ቀጥታ፡

ፒኤስጂ የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ባለቤት ሆነ

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 6/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ መርሐ ግብር ፒኤስጂ አስቶንቪላን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ማምሻውን በኦስትሪያ በሚገኘው ሬድ ቡል አሬና በተካሄደው ጨዋታ ክቪቻ ክቫራትስኬሊያ እና ዴዚሬ ዱዌ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

የ17 ዓመቱ ታዳጊ ብሪያን ማጆ የአስቶንቪላ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ጨዋታው አዝናኝ እና በርካታ የግብ እድሎች የተፈጠሩበት ነበር።

ፒኤስጂ የአውሮፓ አሸናፊ አሸናፊዎች ዋንጫ አንስቷል።

በሉሲስ ኤነሪኬ የሚመራው ፒኤስጂ ባለፈው የውድድር ዓመትም ላይ ቶተንሃምን በተመሳሳይ በመለያ ምት አሸንፎ የዋንጫው ባለቤት እንደነበር የሚታወስ ነው። 

የፈረንሳዩ ክለብ የውድድር ዓመቱን የመጀመሪያ ዋንጫ አግኝቷል።

አስቶንቪላ ዋንጫውን በብቸኝነት ያነሳው  እ.ኤ.አ በ1982 ባርሴሎናን በማሸነፍ  ነበር። ከ44 ዓመት በኋላ ዋንጫውን የማንሳት ህልሙ አልተሳካም።

የ34 ዓመቱን ሶማሊያዊ ዳኛ ኦማር አርታን ጨዋታውን በዋና ዳኝነት መርቷል።

ይህም በውድድሩ የ51 ዓመታት ታሪክ ውስጥ የአሸናፊዎች አሸናፊ ጨዋታን የመሩ የመጀመሪያው የአውሮፓ ዜግነት የሌላቸው ዳኛ አድርጓቸዋል።

የአውሮፓ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የክለቦች ውድድር አሸናፊዎችን የሚያገናኝ የዓመቱ ማጠቃለያና አዲስ የውድድር ዘመን መክፈቻ መርሐ ግብር ነው።

የጨዋታው አሸናፊው ፒኤስጂ የአምስት ሚሊዮን ዩሮ የገንዘብ ሽልማት የሚያገኝ ሲሆን፥ ተሸናፊው አስቶንቪላ ደግሞ አራት ሚሊዮን ዩሮ ወደ ካዝናው ያስገባል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም