ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
Oct 3, 2026 1
አዲስ አበባ፣መስከረም 23/2019 (ኢዜአ):-የዘንድሮው የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በባህላዊ አልባሳት አጊጠው ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ በርካታ ሰዎች በዓሉ ወደሚከበርበት ወደ ኢሬቻ ፓርክ እያቀኑ ይገኛል። በበዓሉ አከባበር ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ አባ ሙዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ታድመዋል፡፡ የበዓሉ ታዳሚዎችም የኦሮሞ ሕዝብን ባህል በሚያንጸባርቁ አልባሳትና ጭፈራዎች ታጅበው በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ። የኦሮሞ ገዳ ስርዓት አንድ አካል እና መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እየተከበረ ነው። የ2019 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ነው።
የአፋር ክልል ምክር ቤት የተለያዩ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ
Oct 2, 2026 153
ሰመራ ፤መስከረም 22/2019 (ኢዜአ)፦ የአፋር ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰመሠተዳድር አወል አርባ ያቀረቡትን የክልሉን የስራ አስፈፃሚ አካላትን ሹመት ተቀብሎ አፅድቋል። የአፋር ክልል ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 7ኛ የምርጫ ጊዜ 1ኛ የሥራ ዘመን የመንግሥት ምስረታ ጉባኤ የተለያዮ ሹመቶችን በማፅደቅ ተጠናቋል። እንዱሁም ጉባዔው የአፋር ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ስራ አመራር ቦርድ አባላትን ሰይሟል። በዚህም መሠረት ፦ 1. አቶ ሐሚድ ዱላ -ምክትል ርዕሰ መሥተዳድርና እና መሬት ቢሮ ኃላፊ - 2. አቶ ወልኦ አይትሌ - የመንግስት ተጠሪ 3. መሐመድ አህመድ ዓሊ - የፐለቲካ ዘርፍ ኀላፊ 4. ኢብራሂም ዓሊ ዑስማን - የአሰተዳደር ዘርፍ ኀላፊ 5. አቶ አህመድ ሁሴን መሐመድ -በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የመልካም አስተዳደር ክላስተር አሰተባባሪ እና የመንግስ ልማት ድርጅቶች ኤጀንሲ ኃላፊ 6. አቶ ዓሊ መሐመድ መህሙድ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ 7. አቶ አሕመድ እብራሂም ዑመር - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ 8. አቶ መሐመድ ሑሴን ዓሊሳ - የሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ 9. አቶ አሕመድ መሐመድ ቦዳያ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ 10. አቶ ዑመር ኑር አርባ - የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ 11. ጎዖቦ አባካ -የክልሉ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ 12. አቶ ዓሊ ዜይኑ አብዱሰመድ - የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ 13. አቶ ሐንፈሬ አሊሚራህ ሐንፈሬ - የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 14. አቶ ወለዕ ዊቲካ ዑንዴ - የክልሉ መስኖና ተፋሰስ ልማት ቢሮ ኃላፊ 15. አቶ መሐመድ አሕመድ ዓሊ - የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ ያሲን ሐቢብ አሕመድ - የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ 17. ወይዘሮ አሲያ ከማል ዩሱፍ - የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ 18. አቶ ኢብራሂም መሐመድ ዓሊ - የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ 19. አቶ አሊ ባሂኔ አሊ - የማአድን ልማት ቢሮ 20. ኢንጂነር ያሲን ዓሊ ዑስማን - የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ 21. አቶ አሕመድ ሑመድ አብደላ - የክልሉ ሠላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ 22.አቶ አሕመድ ሻሚ ኡመር - የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ 23. ወይዘሮ አሚና ሴኮ ቢዳሩ - የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ 24. ወይዘሮ ኤይሣ ያሲን - የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ 25. አቶ አሕመድ አብዱልቃድር - የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 26. አቶ አወል አብዱ አወል - የክልሉ ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ ኃላፊ 27. አቶ መሐመድ ዓሊ ቢዕዶ - የክልሉ መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ 28. አቶ አስኬር መሐመድ - የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም የክልሉ ዞኖች አመራሮች 29. አቶ ናስር ሀመዱ ናስር - የአውሲ ረሱ ዞን አስተዳደር 30. አቶ መሐመድ ሙሳ - የኪልበ ቲረሱ ዞን አስተዳደር 31. አቶ ሁሴን መሐመድ - የገቢረሱ ዞን አስተዳደር 32. አቶ ሑሴን መሐመድ ዘሀብ - የፈንቲረሱ ዞን አስተዳደር 33.አቶ አሊ ማቴ - የሀሪ ረሱ ዞን አስተዳደር 34. አቶ ማቴ ሑመድ - የማሂረሱ ዞን አስተዳደር የአፋር ብዙሃን መገናኛ የቦርድ አመራር አቶ መሐመድ ዓሊ ቢኢዶ - የቦርዱ ሰብሳቢ ወ/ሮ ኤይሻ ያሲን - ፀሓፊ አቶ አሕመድ ሑመድ አብደላ - አባል አቶ አሕመድ መሐመድ ቦዳያ - አባል
ብሔራዊ ጥቅም - የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ቀይ መስመር
Oct 2, 2026 245
ትልቅ ሀገር ፤ ትልቅ ሕዝብ ፣ ታላቅ ርዕይ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ባለው የረዥም ዘመን ታሪክ በተለያዩ ታሪካዊ፣ ጂኦፖለቲካዊና ውስጣዊ የፖለቲካ ሁነቶች ውስጥ አልፏል። የዓለም መንግሥታት ማኅበር ፣ በመቀጠልም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች አባል በመሆን ለዓለም አቀፍ ሕግ የበላይነት፣ ለሉዓላዊነትና ለጋራ ደህንነት መከበር የጸና አቋም ስትሟገት ቆይታለች። በዚህ መርህ መሰረት ባደረገ ዲፕሎማሲያዊ አካሄዷ፣ ኢትዮጵያ ለፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መጠናከር፣ ለቀጣናዊ ወንድማማችነት እንዲሁም ለአፍሪካ ሀገራት የነፃነት ትግል ትልቅ ድጋፍ በማድረግ የአህጉሪቱ የነፃነትና የአንድነት ምልክት መሆን ችላለች። የዚህ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ውጤት በመሆንም፣ መዲናዋ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት (የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት) እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቷ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከልነቷን አስመስክራ ቀጥላለች። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ታሪክ ከህልውና፣ ነጻነት እና ብሔራዊ ጥቅሟን ከማስከበር ጋር ተሳስሮ የዘለቀ የጽናት ጉዞ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለብሔራዊ ጥቅሟና ለሉዓላዊነቷ የማይደራደር ቀይ መስመር በመዘርጋት፣ የጂኦፖለቲካዊ ውጣ ውረዶችን በብልሃትና በጽናት ስትሻገር ቆይታለች። በዚህም መስመር ለዘመናት በዓለም አቀፍ መድረኮች ጥቅሞቿን አስጠብቃለች። ለሌሎች ጥቅምም ቆማለች። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ስኬት ሆኖ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል ነው። ይህ ድል፣ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት ከመሆኑ ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ እኩል ሀገር እንድትታይና የዲፕሎማሲያዊ ገዢነት ምሳሌ እንድትሆን አድርጓታል። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ ከረጅም ታሪካዊ መሠረቱና የፓን-አፍሪካኒዝም ማዕከልነቱ ባልተራቀቀ መልኩ፣ አሁን ባለንበት ዘመን አዲስ የልማት፣ የሉዓላዊነትና የስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ ምዕራፍ ውስጥ ይገኛል። የመደመር መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት መርሆዎች በአዲስ መነቃቃት ላይ ይገኛል። የዚህ አዲስ የዲፕሎማሲ እይታ ዋና መሠረት ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ጥቅምንና ሉዓላዊነትን ቀይ መስመር ያደረገ፣ ነገር ግን ለጎረቤት ሀገራት ሰላም፣ ልማትና የጋራ እድገት ቅድሚያ የሚሰጥ ተግባራዊ አቀራረብ ነው። የመደመር መንግስት ዲፕሎማሲ አብሮ የመበልጸግ ፅንሰ-ሐሳብን ያቀነቅናል። ኢትዮጵያ ሰላምና ልማት የሚረጋገጠው ጎረቤቶቿ ሰላምና ልማት ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ በማመን "ቅድሚያ ለጎረቤት" የሚል መርህ ይከተላል። ይህ መርህ ከቀደመው ባህላዊ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ተሻግሮ ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ፣ ንግድና መሠረተ-ልማት ትስስር ተቀይሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጎረቤት ሀገራት መሪዎች በተለይም በቅርቡ ከኬኒያና ከጂቡቲ መሪዎች ጋር ያደረጓቸው ውይይቶች የአፍሪካ ቀንድን የማስተሳሰር ጥረት ማሳያ ናቸው። ይህ የኢኮኖሚ ትስስር በተጨባጭ የሚገጥም ጭምር ነው። ኢትዮጵያ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬኒያ፣ ለጂቡቲና ለሱዳን በማቅረብ ቀጣናውን በኢነርጂ ድልድይ አስተሳስራለች።አዲስ አበባን ከጂቡቲ ወደብ የሚያገናኘው የባቡር መስመርና ወደ ኬኒያ (ላሙ ወደብ) የሚያቀኑት የላፕሴት (LAPSSET) ኮሪደር ፕሮጀክቶች የንግድ ፍሰቱን ለማሳለጥ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው።የጋራ የውሃ ሀብቶችን በጋራ የመጠቀምና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ቀጠናዎችን የማስፋፋት ሥራዎች ተከናውነዋል። ነገር ግን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስከብሩ አበይት አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የማትንበረከክና የማታወላውል አቋም አላት።ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊና የዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች ቢኖሩበትም፣ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብቷን በማስከበር የግድቡን ግንባታና የውሃ ሙሌት በውጭ ጫና ሳታቋርጥ ከፍጻሜ አድርሳለች። ለዘመናት የቆየውን ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ መሠረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ ዘላቂና ሕጋዊ የባህር በር ፍላጎቷን በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነትና ግዛት አንድነቷን በተግባር የተጻረሩና አላስፈላጊ ጫናዎችን ለመጫን የሞከሩ አካላትን ዓለም አቀፍ ሕግንና ደንብን መሠረት ባደረገ መልኩ የመመከትና ምላሽ ለመስጠትም ወደ ኋላ የማትል መሆኗን በተግባር አሳይታለች።
አዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓልን የሚታደሙ እንግዶችን እየተቀበለች ነው
Oct 2, 2026 159
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22/2019(ኢዜአ):- አዲስ አበባ ነገ በሚከበረው ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓልን የሚታደሙ እንግዶችን እየተቀበለች ነው። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ያላት ናት። ይህን ታላቅነቷን ከሚያረጋግጡ ሀብቶቿ መካከል ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶቿ፣ ባህሎችና የቱሪስት መስህቦቿ ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ መካከልም ከገዳ ስርዓት የሚመነጨው ኢሬቻ አንዱ ነው። ኢሬቻ በየዓመቱ በልዩ ልዩ ኹነቶች በአደባባይ የሚከበር ሲሆን፤ ዘንድሮም ነገ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ላይ የሚታደሙ ተሳታፊዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች ህብረ ዝማሬዎች በማሰማት እና ልዩ ልዩ ባህላዊ ክዋኔዎችን በማሳየት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ። የኢዜአ ሪፖርተሮች በአዲስ አበባ ቅኝት ባደረጉባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ነገ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበረውን ኢሬቻ በዓል ለመታደም የመጡትን እንግዶችን ከተማዋ እየተቀበለች ነው። በበዓሉ ላይ የሚታደሙ እንግዶች የጤና እና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚያገኙባቸው አካባቢዎችም ተዘጋጅተው ወደ ስራ ገብተዋል።
ፖለቲካ

ከአባይ እስከ ቀይ ባህር - የኢትዮጵያ አይበገሬነት እና የግብጽ ሴራ
Oct 2, 2026 312
ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ጉዞዋ የብዙ ውጫዊ እና ውስጣዊ ፈተናዎች ማዕከል ሆና የቆየች ሀገር ናት።ሀገሪቱ ያሏትን ተፈጥሮአዊ ሀብቶች እንዳትጠቀም ፣የጂኦፖለቲካዊ አሰላለፍ ውስጥ የሚገባትን ቦታ እንዳትይዝ ለዘመናት የተደራጀ እና የተቀናጀ ሴራ እና ጫና ሰለባ ሆናለች። ከእነዚህ ዘመናትን ከተሻገሩ ሴራዎች ጀርባ ደግሞ ግብጽ ትገኛለች። የግብፅ አቋም እና የውጭ ፖሊሲ በዋናነት የሚያተኩረው የዓባይን ወንዝ ውኃ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የተረጋጋች፣ጠንካራ እና በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያ እንዳትፈጠር በማድረግ ላይ ነው። ግብፅ ይህን ዓላማዋን በተለያዩ ጊዜያት በቀጥታ በጦርነት ለማስፈጸም ያደረገችው ጥረት በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ሽንፈት ተከናንባ እንድትመለስ አድርጓታል።ይህ አልሳካ ሲላት ደግሞ የኢትዮጵያን የውስጥ ተቃዋሚዎች እና አማጺ ቡድኖችን በመደገፍ ሀገሪቱን የማዳከም ስልት ስትከተል ኖራለች። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ባሉት አስርት ዓመታት፣ ግብፅ በአፍሪካ እና በአረብ ዓለም ውስጥ ተፅዕኖዋን ለማስፋት ስትጥር፣ የዓባይ ተፋሰስን እና ቀይ ባሕርን ለደህንነቷ እንደ ዋና መሠረት አድርጋ ተመልከታቸዋለች።ኢትዮጵያ፣ በዓባይ ወንዝ ላይ ያለች ትልቅ እና እየጎለበተች ያለች ሀገር በመሆኗ በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም ሴራዋን አጠናከረች።ለዚህም ዓላማ ስኬት በሰሜን ኢትዮጵያ የተዳፈነ እሳት ማስቀመጥ ነበረባት።ኤርትራን ለመገንጠል፤ ጉዳይ ፈጻሚውን ሻዕቢያን መመስረት ግቧ አደረገች። የኤርትራ ነፃነት ግንባር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1960 በካይሮ በተሰደዱ የኤርትራ ፖለቲከኞች እና ተማሪዎች ተመሠረተ። በዚህ ሂደት ግብፅ የኤርትራ የመገንጠል እንቅስቃሴ እንዲፋጠን ፖለቲካዊ ምህዳር የፈጠረች ሲሆን፣ የግብፅ ሚዲያዎች ደግሞ ለእዚህ እኩይ ዓላማ የሚያግዝ ፕሮፓጋንዳ አሰራጮች ነበሩ። በዚህ አሰላለፍ ውስጥ ሻዕቢያ የግብፅ ዋና ስትራቴጂካዊ መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል። ግብፅ ለሻዕቢያ አስፈላጊውን ወታደራዊ፣ የገንዘብ እና የዲፕሎማሲያዊ ሽፋን በመስጠት በሰሜን ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ለተካሄደው ውጊያ ስንቅ እና ትጥቅ እንዲያገኝ አድርጋለች። የኤርትራ መገንጠል ዋነኛ ውጤት ኢትዮጵያ ታሪካዊ የባህር በሮቿን አጥታ የተዘጋች ሀገር እንድትሆን ማድረግ ነበር። ይህ ደግሞ የግብፅን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ያሳካ እርምጃ ሆኗል። ለዚህ እኩይ ዓላማ ለተወለደው ቡድን ደግሞ ቀጥተኛ የገንዘብ፣ የወታደራዊ እና የስልጠና ድጋፍ የመስጠት ፖሊሲን ተከትላለች።በግብፅ ስሌት፣ ለእንደዚህ ዓይነቶቹ አካላት የሚደረገው ድጋፍ በተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት ላይ ጫና ለመፍጠር ይረዳል የሚል ነው።በመጠኑ የተሳካለት ቢመስልም ያሰበችውን ማግኘት አልቻለችም።ብርቱዋ ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አሳክታ አጀንዳዋን ቀይ ባህር ላይ አድርጋለች። ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ፖለቲካዊ ጫና እንደ ጠቃሚ መንገድ አድርጋ ቀጠለችበት። ግብፅ ከሻዕቢያ ባለፈ ለሀገር ውስጥ ታጣቂዎች ድጋፍ በመስጠት የተወሰኑ የትንኮሳ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ ረድታለች። አስመራ በታሪክ በተረጋገጠ መልኩ የፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎች ሁሉ መነሻ እና ማዕከል ሆና አገልግላለች። ስውሩ ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን መተግበር እንዳትችል አደረጋት። የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን ከማድረግ አንጻር የራሱን መጥፎ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። አሁንም ግብጽና ሻዕቢያ በቀረጹት ኢትዮጵያን የማዳከም ሥራ ላይ ሕገ-ወጡ ሕወሓት በዋና ተላላኪነት እና ጉዳይ ፈጻሚነት ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ሕወሓት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በሻዕቢያ የፖለቲካ እና የወታደራዊ ሥልጠና ሲያገኝ ነበር።ሕወሓት ሥልጣን በያዘበት ወቅት፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ የባሕር በር ባለቤትነት መብት ከሕግ አግባብ ውጭ አሳልፎ በመስጠት የሻዕቢያን እና የግብፅን ዓላማ በተሻለ መልኩ አሳክቷል። ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ ምክንያት በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለወደብ ኪራይ እንድታወጣ ተገዳለች። ይህም የኢኮኖሚ እድገቷን የገታ እና ለውጭ ጥገኝነት የዳረጋት ዋነኛ ምክንያት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ ኢትዮጵያ የነበራትን ታሪካዊ እና ስትራቴጂካዊ የበላይነት እንድታጣ አድርጓታል። የውስጥ አለመረጋጋት እና ጦርነቶች ዓባይን ጨምሮ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቿን በጊዜው እንዳትጠቀም እንቅፋት ሆነው ቆይተዋል። አሁንም ቢሆን ግብፅ ከኢትዮጵያ አልፋ የአፍሪካ ቀንድን ወደ አንድ ግዙፍ የጦር ሜዳ ለማሸጋገር ለሚሰሩ ወገኖች ይፋዊ ወታደራዊና የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት ቀጣናዊ ስጋት መደቀኗን ቀጥላበታለች።] ኢትዮጵያ ለዘመናት በወራሪዎችና በውጭ ተጽዕኖዎች ሳትንበረከክ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረችበት ምስጢር፣ ታሪካዊ ጥንካሬዋንና የሕዝቦቿን አንድነት መሠረት ባደረገ ጽናት ነው። ግብፅ የኢትዮጵያን ግዛት ለመያዝ ያደረገቻቸው ተደጋጋሚ የወረራ ሙከራዎች በጉራዕና በጉንደት አውደ ውጊያዎች በኢትዮጵያውያን ጀግንነት ተመክተዋል። በተመሳሳይ መልኩ በዓለም አቀፍ መድረኮች፣ በወገንተኛ ሚዲያዎችና በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ለዘመናት ሲሰራጩ የቆዩ ሀሰተኛ መረጃዎችና የሳይኮሎጂካል ጦርነቶች በኢትዮጵያ እውነተኛ ዲፕሎማሲ ተሸንፈዋል ። አሁንም የግብፅና የኤርትራ (የሻዕቢያ) ወቅታዊ ስትራቴጂካዊ አሰላለፍም ሆነ የሕወሓት ተላላኪነት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጊዜያዊ ፈተናዎች ሆነው የሚያልፉ አኩይ ተግባራት እንጂ የኢትዮጵያን የሺህ ዓመታት የሀገርነት መሠረት ሊያናጉ አልቻሉም። ከዚህ አኳያ ያለፈውን ታሪክ በጥልቀት መረዳት፣ የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ መገንዘብና የጥፋት አሰላለፎችን ማወቅ የዛሬዋንና የነገዋን የበለጸገችና የተከበረች ኢትዮጵያ ለመገንባት፣ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ወሳኝና መተኪያ የሌለው መንገድ ነው። ኢትዮጵያ ለታሪካዊ ጠላቶቿ በየትኛውም መልኩ የማትንበረከክ ጽኑ አገር መሆኗን ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ታረጋግጣለች!
አቶ ኦርዲን በድሪ ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጡ
Oct 2, 2026 202
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ) ፦ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ከመስከረም 21/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል። በዚሁ መሠረት፦ 1ኛ ወይዘሮ ረምዚያ አብዱልወሃብ ቴክኒክና ሞያ ትምህርት እና ስልጠና ኤጀንሲ ኃላፊ 2ኛ ወይዘሮ ፈቲያ ሳኒ የሴቶችና ህጻናት ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ምክትል ሀላፊ 3ኛ ወይዘሮ ፈሪሃ መሀመድ የሀረር ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምክትል ዲን 4ኛ አቶ ታመነ ፍቃድ የብቃት ማረጋገጫ ማዕከል ኃላፊ 5ኛ አቶ ረኢስ ዩሱፍ የሀረር ማዘጋጃ ቤት ምክትል ኃላፊ 6ኛ ኤልያስ ዩኒስ የሀረሪ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ኃላፊ 7ኛ ዶ/ር አብዱልሀኪም ኢምራን ጀጎል ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ 8ኛ ወይዘሮ ሙና ኢስሀቅ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ባለስልጣን ኃላፊ 9ኛ አቶ ሰሚር አብዱላሂ ኢንተርፕራይዝ ልማት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ምክትል ኃላፊ 10ኛ አቶ አብዱልሀፊዝ አህመድ የሀረሪ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ኃላፊ 11ኛ አቶ ኤልያስ አብዱረህማን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ኃላፊ 12ኛ አቶ አብዱልሀኪም አብዱማሊክ የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ አደረጃጀት ጉዳይ አማካሪ 13ኛ አቶ ኃይለጊዮርጊስ መገርሣ የርዕሰ መስተዳድሩ የኢኮኖሚ አማካሪ ሆነው ተሹመዋል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የአስፈጻሚ አካላት ሹመት አጸደቀ
Oct 2, 2026 301
አርባምንጭ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ)፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ያቀረቧቸውን የአስፈጻሚ አካላት ሹመት ተቀብሎ አጸደቀ። የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት መስራች ጉባኤውን በአርባ ምንጭ ከተማ እያካሄደ ይገኛል። በዚሁ ወቅትም የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) አዲስ ለተመሰረተው የክልሉ ምክር ቤት ያቀረቧቸውን የአስፈጻሚ አካላት ሹመት ምክር ቤቱ ተቀብሎ አጽድቋል። በዚህም መሰረት፡- 1ኛ. ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) - የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ 2ኛ. ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ 3ኛ. አቶ ንጋቱ ዳንሳ - በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የትራንስፖርትና መንገድ ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ 4ኛ. ካርታ ካስኬ (ዶ/ር) - የግብርና ቢሮ ኃላፊ 5ኛ. አቶ ዳዊት ደሳለኝ - ጤና ቢሮ ኃላፊ 6ኛ. ወ/ሮ ወይኒቱ መልኮ - የክልሉ ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ 7ኛ. መስፍን መንዛ (ዶ/ር) - የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ 8ኛ. አቶ ሃይለማሪያም ተስፋዬ - የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ኃላፊ 9ኛ. አቶ ብርሃኑ ዘውዴ - የክልሉ ሲቪል ሠርቪስ ኮሚሽን ኃላፊ 10ኛ. አቶ ተፈሪ አባቴ - የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ 11ኛ. አቶ ታደለ ወልደሚካኤል - የክልሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ኃላፊ 12ኛ. ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) - የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ 13ኛ. አቶ መንግስቱ በየነ - ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ 14ኛ. አቶ ኤኬል ነትር - የክልሉ መስኖና ቆላማ ቢሮ ኃላፊ 15ኛ. ወ/ሮ አለምነሽ ደመቀ - ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ 16ኛ. አቶ ሙሉቀን ታደሰ - የክልሉ ፍትህ ቢሮ ኃላፊ 17ኛ. ኢንጂነር ፍሬዘር ኮርባይዶ - የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ 18ኛ. አቶ አቤነዘር ተረፈ - የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ 19ኛ. አቶ ተወልዴ ተስፋዬ - የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ 20ኛ. አልማዝ ባልታ (ዶ/ር) - የክልሉ ፕላን ልማት ቢሮ ኃላፊ 21ኛ. ሰለሞን ቡኬ (ዶ/ር) - የክልሉ ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ 22ኛ. አቶ ወንድማገኝ ደግፈ - የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሹመው ቃለ-መሐላ ፈፅመዋል። በተጨማሪም አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ፣ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር) የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የፖለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ እንዲሁም አቶ ተስፋዬ ደፋሩ ደግሞ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው ተመድበዋል።
የዘላቂ ሰላም ግንባታና የልማት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ የጋራ አጀንዳችን ነው
Oct 2, 2026 230
ጎንደር፣ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ) ፡-የሀገር ብሄራዊ ጥቅም፣የዘላቂ ሰላም ግንባታና የልማት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ የጋራ አጀንዳችን ነው ሲሉ የጎንደር ከተማና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ተገን ደረጀ ገለፁ። በጎንደር ከተማና አካባቢው የሚንቀሳቀሱ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የውይይት መድረክ አካሒደዋል። ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የጎንደር ከተማና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ሰብሳቢ ተገን ደረጀ፤ በጎንደር ከተማ እና አካባቢው በመከናወን ላይ የሚገኙ ዘርፈ ብዙ የልማት ስራዎችን አድንቀዋል። በተለይም የኮሪደር ልማት፣ የመሶብ አንድ ማእከል አገልግሎት፣ የቅርሶች እድሳትና ጥበቃ እንዲሁም ሌሎች ልማቶችን በማንሳት እመርታና ስኬት የተመዘገበበት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም የሀገር ብሄራዊ ጥቅም፣ የዘላቂ ሰላም ግንባታና የልማት ጉዳይ ለድርድር የማይቀርብ የጋራ አጀንዳችን በመሆኑ በአብሮነትና በትብብር እንሰራለን ብለዋል። በጎንደር ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ስራ አስፈጻሚ አቶ ዝናህወርቅ ታደሰ፤ በበኩላቸው የሀገር ልማትና እድገት የሚረጋገጠው በዜጎች ሁለንተናዊ ትብብርና ትጋት መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም በፖለቲካ ረገድ የሃሳብ ልዩነት ቢኖርም በሀገር ሉአላዊነት፣ በልማትና በሰላም ግንባታ ዙሪያ ያለምንም ልዩነት መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል። በዚህም ፓርቲያቸው ጠንካራ አቋም ያለው መሆኑን አንስተው ለሀገር ሰላም፣ ልማትና የዜጎች ተጠቃሚነት ይበልጥ ተቀራርበን እንሰራለን ሲሉ አረጋግጠዋል። በብልፅግና ፓርቲ የጎንደር ከተማ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ምትኩ አንዳርጌ፤ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሰላም፣ በልማትና በብሄራዊ ጥቅም ላይ ከመንግስት ጋር በመተባበርና ይበልጥ በመቀራረብ እንዲሰሩ ጠይቀዋል። በከተማዋ እየተካሄደ ያለውን ልማትና ዘላቂ ሰላም አጠናክሮ ለማስቀጠል የውስጥ አንድነትን ማጠናከር ወሳኝ መሆኑን አንስተዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፣ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ የወጣቶች ማህበራትና የከተማ አስተዳደሩ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክርቤት የተለያዩ የካቢኔ አባላት ሹመት አፀደቀ
Oct 2, 2026 246
ታርጫ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ )፡-የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ምክር ቤት የክልሉ ርዕሰመሠተዳድር አቶ ፍቅሬ አማን ያቀረቡትን የክልሉን የስራ አስፈፃሚ አካላትን ሹመት ተቀብሎ አፅድቋል። በዚህም መሠረት 1. ወ/ሮ ሕይወት አሰግድ፦ የክልሉ ንግድና ኢንቨስት መንግ ቢሮ ኃላፊ 2. አቶ የሺዋስ ዓለሙ፦የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ 3. ኢንጂነር በየነ በላቸዉ፦ የክልሉ ዉሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ 4. አቶ እንዳሻዉ ከበደ፦ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ 5. አቶ ፋንታሁን ብላቴ፦ የክልሉ ስራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ 6. አቶ ሰለሞን ካሳሁን፦ የክልሉ ባህል፣ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ 7. ወ/ሮ ሀሲያ አሊ፦ የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ 8. አቶ ሀብታሙ ካፍቴን፦ የክልሉ ደን፣አካባቢ ጥበቃና አየር ንብረት ለዉጥ ቁጥጥር ቢሮ ኃላፊ 9. አቶ ሙሉጌታ ወ/ሚካኤል፦ የክልሉ ጤና ቢሮ ኃላፊ 10. አቶ በድሉ መዓዛ፦ የክልሉ ቆላማና አርብቶ አደር ቢሮ ኃላፊ 11. አቶ ዘመድኩን ሰለሞን፦ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ 12. አቶ በላይ ተሰማ፦ የክልሉ ከተማልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ 13. አቶ አንድነት አሸናፊ፦ የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ 14. አቶ ተመስገን ከበደ፦ የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ 15. ወ/ሮ አሰለፈች መብራቱ፦ የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ 16. አቶ ፌልታሞ ዲብሎ ፦ የክልሉ መንገድ ልማትና ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ 17. ወ/ሮ ቤተልሔም ዳንኤል፦ የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ኃላፊ ተሿሚዎቹ በምክር ቤቱ ፊት ቀርበዉ ቃለመሃላ ፈፀመዋል

ማህበራዊ
የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው
Oct 3, 2026 1
አዲስ አበባ፣መስከረም 23/2019 (ኢዜአ):-የዘንድሮው የሆረ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓል በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው። በበዓሉ ላይ ለመታደም ከተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች በባህላዊ አልባሳት አጊጠው ወደ አዲስ አበባ የተጓዙ በርካታ ሰዎች በዓሉ ወደሚከበርበት ወደ ኢሬቻ ፓርክ እያቀኑ ይገኛል። በበዓሉ አከባበር ላይ አባ ገዳዎች፣ አባ መልካዎች፣ አባ ሙዳዎች፣ ሃደ ሲንቄዎችና ወጣቶችን ጨምሮ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ታድመዋል፡፡ የበዓሉ ታዳሚዎችም የኦሮሞ ሕዝብን ባህል በሚያንጸባርቁ አልባሳትና ጭፈራዎች ታጅበው በድምቀት እያከበሩ ይገኛሉ። የኦሮሞ ገዳ ስርዓት አንድ አካል እና መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በዓል እሴቱን በጠበቀ መልኩ በድምቀት እየተከበረ ነው። የ2019 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሃሳብ እየተከበረ ነው።
አዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓልን የሚታደሙ እንግዶችን እየተቀበለች ነው
Oct 2, 2026 159
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22/2019(ኢዜአ):- አዲስ አበባ ነገ በሚከበረው ሆራ ፊንፊኔ የኢሬቻ በዓልን የሚታደሙ እንግዶችን እየተቀበለች ነው። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ያላት ናት። ይህን ታላቅነቷን ከሚያረጋግጡ ሀብቶቿ መካከል ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶቿ፣ ባህሎችና የቱሪስት መስህቦቿ ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ መካከልም ከገዳ ስርዓት የሚመነጨው ኢሬቻ አንዱ ነው። ኢሬቻ በየዓመቱ በልዩ ልዩ ኹነቶች በአደባባይ የሚከበር ሲሆን፤ ዘንድሮም ነገ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። ሆራ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ላይ የሚታደሙ ተሳታፊዎች በተለያዩ አቅጣጫዎች ህብረ ዝማሬዎች በማሰማት እና ልዩ ልዩ ባህላዊ ክዋኔዎችን በማሳየት ወደ አዲስ አበባ እየገቡ ይገኛሉ። የኢዜአ ሪፖርተሮች በአዲስ አበባ ቅኝት ባደረጉባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ነገ በሆራ ፊንፊኔ የሚከበረውን ኢሬቻ በዓል ለመታደም የመጡትን እንግዶችን ከተማዋ እየተቀበለች ነው። በበዓሉ ላይ የሚታደሙ እንግዶች የጤና እና ሌሎች አገልግሎቶችን የሚያገኙባቸው አካባቢዎችም ተዘጋጅተው ወደ ስራ ገብተዋል።
ኢሬቻ የአንድነትና የእርቅ እሴትን የሚያጠናክር ነው – አባ ገዳዎች
Oct 2, 2026 220
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22/2019(ኢዜአ):- ኢሬቻ የአንድነት፣ የፍቅር፣ የይቅርታና የሰላም እሴቶችን ለማጠናከር አስተዋጽኦው ከፍተኛ መሆኑን አባ ገዳዎች ገለጹ። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ያላት ሀገር ናት። ይህን ታላቅነቷን ከሚያረጋግጡ ሀብቶቿ መካከል ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶቿ፣ ባህሎችና የቱሪስት መስህቦቿ ተጠቃሽ ናቸው። ከእነዚህ ባህላዊ ሀብቶቿ መካከል ደግሞ ከገዳ ስርዓት የሚመነጨው የኢሬቻ በዓል ተጠቃሽ ነው። ኢሬቻ በየዓመቱ በልዩ ልዩ ሁነቶች በአደባባይ የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ነገ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም ከነገ በስትያ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። የበዓሉን አከባበር በተመለከተ ኢዜአ ያነጋገራቸው አባ ገዳ ጉጂ ጃርሶ ዱጎ፣ ኢሬቻ ማህበረሰቡ ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት፣ ይቅር የሚባባልበትና በጋራ የሚመካከርበት የአንድነት በዓል ነው ብለዋል። በዘንድሮው ኢሬቻ በተለይ የአንድነትና የፍቅር መልዕክቶች የሚንጸባረቁበት መሆኑን ጠቁመው፤ የበዓሉ ታዳሚዎች በአንድነት መንፈስ ማክበር እንዳለባቸው ገልጸዋል። ከባሌ ዞን የመጡት አባ ገዳ አብዱባሻ መሐመድ በበኩላቸው፣ ኢሬቻ ባህልንና ታሪክን ከማስተዋወቅ ባሻገር ለቱሪዝምና ለኢኮኖሚ እድገት ያለውን አስተዋፅኦ ጠቁመዋል። ኢሬቻ ከሀገር ውስጥና ከውጭ የሚመጡ ጎብኚዎችን በማሰባሰብ የባህል ልውውጥንና የቱሪዝም እንቅስቃሴን ለማሳደግ አቅም እንዳለውም ገልጸዋል። ኢሬቻ ከአባቶችና ከእናቶች የተላለፈ የምስጋና ባህል መሆኑን ጠቅሰው፣ ሰዎች ወደ ኢሬቻ ከመምጣታቸው በፊት ከተቀያየሙት ሰው ጋር ይቅርታና እርቅ በመፈጸም ማክበር እንደሚገባ ያስገነዘቡት ደግሞ አባ ገዳ አዲሱ ሽብሩ ናቸው። አባ ገዳዎቹ እንደገለጹት የኢሬቻን የአብሮነትና የፍቅር እሴቶችን ለቀጣዩ ትውልድ በማስተላለፍ ባህሉን ማስቀጠል ይገባል።
በክልሉ እድሜያቸው የደረሰ ህፃናትን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት መረባረብ ያስፈልጋል
Oct 2, 2026 171
ባህር ዳር፣ መስከረም 22/2019(ኢዜአ):- በአማራ ክልል ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ሕፃናትን ወደ ትምህርት ገበታ ለማምጣት ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን እንዲወጡ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ጥሪ አቀረቡ። ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ አረጋ ከበደ በጉባኤው ማጠናቀቂያ እንዳሉት፤ በክልሉ የመማር ማስተማር ሥራውን ምቹና የተሻለ ለማድረግ የንቅናቄ ሥራ ተጀምሯል። ለዚህም በክልሉ ከጸጥታ ጋር በተያያዘ በመማር ማስተማር ሥራው ላይ የደረሰውን ጫና መቀልበስ የሚያስችሉ ተግባራት በተቀናጀ አግባብ እየተከናወኑ እንደሚገኝ ገልጸዋል። በተለይም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል በኩል ሰፊ ሥራ መሠራቱን አንስተው፣ በተያዘው ዓመትም በስምንት ዋና ዋና ከተሞች ሞዴል ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ታቅዷል ብለዋል። ትምህርት ለሁሉም የልማት አቅሞች መነሻ መሆኑን ያነሱት ርዕሰ መስተዳድሩ፣ ለዚህም ተደራሽነትንና ጥራትን ለማረጋገጥ ሰፊ ሥራ እየተሠራ ይገኛል ነው ያሉት። በዚህ የትምህርት ዘመን በክልሉ ከ7 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎችን መዝግቦ ለማስተማር ርብርብ እየተደረገ ሲሆን እስካሁን 70 በመቶ የሚሆነውን ማሳካት መቻሉን አስረድተዋል። ባለፈው የትምህርት ዘመን 59 በመቶ ተማሪዎችን ማስተማር እንደተቻለ አስታውሰው፤ በአዲሱ የትምህርት ዘመን እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት የተሻለ አፈጻጸም ተመዝግቧል። ይሁን እንጂ አሁንም ድረስ ወደ ትምህርት ገበታ ያልመጡ እና ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሁሉም ሕፃናት ወደ ትምህርት ገበታው እንዲመጡ መረባረብ ይገባል ነው ያሉት። ለዚህም ምሁራን፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ ወላጆች፣ ወጣቶች፣ ሴቶችን ጨምሮ መላው ማኅበረሰብ እገዛና ድጋፍ ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል። እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ በትምህርት ዘርፉ የሚስተዋለውን ፍትሐዊነትና ተደራሽነት ችግር የሚያቃልሉ ሥራዎችም ይከናወናሉ ብለዋል። የምክር ቤት አባላትም ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ሕፃናት የትምህርት ዕድል ተቋዳሽ እንዲሆኑና ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ የጎላ ሚናቸውን እንዲወጡ የላቀ ጥረት እንደሚጠበቅ አስረድተዋል። ምክር ቤቱ ለሁለት ቀናት ያካሄደውን መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ማጠናቀቁ ይታወቃል።
ኢኮኖሚ
የባህል አልባሳት ዲዛይን የሸማቹን ፍላጎት በማርካት የንግድ እንቅስቃሴውን እያነቃቃ ነው
Oct 2, 2026 152
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22/2019(ኢዜአ):-ለኢሬቻ በዓል የቀረበው አዳዲስና ዘመናዊ የባህል አልባሳት ዲዛይን የሸማቹን ፍላጎት በማርካት የንግድ እንቅስቃሴውን እያነቃቃ መሆኑ ተገለጸ። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ ያላት ሀገር ናት። ይህን ታላቅነቷን ከሚያረጋግጡ ሀብቶቿ መካከል ሀይማኖታዊ፣ ባህላዊ፣ ታሪካዊ እና ሰው ሰራሽ ቅርሶቿ፣ ባህሎችና የቱሪስት መስህቦቿ ተጠቃሽ ሲሆኑ ከእነዚህ መካከልም ከገዳ ስርዓት የሚመነጨው ኢሬቻ አንዱ ተጠቃሽ ነው። ኢሬቻ በየዓመቱ በልዩ ልዩ ሁነቶች በአደባባይ የሚከበር ሲሆን ዘንድሮም ነገ በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ እንዲሁም ከነገ በስትያ ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ "ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት" በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። በኢሬቻ በዓል ዋዜማ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሱቆች አይነተ ብዙና ማራኪ ዲዛይን ባላቸው ባህላዊ አልባሳትና ጌጣጌጦች ደምቀው ይታያሉ። የኢዜአ ሪፖርተር ተዘዋውሮ በተመለከታቸው የባህላዊ አልባሳት መሸጫ ሱቆች የሸማቾችን ቀልብ የሚስቡ የኢትዮጵያውያን ውብ እጅ ስራዎች ግብይት ደርቷል። ነጋዴዎችና ደንበኞች የባህል አልባሳት በዓይነትና በመጠን በገበያው ላይ መቅረባቸው ለብዙዎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ገበያውን እያነቃቁ መሆኑን ተናግረዋል። በባህል አልባሳት ንግድ ላይ የተሰማሩት ሮባ ጌታቸው ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባህላዊውን ከዘመናዊው የእጅ ሥራ ጋር ያቀናጁ የባህል አልባሳት በገበያው በስፋት ቀርበዋል። የባህል አልባሳቱ የኦሮሞ ህዝብ ባህል ይበልጥ እንዲያድግና ህብረተሰቡ ለባህሉ እድገት ፍላጎት እንዲያሳድር ከማድረጉም በላይ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል ብለዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጭ ነጋዴ አለሚቱ ደንደና በበኩላቸው፤ የኢሬቻ በዓል ድባብ ገበያውን እያነቃቃ መሆኑን ገልጸዋል። በየዓመቱ የሚወጡ አዳዲስ የሀገር ባህል አልባሳት ዲዛይኖች ተፈላጊነት እያደገ መምጣቱን ገልጸው፤ በሸማቾች ምርጫ በተመጣጣኝ ዋጋ በተለያዩ ዲዛይኖች ለህጻናትና አዋቂዎች ቀርበዋል ብለዋል። በዓሉን ምክንያት በማድረግ የሀገር ባህል ልብስ ግብይት ላይ ያገኘነው ወጣት ቶለሳ ሽጉጤ፤ የባህል አልባሳቱ የኦሮሞን ህዝብ ታሪክና ባህል የሚገልጹ፣ በተለያዩ ዲዛይን በከፍተኛ ጥራት የተዘጋጁ መሆናቸውን ገልጿል። ወጣት ኪያ በጂጋ በበኩሉ ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ከሚያከብራቸው በዓላት አንዱ መሆኑን ገልጾ፤ በየዓመቱ በተለያዩ ዲዛይኖች የሚዘጋጁ የሀገር ባህል አልባሳት ተወዳጅነትን አትርፈዋል፤ በዓሉንም በደስታ እንድናከብር አስተዋጽኦ አድርገዋል ብሏል። የባህላዊ እሴታቸውን ጠብቀው በተመጣጣኝ ዋጋ ሳቢና ዘመናዊ ሆነው ለገበያ በመቅረባቸው ህብረተሰቡ ደስ ብሎት እየገዛቸው መሆኑን የገለጸው ደግሞ ወጣት ደገፋ ኃምቢሳ ነው።
በክልሉ የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Oct 2, 2026 91
ባህር ዳር ፤ መስከረም 22/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለፁ። የአማራ ክልል ምክር ቤት 7ኛ ዙር፣ 1ኛ ዓመት የስራ ዘመን መስራች እና 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ዛሬ ተጠናቋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ እንደገለጹት፤ የክልሉ መንግስት የህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ ለማድረግ ርብርብ ያደርጋል። በዚህ በጀት ዓመት ለነባርና አዳዲስ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እንዲሁም ለሌሎች ስራዎች ከ31 ነጥብ 1 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት ተይዞ ወደ ስራ መገባቱን ተናግረዋል። በጀቱ ቅድሚያ ለሚሰጣቸው ወሳኝ ፕሮጀክቶች በውጤታማነትና በፍትሃዊነት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል እንደሚደረግም አረጋግጠዋል። በተለይም የከተማና የገጠርን ትስስር ለማጠናከር የሚያስችሉ የመንገድ መሰረተ ልማቶች በተገቢው ሁኔታ ይፈጸማሉ ብለዋል። የንፁህ መጠጥ ውሃ ተቋማትን ለተጠቃሚው ማህበረሰብ ተደራሽ በማድረግ በኩልም በርካታ ስራዎች እንደሚከናወኑ ገልጸዋል። የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግሩን ለማሳለጥና የግብርና ዘርፉን ከዝናብ ጥገኝነት ለማላቀቅ የሚያግዙ የመስኖ ተቋማት ፕሮጀክቶች ግንባታም በተጠና መንገድ እንደሚከናወን አረጋግጠዋል። የኃይል አቅርቦት ክፍተትን ለማቃለልም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ከመነጋገር ባለፈ አማራጭ የኃይል አቅርቦቶችን መጠቀም እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም በማሳደግም ተኪ ምርትም ሆነ ለውጭ ገበያ የሚቀርቡ ሌሎች ምርቶችን በብዛትና በጥራት በማምረት ዘርፉን የማሳደግ ስራ ትኩረት እንደተሰጠውም አመልክተዋል። የልማት ስራዎችን ውጤታማነት ለማረጋገጥ ህብረተሰቡ በገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግ የምክር ቤት አባላት አበክረው መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ፋንቱ ተስፋዬ በበኩላቸው፤ በሁሉም ዘርፍ የቀረቡ እቅዶች በውጤታማነት ተፈጻሚ እንዲሆኑ የምክር ቤት አባላት የሚጠበቅባቸውን ሚና ይወጣሉ ብለዋል።
የኢትዮጵያ የማንሰራራት ዘመን ማንጸባረቂያ - የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት
Oct 2, 2026 148
አዲስ አበባ፤መስከረም 22/2019 (ኢዜአ)፦የዳመርጆግ - ደወሌ የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት የኢትዮጵያን ምጣኔ ሀብታዊ እድገት ከማፋጠን ባለፈ ሀገሪቷ ከጅቡቲ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ሲሉ የምጣኔ ሀብት ምሁራን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በመሰነቅ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተጋች ትገኛለች። በጅቡቲ ዳመርጆግ እና በኢትዮጵያ ደወሌ መካከል የሚገነባው የ120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እድገቷን ለማፋጠን ከጀመረቻቸው የልማት ፕሮጀክቶች መካከል ይጠቀሳል። የፕሮጀክቱንም ግንባታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)፣ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጌሌ እና የዳንጎቴ ግሩፕ ፕሬዚዳንት አሊኮ ዳንጎቴ በቅርቡ አስጀምረዋል። ፕሮጀክቱም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ (EIH) እና በዳንጎቴ ግሩፕ መካከል በተደረገ አጋርነት የሚተገበር ሲሆን፤ ከአንድ ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር በላይ የተጣራ የነዳጅ ምርቶችን የመያዝ እና የማስተላለፍ አቅም እንደሚኖረው የግንባታው ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ መገለጹ የሚታወስ ነው። የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር ፕሬዝዳንት እና በአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሀና ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ በቅርቡ ግንባታው የተጀመረው የኢትዮጵያ-ጅቡቲ የነዳጅ ምርቶች ማስተላለፊያ መስመር ኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ ከጅቡቲ ነዳጅን ለማስገባት የተሽከርካሪ አማራጮች የምትጠቀም መሆኗ አስተማማኝ የሆነ የነዳጅ አቅርቦት እንደ ሀገር እንዳይኖር እንቅፋት ሲፈጥር መቆየቱን ገልጸዋል። በቅርቡ በኢትዮጵያ-ጅቡቲ በሁለቱ ሀገራት የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት ግንባታ መጀመር የሀገሪቷን የነዳጅ ፍላጎት ለማሟላት እንደሚረዳ ተናግረዋል። አንድ ኢንቨስትመንት ፋይዳው የሚለካው በኢኮኖሚ ላይ ከሚያበረክተው አስተዋጽኦ ባሻገር ለዜጎች በሚፈጥረው የስራ እድል ጭምርም መሆኑን በማንሳት የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክቱ ከዚህ አኳያ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው እንደሆነም አብራርተዋል። ሌላኛው የምጣኔ ሀብት ምሁር ብርሃኑ ዓለሙ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በሀገሪቷ የሚከናወኑ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ስራዎች፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እንዲሳለጡ እንደ ሀገር የነዳጅ ክምችትን ማሳደግ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል። ከዚህ አኳያ የዳመርጆግ-ደወሌ የነዳጅ ማስተላለፊያ መስመር ፕሮጀክት አስተማማኝ እና በተለያዩ ምክንያቶች የማይዋዥቅ የነዳጅ አቅርቦት እንዲኖር ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል። ፕሮጀክቱ ለአምራች ኢንዲስትሪዎች የነዳጅ አቅርቦት ፍላጎት ምላሽ የመስጠት አቅምን የሚያሳድግ፣ ለመካናይዝድ ግብርና ምርታማነት ለትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ውጤታማነት ትልቅ ሚና ያለው ፕሮጀክት እንደሆነ አብራርተዋል። ምሁራኑ ኢትዮጵያ አቅዳ የምታከናውናቸው ግዙፍ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች የራሷን ኢኮኖሚያዊ እድገት ከማረጋገጥ ባለፈ ለአሁጉሪቷ እድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ መሆናቸውን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የጀመሩት ፕሮጀክትም እንደ ማሳያነት መሆኑን ገልጸዋል። በሁለቱ ሀገራት የተጀመረው ፕሮጀክት የጋራ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን የሚያሳድግ፣ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ይበልጥ የሚያጠናክር ነውም ብለዋል።
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የፖሊሲ እርምጃዎች ዓለም አቀፍ የባንክና የፋይናንስ ተቋማትን ኢንቨስትመንት የሚያበረታቱ ናቸው
Oct 2, 2026 202
አዲስ አበባ፤መስከረም 22/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ የፋይናንስ ዘርፍ የፖሊሲ እርምጃዎች የሀገር ውስጥ ባንኮችን ተወዳዳሪነት በማሳደግ ዓለም አቀፍ የባንክና የፋይናንስ ተቋማትን ኢንቨስትመንት የሚያበረታቱ መሆናቸውን የግሎባል አልያንስ ፎር ባንኪንግ ኦን ቫልዩስ ዋና ዳይሬክተር ማርቲን ሮነር ገለጹ። የኢትዮጵያ ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር ንግድና ኢንቨስትመንትን በማበረታታት የፋይናንስ ኢንዱስትሪው እንዲያንሰራራ እያደረገ ነው። በዚህም ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ያላት ኢትዮጵያን የባንክ ኢንዱስትሪ ለዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት ክፍት በማድረግ ታሪካዊ ዕድልን ከፍቷል። የግሎባል አልያንስ ፎር ባንኪንግ ኦን ቫልዩስ ዋና ዳይሬክተር ማርቲን ሮነር ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ ብዝኅ ኢኮኖሚ ልማት የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስፋት ክፈተኛ አቅም አለው። በሀገር በቀል የተሟላ ማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ ግብር የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ክፍት መደረጉም የኢትዮጵያን ዕምቅ አቅም መጠቀም ለሚሹ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ወርቃማ ዕድል ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ ዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓትም ዓለም አቀፍ የባንክና ፋይናንስ ተቋማት ኢንቨስት የሚያደርጉበትን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን ገልጸዋል። የፋይናንስ ዘርፍ ለኢንቨስትመንት ክፍት መደረጉም የሀገር ውስጥ ባንኮችን የተወዳዳሪነት አቅም በማጎልበት ጥራትና ብቃት ለው አገልግሎት የሚሰጡበትን ተነሳሽነት እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል። በሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የተከናወኑ መጠነ ሰፊ ዘመናዊ የፋይናንስ ዘርፍ የፖሊሲ እርምጃ ዘመኑ የሚጠይቀውና አስፈላጊ ጉዳይ መሆኑን አንስተዋል። የኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ እርምጃም የፋይናንስ ዘርፉን በትክክለኛ የዕድገት አቅጣጫ የሚመራበትን ስኬት እያስመዘገበ መሆኑን አመላክተዋል። ለአብነትም የካፒታል ገበያ፣ የገንዘብና የውጭ ምንዛሬ የፖሊሲ እርምጃዎች ኢትዮጵያን ለዓለም አቀፍ የባንክና የፋይናንስ ተቋማት የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት የስበት ማዕከል የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። የኢትዮጵያ መዋቅራዊ የፋይናንስ ዘርፍ ፖሊሲ እርምጃም የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ከፍታ ብሩህ ጊዜ እንደሚጠብቀው አመላካች እንደሆነ ገልጸዋል። በጥቂት ዓመታት ውስጥ የታየው ውጤት ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነታቸውን ገልፀዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ ነው
Oct 1, 2026 233
አዲስ አበባ፣መስከረም 21/2019(ኢዜአ)፡-የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት የኢትዮጵያን የዲጂታል እመርታን የሚያሳልጥ የሰው ሃይል እያፈራ መሆኑን የትምህርት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ገለጹ። ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ባላት ኢትዮጵያ የዲጂታል ኢትዮጵያ ስትራቴጂ በሁሉም መስክ የሀገርን ማንሰራራት የሚያበስር እመርታዊ ውጤት እያስገኘ ነው። የኢትዮጵያ የሳይንስ፣ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ የ50 ዓመታት የምርምር፣ ኢኖቬሽን፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ኢንተርፕርነርሽፕ ጉዞን እና ቀጣይ ሥራዎች ላይ ያተኮረ ጉባኤ በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም ተካሂዷል። ለሦስት ቀናት በተካሄደው ጉባኤ ማጠናቀቂያም የኢትዮጵያ ተሰጥኦ እና ተውህቦ ማበልፀጊያ ኢንስቲትዩት የቡራዩ ተሰጥኦ ልማት ትምህርት ቤት ያሰለጠናቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ተማሪዎችን አስመርቋል። በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የቡራዩ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ዋና ዳይሬክተር መሳይ ኃይለማሪያም ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችን በማሰልጠን የኢትዮጵያን የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል የሰው ኃይል እያፈራ ነው። በትምህርት ቤቱ ሥልጠና የሚሰጣቸው ባለልዩ ተሰጥኦ ወጣቶችም ከፍተኛ የማሰብ፣ የማገናዘብና የመተንተን አቅማቸውን ታሳቢ ባደረጉ መስፈርቶች ተመልምለው የሚሰለጥኑ መሆናቸውን ተናግረዋል። በዚህም ታዳጊዎች የፈጠራ ክህሎትና ልዩ ተሰጧቸውን በማበልጸግ ችግር ፈቺ የመፍትሔ ውጤቶችን የሚያፈልቁበት ወሳኝ ዕድል እንዲፈጠርላቸው እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል። ተመራቂዎችም በትምህርት ቤቱ ቆይታቸው ንድፈ ሃሳብን ከተግባር ተኮር ያቀናጀ ዕውቀትና ክህሎት ማግኘታቸውን አስረድተዋል። ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የሚመለከታቸው አካላትም ታዳጊዎች ክህሎታቸውን የሚያበለጽጉበትን ዕድል በማመቻቸት ቀጣይነት ያለው ሥራ በመሥራት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። ተመራቂ ተማሪዎቹ በበኩላቸው፤ የልዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ትምህርት ቤት ተፈጥሯዊ ተሰጥኦቸውን በተግባር ልምምድ የታገዘ ሥልጠና የሚያገኙበትን የዕውቀትና ክህሎት ማበልፀጊያ ዕድል መፍጠሩን ገልጸዋል። ከአስተያየት ሰጪዎቹ መካከል ማክዳ ወርቅሸት፤ ትምህርት ቤቱ ልዩ ተሰጥኦቸውን የሚያበለጽጉበትን ወሳኝ ትምህርትና ሥልጠና ዕድል ሰጥቶናል ብላለች። የሥልጠና ቆይታቸውም የልዩ ተሰጥኦ ዕውቀትና ክህሎታቸውን በማበልጸግ ከዓለም አቀፍ የዲጂታል ተወዳዳሪነትን እንደሚያጎለብትላቸው ገልጻለች። የኢትዮጵያ ዲጂታል ልማት የቴክኖሎጂ ልዩ ተሰጧቸውን የምናጎለብትበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሮልናል ያለው ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጪ ወጣት በተሻለ አበበ ነው። በአሁኑ ወቅት የክረምት ሥልጠናዎችና ልዩ ልዩ የፈጠራ ማሳያ መድረኮች በርካታ ዕድሎችን በመፍጠር ተሰጥኦ ያላቸው ወጣቶች የሚጠቀሙበትን ዕድል እንደፈጠረላቸው ገልጿል። ወጣቶችም የኢንተርኔት አክሰስንና አዳዲስ ዕድሎችን በመጠቀም የራስን ጥረት ማዕከል በማድረግ አዳዲስ ሶፍትዌሮችን በማልማት ዕድሉን መጠቀም እንዳለባቸው መልዕክት አስተላልፏል።
በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል ነው
Oct 1, 2026 165
ሸገር ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እየተሰጠ ያለው ትምህርት ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ መሆኑን የኦሮሚያ ዲያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ገለጹ። የኦሮሚያ ዲያስፖራ አባላቱ ለኢሬቻ በዓል አከባበር ወደ ሀገር ቤት የመጡ ሲሆን፣ በሸገር ከተማ በሚገኘው የሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው እየጎበኙ ነው። የዲያስፖራ አባላቱ በኢንስቲትዩቱ በተከናወኑ የዲጂታል ልማት ስራዎቹ መደመማቸውንም ገልጸዋል። ከአሜሪካ የመጡት ዶክተር ተመስገን ሻሾ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተመለከቱት ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችልና ለተተኪው ትውልድ ትልቅ ተስፋ የሚሰጥ ነው። "ዓለም በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እየተደገፈች ያለችበት ወቅት በመሆኑ፣ ሀገራችን ለተለያዩ የሥራ ዘርፎች ከውጭ ይገቡ የነበሩ ቴክኖሎጂዎችን በሀገር ውስጥ ለመተካት የጀመረችው እንቅስቃሴ እጅግ የሚበረታታ ነው" ብለዋል። በተለይም ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እንዲደገፉና ብቁ እንዲሆኑ ለማድረግ የተሰራውን ስራ ያደነቁት ዶክተር ተመስገን፤ አሁን የተጀመሩት ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ በተሻለ የልማት ጉዞ ላይ መሆኗን የገለጹት ዶክተር ተመስገን፤ በተለይም የዲያስፖራው ማህበረሰብ አባላት በሀገራቸው መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ የልማቱ አካል እንዲሆኑ ጥሪያቸውን አቅርበዋል። ከደቡብ አፍሪካ የመጡት አቶ ኡመር ኡስማን በበኩላቸው፤ በኢንስቲትዩቱ ባዩት ስራ እጅግ መደሰታቸውን ገልጸው፣ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የሚከናወኑት ተግባራት ትውልዱ በሀገሩ ሰርቶ እንዲለወጥ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳላቸው አስረድተዋል። በኦሮሚያ ክልል በቴክኖሎጂው ዘርፍ እየተከናወነ ያለው ስራ ሀገራችን በቴክኖሎጂ አስተማማኝ አቅጣጫ ላይ መሆኗን የሚያመላክት መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። ሀገሪቱ በአስተማማኝ የዕድገት መስመር ላይ የምትገኝ መሆኗን በመጠቆም፣ ዲያስፖራው በሀገሩ መዋዕለ ንዋዩን በማፍሰስ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። በተመሳሳይ ከኖርዌይ የመጡት ወይዘሮ ሌንሴ ለሜሳ፤ በኢንስቲትዩቱ ለተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ትምህርት ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው፤ ይህም ወጣቶች በሀገራቸው ጥራት ያለው ትምህርት አግኝተው በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን እውቀት እንዲጨብጡ የሚያስችል ነው ብለዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተስፋዬ ዲማ እንዳሉት፤ ጉብኝቱ በየዓመቱ በኢሬቻ ሳምንት በክልሉ የሚገነቡ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የመጎብኘት ባህል አካል ነው። አክለውም በኢንስቲትዩቱ በክልሉ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሰልጥነው ለነገዋ ሀገር ተስፋ የሚሆኑበትን አሰራር መመልከታቸው ወሳኝ መሆኑን ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ዲያስፖራ ጉዳይ ዳይሬክተር አቶ አሚን ጁንዲ በበኩላቸው፤ ኢንስቲትዩቱ ከተቋቋመ አንድ ዓመት የሞላው መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ እስካሁን በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ከ200 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) የተደገፈ ትምህርት እየሰጠ ይገኛል ብለዋል። ይህም ከፍተኛ የዕውቀት ብቃት (IQ) ያላቸውን ተማሪዎች በማፍራት ሀገራቸውን ተወዳዳሪ ለማድረግ ያለመ ስራ መሆኑን ያብራሩት አቶ አሚን፤ የጉብኝቱ ዋና ዓላማም በሀገራችን እየመጣ ያለውን ሁለንተናዊ ለውጥ በተግባር በማሳየት አባላቱ ሀገራቸውን በዕውቀትም ሆነ በኢንቨስትመንት ለመደገፍ እንዲዘጋጁ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
በዲጂታል ዘመን የግለሰብ መረጃ እና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን በአግባቡ መንከባከብ ወሳኝነት አለው
Sep 30, 2026 135
አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2019 (ኢዜአ) ፦ በዲጂታል ዘመን የግለሰብ መረጃ እና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን በአግባቡ መንከባከብ ወሳኝ መሆኑን የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ገለጸ። ባለስልጣኑ ከኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ጋር በመተባበር በግል ዳታ ጥበቃ ዙሪያ ያዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ የውይይት መድረክ እየተካሄደ ይገኛል። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሚሊዮን ኃይለሚካኤል በዲጂታል ዘመን የግላዊነትንና የዜጎችን እምነት ለመጠበቅ ዳታን መንከባከብ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። እንዲሁም የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 1321/2016 መረጃን በኃላፊነትና በግልጽነት ለማስተዳደር ጠንካራ የሕግ ማዕቀፍ መዘርጋቱን ገልጸዋል። ጠበቆችም የደንበኞቻቸውን መረጃ በሥራቸው የሚይዙ በመሆናቸው በዘርፉ ትልቅ ባለድርሻ አካል መሆናቸውን አስረድተዋል። አቶ ሚሊዮን አያይዘውም የተገኘው ግንዛቤ ብቻውን በቂ ባለመሆኑ ወደ ተግባር ሊለወጥ እንደሚገባ አስረድተዋል። የኢትዮጵያ ፌዴራል ጠበቆች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ተስፋዬ ደረሰ በበኩላቸው ጠበቆች የደንበኞቻቸውን ምስጢራዊ መረጃ በሕጉ መሠረት መጠበቅ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ጠበቆች ሕጉን ከማክበር ባለፈ ደንበኞቻቸው የግል ዳታ ጥበቃ ሕጉን እንዲያከብሩ የሙያ ማማከር ኃላፊነት እንዳለባቸው ገልጸዋል።
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተከናወኑ ውጤታማ ሥራዎች ለኢትዮጵያ ብልፅግና እውን መሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው
Sep 29, 2026 207
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ለኢትዮጵያ ብልፅግና እውን መሆን መሰረት የሚጥሉ ውጤቶች ማስመዝገባቸውን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) ገለጹ። የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፉን ውጤቶች ይበልጥ ለማላቅ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የማስደገፉ ስራ ሊጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ምርምር ፈጠራና ኢንተርፕርነርሽፕ ላይ ያተኮረ ጉባኤ በሳይንስ ሙዝየም እያካሄደ ነው። በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ስራ ስምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት ለኢትዮጵያ ብልፅግና እውን መሆን መሰረት የሚጥሉ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ምክር ቤቱ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ምቹ ምህዳር የሚፈጥሩ አዋጆች ስራ ላይ እንዲውሉ በሰፊው ሲሰራ ቆይቷል። ለአብነትም የኤሌክትሮኒክ ፊርማ፣ የኮሙኒኬሽን አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክ ግብይት፣ የዲጂታል መታወቂያ እና የግል መረጃ ጥበቃ አዋጆች በምክር ቤቱ ጸድቀው ስራ ላይ ከዋሉ መካከል እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል። ምክር ቤቱ ህግ ማውጣት ብቻ ሳይሆን የወጡ ህጎች ተግባራዊ መሆናቸውን የክትትል እና ቁጥጥር ስራውን በላቀ ቁርጠኝነት ሲሰራ መቆየቱንም አንስተዋል። የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አጠቃላይ አፈጻጸም እንዲሁም የዲጂታል 2030 ዕቅድ ተግባር ክትትል እየተደረገ ግብረ መልስ የመስጠት ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉንም አክለዋል። በዘርፉ በተሰሩ ስራዎች ለኢትዮጵያ ብልፅግና እውን መሆን መሰረት የሚጥሉ ውጤቶች እንደተገኙ ጠቁመው፤ አሁንም ይበልጥ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፉን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር በማቀናጀት ዕድገቱን ለማፋጠን አበክሮ መስራት ይገባል ብለዋል። የሳይበር ጥቃቶችን አስቀድሞ መከላከል እና ጉዳቱን መቀነስ ወሳኝ ነው ያሉት ሰብሳቢው ለዚህ ደግሞ በዘርፉ ያሉ ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ስራዎቻቸውን ማጠከር እንደሚጠበቅባቸው አመልክተዋል።
ስፖርት
2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ ተካሄደ
Oct 1, 2026 172
ቢሾፍቱ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢሬቻ በዓልን በማስመልከት 10 ኪሎ ሜትር የሚሸፍነው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ ተካሂዷል። ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ መግባባትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል። በዓሉ የኦሮሞን ባህልና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላለፍ አልፎ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርንና ፍቅርን በማሳደግ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል። የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማም ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማሳወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው በዚህ የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አትሌቶች እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል። በዚሁ መሰረት በወንዶች አትሌት ጅራታ ሌሊሳ (ከሸገር) 1ኛ፤ አትሌት ለሚ ተሾመ (ከሸገር) 2ኛ፤ አትሌት አቤል ቼቤት (ከኡጋንዳ) 3ኛ በመውጣት ውድድሩን አሸንፈዋል። እንዲሁም በሴቶች አትሌት ብርነሽ ደሴ (ከፀዳይ ባንክ) 1ኛ በመውጣት የ2019 የ2ኛው የኢሬቻ ታላቅ ሩጫ አሸናፊዎች ሆነዋል። በሥነ ሥርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ባህልና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሮዛ ቢያ ባደረጉት ንግግር፣ ኢሬቻ ፍቅርንና አንድነትን በማጠናከር ለብሔራዊ መግባባት መሠረት በመጣል ረገድ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። ይህንን በስፖርት በማስደገፍ የተጀመረውን ሀገር አቀፍ የመግባባት ጉዞ ወደ ላቀ ደረጃ እናሳድጋለን ብለዋል። የቢሾፍቱ ከተማ ከንቲባ አቶ አለማየሁ አሰፋ በበኩላቸው፤ የኢሬቻ ሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የሀገሪቱን ቱሪዝም እያሳደገ መሆኑን ገልጸዋል። የቢሾፍቱ ከተማም ከምንጊዜውም በላይ ዘንድሮ የኢሬቻ እንግዶችን ለመቀበል በኮሪዶር ልማት አጊጣ እየጠበቀች መሆኑን ተናግረዋል።
2ኛው የኢሬቻ ሩጫ “ኢሬቻ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል
Oct 1, 2026 128
ቢሾፍቱ ፤መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦ የ2019 የኢሬቻ በዓል ዋዜማን በማስመልከት የተዘጋጀው 2ኛው የኢሬቻ ታላቁ ሩጫ “ኢሬቻ፡ ለሀገራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ በቢሾፍቱ በመካሄድ ላይ ይገኛል። ኢሬቻ የምስጋና፣ የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት በዓል ከመሆኑ በላይ፣ የተለያዩ ብሔሮችና ብሔረሰቦችን አንድ ላይ የሚያመጣ እንዲሁም መግባባትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነትን የሚያጠናክር የጋራ መድረክ እየሆነ መጥቷል። በዓሉ የኦሮሞን ባህልና እሴት ከትውልድ ወደ ትውልድ ከማስተላለፍ አልፎ፣ በልዩነት ውስጥ መከባበርንና ፍቅርን በማሳደግ የኢትዮጵያ የጋራ ሀብት በመሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራችንን ለማስተዋወቅ ዕድል እየፈጠረ ይገኛል። የዚህ የጎዳና ላይ ሩጫ ዓላማም ኢሬቻ የወንድማማችነት፣ የአንድነትና የይቅርታ መድረክ መሆኑን ለዓለም በማሳወቅ ሳቢነቱን ማሳደግ መሆኑ ተገልጿል። 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ባለው በዚህ የኢሬቻ የጎዳና ላይ ሩጫ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር አትሌቶች እንዲሁም ከ50 ሺህ በላይ ሰዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን 16 ጎሎችን በማስቆጠር ሲሸልስን አሸነፈ
Sep 30, 2026 180
አዲስ አበባ ፤መስከረም 20/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ሲሸልስን 16 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ረትቷል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ንግሥት በቀለ፣ ታሪኳ ዴቢሶ፣ እሙሽ ዳንኤል፣ አረጋሽ ካልሳ እና ቤተልሄም መንተሎ በተመሳሳይ ሁለት ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። ምኅረት አየለ፣ እፀገነት ግርማ፣ ቱሪስት ለማ፣ ሚለን ጋይም፣ ዳግማዊት ሰለሞን እና ማህሌት ምትኩ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። የሀገራቱ ሁለተኛ የወዳጅነት ጨዋታ ቅዳሜ መስከረም 23 ቀን 2019 ዓ.ም ይካሄዳል። ቻለው ለሜቻ በሁለት ዓመት ውል የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆነው ባለፈው ሳምንት መሾማቸው የሚታወስ ነው። ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር የሁለተኛ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች። የወዳጅነት ጨዋታዎች የብሔራዊ ቡድኑ የማጣሪያ ዝግጅት አካል ናቸው።
በህብረ ቀለማት ያሸበረቀው የባህር ዳር ስታዲየም
Sep 30, 2026 147
ባህርዳር ፤መስከረም 20/2019 (ኢዜአ) ፦ በህብረ ቀለማት ያሸበረቀው የባህርዳር ስታዲየም በህብረ ቀለማት ያሸበረቀው የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከደጋፊዎች ቁጥርና ተጫዋቾች ጋር ተዳምሮ ለትናንቱ ምሽት ድምቀት ሆኖ አልፏል ። የባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን ከበርካታ ዓመታት የስደት ጨዋታ በኋላ ወደ ሀገሩ በመመለስ በደጋፊው ፊትና በለመደው አየር ንብረት እንዲጫወት መልካም ዕድል ፈጥሯል። ባህር ዳር በጣና ሀይቅ የተከበበችና በዘንባባ ዛፎች የተዋበች ስትሆን በስታዲየሙ የተገጠሙት ባለነጭና ሰማያዊ ወንበሮችም የከተማዋን የተፈጥሮ ጸጋ የሚያንጸባርቁ ይመስላሉ። የስታድየሙ የእግር ኳስ ሜዳ ደረጃውን የጠበቀ አረንጓዴ ሣር የለበሰ ሲሆን፣ በሜዳው ዙሪያ የሚገኘው የመሮጫ መም ደግሞ በቀይ ቀለም ደምቆ የተገነባ መሆኑ ስታዲየሙን በህብረ ቀለማት የተሞላ አድርጎታል። ስታዲየሙ የካፍን ይሁንታ ያገኘ ብቸኛው የሀገራችን ስታዲየም በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን በሌሎች ሀገራት በስደት ሲጫወት ከነበረበት ወደ ቤቱ በመመለሰ ጨዋታውን በደጋፊው ፊት እንዲያኪያሂድ በማድረጉ የሀገር ባለውለታ አድርጎታል። በትላንቱ በዋሊያዎቹና በሴኔጋል ብሄራዊ ቡድን መካከል በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ደጋፊው ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል 90 ደቂቃ ሙሉ ቆሞ ብሔራዊ ቡድናችንን ሲያበረታታ መመልከቱ ደግሞ ሌላው የስታዲየሙ ውብ ትእይንት ነበር ። ስታዲየሙን ከአፍ እስከ ገደፉ የሞላው ደጋፊ ዋሊያዎቹ 1 ለ 0 እየተመሩም የተለያዩ ዝማሬዎችን በማሰማትና በእንቅስቃሴ ድጋፉን ሲገልጽ አምሽቷል። ይህም የስታዲየሙን እግር ኳስ ከውጤት በላይ ነው የሚለውን ያረጋገጠ የስሜት፣ የፍቅር፣ የወንድማማችነት መድረክ መሆኑን ያንጸባረቀና የውበት ድባቡን ከፍ ያደረገ ነበር። የሴኔጋል እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ፓትሪክ ቬራ ከጨዋታ በፊት “ይህ ሜዳ ለእኛ ይበልጥ ተስማሚ ነው” በማለት የጥራት ደረጃውን መግለጻቸው ደግሞ የስታዲየሙን ብቃትና ዓለምአቀፋዊነት ያረጋገጠ ነበር ። በሌላ በኩል የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ከጨዋታው በኋሏ በሰጡት አስተያየት “በጠባብ ውጤት ብንሸነፍም በመልካሙ ድጋፍ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገናል” ማለታቸው ደግሞ ሌላው ደጋፊው ለስታዲየሙ ድምቀት ተጨማሪ አቅም መሆኑን ያሳየ ነው።
አካባቢ ጥበቃ
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን እያጎለበተ ነው
Oct 1, 2026 124
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን በማጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል። በተለይም የከተሞችን ሁለንተናዊ ጽዳትና ውበት ከማሻሻል ባሻገር ለአካባቢ ጥበቃና ሥነ-ምኅዳር ድኅንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የጽዱ ኢትዮጵያ ተነሳሽነት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ዘመናዊ ምኅዳርን በማጎናጸፍ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳርቻና መሰል ውጤታማ የልማት ሥራዎችን የሚያፋጥን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንም የሕብረተሰብ ተሳትፎን በማሳደግ የጽዱ ኢትዮጵያን ግብ የሚያሳካ የአካባቢ ጥበቃ፣ የጽዳትና ውበት ባህልን የሚያጎለብት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እያካሄደ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም በመጀመሪያው ዙር "ውበት ይንቃ፤ ብክለት ይብቃ" በሚል መሪ ሀሳብ ለስድስት ወራት የብክለት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መከናወኑን አስታውሰዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ "ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዳት ባህልን ማጠናከር የሚያስችል መሰረት መጣል እንደተቻለ አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም ለ3 ወራት የሚቆይ 3ኛ ዙር ''የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል። በየዓመቱ የሚካሄዱት የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄም የማኅበረሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ በማጎልበት ተቋማት በብክለት መከላከል ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ እያደረገ ነው ብለዋል። መርሐ ግብሩም የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋትና መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ በውጤታማነት በማስፈጸም ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር በቀጣይም ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃን ለማረጋገጥና ብክለትን ለመከላከል የተቀናጁ የአካባቢ የጽዳትና ውበት ጥበቃ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።
የኤልኒኖ ክስተት ተጽዕኖዎችን ለመከላከል መዘጋጀት ይገባል
Sep 29, 2026 192
አዲስ አበባ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦የኤልኒኖ ክስተት የሚያመጣቸውን መልካም እድሎች ለመጠቀምና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የኤልኒኖ ክስተት ከጥቅምት ወር ጀምሮ በከፍተኛ ሁኔታ እየጠnነከረ ይሄዳል። ኤልኒኖ በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ አካባቢዎች እንዲሁም በልግ ዋነኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑ የደቡብ አጋማሽ የሀገራችን ክፍሎች ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠን እና ስርጭት እንዲኖር አስተዋፅኦ ያደርጋል ብለዋል። ከጥቅምት ጀምሮ የሚኖረው የዝናብ መጠንና ስርጭት በተለይም ለሱማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ ለጉጂ፣ ለቦረና፣ ለሲዳማ እና ለደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎች እጅግ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ተናግረዋል። ይህም ዝናብ ከወዲሁ የመስኖ ስራዎችንና የተለያዩ የግብርና እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን፣ እንዲሁም ለአርብቶ አደሩና ለከፊል አርብቶ አደሩ የእንስሳት መኖ አቅርቦትን በማሻሻል በእንስሳት ምርትና ምርታማነት ላይ ከፍተኛ አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የምዕራብ ህንድ ውቅያኖስም በከፍተኛ ሁኔታ እየሞቀ ይገኛል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የኤልኒኖ ክስተት እና የህንድ ውቅያኖስ ሙቀት መጨመር በአንድ ጊዜ በሚጣመሩበት ወቅት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንዲኖር ያደርጋል ብለዋል። በዚህም መሰረት ከጥቅምት አጋማሽ ጀምሮ በምስራቅ አማራ፣ በምስራቅ እና በመካከለኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ የመፈጠር እድሉ ከፍተኛ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከመደበኛ በላይ በሚኖረውና ተደጋጋሚነት ባለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በዋቢ ሸበሌ እና በገናሌ ዳዋ ተፋሰሶች አካባቢዎች ቅጽበታዊ ጎርፍ የመከሰት እድሉ እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡ ይህም በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ሊያሳድር ስለሚችል ከወዲሁ በዋቢ ሸበሌ፣ በኦጋዴን እና በገናሌ ዳዋ አካባቢዎች የተቀናጀ የወንዝ አመራር ስርዓትን መተግበር አስፈላጊ መሆኑ ገልጸዋል፡፡ በዘንድሮው የበጋ ወቅት ከመደበኛ በላይ የሚኖረው የዝናብ መጠን ያለው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ሊከሰቱ የሚችሉ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን ለመከላከል ለማህበረሰቡ ተደጋጋሚነት ያለው የግንዛቤ መፍጠሪያ ስራዎችን በመስራት ላይ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያ የቀጣናው የታዳሽ ኃይል ማዕከል
Sep 27, 2026 431
ኢትዮጵያ በውሃ፣ በንፋስ፣ በፀሐይ እና በጂኦተርማል ሀብቶቿ ለታዳሽ ኃይል ልማት እጅግ ግዙፍ አቅም ያላት ሀገር ስትሆን፤ የመደመር መንግስት ይህንን የተፈጥሮ ጸጋ በብቃት በመጠቀም የኢትዮጵያን የኢነርጂ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ታላላቅ ሥራዎችን አከናውኗል። በዚህ ረገድ የመደመር መንግስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ከማጠናቀቅ ባሻገር ሌሎች የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በማልማት ረገድ ያከናወነው ስራ ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ የታዳሽ ኃይል ልማቷን ከራሷ አልፎ ለጎረቤት አገራት በማዳረስ ቀጣናውን በኢነርጂ የማስተሳሰር ስትራቴጂካዊ ሚናዋን በተግባር እያሳየች ትገኛለች። እንደ ሱዳን፣ ጂቡቲ እና ኬንያ ላሉ አገራት የሚደረገው የኤሌክትሪክ ሃይል ንግድ የምስራቅ አፍሪካን አገራት በኢነርጂ በማስተሳሰር በጋራ ማደግ እንደሚገባ ያሳየ ነው።ይህ የሃይል ትብብር የአፍሪካን አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና እውን ለማድረግ እና በቀጣናው የኃይል ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሰረት ሆኖ ቀጥሏል።
አረንጓዴ ኢትዮጵያን ለመጪው ትውልድ
Sep 27, 2026 241
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የዛሬን ጊዜያዊ ፍላጎት ለማሟላት ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የተሻለች፣ ለኑሮ ምቹ እና በምግብ እራሷን የቻለች ኢትዮጵያን እንዲረከብ የተነደፈ ስትራቴጂካዊ ሀገራዊ ራዕይ ነው። በየዓመቱ በቢሊዮኖች የሚቆጠሩ ችግኞችን በመትከል የሚከናወነው ይህ ዘመቻ፣ ለበርካታ አስርት ዓመታት ተደምስሶ የነበረውን የደን ሽፋን በመመለስ፣ የአፈር መሸርሸርን በመግታት እና የስነ-ምህዳር ሚዛንን በማስተካከል ረገድ መሠረታዊ ቅያሬ እያመጣ ይገኛል። ዛሬ የሚተከለው እያንዳንዱ ችግኝ የነገዋ ኢትዮጵያ ንጹህ አየር፣ አስተማማኝ የውኃ ሀብት እና ለም መሬት እንዲኖራት የሚያስችል መሠረት በመሆኑ፣ የወደፊቱን ትውልድ ከድርቅ፣ ከበረሃማነት እና ከአየር ንብረት መዛባት ስጋት የሚታደግ ብሔራዊ ዋስትና ነው። ከዚህም በተጨማሪ ይህ መርሃ ግብር ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ ከግብርና ምርታማነት፣ ከኢኮኖሚ እድገት እና ከአረንጓዴ ኢነርጂ ልማት ጋር በመቀናጀት የሚተገበር በመሆኑ፣ ለወደፊቱ ትውልድ የተረጋገጠ የልማትና የህይወት መሰረት የሚጥል ነው። አረንጓዴ አሻራን የመትከልና የመንከባከብ ባህል በህፃናትና በወጣቶች ዘንድ እንዲሰርጽ በማድረግ፣ ሀገርን የመጠበቅና የመንከባከብ ኃላፊነት በትውልድ ቅብብሎሽ እንዲሸጋገር ያደርጋል። በመሆኑም የአረንጓዴ አሻራ ጥረት የዛሬው ትውልድ ለነገው ትውልድ የሚያስረክበው ታላቅ ተግባር ነው።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ
Sep 21, 2026 837
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 985
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 877
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 1063
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የወጣቱ የዲጂታል ክህሎትና የኢትዮጵያ ነገ
Oct 1, 2026 133
በዜናው ፈንቴ!! ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይን ሰንቃ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመትጋት ላይ ትገኛለች። በአሁኑ ወቅት ዓለማችን በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በፈጣን የቴክኖሎጂ ምጥቀት በመመራት ላይ ትገኛለች። የካፒታልና የጉልበት ብዛት ብቻቸውን የአንድን ሀገር የበላይነት የሚያረጋግጡበት ዘመን አክትሞ የዲጂታል እውቀትና ፈጠራ የኢኮኖሚ ጥንካሬ ዋና መስፈርት ወደመሆን ተሸጋግሯል። የፋይናንስ ሥርዓቱ፣ የንግድ ክፍለ-ኢኮኖሚው፣ የትምህርትና ሕክምና አገልግሎቱ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በዲጂታል መሠረተ-ልማት ላይ የተደገፉ ሆነዋል። በዚህ እጅግ ተወዳዳሪ በሆነው የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ ተመዝኖ ለመገኘትና ውድድሩን በአሸናፊነት ለማጠናቀቅ የቴክኖሎጂ እውቀትን መታጠቅ የቅንጦት ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የቴክኖሎጂ እውቀት ወጣቶችን በግል፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ ዘርፍ ተወዳዳሪ የሚያደርጉ በርካታ መሠረታዊ ጥቅሞች አሉት። የወረቀት ገንዘብና ባህላዊ የገበያ መስተጋብር በዲጂታል ክፍያዎች እና በኢ-ኮመርስ እየተተኩ ነው። የቴክኖሎጂ እውቀት ያለው ወጣት በቀላሉ ዓለም አቀፍ የንግድ እድሎችን የመጠቀምና የፋይናንስ አካታችነት ተጠቃሚ የመሆን አቅም ይኖረዋል። ባህላዊ የሥራ አማራጮች እየጠበቡ ባሉበት በዚህ ዘመን፣ የቴክኖሎጂ እውቀት የታጠቀ ወጣት በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በአለበት ሆኖ በዓለም አቀፍ ገበያ ሥራ በመቀጠርና የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ረገድ ከፍተኛ እድል አለው። በተጨማሪም ቴክኖሎጂ ወጣቶች በትንሽ ካፒታል ትላልቅ የፈጠራ ሀሳቦችን ወደ ስታርታፕ ቢዝነሶች እንዲቀይሩ ያስችላቸዋል። በሰው ሰራሽ አስተውሎትና በዳታ ሳይንስ የታገዙ መፍትሔዎች የማህበረሰቡን መሠረታዊ ችግሮች መፍታት ይችላሉ። መረጃን በስርዓት የመተንተን፣ ውስብስብ ችግሮችን በጥበብ የመፍታትና ምክንያታዊ ውሳኔዎችን የመስጠት አቅምን ማሳደጉም ሌላው የቴክኖሎጂ እውቀት ጥቅም ነው። በተለይም በአሁኑ ወቅት የሀገራችን የፋይናንስ ሥርዓት በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ዲጂታል አሠራር እየተሸጋገረ ይገኛል። የባንክ አገልግሎቶች፣ የገንዘብ ዝውውሮች፣ የንግድ ክፍያዎችና የዕለት ተዕለት መስተጋብሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በሞባይል ባንኪንግ፣ በቴሌብር፣ በኢ-ብር እና በሌሎች የዲጂታል ክፍያ አማራጮች የታገዙ ሆነዋል። ይህ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር አገልግሎትን ፈጣንና ቀልጣፋ ከማድረጉ ባሻገር፣ ከዚህ ቀደም የባንክ አገልግሎት ያላገኙ ሰፊ የማህበረሰብ ክፍሎችን በፋይናንስ ሥርዓቱ ውስጥ በማካተት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ነገር ግን የዚህን ዘመናዊ አሠራር ፍሬ ሙሉ በሙሉ ለማጨድና የፋይናንስ አካታችነትን እውን ለማድረግ የዲጂታል ፋይናንስ እውቀት ከመቸውም ጊዜ በላይ ወሳኝ ሆኗል። ባህላዊው የባንክ አሠራር በአካል ወደ ቅርንጫፍ በመሄድና በባንክ ሠራተኞች ቀጥተኛ ድጋፍ የሚከናወን እንደመሆኑ፣ የቴክኖሎጂ እውቀት ማነስ ከፍተኛ ችግር አይፈጥርም ነበር። የዲጂታል ፋይናንስ ሥርዓት ግን ሙሉ በሙሉ በምስጢራዊነትና በግል ኃላፊነት ላይ የተመሠረተ ነው። የሞባይል ባንኪንግ ወይም የዲጂታል ዋሌት አገልግሎቶችን ስንጠቀም የምንጠቀማቸው የምስጢር ቁጥሮች እና አንድ ጊዜ ብቻ የሚያገለግሉ የማረጋገጫ ኮዶች ለሌላ ወገን ተልፈው ሊሰጡ የማይገባቸው የግል ቁልፎቻችን ናቸው። እውቀቱ የሌለው ሰው ግን አገልግሎቱን ለመጠቀም፣ ገንዘብ ለመላክ ወይም ለማውጣት የሌሎችን ሰዎች እርዳታ ለመጠየቅ ይገደዳል። ይህ ደግሞ የምስጢር ቁጥርን አሳልፎ ለመስጠትና ለገንዘብ ዘረፋ በሰፊው ያጋልጣል። ስለሆነም የዲጂታል ፋይናንስ አሠራርን በስፋት ከመዘርጋት ጎን ለጎን፣ እያንዳንዱ ዜጋ የዘርፉን መሠረታዊ እውቀት እንዲጨብጥ ማድረግ የህልውና ጉዳይ ነው። እውነተኛ የፋይናንስ አካታችነት ማለት አካውንት መክፈት ወይም አፕሊኬሽን መጫን ብቻ ሳይሆን፤ አሠራሩን በጥበብ፣ በደህንነት እና በራስ ተማምኖ የመጠቀም አቅም መገንባት ጭምር ነው። የዲጂታል ፋይናንስ እውቀት የራሳችንንና የቤተሰባችንን ሀብት ከዘረፋ የመጠበቂያ ጋሻችን በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ዜጋ ይህን እውቀት በመጨበጥ ራሱን ከአጭበርባሪዎች ሊጠብቅና የዘመናዊው ኢኮኖሚ እውነተኛ ተጠቃሚ ሊሆን ይገባል። ይህን አጠቃላይ እውነታ በማስመልከት የኢትዮጵያ መንግሥት፣ ወጣቶችን በዲጂታል እውቀት ለማብቃትና ሀገሪቱን የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስትራቴጂካዊ እርምጃዎችን በመውሰድ ላይ ይገኛል። ከእነዚህ ጥረቶች መካከል ግንባር ቀደሙ የኢትዮጵያ ሰባት ሚሊዮን ኮደሮች ሥልጠና ነው። ይህ የስልጠና ፕሮጀክት፣ ወጣቶች በነጻ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የቴክኖሎጂ ሥልጠናዎችን እንዲያገኙ መንገድ ከፍቷል። ፕሮግራሙ ይፋ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በየቀኑ እየተመዘገቡ ሥልጠናቸውን በመከታተል ላይ ይገኛሉ። ፕሮግራሙ ማንኛውም ወጣት ባለው ስማርትፎን፣ ታብሌት ወይም ኮምፒውተር በራሱ ጊዜና ፍጥነት ኦንላይን መማር እንዲችል ተደርጎ የተቃኘ በመሆኑ ከከተማ እስከ ገጠር ያሉ ወጣቶችን የማካተት አቅም አለው። ሥልጠናውን ያጠናቀቁ ወጣቶች ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የክህሎት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቶችን እያገኙ ሲሆን፣ ይህም በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ እድሎችን ለማግኘት በር ከፍቶላቸዋል። ይህ ጥረት የኢትዮጵያን "ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030" ስትራቴጂ ለማሳካትና ሀገሪቱን በአፍሪካ ዋና የኢኖቬሽንና የቴክኖሎጂ ማዕከል ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት፤ "ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ ላይ የምታደርገው ኢንቨስትመንት የወደፊት እጣ ፈንታዋን የሚወሰን ስትራቴጂ ነው። ወጣቶችና ምሁራን ይህንን የቴክኖሎጂ ማዕበል ተከትለው ሙያቸውን በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ካስደገፉ፣ የሀገራቸውን ችግር ከመፍታት ባለፈ በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ እና ተፈላጊ የመሆን ሰፊ እድል አላቸው" ማለታቸው ይታወሳል። የዲጂታል ዘመን ማዕበል ወደፊት ከመገስገስና ዓለምን ከመቀየር አይቆምም። የቴክኖሎጂ እውቀትን መታጠቅ ለወጣቱ የነገው ስኬት መያዣ፣ ለሀገራችን ደግሞ የኢኮኖሚ እድገት ማፋጠኛ ሞተር ነው። የመንግሥት የኮደሮች ሥልጠና ወጣቶች አቅማቸውን የሚያወጡበትና በዓለም አቀፍ መድረክ ተወዳዳሪ የሚሆኑበት ትልቅ እድል በመሆኑ፣ እያንዳንዱ ወጣት ይህን ወርቃማ እድል በመጠቀም የቴክኖሎጂ እውቀቱን ሊያዳብርና የዲጂታሏ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተሳታፊ ሊሆን ይገባል።
በፈተናዎች የማትታወክ ታላቅ ሀገር- ኢትዮጵያ
Oct 1, 2026 166
ኢትዮጵያን ታላቅ የሚያሰኛት በርካታ ታሪካዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሮአዊ ምክንያቶችን ማንሳት ይቻላል። ጥንታዊቷ ኢትዮጵያ ከውስጥም ከውጭም ለሚገጥሟት ተደራራቢ ፈተናዎች በቂና ምልዑ ምላሽ የመስጠት የካበተ ልምድ፣ ጥበብና አቅም አላት። በታሪኳ አያሌ ውጣ ውረዶችንና ማዕበሎችን አስተናግዳ ያለፈች ቢሆንም፣ አንድም ጊዜ ቢሆን ታላቅነቷን፣ ነጻነቷንና ኩራቷን አጥታ አታውቅም። ለዚህ ነው በባዕዳን እጅ ያልወደቀችው፤ ለዚህ ነው ተስፈኛና ተስፋፊ ጠላቶቿን በማሳፈር በተግባር የተፈተነ ዝናን የተቀዳጀችው። በክብርና በነጻነት መሠረት ላይ የተገነባችው ታላቋ ኢትዮጵያ፣ ዛሬም በማይናወጥ አቋም ጽንታ ቆማለች። ኢትዮጵያውያን በዘመናት ሁሉ ሉዓላዊነታቸውንና ህልውናቸውን የሚፈታተን ሙከራ በተደረገ ቁጥር በጀግንነትና በጽናት አጸፋ የመመለስ ታሪካዊ ባህል አላቸው። የሕዝቦቿ ጠንካራ የአንድነትና የነጻነት መንፈስ ማንም በማይገምተው መልኩ ጠላትን እያሳፈረ የወዳጅን ልብ ሲሞቅ ኖሯል፤ ዛሬም ቀጥሏል። ሀገር በጫናዎችና በፈተናዎች ውስጥ በወደቀች ቁጥር ሕዝቦቿ ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን በመተው ለአንዲት ኢትዮጵያ ህልውና በአንድነት የቆሙበት አጋጣሚ በርካታ ነው። አድዋ ላይ የተቀዳጀነው ድል የዚሁ የማይናወጥ የአንድነት፣ የጽናትና የጥቁር ህዝቦች የነጻነት ምልክት ነው። ይህ የነጻነትና የሉዓላዊነት ፍቅር በትውልድ ዘንድ እንደ ሕያው እሳት እየተሸጋገረ የመጣ በመሆኑ፣ ሀገሪቱን ከማንኛውም ወቅታዊ ማዕበል በላይ አድርጎ አቆይቷታል። እንደ ዳግማዊ ዓድዋ የሚቆጠረው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያውያን የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ብቻ አይደለም። የይቻላል፣ የአይበገሬነት እና የጽናታችን ዘመን ተሻጋሪ የታሪክ አሻራ እንጂ። ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም፣ ገንዘብና እውቀት ይህንን ታላቅ ተጋድሎ በመፈጸም ዓለምን ማስደመም ችለዋል። ግድቡ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም የማደግና የመለወጥ ትልቅ አቅም ያላት ሀገር መሆኗን ማረጋገጫ ነው። ለም መሬቷን፣ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን፣ ማዕድኖቿን፣ ወንዞቿንና የሥራ ወዳዱን ሕዝቧን አስተናጅታ ወደፊት የምትገሰግስበትን መንገድ አመላክቷል። ኢትዮጵያ በየዘመናቱ የሚገጥሟትን ወቅታዊ ፈተናዎች በብልህነትና በጽናት በማለፍ፣ የወደፊት ብሩህ ተስፋዋን መገንባት የምትችል ሀገር መሆኗን በዚሁ ታላቅ ፕሮጀክት ደግማ አረጋግጣለች። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በመደመር እሳቤ እየተመራች ታላቅነቷን እያስቀጠለች ትገኛለች። የመደመር መንግሥት ዋና ዓላማ ኢትዮጵያ በልኳ እንድትቀመጥ ማድረግ ነው። የኢትዮጵያ ልክ ደግሞ ነጻነቷን፣ ኩራቷን፣ የልማት ፍላጎቷንና ታላቅነቷን ማስቀጠል መቻል ነው። በታሪክ አጋጣሚዎች የሚያጋጥሙ የውስጥ ችግሮችን እንደ መልካም አጋጣሚ በመውሰድ፣ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላቶችና የውስጥ ባንዳዎች ሀገሪቱን ለማዳከም ይሞክራሉ። ነገር ግን ኢትዮጵያ ባዕዳንንና ባንዳዎችን ማሳፈር የሁልጊዜ ተግባሯ ነው። የመደመር እሳቤ ሀገሪቱን ከድህነት አውጥቶ ከታሪኳና ከገጽታዋ ጋር የሚመጥን ደረጃ ላይ ለማስቀመጥ ይተጋል። ይህ አካሄድ የሰው ኃይልን፣ የተፈጥሮ ጸጋን፣ ባህላዊና ታሪካዊ ሀብቶችን አስተናብሮ ለጋራ ብልጽግና ማዋልን መዳረሻው ያደረገ ነው። የውስጥ ልዩነቶችን ወደ ውበትና ጥንካሬ በመቀየር፣ ኢትዮጵያን በራሷ እግር በጽኑ እንድትቆም ያደርጋል። ዛሬም የማትናወጠውና የማትሸበረው ኢትዮጵያ በልጆቿ ብርቱ ክንድ ወደፊት እየተመለከተች በፍጥነት እየተራመደች ነው። ኢ-ፍትሐዊነትን ለማረም፣ ሉዓላዊነቷን ለማጽናት እና የሕዝቡን የልማት መሻት ለመፈጸም ጥረት እየተደረገ ይገኛል። ወቅታዊ ማዕበሎች፣ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ውጣ ውረዶች ወይም የውጭ ጫናዎች የቱንም ያህል ቢበረቱ፣ የኢትዮጵያን ሕልውናና ታላቅነት ሊያናውጡት አይችሉም። የኢትዮጵያን ታላቅነት እውን የሚያደርጉና ኢትዮጵያውያን በሀገራቸው እንዲኮሩ የሚያደርጉ ሜጋ ፕሮጀክቶች እውን እየሆኑ ነው። በኮሪደር ልማት የከተሞችን ገጽታ በመቀየር ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ በማድረግ ላይ ይገኛል።በሌማት ትሩፋት የዜጎችን የምግብ ዋስትና የሚያረጋግጥና የካፒታል አቅምን የሚያሳድግ ስራ ነው። በገበታ ለሀገር እና በገበታ ለትውልድ የተፈጥሮ ሀብቶችንና የታሪክ ስፍራዎችን ወደ ትልቅ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ አቅም የለወጡ ፕሮጀክቶች ናቸው። በግብርናው ዘርፍ የተመዘገበው የስንዴ ምርታማነት፦ ሀገሪቱን ከፈላጊነት ወደ ላኪነት ያሸጋገረ የብሄራዊ አቅም ማሳያ ነው። በትክክለኛ ጎዳና ላይ የምትገኘው ኢትዮጵያ በምንም የማትናወጥና የማትሸበር ሀገር ናት። ኢትዮጵያ ትናንት በጽናት አልፋለች፤ ዛሬም ፈተናዎችን በልማትና በአንድነት እያሸነፈች ትራመዳለች። ነገም ቢሆን ጠላቶቿን እያሳፈረች፣ ሉዓላዊነቷን አስከብራ፣ የታሪኳና የጽናቷ ባለቤት እንደሆነች በከፍታና በክብር ጉዞዋን ትቀጥላለች።
የቀጣናው ልማት እና ስበት ማዕከል - ኢትዮጵያ
Sep 30, 2026 220
ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ እና በአፍሪካ ቀንድ ቀጣና ታሪካዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና በዘላቂ ሰላምና ጸጥታ ማስከበር ስራዎች ውስጥ ዘመን አይሽሬ ሚና ያላት ሀገር ናት። ኢትዮጵያ በቀጣናው ዲፕሎማሲ ማዕከል ሆና እያገለገለች ሲሆን፣ ለዚህም በምስራቅ አፍሪካ ልማት በይነ-መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ምስረታ እና ማጠናከር ውስጥ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ የቀጣናው ሀገራት በትብብር እንዲሰሩ መንገድ የጠረገችበትን ታሪክ ማንሳት ይቻላል። በቀጣናው ያለውን የአልሸባብ እና መሰል አክራሪ ቡድኖችን ስጋት በመቀነስ ረገድ የድንበር እና የቀጣናውን ደህንነት ለማስጠበቅ ግንባር ቀደም ሚናም እየተወጣች መሆኗን ማንሳት ይቻላል። ይህ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ ህብረት ስር በመሆን በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ በሶማሊያ እና በሩዋንዳ ሰላም አስከባሪ ሰራዊት በማሰማራት በሀገራቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የማይተካ ሚና የተጫወተችና አሁንም በሶማሊያና ደቡብ ሶዳን የቀጠለች የቀጣናው አርአያ ናት። ኢትዮጵያ በቀጣናው ግጭቶች በዘላቂነት ተወግደው የልማት ትስስሮች እንዲፋጠኑ በሰላም ማስከበር ተልዕኮም ጭምር ከፍተኛ ሚና እየተወጣች ትገኛለች። ቀጣናው በኢኮኖሚ እና መሠረተ-ልማት የበለጠ እንዲተሳሰር የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ለማጠናከር ቀጣይነት ያለው ስራ ሰርታለች። ለአብነትም ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እንዲሁም ለኬንያ የኤሌክትሪክ ሃይል በማቅረብ የቀጠናውን የሃይል ትስስር እውን እያደረገች ትገኛለች። በትራንስፖርት እና የሎጂስቲክስ ዘርፍም የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀጣናውን ሀገራት በማስተሳሰር ሂደት የአንበሳውን ሚና እየተወጣ ይገኛል። በተጨማሪም ከሱዳን፣ ከደቡብ ሱዳን፣ ከሶማሊያ እና ከኤርትራ በተለያየ ምክንያት ለተሰደዱ ወገኖች ጋሻ እና መከታ በመሆን ዓለም አቀፍ ምስጋና የተቸራት ሀገር መሆኗንም መጥቀስ ይቻላል። ዛሬም ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና አጋርነትን ማዕከል ያደረጉ ትብብሮች እንዲጠነክሩ ከየትኛውም ጊዜ በላይ ተግታ እየሰራች ትገኛለች። ባለፉት ጥቂት ዓመታት በቁርጠኝነት እየሄደችበት የሚገኘው ይህ መንገድ የቀጣናውን የጋራ ተጠቃሚነትና ራስን የመቻል ጥረት የሚያፋጥን መሆኑ እሙን ነው። ሂደቱ ኢትዮጵያ ከጥንት ጀምሮ ከጎረቤት ሀገራት ጋር አብሮ ለመልማት ያላትን ጽኑ ፍላጎት በገሃድ እየገለጠ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ቀናትም በምሥራቅ አፍሪካ መሪዎች መካከል የተደረጉት በከፍተኛ ደረጃ የሚታዩት ውይይቶች ቀጣናዊ ትስስርን እና የኢኮኖሚ አቅምን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የተወሰዱ ቁርጠኛ እርምጃዎችን ያሳያሉ። እነዚህ ግንኙነቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ለማስቀደም እና እምነትን ለመገንባት እድል የሚፈጥሩ ናቸው። ኢትዮጵያ እና ጂቡቲ ከዳመርጆግ እስከ ደወሌ የሚዘረጋውን 120 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የተጣራ ነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧ መስመር ፕሮጀክት ይፋ ያደረጉ ሲሆን፣ ይህም የድንበር ተሻጋሪ ንግድ እንቅስቃሴን በከፍተኛ ሁኔታ ይለውጣል ተብሎ ይጠበቃል። በሌላ በኩል የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ግንኙነቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ውይይት በአዲስ አበባ አካሂደዋል። በተለይ 120 ኪሎ ሜትር የነዳጅ ማስተላለፊያ ቧንቧው፣ የባሕር ዳርቻ የነዳጅ ማከማቻና ማሰራጫን ከሀገር ውስጥ የመሰረተ ልማት አውታሮች ጋር ለማገናኘት የታቀደ የልማት ስራ ነው። የቧንቧው የማከማቸት አቅም 400 ሚሊዮን ሊትር ነው። ይህ የነዳጅ ቧንቧ መስመር በኢትዮጵያና ጂቡቲ የንግድ ኮሪደር ላይ ያለውን ትልቅ ማነቆ የሚቀርፍ ነው። የቧንቧ መስመሩ መዘርጋት በመንገድ ላይ የሚባክነውን ጊዜ ይቀንሳል፤ የትራንስፖርት ወጪን ይቀንሳል፣ እንዲሁም የነዳጅ አቅርቦትን አስተማማኝ የሚያደርግ ሲሆን ይህም በቀጣናው ላሉ የንግድ ተቋማትና ድርጅቶች ትልቅ ጥቅም ይሰጣል። ዛሬም በላሙ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ እና ሌሎች መሪዎች ከዳንጎቴ ጋር በመሆን የ16 ቢሊዮን ዶላር ነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት ግንባት የመሠረት ድንጋይ አኑረዋል። በላፕሴት ኮሪደር አቅራቢያ የሚገኘው ይህ ማጣሪያ ኬንያ፣ ኢትዮጵያ፣ ኡጋንዳ፣ ታንዛኒያ፣ ደቡብ ሱዳን እና የኮንጎ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክን ያካተቱ ገበያዎችን ለማገልገል የታለመ ነው። ዳንጎቴ ለምሥራቅ አፍሪካ መንግሥታት የ30 በመቶ የድርሻ ባለቤትነት እንዲኖራቸውም ጋብዟል። ፕሮጀክቱ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2030 ይጠናቀቃል ተብሎ የታቀደ ሲሆን፣ ከ50 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ እድሎችን እንደሚፈጥር ተገምቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እነዚህ ጅምር ስራዎች መሬት እንዲነኩ እና ፍሬ እንዲያፈሩ በከፍተኛ ትጋት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። የቅርብ ጊዜ እንቅስቃሴዎቻቸው ዲፕሎማሲን ወደ ተጨባጭ ውጤት የመቀየር ጉዞ ማሳያ ነው። ይህ አካሄድ በአፍሪካ ቀንድ እና ምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የመሰረተ ልማት ዝርጋታ እና ጠንካራ የንግድ ትስስርን ለማጠናከር ተስፋ ሰጪ ጥረት መሆኑን ማየት ይቻላል። በጥቅሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በዚህ ቀጣና እየተወጡ ያሉት የመሪነት ሚና ኢትዮጵያን እንደ ትልቅ ገበያ፣ በድንበር ተሻጋሪ መሰረተ ልማት አጋር እና ለተሻለ ቀጣናዊ ቅንጅት አነቃቂ ኃይል ሆና እንድትቀጥል ያደርጋታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በቀጣናው የልማት ማዕከል እንድትሆን የጀመሩትን በጎ እርምጃ ወደ ሌሎች በማጋራት የአፍሪካ ቀንድን የበለጠ ለማስተሳሰር ምቹ መደላደል ይፈጠራል። በታሪክ ኢትዮጵያ ያካበተችውን የቀጣናው ልማት እና ስበት ማዕከልነቷን ለማስቀጠል የሚያስችል እንቅስቃሴ ነው።
ኢትዮጵያ የሥነ-ምግብ መሶብ፤ አፍሪካዊት የጤናማ ትውልድ ግንባታ ተምሳሌት
Sep 30, 2026 110
በአፍሪካ ሕፃናት ላይ የሚያጋጥመው የምግብና የሥነ-ምግብ ደኅንነት ችግር ከጤና ተቋማት አቅም የዘለለና የፖሊሲ አፋጣኝ ጣልቃ ገብነትን የሚጠይቅ ብሔራዊና አህጉራዊ አጀንዳ ነው። የግብርና፣ የጤና፣ የውሃ፣ የትምህርት፣ የገቢ ማስገኛና የማኅበራዊ ጥበቃ ፖሊሲዎች በተቀናጀ መንገድ የሚመልሱት ብሔራዊ የልማት ጉዳይ ነው። ሕፃናትን ለመመገብ የሚያስፈልገው ምግብ ከየት ይመጣል? የሚመረተውስ በቂና ገንቢ ነውይ? ሀገራት ይህን ታላቅ ሀላፊነት በራሳቸው ሀብትና ተቋም ለማስቀጠል ምን ያህል ተዘጋጅተዋል? የሚሉት ጥያቄዎች ዛሬ ላይ ሊመለሱ የሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮች ናቸው። እነዚህ ወሳኝ ሐሳቦች በአሜሪካ ኒውዮርክ ከተማ በተካሄደው 81ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ጎን ለጎን በተካሄደው ''Our Children Cannot Wait'' መድረክ ላይ በሰፊው ተስተጋብተዋል። መድረኩ የሕፃናትን ሕይወት መጠበቅ የነገ ተስፋ ሳይሆን የዛሬ አጭርና ግልጽ ውሳኔ መሆኑን በደማቅ ሁኔታ አሳይቷል። የአፍሪካ የሥነ-ምግብ ሉዓላዊነት ጥሪ፤ በአህጉሪቷ መሪዎች አንደበት!! የአፍሪካ ሕብረት የሥነ-ምግብ ሻምፒዮን እና የሌሶቶ ንጉሥ ሌትሲ ሳልሳዊ በአህጉራዊው መድረክ ላይ እንዳሰመሩበት፣ አፍሪካ የልጆቿን ሥነ-ምግብ በራሷ መንግሥታትና ሃብት ማስተዳደር የሚያስችላትን የሥነ-ምግብ ሉዓላዊነት ማጠናከር አለባት። የአንድ ሀገር የወደፊት አቅም ከሚገለጽባቸው መለኪያዎች መካከልም የሕፃናቷ ጤናና የአእምሮ እድገት ይገኙበታል። ይህ አቋም የውጭ እርዳታን ሙሉ በሙሉ በመካድ የቀረበ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ፋይናንስና የራስን አቅም ከዘላቂ የምግብ ሥርዓት ጋር የማጣመር ራዕይ ነው። የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶም በበኩላቸው የሕፃናት ሥነ-ምግብ ደኅንነት ከአስተማማኝ የሰው ሃብት ግንባታ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ መሆኑን አንስተዋል። የሕፃናትን ሕይወት ማዳን መርሆዎችና የተግባር ጥሪ በሚል ዐበይት ርዕስ የቀረበው ሰነድም፤ የሕፃናትን ሕይወት መጠበቅ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ብሔራዊ አጀንዳነት ቀርቧል። የሀገር ውስጥ ፋይናንስን ማጎልበትና ዓለም አቀፍ አጋርነቶች በሀገራት በሚመሩ ዕቅዶች ላይ እንዲመሰረቱ ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ የሥነ-ምግብ ደኅንነት ሉዓላዊነት ትልም፤ የጤናማ ትውልድ ግንባታ መሰረት!! ኢትዮጵያ እስከ 2030 ድረስ ከሁለት ዓመት በታች ባሉ ሕፃናት ላይ መቀንጨርን ለማስወገድ የያዘችውን የ15 ዓመት ብሔራዊ ግብ የሰቆጣ ቃል ኪዳንን በመተግበር ላይ ትገኛለች። ይህ ጥረት በጤና ዘርፍ ብቻ የተገደበ አይደለም። ግብርናን፣ ውሃን፣ ትምህርትን፣ ገቢ ማስገኛንና ሌሎች ዘርፎችን በማስተሳሰር የሥነ-ምግብ ጉዳይን ከምግብ ምርት እስከ ቤተሰብ ማዕድ ድረስ በሚዘልቅ ሁለንተናዊ አቅጣጫ ለመመለስ የሚያስችል ሥርዓት እየተገነባ ነው። በዚህ ሰንሰለት ውስጥ የምግብ ብዝኅነት የላቀ ሚና አለው። የወተት፣ የእንቁላል፣ የዶሮ ሥጋ፣ የማር፣ የአትክልትና የፍራፍሬ ምርትን በማቀናጀት የሚተገበረው የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብርም የምግብ መጠንን ከማሳደግ ባሻገር የምግብ ዓይነትና ጥራትን ለማስፋት የሚያግዝ አቅጣጫ ሆኗል። በተመሳሳይ የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የሀገር ውስጥ የስንዴ አቅርቦትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ለማጠናከር ያግዛል። ይሁንና የሥነ-ምግብ ደኅንነት ከአንድ የሰብል ምርት በላይ ስለሆነ ስንዴን ከሌሎች የምግብ ምርቶች ጋር ማጣመር የተሟላ የምግብ መሶብ ለመገንባት ወሳኝ ነው። የ2023 ብሔራዊ የምግብና ሥነ-ምግብ ስትራቴጂ መነሻ ጥናት እንደሚያመለክተው 39 በመቶ የሚሆኑ ከአምስት ዓመት በታች ሕፃናት የመቀንጨር ተጠቂ እንደነበሩ ያመላክታል። የካናዳ ዓለም አቀፍ የሥነ-ምግብ ድርጅት ኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የ2024 ግምገማ እንደሚያሳየው በሀገሪቱ ከ6 ሚሊዮን በላይ ሕፃናት የመቀንጨር ተጠቂዎች ናቸው። ለዚህም የኢትዮጵያ ሁለንተናዊ የሥነ-ምግብና የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ አጀንዳ ወሳኝ የምላሽ መስጫ አቅም መገንባ መሳሪያ ሆኖ ይጠቀሳል። የሥነ-ምግብ ብዝኅ ምርታማነት አቅም፤ የሕፃናት የሥነ-ምግብ ደኅንነት ዋስትና መቀንጨር የሕፃናትን የዕድገት አቅም ይጎዳል። ደም ማነስም በእናቶች፣ በሕፃናትና በሴቶች ጤና ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል። ሲዳመርም የዛሬ የሥነ-ምግብ ችግር የነገ የትምህርት፣ የምርታማነትና የኢኮኖሚ ጉዳይ ይሆናል። የኒውትሪሽን ኢንተርናሽናል የሥነ-ምግብ ዋጋ ትንታኔ እንደሚስረዳው፤ የኢትዮጵያ የሥነ-ምግብ ኢንቨስትመንት የትውልድ ዘላቂነትን የሚያስጠብቅ ወሳኝ አጀንዳ መሆኑን ያብራራል። የኢትዮጵያ የሰቆጣ ቃልኪዳን፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ ግብር፣ የስንዴ ምርታማነትና አጠቃላይ ሁለንተናዊ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ እመርታዊ ስኬትም ጤንነቱ የተጠበቀና ቀጣይነት ያለው ሀገር ተረካቢ ትውልድ የመገንባት አቅጣጫን የተከተለ ራዕይ ነው። ከአስመጪነት ወደ ራስን መመገብ፤ የኢትዮጵያ የግብርና ምርታማነት ፍኖት በኒውዮርክ በተካሄደው የተባበሩት መንግሥታት የ2026 ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ጫናን መቋቋም የሚችለውን የስንዴ ምርት በማስፋፋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ከስንዴ አስመጪነት ወደ አፍሪካ ትልቋ የስንዴ አምራችነት መሸጋገሯን አብስረዋል። ይህ ታላቅ ስኬት አፍሪካ በራሷ አቅም ራሷን መመገብ እንደምትችል የሚያሳይ ትልቅ ተምሳሌታዊ መልዕክት ነው። የምግብ ዋስትና ከውጭ ገበያ በመግዛት ብቻ የሚጠበቅ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ምርት፣ የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ መስኖና የገበያ ሥርዓትን በማጣመር የሚገነባ የሉዓላዊነት ማሳያ መሆኑን አሳይቷል። ይህንንም አፍሪካ በራሷ አቅም ራሷን መመገብ እንደምትችል የሚያስተምር ተምሳሌታዊ መልዕክት ሆኖ ተላልፏል። ይህ መልዕክትም የምግብ ዋስትና ከውጭ ገበያ በመግዛት ብቻ የሚጠበቅ ጉዳይ ሳይሆን የሀገር ውስጥ ምርት፣ ቴክኖሎጂ፣ የተሻሻሉ ዝርያዎች፣ መስኖና የገበያ ሥርዓትን በማጣመር የሚገነባ አቅም መሆኑን ነው። በተለይም በማዕድ ላይ የሚቀርበው ምግብ ብዝኅነት ሕፃናትና ቤተሰቦች የተመጣጠነ ሥርዓተ ምግብ የሚያገኙበት ነው። ሕፃናት በትክክለኛው ዕድሜ ተገቢውን ምግብ ማግኘታቸውም ጤናማ ትውልድ የመገንባት ወሳኝ አቅም ይሆናል። የኢትዮጵያ ማዕድ ምልዑነት፤ የትውልድ ግንባታ መሰረት የገበሬው የምርታማነት አቅም ምግብ በበቂና ተመጣጣኝ ዋጋ ለቤተሰብ እንዲደርስ ያግዛል። ቤተሰቡ የተለያየና ገንቢ ምግብ ሲያገኝ የሕፃናት ሥነ-ምግብ ደኅንነት ይጠናከራል። ጤናማ ሕፃናት ደግሞ በትምህርት የተሻለ የመማር፣ በኋላም በሥራ የመሳተፍና ምርታማ የመሆንና ሀገርን የመገንባት አቅም ይኖራቸዋል። ከሰቆጣ ቃል ኪዳን እስከ ሌማት ትሩፋት፣ ከአትክልትና ፍራፍሬ እስከ ወተት፣ እንቁላልና ማር፣ ከመስኖ ስንዴ እስከ የቤተሰብ የምግብ ቅርጫት ድረስ የተመዘገቡ እመርታዊ ለውጦችም የዛሬ የምግብ ምርት ውሳኔ የነገ ትውልድ ጤና ላይ የተመሰረተ መሆኑን በግልጽ ያመላክታል። የአፍሪካ መሪዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 2026 ጠቅላላ ጉባኤ ያነሱት ጥያቄም ሕፃናትና ታዳጊ ልጆች እስኪያድጉ ድረስ እራሳቸውን መጠበቅ አይችሉም የሚለውን ነው። የምግብና የሥነ-ምግብ ደኅንነትን የማረጋገጥ ጉዳይም የዛሬ የልማት ውሳኔ ብቻ ሳይሆን ውጤቱ በነገ ጤናማ፣ የተማረና ምርታማ ትውልድ ላይ የተመሰረተ ይሆናል። የኢትዮጵያ የምግብና ሥነ-ምግብ ጉዞ ከአፍሪካ የሥነ-ምግብ ሉዓላዊነት ጥሪ ጋር የተቆራኘ በመሆኑ የራስን ምግብ ማምረት የዛሬን ማዕድ ለመሙላት ብቻ ሳይሆን፣ ነገ ሀገርን የሚረከብ ጤናማ፣ የነቃና ብቁ ትውልድ ለመገንባት የሚያስችል የዘላቂ ልማት ምሰሶ ነው።
ትንታኔዎች
ብሔራዊ ጥቅም - የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ቀይ መስመር
Oct 2, 2026 245
ትልቅ ሀገር ፤ ትልቅ ሕዝብ ፣ ታላቅ ርዕይ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ባለው የረዥም ዘመን ታሪክ በተለያዩ ታሪካዊ፣ ጂኦፖለቲካዊና ውስጣዊ የፖለቲካ ሁነቶች ውስጥ አልፏል። የዓለም መንግሥታት ማኅበር ፣ በመቀጠልም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መስራች አባል በመሆን ለዓለም አቀፍ ሕግ የበላይነት፣ ለሉዓላዊነትና ለጋራ ደህንነት መከበር የጸና አቋም ስትሟገት ቆይታለች። በዚህ መርህ መሰረት ባደረገ ዲፕሎማሲያዊ አካሄዷ፣ ኢትዮጵያ ለፓን-አፍሪካኒዝም እንቅስቃሴ መጠናከር፣ ለቀጣናዊ ወንድማማችነት እንዲሁም ለአፍሪካ ሀገራት የነፃነት ትግል ትልቅ ድጋፍ በማድረግ የአህጉሪቱ የነፃነትና የአንድነት ምልክት መሆን ችላለች። የዚህ ታሪካዊና ዲፕሎማሲያዊ ስኬት ውጤት በመሆንም፣ መዲናዋ አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት (የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት) እና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቷ ዲፕሎማሲያዊ ማዕከልነቷን አስመስክራ ቀጥላለች። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ታሪክ ከህልውና፣ ነጻነት እና ብሔራዊ ጥቅሟን ከማስከበር ጋር ተሳስሮ የዘለቀ የጽናት ጉዞ ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ ለብሔራዊ ጥቅሟና ለሉዓላዊነቷ የማይደራደር ቀይ መስመር በመዘርጋት፣ የጂኦፖለቲካዊ ውጣ ውረዶችን በብልሃትና በጽናት ስትሻገር ቆይታለች። በዚህም መስመር ለዘመናት በዓለም አቀፍ መድረኮች ጥቅሞቿን አስጠብቃለች። ለሌሎች ጥቅምም ቆማለች። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ታሪክ ውስጥ አንድ ትልቅ ስኬት ሆኖ የሚጠቀሰው የዓድዋ ድል ነው። ይህ ድል፣ የጥቁር ሕዝቦች የነፃነት ምልክት ከመሆኑ ባሻገር ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ እኩል ሀገር እንድትታይና የዲፕሎማሲያዊ ገዢነት ምሳሌ እንድትሆን አድርጓታል። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ ከረጅም ታሪካዊ መሠረቱና የፓን-አፍሪካኒዝም ማዕከልነቱ ባልተራቀቀ መልኩ፣ አሁን ባለንበት ዘመን አዲስ የልማት፣ የሉዓላዊነትና የስትራቴጂካዊ ተፅዕኖ ምዕራፍ ውስጥ ይገኛል። የመደመር መንግሥት ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ የሀገሪቱን የውጭ ግንኙነት መርሆዎች በአዲስ መነቃቃት ላይ ይገኛል። የዚህ አዲስ የዲፕሎማሲ እይታ ዋና መሠረት ኢትዮጵያዊ ብሔራዊ ጥቅምንና ሉዓላዊነትን ቀይ መስመር ያደረገ፣ ነገር ግን ለጎረቤት ሀገራት ሰላም፣ ልማትና የጋራ እድገት ቅድሚያ የሚሰጥ ተግባራዊ አቀራረብ ነው። የመደመር መንግስት ዲፕሎማሲ አብሮ የመበልጸግ ፅንሰ-ሐሳብን ያቀነቅናል። ኢትዮጵያ ሰላምና ልማት የሚረጋገጠው ጎረቤቶቿ ሰላምና ልማት ሲያገኙ ብቻ እንደሆነ በማመን "ቅድሚያ ለጎረቤት" የሚል መርህ ይከተላል። ይህ መርህ ከቀደመው ባህላዊ የፖለቲካ ዲፕሎማሲ ተሻግሮ ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ፣ ንግድና መሠረተ-ልማት ትስስር ተቀይሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጎረቤት ሀገራት መሪዎች በተለይም በቅርቡ ከኬኒያና ከጂቡቲ መሪዎች ጋር ያደረጓቸው ውይይቶች የአፍሪካ ቀንድን የማስተሳሰር ጥረት ማሳያ ናቸው። ይህ የኢኮኖሚ ትስስር በተጨባጭ የሚገጥም ጭምር ነው። ኢትዮጵያ ታዳሽ የኤሌክትሪክ ኃይል ለኬኒያ፣ ለጂቡቲና ለሱዳን በማቅረብ ቀጣናውን በኢነርጂ ድልድይ አስተሳስራለች።አዲስ አበባን ከጂቡቲ ወደብ የሚያገናኘው የባቡር መስመርና ወደ ኬኒያ (ላሙ ወደብ) የሚያቀኑት የላፕሴት (LAPSSET) ኮሪደር ፕሮጀክቶች የንግድ ፍሰቱን ለማሳለጥ ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ ናቸው።የጋራ የውሃ ሀብቶችን በጋራ የመጠቀምና ድንበር ተሻጋሪ የንግድ ቀጠናዎችን የማስፋፋት ሥራዎች ተከናውነዋል። ነገር ግን ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የሚያስከብሩ አበይት አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ የማትንበረከክና የማታወላውል አቋም አላት።ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከፍተኛ የጂኦፖለቲካዊና የዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች ቢኖሩበትም፣ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የመጠቀም ተፈጥሯዊ መብቷን በማስከበር የግድቡን ግንባታና የውሃ ሙሌት በውጭ ጫና ሳታቋርጥ ከፍጻሜ አድርሳለች። ለዘመናት የቆየውን ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ መሠረት በማድረግ፣ ኢትዮጵያ ዘላቂና ሕጋዊ የባህር በር ፍላጎቷን በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሠራች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነትና ግዛት አንድነቷን በተግባር የተጻረሩና አላስፈላጊ ጫናዎችን ለመጫን የሞከሩ አካላትን ዓለም አቀፍ ሕግንና ደንብን መሠረት ባደረገ መልኩ የመመከትና ምላሽ ለመስጠትም ወደ ኋላ የማትል መሆኗን በተግባር አሳይታለች።
ከአባይ እስከ ቀይ ባህር - የኢትዮጵያ አይበገሬነት እና የግብጽ ሴራ
Oct 2, 2026 312
ኢትዮጵያ በረጅም የታሪክ ጉዞዋ የብዙ ውጫዊ እና ውስጣዊ ፈተናዎች ማዕከል ሆና የቆየች ሀገር ናት።ሀገሪቱ ያሏትን ተፈጥሮአዊ ሀብቶች እንዳትጠቀም ፣የጂኦፖለቲካዊ አሰላለፍ ውስጥ የሚገባትን ቦታ እንዳትይዝ ለዘመናት የተደራጀ እና የተቀናጀ ሴራ እና ጫና ሰለባ ሆናለች። ከእነዚህ ዘመናትን ከተሻገሩ ሴራዎች ጀርባ ደግሞ ግብጽ ትገኛለች። የግብፅ አቋም እና የውጭ ፖሊሲ በዋናነት የሚያተኩረው የዓባይን ወንዝ ውኃ ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር የተረጋጋች፣ጠንካራ እና በኢኮኖሚ የበለጸገች ኢትዮጵያ እንዳትፈጠር በማድረግ ላይ ነው። ግብፅ ይህን ዓላማዋን በተለያዩ ጊዜያት በቀጥታ በጦርነት ለማስፈጸም ያደረገችው ጥረት በጀግኖች ኢትዮጵያዊያን ሽንፈት ተከናንባ እንድትመለስ አድርጓታል።ይህ አልሳካ ሲላት ደግሞ የኢትዮጵያን የውስጥ ተቃዋሚዎች እና አማጺ ቡድኖችን በመደገፍ ሀገሪቱን የማዳከም ስልት ስትከተል ኖራለች። ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ ባሉት አስርት ዓመታት፣ ግብፅ በአፍሪካ እና በአረብ ዓለም ውስጥ ተፅዕኖዋን ለማስፋት ስትጥር፣ የዓባይ ተፋሰስን እና ቀይ ባሕርን ለደህንነቷ እንደ ዋና መሠረት አድርጋ ተመልከታቸዋለች።ኢትዮጵያ፣ በዓባይ ወንዝ ላይ ያለች ትልቅ እና እየጎለበተች ያለች ሀገር በመሆኗ በተፈጥሮ ሀብቷ እንዳትጠቀም ሴራዋን አጠናከረች።ለዚህም ዓላማ ስኬት በሰሜን ኢትዮጵያ የተዳፈነ እሳት ማስቀመጥ ነበረባት።ኤርትራን ለመገንጠል፤ ጉዳይ ፈጻሚውን ሻዕቢያን መመስረት ግቧ አደረገች። የኤርትራ ነፃነት ግንባር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1960 በካይሮ በተሰደዱ የኤርትራ ፖለቲከኞች እና ተማሪዎች ተመሠረተ። በዚህ ሂደት ግብፅ የኤርትራ የመገንጠል እንቅስቃሴ እንዲፋጠን ፖለቲካዊ ምህዳር የፈጠረች ሲሆን፣ የግብፅ ሚዲያዎች ደግሞ ለእዚህ እኩይ ዓላማ የሚያግዝ ፕሮፓጋንዳ አሰራጮች ነበሩ። በዚህ አሰላለፍ ውስጥ ሻዕቢያ የግብፅ ዋና ስትራቴጂካዊ መሳሪያ ሆኖ አገልግሏል። ግብፅ ለሻዕቢያ አስፈላጊውን ወታደራዊ፣ የገንዘብ እና የዲፕሎማሲያዊ ሽፋን በመስጠት በሰሜን ኢትዮጵያ ለረጅም ዓመታት ለተካሄደው ውጊያ ስንቅ እና ትጥቅ እንዲያገኝ አድርጋለች። የኤርትራ መገንጠል ዋነኛ ውጤት ኢትዮጵያ ታሪካዊ የባህር በሮቿን አጥታ የተዘጋች ሀገር እንድትሆን ማድረግ ነበር። ይህ ደግሞ የግብፅን የረጅም ጊዜ ስትራቴጂካዊ ፍላጎት ያሳካ እርምጃ ሆኗል። ለዚህ እኩይ ዓላማ ለተወለደው ቡድን ደግሞ ቀጥተኛ የገንዘብ፣ የወታደራዊ እና የስልጠና ድጋፍ የመስጠት ፖሊሲን ተከትላለች።በግብፅ ስሌት፣ ለእንደዚህ ዓይነቶቹ አካላት የሚደረገው ድጋፍ በተከታታይ የኢትዮጵያ መንግሥታት ላይ ጫና ለመፍጠር ይረዳል የሚል ነው።በመጠኑ የተሳካለት ቢመስልም ያሰበችውን ማግኘት አልቻለችም።ብርቱዋ ኢትዮጵያ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አሳክታ አጀንዳዋን ቀይ ባህር ላይ አድርጋለች። ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ፖለቲካዊ ጫና እንደ ጠቃሚ መንገድ አድርጋ ቀጠለችበት። ግብፅ ከሻዕቢያ ባለፈ ለሀገር ውስጥ ታጣቂዎች ድጋፍ በመስጠት የተወሰኑ የትንኮሳ ድርጊቶችን እንዲፈጽሙ ረድታለች። አስመራ በታሪክ በተረጋገጠ መልኩ የፀረ-ኢትዮጵያ እንቅስቃሴዎች ሁሉ መነሻ እና ማዕከል ሆና አገልግላለች። ስውሩ ጣልቃ ገብነት ኢትዮጵያ ትልልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን መተግበር እንዳትችል አደረጋት። የተረጋጋች ኢትዮጵያን እውን ከማድረግ አንጻር የራሱን መጥፎ ጠባሳ ጥሎ አልፏል። አሁንም ግብጽና ሻዕቢያ በቀረጹት ኢትዮጵያን የማዳከም ሥራ ላይ ሕገ-ወጡ ሕወሓት በዋና ተላላኪነት እና ጉዳይ ፈጻሚነት ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ሕወሓት ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ በሻዕቢያ የፖለቲካ እና የወታደራዊ ሥልጠና ሲያገኝ ነበር።ሕወሓት ሥልጣን በያዘበት ወቅት፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ የባሕር በር ባለቤትነት መብት ከሕግ አግባብ ውጭ አሳልፎ በመስጠት የሻዕቢያን እና የግብፅን ዓላማ በተሻለ መልኩ አሳክቷል። ኢትዮጵያ የባሕር በር በማጣቷ ምክንያት በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለወደብ ኪራይ እንድታወጣ ተገዳለች። ይህም የኢኮኖሚ እድገቷን የገታ እና ለውጭ ጥገኝነት የዳረጋት ዋነኛ ምክንያት ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን በቀይ ባሕር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ አካባቢ ኢትዮጵያ የነበራትን ታሪካዊ እና ስትራቴጂካዊ የበላይነት እንድታጣ አድርጓታል። የውስጥ አለመረጋጋት እና ጦርነቶች ዓባይን ጨምሮ ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶቿን በጊዜው እንዳትጠቀም እንቅፋት ሆነው ቆይተዋል። አሁንም ቢሆን ግብፅ ከኢትዮጵያ አልፋ የአፍሪካ ቀንድን ወደ አንድ ግዙፍ የጦር ሜዳ ለማሸጋገር ለሚሰሩ ወገኖች ይፋዊ ወታደራዊና የፕሮፓጋንዳ ድጋፍ በመስጠት ቀጣናዊ ስጋት መደቀኗን ቀጥላበታለች።] ኢትዮጵያ ለዘመናት በወራሪዎችና በውጭ ተጽዕኖዎች ሳትንበረከክ ሉዓላዊነቷን አስከብራ የኖረችበት ምስጢር፣ ታሪካዊ ጥንካሬዋንና የሕዝቦቿን አንድነት መሠረት ባደረገ ጽናት ነው። ግብፅ የኢትዮጵያን ግዛት ለመያዝ ያደረገቻቸው ተደጋጋሚ የወረራ ሙከራዎች በጉራዕና በጉንደት አውደ ውጊያዎች በኢትዮጵያውያን ጀግንነት ተመክተዋል። በተመሳሳይ መልኩ በዓለም አቀፍ መድረኮች፣ በወገንተኛ ሚዲያዎችና በማኅበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ለዘመናት ሲሰራጩ የቆዩ ሀሰተኛ መረጃዎችና የሳይኮሎጂካል ጦርነቶች በኢትዮጵያ እውነተኛ ዲፕሎማሲ ተሸንፈዋል ። አሁንም የግብፅና የኤርትራ (የሻዕቢያ) ወቅታዊ ስትራቴጂካዊ አሰላለፍም ሆነ የሕወሓት ተላላኪነት በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ጊዜያዊ ፈተናዎች ሆነው የሚያልፉ አኩይ ተግባራት እንጂ የኢትዮጵያን የሺህ ዓመታት የሀገርነት መሠረት ሊያናጉ አልቻሉም። ከዚህ አኳያ ያለፈውን ታሪክ በጥልቀት መረዳት፣ የታሪካዊ ጠላቶችን ሴራ መገንዘብና የጥፋት አሰላለፎችን ማወቅ የዛሬዋንና የነገዋን የበለጸገችና የተከበረች ኢትዮጵያ ለመገንባት፣ ሀገራዊ አንድነትን ለማጠናከር እንዲሁም ብሔራዊ ጥቅምን ለማስከበር ወሳኝና መተኪያ የሌለው መንገድ ነው። ኢትዮጵያ ለታሪካዊ ጠላቶቿ በየትኛውም መልኩ የማትንበረከክ ጽኑ አገር መሆኗን ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ታረጋግጣለች!
የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሳኤ
Oct 1, 2026 144
በመጽሔት አንለይ ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ ሰንቃ እየተጋች የምትገኝ የገናና ሥልጣኔና የታሪክ ማኅደር፣ የቱባ ባህልና የሕብረብሔራዊ አንድነት ካስማ ናት። በክትመትና ከተሜነት ሥልጣኔም የሺህ ዘመናት የሥልጣኔ ዐሻራ በጉያዋ ታቅፋለች። የከተሜነት አመጣጥ የሁሉም ክፍለ አህጉራት አባል ሀገራት የጋራ ታሪክ ነው። አፍሪካም ከጥንት ጀምሮ የተደራጁና የደረጁ የከተማ ሥልጣኔዎች የታሪክ መናኸሪያ መሆኗን ድርሳናትና መዛግብት ያስረዳሉ። ጥንታውያኑ የአክሱም፣ ጎንደርና ሐረር በኢትዮጵያ፤ ቲምቡክቱ፣ ካኖና ኦዮ በምዕራብ አፍሪካ፤ ግሬት ዚምባብዌ በደቡብ አፍሪካ፤ ኪልዋና ሞምባሳ በሕንድ ውቅያኖስ ዳርቻ የአፍሪካ ከተሜነት ሥልጣኔ ረጅም ታሪክ እንዳለው አስረጂዎች ናቸው። በአሁኑ ወቅትም አፍሪካ የዓለም አቀፍ ቱሪስቶችን ቀልብ የሚስቡ ማራኪ፣ ውብና ጽዱ ገጽታን የተላበሱ ከተሞችን መገንባቷን ኪጋሊ፣ ራባት፣ ኮቶኑ፣ ታንጀር፣ ማራካሽ፣ አቡጃ፣ ጋቦሮኔ፣ ዊንድሁክ፣ ኬፕ ታውን እና መሰሎችም ሁነኛ አብነቶች ናቸው። በአፍሪካ ከተማና የከተሜነት ሥርዓትና ምኅዳር ከጉስቁልና ወደ ተሻለ የልዕልና መንገድ የሚያመራበት ከፍተኛ ዕድል አለው። ይህም የአህጉሪቷ የከተማ ሕይወት በተሰናሰለ መሰረተ ልማት የሚመራና ብሩህ ተስፋ ያለው መሆኑን ያስረዳል። ኢትዮጵያ፤ የጥንታዊ ሥልጣኔ ዐሻራ ያረፈባቸው ከተሞች ሀገር!! የኢትዮጵያ የከተሜነት ዐሻራ ከጥንታዊ የሥልጣኔ ታሪኳ ጋር ተሰናስሎ የቀጠለና ያልተቋረጠ ሂደት ነው። አክሱም የንግድና የሥልጣኔ ማዕከል፣ ሐረር የንግድ፣ የባህልና የኃይማኖት መናኸሪያ ሆና ቆይታለች። ጎንደር ደግሞ የኢትዮጵያ ንጉሣዊ አስተዳደር ማዕከል ሆና በማገልገል ታሪክ ሰርታለች፤ ሰንዳለችም። አዲስ አበባ ደግሞ በዘመናዊ ኢትዮጵያ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ማዕከል በመሆን የኢትዮጵያ ዘመናዊ የከተሜነት ጉዞን መርታለች፤ እየመራችም ይገኛል። የከተማ ዕድገት ፈጣን ሲሆን ተጓዳኝ ጫናዎችም ይመጣሉ። የዓለም ባንክ በአዲስ አበባ ላይ ያደረገው የከተማ ጽናት ጥናት ፈጣን የከተማ ዕድገት ከጎርፍ፣ ከውሃ እጥረት፣ ከትራንስፖርት፣ ከሥራ አጥነትና ከማህበራዊ ተጋላጭነት ጋር የሚያያዙ ጫናዎችን እንደሚያመጣ ያመለክታል። ከዓመታት በፊትም አዲስ አበባና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች በመሰረተ ልማት ክፍተትና በእርጅና ብዛት የሚያቃናቸውን የለውጥ አብዮት ሲጠባበቁ እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው። በዚህም የኢትዮጵያ የከተማ ትንሳኤ ትርጉሙ የከተሞችን ፊት በማስዋብ ብቻ የተወሰነ እንዳልሆነ መመልከት ይቻላል። የኑሮ ጥራትን፣ ምርታማነትን፣ የሥራ ዕድልን፣ የመጓጓዣ ቅልጥፍናን፣ የአካባቢ ጥበቃንና የሕዝብ ተሳትፎን አስናስሎ የሚጓዝ ሂደትን መፍጠር ይጠይቃል። ከቢሮ ጽዳትና ውበት ወደ የኢትዮጵያ ከተሞች የትንሳኤ ብስራት፤ ከእርጅና ወደ ልዕልና!! በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራው የመደመር መንግሥት በኢትዮጵያ ሀገራዊ ለውጡ ማግስት ጽዳትና ውበት ለኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ይገባል የሚል ጽኑ አቋምን አብስሯል። በዚህም በመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቢሮ ዕድሳት ማራኪ የሥራ ከባቢን መፍጠር አስችሏል። በቢሮ ዕድሳት የተመዘገበው እመርታዊ ውጤትም የኢትዮጵያ ከተሞችን የውበት አክሊል የሚያጎናጽፍ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የሚገነባበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም የኢትዮጵያ ከተሞችን በማፍካት የከተሜነት የአኗኗር ምኅዳር ዝማኔን የውበት አክሊል አቀዳጅቷል። ይህ ለውጥም የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የተደራሽነት አድማስን በበርካታ ከተሞች የኮሪደር፣ የፓርኮች፣ የአረንጓዴ ስፍራዎች፣ የቅርስ ጥበቃና ማራኪ የሕዝብ መዝናኛ ግንባታ በማስፋፋት የኢትዮጵያን ልክና መልክ ገልጠዋል። የአዲስ አበባ የገበታ ለሸገር ፕሮጀክቶች፣ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማቶች እመርታም የሕዝብን የከተሜነት የአኗኗር ሥርዓት ከከተማ ሕይወት ጋር የማስተሳሰር ተምሳሌቶች ናቸው። በክልሎችም ተመሳሳይ የከተማ ውበት፣ የቱሪዝም፣ የቅርስና የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራዎች ልማት በስፋት ተከናወነዋል፤ እየተከናወኑም ነው። የዚህ ሂደት ዋና እሴት ውበት ብቻ እንዳልሆነ ያሳያል። የተሻለ የከተሜነት ምኅዳር ምቹ የንግድ፣ ቱሪዝም፣ መዝናኛ፣ ማህበራዊ ትስስርና የከተማ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴን በመፍጠር ጉልህ አስተዋጽኦ አለው። ይህም የከተሞችን የኢኮኖሚ መነቃቃት የሚያሳልጥ የመሰረተ ልማት ግንባታና የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ገበታ ለሸገር ከገለጣት አዲስ አበባ የተሻገረው፤ የገበታ ለሀገርና ለትውልድ እመርታ!! የኢትዮጵያ ከተሞች ለውጥ ዘላቂ የከተሜነት ሽግግርን የማፋጥን መሰረት እየጣለ ይገኛል። የአዲስ አበባን ልማት ከክልል ከተሞች፣ የከተማ ልማትን ከገጠር ምርት፣ ቱሪዝም ከቅርስ ጥበቃ፣ የሕዝብ መዝናኛ ሥፍራን ከኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ጋር አሰናስሎ ማስቀጠልም ቀጣይነት ያለው ሥራን ይጠይቃል። በዚህ አቅጣጫ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጪነት ገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገርና ገበታ ለትውልድ በተሰኙት የልማት ሐሳቦች የተገነቡ ማራኪ የልማት ፕሮጀክቶች የተፈጥሮ፣ የባህል፣ የቱሪዝምና የሕዝብ መዝናኛ ሃብቶችን ወደ ኢኮኖሚያዊ እሴት መቀየር ያስቻሉ ናቸው። በአዲስ አበባ በገበታ ለሸገር የተገነቡት የአንድነት፣ ወዳጅነትና የእንጦጦ ፓርኮች የመዲናዋን ስምና ግብር ከገለጡት የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ጋር ተዳምረው ማራኪ የመስህብ መዳረሻ ምኅዳርን ፈጥረዋል። ይህም የከተማ ልማት ከውበት ወደ ምርታማነት መሻገሩን የሚያሳይ ወሳኝ ብስራት ነው። በገበታ ለሀገር የተገነቡት የጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ሐላላ ኬላ፣ ኮይሻና ሌሎች የኢኮኖ ቱሪዝም መዳረሻ ሥፍራዎችም የኢትዮጵያን ጥንታዊ የከተሜነት ሥልጣኔ ከዘመናዊ የዓለም ከተሜነት ጋር ያሰናሰሉ የልማት ብስራቶች ናቸው። ፕሮጀክቶቹም የኢትዮጵያን የማድረግ አቅም በተግባር አስመስክረዋል። የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶችም የተገነቡት የሎጎ ሐይቅ፣ ዓርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት፣ ኒን ሊ ፓልም ስፕሪንግ ሎጅ፣ የሸበሌ ሪዞርት፣ ደንዲ ኢኮ-ሎጅ እና ሌሎችም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የቱሪዝም ዘርፍ የማንሰራራት ጉዞ በማነጽ የብልፅግናን ብርሃን ፈንጥቀዋል። የከተማ እመርታ የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኘዎችን የስበት ማዕከል እንደሚያደርግ ሁሉ፤ የተደራጀ ከተማም የተመቻቸ የንግድና ኢንቨስትመንት ምኅዳርን በመፍጠር የምርታማነት አቅም ያጎለብታል። የከተማ መሰረተ ልማት ደግሞ ምርታማነትን ያሳድጋል። ሦስቱ ሲጣመሩም ከተማ የኢኮኖሚ ሞተር ትሆናለች። የኢትዮጵያ ከተሞች የወደፊት ሕልም!! የከተሞች ትንሳኤ የሚለካው በአዲስ እሳቤ ተሰናስለው በሚገነቡ መሰረተ ልማቶች መሆኑ እሙን ነው። የከተማ ልማት ሲቀጥል ተመጣጣኝ መኖሪያ ቤት፣ ውሃና ፍሳሽ፣ የቆሻሻ አያያዝ፣ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ አረንጓዴ ስፍራ፣ የአካባቢ ጽናትና የሥራ ዕድል ፈጠራን አብረው መሄድ አለባቸው። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የ2025 የከተማ ትንበያም የከተማ ልማትን ከሁሉን አቀፍ፣ አስተማማኝ፣ ጽኑና ዘላቂ የከተማ ሕይወት ጋር አቆራኝቶ መምራት እንደሚስፈልግ ያመላክታል። ይህም ለኢትዮጵያ ከተሞችን ማስዋብ እና መሰረተ ልማትን ማስፋፋት አንዱ ክፍል ሲሆን፤ የከተማን ኢኮኖሚ ማሳደግ፣ ሥራ መፍጠር፣ ለዜጎች የተሻለ የኑሮ ዕድል መፍጠርና የከተሞችን የወደፊት እጣ ፋንታ የሚወስን ሽግግርን የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ትምህርት ይሰጣል። ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ ከተሞች የነገ ሽግግራቸውን የሚያፋጥን ምቹ መደላድል ፈጥረዋል። የኢትዮጵያ ከተሞች ትንሳኤ፤ ከእርጅና ወደ ልዕልና የዓለም ከተሞች የሚያመሳስላቸው አንድ የታሪክ እውነት አለ። ከተማ በአንድ ቀን የሚገነባ ሳይሆን በትውልድ ቅብብሎሽ በሚደረግ የዕውቀት፣ የሥራ፣ የዕቅድና የፈጠራ ሥራ የሚቀጥሉ ናቸው። ኢትዮጵያም ከአክሱም እስከ ጎንደር፣ ከሐረር እስከ አዲስ አበባ ረጅሙ የከተሜነት ታሪክ አላት። ዛሬ የተከፈተው አዲስ ምዕራፍም የአረጁና የኮሰመኑ ከተሞች አዲስ የከተሜነት ቅርፅና መልክ የሚይዙበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም አዳዲስ ከተሞችን በተቀናጀ ዕቅድ በመገንባት ከተሞችን የኢኮኖሚ ዕድገት ሞተር እያደረገ ነው። በዚህም በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክቶች ድሬ ዳዋ፣ ሐረር፣ አዳማ፣ ባሕር ዳር፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ አርባ ምንጭ፣ ሐዋሳ፣ ሶዶ፣ ጅግጅጋ፣ አሶሳ፣ ነቀምትና ሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞችን ከእርጅና ወደ ልዕልና የተሸጋገሩበትን ወርቃማ ዕድል ፈጥሮላቸዋል። የአዲስ አበባ፣ የጎንደር አብያተ መንግሥታት፣ የጅማ አባጅፋር ቤተ-መንግሥትና ሌሎች ከተሞች የቅርስ ዕድሳቶችም ታሪክን ለትውልድ በማሻገር ከተሞቹን ተደማሪ የውብት አከሊልን አቀዳጅቷል። የከተሞቹ የኮሪደር ልማትም ከእርጅና ወደ ልዕልና የሚለው ሐሳብ የከተሞችን የቆዩ መዋቅራዊ የመሰረተ ልማት ግንባታ ችግሮች በአዲስ ዕይታ የመፍታት የሽግግር ተምሳሌት ነው። የኢትዮጵያ ከተሞች ዛሬ የሚገኙበት የለውጥ ሂደትም በዚህ ሰፊ የዓለም የከተሜነት ጉዞና ሥልጣኔ የሚታይ ነው። ጥንታዊ የከተሜነት ሥልጣኔን የወረሰች ኢትዮጵያም የወደፊቱን የከተሜነት ምኅዳር በዕውቀት፣ ፈጠራ፣ መሰረተ ልማት፣ በባህልና በሰው ኃይል መቅረፅ የሚያስቻለትን መሰረት በመጣል ወሳኝ አቅም ገንብታለች።
ግብርና - የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከፍታ ማሳያ
Sep 30, 2026 310
ለትልቅ ሀገር ፣ትልቅ ህዝብና ታላቅ ርዕይ ስኬት መሰረት የሆነው የኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ለረጅም ጊዜ ከቆየበት ዝናብ ጠባቂነትና ባህላዊ አሰራር ወጥቶ ወደ ዘመናዊና ምርታማነት ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። ላለፉት አያሌ ዓመታት የሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት በከፍተኛ ሁኔታ የተፈተነ ቢሆንም፣ በቅርብ ዓመታት የተተገበሩ የሪፎርም ስራዎች ዘርፉን የሀገራዊ እድገትና የብልጽግና ዋነኛ ሞተር አድርገውታል። ይህ እመርታ ግብርናን ማዘመን ብቻ ሳይሆን፣ አጠቃላይ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ አቅምና ብሔራዊ ክብር ወደ ላቀ ከፍታ እያሸጋገረ ይገኛል። የዚህ ለውጥ ቀዳሚው ማሳያ የሀገሪቱ የስንዴ ፍጆታ ከውጭ ዕርዳታና ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ መላቀቁ ነው። ቀደም ሲል በየዓመቱ በአማካይ እስከ አንድ ቢሊዮን የሚጠጋ የአሜሪካ ዶላር በመመደብ ስንዴን ከውጭ ስታስገባ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ ዛሬ ያንን ታሪክ በመቀየር በራስ አቅም እንድታመርት አድርጓል። ለአርሶ አደሩ እየቀረቡ ያሉ የተሻሻሉ የግብዓት ዓይነቶች፣ የኩታ ገጠም (ክላስተር) እርሻ ስልት መስፋፋት እና በበጋ መስኖ ስንዴ ልማት የተመዘገበው ስኬት ሀገሪቱ ምርቱን ወደ ተለያዩ ሀገራት እንድትልክ አስተዋጽኦ አድርገዋል። የግብርና መሸጋገሪያ ርካብ መረማመጃው ብዙ ነው። ምርትን በመጠን በዓይነትና በጥራት ማምረት ፣ ብሎም የገበያ ትሰስር መፍጠር ፣ አካባቢንና ሥነ ምኅዳርን በዕምቅ ዐቅምነት መጠቀም ጊዜን ከምርት ወቅትና ከመድረስ አንጻር መረዳት ፣ በምርምርና በቴክኖሎጂ የማምረት ዐቅምን በብዙ እጥፍ ማሳደግ የርካቡ መሸጋገሪያዎች ናቸው።…የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 167 ይህ የምግብ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥ ጉዞ በሀገር በቀል እውቀትና ጉልበት የተመሰረተ መሆኑ፣ ለዘመናት ይስተዋሉ የነበሩ የኢኮኖሚ ስብራቶችን በመጠገን ረገድ የላቀ አስተዋጽኦ አበርክቷል። የግብርናው ማበብ በዘርፉ ላይ ብቻ የቆመ ሳይሆን የሀገሪቱን የማኑፋክቸሪንግና የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎችን በከፍተኛ ሁኔታ እያነቃቃ ይገኛል። በርካታ የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ፋብሪካዎች የሚሆን አስተማማኝና ጥራት ያለው የጥሬ ዕቃ አቅርቦት በሀገር ውስጥ መመረት መጀመሩ የሀገር በቀል ኢኮኖሚውን መሰረት አጽንቶታል። ከዚሁ ጎን ለጎን፣ እንደ ቡና ያሉ ስትራቴጂካዊ የወጪ ንግድ ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ያላቸው ተወዳዳሪነትና የጥራት ደረጃ ማደጉ የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ ገቢ አቅም በከፍተኛ ደረጃ አሳድጎታል። የገጠሩ አምራች ማህበረሰብ ምርታማነቱ ሲጨምርና የገቢ አቅሙ ሲጎለብት፣ በከተሞች ያለውን የንግድ ልውውጥና የኢንዱስትሪ ምርቶች ፍላጎት አብሮ በማሳደግ የገጠርና የከተማን የንግድ ትስስርን አዘምኗል። ይህ የግብርና እመርታ በሀገር ውስጥ ከታየው የምርት ዕድገት ባለፈ፣ የኢትዮጵያን የጂኦ-ፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪነትና ዓለም አቀፍ አመኔታ ከፍ ያደረገ ብሔራዊ ድል ነው። ለዚህ ማረጋገጫው ደግሞ የተባበሩት መንግስታት የምግብ እና እርሻ ድርጅት (ፋኦ) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እ.አ.አ በ2024 ያበረከተው የ"አግሪኮላ" (Agricola Medal) ሜዳልያ ከፍተኛ የክብር ሽልማት ነው። ይህ ታሪካዊ ሽልማት ሀገሪቱን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ፣ በበጋ መስኖ ስንዴ ምርት ራስን ለመቻልና ድህነትን ለመቀነስ ለታየው ቁርጠኛ አመራር የተሰጠ ዓለም አቀፍ እውቅና ነው። ይህ የግብርናው እመርታ የኢትዮጵያን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ብሔራዊ ክብር፣ የኢኮኖሚ ነጻነት እና ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ ፈጣሪነቷን ወደ ላቀ ከፍታ አሸጋግሯል። የግብርናው ዘርፍ ኢትዮጵያ ከነበረችበት የጥገኝነት ታሪክ ሙሉ በሙሉ ወጥታ በራስ አቅም ያለመችው ብልጽግና እውን ማድረግ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ አቅም ነው።
ልዩ ዘገባዎች
የግብፅ የሴራ ፖለቲካ ውድቀት እና ያከተመለት የቅኝ ግዛት እሳቤ
Oct 1, 2026 175
ኢትዮጵያ እና ግብፅ በአንድ በማይለወጥ ተፈጥሯዊና ጂኦግራፊያዊ እውነታ ለዘመናት የተሳሰሩ ሀገራት ናቸው፤ ይኸውም ከኢትዮጵያ ተራራዎች የሚፈልቀው ታላቁ የዓባይ ወንዝ ነው። ነገር ግን ግብፅ ለዘመናት ከተከተለችው የተዛባና ራስ ወዳድነት የሰፈነበት የዓባይ ወንዝ አጠቃቀም አኳያ አንድ መሠረታዊ እና ፍትሃዊ ጥያቄ ግንባር ቀደም ሆኖ ይነሳል፦ የውሃው ምንጭ ባለቤት የሆኑት ኢትዮጵያውያን ተፈጥሯዊ ሀብታቸውን እንዳይጠቀሙና ከድህነት እንዳይወጡ የማገድ መብት ለግብፅ ማን ሰጣት? ይህ ጥያቄ የውሃ ክፍፍል ጉዳይ ብቻ ሳይሆን፣ ግብፅ በቅኝ ግዛት ዘመን የተገኙ ኢ-ፍትሃዊ ጥቅሞችን ለማስቀጠል ስትል የኢትዮጵያን የመልማት መብት ለማካድ የምትከተለው አሉታዊና አጥፊ ሴራ አካል ነው። ታሪክ እንደሚያሳየው ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ብቸኛ ተጠቃሚ ለመሆን በማሰብ፣ ኢትዮጵያን በወታደራዊ ጥቃት፣ በውክልና ጦርነቶች እና በድብቅ የዲፕሎማሲ ሸፍጦች ለማዳከም ስትጥር ቆይታለች። በ19ኛው ክፍለ ዘመን አጋማሽ በኬዲቭ ኢስማኢል ፓሻ መሪነት የተካሄደውና እ.አ.አ በ1875 በጉንደት እንዲሁም በ1876 በጉራ ጦርነት የግብፅን ዕብሪት ያስተነፈሰ የታሪክ ምዕራፍ ነበር። የግብፅ ሴራዎች ከዘመን ዘመን መልክ ቢቀይሩም ዋናው ዓላማቸው ሁልጊዜም ኢትዮጵያን ማዳከም ነው፤ ግብጽ ከቀጥተኛ ወታደራዊ ሽንፈት በኋላ፣ በገማል አብዱል ናስር ዘመን (1956–1970) ስልቷን በመቀየር ወደ ስውር የጥፋት ዘመቻ ተሸጋገረች። በዚህም ዲፕሎማሲን እንደ መሳሪያ በመጠቀም፣ የኦጋዴን ግጭት በማቀጣጠል እና የኢትዮጵያን የውሃ መሠረተ ልማት ስራዎች ብድር እንዳይሰጥ ዘመቻ በማድረግ ጠላትነቷን በግልጽ አሳይታለች። የዚህ ዘመን የከፋ ሴራ ማሳያ ደግሞ እ.አ.አ በ1959 ከሱዳን ጋር ብቻ የተፈረመው ኢ-ፍትሃዊ የዓባይ ውሃ ስምምነት ሲሆን፣ እሱም ኢትዮጵያን እና ሌሎች የተፋሰሱ ሀገራትን ሙሉ በሙሉ በማግለል ወንዙን በብቸኝነት ለመቆጣጠር የተደረገ ህገ-ወጥ እርምጃ ነበር። በአንዋር ሳዳት ዘመን (1970–1981) ደግሞ ግብፅ ዓባይን እንደ የፖለቲካ መሳሪያ በመጠቀም ኢትዮጵያን ለማዳከም አዲስ የጸጥታ ስጋት ፈጠረች፤ ይህም ሳዳት በኢትዮጵያ የውሃ ግድቦች ላይ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ በግልጽ በማስፈራራት ራስ ወዳድነታቸውና የኃይል ፖለቲካ ፍላጎታቸውን በግልጽ አሳይተዋል። በሆስኒ ሙባረክ ዘመን (1981–2011) ግብፅ ቀጥተኛ የጦርነት አቅሟ በመዳከሙ ወደ ስውር ቀጣናውን የመክበብ አካሄድ ቀይራለች። በዚህም የታጠቁ አማጽያንን በድብቅ በመደገፍ እና ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድጋፎችን በማስተጓጎል የኢትዮጵያን የልማት ጉዞ ለመግታት ሴራዎችን መጎንጎኗን ቀጥላለች። ከፕሬዝዳንት አብዱልፋታህ ኤል-ሲሲ መምጣት ጋር የግብፅ ሴራ ይበልጥ እየሰፋ መጥቷል። ዲፕሎማሲን እንደ መሸፈኛ በመጠቀም፣ ወታደራዊ ጥምረቶችን በመፍጠር እና በባህር ዳርቻዎች ኃይል በማሰባሰብ ኢትዮጵያን የማፈን እና የመክበብ አደገኛ የፖሊሲ አካሄድን መከተል ጀምራለች። ግብፅ የኢትዮጵያን ልማት እንደ “ቀይ መስመር” በመፈረጅ፤ የተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት እና የአረብ ሊግን በመጠቀም የግድቡ ሙሌት ስራዎችን ለማስተጓጎል ጸረ-ኢትዮጵያ ጫናዎችን አድርጋለች። ነገር ግን የኢትዮጵያ ጽናት እና የልማት ቁርጠኝነት የግብፅን የከበባ እና የጥፋት ፖሊሲዎች አምክኗል፤ የዘመናት ጫናዎችና ሴራዎችንም ከንቱ አድርጓል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታም ግብፅ የኢትዮጵያ ሃብቶችም ሆነ የህዝቦቿን የነገ እጣ ፈንታ በጉልበት መቆጣጠር እንደማትችል ያሳየ ህይው ምስክር ሆኗል። ከዚህ ረጅም የታሪክ ሂደት መረዳት የሚቻለውም፤ የግብፅ ዛቻዎች እና ማስፈራሪያዎች የዓባይ ወንዝን ዕጣ ፈንታን ሊወስኑ እንደማይችሉ ነው። ይልቁንም ለሁሉም የሚበጀው ኢትዮጵያ የውሃ ሃብቷን ተጠቅማ ድህነትን የማሸነፍ ውጥኗ ፍትሃዊ እና ማንም ሊነጥቀው የማይችል የሕልውና ጉዳይ መሆኑን በቅጡ ያስገነዘበ ሆኗል። ዛሬ ላይ በተፋሰሱ ሀገራት እየጨመረ የመጣው የህዝብ ቁጥር እና የአየር ንብረት ለውጥ በፍትሃዊነትና በትብብር እንዲሰሩ ያስገድዳቸዋል። ከዚህ አኳያ ዘላቂ ሰላምና ልማት የሚረጋገጠው ግብፅ የቅኝ ዘመን ኢ-ፍትሃዊ የይገባኛል ጥያቄዋን ስትተው እና የሁሉንም ተፋሰስ ሀገራት ፍትሃዊና ምክንያታዊ የውሃ አጠቃቀም መርህ የተቀበለ የትብብር ማዕቀፍ ሲሰፍን ብቻ ነው።
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 13978
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22845
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15868
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
መጣጥፍ
ኢትዮጵያ እና ቡና
Sep 30, 2026 223
ኢትዮጵያ- ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ ፤ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ የተገኘውና በዓለም ላይ የተስፋፋው ቡና ተቆልቶና ተፈጭቶ በብዛት የሚጠጣ ተፈለጊና ተወዳጅ ምርት በመሆን የዓለምን ገበያ ተቆጣጥሮት ይገኛል። በተለይም በማደግ ላይ ባሉ አገሮችም እስከ 25 ሚሊዮን የሚደርሱ የአርሶ አደሮች የዓለምን 80 በመቶ ቡና እንደሚያመርቱ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያን ጨምሮ ብራዚል፣ ቪትናም እና ኮሎምቢያ ተጠቃሽ አገሮች ሲሆኑ ሌሎችም ይጠቀሳሉ። በመሆኑም የቡናን ዓለም አቀፍ ግብይትና ተፈላጊነት እንዲሁም የተጠቃሚዎች ብዛት መሰረት በማድረግ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በአውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ጥቅምት 1 የዓለም የቡና ቀን አድርጎ ሰይሞታል። በዚሁ መሰረትም የመጀመሪያው የዓለም የቡና ቀን እ.ኤ.አ ከጥቅምት 1 ቀን 2015 ጀምሮ በመከበር ላይ መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ። ቡና ለኢትዮጵያዊያን የገቢ ምንጭ ብሎም የባህል መገለጫ፣ የእንግዳ መቀበያ፣ የአብሮነት ማሳያ፣ የማኅበራዊ ትስስርና የውይይት መድረክም ነው። የኢትዮጵያ ቡና በልዩ ልዩ የጣዕም የሚገለጽና በእጅጉም ተፈላጊ ምርት በመሆኑ በተለይም በአርሶ አደሮች ህይወትና አጠቃላይ በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ ወሳኝ ድርሻ አለው። በአንዳንድ አካባቢዎች ቡና ተፈልቶ ከአንድ እስከ ሶስተኛ ዙር የመጠጣት ልምድም አለ። ምንም እንኳን አጠራራቸውና ከእያንዳንዱ ዙር ጋር የሚያያዙ ትርጓሜዎች በአካባቢው ባህል መሠረት የሚለያይ ቢሆንም የመጀመሪያው “አቦል”፣ ሁለተኛው “ቶና” እንዲሁም ሶስተኛው “በረካ” እየተባለ ይጠራል። የዚህ የቡና ስነ ስርአት ዋነኛ ዓላማ በተደጋጋሚ መጠጣት ሳይሆን በአንድነት መቆየትን፣ ለሌላው ጊዜ መስጠትንና የማኅበረሰብ ትስስርን የሚያጠናክሩ የባህል ምልክቶች ናቸው። ከቡናው ጋር የሚቀርብ (የቡና ቁርስ) እንደየ ሁኔታው ፋንዲሻ፣ ቆሎ፣ ዳቦ ወይም ሌሎች ቀለል ያሉ ምግቦች የሚቀርቡ ሲሆን እጣን አጭሶ በመመራረቅ የሚጠጣም ይሆናል። በዘመናዊው ዓለም ቡና የንግድ፣ የሥራና የመዝናኛ አካል ሆኗል። በቡና ቤቶች፣ በሥራ ቦታዎችና በዘመናዊ የቡና ማቅረቢያ ሥፍራዎች ሰዎች ይገናኛሉ። ሆኖም በኢትዮጵያ ባህላዊ የቡና ሥነ ሥርዓት ውስጥ ያለው ልዩ ትርጉም ከጣዕምና ከንግድ በላይ ይዘልቃል። ከቤት እስከ ጎረቤት ፤ ከታሪክ እስከ ትውልድ የቆየ ትስስር ያለው የኢትዮጵያን ልዩ መገለጫ ባህል ነው። የቡና ባህላዊ ሥነ ሥርዓትን በማስተዋወቅ እንዲሁም የቡና ታሪክን ከተፈጥሮ ሃብት ጋር አጣምሮ በማሳየት የሀገሪቱን ባህላዊ ቅርስ ለዓለም ማስተዋወቅ ያስፈልጋል። የኢትዮጵያ ቡና የባህል ይዘቱ እንዳለ ሆኖ ለሀገሪቷ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ በመሆን ለእድገትና ማንሰራራት ሁነኛ መሰረት እየሆነ ይገኛል። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የቡና ቀን የቡና ዘርፍ ለዘላቂ ልማት የሚኖረውን አስተዋጽኦ በማድረግ “ቡና የዘላቂ መፍትሄ አካል” በሚል መሪ ሃሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ በነገው እለት የሚከበር ይሆናል።
የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ
Sep 29, 2026 172
ጋምቤላ ፤ መስከረም 19/2019 (ኢዜአ)፦ የሰውና የተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ የጋምቤላ ክልል በሰፊ የተፈጥሮ ሀብት፣ የውሃ ሀብት፣ ደኖች፣ የሣር ምድሩና በዱር እንስሳትና ብዝሃ ሕይወት እምቅ ሃብት ያለው መሆኑ ይታወቃል። የአኙዋሃና የማጃንግ የተፈጥሮ ሃብቶች ለልዩ የቱሪዝም መስህቦች ሆነው ይጠቀሳሉ። በተለይም ጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ በሰፊ የሳር ሜዳዎች፣ በውሃ አካላትና በተለያዩ የዱር እንስሳት የበለፀገ የተፈጥሮ ሀብት ነው። የዱር እንስሳት ጉብኝት፣ የአዕዋፍ እይታ፣ የተፈጥሮ ጉዞና አጠቃላይ የኢኮ-ቱሪዝም ሃብት ፓርኩ የታደለ ነው። በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወንዞችና ረግረጋማ መሬቶች፣ የደን ሃብት ከሰዎች አኗኗርና የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ጋር በማሰናሰል የቱሪዝም ሃብት ማድረግ ተችሏል። በመሆኑም ጋምቤላ ያለውን የተፈጥሮና የባህል እምቅ ሃብት በዘላቂነት በማልማት፣ የተፈጥሮ ጥበቃን ከቱሪዝም ልማት ጋር በማስተሳሰር ለኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራና ለማህበረሰብ ተጠቃሚነት አዲስ አቅም መፍጠር እየተቻለ ነው። የባዮስፌር ሪዘርቭ ዋና ዓላማ ተፈጥሮን ከሰው ልጅ የኢኮኖሚና የኑሮ ሁኔታ ጋር በማጣጣም የብዝሃ ሕይወት ጥበቃ፣ የዘላቂ ልማትና የምርምር ከባቢን መፍጠር በመሆኑ በዚሁ መሰረትም የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ እና የማጃንግ የተፈጥሮ ደን በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ሊመዘገብ ችሏል። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ ከ1 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የሚሸፍን ሰፊ ምድር ያካለለ ሲሆን በውስጡ በርካታ የዱር እንስሳትና የዕፅዋት ዝርያዎች ይገኛሉ። በጥብቅ ደኑ ውስጥ ከ1 ሺህ በላይ የዕፅዋት፣ ከ327 የሚልቁ የአእዋፍ፣ ከ86 በላይ አጥቢና ተሳቢ የእንስሳት ዝርያዎች መኖራቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የአኙዋሃ ባዮስፌር ሪዘርቭ የተፈጥሮ ሃብት ብቻ ሳይሆን የሰውና ተፈጥሮ መልካም ትስስር ማሳያ፣ የዱር እንስሳት ሃብት ኮሪደር እና የዘላቂ ልማት ማዕከል ነው ማለት ይቻላል። የአካባቢው ሕዝብ ከተፈጥሮው ጋር ተስማምቶ በመኖር የተፈጥሮ ሃብትን በመጠበቅና ለትውልድ ጠብቆ በማቆየት ረገድ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው ነው። በ225 ሺህ 490 ሄክታር ላይ የተንጣለለው የማጃንግ የተፈጥሮ ደንም በውስጡ 550 የዕፅዋት ዝርያዎች፣ 33 የአጥቢ እንስሳት ዝርያዎች እንዲሁም 130 የአእዋፍ ዝርያዎች እንዳሉት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ዝቅተኛና ከፍተኛ መልክአ ምድርን አካቶ የያዘው ጥብቅ የተፈጥሮ ሃብቱ በተለይም ለንብ ማነብና ለፍራፍሬ ልማት እጅግ ተመራጭ አካባቢ ነው። የጋምቤላ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል፣ ለምግብ ዋስትና እንዲሁም ለቱሪዝም ዘርፉ ወሳኝ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል።