ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት
May 14, 2026 87
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከብሩንዲ ጋር ለሚያደርገው ሁለተኛ ዙር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሁለተኛ ቀን ልምምዱን ዛሬ አድርጓል። አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ትናንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ዝግጅታቸውን የጀመሩ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ሁሉም ተገኝተው ልምምዳቸውን አከናውነዋል። በብሔራዊ ቡድኑ የሁለተኛ ቀን ዝግጅት ተጫዋቾች የእርስ በእርስ ጨዋታዎችን በማድረግ አቋማቸውን መፈተሻቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከብሩንዲ ጋር ግንቦት 16 የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው፣ የመልስ ጨዋታውን ግንቦት 23 ቡጁምቡራ ላይ ያከናውናል። 10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ። በዓለም ዋንጫው አፍሪካ ሞሮኮን ጨምሮ በአምስት ሀገራት ትወከላለች። በማጣሪያ የሚያልፉ አራት የአፍሪካ ሀገራት በሶስት ዙሮች በሚደረጉ ጨዋታዎች ይለያሉ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
May 14, 2026 71
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ ሶስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተለያዩ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው። ማምሻውን በተደረገው የ3000 ሜትር መሰናክል የወንዶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ገመቹ ጎዳና 8 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ወጥቷል። አትሌት ገመቹ ለኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ሶስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል። በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል። በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ አትሌት ምስጋና ኃይሉ እና በ400 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት አጃይባ አልዩ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘታቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው ሶስት የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሶስት የነሐስ በድምሩ ሰባት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በጋና አክራ እየተካሄደ የሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
አንጋፋው የእግር ኳስ ሰው ጌታቸው ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
May 14, 2026 81
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች፣ ዓለም አቀፍ ዳኛ እና አመራር የነበሩት ጌታቸው ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ጌታቸው ገብረማርያም በተጫዋችነት ለኦሜድላ እና ጥጥ ማኅበር እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውተው ያሳለፉ ሲሆን በመቀጠል ለረጅም ዘመናት በዓለም አቀፍ ዳኝነት ጭምር በሚታወቁበት የዳኝነት ሙያ አገልግለዋል። ከዳኝነት ከተገለሉ በኋላም በኮሚሽነርነት፣ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች በጥቅሉ ከ60 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በማገልገል ማሳለፋቸውን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። የአቶ ጌታቸው ገብረማርያም ሥርዓተ ቀብር ነገ በአማኑኤል ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይፈፀማል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአንጋፋው የእግር ኳስ ሰው ጌታቸው ገብረማርያም ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል።
አየር መንገዱ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ በማንቀሳቀስ እና በመጠገን ረገድ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ነው
May 14, 2026 184
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ በማንቀሳቀስና በመጠገን በአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ። አየር መንገዱ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ዛሬ የመሬት ላይ አውሮፕላን ትዕይንት (Static Air Show) አካሂዷል። አውሮፕላኖች ለሕዝብ ዕይታ የሚቀርቡበትን ትዕይንት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ከፍተውታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለማክበር የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማከናወን ላይ ይገኛል። ዛሬ የቀረበው የመሬት ላይ አውሮፕላን ትዕይንትም የዚሁ ክብረ በዓል አካል መሆኑን ገልጸዋል። ይህ መርሃ ግብር አየር መንገዱ በየዓመቱ 21 ሚሊዮን መንገደኞችን እና 850 ሺህ ቶን ጭነት ለማጓጓዝ የሚጠቀምባቸውን ዘመናዊ አውሮፕላኖች ለማህበረሰቡ ያስተዋወቀበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁል ጊዜም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ በማንቀሳቀስ እና በመጠገን ረገድ በአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑንም አረጋግጠዋል። ይህም አየር መንገዱን በአህጉሪቷ እጅግ ስኬታማ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም ዘመናዊና አዳዲስ አውሮፕላን ስብስብ (Young Fleet) ያለው ተወዳዳሪ አየር መንገድ እንዳደረገው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ 147 አውሮፕላኖች እንዳሉት የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ አሁን ላይ እያደገ ከመጣው ፍላጎት አኳያ ቁጥሩ በቂ አለመሆኑን አስረድተዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች ከ100 በላይ አውሮፕላኖች መታዘዛቸውን ጠቁመዋል። አየር መንገዱ በአምስት አህጉራት፣ በ82 ሀገራት እና በ140 መዳረሻዎች በረራ በማድረግ ሰዎችን በማገናኘትና ባህላዊ ትስስር በመፍጠር ረገድ አስደናቂ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝም አብራርተዋል። አየር መንገዱ ላለፉት 80 ዓመታት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በአፍሪካ ሰማይ ላይ ቀዳሚ መሆኑን አመልክተው፤ ሀገራትን በማቀራረብና በዓለም አቀፍ የባህልና የንግድ ልውውጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ሲጫወት መቆየቱን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታሪክ፣ የፅናት፣ የሀገር ግንባታ ውጤትና የአፍሪካውያን የትስስር ተምሳሌት ነው
May 14, 2026 167
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታሪክ፣ የፅናት፣ የሀገር ግንባታ ውጤትና የአፍሪካውያን የትስስር ተምሳሌት መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የመሬት ላይ አውሮፕላን ትዕይንት (Static Air Show) መርሃ ግብር በአየር መንገዱ ቅጥር ግቢ አካሂዷል፡፡ እንዲሁም አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የባህል ልውውጥ ወሳኝ ሚና እየተወጣ መሆኑን የሚያንፀባርቅ ዓለም አቀፍ የባህል ቀን በስካይ ላይት ሆቴል አክብሯል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከተመሰረተ ጥቂት ወራት በኋላ የተቋቋመ ታሪካዊ ተቋም ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ህዝቦችን እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን የማሳለጥ ተልዕኮ ሰንቆ መነሳቱን አስታውሰዋል፡፡ አየር መንገዱ ባለፉት አስርት ዓመታት አፍሪካን ከቀረው ዓለም ጋር ድልድይ ሆኖ በማገናኘት መንገደኞችና ሸቀጦችን አጓጉዟል፤ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲ እንዲሳለጥ አድርጓል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ቀዳሚ የአቪዬሽን ግሩፕ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አየር መንገዶች አንዱ መሆን መቻሉንም ገልጸዋል፡፡ መንግስት ሁሉን አቀፍ ሪፎርም በማድረግ የዘርፉን መሰረተ ልማት በማዘመን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የሀገራዊ ለውጥ አጀንዳ ማዕከል እንዲሆን አድርጓል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢኮኖሚ ስትራቴጂያዊ ምሰሶና የአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ በአቪዬሽንና ሎጂስቲክስ ያላትን መሪነት የሚያጠናክሩ ፖሊሲዎች ገቢራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡ የአውሮፕላን ትዕይንቱ አየር መንገዱ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበውን የቴክኖሎጂ እድገትና የብቃት ጉዞ የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የአቪዬሽን፣ ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ስርዓት እና በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስር ወደላቀ አህጉራዊ ውህደት ለመሸጋገር በትጋት እንሰራለን ብለዋል፡፡ ለአየር መንገዱ ስኬታማ ጉዞ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቀድሞና የአሁኑ መሪዎች፣ ፓይለቶች፣ መሐንዲሶችና ለመላው ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል። አየር መንገዱ በአምስት አህጉራት፣ በ82 ሀገራት እና በ140 መዳረሻዎች በረራ በማድረግ ሰዎችን በማገናኘትና ባህላዊ ትስስር በመፍጠር ረገድ አስደናቂ ሚና እየተወጣ መሆኑ ይታወቃል። አየር መንገዱ ላለፉት 80 ዓመታት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በአፍሪካ ሰማይ ላይ ቀዳሚ ነው።
ፖለቲካ
ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት መወጣትና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ተችሏል
May 14, 2026 177
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ማንኛውንም ግዳጅ በብቃት መወጣትና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚችል የፖሊስ ኃይል መገንባቱን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲካሄድ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉ ተጠቅሷል። ኮሚሽኑ በዘመናዊ አድማ ብተና የሰለጠኑ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ምረቃ ሥነ ሥርዓት ኮልፌ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ማሰልጠኛ ግቢ የተለያዩ የአድማ መከላከል፣ የተሽከርካሪ እና ልዩ ልዩ ወታደራዊ ትርኢቶች አቅርቧል። በመርሐ ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል መከላከል ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል መላኩ ፋንታ፣ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ምክትል ኮሚሽነር ጀነራል ርዕስቱ ይርዳው፣ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ቃል አቀባይ ረዳት ኮሚሽነር ሞገስ ቸኮል፣ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ ታምራት ሙልጌታ(ዶ/ር) እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኮሚሽኑ ባለፉት ዓመታት ጠንካራ ሥራዎችን በማከናወን የተሰጡትን ተልዕኮዎች በብቃት ሲወጣ ቆይቷል። በዚህም በሀገር ደረጃ የተሻለ ሰላምና ደኅንነት እንዲኖር ማስቻሉን ጠቁመው፤ ይህንንም ከሌሎች የፀጥታ ተቋማት ጋር በመቀናጀት እውን ማድረጉን አንስተዋል። ጠንካራ መንግሥትና ሕዝብ ያላት ሀገር ጠንካራ የፖሊስ ሠራዊት ሊኖራት እንደሚገባ ገልጸው፣ በዚህም ባለፉት ዓመታት የሰለጠነ፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሚሰጠውን ማንኛውንም ግዳጅ መወጣትና የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ የሚችል የፖሊስ ኃይል መገንባት መቻሉን ጠቁመዋል። ዛሬ የተመረቁትም በሀገር ውስጥ የሰለጠኑ፣ የበቃ የፖሊስ ኃይል በተለይም የአድማ ብተና ኃይል፣ አድማን በዘመናዊ መንገድ መከላከል የሚያስችል አቅም ያለው መሆኑን ገልጸዋል። አሁን ላይ ፖሊስ በወሰዳቸው ጠንካራ ሥልጠናዎች የበቃ የሰው ኃይል መፈጠሩንና በቁጥሩም በአቅሙም ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። እንዲሁም የሎጂስቲክስ አቅማቸው ያደጉ ሀገራት የሚጠቀሙባቸው ዘመናዊ የአድማ ብተና ተሽከርካሪዎች፣ ድሮኖችና ሌሎች ትጥቆች መኖራቸውን ጠቅሰው፤ ይህንን ማከናወን የሚችል የሰው ኃይል ባለቤት መሆን መቻሉንም ገልጸዋል። በዚህም ዘመኑን የዋጀ ቴክኖሎጂና የሎጂስቲክስ አቅም እንዲሁም የታጠቃቸውን ዘመናዊ መሣሪያዎች በመጠቀም የመላው ሀገሪቱን ደኅንነት እያረጋገጠ ይገኛል ብለዋል።
ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ
May 14, 2026 169
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6 /2018 (ኢዜአ):- የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በህንድ ዛሬ በተጀመረው የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ በመሳተፍ ላይ ናቸው። ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) ከስብስባው ጎን ለጎን ከደቡብ አፍሪካው የዓለም አቀፍ ግንኙነትና ትብብር ሚኒስትር ሮናልድ ላሞላ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በሀገራቱ የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያተኮረ ሲሆን ሚኒስትሮቹ በደቡብ አፍሪካ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ያሉ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት መስማማታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
የምርጫ ሂደቱ ምቹ የፉክክር ድባብ የተፈጠረበት ነው- የፖለቲካ ፓርቲዎች
May 14, 2026 144
ባህር ዳር፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ የምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ከመሆኑም ባሻገር ምቹ የፉክክር ድባብ የተፈጠረበት መሆኑን በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሂደቱም ሆነ በውጤቱ የህዝብን አመኔታ ያተረፈ እንዲሆን፣ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቋቁመው በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ። እስካሁን ባለው የእጩዎችና የመራጮች ምዝገባ፣ ብሎም የምረጡኝ ቅስቀሳው ጥሩ ሂደት ላይ መሆኑን አረጋግጠዋል። የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ምክትል ሊቀመንበር መልካሙ ፀጋዬ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ለዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ ከአንድ ዓመት በፊት ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግ ቆይቷል። በአሁኑ ወቅትም ፓርቲው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓም ለሚካሔደው ጠቅላላ ምርጫ በቂ ቁጥር ያላቸው እጩዎችን ማስመዝገብ መቻሉን ገልጸዋል። ፓርቲው ለሀገርና ለህዝብ የሚበጁ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጂዎችንና ፕሮግራሞችን የማስተዋወቅ ስራ በስፋት እየሰራ እንደሚገኝም ነው ያነሱት። በቅስቀሳው ወቅትም ከስሜት ቀስቃሽ ሃሳቦችና አስተያየቶች በመቆጠብ፣ የምርጫ ህጉን ብቻ መሰረት በማድረግ እየተሰራ እንደሆነ ጠቅሰዋል። በምርጫው አሸናፊ ሆኖ ለመገኘትም፣ የተመቻቸውን የመገናኛ ብዙሃን የሰዓት ድልድል በመጠቀም የምረጡኝ ቅስቀሳና ክርክር እያካሄዱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሰላማዊና አሳታፊ በሆነ መንገድ እንዲከናወን እየሰራን ነው ያሉት ደግሞ የአማራ ዴሞክራሲ ሃይሎች ንቅናቄ (አዲሃን) ስራ አስፈፃሚ አባል አዲሱ ጉልላት ናቸው። ለምርጫው በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ በፀጥታና መሰል ዘርፎች አማራጭ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለህዝብ ለማስተዋወቅ በመገናኛ ብዙሃን ሰፊ እድል መፈጠሩንም ተናግረዋል። እስካሁን ባለው እንቅስቃሴ ምንም ዓይነት የማዋከብና የማንገላታት ችግር እንዳልደረሰባቸው አመልክተው፤ ይህም ምርጫውን ዴሞክራሲያዊ በሆነ አግባብ ለማጠናቀቅ አስቻይ ሁኔታ መኖሩን የሚያመላክት ነው ብለዋል። ምርጫ ለአንድ ሀገር ህጋዊና በህዝብ ይሁንታን ያገኘ መንግስት ለማቋቋም ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህ እንዲሳካም ፓርቲያቸው ሰላማዊ የትግል አማራጭን በመከተል እየሰራ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የሰሜን ኢትዮጵያ አስተባባሪ ኃይለማርያም ብርሃኑ በበኩላቸው፤ ለምርጫው ስኬታማነት በጋራ ምክር ቤት ውስጥ ታቅፈን በትብብር እየሰራን ነው ብለዋል። በመሆኑም ከምርጫ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የሚገጥሙ ችግሮች በሰለጠነ አግባብ እየተፈቱ መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም እስከ መጨረሻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የቆዩ የሀሳብ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ታሪካዊ ዕድል ነው
May 14, 2026 258
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ለዘመናት የቆዩ የሀሳብ ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ ለመፍታትና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ታሪካዊ ዕድል መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ገለጸ። በኢትዮጵያ ለዘመናት ስር የሰደዱ የሃሳብ ልዩነቶችን በንግግር ለመፍታትና በሃሳብ የበላይነት የሚያምን ትውልድ ለመፍጠር ታቅዶ የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር፣ አሁን ላይ አዲስና ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል። ኮሚሽኑ በሁሉም ክልሎች፣ በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች፣ በፌዴራል ተቋማት እና በውጭ በሚኖሩ ዜጎች ዘንድ ያለውን የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት በስኬት አጠናቋል። ከወረዳ ጀምሮ እስከ ማዕከል ድረስ በግልጽነት በተከናወነው በዚህ ሂደት፣ ለዋናው ሀገራዊ ጉባኤ የሚሳተፉ ተወካዮች ተለይተዋል። ለምክክሩ ከተለያዩ ማህበረሰቦች አሳታፊ በሆነ መልኩ ግብዓቶች የተሰበሰበ ሲሆን፤ ይህ ተግባር ኮሚሽኑ ወደ ዋናው ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ መሸጋገር የሚያስችለውን አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ኮሚሽኑ ዋናውን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስችሉ የዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ ነው። ይህም ኢትዮጵያ ልዩነቶቿን በሰለጠነ መንገድ በመፍታት የተሻለች ሀገር ለመገንባት የምታደርገውን ጥረት የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት፤ ሀገራዊ ምክክሩ ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባትና ለቀጣዩ ትውልድ የምትመች ሀገር ለማስረከብ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ በውይይት የምትጸና ሀገር ሁለንተናዊ ጥንካሬ ከመጎናጸፏ ባለፈ ዜጎቿን ለላቀ ተጠቃሚነትና ለጋራ ብልፅግና የምታበቃበት ሰፊ ዕድል እንደሚፈጥርም ተናግረዋል፡፡ ይህ የታሪክ ምዕራፍ ብሔራዊ መግባባትን ለመፍጠርና የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ ብሎም ለሀገር ግንባታ አስተማማኝ መሠረት የሚጥል መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ዘላቂ ሀገራዊ መግባባትን ለማጎልበት በሚከናወኑ ስራዎች የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን ጠቅሰው፤ ለምክክሩ ስኬትም ያልተቋረጠ ተሳትፎ እና ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሰላማዊ የውይይት ባህል እንዲዳብርና ሀገራዊ መግባባት እንዲሰፍን እያከናወኑት ያለው የላቀ ሚና በቀጣይም በታላቅ ተነሳሽነት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። የበለጸገች ሀገርን በጋራ ለመገንባት ያለውን መልካም ዕድል በመጠቀም እያንዳንዱ ዜጋ ያለውን ሚና በተሻለ መንገድ እንዲያበረክትም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ መላው ህዝብ በታላቅ የኃላፊነት ስሜትና በንቁ ተሳትፎ በሂደቱ ሲሳተፍ እንደነበር ጠቅሰው አሁንም ወሳኝ ምዕራፍ ላይ የደረሰው የምክክር ሂደት በስኬት እንዲጠናቀቅ አበርክቶውን ማጣናከር ይገባዋል ነው ያሉት፡፡
ብልጽግና ፓርቲ የተገበራቸው ሰው ተኮር የልማት ተግባራት ስኬታማ ናቸው - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
May 14, 2026 203
አርባ ምንጭ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ ብልጽግና ፓርቲ ተግባራዊ ያደረጋቸው ሰው ተኮር የልማት ስራዎች ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ከማድረግ አኳያ ስኬታማ በመሆናቸው ተጠናክረው ይቀጥላሉ ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ። የጋሞ ዞንን ወክለው ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደሩ ዕጩዎችን የሚያስተዋውቅ የድጋፍ ሰልፍ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል። በመርሃ-ግብሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርና የአርባ ምንጭ ምርጫ ክልል ዕጩ የሆኑት አቶ ጥላሁን ከበደ ብልጽግና ፓርቲ በየደረጃው የህዝቡን የልማት ጥያቄ እየመለሰ ያለ ሰው ተኮር ፓርቲ ነው ብለዋል። ፓርቲው ትናንትናና ዛሬ ስራ ላይ ያለ ለነገም ያለ እረፍት እየተጋ የሚቀጥል ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር የሚያሻግር የህዝብ ፓርቲ ነው ሲሉም ተናግረዋል። ህዝቡ የልማትና የሰላም ባለራዕይ የሆነውን ብልጽግና ፓርቲን በመምረጥ ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በማሻገር ተጠቃሚነቱን ማስቀጠል እንደሚገባውም ነው ጥሪ ያቀረቡት። 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በምርጫው ሂደት ህዝቡ የበኩሉን እንዲወጣም መልዕክት አስተላልፈዋል። የዞኑ ህዝብ ከ2010 ዓ/ም ጀምሮ የብልጽግና ፓርቲ ሁለንተናዊ የልማት ትሩፋቶችን እያጣጣመ ይገኛል ያሉት ደግሞ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) ብልጽግና ፓርቲ በውጤት የታጀበ ፓርቲ ነው ብለዋል። ፓርቲው ቃልን በተግባር የሚፈጽም በመሆኑ የዞኑ ህዝብ ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓም በሚካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ብልጽግና ፓርቲን በመምረጥ የተጀመረው ልማት እንዲጠናከር የበኩሉን እንዲወጣ አሳስበዋል። የአርባ ምንጭ ከተማ ከንቲባ መስፍን መንዛ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ከተማ አስተዳደሩ ምርጫው በህዝቡ ዘንድ ፍጹም ቅቡልነት ያለውና ሰላማዊ እንዲሆን እየሠራ ይገኛል ብለዋል። ፓርቲው የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ የሚጨበጥ፣ የሚቆጠርና የሚታዩ ልማቶችን ሠርቶ እያሳየ ያለ ነው ሲሉም ገልጸዋል። በየአካባቢው እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የከተማዋ ነዋሪዎች ብልጽግና ፓርቲን እንዲመርጡም ነው መልዕክት ያስተላለፉት። በመርሃ-ግብሩ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ሴቶች፣ ወጣቶችና ሌሎች የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በጠቅላላ ምርጫው የወጣቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት ተደርጓል
May 14, 2026 363
ጭሮ /ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፡-በጠቅላላ ምርጫው የወጣቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ወጣቶች ማህበር አስታወቀ። የወጣቶች ሁለንተናዊ ተሳትፎ ለጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እና ለሀገር መፃኢ ዕድል ቁልፍ መሣሪያ ነው። በዞኑ ወጣቶች በምርጫው ሂደት ንቁ ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ ሰፊ ቅስቀሳ ተደርጓል። የወጣቶችን የምርጫ ተሳትፎ ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ወጣቶች በታዛቢነት እና በምርጫ አስፈጻሚነት እንዲሳተፉ በማድረግ የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ እየተሰራም ይገኛል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የምዕራብ ሐረርጌ ዞን ወጣቶች ማህበር ሰብሳቢ ወጣት ሙርቴሳ መሐመድ እንደገለፁት፤ በጠቅላላ ምርጫው እውን በሚሆነው የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ የወጣቶችን ተሳትፎ ማሳደግ ላይ ትኩረት ተደርጓል። ወጣቱ በዕውቀት ላይ ተመስርቶ እንዲመርጥ እስከ ታችኛው የአስተዳደር እርከን የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እየተሰጠ ነው ብለዋል። ምርጫ ለሰላምና ለዴሞክራሲ ግንባታ መሰረታዊ ጉዳይ በመሆኑ ወጣቱ በንቃት በመሳተፍ ሰላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። ለዚህም ማህበሩ ግንዛቤ ከመስጠት ባለፈ፣ በዞኑ በሚገኙ 15 ወረዳዎችና 5 ከተሞች ውስጥ ሂደቱን የሚከታተሉ 2 ሺህ 756 የምርጫ ታዛቢዎችን መድቧል ነው ያሉት። ወጣቱ የአንድ ሰው ድምጽ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ያለውን ወሳኝነት በመረዳት በካርዱ የሚበጀውን የፖለቲካ ፓርቲ በዕውቀት እንዲመርጥም ጥሪ አቅርበዋል። ከጭሮ ከተማ ወጣቶች መካከል ወጣት አብደላ መሐመድ እና ወጣት መሐመድ ሐሰን በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በከተማው ወጣቶች ማህበር በኩል በተፈጠረው ግንዛቤ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል። በምርጫ ካርዳቸው ለሀገር ግንባታ የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥም በመገናኛ ብዙሃን እና በተለያዩ አማራጮች የሚደረጉ የምርጫ ቅስቀሳዎችን እየተከታተሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
ምርጫው ስኬታማ እንዲሆን የበኩላችንን ለመወጣት ተዘጋጅተናል
May 14, 2026 225
ደደር፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፡- 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ስኬታማ እንዲሆን የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የደደር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የደደር ከተማ ነዋሪዎች፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸዋል። ነዋሪዎቹ ምርጫው ስኬታማ እንዲሆንና ያለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከናወን ከሚመለከታቸው የሰላም፣ የቁጥጥርና ሌሎች አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ከነዋሪዎቹ መካከል አባገዳ አብዱማሊክ ጁንዲ፤ ምርጫው ነፃና ሰላማዊ ሆኖ እንዲካሄድ የላቀ ድርሻና ኃላፊነት እንዳለባቸው በመገንዘብ እንቅስቃሴ እያደረጉ ነው። ህዝቡ በምርጫው እንዲሳተፍ ለማድረግ ከሁሉም አካላት ጋር በመቀናጀት መስራታቸውን ጠቁመው፤ መራጩ ህዝብም በድምጽ መስጫ ወቅት ይበጀኛል ለሚለው ፓርቲ ድምጹን እንዲሰጥና ምርጫው ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ እየሰሩ መሆኑን ተናግረዋል። ምርጫው የዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ማረጋገጫ ነው ያሉት ደግሞ በደደር ከተማ በንግድ ስራ የሚተዳደሩት አቶ አብዱሹ አህመድ ናቸው። የመራጮች ምዝገባ መካሄድ ከጀመረበት እለት አንስቶ ህዝቡን የማንቃት ሥራ እየሰሩ መሆኑን አንስተው ምርጫው ያለምንም ችግር ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ የበኩሌን እወጣለው ሲሉም አክለዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ አድናን ሻፊ በበኩላቸው፤ የምርጫውን እለት በጉጉት እየጠበቁና በተለይም ምርጫው በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል። ምርጫው ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲካሄድ እንዲሁም ወጣቶች በንቃት እንዲሳተፉ የበኩላቸውን ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የጠቆሙት ደግሞ አቶ አብደላ አህመድ ነው። ለምርጫው ሰላማዊነትና ስኬት በተለይም ወጣቶችን በማስተባበር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል።
በወሰድነው የመራጭነት ካርድ ለሀገር ልማትና ዕድገት ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል
May 14, 2026 200
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ ለሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የወሰዱትን የመራጭነት ካርድ ለሀገር ልማትና ዕድገት ይበጃል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን አስተያየት የሰጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24/2018ዓ.ም መራጮች ድምፅ ይሰጣሉ። የዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባም ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 28/2018 ዓ.ም የተከናወነ ሲሆን ሁለት የበዓል ቀናትን ሳይጨምር እስከ ሚያዚያ 14/2018 ዓ.ም በማራዘም ተካሂዶ ተጠናቋል። በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ድምፅ መስጫ ካርድ ላልወሰዱ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች፣ በዩኒቨርሲቲ ለሚገኙ ተማሪዎችና በካምፕ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በልዩ ሁኔታ እስከ ሚያዝያ 24 ቀን 2018ዓ.ም በማራዘም አጠናቋል። መራጮች በዲጂታል "ምርጫዬ" መተግበሪያና በየምርጫ ጣቢያዎች በአካል በመገኘት ከ50 ሚሊየን 514 በላይ መራጮች ድምፅ መስጠት የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ መውሰድ ችለዋል። በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫም 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የፖሊሲ አማራጭ ሃሳባቸውን ለህዝብ በማስተዋወቅ ላይ ናቸው። በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫ ታዛቢነት ዕውቅና የተሰጣቸው 55 የሀገር ውስጥ ድርጅቶችም በተለያዩ አካባቢዎች ከ60ሺህ 277 በላይ ወኪሎችን አሰማርተዋል። በመራጮች ትምህርት ላይ ዕውቅና የተሰጣቸው 169 የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶችም ለመራጩ ህዝብ የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትና ስልጠና እየሰጡ ይገኛሉ። በአዲስ አበባ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመመዝገብ ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ለሀገርና ለሕዝብ ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተዋል። ከመዲናዋ ነዋሪዎች መካከል ወርቁ ፍቃዱ እንደገለጹት፤ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ ከማውጣት ጀምሮ የምርጫውን ቀን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ እየሩሳሌም ሀረገወይን በበኩላቸው፤ በምርጫ ካርዳቸው ለሀገር ልማትና ዕድገት ዕውን መሆን ለሚሰራ ፓርቲ ይሁንታ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። ሌሊሳ ጋዲሳም እንዲሁ፤ የምርጫ ካርድ በማውጣት ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የድምፅ መስጫ ቀኑን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ አረጋግጠዋል። የምርጫ ሂደትም ፍትሀዊ፣ ነጻ፣ ዴሞክራሲያዊና ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩሉን አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የመዲናዋ ነዋሪ ወደሬ ገብረጻዲቅ እንደተናገሩት፤ ምርጫ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም፤ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት አድርገዋል። አቶ ድሪቢሳ ጥሩነህ በበኩላቸው፤ ምርጫው ሕገ-መንግሥታዊ የመምረጥና መመረጥ ዴሞክራሲያዊ ማረጋገጫ ወሳኝ መድረክ በመሆኑ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ለሀገር ሰላም፣ ልማትና ዕድገት መረጋገጥ ለሚሰራ ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት ከወዲሁ ተዘጋጅቻለሁ ያሉት ደግሞ አቶ ተሾመ አስፋው ናቸው።

ማህበራዊ
ኢትዮጵያ በሕዝቦች መተባበር የጠነከረች፣ ልዩነትን ወደ ውበት የቀየረች፣ በኅብረ ብሔራዊ ቀለም የደመቀች መሆኗን ለዓለም ማሳየት ይገባል
May 14, 2026 120
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሕዝቦች መተባበር የጠነከረች፣ ልዩነትን ወደ ውበት የቀየረች፣ በኅብረ ብሔራዊ ቀለም የደመቀች መሆኗን ለዓለም ማሳየት እንደሚገባ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ ገለጹ፡፡ ዛሬ የተጀመረውና እስከ ግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የሚቆየው ሀገር አቀፍ የባህል እና ቋንቋ ሳምንት "የባህል ልማት ለኅብረብሔራዊ አንድነት" በሚል መሪ ኃሳብ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል። በመርሐ ግብሩ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቅሰሙ ማሞ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ተሳታፊዎች ታድመዋል፡፡ የጤና፣ ማኅበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቅሰሙ ማሞ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያውያን የብዝሃ ማንነትና ባህል ባለቤት፣ ለዘመናት በአብሮነት የኖሩ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ኢትዮጵያውያን በርካታ ታሪካዊና ወቅታዊ ፈተናዎችን በጋራ ተሻግረው ለሀገር ግንባታ ትልቅ ድርሻ ማበርከታቸውን ገልጸው፤ ብዝሃ ባህላዊና ሃይማኖታዊ በዓላት በሕዝቦች መካከል አንድነት እና ትስስር እንዲጠናከር አስችለዋል ብለዋል፡፡ ባህል የትውልድ ማንነት መገለጫ ብቻ ሳይሆን የልማት፣ የሰላምና የዲፕሎማሲ ኃይል ነው ያሉት ሰብሳቢዋ፤ ኢትዮጵያውያን ያላቸውን እምቅ የባህል፣ የቋንቋ፣ ቅርስና ሀገር በቀል ዕውቀት በአግባቡ ጥቅም ላይ ማዋል እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ የሰው ልጆች መገኛ፣ የጥንታዊ ባህልና የስልጣኔ መነሻ መሆኗን ታሳቢ በማድረግ ለዓለም ለማስተዋወቅ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡ ሀገር አቀፍ የባህል እና ቋንቋ ሳምንቱ የኢትዮጵያ የባህል ትርኢት ከማሳየት ባለፈ በሕዝቦች መካከል ትስስርን በመገንባት የጋራ እሴቶችን ለወጣቱ ትውልድ የሚያስተላልፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኢትዮጵያ በሕዝቦች መተባበር የጠነከረች፣ ልዩነትን ወደ ውበት የቀየረች፣ በሕብረብሔራዊ ቀለም የደመቀች ሀገር መሆኗን ለዓለም የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ የሕዝቡን መልካም እሴቶች በመጠበቅ ለትውልድ ለማስተላለፍና ለማበልጸግ በጋራ መቆም ይገባል ያሉት ሰብሳቢዋ፤ ሁሉም ለሰላም፣ ለአንድነትና ለባህል ልማት በጋራ መስራት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያዊያን ባህላዊ ዕሴቶች የእርስ በእርስ መስተጋብርን በማጠናከር ለሀገር ዘላቂ ልማት ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ ነው
May 14, 2026 87
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያዊያን በሕብር ያሸበረቁ ባህላዊ ዕሴቶች የእርስ በእርስ መስተጋብርን በማጠናከር ለሀገር ዘላቂ ልማት ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሚገኙ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ ገለጹ። የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ''የባህል ልማት ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት'' በሚል መሪ ሃሳብ ከዛሬ ግንቦት 6 እስከ 10/2018 ዓ.ም የሚቆይ ሀገር አቀፍ የባህልና ቋንቋ ሳምንት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በባህል ሳምንቱ መክፈቻ ላይ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጤና፣ ማህበራዊ ልማት፣ ባህልና ስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወርቀሰሙ ማሞ፣ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ፣ ተጋባዥ እንግዶችና የባህል ሳምንት ተሳታፊዎች ታድመዋል። በዚሁ ወቅት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ እንዳሉት፤ የባህል ሳምንቱ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር የህዝብ ለህዝብ የባህል ትስስርና ትውውቅን ለማጠናከር ታልሞ የተዘጋጀ ነው። በባህልና ቋንቋ ሳምንቱም የባህላዊ አልባሳት፣ ምግቦች፣ የዕደ ጥበብ ውጤቶች፣ የባህል መገለጫዎችና ዕሴቶች ለህዝብ ዕይታ ክፍት መሆናቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በብዝኅነት ያሸበረቁ ውብ ባህላዊ ዕሴትና መገለጫዎች ባለቤት ናት ያሉት ሚኒስትሯ፤ የህዝብን ባህልና ቋንቋ በማልማት ለህዝብ አብሮነት እንዲውሉ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ባህሎች የህዝብ አብሮነት፣ አንድነትና የጋራ መግባባት መሠረቶች መሆናቸውን አስገንዝበዋል። የኢትዮጵያዊያን ዕሴቶችም የእርስ በዕርስ መስተጋብርን በማጠናከር ለሀገር ዘላቂ ሰላምና ልማት ጉልህ ፋይዳ እያበረከቱ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የህዝብን በብዝኅነት ያሸበረቁ ኅብረ ብሔራዊ ዕሴቶች በፖሊሲ የተደገፈ ልማት በማካሄድ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን አንስተዋል። የባህልና ቋንቋ ሳምንቱም የኢትዮጵያን ቱባ ባህላዊ ዕሴቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ለትውልድ ለማስተላለፍ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር አንስተዋል። የህዝቦች አብሮነትና ትስስር ይበልጥ እንዲጠናከር እንዲሁም የበለጸገች ኢትዮጵያን ለመፍጠር በሚደረገው ጉዞም የባህል ልማት ወሳኝና የማይተካ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አብራርተዋል። የዜጎች የባህላዊ ዕሴቶችም የኢትዮጵያን የቱሪዝም ዘርፍ በማነቃቃት ከፍተኛ አቅም እየፈጠረ እንደሚገኝ አንስተዋል። የተለያዩ ባህሎችን ለቱሪዝም ልማት በማዋል የኢኮኖሚ ምንጭ እንዲሆኑም ዘርፉን በዘላቂነት መደገፍ የሚያስችሉ የባህል መሠረተ ልማቶች እየተካሄዱ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ለሀገራዊ መግባባትና ለሰላማዊ ምክክር ሂደት ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል
May 14, 2026 96
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ለሀገራዊ መግባባትና ለሰላማዊ ምክክር ሂደት ስኬታማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረከቱ የሀገር ባለውለታ ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር የነበሩት የዘገየ አስፋው ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል። በሥርዓተ ቀብሩ ላይ የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር፣ የጠቅላይ ሚኒስትር የማኅበራዊ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሙዓዘ ጥበባት ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሳ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያን ጨምሮ ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ለኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በሰጡት ምስክርነት፣ ግለሰቡን በሁለት ታላላቅ የታሪክ ምዕራፎች ውስጥ የነበሩ "የጽናት ተምሳሌት" መሆናቸውን ገልጸዋል። በመጀመሪያው ምዕራፍ፣ በወጣትነት ዘመናቸው ለአርሶ አደሩ ድምፅ በመሆን ለማኅበራዊ ፍትሕ የቆሙ የለውጥ ኮከብ እንደነበሩ አውስተዋል። በሁለተኛውና በአሁኑ ምዕራፍ ደግሞ፣ "አገልግያለሁ ይበቃኛል" ሳይሉ የሀገሪቱን ሰላም በምክክር ለማምጣት በሰሩት ስራ የሀገር ፍቅራቸውን በተግባር ማሳየታቸውን ተናግረዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)፣ ከኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ጋር የቆየ ትውውቅ እንደነበራቸው ገልጸዋል። ኮሚሽነሩ ታሪካዊውን "የመሬት ላራሹ" አዋጅ ተረቆ እንዲጸድቅና በሥራ ላይ እንዲውል በማድረጋቸው ረገድ የማይተካ ሚና የተጫወቱ የሀገር ባለውለታ መሆናቸውን መስክረዋል። ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በስራ መስካቸውም ሆነ በተማሪነት ዘመናቸው የነበራቸውን ጠንካራ ስብዕና የቅርብ ወዳጆቻቸው መስክረዋል። የቀድሞው የቀዳማይ ኃይለ ሥላሴ የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት የክፍል ጓደኛቸው አባቢያ አባጆቢር አባጅፋር፣ ኮሚሽነሩ በትምህርታቸው እጅግ ጎበዝ እንደነበሩና በሥራ ዘመናቸውም "የመሬት ላራሹ" አዋጅ እንዲጸድቅ በማድረግ በኢትዮጵያ የፍትሕ ሥርዓት ላይ የማይረሳ አሻራ ማኖራቸውን ገልጸዋል። በተመሳሳይ አቶ አድማሱ ካሳ፤ ግለሰቡ በሥራቸው ታታሪና ውጤታማ እንደነበሩ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
በአዲስ አበባ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ዕውን ሆነዋል
May 14, 2026 140
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ በአዲስ አበባ የነዋሪዎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ዕውን መሆናቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ። ከንቲባ አዳነች አቤቤ በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባውን 29ኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል፡፡ በምርቃት ሥነ-ስርዓቱ ላይ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ባስተላለፉት መልዕክት፤ መዲናዋን ውብ ገፅታ ከሚያላብሱ የልማት ውጤቶች ባሻገር ውጤታማ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎች እየተሰሩ ነው ብለዋል። በልደታ ክፍለ ከተማ ለአገልግሎት የበቃውን 29ኛ የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ጨምሮ የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ በርካታ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ዕውን መሆናቸውን ገልጸዋል። በልደታ ክፍለ ከተማ በጎነት መንደር ላይ የተገነባው የምገባ ማዕከልም የአገልግሎት አቅምና ተደራሽነት በማስፋት ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የሀገር ባለውለታዎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል። ዳሸን ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በጎነት ሰፈር 29ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በማስገንባት ላሳየው ቁርጠኝነት ምስጋና አቅርበዋል። በቅርቡ ሁለት የምገባ ማዕከላት ወደ ሥራ እንደሚገቡም አረጋግጠዋል። የልደታ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ልዕልቲ ግደይ በበኩላቸው፤ የምገባ ማዕከሉ ለክፍለ ከተማው 3ኛ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ የምገባ ማዕከል ጧሪና ደጋፊ የሌላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች በቀን አንድ ጊዜ ማዕድ እንደሚቋደሱ ገልጸዋል። ኢዜአ ያነጋገራቸው የማዕከሉ ተጠቃሚ ወይንሸት ከበደ እንዳሉትም፤ የምገባ ማዕከሉ የአቅመ ደካሞችን የኑሮ ሸክም የሚያቃልል ነው። ሌላኛው የማዕከሉ ተጠቃሚ ዘካሪያስ ገዝሙ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ መንግስት የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎችን እየሰራ መሆኑን ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል። በበጎነት መንደር የተገነባው 29ኛ የምገባ ማዕከልም የበርካታ እጅ አጠር ዜጎችን የኑሮ ጫና የሚቀንስ ነው ያሉት ደግሞ አካሉ ከፈለኝ ናቸው።
ኢኮኖሚ
አየር መንገዱ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ በማንቀሳቀስ እና በመጠገን ረገድ በአፍሪካ ግንባር ቀደም ነው
May 14, 2026 184
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ በማንቀሳቀስና በመጠገን በአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈፃሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ። አየር መንገዱ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ዛሬ የመሬት ላይ አውሮፕላን ትዕይንት (Static Air Show) አካሂዷል። አውሮፕላኖች ለሕዝብ ዕይታ የሚቀርቡበትን ትዕይንት የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) እና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ከፍተውታል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ አየር መንገዱ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ለማክበር የተለያዩ መርሃ ግብሮችን በማከናወን ላይ ይገኛል። ዛሬ የቀረበው የመሬት ላይ አውሮፕላን ትዕይንትም የዚሁ ክብረ በዓል አካል መሆኑን ገልጸዋል። ይህ መርሃ ግብር አየር መንገዱ በየዓመቱ 21 ሚሊዮን መንገደኞችን እና 850 ሺህ ቶን ጭነት ለማጓጓዝ የሚጠቀምባቸውን ዘመናዊ አውሮፕላኖች ለማህበረሰቡ ያስተዋወቀበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሁል ጊዜም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሆኑ አውሮፕላኖችን በመግዛት፣ በማንቀሳቀስ እና በመጠገን ረገድ በአፍሪካ ቀዳሚ መሆኑንም አረጋግጠዋል። ይህም አየር መንገዱን በአህጉሪቷ እጅግ ስኬታማ፤ በዓለም አቀፍ ደረጃም ዘመናዊና አዳዲስ አውሮፕላን ስብስብ (Young Fleet) ያለው ተወዳዳሪ አየር መንገድ እንዳደረገው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ 147 አውሮፕላኖች እንዳሉት የገለጹት ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ አሁን ላይ እያደገ ከመጣው ፍላጎት አኳያ ቁጥሩ በቂ አለመሆኑን አስረድተዋል። ለዚህም ይረዳ ዘንድ ከቦይንግ እና ኤርባስ ኩባንያዎች ከ100 በላይ አውሮፕላኖች መታዘዛቸውን ጠቁመዋል። አየር መንገዱ በአምስት አህጉራት፣ በ82 ሀገራት እና በ140 መዳረሻዎች በረራ በማድረግ ሰዎችን በማገናኘትና ባህላዊ ትስስር በመፍጠር ረገድ አስደናቂ ሚና እየተወጣ እንደሚገኝም አብራርተዋል። አየር መንገዱ ላለፉት 80 ዓመታት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በአፍሪካ ሰማይ ላይ ቀዳሚ መሆኑን አመልክተው፤ ሀገራትን በማቀራረብና በዓለም አቀፍ የባህልና የንግድ ልውውጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ሲጫወት መቆየቱን ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታሪክ፣ የፅናት፣ የሀገር ግንባታ ውጤትና የአፍሪካውያን የትስስር ተምሳሌት ነው
May 14, 2026 167
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡-የኢትዮጵያ አየር መንገድ የታሪክ፣ የፅናት፣ የሀገር ግንባታ ውጤትና የአፍሪካውያን የትስስር ተምሳሌት መሆኑን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ አየር መንገድ 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የመሬት ላይ አውሮፕላን ትዕይንት (Static Air Show) መርሃ ግብር በአየር መንገዱ ቅጥር ግቢ አካሂዷል፡፡ እንዲሁም አየር መንገዱ በዓለም አቀፍ የባህል ልውውጥ ወሳኝ ሚና እየተወጣ መሆኑን የሚያንፀባርቅ ዓለም አቀፍ የባህል ቀን በስካይ ላይት ሆቴል አክብሯል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከተመሰረተ ጥቂት ወራት በኋላ የተቋቋመ ታሪካዊ ተቋም ነው፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓለም አቀፍና በአህጉር አቀፍ ደረጃ ህዝቦችን እና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎችን የማሳለጥ ተልዕኮ ሰንቆ መነሳቱን አስታውሰዋል፡፡ አየር መንገዱ ባለፉት አስርት ዓመታት አፍሪካን ከቀረው ዓለም ጋር ድልድይ ሆኖ በማገናኘት መንገደኞችና ሸቀጦችን አጓጉዟል፤ ንግድና ኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝምና ዲፕሎማሲ እንዲሳለጥ አድርጓል ብለዋል፡፡ የአፍሪካ ቀዳሚ የአቪዬሽን ግሩፕ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ፈጣን እድገት እያስመዘገቡ ካሉ አየር መንገዶች አንዱ መሆን መቻሉንም ገልጸዋል፡፡ መንግስት ሁሉን አቀፍ ሪፎርም በማድረግ የዘርፉን መሰረተ ልማት በማዘመን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የሀገራዊ ለውጥ አጀንዳ ማዕከል እንዲሆን አድርጓል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኢኮኖሚ ስትራቴጂያዊ ምሰሶና የአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ መሆኑን ጠቅሰው፤ በኢትዮጵያ በአቪዬሽንና ሎጂስቲክስ ያላትን መሪነት የሚያጠናክሩ ፖሊሲዎች ገቢራዊ እንደሚደረጉ ገልጸዋል፡፡ የአውሮፕላን ትዕይንቱ አየር መንገዱ ባለፉት ዓመታት ያስመዘገበውን የቴክኖሎጂ እድገትና የብቃት ጉዞ የሚያሳይ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ ለአካባቢ ጥበቃ ተስማሚ የአቪዬሽን፣ ዘመናዊ የሎጂስቲክስ ስርዓት እና በአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስር ወደላቀ አህጉራዊ ውህደት ለመሸጋገር በትጋት እንሰራለን ብለዋል፡፡ ለአየር መንገዱ ስኬታማ ጉዞ አስተዋጽኦ ላደረጉ የቀድሞና የአሁኑ መሪዎች፣ ፓይለቶች፣ መሐንዲሶችና ለመላው ሰራተኞች ምስጋና አቅርበዋል። አየር መንገዱ በአምስት አህጉራት፣ በ82 ሀገራት እና በ140 መዳረሻዎች በረራ በማድረግ ሰዎችን በማገናኘትና ባህላዊ ትስስር በመፍጠር ረገድ አስደናቂ ሚና እየተወጣ መሆኑ ይታወቃል። አየር መንገዱ ላለፉት 80 ዓመታት ዘመናዊ አውሮፕላኖችን በመጠቀም በአፍሪካ ሰማይ ላይ ቀዳሚ ነው።
በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን እያደረጉ ነው
May 14, 2026 89
ሀዋሳ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡-በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን እያደረጉ መሆኑን የሲዳማ ክልል የእርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ ገለጹ። "ከተረጂነት ወደ ምርታማነት" በሚል መሪ ሃሳብ በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እና በግብርና ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በሐዋሳ ከተማ ተካሄዷል። በመድረኩ ላይ የተገኙት የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ኃላፊ መምሩ ሞኬ፤ በክልሉ አዳዲስ የግብርና ኢንሼቲቮች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛሉ ብለዋል። በተለይም በሰብል ልማት፣ በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በእንስሳት ሀብት ልማት በስፋት ስለመሰራቱ አንስተዋል። በመሆኑም በክልሉ በግብርናው ዘርፍ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች በቤተሰብ ደረጃ በምግብ ራስን የመቻል ጥረትን እውን እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሸን ኮሚሽነር ወገኔ ብዙነህ፤ እንደ ሀገር የተያዙ በምግብ ራስን የመቻል ግቦችን በመከተል በክልሉ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ እና ውጤትም እየተገኘባቸው ነው ብለዋል። በዚህም ከጥቂት ዓመት በፊት እህል ሲሰፈርላቸው የነበሩ በርካታ አርሶ አደሮች ከችግርና ድህነት የወጡ መሆኑን አንስተው በክልሉ የተጀመሩ የግብርና ልማት ኢንሼቲቮች በስፋት የሚቀጥሉ መሆኑን ተናግረዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር ለማ መሰለ (ዶ/ር)፤ በበኩላቸው በክልሉ ለአደጋ ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም የመገንባት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የክልሉን ልዩ ፀጋና አቅም በመለየት በተሰሩ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎች ለሀገር የተረፉ የግብርና ምርቶች እየተመረቱ ይገኛሉ ብለዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የቡና ላኪነት ሚና ይበልጥ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥታለች
May 14, 2026 126
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የቡና ላኪነት ሚና ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂ ተግባራዊ በማድረግ በትኩረት እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ ገለጹ። ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት የአፍሪካ ቡና ጉባኤን ለማስተናገድ የሚያስችላትን ስምምነት ከኢንተር-አፍሪካ የቡና ድርጅት (Inter-African Coffee Organization) ጋር ተፈራርማለች። ስምምነቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሀደራ አበራ እና የኢንተር-አፍሪካ የቡና ድርጅት ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ሰለሞን ሩቴጋ ፈርመውታል። አምባሳደር ሀደራ በወቅቱ እንደገለጹት፤ አፍሪካ በቡና ምርት የታደለች አህጉር ብትሆንም ከዘርፉ ተገቢውን ጥቅም ሳታገኝ ቆይታለች። ቡና ለኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ዕድገትን ከማረጋገጥ ባለፈ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ሕይወታቸውን የሚመሩበት ዋና የግብርና ምርት መሆኑን አብራርተዋል። ኢትዮጵያ በቡና ዘርፍ ውጤታማ የሚያደርጓትን የተለያዩ ተግባራት በትኩረት እያከናወነች እንደሚገኝ ሚኒስትር ዴኤታው ገልጸው፤ እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላትን የቡና ላኪነት ሚና ለማሳደግ የሚያስችል ስትራቴጂን ተግባራዊ አድርጋ እየሠራች ነው ብለዋል። በዘርፉ የተሰማሩ አርሶ አደሮችን ምርታማነት ለማሳደግ፣ አቅማቸውን መገንባትና የቡና ጥራትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል። ስምምነቱ ኢትዮጵያ ከኢንተር-አፍሪካ የቡና ድርጅት ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር መሆኑን ጠቁመው፤ በቀጣይም 25 ቡና አምራች የአፍሪካ ሀገራት የሚሳተፉበትን ይህንን ጉባኤ በተሳካ ሁኔታ ለማስተናገድ ኢትዮጵያ ሙሉ ቁርጠኛ መሆኗን አረጋግጠዋል። የኢንተር-አፍሪካ የቡና ድርጅት ዋና ጸሐፊ አምባሳደር ሰለሞን ሩቴጋ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ይህንን ትልቅ የአፍሪካ የቡና ጉባኤ ለማስተናገድ በመስማማቷ ድርጅታቸው የተሰማውን ከፍተኛ ደስታ ገልጸዋል። ዋና ጸሐፊው አክለውም፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ያላት የቡና ተወዳዳሪነትና ያካበተችው ሰፊ ልምድ ጉባኤው ስኬታማ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ያላቸውን እምነት ገልጸው፤ ለዝግጅቱ መሳካት ድርጅታቸው አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለጹት፤ በአፍሪካ ውስጥ ኢትዮጵያን ጨምሮ 25 ቡና አምራች ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት በመገናኘት የቡና ምርትና ምርታማነትን በተመለከቱ አጀንዳዎችና በዘርፉ ላይ በሚስተዋሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ በመምከር የመፍትሔ አቅጣጫ ሲያስቀምጡ ቆይተዋል። ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት በቡና ዘርፍ ላይ የሚመክር ስብሰባ የምታስተናግድ መሆኗ ሀገሪቱ ከዘርፉ ማግኘት የሚገባትን ጥቅም እንድታገኝና ልምዷን ለሌሎች ሀገራት እንድታካፍል ትልቅ በር ይከፍታል ነው ያሉት። በተጨማሪም አፍሪካውያን ነጻ የንግድ ቀጣናን ተጠቅመው እርስ በእርስ ቡና መገበያየት የሚችሉበትን ምቹ መድረክ እንደሚፈጥርም አመልክተዋል። ዝግጅቱ የሀገሪቱን የቱሪዝም ዘርፍ ከማነቃቃት ባለፈ የኢትዮጵያን ልዩ ልዩ የቡና ዝርያዎችና ባህላዊ የቡና አፈላል ሥርዓት ለዓለም ይበልጥ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ እንደሚፈጥር አስገንዝበዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የምርምር ማዕከሉ የመድኃኒት ምርምርና ስርጸት ውጤታማነትን የሚያሳድግ አዲስ አቅም እየፈጠረ ነው
May 14, 2026 131
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የተገነባው የምርምር ማዕከል የመድኃኒት ምርምርና ስርጸት ውጤታማነትን የሚያሳድግ አዲስ አቅም መፍጠሩን የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር መሳይ ወልደማርያም ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በዘመናዊ መልክ የተገነባውን የምርምር ማዕከል መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም መርቀው ሥራ አስጀምረዋል። በአርማወር ሐንሰን የምርምር ተቋም ቅጥር ግቢ የተገነባው ዘመናዊ ተቋም ከመሠረተ ልማት ግንባታ ባለፈ፤ ራሷን የቻለችና ጤናማ የሆነች ኢትዮጵያን ዕውን ለማድረግ የሚተጋ የላቀ የዕውቀት ማዕከል ነው። የምርምር ማዕከሉም 40 ላቦራቶሪዎችን፣ የላቁ የጂኖሚክስ እና የባዮ ኢንፎርማቲክስ፣ በሀገር ውስጥ የሚመረቱ መድኃኒቶችን ጥራትና ብቃት የሚያረጋግጥ የባዮ ኢኩዊቫለንስ ማዕከላትን አካቷል። የተለያዩ የመድኃኒት አምራች ኩባንያዎችም በአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት በዘመናዊ መልክ የተገነባውን የምርምር ማዕከል ጎብኝተዋል። የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር መሳይ ወልደማርያም፤ ጉብኝቱ የሚበለፅጉ የምርምር ውጤቶች ሽግግር ውጤታማነትን ለማስጠበቅ ያለመ ነው ብለዋል። ማዕከሉ የመድኃኒት ምርምርና ስርጸት ተወዳዳሪነትን በማሳደግ ከፍተኛ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል። በማዕከሉም የመድኃኒት ምርምርና ስርጸት ሥራዎችን በላቀ መንገድ ማከናወን የሚያስችል አዲስ አቅም መፍጠር እንደተቻለ ተናግረዋል። በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛው የመድኃኒት ተነጻጻሪነት ፍተሻ በማዕከሉ መገንባቱም ከኢትዮጵያ ባሻገር ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር የላብራቶሪ አገልግሎት መስጠት እንደሚያስችል አንስተዋል። የአርማወር ሐንሰን የምርምር ኢንስቲትዩት የሀገር በቀል ዕውቀቶችን መነሻ በማድረግ የተለያዩ በሽታዎችን ሕክምና መስጠት የሚያስችሉ ስምንት የምርምር ውጤቶች መበልፀጋቸውን ገልጸዋል። በምርምር የበለፀጉ ውጤቶችም እንደ ዋና ንጥረ ነገር የሚያገለግሉና ክትባትን በተሻሻለ ቴክኖሎጂ መስጠት የሚያስችሉ መሆናቸውን አስረድተዋል። የኢትዮጵያ መድኃኒት አምራቾች ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶክተር ታደሰ ተፈሪ፤ በኢትዮጵያ በፖሊሲ ማዕቀፍና በተለያዩ የማሻሻያ እርምጃዎች የተሻለ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ገልጸዋል። የምርምር ማዕከሉም የኢትዮጵያን የጤና ዘርፍ የጥናትና ምርምር ውጤታማነት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑን ተናግረዋል። የአዲስ አበባ ከተማ የባህል ሕክምና አዋቂዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት መጋቤ ጥበብ መሪጌታ መንግስቱ ደስታ በበኩላቸው፤ ማዕከሉ የባህል ሕክምና ውጤታማነትን ለማሳደግ ከፍተኛ እገዛ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። ማዕከሉ በዘርፉ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎችን የሚያግዝ መሆኑን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ አነስተኛ መድኃኒት አምራቾች ዘርፍ ማኅበር ፕሬዝዳንት ሀሺም አሕመድ ናቸው። የዜኒት ገብስ እሸት ኢትዮጵያ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሰለሞን ገብረእግዚእ በበኩላቸው፤ በማዕከሉ የተፈጠረው የምርምር ምኅዳር የመድኃኒት አምራቾችን አቅም ለማጎልበት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሮች እያሰራጨ ነው
May 14, 2026 221
አሶሳ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ ከአሶሳ ዩኒቨርሲቲ ያገኟቸው የተሻሻሉ የእንስሳት ዝርያዎች በእንስሳት እርባታ ስራቸው የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸው በአሶሳ ዞን የኡራ ወረዳ አርሶአደሮች ተናገሩ። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማዕከል የተሻሻሉ የፍየል ዝርያዎችን በኡራ ወረዳ ለሚገኙ አርሶአደሮች አሰራጭቷል። ዩኒቨርሲቲው በረጅም ጊዜ ምርምር ያገኛቸውና ለአርሶ አደሮቹ ያሰራጫቸው ፍየሎች በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ መንታ ግልገሎችን የሚወልዱና በሽታን የሚቋቋሙ መሆናቸውም ተገልጿል። ፍየሎቹን የተረከቡት የወረዳው አርሶአደሮች ለኢዜአ እንደሚሉት፤ የእንስሳት ዝርያዎቹ በምርታማነታቸውም ሆነ በሽታን በመቋቋም ረገድ ካሏቸው ጠቀሜታ አንጻር የኑሮ ደረጃቸውን ለማሻሻል ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ። የተሻሻሉ የፍየል ዝርያ ማግኘታቸው የእንስሳት እርባታ ዘርፍን በሳይንሳዊ መንገድ በማከናወን የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርጋቸውም ተናግረዋል። አርሶአደር ዘካሪያ መርሱቅ እና ዘይነብ መኮነን በአሁኑ ወቅት የሚያረቧቸውን ፍየሎች አስፈላጊውን እንክብካቤ እያደረጉላቸው እንደሆነ ገልፀው ከዩኒቨርሲቲው ያገኟቸው ፍየሎች ደግሞ የእንስሳት እርባታ ስራቸውን በተሻለ መልኩ ለመስራት ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል። ለፍየል ዝርያዎቹ አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግና አብዝተው በማርባት ከራሳቸው ባለፈ ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ተደራሽ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውንም ገልጸዋል። ሌላው አርሶአደር ሙሐመድ ሳሌ በበኩላቸው፤ ከዩኒቨርሲቲው ባገኙት የተሻሻለ የፍየል ዝርያ በእንስሳት እርባታ ዘርፍ በስፋት ለመሰማራት ማቀዳቸውን ተናግረዋል። የእንስሳት መኖ እና መጠለያ በማዘጋጀት ከወዲሁ በእርባታው ዘርፍ ውጤታማ ለመሆን እየሰሩ መሆናቸውንም አብራርተዋል። የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተሻሻሉ የሰብል እና የእንስሳት ዝርያዎችን ለአርሶአደሩ በማድረስ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር አዎንታዊ ሚና እየተጫወተ ነው ያሉት ደግሞ የኡራ ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታጀዲን ሙሐመድ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው ከዚህ በፊት በምርምር ያወጣቸው የጤፍ ዝርያ የወረዳውን አርሶአደሮች ተጠቃሚ ያደረገ መሆኑን ጠቁመው፤ አሁንም የእንስሳት እርባታ ዘርፍን በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ የጀመረው የምርምር ስራ የሚደነቅ ነው ብለዋል። የተሻሻሉ የፍየል ዝርያዎችን የተረከቡ አርሶአደሮች ውጤታማ እንዲሆኑ የወረዳው አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።
የግለሰቦችን የግል መረጃ ለታለመለት ዓላማ ብቻ ማዋል የሚያስችል የተጠናከረ የግል ዳታ ጥበቃ እየተከናወነ ነው
May 13, 2026 288
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ተቋማት የግለሰቦችን የግል መረጃ ለታለመለት ዓላማ ብቻ ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያስችል የተጠናከረ የግል ዳታ ጥበቃ እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ባልቻ ሬባ ገለጹ፡፡ የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1321/2016 ትግበራና አፈጻጸምን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ባልቻ ሬባ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ ተቋሙ በህግ በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ለግለሰቦች መረጃ የግል ዳታ ጥበቃ እየተደረገ ነው ብለዋል። በዓለም ላይ እየታየ የመጣው ፈጣን የቴክኖሎጂ ዕድገት ለአዋጁ መውጣት ምክንያት መሆኑን ገልጸው፤ የግል መረጃዎች በአግባቡ ካልተያዙ ላልተፈለገ ዓላማ በመዋል የግለሰቦችን መብት እንዲጣስ ያደርጋል ብለዋል፡፡ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ አካል የሆነው የግል ዳታ ጥበቃ ሀገራዊ ፖሊሲ ለመቅረጽና ስትራቴጅ ለመንደፍ ግብዓት ሆኖ እንደሚያገለግል ተናግረዋል። ተቋማትም የግለሰቦችን ዳታ ህጋዊ እና ሃላፊነት በተሞላበት አግባብ መጠቀም እና መጠበቅ እንዳለባቸው ገልጸዋል። የግለሰቦችን መረጃ ከታለመለት ዓላማ ውጭ የሚጠቀሙ ተቋማት ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር እንዳለ ገልጸው፤ ግለሰቦች የግል ዳታ ጥሰት ሲያጋጥማቸው ለተቆጣጣሪው አካል ሪፖርት የሚያደርጉበት ፖርታል ተዘጋጅቷል ብለዋል። በኢትዮጵያ አየር መንገድ የሳይበር ደህንነት ከፍተኛ ተንታኝ ቤተልሔም መንግስቱ አየር መንገዱ በግል ዳታ ጥበቃ ዙሪያ የካበተ ልምድ እንዳለው ገልጸዋል። በተቋሙ በየጊዜው በግል ዳታ ጥበቃ ማዕቀፉ ዙሪያ ለሰራተኞቹ ግንዛቤ እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የህግና ፖሊሲ ዳይሬክተር ሳሙዔል ዓለሙ፤ በሀገር አቀፍ ደረጃ 42 ሚሊዮን ዜጎች ብሔራዊ ድጂታል መታወቂያ መውሰዳቸውን ገልጸዋል። በምዝገባ ወቅት ከግለሰቦች የሚወሰዱ ዳታዎች ለታለመላቸው ዓላማ ብቻ እንዲውሉ ጥበቃ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር የዋና ዳይሬክተር ልዩ አማካሪ ፍቅረ ሥላሴ ጌታቸው በበኩላቸው፤ የግል ዳታ ጥበቃ ለዲጂታል ሽግግር መሰረት መሆኑን አንስተዋል። በግለሰቦችና ተቋማት መካከል መተማመን መፍጠር እንደሚያስችል አብራርተዋል፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ሳይንስ ሙዚየምን ጎበኙ
May 13, 2026 301
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በሳይንስ ሙዚየም ጉብኝት አድርገዋል። የሁለቱ ሀገራት መሪዎች በሳይንስ ሙዚየም ያደረጉት ጉብኝት፤ ለሁለቱ ሃገራት የመጪው ዘመን የላቀ ፈጠራ፣ ቴክኖሎጂ እና ከፊት ላሉ ሰፊ ዕድሎች ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ያንጸባረቁበት መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። ጉብኝቱ ተሻጋሪ ርዕይን የሰነቀ አጋርነት፤ ኢትዮጵያና ፈረንሳይ መጻኢ ጉዟቸው ብሩህ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑም ተገልጿል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት
May 14, 2026 87
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከብሩንዲ ጋር ለሚያደርገው ሁለተኛ ዙር የዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የሁለተኛ ቀን ልምምዱን ዛሬ አድርጓል። አሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ለ30 ተጫዋቾች ጥሪ በማድረግ ትናንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሜዳ ዝግጅታቸውን የጀመሩ ሲሆን ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ሁሉም ተገኝተው ልምምዳቸውን አከናውነዋል። በብሔራዊ ቡድኑ የሁለተኛ ቀን ዝግጅት ተጫዋቾች የእርስ በእርስ ጨዋታዎችን በማድረግ አቋማቸውን መፈተሻቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከብሩንዲ ጋር ግንቦት 16 የመጀመሪያ ጨዋታውን በሜዳው፣ የመልስ ጨዋታውን ግንቦት 23 ቡጁምቡራ ላይ ያከናውናል። 10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል። በውድድሩ ላይ 24 ሀገራት ይሳተፋሉ። በዓለም ዋንጫው አፍሪካ ሞሮኮን ጨምሮ በአምስት ሀገራት ትወከላለች። በማጣሪያ የሚያልፉ አራት የአፍሪካ ሀገራት በሶስት ዙሮች በሚደረጉ ጨዋታዎች ይለያሉ።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ሶስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
May 14, 2026 71
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ ሶስተኛ ቀኑን ባስቆጠረው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተለያዩ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ናቸው። ማምሻውን በተደረገው የ3000 ሜትር መሰናክል የወንዶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ገመቹ ጎዳና 8 ደቂቃ ከ41 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ወጥቷል። አትሌት ገመቹ ለኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ሶስተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል። በውድድሩ ላይ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሳሙኤል ፍሬው ሶስተኛ በመውጣት የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት ሆኗል። በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ አትሌት ምስጋና ኃይሉ እና በ400 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት አጃይባ አልዩ የወርቅ ሜዳሊያ ማግኘታቸው ይታወቃል። ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው ሶስት የወርቅ፣ አንድ የብር እና ሶስት የነሐስ በድምሩ ሰባት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች። በጋና አክራ እየተካሄደ የሚገኘው 24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ ግንቦት 9 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
አንጋፋው የእግር ኳስ ሰው ጌታቸው ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
May 14, 2026 81
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች፣ ዓለም አቀፍ ዳኛ እና አመራር የነበሩት ጌታቸው ገብረማርያም ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ጌታቸው ገብረማርያም በተጫዋችነት ለኦሜድላ እና ጥጥ ማኅበር እንዲሁም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫውተው ያሳለፉ ሲሆን በመቀጠል ለረጅም ዘመናት በዓለም አቀፍ ዳኝነት ጭምር በሚታወቁበት የዳኝነት ሙያ አገልግለዋል። ከዳኝነት ከተገለሉ በኋላም በኮሚሽነርነት፣ በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተለያዩ የሥራ ኃላፊነቶች በጥቅሉ ከ60 ዓመታት በላይ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ላይ በማገልገል ማሳለፋቸውን ፌዴሬሽኑ ገልጿል። የአቶ ጌታቸው ገብረማርያም ሥርዓተ ቀብር ነገ በአማኑኤል ቤተ-ክርስቲያን ከቀኑ 9 ሰዓት ላይ ይፈፀማል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በአንጋፋው የእግር ኳስ ሰው ጌታቸው ገብረማርያም ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእግር ኳስ ቤተሰብ እና ለሙያ ባልደረቦች መፅናናትን ተመኝቷል።
በአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች
May 14, 2026 90
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 6/2018 (ኢዜአ)፦ በ24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። በ800 ሜትር ሴቶች ፍፃሜ አትሌት ምስጋና ኃይሉ 1 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ ከ02 ማይክሮ ሴኮንድ በመግባት አንደኛ ወጥታለች። ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች። ትዕግስት አያና ስድስተኛ እና ሀብታም ገበየሁ ሰባተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። በ400 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት አጃይባ አልዩ የመጀመሪያውን ወርቅ ለኢትዮጵያ ማስገኘቷ ይታወቃል። በ800 ሜትር ፍጻሜ ቦትስዋናዊቷ ኖዌ ኦራቲሌ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ስትጨርስ የኒጀሯ አትሌት ቡባከር ሰሚራ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች። ኢትዮጵያ እስከ አሁን በሻምፒዮናው ሁለት የወርቅ፣ አንድ የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ አራት ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
አካባቢ ጥበቃ
የዱር እንስሳትን እና መኖሪያ አካባቢያቸውን የመጠበቅና የማልማት ሥራ ይጠናከራል
May 14, 2026 313
ሮቤ፤ ግንቦት 6/2018(ኢዜአ)፦ የዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸውን በመጠበቅና በማልማት ለቱሪዝም መስህብነት የማዋል ሥራው እንደሚጠናከር የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ገለጸ። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ጥበቃን ይበልጥ ለማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ሁለተኛው ዙር የዱር ሕይወት ጠባቂዎች (ሬንጀሮች) ምረቃ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩመራ ዋቅጅራ እንደገለጹት፤ የዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸውን በመጠበቅና በማልማት ለቱሪዝም መስህብና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የማዋል ሥራ በትኩረት እየተከናወነ ነው። ባለስልጣኑ የሀገሪቱን የተፈጥሮ ጸጋዎች ለላቀ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማዋል፣ የዱር እንስሳትንና መኖሪያ አካባቢያቸውን የመጠበቅና የማልማት ሥራን በልዩ ትኩረት እያከናወነ መሆኑን አስታውሰው፣ ይህም የቱሪዝም መስህብነትን በማሳደግ ረገድ ጉልህ ሚና ይኖረዋል ብለዋል። ባለሥልጣኑ ባለፉት ስልሳ ዓመታት የዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸው ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፉ የተለያዩ የጥበቃና የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን እንደቆየና ይህም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል። በፓርኮች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ ተፅዕኖዎችን በመከላከል የጥበቃና የልማት ሥራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር በተከናወኑ ሥራዎች አበረታች ለውጦች እየተመዘገቡ መምጣታቸውንም አመልክተዋል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክን ለማልማትና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታውን ይበልጥ ለማሳደግ እየተከናወኑ ያሉ የኢኮ-ቱሪዝምና ሌሎች የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች የጥረቱ ማሳያዎች እንደሆኑም አንስተዋል። ዋና ዳይሬክተሩ እንዳሉት፣ የዱር ሕይወት ጠባቂዎች (ሬንጀሮች) መመረቅ በዘርፉ የሚታዩ ህገወጥ ተግባሮችን ለመከላከልና የተፈጥሮ ኃብት ጥበቃ ሥራውን ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችል ነው። የዱር እንስሳትና የመኖሪያ አካባቢያቸውን ከጥፋት ለመታደግ ከዘላቂ የቱሪዝም ልማት ጋር በማጣመር ለኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲውሉ ማድረግ ይገባል ሲሉም ዳይሬክተሩ አመልክተዋል። የባሌ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም ኃይሌ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ብሔራዊ ፓርኩን ከተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ለመከላከል ከፓርኩ አስተዳዳርና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር እየተሰራ ነው። በዚህም ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ ተግዳሮቶች እየቀነሱ፤ የጥበቃና የልማት ተግባራትም እየተሻሻሉ መጥተዋል ብለዋል። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ኃላፊ ሻሚል ከድር በበኩላቸው፤ በፓርኩ ለሦስት ወራት በጥበቃና ሌሎች መሰል ሥራዎች ላይ ስልጠና የወሰዱ 44 ሬንጀሮች መመረቃቸውን ገልጸዋል። ሬንጀሮቹ በጥበቃ ሳይንስ፣ በስና ምግባር፣ በአካል ብቃትና ሌሎች ክህሎቶችን ማግኘታቸውን ተናግረዋል። ተመራቂ ሬንጀሮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፤ የወሰዱት በተግባር የተደገፈ ዘመናዊ ሥልጠና በእውቀት ላይ የተመሰረተ የጥበቃ ሥራን ለማከናወን እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል። ለሥልጠናው መሳካት አስተዋጽኦ ለነበራቸው አካላት እውቅናና የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን የተለያዩ ባለድርሻ አካላትም ፓርኩን ጎብኝተዋል። በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ሆኖ የተመዘገበው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ የደጋ አጋዘን፣ ቀይ ቀበሮና ሌሎች በርካታ የዱር እንስሳትና ዕጽዋት መገኛ ነው።
ማዕከሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በግብርና ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ እያገዘ ነው
May 13, 2026 275
ጂንካ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፡-የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በግብርና ዘርፍ ተጨባጭ ለውጥ እንዲመጣ ማገዙን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አለማየሁ ባውዲ ገለጹ። የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ አለማየሁ ባውዲና ሌሎች አመራሮች የማዕከሉን የሥራ እንቅስቃሴ ዛሬ ጎብኝተዋል። በዚህ ወቅት አፈ ጉባኤው እንዳሉት፣ የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል የአርሶና የአርብቶ አደሩን ችግር የሚፈቱና ምርታማነትን የሚያሳድጉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅና በማላመድ በዘርፉ ተጨባጭ ውጤት እያመጣ ነው። ማዕከሉ በግብርናው ዘርፍ እያከናወነ ያለው የጥናትና ምርምር ሥራ በክልሉ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ እየተደረገ ላለው ጥረት ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱንም ገልጸዋል። ማዕከሉ ያፈለቃቸውን የግብርና ቴክኖሎጂዎች ወደ አርሶና አርብቶ አደሩ በማውረድ ግብርናውን ለማዘመንና የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራትንም አጠናክሮ እንዲቀጥል አስገንዝበዋል። የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ወላይቴ ቢቶ በበኩላቸው፣ የምርምር ማዕከሉ ተግባር በተለይም በቆላማ አካባቢዎች በመስኖ ልማት የአርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሳደግ እና የምግብ ዋስትናውን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በቆላማ አካባቢዎች በመስኖ ልማት የመጣውን ተጨባጭ ለውጥ በማስፋት ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለመሸጋገር የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት ማዕከሉ የጀመረውን እገዛ ሊያጠናክር ይገባል ሲሉም አስገንዝበዋል። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር አብዮት ሙላቴ (ዶ/ር) የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ በግብርና ዘርፍ ተጨባጭ ውጤት እንዲመዘገብ እያገዘ መሆኑን አንስተዋል። በክልሉ ቀደም ሲል በሰብል ልማት በሄክታር ከ30 ኩንታል ያነሰ ምርት ይገኝ እንደነበር አስታውሰው፣ የምርምር ማዕከላት የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ ማላመዳቸውን ተከትሎ በሄክታር ከ40 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት ተችሏል ብለዋል። ለውጤቱ በአነስተኛ ቦታ ብዙ ምርት ማግኘት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ማድረግ መቻሉ ሌላው ምክንያት መሆኑንም ጠቅስዋል። እንደ አብዮት (ዶ/ር) ገለጻ፣ ማዕከሉ የሩዝ ምርት ባልተለመደባቸው አካባቢዎች ጭምር የሩዝ ልማትን በማላመድና በማስፋፋት ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል። የጂንካ ግብርና ምርምር ማዕከል ዋና ዳይሬክተርና የሰብል ተመራማሪ ተክሌ ዮሴፍ (ዶ/ር) በበኩላቸው የምርምር ማዕከሉ የተጣለበትን ተልዕኮ በብቃት ለመወጣት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ከማዕከሉ የሚወጡ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችና የምርምር ውጤቶችን በአርሶና አርብቶ አደሩ ማሳ በማስፋት ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደተቻለም አመልክተዋል። ማዕከሉ በተለይም በዝናብ አጠር አካባቢዎች በመስኖ የሚለሙ እና ምርትን በእጥፍ የሚያሳድጉ የሰብል ዝርያዎችን እያላመደ መሆኑን ጠቁመው፣ ይህም በአርብቶ አደሩ አካባቢ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለውን ጥረት ያግዛል ብለዋል ።
ዩኒቨርሲቲው ሳይንሳዊ የብዝሃ ደን ልማት ስራን የሚደግፍ የዘር ባንክ ሊያቋቁም ነው
May 12, 2026 386
ጎንደር፤ ግንቦት 4/2018 (ኢዜአ)፡- ጎንደር ዩንቨርሲቲ ሳይንሳዊ የብዝሃ ደን ልማት ስራን የሚደግፍ ሀገር በቀል የደን ዛፎች የዘር ባንክ ለማቋቋም የሚያስችሉ ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አስታወቀ። በዩኒቨርሲቲው የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የደን ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ አስማማው ዓለሙ (ዶ/ር) እንደገለጹት የሚቋቋመው የዘር ባንክ የሚስተዋለውን የደን ዘር ጥራትና አቅርቦት ችግር የሚፈታ ነው። የዘር ባንኩ መቋቋም ችግኞች ለአካባቢው ስነ ምህዳር ተስማሚነታቸውን በምርምር በማረጋገጥ የጽድቀት መጠናቸውን ለማሻሻል አስፈላጊ መሆኑን አመላክተዋል። በተጨማሪም በሽታን፣ ተባይንና ድርቅን በመቋቋም ከአካባቢው ጋር በፍጥነት ተላምደው ውጤታማ መሆን የሚችሉ የደን ዛፍ ዝርያዎችን ለማቆየት የሚያስችል መሆኑን ጠቁመዋል። የዘር ባንኩ በምርምር ጣቢያዎች ተሞክረውና የጥራት ደረጃቸው በቤተ -ሙከራ ተፈትሾ ያለፉ የደን ዛፍ ዘሮችን በሳይንሳዊ መንገድ ጠብቆ ለማቆየት አጋዥ ሚና ይጫወታል ሲሉም አክለዋል። በዚህም የሀበሻ ጽድ፣ የኮሶ ዛፍ፣ ዋንዛ፣ ወይራና የአካሽያ ግራር የመሳሰሉ የደን ዛፎችን በሳይንሳዊ መንገድ በመንከባከብ ዘር የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል። እስካሁን በተሰራው ስራም 13 አይነት የዛፍ ዝርያዎችን በማላመድ በአሁኑ ወቅት 254 ኪሎ ግራም ዘር በከተማዋ በተቋቋሙ የችግኝ ጣቢያዎች እንዲፈሉ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል። በተጨማሪም በከተሞች የኮሪደር ልማት የአረንጓዴ የጥላ ዛፍ ችግኞችን ለማቅረብ የሚያስችል ሰርቶ ማሳያ በማቋቋም ላይ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡ በአካባቢው ጥራት ያለው ዘር አቅራቢ ኢንተርፕራይዝ ባለመኖሩ ለደን ልማት ስራው እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል ያሉት ደግሞ በዩኒቨርሲቲው የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ካህሌ ጀንበር (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የዘር ባንኩ መቋቋም እንደ ሀገር እየተካሄደ የሚገኘውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ስኬታማና ውጤታማ ለማድረግ የሚያግዝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል
May 11, 2026 463
አዲስ አበባ፤ግንቦት 3/2018 (ኢዜአ)፡-73ኛው የታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የአየር ንብረት ትንበያ ፎረም (GHACOF 73) ግንቦት 10 እና 11 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይደረጋል። ፎረሙ የሚካሄደው “የአየር ንብረት አገልግሎቶች፤ ለአይበገሬነት እና ዘላቂ ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን(ኢጋድ) የአየር ንብረት ትንበያ እና የመተግበሪያ ማዕከል(ICPAC) ከልማት አጋሮች ጋር በመሆን ፎረሙን እንዳዘጋጀው ተገልጿል። ስብሰባው ትንበያ ከመስጠት ባለፈ ትንበያዎቹን ወደ ተግባር መቀየር እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ ዝግጅት እርምጃዎችን ማጠናከርን ያለመ ነው። የአየር ንብረት መረጃዎች አርሶ አደሮች ፣ የጤና ባለሙያዎችን እና የአደጋ ስጋት አመራሮችን በቀጥታ እንዲደግፉ ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢጋድ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። በብሔራዊ የሚቲዎሮሎጂ ተቋማት መካከል ያለውን ትብብር ማጠናከር ሌላኛው የመወያያ አጀንዳ ነው። መድረኩ ለታላቁ የአፍሪካ ቀንድ ግብርና እና የውሃ ሀብት ወሳኝ የሆነውን ከእ.አ.አ ከጁን እስከ ሴፕቴምበር 2026 ያለውን የዝናብ ወቅት ትንበያ ይቀርብበታል። ሚኒስትሮች፣ የምርምር ተቋማት፣ ሰብአዊ ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማህበራት እና የግል ባለሀብቶች ይሳተፋሉ።ይህ የተሳታፊዎች ስብጥር ሳይንስን ከፖሊሲ ጋር ለማገናኘት የታለመ ነው። የአየር ንብረት መዛባት የሩቅ ስጋት መሆኑ ቀርቶ በደጃፋችን ላይ ያለ ተጨባጭ አደጋ ነው ያለው ኢጋድ ፎረሙ በታላቁ የአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ ማህበረሰቦች በቂ መረጃ እንዲኖራቸውና አስቀድመው ዝግጁ እንዲሆኑ ማስቻል ላይ ትኩረቱን ያደረገ መሆኑን አመልክቷል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ ነው
May 13, 2026 292
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሕብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ በጸጥታ፣ በዘላቂ ልማት እና በሰብአዊ መብቶች ዙሪያ ያላቸውን ትብብር ይበልጥ ተቋማዊ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመዋል። ስምምነቱን የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ፈርመውታል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በዚሁ ወቅት በሰጡት መግለጫ፣ የአፍሪካ ህብረት ለታዳጊው ዓለም የፍትህ ድምፅ እና ለባለብዙ ወገን ግንኙነት ዋነኛ መገለጫ መሆኑን ገልጸዋል። አጋርነታቸውን ይበልጥ ተቋማዊ የሚያደርገው ይህ ስምምነት በቁልፍ ዘርፎች ላይ የተመዘገቡ ስኬቶችንና የወደፊት ዕቅዶችን መነሻ ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል። አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ በቋሚ አባልነት አለመካተቷን ታሪካዊ ኢ-ፍትሃዊነት ነው ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ይህም የምክር ቤቱን ተቀባይነትና ውጤታማነት እንደሚጎዳው አስገንዝበዋል። በተጨማሪም ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ሊስተካከል እንደሚገባ ጠቅሰው አፍሪካ ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወጥታ ለአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር የማምረቻና የማጣሪያ ማዕከል መሆን እንዳለባት ጠቁመዋል፡፡ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በበኩላቸው፣ የአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ እና የተባበሩት መንግሥታት የ2030 አጀንዳ የተጣጣሙ መሆናቸውን ገልጸዋል። በአፍሪካ ቀንድ ያሉ ፈተናዎችን ለመፍታት በቅርበት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ማሻሻያ ተደርጎ የአፍሪካ ሀብቶች ጥቅም ላይ እንዲውሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በናይሮቢ የተካሄደው የ"አፍሪካ ፎርዋርድ" (Africa Forward) ጉባኤ ውጤቶች ክትትል እንዲደረግባቸው አሳስበዋል፡፡ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር መብትን ጨምሮ ቋሚ መቀመጫና ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት የሚለውን የአህጉሪቱን ጥያቄ በድጋሚ አረጋግጠዋል። ይህ ስምምነት በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ስልታዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚያሸጋግረው ይጠበቃል። 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄዱ ይታወቃል፡፡
አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ነው
May 13, 2026 304
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረግ የዓለም አቀፍ ተቋማትን ኢ-ፍትሐዊነት የሚያንጸባርቅ ተግባር መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት እየተካሄደ ነው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የመንግስታቱ ድርጅት በሁሉም ዘርፎች ቀዳሚ ተግባር አፍሪካን የማድረግ የፖለቲካም ሆነ የሞራል ግዴታ አለበት። አፍሪካ አህጉራዊ ግጭቶችን በማርገብ፣ አህጉራዊ ዕድገትና ብልፅግናን ለማረጋገጥ የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ፤ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣናና ሌሎች የሰላምና ጸጥታ ኢኒሼቲቮች አስደናቂ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ በዓለም ሁለንተናዊ እንቅስቀሴ ላይ ያላት ሚና የጎላ መሆኑን እንገነዘባለን ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ በታሪክና በዓለም ኢ-ፍትሐዊ አሰራር የደረሰባትን በደል ለመቀልበስ የምታደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት ከቅኝ ግዛት ባልወጡበት ወቅት የተቋቋሙ ዓለም አቀፍ ተቋማት አህጉሪቱ በፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ መቀመጫ እንዳይኖራት ማድረጋቸው ተገቢ አለመሆኑን ገልጸዋል። አፍሪካ ባልተሳተፈችበት የተቋቋሙ የዓለም አቀፍ ተቋማት ኢ-ፍትሐዊነት አፍሪካን ብዙ አሳጥቷታል ያሉት ዋና ጸሀፊው፤ አፍሪካዊ ችግሮችን በአፍሪካ ለመፍታት የተጀመሩ ኢንሼቲቮችን መደገፍ እንደሚገባ ተናግረዋል። የመንግሥታቱ ድርጅት አፍሪካዊ ግጭቶች በአፍሪካ ማዕቀፍ እንዲፈቱ በመሪነት ከመሳተፍ ባለፈ የአፍሪካ ሕብረትን ጥረት እንደሚደግፍ ጠቁመዋል። አፍሪካ በወሳኝ ማዕድናትና በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ትልቅ አቅም እንዳላት ገልጸው፤ ሀብቷን እሴት በመጨመር ለዓለም ገበያ የምታቀርብበትን መንገድ መቀየስ ይገባል ብለዋል።
አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም ለማቋቋም ወሰነች
May 13, 2026 228
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ አፍሪካ ለ2030 እና አጀንዳ 2063 ግቦች የሚያስፈልጋትን የልማት ፋይናንስ ለማግኘት የተዛባውን የዓለም የፋይናንስ ስርዓት የሚያጣጥም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (African Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ሕብረትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 10ኛ ዓመታዊ ኮንፍረንስ በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እየተካሄደ ነው። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀ-መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ መድረኩ በአፍሪካ ሰላምና ጸጥታ፣ ዘላቂ ልማት፣ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ አስተዳደርና በተለዋዋጭ ዓለም የአፍሪካ ፈተናዎች ዙሪያ የሚያተኩር ነው። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነትን ጨምሮ የዓለም ነባራዊ ሁኔታ በአሕጉሪቱ ላይ የሚያደርሰውን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚደረግ ጥረት ቢኖርም በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች የሚሰቃዩበትና የሚሰደዱበት አስቸጋሪ ሁኔታ ተፈጥሯል ብለዋል። ይሄውም በአፍሪካ አስተማማኝና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት በሚደረገው ጥረት ላይ እንቅፋት እየፈጠረ መሆኑን በመጥቀስ፣ ከጸጥታ ባለፈ በመልካም አስተዳደር፣ በልማትና የማይበገር ኢኮኖሚ በመገንባት አስቻይ ሁኔታ መፍጠር እንደሚገባ ገልጸዋል። በአፍሪካ የልማት ፋይናንስ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን የገለጹት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር፤ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ አስተዳደር የአጀንዳ 2063 እና 2030 ግቦችን ለማሳካት እንቅፋት ፈጥሯል ብለዋል። በተለይም ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የተቋቋሙና አሁንም ያለው ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ለአፍሪካ ፍላጎትና እውነታ ምላሽ የማይሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል። በመሆኑም አፍሪካን ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ስርዓት ጋር ለማጣጣም የራሷን የብድር ደረጃ መመጠኛ ተቋም (Africa Rating Agency) ለማቋቋም መወሰኗን ገልጸዋል። ይሄውም የአፍሪካ ሕብረት በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ሲሰራ ቆይቶ እ.አ.አ በመጪው ሰኔ ወር 2026 በሞሪሼስ በይፋ እንደሚጀመር አስታውቀዋል። የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በአፍሪካ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩን ገልጸው፤ በብዙ ሀገራት የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ንሯል፤ በአንዳንድ ሀገራት የነዳጅ ዋጋ ከ100 እስከ 150 በመቶ ጨምሯል ነው ያሉት። የአፍሪካ ሕብረት ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጋር በትብብር ሲሰራ መቆየቱን በመጥቀስ፣ የእርስ በርስ ትብብሩን ለማጠናከር በቅርበት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል። ሁለቱ ተቋማት አጋርነታቸውን ማጠናከር እንዳለባቸው በመግለጽ፤ በተቋማቱ መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ትብብር ወደፊት ማሻገር ያስፈልጋል ብለዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በአዲስ አበባ ይካሄዳል
May 13, 2026 269
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 5/2018(ኢዜአ)፦ 10ኛው የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የከፍተኛ ደረጃ ውይይት በሕብረቱ ዋና መቀመጫ ዛሬ በአዲስ አበባ ይደረጋል። በውይይቱ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እንደሚገኙ ይጠበቃል። ውይይቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል በአፍሪካ ልማት እና በዓለም አቀፍ አስተዳደር ዙሪያ ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማጠናከርን ያለመ ነው። በሁለቱ ድርጅቶች መካከል ያለውን ቅንጅት፣ የጋራ ተጠያቂነት እና ትብብርን በልማት፣ በአስተዳደር፣ በሰብአዊ ድጋፍ እና በሰላም ግንባታ ቅድሚያ በሚሰጣቸው ጉዳዮች ያላቸውን ትስስር ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ይካሄዳል። በዚህ የከፍተኛ ደረጃ ውይይት ላይ በርካታ ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች የሚዳሰሱ ሲሆን፣ በተለይም የአጀንዳ 2063 እና የሁለተኛው የአስር ዓመት ምዕራፍ የትግበራ ዕቅድ አፈፃፀምን ማፋጠን እንዲሁም አፍሪካን በዓለም አቀፍ ፖሊሲ እና አስተዳደር ውስጥ ያላትን ማዕከላዊ ሚና መጠበቅ በሚሉ አጀንዳዎች ላይ ትኩረት ያደርጋል። በተጨማሪም "ከጥገኝነት ወደ ሉዓላዊነት" የተሸጋገረ የልማት ፋይናንስ፣ የ2026 የአፍሪካ ሕብረት የዓመቱ መሪ ቃል የሆነው ዘላቂ የውሃ አቅርቦት እና የንጽህና አጠባበቅ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተቋማት ሪፎርም እና አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ያላትን ውክልና የተመለከቱ ጉዳዮች ውይይት ይደረግባቸዋል። መድረኩ ለአህጉራዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ማምጣት፣ የአገር ውስጥ ሀብት ማሰባሰብን ማሳደግ፣ የወጣቶች እና የሴቶች ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንዲሁም በአህጉራዊ እና በዓለም አቀፍ የልማት የቅድሚያ ትኩረቶች መካከል ያለውን ትስስር ማጠናከር ወሳኝ መሆኑ አጽንኦት የሚሰጥበት እንደሆነ ተመላክቷል። ከውይይቱ ከሚጠበቁ ውጤቶች መካከል የተሻለ ስትራቴጂካዊ ቅንጅት፣ ፍትሐዊ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሥርዓት ለውጥ፣ በአፍሪካ ህብረት የዓመቱ መሪ ቃል ዙሪያ ጠንካራ ቅንጅት መፍጠር እና በተባበሩት መንግሥታት ሥርዓት ውስጥ ፍትሐዊ የአፍሪካ ውክልና እንዲኖር የቀረቡ ጥሪዎችን ማጠናከር እንደሚገኙበት ህብረቱ ለኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ የውይይቱን ውጤቶች አስመልክቶ የጋራ መግለጫ ይሰጣሉ።
ሐተታዎች
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 10, 2026 668
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 2/2018 (ኢዜአ)፡- በዚህ ዝግጅታችን በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን በወፍ በረር በመቃኘት ማስታወስ ይሆናል። በመሆኑም በዚህ ሳምንት በሀገራችን ሁሉም ክልሎች ምን ምን ዋና ዋና ጉዳዮች ነበሩ ስንል እንጠይቃለን? የጠቅላይ ሚኒስትሩ ምልከታ- በሱሉልታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳምንቱ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱሉልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሄክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ሰብል ጎብኝተዋል። መንግሥት በግብርናው ዘርፍ በወሰዳቸው ስትራቴጂካዊ እርምጃዎች እየተገኙ ያሉ ውጤቶች አመርቂና ለቀጣይ ሥራዎች ስንቅ መሆናቸውን በጉብኝታቸው ወቅት ተናግረዋል። መሬት ጦም ማደር የለበትም በሚል ጽኑ እምነት የተጀመረው የበጋ ስንዴ ልማት አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ስለመሆኑም አንስተዋል። ከልመና ራሳችንን መገላገል አለብን፤ ሊታረስና ሊለማ የሚችል መሬት መታረስ አለበት በሚል ጽኑ እምነት የበጋ ስንዴ ልማት መጀመሩን አስታውሰው፤ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት አሁን ላይ አስደማሚ ውጤት እያስመዘገበ ይገኛል ብለዋል። የቱሪዝም ልማት የወፍ በረር ጉዟችን የቀጠለ ሲሆን ከሱሉልታ ቀጥታ ወደ አማራ ክልል ባህር ዳር አምርተናል። የባህር ዳር መዳረሻችን በጣና ሐይቅ ደቡባዊ ዳርቻ ላይ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ወጪ የተገነባው ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት ይሆናል። የሪዞርቱ ግንባታ ተጠናቆ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፤ ባሳምንቱ ተመርቆ በይፋ ስራ ጀምሯል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) "ገበታ ለሀገር" እቅድ መሰረት በሐይቁ ሌላኛው አቅጣጫ ከሚገኘው የጎርጎራ ብርሃን (ጎርጎራ ኢኮ ሪዞርት) ጋር በመቀናጀት የጣናን የቱሪዝም ቀጣና ለማነቃቃት አላማ በማድረግ ፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መገንባቱ ተመላክቷል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በባህርዳር ከተማ ቆይታቸው በ3 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር የሚገነባውን ፎር ፖይንትስ ባይ ሸራተን ጣና የሆቴል ፕሮጀክት ግንባታም አስጀምረዋል። በሚድሮክ ኢንቨስትመንት የሚገነባው ይህ ዓለም አቀፍ ሆቴልም በ18 ወራት ውስጥ ተገንብቶ የሚጠናቀቅ መሆኑ ታውቋል። የመልካ ቁንጡሬ ሁነት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ከኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀንን በዩኔስኮ በተመዘገበው በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ በሳምንቱ በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሯል። የአፍሪካ ዓለም አቀፍ የቅርስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ10ኛ ጊዜ፣ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ4ኛ ጊዜ በመልካ ቁንጡሬ–ባልጩት አርኪዮሎጂና ፓሊዮንቶሎጂ መካነ ቅርስ ስፍራ ተከብሯል። በዚሁ መርሃ ግብር ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ህይወት ኃይሉ፤ ባህላዊና የተፈጥሮ ቅርሶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን አስተዋጽኦ ለማጎልበት የሚያስችሉ ተግባራት ይቀጥላሉ ብለዋል። ሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ የሀዋሳ ሀይቅ ዳርቻ ልማት የዲዛይን ሥራ ተጠናቅቆ ለህዝብ ይፋ የተደረገውም በዚሁ ሳምንት ነው። የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በወቅቱ እንደገለጹት ከተማዋን ለኑሮ፣ ለስራ፣ ለቱሪዝምና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ ለማድረግ የተከናወኑ የልማት ስራዎች ውጤት እያስገኙ ነው። የልማት ስራዎቹ ከተማዋ ሀገር አቀፍ ስብሰባዎችን¸፣ ስፖርታዊ ውድድሮችና ሌሎች ኩነቶችን በማስተናገድ ተመራጭ እየሆነች እንድትመጣ አድርገዋታል ብለዋል። የሀይቅ ዳርቻ ልማቱ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትና የተወዳዳሪነት አቅም ለመፍጠር ያለመ መሆኑን ጠቁመው ለተግባራዊነቱ በትብብር እንደሚሰራ አመላክተዋል። የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጥራቱ በየነ በበኩላቸው በሀዋሳ ከተማ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥሉ ብለዋል። የሀዋሳ ሐይቅ ዳርቻን በማልማትና ከአካባቢው መስህቦች ጋር በማስተሳሳር ሀይቁን የቱሪዝም ማዕከል የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል። ጅማ ዞን ጎማ ሁለት በጅማ አጠር ያለ ቆይታችን ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጅማ ዞን ጎማ ሁለት የምርጫ ክልል የብልጽግና ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው መቅረባቸውን በማስተዋወቅ የቅስቀሳ መርሃ ግብር ተካሂዷል። በዚህ የቅስቀሳ ስነ ስርአት ላይ የፓርቲው አባላትና አመራሮች እንዲሁም ደጋፊዎች በመውጣት የተሳተፉበት መሆኑን ለማየት ችለናል። በመርሃ ግብሩ ላይ በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ነመራ ቡሊ፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፎች እድገት እያስመዘገበች መሆኑን ገልጸው በመደመር እሳቤ የኢትዮጵያን እድገትና ማንሰራራት ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ርዕሰ መስተዳድሩ በሚወዳደሩበት ምስራቅ ጉራጌ ዞን ደቡብ ሶዶ ወረዳ የምርጫ ቅስቀሳና እጩ የማስተዋወቅ መርሐ ግብር የተካሄደውም በዚሁ ሳምንት ነበር። ርዕሰ መስተዳድሩ በወቅቱ እንዳሉት ብልፅግና ፓርቲ የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችንን ሲያከናውን ቆይቷል። በባለፉት የለውጥ ዓመታት የሀገርን እድገትና የህዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ያረጋገጡ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን በመተግበር ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገቡን ተናግረዋል። የሽንሌ እመርታ በሳምንቱ በሶማሌ ክልል ሽንሌ ወረዳ የተገነባው የ10 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የኮንክሪት አስፋልት መንገድና በሽንሌ ጠቅላላ ሆስፒታል የተገነባው የኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካ በክልሉ ርእሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ እና በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ ተመርቋል። በሽንሌ ወረዳ የመርማርሳ ከተማን ከድሬዳዋ ጋር የሚያስተሳስር የ3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የአስፋልት መንገድ ግንባታንም አስጀምረዋል። የተገነቡት የልማት ስራዎች በተለይም ለወረዳው እመርታ መሆኑን የገለጹት አመራሮቹ በክልሉ ያለውን እምቅ ሃብት የማልማትና የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ስራዎች ይቀጥላሉ ብለዋል። ሳተላይት በሐረር የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀቢያ ጣቢያ ተከላ ስራ የክልሉ ርእሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በተገኙበት በዚሁ ሳምንት ተጀምሯል። የሳተላይት የመገኛ መረጃ መቀበያ ጣቢያው በክልሉ ለሚከናወኑ የልማት ስራዎች ከፍተኛ እገዛ የሚያደርግ ሲሆን የመረጃ ግብዓት ከመሆን አኳያም ፋይዳው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል። የመንገድ ዲዛይን፣ አጠቃላይ የኮንስትራክሽን ስራ ለሚያከናውኑ፣ የመሬት አጠቃቀምን በጥንቃቄ ለመቆጣጠር፣ ለይዞታ መረጋገጫና ሌሎችም የተሟላ መረጃ ለመስጠት የሚጠቅም መሆኑ ታውቋል።
የአፍሪካዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣረ ዎዴ ማያ - በአዲስ አበባ
May 6, 2026 707
ፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ጉባኤ በአዲስ አበባ፣ በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ይህ ጉባኤ ከሚያዚያ 29 እስከ 30 ቀን 2018 ዓ.ም "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ አህጉራዊ መድረክ ነው። የአህጉሪቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎች እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ፤ የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ አልሟል። ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) በዲጂታል መገናኛ ብዙኅን የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክትና ገፅታ ለዓለም የሚያስተዋውቅ ዓለም አቀፍ አንቱታን ያተረፈ የአህጉሪቷ የዘርፉ ፈርጥ ነው። ለኢትዮጵያ ጥልቅ ፍቅር ያለው ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበርና የዲጂታል ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) አዲስ አበባ ገብቷል። በጉባኤው ላይ የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) መገኘትም የአፍሪካን የዲጂታል ገፅታ መቀየር የሚያስችል የአህጉራዊ ይዘት ፈጠራ ትብብርን ለመፍጠር ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ይጠበቃል። የአየር በረራ መሐንዲስ ስልጡኑ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የዲጂታል ታሪክ ተራኪነት ጉዞ በሀገረ ቻይና ትምህርቱን በሚከታተልበት ወቅት ነበር የዩቱዩብ ይዘት ፈጠራን መሞከር የጀመረው። የመጀመሪያዎቹ የዲጂታል ይዘት ፈጠራ ሥራዎቹም አስቂኝ የነበሩ ቢሆንም ወላጅ አባቱ የአፍሪካን በጎ ገፅታ ለዓለም ማስተዋወቅ እንዳለበት የሰጡትን ምክር ተከትሎ ጉዞውን ቀይሯል። ባህላዊ ግንኙነትን ለማጠናከር የቻይንኛ ቋንቋ ቪዲዮዎችን ያዘጋጅ የነበረው ዎዴ ማያ፤ ወደ ጋና ተመልሶ በሰራቸው የመጀመሪያ ምዕራፍ ሥራዎቹ የሚፈለገውን ያህል ዕውቅና አላስገኙለትም ነበር። መነሻውን በአዲስ አበባ በማድረግ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ አህጉሪቷን ለማስተዋወቅ ከሰራቸው ይዘቶች ውስጥ በሩዋንዳ የሰራው ቪዲዮ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ዕውቅናው እንዲናኝ አድርጎታል። ኢትዮጵያ በእርሱ አተራረክ ማዕከላዊ ስፍራ እንዳላት የሚናገረው ዎዴ ማያ፤ የአፍሪካን ያልተነገሩ ስኬቶችና የአፍሪካዊያን ፅናት በተከታታይ ለዓለም ማስተዋወቁን ተያይዞታል። አሁን ላይ የአፍሪካን ለውጥ፣ ተስፋና ዕድሎች ለዓለም ማህበረሰብ የሚያስተዋውቁ ዘጋቢ ፊልሞችን በመስራት የአህጉሪቷን ስሁት ትርክት በመቀየር ረገድ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ሰዎች አንዱ ሆኗል። በሚሊዮን የሚቆጠር ዕይታ ያላቸውን ዘጋቢ ፊልሞቹና የጉዞ ታሪኮችም ጊዜ ያለፈባቸው ስሁት ትርክቶችን በመሞገት የአፍሪካን ተስፋና ዕድሎች ለዓለም በመግለጥ ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የኢትዮጵያን ዕድገትና ተስፋ ደጋግሞ የተረከው ዎዴ ማያ፤ በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS) ወደ አዲስ አበባ መምጣቱም መድረኩን ተምሳሌታዊና ስልታዊ ያደርገዋል። ይህም የበርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) የግል ጉዞ ከመሆኑም በላይ፤ ኢትዮጵያ የአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ መድረክ ፈጠራና የታሪክ አተራረክ ለውጦች ማዕከላዊ ሚና በተግባር ያስመሰክራል። በዚህ ጉባኤ፤ እንደ ዎዴ ማያ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መሰባሰብ የአፍሪካን የዲጂታል ሥነ-ምኅዳር በማጠናከር ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉራቸውን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም ለማስተዋወቅ ጉልህ ፋይዳ አለው። ለኢትዮጵያም የዎዴ ማያ መገኘት ሀገሪቱ ለአፍሪካ ዲጂታልና ባህላዊ ሕዳሴ ያላትን ቁርጠኝነት የበለጠ በማሳደግ አዲስ አበባን የአፍሪካ የዲጂታል ገፅታ ግንባታ ሃሳቦች መነሻነት በተግባር ያረጋግጣል።
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች
May 3, 2026 785
የቴክኖሎጂ እምርታ -ሌላው የኢትዮጵያ ከፍታ ጉዞ አመላካች በሙሴ መለሰ በኢትዮጵያ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የታየው የቴክኖሎጂ ለውጥ ወደ ዘመናዊው የዲጂታል ምህዳር እያሸጋገራት ይገኛል።የፖሊሲ ማሻሻያዎች፣ የመሰረተ ልማት እና የተቋማት ግንባታ ስራዎች ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በምታደርገው ጉዞ ውስጥ የሚጠቀሱ ዋንኛ ስራዎች ናቸው። ለውጡን ተከትሎ መንግስት "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን ስትራቴጂ በመቅረጽ የዲጂታላይዜሽን ስራውን የሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ምሰሶ አድርጎታል። የለውጡ መንግስት ስልጣን ከያዘ በኋላ ቴክኖሎጂን እንደ አንድ የኢኮኖሚ ምሰሶ በመቁጠር "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025" የተሰኘውን አጠቃላይ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር ገባ።ይህ ስትራቴጂ የሀገሪቱን የዲጂታል ጉዞ ከመሰረቱ የለወጠ ሲሆን፣የመጀመሪያው ትልቅ እርምጃም የቴሌኮም ዘርፉን ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት ማድረግ ነበር። የቴሌኮም ዘርፉ ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉ የሳፋሪኮም ወደ ኢትዮጵያ መግባትና የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቶችን የማዘመን ስራ የኢንተርኔት ተደራሽነት እንዲሰፋ ምክንያት ሆኗል።በተለይም የአምስተኛ ትውልድ (5G) ቴክኖሎጂ አገልግሎት መጀመር ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂ ተጠቃሚ እንድትሆን አስችሏታል። የቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ለውጡ የፋይናንስ ዘርፉ ላይ ውጤት አምጥቷል።እንደ ቴሌብር (telebirr) ያሉ የዲጂታል ክፍያ አማራጮች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ ምንም የባንክ ሂሳብ በስልካቸው ብቻ ግብይት እንዲፈጽሙ በማድረግ፣ ሀገሪቱ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር ትልቅ መደላድል ፈጥረዋል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ረገድ የተመዘገቡት ስኬቶችም የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ አድማስ ይበልጥ አስፍተውታል። የኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ኢንስቲትዩት መቋቋም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላትን ራዕይ ለዓለም ያሳየችበት አጋጣሚ ነው።ኢንስቲትዩቱ በአሁኑ ወቅት በጤናው ዘርፍ የካንሰር ህመምንና የሳምባ በሽታዎችን ቀድሞ መለየት የሚያስችሉ የኤአይ ውጤቶችን አበልጽጓል። በግብርናውም ረገድ የአፈርን ለምነትና የሰብል በሽታን በቴክኖሎጂ የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ ይህም በምግብ ዋስትና ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ሌላው ትልቅ ስኬት የሀገር በቀል ቋንቋዎችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ ተወዳዳሪ ለማድረግ የተሰሩ የቋንቋ ፕሮሰሲንግ (NLP) ስራዎች ናቸው። ይህም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች በዘመናዊ የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች ውስጥ እንዲካተቱና ለተጠቃሚው ምቹ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል። የፋይዳ (Fayda) ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮጀክት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎችን መረጃ በአንድ ማዕከል በመሰብሰብ፣ ለባንክ፣ ለጤናና ለሌሎች ማህበራዊ አገልግሎቶች አስተማማኝ መሠረት ጥሏል። በአሁኑ ወቅት ዜጎች እንደ ፓስፖርት ማደስ፣ የንግድ ፈቃድ ማውጣትና ግብር መክፈል ያሉ አገልግሎቶችን ከቤታቸው ሆነው በኢንተርኔት ማከናወን መቻላቸው የለውጡ ፍሬያማነት ማሳያ ነው።የሳይንስ ሙዚየምም የወጣቶችን የፈጠራ አቅም የሚያሳይና የሀገሪቱን ቴክኖሎጂ የሚደግፍ ትልቅ አቅም ሆኗል።የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 በቅርቡ መጠናቀቁ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የ2025 ስትራቴጂው መጠናቀቁን ተከትሎ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን ታህሳስ 11 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ ማስጀመራቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በወቅቱ ባስተላለፉት መልዕክት ተደራሽነትን ማስፋት፣ ለዜጎች እኩል እድል መፍጠር እንዲሁም በዜጎችና ተቋማት መካከል መተማመንን ማጎልበት ደግሞ የስትራቴጂው ቁልፍ መሰረታዊ ትልሞች መሆናቸውን ገልጸዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ም ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት በማድረግ መዘጋጀቱን አንስተዋል።ትልሞቹ እንዲሳኩም በተለይ የህዝብ ዲጂታል መሠረተ ልማት ማስፋት ላይ ትልቅ ስራ እንደሚከናወን ጠቁመው፤ ይህም ዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰው ተኮር ሆኖ የዜጎችን ኑሮ እንዲያሻሽል ትልቅ አቅም ይፈጥራል ብለዋል። በአጠቃላይ በዲጂታል ኢትዮጵያ የሚከናወኑ ስራዎች የመደመር መንግስት በቀለለ ቢሮክራሲ ታላላቅ ስትራቴጂዎችን እውን ለማድረግ ከያዘው ግብ ጋር የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 እንዲሳካም ሁሉም በትብብር መስራት እንዳለበት ነው ጥሪ ያቀረቡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዲጂታል 2030ን ይፋ ሲያደርጉ የነበረው ትልቁ መልዕክት ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዓለም ተመልካች ሳይሆን ተሳታፊና መሪ ትሆናለች የሚል ነው። ስትራቴጂው በዋናነት"የፋይዳ" ዲጂታል መታወቂያን ከሁሉም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጋር በማቀናጀት፣ ለዜጎች ቀልጣፋ አሰራርን መፍጠር፣ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዲጂታል ስራ እድሎችን ለወጣቶች ማመቻቸት እና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የቴክኖሎጂና የፈጠራ ማዕከል (Innovation Hub) አድርጎ መገንባትን እንደ ዋነኛ ግብ አስቀምጧል። ይህም ሁሉን አቀፍ የኢንተርኔት ተደራሽነትን በማረጋገጥ፣ የመንግስት አገልግሎቶችን መቶ በመቶ ወረቀት አልባ በማድረግ እና የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) በግብርና፣ በጤናና በኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ በስፋት በመተግበር የምርታማነት አብዮት መፍጠርን ያለመ ነው። በዚህ ረገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ሕብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ (Champion) ሆነው መሾማቸው ኢትዮጵያ በዘርፉ የጀመረችው ስራ በአህጉራዊ ደረጃ ያለውን ተቀባይነትና የተሰጣትን ትልቅ ኃላፊነት የሚያሳይ ነው።ኢትዮጵያ አሁን ላይ የደረሰችበት የቴክኖሎጂ ከፍታ፣ ሀገሪቱን በአፍሪካ የቴክኖሎጂ ተፎካካሪ ብቻ ሳይሆን የፈጠራ ምንጭ እንድትሆንም እያደረጋት ይገኛል። በዚህ ረገድም የቀጣዩ ዲጂታል 2030 ስትራቴጂ ስኬትም ኢትዮጵያን ሙሉ በሙሉ ወረቀት አልባና በቴክኖሎጂ የበለጸገች ሀገር የማድረግ ራዕይን ለማሳካት እና ለሀገራዊ ብልጽግና እንደ ቁልፍ ሞተር ሆኖ ያገለግላል።
የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር
May 3, 2026 653
ክልሎች፤ሚያዝያ 25/2018 (ኢዜአ)፡-የክልሎች ቅኝት በወፍ በረር በሳምንቱ በክልሎች የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮች በወፍ በረር ሲቃኙ ይህንን ይመስላሉ!!! 👉ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የተገነቡትን የቶዮ ሶላር ኢነርጂ ምዕራፍ ሁለት፣ የኦሪጂን እና የሉሚንቴክ የሶላር ፋብሪካዎችን እንዲሁም የኤች.ዜድ ጋዝ ማምረቻ ፋብሪካን በይፋ መርቀዋል። እነዚህ የሶላር ፋብሪካዎች በጋራ በዓመት 11.3 ጊጋ ዋት ንጹሕ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላቸው ሲሆን፣ የኤች.ዜድ ጋዝ ፋብሪካ ደግሞ በዓመት 900 ቶን ኦክስጅን፣ 40,000 ቶን ናይትሮጅን እና 7 ቶን ሃይድሮጅን ለገበያ ያቀርባል። ይህ ክንውን የኢትዮጵያን የታዳሽ ኃይል ልማት ለማፋጠን፣ የኢነርጂ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ዘላቂ፣ የማይበገር ሁለንተናዊ እድገት ዕውን ለማድረግ የተነደፈውን ስትራቴጂ ለማሳካት ትልቅ ምዕራፍ ተደርጎ ይወሰዳል። 👉እንቁላልን ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት የማቆየት ልምምድ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፤ የዶሮ እንቁላል ሳይበላሽ ለሁለት ዓመት ያህል ማቆየት የሚያስችል ቴክኖሎጂን ወደ ተግባር ለማስገባት ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል። በዩኒቨርሲቲው የእንስሳት ሕክምናና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር ማስተዋል ብርሃን፤ ዩኒቨርሲቲው የእንቁላል ምርት ብክነትና ብልሽትን ለማስቀረት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። በዚህም እንቁላልን እስከ ሁለት ዓመት ያለ ምንም ብልሽት ማቆየት የሚያስችለውን ቴክኖሎጂን የማላመድና የማስተዋወቅ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። ቴክኖሎጂው በአንድ ሊትር ውሃ ውስጥ 30 ግራም የኖራ አፈር ወይም ላይም ስቶን ጨምሮ በማዋሃድ እስከ 12 እንቁላሎችን ሳይበላሽ የሚያስቀምጥ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ ተመራጭ ነው ያሉት። ይህም እስካሁን ባለው አንድ ትኩስ እንቁላል ሳይበላሽ መቆየት የሚችለው እስከ ሁለት ሳምንት መሆኑን ጠቁመው ቴክኖሎጂው ይሄን ችግር በመሰረታዊነት የሚቀይር ነው።፡ ቴክኖሎጂውን በስፋት በማስተዋወቅና በማላመድ ረገድም ተግባር ተኮር ስልጠናዎችን በመስጠት ችግር ፈቺነቱን የማሳየት ስራ እየተሰራ መሆኑንም አስረድተዋል። 👉የአፋር ጥጥ ተስፋ ሰጪ ፀጋ! የአፋር ክልል የበርካታ የተፈጥሮ ፀጋዎች ባለቤት ነው፤ ሆኖም እነዚህን እምቅ ሀብቶች ወደ ልማት በመቀየር ከፀጋዎቹ ተቋዳሽ ለመሆን ሳይቻል ለረጅም ተቆይቷል። አሁን ግን ከፀጋዎቹ አንዱ የሆነውን ተፈጥሯዊ ጥጥ (Organic Cotton) ለማምረት ተስፋ ሰጪ ተግባራት እየተከናወኑ ነው። በሰመራ በተካሄደ የውይይት መድረክም በግብርና ሚኒስቴር የጥጥ ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ሳምሶን አሰፋ፤ የአፋር ክልል ጥጥን በመስኖ ማልማት የሚቻልበት አቅም ያለው በመሆኑ ልማቱን ማስፋፋት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዋል። በሀገራችን የጥጥ ልማትን ለማስፋፋት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው፤ ባለፈው የምርት ዘመን እንደ ሀገር በስድስት ክልሎች 110 ሺህ ሄክታር መሬት በጥጥ መልማቱን ተናግረዋል።በዚህም 79 ሺህ ሜትሮክ ቶን የተዳመጠ ጥጥ በማምረት ለኢንደስትሪዎች ማቅረብ እንደተቻለ ነው የገለፁት። 👉የሸማቹ ሸክም ይቀላል! የኢትዮጵያ ህብረት ሥራ ኮሚሽን “ወደ ቀበሌ መድረስ” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ስድስት ከተሞች ሀገር አቀፍ የህብረት ሥራ ማህበራት ሪፎርም የንቅናቄ መድረክ ሲያካሄድ የህብረት ስራ ማህበራት ከእንግዲህ የሸማቹን ሸክም ሊያቀሉ ይገባል የሚል ሀሳብ ተነስቷል። በሀዋሳው በተካሔደው የማጠናቀቂያ መርሃ ግብር ላይ የግብርና ሚኒስትሩ አዲሱ አረጋ በቪዲዮ ኮንፈረንስ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት በተለያዩ መስኮች የበለጸገችና ህብረ ብሔራዊት ሀገር ለመፍጠር ዘርፈ ብዙ የሪፎርም ስራዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን አንስተዋል። በተከናወኑ ተግባራትም ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደረጉ በርካታ ለውጦች እየተመዘገቡ መሆኑን አክለዋል። የመንግስትን፣ የግሉ ዘርፍንና የዜጎችን የካፒታል አቅምና ዕውቀትን ደምረው የያዙት የህብረት ስራ ማህበራት ግብርናውን በማሻገር የአርሶና አርብቶ አደሩን ህይወት በመቀየር ረገድ ትልቅ አቅም እንዳላቸው ገልፀው የፋይናንስ አቅርቦት ችግርን በመፍታትና የግብይት ሰንሰለቱን በማሳጠር የሸማቹን ህብረተሰብ ሸክም ያቀላሉ ተብሎ እንደሚታመንም አስረድተዋል። 👉ምርምር ለቀጣናዊ ትስስር በጅማ ዩኒቨርሲቲ "ቀጠናዊ ሰላምና ትብብር ለዘላቂ ልማት" በሚል መሪ ሀሳብ በተካሄደው ዓለም አቀፍ የምርምር ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለችበት ቀጣና የሚታዩ ፍላጎቶችን ለማሟላትና ተግዳሮቶችን ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ለመፍታት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰሩ ጥናቶች ትኩረት ሊሰጡ እንደሚገባ ተነስቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ኮራ ጦሽኔ ቀጣናውን በልማት ለማስተሳሰር በሚደረግ ጥረት የትምህርት ተቋማቱ የጥናትና ምርምር ድጋፍ ከፍተኛ ሚና አለው ያሉ ሲሆን ለዚህም ተቋማቱ ኢኮኖሚያዊ ትስስርን የሚያሳድጉ እና ማህበራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት የሚያግዙ የፖሊሲ መነሻ ሀሳቦችን በጥናትና ምርምር እንዲያፈልቁ አሳስበዋል። የሚወጡ ጥናቶች በቀጣናው በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችሉ ሊሆኑ እንደሚገባ የተጠቀሰ ሲሆን ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራን በመተግበር እያከናወነች ያለችው ተግባር በተመክሮነት ቀርቦ አድናቆትን አስገኝቶላታል። 👉ሻይ ቅጠል አሁን አሁን አርሶ አደሩ በተለያዩ ኢንሼቲቮች በሚከናወኑ የግብርና ልማት ትግበራዎች ተጠቃሚነቱን እያረጋገጠ ይገኛል። በርካታ አርሶ አደሮች በሻይ ቅጠል ልማት ኢንሼቲቭ በመሰማራት ገቢን ከማሳደግ ባለፈ ለሌሎችም ሰፊ የስራ ዕድል እየፈጠሩ ይገኛሉ። በጅማ ዞን የሻይ ቅጠል ልማትን ከማስፋፋት ባለፈ የበያ ትስስር የመፍጠርና ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለፋብሪካ ለማቅረብ ለአርሶ አደሩ ግንዛቤ እየተሰጠ መሆኑም ተገልጿል። የዞኑ ግብርና ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቲጃኒ ተማም፤ በዞኑ የሻይ ቅጠል ልማትን በኢኒሼቲቨን መልክ በመተግበር የአርሶ አደሩን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከማሳደግ ባለፈ ለበርካቶች የስራ ዕድል እየተፈጠረ ነው። ዘንድሮም ስራውን ለማስቀጠል በተመረጡ 6 ወረዳዎች በመጪው ክረምት የሚተከሉ 50 ሚሊዮን ችግኞች የተዘጋጁ ሲሆን ህዝብን በማሳተፍም ወደ 2 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬትን ለመሸፈንም ታስቧል። ጥቅሙ የገባቸው አርሶ አደሮችም የሰብል ልማቱን ለጊዜው ተወት በማድረግ በሻይ ቅጠል ልማት ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ይናገራሉ። በዞኑ የሰቃ ጨቆርሳ ወረዳ አርሶ አደር ሲራጅ ሼክ ከድር በሻይ ቅጠል ልማት ላይ መሳተፍ ከጀመሩ ወዲህ ገቢያቸው መጨመሩን ተናግረዋል። አርሶ አደር ሱልጣን አባሞጋ በበኩላቸው ተሰማርተውበት ከነበረው የሰብል ልማት ወደ ሻይ ቅጠል ልማት በመሰማራት ተጠቃሚ መሆናቸውን አስረድተዋል። የአካባቢ ፀጋን ተገንዝቦ ወደ ስራ መግባት ተጠቃሚነትን እንደሚያመጣ ማሳያ ሊሆን ይችላል። 👉ተስፋዎች ከሳምንቱ አንኳር ጉዳዮች መካከል በሆሳዕና ከተማ የተካሄደው የሞዴል ኢንተርፕራይዞች ደረጃ ሽግግር እውቅና መርሃ ግብር ይጠቀሳል። "የኢንተርፕራይዞች ሽግግር ለእመርታዊ እድገት" በሚል መሪ ሀሳብ የተከናወነው የዕውቅና መድረክ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) በተገኙበት ነው የተካሄደው። እሳቸው እንደገለፁት፤ ኢንተርፕራይዞቹ ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ በመተካትና ለውጪ ገበያ የሚቀርቡ ምርቶችን ከማምረት በተጨማሪ ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል እየፈጠሩ ነው። በክልሉ በገጠርና በከተማ በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ዘርፍ ከ25 ሺህ በላይ ኢንተርፕራይዞች በተለያዩ መስኮች መሰማራታቸው የተገለፀ ሲሆን ባለፉት ዘጠኝ ወራት በክልሉ በጥቃቅንና በአነስተኛ ደረጃ የሚገኙ 4 ሺህ 948 ኢንተርፕራይዞችን የማሸጋገርና 495 ሞዴል ኢንተርፕራይዞችን የመለየት ስራ መሰራቱም እንዲሁ። ከኢንተርፕራይዝ ወደ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሸጋገሩ አምራቾች እንደተናገሩት ሽግግሩ ስራቸውን በተሻለ ሁኔታ ለመከወን እንደሚያግዛቸው ገልጸዋል። 👉ትምህርትና አርብቶ አደሩ የወፍ በረር ቅኝታችንን ስንቀጥል ጋምቤላ እንደርሳለን፤ በሳምንቱ በጋምቤላ ከተማ በተካሄደ መድረክም የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የተለያዩ ተግባራት ሲከናወኑ መቆየታቸውም ተመልክቷል። በለውጡ ዓመታት የአርብቶ አደሩን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤት መመዝገባቸውም እንዲሁ። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ እንዳሉት የአርብቶ አደሩን የትምህርት ተደራሽነትና ጥራት ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና የገዘፈ መሆኑም በመድረኩ መገለፁን ቅኝታችን ዳሶታል። 👉ልወቅሽ ኢትዮጵያ ሁነቶቹን ጠቅለል አድርጎ የዳሰሰው ቅኝታችን ደግሞ በስድስት ከተሞች ለማካሄድ ዕቅድ የተያዘለትና እስካሁን በጅማ፣ በሀዋሳና በደብረ ብርሃን ከተሞች የተካሄደው የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ታላቁ ሩጫ" ከተሞቹን ከማስተዋወቅ የዘለለ ፋይዳውን በመርሃ ግብሩ ላይ በተላለፉ መልዕክቶቹ አሳይቷል። ለአብነት በጅማ የተካሄደው ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የሚለውን የጤና ጉዳይን ያነሳ ነበር። በአዳማ ከተማ የተከናወነው ሁነት ደግሞ በመኪና ውድድር ታጅቦ የተከናወነና የቱሪዝም መስህቦችን ማስተዋወቅን ታላሚ ያደረገ ነበር። ‘’ለሀዋሳ ከፍታ እንሮጣለን’’ በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀው ሁነትም ከጅማና አዳማው ሁነት የተለየ እሳቤንም ሆነ መልዕክትን አልያዘም። ሁሉም ሁነቶች ከዋነኞቹ አምስት ምጣኔ ሃብታዊ አምዶች መካከል አንዱ የሆነውን ቱሪዝም ልማት በማጠናከር የማህበረሰቡን የዘርፉ ተጠቃሚነት ማላቅን ታሳቢ ማድረጋቸውን መመልከት ተችሏል። ቅኝቶቻችን በወፍ በረር ይህንን ይመስላሉ!! የሳምንት ሰው ይበለን!!!
ትንታኔዎች
ለተቃና ነገ የኢትዮጵያ ትጋት አንዱ መገለጫ
May 11, 2026 1432
በዮሐንስ ደርበው ኢትዮጵያ ከምትከውናቸው ዐበይት ጉዳዮች መካከል ሰው ተኮር ተግባራት ቀዳሚው ነው። በአዲስ አበባ በተካሄደው ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ፤ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ኢትዮጵያ ለልማት በምታደርገው ጥረት ሰው ተኮር የልማት አቅጣጫ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ጉዳዮች አንዱ ነው ብለዋል። መንግሥት መጪው ትውልድ ጤናማ፣ ብቁ እና ውጤታማ እንዲሆን የቀዳማይ ልጅነት ፕሮግራምን ማዕከል አድርጎ ሁሉን አቀፍ ሥራ እየተገበረ ስለመሆኑም አስረድተዋል። በዚህም መሠረት፤ የልጆች ትምህርት ቤቶችን ማስፋፋት፣ የምገባ ሥርዓትን ማሳደግ፣ የሕጻናት መጫወቻ ሥፍራዎች ግንባታ ላይ ተጨባጭ ውጤቶች መምጣታቸውንም ነበር የጠቀሱት። ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማትና ትምህርት ፖሊሲ የዘላቂ ብልጽግና መንገዳችን ከሆነው የመደመር ዕሳቤ ጋር በተናበበ መልኩ እየተተገበረ በስኬት ቀጥሏልም ብለዋል። ኢትዮጵያ ለነገ የተዘጋጀ ትውልድ ለመገንባት በሕግና በፖሊሲ የተደገፉ የቀዳማይ ልጅነት ኢኒሼቲቮችን እየተገበረች እንደምትገኝም አስታውቀዋል። ለአብነትም፤ በ2015 ተሻሽሎ የፀደቀው ሀገር አቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ልማት እና ትምህርት የፖሊሲ ማዕቀፍ እንዲሁም በ2017 የፀደቀውን አጠቃላይ የትምህርት አዋጅ መሠረት በማድረግ ከ35ሺህ በላይ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመላው ሀገሪቱ እየተተገበረ መሆኑን አንስተዋል። በመንግሥት ተቋማት የሕጻናት ማቆያ ማዕከላት ተከፍተው አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን በመጠቆምም፤ ኢትዮጵያ የሕጻናትን ደኅንነት ማሻሻል የሚያስችል ጉልኅ ብሔራዊ መርሐ-ግብር መጀመሯን አንስተዋል። በሰቆጣ ቃል ኪዳን አማካኝነት የ15 ዓመት ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ከሁለት ዓመት በታች በሆኑ ሕጻናት ላይ የሚደርሰውን መቀንጨር በ2022ዓ.ም ዜሮ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑንም ነው ያስገነዘቡት። የሌማት ትሩፋትና የአልሚ ምግቦች ምርታማነት የሕጻናትን ጉዳት ለመቀነስና የልጆችን ጤናማነት መጨመር እያስቻሉ እንደሚገኙም ነው የተናገሩት። ኢትዮጵያ ለዘላቂ የልማት ግቦችና ለሕጻናት መብቶች ጥበቃ የገባቻቸውን ቃል ኪዳኖች ወደ ተግባር እየለወጠች መሆኑን በማንሳት፤ ይህንንም አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል። መንግሥት ብልጽግናን ለማረጋገጥ የተቀናጀ የቀዳማይ ልጅነት ልማትን በመላ ሀገሪቱ ለማስፋት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም አመላክተዋል። በዚህም መሠረት፤ በጀት በመመደብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ የተማሪዎችን ምገባ በማስፋፋት ውጤት ማምጣቱን ነው የሚያብራሩት። ልጆች በአካልና በመንፈስ የሚጎለብቱባቸው የስፖርትና የመዝናኛ ቦታዎች በየአካባቢው በመገንባት፣ በኮሪደር ልማት ለልጆች ምቹ ሥፍራ እየተፈጠረ መሆኑንም በመጥቀስ። ልጆች ላይ መሥራት በነገ ሀገር፣ አኅጉር እና ዓለም ላይ መሥራት በመሆኑ በትጋት ማስቀጠል እንደሚገባም በአጽንኦት ይናገራሉ። አፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ተግዳሮቶችን ለመፍታት የራሷን መፍትሔዎች በማፍለቅ፣ በብሔራዊ የልማት አጀንዳዋ እያካተተች መሆኑን የሚገልጹት ደግሞ የአፍሪካ ቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ከበደ ወርቁ ናቸው። በሕጻናት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ማንኛውም ሀገር በመጪው ትውልድ ላይ ሊያደርጋቸው ከሚችላቸው እጅግ አስፈላጊ ኢንቨስትመንቶች አንዱ መሆኑንም ያነሳሉ። አፍሪካ በቀዳማይ ልጅነት ልማት ላይ ያሉባትን ተግዳሮቶች ከመጋፈጥ ባለፈ፤ የራሷን መፍትሔዎች እያመነጨች መሆኑንና ጉዳዩን የብሔራዊ ልማት አጀንዳዋ አካል እያደረገችው እንደምትገኝም ገልጸዋል። አዲስ አበባ ይህን ዓለምአቀፍ የቀዳማይ ልጅነት ጉባዔ እንድታስተናግድ የተመረጠችበት ዋና ምክንያትም፤ በዘርፉ እያከናወነች ያለው ተግባር አርዓያነት ያለው በመሆኑ ነው ብለዋል። ከተማዋ የጤና እና የሥርዓተ-ምግብ አገልግሎቶችን ያካተተ የተቀናጀ ዘርፈ-ብዙ አሠራር መዘርጋቷን ጠቅሰው፤ የቅድመ 1ኛ ደረጃ ትምህርት እና የቀን የሕጻናት እንክብካቤ ማዕከላትን በከተማ አቀፍ ስትራቴጂ ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝም ጠቁመዋል። የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በበኩላቸው፤ መዲናዋ በቀዳማይ ልጅነት ያመጣችው ተጨባጭ ውጤት በአርዓያነት እንድትጠቀስ እንዳደረጋት አንስተዋል። በሕጻናት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ዓመታት የሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች፤ በትምህርት፣ በሰው ሃብት ልማትና በኢኮኖሚ ዕድገት ላይ ረጅም ጊዜ የሚቆይ ፋይዳ እንዳለውም አስረድተዋል። በዚህም በአዲስ አበባ ፍትሐዊና አካታች የቀዳማይ ልጅነት ልማት መርሐ-ግብርን ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ የትውልድ ግንባታ ሥራ እየተሠራ እንደሚገኝ አረጋግጠዋል። "ሕጻናት የአዲስ አበባ የነገ ተስፋዎች" የሚል ፍኖተ ካርታ በመቅረጽ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን ለሚሆኑ ከስድስት ዓመት በታች ሕጻናት ሁለንተናዊ ዕድገት መረጋገጥ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። በትምህርት ቤት ምገባ መርሐ-ግብርም ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ ዩኒፎርምና በቀን ሁለት ጊዜ ምግብ በማቅረብ በሕጻናት ክብካቤ ተጨባጭ ለውጥ መጥቷል ነው ያሉት። የሕጻናት ማቆያና መጫወቻ የመሠረተ-ልማት ግንባታ፤ ሕጻናት ነፃ የሕክምና፣ የምገባና የሥነ-ልቦና አገልግሎት የሚያገኙበትን ዕድል መፍጠሩን አስረድተዋል። የቀዳማይ ልጅነት መርሐ-ግብር በ2015 ዓ.ም ሲጀመር በዕድገት ወደ ኋላ የቀሩ የሕጻናት መጠን ከነበሩበት 13 በመቶ አሁን ላይ ወደ 10 በመቶ ዝቅ ማድረግ መቻሉን ከንቲባዋ አመላክተዋል። አክለውም፤ የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዝግጁነታቸው ከነበረበት 49 በመቶ አሁን ወደ 90 በመቶ ማደጉንም ተናግረዋል። ሀገር በሁሉም ዘርፍ የበቃ መጪ ትውልድ እንዲኖራት መንግስት የያዘው ጥረት በሚፈለገው መጠን ለውጤት እንዲበቃ የሁሉንም ትኩረትና ተሳትፎ ይሻል። ለነገ በሁሉም ዘርፍ የዳበረ ትውልድና የበለጸገች ኢትዮጵያ እውን መሆን ዛሬ ላይ እየተደረገ ያለው ርብርብ የሀገራችንን መፃኢ ብሩህ ተስፋ ይበልጥ የሚያለመልም ነውና ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል።
ትኩረት የተሰጠው የሕጻናት ስነምግብ
May 10, 2026 508
በሙሴ መለሰ በዓለም ላይ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናት ሙሉ አካላዊ እና አዕምሯዊ አቅማቸውን ላይ ሳይደርሱ እድሜያቸውን ይቆጥራሉ። የዚህ ልብ ሰባሪ ክስተት መነሻ መቀንጨር (stunting) ይባላል። የስነ ምግብ ባለሙያዎች መቀንጨርን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስር የሰደደ ቀውስ ያስከተለ እና የጉዳቱ መጠን የገዘፈ ነገር ግን የአስከፊነቱን ያህል በቂ ትኩረት ያላገኘ ጉዳይ ነው ይሉታል። ብዙ እንደ ግጭቶች እና ሌሎች የዓለም ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ቀውሶች አርዕስተ ዜና ሲሆን አይታይም። በቀላሉም የህዝብን ትኩረት አይስብም። ይሁንና የመቀንጨር ጉዳቶች ትውልድ ተሻጋሪ የሆኑ መዘዞች እና የአንድ ሀገር ልማትና ጉዞ ላይ ሊቀለበስ የማይችል ጣጣን ያስከትላል። የህጻናትን ሰውነት ቀስ በቀስ እየጎዳ አዕምሯቸው እና የመፍጠር አቅማቸውን እያደከመ በመሄድ፣ በድምጽ አልባነቱ ውስጥ ውስጡን ዘላቂ መዘዝ እያመጣ ይገኛል። መቀንጨር ህጻናትን በለጋ እድሜያቸው ጊዜ ብቻ ጎድቶ የሚያበቃ ቢሆን መልካም ነበር ዳፋው እስከ ህይወታቸው መጨረሻ የሚከተላቸው ነው። ህጻናት እጅግ በጣም ቁልፍ በሚባለው የእድሜ ክልል ማለትም ከተወለዱ እስከ ሁለት ዓመት ባለው ጊዜ ተመጣጣኝ ምግብ ማግኘት ሲገባቸው በምግብ እጦት ምክንያት እድገታቸው አሉታዊ ተጽእኖ ይደርስባቸዋል። የመቀንጨር ጉዳት አካላዊ ብቻ ጉዳት አድርጎ ማየት የችግሩን ሙሉ ምስል እንደማያሳይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ይገልጻል። የመቀንጨር ችግር ያለባቸው ህጻናት ትምህርታቸውን በሚገባ መከታተል እንደማይችሉና በሽታ ተጋላጭነታቸው የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ከሚያገኙ ህጻናት ጋር ሲነጻጻር እጅጉን ሰፊ እንደሆነ አመልክቷል። የአዕምሮ እድገት ውስንነት በማምጣት አቅማቸውን በሚገባ አውጥተው እንዳይጠቀሙ ያደርጋል። ህጻናት በምግብ እጦት መቀንጨራቸውን ዩኒሴፍ የህጻናት መብቶች ጥሰት ሲል ይገልጸዋል። ይህም ትውልድ ለአንድ ሀገር የሚኖረው ድርሻ እንዲኮስስ ያደርጋል። መቀንጨር ድምጽ የለውም ኢኮኖሚን በአንድ ጊዜ አያቃውስም ወይንም ህዝብ ላይ ቶሎ ስጋትን አይጭርም ግን ጉዳቱ አያሌ ነው። በዓለም ላይ ከአምስት ዓመት በታች ከሚገኙ ህጻናት መካከል 23 ነጥብ 2 በመቶው የመቀንጨር ሰለባ መሆናቸውን የዓለም ጤና ድርጅት መረጃ ያመለክታል። ይህ ችግር የህጻናትን አካላዊና አዕምሯዊ አቅም ከመንጠቅ ባለፈ፣ የሀገርን የረጅም ጊዜ እድገት ወደ ኋላ የሚጎትት መዋቅራዊ ሳንካ ሆኖ ቀጥሏል። በኢትዮጵያ መቀንጨርን ማጥፋት ከምግብ እና ጤና ግቦች በዘለለ ሀገር እንድትበለጽግና እንድታድግ ከሚደረገው ብሄራዊ ውጥን ጋር የተቆራኘ የህልውና ጉዳይ ነው። የምግብ እና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እድገት መሳካት የጀርባ አጥንት ለሆነው አምራች እና ተመራማሪ ሀይል ግንባታ ያለው አስተዋጽዖ ከፍ ያለ መሆኑ ይታመናል። ምንም እንኳ በሀገራችን የመቀንጨር ምጣኔ እ.አ.አ በ1990ዎቹ ከነበረበት 60 በመቶ ወደ 39 በመቶ ቢቀንስም፣ አሁንም ችግሩ ሙሉ በሙሉ ያልተወገደ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን አስከፊ አዙሪት ለመስበር በ2007 ዓ.ም የሰቆጣ ቃል ኪዳን የተሰኘ ታሪካዊ መርሃ ግብር ይፋ ተደርጓል። ይህ ታሪካዊ ቃል ኪዳን በ15 ዓመታት ፍኖተ ካርታ ውስጥ ሦስት ዋና ዋና የትግበራ ምዕራፎችን አካትቶ የያዘ ነው። የመጀመሪያው የኢኖቬሽን ምዕራፍ (2010-2013 ዓ.ም) በ40 ወረዳዎች ላይ ትኩረት በማድረግ የባለድርሻ አካላትን ቅንጅታዊ አሰራር ውጤታማነት ያረጋገጠበት ሲሆን፣ ቀጥሎ የመጣው የማስፋፋት ምዕራፍ (2014-2018 ዓ.ም) የትግበራ ሽፋኑን ወደ 314 ወረዳዎች አሳድጓል። በዚህ ምዕራፍ በ2017 በጀት ዓመት ብቻ 2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ህጻናት እና 1 ነጥብ 4 ሚሊዮን እናቶችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል። በአሁኑ ወቅት የተጀመረው የመጨረሻው የማስፋት ምዕራፍ (2019 – 2023 ዓ.ም) ደግሞ የተገኙ ልምዶችን በመቀመር እና ማህበረሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ መቀንጨርን በኢትዮጵያ ዜሮ ለማድረግ የታለመበት ወሳኝ የታሪክ ምዕራፍ ነው። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት መጋቢት 26 ቀን 2018 ዓ.ም የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን፣ ስርዓተ ምግብና ሰቆጣ ቃል ኪዳን፣ የጤና መድህን፣ የጽዱ ኢትዮጵያ የማስፋፊያ አድቮኬሲና የጤና ኤክስቴንሽን ፕሮግራም ማሻሻያ የ2018 ዓ.ም የስድስት ወራት ዕቅድ አፈፃፀምን በተመለከተ በበይነ መረብ ውይይት አካሂደው ነበር። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚ ወቅት የምግብ እና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ እድገት መሳካት የጀርባ አጥንት ለሆነው አምራች እና ተመራማሪ ኃይል ግንባታ ያለው አስተዋጽኦ ከፍ ያለ መሆኑን አንስተዋል። በውይይቱ ላይ ከተነሱት ጉዳዮች አንዱ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ነበር። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሰቆጣ ቃል ኪዳን ትግበራ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን ገልጸው በዚህም በቃል ኪዳኑ የ15 ዓመት ፍኖተ ካርታ መሰረት የመጨረሻው የአምስት ዓመት የማስፋት ምዕራፍ (2019 – 2023 ዓ.ም) የትግበራ ማስፈፀሚያ እቅድ መጽደቁን ጠቅሰዋል። በዚህም የመቀንጨርንና ሌሎች የስርዓተ ምግብ ችግሮች ምጣኔን በፍጥነት ለመቀነስ የተገኙ ልምዶች በመቀመር፣ ማህበረሰቡን በባለቤትነት የማሳተፍ ስራን ማጠናከር እንደሚገባም አንስተዋል። የሰቆጣ ቃል ኪዳን ስኬታማነት ኢትዮጵያ በዓለም ስርዓተ ምግብ ውስጥ ታሪካዊ አሻራ እንድትጥል ከማድረጉም ባለፈ፣ ጤናማ፣ ምርታማና የነገዋን ብሩህ ኢትዮጵያ የሚገነባ ብቁ ትውልድ ለማፍራት ዋስትና የሚሰጥ ነው። ይህ ጉዞ ከመንግስት የፖለቲካ ቁርጠኝነት ባለፈ፣ መላው ማህበረሰብ እና ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ድጋፋቸውን በማጠናከር ለመጪው ትውልድ የገቡትን የህልውና ቃል ኪዳን በተግባር የሚመሰክሩበት ነው። በአጠቃላይም በአሁኑ ሰዓት የህጻናት መቀንጨርን ለመከላከልም ሆነ አጠቃላይ ምግብን በዓይነትም ሆነ በጥራት በገበታ ሙሉ ለማድረግ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አነሳሽነት በመላው ሃገሪቱ እየተተገበረ የሚገኘው የሌማት ትሩፋት በዚህ ረገድ ከፍተኛ እገዛ እያደረገ መሆኑ ይታወቃል። ድህነትን ማሸነፍ ሃገራዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ግቧ የሆነው ሃገራችን በሁሉም መስክ እያስመዘገበች ያለችው ስኬት የምግብ ሉዓላዊነቷን በማረጋገጥ የዜጎችን ጤንነት በተሟላ መልኩ ማስጠበቅ የሚያስችላትም ነው።
ባሳለፍነው ሣምንት ...
May 9, 2026 738
ከሚያዝያ 25 እስከ ግንቦት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … · ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ የዘንድሮው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ባሳለፍነው ሳምንት የተከፈተ ሲሆን፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ፤ ውጤት ተኮር አመራራችን ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የኢንዱስትሪ መስፋፋት ተንጸባርቋል ብለዋል። የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት ዐቅም ከ47 በመቶ ወደ 67 በመቶ ከፍ በማድረግ፣ ባለፉት አራት ዓመታት ከ2 ሺህ 800 በላይ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ተችሏል ብለዋል። ኤክስፖው ከመላው ሀገሪቱ የተውጣጡ ንቁ አምራቾችን እና ስታርትአፖችን በጨመረ ዐቅም በአንድነት ማሰባሰቡን ጠቁመው፤ በጋራ በመሆን ይህንን ጠንካራ መነቃቃት በማስቀጠል ለሚመጣው ትውልድ ጽኑ፣ በኢንዱስትሪ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች ኢትዮጵያን እንገነባለን ብለዋል። · 85ኛው የጀግኖች ዓርበኞች በዓል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ለ85ኛው የጀግኖች ዓርበኞች በዓል ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት፤ ሚያዝያ 27 ቀን ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ዓርበኞች የፋሽስትን ወረራ የቀለበሱበትና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበሩበት በዓል መሆኑን አውስተዋል። አሁን ላይ የኢትዮጵያ ብልጽግና እንዲሳካ ብሔራዊ ዓርበኞችን ይፈልጋል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የራስ ፍላጎትን፣ ባንዳነትን እና ወራሪን እምቢ የሚል ዓርበኝነት እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። የኢንዱስትሪ ዓርበኞች፣ የግብርና ዓርበኞች፣ የጸጥታ ዓርበኞች፣ የፖለቲካ ዓርበኞች፣ የንግድ ዓርበኞች፣ የዲፕሎማሲ ዓርበኞች፣ የመንግሥት አገልጋይ ዓርበኞች፣ የሕክምና ዓርበኞች፣ የትምህርት ዓርበኞች፣ ወዘተ. . . ያስፈልጉናል ሲሉም አብራርተዋል። ይህን በዓል የምናከብረው የየራሳችንን የዓርበኝነት ደረጃ በመገምገም ነው፤ በዚህም መሠረት ለኢትዮጵያ ምን ያህል ዓርበኞች ነን? ማለት ይገባናል ብለዋል በመልዕክታቸው። በተመሳሳይ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባስተላለፉት የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ዓርበኞቻችን ታሪክ የሠሩት የውስጥ ባንዳንና የውጭ ባዳን ድል ነሥተው ነው፤ እኛም የአባቶቻችን ልጆች በመሆናችን አሁንም ያንን ድል እንደግመዋለን ብለዋል። ዛሬ የዓርበኝነት ትርጉሙ ዘርፈ ብዙ ሆኗል ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የዚህ ዘመን ዓርበኝነት በሥራ መትጋትና በዕውቀት መመራት፣ የድህነትን ታሪክ ለመቀየር ቆርጦ መነሣት፣ የተሻለች የነገዋ ኢትዮጵያን በላባችን መገንባት ነው ሲሉም አስረድተዋል። ስለሆነም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በዲፕሎማሲ መስኮች ድልን እያስቀጠልን፤ በተደመረ ዐቅም ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ማማ የሚያወጣ የዘመኑ ዓርበኛ ልንሆን ይገባል ነው ያሉት። · የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጥረት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ሱልልታ ወረዳ በ2 ሺህ 150 ሔክታር መሬት ላይ የለማ የስንዴ ማሳን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት የጎበኙ ሲሆን በወቅቱም፤ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የጀመርነው ጥረት በላቀ ውጤት ቀጥሏል ብለዋል። · የኢትዮጵያና አዘርባጃን ግንኙነት በይበልጥ መጠናከር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት ከኔዘርላንድስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሮብ ጄተን ጋር ውጤታማ የሥልክ ውይይት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ መመክራቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ በተለያዩ ዘርፎች ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚያስችሉ መንገዶች ላይ ሐሳብ ተለዋውጠናል ብለዋል። ·የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት፤ የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ በሚል መሪ ሐሳብ ባለፉት ዓመታት በሚዲያ ዘርፍና ተቋማት ላይ የተመዘገቡ ስኬቶች የቀረቡበት የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በዚሁ ወቅትም፤ ባለፉት ስምንት ዓመታት የሚዲያ ምኅዳሩን በዴሞክራሲያዊ ዐውድ ለመዋጀት በወሰድነው እርምጃ ለሀገር ግንባታ የሚረዳ መሠረት ተጥሏል ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። ይህ ውጤት እንዲቀጥልም ሚዲያዎች ከዋልታ ረገጥነትና ከጽንፈኝነት ወጥተው በእውነት ላይ የተመሠረተ ትርክት በመገንባት፣ ለጋራ ማንነትና ለብሔራዊ መግባባት በቁርጠኝነት ሊሠሩ እንደሚገባ አሳስበዋል። ሚዲያዎቻችን በሰው ሠራሽ አስተውሎት እና በጥናት የታገዘ ጥልቅ ትንተና በማቅረብ፣ ከአርዕስት ሽያጭ ባለፈ ለሀገር አጀንዳዎች ትኩረት መስጠት ይኖርባቸዋልም ነው ያሉት። ተግባራቸውም በዓላማ፣ በዕይታ፣ በሙያዊ ብቃትና ለሕዝብ ቅርብ በመሆን ላይ ተመስርቶ፣ ሚዛናዊነትን በጠበቀ መልኩ ለሀገር ብልጽግና መንገድ ጠራጊና ችግር ፈቺ ሆነው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል። · ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) በጂቡቲው ፕሬዚዳንት በዓለ ሢመት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ባሳለፍነው ሳምንት በተመራጩ የጂቡቲ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጊሌ በዓለ ሢመት ሥነ-ሥርዓት ለመታደም ወደ ጅቡቲ አቅንተዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ባስተላለፉት መልዕክትም፤ ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ለሀገራቸው የሚሰጡት አገልግሎት ሁለንተናዊ እድገትን እንዲያስቀጥል ልባዊ ደስታዬንና መልካም ምኞቴን ልገልጽ እወዳለሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ እና በጂቡቲ መካከል ያለው የቆየ ወዳጅነት እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለሕዝቦቻችን የጋራ ብልጽግና እንዲሁም ለቀጣናችን ሰላምና መረጋጋት መጠናከር መሰረት እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል በመልዕክታቸው። · የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መመረቅ ሪዞርቱ ባሳለፍነው ሳምንት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የተመረቀ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅትም ለባሕር ዳርና ለአካባቢው ዘርፈ ብዙ ትሩፋት ይዞ የመጣ መሆኑን ተናግረዋል። የፈለገ ግዮን ኢኮ ሪዞርት መንግሥት ለቱሪዝም መዳረሻዎች የሰጠው ትኩረት ምን ውጤት እንዳመጣ በገሐድ የሚነበብበት ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸው፤ የአካባቢውን የቱሪዝም መሥመርና ሠንሠለት የሚያጠናክር ማረፊያና መዳረሻ ነው ብለዋል። ሪዞርቱ ዘመናዊ እና ቅንጡ የእንግዳ ማረፊያዎች፣ የመዝናኛ ሥፍራዎች፣ ሱቆች፣ አምፊ ቴአትር እና መሰል መሠረተ ልማቶችን አሟልቶ ጣናን ተንተርሶ የተሠራ መሆኑንም አብራርተዋል። በተመሳሳይ ባሳለፍነው ሳምንት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚያው በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ደረጃውን ያሟላ Four Points by Sheraton ሆቴል የግንባታ ፕሮጀክት በይፋ አስጀምረዋል። በርካታ አገልግሎቶችን አሟልቶ በ18 ወራት ግንባታው የሚጠናቀቀው ይህ ሆቴልም የግል ባለ ሀብቱ በሀገራችን የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ውስጥ ያለውን ሚና የሚያሳይ ነው ብለዋል። ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በተለያዩ ዘርፎች እያመጣ ያለውን ለውጥ አድንቀው፤ ይህ የሆቴል ግንባታም ለባሕር ዳር በጸጋ ላይ ጸጋ የሚጨምር መሆኑን ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ4ኛው የኢትዮጵያ ታምርት ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ማጠቃለያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሰላፍነው ሳምንት ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአራተኛው የ"ኢትዮጵያ ታምርት" ዓለም አቀፍ ኤክስፖ ማጠቃለያ ላይ የተመለከትናቸው የጥራትና የፈጠራ ውጤቶች የሀገራችንን የማምረት ዐቅም የሚያረጋግጡ ናቸው ብለዋል። ኢትዮጵያ ታምርት የሉዓላዊነታችን መሠረት የብልጽግናችን ምሦሶ ነው ያሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ኢትዮጵያ በኢንዱስትሪ ዘርፍ እያሳየችው ያለው ተጨባጭ ዕድገት የብልጽግናችን ማብሠሪያ እየሆነ ይገኛል ሲሉ ገልጸዋል። የሀገር ሉዓላዊነትና ነጻነት በምልዓት የሚረጋገጠው በምርት ራስን በመቻል መሆኑን በመገንዘብ የተጀመረው ይህ ንቅናቄ፤ ተኪ ምርትን በማሳደግ፣ የፋብሪካዎችን ዐቅም በመገንባት እና የሥራ ባህልን በመለወጥ ረገድ ከፍተኛ ስኬት ማስመዝገቡን አስታውቀዋል። መንግሥት ለዘርፉ ምቹ ፖሊሲዎችንና ድጋፎችን ማመቻቸቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠው፤ ቀጣዩን ኤክስፖ ይበልጥ በፈጠራና በስብጥር የላቀ ለማድረግ እንሠራለን ሲሉ አመላክተዋል። #Ethiopian_News_Agency #ባሳለፍነው_ሳምንት #ኢዜአ
የ471 ሚሊዮን ተከታዮች ባለቤት የሆኑ የ30 ሀገራት ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሚሳተፉበት ታሪካዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ
May 6, 2026 698
በመጀመሪያው የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS 2026) ላይ ለመሳተፍ፣ ከ30 የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡና በአጠቃላይ 321 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው 61 ታዋቂ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ወደ አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል። እነዚህንም 150 ሚሊዮን ተከታዮች ያሏቸው 120 ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ የይዘት ፈጣሪዎች ይቀላቀሏቸዋል። ታሪካዊው ጉባኤ ነገ እና ከነገ በስቲያ በአድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ጉባኤው በፐልስ ኦፍ አፍሪካ ሚዲያ እና በኤጂኤ ቴክ ኢንተርፕራይዝ የጋራ ትብብር የተዘጋጀም ነው። በአፍሪካ የዲፕሎማሲ ማዕከል አዲስ አበባ የሚካሄደው ይህ ጉባኤ የአፍሪካን ዲጂታል የወደፊት ዕጣ ፈንታ እንደገና ለመቅረጽ ያለመ ነው። ጋናዊው ታዋቂ ዩቲዩበር እና የዲጂታል ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ በብዙዎች ዘንድ የሚታወቅበት ስም ነው) ዛሬ ማለዳ አዲስ አበባ ገብቷል። ሴራሊዮናዊው ቦይዜ ክሪሽ፣ ቤኒናዊቷ ሬጌ ቦይዘር፣ ሴኔጋላዊው ጃው ኬቹፕ እና ስዊዛላንዳዊው ጎጎ እስዋቲኒ ኤምኤም ሌሎች ለጉባኤው የገቡ የዲጂታል ሚዲያ ተጽእኖፐ ፈጣሪዎች ናቸው። የማህበራዊ ሚዲያ ተፅእኖ ፈጣሪዎቹ በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል። ጉባኤው በአፍሪካ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የሚሰባሰቡበት፣ ስለራሳቸውና ስለ አፍሪካ የሚናገሩበት፣ እንዲሁም ስለ ይዘት ፈጠራና ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች የሚወያዩበት መድረክ ነው። ይህም ተጽእኖ ፈጣሪዎቹን በአንድ መድረክ የማገናኘት ትልቅ አጋጣሚን ፈጥሯል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በመጠቀም የይዘት ፈጣሪነት የወደፊት ሁኔታ፣ የአፍሪካ አዎንታዊ ገጽታን መገንባት እና የዲጂታል ተጽዕኖን ከአፍሪካ ህብረት የ2063 አጀንዳ ጋር ማጣጣም በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሶስት የከፍተኛ ደረጃ የፓናል ውይይቶች ይካሄዳሉ። ጉባኤው "በችግር ላይ የተመሰረተ" ዘገባን በእውነተኛ የአፍሪካ የዕድገት ታሪኮች ለመተካት የታለመ ስትራቴጂካዊ እርምጃ መሆኑም ተመልክቷል። የአፍሪካ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን ቱሪዝም በከፍተኛ ሁኔታ የማስተዋወቅ እድሉ ሰፊ ነው። እነዚህ የይዘት ውጤቶች የአፍሪካን መልካም ገጽታ ለዓለም፣ የኢትዮጵያንም መልካም ገጽታ ለአፍሪካውያን ማሳየት የሚችሉ ናቸው። ጉባኤው ሐሙስ ዕለት በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚጀመር ሲሆን፣ ከ470 ሚሊዮን በላይ የዲጂታል ተከታዮች አይኖች በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ላይ አርፈዋል። ይህም አፍሪካ የራሷን ታሪክ ራሷ መተረክ የጀመረችበት አዲስ ዘመን ማሳያ ሆኗል።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 5302
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 3407
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 9197
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 7681
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
የከተማ ግብርናን ከጤና ሙያው ጋር ያጣመረው ወጣት
May 14, 2026 124
በቀደሰ ተክሌ (ከሚዛን አማን) የሰው ልጅ የሕይወት ኡደት በጊዜ የታጠረ ነው። የሰውነት ሚዛን ተለክቶ ውብ ሆኖ የሚገኘው ደግሞ በዚህ የጊዜ ምጣኔ ውስጥ ስኬታማ ሥራ ሰርቶ ተገቢው ቦታ ላይ ሲገኙ ብቻ ነው። ጠንካራ ሰዎች በዕድሜ ዘመናቸው የተሰጣቸውን ጊዜ በአግባቡ ተጠቅመው ስኬት ላይ ይደርሳሉ። ለጊዜ ብዙም ትርጉምና ዋጋ የማይሰጡ ሰዎች ደግሞ እንቅስቃሴያቸውን በጊዜ ስለማይገደብና በዚያው ልክ ተሯሩጠው ስለማይሰሩ ስኬታማ ሳይሆኑ ዘመናቸውን በችግር ያሳልፋሉ። ሰው ሲፈጠር ይህን በማመዛዘን የተሻለውን መንገድ ይጠቀም ዘንድ ደግሞ አዕምሮ ተሰጥቶታል። ማንም ሰው በኑሮ ከመመራት ይልቅ ራሱ ኑሮን መምራት የሚችለው ጠንክሮ ሲሰራ ነው። የአንድ ጠንካራ የሥራ ሰው አንዱ መለኪያ ደግሞ የጊዜ አጠቃቀሙ ነው። ጊዜውን በማብቃቃት ካለው ሥራ ተጨማሪ ሥራ ፈጥሮ የሚሰራና ለበለጠ የሚተጋ ስኬታማ ሕይወትን መምራት ይችላል። በሚዛን አማን ከተማ ኢዜአ ያነጋገርው ወጣት ይህን በተግባር በማረጋገጥ ለሌሎች ምሳሌ የሚሆን ነው። ወጣት ዳዊት ባይቴንስ ይባላል። ከተሰማራበት የጤና ዘርፍ ጎን ለጎን ባለው ትርፍ ጊዜ በከተማ ግብርና ሥራ ተሰማርቶ ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ይገኛል። ሰርቶ ለመለወጥ ካላው ፍላጎትና ቁርጠኝነት የተነሳ በሕይወቱ ምንም አይነት ጊዜ እንዲባክንበት አይፈልግም። እያንዳንዷን ሰዓትና ደቂቃ ትርጉም ባለው መልኩ ለሥራ ያውላል። ይህ የመነጨው ደግሞ ከሥራ ወዳድነቱ ነው። ሲሰራ ውሎ ሲሰራ ቢያድር ደከመኝና ሰለቸኝን አያውቅም። ለእዚህ ባህሪው እርሾ የሆነው ደግሞ በልጅነቱ ወላጆቹን በግብርና ሥራ እያገዘ ማደጉ ነው። በትምህርቱም ወደ ኋላ ሳይል ጠንክሮ በመማር ስኬታማነቱን አስመስክሯል። የኮሌጅ ትምህርቱን በፋርማሲ የተመረቀው ወጣቱ በአሁን ወቅት በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ቲቺንግ ሆስፒታል በጤና ባለሙያነት እየሠራ ይገኛል። የጤና ተቋም ሥራው ቀንና ማታ በፈረቃ የሚሰራ በመሆኑ ከሆስፒታል ሥራው ውጪ ሲሆን ከተማ ወጥቶ በመዝናናት አሊያም በዋዛ ፈዛዛ የሚያሳልፈው ጊዜ የለውም። ከጤና ሥራው ጎን ለጎን በቤቱ ዙሪያ ያለውን ባዶ መሬት እያለማ ይገኛል። የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን ተከትሎ በተለይ ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ይህን የግብርና ልማት ስራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። የግብርና ሥራውን የጀመረው በጤና ሙያ ሥራው በወር ከሚያገኘው ደመወዝ ባሻገር ተጨማሪ የገቢ ምንጭ ለማግኘት አስቦ ነው። "የግብርና ምርቱ ለቤት ውስጥ ፍጆታ ባውለው እንኳ ወጪዬን ይቀንሳል" የሚለውም ሌላው መነሻ ምክንያቱ ነበረ። በዚህም ባለው ጠባብ መሬት ላይ ቆስጣ፣ ጥቅል ጎመን፣ ካሮትና መሰል የጓሮ አትክልቶችን አልምቶ በመጠቀም "ምግቤን ከጓሮዬ" የሚለውንም ንቅናቄ በተግባር አሳይቷል። በጓሮ ያለማቸውን ምርቶች ለቤተሰብ ፍጆታ ማዋሉም ከወጪ እንደታደገው ነው የገለጸው። የአካባቢው መሬት ያለስስት ከሚያበቅላቸው ፍራፍሬዎች መካከል ሙዝ በቀዳሚነት ይጠቀሳል። ወጣት ዳዊትም በጓሮ አትክልት የጀመረውን ሥራ በማስፋት በቤቱ ዙሪያ የሙዝ ልማት ስራውን አጠናክሯል። የሙዝ ምርቱም ከቤት ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለገበያም እያቀረበ ነው። ዛፉም ጥላ ሆኖ እያገለገለው ነው። ሁሌም ለተጨማሪ ሥራ የሚተጋው ይህ ባለ ራዕይው ወጣት ምርጥ የቡና ዘር ከግብርና ባለሙያዎች በመውሰድ ችግኝ አዘጋጅቶ ለአርሶ አደሮች ያሰራጫል። አምና የቡና ችግኝ ተከላ ወቅት ከ15 ሺህ በላይ የቡና ችግኞችን በጓሮው አዘጋጅቶ በመሸጥ ተጠቃሚ ሆኗል። ከጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ባሻገር በቆሎ በማልማትም ተጠቃሚነቱን እያሳደገ ነው። ወጣት ዳዊት ባለው ጠባብ የከተማ ማሳ ላይ እነዚህን ልማቶች እያከናወነ ያለው በአንድ ጊዜ አይደለም። እንደ የአዝመራው ተስማሚነት አፈራርቆ የማልማት ጥበብንም ተክኗል። በቆሎ ደርሶ የተነሳበት ማሳ ላይ ሌሎች አትክልቶችን ያለማል። በሌላ በኩል ደግሞ ጥምር የእርሻ ሥርዓትን በመከተል በሙዝና ሌሎች ፍራፍሬዎች ስር ባለ ክፍት ቦታ ላይ ቡና ያለማል፤ የአትክልት ችግኞችንም ያዘጋጃል። ይህ ብልህነት የተሞላው የከተማ ግብርና ልማት ሥራው የከተማ ቤቱን የገጠር ሞዴል አርሶ አደር ማሳ አስመስሎታል። ወደፊት የተቀናጀ የግብርና ልማት ጣቢያን የመፍጠር ዓላማ እንዳለው የገለጸው ወጣቱ፣ በቅርቡም በንብ ማነብ ሥራ ውስጥ ለመሰማራት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው የተናገረው። ለዚህም የቀፎ ግዥና የቀፎ ማስቀመጫ ቦታ ዝግጅት ሥራ ላይ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት በገበያ እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት መቋቋም የሚቻለው ሰርቶ ውጤታማ ሲኮንና ገቢን ማሳደግ ሲቻል ነው የሚል እምነት አለው። ወጣቱ እንደሚለው ምርት የሚያመርት ሰው እየበዛ ሲመጣ ገበያው ይረጋጋል። በመሆኑም ሰዎች ሁሉንም ነገር ከገበያ ከመግዛት ይልቅ ባላቸው ትንሽ መሬት ላይ የተወሰነ ምርት በማምረት ለቤት ውስጥ ፍጆታ እንዲጠቀሙ ይመክራል። ከመደበኛ የመንግሥት ሥራው ጎን ለጎን የተሰማራበት የከተማ ግብርና ልማት ሥራ ወጪውን ከመቆጠብ አልፎ ተጨማሪ ገቢ እያስገኘለት በመሆኑ በቀጣይም ልማቱን ለማጠናከር ሞራል እንደሆነው ተናግሯል። እሱ እንደሚለው ከሆነ በአካባቢው በርካታ ወጣቶች የቤተሰቦቻቸውን ማሳ ትተው በከተማ ያለ ሥራ ጊዜያቸውን ሲያሳልፉ ማየት የተለመደ ነው። ነገር ግን ነገን የተሻለ ለማድረግ ዛሬ የወጣትነት ጊዜን ጠንክረን ልንሰራ ይገባል ይላል። ወጣቶችም ያላቸውን ጉልበትና ጊዜ በመጠቀም ሀብት ማፍራት የሚያስችላቸውን ሥራ መሥራት እንዳለባቸው ይመክራል። በተለይ የእርሻ መሬት ያላቸው ወጣቶች በግብርና ሥራ ራሳቸውን መለወጥ፣ ቤተሰቦቻቸውን መመገብ፣ ገበያ ማረጋጋትና በሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ውስጥ አሻራቸውን ማሳረፍ እንዳለባቸው ነው የገለጸው። የሚዛን አማን ከተማ ግብርና፣ አካባቢ ጥበቃና ኅብረት ሥራ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዘሪሁን መንግሥቱ የወጣት ዳዊት ታታሪነት ለብዙዎች ተሞክሮ እንደሚሆን ነው የገለጹት። በተለይ የከተማ ግብርናና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮችን መሠረት በማድረግ ያከናወናቸው ተግባራት በትንሽ መሬት መስራት ከተቻለ ገበያን ማረጋጋት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ነው ብለዋል። ጽህፈት ቤቱ ወጣቱንና የእሱን ፈለግ ተከትለው የሚሠሩ ወጣቶችን ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። ኃላፊው እንዳሉት በአሁኑ ወቅትም በሌማት ትሩፋት የሥራ ዘርፎች ወጣቶች በብዛት እንዲሰማሩ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው። በራስ ተነሳሽነት ያላቸውን ጊዜ አብቃቅተው ወደልማት የገቡ እንደ ወጣት ዳዊት ያሉ ወጣቶች ቢበራከቱ ለግብርናው ዘርፍ ኢኮኖሚ የሚኖራቸው አዎንታዊ ሚናም የጎላ ነው። ማንም ሰው ኑሮን አሸንፎ ወጤታማ ለመሆን እንደ ወጣት ዳዊት በሥራ መትጋት ይኖርበታል። ወቅቱ ያለን ጊዜ አብቃቅቶ ተጨማሪ ሥራዎች መስራት የግድ የሚልበት ወቅት ነው። ለብዙዎች በቅጥር ሰርቶ በሚገኝ ገቢ ብቻ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት አስቸጋሪ በመሆኑ አማራጮችን መጠቀም ያስፈልጋል። ለእዚህም እንደወጣት ዳዊት በዙሪያችን ምን ሀብት አለ በሚል ለይቶ ጥቅም ላይ ማዋል ያስፈልጋል። ጊዜን ከጉልበት ጋር አጣምሮ መጠቀምም እንዲሁ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው። የሰው ልጅ በሕጻንነትና በእርጅናው ዕድሜ የፈለገውን ማድረግ፣ ወጥቶና ወርዶ ሀብት ማፍራት አይችልም። ይህ የሚሆነው በወጣትነትና በጎልማሳነት ዕድሜ ብቻ ነው። በመሆኑም ለነገ ያለምነውን በጊዜው ማሳካት የምንችለው ዛሬ ጠንክረን ስንሰራ ነው። ስለዚህ የወጣትነት ዕድሜያችንን በውጤት ለማጀብ ጠንክረን ልንሠራበት ይገባል። ሥራ ክቡር ከመሆን በላይ ጠንክሮ የሰራውንም ያስከብራል፤ ይለውጣል፤ ሰላም !
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ
Apr 25, 2026 1566
አዲስ ምዕራፍ- ከዜጎች ደጃፍ እስከ እጅ ስልክ በቁምልኝ አያሌው በአንድ ሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት ውስጥ የመንግሥት አገልግሎት ጥራት ከሰው ልጅ የደም ዝውውር ጋር ይመሰላል። በሌላ በኩልም፣ የአገልግሎት አሰጣጥ የዜጎች የሞራልና የፍትሕ ልዕልና መለኪያ ተደርጎ ይወሰዳል። መንግሥት ለዜጎቹ የሚያቀርባቸው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶች ጥራት፣ ፍጥነትና ፍትሐዊነትም የሀገርን ፖለቲካዊ መረጋጋትና የኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚበይኑ መጋቢዎች ናቸው። ታዋቂው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ምሁር ፍራንሲስ ፉኩያማ እንደሚሉት፤ "የመንግሥት ተቋማት ብቃት (State Capacity) ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለዴሞክራሲ መረጋጋት መሠረት ነው።" መልካም አስተዳደር የሰፈነበት ሥርዓት የሕዝብ አመኔታን በመጨመርና ማህበራዊ እኩልነትን በማስፈን ለዘላቂ ሰላም የማይተካ ሚና ይጫወታል። ይህም ሀገርን በኢኮኖሚ ለማሳደግና ለማበልጸግ በሚደረገው ርብርብ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። ሌላኛው የኢኮኖሚክስ ምሁር ጆሴፍ ስቲግሊዝ በበኩላቸው፤ "ውጤታማ መንግሥት ማለት ዜጎቹን በግልጽነትና በተጠያቂነት የሚያገለግል፣ በሂደቱም የህዝብ አመኔታን መገንባት የሚችል ነው" ሲሉ አጽንኦት ይሰጣሉ። በአንፃሩ፤ የአገልግሎት ክፍተትና የአስተዳደር ጉድለት ለሀብት ብክነት፣ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር በር በመክፈት ዜጎችን ለከፍተኛ ምሬት በማጋለጥ አመኔታን ያሳጣል። ይህንን እንግልት ለማቃለል ሀገራት አገልግሎትን የሚያዘምን ፈጣንና ቀልጣፋ የዲጂታል ሥርዓት እየዘረጉ ይገኛል። ኢትዮጵያም ይህንን መርህ በመከተል ዘገምተኛ አሰራር ከወለደው የ"እጅ መንሻ" (ሙስና) ልምምድ በመላቀቅ ዘመናዊና ግልጽ የዲጂታል ሽግግርን በማፋጠን ላይ ትገኛለች። ይህም ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ሉዓላዊነትን የሚያጎናጽፍ ወሳኝ የልማት ምኅዳር እየፈጠረ ነው። የመደመር መንግሥት ዕሳቤ፤ በተቋማት ግንባታና አገልግሎት ጥራት!! በመደመር ፍልስፍና ውስጥ የመንግሥት ተቋማት ግንባታ የሀገር ግንባታ የጀርባ አጥንት ተደርገው ይወሰዳሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመደመር መንግሥት መጽሐፋቸው ገፅ-129 እንዳሰፈሩት፤ ''የመደመር መንግሥት ከውስብስብ ቢሮክራሲ ተላቀው የመደመር ለውጥ የሚያመጡ ተቋማት ውቅር ነው። በመሆኑም ተቋማት ከተለመደ ''የሥራ ሂደት መር'' አካሄድ መላቀቅ ይጠበቅባቸዋል። አደረጃጀታቸውንም ለሚያገለግሉት ሕዝብ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያገኙ ወደሚረዳቸው አደረጃጀት መሸጋገር አለባቸው። ለመደመር መንግሥት ሕዝቡን ማገልገል ከቢሮክራሲ በላይ ነው'' በሚል አስገንዝበዋል። ለዚህም ነው ተቋማት የሰውን ልጅ አቅምና ዕውቀት አቀናጅተው ለጋራ ዓላማ የሚያውሉ ሕያው መዋቅሮች ናቸው የሚባለው። በመደመር ዕሳቤ ጠንካራ ተቋማት ማለት በግለሰቦች ፍላጎትና ስሜት ላይ ያልተመሰረቱ ይልቁንም በሕግና በሥርዓት የሚመሩ መሆን አለባቸው። በመደመር መንግሥት መፅሐፍ ገፅ-130 እንደሰፈረው፤ ''በየተቋማት ያሉ የመንግስት ሠራተኞች ሕዝቡን ከቢሮክራሲው በላይ የሚመለከቱ እንዲሆኑ ይጠበቃል። አገልጋይነትን የተላበሱ መሆን ይጠበቅባቸዋል።'' መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ይህንን ዕሳቤ በተግባር የሚተረጉም ነው። ግለሰባዊ ንክኪን በመቀነስና አሰራርን በቴክኖሎጂ በመተካት ተቋማት ከግለሰቦች መልካም ፈቃድ ይልቅ በሥርዓት ወደሚመራ ተቋማዊ ብቃት መሸጋገርን ያሳያል። የአገልግሎት ጥራትና የዜጎች ክብር በመደመር መንግሥት ትልቅ ትኩረት የተሰጠው ሰው ተኮር የልማት ነጥብ ነው። ''ለሕዝቡ ቅድሚያ የማይሰጥ አመራርም ሆነ ሠራተኛ የመደመር መንግሥት ወገን አይደለም። እንዲህ ዓይነቱን ግለሰብም ሆነ አይቶ እንዳላየ በማለፍ የማይታገል ሰው በመደመር መንግሥት ውስጥ ዕድል ፈንታ የለውም'' በሚል በመደመር መንግሥት መፅሐፍ የሰፈረው ግልፅ መልዕክትም መንግሥት የአገልጋይነት እንጂ የገዥነት መንፈስ ሊኖረው እንደማይገባ በጉልህ ያመላክታል። የአገልግሎት ጥራት መሻሻልም ዜጎች በሀገራቸው ተቋማት ክብራቸውና መብታቸው ተጠብቆ ያለ እንግልት የሚገለገሉበትን ምኅዳር ይፈጥራል። በተቋማት አገልግሎት የዜጋ እርካታ (Citizen Satisfaction) ዋነኛ የፖለቲካል ኢኮኖሚ ዕድገት ምንጭ ተደርጎ ይወሰዳል። በመደመር መንግስት ዕይታ የብልሹ አሰራር መታገያ ስትራቴጂ በጩኸትና በቅጣት ብቻ የሚመጣ ሳይሆን አሰራርን በማዘመን ጭምር ነው። የመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ሌብነትን የማይጋብዝ ሥርዓት የፈጠረ (Systemic Prevention) ስትራቴጂክ አቅጣጫ ሆኗል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማትና የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመደመር መንግሥት መሠረታዊ የተቋማት ሪፎርም ትግበራን (Institutional Reform) የሚያሳዩ ናቸው። ይህም ተቋማትን ከመዋቅራዊ ሽግግርና ለውጥ ባለፈ የተቋማት ሠራተኞችን ከመንግሥት ሠራተኛነት ወደ ሕዝብ አገልጋይነት የአስተሳሰብ ለውጥ (Paradigm Shift)፣ ኋላ ቀር አሰራርን በዲጂታል የቴክኖሎጂ አማራጭ የሚተካ (Technology Integration)፣ አገልግሎትን ለሁሉም ዜጋ በእኩልነት፣ በቅርበትና ፍትሐዊነት የማዳረስ ፅንሰ ሃሳባዊ ግብን በተግባር ያረጋገጠ ሆኗል። ይህ ታላቅ ተግባርም ኢትዮጵያ በመደመር ዕሳቤ የጀመረችውን የብልፅግና ጉዞ የሚያፋጥንና ዜጎች በመንግሥታቸው ላይ ያላቸውን አመኔታ በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ መሠረት ነው። የዲጂታል ኢትዮጵያ ርዕይና ስትራቴጂክ ሽግግር!! ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው ለግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና አይሲቲ ዘርፎች ወሳኝ የልማት ዕድሎችን ፈጥሯል። በዚህ ሰፊ መርሃ ግብር ውስጥ የዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ እንደ ዋነኛ የብልፅግና ምሰሶ ተወስዷል። በ"ዲጂታል ኢትዮጵያ-2025" ስትራቴጂ የተጀመረውና በስኬት የተጠናቀቀው ጉዞ ዛሬ ላይ ሀገሪቷን ወደ "ዲጂታል ኢትዮጵያ-2030" አሸጋግሯታል። ይህ ስትራቴጂ ዜጎች ካሉበት ቦታ ሆነው አገልግሎት የሚያገኙበትን ምኅዳር በመፍጠር በሰው ንክኪ የሚፈጠሩ ብልሹ አሰራሮችንና የአገልግሎት እንግልትን በማስቀረት ረገድ ታሪክ ቀያሪ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። የልማትና ዕድገት ምሁሩ አማርትያ ሴን፤ "ልማት የሰው ልጅ ምርጫና የመገልገያ አቅሙን ማስፋፊያ መሣሪያ ነው" በማለት የሚገልጹት ስለልማት ከፍ ያለ ትርጉም ይሰጠናል። የኢትዮጵያ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትም ዜጎች የሚያጋጥሟቸውን እንግልቶች በማስወገድ ትኩረታቸውን በልማት ላይ እንዲያደርጉ በማስቻሉ፣ ይህንን የልማት ፅንሰ-ሃሳብ በተግባር እየተረጎመ ይገኛል። የአንድ ጣሪያ በረከትና የቅልጥፍና ተምሳሌት - መሶብ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚያዚያ 18/2017 ዓ.ም የተመረቀው የፌዴራል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ለተቋማዊ ሽግግር መነሻ ሆኗል። ቁልፍ የመንግሥት አገልግሎቶች በአንድ ጣሪያ ስር መሰባሰባቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራቱን ወደ ከፍተኛ ደረጃ አሸጋግሮታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ይህ ማዕከል ዜጎች ጊዜያቸውንና ሀብታቸውን በመቆጠብ ጥራት ያለው አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ ለዘመናት የቆየውን ምሬት የሚቀለብስ የሪፎርም እርምጃ ነው። በወቅቱ ሲጀመር 12 የነበሩት ፌዴራል ተቋማት፤ አሁን ላይ 23 በመሻገር አገልግሎታቸውን እየሰጡ ይገኛል። ይህም የዜጎች እንግልት በማስቀረት ታላቅ እፎይታን ፈጥሯል። እነዚህ ተቋማት፦ የብሔራዊ መታወቂያ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት፣ የገቢዎች ሚኒስቴር፣ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የትምህርት ስልጠና ባለስልጣን፣ ኢትዮ ፖስታ፣ ኢትዮ ቴሌኮም፣ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን፣ የኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ የጤና ሚኒስቴር፣ የፍትሕ ሚኒስቴር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ የትምህርት ምዘናና የፈተናዎች አገልግሎት ናቸው። መነሻውን አዲስ አበባ ከተማ የፌዴራል ተቋማት በአንድ በማሰባሰብ የጀመረው ይህ አገልግሎት አሁን ላይ በሁሉም ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እየሆነ ነው። ይህም የመልካም አስተዳደር እጦትን የሚያቃልል ታሪክ ቀያሪ መደላድል ፈጥሯል። አዲስ መሶብ - የተንቀሳቃሽ አገልግሎት ተስፋ!! በመዲናችን ሚያዚያ 14 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው መሶብ የአንድ ማዕከል ተንቀሳቃሽ አገልግሎት፣ "መንግሥት ወደ ዜጋው ይሄዳል" (Citizen-Centric Governance) የሚለውን የዘመናዊ አስተዳደር ፍልስፍና በተግባር ያሳየ ነው። በፀሐይ ኃይልና በፈጣን ኔትወርክ የታገዘው ይህ ተንቀሳቃሽ አገልግሎት የስምንት ተቋማትን 36 ዓይነት አገልግሎቶች ወደ ህዝቡ ደጃፍ በማምጣት ረገድ ተምሳሌት ሆኗል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅቱ እንደገለጹት፤ ከተማዋ ለዘመናት ስር በሰደደ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር ተተብትባ ብትቆይም፣ የመሶብ ዲጂታል አገልግሎት ግን ለተገልጋዩ እውነተኛ እፎይታን ይዞ መጥቷል። የቀጣዩ ዘመን ግብ - አገልግሎትን በእጅ ስልክ!! ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቀጣይ አገልግሎቱን ወደ ዜጎች የእጅ ስልክ የማሸጋገር ግብ መኖሩን አረጋግጠዋል። ይህ ሽግግር ሙሉ በሙሉ ስኬታማ እንዲሆን የዲጂታል መታወቂያ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። ዜጎችን በዲጂታል መታወቂያ መለየት መቻሉ የአሰራር ግልጽነትን ከመጨመሩም በላይ መንግሥት አገልግሎቱን ለማን እየሰጠ እንደሆነ በትክክል እንዲያውቅ ያስችለዋል። ተገልጋይን አክብሮ፣ ስርቆትና "እጅ መንሻን" አስቀርቶ አገልግሎት መስጠት የባህል ለውጥ ይጠይቃል። ለዚህም ሲቪል ሰርቪሱን በማዘመን፣ ቴክኖሎጂንና የባህል ለውጥን በማቀናጀት የእጅ መንሻን ባህል የሚያስቀር መሠረት እየተጣለ ይገኛል። ለዚህ ለውጥ ስኬት እያንዳንዱ ዜጋና ተቋም የበኩሉን ሊወጣ ይገባል። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲጂታል ልማት መርሃ ግብርና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሙስናን በማድረቅ ፍቱን መፍትሔ እየሰጡ ይገኛሉ። ይህም ሀገሪቷን ከቆየችበት የ"እጅ መንሻ" አዙሪት አውጥቶ፣ ተቋማት ለዜጎች ክብር ወደሚያሳዩበት አዲስ ምዕራፍ አሸጋግሯታል። ይህ ጉዞ እመርታ ነው፤ ግልጽነትን በማንገስና የህዝብን እርካታ በመጨመር የብልጽግና ጉዞውን የሚያፋጥን ነው።