በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ፖላንድ ደርሷል - ኢዜአ አማርኛ
በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ፖላንድ ደርሷል
አዲስን አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ (World Athletics Indoor Championship) ከመጋቢት 11 እስከ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በፖላንድ ቶሩን ከተማ ይካሄዳል።
በሻምፒዮናው ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ቶሩን ከተማ መድረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
አትሌቶቹ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የመጀመሪያ ልምምዳቸውን ዛሬ እንደሚያደርጉ አመልክቷል።
ልዑካን ቡድኑ 6 አትሌቶች፣አንድ ቡድን መሪ፣አንድ የቴክኒክ ቡድን መሪ እና አንድ አሰልጣኝ ያካተተ ነው።
ነገ በሚጀመረው ውድድር ከ118 ሀገራት የተወጣጡ 674 አትሌቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል።