ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ - ኢዜአ አማርኛ
ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ
አርባምንጭ ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ።
በጋሞ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ በፍጥነት እንዲደርስ የተጀመረው የመንገድ ከፈታ ሥራው በቀጣይ ሶስት ቀናት ይጠናቀቃል
በጋሞ ዞን በተፈጥሮ አደጋ ለተጎዱ ወገኖች እየተደረገ ያለው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል።
መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን ጨምሮ ባለሃብቶችና ሌሎች አካላት በድጋፍ ስራው ላይ ያልተቋረጠ ተሳትፎ እያደረጉ ይገኛሉ።
የግብርና ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ በጋሞ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋ ለደረሰው የህይወት መጥፋትና የሃብት ውድመት የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል።
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ፤ ሚኒስቴሩ በተፈጥሮ አደጋው ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ከ35 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።
ሚኒስቴሩ ካደረገው የ35 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በተጨማሪ ሁለት ፒክ አፕ ተሽከርካሪዎችን መለገሱን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ችግሩን በጥናት ላይ በመመስረት በዘላቂነት ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ሚኒስቴሩ ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት የበኩሉን እንደሚወጣም አቶ አዲሱ አረጋግጠዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በበኩላቸው፤ ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ በክልሉ ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በህይወት የተረፉ ወገኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም የአጭር እና የረዥም ጊዜ ዕቅድ አውጥተን እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።
በተመሳሳይም የኤም ኤስ አይ (ማሪ ስቶፕስ) ኢትዮጵያ 3 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የተለያዩ ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን የድርጅቱ ካንትሪ ዳይሬክተር አበበ ሽብሩ (ዶ/ር) ገልጸዋል።
ሜሪ ጆይ ኢትዮጵያ የአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ በበኩሉ 100 ሺህ ብር እና የ50 ሺህ ብር ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
እንዲሁም ተልዕኮ ለትውልድ ቤተክርስቲያን በአርባ ምንጭ እና በወላይታ ሶዶ ቅርንጫፎች በጋራ የ100 ሺህ ብር ድጋፍ ማድረጉን የቤተክርስቲያኗ ባለ ራዕይ ዘላለም ጌታቸው ገልጸዋል።