ቀጥታ፡

ነዳጅን በቁጠባ እንጠቀም - ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018(ኢዜአ)፦ የመዲናዋ ነዋሪዎች ነዳጅን በቁጠባ በመጠቀም ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ወቅት በመካከለኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገራት አቅርቦቱን እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ገልጸዋል።

ችግሩ ተፈትቶ የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት ወደ መደበኛ ሁኔታ እስኪመለስ ድረስ ነዳጅን በቁጠባ መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ስለሆነም የከተማዋ ነዋሪዎች አጫጭር መንገዶችን በእግር በመጓዝ፣ እንዲሁም የብስክሌት አማራጮችን እና የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ትብብር እንዲያደርጉ ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም