ቀጥታ፡

ጠቅላላ ምርጫው የኢትዮጵያን ቀጣይ እድገትና ብልፅግና የምንወስንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው

ገንዳውኃ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን ቀጣይ እድገትና ብልፅግና የምንወስንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳውኃና መተማ ዮሃንስ ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ። 

ካርድ በመውሰድ ለሀገር ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል-የሮቤ ከተማ ነዋሪዎች

በዞኑ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። 

ነዋሪዎቹ ፤7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን እድገትና ብልፅግና ቀጣይነት ስለሚወስን ተመዝግበን የወሰድነውን ካርድ በመጠቀም የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲን እንመርጣለን ብለዋል።

ከመራጮቹ መካከል የገንዳ ውሃ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ኤልሳ አበጋዝ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች የኢትዮጵያን ቀጣይ እድገትና ብልፅግና የሚወስኑበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። 


 

​በዚህም እስካሁን በአካባቢያቸው እየተካሄደ ያለው የቅድመ ምርጫ ተግባራት ሰላማዊና አሳታፊ በሆነ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠሉ የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

​ምርጫው በሰላማዊ መንገድ መንግስት በመመስረት የልጆቻቸውን የወደፊት ተስፋና የሃገሪቱን መጻኢ እድል የሚወስን በመሆኑ ካርድ ከማውጣት ጀምሮ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።

ሌላኛዋ የዚሁ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አስረስ አበበ በበኩላቸው፤ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማጎልበት አስፈላጊ ነው ብለዋል። 

​በምርጫው መሳተፍ ህገ መንግስታዊ መብትን ከመጠቀም ባለፈ ለሀገር ሰላምና ልማት ኃላፊነትን መወጣት መሆኑን በማመን ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ ማውጣታቸውን አንስተዋል። 


 

ምርጫው ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገትን ያረጋግጣል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለጸው ደግሞ በዞኑ የመተማ ዮሃንስ ከተማ ነዋሪ ወጣት በላይነህ ብርሃኑ ነው። የእርሱ ድምጽ ለአገር ግንባታ ያለውን ሚና በመገንዘብ ካርድ ማውጣቱን ገልጿል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም