አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ በ28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎችም ተሞክሮዎቿን ታስተዋውቃለች
Nov 30, 2023 46
  አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ፦ኢትዮጵያ በዱባይ በሚካሔደው 28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎችንም ተሞክሮዎቿን ለዓለም እንደምታስተዋውቅ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ 28) በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፤ በዱባይ መካሄድ ጀምሯል። ዶክተር ፍጹም ይሄንን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት በስፍራው ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ኤግዚቢሽን በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገበችውን ስኬትና ሌሎችንም ተሞክሮዎች ለዓለም ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስራዋን በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ አውደ ርእይ/ፓቪሊዮን/ በማስተዋወቅ ላይ መሆኗንም ገልጸዋል። በ1ሺህ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ትልቅ ኢግዚብሽን በማዘጋጀት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በተጨባጭ ለውጥ እያመጣች መሆኗን የምናሳይበት ነው ብለዋል። በጉባኤውም መሪዎች ንግግር በማድረግ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚዘጋጁ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፍ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ዙሪያ ድምጿን ታሰማለች ብለዋል። በዚህም በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን በማስተዋወቅ ብሎም እያጋጠሙ በሚገኙ ተግዳሮቶች ዙሪያ የአፍሪካ ድምጽ በመሆን ትልቅ ተሳትፎ ይኖረናል ሲሉም ገልጸዋል። በዚህ ኤግዚቢሽንም በተለያዩ ዞኖች ማለትም የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ ኢንሼቲቭ እና ያስገኘውን ጥቅሞች በተመለከተ ለዕይታ ይቀርባል ብለዋል። በተጨማሪም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በማጉላት ዘላቂ የግብርና ልማት ተሳትፎዎች ላይ በማተኮር በስንዴ ልማት እምርታዊ ለውጥ የታየበት ነውም ብለዋል።
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የሙስና ወንጀልን በጋራ መከላከል ይገባል- አቶ ታዬ ደንደዓ
Nov 30, 2023 42
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት መሳካት የሙስና ወንጀልን በጋራ መከላከል ይገባል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደዓ ገለጹ። የሰላም ሚኒስቴር ሰራተኞች 20ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በማስመልከት "ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል" በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ ታዬ ደንደዓ፤ በአንድ ሀገር የሙስና መስፋፋት ለበርካታ ችግሮች ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።   የሀገር የእድገት ጸርና የህዝቦች የምሬት ምክንያት ከመሆንም ባለፈ ለሰላምና መረጋጋት እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያም የሙስና ወንጀል የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሙስና መከላከል ስራ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁላችንም በጋራ መከላከል ይጠበቅብናል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት መሳካት የሙስና ወንጀልን በጋራ መከላከል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።   የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው፤ የሙስና ወንጀል የበርካታ ችግሮች ምክንያት በመሆኑ የጋራ ትግልን የሚጠይቅ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ዘርፎችን በመለየት የመከላከልና የህግ ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በሁሉም ሴክተሮች ህብረተሰቡ የመከላከሉ ስራ አጋዥ በመሆን ሙስናን እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። የጸረ-ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ ባከናወናቸው ተግባራት 9 ቢሊየን ብር እና 4 ሚሊየን ካሬ ሜትር መሬትን ከሌብነት ማትረፍ እንደተቻለ መገለጹ ይታወቃል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመስከረም ወር የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የመክፈቻ ሥነስርዓት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መንግስት የሙስና መከላከል ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸው ይታወሳል።  
የጤና መድህን አገልግሎትን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል
Nov 30, 2023 48
ቦንጋ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ) ፦ በሀገሪቱ የጤና መድህን አገልግሎት ስርዓትን በማጠናከር ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ገለጸ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።   በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ያምሮት አንዷለም እንዳሉት፤ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት በርካታ የሀገሪቱ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። በተለይም በከተማና በገጠር መደበኛ ባልሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ዜጎች ያለምንም ስጋት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ጉልህ ሚናን እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል። በመሆኑም አገልግሎቱን ይበልጥ በማጠናከር ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ እንዲያደርግ ልምዶችን በመቀመር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ያመለከቱት። የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ከጀመረ ወዲህ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ በተለይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እፎይታን ፈጥሯል ብለዋል። በቀጣይም አገልግሎቱን ከማጠናከር አንጻር የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመድሃኒት አቅርቦትና ሌሎች ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ መንገድ እንደሚሰራ ገልፀዋል። አገልግሎቱን የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥርና ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው የህዝብን ፍላጎት ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች እንደሚጠናከሩም ተናግረዋል።   የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በበኩላቸው በክልሉ አገልግሎቱን ለማጠናከር ያሉት ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሄ ለመስጠት የንቅናቄ መድረኩ ማስፈለጉን ጠቁመዋል። በክልሉ እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ የነባር አባላት እድሳትን 95 በመቶ እንዲሁም አዲስ አባላትን የመመዝገቡ ሥራን ደግሞ 75 በመቶ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ገልጸዋል። መድረኩን የታደሙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ በበኩላቸው የጤና መድህን አገልግሎት ዜጎች ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ በመሆኑ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል። አገልግሎቱ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ዓመታዊ የጤና መድህን ወጪያቸውን መሸፈን የማይችሉ ዜጎች በመንግስት እንዲሸፈንላቸው በማድረግ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ136 ሺህ በላይ የጤና ማህበረሰብ የጤና መድህን አባላት ከነቤተሰቦቻቸው በየደረጃው የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውም ተገልጿል። የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት መድረክ ላይ ባለፈው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ወረዳዎች የዕውቅናና የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን የቀጣይ ስራን ማጠናከር የሚያስችል ስምምነትም ተፈርሟል።
የፌዴራል ድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ
Nov 30, 2023 44
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦በበቂ መረጃ የተደገፉ ስራዎችን ማከናወን ለፌዴራል ድጎማ በጀት ቀመር ማሻሻል ሂደት ቁልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች የፌደራል ድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮችን ጨምሮ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልሎችና የፌዴራል መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈሉበትን፤ እንዲሁም የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚሰጥበትን ቀመር የመወሰን፤ ከሀገራዊ ኃላፊነቶቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱም የተጣሉበትን ኃላፊነቶችና የወጡ ሕጎችን ተከትሎ የሕገ መንግሥት የበላይነት፣ ሕገ መንግስታዊነት፣ ዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሀገራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል በክልሎች መካከል ውጤታማና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ የሚረዳ የፌዴራል ድጎማና የጋራ ገቢዎች ቀመር እንዲዘጋጅ በማድረግ፤ የማከፋፈያ ቀመሮቹ በፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና በክልሎች የተመጣጠነ እድገት ላይ ያላቸዉን አንድምታ እንዲጠና በማድረግ ሰፊ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አንስቷል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አሁን ያለው ቀመርና አፈጻጸሙ እንደገና መፈተሽ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከቋሚ ኮሚቴውና ከሚመለከታቸው የፌደራል ባለድርሻ አካለት ጋር ግብዓት ለመሰብሰብ የታለመ መድረክ ነው ብለዋል፡፡ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የፊስካል ፌዴራሊዝም ሪፎርም መደረጉንና በርካታ ውጤቶች የተገኙበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡   በቀጣይም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎችን በተገቢው የሕግ አግባብ ለመመለስ ቁርጠኝነት እንደሚፈልግና ለዚህም ሁሉም ባለ ድርሻ አከላት በርብርብና በእኔነት ስሜት ሊሰራ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡ በቀጣይ ለሚደረገው የቀመር ማሻሻል ስራ ከሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ጋር ተያይዞ በጥናትና በበቂ መረጃ የተደገፉ ስራዎችን መስራት ለቀመር ማሻሻል ሂደት ቁልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡ በመደረኩ የሚነሱ አስተያየቶችና ሀሳቦች ቋሚ ኮሚቴው ለሚያዘጋጀውና ለምክር ቤት ለሚቀርበው ሀገራዊ ሰነድ ትልቅ ግብዓት ሆኖ እንደሚወሰድም ነው የገለጹት፡፡ ለቀመር ዝግጅት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ወቅታዊና ተአማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ የጋራ ስምምነት መደረሱን ተጠቅሷል። በመረጃ አቅርቦት ረገድ ሃላፊነት የተጣለባቸው የፌዴራልና የክልል ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ መቀመጡን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡            
ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የአገው ብሄረሰብ ቋንቋን ከማሳደግ በላይ ባህሉን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል
Nov 30, 2023 46
ሰቆጣ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ) ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የአገው ብሄረሰብ ቋንቋን ከማሳደግ በላይ ባህሉን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ገለጹ። በዞኑ 18ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን "ብዝሃነትና እኩልነት፤ለአገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በደም ልገሳና በፓናል ውይይት ተከብሯል።   የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንታይቱ ካሴ እንዳሉት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መከበር የአገው ብሄረሰብ ማንነት እንዲንፀባረቅና እንዲታውቅ አድርጓል። ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ለብሄር ብሄረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር እድል ከመስጠቱም ባለፈ በቋንቋ መማርና መዳኘት እንዲችሉ ማድረጉን አስታውሰዋል። በተለይም የአገው ብሄረሰብን ታሪክ፣ ባህልና ማንነት በማጎልበት ትልቅ ለውጥ ማምጣት መቻሉን አፈ ጉባዔዋ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ብሄራዊ ማንነትን በማጎልበት ለሰላምና ሉዓላዊነት መከበር ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በፅናትና በአንድነት ሊሰሩ እንደሚገባ አብራርተዋል። የአገርን አንድነትንና ሉዓላዊነትን አደጋ የሚጥሉ ጉዳዮችን በውይይትና በምክክር የመፍታት ባህል የማዳበር አስፈላጊነትንም ነው የጠቆሙት። የበዓሉ ተሳታፊ ወጣት ገነት ሰፊው እንዳለችው፤ ፌዴራላዊ ስርዓቱ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር እድልን ከመፍጠር ባሻገር ባህልና ማንነትን ለማንፀባረቅ ትልቅ ጠቀሜታ አስገኝቷል። "ወጣቱ ባህሉን ማንነቱን በአግባቡ ተረድቶ ህብረ ብሄራዊት አገርን ለመገንባት በሚደረገው ሂደት የበዓሉ መከበር ትልቅ ሚና አለው" ብላለች። "ከሚነጣጥሉን ትርክቶችና ከመገፋፋት ይልቅ አንድ በሚያደርጉ ትርክቶች መግባባት ያስፈልጋል" ያለችው ወጣት ገነት፤ ወጣቱ ለአገር ልማትና ለውጥ በእኩልነት መሰለፍ እንደሚገባ ገልፃለች። “የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እንድንቆም ትልቅ መሰረት የጣለ ነው” ያሉት ደግሞ የፃግብጅ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሃብታሙ ደባሽ ናቸው። ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ “ባህልን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል” ብለዋል።  
የሚታይ

ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው
Nov 30, 2023 59
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል የጉባኤውን መካሄድ በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። ጉባኤው "ማህበራዊ ምክክርን እና የጎለበተ ምርታማነትን በመጠቀም ማህበራዊ ፍትህን ማላቅ" በሚል መሪ ሃሳብ ከኅዳር 24 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ኩነቶች ይካሄዳል ብለዋል። በጉባዔው ባለድርሻ አካላት በጋራ ሆነው ስኬቶች የሚገመገሙበት፣ ልምዶች የሚቀመሩበት ለዘርፉ መጠናከር የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ይሆናል ብለዋል። የዓለም ሥራ ድርጅት ሲቋቋም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀዳሚነት አባል መሆኗን አስታውሰው ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች ላይ ሁሌም ግንባር ቀደም ሚና እንደምትጫወት ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል። በመስኩ ሥራቸውን በአግባቡ በመከወን ውጤታማ መሆን የቻሉ አካላትና ሠራተኞች ዕውቅና የሚሰጥበት መርሃ ግብር መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል። በጉባዔው ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር ያለውን ትብብር እና ስኬቶች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች የሚፈታበት አቅጣጫ ላይ የጋራ ሀሳብ የሚያዝበት መሆኑንም ገልጸዋል።        
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ዘርፉን በስፋት ለመደገፍ የሚያስችል የወለድ ተመን ማሻሻያ አደረገ
Nov 30, 2023 63
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የግብርና ዘርፉን በስፋት ለመደገፍ የሚያስችል የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ። ባንኩ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር 11 ነጥብ 5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል። በማሻሻያው በሊዝ ፋይናንስና በፕሮጀክት ፋይናንስ የብድር ሞዳሊቲ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶችን ማካተቱም ተመላክቷል። ባንኩ ዛሬ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመላከተው ከምስረታው ጀምሮ ለግብርና ዘርፉ ትኩረት በመስጠት ሲደግፍ የቆየ የፖሊሲ ባንክ መሆኑን በመጥቀስ ግብርናውን ለማሻሻል መንግስት እየወሰደ ያለውን እርምጃ ማሳካት እንዲቻልና የግብርና ሴክተሩን በማነቃቃት በዘርፉ የግል ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት እና ለመሳብ የባንኩ የሥራ አመራር ቦርድ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አሳውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዓመታት ባካሄደው ሪፎርም የነበሩበትን ተግዳሮቶች እየቀረፈና አዳዲስ አገልግሎቶችን ለደንበኞች እያቀረበ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ በመግለጫው የተመላከተ ሲሆን ይህ የወለድ ተመን ማሻሻያም ወቅቱን የጠበቀ እና በአገራችን ያለውን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማዕከል ያደረገ መሆኑን አብራርቷል፡፡ ባንኩ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ዮሐንስ አያሌው እንዳሉት፣ “የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ኢትዮጵያ ያላትን ከፍተኛ የሆነ ያልታረሰ የመሬት ሀብት ወደ ስራ ለማስገባት፤ ባለሀብቶች፣ አርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የበለጠ እንዲበረታቱ ለማድረግ በግብርና ዘርፍ በአነስተኛ፣ መካከለኛና የኮርፖሬት ፕሮጀክት ብድር ለሚጠይቁ ይጠበቅ የነበረው የ11.5 በመቶ የማበደሪያ የወለድ ተመን ወደ 7 በመቶ ዝቅ አድርጓል።” ባንኩ ስራ ላይ ያዋለው ይህ ማሻሻያ ዘርፉን ለማሳደግ ያቀደው ስትራቴጅያዊ ሪፎርም አካል ሲሆን፣ መንግስት የግብርና ዘርፉን ለማሳደግ እየሰራ ያለውን ስራ የበለጠ የሚያግዝ መሆኑንም ገልፀዋል። ባንኩ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉ በአምራች ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች በጥሬ እቃ አቅርቦት እጥረት ምክንያት የነበረባቸውን ዝቅተኛ የማምረት አቅም በማሻሻልና በውጭ ምንዛሬ የሚገቡ ምርቶችን ለመቀነስ ከመርዳቱም በላይ ሀገራችን በዘርፉ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንድታገኝ የሚያግዝ መሆኑም ተብራርቷል። በተጨማሪም የተደረገው የወለድ ተመን ማሻሻያ የምግብና የኢንዱስትሪ ሰብሎች ላይ ያተኮረ ሥራ በኢንቨስተሩ እንዲሰራ የሚያበረታታ ሲሆን፣ የምግብ ፍላጎትንና ለኢንዱስትሪ የሚሆኑ የጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት ሙሉ በሙሉ በአገር ውስጥ ምርቶች ከማሟላት ጎን ለጎን፣ የምግብ ዋጋ ንረትን ለማረጋጋትና የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሳደግ እንደ መንግስት እየተሰራ ያለውን ስራ እንደሚያጠናክር ይጠበቃል። ለከፍተኛ፣ ለአነስተኛና መካከለኛ የግብርና ፕሮጀክቶች የተደረገው የማበደሪያ ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ባንኩ ለዘርፉ ዕድገት ያለውን ቁርጠኛ አቋም ያሳየበት መሆኑም በመግለጫው ተመላክቷል። በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የሀገራችንን ኢኮኖሚያዊ ልማት በተሻለ ደረጃ እንዲረጋገጥ አሁን በገበያው ውስጥ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሳት በተመረጡ ዘርፎች ለተሰማሩ እና ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለሚያንቀሳቅሱ ተበዳሪዎች በሌሎች አገልግሎቶች ላይ መጠነኛ የወለድ ተመን ማሻሻያ ማድረጉ ተጠቁሟል።
በሀገር ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የወጣቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል - ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ
Nov 30, 2023 72
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦በሀገር ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የወጣቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አንዳለበት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናገሩ። የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርኃ ግብር የወጣቶችን ስብዕና እና ተጠቃሚነት በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያግዙ ተግባራትና በስብዕና ግንባታ ላይ አበረታች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በሀገር ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የወጣቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። በስብዕና ግንባታ፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ከማድረግ ባለፈ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እለቱን በማስመልከት ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ከአባቶቻቸው የወረሱትን የጀግንነትና የጽናት መንፈስ በመላበስ ለአፍሪካ ብልጽግና ምሳሌ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ወጣቶች ችሎታቸውንና ፈጠራቸውን ለበጎ ነገር መጠቀም ከቻሉ የአህጉሪቷን ብሩህ ተስፋ ማለምለም የሚችል እምቅ ጉልበት እንዳላቸው አስረድተዋል።   16ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርኃ ግብር "ድንበር ተሻጋሪ የወጣቶች እንቅስቃሴ ለፓን-አፍሪካኒዝም" በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል።
የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በማጉላትና ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠየቀ
Nov 30, 2023 78
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በማጉላትና ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር ሂደት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ተጠየቀ። የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ጋር በመተባበር ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ በሚኖረው ፋይዳ ላይ ከተለያዩ የሲቪል ድርጅት ተወካዮች ጋር ምክክር ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፤ የኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀል ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ስለመሆኑ አብራርተዋል። የብሪክስ አባል መሆን በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በአማራጭ የልማት ፋይናንስ ምንጭ ማስፋት እና አጋርነትን ለማጎልበት የሚረዳ መሆኑንም አንስተዋል። ብሪክስ የሁሉም አመለካከት ማዕከልና በዓለም ትልቅ ምጣኔ ኃብታዊ ጉልበት ያለው ስብስብ መሆኑንም አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ድምጿን ለማሰማት ተጨማሪ ዕድል የሚሰጥ በመሆኑ ትልቅ ዲፕሎማሲ ስኬት መሆኑን ገልፀዋል። ኢትዮጵያ ብሪክስን የተቀላቀለችው ከየትኛውም ርዕዮተ-ዓለም ጎራ ለመወገን ሳይሆን፤ ከሁሉም የዓለም አገራት ጋር የጋራ ልማትን ለማረጋገጥ እና ብሔራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ መሆኑንም አምባሳደር ምስጋኑ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ የገፅታ ግንባታ እና የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ዕውቅና እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የላቀ ሚና እንዳላቸው ጠቅሰው፤ የተዘጋጀው መድረክም ዋነኛ ዓላማ በብሪክስ ዙሪያ ሰፊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ለማስቻል ነው ብለዋል። በመሆኑም የኢትዮጵያን መልካም ገፅታ በማጉላትና ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር ሂደት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጠይቀዋል።   የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅት ባለሥልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፋሲካው ሞላ፤ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች የውጭ ጉዳይን ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ለሀገር አስተዋጽዖ እያበረከቱ መሆኑን ጠቅሰዋል። በብሪክስ አባልነት ጉዳይ ግንዛቤ መፈጠሩም ማኅበራቱ የበኩላቸውን ሚና በላቀ መልኩ እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን ገልፀዋል። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ጥያቄ በይፋ ተቀባይነት ያገኘው ባሳለፍነው ወርኅ ነሐሴ በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የብሪክስ አባል ሀገራት 15ኛ ጉባዔ መሆኑ ይታወቃል። ኢትዮጵያን ጨምሮ ቡድኑን አዲስ የተቀላቀሉ አገራት ከመጪው የፈረንጆች አዲስ ዓመት መባቻ ጀምሮ የብሪክስ ሙሉ አባልነትን የሚያረጋግጡ ይሆናል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ዶክተር የቻለ ደጉ፤ ብሪክስ የሲቪክ ማኅበረሰብ አወቃቀር ላይ ወደፊት አማራጭ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል። በአባል ሀገራት ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት ጥበቃ ሚናቸውን እንዲወጡም ብሪክስ ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት አንስተዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ትነበብ ብርሃኔ፤ ኢትዮጵያ ወደ ብሪክስ መግባቷ ለልማትና አጋርነት መጎልበት የሚጠቅም በመሆኑ መልካም ዕድል መሆኑን ገልፀዋል። አባል ሀገራት በየራሳቸው የጋራ ስምምነት የሚመሩበት ስብስብ በመሆኑ ብሔራዊ ጥቅሞች እንደተጠበቁ ሆነው በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አቅም ግንባታ ላይም በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባው ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በፐብሊክ ዲፕሎማሲው መስክ ለኢትዮጵያ ገጽታ ግንባታና ልማት መጎልበት መሥራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።    
ማስታወቂያ
ፖለቲካ
በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ የሙስና ወንጀልን በጋራ መከላከል ይገባል- አቶ ታዬ ደንደዓ
Nov 30, 2023 42
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት መሳካት የሙስና ወንጀልን በጋራ መከላከል ይገባል ሲሉ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደዓ ገለጹ። የሰላም ሚኒስቴር ሰራተኞች 20ኛውን ዓለም አቀፍ የጸረ-ሙስና ቀን በማስመልከት "ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው፤ በሕብረት እንታገል" በሚል መሪ ሃሳብ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የሰላም ሚኒስቴር ዴኤታ ታዬ ደንደዓ፤ በአንድ ሀገር የሙስና መስፋፋት ለበርካታ ችግሮች ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።   የሀገር የእድገት ጸርና የህዝቦች የምሬት ምክንያት ከመሆንም ባለፈ ለሰላምና መረጋጋት እንቅፋት መሆኑን ገልጸዋል። በኢትዮጵያም የሙስና ወንጀል የሚያስከትለውን ችግር ለመከላከል የሚያስችሉ ተግባራት ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። የሙስና መከላከል ስራ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ባለመሆኑ ሁላችንም በጋራ መከላከል ይጠበቅብናል ነው ያሉት። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ለሚደረገው ጥረት መሳካት የሙስና ወንጀልን በጋራ መከላከል ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።   የፌዴራል ሥነ ምግባርና ጸረ ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር እሸቴ አስፋው፤ የሙስና ወንጀል የበርካታ ችግሮች ምክንያት በመሆኑ የጋራ ትግልን የሚጠይቅ ነው ብለዋል። ኮሚሽኑ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ ዘርፎችን በመለየት የመከላከልና የህግ ተጠያቂነትን ለማስፈን እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በሁሉም ሴክተሮች ህብረተሰቡ የመከላከሉ ስራ አጋዥ በመሆን ሙስናን እንዲታገል ጥሪ አቅርበዋል። የጸረ-ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ ባከናወናቸው ተግባራት 9 ቢሊየን ብር እና 4 ሚሊየን ካሬ ሜትር መሬትን ከሌብነት ማትረፍ እንደተቻለ መገለጹ ይታወቃል። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በመስከረም ወር የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት የመክፈቻ ሥነስርዓት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ መንግስት የሙስና መከላከል ስራን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ማረጋገጣቸው ይታወሳል።  
በህብረ-ብሄራዊ ማንነት ለተሳሰረ ህዝብ ፌዴራሊዝም ሁነኛ መፍትሔ ነው
Nov 30, 2023 50
ቦንጋ ፤ህዳር 20/2016 (ኢዜአ):- በሀገሪቱ ብዝሃነትን ለማስተናገድና ሰላምና ልማትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የፌዴራል ሥርዓት ሁነኛ መፍትሄ መሆኑን የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን ገለፁ። "ብዝሃነትና ዕኩልነት ለአገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ የዘንድሮው 18ኛው የብሔር፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ፕሮግራሞች ዳይሬክተር ዶክተር ዬረቾ ብርሃኑ እንዳሉት፤ በአገራችን የፌዴራል ሥርዓትን ህብረ-ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር ሁነኛ መፍትሔ ነው። ራስን በራስ የማስተዳደር ስርዓትን በማበጀት በልዩ ልዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚነሱ ጥያቄዎች ዘላቂ ምላሽ እንዲያገኙና ማንነታቸው ተከብሮ እንዲኖሩ የሚያስችል መሆኑንም ተመራጭ እንዳደረገው አንስተዋል። አገርን ሊገልፅ የሚችል የተለያየ ማንነት ያላቸው ተማሪዎችን የያዙት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የፌዴራሊዝም ስርዓት መሬት እንዲይዝ ከማድረግ አኳያ ከፍተኛ ሚና ሊጫወቱ እንደሚገባም አንስተዋል። ''ወጣቱ ትውልድ ብዝሃ ማንነትን በመረዳት ሃላፊነቱን እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅብናል'' ያሉት በዩኒቨርሲቲው የመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ልዩ ረዳት አቶ ጌትነት ገብረሚካኤል ናቸው። በክብረ በዓሉ ላይም ዕለቱን አስመልክቶ የተሰናዱ ልዩ ልዩ ስፖርታዊ ውድድሮችና ኪነ ጥበባዊ መርሃ ግብሮች ተስተናግደዋል።    

የብሔር ብሔረሰቦች በዓል መከበሩ የብሔረሰቦቹን ማንነት ከማሳወቅ ባለፈ ለህገ መንግስት አስተምህሮ የተሻለ እድል ፈጥሯል
Nov 30, 2023 51
ህዳር 20/2016(ኢዜአ) ፡- የብሔር ፣ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል መከበር የብሔረሰቦቹን ማንነት ከማሳወቅ ባለፈ በህገመንግስት አስተምህሮ ላይ ጉልህ ድርሻ እንዳለው የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ገለጸ። የኦሮሚያ ክልል የዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች በዓል በተለያዩ ተግባራትና የስራ ጉብኝቶች እንደሚከበርም ገልጿል። ክልሉ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚከበረው በዓል ባለው ተሳትፎና በክልሉ ደረጃ የአከባበር መርሃ ግብሩን አስመልክቶ የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት(ጨፌ ኦሮሚያ) ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥቷል። የጨፌ ኦሮሚያ ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ኤሊያስ ኡመታ በመግለጫቸው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን የብሔሮቹ የቃል ኪዳን ሰነድ የሆነው ህገ መንግስት የጸደቀበትን ታሳቢ ተደርጎ የሚከበር መሆኑን አንስተዋል። ቀኑ ለተከታታይ ዓመታት በመከበሩ ለኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ያስገኛቸው በርካታ ትሩፋቶች እንዳሉ ጠቁመዋል።   በተለይም በዓሉ የብሔረሰቦቹን ማንነት በአደባባይ በማውጣትና በፌዴራሊዝም እና ህገ መንግስታዊ አስተምህሮቱ ላይ ያስገኛቸው ግንዛቤዎችን በማከል። ክልሉ የዘንድሮውን በዓል ከወትሮው በተለየ በልዩ ልዩ ተግባራትና በስራ ጉብኝት እንደሚያከብር ያነሱት አቶ ኤሊያስ፤ በተለይም በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተከናወኑ ተግባራትን ማየትና ህብረተሰቡን ለበለጠ የልማት ተግባራት ማንቀሳቀስ ከበዓሉ መርሃ ግብር ዋነኛው መሆኑን አውስተዋል። ህብረተሰቡ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ ማድረግ፣ የፓናል ውይይቶች፣ ልዩ ልዩ ባዛርና ዐውደ ርዕይ፣ ነጻ የጤና አገልግሎትና የደም ልገሳ እንዲሁም ማስ ስፖርት ከመርሃ ግብሮቹ መካከል ተጠቃሾች ናቸው። የኦሮሚያ ክልል የህዝቡን ባህልና እሴት የሚያንጸባርቁለትን ልዑካን ይዞ ጅግጅጋ በሚከበረው በዓል ላይ ለመሳተፍ ዘርፈ ብዙ ዝግጅቶችን ማጠናቀቁን ያነሱት አቶ ኤሊያስ ፤ ለዚህም አንድ አብይ ኮሚቴና ልዩ ልዩ ንዑሳን ኮሚቴዎች አስቀድመው መዋቀራቸውን ተናግረዋል። በዓሉን ለመታደም ክልሉን አቋርጠው ለሚያልፉ ብሔር ብሔረሰቦች መልካም አቀባበል፣ መስተንግዶና ሽኝት እንደሚደረግ አንስተው፤ በዚህ አጋጣሚ ህዝቡ ወንድምነቱን፣ ፍቅሩንና መልካም እሴቱን አጉልቶ እንዲያንጸባርቅ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰፈነውን ሠላም በመጠበቅ የህዝብን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ-አቶ አሻድሊ ሃሰን
Nov 30, 2023 50
ግልገል በለስ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ) ፦በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰፈነውን ሠላም በመጠቀም የህዝብን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ርዕሰ መስተዳድር አሻድሊ ሃሰን ገለጹ። በክልሉ 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ማጠቃለያ በዓል በመተከል ዞን ግልገልበለስ ከተማ ዛሬ ተከብሯል። በበዓሉ ላይ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻድሊ እንዳሉት ህብረተሰቡ፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት፣ ፖሊስና ሌሎች በከፈሉት መስዋዕትነት በመተከል ዞን ሰላምና መረጋጋት ሰፍኗል። በአካባቢው የተረጋገጠውን ሰላም ተከትሎም በግለሰቦች ያለአግባብ የተያዙ ሰፋፊ መሬቶችን በማስለቀቅ ለሚያለሙ ግለሰቦች እንዲተላለፍ መደረጉን ገልጸዋል። "በዚህም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት ለማከናወን ተችሏል" ብለዋል። የአካባቢውን የተፈጥሮ ፀጋ በተሻለ አልምቶ ወደ ሀብት በመቀየር የክልሉን ህዝብ ብሎም አገርን ወደ ብልጽግና ማሻገር የክልሉ ዋነኛና ቀዳሚ ተግባር ተድርጎ እየተሠራ መሆኑንም አስታውቀዋል። "የክልሉን ህዝብ ከልማት የተሻለ ተጠቃሚ ማድረግ የሚቻለው የሰፈነው ሰላም ተጠናክሮ ሲቀጥል ነው" ያሉት አቶ አሻድሊ፣ ቀደም ሲል በዞኑ ተከስቶ ነበረው የሠላም እጦት እንዳይደገም ሁሉም ለሰላም ዘብ መቆሙን እንዲያጠናከር አሳስበዋል። የልማት ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በአብሮነት መንቀሳቀስ እንደሚገባ አቶ አሻድሊ ጠቅሰው፣ "ለዚህም ከሚበታትኑን ይልቅ እንደ ሀገር አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ይገባናል" ሲሉ አስገንዝበዋል።   የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ዶክተር ተመስገን ዲሳሳ በበኩላቸው በክልሉ የዴሞክራሲ ተቋማት ሃላፊነታቸውን በገለልተኝነት እንዲወጡ በማድረግ ዴሞክራሲን ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል። መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን እየተሰሩ ያሉ ሥራዎችን ውጤታማነት ለመከታተል ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ዋና አፈጉባኤው አመልክተዋል። የክልሉ ህብረተሰብ የማንነቱ መገለጫ የሆኑ እሴቶቹን ጠብቆ ከማሳደግ ባለፈ ከሌሎች የአገሪቱ ህዝቦች ጋር ህብረብሔራዊ አንድነቱን ማጠናከር እንዳለበትም አስገንዝበዋል። "በመተከል ዞን የሰፈነው ሰላም ለዞኑ ልማት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል" ያሉት የመተከል ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ለሜሳ ዋውያ በበኩላቸው፣ የዞኑ አመራሮችና ባለሙያዎች ለመልሶ ግንባታ ርብርብ እያደረጉ መሆኑን አስረድተዋል። ባለሀብቱ ወደዞኑ በመግባት በእርሻ፣ በማዕድን፣ በቱሪዝምና ሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሠማራም ዋና አስተዳዳሪው ጥሪ አቅርበዋል። ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል አቶ አወድ ሙሳ ከዚህ በኋላ የመተከል ዞን ብሎም የክልሉ ሠላም እንዲታወክ እንደማይፈልጉ ገለጸው፣ "በአካባቢው የሰፈነውን ሰላም ለማጠናከር የበኩሌን እወጣለሁ" ብለዋል።   ወይዘሪት ትዕግስት ዲቢሳ በበኩሏ እንዳለችው ባለፉት ዓመታት በተከበሩ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል የማንነት መገለጫ የሆኑ እሴቶቾ ጎልተው ወጥተዋል። በዓሉ እርስ በርስ ለመተዋወቅና አብሮነትን ለማጠናከር ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቁማ፣ በዓሉን ለኢኮኖሚ ጠቀሜታ በማዋል በኩል ተጨማሪ ሥራ ያስፈልጋል ብላለች። በዓሉ "ብዝሃነት እና እኩልነት ለአገራዊ አንድነት" በሚል መርህ በግልገል በለስ ስታዲየም ሲከበር የብሔር ብሔረሰቦች ሙዚቃና ስፖርታዊ ውድድሮች ቀርበዋል። ለበዓሉ ስኬት የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላትም ሽልማት ተሰጥቷል። በበዓሉ ላይ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የመተከል ዞንና የግልገል በለስ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።  
 ለአካባቢያችን ዘላቂ ሰላም የድርሻችንን እንወጣለን - የተሃድሶ ሰልጣኞች 
Nov 30, 2023 82
ደሴ፤ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦ በተሃድሶ ስልጠና ያገኘነውን ዕውቀት ተጠቅመን ለአካባቢያችን ዘላቂ ሰላም የድርሻችንን እንወጣለን ሲሉ በኮምቦልቻ ጮሬሳ ጊዜያዊ ማቆያ የተሃድሶ ስልጠና ያጠናቀቁ ግለሰቦች ገለጹ። በምስራቅ አማራ ኮማንድ ፖስት የኮምቦልቻ ጮሪሳ ጊዜያዊ ማቆያ የተሃድሶ ስልጠና የወሰዱ ግለሰቦች ወደ ማህበረሰቡ ተቀላቅለዋል። ከሰልጣኞቹ መካከል አቶ ታደሰ ግዛው በሰጡት አስተያየት፤ በጊዜያዊ ማቆያው ስለ አማራ ክልል አሁናዊ ሁኔታ በትክክል ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። በተለይ ስለ ሰላም አስፈላጊነት፣ ስለ አብሮነትና የግጭት አስከፊነት በስልጠናው በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ጠቁመው፤ ያገኙትን እውቀት ተጠቅመው ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻቸውን እንደሚወጡ ገልጸዋል። ''በቆይታዬ ሰብዓዊ መብቴ ተጠብቆ ቆይቻለሁ፤ ከስህተታችን ተምረናል ለዘላቂ ሰላም መሰፈን ራሳችንን አዘጋጅተናል'' ብለዋል። አቶ የአብቃል ቢታው በበኩላቸው፤ በቆይታቸው ሰብዓዊ መብታቸው ተጠብቆ ትምህርት ማግኘታቸውን አመልክተዋል። ስለ ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታና አብሮነት የተሰጣቸው ስልጠናም አሁን ያጋጠመውን ችግር በትክክል ተገንዝበው ለዘላቂ ሰላም የድርሻቸውን ለመወጣት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። የተፈጠረላቸው ግንዛቤ በመጠቀም የተሳሳቱትን ወደ ሰላም እንዲመጡ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ''ከተሃድሶ ስልጠናው ያገኘሁትን ዕውቀት ተጠቅሜ ስለ ሰላምና አብሮነት አስተምራለሁ ያለችው'' ደግሞ ወይዘሪት ጤና ጌትነት ናት። ''ሰላም ከራስ፣ ከቤተሰብና ከአካባቢ እንደሚጀምር ተገንዝቢያለሁ፤ ቤተሰቦችን በማስተማር ሁሉም ለሰላም ዘብ እንዲቆሙ የድርሻዬን እወጣለሁ'' ብላለች።   በፌዴራል ፖሊስ የሰሜን ምስራቅ ሬጅመንት አምስት ሻለቃ አዛዥ ምክትል ኮማንደር ኩራባቸው እንዳለ እንደገለጹት፤ አውቀውም ሆነ ሳያውቁ የተሳሳቱትን ግለሰቦች በማስተማር የመመለስ ስራ እየተካሄደ ነው። እንዲሁም ሰልጣኞች በቆይታቸው የአገሪቷን ነባራዊ ሁኔታ በማሳወቅ ለአካባቢያቸው ሰላም ዘብ እንዲቆሙ ግንዛቤ እንዲያገኙ መደረጉን አስረድተዋል። ሰልጣኞች ወደ ማህበረሰቡ ሲቀላቀሉም ሰለ ሰላም በማስተማር የድርሻቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል። "እርስ በእርስ እያጋጩ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ችግር የሚፈጥሩትን ሁላችንም መታገልና ማውገዝ ይኖርብናል'' ያሉት ደግሞ በፌዴራል ፖሊስ ሰሜን ምስራቅ መምሪያ ምክትል አዛዥ ኮማንደር ሰይድ እንድሪስ ናቸው። ሰልጣኞች በቆይታቸው ያገኙትን እውቀትና ግንዛቤ በመተግበር ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን በንቃት መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።  
በዓሉ የኢትዮጵያውያንን ህብረብሔራዊ አንድነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት አጉልቶ ያሳየ ነው- ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ
Nov 30, 2023 59
ሰመራ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ) ፦ የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል የኢትዮጵያውያንን ህብረብሔራዊ አንድነት፣ እኩልነትና ወንድማማችነት አጉልቶ ያሳየ ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ ገለጹ። በአፋር ክልል ደረጃ 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል በሰመራ ሎጊያ ከተማ በዛሬው ዕለት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የተገኙት የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ በዓሉ የኢትዮጵያውያንን ህብረብሔራዊ አንድነት ከማጠናከር ባለፈ በወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ እኩልነትን አጉልቶ ያሳየ ነው።   እንደ አቶ አወል ገለጻ፣ ከአገራዊ ለውጡ ወዲህ የአፋር ህዝብን በውሳኔ ሰጪነት ያካተተ ሥርዓት በመፈጠሩ ክልሉና ህዝቡ ከአጋር ወጥቶ በአገራዊ አንድነት የጎላ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ላለፉት ዓመታት የተከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል የአፋር ህዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ አብሮነትና እኩልነትን እንዲያጠናክር ከማድረግ ባለፈ ህብረብሔራዊ አንድነቱን ለማጎልበት እንዳስቻለውም ተናግረዋል።   የአፋር ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ አሲያ ከማል በበኩላቸው፣ በዓሉ አብሮነትን ከማጠናከር ባለፈ ብዝሃነት ጎልቶና ደምቆ የሚታይበት ነው ብለዋል። ህብረብሔራዊ አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ዛሬ በክልል ደረጃ የተከበረው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ቀደም ባሉ ቀናት በዞንና ወረዳ መዋቅሮችና የተለያዩ ተቋማት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ፣ የፌዴራል እና የአፋር ክልል ፖሊስ አባላት እንዲሁም የተለያዩ የህብረተሰብ ከፍሎች ተገኝተዋል።
በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ ወንድማማችነትን ማጠናከር ለኢትዮጵያ አንድነት መጽናት ትልቅ ሚና አለው
Nov 30, 2023 45
ሚዛን አማን፤ ኅዳር 20/2016 (ኢዜአ) ፡- በብዝሃነት ላይ የተመሠረተ ወንድማማችነትን ማጠናከር ለኢትዮጵያ አንድነት መጽናት ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ መቱ አኩ ተናገሩ። "ብዝሃነትና ዕኩልነት ለሀገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ 18ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በክልሉ ቴፒ ከተማ እየተከበረ ነው። የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ መቱ አኩ እንዳሉት፤ በዓሉ የተለያዩ ብሔረሰቦች በጋራ መድረክ ተገናኝተው እሴቶቻቸውን የሚለዋወጡበት የኢትዮጵያዊነት ዓርማ ነው። እንደ ሀገር ኢትዮጵያዊ አንድነታችንን ለማጎልበት ብዝኅነት ላይ የተመሠረተ ወንድማማችነትን ማጠናከር አስፈላጊ ነው፤ ብለዋል። የብሔር ብሔረሰቦች ቀን መከበር አንድነታችንን ከማጠናከር ባለፈ በሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የእስካሁን ተሞክሮዎች የሚፈተሹበት የአንድነት መገለጫ መድረክ መሆኑን አስረድተዋል። ለብዝሃነት እውቅና መስጠት እና ሕገ መንግስታዊ ዋስትናን ማረጋገጥ የሁሉም አካላት ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው ለኅብረ ብሔራዊ አንድነት መጎልበት በጋራ መረባረብ እንደሚገባም ተናግረዋል። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ፀጋዬ ማሞ በበኩላቸው ኢትዮጵያ በብሔር ብሔረሰቦች ልዩነት ውሰጥ ባለ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት የምትደምቅ ሀገር ነች ብለዋል። በንግግራቸውም "የኔ ብሔር ብቻ" የሚል አስተሳሰብ ለኢትዮጵያ የማይጠቅም መሆኑን ገልጸው ሁሉም ብሔረሰቦች በጋራ ሀገራቸው እኩል ዕድል እንዳላቸው ተናግረዋል። ''ከሁሉም ብሔረሰቦች ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘን ከሰራን ለክልሉ ዕድገት ብሎም ለሀገር ከፍታ ጉልህ አሻራ የማሳረፍ ዕድል አለን'' ነው ያሉት። በቴፒ ከተማ እየተከበረ ባለው 18ኛው ክልል አቀፍ የብሔር ብሔረሰቦች ቀን በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ሁሉም ብሔረሰቦች ተወካዮች እና የዞን እንዲሁም የክልል ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ነው።  

ማህበራዊ
የጤና መድህን አገልግሎትን ለሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ተደራሽ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቷል
Nov 30, 2023 48
ቦንጋ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ) ፦ በሀገሪቱ የጤና መድህን አገልግሎት ስርዓትን በማጠናከር ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ገለጸ። በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የ2016 ዓ.ም የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን የንቅናቄ መድረክ በቦንጋ ከተማ ተካሂዷል።   በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ጤና መድህን አገልግሎት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ያምሮት አንዷለም እንዳሉት፤ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስርዓት በርካታ የሀገሪቱ ዜጎችን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። በተለይም በከተማና በገጠር መደበኛ ባልሆነው የኢኮኖሚ ዘርፍ ተሰማርተው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ በማድረግ ዜጎች ያለምንም ስጋት የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ጉልህ ሚናን እየተጫወተ ይገኛል ብለዋል። በመሆኑም አገልግሎቱን ይበልጥ በማጠናከር ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ እንዲያደርግ ልምዶችን በመቀመር የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ነው ያመለከቱት። የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ከጀመረ ወዲህ የህብረተሰቡ ተጠቃሚነት እያደገ መምጣቱን የገለጹት ምክትል ዋና ዳይሬክተሯ በተለይም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ላሉ የህብረተሰብ ክፍሎች እፎይታን ፈጥሯል ብለዋል። በቀጣይም አገልግሎቱን ከማጠናከር አንጻር የሚነሱ የአገልግሎት አሰጣጥ፣ የመድሃኒት አቅርቦትና ሌሎች ችግሮችን ለይቶ ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር በተቀናጀ መንገድ እንደሚሰራ ገልፀዋል። አገልግሎቱን የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ቁጥርና ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው የህዝብን ፍላጎት ተደራሽ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች እንደሚጠናከሩም ተናግረዋል።   የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ኢብራሂም ተማም በበኩላቸው በክልሉ አገልግሎቱን ለማጠናከር ያሉት ችግሮችን ነቅሶ በማውጣት መፍትሄ ለመስጠት የንቅናቄ መድረኩ ማስፈለጉን ጠቁመዋል። በክልሉ እስከ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ የነባር አባላት እድሳትን 95 በመቶ እንዲሁም አዲስ አባላትን የመመዝገቡ ሥራን ደግሞ 75 በመቶ ለማጠናቀቅ መታቀዱን ገልጸዋል። መድረኩን የታደሙት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ በላይ ተሰማ በበኩላቸው የጤና መድህን አገልግሎት ዜጎች ፍትሃዊ የጤና አገልግሎት እንዲያገኙ እያስቻለ በመሆኑ ሊጠናከር እንደሚገባ ተናግረዋል። አገልግሎቱ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ዓመታዊ የጤና መድህን ወጪያቸውን መሸፈን የማይችሉ ዜጎች በመንግስት እንዲሸፈንላቸው በማድረግ ፍትሃዊነትን ያረጋገጠ መሆኑን ጠቁመዋል። በክልሉ ባለፈው ዓመት ብቻ ከ136 ሺህ በላይ የጤና ማህበረሰብ የጤና መድህን አባላት ከነቤተሰቦቻቸው በየደረጃው የህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውም ተገልጿል። የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተሳተፉበት መድረክ ላይ ባለፈው ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ዞኖችና ወረዳዎች የዕውቅናና የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን የቀጣይ ስራን ማጠናከር የሚያስችል ስምምነትም ተፈርሟል።
ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የአገው ብሄረሰብ ቋንቋን ከማሳደግ በላይ ባህሉን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል
Nov 30, 2023 46
ሰቆጣ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ) ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የአገው ብሄረሰብ ቋንቋን ከማሳደግ በላይ ባህሉን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ገለጹ። በዞኑ 18ኛው የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን "ብዝሃነትና እኩልነት፤ለአገራዊ አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ በደም ልገሳና በፓናል ውይይት ተከብሯል።   የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንታይቱ ካሴ እንዳሉት፤ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን መከበር የአገው ብሄረሰብ ማንነት እንዲንፀባረቅና እንዲታውቅ አድርጓል። ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ለብሄር ብሄረሰቦች ራስን በራስ የማስተዳደር እድል ከመስጠቱም ባለፈ በቋንቋ መማርና መዳኘት እንዲችሉ ማድረጉን አስታውሰዋል። በተለይም የአገው ብሄረሰብን ታሪክ፣ ባህልና ማንነት በማጎልበት ትልቅ ለውጥ ማምጣት መቻሉን አፈ ጉባዔዋ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ብሄራዊ ማንነትን በማጎልበት ለሰላምና ሉዓላዊነት መከበር ሁሉም ብሄር ብሄረሰቦች በፅናትና በአንድነት ሊሰሩ እንደሚገባ አብራርተዋል። የአገርን አንድነትንና ሉዓላዊነትን አደጋ የሚጥሉ ጉዳዮችን በውይይትና በምክክር የመፍታት ባህል የማዳበር አስፈላጊነትንም ነው የጠቆሙት። የበዓሉ ተሳታፊ ወጣት ገነት ሰፊው እንዳለችው፤ ፌዴራላዊ ስርዓቱ በአፍ መፍቻ ቋንቋ የመማር እድልን ከመፍጠር ባሻገር ባህልና ማንነትን ለማንፀባረቅ ትልቅ ጠቀሜታ አስገኝቷል። "ወጣቱ ባህሉን ማንነቱን በአግባቡ ተረድቶ ህብረ ብሄራዊት አገርን ለመገንባት በሚደረገው ሂደት የበዓሉ መከበር ትልቅ ሚና አለው" ብላለች። "ከሚነጣጥሉን ትርክቶችና ከመገፋፋት ይልቅ አንድ በሚያደርጉ ትርክቶች መግባባት ያስፈልጋል" ያለችው ወጣት ገነት፤ ወጣቱ ለአገር ልማትና ለውጥ በእኩልነት መሰለፍ እንደሚገባ ገልፃለች። “የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ኢትዮጵያዊያን በአንድነት እንድንቆም ትልቅ መሰረት የጣለ ነው” ያሉት ደግሞ የፃግብጅ ወረዳ ነዋሪ አቶ ሃብታሙ ደባሽ ናቸው። ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ “ባህልን ለማጎልበት ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል” ብለዋል።  
የአካል ጉዳተኞች ቀን የፊታችን ሰኞ በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል
Nov 30, 2023 43
አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ)፦ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን የፊታችን ሰኞ ኅዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች እንደሚከበር ተገለጸ። እለቱን በማስመልከት የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን የጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ እለቱ የሚከበረው አካል ጉዳተኞችን ከዘላቂ የልማት ስትራቴጂዎች ጋር በማስተሳሰር ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ማረጋገጥ እንዲቻል ግንዛቤ በመፍጠር መሆኑን ገልጸዋል። አካል ጉዳተኞችን ከዘላቂ የልማት ስትራቴጂዎች ጋር በማስተሳሰር ሰብዓዊና ዴሞክራሲዊ መብት ማረጋገጥ እንዲቻል ግንዛቤ የሚፈጠርበት መሆኑን አንስተዋል። የአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል አጠቃላይ ሕግ ለማፅደቅ ረቂቅ ሰነድ መዘጋጀቱንም ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማኅበራት ፌዴሬሽን ዋና ዳይሬክተር አባይነህ ጉጆ፤ እለቱ ሲከበር የአካል ጉዳተኞችን ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሕዝብ ንቅናቄ በመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል።   ዓለም አቀፉ የአካል ጉዳተኞች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ32ኛ፤ በኢትዮጵያ ደግሞ "ለአካል ጉዳተኞች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት እና ዘላቂ የልማት ግቦች ስኬት ትርጉም ያለው ትብብር!" በሚል መሪ ሃሳብ ለ31ኛ ጊዜ የሚከበር ይሆናል።  
በሀገር ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የወጣቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል - ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ
Nov 30, 2023 72
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦በሀገር ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የወጣቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አንዳለበት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናገሩ። የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርኃ ግብር የወጣቶችን ስብዕና እና ተጠቃሚነት በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ በማተኮር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ተካሂዷል።   በመድረኩ ላይ የተገኙት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፤ የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በሚያግዙ ተግባራትና በስብዕና ግንባታ ላይ አበረታች እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በሀገር ልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ሂደት የወጣቶች ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። በስብዕና ግንባታ፣ በፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ምክክር ከማድረግ ባለፈ ወጣቶች በሀገራዊ ጉዳዮች የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እለቱን በማስመልከት ግንዛቤ የተፈጠረበት መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ወጣቶች ከአባቶቻቸው የወረሱትን የጀግንነትና የጽናት መንፈስ በመላበስ ለአፍሪካ ብልጽግና ምሳሌ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡ ወጣቶች ችሎታቸውንና ፈጠራቸውን ለበጎ ነገር መጠቀም ከቻሉ የአህጉሪቷን ብሩህ ተስፋ ማለምለም የሚችል እምቅ ጉልበት እንዳላቸው አስረድተዋል።   16ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ወር የማጠቃለያ መርኃ ግብር "ድንበር ተሻጋሪ የወጣቶች እንቅስቃሴ ለፓን-አፍሪካኒዝም" በሚል መሪ ሃሳብ ተካሂዷል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ በ28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎችም ተሞክሮዎቿን ታስተዋውቃለች
Nov 30, 2023 46
  አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ፦ኢትዮጵያ በዱባይ በሚካሔደው 28ኛው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የአረንጓዴ አሻራና ሌሎችንም ተሞክሮዎቿን ለዓለም እንደምታስተዋውቅ የፕላንና ልማት ሚኒስትሯ ዶክተር ፍጹም አሰፋ ገለጹ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ 28) በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፤ በዱባይ መካሄድ ጀምሯል። ዶክተር ፍጹም ይሄንን አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ እንደገለጹት በስፍራው ኢትዮጵያ ያዘጋጀችው ኤግዚቢሽን በአረንጓዴ አሻራ ያስመዘገበችውን ስኬትና ሌሎችንም ተሞክሮዎች ለዓለም ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ ይፈጥራል። ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማት ስራዋን በአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ በተዘጋጀው የኢትዮጵያ አውደ ርእይ/ፓቪሊዮን/ በማስተዋወቅ ላይ መሆኗንም ገልጸዋል። በ1ሺህ 500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ትልቅ ኢግዚብሽን በማዘጋጀት ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ በተጨባጭ ለውጥ እያመጣች መሆኗን የምናሳይበት ነው ብለዋል። በጉባኤውም መሪዎች ንግግር በማድረግ ከዚህ ጋር በተያያዘ የሚዘጋጁ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፍ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ዙሪያ ድምጿን ታሰማለች ብለዋል። በዚህም በዘርፉ የተከናወኑ ስራዎችን በማስተዋወቅ ብሎም እያጋጠሙ በሚገኙ ተግዳሮቶች ዙሪያ የአፍሪካ ድምጽ በመሆን ትልቅ ተሳትፎ ይኖረናል ሲሉም ገልጸዋል። በዚህ ኤግዚቢሽንም በተለያዩ ዞኖች ማለትም የኢትዮጵያን አረንጓዴ አሻራ ኢንሼቲቭ እና ያስገኘውን ጥቅሞች በተመለከተ ለዕይታ ይቀርባል ብለዋል። በተጨማሪም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራዎችን በማጉላት ዘላቂ የግብርና ልማት ተሳትፎዎች ላይ በማተኮር በስንዴ ልማት እምርታዊ ለውጥ የታየበት ነውም ብለዋል።
የፌዴራል ድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት ተካሄደ
Nov 30, 2023 44
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦በበቂ መረጃ የተደገፉ ስራዎችን ማከናወን ለፌዴራል ድጎማ በጀት ቀመር ማሻሻል ሂደት ቁልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሆናቸው ተገለጸ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የድጎማ የጋራ ገቢዎች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፌዴራል ተቋማት ከፍተኛ ሃላፊዎች የፌደራል ድጎማ በጀት ቀመር ለማሻሻል በሚያስችሉ የቅድመ ዝግጀት ሥራዎች ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በመድረኩ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላትና የክልል ርዕሳነ መስተዳደሮችን ጨምሮ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ከገቢዎች ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የክልሎችና የፌዴራል መንግሥት የጋራ ተብለው የተመደቡ ገቢዎች በሁለቱ መካከል የሚከፋፈሉበትን፤ እንዲሁም የፌዴራሉ መንግሥት ለክልሎች ድጎማ የሚሰጥበትን ቀመር የመወሰን፤ ከሀገራዊ ኃላፊነቶቹ መካከል በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ምክር ቤቱም የተጣሉበትን ኃላፊነቶችና የወጡ ሕጎችን ተከትሎ የሕገ መንግሥት የበላይነት፣ ሕገ መንግስታዊነት፣ ዘላቂ ሰላም፣ ዴሞክራሲ ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም አንድ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ማህበረሰብ ለመገንባት ሀገራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት የበኩሉን ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡ በሌላ በኩል በክልሎች መካከል ውጤታማና ፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልን ለማረጋገጥ የሚረዳ የፌዴራል ድጎማና የጋራ ገቢዎች ቀመር እንዲዘጋጅ በማድረግ፤ የማከፋፈያ ቀመሮቹ በፍትሃዊ የሀብት ክፍፍልና በክልሎች የተመጣጠነ እድገት ላይ ያላቸዉን አንድምታ እንዲጠና በማድረግ ሰፊ ስራዎች ሲሰራ መቆየቱን አንስቷል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር አሁን ያለው ቀመርና አፈጻጸሙ እንደገና መፈተሽ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከቋሚ ኮሚቴውና ከሚመለከታቸው የፌደራል ባለድርሻ አካለት ጋር ግብዓት ለመሰብሰብ የታለመ መድረክ ነው ብለዋል፡፡ ሀገራዊ ለውጡን ተከትሎ የፊስካል ፌዴራሊዝም ሪፎርም መደረጉንና በርካታ ውጤቶች የተገኙበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡   በቀጣይም የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄዎችን በተገቢው የሕግ አግባብ ለመመለስ ቁርጠኝነት እንደሚፈልግና ለዚህም ሁሉም ባለ ድርሻ አከላት በርብርብና በእኔነት ስሜት ሊሰራ እንደሚገባም ነው ያሳሰቡት፡፡ በቀጣይ ለሚደረገው የቀመር ማሻሻል ስራ ከሚደረግ ቅድመ ዝግጅት ጋር ተያይዞ በጥናትና በበቂ መረጃ የተደገፉ ስራዎችን መስራት ለቀመር ማሻሻል ሂደት ቁልፍ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መሆናቸውንም አስገንዝበዋል፡፡ በመደረኩ የሚነሱ አስተያየቶችና ሀሳቦች ቋሚ ኮሚቴው ለሚያዘጋጀውና ለምክር ቤት ለሚቀርበው ሀገራዊ ሰነድ ትልቅ ግብዓት ሆኖ እንደሚወሰድም ነው የገለጹት፡፡ ለቀመር ዝግጅት የሚያስፈልጉ መረጃዎች ወቅታዊና ተአማኒነት ያላቸው እንዲሆኑ በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማከናወን እንደሚገባ የጋራ ስምምነት መደረሱን ተጠቅሷል። በመረጃ አቅርቦት ረገድ ሃላፊነት የተጣለባቸው የፌዴራልና የክልል ተቋማት ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አቅጣጫ መቀመጡን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡            
በአዲስ አበባ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን ሆነዋል
Nov 30, 2023 46
አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎቶች ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡ በአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ አመት ዕቅድ አፈጻጸሙን ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ገምግሟል፡፡   የቢሮው ምክትል ሃላፊ መስፍን አሰፋ፤ በሩብ አመቱ አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን፣ የፍጆታ ምርት አቅርቦትን በማሳለጥና ህገ ወጥ ንግድን በመከላከል በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ የቢሮውን አገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊ በማድረግና ለደንበኞች እርካታ ለመፍጠር የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በኦን ላይን እንዲሰጥ ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል። የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ በኦን ላይን መሆኑም የደንበኞችን እንግልትና ተጨማሪ ወጪ ያስቀረ መሆኑን ገልጸዋል። የምርት አቅርቦትና ፍላጎት አለመጣጣምን ተከትሎ የሚከሰተውን የኑሮ ውድነት ለመቆጣጠር ነባር የእሁድ ገበያዎችን የማስፋት ተግባር መከናወኑን ገልፀዋል፡፡ አሁን ላይ የእሁድ ገበያ ማዕከላት ቁጥር 172 መድረሱን የገለጹት ምክትል ሃላፊው በተሰራው ስራ ህብረተሰቡ ጥራት ያለው ምርት በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኝ ማስቻሉን ገልጸል፡፡ የግብርና ምርቶች እጥረት እንዳያጋጥም በአምስቱ የመዲናዋ መግቢያ በሮች ዘመናዊ የግብርና ምርቶች ማዕከላት እንዲገነቡ መደረጉን ጠቅሰዋል፡፡ በዚህም በለሚ ኩራ፣ ኮልፌና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች የተገነቡት ዘመናዊ የገበያ ማዕከላት ግንባታቸው ተጠናቀው ስራ መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል በተደረገ የክትትልና የቁጥጥር ስራ ከ10 ሺህ በላይ ህገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡  
ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባኤ ሊካሄድ ነው
Nov 30, 2023 59
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የዓለም የሥራ ድርጅት (ILO) አባል የሆነችበትን 100ኛ ዓመት በማስመልከት ሀገር አቀፍ ጉባዔ ሊካሄድ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ። የሥራና ክህሎት ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል የጉባኤውን መካሄድ በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል። ጉባኤው "ማህበራዊ ምክክርን እና የጎለበተ ምርታማነትን በመጠቀም ማህበራዊ ፍትህን ማላቅ" በሚል መሪ ሃሳብ ከኅዳር 24 እስከ 26 ቀን 2016 ዓ.ም በተለያዩ ኩነቶች ይካሄዳል ብለዋል። በጉባዔው ባለድርሻ አካላት በጋራ ሆነው ስኬቶች የሚገመገሙበት፣ ልምዶች የሚቀመሩበት ለዘርፉ መጠናከር የሚያግዙ ምክረ ሀሳቦች የሚንሸራሸሩበት ይሆናል ብለዋል። የዓለም ሥራ ድርጅት ሲቋቋም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ በቀዳሚነት አባል መሆኗን አስታውሰው ይህም ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች ላይ ሁሌም ግንባር ቀደም ሚና እንደምትጫወት ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል። በመስኩ ሥራቸውን በአግባቡ በመከወን ውጤታማ መሆን የቻሉ አካላትና ሠራተኞች ዕውቅና የሚሰጥበት መርሃ ግብር መዘጋጀቱንም አስታውቀዋል። በጉባዔው ከዓለም የሥራ ድርጅት ጋር ያለውን ትብብር እና ስኬቶች፣ የገጠሙ ተግዳሮቶች የሚፈታበት አቅጣጫ ላይ የጋራ ሀሳብ የሚያዝበት መሆኑንም ገልጸዋል።        
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ስድስት ተቀራራቢ ፕላኔቶች ማግኘታቸውን ገለጹ 
Nov 30, 2023 45
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፦ ስድስት ተቀራራቢ ፕላኔቶች ማግኘት መቻላቸውን በአሜሪካ የቺካጎ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች አስታወቁ። ተገኙ የተባሉት ፕላኔቶች በራሳቸው የጸሃይ ስርአት ዙሪያ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ስርአቱን የጠበቀና ሙዚቃዊ ስልት ያለው መሆኑንም ተመራማሪዎቹ ይፋ ባደረጉት ምስል ገልጸዋል። ኤች ዲ 110067 የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ፕላኔቶቹ ኮማ ቤሬኒሲስ ከተባለው የህብረ ክዋክብት ስብስብ በአንድ መቶ የብርሃን አመታት ይርቃሉ መባሉን ኔቸር የተባለውን የምርምር መጽሄት ጠቅሶ ዩ ፒ አይ በድረ ገጹ አስነብቧል። የፕላኔቶቹ መገኘት ስለፕላኔቶች አፈጣጠር እና ዝግመተ ለውጥ አዲስ እይታ ሊፈጥር ይችላል የሚሉት የጥናት ቡድኑ መሪ ራፋኤል ሊዩክ “መሰል ግኝቶች ኔፕቱን በተባለችው ፕላኔት ዙሪያ ያሉ አካላት እንዲታወቁ እድል ይፈጥራል” ማለታቸውን ዘገባው አስታውሷል። “ምድር ካለችበት የጸሃይ ስርአት ውጪ ያሉ ሌሎች ፕላኔቶች አፈጣጠር፣ ቆይታ፣ የተሰሩበት ነገር ውሃ ስለመያዛቸው እና ሌሎች ጉዳዮች የጥናቱ መነሻ እንዲሆን አስችሏል” ብለዋል ተመራማሪው። የአሜሪካው ብሄራዊ የጠፈር ምርምር ኤጀንሲ ናሳ ከአውሮፓ የጠፈር ጥናት ድርጅት ጋር በመሆን በተላኩት ሳተላይቶች የክዋክብቱን የብርሃን መጠን፣ ከሌሎች ከዋክብት ጋር ያላቸውን መስተጋብር መመልከት እንደተቻለም ተገልጿል። እንደ ተመራማሪዎቹ ገለጻ ፕላኔቶቹ እርስ በእርስ ያላቸውን ርቀት የሚያስጠብቁበት ሬዞናንስ የተባለው ስርአት ያላቸው በመሆኑ በጸሃይ ዙሪያ ያሉት በርካታ ክዋክብት በሚያደርጉት መሽከርከር የሚጋጩባቸው አጋጣሚዎች በእጅጉ አናሳ መሆኑን በዘገባው ተመላክቷል።  
የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ችግር ፈቺና ፈርጀ ብዙ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለተጠቃሚዎች እያሻገረ ነው 
Nov 29, 2023 193
ጂንካ፤ ህዳር 19/2016 (ኢዜአ)፡- የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ውጤታማ፣ ችግር ፈቺና ፈርጀ ብዙ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለተጠቃሚዎች ለማሻገር አትኩሮ እየሰራ መሆኑን ገለጸ ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የኮሌጁ ዲን አቶ ካሳሁን ጌታቸው እንዳሉት፤ ኮሌጁ ችግር ፈቺ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በማፍለቅ ለማህበረሰቡ በማሸጋገር ተጠቃሚ ለማድረግ አልሞ እየሰራ ይገኛል። ኮሌጁ በአካባቢው የሚገኙ ያልተነኩ አቅሞችን ለመጠቀም የተጀመሩ ጥረቶችን ለማገዝ የማህበረሰቡን ድካም የሚቀንሱና ውጤታማነትን የሚያጎለብቱ ቴክኖሎጂዎች ማፍለቅና ማሸጋገር ላይ ዋናው ትኩረት አድርጎ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል ። በተለይ ኮሌጁ ''ኢትዮጵያ ታምርት'' በሚል መሪ ሀሳብ በተጀመረው አገራዊ ንቅናቄ በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ማሽነሪዎችን በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት ባደረገው እንቅስቃሴ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ጠቁመዋል። ለአብነት በኮሌጁ ከተሰሩ የፈጠራ ስራዎች መካከል ከ30 እስከ 40 ሜትር ጥልቅ ጉድጓድ መቆፈር የሚያስችል ማሽን መሰራቱን ያነሱት አቶ ካሳሁን ከውጭ ሲገባ ከሚጠይቀው ወጪ አንጻር እጅግ ዝቅተኛ በሆነ ዋጋ ለማህበረሰቡ እየቀረበ እንደሚገኝ ነው የተናገሩት። ኮሌጁ የአርሶ አደሮችን ድካም ለማቃለል ከፈጠራቸው ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂዎች መካከል የበቆሎ መፈልፈያ፣ የገብስና የጥራጥሬ መፈተጊያ ማሽኖች ይገኙበታል። የገብስና የጥራጥሬ መፈተጊያ ማሽኑም በባህላዊ መንገድ ጤፍ፣ ማሽላና ሌሎች ሰብሎችን በመውቃት የሚገጥመውን የምርት ብክነት መቀነስ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መሆኑን አመላክተዋል።   በኮሌጁ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ባለሙያ አቶ እስጢፋኖስ እያሱ በኮሌጁ የፈለቁ ማሽኖች የኃይል አማራጭ ስላላቸው መብራት በሌለባቸው አካባቢዎች በነዳጅ የሚሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። ይህም ከኃይል አቅርቦት ጋር የሚስተዋሉ ችግሮችን መቅረፍ የሚያስችል ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ ነው ያሉት። ማሽኑ የኃይል አማራጭ እንዲኖረው መደረጉ አርሶ አደሮች እና በግብርና ላይ የተሰማሩ ኢንቬስተሮች ማሽኑን በተለያየ ቦታ በማንቀሳቀስ መጠቀም እንዲችሉ ታስቦ እንደተሰራም አስረድተዋል። በተለይ ተቋሙ የፈጠረው የጥራጥሬ መፈተጊያ ማሽን ስንዴ፣ ገብስ፣ ማሽላ እና ሩዝ መፈተግ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል። ይህም የአርሶ አደሩን ጊዜና ጉልበት ከመቆጠቡም ባሻገር የምርት ብክነትን ያስቀራል ብለዋል። በገጠር አካባቢዎች በስፋት የሸክላ ሥራ የሚተገበርና አሰራሩም ሁዋላ ቀር በመሆኑ ከዘርፉ የሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ጥቅም አነስተኛ መሆኑን የገለፁት አቶ እስጢፋኖስ፤ ስራው በሰው ጉልበት በመሰራቱ እጅግ አድካሚ እንደሆነም አንስተዋል። ኮሌጁ ይህን ችግር በማየት የሸክላ አፈር መፍጨት፣ ማቡካትና የተለያዩ ቅርፆችን እንዲይዝ የሚያደርግ ዘመናዊ የሸክላ መስሪያ ማሽን መስራት ችሏል ብለዋል። ኮሌጁ የእርሻ ስራውን ለማዘመን እና የከብት እርባታውን አዋጭ ለማድረግ ከሚያግዙ ቴክኖሎጂዎች መካከል አነስተኛ የእርሻ ትራክተር እና የወተት መናጫ ማሽን እና ሌሎችንም ማፍለቅ መቻሉንም ገልጸዋል ።   በፈጠራ ስራዎች ላይ ከተሳተፉ የኮሌጁ ተማሪዎች መካከል ተማሪ ሙሉቀን አለማየሁ ለኢዜአ እንደገለፀው በኮሌጁ 30 በመቶ የንድፈ ሃሳብ፣ 70 በመቶ የሚሆነውን ደግሞ በተግባር ልምምድ እንደተማሩ ተናግሯል። የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በአሁኑ ወቅት በግብርና፣ በማኑፋክቸሪንግ፣ በኮንስትራክሽን እና በሌሎች ተዛማጅ የትምህርት መስኮች 501 ነባር ተማሪዎችን እያሰለጠነ ሲሆን ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ደግሞ 600 ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በዝግጅት ላይ ይገኛል። ከመደበኛ የመማር ማስተማር ሰራው ጎን ለጎን 1 ሺህ ለሚሆኑ ሰልጣኞች በገበያ አዋጭነትና ስራ ፈጠራ ላይ አጫጭር ስልጠናዎችን ለመስጠት መዘጋጀቱንም ከኮሌጁ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።      
የ5-ጂ ሞባይል ኔትዎርክ መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ ነው
Nov 29, 2023 63
አዲስ አበባ ፤ህዳር 19/2016 (ኢዜአ):- በኢትዮጵያ የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መስፋፋት የዲጂታል ልማትን ከማፋጠን ባለፈ ሀገራዊ የምጣኔ ኃብት እድገትን ለማረጋገጥ ሚናው የላቀ መሆኑን የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ገለጹ። ኢትዮ-ቴሌኮም የአምስተኛውን ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ በጅግጅጋ ከተማ በይፋ አስጀምሯል። የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ፤ በማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በዓለም ላይ እጅግ ፈጣን የሚባለውን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ ኢትዮጵያ መጠቀም ጀምራለች ብለዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) ኔትዎርክ ተጠቃሚ ከሆኑ የዓለም አገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ መሆኗንም ጠቅሰዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ ቀደም ሲል በአዲስ አበባ እና አዳማ በይፋ መጀመሩን አስታውሰው፤ አሁን ላይ በሱማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በመጀመሩ እንኳን ደስ ያላችሁ ብለዋል። በኢትዮጵያ የማስፋፋት ሥራው በልዩ ትኩረት እየተከናወነ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይም ተጠናከሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል። የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት የማስፋፋት ሥራ ለዲጂታል ኢትዮጵያ እውን መሆን የላቀ አስተዋጽዖ እንዳለውም ገልፀዋል። የ5-ጂ ኔትዎርክ አገልግሎት በጅግጅጋ ከተማ መጀመሩም የንግድና የመረጃ ሥርዓቱን ለማሳለጥና የመንግሥትን አገልግሎት አሰጣጥ የሚያቀላጥፍ መሆኑን ጠቅሰዋል።   የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር ኢብራሂም ኡስማን፤ የቴክኖሎጂው እውን መሆን በክልሉ ለተጀመሩ የልማት ሥራዎች መፋጠን እንዲሁም በተለያዩ ሴክተሮች ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያግዝ መሆኑን ገልፀዋል። በጅግጅጋ ኢዜአ ካነጋገራቸው የከተማዋ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ራሁ ጠይብካስ እና አብዱረዛቅ ሐሰን የአምስተኛው ትውልድ (5-ጂ) የሞባይል ኔትዎርክ አገልግሎት መጀመር በንግዱም ይሁን በሌሎች አገልግሎቶች ተጠቃሚ የሚያደርግ በመሆኑ ተደስተናል ብለዋል። የ5-ጂ የኔትዎርክ አገልግሎት በተለይም ለስማርት ሲቲ፣ ስማርት ትራንስፖርት፣ የትምህርት ሥርዓት፣ ለጤና፣ ለውሃ፣ የግብርና ልማት፣ ለንግድና የፋይናንስ ሴክተር፣ ለኢንዱስትሪ፣ ለስማርት የመንግሥት አስተዳደር እና ሌሎችም ሴክተሮች የላቀ አበርክቶ እንዳለው ይነገራል።
አብርሆት ቤተመጻሕፍት የቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰልጣኞችን ተቀበለ
Nov 28, 2023 74
አዲስ አበባ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ)፦ የአብርሆት ቤተመጻሕፍት አምስተኛ ዙር የቴክኖሎጂ እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሰልጣኞችን ዛሬ ተቀብሏል። ለሰልጣኞቹም የቤተመጻሕፍቱ ዳይሬክተር ኢንጂነር ውብአየሁ ማሞ አቀባበል ያደረጉ ሲሆን የእንኳን ደህና መጣቹ መልእክትም አስተላልፈዋል። አብርሆት ቤተመጻሕፍት ቀደም ሲልም በአራት ዙሮች 500 ሰልጣኞችን የተቀበለ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን በአሁኑ ዙር የከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ መስፈርቱን ያሟሉ 200 ተማሪዎችን በመቀበል ለ4 ወራት የሚሰጠውን ስልጠና እንዲቀላቀሉ ተደርጓል። እነዚህ ተማሪዎች በቆይታቸው Data Structure ፣ Algorithm እንዲሁም የ Arteficial Intelligence ስልጠና እንደሚወስዱ ተገልጿል። ሰልጣኞቹ የተማሩትን የቴክኖሎጂ እውቀት በመጠቀምም ችግር ፈቺ አንዲሁም አለምአቀፋ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው መሆኑን አብርሆት ቤተመጻሕፍት ለኢዜአ የላከው መረጃ ያመለክታል።
ስፖርት
በስፖርት ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም መጠቀም ይገባል
Nov 30, 2023 52
አሶሳ፤ ህዳር 20/2016 (ኢዜአ)፡- በስፖርት ማህበራዊ ትስስርን በማጠናከር ለዘላቂ ሰላም መስፈን መጠቀም ይገባል ሲሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዋና አፈጉባኤ ዶክተር ተመስገን ዲሳሳ አስገነዘቡ። በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 18ኛውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በዓል ምክንያት በማድረግ በመተከል ዞን ግልገል በለስ ከተማ ዛሬ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ተካሂዷል።   የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ዶክተር ተመስገን ዲሳሳ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ስፖርት የሚያስገኘውን ሁለንተናዊ ጠቀሜታ ለዘላቂ ሠላም ማዋል ይገባል። "ስፖርት የህብረተሰቡን ማህበራዊ ትስስር ለማጠናከር የላቀ ጠቀሜታ አለው " ያሉት ዋና አፈ ጉባኤው በዚህም ዘርፉን ለዘላቂ ሰላም መስፈን መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የውድድሩ ዓላማም በዓሉን ምክንያት በማድረግ የእርስ በርስ ግንኙነትን ማጠናከር መሆኑን የገለጹት ደግሞ የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የሱፍ አልበሽር ናቸው። በዚሁ በሶስት ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችን ጨምሮ የግልገል በለስ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።  
ፌዴሬሽኑ ለክልሎችና ክለቦች ማጠናከሪያ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ማበረታቻ ሽልማት ሰጠ
Nov 27, 2023 92
መቀሌ ፤ ህዳር 17/2016 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለክልሎችና ክለቦች አትሌቲክስ እንቅስቃሴ ማጠናከሪያ ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ ማበረታቻና ሽልማት ሰጠ። ፌዴሬሽኑ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የሁለት ሚሊዮን ብርም ድጋፍ አድርጓል። ፌዴሬሽኑ ሽልማቱንና ድጋፉን ያደረገው በመቀሌ ከተማ ባካሄደው 27ኛ ጠቅላለ ጉባዔ ማጠቃለያ ላይ ነው። ድጋፉ የተሰጠው ስምንት ክለቦች፣ ሁሉም ክልሎችና ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በዘርፉ ያደረጉትን እንቅስቃሴ በመገምገም መሆኑ ተመላክቷል። በዚህም ከፍተኛው 300 ሺህ ብር፣ ዝቅተኛው ደግሞ 40 ሺህ ብር ለክለቦቹ እና ለክልሎቹ ተሰጥቷቸዋል። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ለክለቦቹና ለክልሎቹ የማበረታቻ ሽልማትና ድጋፍ የተደረገው አትሌቲክስን ለማስፋፋትና ለማጠናከር የሚያደርጉትን ጥረት ለማገዝ መሆኑን ተናግራለች። በእያንዳንዱ ክልልና ከተማ አስተዳደር የሚገኙ የስፖርት አመራሮችና አሰልጣኞች ለዘርፉ ልማት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንዲያጠናክሩም አሳስባለች። የክለቦች፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደር የስፖርት አመራሮችና አሰልጣኞች ፌዴሬሽኑ የሰጣቸውን ድጋፍ የውስጥ አቅማቸው ለማጎልበትና ተተኪ አትሌቶች በፕሮጀክት አቅፈው ለማሰልጠን እንደሚረዳቸው ለኢዜአ ገልጸዋል። ይህ በእንዲህ እያለ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሁለት ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር አቶ ጌታቸው ረዳ ድጋፉን ከረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ ተቀብለዋል። አቶ ጌታቸው ፌዴሬሽኑ ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ ኢትዮጵያውያን በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።            
የአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት በማርሻል አርት ስፖርት ያሰለጠናቸውን ወጣቶችና ታዳጊዎች አስመረቀ
Nov 26, 2023 214
አዲስ አበባ፤ ህዳር 16/2016 (ኢዜአ)፦የአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት ለሁለት ዓመታት በማርሻል አርት ስፖርት ያሰለጠናቸውን 32 ወጣቶችና ታዳጊዎች አስመረቀ። የታዳጊዎችና ወጣቶቹ ስልጠና ድርጅቱ ባመቻቸው በጎ ፈቃደኛ የማርሻል አርት ባለሙያ የተከናወነ ሲሆን ስልጠናውን አጠናቀው በዛሬው እለት ለምርቃት በቅተዋል። ተመራቂዎቹ በስልጠናው የአካል ብቃትና የስነ ልቦና ዝግጁነት እንዲኖራቸው በማድረግ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ የሰጣቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከተመራቂዎቹ መካከል ድንቁ ረጋሳ፣ ነብዩ ዳንኤል እና ቅድስት ረጋሳ የስልጠናው እድል ስለተመቻቸላቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በቀጣይ በዚህ ስፖርት ተሻለ ደረጃ ለመድረስ እንደሚሰሩና ሌሎች ወጣቶችንም ለማሰልጠን ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። በአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት የማርሻል አርት ስፖርትን በበጎ ፈቃደኝነት እያሰለጠነ የሚገኘው ኢንትርናሽናል ኢንስትራክተር አብዱልቃድር ረጌሶ፤ ስፖርቱ በተለይ ለወጣቶችና ታዳጊዎች በብዙ መልኩ ጠቃሚ መሆኑን አስረድቷል። የነገ ሀገር ተረካቢ ወጣቶችን በሥነልቦና፤ በአካል ብቃትና በራስ መተማመን እንዲያድጉ ለማድረግ የድርሻውን አስተዋጽኦ በማድረጉ ደስተኛ መሆኑንም ገልጿል። በድርጅቱ የልጆች መምሪያ ጉዳይ ኃላፊ ወይንሸት ዳምጠው፤ ድርጅቱ ታዳጊ ህፃናትና ወጣቶችን ከማሳደግና ከማስተማር ባለፈ ስፖርታዊ ሥልጠናዎችን ሲሰጥ እንደነበር ገልፀዋል። በቀጣይም እንዲህ ዓይነቱ ስፖርት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸው የዛሬ ተመራቂዎችም የማርሻል አርት ስፖርትን በማሳደግ የደርሻቸውን እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል። የአበበች ጎበና በጎ አድራጎት ድርጅት በ1972 ዓ.ም በክብር ዶክተር አበበች ጎበና አማካኝነት የተመሰረተ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።  
አካባቢ ጥበቃ
አፍሪካ በተ.መ.ድ የአየር ንብረት ጉባዔ /ኮፕ 28/ የጋራ አጀንዳዋን በአንድ ድምፅ ታሰማለች
Nov 28, 2023 77
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 18/2016 (ኢዜአ) ፡- አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ /ኮፕ 28/ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል "አንድ ድምፅ" ታሰማለች ሲል አፍሪካ ኅብረት ገለፀ። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ 28) በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፤ በዱባይ ከነገ በስቲያ ይጀመራል። በጉባዔው የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የተደረሱ ስምምነቶችና ድንጋጌዎች ተግባራዊነታቸው ምን ላይ እንደደረሰ ይገመግማል። ጎን ለጎን አገራት የአየር ንብረት ለማቋቋም በተለይም የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማስፋት እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች ምክክር ይደረግባቸዋል። ታዳጊ አገራት በአየር ንብረት ለውጥ የሚደርስባቸውን አደጋ ለመቋቋምና የኃይል ሽግግር እንዲያደርጉ የሚያስችሉ የፋይናንስ አቅርቦት ላይም ጉባዔው ትኩረት ያደርጋል ተብሏል። በተጨማሪም የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አገራት አዲስ የትብብር ማዕቀፍ ሊፈጥሩ እንደሚችሉም ጉባዔው ከወዲሁ ትልቅ ግምት ተሰጥቶታል። ጉባዔውን በማስመልከት ኢዜአ ያነጋገራቸው የአፍሪካ ሕብረት የግሪን ዎል ኢንሼቲቭ ዳይሬክተር ኢልቪስ ፖል፤ አፍሪካ አጀንዳዋን በጉባዔው በአንድ ድምፅ ታሰማለች ብለዋል። ጉባዔው ከዚህ ቀደም በአህጉሪቱ የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም የተደረሱ ስምምነቶች ወደ ተግባር ለመቀየርና በዘርፉ የፋይናንስ አቀርቦትን ለማስፋት ዕድል እንደሚፈጥር ገልፀዋል። የአፍሪካ ሕብረት የግብርና፣ የገጠር ልማት፣ የብሉ ኢኮኖሚና የዘላቂ አካባቢ ኮሚሽነር አምባሳደር ጆሴፋ ሳኮ፤ አፍሪካ በጉባዔው በንቃት ትሳተፋለች ብለዋል።   በተለይም በቅርቡ በኬንያ ናይሮቢ በተካሄደው የአፍሪካ ሕብረት የአየር ንብረት ጉባዔ በጋራ የተያዙ አቋሞች አፍሪካ በጉባዔው ውጤታማ ተሳትፎ እንዲኖራት መሠረት ይጥላል ብለዋል። ይህንንም ተከትሎ አፍሪካ በጉባዔው የአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም ቀዳሚ አጀንዳዋ ታደርጋለች ነው ያሉት። አፍሪካ ምንም እንኳን የበካይ ጋዝ ልቀቷ አነስተኛ ቢሆንም በአየር ንብረት ለውጥ አህጉሪቱ ድርቅ፣ ጎርፍና መሰል የተፈጥሮ አደጋዎች እያስተናገደች ትገኛለች። አፍሪካ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ የደረሰባትን ጉዳት ለመቋቋምና ወደ ታዳሽ ኃይል ሽግግር እንድታደርግ የፋይናንስ ድጋፍ ማፈላለግ ሌላኛው አጀንዳዋ እንደሚሆን አንስተዋል። የዓለም ሙቀት የመጨመር ምጣኔ በአማካይ ከ1 ነጥብ 5 እስከ 2 ዲግሪ ሴሊሽየስ ለማድረግ የተደረሰው የፓሪስ ሥምምነት እውን ለማድረግ እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2030 የዓለም የበካይ ጋዝ የልቀት ምጣኔ ከ28 እስከ 40 በመቶ መቀነስ እንዳለበት የተባበሩት መንግሥታት ደርጅት መረጃ ያሳያል። በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ዱባይ ኅዳር 20 የሚጀምረው የመንግሥታቱ ድርጅት የአየር ንብረት ጉባዔ (ኮፕ 28) እስከ ታህሳስ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል።
በክረምቱ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከሉ ችግኞች ውስጥ 60 በመቶ በጥምር ግብርና የለሙ ናቸው--ዶክተር ግርማ አመንቴ
Nov 26, 2023 147
ሀዋሳ ፤ህዳር 16/2016 (ኢዜአ)፦ በሁለተኛው ምዕራፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት በጥምር ግብርና የለሙ መሆናቸውን የግብርና ሚንስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ ገለጹ። ህብረተሰቡ ለተተከሉ ችግኞች ተገቢውን እንክብካቤ እንዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል። ሚኒስትሩ ባለፈው የክረምት ወቅት በሲዳማ ክልል በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለተተከሉ ችግኞች እየተደረገ ያለውን የእንክብካቤ ሥራ ዛሬ በመስክ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት ዶክተር ግርማ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በመንግስት አቅጣጫ መሠረት በሁለተኛው ምዕራፍ ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 60 በመቶ የሚሆኑት በጥምር ግብርና እንዲለሙ ተደርጓል። በእዚህም ፍራፍሬና የእንስሳት መኖን በጥምር ለማልማት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል። ከሚተከሉ ችግኞች 60 በመቶውን በጥምር ግብርና እንዲለማ የተደረገበት ምክንያት የግብርና ምርትና ምርታማነትን በዘላቂነት ለማሳደግ ታስቦ መሆኑንም አስረድተዋል። ቀሪዎቹ የተተከሉ ችግኞች ለደን ልማትና ለከተማ ውበት የሚያገለግሉ መሆናቸውንም ዶክተር ግርማ ገልጸዋል። “በክረምቱ ለተተከሉ ችግኞች በህዝብ ተሳትፎ እየተደረገ ባለ የእንክብካቤ ሥራ የተሻለ የጽድቀት መጠን ላይ ይገኛሉ” ብለዋል። "የጥምር ግብርና በአርሶ አደሩ ማሳ ላይ የሚሰራና አርሶ አደሩም ጥቅሙን እስካየ ድረስ በየቀኑ የማረም፣ ውሃ የማጠጣትና የመንከባከብ ሥራ ስለሚሰራ የጽድቀት መጠኑ ከፍ ይላል" ብለዋል። በዚህ ረገድ በሲዳማ ክልልም ሆነ እንደአገር የተሰራው ሥራ መልካም መሆኑን ጠቅሰው፤ በበጋ ወራትም የችግኝ እንክብካቤ ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል።   የሲዳማ ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ መምሩ ሞኬ በበኩላቸው እንዳሉት፣ በክልሉ በአረንጓዴ አሻራ የተያዘውን መርሃ ግብር ለማሳካት እየሰራ ነው። በክልሉ ባለፈው ዓመት ብቻ ስነ ምህዳርን መሠረት ባደረገ መልኩ 306 ሚሊዮን የተለያየ ጥቅም የሚሰጡ ችግኞች መተከላቸውን ጠቁመዋል። የጥምር ግብርና ልማትን ለማሳካት ለቡና፣ ፍራፍሬ እና እንስሳት መኖ ልማት ትኩረት መሰጠቱንም አስታውሰዋል። በክልሉ የተተከሉ ችግኞች የጽድቀት መጠን በአማካይ ከ85 በመቶ በላይ መሆኑን ገልጸው፣ ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ለችግኞች የሚደረገው የእንክብካቤ ሥራ ቀጣይ እንደሚሆን አመልክተዋል።   በሲዳማ ክልል ሸበዲኖ ወረዳ የሞርቾ ነጋሽ ቀበሌ አርሶ አደር ጦና ጦምራ በሰጡት አስተያየት ስልጠና ወስደው የጥምር ግብርና ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል። ባላቸው አነስተኛ መሬት ላይ የተሻሻሉ የአቮካዶ ችግኞችን ከቡናና እንሰት ጋር አቀናጅተው ማልማታቸውን ገልጸዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ ካለሙት አቦካዶ 25 ኩንታል ለይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪ በማቅረብ 87 ሺህ ብር ገቢ ማግኘታቸውን ተናግረዋል። በቀጣይ ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ 580 የአቮካዶ ችግኞችን በመትከል እየተንከባከቡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።        
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ ቀንድ ተጨማሪ የ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዮሮ አስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ አደረገ
Nov 30, 2023 58
አዲስ አበባ፤ ህዳር 20/2016(ኢዜአ):- የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን በአፍሪካ ቀንድ ለተከሰተው የጎርፍ አደጋ ተጨማሪ የ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዮሮ አስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል። ኮሚሽኑ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያደርገው በሶማሊያ፣ በኢትዮጵያ እና በኬንያ በተከሰቱ የጎርፍ አደጋዎች ለተጎዱ ወገኖች መሆኑን የአውሮፓ ሲቪል ጥበቃ እና የሰብአዊ እርዳታ ስራዎች (ECHO) ትናንት ባውጣው መግለጫ አስታውቋል። ኮሚሽኑ በመግለጫው እንዳመለከተው፤ በሶማሊያ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተለይም በጁባ ወንዝ ተፋሰስ አካባቢ ለሚገኙ ዜጎች የ2 ሚሊዮን ዮሮ ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚደረግም አመልክቷል። ይህም የገንዘብ ድጋፍ በሶማሊያ በቅርቡ በኤልኒኖ ምክንያት በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ እና ለተፈናቀሉ ሰዎች ከዚህ በፊት ከተመደበው 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዮሮ ሰብአዊ እርዳታ በተጨማሪ የተሰጠ ነው ብሏል መግለጫው። ኮሚሽኑ በኢትዮጵያም በጎርፍ ለተጎዱ አካባቢዎች 1 ሚሊዮን ዮሮ ተጨማሪ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጾ፤ ድጋፉም ጎርፉ ጉዳት ባደረሰባቸው አካባቢዎች መጠለያ ለመሥራት፣ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ለማከፋፈል፣ የውሃ ማጣሪያ እና ለህክምና አገልግሎት እንደሚውል አስታውቋል። የገንዘብ ድጋፉ በሶማሌ፣ ኦሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች በአውሮፓ ህብረት የአደጋ ጊዜ ምላሽ ከጎርፉ በፊት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን ለመሥራት ከተሰጠው የ2 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዮሮ አፋጣኝ እርዳታ በተጨማሪ የተሰጠ መሆኑን ኮሚሽኑ አመልክቷል። ይህም በቅርቡ በኢትዮጵያ ለተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምላሽ አጠቃላይ የአውሮፓ ህብረት ያደረገውን የገንዘብ ድጋፍ ወደ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዮሮ እንደሚያሳድገው መግለጫው አመልክቷል።  
ኢጋድ ና ሱዳን   በሀገሪቱ የተፈጠረውን  ቀውስ በሚረግብበት ሁኔታ ላይ  ለመምክር ተስማሙ
Nov 27, 2023 110
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 17/2016(ኢዜአ)፡- ኢጋድ ና ሱዳን በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ በሚረግብበት ሁኔታ ላይ ለመምክር ተስማሙ። የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር መንግስት ሊቀመንበር አብዱልፈታህ አልቡርሃን እና የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ በሱዳን ቀውስ ላይ አስቸኳይ ምክክር ለማድረግ መስማማታቸውን የሱዳን መንግስት አስታወቀ፡፡ አል ቡርሃን በሀገሪቱ የተፈጠረውን ቀውስ ለመፍታት በሚቻልበት ጉዳይ ላይ ከኢጋድ ሊቀመንበር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ለመምከር ፍላጎታቸውን ያሳዩት ከጅቡቲው ፕሬዝዳንት እስማኤል ኦማር ጌሌ በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡ አልቡርሃን እና የኢጋድ ሊቀመንበር ምክክራቸውን በሳውዲ አረቢያ እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን የሱዳን ታጣቂ ሃይሎችና ፈጠኖ ደራሽ ሃይሉ በምክክሩ እንደሚገኙም የሱዳን መንግስት መግለጫ አመልክቷል፡፡ በመግለጫው የኢጋድ አስቸኳይ ጉባኤ የሱዳንን አሁናዊ የግጭት ሁኔታ እንዲፈታ ከሁሉም አካላት ስምምነት ላይ ተደርሷል ብሏል፡፡ የአፍሪካ ህብረት የሰላምና የፀጥታ ምክር ቤት ቅዳሜ እለት ባወጣው መግለጫ በሱዳን ያለውን ግጭት አውግዞ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በሀገሪቱ የተኩስ አቁም እንዲደረግ መጠየቁን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ፓኪስታን የብሪክስ/BRICS/ አባል ለመሆን ጥያቄ አቀረበች
Nov 25, 2023 114
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 14/2016 (ኢዜአ) ፦ ፓኪስታን የብሪክስ አባል ሀገራትን ለመቀላቀል ጥያቄ ማቅረቧን የፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ብሪክስ ለታዳጊ አገራት ጠቃሚ ቡድን መሆኑንም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመልክቷል። የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ሙምታዝ ዛህራ ባሎክ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ፓኪስታን የብሪክስ አባል ለመሆን ጥያቄ ማቅረቧን አረጋግጠዋል።   ሀገሪቱ የቡድኑ አባል ለመሆን ጥያቄ ያቀረበችው ቡድኑ ግልጽነት የተሞላበት፣ ብዙሃኑን ያቀፈና አካታች በመሆኑ መሆኑንም ቃል አቀባይዋ ተናግረዋል። በዚህም ፓኪስታን የቡድኑ አባል ብትሆን በቀጣይ ለሚፈጠረው አለም አቀፍ ትብብር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራት አብራርተዋል። ፓኪስታን ከብዙዎቹ የብሪክስ አባል ሀገራት እንዲሁም ከአዳዲሶቹ ጥያቄ ያቀረቡ አገራት ጋር ወዳጅነት እንዳላት መግለጻቸውን ዥንዋ አስነብቧል። ቃል አቀባይዋ አክለውም “ቡድኑ ፓኪስታን ያቀረበችው የአባልነት ጥያቄ የትብብርና አብሮ የመለወጥ ፍላጎት የያዘ ጥያቄ መሆኑን መሰረት አድርጎ ቀና ምላሽ እንደሚሰጠን ተስፋ እናደርጋለን" ብለዋል። ብሪክስ በአሁኑ ወቅት በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተካተቱበት የኢኮኖሚ ቡድን ሲሆን በነሀሴ ወር በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 15ኛው የቡድኑ የመሪዎች ጉባኤ የኢትዮጵያን፣ የኢራንን፣ የአርጀንቲናን፣ የግብፅን፣ የሳዑዲ አረቢያንና የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶችን የአባልነት ጥያቄ መቀበሉ ይታወሳል።
አፍሪካ ከአጋር አከላት ጋር በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት ለመስራት ዝግጁ ናት - ሙሳፋቂ መሃመት 
Nov 21, 2023 146
አዲስ አበባ ፤ ህዳር 11/2016 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ በሁሉም ዘርፍ ካሉ አጋር አከላት ጋር በትብብርና በጋራ ተጠቃሚነት ለመስራት ዝግጁ ናት ሲሉ የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳፋቂ መሃመት ተናገሩ። በጀርመን በርሊን በተካሄደው የ'ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳፋቂ መሃመት አፍሪካ የጋራ ተጠቃሚነት ለሚያረጋግጡ ተግባራት በሯ ክፍት ነው ብለዋል። በአህጉሪቷ ያለውን የኢንቨስትመንት ሀብት በሁለትዮሽ ትብብር በማሳደግ የጋራ ተጠቃሚነትንና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ዝግጁ ነን ሲሉም ነው ያረጋገጡት። የአፍሪካ ሀገራት እንደ ጀርመንና ቻይና ካሉ ሀገራት ጋር ሚዛኑን በጠበቀ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነት እየሰሩ መሆኑንም አውስተው ''ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤም በዚህ ረገድ ጉልህ ሚና እንደሚጫወት ተናግረዋል። እንደ አህጉር በኢንቨስትመንት መዳረሻዎችና በሌሎች መስኮች የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታትም አጋር አካላት በትብብር መስራት እንደሚገባቸው ማመልከታቸውን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል። በ2017 የጀርመን የጂ20 ፕሬዝዳንትነት ዘመን የተጀመረው የጂ20 'ኮምፓክት ዊዝ አፍሪካ' ጉባኤ ለውጥ ተኮር በሆኑ የአፍሪካ ሀገራት፣ በጂ 20 አጋሮች ብሎም ከእነዚህ ባሻገር ባሉ አካላት መካከል የንግግር እና የትብብር መድረክ ሆኗል።
ሐተታዎች
"ድሽታ ግና'' የኣሪዎች የምስጋናና የምርቃት በዓል!
Nov 30, 2023 48
በጣፋጩ ሰለሞን (ኢዜአ) በኦሞ ሸለቆ አካባቢ በማጎ ብሔራዊ ፓርክ አቅራቢያ የሚገኙት አሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡ ''ኣሪ ኣፍ'' ወይም ''ኣሪኛ'' የተሰኘ የመግባቢያ ቋንቋም አላቸው፤ ከኦሞቲክ የቋንቋ ነገድ ይመደባል። የኣሪ ማህበረሰብ የኢኮኖሚ መሰረት ጥምር ግብርና ሲሆን፤ አካባቢውም ቆላ፣ ደጋ እና ወይና ደጋ የአየር ጠባይ አለበት። ኣሪዎች የቤት አሰራራቸው፣ የሙዚቃ ጥበባቸው፣ የአጨፋፈር ስልታቸው፣ አለባበስና አጋጌጣቸው እጅግ ማራኪና የቱሪስት ቀልብን የሚስብ ነው። እግር ጥሎት ወደ አካባቢው ያቀና እንግዳ ባይተዋርነት እንዳይሰማው የሚያደርገው የኣሪዎች የእንግዳ አቀባበል ባህል የሚደነቅ ነው። አሪዎች ለቤታቸው እንግዳ የሆነን ሰው ''አቦቶ፤ ደኣይቶ'' - ውይ በሞትኩልህ! እንደማለት ነው እያሉ ደረታቸውን እየደቁ ይቀበላሉ። ለእንግዳው አርደውና አብልተው ሲመሽ ደግሞ እግሩን አጥበው አልጋቸውን ለቀው መሬት አንጥፈው ያስተኛሉ። የራሳቸው የጊዜ ቀመር አቆጣጠር ያላቸው ኣሪዎች ''ሎንጋ'' በተሰኘው የታህሳስ ወር አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት ይቀበላሉ። ይሄው አዲስ ዓመታቸው ደግሞ ''ድሽታ ግና'' የሚል መጠሪያ ያለው ትልቅ ዓመታዊ ክብረ በዓላቸው ነው።   የኣሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የባህል፣ የታሪክ፣ የቅርስ ጥናትና ልማት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዳኜ ገብሬ እንደሚሉት የአዲስ ተስፋና ወንድማማችነት ተምሳሌት የሆነው ድሽታ ግና በማህበረሰቡ ዘንድ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው በዓል ነው። የብሔረሰቡ የዘመን መለወጫ የሆነው የ"ድሽታ ግና" በዓል የሁለት ቃላት ጥምር ሲሆን ''ድሽታ'' ምስጋና "ግና'' ደግሞ ምርቃትን ይወክላል። የ"ድሽታ ግና" በዓል አርሶ አደሩ የዘራው ዘር ፍሬ አፍርቶ ጎተራው፣ ከብቶች ተዋልደው ጋጥ ሲሞላና ቤቱ በበረከት ሲትረፈረፍ ፈጣሪን የሚያመሰግኑበት፤ በባህል መሪዎች ቡራኬ የሚሰጥበት ታላቅ የምስጋናና የምርቃት በዓል ነው። በባህሉ መሰረትም ወደ አዲሱ አመት ቂምና ቁርሾን ይዞ መሻገር አይቻልም። ስለዚህ ከበዓሉ በፊት በዳይና ተበዳይ "ይቅር" ተባብለው ቂም በቀልን ከአሮጌው ዓመት ጋር ሸኝተው በፍቅር አዲሱን ዓመት እንደሚቀበሉ ነው አቶ ዳኜ የሚናገሩት፡፡ በዚህም መሰረት አንድ የኣሪ ማህበረሰብ አባል በዓሉ ከመድረሱ በፊት "በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ያስቀየምኩት ካለ" በሚል በየቤቱ እየተዟዟረ ይቅርታ ይጠይቃል። በዚህ አጋጣሚ ምናልባት እስከ ህይወት መጥፋት ድረስ የሚደርስ በደል ከተፈፀመ በዳዩ ሽማግሌ ልኮ ፀፀቱን ገልፆ ተበዳይን ተማፅኖ ይቅርታ ይጠይቃል፤ ይቅርታም ይደረግለታል። በየቤቱ ይቅርታ የሚጠይቅበት ምክንያት ቂምና ቁርሾ ወደ አዲሱ ዓመት መተላለፍ ስለሌለበት ነው። ቂምና ቁርሾ በውስጡ ይዞ በዓሉን የሚያከብር አሊያም የበዓል ድግስ ደግሶ ጎረቤት ጠርቶ ማብላት በብሔረሰቡ ዘንድ በጥብቅ የተከለከለ እንደሆነ አቶ ዳኜ ይገልፃሉ። አንድ የኣሪ ማህበረሰብ አባል ዕርቅ ከፈፀመ በኋላ "አርሼ ጥሩ ምርት አግኝቻለሁ፤ ነግጄ አትርፊያለሁ፣ ከብቶቼ ጋጣ ሞልተውልኛል፣ ቤቴ በበረከት ተትረፍርፏል" ሲል ካገኘው ላይ ቀንሶ ድል ያለ ድግስ ይደግሳል። ድግሱ የተራበውን በማብላት፣ የተቸገረውን በመጎብኘት ፈጣሪ ላደረገላቸው በጎ ነገር ከሌሎች ጋር አብሮ ማዕድ በመቋደስ ለፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት እንደሆነም አቶ ዳኜ ይናገራሉ። የ"ድሽታ ግና" በዓል እሸት የሚቀመስበት ነው። በበዓሉ ዕለት የኣሪ ባላባቶች እሸቱን፣ ወተቱን፣ ማሩን ከቀመሱ በኋላ መጪው ዘመን የተባረከ፣ የጥጋብ፣ የሰላምና የጤና እንዲሆን ይመርቃሉ። የሰላምና የአብሮነት እንዲሁም ያለፈውን ዘመን በመተው በአዲስ ተስፋ እጅ ለእጅ በመያያዝ ወንድማማችነትን በማጠናከር ሰርቶ በመለወጥ እና ለሌላው መትረፍን ጭምር የሚያበረታታ በዓል ነው። የብሄረሰቡ ተወላጅ የሆኑት አቶ ፍቃዱ ጋሲ በእንደሚናገሩት፤ የ"ድሽታ ግና" በዓል የፍቅር፣ የአንድነትና የይቅርታ አስተምህሮ ያለው አብሮነትን የሚያጠናክር ነው። በዓሉ የተጣላውን የሚያስታርቅ የተራራቀውን የሚያቀራርብ በመሆኑ በየዓመቱ በጉጉት ይጠበቃል። የዕድገትና ለውጥ መሰረት ጭምር ተደርጎ የሚወሰድ ነው። የዘንድሮውን የ"ድሽታ ግና" በዓልም አብሮነትን፣ አንድነትን፣ መረዳዳትን በሚያጎላ ብሎም የባህሉን እሴት በጠበቀ መልኩ ለማክበር መዘጋጀታቸውን አቶ ፍቃዱ ይገልጻሉ። የ"ድሽታ ግና" በዓል ጠቃሚ ባህላዊ እሴቶች ያሉትና ከትውልድ ወደ ትውልድ እየተሸጋገረ የመጣ ነው። አሁንም በዓሉ ባህላዊ እሴቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር በማስተማር ሃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ነው በአጽንኦት የተናገሩት። የ"ድሽታ ግና" በዓል ከመድረሱ አስቀድሞ እናቶች ከእንሰት እና ከእንስሳት ተዋጽኦ የሚገኙ ለክብር እንግዶችና ለአባ ዎራዎች የሚቀርቡ ባህላዊ ምግቦችን የማዘጋጀት ስራ ላይ እንደሚጠመዱ የገለጹት ደግሞ የብሔረሰቡ አባል ወይዘሮ ደብሪቱ ኣዳዮ ናቸው። ወጣት ሴቶችና ወንዶች ደግሞ ቤት በማስዋብ እና ግቢ በማሳመር ስራ ላይ ይሳተፋሉ። በበዓሉ ወቅትም በቤት ውስጥ የተዘጋጁ ምግቦች በዓይነታቸው ተለይተው ይቀርባሉ። ጥሩ ምግብ ያዘጋጀችና ምግቧ ጣፋጭ የሆነላት ሴት በግጥምና በዜማ ትወደሳለች። የ"ድሽታ ግና" በዓል "የተጣሉትን በማስታረቅ፣ ከተቸገሩ ወገኖች ጋር ቤት ያፈራውን አብሮ በመቋደስ ፣የታመሙትን በመጠየቅ በጋራ የምናከብረው ልዩ በዓል ነው" ያሉት ወይዘሮዋ "ድሽታ ግና" ፍቅር፣ አንድነት እና በጎነት ጎልቶ የሚታይበት ዕለት እንደሆነም ነው የገለጹት። በድሽታ ግና በዓል "በዕርቅ የማይቋጭ ጥል፣ የማይድን ቁስል፣ የማይሽር ጠባሳ የለም" ብለዋል። በነዋሪው ዘንድም ለዘመናት ለዘለቀው ሰላምና አንድነት እንዲሁም ጠንካራ የስራ ባህል መሰረት ነው፡፡ የኣሪ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤሊያስ ቃሾ በበኩላቸው፤ በዓሉ ከኣሪ ማህበረሰብ አልፎ ለመላው ኢትዮጵያዊያን የሚሆን "በርካታ ጠቃሚ እሴቶችን በውስጡ የያዘ ነው" ሲሉም ይገልጻሉ። "ድሽታ ግና" ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትን፣ መረዳዳትን እና አብሮነትን የሚያስተምር ህዝብ ለህዝብ የሚያቀራርብ ዕሴት ያለው በዓል ነው፡፡ የ"ድሽታ ግና" በአል ከጥንት አባቶቻችን ጀምሮ ሲወርድ ሲዋረድ የመጣ በዓል ቢሆንም የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ተደብቆ የኖረ ቱባ ባህል መሆኑን አንስተዋል። ሃላፊው እንዳሉት የ"ድሽታ ግና" በዓል ከለውጡ ማግስት በመንግስት በተሰጠው ትኩረትና ባገኘው ዕውቅና የአደባባይ በዓል ሆኖ በመከበሩ "የአገር ውስጥና የውጭ አገራት ቱሪስቶች እንዲጎበኙት በር ከፍቷል" ብለዋል። የ"ድሽታ ግና" በዓል እንደ ሌሎች ዕውቅና እንዳገኙ ክብረ በዓላት አድጎ፣ ጎልብቶ እንዲሁም ዕውቅና አግኝቶ ከአገራችን አልፎ የዓለም ቅርስ እንዲሆን የመላ ኢትዮጵያዊያንን እገዛ ያስፈልጋል። የዘንድሮው የድሽታግና በዓል ''ድሽታ ግና ለዘላቂ ሰላም እና ለፈጣን ልማት'' በሚል መሪ ሀሳብ በዞኑ ሁሉም አካባቢዎች በድምቀት እንደሚከበር የተናገሩት ደግሞ የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ናቸው። በዓሉ "የመተሳሰብ፣ የመረዳዳትና የዕርቀ-ሰላም በመሆኑ የተጣላውን በማስታረቅ፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይከበራል" ብለዋል። ሰላምና ወንድማማችነትን የሚሰብከው "ድሽታ ግና" የአሮጌው ዘመን ማጠቃለያና አዲሱን ዘመን ብስራት ከአጎራባች ዞኖች እና ከመላው ኢትዮጵያዊያን ጋር ዕሴቱን በጠበቀ መልኩ በአደባባይ በጋራ ለማክበር አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል። የ"ዲሽታ ግና" ዕሴቶች አገር በቀልና በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው መሆኑን ያነሱት ዋና አስተዳዳሪው፤ እንደአገር ዘላቂ ሰላምና ልማት እንዲሁም የብልጽግና ጉዞን ለማጠናከር "ለተወጠኑ ግቦች ስኬት የሚኖረው ፋይዳ ከፍተኛ በመሆኑ ልንጠቀምበት ይገባል" ብለዋል። ከወርሃ ህዳር አጋማሽ ጀምሮ ከቤተሰብ እስከ ኣሪ ባላባቶች ቅደም ተከተሉን ጠብቆ የሚከበረው የ"ድሽታ ግና" በዓል ታህሳስ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ደግሞ የአዲስ ዓመት ብስራት ይታወጅበታል። በዕለቱ በጂንካ ከተማ በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በድምቀት ይከበራል። ''ዑሳ ዎም ዣዕሼ !'' እንኳን አደረሳችሁ!
ኢሬቻ የአብሮነት ማሰሪያ ሐረግ
Oct 6, 2023 667
ኢሬቻ የአብሮነት ማሰሪያ ሐረግ (አሸናፊ በድዬ) ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነው፤ ከክረምት ወቅት መለያየትና መራራቅ በኋላ ሰዎች በአብሮነት ብርሃን ለማየት ያበቃቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት። ስለ ሰላምና አንድነት የሚዘመርበት፣ ስለመጪው ጊዜ መልካም ምኞት የሚገለጥበት፣ ሁሉን ላደረገ ፈጣሪ ምስጋና የሚቸርበት የአብሮነት በዓል ነው። በልመናው፣ በምርቃቱ፣ በምስጋናው ሁሉ ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!) የሚሉ ድምፆች ይስተጋባሉ።   "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! የእውነትና የሰላም አምላክ! ከስህተትና ከክፉ ነገሮች ሁሉ ጠብቀን! ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ!" በማለት ይመረቃል። ሕዝቡም ይሁንልን ይደረግልን ሲል "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ!" ይላል። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም በማግስቱ እሑድ መስከረም 27 ቀን በቢሾፍቱ ሆራ ሀርሰዲ ይከበራል። የክራምት ወራት እንዳበቃ የሚከበረው "ኢሬቻ መልካ" (በውሃ ዳርቻ የሚከበር) ሲሆን በዓመቱ አጋማሽ ላይ የሚከበረው "ኢሬቻ ቱሉ" ደግሞ በተራራማ ቦታ የሚከበር ነው። ኢሬቻ መልካ የሚከበረው በመስከረም ወር ከመስቀል በዓል በኋላ ሲሆን፤ የክረምት ወራት የዝናብ፣ የደመና፣ የጭቃና የረግረግ ወቅት አልፎ ለፈካው ወራት በመብቃቱ ምስጋና የሚቀርብበት ነው። ኢሬቻ ቱሉ የሚከበረው የበጋው ወራት አልፎ የበልግ ዝናብ በሚጠበቅበት ወቅት ነው። በዚህም ፈጣሪ ''እርጥበት አትንፈገን፣ ወቅቶች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይምጡ፤ የዝናብ ንፋስ ስጠን'' በማለት ለፈጣሪ ተማጽኖ የሚቀርብበት ነው። "ይህን ተራራ የፈጠርክ ፈጣሪ ወቅቱን የሰላም አድርግልን፣ የሰላም ዝናብ አዝንብልን፣ ጎርፍን ያዝልን፣ የተዘራው ፍሬ እንዲያፈራ እንለምንሃለን" እያለ በኢሬቻ ቱሉ ላይ ፈጣሪውን ይለምናል፡፡ በኢሬቻ በዓል የፈጣሪ ምህረት፣ ዕርቅ፣ እዝነት እና በዓሉ የሰላም በዓል እንዲሆን ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ኦሮሞ ፈጣሪውን ይጠይቃል፤ ይማፀናል፤ ለተደረገለትም ነገር ሁሉ ያመሰግናል። የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን፤ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር የቆየ በዓል ነው። በዓሉ በዋናነት በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፤ በቢሾፍቱ ከተማ በሆራ ሀርሰዲ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ታድሞ የሚከበር ቢሆንም በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖችና ወረዳዎች በድምቀት ይከበራል። የኦሮሞ ሕዝብ ምድርን እና ሰማይን ለፈጠረው ፈጣሪ "ዋቃ" ምስጋናውን ለማድረስ የኢሬቻ በዓልን ያከብራል ይላሉ አባገዳዎች። የኦሮሞ ሕዝብ በዕድሜ ልዩነት ሳይገደብ የኢሬቻ በዓልን ለዘመናት በጋራ፣ በአንድነትና በፍቅር ሲያከብር ቆይቷል። በዝናባማው የክረምት ወቅት በጅረቶችና ወንዞች መሙላት ምክንያት ተራርቆ የቆየው ዘመድ አዝማድ በኢሬቻ በዓል ማክበሪያ ሥፍራ ይገናኛል፤ ይጠያየቃል፤ ናፍቆቱንም ይወጣል። አባቶች ክረምት በለሊት ይመሰላል ይላሉ። ለሊት ደግሞ ጨለማ ነው። ጨለማው ሲነጋ ደግሞ ብርሃን ነው፤ ብርሃን ደግሞ ውበት ነው፤ መታያና መድመቂያም ነው። ለዚህ ነው በኢሬቻ በዓል አከባበር ላይ ሁሉም ውብ የባህል ልብሱን በመልበስ በደስታ በዓሉን ለማክበር የሚመጣው። ሕዝቡ በዓሉ ወደሚከበርበት ሥፍራ የሚሄደው በተናጠል ሳይሆን በሕብረትና በአንድነት ነው፡፡ ለዚህ ነው ኢሬቻ የአንድነትና የአብሮነት በዓል ነው የሚባለው። በኢሬቻ ልዩነት የለም፤ ፀብ የለም፤ ክፋት የለም፤ ይልቁንም ምስጋና ይጎርፋል፤ ፍቅር ይሰፍናል፤ አብሮነት ያብባል። ኢሬቻ በኦሮሞ ሕዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው የሰላምና የአብሮነት ምልክት ሲሆን፤ የኢሬቻ በዓልን ለማክበር የሚወጣው ታዳሚም እንደ እርጥብ ሣር ወይም አበባ ያለ እርጥብ ነገር በእጁ ይዞ የበዓሉን ስነ-ስርዓት ያከናውናል። ይህን የሚያደርገውም "ፈጣሪያችን ሆይ አንተ ያፀደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመሰግንሃለን" በማለት የፈጣሪን መልካምነት ለማሳየት ነው። በሌላ በኩል እርጥብ ሣር የልምላሜ ምልክት በመሆኑ የመልካም ምኞት መግለጫም ጭምር በመሆኑ ነው በኢሬቻ በዓል እርጥብ ሣር የሚያዘው። የኦሮሞ ሕዝብ ለሰላም ትልቅ ሥፍራ ይሰጣል። ሰላም ካለ ሁሉም ነገር አለ ብሎም ያምናል። በምርቃቱም "ቡና ፊ ነጋአ ሂንደቢና" ብሎ ይመራረቃል። ቡናና ሰላም አያሳጣችሁ ማለት ነው። ለዚህም ነው በኢሬቻ በዓል ለመላው የሰው ልጅ ሰላምና ደኅንነት ፈጣሪ የሚለመነው። ሳል ይዞ ስርቆት፤ ቂም ይዞ ፀሎት እንዲሉ አበው በኢሬቻ የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ረስቶ በንጹህ ልቦና ፈጣሪ ንጹህ ወዳደረገው የውሃ አካል ይሄዳል፤ በዚያም ፈጣሪውን ያመሰግናል። የኢሬቻ በዓል ሲከበር ከሚከወኑ ሥርዓቶች መካከል ሴቶች ሲቄ፣ እርጥብ ሣር እንዲሁም ጮጮ ይዘው ከፊት ሲመሩ አባ ገዳዎች ደግሞ ቦኩ፣ አለንጌ እና ሌሎችንም በበዓሉ ሥርዓት የሚፈቀዱትን ሁሉ በመያዝ ወደ ሥርዓቱ አከባበር ያመራሉ። ኦ ያ መሬሆ…………………መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ኡማ ሁንዳ መሬሆ…………………ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ ለፋ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ ያ ዋቃ መልካ ኡምቴ መሬሆ………………… ያ መሬሆ መሬሆ………………… መሬሆ እያሉ ያመራሉ። የሁሉ ፈጣሪ፣ ምድርን የፈጠርክ፣ ወንዙን የፈጠርክ . . . ምስጋና ለአንተ ይሁን በማለት ያመሰግናሉ፤ ይዘምራሉ። የኢሬቻ በዓል ሥነ-ሥርዓት በአባመልካ ተከፍቶ በአባ ገዳዎች ተመርቆ ከተጀመረ በኋላ መላው ሕዝብ በአንድነት ሥርዓቱን ያከናውናል። ኢሬቻ ሁሉም በጋራ የሚያከብረው፣ የሁሉም ማጌጫ፣ መድመቂያ እና የአብሮነት መገለጫ ነው። ብሔር ብሔረሰቦች የሚታወቁበትን ባህላዊ ልብስ በመልበስ በቋንቋቸው ፈጣሪን እያመሰገኑ በዓሉን በአንድነት ያከብራሉ። ለዚህም ነው ኢሬቻ ከኦሮሞ ሕዝብ አልፎ የመላው ኢትዮጵያውያን በዓልና መገለጫ ነው የሚባለው። በርካታ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዲ በዓላት ላይ ለመታደም ወደ አገር ቤት ይመጣሉ። የውጭ አገራት ጎብኚዎችና እንግዶችም በትዕይንቱ ይታደማሉ። ለአብነትም ባሳለፍነው ዓመት ከኬንያ አገር የመጡ ልዑካን በዚህ በዓል ላይ በመታደም የበዓሉን ትልቅነት እና የኢትዮጵያውያን የአብሮነት መገለጫ መሆኑን መመስከራቸው ይታወሳል። በዚህ ዓመትም የሦስት ጎረቤት አገራት ልዑካን በዚህ በዓል ላይ እንደሚታደሙ የተገለጸ ሲሆን፤ የኬንያ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ አገራት ተወካዮች እንደሚታደሙ ይጠበቃል። አያሌ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ያሉት ይህ የምስጋና በዓል እውነተኛ ወንድማማችነት የሚታይበት፣ አንድነት የሚጎላበት፣ አብሮነት የሚጠናከርበት፣ ሰላምና ተስፋ የሚታወጅበት ትልቅ አገራዊ እሴት ነው። በባህል አልባሳትና ጌጣጌጦች፣ ባህላዊ ምግቦችና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦችና ተቋማት ኢሬቻና መሰል የአደባባይ በዓላትን እንደመልካም የገበያ አማራጭ ይጠቀሙባቸዋል። ኢሬቻ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች በስፋት የሚተዋወቁበት ታላቅ መድረክ ነው። በእርግጥም ይህንን ውብ የጋራ እሴት ጠብቆ ለትውልድ ማስተላለፍ ያስፈልጋል። ኢሬቻ የምስጋና በዓል ነውና በምስጋና እንደጀመርን በምስጋናና ምርቃት እንሰነባበት። "ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! ከመጥፎ ነገር ጠብቀን! ንጹህ ዝናብ አዝንብልን! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! እውነትን ትቶ ከሚዋሽ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)  
"በገበታ ለትውልድ" የሚለማው የደንቢ ሀይቅ
Oct 4, 2023 628
"በገበታ ለትውልድ" ስለሚለማው የደንቢ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ምን ያህል ያውቃሉ? (በቀደሰ ተክሌ ከሚዛን አማን) ደንቢ ሃይቅ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ሲሆን በእኛ የዘመን ቀመር በ1970ዎቹ የተሠራ ነው። በተፈጥሮ መስህቦች የተከበበው የደንቢ ሰው ሰራሽ ሃይቅ ለአካባቢው ብርሃንን ይፈነጥቅ ዘንድ የተሰራውን የቀድሞ የደንቢ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድብን ተከትሎ የተፈጠረ ሃይቅ ነው። የደንቢ ሃይቅ ለአካባቢው ማህበረሰብ ባለውለታ ነው፤ የመጀመሪያውን የኤሌክትሪክ ብርሃን ያገኙበት ነውና። ኤሌክትሪክ ማመንጫ ግድቡ ከመልክዓ ምድሩ ጋር እንዲስማማ ተደርጎ የተገነባ በመሆኑ ውሃው ከላይ ወደ ታች በሁለት ምዕራፍ ቁልቁል እንዲወረወር ዕድልን ፈጥሮለታል። የመጀመሪያው የኤሌክትሪክ ሃይልን ለማመንጨት በዝግታ የሚወርደው ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ሃይል አመንጭቶ ሲወጣ እጅግ ውብ የሆነ ፏፏቴን ፈጥሮ ወደ ታች የሚወርደው ነው። የደንቢ ፏፏቴ ከሃይቁ ወረድ ብሎ ስለሚገኝ "ደንቢ ሃይቅና ፏፏቴ" እየተባለ ይጠራል። ሃይቁን አይቶ ፏፏቴውን ሳያዩ መመለስ የማይቻል ነገር ነው። የደንቢ ፏፏቴ ከላይ ከዓለት ዓለት እየተጋጨ ሲወረወር የሚያሰማውን በግርማ ሞገስ በታጀበ ድምጽ፤ በተራራ ቀበቶ ተገምዶ ወደ ማረፊያ ቦታው ሲምዘገዘግ በለመለመው መስክ ላይ አሻግረው የሚቃኙት የተፈጥሮ ውበት ነው። ያሻው ወደ ተራራው ጫፍ ጠጋ ብሎ እንደ ጢስ በሚተነው የውሃ አካል ፊቱን እያስመታ አልያም ከሃይቁ ፊት ለፊት ራቅ ብሎ ተቀምጠው እየተመለከቱ መንፈስን የሚያድሱበት ውብ የፏፏቴ ሥፍራ ነው።   ከላይኛው የግድቡ አናት ወደ ታችኛው ለመውረድ 640 ደረጃዎችን አቆልቁሎ መጓዝን ይጠይቃል። ይህ ትዕይንት ደግሞ የደንቢ ሃይቅ ሌላኛው መስህብ ነው። የደረጃዎቹን የመውጣትና የመውረድን ድካም አረንጓዴ ካባ የደረበው የሥፍራው ልምላሜ እንዲዘነጋ ያደርጋል። የደንቢ ሃይቅ አካባቢ ቀልብን ስቦ ድካምና ሌላ ሃሳብን አስትቶ ሃሴትን የሚያጎናጽፍ የተፈጥሮ ፀጋን የታደለ ነው። የደንቢ ሃይቅና ፏፏቴ ግርማ ሞገስ ምስጢሩ የአካባቢው ደን ነው። በረጃጅም እድሜ ጠገብ የሃገር በቀል ዛፎች የተከበበ ነው። በእምቅ ደኑ ውስጥ የሚገኙ አዕዋፋት ለሚገባ ለሚወጣው ሁሉ እንደየ ፀጋቸው ያዜማሉ። ጉሬዛዎችና ጦጣዎች ከዛፍ ወደ ዛፍ እየዘለሉ እጅ ይነሳሉ። ይህ አካባቢ የተጎናጸፈው የቱሪዝም ፀጋ ከብዙዎች ዐይን ርቆ ቆይቷል። አሁን ግን በቃ ብሎ ሚሊዮኖች ሊጎበኙት ጊዜው ተቃርቧል። አካባቢው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምሥረታን ተከትሎ ወደ ሥፍራው ጎራ ለሚሉ ሚኒስትሮችና የሃገር መሪዎች የማስተዋወቅ ሥራ በመሠራቱ "የገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክት አንዱ አካል ሊሆን ችሏል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ቦታው ድረስ በመሄድ፣ በማየትና ለዓለም ጭምር በማስተዋወቅ የደንቢ ሎጅ ግንባታን የመሠረት ድንጋይ አስቀምጠዋል። በመድረኩ ኢንቨስትመንት ግሩፕ የሚለማው የደንቢ ሃይቅ ሎጅ ፕሮጀክት በአንድ ዓመት ተኩል የጊዜ ገደብ ውስጥ የሚጠናቀቅ ነው። በተጨማሪም በደንቢ ሃይቅ ሎጅ አቅራቢያም ሌላው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረት ድንጋይ የተቀመጠለት የአየር ማረፊያ ግንባታ ፕሮጀክት ይበልጥ አካባቢውን የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የሚያስችል ነው። የሎጅ ግንባታው ተጠናቆ ወደ ሥራ ሲገባ፤ ደንቢ ላይ ያረፈ ጎብኚ ከ40 በላይ የሚፍለቀለቁ የዑሲቃ ፍል ውሃ ቦታዎችን፣ የጋርንናንሳ ተራራን እና ሌሎች የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቤንች ሸኮ ዞን የተፈጥሮ ፀጋዎችን በቅርብ ርቀት መጎብኘት ይችላል። የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ እና የፋይናንስ እና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ ሳሙኤል አሰፋ በርካታ የቱሪዝም ሃብቶችን በዙሪያው አቅፎ የያዘው ደንቢ በቅርቡ የቱሪዝም ኢኮኖሚ አነቃቂ ሃይል ይሆናል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በነደፉት የ"ገበታ ለትውልድ" ፕሮጀክት ሲለማ ከሃገር ውስጥ ባሻገር ከሃገር ውጭ በርካታ ጎብኚዎችን በማስተናገድ የውጭ ምንዛሬ የሚገኝበት ፕሮጀክት መሆኑንም ሳይዘነጉ። እንደዚህ አይነት ሃገራዊ ፕሮጀክቶች በአካባቢያቸው የተለመዱ አለመሆናቸውን ጠቅሰው የመንግስትን እይታና በአካባቢው ያለውን ሃገራዊ አቅም ወደ ኢኮኖሚ ለመቀየር ትልቅ ትርጉም ያለው መሆኑንም አድንቀዋል። የቤንች ሸኮ ዞን በርካታ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ መስህብ ሃብቶች እንዳሉት ገልጸው የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያለውን ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለመቀላቀል መንግስት የከፈተውን መልካም አጋጣሚ መጠቀም እንደሚገባ ነው የጠቆሙት። ከአንድ ዓመት ተኩል በፊት መሠረት ተቀምጦለት እየተገነባ ያለውን የሚዛን አማን ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ግንባታን መልካም አጋጣሚውን ለመጠቀም አንዱ ዕድል እንደሆነም ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ለመጎብኘት የሚመጡ እንግዶችን ቆይታ ለማራዘም እና ወደውት ተደስተው እንዲመለሱ ለማስቻል ከወዲሁ በቂ ዝግጅት እናደርጋለን ያሉ ሲሆን በቅርብ ርቀት ያሉ የቱሪስት መዳረሻዎችን ምቹ የማድረግ ሥራም በትኩረት ይከናወናል ብለዋል። የሚዛን አማን ከተማ ነዋሪው አቶ ያሬድ ካንጃ ደንቢ በቅርብ ርቀት ቢገኝም ያልለማ በመሆኑ ብዙዎች የመጎብኘት ዕድል እንዳላገኙ ተናግረዋል። ደንቢ ሃይቅ እና ፏፏቴ ከሃይቅነትና የቱሪስት መስህብነት ባሻገር በሥራ ዕድል ፈጠራም ጭምር ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ አለው ነው ያሉት። የሎጁ መገንባት የዞኑን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ወደ ዓለም ገበያ ያስገባል የሚል ተስፋ መሰነቃቸውንም አቶ ያሬድ አልሸሸጉንም። "እንደ አካባቢው እምቅ የተፈጥሮ ሃብት አቅም አንጻር ይህ ጅምር ነው፤ በቀጣይ በርካታ ፕሮጀክቶችን እንጠብቃለን" ብለዋል።      
የብርቅዬዎችን አምባ በዩኔስኮ መዝገብ ላይ እናቆይ! 
Sep 30, 2023 847
በመሐመድ ረሻድ ባሌ ሮቤ(ኢዜአ) ኢትዮጵያ የብዙ ሕብረ ብሔራዊ ባህልና ማንነት ያሏቸው ሕዝቦች ሀገር ነች። የተፈጥሮ ገፅታዋ በልዩነት ውስጥ አንድነትን፣ በብዝሃነት ውስጥ ህብረትን አጎናጽፏታል። ከህዝቦቿ ጥምር ውበት ባለፈ ተፈጥሮ ያደላት የበርካታ ጸጋዎች ባለቤትም ናት። መስራት የሚገባውን ያክል ሳይሰራበት ቢቆይም አሁን ላይ እነዚህን ተፈጥሯዊ ሃብቶች የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማሳደግና የዘርፉን ተጠቃሚነትም ለማሳደግ እየተሰራባቸው ይገኛል። በዚህ ረገድ ሥሙ በቀዳሚነት ጎልቶ የሚነሳው ባለብዙ የተፈጥሮ ውበት ባለቤት የሆነውና "አንድ ፓርክ ብዙ ዓለማት (One Park Many World)" ተብሎ የሚታወቀው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ አንዱና ዋነኛው ማሳያ ነው። በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ባሌ ዞን የሚገኘው ይህ ብሔራዊ ፓርክ ከአዲስ አበባ በ411 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። በድንቅ የተፈጥሮ ጸጋ የታደለው ይህ ስፍራ እንኳን ደህና መጣችሁ የሚያሰኝ ሃሴትን የሚሞላ ግርማ ሞገስን የተላበሰ ነው።   ፓርኩ በሀገራችን ከሚገኙ 27 ብሄራዊ ፓርኮችና ሌሎች ጥብቅ ደን ስፍራዎች አንዱ ነው። በውስጡ በርካታ የብዝሃ-ህይወት ሃብትን የያዘና የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስብ ነው። የደጋ አጋዘን፣ቀይ ቀበሮ፣ትልቁ ፍልፈል፣ የሳነቴ አምባ፣ የሀረና ጥቅጥቅ ደን ፓርኩ ከሚታወቅባቸው ብርቅዬዎች መካከል በዋነኞቹ ናቸው። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በ2 ሺህ 150 ካሬ ኪሎ ሜትር ስፋት ላይ ተከልሎ የተመሰረተው በ1962 ዓ.ም ሲሆን በውስጡ ከ1 ሺህ 600 በላይ የተለያዩ የእጽዋት ዝርያዎች፣ ከ78 ዓይነት በላይ አጥቢ የዱር እንስሳት እና 300 የሚደርስ ዝርያ ያላቸው አዕዋፍን ይዟል። ከነዚህ መካከል 32 የእጽዋት ዝርያዎች እና በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙ 31 ብርቅዬ የዱር እንስሳት እንደሚገኙበትም ከብሔራዊ ፓርኩ ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡ ጥቂት ስለ ብሔራዊ ፓርኩ ጸጋዎች፦ ⦁ የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) - የሳነቴ አምባ የሳነቴ አምባ የተፈጥሮ ድንቅ ስራ የሚታይበት የፓርኩ ልዩ ገፅታ የሚንፀባረቅበት ነው። ስፍራው በአፍሪካ ካሉት ፕላቶዎች በስፋቱ 17 በመቶ የሚሸፍን ሜዳማና ትልቁ የአፍሮ አልፓይን አምባ ወይም የሰማይ ላይ ደሴት(The Island in the Sky) ነው፡፡ ይህ ውርጫማ ስፍራ የከፍተኛ ተራራዎች መገኛ ሲሆን፤ በሀገራችን በከፍታው ሁለተኛ የሆነውና ከባህር ጠለል በላይ 4ሺህ 377 ሜትር ከፍታ ያለው የቱሉ ዲምቱ ተራራ መገኛም ነው፡፡ የሳነቴ አምባ ከመልክዓ ምድሩ አቀማመጥ ባሻገር የዝናብ ውኃን የመሰብሰብና የማጥራት አቅም ያለው ድንቅ መልክዓ ምድር ነው። በተለይ በአካባቢው የሚገኙ የባሌ ፍልፈሎች ከጠላቶቻቸው ለማምለጥ ሲሉ የሚሰሯቸው እልፍ ጉድጓዶች ውኃው ወደ ከርሰ ምድር እንዲሰርግ ከፍተኛውን ሚና ይወጣሉ። ይህም ከ40 የሚበልጡ ጅረቶች ከፓርኩ እንዲፈልቁ ምክንያት ሆኗል። ጅረቶቹ አቅማቸውን በማሰባሰብ እንደ ዋቤ ሸበሌ፣ ገናሌ፣ ዌልመልና ዱማል የመሳሰሉ ትላልቅ ወንዞችም መነሻ ቦታ ነው፡፡ ከዚህ የተነሳ ሳነቴ የ'ውኃ ጋን' የሚል ስያሜንም እንዲያገኝ ምክንያት ሆኗል። ከሳነቴ አምባ የሚፈልቁት እነዚህ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞች በዞኑ የደሎ መናና ሀረና ወረዳ ለሚገኙ የአርብቶ አደር ማህበረሰብ የዘመናዊ መስኖ ልማት ምንጭ እየሆኑም መጥተዋል። በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የግንባታ ሥራውን ከሶስት ዓመት በፊት ያስጀመሩትና ተጠናቆ ለአገልግሎት ሲበቃ ከ11 ሺህ ሄክታር መሬት በላይ የማልማት አቅም ያለው የዌልመል ዘመናዊ የመስኖ ልማት ፕሮጄክት አንዱ ማሳያ ነው። ኢትዮጵያን ጨምሮ በኬንያና ሶማሊያ የሚኖረው ከ30 ሚሊዮን በላይ ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ህልውው ከዚህ አካባቢ በሚፈልቁ ተፋሰሶች ላይ የተመሰረተ መሆኑን በብሔራዊ ፓርኩ የዱር እንስሳት ክትትልና የምርምር ቡድን መሪ አቶ ሴና ገሼ ያስረዳሉ። ⦁ "የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት" የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በሀገራችን በጥቅጥቅ ደን ሽፋኑ ከያዮ ደን ቀጥሎ የሁለተኛነትን ስፍራ የያዘው የሀረና የተፈጥሮ ደን ሀብት መገኛም ነው፡፡ ደኑ የፓርኩን 1ሺህ ካሬ ኪሎ ሜትር ገደማ ይሸፍናል፡፡ ከሀገራችን አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ለካርቦን ንግድ ታጭተው ህብረተሰቡ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆን እያገዙ ከሚገኙ የሀገራችን ድንቅ ደኖች ውስጥም አንዱ ሆኗል። የሀረና የተፈጥሮ ደንን በአሳታፊ የደን ልማት አስተዳደር አርሶ አደሩን በ38 የደን ማህበራት በማደረጃት ባለፉት አራት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች ከ179 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ከከርቦን ንግድ ሽያጭ መገኘቱን በኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዕቅድ ክትትል የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ቀነዓ ያደታ ይገልጻሉ። የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በውስጡ ባሉት የእጽዋት እና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት ሲታይ ከዓለም በ34ኛ፣ ከአፍሪካ ደግሞ በ12ኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በተለይ ፓርኩ በውስጡ ከሚገኘው እጽዋትና የእንስሳት ብዝሃ ህይወት በተጓዳኝ ለአዕዋፍ ዝርያ ካለው ምቹ ሁኔታ የተነሳ “Bird Site International” የተሰኘ ዓለም አቀፍ ድርጅት "በዓለም ከሚገኙ ምቹ የአዕዋፍ መገኛዎች አንዱ ስለመሆኑም አብነቱን ይሰጣል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ከላይ የተጠቀሱ እውናታዎችን ጨምሮ ሌሎች የፓርኩ እምቅ አቅሞችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት እ.ኤ.አ. በ2009 በጊዜያዊ መዝገቡ ላይ ማስፈሩም ይታወሳል። መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ በርካታ ባለድርሻ አካላት ባለፉት ዓመታት ቅርሱ በቋሚነት በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ከድር ያስታውሳሉ። በተለይ ፓርኩ በድርጅቱ በቋሚ የቅርስ መዝገብ ላይ እንዳይሰፍር ማነቆ ሆነው ከቆዩት መካከል ልቅ ግጦሽ፣ የሰደድ እሳት፣ ህገ ወጥ ሰፈራ ሲሆኑ፤ ችግሮቹ አሁንም ያልተሻገርናቸውና የሁሉንም ትኩረት የሚሹ ናቸው ይላሉ። በተለይ በፓርኩ አልፎ አልፎ የሚያጋጥመው ሰደድ እሳት የብርቅዬ የዱር እንስሳትን መኖሪያና ምግባቸውን ስለሚያሳጣቸው በቀጣይነት በትኩረት ሊሰራበት እንደሚገባም ያስረዳለሁ። ⦁ "ፓርኩን ለማቆየት የተከፈለ የህይወት መስዋዕትነት" ይህ የብርቅዬዎች አምባ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ በተላይም የባሌ ህዝብ፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አያሌ መስዋዕትነት ከፍለዋል። በተለይ በ2007 ዓ.ም ፓርኩ ላይ ተነስቶ የነበረው የሰደድ እሳት በባሌ ህዝብ ዘንድ የማይረሳ ጠባሳ ጥሎ ማለፉን ነው አቶ ሻሚል ያስታወሱት። በግንዛቤ ማነስ ጭምር ግለሰቦች ለከብቶቻቸው የተሻለ መኖ ለማግኘት በማሰብና ለማር ቆረጣ በፓርኩ ክልል ውስጥ እሳት በመለኮስ ያስነሱትን ቃጠሎ ከሌሎች ጓደኞቹ ጋር ለማጥፋት ጥረት ሲያደርግ ህይወቱን ያጣውን የፓርኩን ሰራተኛና የአካባቢ ተቆርቋሪ ወጣት ቢኒያም አድማሱን በማሳያነት አቅርበዋል፡፡ ወጣቱ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና በሚል በፓርኩ ውስጥ የማስታወሻ ሀውልት ቆሞለታል። እንዲሁም በተጠናቀቀው የ2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ባካሄደው ዓመታዊ ግምገማ የተፈጥሮ ሀብት ጀግና ለሆነው ለቢኒያም አድማሱ ቤተሰቦች ዕውቅናና ሽልማት ሰጥቷል። እንዲያም ሆኖ ግን ጠባሳው በብዙ የአካባቢ ተቆርቋሪዎች ዘንድ ሁሌም የሚታወስ ነው፡፡ ይህ በብዝሃ ህይወት ስብጥሩና በአያሌ ጸጋዎች የተንበሸበሸው የብርቅዬዎች አምባ በቅርቡ በሳውዲ አረቢያ ሪያድ ተካሂዶ በነበረው 45ኛው የተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ቅርስ ጉባኤ ላይ በኢትዮጵያ ሁለተኛው ታላቅ የተፈጥሮ ቅርስና በዓለም ደግሞ 11ኛው ቅርስ በመሆን በቋሚነት መመዝገቡ ሁሉንም የአገሪቱን ዜጎች አስደስቷል። ፓርኩ በዓለም ቅርስነት መመዝገቡ ለቅርሱ የሚደረግለትን ጥበቃ ለማጠናከርና መስህብነቱን ለመጨመር እድል እንደሚፈጥር የዞኑ ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ ሮብዳ ጃርሶ ይገልጻሉ። እንዲሁም ፓርኩ በዩኔስኮ እውቅና ማግኘቱ የቱሪስት ፍሰቱን በማሻሻል ከቱሪዝም የሚገኘውን ዓመታዊ ገቢ በማሳደግ ሀገርና ሕዝብ ከዘርፉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዕድል የሚፈጥር ነው ይላሉ። ቅርሱን በዩኔስኮ ማስመዝገብ ብቻውን ግብ አይደለም ያሉት ወይዘሮ ሮብዳ ህብረተሰቡ ተንከባክቦ ለዛሬ ያቆየውን ቅርስ በዘላቂነት መጠበቁ ላይ እንዲበረታም አሳስበዋል። በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ሰው ሰራሽ ጫና ሊቀነሱ የሚያስችሉ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ገቢራዊ እያደረጉ ከሚገኙ መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት መካከል የፍራንክፈርት ዞሎጂካል ሶሳይቲ ድርጅት የባሌ ዞን ቅርንጫፍ አስተባባሪ አቶ አብዱርቃድር ኢብራሂም የፓርኩ የጥበቃ ሥራ የአካባቢውን ማህበረሰብ ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ይናገራሉ። በተለይ በፓርኩ አጎራባች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች በፓርኩ ላይ እያደረሱሷቸው ያሉ ጫናዎችን ለመቀነስ ህይወታቸውን የሚመሩበት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ተጽዕኖውን መቀነስ እንደሚቻል ያምናሉ። ፓርኩን በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ላይ ለማስፈር የተደረገው የተቀናጀ ጥረት እንዳለ ሆኖ ይሄው ገጽታውና ክብሩ ተጠብቆ እንዲቆይ ከፍተኛ ጥረትና ቁርጠኝነትን እንደሚጠይቅም በአጽኖኦት ያስረዳሉ። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ነፊሳ መሐመድ እንዳሉት ፓርኩን ለመጎብኘት ለሚመጡ የሀገር ውስጥና የውጭ አገር ጎብኝዎች የዕደ ጥበብ ቁሳቁሶችን በመሸጥ በሚያገኙት ገቢ ህይወታቸውን እየመሩ ናቸው። እንደሳቸው እምነት በአሁኑ ወቅት ፓርኩ በቋሚነት በዓለም ቅርስነት በመመዝገቡ ለቅርሱ የሚያደርጉትን ጥበቃ ይበልጥ እንዲያጠናክሩ መነሳሳትን የሚፈጥር ነው። የመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ መምህርና በአካባቢ ሳይንስ ላይ ምርምር የሚያደርጉት አቶ አልይ መሐመድ እንዳሉት በፓርኩ አካባቢ የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፓርኩ በሚፈለገው ደረጃ ተጠቃሚ ቢሆኑ የጥበቃውን ሥራ በእጅጉ ያቃልላል የሚል እምነት አላቸው። ይህ ደግሞ የባለቤትነት ስሜትን በሚፈለገው ደረጃ እንዲያዳብሩ የሚያደርግም ነው። በመሆኑም በፓርኩ ላይ እየደረሰ የሚገኘውን ጫና ለመቀነስ የአካባቢውን ማህበረሰብ ከብሔራዊ ፓርኩ በኢኮ-ቱሪዝምና ተያያዥ ጉዳዮች ተጠቃሚ በማድረግ የባለቤትነት አስተሳሰብን ማጎልበት እንደሚያስፈልግም ያስረዳሉ። በተለይ ለማህበረሰቡ አማራጭ የግጦሽና የሰፈራ ቦታ፣ የማገዶ፣ የኃይል አቅርቦትና ሌሎች አማራጮች በቀጣይ እንዲቀርቡለት የማድረግ ስራ ቢሰራ በፓርኩ ላይ የሚደርሰውን ጫና ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ እንደሚቻልም ይመክራሉ። ከሀገር አልፎ የዓለም ቅርስ የሆነውን የብርቅዬዎች አምባ የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ በዩኔስኮ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ለማቆየት የሚያግዙ ሥራዎችን ከወዲሁ አቅደው እየሰሩ መሆኑን የፓርኩ ኃላፊ አቶ ሻሚል ያስረዳሉ። ብሔራዊ ፓርኩን በሚያዋስኑ ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ስለብዝሃ ህይወት ጥቅምና ተጓዳኝ ጉዳዮች በቂ ግንዛቤ አግኝተው በጥበቃው የድርሻቸውን እንዲወጡ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማዳበሪያ ሥራዎች እየተከወኑ መሆናቸውንም ገልጸዋል። የዓለም ቅርስ የሆነው የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርክ ብዝሃ ህይወትን በዘላቂነት መንከባከብና መጠበቅ የሚያስችሉ ሀገር በቀልና ዘመናዊ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ፓርኩን በድርጅቱ ቋሚ መዝገብ ውስጥ ከማቆየት ባለፈ ከዘርፉ የሚገኘውን ዘላቂ ጥቅም ለማረጋገጥ ሁሉም የድርሻውን በቁርጠኝነትና በፅናት ሊወጣ ይገባል።  
ትንታኔዎች
ከገበታ ወደ ገበያ
Sep 24, 2023 636
(ሰለሞን ተሰራ) ኢትዮጵያ ከ10 ሺ ዓመታት በፊት ከኒዮሊቲክ አብዮት ዘመን ጀምሮ የበርካታ አዝእርትና እንስሳት ሀብት መፍለቂያ ሆና ዛሬ ላይ ደርሳለች። ከዚያ ዘመን ጀምሮ የአገራችን ገበሬ በስራ ያካበተውንና በተፈጥሮ የተሰጠውን ችሎታ በመጠቀም ዘመናዊና ቴክኖሎጂ በወለዳቸው መሳሪያዎች ሳይታገዝ፣ በየጊዜው የአፈሩ ለምነት እየቀነሰ ከሄደው መሬትና ባህላዊ የአስተራረስ ዘዴ ጋር እየታገለ ቁጥሩ እየናረ የሚሄደውን ህብረተሰብ ከመመገብ ወደ ኋላ ብሎ አያውቅም። ግብርናው ከቀደሙት ጊዜያት በተለየ ሁኔታ ትኩረት ባገኘበት በዚህ ዘመንም ከተደቀኑበት እጅ ጠምዛዥ ጉዳዮች ጋር ግብግብ ውስጥ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ፣ ድርቅ፣ የፖለቲካና የገበያ አለመረጋጋት፣ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ውስንነት፣ የተፈጥሮ አደጋ፣ የዘርፉ ኢንቨስትመንት አለመዳበር የዘርፉ ተግዳሮት ሆነው ቀጥለዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን በ78ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ባደረጉት ንግግር በተለይ የአየር ንብረት ለውጥን ተጽእኖ በሚገባ አመላክተዋል። የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ በተለይ በአፍሪካና በሌሎች በማደግ ላይ ያሉ አገራት ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰው ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ቀውስ ሁሉን አቀፍ መፍትሄ እንዲበጅ እየሰራች መሆኗን ተናግረዋል። በተለይ ኢትዮጵያዊያን ከጫፍ ጫፍ እየተሳተፉበት ያለው የአረንጓዴ አሻራ መርኃ ግብር የዚህ ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን አንስተዋል። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ላለፉት ተከታታይ አራት ዓመታት በሰራችው ስራ በአካባቢ ጥበቃና በግብርናው ዘርፍም ውጤት ማግኘቷ እሙን ነው። ነገር ግን ፈተናዎቹን በድል ለመሻገር የሚደረጉ ጥረቶችና በዘርፉ የተገኙ አበረታች ውጤቶች እንደተጠበቁ ሆነው አሁንም ዘርፉን በሰለጠነ የሰው ሃይል፣ በተደራጀ የግብርና መሳሪያና ማቀነባበሪያ በመደገፍ አገርና ህዝብ ከግብርናው ዘርፍ ማግኘት ያለባቸውን ጥቅም እንዲያገኙ ለማስቻል ብዙ መስራት ይጠይቃል። በተለይ የግብርና ሜካናይዜሽንን ከማስፋፋትና ዘመናዊ የግብርና ግብዓቶችን በበቂ ሁኔታ ከማቅረብ አኳያ መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረት የበለጠ መጠናከርና ማደግ ይኖርበታል። የግብርናና የገጠር ልማት የፋይናንስና ብድር አቅርቦትን ማጠናከር እንዲሁም የአካባቢና ስነ ምህዳር ጥበቃ ስራዎችን በዘላቂነት መተግበር ያሻል። በተለይ ኢትዮጵያ በልዩ ትኩረት እየሰራችበት ያለውን የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ ጉዳይ ከዚህ ቀደም የነበረውን የግብርና አሰራር በመቀየርና አማራጮችን በማማተር እውን ማድረግ ይጠይቃል። ኢትዮጵያ በዝናብ ወይም በመስኖ መልማት የሚችል ያልተነካ ሰፊ መሬት እንዳላት የሚታወቅ ሲሆን ይህን ያልታረሰ መሬት በአግባቡ በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ አንዱ አማራጭ ነው። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግብርናው ከ34 በመቶ በላይ የጠቅላላ የአገር ውስጥ ምርት ድርሻ ይዟል፡፡ በተጨማሪም ዘርፉ 79 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች መተዳደሪያ ሲሆን በተመሳሳይ 79 በመቶ የሚሆነውን የውጭ ንግድ ገቢ በመሸፈንና ለአገር ውስጥ ኢንቨስትመንትና ገበያ የጥሬ እቃ አቅራቢ በመሆንም ይታወቃል። መንግስት በግብርናው ዘርፍ የወሰዳቸው የሪፎርም ስራዎችና ግብርናን ከአረንጓዴ አሻራ ጋር በማስተሳሰር የሰራቸው ስራዎች ፍሬ ማፍራት ጀምረዋል። በተለይ የስንዴ ምርታማነትን በማሳደግ ከራስ ፍጆታ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የተሰራው ስራ ቀዳሚ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ብቻ የስንዴ ምርታማነቷን በ27 በመቶ ማሳደግ መቻሏ ስንዴ ከመሸመት ወደ መላክ የመሸጋገሯ ማረጋገጫ ሆኗል። በጠቅላይ ሚኒስተር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ በዚህ ረገድ የሚታይ ለውጥ እያሳየ ሲሆን በተሰራው ውጤታማ ስራ ባለፈው በጀት ዓመት ኢትዮጵያ ከውጭ ስንዴ አላስገባችም። በዚህም 1 ቢሊዮን ዶላር ማዳን መቻሏን የግብርና ሚኒስትሩ ዶክተር ግርማ አመንቴ በቅርቡ ማሳወቃቸው ይታወሳል። ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት 15 ነጥብ 4 ሚሊዮን ቶን ስንዴ ያመረተች ሲሆን በተያዘው ዓመት ደግሞ ምርቱን ወደ 19 ነጥብ 5 ሚሊዮን ቶን ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል። ይህንኑ ግብ ለማሳካት ደግሞ የስንዴ ማሳዋን በማሳደግ 5 ነጥብ 6 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል ለመሸፈን እየሰራች ነው። ከዚህ ውስጥ በመስኖ የሚለማ ስንዴን በ2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት ላይ በመዝራት በመስኖ የሚለማውን ስንዴ በ54 በመቶ ለማሳደግ እየሰራች ነው። ይህ ደግሞ በቀጣይ ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ምርቱን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንደሚያስችል ዶክተር ግርማ አመንቴ ተናግረዋል። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመላክተው የግብርናው ዘርፍ በአስር ዓመቱ የልማት ዕቅድ የመጀመሪያዎቹ 3 ዓመታት (2013-2015) በዋና ዋና ተግባራት ከዕቅድ በላይ ዕድገት አስመዝግቧል። በዚህም ዘርፉ በ2013 ከነበረበት 5 ነጥብ 1 በመቶ በ2014 ወደ 5 ነጥብ 8 በመቶ ያደገ ሲሆን በ2015 ደግሞ 6 ነጥብ 3 በመቶ እድገት አስመዝግቧል። ግብርናውን ለማሳደግ ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዘው የሰብል ምርት ሲሆን ለዘርፉ ማደግ 65 ነጥብ 5 በመቶ አስተዋጽኦ አበርክቷል። ደን ልማት 8 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም የእንሰሳት ሃብት ልማቱ 25 ነጥብ 9 በመቶ ድርሻ ይዘዋል። በ2015 ዓ.ም ጠቅላላ 627 ሚሊዮን ኩንታል ሰብል ለማምረት ታቅዶ ከተቀመጠው ግብ በላቀ ደረጃ 639 ሚሊየን ኩንታል ምርት ማግኘት ተችሏል። ከበጋ ስንዴ ልማት ጎን ለጎን በቅርብ ጊዜ የተጀመሩ የቡና፣ አቮካዶና አኩሪ አተር የመሳሳሉት ትላልቅ የግብርና ልማት ስራዎች በተመሳሳይ ውጤት ታይቶባቸዋል። የአዝርት፣ የአትክልት፣ ፍራፍሬና ስራስር ምርት ከፍተኛ የዕድገት ሽግግር የታየባቸው ናቸው። በአረንጓዴ አሻራ፣ በሌማት ትሩፋትና በከተማ ግብርና ተሞክሮ ሊወሰድበት የሚችል አፈጻጸም መመዝገቡ በሪፖርቱ ተመላክቷል። ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የስንዴ ምርት ከውጭ ገበያ ስትገዛ የኖረች ሲሆን በተለይም በተለያዩ ጊዜያት የሚፈጠሩ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች አቅርቦቱን ሲያስተጓጉሉት ቆይተዋል። አሁን ላይ ሙሉ በሙሉ የስንዴና የገብስ ምርትን በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የቻለች ሲሆን የሩዝ ፍላጎቷን ደግሞ 50 በመቶ መሸፈን ችላለች። በስንዴ ምርታማነት የተገኘውን ተሞክሮ ወደሌሎች ሰብሎች በማስፋት የገቢ ምርቶችን በቀጣይ ለመተካት በትኩረት እየተሰራበት ይገኛል። ይህንን ለማሳካት መንግሥት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ይታመናል። በተለይ ለግብርና ዘርፉ የተሻለ በጀት መመደቡ፣ እስካሁን ለመጣውና ለወደፊትም ይመጣሉ ተብለው ለሚታሰቡ ለውጦች ትልቅ ምክንያት ነው። ለምሳሌ የ2015 ዓ.ም. በአገሪቱ ለተለያዩ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ከተመደበው 786 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በጀት ውስጥ፣ ለግብርናው ዘርፍ 34 በመቶ የሚሆን በጀት ተመድቧል። ይህ ደግም ከለውጡ በፊት ከአሥር በመቶ ያልበለጠ በጀት ጋር ሲነፃፀር እጅግ ከፍተኛ ያደርገዋል። በተጨማሪም መንግሥት ለኩታ ገጠምና ለመስኖ እርሻ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱ፣ ሙሉ በሙሉ በዝናብ ላይ ጥገኛ የሆነውን የግብርና ስራ በመስኖ የታገዘ እንዲሆንና አርሶ/አርብቶ አደሩ በዓመት ከአንድ ጊዜ በላይ እንዲያመርት ማድረጉ ውጤቱን ጉልህ አድርጎታል። እንደ ስንዴ፣ በቆሎ፣ ሩዝ፣ ቡና፣ አቦካዶ ሁሉ በግብርና ሚኒስቴር ከተያዙና በልዩ ትኩረት ከሚከናወኑ ዕቅዶች አንዱ የማር ምርትን ማሳደግ ሲሆን፣ በአሥር ዓመቱ የልማት ዕቅድ ውስጥ እንደተመላከተውም የማር ምርትን በማዘመን ምርቱን ለማሳደግ በስፋት ይሰራል። በኢትዮጵያ ለማር ምርት ተስማሚ የሆነ አግሮ ኢኮሎጂና ብዛት ያላቸው ዕፅዋት መኖራቸው የሚመረተው ማር የተፈጥሮ ጥራት እንዲኖረው ያግዛል። ይህንኑ ዕምቅ ሀብት ትኩረት ሰጥቶ ማልማት ከተቻለ ከ500 ሺሕ ቶን በላይ ማርና ከ50 ሺሕ ቶን በላይ ሰም ማምረት እንደሚቻል ባለሙያዎች ያስረዳሉ። የኢትዮጵያ እንስሳት ሀብት ኢንስቲትዩት ባወጣው መረጃ በሀገሪቱ አለ ተብሎ ከሚገመተው ሰባት ሚሊዮን የንብ መንጋ ውስጥ 90 በመቶው በባህላዊ ቀፎ ውስጥ የሚገኝ ነው። የንብ መንጋዎቹ በባህላዊ ቀፎ ከመኖራቸው በተጨማሪ በጫካ መገኘታቸው ሃብቱ ለአገር ዕድገት በሚፈለገው ልክ እንዳይውል አድርጎታል። ያም ቢሆን ባለፈው ዓመት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው “የሌማት ትሩፋት” ለማር ምርት ትኩረት የሰጠ በመሆኑ ዘመናዊ የንብ ማነብ ዘዴ እንዲስፋፋ ተደርጓል። በዚህም የማር ምርታማነትን በዓመት ወደ 98 ሺህ ቶን ማሳደግ መቻሉ በቅርቡ መገለጹ ይታወሳል። ምርቱን በእጥፍ ለማሳደግ እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑም እንዲሁ። ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የማር ምርት የማምረት አቅም ካላቸው አሥር ሀገሮች አንዷ በመሆኗ ሃብቱን ለማልማት ሁሉም ሊረባረብ ይገባል። በአጠቃላይ መንግሥት ለአረንጓዴ ልማት/አሻራ፣ ለአፈርና አካባቢ ጥበቃ የሰጠው ትኩረት ሁሉን አቀፍ የግብርና ዕድገት እንዲመጣ መሠረት ሆኗል። በተጨማሪም መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሌማት ትሩፋትና ምግባችን ከደጃችን መርሐ ግብር ኅብረተሰቡ የከተማ ግብርናን እንዲያስፋፉ በገጠርም ሆነ በከተማ ያከናወነው ተግባር ውጤት አስመዝግቧል። በአጠቃላይ ባለፉት አምስት ዓመታት ዘርፉን ለማዘመን የተከናወኑ የልማትና የሪፎረም ሥራዎች ግብርናውን ከአዝጋሚ ጉዞ በማውጣት ወደ ፈጣንና አስተማማኝ ጉዞ ማሸጋገር ችለዋል። ኢትዮጵያ አሁንም አያሌ ያልተነኩ ዕምቅ ሀብቶች ያሏት መሆኗን እንደ እድል በመውሰድ ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል። ይህን ማድረግ ስትችል የግብርና ሽግግር ይረጋገጣል። ግብርናውን ለማሻገር ደግሞ በፋይናንስ፣ በግብአት፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሰለጠነ የሰው ሀይል ልማት ላይ በትኩረት መስራት ያሻል። ወጣቱ ግብርናን እንደ ንግድ (Agri-Bussiness) ማየትና በዚያው ልክ መስራት ይጠበቅበታል። በዚህ ልክ በርብርብ ሲሰራ ግብርናን በማሸጋገር ገበታን ከመሙላት ወይም ከፍጆታ አልፎ ገበያን ማማተር ይቻላል።    
 ኢትዮጵያ እና መስከረም
Sep 22, 2023 632
(በአየለ ያረጋል) መቼስ ሀገሬው መስከረምን ሲናፍቅ ‘ለብቻ’ ነው። በባህሉ፣ በትውፊቱ፣ በስለ-ምኑ፣ በኪነ-ቃሉ እና ስነ-ቃሉ ልዩ ሥፍራ ይሰጠዋል ለመስከረም። እንደ መስከረም ክብር፣ ሞገስ እና ፀጋ የተቸረው የትኛው ወር ይሆን? ማንም! ሀገሬው ለቆንጆ ልጁ ስም ሲያወጣ ‘መስከረም’ እንጂ በሌላ ወር ሰይሞ ያውቃል? አያውቅም። በኢትዮጵያ ምድር መስከረም ለሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን ለእንስሳት እና አዕዋፋት ራሱ ልዩ ጊዜ ነው። ‘ኢትዮጵያ ነይ በመስከረም…’ እንዲሉ መስከረም ለኢትዮጵያ ውበቷ፣ ቀለሟ፣ ትዕምርቷ፣ የባህር ሃሳቧ መባቻ ነው። ተናፋቂው መስከረም ዝም ብሎ ወር ብቻ አይመስልም። እውቁ ሠዓሊ እና ባለቅኔ ገብረክርስቶስ ደስታ መስከረምን “… በሽቱ መዓዛህ ለውጠው ዓመቱን፤ ይታደስ ያረጀው ፍጥረት ሌላ ይሁን…” ሲል የአዲስ ተስፋና መንፈስ መሻቱን አሳይቷል። ተወዳጇ ድምፃዊት እጅጋየሁ ሽባባው ደግሞ “… መስከረም ለምለሙ፣ መስከረም ለምለሙ፣ ብሩህ ዕንቁጣጣሽ ደስታ ለዓለሙ…” ትለዋለች መስከረምን ስታዜመው። እንደየ ንፍቀ ክበቡ ዓመታት በወራት ሲመነዘሩ የራሳቸው መልክና መገለጫ አላቸው። ኢትዮጵያም ከጎርጎሮሳዊያኑ የዘመን ቀመር በሰባት ዓመት ከስምንት ወራት ልዩነት ያለው የራሷ የዘመን ቀመር አላት። ኢትዮጵያ ብቸኛዋ ባለ 13 ወራት ሀገር ነች። ወራቱም መጸው(መኸር)፣ ሐጋይ(በጋ)፣ ፀደይ(በልግ) እና ክረምት በሚል በአራት ወቅቶች ይከፈላሉ። ወቅቶቹም የራሳቸው ጸባይ፣ ክዋኔ፣ ትውስታና ትዕምርት ይቸራቸዋል። እያንዳንዱ ወርም እንደዚሁ። ከዘመን መባቻው መስከረም እስከ ማዕዶተ-ዘመኗ ጳጉሜን ወራቱ በሰማይና በምድሩ ተፈጥሯዊ፣ ባህላዊና መንፈሳዊ ውቅራቸው ግላዊ ገጽታ ይነበብባቸዋል። የወራቱ ቅላሜ እና ሕብርነት ልዩ መልክዓ-ኢትዮጵያን ይፈጥራል። ‘የ13 ወር ፀጋ’ የሚለው መጠሪያም በ‘ምድረ ቀድምት’ እስኪተካ ድረስ ለብዙ አሥርት ዓመታት መለያ ሆኖ ዘልቋል። ይህን መለያ ስም ያወጡት እና የኢትዮጵያ ቱሪዝም አባት የሚሰኙት አቶ ኃብተሥላሴ ታፈሠ “ኢትዮጵያ የ13 ወራት ፀሐይ ባለቤት ናት። ስያሜው ከምንም የፖለቲካና ሃይማኖት ጋር ንክኪ የለውም” ብለው ነበር። የኢትዮጵያ ወራት ስያሜ ከመልክና ግብራቸው ይመነጫል። የወራት መባቻው መስከረም እንደዛው። ሊቃውንት መስከረምን ሲፈትቱት መስ - 'ዐለፈ፤ ከረመ' ይሉትና “ክረምቱን ማስከረሚያ፤ የጥቢ መባቻ" ወርኅ ሲሉ ያመሰጥሩታል። መስከረም ዘመን ያስረጃል፤ አዲስ ሕይወትና ተስፋ ደግሞ ይደግሳል። አንዳንዴም ይህ ወር ዘመን መለወጫ፣ ዕንቁጣጣሽ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ተብሎም ይጠራል፡፡ 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ከሚሰባረቅባቸው ወራት አንዱ መስከረም ነው። መስከረም አገርኛ አለባበስ፣ አገርኛ ዝማሬ፣ አገርኛ ጨዋታ፣ አገርኛ ትውፊትና ቀለም በመስከረም በዓላት በተግባር ይታያል። መስከረም ሁለንተናዊ ውበቱ ድንቅ ነው፤ ትዕምርቱም ጉልህ ነው። የመልክዓ-መስከረም ድምቀት ማሳያዎች ዘመን መለወጫ በኢትዮጵያ ዘመን ስሌት ቀለበት መስከረም 1 ቀን ዘመን ይለወጣልና። የዘመን መለወጫ በዓል ‘ርዕሰ ዓውደ- ዓመት’ ይሰኛል። የባህር ሐሳብ ሊቃውንት መስከረም ለምን የዘመን መለወጫ እንደሆነ ሲያትቱ “ብርሃናት /ፀሐይ፣ ጨረቃ፣ ከዋክብት/ የዓመት ዑደታቸውን በጳጉሜ ወር ጨርሰው በመስከረም ወር ስለሚጀምሩ ነው” ይላሉ። በመስከረም ሌሊቱ ከቀኑ እኩል ነው። ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር “ቀዳማይ፣ ርዕሰ ክራሞት፣ መቅድመ አውርኅ፣ ርዕሰ ዐውደ-ዓመት፣ የክረምት ጫፍ መካተቻ፣ የመፀው መባቻ” ይሉታል ወርኃ መስከረምን። እናም ዘመነ ማዕዶቷን፤ ወርኅ ተውሳኳን ‘ጳጉሜን’ ተሻግሮ መስከረምን መሳም ይጓ'ጓ'ል። የመስከረም ጥባት በአያሌው ይሻታል። 'መስከረም ሲጠባ ወደ አገሬ ልግባ …’ እንዲሉ የተሰደዱት በአዲስ ዓመት መባቻ የአገራቸውን አፈር ለመሳም ያማትራሉ። ’አበባዬ ሆይ፤ አበባዬ ሆይ’ የሚሉ ሕፃናት ተስፋና ምኞታቸውን በወረቀት ያቀልማሉ፤ የአበባ ስዕላት ይዘው በየደጃፉ ይሯሯጣሉ፤ የ’ዕደጉ’ ምርቃት ያገኛሉ፤ በደስታ ይንቦጫረቃሉ። በዚህ ድባብ ነው እንግዲህ መስከረምን የግዑዛንም የሕይወታውያንም የነፃነት፣ የተስፋና የፍቅር ወርኅ ተደርጎ የሚናፈቀው። የብዙ ሺህ ዘመናት ባለታሪኳ ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ አዱኛ ሳይርቃት በእርስ በርስ ጦርነት፣ በጠላት ፍላፃዎች እና በድንቁርና ብዛት... ሰንኮፎቿ ሳይነቀሉ በመልከ-ብዙ ምስቅልቅሎሽ ውስጥ ዛሬ ደርሳለች። ጊዜው የኢትዮጵያን መስከረም ያስናፍቃል። ዕንቁጣጣሽ መስከረም በአደይ አበባ የሚያሸበርቅ ወር ነው። የነገረ-ዕንቁጣጣሽ የትመጣ መልከ-ብዙ አተያዮች ይጠቀሳሉ። ለምሳሌ “ዕንቁ – ዕፅ አመጣሽ” ብሎ የአበባ መፈንዳት ለማመላከት እንደሆነ የሚጠቅሱ አሉ። ንግሥት ሳባ /አዜብ/ ወደ ንጉሥ ሰሎሞን የእጅ መንሻ ይዛ ስትሄድ ንጉሡም “ዕንቁ ለጣትሽ ጌጥ ይሁንሽ” በሚል ቀንና ከሌሊት የሚያበራ ቀለበት ስለሰጣት ነው የሚል አፈታሪክም ይነገራል። የስያሜው መነሻ ያም ሆነ ይህ መስከረም ለመልክዓ-ምድሩ፣ ለሰውና ለእንስሳት ሁሉ ‘ፍስሐ ወተድላ’ የሆነ ወር ነው። በመስከረም ምድር በዕንቁጣጣሽ ትፈካለች፤ በአበቦች ታጌጣለች፤ ውኆች ይጠራሉ። ሰማዩም የክብረ-ሰማይ ብርሃኑን ያጎላል። ጥቁር ደመና ጋቢ ይገፈፋል፤ ክዋክብት እንደፈንዲሻ በዲበ-ሰማይ ይደምቃሉ። ዕጽዋትና አዝዕርት እንቡጦች ይፈነዳሉ። የመብረቅ ነጎድጓድ ተወግዶ የሰላምና የሲሳይ ዝናብ ይዘንባል። እንስሳት የጠራ ውሃ እየጠጡ፣ ለምለም ሳር እየነቸረፉ ይቦርቃሉ። እርሻ የከረሙ በሬዎች፣ ጭነት የከረሙ አህዮች መስከረም አንጻራዊ የእፎይታ ወራቸው ነው። ነጎድጓድ በአዕዋፋት ዝማሬ ይተካል። ንቦች አበባ ይቀስማሉ፤ ቀፏቸውን ያደራሉ። ቢራቢሮ ሳትቀር ‘በመስከረም ብራ ከኔ በላይ ላሳር..’ ብላ ትከንፋለች። በ’ዕንቁጣጣሽ’ ምድር ብቻ አይደለችም የምትዋበው። መስከረም ለሰው ልጆችም በተለይም ለወጣቶች የፍቅር፣ የእሸት እና የአበባ ወር ነው። የሰላም፣ የንጹህ አየር፣ የጤና ድባብ ያረብባል። የጋመ በቆሎ እሸት ጥብስ፤ ቅቤ ልውስ፤ ቅቤ በረካ ይናፈቃል። የተጠፋፋ ዘመድ አዝማድ ይገናኛል። ‘ሰኔ መጣና ነጣጠለን’ ብለው ወርኃ ሰኔን የረገሙ ተማሪዎች ተናፋቂያቸውን ያገኛሉና ‘መስከረም ለምለም’ ብለው ያሞካሹታል። የገበሬው የሰብል ቡቃያ ያብባል፤ እሸት ያሽታል። ጉዝጓዝ ሣር፣ ትኩስ ቡና ይሽታል። ደመራ ወመስቀል ሊቃውንት የደመራን የትመጣን ሲፈትቱ ‘ደመረ፣ ተሰባሰበ’ ይሉታል። ጎረቤት፣ የሩቅ የቅርብ ዘመድ አዝማድ ተደምሮ የሚከውነው ነውና። ነገረ መስቀሉ እምነቱ፣ ባህሉ፣ ትውፊቱ ብዙ ነው። መስቀል በሃይማኖተ-አበው ሀተታ ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለምን ለማዳን፣ ለፍጡር የሰው ልጆች ያለውን ጥልቅ ፍቅር የገለጸበት ዓርማ ነው። በዚህም መስቀልን አማኝ ምዕመናን እና ካህናት የደኅንነትና የእምነት ምልክታቸው፤ የርኩስ መንፈስ ማባረሪያ መሳሪያቸው አድርገው ይመለከቱታል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መስከረም 10 ቀን ‘ተቀጸል ጽጌ’ በሚል የክርስቶት መስቀል ግማድ (ቀኝ እጁ ያረፈበት ክፋይ) ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ኢትዮጵያ የገባበትን ቀን ታከብረዋለች፤ መስከረም 17 ቀን ደግሞ መስቀሉ የተገኘበትን። መስከረም 16 እና 17 ቀን የሚከበረው የደመራ መስቀል በዓል ከሃይማኖታዊ አስተምህሮው ባለፈ ባህላዊ ትውፊትነቱ የጎላ በመሆኑ በአብዛኛው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ይናፈቃል። ደመራና መስቀል የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታ፣ አብሮነት፣ የምስጋና፣ የተስፋ… እሴቶች የሚገለጹበት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ክብረ-በዓል ነው። ደመራ እና መስቀል በዓላት ሃይማኖታዊ የአደባባይ በዓል ቢሆንም እንደየ አካባቢው ባህል፣ መንፈሳዊነት፣ ትውፊት፣ ዕውቀት አገርኛ ህብር ጥበባት የሚጎሉበት፣ አገር የውበት አክሊል የምትደፋበት ዕለት ነው። መስቀል የዓለማችን የማይዳሰስ የኢትዮጵያ ወካይ ቅርስ መዝገብ ሥር ሰፍሯል። በመስቀል አገርኛ ቀለም ይጎላል። 'አገር፣ ቀለም፣ ዘመን' እንደሸማው በድርና ማግነት ይሰባረቃሉ። የባህር ማዶ ጎብኚዎች በአግራሞትና መደነቅ ሲናገሩ ይደመጣሉ። የዕንቁጣጣሽ ተከታይ የመስከረም መልክ ነው መስቀል። የደመራ አደማመር እና ማብራት ሥነ-ሥርዓት በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች ተመሳሳይ እንዳልሆነ ደራሲ ካሕሳይ ገብረእግዚአብሔር ይተርካሉ። በትግራይ፣ በጎንደር፣ በወሎ፣ በዋግኸምራ፣ በአዊና በከፊል ጎጃም ደመራ ማታ ላይ ተደምሮ ንጋት ላይ ይለኮሳል። በከፊል ጎጃም፣ በሸዋ፣ በአዲስ አበባ፣ በጉራጌ፣ በጋሞ፣ በወላይታና ሌሎች የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ደግሞ እንደየ አካባቢው ተለምዶ መስከረም 16 ከእኩለ ቀን ጀምሮ እስከ አመሻሽ ድረስ ደመራው ይለኮሳል። መስቀል በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ርዕሰ ዓውደ-ዓመት ይመስላል። በደቡብ ኢትዮጵያ መስቀል ከሃይማኖታዊ ይዘቱ ባህላዊ ጎኑ ይጎላል። ጉራጌዎች፣ ጋሞዎችና ሌሎችም መስቀልን ከሁሉም በዓላት የበለጠ ይናፍቁታል። የተራራቁ ቤተሰቦች የሚገናኙበት የፍቅር፣ የደስታና የእርቅ በዓል ነው መስቀል። በጋሞ ብሔረሰብ ባህል በዋዜማው ሰው ቢሞት እንኳን በሌሊት ተወስዶ ይቀበራል እንጂ ለቅሶ እንደማይለቀስ ይነገራል፤ ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳቱም ልዩ መኖ እንደሚቀርብላቸው ይነገራል። ለጥምቀት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ እንደሚባለው በጋሞዎች ደግሞ ‘ለመስቀል ያልሆነ ዱንጉዛ ይበጣጠስ’ በሚመስል መልኩ የባህል ልብስ አለባበስ እንደሚዘወተር መምህር ካሕሳይ (በሕብረ-ብዕር ድርሰታቸው) ጽፈዋል። መስቀል በጉራጌዎች ዘንድ እንደ አውራው በዓል ይቆጠራል። ለመስቀል ዓመቱን ሙሉ ዝግጅት ይደረጋል። አባወራው ሰንጋ ለመግዛት፣ እማወራ ማጣፈጫውን ለማዘጋጀት፣ ወጣቶች ደመራና ደቦት ለማዘጋጀት፣ ልጆች ምርቃት ለመቀበል የየራሳቸውን ይዘጋጃሉ። ቤተሰብ ወዳጅ ዘመድ የሚጠያየቅበት፣ ለትዳር የደረሱ ሚስት የሚያጩበትና የሚመርጡበት ጥላቻና ቂም በፍቅርና በይቅርታ የሚታደስበት ነው። በጉራጌዎች ዘንድ መስቀል ትልቅ ቦታ ይቸረዋል። መስቀል እንደየአካባቢውና ባህሉ የሚናፈቅበት ዕልፍ ገጽታዎች አሉት። ለምሳሌ እኔ በተወለድኩበት ገጠራማ አካባቢ ያለውን በወፍ በረር እንቃኘው! በደመራ ዋዜማ ቀናት ልጆች ተራራ ለተራራ፣ ወንዝ ለወንዝ፣ ቋጥኝ ለቋጥኝ በልጅነት ወኔና ስስት በመዞር ለደመራ የሚሆን እንጨት፣ አደይ አበባ፣ ደቦት(ችቦ) ያጠራቅማሉ። ልክ መስከረም 16 አመሻሽ ከብቶች ወደ ግርግም ከገቡ የመንደሩ ወጣቶች ወደ ‘አፋፍ’ ይወጣሉ። ደመራ ወደሚደመርባት ሥፍራ። ሁሉም የአንድ ዕድር አባላት ቤተሰብ ተወካዮች ባሉበት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት የደመራው ሥራ ይጠናቀቃል። ደመራው ሲጠናቀቅ ወደየ ቤታችን እንበታተናለን። (አዲስ አበባን ጨምሮ በከተሞች እንደሚደረገው በመስከረም 16 አመሻሽ ደመራው አይለኮስም። ይልቁኑ መስከረም 16 ለ17 አጥቢያ ጀምሮ ይለኮሳል እንጂ።) ለመስከረም 17 አጥቢያ ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ ሁሉም ሰው ከየቤቱ ደቦቱ (ችቦውን) እየለኮሰ ‘እዮሃ ደመራ’ እያለ ወደ ደመራው ሥፍራ ይተማል። እንደየ ግለሰቡ ቤት እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ መጓዝ ሊጠይቅ ይችላል። የመስከረም እኩሌታ አረንጓዴያማ ውብ ማሳ ከየቤቱ ከሚወጡ የችቦ እሳት ነበልባል ብርሃን ይታጀባል። ከሌሎች አጎራባች የመንደር ደመራዎች ቀድሞ ለመለኮስ ጉጉቱ የትየለሌ ነው። ከቤት እስከ ደመራው ሥፍራ እስኪደርሱ ድረስ ሰዎችን፣ በረት ያሉ ከብቶቹንና የጓሮ አዝመራውን ጨምሮ ሕይወታዊያንን በሙሉ “እንጎረጎባህ፤ እንጎረጎባችሁ” ይባላል። የተጠያቂው ሰው ምላሽ ደግሞ “ዓመት ዓመቱን ያድርስህ” የሚል ይሆናል። ከደመራ ግጥም ተዘውታሪ ስንኞች መካከልም፡- “እዮሃ አበባዬ፣ መስከረም ጠባዬ፣ እዮሃ አረሬ አረሬ፣ መስቀል ጠባ ዛሬ፣ በሸዋ በትግሬ…” የሚለው ይጠቀሳል። ከደመራው ሥፍራ ስንደርስ የ’እንጎረጎባህ!’ ድምፆች ይበረታሉ። የ’ዓመቱን ያድርስህ’ መልስ ካልሆነም እኩይ አፀፋ ይኖራል። ሁሉም ከተሰባሰበ በኋላ ደመራን የሚያሞካሹና የአዲሱን ዓመት መልካምነት የሚመኙ ‘እዮሃ አበባዬ” ግጥሞች እየተደረደሩ ደመራው ሦስት ጊዜ እንቧለሌ ይዞራል። በዕድሜ ታላቅ እና የተከበረ ሰው በቅድሚያ ደመራውን ይለኩሳል። ቀጥሎ ሁሉም ወደ ደቦቱን(ችቦውን) ወደ ደመራው ውስጥ ያስገባል። ደመራውም ይቀጣጠላል። የእሳቱ ነበልባል በመስከረም የንጋት ውርጭና ብርድ ላይ ያይላል። ሁሉም በደመራው ዙሪያ ተኮልኩሎ የክረምት ወራት ትዝታ ይነሳል፤ ሹፈት፣ ቀልድና ቁምነገር በየፈርጁ ይሰለቃል። ሌሊቱ የአህያ ሆድ እስኪመስል ይቀጥላል። የተጣላም ይታረቃል። የደመራው አምድ (ምሰሶ) አወዳደቅ ለማየት ሁሉም በጉጉት ይጠብቃል። ምሰሶው ወደ ምሥራቅ ከወደቀ የጥጋብ ዓመት፤ ወደ ምዕራብ ከሆነ ግን የችጋር ዓመት ተደርጎ ይታመናል። ከደመራው ሁነቶች አንዱ ባህሉ የበቆሎ እሸት ናፍቆት ነው። የደመራው ምሰሶ ከወደቀ በኋላ በአቅራቢያ ካለ የበቆሎ ማሳ በቆሎ እሸት ይመጣል። በመስቀል ደመራ ፍም ተጠብሶ ይበላል። ባለበቆሎው ሰው ዓመታዊ ደንብ ስለሆነ የበቆሎ ማሳዬ ተጎዳብኝ ብሎ አይቆጣም። ከደመራው ዓመድ ግንባራችን ላይ መስቀለኛ ምልክት ማድረግ እና ‘የዛሬ ዓመት አድርሰኝ’ ስለት ይቀጥላል። ሰማዩ የአህያ ሆድ ሲመስል ልጆች በደቦ ወደ መንደር ለመንደር በመዞር ‘እንጎረጎባችሁ’ እንላለን። የቤቱ ባለቤትም በሳህን፣ ጣሳ ወይም ሌላ ዕቃ ጤፍ ዱቄት ይሰጣል። የሰበሰብነውን ዱቄት ይዘን ወደ ደመራው ሥፍራ እንመለሳለን። በደመራው ጉባዔ ተወስኖ ከዕድሩ ለተመረጠች ቀጭን እመቤት (ባለሙያ ሴት) ዱቄት ይሰጣትና በ17 ምሽት ለሚኖረው የእራት ሰዓት ዝግጅት በአነባበሮ መልክ ዱቄት አብኩታና ጋግራ ታቀርባለች። መስቀል የወል ክብረ በዓል ነው። የመስቀል ዕለት (መስከረም 17) በግ ይታረዳል። እህል ውሃ ቀርቦ የመንደሩ ሰው በጋራ ሲጫወት ይውላል፤ በሕብረት ይበላል። ለመስቀል የተጣላ ጎረቤት ይታረቃል። ልጆች በሕብረት ይቦርቃሉ። የመስቀል ትዝታ በእኛ መንደር ይናፈቃል። ሁሉም እንደየ ቀየው ትውፊት እና ልማድ ይህን ሁነት ይናፍቃል….!! ጊፋታ ጊፋታ/ ግፋታ ማለት ትርጉሙ በኩር ወይም ታላቅ ማለት ሲሆን በለኬላ ትርጓሜው መሻገር ማለት ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ አዲስ ዓመት አንድ ብሎ የሚጀመርበት የአዲስ ዓመት መግቢያና የብርሃን ጊዜ ማብሰሪያ ነው፡፡ ከአሮጌ ወደ አዲስ፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን መሻገር የሚለውንም ይገልጻል፡፡ ጊፋታ የዓመቱ የመጀመሪያ ወር ስያሜ ነው፡፡ በወላይታ ብሔረሰብ ዘንድ መስከረም ወር በገባ ከቀን 14 እስከ 20 መካከል የሚውለው እሑድ አዲሱን ዓመት የሚቀበሉበር ዕለት ይሆናል፡፡ በዓሉ የሚውልበት እሑድ ስሙም ‹‹ሹሃ ወጋ›› የእርድ እሑድ ይባላል፡፡ እሑድ የአዲስ ቀን ብሥራትም ነው፡፡ ቀጣዮቹ የሳምንቱ ቀናት የየራሳቸው ስያሜና አከባበር አላቸው። ለአብነት ‹‹ጋዜ ኦሩዋ›› ማንሳት ይቻላል። የአዲስ ዓመት አራተኛ ቀን ነው። የሰፈሩ ወጣቶች በየመንደሩ በታዋቂ የአገር ሽማግሌዎች ደጅ ተሰባስበው የግፋታ በዓል ባህላዊ ጨዋታ የሆነውን ጋዜ በጋራ ሆነው ‹‹ሀያያ ሌኬ›› እያሉ ትከሻ ለትከሻ ተቃቅፈው የሚጫወቱበትና ልጃገረዶችን ሎሚ በመለመን የሚፈልጓትን የሚመርጡበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ቀን ነው፡፡ በዕለቱ ልጃገረዶች አንድ ላይ ሆነው በየቡድን ቁጭ ብለው ወንዴና ሴቴን ከበሮ እየመቱ ‹‹ወላወላሎሜ›› እያሉ የሚመርጡትን ወንድ ሎሚ በመስጠት የሚመርጡበት፣ እንዲሁም ሴቶች ለሚዜነትና ለጓደኝነት ከመረጧት ሴት ጋር በጥርስ አንድ ሎሚን ለሁለት የሚከፋፈሉበትና ስማቸው ሲጠራሩ ‹‹ሎሜ ሎሜ›› የሚባባሉበት ጨዋታ የሚጫወቱበት ዕለት ጋዜ ኦሩዋ ነው፡፡ ግፋታ ሲሸኝ ጥቅምት በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ማክሰኞ ሆኖ የሽኝት በሬ ታርዶ ከተበላ በኋላ ቶክ ጤላ የተባለውን ምሽት በችቦ ያባርራሉ፡፡ ዜማ በተቀላቀለበት ጩኸት ችቦ ይዘው ‹‹ኦሎ ጎሮ ባ! ሳሮ ባዳ ሳሮ ያ!›› ይላሉ፡፡ ትርጓሜውም ጊፋታ በሰላም ሄደሽ በሰላም ነይ! ማለት ነው፡፡ ዮ …ማስቃላ በጋሞዎች ዘንድ በየዓመቱ በጉጉት የሚጠበቀው «ዮ ማስቃላ» የዘመን መለወጫ በዓል በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ቅበላው ተከብሮ በዚሁ ወር መጨረሻ «ዮ ማስቃላ» ሽኝት በዓል በድጋሚ በድምቀት ይከበራል። መስከረም ወር የመጀመሪያው ቀን በጋሞ ዞን ”ሂንግጫ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ይህም አዲሱን ዓመት ለመቀበል ዝግጅት የሚደረግበት ቀን ነው። ጋሞዎች ዓመቱን ሙሉ ገንዘብ በመቆጠብ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ዝግጅት ይደረጋል። ወንዶች ለበዓሉ የሚሆን ሠንጋ መግዣ፣ ለልጆች ልብስ እና ጌጣጌጥ ማሟያ፤ እናቶች ደግሞ ለቅቤ፣ ለቅመማቅመም፣ ለባህላዊ ምግቦች እና መጠጦች እህል መግዣ የሚሆን ገንዘብ ያጠራቅማሉ። በጋሞ ዞን የማስቃላ በዓል ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንሳስት እና ለአዕዋፋትም ጭምር ነው ተብሎ ይታመናል፤ በዕለቱ ምግብ ከሰው አልፎ ለእንሳስት እና ለአዕዋፍም ይትረፈረፋል። ለከብቶችም የግጦሸ መሬት በየአካባቢው ይከለላል። በተለያዩ አጋጣሚዎች የተጣሉ ታርቀው፣ የተራራቁ ዘመድ አዝማድ እና ወዳጆች ተሰባስበው በዓሉን በጋራ እንዲያከብሩ ማድረግ የጋሞ ማስቃላ በዓል መገለጫ ነው። በጋሞ ብሔረሰብ የሚከበረው የማስቃላ በዓል በሶፌ ሥርዓት የታጀበ ነው። የቀደመው ዓመት ማስቃላ በዓል ከተከበረ በኃላ የተጋቡ ሙሽሮች ከመስከረም አጋማሽ ጀምሮ ማምሻውን በአደባባይ ከመላው ሕብረተሰብ ጋር የሚቀላቀሉበት እና ሁለቱም ተጋቢ ቤተሰቦች አንድ ላይ ሆነው ደስታቸውን የሚገልፁበት ሥርዓት ነው። የመጨረሻው የማስቃላ ሽኝት በዓል ነው፤ ይህ ሥርዓት እንደየአባወራው አቅም በፈቀደ መጠን የሚፈፀም ነው። በዚህ ዕለት ሁሉም ያለ ፆታ ልዩነት በአደባባይ ላይ ወጥተው ያኑረን እስከ ወዲያኛው እንኖራለን እያሉ ይጨፍራሉ። ከዚህ በኋላ ለመጪው ዓመት በሰላም በጤና ያድርሰን ተባብለው ፈጣሪን በመማፀን ዝግጅቱ ይቋጫል። ያሆዴ መስቀላ የክረምቱ ወራት አልፈው መስኩ በልምላሜና በአደይ አበባ ሲያሸበርቅ በሃድያዎች ዘንድ ትልቅ ዝግጅት አለ - ያሆዴ መስቀላ። “ያሆዴ“ ማለት እንደ ብሔሩ የባህል ሽማግሌዎች ትርጓሜ እንኳን ደስ አላችሁ፤ የሚል የብስራት ትርጉም ያለው ሲሆን ”መስቀላ” ማለት ደግሞ ብርሃን ፈነጠቀ ማለት ነው፡፡ በመሆኑም ያሆዴ መስቃላ ብርሃን ፈነጠቀ እንኳን ደስ አላችሁ የሚል ትርጉም አለው። በዓሉ በወርኃ መስከረም 16 የሚከበር ሲሆን ወሩ ብርሃን፣ ብሩህ ተስፋ፣ ሰላም፣ ፍቅር፣ ረድኤት፣ በረከት የሚሞላበት ተምሳሌት ወር ተደርጎ ይቆጠራል። የሃድያ አባቶች ”ከባለቤቱ የከረመች ነፍስ በያሆዴ መስቀላ ትነግሳለች“ የሚል ብሂል አላቸው። የሃድያ አባቶች እንደ ዘመን መለወጫ የመጀመሪያ ቀን አድርገው በመውሰድ ማንኛውንም ዓይነት ክስተት ከዚያ ጋር አያይዘው እንደሚቆጥሩ ይነገራል። በዓሉ ከመድረሱ በፊት ሁሉም የቤተሰብ አባላት በዓሉን ለማድመቅ የየራሳቸው ድርሻ አላቸው። በብሔሩ አባቶች አብሮነታቸውን ከሚያጠናክሩባቸው ማኅበራዊ እሴቶች መካከል አንዱ ቱታ/ሼማታ/ሲሆን ይህ ማለት በዓሉን ምክንያት በማድረግ የተደራጀ ቋሚ የሆነ ከአራት እስከ ስምንት አባላትን የያዘና በሥጋ ቅርጫ የተደራጀ ማኅበር ነው። የዚህ ማኅበር አባላት ግንኙነት ያላቸው የሚተሳሰቡ የኢኮኖሚ አቅማቸውም ተቀራራቢነት ያለው ሲሆን በመቀናጀት የበዓሉ እለት ከመድረሱ በፊት በጋራ ገንዘብ ማስቀመጥ ይጀምራሉ፤ በበዓሉ ወቅትም ለእርድ የሚሆን በሬ መግዣ ገንዘብ እንዳይቸገሩና በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ ሕብረታቸው ትልቅ ሚና ይጫወታል። ከመጋቢት ወር ጀምሮ ለከብቶች የግጦሽ ሳር የሚሆን ቦታ ከልሎ በማስቀመጥ የበዓሉ ቀን ከብቶች ተለቀውበት እንዲጠግቡ የሚደረግ ሲሆን በአዲስ ዓመት መግቢያ እንኳን የሰው ልጅ እንሰሳትም ቢሆኑ መጥገብ እንዳለባቸው እንዲሁም የጥጋብ ዘመን እንዲሆን በብሔሩ በዓሉ ለሰው ብቻ ሳይሆን እንሰሳትም ሆዳቸው ሳይጎድል አዲሱን ዓመት መቀበል እንዳለባቸው በመታመኑ ልዩ ትኩረት ይሰጣቸዋል። ኢሬቻ ኢሬቻ ከመስከረም ደማቅ መልኮች አንዱ ነው። ኢሬቻ የዘመነ መፀው መጀመሪያ ሁነት ነው። የኢሬቻ ክብረ በዓል ኢሬቻ ቢራ (መልካ) በሐይቆች ወይም በወንዞች ዳር የሚከበር ነው። ከክረምት ወደ መፀው መሸጋገርን ምክንያት በማድረግ የሚከወን የምስጋና በዓል ነው። በኦሮሞ ዘንድ ለዘመናት የሚከበር እና ከገዳ ሥርዓት ጋር የተቆራኘ እንደሆነ ይነገራል። ኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ ለፈጣሪ (ዋቃ) የክረምት ወቅትን በማሳለፉ፣ ወይንም ወደ አዲስ ዓመት በማሸጋገሩ የሚቀርብ ምስጋና ነው። ‹‹ዋቃ›› ፍጥረተ ዓለምን ያስገኘውና ሒደቱንም የሚያስተናብረው አንድ አምላክ ማለት ነው፡፡ ‹‹ኢሬቻ ሰላም ነው፣ ሰላም ጥልቅ ትርጉም አለው፣ ሰው ከሰው ጋር፣ ሰው ከራሱ ጋር፣ ሰው ከተፈጥሮ ጋርና ሰው ከፈጣሪው ጋር ሰላም ሊኖረው ይገባል፤›› የሚለው ጽንሰ ሐሳብ የክብረ በዓሉ ጭብጥ ነው፡፡ ለሕዝቡና ለአገሩ ምርቃትና መልካም ምኞት የሚገለጽበትም ነው-ኢሬቻ። ታዲያ ማንኛውም ሰው ወደ በዓሉ ሥፍራ ሲሄድ አለባበሱን ማሳመር ይጠበቅበታልኢሬቻ ከመስቀል በኋላ ይከበራል። በቢሾፍቱ ከተማ የሚከበረው የ'ሆራ አርሰዲ' እንዲሁም ‘ሆራ ፊንፊኔ’ ከፍተኛ ሕዝብ ቁጥር በታደመበት በድምቀት ይከበራል። በሌሎችም የኦሮሚያ አካባቢዎች በተለያዩ ክዋኔዎች እንዲሁ ይከበራል። ኢሬቻ እንደ ዕንቁጣጣሽ በመስከረም ጥባት ውሃ ጎድሎ፣ የተራራቀ ዘመድ አዝማድ የሚገናኝበት ነው። በተለያዩ ጸሐፍት እንደተጠቀሰው፣ ኢሬቻ አንድም ‘ዋቃ’ ከብርድና መብረቅ፣ ከጎርፍ፣ ከአውሎ ነፋስ እና መሰል የክረምት ተፈጥሯዊ ክስተቶች ጠብቆ ወደ ብራ እና ፀሐያማው የመፀው ወቅት በሰላም ስላሸጋገረ፣ አንድም በዋቃ ፈቃድ ዝናብ ዘንቦ፣ መሬቱ ረስርሶ፣ አዝመራው ለምልሞ፣ መልካም ፍሬ በመታየቱ፣ እሸት በመስጠቱ ስለማያልቀው ቸርነቱ ለማመስገን ነው። ከክረምቱ ጨለማ ወደ ብርሃን የማለፍ ብሥራት ነው ኢሬቻ። በሌላ በኩል ደግሞ መጪው አዲሱ ዓመት የተባረከና የተቀደሰ፣ የደስታና የብልፅግና፣ የተድላና ፍስሃ ይሆን ዘንድ መልካም ምኞትን የመግለጫ በዓልም ነው። በኢሬቻ ክዋኔ አባ ገዳዎችና የሕዝብ መሪዎች ይመርቃሉ። በኦሮሞ ሕዝብ ባህላዊ አለባበሱን በማጌጥ ወደ ክብረ-በዓሉ የሚያመሩ ኢሬቻ አክባሪዎች እርጥብ ሳር እና አደይ አበባን ይይዛሉ። ከኢሬቻ ክብረ-በዓል የምርቃት ስንኞች መዘን እንሰናበት። “… ለምድራችን ሰላም ስጥ! ለወንዞቻችን ሰላም ስጥ! ከጎረቤቶቻችን ጋር ሰላም ስጠን! ለሰውም ለእንስሳቱም ሰላም ስጥ! ከእርግማን ሁሉ አርቀን! ከረሃብ ሰውረን! ከበሽታ ሰውረን! ከጦርነት ሰውረን! ሀዬ! ሀዬ! ሀዬ! (አሜን! አሜን! አሜን!)
ያሆዴ- የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት
Sep 22, 2023 766
(በማሙሽ ጋረደው ከሆሳዕና) ያሆዴ የሃድያ ብሔር የአዲስ ዘመን መሸጋገሪያ በዓል ነው። በዓሉ ሲከበር ቂምና ቁርሾ ተወግዶ ያለፈው ዓመት መልካምና በጎ ያልሆነ ሁኔታ ታይቶ ለቀጣይ ስኬት አዲስ ተስፋና ልምላሜ ሰንቆ የሚሻገሩበት በዓልም እንደሆነ ይነገራል። ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የሃድያ ዞን አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ታምሬ ኤርሚያስ እንዳሉት ሃድያ የራሱ የሆነ የጊዜ አቆጣጠር ባህል፤ ልማድ፤ ወግና ስርዓት አለው። ለዚህም እንደ ማሳያ በብሔሩ ዘንድ በከፍተኛ ድምቀት የሚከበረውን የያሆዴ ክብረ በዓል ለአብነት ጠቅሰዋል። በዓሉ የአዲስ ተስፋና ልምላሜ ምልክት ተደርጎ እንደሚወሰድ የተገለጸ ሲሆን በተለይም የሚመጣው ዘመን የስኬት እንዲሆን እያንዳንዱ ካለፈው ዓመት ስኬትና ውድቀት ልምድ እየቀመረ ሃገር ሰላም እንዲሆን ተመራርቀው በደስታ እየተበላ፤ እየተጠጣ የሚከበር በዓል መሆኑንም ተናግረዋል። በብሔሩ ዘንድ ልዩ ቦታ የሚሰጠው የያሆዴ ክብረ በዓል አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበትም ነው። በዓሉ ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ክዋኔዎች የሚከበር ሲሆን በዓሉ መቅረቡን ታዳጊ ልጆች በተለያዩ ገላጭ በሆኑ ድርጊቶች እንደሚያበስሩ አቶ ታምሬ ተናግረዋል። በተለይም ታዳጊዎቹ ያሆዴ መድረሱን ለማብሰር ከነሐሴ አጋማሽ ጀምሮ እስከ ጳጉሜ መጨረሻ ድረስ በብሔሩ አጠራር ገምባቡያ ወይም (ዋሽንት) በመጠቀም የተለያዩ ጥዑመ ዜማዎችን በማሰማት በዓሉ መቅረቡን ያበስራሉ። በሃድያ ብሔር ዘንድ የአዲስ ዘመን ብስራት “ያሆዴ" የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰድ በዓል መሆኑንም አመልክተዋል። ይህም የሆነበት ምክንያት በመስከረም ሰውና እንስሳ ከዶፍ ዝናብ፣ ከውርጭ፣ ከጤዛና ከጭቃ፣ ከጉም፤ ከጭጋግና ጽልመት ነጻ ይሆናሉ። ምድሩ በሃምራዊ ቀለም ደምቆ ያሸበርቃል። ፀሐይ ሙሉ ገላዋን ገልጣ ጸዳሏን ትሰጣለች። በመሆኑም በስራ የደከመ ሰውነት ዘና፣ የታመመ ቀና ይልበታል፣ ልጅ አዋቂ የደስታ ነጋሪቱን ይጎስማል፣ የፍቅር ጽዋ ይጠጣል፣ የአእምሮ እርካታ ይነግሳል፣ በሁሉም ነገር ደስታ ይሰፍናል ወርሃ መስከረም በጥጋብና ደስታ ይጀመራል ።   በዓሉ ከመግባቱ በፊት የራሱ የሆነ የሥራ ክፍፍል ኖሮት ቅድመ ዝግጅት የሚደረግበት መሆኑን ያነሱት ሃላፊው የቤተሰብ አባላት ሁሉም በየድርሻቸው ሃላፊነታቸውን እየተወጡ እንደሚጠብቁት ተናግረዋል። ለአብነትም ለበዓሉ መድመቅ በዓሉ ከመድረሱ ሦስትና አራት ወራት በፊት በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት የሚወጡት ድርሻ አላቸው። የሃድያ አባቶች የያሆዴን የዘመን መለወጫ በዓል የሚያከብሩት በቅንጅት አማካኝነት ከአራት እስከ ስድስት ሰው በመሆን ተቀናጅተው ሰንጋ በመግዛት ነው። ለበዓሉ ሰንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ ማስቀመጥ የሚጀምሩትም ቀደም ብለው ነው ። እናቶች በዓሉ ከመቃረቡ ከሦስትና እና አራት ወራት በፊት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ለማጠራቀም በሚገቡት (ዊጆ) በተሰኘ ዕቁብ ቅቤ ማከማቸት ይጀምራሉ። በተጨማሪም ለስጋ መብያና ለአተካና መስሪያ የሚሆን እንሰት በመለየትና በመፋቅ፣ ቆጮ፣ ሜሬሮና፣ ቡላን ጨምሮ የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት የድርሻቸውን ይወጣሉ። የደረሱ ልጃገረዶች የቤቱን ወለል ቆፍረው ይደለድላሉ፣ የተለያዩ ውበት የሚሠጡ ቀለማትንና የተለያዩ ኖራዎችን በመጠቀም የቤቱን የውስጥና የውጭ ግርግዳን በመቀባት ያስውባሉ። ወጣቶች ከነሐሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚመርጡላቸውን ዛፍ፣ ግንድ ቆርጠው ለምግብ ማብሰያና ለደመራ የሚሆን ችቦ የማዘጋጀት ኃላፊነታቸውን እየተወጡ ይቆያሉ። ከመስከረም መግቢያ ጀምሮ ያሉ የቅዳሜ ገበያዎች ስያሜ (መቻል ሜራ ) የእብድ ገበያ በመባል ይጠራሉ።እነዚህ የግብይት ቀናት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የግብይት ቀናት በተረጋጋ መንገድ የሚተገበሩ ባለመሆኑና በጠዋት ቆሞ በጊዜ የሚበተን ገበያ በመሆኑ (መቻል ሜራ) የእብድ ገቢያ የሚል ስያሜ አሰጥቶታል ነው ያሉት አባቶች ሰንጋ ገዝተው ለመብላት ባደራጁት (ቱታ) ቅንጃ አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ ወደ መቻል ሜራ (እብድ ገበያ) በመሔድ የሚፈልጉትን ሰንጋ ገዝተው ይመለሳሉ። ገንዘብ ያላስቀመጡና በወቅቱ ማግኘት የማይችሉ አባወራዎች በዓሉን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተደስተው እንዲያሳልፉ ሌላኛው አማራጭ (ሃባ) በመባል የሚታወቅና ምንም ገንዘብ የሌላቸው ሰዎች ለበዓሉ የሚሆን ሰንጋ በብድር የሚወስዱበት በብሔሩ ተወላጆች ዘንድ የኖረ የመተጋገዝና የመተሳሰብ እሴት አንዱ ነው። የሚፈልጉትን ሰንጋ ከመረጡ በኋላ እህል በሚደርስበት በታህሳስና በጥር ለመክፈል በዱቤ ይወስዳሉ። የበሬ ነጋዴውም ያለ ማንገራገር ሰንጋውን በመስጠት ወቅቱ ሲደርስ ገንዘቡን ለመውሰድ ተስማምቶ ይሰጥና ወቅቱን ጠብቆ ገንዘቡን ይወስዳል። በትውስት ተወስዶ ገንዘብ ያልከፈለ አባወራ ለቀጣይ የዘመን መለወጫ አይደርስም ተብሎ በብሔሩ ዘንድ ስለሚታመን በተስማሙበት ወቅት ገንዘቡን የመስጠት ግዴታቸው የተጠበቀ ነው።   ሌላኛው አስተያየት ሰጪ የመምሪያው ባለሙያ አቶ ይዲድያ ተስፋሁን እንዳሉት በዓሉ ያለው ለሌለው አካፍሎ በጋራ የሚበላበትና ወደ አዲስ ዘመን በጠንካራ አብሮነት የሚሻገሩበት ነው። በመሆኑም የያሆዴ በዓል በዜጎች መካከል ጠንካራ አንድነትና አብሮነትን መሰረት ያደረጉ ዕሴቶች ያሉበት መሆኑን አንስተው ለትውልድ ግንባታ የሚሆኑ ዕሴቶችን አጎልብቶ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል ። ለበዓሉ ዋዜማ ከሚዘጋጁ ሁነቶች መካከል አተካና ልዩ ቦታ የሚሰጠው ነው። አተካና በተለይም ለዚህ በዓል ከዚህ ባሻገር ለትልልቅ እንግዶች ከሚዘጋጁ ምግቦች መካከል አንዱ ነው። አተካና ከወተት፣ ከቅቤ፣ አይብና ቡላ የሚዘጋጅና በበዓሉ የምግብ ፍላጎትን የሚከፍት ተበልቶ የማይጠገብ በእናቶች የሚዘጋጅ ጣፋጭ ምግብ ነው። የበዓሉ ዋዜማ አተካን ሂሞ (የአተካና ምሽት) የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን በዓሉን ለማክበር ከሩቅም ከቅርብም የተሰበሰበ ቤተሰብና እንግዶች በናፍቆት የሚመገቡት ምግብ ነው። በዚሁ ዕለት በአካባቢው ትልቅ የሚባል አባወራ (አዛውንት) ቤት ችቦ (ሳቴ ) ተዘጋጅቶ ማምሻውን አባቶች ወይም የሃገር ሽማግሌዎች የማቀጣጠያ (ጦምቦራ) ደመራ ማቀጣጠያ ይዘው ይወጣሉ። ከዚያም የአካባቢው ማህበረሰብም የሃገር ባህል ልብስ ለብሰው እንዲሁም ወጣቶች ተሰብስበው ያሆዴ ይጨፍራሉ። የሃገር ሽማግሌዎች ይመርቃሉ፤ ከዚያም የተዘጋጀውን ችቦ በእሳት ለኩሰው ያበራሉ። ይህም አዲስ ዘመን መግባቱን ማብሰርና ዓመቱ የብርሃን ዓመት እንዲሆን መልካም ምኞት የሚገለፅበት ነው። ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ ወጣቶች ያሆዴ (ኦሌ) ጭፈራ ሲጫወቱ ያነጋሉ። ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ አይጨፈርም። ወጣት ደመቀ አባቴ የሆሳዕና ከተማ ነዋሪ ሲሆን ስለ በዓሉ አስተያየቱን ሲሰጥ ''በአባቶች ደመራው ከተቀጣጠለ በኃላ እኛ ወጣቶች ያሆዴ ....ያህዴ....ሆያ ሆ... /ኦሌ/ ጭፈራ እየተጫወትን እናነጋለን፤'' ይህ ጭፈራ ከያሆዴ በዓል ውጭ ስለማይጨፈር በዓሉን ቀን በጉጉት እንደሚጠብቁት ተናግሯል። ተራርቀው የቆየ ወዳጅ ዘመድ ተሰብስቦ ያለምንም ልዩነት ችግርም ካለ በዕርቅና ሰላምን በማውረድ የሚመጣው ዘመን የልምላሜና የስኬት እንዲሆን ተመራርቀው የሚለያዩበት በዓል በመሆኑ በተስፋ የሚጠብቁት እንደሆነ ነው ወጣቱ የሚናገረው። የበዓሉ እለት ለዕርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኃላ የባህል ሽማግሌዎች (ጋቢማ ) ሥርዓት ያከናውናሉ። ክዋኔውም የበሬውን ሻኛ በለጋ ቅቤና በሠርዶ ሳር በመቀባትና ወተት በማፍሰስ ይከናወናል። ይህም በሚከናወንበት ወቅትም ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሃገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን በማለት (ፋቴ) ዳግም ምርቃት ፈጽመው በሬው ይጣልና የዕርድ ሥርዓት ይካሔዳል። በዕለቱም ከታረደው ሥጋ ቅምሻ በጋራ ይበሉና ቀሪውን ለማህበሩ (ለቱታ) አባላት ክፍፍል ይፈፀማል። ከእርድ ሥርዓቱ በኃላ በማግስቱ ልጆች ወደ ወላጆቻቸው ዘራሮ የሚባል አበባ ይዘው እየጨፈሩ ያስማሉ -ይመረቃሉ የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባባላሉ፤ ከስጋውም ፣ከቦርዴውም ፣ ከአተካናውም የሚመገቡበት ክዋኔ (ሚክራ) በመባል ይታወቃል። ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ስጋና (ዘራሮ) አደይ አበባ ጭምር ይዘው የሚሔዱበት እንዲሁም ያላገቡ ወጣቶች ለትዳር የሚሆናቸውን አጋር የሚፈልጉበትና የሚያጩበት ባህልም ያለው ነው ያሆዴ ክብረ በዓል። ከእርድ ስነ ስርዓቱ በኋላ ከሶስት ሳምንታት እስከ ወር ለሚሆን ጊዜ የመጠያየቂያና የመረዳጃ ወቅት ይሆናል። የያሆዴ በዓል ያሉ ዕሴቶች ለህዝብ ትስስር፣ ጠንካራ የስራ ባህልና ዘላቂ ሰላም ግንባታ ያላቸውን ሚና ለማላቅ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደምገባ የሚያነሱት በዋቸሞ ዩኒቨርስቲ የህዝብ ግንኙነትና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የአቶ ዳንኤል ገዴ በዚህ ላይ በአከባቢው ያሉ የማህበረሰብ ልምዶችና ወጎች ለትውልድ እንዲሸጋገሩ መስራትና የሃገር በቀል ዕውቀትን ማጠናከር እንደምገበባ ተናግረዋል። በዚህ ረገድ የዋቸሞ ዩኒቨረሲቲ የሃድያን ብሔር የዘመን አቆጣጠር ታሪክ : ባህልና ቋንቋ እንዲሁም ሌሎች ዕሴቶች ተሰንደው እንዲቀመጡና ለማስተማሪያነት እንዲውሉ ለማስቻል በጥናትና ምርምርና የተደገፈ ስራ በመስራት ላይ መሆኑን አመላክተዋል። በተጨማሪም ባህሉ ይበልጥ እንዲታወቅና በዩኔስኮ ተመዝግቦ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሚገባውን ጥቅም እንዲያመጣና ከቱሪዝም አንጻር ሚናውን እንዲጫወት ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል።
የመኔ ሸድዬ ባሮ - የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት
Sep 20, 2023 1332
በሽመልስ ጌታነህ (ኢዜአ) የመኔ ሸድዬ ባሮ የካፈቾ ብሄር ከአሮጌው ዘመን ወደ አዲሱ የሚሸጋገሩበት፣ የአዲስ ዘመን ብስራትና የዘመን መለወጫ በዓል ነው። በዓሉ የጠንካራ የስራ ባህል፣ የአብሮነትና የሰላም ተምሳሌት በዓል እንደሆነ ይነገርለታል። በዚህም የካፋ ብሄር ለዘመናት የገነባውና ጠንካራ የስራ ባህል፤ ተፈጥሮን የመጠበቅና የመንከባከብ እንዲሁም ከተለያዩ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር ተቻችሎና ተፈቃቅሮ የሚኖር ሲሆን ቱባ ዕሴቱ ዛሬም ላለው ትውልድ መሰረት መሆኑን ያምኑበታል። የተለያዩ የታሪክ ድርሳናት እንደሚያሳዩት ከሆነ የካፋ ህዝብ ጠንካራ ንጉሳዊ ሥርዓት የነበረው፤ የታሪክና የቱባ ባህል ባለቤትም ነው። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉት የታሪክ ባለሙያና የሀገር ሽማግሌ አቶ አሰፋ ገብረማሪያም የካፈቾ ብሄር ዘመን መለወጫ በሃገሬው አጠራር ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል የካፋ ህዝብ ከሚያከብራቸው በርካታ በዓላት ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ። በዓሉ ያለውን ግዝፈት ሲያመለክቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ ፀሐፍት ጭምር “ታላቁ በዓል ወይም (ግሬት ፌስቲቫል)” ተብሎ እንደሚጠራም ተናግረዋል። በዓሉ ታሪካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ዳራ ያለው ሲሆን ከጥንት ካፋ ንጉስ ጀምሮ በየአመቱ በድምቀት የሚከበር በዓል እንደሆነም ጠቁመዋል። የካፋ ህዝብ ከ14ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ ከጎሳ መሪነት አንስቶ ጠንካራ የመንግስት መዋቅር የነበረው ታላቅ ህዝብ እንደሆነ ያነሱት አቶ አሰፋ፣ በዚህም በዓሉ በዘመኑ የነበሩ መንግስታት በዓል እንደነበረም አብራርተዋል። ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም የሚገመገምበት ጥሩ የሠራና የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገበ የሚሸለምበትና ለበለጠ ሥልጣን የሚታጭበት፤ ሰነፉ ደግሞ የሚወቀስበትና ስልጣኑ የሚነጠቅበት ታላቅ በዓልም ነው ብለዋል። ይህም በብሄሩ ዘንድ ለዘመናት የተሻገረ የጠንካራ የሥራ ባህል ግንባታ መሰረት ሆኖ የቆየ መሆኑን አንስተዋል። ይህ ሁሉ ሲከናወን በማህበረሰባዊ የህግ ተገዥነት መሰረት መሆኑ የተለየ እንደሚያደርገው ገልጸው ከሁሉ በፊት ሰላምን በማስቀደም መንግስትንና ህግን ማክበር እንዲሁም ህግ የሚመራው ህዝብ የበላይ መሆኑን አመላካች ሥርዓት መሆኑን አንስተዋል። በዓሉ ከአዝመራ ጋር የተያያዘ የዘመን አቆጣጠርን ተከትሎ እንደሚከበርም የታሪክ ባለሙያው አቶ አሰፋ ይገልጻሉ። እንደ ታሪክ ተመራማሪው ገለጻ የካፋ ህዝብ አብዛኛው አርሶ አደር አልፎም አርብቶ አደር ሲሆን ለአዝመራ የተለየ ትኩረት ይሰጣል፤ በዓሉ ሊከበር 77 ቀናት ሲቀሩት ህዝቡ የአዲስ ዘመን መለወጫ ብሎ ሃምሌ አንድ አዝመራውን እንደሚጀምርም ጠቁመዋል። የአዝመራ ወቅት ሊገባደድ 25 ቀናት ሲቀሩት (ከሼ ዋጦ) ብሎ አዝመራውን ያጠናቅቃል። ወቅቱም ጨለማው አልፎ በብርሃን የሚተካበት፤ ክረምቱ ለበጋ ቦታውን የሚለቅበት በመሆኑ አዲስ አመት መድረሱን ያሳውቃል። ያን ጊዜ በጥንት የካፋ ምክርቤት ከሚገኙ ሰባት የሚክረቾ አባላት ውስጥ አንዱ የሆነው አዲዬ ራሾ ፤ የንጉሱ መቀመጫ በሆነው ቦንጌ ሸምበቶ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫው ለሚመጣው ህዝብ መንገዶችን በማፅዳት እና ለወንዞች ድልድይ በማበጀት በዓሉ መድረሱን ያበስራል። ያን ጊዜ በዓሉን ለማክበር ህዝብ ከያለበት አቅጣጫ ወደ ቦንጌ ሸምበቶ ይተማል። ህዝቡ በቦንጌ ሸምበቶ ከተሰበሰበ በኋላም ንጉሱ በተገኙበት የእያንዳንዱ ወራፌ ራሾ ሥራ ይገመገማል፤ ጥሩ ሥራ የሠራ ጠንካራ መሪ ይሸለማል፤ ለበለጠ ስልጣንም ይታጫል፤ ሀላፊነቱን በተገቢ ሁኔታ ያልተወጣው ደግሞ ይመከራል፣ ይወቀሳል አልፎም ስልጣኑን ይነጠቃል። ዛሬም ሀገራችን ይህ አይነቱን ጠንካራ የሥራ ባህል አብዝታ ትሻለች፤ እንዲህ አይነት ሀገር በቀል ዕውቀቶች ትውልዱን በጠንካራ ሥነ-ምግባርና የሥራ ባህል ለመገንባት ትልቅ ድርሻ አላቸው። በተጨማሪም በዓሉ ቅሬታዎችን ለመፍታትና ሰላምን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ፤ ቂምና ጥላቻን ይዞ ወደ ንጉሱ ፊት መቆምም ይሁን ወደ አዲሱ ዓመት መሻገር ነውር ተደርጎ የሚወሰድ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወደ በዓሉ ከመምጣቱ አስቀድሞም ይሁን በበዓሉ ወቅት የተጣላ ይታረቃል፤ ጥላቻም በፍቅር ይተካል ብለዋል የታሪክ ተመራማሪው። እንዲህ አይነቱ ሀገር በቀል ዕውቀት ጠንካራ ባህል ለመገንባት፤ ቅራኔዎችን በሰላም ለመፍታትና ማህበራዊ ግኑኝነቶችን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ ስላላቸው በትምህርት ሥርዓት ውስጥ አካቶ ማስተማርና ለቀጣዩ ትውልድ ማስተላለፍ ይገባል ሲሉም ሃሳባቸውን አካፍለዋል። ሌላኛው የሀገር ሽማግሌና የካፋ፣ጫራ እና ናኦ የባህል ምክርቤት አባል አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም እንደሚሉት የካፋቾ ''የመኔ ሸድዬ ባሮ'' በዓል ማህበራዊ ግንኙነትን በማጠናከሩ ረገድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው በዓል ነው። ምክንያቱ ደግሞ፣ በዓሉን ለማክበር በአካባቢው ያሉ፣ በሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች የሚገኙ እንዲሁም ባህር ማዶ የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች የሚሰበሰቡበት ታላቅ በዓል ስለሆነ ነው ብለዋል። በዚህም የተራረቀ የሚገናኝበት፤ የተጠፋፋ የሚጠያየቅበት ሲሆን ህዝቡ በአንድ ላይ ተሰብስቦ በንጉሱ ተመርቆ፣ በልቶ ጠጥቶ እንዲሁም ተጫውቶ ወደ ቀጣዩ አመት በደስታና በታላቅ ተስፋ የሚሸጋገርበት እንደሆነም አብራርተዋል። ይህ ባህል በተለያዩ ምክንያቶች ከ120 ዓመታት በላይ ሳይከበር እንደቆየ የገለፁት አቶ ፀጋዬ ገብረማሪያም ዳግም መከበር ከጀመረበት ስምንት ዓመታት ወዲህ የነበረውን ታሪክና ባህል በሚያስቀጥል መልኩ በየዓመት በድምቀት እየተከበረ መሆኑንም አንስተዋል። ወጣቱ ትውልድ ባህሉንና ታሪኩን አውቆ እንዲኖርና እንዲያስቀጥል ግንዛቤ የመፍጠርና የማስተማር ሥራ በሰፊው እየተሠራ እንደሆነም ገልፀዋል። ከዚህ ባለፈም ባህሉንና ታሪኩን ለማስቀጠል የባህል ምክር ቤቱ የወረዳ የባህል ምክር ቤቶችን የማጠናከር፣ ታሪካዊ ቅርሶችን የመሰብሰብና የማደራጀት ሥራ እየሠራ ነውም ብለዋል። በዓሉ አንድነትን የሚያጠናክር፣ ጠንካራ የሥራ ባህልን የሚያበረታታ እና የተፈጥሮ ጥበቃን የሚያጠናክር በመሆኑ ከካፋ ብሔረሰብ በዓልነቱ ባለፈ የሀገርና የአለም ቅርስና ሀብት እንዲሆን ሰፊ ርብርብ ማድረግ እንደሚገባም አቶ ፀጋዬ አሳስበዋል። የካፋቾ ዘመን መለወጫ በዓል (የመኔ ሸድዬ ባሮ) መሠረቱን ሳይለቅ ለትውልድ እንዲተላለፍ በዞን ደረጃ እየተሠራ መሆኑን የገለፁት የካፋ ዞን ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ተሾመ አምቦ ዘንድሮም ለዘጠነኛ ጊዜ በአደባባይ ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። በዓሉ በሁሉም የካፋ ህዝብ በጋራ ያለምንም ልዩነት የሚከበር ታሪካዊ በዓል ሲሆን አለም አቀፋዊ እውቅና አግኝቶ በዩኔስኮ እንዲመዘገብ ለማስቻል ከተለያዩ ምሁራንና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመሆን የተለያዩ ጥናቶች እየተሠሩ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ በበዓሉ ንጉሱ የተራቡትን የሚመግቡበት (ጮንጎ) የተሰኘ ስርዓት የሚፈፀምበትና የተጣሉ የሚታረቁበት ስርዓት እንደሚፈፀም የገለፁት አቶ ተሾመ አሁንም በዓሉ በየዓመቱ ሲከበር ይህ ሥርዓት ይከወናል ብለዋል። ቀጣይ ይህን በዓል በሰፊው አስተዋውቆ ወደ ቱሪዝም በማሳደግ ህዝቡ ከዘርፉ የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆን የሚያስችሉ ሥራዎች እንደተጀመሩም ሃላፊው ገልፀዋል። የዘንድሮው የ2016 ዓ.ም የካፊቾ ዘመን መለወጫ በዓል በቦንጋ ከተማ ከመስከረም 12 እስከ መስከረም 13/2016 ዓ.ም በፓናል ውይይትና በተለያዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበርም ጠቁመዋል።  
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 5583
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 10553
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በጂንካ ከተማ የተመረተው 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው የስኳር ድንች "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል ተመዘገበ
Mar 13, 2023 4002
ጂንካ መጋቢት 4/2015 (ኢዜአ):- በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር የተመረተው እና 23 ኪሎ ግራም የሚመዝነው ስኳር ድንች በአፍሪካ የድንቃ ድንቆች መዝገብ "በአፍሪካ ትልቁ ስኳር ድንች" በሚል መመዝገቡ ተገለጸ። በአዲስ አበባ በተካሄደው የእውቅና ስነስርዓት ላይ የአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ስራ አስኪያጅ አቶ አሸናፊ አለም ለስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜአለው የእውቅና ምስክር ወረቀት አስረክበዋል። ከዚህ ቀደም በአፍሪካ 10 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መቅረቡን አቶ አሸናፊ ለኢዜአ ገልጸዋል።   “ነገር ግን 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች በአፍሪካ ደረጃ ሲቀርብ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው” ብለዋል። በዓለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ 37 ኪሎ ግራም የሚመዝን ስኳር ድንች መመዝገቡንና በደሙዝ ሰፈር የተገኘው ስኳር ድንች በ14 ኪሎ ግራም ዝቅ ብሎ ከዓለም የ”ሁለተኛነት” ደረጃ ላይ እንደሚያስቀምጠው አመልክተዋል። የስኳር ድንቹ ባለቤት አቶ ኢሳያስ ጊዜያለው ስኳር ድንቹ በአፍሪካ ድንቃ ድንቆች መዝገብ ላይ በመስፈር የኢትዮጵያን ስም በማስጠራቱ መደሰታቸውን ገልጸዋል።   ስኳር ድንቹ እውቅና እንዲያገኝ የዜና ሽፋን ለሰጠው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ምስጋቸውን አቅርበዋል። ኢዜአ የካቲት 19 ቀን 2015 ዓ.ም “በጂንካ ከተማ ደሙዝ ሰፈር 23 ኪሎ ግራም የሚመዝን አንድ የስኳር ድንች መመረቱ ተገለጸ” በሚል መዘገቡ የሚታወስ ነው።
ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ እውቅና አገኙ
Mar 9, 2023 4851
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 30/2015 የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በጤና ልማት ዘርፍ በሴት አመራርነት ላበረከቱት አስተዋጽኦ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው በአፍሪካ ዓለም አቀፍ የጤና አጀንዳ ኮንፈረንስ (AHAIC)2023 ላይ እውቅና ተሰጣቸው። ሚኒስትሯ በሩዋንዳ ኪጋሊ ትላንት በተካሄደው Africa Health Agenda International Conference (AHAIC) 2023 ላይ የተበረከተላቸውን Women in Global Health Award የእውቅና ሽልማት በተወካያቸዉ በኩል ተቀብለዋል። እውቅናው በጤና ልማት ውስጥ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመቋቋምና በመፍታት፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና ፍትሀዊ ተደራሽነት እንዲሁም ሁሉን አቀፍ የጤና አገልግሎት ሽፋን ላይ ትኩረት ሰጥተው ለሚሰሩ አመራሮች የሚሰጥ መሆኑም ተመላክቷል። ለመጪዎቹ ትውልዶች አርዓያ ለሆኑ የአፍሪካ ሴት መሪዎች የሚሰጠው ሽልማቱ የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰም ለዜጎች የተሻለና ዘላቂ ጤናን ለማምጣት በሚደረግ ጥረት ውስጥ ላበረከቱት የላቀ የመሪነት ሚና ከአምሪፍ ሄልዝ አፍሪካ እውቅናውን አግኝተዋል።
በብዛት የታዩ
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 10553
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 7602
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 7461
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 7456
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  

በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 6947
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 6596
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
ተመድ በሶሪያ በርዕደ መሬት ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚውል የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
Feb 15, 2023 6169
አዲስ አበባ (ኢዜአ) የካቲት 8/2015 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በሶሪያና ቱርክ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ ሶሪያውያንን ለማገዝ የ397 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ጥሪ አቀረቡ። ዋና ጸሓፊው ጥሪውን ያቀረቡት ባሳለፍነው ሳምንት በቱርክና በሶሪያ ድንበር አቅራቢያ በደረሰው ርዕደ መሬት ሳቢያ ከቤታቸው የተፈናቀሉ አምስት ሚሊዮን የሚጠጉ ሶሪያውያንን ለማገዝ ነው። በኒውዮርክ በሰጡት መግለጫ ሶሪያውያኑን ለማገዝ የተጠቀሰው የገንዘብ መጠን ለሶስት ወራት ጊዜ ብቻ የሚበቃ መሆኑን ጠቅሰው የሚመለከታቸው ሁሉ የድርሻቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል። ከአደጋው በኋላ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 50 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ ድጋፍ ማቅረቡን ገልጸው ተጨማሪ እገዛዎች አሁንም እንደሚያስፈልጉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በድርጅቱ ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማትና አጋር አካላት በጋራ በሚያቀርቡት ገንዘብ፤ አስቸኳይ ድጋፍ ለሚፈልጉ ሶሪያውያን የመጠለያ፣ የጤና፣ የምግብ እንዲሁም ሌሎች አስቸኳይ ድጋፎች እንደሚደረጉ አብራርተዋል። ተመሳሳይ የድጋፍ ማዕቀፍ በቱርክ ድንበር ለሚገኙ ዜጎች እየተጠናቀቀ እንደሚገኝም ዋና ጸሓፊው ተናግረዋል።
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ)
Jan 25, 2023 6012
ሽሬ ወአክሱም (የአልፎ ሂያጁ ማስታወሻ) አየለ ያረጋል (ኢዜአ) መዳረሻዬ ሽሬ እንዳስላሴ ነው። ለዘገባ ሥራ ከባህርዳር- ጎንደር- ደባርቅ- ሸሬ መንገድ ከሚዲያ ባልደረቦች ጋር እየተጓዝኩ ነው። የጥምቀት ሙሽራዋ ጎንደር እየተኳኳለች ነበር። ደባርቅ ከመድረሴ በፊት ዳባት ትገኛለች-የደጃች አያሌው ብሩ ቁርቁር ከተማ። ደጃች አያሌው ትውልዳቸው በጌምድር ጋይንት ቢሆንም ግዛታቸውና ኑሯቸው ዳባት ነበር። ሞገደኛው ደጃዝማች አያሌው ብሩ በጎንደር ማኅበረሰብ ዘንድ ዝናቸው የናኘ ነው። ደጃዝማች አያሌው በ20ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ (ከልጅ ኢያሱ እስከ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመነ-መንግሥት) ታሪካዊ ክንውኖች ጉልህ ተሳትፎ አላቸው። አንዷን ብቻ ልምዘዝ። ራስ ተፈሪ ‘ንጉሠ-ነገሥት አጼ ኃይለሥላሴ’ ደጃች አያሌው የቅርብ ዘመዳቸውን ራስ ጉግሳ ወሌ ብጡልን (የንግሥት ዘውዲቱን ባለቤት) ወግተው የጎንደር ግዛት ‘ራስ’ ተብለው ለመሾም ቃል ቢገባላቸውም፤ ተልዕኳቸውን ተወጥተው ቃሉ ባለመፈጸሙ ደጃዝማቹ ከአጼው ጋር መቀያየማቸው አልቀረም። በዚህም:- "አያሌው ሞኙ፣ ሰው አማኙ ሰው አማኙ፣ የአያል ጠመንጃ፣ ስሟን እንጃ ስሟን እንጃ…” በማለት የጎንደር አዝማሪ አዚሟል። ዛሬም ይህ ግጥም የብዙ ባህላዊ ዘፈኖች አዝማች ነው። ደጃች አያሌው ብሩ ደፋር ናቸው ይባላል። ከአጼ ኃይለሥላሴ ጋር ቢቀያየሙም በ1928 ዓ.ም ፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ ሲመጣ ቅድሚያ ለአገሬ ብለዋል። ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘው የዶክተር ሀራልድ ናይስተሮም (ትርጉም ገበየሁ ተፈሪ እና ደሳለኝ አለሙ) መጽሐፍ እንደተጠቀሰው ደጃች አያሌው “ንጉሡ እንደኛ ሰው ናቸው። ኢትዮጵያ ግን የሁላችንም ናት" ብለው ጦራቸውን መርተው በሽሬ ግንባር ዘምተዋል። ጉዟችን ቀጥሏል። ደባትን እያለፍን ነው። ‘እንኳን ደህና መጡ፤ ወደ ጭና ታሪካዊቷ ሥፍራ’ የምትለዋን ታፔላን በስተግራ እያየን ወደ ደባርቅ ገሰገስን። የሰሜን ተራሮች የብርድ ወጨፎ ያረሰረሳትን ደባርቅን ከማለፋችን ሊማሊሞ ጠመዝማዛ ቁልቁለት ተቀበለን። አስፈሪ የሊማሊሞ መልክዓ ምድር የደጋው ሰሜን ውርጭ እና የተከዜ በርሃ ኬላ ነው። ባለቅኔው ጸጋዬ ገብረመድህን “የሰማይ የምድሩ ኬላ፣ የየብስ የጠፈሩ ዋልታ አይበገር የዐለት ጣራ፣ አይመክተው መከታ ሊማ-ሊሞ አድማስ ሰበሩ፣ በጎማ ፈለግ ይፈታ? በትሬንታ እግር ይረታ?…” ብሎ የመኪና መንገድ ተገንብቶበት በማየቱ ግርምቱን የተቀኘለትም ለዚህ ይመስላል። ከሊማሊሞ ቁልቁለት በኋላ አዲ-አርቃይ፣ ዛሪማ፣ ማይፀብሪ እና ሌሎች የጠለምት ወረዳ ከተማዎችን አልፈን፤ የዋልድባ ረባዳማ አካባቢዎችን ተሻግረን ተከዜ ወንዝ ደረስን። የዚህን መንገድ እና ተከዜ ወንዝን ሳስብ የሀዲስ ዓለማየሁ ትዝታ አስተከዘኝ። የፋሺስት ኢጣሊያ ወራሪ ጦር የወገንን ጦር ፊት ለፊት መቋቋም ሲሳነው በሰው ልጆች ላይ ተደርጎ የማያውቅ መርዝ በጅምላ የፈጀበት አሳዛኝ ታሪክ ነበር። በተከዜ ወንዝ ውሃን በመመረዝ የወገን ጦር ያለቀበት ሥፍራ ነው። የተከዜ ሸለቆ በኢትዮጵያዊያን ደምና አጥንት ዋጋ የተከፈለበት ነው። ሀዲስ ዓለማየሁ በአንድ ዕለት የተመለከቱትን እንዲህ ጽፈውታል። “የተከዜ ውሀ እመሻገሪያው ላይ ሰፊና ፀጥ ያለ ነው። ታዲያ ያ ሰፊ ውሀ፤ ገና ከሩቅ ሲያዩት ቀይ ቀለም በከባዱ የተበጠበጠ ይመስላል። “ምን ነገር ነው፤ ምን ጉድ ነው?” እየተባባልን ቀረብ ስንል መሻገሪያው በቁሙም በወርዱም ከዳር እስከ ዳር ሬሳ ሞልቶበት የዚያ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው። የሰው ሬሳ፣ የፈረስ እና የበቅሎ ሬሳ፣ ያህያ ሬሳ፣ ያውሬ ሬሳ፥ ሬሳ ብቻ! እግር ከራስ ራስ ከእግር እየተመሰቃቀለ እየተደራረበ ሞልቶበት፥ የዚያ ሁሉ ሬሳ ደምና ፈርስ ነው”። ይሉናል። ቀጥለውም “በእውነቱ እንዲህ ያለውን መሳሪያ ምንም ጠላት ቢሆን በሰው ላይ ለማዋል የሚጨክን ሰው፥ ሰብዓዊ ስሜት የሌለው፣ አለት ድንጋይ የተፈጠረበት መሆን አለበት፤ እንዲህ ያለውን መሳሪያ በሰው ላይ ማዋል ሰብዓዊ ህሊና ሊሸከመው የማይችል እጅግ ከባድ መሆኑን ዓለም ሁሉ ያወቀውና ያወገዘው በመሆኑ የኢጣሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ ላይ ከማድረጉ በቀር “ሌላ መንግሥት በሌላ አገር ላይ አደረገ’ ሲባል ተሰምቶ የሚያውቅ አይመስለኝም” ብለዋል። ከተከዜ ባህር ማዶ ጉዞዬ ያገኘኋት ሌላዋ ታሪካዊ ሥፍራ እንዳባጉና ናት። እንዳባጉና የወገን ጦር ትልቅ ገድል የፈጸመበት ነው። ጀግኖች አባቶቻችን የጠላት ታንክ ሳያስፈራቸው የጠላት ጅምላ ጨራሽ ቦምብ ጣይ አውሮፕላን ተቋቁመው ጠላትን ድባቅ የመቱበት፤ ወደ አክሱም እንዲያፈገፍግ ያደረጉበት ሥፍራ ነው። “የጠላት ቦምብ ጣይ አውሮፕላን በጦር ሜዳው ትንንሽ ቦምቦች አውቶማቲክ ጠመንጃ ይተኩስ ነበር። አቢሲኒያኖች ደግሞ ከጠላት ጋር ግብግብ ገጥመው ጉዳይም አልሰጡትም ነበር…” ይላል ዶክተር ሀራልድ ‘የተደበቀው ማስታወሻ’ በተሰኘ መጽሐፉ። ይህ አካባቢ በሀገር ፍቅር የነደዱ ኢትዮጵያዊያን ደም ያፈሰሱበት፣ አጥንት የከሰከሱበት፤ ለኢትዮጵያ መስዕዋትነት የከፈሉበት ነው። ይህ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር ዋጋ የተከፈለበት ቀጣና ነው። ቀኑ ተገባዷል። ጉዟችን እንደቀጠለ ነው። እኔም የማሽላ ማሳዎችን ግራ ቀኝ እየተመለከትኩ ለዕለቱ መዳረሻችን ወደሆነችው ሽሬ ከተማ ገባን። ሽሬ በትግርኛ ‘ሽረ’ ሲሉት ይደመጣሉ። በእርግጥ ሽሬን ለመጀመሪያ ጊዜ መርገጤ ነው። ዕለቱም ጥር ሥላሴ ነው። ሽሬ በጥር ሥላሴ ትደምቃለች፤ ሙሉ ስሟም ሽረ እንዳስላሴ ነው። የሽሬ ሥላሴ ጠበል ሽሬ ደርሰን ማረፊያችንን ያዝን። ጊዜው በጣም አልመሸምና ከተማዋን በቀላሉ መቃኘት ይቻላል። ሽሬ ሰፊና ደማቅ የዞን ከተማ ናት። ከመካከላችን የአንደኛው ባለሙያ ቤተሰቦች ሽሬ ነበሩና አስጠሩን። ለሥላሴ ጠበል ግብዣ። ባል እና ሚስቱ ከልክ በላይ መስተንግዶ አደረጉልን። ‘ጠብ እርግፍ አድርገው አስተናገዱን’ ማለት ይቀላል። እንግዳ መቀበል ነባር ኢትዮጵያዊ እሴታችን ቢሆንም ጦርነት ውስጥ ለቆየ አካባቢ የተለየ መልክ ነበረው። እንግዳ አቀባበላቸው በእርግጥም የመሃል አገር ሰው የናፈቃቸው ይመስላል። የተትረፈረፈ እህልና ውሃ አቅርበው በ’ብሉልን፤ ጠጡልን’ ተማጽኗቸው የተነፋፈቀ ቤተ-ዘመድ ግብዣ አስመሰሉት። የሥላሴው ጠበል የሸሬ ጠላ ቀረበ። የሸሬ ጠላ ሳስታውስ ፕሮፌሰር ሽብሩ ተድላ ታወሱኝ። የወቅቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምሀሩ ፕሮፌሰር ሽብሩ በዘመነ ደርግ በዕድገት በሕብረት ዘመቻ ተማሪዎቻቸውን ይዘው ሽሬ ዘምተው ነበር። በወቅቱ ታዲያ የሸሬ ጠላ ፍቅር ይዟቸው በየጊዜው ሲኮመኩሙ የተመለከቱ ሰዎች ‘ፕሮፌሰሩ ከጠፉ የሚገኙት ጠላ ቤት ነው’ ሲባሉ እንደነበር ‘ከጉሬ ማርያም እስከ አዲስ አበባ’ በተሰኘው ግለ ታሪካቸው አስፍረዋል። ከግብዣ መልስ ከማረፊያ ሆቴል ላይ ሆኜ ከተማዋን ስቃኛት ከጦርነት ድባቴ የተላቀቀች ይመስላል። የአመሻሽ ሕዝቡ እንቅስቃሴም ሆነ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ የሚሰሙ የመዝናኛ ቤቶች ሙዚቃዎች የከተማዋን አሁናዊ መልክ የገለጠልኝ ነበር። ንጋት ላይ በቁርስና ቡና ሰዓታት ከሰዎች ጋር መስተጋብሬ ጀመረ። በጦርነት አዙሪት የከረመችው ሽሬና አካባቢው ኑሮ እጅጉን የከበደ ነበር። መልከ-ብዙ ማህበራዊ ቀውሶች አስተናግደዋል። አሁናዊ ምላሻቸው “ተመስገን፤ ያ ሁሉ አለፈ” የሚል ነው። ገበያው ተረጋግቷል፤ ማህበራዊ ኑሮ ተመልሷል። ድህረ-ሰላም ስምምነት ለሽሬ ነዋሪዎች ሁለንተናዊ እፎይታን አንብሯል። ከቀናት በኋላ በአክሱም የታዘብኩትም እንዲህ ነው። ኑሮን ያቀለለው የተቋማት አገልግሎት ጅማሮ በመጀመሪያ ዘገባ ስራዬ መሰረተ ልማትን አገልግሎት ቃኘሁ። ባንክ፣ ቴሌ፣ ሆስፒታል… መሰሎቹን። ተጠቃሚዎችንም፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ስራ ሃላፊዎችንም አነጋገርሁ። ከሰላም ስምምነቱ ማግስት ጀመሮ ተቋማቱ ወደስራ መመለሳቸው ከሁለንተናዊ ችግር እንደታደጋቸው ያነሳሉ። በትራንስፖርት እየተንቀሳቀሱ፣ በኤሌክተሪክ ስራዎቻቸውን እየከወኑ ነው። ለሁለት ዓመታት የተቋረጠው አገልግሎት አቅርቦት እና የአገልግሎት ፈላጊዎች ፍላጎት ግን አሁንም ሙሉ በሙሉ ተመጣጣኝ እንዳልሆነ የተጠቃሚዎችም፤ የአገልግሎት ሰጭዎችም ሀሳብ ነው። በሽሬ ስሁል ሆስፒታል የተመለከትኳቸው፤ ያነጋገርኳቸው፤ ከታዳጊዎች እስከ አዛውንት ዕድሜ ያሉ ህሙማን የሰላም አየር ማግኘታቸው የሕይወታቸው ዑደት እንዲቀጥል አድርጓል። ድንገተኛም ሆነ ነባር ህመም ያለባቸው ሰዎች በነጻ እየታከሙ ነው ያገኘኋቸው። ሰላም ከሌለ መታከም ቀርቶ በቅጡ ማስታመም፤ በወጉ መቀበርም እንደማይቻል ገልጸውልናል። የጤና፣ የባንክና የቴሌኮም አገልግሎት የግብዓት ክፍተቶች የማሟላት ሰራዎች እየተከናወኑ መሆኑንም በፌዴራል ደረጃ በየተቋማቱ የተመደቡ አስተባባሪዎች አረጋግጠውልኛል። የጸጥታ አካሉና የህብረተሰቡ ትብብርም የሚያስቀና እንደሆነ ግለሰቦችም፤ የጸጥታ አካላትም ነግረውኛል። አክሱም ጺዮን ማርያም፣ ሽሬ ስላሴ ንግስ፣ የጥምቀት በዓላት ከሶስት ዓመታት በኋላ በአደባባይ ታቦት ወጥቶ ተከብሯል። የፌዴራል ፖሊስ ተወካዮችም ይህንኑ ነው ያረጋገጡልኝ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት ከከተማ ነዋሪዎች ጋር ያላቸው ግንኙነት ቤተሰባዊ የሆኑ ይመስላል። እንቅስቃሴያቸውም የሰላማዊ ቀጠና መልክ ያለው ነው፤ ዩኒፎርም ከመልበሳቸው በስተቀር ጀሌያቸውን ይንቀሳቀሳሉ። ይህ ደግሞ መተማመን ከመፍጠር ባለፈ ጦርነት ውስጥ ለቆየ ማህበረሰብ ከስነ ልቦና ጫና እንዲላቀቅ አይነተኛ ሚና እንደላው ይሰማኛል። ኢ-መደበኛ የሽሬና አክሱም ወጎች ያረፍኩበት ሆቴል ባለቤት ‘አደይ’ ተግባቢ ናቸው። ደግ እናት ይመስላሉ። ከገባን ጀምሮ ‘ጠላ ተጎንጩ፤ ቡና ጠጡ’ ጭንቃቸው ነው። ሁለት ቀን ቡና አስፈልተውልናል፤ ጠላ አቅርበው ዘክረውናል። ይህ ሁሉ ሲሆንም ለከተማው እንግዳ መሆናችንን እንጂ ስለሙያችንም ሆነ ስለሌላ ማንነታችን አያውቁም ነበር። ብዙ መጨዋወትና ውሎ አዳር በኋላ ነው ጋዜጠኛ ስለመሆናችን ያወቁት። አደይ ተጨዋች ናቸው። አማርኛ ያዝ ቢያደርጋቸውም ጨዋታቸው ‘ኩርሽም’ ነው- ተሰምቶ የማይሰለች። በአጋጣሚ ‘ሰለክላካ’ ስለምትባለዋ ታሪካዊ ሥፍራ ጠይቄያቸው እያወጋን ነበር። ‘እንደእናንተ ወጣቶች ሳለን ‘ሰለክላካን ያላዬ ሸዋን ያመሰግናል’ ይባል ነበር። ታዲያ አንድ የሸዋ ሰው መጣና ሰለክላካን አየና ‘በቃ ይቺ ናት’ ሰለክላካ’ ብሎ ተገረመ” ብለው አሳቁን። (የፍቅር እስከ መቃብር መሪ ገጸ-ባህሪው ‘በዛብህ’ ወደ ዲማ ጊዮርጊስ ሄዶ ‘የዲማ መልኳ እና ዝናዋ’ ተጣርሶበት እንደተገረመበት ቅጽበት መሆኑ ነው)። አደይ የተጀመረው ሰላም ፍጹም ምሉዕ ሆኖ ወደ ቀደመ ኢትዮጵያዊ መልካችን የምንመለስበት ጊዜ እንዲመጣ ይሻሉ። ከጦር-ነት ወደ ሰላም-ነት! ቆንጂዬዋ ፊዮሪ የኮሌጅ ተማሪ ነበረች። በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት ጀምሮ በኋላም በጦርነት ሳቢያ ትምህርቷን ካቆመች ሦስት ዓመታት ሆኗታል። ጦርነቱ ከቆመ በኋላ የጀበና ቡና ጀምራለች። ደንበኞቿ ሰብሰብ ብለን እንቀመጣለን። ፊዮሪ ከስኒ ማቅረቢያዋ ላይ አነስተኛ ጀበናዋን፤ የሚያማምሩ ስኒዎቿን እና መዓዛው ከሚያውድ የዕጣን ማጨሻዋ ጋር ሰድራ ይዛ ትቀርባለች። ከመካከላችን ካለው ጠረጴዛ ላይ ታስቀምጥና እርሷም ወንበር ይዛ ከመካከላችን ትቀመጣለች። ቡናው እስኪሰክን ጨዋታዋን ታስኮመኩመናለች። ቡናው ከሰከነ በኋላ ቡናዋን ቀድታ ለእያንዳንዳችን በእጃችን እያነሳች ትሰጣለች። በሽሬ ቡና የሚቀርበው በዚህ መልክ ነው። ለፊዮሪ እና መሰሎቿ ጦርነቱ ክፉ ጠባሳ መጣሉ፤ ተስፋቸው ላይ መጥፎ አሻራ ማስቀመጡን ታነሳለች። አሁን ግን ብሩህ ተስፋ ሰንቃለች። ስለነገዋም “ሰላሙ ይዝለቅልን፤ ትምህርቴን ለመቀጠል እመኛለሁ” ትላለች። አክሱም ከሽሬ በስተሰሜን 60 ኪሎ ሜትር ይርቃል። ከሽሬ አክሱም ስንንቀሳቀስ ከጥምቀት ዕለት በስተቀር ገበሬው የግብርና ሥራዎቹን እየከወነ ነበር። አርሶ አደሩ ያርሳል፤ መስኖውን ያለማል። የተዘራውን ውሃ ያጠጣል። የበቀለ ቡቃያውን ይኮተኩታል። ከጦርነት ወደ ልማት መዞሩን ዐይኔ ታዝቧል። በጥምቀት ዋዜማ፤ የከተራ በዓል ዕለት ሁለት ጎራማይሌ የረፋድ ትዕይንቶችን ላንሳ። ከአክሱም ከተማ ወደ አድዋ እና ሽሬ መገንጠያ አካባቢ ሰፊ የቀንድ ከብት ገበያ ነበር። እውነተኛ የዓመት በዓል ገበያ መልክ ያለው ትዕይንት ነበር። በተለይም የፍየል ዋጋ በተመጣጣኝ ዋጋ እየተገበያዩ እንደነበር ሰምቻለሁ። ታሪካዊቷን አክሱም ከተማ ለመጨረሻ ጊዜ የረገጥኳት/የተሳለምኳት ከአራት ዓመት በፊት በ2011 ዓ.ም ይመስለኛል። ከገበያው ቀጥሎ በታቦተ-ጽዮን መገኛዋ ርዕሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ደጅ፣ በጥንታዊያኑ የአክሱም ሐውልት መገኛ አደባባይ ነበር። ከጽዮን በስተምዕራብ በአርባቱ እንሰሳ በኩል፤ በቅዱስ ያሬድ ዋርካ… አድርጌ በጽዮን ዋናው በር ደረስኩ። ማራኪ የአክሱም የኮብልስቶን መንገዶች ኦና ናቸው። የወትሮው ግርግር ናፍቋቸዋል። ከጽዮን ቅጥር ግቢ በዋናው በር በስተውጭ አነስተኛ እና ብቸኛ ዋንዛ በኮብልስቶን መሃል ነበረች። ዛሬም ለምልማ አለች። በዚህ አካባቢ ድሮ የነጭ ጎብኚ ጋጋታ፣ የጽዮን ደጅ ጠኚ ምዕመን… የተጨናነቀ ነበር። እንደ ድሮው የፎቶ አንሺ ግርግር፣ የአክሱም መስቀል ቀርጸው የሚሸጡ ወጣቶች ጫጫታ የለም። ይልቁንም እርጥባን የሚሹ አቅመ ደካሞችና ህፃናት ነበሩ። ጦርነት የሥፍራዋን መልክ አጠይሞታል። ያም ሆኖ ከተማዋ የንግድ እንቅስቃሴ ሙሉ በኩሉሄ ባይባልም ወደነበረበት እየተመለሰ ነው። የግልም ሆነ የመንግሥት ባንኰች ሥራ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። ከአክሱም ሐውልት ወደ ሌላ ሰፈር አቀናሁ። ትርሐስ ገና ታዳጊ ልጅ ነች። ጠይም፤ ስርጉድ፣ ሳቂታና ተረበኛ አይነት ልጅ ነች። እንደ ሽሬዋ ፊዮሪ መንገድ ዳር የጀበና ቡና እየሰራች ነው። ከሩቅ የመጣን እንግዶች መሆናችንን ስታውቅ፤ ደስታዋ ከገጿ ይነበብ ነበር። ያለፉ ጊዜያትን ሰቆቃ አጫወተችን። ስለቀጣይ ዕጣ ፈንታዋ እና ዕቅዷ ስታወራ ትቆይና “የሰው ልጅ ግን በጣም ከሃዲ ነው። ከወራት በፊትኮ ስለቢዝነስ አላስብም ነበር። መቼ እሞታለሁ እንጂ” ብላ ራሷን ትወቅሳለች። ወደ ሰማይ አንጋጣ ፈጣሪዋን ታመሰግናለች። ጦርነት ተራውንም ሕዝብ ለመልከ-ብዙ ቀውስ ዳርጎት እንደቆየ ታነሳለች። ዛሬ ሁሉ አልፎ ሰላም መውረዱ ለመጨዋወት መብቃቷ ለእርሷ ትልቅ ብሥራት ነው። ይህ ለትርሐስ ብቻ ሳይሆን ለመላው አክሱማዊያን መሆኑ እሙን ነው። አክሱም ከተማ በመከላከያ ሠራዊት ቁጥጥር ሥር ከዋለችበት ጊዜ ጀምሮ በከተማዋ በሻለቃ አዛዥነት የተሰማራ የፌደራል ፖሊስ አባልም ያጋጠመውን አሳዛኝ ገጠመኞች አጫውቶኛል። ጦርነቱ ቢራዘም ኖሮ በተራው ሕዝብ ላይ ምን ያህል የከፋ ጉዳት ይደርስ እንደነበር በአሳዛኝ ሁኔታ ገልጾልኛል። አክሱሞች ያን ሁሉ አልፈው ሰላም አየር ነፍሶ፣ ከስጋት ቆፈን ተላቀው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ ተመልሰዋል። የዛሬ ሳምንት ሰርክ(11 ሰዓት) ላይ አክሱም የከተራ በዓል በድምቀት አክብራለች። ታቦተ-ጽዮን ወደ ባህረ- ጥምቀቱ ስትወርድ፤ ወግና ሥርዓቱ ተጠብቆ፣ ሕዝቡ በሀበሻ ነጫጭ አልባሳት፣ ካህናት በልብሰ ተክህኖ ደምቀው … እየተከወነ ነበር። አንዲት እናት ለአማርኛ ተናጋሪ በቀረበ አነጋገር እያለቀሱ ታቦት እየሸኙ ነው። ትኩር ብዬ ሳያቸውም ዕንባቸው ዱብ ዱብ ይላል። “ከዚያ ሁሉ መከራ አልፎ ለዚህ በቃን፤ ተመስገን” እያሉ እልልታውን ያቀልጡታል። በደስታ እያነቡ ነበር። ይህ ስሜት የብዙኃኑ አክሱማዊያን እናቶች እንደሆነ መገመት ቀላል ነው። አክሱም በኮቪድ እና በኋላም በጦርነቱ ምክንያት ባህረ-ምቀት ታቦት ወጥቶ ሲከበር ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር። ከወትሮው በተለየ ድምቀትና ውበት በሰላምና በደስታ፤ በአደባባይ እልልታና ሆታ በማክበራቸው ልዩ ስሜት ፈጥሮባቸዋልና! እናም በአክሱም የከተራ ሆነ የበዓለ-ጥምቀት ክብረ-በዓላት በሰላም ስምምነቱ ማግስት በድምቀት ተከውኖ አለፈ። የሃይማኖት አባቶቹም ሆኑ ምዕመኑ በሰጡት ቃለ መጠይቅም የዘንድሮው ክብረ-በዓል ካለፉት ዓመታት ነባራዊ ሁኔታ ጋር እያነጻጸሩ፤ ትልቅ ብሥራትና መልክ እንዳለው ገልጸዋል። ሰላም እንዲጸና፤ ነባር ኢትዮጵያዊ አንድነትና መተባበር እንዲመለስ ጽኑ መሻታቸውን ነግረውናል። በበጎ ቀን የማውቃትን አክሱም፤ ከረዥም ጊዜ በኋላ አሁናዊ መልኳን ታዝቤ፤ የነገ ትዝታ ሰንቄ ተመለስኩ!! ሰላም ለኢትዮጵያ!!
መጣጥፍ
“ዮ-ማስቃላ''- ሁሉም የሚደሰትበት በዓል
Sep 23, 2023 812
በሳሙኤል አየነው የሰላም፣ የአብሮነት፣ የፍቅር፣ የመቻቻልና የአንድነት ተምሳሌት የሆነው የጋሞ ብሔር የዘመን መለወጫ በዓል “ዮ-ማስቃላ” ከወርሃ መስከረም አጋማሽ ጀምሮ በተለያዩ ባህላዊ ሁነቶች በድምቀት ይከበራል ። በተለያየ ምክንያት በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ተራርቀው የነበሩ ወገኖች ወደ የአካባቢያቸው በመመለስ ከቤተሰቦቻቸው ብሎም ከቀየው ህብረተሰብ ጋር አብረው የሚያከብሩት የዓመቱ ታላቅ በዓል ነው ። ታዲያ በዓሉን በድምቀት ለማክበር ወንዶች ሰንጋ በሬ ለመግዛት እንዲሁም ለትዳር አጋሮቻቸውና ለልጆቻቸው ልብስና ጌጣ ጌጥ የሚሆን ገንዘብ መቆጠብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን ሴቶችም ለባህላዊ ምግቦች፣ ለቅመማ ቅመም፣ ለቅቤና ለባህላዊ መጠጦች እህል ግዥ የሚሆን ገንዘብ ዓመቱን ሙሉ ሲቆጥቡ ይከርማሉ። መስከረም ወር ከገባበት ዕለት አንስተው ወንዶችም ሆኑ ሴቶቹ በቆጠቡት ገንዘብ በየፊናቸው ለበዓሉ የሚሆኑ ቁሳቁሶችን ማቅረብ ይጀምራሉ። ይህም የዝግጅት ጊዜ “እንግጫ” በመባል ይጥራል። በ”ዮ--ማስቃላ” ጊዜ አብሮነት እንጂ ግለኝነት የሚባል ነገር በጋሞዎች ዘንድ ፈጽሞ አይታሰብም፤ አብሮ እርድ ማካሄድ፣ አብሮ መመገብ፣ አብሮ መጠጣት፣ አብሮ መጫወት የጋሞዎች መገለጫ ነው። እንደ ሌሎቹ በዓላት ሁሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችም በዓሉን እንዴት እናሳልፍ የሚል ስጋት አያድርባቸውም። ምክንያቱም የሌለውም ካለው ጋር አብሮ የሚቋደስበት፣ የሚደሰትበት፣ የሚተሳሰብበትና የሰብአዊነት ልክ የሚንጸባረቅበት ልዩ ድባብ ያለው በዓል ነውና ዮ-ማስቃላ ። የጋሞ የሀገር ሽማግሌ አቶ አመሌ አልቶ ስለ “ዮ--ማስቃላ” በዓል በትንሹ እንዲያወጉን ጠይቀናቸው በዓሉ ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን እንስሳትና አዕዋፋት ሁሉ የሚደሰቱበት እንደሆነ ነግረውናል። በአካባቢው ቋንቋ ተፈጥሮ ሁሉ በዓሉን በደስታ እንደሚያሳልፍ ለመግለጽ “ካፎስ ካናስ ማስቃላ” በማለት የሚገለጽ ስሆን “ለሰው ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትም መስቀል ነው” እንደማለት ነው ብለዋል። በዓሉ ከመድረሱ ከሶስት ወራት አስቀድሞ በየአካባቢው ለእንስሳት የግጦሽ ሥፍራ ተከልሎ የሚዘጋጅ ሲሆን ችቦው በሚለኮስበት በደመራው ዕለት የቤት እንስሳት በሙሉ በዚያው የሚሰማሩ ይሆናል። ዓመቱን ሙሉ ሲያርሱ የነበሩ የእርሻ መሣሪያዎችም በበዓሉ ጊዜ ታጥበውና በቅቤ ታሽተው በክብር ይቀመጣሉ። ክብር ለሰው ልጆች ብቻ ሳይሆን ለእንስሳትና ለእርሻ መሣሪያዎችም ይሰጣል። በባህሉ መሠረት ችቦ በሚወጣበት ሰዓት አባት የራሱን ችቦ ለኩሶ የቤቱን ምሰሶ፣ የከብቶችን ጋጣና የበር ጉበኖችን ግራና ቀኝ በችቦው ጫፍ በማነካካት ወደ ውጭ ካወጣ በኋላ ወንድ ልጆች የየራሳቸውን ችቦ ተራ በተራ እየለኮሱ አባታቸውን ተከትለው “ዮ---ማስቃላ” እያሉ ወደ ደመራ ቦታ ያመራሉ። ከዚያም አባት በቅድሚያ ችቦውን ከለኮሰ በኋላ ልጆች ደግሞ ተከትለው ደመራውን ይለኩሳሉ። ከዚህ ፕሮግራም መልስ ወደ ቤት ተመልሰው የተዘጋጀውን ገንፎ በአንድ ወጭት ላይ “ዮ--ማስቃላ”እያሉ ሁሉም የቤተሰብ አባላት፣ ዘመድ አዝማድና ጎረቤት ተሰባስበው በጋራ ይመገባሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል በዋናነት እርድ የሚከወን ሲሆን ቁርጥ፣ ጎረድ ጎረድ፣ ክትፎና የወጣ ወጥ ዓይነቶች ተሠርተው ለምግብነት ይቀርባሉ። ከባህላዊ ምግቦች ደግሞ የገብስ ቅንጬ፣ የቆጮና ገብስ ውህድ ቂጣ፣ የቡላ ፍርፍር፣ ሀረግ ቦዬ፣ እንዲሁም ከመጠጥ አይነቶች ደግሞ ቦርዴ፣ ጠላ፣ የማርና የቦርዴ ጠላ ውህድና ሌሎች ተወዳጅ ምግቦችና መጠጦች ይዘጋጃሉ። በ”ዮ--ማስቃላ” በዓል ዕለት የሚቀራረቡ ጎረቤታሞች በጋራ ሆነው አማካይ በሆነ ሥፍራ ላይ የእርድ ሥነሥርዓት ያከናውናሉ። የእርድ ሥነ-ሥርአቱም በደመራው ዕለትና ማግስት እንደ ህብረተሰቡ ይሁንታ የሚፈጸም ይሆናል። ከማግስቱ ጀምሮ የተዘጋጀውን ሥጋ በጋራ እየበሉና እየጠጡ የበዓሉን ድባብ የሚያስቀጥሉ ሲሆን “ዱንግዛ” በተሰኘው የጋሞ ባህላዊ ጥበብ ልብስ ደምቀው በጌጣጌጥ አሸብርቀው ሁሉም በየአደባባዩ በባህላዊ ጫዋታዎች እየተደሰተ በዓሉን ያከብራል። ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነትና አብሮነት ካለ በአዲሱ ዓመት ምድሪቱ ተገቢውን ምርት እንደምትሰጥ ሁሉም ሰው በተሰማራበት መስክ ውጤታማ እንደሚሆን ይታመናል። ከዚም የተነሳ በአሮጌው ዓመት ሃዘን ላይ የነበሩ ወገኖች ሙሉ በሙሉ ሀዘናቸውን በመተው በአዲስ መንፈስ ወደ መደበኛው ህይወት ይመለሳሉ። የተጣሉ ወገኖች ቂም ይዘው አዲስ ዓመትን መሻገር በጋሞዎች ዘንድ ነውር በመሆኑ በባህላዊ ሸንጎ ሥርአት /ዱቡሻ/ በጋሞ አባቶች አሸማጋይነት እርስ በርስ ተነጋግረው በመታረቅ አዲሱን ዓመት በጋራ ያበስሩታል። በሌላ መንገድ “ዮ..ማስቃላ” በዓል ተጠብቆ ወጣቶች የሚተጫጩበት፣ የተጫጩት ደግሞ ጋብቻ የሚከውኑበት እንዲሁም ያገቡት በየገበያው ዕለት “ሶፌ” የሚባል ሥነ-ሥርዓት በማከናወን በማህበራዊ ህይወት ማህበረሰቡን በይፋ የሚቀላቀሉበት መሆኑን ጋሽ አመሌ አውግተውናል። ጋሞዎች ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር በመሆን በአብሮነት ለሁለት ሳምንታት በደስታ ካሳለፉ በኋላ ወደ ግብርና ሥራቸው በመመለስ ቀደም ሲል በክብር ያስቀመጧቸውን የእርሻ መሣሪያዎች በማንሳት ወደ እርሻ ሥራ ይገባሉ። እስከ ታህሳስ ወር መውጫ ድረስ የበዓሉ ድባብ ሳይጠፋ ይቆይና በመጨረሻም የመሰናበቻ ድግስ ወይም “ጮዬ ማስቃላ” በማዘጋጀት በህብረት ከተመገቡና ከጠጡ በኋላ የዓመት ሰው ይበለን፣ ዓመቱ የሰላም፣ የጤና፣ የበረከት ይሁን በማለት በመመራረቅ “ዮ--ማስቃላ”ን ይሸኛሉ። በዓሉ የህዝቡን ሰላም ፣አንድነትና አብሮነት የሚያንጸባርቅ ልዩ በዓል ነው በማለት የጋሞ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ አቶ ሞናዬ ሞሶሌ የጋሞ የሀገር ሽማግሌ የሆኑት የአቶ አመሌ አልቶን ሃሳብ ይጋራሉ። ባህላዊ እሴቱ ከትውልድ ወደ ትውልድ ተጠብቆ እንዲቆይ “ዮ--ማስቃላ” ትልቅ ድርሻ አለው። የባህል እሴቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፉ በጥናትና ምርምር በማስገፍና የቋንቋና ባህል አውደ ጥናት በየዓመቱ እየተደረገ እንደሆነም ነግረውናል። አባቶች በልዩነት ውስጥ ያለንን አንድነት እንዳቆዩልን ሁሉ ወጣቶችም ኢትዮጵያዊ ለዛ ያላቸው የጋራ እሴቶች ሳይበረዙና ሳይከለሱ ጠብቀው ለትውልድ የማስተላለፍ ሃላፊነት አለባቸው የሚለውን የንግግራቸው ማሳረጊያ አድርገዋል።              
የዕልፍ ሕጻናትን ዕጣ ፈንታ ከሞት ወደ ሕይወት የለወጠው ወጣት ላሌ ላቡኮ 
Sep 8, 2023 1213
በሀገራችን በርካታ አካባቢዎች የታዳጊዎችን ተስፋና ህልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የሚገዳደሩ ከባህላዊ እምነት ጋር የተቆራኙ አይነተ ብዙ ጎጂ ባህላዊና ልማዳዊ ድርጊቶች እና ክዋኔዎች አሉ። ለአብነትም ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የተለመደው እና ከህጻናት ጥርስ አበቃቅል ጋር የተያያዘው ’ሚንጊ' የሚሰኘው ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ይጠቀሳል። በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣቸዋል። ከዚህ ጋር በማገናኘትም የሚወለዱ ህጻናት የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ከሆነ እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥመዋል። ይህ ልማድ “ሚንጊ” ተብሎ የሚጠራ ሲሆን አያሌ ህጻናትን ቀጥፏል። ይህ ብቻም ሳይሆን የማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። ሚንጊ ተብለው የተፈረጁ ህጻናት በማህበረሰቡ ዘንድ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… እንደሚያመጡ ስለሚቆጠር ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል ዕጣ ይገጥማቸዋል። ሚንጊንና መሰል በየማህበረሰቡ ዘንድ ለዘመናት የተለመዱ ጎጂ ድርጊቶችን ለማስቀረት እና ማህበረሰብ አቀፍ ለውጥ ለማምጣት ግን ውስብስብ እና ጊዜ የሚጠይቅ ጉዳይ ነው። ላሌ ላቡኮና መሰል ብርቱና አርቆ አሳቢ ሰዎች ግን ባደጉበት ብርቱ ጥረት የማህብረሰብን አስተሳስብ በመለወጥ ለዘመናት ለሚከወኑ ውስብስብ ችግሮችን መፍትኤ መስጠት ችለዋል። ላሌ ላቡኮ በተወለደበት ቀዬ እና አባል በሆነበት ደመ ከልብ ሆነው የሚቀሩ ህጻናትን ዕጣ ፈንታ ከወንዝ፣ ከገደልና ከጫካ ከመጣል ተርፈው ለወግና ማዕረግ እንዲበቁ አስችላል። በአጉል ባህል ሕይወታቸውን የሚነጠቁ ዕልፍ አዕላፍ ህጻናት ነፍስ እንዲዘሩ በማድረግ ትውልድ ያሻገረ፣ ማህበረሰብን የለወጠ አርበኛ ነው። ላሌ ላቡኮ ይህን ነባር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ለመቃወምና መፍትሄ ለማምጣት ያነሳሳው ሁለት እህቶቹን ጨምሮ ምንም ነፍስ ያላወቁ ሕጻናት በሚንጊነት ተፈርጀው ሲቀጠፉ በማየቱና በመስማቱ እንደሆነ ይናገራል። ከ17 ዓመታት በፊት ‘ኦሞ ቻይልድ’ በሚል ባቋቋመው ድርጅት 'ሚንጊ' የተባሉ 58 ሕፃናትን ከገዳዮች ፈልቅቆ ከሕልፈት ወደ ሕይወት ለውጧል፣ ለቁም ነገር ለማብቃትም እያስተማራቸው ይገኛል።   እህቶቹን ጨምሮ የትውልድ መንደሩ ሕጻናትን ሕይወት ለመቀጠፍ የዳረጋቸው የሚንጊ ድርጊት የሚፈጸመው፣ በማህበረሰቡ ዕውቀት ማነስ ነው ብሎ ያምናል። በዚህም ይህን አስከፊ ድርጊት እና አስተሳሰብ ለመቀየር ቆርጦ በመነሳቱ ቤተሰቡን ጨምሮ ከማህበረሰቡ መገለል እስከ ማስፈራሪያ ጥቃቶች አስተናግዷል። እርሱ ግን ፈተናዎች ሳይበግሩት በዓላማው ጸንቶ፣ ትዕግስትና ብልሃት ተላብሶ ሸውራራ ማህበረሰብ አቀፍ አመለካከቶችን መስበር ችሏል። የሚንጊ ባህል አሁንም ሙሉ ለሙሉ እንዳልተቀረፈ የሚናገረው ላሌ፣ ስር ነቀል የአስተሳስብ ለውጥ ለማምጣት ለህብረተሰቡ አሁንም ብርቱ ግንዛቤ የመፍጠር ስራዎች እንደሚገቡ ገልጿል። ላሌ በመሰረተው ድርጅት ከሚማሩ ሕጻናት ባሻገር ከ300 በላይ ህጻናት ከቤተሰባቸው ዘንድ ሆነው ለመማር እንዲችለኩ ማድረጉንም ይናገራል። ሕፃናቱን ከሞት አፋፍ ታድጎ ከራሳቸው ሕልውና ባለፈ ለቁም ነገር እንዲበቁና ለሀገርና ለወገን የሚበጁ ሰዎች እንዲሆኑ በመስራቱ አዕምራዊ እርካታ እንደሚሰማው ይገልጻል። ላሌ የሚንጊን ጎጂ ድርጊት ከመታደጉ በተጨማሪ በደቡብ ኦሞ ትምህርት ቤት ገንብቶ ከ700 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ ይገኛል። ናሽናል ጂኦግራፊ፣ ቴድ ቶክ፣ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም እና የበጎ ሰው ሽልማት ድርጅት የላሌን ትውልድ የመታደግ ተግባር ዕውቅና ከሰጡት ወስጥ ይጠቀሳሉ።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም