላ ላይ የኢትዮጵያ ስፖርት ባልደረባ የሆነው ይድነቃቸው ተሰማ ነበር። ወጣቶቹም ያለ ምንም ቅድመ ዝግጅት ቡድኑን እንዲሞላ ድንገት ጋበዙት፤ እርሱም የቀረበለትን ጥሪ በደስታ ተቀብሎ በአጋጣሚ ወደ ሜዳ ገባ። ያለ ምንም ልምምድና ዝግጅት በድንገት የተሰለፈው ይድነቃቸው ተሰማ፣ በሜዳ ላይ ያሳየው አስደናቂ ችሎታና ቅልጥፍና ሁሉንም ያስገረመ ነበር። ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያውን ታሪካዊ ጨዋታ 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ሲያሸንፍ፣ ለክለቡ የመጀመሪያውን ድል ያስገኙትን ሁለቱንም ታሪካዊ የማሸነፊያ ግቦች ከመረብ ያሳረፈው ይኸው መንገድ ላይ ተገኝቶ በድንገት የተሰለፈው ታዳጊ ይድነቃቸው ነበር። ይህ ብቃት ገና በታዳጊነቱ በክለቡ ውስጥ ያለውን የማይተካ ቦታ ከማረጋገጡም በላይ፣ የቅዱስ ጊዮርጊስን የድል ጉዞ በደመቀ ሁኔታ እንዲጀመር አድርጓል። ቡሄ በዓል እና የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ያላቸው ታሪካዊ ቁርኝት የክለቡን ጥልቅ ህዝባዊና ባህላዊ መሰረት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ ህያው ምስክር ነው። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ቀዳሚ ፋና ወጊ የሆነው ይህ ታላቅ ክለብ፣ በታሪካዊቷ የነሐሴ 13 ቀን የቡሄ ዕለት የመስራቾቹ የ"ሆያ ሆዬ" ጨዋታና ከተሰበሰበው ሙልሙል ዳቦ ሽያጭ ባገኟት ሁለት ጠገራ ብር የመጀመሪያውን ቡኒና ነጭ ማሊያ መግዛቱ፣ ክለቡ ከህዝብ ማህፀን የወጣ የህዝብ ሀብት መሆኑን ያረጋግጣል። ይህ ከባህልና ከትውፊት ጋር የተቆራኘ አስደናቂ አጀማመር፣ ከጊዜ በኋላ በ1928 ዓ.ም. ለይፋዊ ምስረታው በር ከፋች ከመሆኑም በላይ፣ በታሪካዊው የመጀመሪያ ጨዋታ ላይ እንደ ይድነቃቸው ተሰማ ያሉ የአፍሪካ እግር ኳስ ታላላቅ መሪዎችና ድንቅ ተሰጥኦዎች እንዲፈጠሩ መሰረት የጣለ የኢትዮጵያ ስፖርት ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ነው።
ትንታኔዎች
የቀይ ባህር ደህንነት እና የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ ሚና
Aug 29, 2026 765
(በሙሴ መለሰ) በቀይ ባሕርና በኤደን ባሕረ-ሰላጤ ቀጣናዊ ሰላምና ፀጥታን ለማረጋገጥ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ የሚኖራት ሚና ከፍተኛ ነው። የኢትዮጵያ አብዛኛው ወጪና ገቢ ሸቀጦች በባህር በር በኩል የሚተላለፉ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር እና በኤደን ባህረ ሰላጤ የሚከሰቱ የፀጥታ መደፍረሶች ወይም የሎጂስቲክስ መስተጓጎሎች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ኢኮኖሚ ላይ የራሱን ተጽዕኖ ማሳረፉ የማይቀር ነው። በሆርሙዝ ሰርጥ የተከሰተውን የጸጥታ ቸግር ተከትሎ የተለያዩ የዓለም ሃገራት የቀይባህር መስመር ከባቤል ሜንደብ እስከ ስዊዝ ቦይ ድረስ ያለው ደህንነት አሳስቧቸዋል። ይሄንን ስጋት ለማቃለልም ሆነ የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን መነሻ በማድረግ አንዳንድ ሃገራት በቀጣናው ካሉ የባህር ተጋሪ መንግስታት ጋር በመሆን የመሰረቷቸውን የጦር ሰፈሮች ቢያጠናክሩም አሁንም ቀጣናው በባህር ላይ ውንብድና፣ በህገ-ወጥ ንግድና የሰዎች ዝውውር ወንጀል ለስጋት የተጋለጠ ሆኖ ይገኛል። የአፍሪካ ቀንድ ሰላም ከቀይ ባህር ደህንነት ጋር በቀጥታ የተሳሰረ መሆኑን በጽኑ የምታምነው ኢትዮጵያ፣ ድንበር ተሻጋሪ የፀጥታ ስጋቶችን ለመከላከል በሚደረጉ የባለብዙ ወገን ውይይቶች ላይ በመሳተፍ የበኩሏን አስተዋጽኦ ታበረክታለች። በተለይም ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውርን፣ የጦር መሳሪያ እና የአደንዛዥ ዕፅ ዝውውርን እንዲሁም የባህር ላይ ወንጀሎችን በጋራ ለመመከት የቀጣናው ሀገራት የተቀናጀ ምላሽ እንዲኖራቸው ድጋፍ ታደርጋለች። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር ያላት መልክዐ ምድራዊ ትስስር እና የፀጥታ አጋርነት በቀይ ባህር ቀጣና መረጋጋት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ አለው። በቀጣናው የሚከሰቱ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶች እና የጸጥታ ችግሮች በቀጥታ በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ በመሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ ሰላምን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የትብብር አማራጭን ተከትላ እየሰራች ትገኛለች። የአፍሪካ ቀንድና የቀይባሕር ደኅንነት ሊለያዩ የማይችሉ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው። ኢትዮጵያ በሕዝብ ብዛቷ፣ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴዋና በጂኦ-ፖለቲካዊ አቀማመጧ በቀጣናው ትልቅ ድርሻ ያላት በመሆኑ፣ በሚደረጉ የማሪታይምና የደኅንነት ውይይቶች ላይ የምታደርገው ንቁ ተሳትፎ ለቀጣናው ዘላቂ ሰላም መረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን ሰፊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ተጽዕኖ በመጠቀም፣ ስትራቴጂያዊ የንግድ መስመሮችን ከስጋት ነፃ ለማድረግ በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑ በቅርቡ በናይሮቢ በተካሄደው ዓለም አቀፍ መድረክ በግልጽ ታይቷል። በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው አምስተኛው የቀይ ባህርና የኤደን ባህረ ሰላጤ የባህር ላይ ህግ ማስከበር ውይይት (Maritime Law Enforcement Dialogue) ላይ፣ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን አገራዊና ቀጣናዊ ጥቅሞችን የሚያስጠብቅ ተሳትፎ አድርጓል። ይህም ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና የኢኮኖሚ ትስስር ላይ ያላትን ሚና እና ባለቤትነት አሳይቷል። ለኢትዮጵያ የባህር በር ደህንነት የህልውና ጉዳይ ነው። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለሥልጣን ተወካይ ካፒቴን ክብሩ መስፍን እንደገለጹት፣ የባሕር ላይ ሰላም መደፍረስ በቀጥታ የአገሪቱን ብሔራዊ ኢኮኖሚ ይነካል። አብዛኛው የሀገሪቱ ወጪና ገቢ ንግድ በባህር ላይ የሚካሄድ በመሆኑ፣ በቀይ ባህር ላይ የሚከሰቱ የባሕር ላይ ውንብድናዎችና ህገ-ወጥ እንቅስቃሴዎች የንግድ ፍሰቱን እንዳያስተጓጉሉ በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል። ካፒቴን ክብሩ አክለውም፣ የመርከቦች መድን ዋስትና መናርና የሸቀጦች መዘግየት የሀገሪቱን የንግድ ተወዳዳሪነት እንዳይፈታተኑ፣ ጠንካራና የተቀናጀ የባህር ላይ ቁጥጥር ሥርዓት መዘርጋት አማራጭ የሌለው ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። ይህን ዓለም አቀፋዊ ስጋትን ለመመከት ኢትዮጵያ የጋራ መፍትሔዎችን በማቅረብ ረገድ ግንባር ቀደም ናት። በተለይም ከጎረቤት አገራት ጋር በመቀናጀት "ብሔራዊ የማሪታይም መረጃ ማዕከል" (National Maritime Information Centre) ለመመስረት ያቀደችው ስትራቴጂ፣ ሀገሪቱ ለቀጣናው መረጋጋት ያላትን የረጅም ጊዜ ራዕይ የሚያሳይ ነው። መረጃን በጋራ መለዋወጥና የተቀናጀ የሕግ ማስከበር እርምጃ መውሰድ ለዚህ ስኬት ዋነኛው መሳሪያ እንደሆነ ኢትዮጵያ በጽኑ ታምናለች። በቀይ ባህርና በኤደን ባህረ-ሰላጤ የሚስተዋሉ እንደ ሕገ-ወጥ የሰዎችና የዕፅ ዝውውር እንዲሁም ሕገ-ወጥ አሳ ማጥመድ ያሉ ስጋቶች ድንበር ተሻጋሪ በመሆናቸው፣ እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ቀጣናዊ ኃይሎች ተሳትፎ የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡን ትኩረት ስቧል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC) የቀጣናው አስተባባሪ ሞስታፋ ኤልባና እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላት የፖለቲካና የኢኮኖሚ አቅም ዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች አስተማማኝና የተረጋጉ እንዲሆኑ ትልቅ አስተዋጽኦ አለው። በቀይ ባህር ቀጣና ያላትን ስትራቴጂካዊ ጥቅም ለማስጠበቅና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ዲፕሎማሲያዊና ተግባራዊ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ ቀጥሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅና ወንጀል ጉዳዮች ቢሮ (UNODC)፣ ኢንተርፖል እና ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት (IOM) የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋር በቅርበት በመሥራት ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና ጸጥታ ላይ ያላትን የመሪነት ሚና በታሪካዊ ኃላፊነትና በሕግ አግባብ እያስጠበቀች ትገኛለች። ኢትዮጵያ የባህር ኃሃይልን ጨምሮ በጥብቅ ዲሲፕሊኑ እና በመፈጸም አቅሙ የሚታወቅ ጠንካራ የመከላከያ ሰራዊት ገንብታለች። ይሄ ሰራዊት በተለያየ ጊዜ ችግር ላጋጠማቸው ሃገራት ባሳየው የሰላም ማስከበር ሚናው በውጤታማነቱ የተመሰከረለትም ነው። የቀጣናውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚያስችል ጠንካራ ሃይል አስፈላጊ ስለሆነም በቅርብም በሩቅም ያሉ ሃገራት የኢትዮጵያን የባህር ላይ ህልውና በበጎ ይመለከቱታል። ለዚህም በቅርቡ በአንድ የሃገር ውስጥ ሚዲያ በሰጡት ቃለ-መጠይቅ የባብኤል ሜንደብን እና የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ ሃገራቸው በቂ አቅም ስለሌላት የሌሎች እገዛ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት የጅቡቲ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ፋይናስ ሚኒስትር ኢሊያስ ሙሳ ዳዋሌህ ገለጻ አንዱ ማሳያ ነው። እነዚህ ሁሉ ጉዳዮች አመላካች የሚሆኑት ያለ አግባብ ከባህሩ የተገፋችውና መብቷን የምትጠይቀው ኢትዮጵያ ያላት ዘርፈ ብዙ ዓቅም ለቀጣናውም ለራሷም ሰላምና ደህንነት መረጋገጥ ወሳኝ ሚና ያላት መሆኑን ነው።
የኢትዮጵያ አዲሱ የቱሪዝም ከፍታ!
Aug 29, 2026 226
የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ ከሀገሪቷ ልዩ ፀጋዎች መካከል በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል። ሀገሪቱ ያሏት ጉምቱ ታሪክ፣ ብዝሃ ባህል እና ልዩ የቱሪዝም መዳረሻዎች ለአፍሪካ ስልጣኔ ያላትን ታላቅ ድርሻ የሚያመላክቱ ናቸው። ከላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት አንስቶ እስከ አክሱም ሀውልትና የጁገል ግንብ ድረስ ያሉት ቅርሶች የኢትዮጵያን የታሪክ ጥልቀት እና የባህል ትሩፋቶች በግልጽ ያሳያሉ። እነዚህ ታሪካዊ ሀብቶች በአሁኑ ወቅትም የውጭ ጎብኚዎች፣ ተመራማሪዎች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ቀልብ መሳባቸውን ቀጥለዋል። ከታሪክ ሀብቶቿ ባለፈም ማራኪው የመልክዓ ምድር አቀማመጥ፣ ብቅ ያሉ የዱር እንስሳቶች እና የዜጎች እንግዳ ተቀባይነት የአኗኗር ዘይቤ ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ። መንግስት ቱሪዝምን እንደ አንድ ዋነኛ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመውሰድ ስትራቴጂካዊ የልማት ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል። በተለይም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተቀረጹት የ"ገበታ ለሸገር"፣ "ገበታ ለሀገር" እና "ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክቶች የሀገሪቱን እምቅ የቱሪዝም ሀብት ከማውጣት ባለፈ የገቢ መጠንን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ለውጥ እያስመዘገቡ ነው። ከዚህም መካከል በሶማሌ ክልል በደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያ በዋቢ ሸበሌ ወንዝ ዳርቻ ተገንብቶ በቅርቡ የተመረቀው እና የ"ገበታ ለትውልድ" አካል የሆነው የሸበሌ ሪዞርት አንዱ ማሳያ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምርቃቱ ወቅት እንደገለጹት፣ ሪዞርቱ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቱሪስት መዳረሻ ለማድረግ የገባነውን ቃል በተግባር ያረጋገጠ የምስራቁ የሀገራችን ክፍል ትልቅ ማሳያ ሥራ ነው። ይህ ስራ በታችኛው የዋቢ ሸበሌ ተፋሰስ አካባቢ ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል የፈጠረና የክልሉን የቱሪዝም ገጽታ የቀየረ ነው። በተጨማሪም በመዲናዋ አዲስ አበባ የተገነቡት የወዳጅነት አደባባይ፣ አንድነት ፓርክ፣ ሳይንስ ሙዚየም እና አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት አዳዲስና ተመራጭ የከተማ ቱሪዝም (Urban Tourism) መዳረሻዎች ሆነዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዋና ከተማዋ የተከናወነው ሰፊው የኮሪደር ልማት ሥራ የአዲስ አበባን መልክ በአዲስ ሁኔታ በመግለጥ፣ ከተማዋን ለሰው ልጅ ምቹ፣ ውብ እና የጎብኚዎች ዓይን ይበልጥ የሚያርፍባት የቱሪስት ማዕከል አድርጓታል። ከታሪካዊ ቅርሶች ጥበቃ አንጻርም እድሳት የተደረገላቸው ብሔራዊ ቤተ መንግስት (ኢዮቤልዩ)፣ የጎንደር የአፄ ፋሲል አብያተ መንግስታት፣ የጅማ አባጅፋር ቤተመንግስት እና የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት ለዘርፉ መነቃቃት የጎላ አበርክቶ እያበረከቱ ይገኛሉ። ከዚሁ ጋር ተያይዞ፣ በቅርቡ በዩኔስኮ የዓለም ቅርስነት የተመዘገቡት የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር እና የባልካሌ ውብ ተፈጥሮአዊ ጥንታዊ ቅርሶች የኢትዮጵያን የቱሪዝም ካርታ ይበልጥ አበልጽገውታል። ይህ ዓለም አቀፋዊ እውቅና የሀገሪቱን የባህል እና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጥረት ማሳደጉ ብቻ ሳይሆን፣ ወደ እነዚህ አካባቢዎች የሚመጡ የውጭ እና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎችን ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ በማሳደግ የቱሪዝም ገቢን ለማሳደግ አስችሏል። በሌላ በኩል፣ የቱሪዝም ዘርፉን ስኬት ዘላቂ ለማድረግ የአቪዬሽን እና የእንግዳ ተቀባይነት (Hospitality) አገልግሎቶች ዲጂታላይዝ መሆናቸው ጉልህ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ መዳረሻ ማብዛት፣ የኤሌክትሮኒክስ ቪዛ (e-Visa) አሰጣጥ መዘመኑ እና ወደ ተለያዩ የመዳረሻ አካባቢዎች የሚደረጉ የትራንስፖርት አማራጮች መቃናታቸው ጎብኚዎች ያለ ምንም እንግልት ሀገሪቱን እንዲጎበኙ መንገድ ከፍቷል። ይህም ሀገሪቱ በኮንፈረንስ ቱሪዝም ለአፍሪካ እና ለዓለም አቀፍ ስብሰባዎች ተፈላጊ ማዕከል እንድትሆን አስችሏታል። በተጨማሪም የዲጂታል ቱሪዝም ፕሮሞሽን እና የቅርሶች ጥበቃ ስራዎች በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደገፋቸው ለዘርፉ አዲስ ምዕራፍ አጎናጽፎታል። በማህበራዊ ሚዲያ እና በዲጂታል አማራጮች የሚሰሩ ማስተዋወቂያዎች የኢትዮጵያን ገጽታ ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ በአዲስ መልክ አስተዋውቀዋል። እነዚህ የተቀናጁ የልማት፣ የጥበቃ እና የማስተዋወቅ ስራዎች ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ብቻ ሳይሆን በመላው አህጉር ቀዳሚ የቱሪዝም መዳረሻ የመሆን ራዕይዋን በተግባር እያረጋገጡት ይገኛሉ። ይህንን የመንግስት ጥረት ተከትሎም ከባለሀብቶች እንዲሁም ከዓለም አቀፍ የዘርፉ ተዋንያን የሚመጣው ተሳትፎና የኢንቨስትመንት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መጥቷል። በአጠቃላይ እነዚህ ዘመናዊ መሠረተ ልማቶች፣ የታሪካዊ ቅርሶች ጥገና እና የተፈጥሮ መስህቦች ጥምረት የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ ለኢኮኖሚ እድገት እና ለዘላቂ ልማት ያለውን ድርሻ ወደ ላቀ ደረጃ እያሳደጉት ይገኛል።
የኢትዮጵያውያን የወል እውነት- ሀገራዊ ምክክር
Aug 28, 2026 565
በሙሴ መለስ ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የጋራ መኖሪያ እና የብዝሃነት ውበት ደምቆ የሚታይባት ሀገር ናት ። ዛሬ ላይ ለመድረስም በርካታ ውጣ ውረዶችን፣ እና የታሪክ ምዕራፎችን ተሻግራለች። በነዚህ ምዕራፎች ውስጥም በአብሮነትና በጋራ ሃገራዊ እሳቤ ከተገነቡት የጋራ ማንነቶች ባልተናነሰ መልኩ ያጋጠሙ የታሪክ ስብራቶች የልዩነት እና ያለመግባባት መንስኤ የሚሆኑበትን አጋጣሚም አስተናግዳለች። ልዩነቶችን በጉልበት ወይም በኃይል ሳይሆን፣ በጠረጴዛ ዙሪያ በመነጋገር እና ከነጣይ ትርክት ይልቅ ወደ ሃገራዊ መግባባትና የጋራ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ብሔራዊ መግባባትን ለማምጣትም ሃገራዊ ምክክሩ የራሱን ቁልፍ ሚና በመወጣት በሃገራችን ታሪክ አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑ ይታወቃል። ከአራት ዓመታት በፊት የተቋቋመው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፣ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ሀገር አቀፍ ደረጃ ሰፊ ህዝባዊ ውይይቶችን በማድረግ የህብረተሰቡን አጀንዳዎች በባለቤትነት የማሰባሰብ ሂደቱን በስኬት አከናውኗል። የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ሲቪክ ማህበራት፣ ምሁራን፣ ዳያስፖራዎችና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች በአንድ መድረክ የተሳተፉበት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ለ46 ቀናት ተካሄዶ በስኬት መጠናቀቁ ተበስሯል። ይህ ጉባኤ ዜጎች ሃሳባቸውን በነፃነት የገለጹበት፣ የጋራ መግባባት ላይ የደረሱበት በሀገሪቱ የፖለቲካ ታሪክ ውስጥም የጠመንጃ የበላይነትን በማስቀረት፣ የሀሳብ የበላይነትና የሰላማዊ የውይይት ባህልን ለማስፈን ምቹ ምህዳር የፈጠረ አካታች አካሄድ ነው። ከጉባኤው የተገኙ ምክረ-ሐሳቦችና የተገኙት ልምዶች ወደ ተግባር እየተሸጋገሩ፣ በየደረጃው በሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች መካከል ውይይቱ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን አዲስ ምዕራፍ የሚከፍትም ነው። የጋራ ትርክት ህዝቦች በታሪካቸው፣ በአሁኑ ሁኔታቸው እና በወደፊት ዕጣ ፈንታቸው ላይ ያላቸው የጋራ መረዳትና ስምምነት ሲሆን ይህም አብሮነትን ለማጎልበት ጠንካራ መሰረት ይጥላል። ለዘመናት በጦርነት፣ በኃይልና በፖለቲካ ሽኩቻ ሲንከባለሉ የቆዩ የትርክት ስብራቶችም ከጠመንጃ ይልቅ በሰላማዊ መንገድ በጠረጴዛ ዙሪያ ክርክር ለመፍታት ስለመቻሉም ትልቅ ማሳያ ነው። በምክክሩ ላይ በመላው ሃገሪቱ አሉን የሚሏቸውን ጥያቄዎችና ቅሬታዎች በኃይል በጦር መሳሪያ ለመፍታት ነፍጥ አንግበው ሲታገሉ የነበሩ አካላት ሁሉ እንዲሳተፉ መደረጉም የሒደቱን ስኬታማነት ለዓለም ማህበረሰብ ያሳየ ነው። ከተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች፣የፖለቲካ አመለካከቶችና የኅብረተሰብ ክፍሎች የተወጣጡ አራት ሺህ ተመካካሪዎች የየራሳቸውን የተናጠል ፍላጎት ብቻ ከማንጸባረቅ ተቆጥበው በተለዩ ስምንቱ አበይት አጀንዳዎች ላይ በጋራ መስማማታቸውም የወል ትርክት ግንባታን የውጤታማነት ጉዞ ስኬት በተግባር የገለጠ ነው። ይህ ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሳይሆን ለሀገር ህልውና እና ለጋራ ዕድገት ቅድሚያ የመስጠት ትልቅ የፖለቲካ ብስለትም ነው። ይህ ሂደት እያንዳንዱ ዜጋ በሀገሩ ላይ ሙሉ ባለቤትነትና ደህንነት እንዲሰማው የሚያደርግ ሲሆን የጋራ አገርና የጋራ ዕድል አለን የሚለውን እሳቤ በማጉላትም የወል ትርክትን በጽኑ መሠረት ላይ ይገነባል። ምክክሩ በጥቂት የፖለቲካ ልሂቃን (Elites) መካከል ብቻ የተደረገ ውይይት ሳይሆን እስከ ወረዳ ድረስ ያሉትን የታችኛውን የህብረተሰብ ክፍሎች፣ አርሶ አደሮችን፣ አርብቶ አደሮችንና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ያሳተፈ መሆኑም ትልቅ ትርጉም አለው። ከሕዝብ ቀጥተኛ ተሳትፎ የፈለቁት ምክረ ሀሳቦች ለሀገራዊ ትርክት መጠንከር ወሳኝ ሚና ከመጫወት ባለፈ ሂደቱ በህዝቡ ዘንድ ሙሉ ተቀባይነት ያለው እንዲሆን ያደርገዋል። ምክክሩ ያረጋገጠው ትልቁ እውነት የኢትዮጵያውያን ዕጣ ፈንታ የተሳሰረ መሆኑንና የወል ትርክት ግንባታ የሀገር ህልውና ዋስትናነቱን ነው። ልዩነቶችን ውበት፣ ውይይትን ደግሞ መሳሪያ በማድረግ የተጀመረው ይህ ጉዞ ኢትዮጵያ በቀደመ ታሪኳ የገጠሟትን የታሪክ ስብራቶች በመጠገን ወደ ዘላቂ ብልጽግና፣ ዲሞክራሲና እውነተኛ አንድነት እንድትሸጋገር ያስችላታል።
የኢትዮጵያ የከፍታ ጉዞ ማሳያ የአፍሪካውያን ኩራት - የኢትዮጵያ አየር መንገድ
Aug 27, 2026 354
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከንግድ ተቋምነት ባለፈ የአፍሪካውያንን አንድነት፣ የነፃነት ታሪክና የጋራ ብልጽግና ስትራቴጂን በሰማይ ላይ የገነባ እውነተኛ የፓን አፍሪካዊነት ተምሳሌት ነው። አህጉሪቱ ገና ከቅኝ አገዛዝ ቀንበር ባልተላቀቀችበትና የእርስ በእርስ ትስስር በሌለበት እ.አ.አ ከ1945 ጀምሮ የአፍሪካን ሕዝቦችና መሪዎች በማገናኘት የታሪክ ህያው ምስክር ሆኖ አገልግሏል።ይህ አየር መንገድ፣ የአፍሪካ አዲስ መንፈስ የሚለውን መፈክሩን በተግባር ያረጋገጠ ብሔራዊና አህጉራዊ ኩራትም ነው። አየር መንገዱ ለአፍሪካዊያን የጋራ ዕድገት የሚሠራ መሆኑን የሚያረጋግጠው ዋነኛው ተግባሩ፣ የገንዘብና የቴክኒክ አቅም አንሷቸው የፈረሱ ወይም የተቸገሩ የሌሎች አፍሪካ ሀገራትን ብሔራዊ አየር መንገዶች በጋራ ባለቤትነት መልሶ የማቋቋምና የማጠናከር ዘላቂ ስትራቴጂው ነው። በዚህም በዓለም አቀፍ ደረጃ ትርፋማና ግዙፍ ተቋም ከመሆን ባለፈ የአህጉሪቱን የአቪዬሽን ዘርፍ በጋራ ለማሳደግ የአፍሪካ አየር መንገዶችን የማቋቋምና የመደገፍ” ስትራቴጂካዊ ሥራዎችን በስፋት እያከናወነ ይገኛል። ተቋሙ ከአፍሪካ አየር መንገዶች ማህበር (AFRAA) እና ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መንግስታት ጋር በመተባበር በአህጉሪቱ ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን አስመዝግቧል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ እና የማኔጅመንት (የአመራር) አገልግሎት በመስጠት በርካታ አየር መንገዶችን በማቋቋምና በማጠናከር ቀዳሚውን ሚና እየተጫወተም ይገኛል። በዚህም በምዕራብ አፍሪካ ቶጎ ላይ መቀመጫውን ያደረገው አስካይ (ASKY) አየር መንገድ፣ የማላዊ አየር መንገድ፣ የዛምቢያ አየር መንገድ እና የኮንጎ አየር መንገድ የጊኒ አየር መንገድ እና ሌሎችም የአቪዬሽን ኢንቨስትመንቶች ላይ በሚያደርገው ተሳትፎ ጠንካራ ክንድነቱን አስመስክሯል። አየር መንገዱ አብዛኛውን የኩባንያዎቹን የባለቤትነት ድርሻና ትርፍ ለባለቤት ሀገራቱ መንግሥታት በመተው፣ የአመራር፣ የስልጠናና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ የአፍሪካ አቪዬሽን በጋራ እንዲያድግ አድርጓል። በአቪዬሽን እሴት ሰንሰለት (Aviation Value Chain) ውስጥ ያለውን መዋቅራዊ የበላይነት በመጠቀምም ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች የተቀናጀ የቴክኒክና የስልጠና ድጋፍ ይሰጣል። ተቋሙ በእነዚህ አየር መንገዶች ውስጥ ስትራቴጂካዊ የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ፣ አብዛኛውን የኩባንያዎቹን የባለቤትነት መብትና የንግድ ትርፍ ለባለቤት ሀገራቱ መንግሥታት በመተው፣ ሙሉ የኦፕሬሽንና የማኔጅመንት ኃላፊነቱን በመውሰድ አፍሪካውያን ራሳቸውን እንዲችሉ አድርጓል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአፍሪካ አየር መንገዶችን የማቋቋምና የማጠናከር ስራ ሙሉ በሙሉ በፓን አፍሪካዊነት እና በእውነተኛ አፍሪካዊ የትብብር መንፈስ ላይ የተመሠረተ ታላቅ አህጉራዊ ስራ ነው። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚከተለው ሁለገብ ስትራቴጂ ግቡ የገበያ የበላይነትን መቆጣጠር ሳይሆን፣ አቪዬሽን ለሌላቸው ወይም አየር መንገዶቻቸው ለፈረሱባቸው አፍሪካውያን ወንድም ሀገራት የቴክኒክና የአመራር አቅምን ማካፈልም ነው። የአፍሪካ አየር መንገዶችን በጋራ ባለቤትነት ሲያቋቁም የኢኮኖሚ ጥቅሙን ብቻ አስልቶ ሳይሆን፣ በአፍሪካ የነፃ ንግድ ቀጣና ስምምነት መሠረት የአህጉሪቱን የሰዎችና የዕቃዎች ዝውውርን በማቀላጠፍ የጋራ አፍሪካዊ ብልጽግናን ለማምጣት በማለም ነው። ይህ አካሄድ አህጉሪቱ ከውጭ አየር መንገዶች ጥገኝነት እንድትላቀቅ የሚያደርግ እውነተኛ የፓን አፍሪካዊነት መግለጫ ነው። የራሱን የአብራሪዎች ፣ የኢንጂነሮች እና የበረራ አስተናጋጆችን የሚያሰለጥንበትን ዘመናዊ የአቪዬሽን አካዳሚ በመገንባትም ለአቪዬሽን ዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል በማፍራት ረገድ ቁልፍ ሚናውን እየተጫወተም ይገኛል። የስልጠና እና የጥገና አቅሙ ከፍተኛ እንደመሆኑም ለተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት የአቪዬሽን ባለሙያዎች ፣ እንዲሁም ከአህጉሪቱ ውጭ ላሉ አየር መንገዶች የስልጠና ፣የጥገና እና የቴክኒክ አገልግሎት በመስጠት የአህጉሪቱ የአቪዬሽን የጀርባ አጥንት መሆኑን አስመስክሯል። ይህ አህጉራዊ ትስስር ሀገራት የየራሳቸውን የአቪዬሽን ዘርፍ እንዲያጠናክሩና በንግድ፣ በቱሪዝም እና በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ የአፍሪካ ህብረት የአጀንዳ 2063 ራዕይ እንዲሳካ የበኩሉን ሚና ይጫወታል። በየዓመቱ የተለያዩ ዓለም አቀፍ ሽልማቶችን የሚያገኘው አየር መንገዱ እንደ ኤይር ባስ ኤ 350-1000 ያሉ ዘመኑን የዋጁ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት በአፍሪካ የመጀመሪያ በመሆን በብቸኝነት የሚያበር ሲሆን በአፍሪካ ትልቁን የአውሮፕላን ጥገና ማዕከል እና ዘመናዊ የካርጎ (የጭነት) ተቋም በመገንባትም አገልግሎቱን አዘምኗል:: በመላው ዓለም 26 የሚሆኑ ታላላቅ አየር መንገዶች ያሉበት የስታር አሊያንስ አባል በመሆን ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ግዙፉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በየዓመቱ ለሀገራችን የሚያስገኘው ገቢም ከዋነኛዎቹ የኢኮኖሚ አውታሮች ተርታ ቀዳሚው ያደርገዋል። ዓለምን ያስጨነቀው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በተከሰተበትና ታላላቅ ዓየር መንገዶች በኪሳራ ስራ ባቆሙበት ወቅት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለው ቁርጠኝነትና ጠንካራ አመራር አማካኝነት በካርጎ/በጭነት አገልግሎት ለአፍሪካዊያንና ሌሎች የዓለም ሃገራት መድሃኒቶችንና የህክምና መገልገያዎችን ጨምሮ የተለያዩ ጭነቶችን በማጓጓዝ አለኝታነቱንም ትርፋማነቱንም አረጋግጧል። ለአፍሪካውያን የሚሰራ እውነተኛ አፍሪካዊ ተቋም መሆኑን በተግባር ያረጋገጠው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ዛሬም እንደ ትላንቱ የአህጉሪቱ የልማትና የአንድነት ድልድይ ሆኖ ቀጥሏል። አየር መንገዱ አሁንም የአፍሪካ አዲስ መንፈስ ሆኖ አህጉሪቱን ወደ ላቀ የብልጽግና እና የጋራ የከፍታ ምህዋር መምራቱን በጽናት ይቀጥላል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 12565
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22076
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15110
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 20851
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
የኢትዮጵያ የማዕድን ምርት እመርታ
Aug 21, 2026 885
በሙሴ መለሰ የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ በአገር በቀል የኢኮኖሚና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ታግዞ፣ ባለፉት ዓመታት የታዩበትን የአሰራርና መዋቅራዊ ችግሮች በመቅረፍ ከፍተኛ የመነቃቃት ምዕራፍ ላይ ይገኛል። ዘርፉ በ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት ቁልፍ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት እንደገለጹት፣ ማዕድን በብዝኃ ዘርፍ የልማት ምልከታችን ውስጥ እና በሀገሪቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስት የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ቁልፍ ዘርፍ ሆኖ ይቀጥላል። ባለፉት ሶስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፉ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) ያበረከተው አስተዋጽኦ ከ0 ነጥብ 8 በመቶ በታች የነበረ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት ግን መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረት ከፍተኛ መዋቅራዊ ሽግግር እያመጣ ይገኛል። በ2018 በጀት ዓመት ከዘርፉ 5 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ተችሏል። ይህም ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ92 በመቶ የገቢ ዕድገትና የ27 በመቶ የምርት መጠን ብልጫ ያሳየ ሲሆን፣ ምርቶቹም በዋናነት ወደ ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ አሜሪካ፣ ጀርመን እና ቻይና ተልከዋል። በወጪ ንግድ እድገት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ያለው የወርቅ ምርት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስምንት ወራት 22 ነጥብ 5 ቶን ለውጭ ገበያ የቀረበ ሲሆን እስከ ዓመቱ ማብቂያ 32 ቶን ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። በባህላዊ መንገድ የሚመረተውን የወርቅ ምርት ለማዘመንም መንግሥት የማጣሪያና ማቀለጫ ፋብሪካዎችን በመገንባት ላይ ይገኛል። የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ከውጭ የሚገቡ ስትራቴጂክ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ሰፊ ሥራዎች እየተከናወኑ ነው። በዚህም ለድንጋይ ከሰል ግዢ ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ሙሉ በሙሉ ማስቀረት የተቻለ ሲሆን፣ የሲሚንቶ ምርትም ባለፉት ስምንት ዓመታት ከነበረበት 8 ሚሊየን ቶን አሁን ላይ በዓመት ወደ 14 ሚሊየን ቶን አድጓል። ሀገሪቱ በየዓመቱ ለማዳበሪያ ግዢ የምታወጣውን 2 ቢሊየን ዶላር ለማስቀረትም የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጀምሯል። በተጨማሪም በየዓመቱ ለብረት ምርት ግዢ የሚወጣውን 1 ቢሊየን ዶላር በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት የሚያስችል ግዙፍ ፋብሪካ የመገንባት ስምምነት ተፈጽሞ ወደ ስራ ተገብቷል። የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ በዘርፉ የተሰማሩ ፕሮጀክቶች ዋጋ 10 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ከለውጡ በፊት ከነበረውና ከ100 ሚሊየን ዶላር የማይበልጡ አነስተኛ ኢንቨስትመንቶች በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ስኬት ነው። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ በአፋር ክልል የሚገኘውን ግዙፍ የፖታሽ ክምችት ለማልማት ፈቃድ አግኝቶ ወደ ሥራ ገብቷል። በተጨማሪም ታንታለምን እሴት ጨምሮ ለመላክ ከአሜሪካ ኩባንያ ጋር ድርድር እየተደረገ ሲሆን፣ ለባትሪና ቴክኖሎጂ ወሳኝ የሆኑትን ሊቲየም፣ ኮባልትና ኒኬልን ለማምረት ዝግጅት ተጠናቋል። የኢንቨስትመንት ምህዳሩን ሳቢ ለማድረግ የማዕድን ፈቃድ አሰጣጥ አሰራር ቅድሚያ የመጣን ቅድሚያ ማስተናገድ በሚል መርህ እንዲመራ ተደርጓል። የወጪ ንግድ ኮንትራት ምዝገባና መላኪያ ፈቃዶች፣ እንዲሁም የካዳስተር ሲስተም ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ኤሌክትሮኒክስ አሰራር ተሸጋግረዋል። በ2019 በጀት ዓመት ከዘርፉ 6 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት የታቀደ ሲሆን፣ የመንግሥት ስትራቴጂካዊ እቅድ እ.አ.አ. በ2030 የማዕድን ወጪ ንግድ ገቢን ከ10 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማድረስ ኢትዮጵያን ከአፍሪካ አምስት ቀዳሚ የማዕድን አምራች ሀገራት ተርታ ማሰለፍ ነው። በዘርፉ እየተካሄደ ያለው መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ በውጭ ምርቶች ላይ ያላትን ጥገኝነት በመቀነስ ወደ ኢንዱስትሪ መሪነት የምታደርገውን ጉዞ ያፋጥነዋል። የወርቅ፣ የተፈጥሮ ጋዝ፣ የፖታሽ እና የቴክኖሎጂ ማዕድናት በሀገር ውስጥ እሴት ተጨምሮባቸው ለዓለም ገበያ መቅረባቸው ሀገሪቱ በዓለም አቀፍ የንግድ መድረክ ላይ የሚኖራትን ተጽዕኖ ፈጣሪነት እና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገት ያረጋግጣል።
የአረቡ ዓለም ከግብፅ ምን አተረፈ?
Aug 19, 2026 772
የዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲ አካሄድ በታሪካዊ እውነታዎች እና በኢኮኖሚያዊ ትስስር ላይ እየተመሠረተ በመጣበት በአሁኑ ወቅት፣ ጊዜ ያለፈባቸው የጂኦ ፖለቲካዊ የመጠላለፍ አካሄዶች ዋጋ ቢስነትና ጥቅም አልባነት በግልጽ እየታየ ይገኛል። ለብዙ አስርት ዓመታት ግብፅ የዓረብ ሊግን ለራሷ ጠባብ ፍላጎቶች እና ጂኦፖለቲካዊ አጀንዳዎች ማስፈጸሚያነት በሰፊው ስትጠቀምበት ቆይታለች። ሆኖም ይህ ጥቅምና ጉዳትን ብቻ መሰረት ያደረገ ግንኙነት አንድ መሠረታዊ ጥያቄ ያስነሳል፦ ለመሆኑ የዓረቡ ዓለም ከግብፅ በምላሹ ያገኘው ትርፍ ምንድን ነው? ለዚህ ጥያቄ አጭሩ መልስ ምንም የሚል ነው ሲል “What Has the Arab World Gained from Egypt? Why Ethiopia Belongs in the Arab League?” ፀሐፊው እና በፖለቲካና ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ በቋሚነት የሚተነትነው አስተያየት የሚሰጠው ጅብሪል ላሞ በኢዜአ እንግሊዘኛ ገጽ ባሳፈረው ሐተታ ላይ ፣ የግብጽ ፖሊሲዎች እንዲሁም ለሁለት አስርት ዓመታት የዘለቀው አምባገነናዊ አስተዳደር የጋራ ጥንካሬን ከመፍጠር ይልቅ የቀጣናውን አለመረጋጋት ማባባሳቸውን ገልጿል። እነዚህ ፖሊሲዎች፣ በምሥራቅ አፍሪካ እና በቀይ ባሕር አካባቢም ውጥረትን እያባባሱ እንደሚገኙ አመልክቷል። እነዚህ አካባቢዎች ለዓረቡ ዓለም የራቁ አይደሉም፤ ይልቁንም ለዓረቡ ዓለም ደኅንነት፣ የባሕር ንግድ፣ የኃይል አቅርቦት እንዲሁም የምግብ ዋስትና እጅግ ወሳኝ እና ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ናቸው። የግብፅ ከፋፋይ ቀጣናዊ አካሄድ ከታዩባቸው ጉልህ ማሳያዎች አንዱ በኤርትራ ጉዳይ እና በሰፊው የኢትዮጵያ ግዛት አንድነት ላይ የነበራት ታሪካዊ ጣልቃ ገብነት ነው። ኢትዮጵያን ለማዳከም እና ቀጣናዊ ተፅዕኖዋን ለመግታት በግብጽ ታስበው የተደራጁ ተገንጣይ ኃይሎችን እና ፖለቲካዊ ፕሮጀክቶችን በግልጽ ትደግፍ እንደነበረ ፀሐፊው አውስቷል። ከኢትዮጵያ የኤርትራ መገንጠል በምሥራቅ አፍሪካ ቀውስ የተሞላ ታሪክ ውስጥ አቢይ ክስተት ሲሆን፣ የውጭ ጂኦፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነቶች የሀገራትን እጣ ፈንታ እንዴት እንደሚያናጉ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የዲፕሎማሲ ታሪክ እንደሚያስረዳው፣ የቀድሞው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ እና የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ቡትሮስ ቡትሮስ-ጋሊ፣ ኢትዮጵያን ለማዳከም ታስቦ የተዘረጋውን የኤርትራን የመገንጠል ፕሮጀክት በመደገፍና በማፋጠን ረገድ ትልቅ ሚና ነበራቸው። በተጨማሪም ግብጽ በደቡባዊ የቀይ ባህር ቀጣና የምታካሂደው ቀውስ የመፍጠር እንቅስቃሴ፣ ለዓለም አቀፍ የባህር ንግድና ለቀጣናው ደህንነት ቀጥተኛ ስጋት ደቅኗል። በባብ-ኤል-ማንደብ የባሕር ወሽመጥ አካባቢ ውጥረቶችን በመቀስቀስ እና ተላላኪ ታጣቂ ቡድኖችን በማንቀሳቀስ፣ ወሳኝ የሆኑ የባህር መተላለፊያዎችን የጂኦፖለቲካዊ ግጭት መድረክ አድርጋዋለች። ይህም ለጠቅላላው የዓረብ ዓለም የኢነርጂና የምግብ አቅርቦት መሰረት የሆነውን የደህንነት መዋቅር አደጋ ላይ ጥሎታል፤ ሲሉ ጅብሪል ላሞ ያብራራሉ። ጅብሪል ላሞ በጽሑፉ ላይ እንዳሰፈረው፣ የግብፅ ግልጽ የራስ ወዳድነት እንቅስቃሴዎች ቀጣናዊ ውጥረትን የሚፈጥሩ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ መቀላቀል ግን ለዓረቡ ዓለም እጅግ ከፍተኛ ጥቅም የሚያስገኝ ለውጥ አምጪ ዕድል ይዞ ይመጣል። በመደመር ፍልስፍና አሳታፊ ማዕቀፍ ሥር፣ ኢትዮጵያ ከማግለል ፖሊሲ ይልቅ የዓረቡን ዓለም ውጤታማ በሆነ መልኩ ለማስተሳሰር የሚያስችል የላቀ የዲፕሎማሲ አቅም አላት። በዚህም የአፍሪካ ዋነኛ የዲፕሎማሲ ማዕከል እና የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ የባለብዙ ወገን ትብብሮችን በመቅረጽ ረገድ ያላትን የካበተ ልምድ ታካፍላለች። የኢትዮጵያ ወደ ዓረብ ሊግ የመቀላቀል ጥረት ጊዜያዊ የፖለቲካ ስሌት ሳይሆን፣ የተፈጥሮ የታሪክ ጥሪ ነው። ከ135 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ጥልቅ የሥልጣኔ መሠረት ያላት ይህች የቀይ ባሕር ሀገር፣ አባልነቷ በአፍሪካ እና በመካከለኛው ምሥራቅ መካከል ስትራቴጂካዊ ድልድይ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር ያላት ቁርኝት በሺዎች ለሚቆጠሩ ዓመታት በጋራ ታሪክ፣ ባህል እና የደም ትስስር ላይ የተገነባ ነው። እንደ ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ ባሉ የትምህርት ተቋማት፣ የኢትዮጵያ ጥናቶች በታሪክ ደረጃ ከመካከለኛው እና ከቅርብ ምሥራቅ ታሪክ (Near Eastern Studies) ተመድቦ መጠናቱ፤ የኢትዮጵያ ስልጣኔ ከቀጣናው ጋር ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ውህደት የሚያረጋግጥ ሕያው ማሳያ ነው። የባብ-ኤል-ማንደብ የባህር ወሽመጥ በጭራሽ መሰናክል አልነበረም፤ ይልቁንም ንግድን፣ ባህልን እና ማህበረሰቦችን በቀይ ባሕር በኩል ያገናኘ ዋንኛ መተላለፊያ ሆኖ አገልግሏል። ከንጉሥ አብረሃ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ በኢትዮጵያውያን እና በመካከለኛው ምሥራቅ ሕዝቦች መካከል የጋራ የደም ትስስር እንደነበር የሚያረጋግጡ ዘመናዊ የስነ ህይወት( ጄኔቲክስ) ጥናቶች፣ የዚህን ታሪካዊ ቁርኝት እውነተኛነት በግልጽ ያሳያሉ። በቋንቋና በባህል ረገድ የኢትዮጵያ መንግሥት መሠረት ታሪካዊ ትስስር ያለው ነው። የሀገሪቱ የቋንቋና የሥነ-ጽሑፍ ውርስ ከዓረብኛ፣ አራማይክና ዕብራይስጥ ጋር በጽኑ የተሳሰረ ሲሆን፣ ይህም በምሥራቅ አፍሪካና በአረቢያ ልሳነ-ምድር መካከል ያለውን ጥልቅ የጋራ የሥልጣኔ ቁርኝት ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ ልዩ ቦታ አላት። የመጀመሪያዎቹ ሙስሊሞች ወደ ኢትዮጵያ ተስደው በንጉስ ነጃሺ ከለላ ማግኘታቸው የእስልምናን ህልውና የታደገ ታሪካዊ ክስተት ሲሆን፣ ይህም ሀገሪቱን ከዓረቡ ዓለም ጋር በጽኑ አስተሳስሯታል። እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ፣ የዓረብ ሊግን በኢትዮጵያ ላይ እንደ ተቋማዊ ተፅዕኖ ማሳደሪያ መሣሪያ ግብጽ ስትጠቀምበት ቆይታለች። ግብፅ የውጭ ፖሊሲ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ዕድገት፣ የህዳሴውን ግድብም ሆነ የባሕር በር ጥያቄን እንደ ሥጋት በሚያይ ጊዜ ያለፈበት ስሌት ላይ የተመሠረተ ነው። ግብፅ የራሷን የውሃ አቋም በሊጉ ላይ በመጫን፣ ተቋሙ ከኢትዮጵያ ጋር አላስፈላጊ ውጥረት ውስጥ እንዲገባ አድርጋለች። ጅብሪል ላሞ እንዳመለከተው፣ ከግብጽ የአግላይነት ፖሊሲ ይልቅ የዘመኑ ነባራዊ ሁኔታዎች ሙሉ ትብብርን የሚጠይቁ ናቸው። በመደመር መርህ፣ ኢትዮጵያ ለዓረቡ ዓለም ለዘመናት ከቆዩ የጥላቻ መንገዶች በላቀ ሁኔታ የተሻሉ ጥቅሞችን ማቅረብ ትችላለች። እያደገ የመጣው የኢንዱስትሪ እና የአረንጓዴ ኃይል አቅሟ፣ ኢትዮጵያን ለቀይ ባህር ቀጣና የመረጋጋት ምሰሶ አድርጓታል። የመካከለኛው ምሥራቅ ቀጣና የውሃ እጥረት እና የምግብ ዋስትና ሥጋት በተጋረጠበት በዚህ ወቅት፣ የኢትዮጵያ የውሃ ሀበት እና ለም መሬት ለቀጣናው ወሳኝ የግብርና-ኢንዱስትሪ አጋር ያደርጋታል። የዓረብ ሊግ አባል ሀገራት የ21ኛውን ክፍለ ዘመን ብሔረተኝነት በመሻገር፣ የቀይ ባህርን ቀጣና የሥልጣኔ እውነታ መቀበል ይኖርባቸዋል። አረብ ሊግ እንደ ጅቡቲ፣ ሶማሊያ፣ ኮሞሮስ እና ሞሪታኒያ አባል ሀገራት መያዙ፣ ስብስቡ የተለያዩ ቀጣናዊ እውነታዎችን ማስተናገድ የሚችል መሆኑን ያሳያሉ። የዓረብ ሊግ ሙሉ አባልነት የኢትዮጵያን አፍሪካዊ ማንነት ሳይቀንሰው፣ አህጉሩን ከመካከለኛው ምሥራቅ ጋር የሚያገናኝ ዋነኛ ድልድይ የሚያደርጋት በመሆኑ፤ ሊጉ የኢትዮጵያን አጋርነት በመቀበል ለአዲስ አበባ ተገቢውንና ሕጋዊ ቦታዋን የሚሰጥበት ጊዜ አሁን እንደሆነ በመግለጽ ጅብሪል ላሞ ፅሁፉን ቋጭቷል።