ቀጥታ፡

በክልሉ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በጥራትና ፍጥነት እየተገነቡ ነው

ጅግጅጋ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በክልሉ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በጥራትና ፍጥነት እየተገነቡ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ፤ በጅግጅጋ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን 1ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የታይዋን አስፋልት መንገድ የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል።


 

የመንገዱ መገንባት የከተማዋን የተለያዩ አቅጣጫዎች የሚያገናኝ እና የትራንስፖርት ፍሰትን የሚያሳልጥ መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም መንገዱ በተያዘለት ጊዜ በጥራትና ፍጥነት እየተከናወነ ስለመሆኑ በጉብኝታቸው ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል።


 

በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በጥራትና ፍጥነት እንዲጠናቀቁ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

በመሆኑም በከተሞችም ይሁን በገጠር ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም