ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
አራተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት
Mar 19, 2026 14
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ታደርጋለች። ለማጣሪያው በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ዝግጅታችውን ማድረግ ቀጥለዋል። ቡድኑ የአራተኛ ቀን ልምምዱን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ጋቶች ፓኖም (አል ዓረቢ ሳዑዲ ዓረቢያ) እና ከነዓን ማርክነህ ( አል ሻባብ ኦማን) ብሔራዊ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል። ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።
መገናኛ ብዙኅን የፖለቲካ ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጮቻቸውን ለህዝብ የሚያስተዋውቁበት ምቹ መድረክ እየፈጠሩ ነው
Mar 19, 2026 20
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ መገናኛ ብዙኅን የፖለቲካ ፓርቲዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖሊሲ አማራጮቻቸውን ለህዝብ የሚያስተዋውቁበት ምቹ የክርክር መድረክ እየፈጠሩ መሆኑን የፖለቲካ ፓርቲ የሥራ ኃላፊዎች ገለጹ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ በሚሰጥበት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም 10 ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የምርጫ መወዳደሪያ የፖሊሲ አማራጮቻቸውን እያስተዋወቁ ነው። የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለኢዜአ እንዳሉት፤ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፉክክር ሂደት ፓርቲዎች የፖሊሲ አማራጮችን ለህዝብ የሚያስተዋውቁበት ምቹ ምኅዳር ፈጥረዋል። መገናኛ ብዙኅን የፈጠሩት የፖሊሲ አማራጭ ማስተዋወቂያ የክርክር መድረክም ለዜጎች በነፃነት ይበጀናል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ መስጠት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። የስምረት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ምክር ቤት አባልና የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ምክትል ሰብሳቢ ጠዓመ ዓረዶም፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገር ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም ሊኖራቸው ይገባል ብለዋል። መገናኛ ብዙኅንም የፖለቲካ ፓርቲዎች በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚፎካከሩበትን የፖሊሲ አማራጭ ለህዝብ የሚያስተዋውቁበትን ምቹ የክርክር መድረክ እየፈጠሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎችም በመገናኛ ብዙኅን በተፈጠረው የፖሊሲ አማራጭ የክርክር መድረክ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምና የህዝብን አንድነት ማዕከል በማድረግ ክርክራቸውን ማካሄድ እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል። ስምረት ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በዜጎች መካከል አሰባሳቢና የጋራ ትርክት ለመገንባት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ ጠቅሰው፤ በቀጣይም ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ዲሞክራቲክ ሕብረት ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ሳሙኤል ብርሀኑ በበኩላቸው፤ የምርጫ ሂደት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና በህዝብ አንድነት ላይ እንቅፋት መሆን የለበትም ብለዋል። በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሚፎካከሩ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ቅቡልነት ያለው ጠንካራ መንግስት መመስረት የሚያስችል ምክንያታዊ ክርክር ማድረግ እንደሚኖርባቸው ገልጸዋል። ፓርቲያቸውም የተሻለች ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስተላለፍ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
ኮኬይን በረረቀ መንገድ ደብቃ ለማስተላለፍ የሞከረች ተጠርጣሪ በቦሌ ዓለም- አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ዋለች
Mar 19, 2026 32
አዲስ አበባ፤መጋቢት 10/2018(ኢዜአ)፦ ኮኬይን በረረቀ መንገድ ደብቃ ለማስተላለፍ የሞከረች ተጠርጣሪ በቦሌ ዓለም- አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ውላለች። ሙኪሳ ስቴላ የተባለች ኡጋንዳዊት ግለሰብ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ውስጥ በረቀቀ መልኩ 500 ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ደብቃ ለማስተላለፍ ስትሞክር በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ከማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንጌ ተነስቶ ፊሊፒንስ ማኒላ መዳረሻው የሆነው አውሮፕላን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ትራንዚት ሲያደርግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ባለሙያዎች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በዘመናዊ መሣሪያዎች ባከናወኑት ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር ኮኬይኑ ከእነተጠርጣሪዋ መያዙን መረጃው ጠቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አደገኛ ዕጽዋት ቁጥጥር እና ወንጀል ምርመራ ዘርፍ አባላትም ለተጨማሪ ምርመራ እንደተረከቡት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለ ኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በተከታታይ ቀናት ከለንደን በአዲስ አበባ በኩል ወደ ኬንያ በሚጓዝ አውሮፕላን 86 ኪሎ ግራም ደረቅ ጫት እንዲሁም ከኢጣሊያ ሚላን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ በሚበር አውሮፕላን 17 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ጫት በሕገ-ወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሙከራ ሲደረግ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋሉም ተመላክቷል፡፡ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያም ከ 4 ኪሎ ግራም በላይ ኮኬይን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታወሰው መረጃው፤ ኢትዮጵያ የብዙ አፍሪካ ሀገራት መተላለፊያ ከመሆኗም ባሻገር በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ ተመራጭ የትራንዚት ማዕከልነቷ በመጠናከሩ ከሰላማዊ ተጓዦች ጋር ተቀላቅለው በሕገ-ወጥ ተግባራት የሚሰማሩ በመኖራቸው እንደ ወትሮው ሁሉ በከፍተኛ ዝግጁነት ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ያደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የላቁ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም መቻሉ፤ የሰው ኃይል አቅም መገንባቱ እንዲሁም ግልጽ አሠራር መዘርጋቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚተላለፉ አደንዛዥ ዕጾችና ሌሎችንም ሕገ-ወጥ ቁሶች በከፍተኛ ደረጃ ለመቆጣጠር ማስቻሉን ያመለከተው መረጃው፤ በቀጣይም በተዘረጋው የአሠራር ስርዓት መሰረት የሚወሰዱ ተመሳሳይ የቁጥጥር እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጧል፡፡
የመሬት መንሸራተቱን ተከትሎ የተለየ እንክብካቤ ለሚሹ ሕፃናት፣ነፍሰ ጡርና ለሚያጠቡ እናቶች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል
Mar 19, 2026 26
አርባ ምንጭ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋን ተከትሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች በተለይም የተለየ ትኩረትና እንክብካቤ ለሚሹ ሕፃናት፣ነፍሰ ጡርና ለሚያጠቡ እናቶች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ። የቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ካሠች ኤልያስ እንደገለጹት በጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በርካታ ወገኖች ለሞትና ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን እነዚህን ወገኖች የመደገፍ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአደጋው ከተፈናቀሉት መካከል የተለየ ትኩረትና እንክብካቤ የሚሹ ሕፃናት፣ ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶችን በልዩ ትኩረት እገዛ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ቢሮው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አልሚ ምግቦችን ጨምሮ የተለያዩ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው፤ ድጋፉ ቀጥታ ለተጋላጭ ወገኖች እንዲደርስ በተቀናጀ መልኩ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በአደጋው ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችም ለስነ-ልቦና ችግር እንዳይዳረጉ በባለሙያ ጭምር የታገዘ ድጋፍና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከተፈናቃዮቹ መካከል ወይዘሮ ትዕግስት አጥናፉ፤ ለሕፃናትና እናቶች በተለየ መልኩ እገዛና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ለሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎችን ጨምሮ አልሚ ምግብ፣ ቁሳቁስና መሰል ድጋፎች እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። "በአደጋው ሁለት የቤተሰብ አባላትን እንዲሁም የእርሻ ማሳ እና ቤት ንብረቴን አጥቻለሁ" ያሉት ደግሞ ከማዞ ዶይሳ ቀበሌ የተፈናቀሉት ወይዘሮ ጩናሬ ግርማ ናቸው። ከመኝታ ፍራሽ ጀምሮ የሚያስፈልጋቸውን አልባሳት በድጋፍ እንዳገኙ ገልጸው፣ በተደረገላቸው ድጋፍና የባለሙያ እንክብካቤ እየተበረታቱና ተስፋቸው እየለመለመ መምጣቱን ተናግረዋል። አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ አካላት እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ ብርታት ስለሆናቸውም አመስግነዋል።
በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተተገበሩ የግብርና ምርታማነት ኢንሼቲቮች አስደማሚ ውጤት እያስገኙ ነው
Mar 19, 2026 38
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ተግባራዊ የተደረጉ የግብርና ምርታማነት ኢንሼቲቮች አስደማሚ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ ፈርጋል ራያን ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያና አየርላንድ መካከል የተገነባውን ታሪካዊ ወዳጅነት በግብርና የትብብር መስክ የበለጠ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ፈርጋል ራያን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያና አየርላንድ በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል። ይህ ዘመናትን የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በግብርና ምርታማነት ትብብር ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል። አየርላንድ በድንች ሃብት ልማት ያካበተችውን ልምድና ተሞክሮ ለኢትዮጵያ በማጋራት የዘርፉ ምርታማነት የሚሻሻልበትን ድጋፍ እያደረገች መሆኗን አንስተዋል። በዚህም የሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም የምርምር ውጤቶችን በማውጣት የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እንዲሻሻል እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና ባለአነስተኛ የመሬት ይዞታ አርሶ አደሮችን የሰብል ምርታማነት አቅም በማጎልበት የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ እንደሚገኝ አብራርተዋል። በቀጣይም ሀገራቸው በግብርና ዘርፍ ያላትን ምርጥ ተሞክሮ በማጋራት የኢትጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያንና አየርላንድን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትብብር በማጠናከር የግብርና ሙያተኞችን ለማብቃት እንደሚሰራም አንስተዋል። ከበርካታ ዓመታት በፊት አየርላንድ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በግብርና ምርታማነት ላይ የተፈጠረባት ጫና በዜጎች የምግብ ደኅንነት ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህም መነሻነት በግብርና ዘርፍ የተደረጉ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት ተነሳሽነቶች ያመጡት ለውጥ የበለጸገችና እራሷን የቻለች አየርላንድን መፍጠር እንዳስቻለ አብራርተዋል። በኢትዮጵያም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ተግባራዊ የተደረጉ የግብርና ምርታማነት ኢንሼቲቮች አስደማሚ ስኬቶችን እያስገኙ እንደሚገኝ አንስተዋል። የመንግስትና ዜጎች የግብርና ምርታማነትን የማሳደግ ቁርጠኝነትም የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠር እያስቻለ መሆኑን አንስተዋል።
ፖለቲካ

በአምቦ ከተማ የወጣቶች አደረጃጀቶች ለምርጫው ስኬታማነት የበኩላቸውን ድርሻ እየተወጡ ነው
Mar 19, 2026 52
አምቦ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ) ፡-ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ አካታች፣ ነፃና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት እየተንቀሳቀሱ መሆኑን በአምቦ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የወጣቶች አደረጃጀቶች አስታወቁ። የምርጫው ሂደት ሰላማዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የሲቪክ ማህበራት ሚና ወሳኝ በመሆኑ፣ ኢዜአ በአምቦ ከተማ ከሚንቀሳቀሱ የወጣቶች አደረጃጀቶች ጋር ቆይታ አድርጓል። የአምቦ ከተማ ወጣቶች ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ወጣት ዲቦራ ጉሉማ እንደገለጹት፤ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዲሞክራሲያዊ መንገድ እንዲካሄድ ፌዴሬሽኑ ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት ጀምሮ የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል። የመራጮች ምዝገባ ከተጀመረ አንስቶ ሂደቱ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ ወጣቶችን በማስተባበር ሰፊ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ከምርጫው በፊት የሚካሄዱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክሮችና ውይይቶችን ወጣቶች በንቃት እንዲከታተሉና ጠንካራ ተሳትፎ እንዲኖራቸው እየተሰራ መሆኑንም አመልክተዋል። ምርጫውን ከሚያስፈፅሙ አካላት ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ እንዲሆንና የምዝገባ ሂደቱ እንዲሳለጥ የፌዴሬሽኑ አባል ወጣቶች እስከ ቀበሌ ወርደው የማስተባበር ኃላፊነታቸውን እየተወጡ መሆኑን ጠቁመዋል። የአምቦ ከተማ ወጣቶች ማህበር ፕሬዝዳንት ወጣት ደጄነ ሀይሌ በበኩሉ፤ ምርጫው በህዝብ ዘንድ ተዓማኒነትና ቅቡልነት እንዲኖረው ማህበሩ የወጣት አደረጃጀቶችን ሚና ለማጎልበት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። “ዕድሜያቸው ለምርጫ የደረሱ ወጣቶች በመራጭነት፣ በታዛቢነትና በአስመራጭነት በንቃት እንዲሳተፉ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ምቹ ሁኔታዎችን እየፈጠርን ነው” ነው ብለዋል። በአሁኑ ወቅት በከተማ አስተዳደሩ ሥር በሚገኙ ሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ በሰላማዊ መንገድ እንዲከናወን የማህበሩ ወጣቶች ከፍተኛ እገዛ እያደረጉ መሆኑን አብራርተዋል።
ጠቅላላ ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊና ቅቡልነት ያለው እንዲሆን የጋራ ምክር ቤቱ ሚናውን ይወጣል
Mar 19, 2026 102
ሀዋሳ፤ መጋቢት 10/2018(ኢዜአ)፦ ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነጻ፣ ፍትሃዊና ቅቡልነት ያለው እንዲሆን የምክር ቤቱ አባል የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናቸውን እንደሚወጡ የሲዳማ ክልል ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ገለጸ። የፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር እና ቅስቀሳ አማራጭ ሀሳቦች የሚቀርቡበት ሊሆን ይገባል - ምሁራን የጋራ ምክር ቤቱ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ላይ ያተኮረ ውይይት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ አካሂዷል። የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራሲ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊና የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ በለጠ ሰጌቦ በመድረኩ እንደገለጹት፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዴሞክራሲያዊ፣ ነጻ፣ ፍትሃዊና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው እንዲሆን የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና የጎላ ነው። በክልሉ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ የፖለቲካ ምህዳር መኖሩን ጠቅሰው በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫ ለማድረግ አስቻይ ሁኔታዎች አሉ ብለዋል። በዚህም ተአማኒነት ያለው፣ ነጻ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ እንዲካሄድ ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል። የምርጫ ሥነ ምግባር ህጉን በተከተለ መንገድ አማራጭ ሃሳቦችን በማቅረብ የጋራ ኢትዮጵያን መገንባት እንደሚገባም ተናግረዋል። ለዚህም በምርጫው በሰላማዊ መንገድ ከመንቀሳቀስ ባለፈ የህዝቡን ተሳትፎ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸው፣ ህዝቡ ለመራጭነት የሚያበቃውን ካርድ እንዲወስድ ማነቃቃት ይገባል ብለዋል። በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ዘርፍ ሃላፊና የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ ተስፋዬ ኤርሚያስ በበኩላቸው፤ ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና ተአማኒ እንዲሆን የጋራ ምክር ቤቱ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። የጋራ ምክር ቤቱ ለዴሞክራሲያዊ ሥርአትና ለመድብለ ፓርቲ ግንባታ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቅሰው፣ ለምርጫው ስኬታማነት የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃላፊነታችንን እንወጣለን ነው ያሉት። የጋራ ምክር ቤቱ አባላት በበኩላቸው ፤ መድረኩ በመጪው ጠቅላላ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናቸውን በአግባበ እንዲወጡ የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። በመድረኩ ምርጫው ፍትሃዊ፣ ዴሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ቅቡልነት ያለው ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚና ላይ ያተኮረ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። የሲዳማ ክልል የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት በሀገር አቀፍና በክልል አቀፍ ደረጃ የሚንቀሳቀሱ 23 የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያካተተ መሆኑ ታውቋል።
ኢትዮጵያ የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማረጋገጥ የፈጠረችው ምቹ ምኅዳር በምሳሌነት የሚወሰድ ነው
Mar 19, 2026 99
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማረጋገጥ የፈጠረችው ምቹ ምኅዳር በምሳሌነት የሚወሰድ መሆኑን የአፍሪካ ሕብረት የሴቶች፣ የሰላምና ደኅንነት ልዩ ልዑክ አምባሳደር ላይቤራታ ሙላሙላ ገለጹ። በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ በሚሰጥበት የዘንድሮው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ ከየካቲት 28/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ ይገኛል። መራጮችም "ምርጫዬ" በተሰኘ የዲጂታል መተግበሪያና በየምርጫ ጣቢያዎች በአካል በመገኘት ድምፅ መስጠት የሚያስቻለቸውን የምርጫ ካርድ በመውሰድ ላይ ናቸው። በዘንድሮው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫም 47 ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች 10ሺህ 934 ዕጩዎችን በማስመዝገብ በመገናኛ ብዙኅን አማካኝነት የምርጫ መወዳደሪያ የፖሊሲ አማራጫቸውን እያስተዋወቁ ይገኛሉ። አምባሳደር ላይቤራታ ሙላሙላ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት ሀገራዊ ምርጫ ነፃ፣ ፍትሕዊና ሰላማዊ መሆኑን ለማረጋገጥ የምርጫ ታዛቢ ቡድን እንደሚያሰማራ ገልጸዋል። በአህጉሪቱ ለሚካሄዱ ሀገራዊ የምርጫ ሂደቶች ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሕዊና አካታችነትም የሴቶች የነቃ ተሳትፎ አስፈላጊ መሆኑን ተናግረዋል። ለዚህም የአፍሪካ ሕብረት የሴቶች፣ የሰላምና ደኅንነት ልዩ ልዑክ የአህጉሪቱ ሴቶች በምርጫ ወቅት የመምረጥና መመረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙ የማበረታቻ ድጋፍ እንደሚያደርጉ አንስተዋል። ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ግንቦት ወር የምታካሂደው 7ኛ ጠቅላላ ምርጫም ነፃ፣ ፍትሕዊና አካታችነት ለማረጋገጥ ገንቢ ሚና እንደሚወጡ አስታውቀዋል። በአፍሪካ አብዛኛውን የማህበረሰብ ክፍል የሚሸፍኑት ሴቶች መሆናቸውን አንስተው፤ ሀገራት በሚያካሂዱት ሀገራዊ ምርጫዎች ሴቶች የመምረጥና መመረጥ መብታቸውን መጠቀም ይኖርባቸዋል ብለዋል። በምርጫ ዴሞክራሲያዊነት የሚኖር የሴቶች ተሳትፎ የአመራር ድርሻና የፖለቲካ ውክልናን እንደሚያረጋግጥም አብራርተዋል። ሴቶች በፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስክ ዕድላቸውን መጠቀም ከቻሉ ለማህበረሰብ ለውጥ ወሳኝ መሆናቸውን አምባሳደሯ ያለፉበትን የተሞክሮ መንገድ በአብነት ጠቅሰዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የፈጠረው ምቹ ምኅዳር በምሳሌነት የሚወሰድ መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል። በሚቀጥለው ግንቦት 24/2018 ዓ.ም ድምፅ በሚሰጥበት 7ኛው የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ ሴቶች ትርጉም ባለው መልኩ የመምረጥና መመረጥ መብታቸውን የሚጠቀሙበት ወሳኝ ዕድል እንደሆነ ተናግረዋል።
ጠቅላላ ምርጫው የኢትዮጵያን ቀጣይ እድገትና ብልፅግና የምንወስንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው
Mar 19, 2026 118
ገንዳውኃ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የኢትዮጵያን ቀጣይ እድገትና ብልፅግና የምንወስንበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው ሲሉ በምዕራብ ጎንደር ዞን የገንዳውኃና መተማ ዮሃንስ ከተሞች ነዋሪዎች ገለጹ። ካርድ በመውሰድ ለሀገር ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል-የሮቤ ከተማ ነዋሪዎች በዞኑ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ በተጠናከረ ሁኔታ እየተካሄደ ነው። ነዋሪዎቹ ፤7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን እድገትና ብልፅግና ቀጣይነት ስለሚወስን ተመዝግበን የወሰድነውን ካርድ በመጠቀም የሚበጀንን የፖለቲካ ፓርቲን እንመርጣለን ብለዋል። ከመራጮቹ መካከል የገንዳ ውሃ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ ኤልሳ አበጋዝ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ዜጎች የኢትዮጵያን ቀጣይ እድገትና ብልፅግና የሚወስኑበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። በዚህም እስካሁን በአካባቢያቸው እየተካሄደ ያለው የቅድመ ምርጫ ተግባራት ሰላማዊና አሳታፊ በሆነ መልኩ ተጠናክሮ መቀጠሉ የምርጫውን ዴሞክራሲያዊነት ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። ምርጫው በሰላማዊ መንገድ መንግስት በመመስረት የልጆቻቸውን የወደፊት ተስፋና የሃገሪቱን መጻኢ እድል የሚወስን በመሆኑ ካርድ ከማውጣት ጀምሮ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላኛዋ የዚሁ ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አስረስ አበበ በበኩላቸው፤ ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ለማጎልበት አስፈላጊ ነው ብለዋል። በምርጫው መሳተፍ ህገ መንግስታዊ መብትን ከመጠቀም ባለፈ ለሀገር ሰላምና ልማት ኃላፊነትን መወጣት መሆኑን በማመን ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ ማውጣታቸውን አንስተዋል። ምርጫው ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገትን ያረጋግጣል የሚል እምነት እንዳላቸው የገለጸው ደግሞ በዞኑ የመተማ ዮሃንስ ከተማ ነዋሪ ወጣት በላይነህ ብርሃኑ ነው። የእርሱ ድምጽ ለአገር ግንባታ ያለውን ሚና በመገንዘብ ካርድ ማውጣቱን ገልጿል።
ካርድ በመውሰድ ለሀገር ይበጃል የምንለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል-የሮቤ ከተማ ነዋሪዎች
Mar 19, 2026 126
ሮቤ ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በጠቅላላ ምርጫው ለመራጭነት የሚያበቃቸውን ካርድ በመውሰድ ለሀገር ይበጃል ያሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን የሮቤ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ በብሔራዊ የምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ መሆኑ ይታወቃል። በባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለመራጭነት የሚያበቃቸውንና ለሀገር ይበጃል ብለው ለሚያምኑት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን ለመስጠት የሚያስችላቸውን ካርድ አስቀድመው መውሰዳቸውን አመልክተዋል። በከተማዋ የጄኔራል ዋቆ ጉቱ አደባባይ አካባቢ በጫማ ማስዋብ ሥራ የሚተዳደረው አካል ጉዳተኛ ዘውዱ ከበደ፤ የመራጭነት ካርድ ከወሰዱ ነዋሪዎች መካከል ነው። "የምርጫ ካርዴ ነገ ለሀገር የተሻለ ሥራ የሚሠራ ፓርቲን የምመርጥበት ነው" ያለው ዘውዱ፣ መብቱን ለመጠቀም መመዝገቡንና ሌሎች ወጣቶችም ፈለጉን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርቧል። ወንድማማቾቹ ወጣት መሐመድ ኢድሪስ እና ሐሰን ኢድሪስ በጋራ በመሆን በአቅራቢያቸው በሚገኝ የዜበላ ወለሼ የምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርድ ወስደዋል። ወጣት መሐመድ በሰጠው አስተያየት፣ "ምርጫ የዜግነት መብታችንን የምንጠቀምበትና የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ የምንወስንበት መድረክ በመሆኑ ቀድመን ካርድ መውሰድን መርጠናል" ብሏል። የምዝገባ ሂደቱም ቀላልና ቀልጣፋ በመሆኑ ሌሎችም መራጮች የመመዝገቢያው ጊዜ ሳያበቃ ካርድ ሊወስዱ እንደሚገባ አሳስቧል። ወጣት ሐሰን ኢድሪስ በበኩሉ፣ የምርጫ ካርድ መያዝ የዴሞክራሲያዊ ተሳትፎ መጀመሪያ መሆኑን ጠቅሶ፣ "እኛ ወንድማማቾች እንደመሆናችን በጋራ መጥተን ተመዝግበናል፤ ሌሎችም ቤተሰቦችና ጎረቤቶች ተቀናጅተው በመምጣት ካርዳቸውን ሊወስዱ ይገባል" ሲል ነው መልዕክት ያስተላለፈው። በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ነፍሰ ጡር እናቶችና አካል ጉዳተኞች ለምዝገባ ሲመጡ ቅድሚያ እንዲያገኙ መደረጉ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው የገለጹት ደግሞ ወይዘሮ የስርባ መሐመድ ናቸው። በተለይም ሴቶች በቤተሰብና በማኅበራዊ ሕይወት ያላቸውን ሚና ወደ ፖለቲካዊ ተሳትፎ በመቀየር የመራጭነት ካርዳቸውን በንቃት በመውሰድ በዕድሉ እንዲጠቀሙ ያግዛል ነው ያሉት። ምርጫው ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡም አስተያየት ሰጪዎቹ አረጋግጠዋል። በባሌ ዞን በ5 የምርጫ ክልሎች ሥር በተደራጁ 537 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች ምዝገባ እየተከናወነ ሲሆን ኅብረተሰቡም በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ካርድ በመውሰድ ላይ ይገኛል።
የክልሉ ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት -ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
Mar 18, 2026 458
ደቡብ ኢትዮጵያ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብቱን በተግባር ማረጋገጥ አለበት ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳድሩ በምርጫ ጣቢያ በመገኘት የመራጭነት ካርዳቸውን ወስደዋል። ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ በዚህ ወቅት ሕዝቡ የምርጫ ካርድ በመውሰድ የተጀመረውን የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ለማጠናከር ሚናውን መወጣት አለበት ብለዋል። መንግሥት ነፃ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ ምርጫ ለማካሄድ ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቅሰው፤ ምርጫው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ሕዝቡም ከወዲሁ የምርጫ ካርድ መውሰድ እንዳለበት አንስተዋል። ሌላው በወቅቱ የምርጫ ካርድ የወሰዱት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ደምስ አድማሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዞኑ ሕዝብ በአስቸጋሪ የፈተና ወቅት ላይ ቢገኝም ቀጣይ ዕጣ ፈንታው ላይ የሚወስንበትን ካርድ በመውሰድ ለምርጫው መዘጋጀት እንዳለበት አስገንዝበዋል በዞኑ ለምርጫው ሂደት ስኬታማነት ምቹ ሁኔታዎችን የመፍጠር ሥራ በተቀናጀ መልኩ እየተከናወነ መሆኑንም ተናግረዋል።
የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ
Mar 18, 2026 287
ሀዋሳ ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፡-የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በጠቅላላ ምርጫው ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ በምርጫ ሂደቱ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ፉክክር ለማድረግ የሚያስችል ዝግጁነት ላይ እንገኛለን- ተፎካካሪ ፓርቲዎች የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት በመጪው ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሚካሔደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎችም በጠቅላላ ምርጫው ለመሳተፍና ለመምረጥ የሚያስችላቸውን የምርጫ ካርድ እየወሰዱ ይገኛሉ፡፡ በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች ኢዜአ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች እንደገለጹት ምርጫ ዜጎች መብታቸውን በመጠቀም ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሚናቸውን የሚወጡበት ዕድል በመሆኑ ተመዝግበው ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ ወስደዋል፡፡ ከከተማው ነዋሪዎች መካከል የውቅሮ ቀበሌ ነዋሪ አቶ ተገኝ በቀለ ባለፉት ጊዜያት በተካሄዱ ምርጫዎች እንደተሳተፉና ለዘንድሮ ምርጫም ካርድ ወስደው መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡ ምርጫ ዜጎች መብታቸውን ተጠቅመው ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሚናቸውን የሚወጡበት እድል ነው ብለዋል። በመሆኑም ቤተሰቦቻቸውና የአካባቢያቸው ነዋሪዎች በምርጫው ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ እየቀሰቀሱ መሆኑን የገለጹት አቶ ተገኝ በመገናኛ ብዙሃን የሚደረግ የፓርቲዎችን ክርክር እንደሚከታተሉ ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮ የምርጫ ሂደት በቴክኖሎጂ መታገዙ ዴሞክራሲያዊ ምርጫን ለማካሄድ ያግዛል የሚል እምነት እንዳላቸውም ገልጸዋል። በተለይ ወጣቱ የምርጫ ተሳትፎውን ማጠናከር እንዳለበት የጠቀሱት አቶ ተገኝ፣ ሃገርን በተሻለ መምራት የሚችል ፓርቲን በእውቀት ላይ ተመስርቶ መምረጥ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ ዘንድሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለመምረጥ እንደተዘጋጀች የገለጸችው ወጣት ፍሬህይወት ኪሮስ በበኩሏ የምርጫ ካርድ ወስዳ የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ ለመለየት የፖለቲካ ፓርቲዎችን ክርክር እየተከታተለች መሆኗን ተናግራለች። ለሴቶች ተጠቃሚነት የተሻለ ሀሳብ ያለውን ፓርቲ እንደምትመርጥና ሴቶችም በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው ተናግራለች። በሚኖሩበት አካባቢ ዜጎች በምርጫው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ድርሻቸውን እንዲወጡ በመቀስቀስ እየተሳተፉ መሆኑን የገለጹት አቶ ግርማ የማነህ ናቸው፡፡ በቀደሙት ምርጫዎች የተለያየ ተሳትፎ እንደነበራቸው ገልጸው በመራጭነት መሳተፍ የዜግነት ግዴታም ጭምር ነው ብለዋል፡፡ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ መውሰዳቸውን ገልጸው የፖለቲካ ፓርቲዎች እየደረጉት ያለው ክርክርም ህዝቡ የተሻለውን ፓርቲ ለይቶ እንዲመርጥ እድል እየፈጠረ በመሆኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

ማህበራዊ
ኮኬይን በረረቀ መንገድ ደብቃ ለማስተላለፍ የሞከረች ተጠርጣሪ በቦሌ ዓለም- አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ዋለች
Mar 19, 2026 32
አዲስ አበባ፤መጋቢት 10/2018(ኢዜአ)፦ ኮኬይን በረረቀ መንገድ ደብቃ ለማስተላለፍ የሞከረች ተጠርጣሪ በቦሌ ዓለም- አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር ውላለች። ሙኪሳ ስቴላ የተባለች ኡጋንዳዊት ግለሰብ በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ ውስጥ በረቀቀ መልኩ 500 ግራም የሚመዝን ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ ደብቃ ለማስተላለፍ ስትሞክር በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ከማላዊ ዋና ከተማ ሊሎንጌ ተነስቶ ፊሊፒንስ ማኒላ መዳረሻው የሆነው አውሮፕላን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ትራንዚት ሲያደርግ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ባለሙያዎች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በዘመናዊ መሣሪያዎች ባከናወኑት ጥብቅ ፍተሻና ቁጥጥር ኮኬይኑ ከእነተጠርጣሪዋ መያዙን መረጃው ጠቁሟል፡፡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አደገኛ ዕጽዋት ቁጥጥር እና ወንጀል ምርመራ ዘርፍ አባላትም ለተጨማሪ ምርመራ እንደተረከቡት የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ለ ኢዜአ በላከው መረጃ አመልክቷል፡፡ በተጨማሪም በተከታታይ ቀናት ከለንደን በአዲስ አበባ በኩል ወደ ኬንያ በሚጓዝ አውሮፕላን 86 ኪሎ ግራም ደረቅ ጫት እንዲሁም ከኢጣሊያ ሚላን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በኩል ወደ ኮንጎ ኪንሻሳ በሚበር አውሮፕላን 17 ነጥብ 5 ኪሎ ግራም ጫት በሕገ-ወጥ መንገድ ለማዘዋወር ሙከራ ሲደረግ በብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ባለሙያዎች በቁጥጥር ስር መዋሉም ተመላክቷል፡፡ በያዝነው ሳምንት መጀመሪያም ከ 4 ኪሎ ግራም በላይ ኮኬይን በቦሌ ዓለም-አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታወሰው መረጃው፤ ኢትዮጵያ የብዙ አፍሪካ ሀገራት መተላለፊያ ከመሆኗም ባሻገር በመካከለኛው ምሥራቅ የተፈጠረውን የፀጥታ መደፍረስ ተከትሎ ተመራጭ የትራንዚት ማዕከልነቷ በመጠናከሩ ከሰላማዊ ተጓዦች ጋር ተቀላቅለው በሕገ-ወጥ ተግባራት የሚሰማሩ በመኖራቸው እንደ ወትሮው ሁሉ በከፍተኛ ዝግጁነት ክትትልና ቁጥጥር እየተደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የአቪዬሽን ደኅንነት ዋና መምሪያ ያደረገውን ሪፎርም ተከትሎ የላቁ ቴክኖሎጂዎች መጠቀም መቻሉ፤ የሰው ኃይል አቅም መገንባቱ እንዲሁም ግልጽ አሠራር መዘርጋቱ በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የሚተላለፉ አደንዛዥ ዕጾችና ሌሎችንም ሕገ-ወጥ ቁሶች በከፍተኛ ደረጃ ለመቆጣጠር ማስቻሉን ያመለከተው መረጃው፤ በቀጣይም በተዘረጋው የአሠራር ስርዓት መሰረት የሚወሰዱ ተመሳሳይ የቁጥጥር እርምጃዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጧል፡፡
የመሬት መንሸራተቱን ተከትሎ የተለየ እንክብካቤ ለሚሹ ሕፃናት፣ነፍሰ ጡርና ለሚያጠቡ እናቶች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ ቀጥሏል
Mar 19, 2026 26
አርባ ምንጭ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦በጋሞ ዞን በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና የጎርፍ አደጋን ተከትሎ ለተፈናቀሉ ወገኖች በተለይም የተለየ ትኩረትና እንክብካቤ ለሚሹ ሕፃናት፣ነፍሰ ጡርና ለሚያጠቡ እናቶች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን የክልሉ ሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ። የቢሮ ሃላፊ ወይዘሮ ካሠች ኤልያስ እንደገለጹት በጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በርካታ ወገኖች ለሞትና ለመፈናቀል የተዳረጉ ሲሆን እነዚህን ወገኖች የመደገፍ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል። በአደጋው ከተፈናቀሉት መካከል የተለየ ትኩረትና እንክብካቤ የሚሹ ሕፃናት፣ ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶችን በልዩ ትኩረት እገዛ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ቢሮው ከ1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ አልሚ ምግቦችን ጨምሮ የተለያዩ የምግብና የአልባሳት ድጋፍ ማድረጉን ገልጸው፤ ድጋፉ ቀጥታ ለተጋላጭ ወገኖች እንዲደርስ በተቀናጀ መልኩ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በአደጋው ወላጆቻቸውን ያጡ ልጆችም ለስነ-ልቦና ችግር እንዳይዳረጉ በባለሙያ ጭምር የታገዘ ድጋፍና እንክብካቤ እየተደረገላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ከተፈናቃዮቹ መካከል ወይዘሮ ትዕግስት አጥናፉ፤ ለሕፃናትና እናቶች በተለየ መልኩ እገዛና ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ተናግረዋል። ለሴቶች የንጽህና መጠበቂያዎችን ጨምሮ አልሚ ምግብ፣ ቁሳቁስና መሰል ድጋፎች እየተደረገ መሆኑንም ጠቅሰዋል። "በአደጋው ሁለት የቤተሰብ አባላትን እንዲሁም የእርሻ ማሳ እና ቤት ንብረቴን አጥቻለሁ" ያሉት ደግሞ ከማዞ ዶይሳ ቀበሌ የተፈናቀሉት ወይዘሮ ጩናሬ ግርማ ናቸው። ከመኝታ ፍራሽ ጀምሮ የሚያስፈልጋቸውን አልባሳት በድጋፍ እንዳገኙ ገልጸው፣ በተደረገላቸው ድጋፍና የባለሙያ እንክብካቤ እየተበረታቱና ተስፋቸው እየለመለመ መምጣቱን ተናግረዋል። አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ አካላት እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ ብርታት ስለሆናቸውም አመስግነዋል።
የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች 7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
Mar 19, 2026 71
አርባ ምንጭ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፡- የሀገር መከላከያ ሠራዊት ልዩ ዘመቻዎች ዕዝ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ። በዕዙ የማሰልጠኛ ማዕከል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ቦጃ አጋ ድጋፉን ዛሬ ባስረከቡበት ወቅት እንደገለጹት፣ በዞኑ የተለያዩ ወረዳዎች በተከሰተ አደጋ በወገኖች ላይ በደረሰ ከፍተኛ ጉዳት መላው የዕዙ አባላት ጥልቅ ሀዘን ተሰምቷቸዋል። አባላቱ በተለያዩ ግዳጆችና ሌሎች ተግባራት ላይ ቢሆኑም ባሉበት ሆነው ገንዘብ በማዋጣት ለጋሞ ህዝብ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ዛሬ የ7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል። ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋምና ለዘላቂ መፍትሄ በሚደረገው ጥረትም የዕዙ አባላት ከዞኑ አስተዳደር ጎን እንደሚቆሙ አረጋግጠዋል። ለተጎጂዎች የቀረበውን ድጋፍ የተረከቡት የጋሞ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ተመስገን ኢዩኤል በበኩላቸው፥ የሀገር መከላከያ ሠራዊት ቀዳሚ ተግባሩ የሀገር ሉአላዊነትን ማስከበር ቢሆንም የዕዙ አባላት በዞኑ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል። ከሀገር ውስጥና ከውጭ በተለያዩ አካላት እየተደረገ ያለው ድጋፍና አለኝታነትን የማረጋገጥ ተግባር ተጎጂዎችን ብሎም የዞኑ ህዝብና አስተዳደር እንዲጽናኑ እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል።
በአካባቢው የተገኘውን ሰላም በማጽናት የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን እናስቀጥላለን - የጉሊሶ ከተማ ነዋሪዎች
Mar 19, 2026 57
ጉሊሶ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ):-በምዕራብ ወለጋ ዞን የጉሊሶ ከተማ ነዋሪዎች በአካባቢያቸው ሰላምን በማስፈን የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው በቁርጠኝነት እንደሚሰሩ ገለጹ። ከከተማዋ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በልማት፣ በሰላም እና በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ነዋሪዎች እንደገለጹት፤ በአካባቢያቸው እየተከናወኑ ያሉ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ ተጠናቀው ለአገልግሎት እንዲበቁ ቅድሚያ ለሰላም መስፈን ትኩረት ሊሰጥ ይገባል። ቀደም ሲል የነበሩ የፀጥታና የመልካም አስተዳደር ችግሮች በህዝቡና በፀጥታ አካላት የተቀናጀ ጥረት እየተፈቱ መሆኑን ተናግረዋል። የጉሊሶ ከተማ ነዋሪ ሸህ አብዱ ሀሰን፣ "የአካባቢውን ሰላም በማፅናት የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠል የድርሻችንን እንወጣለን" ብለዋል። ለዚህም የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል። ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ተክሌ ሞሲሳ፤ በአሁኑ ወቅት በህዝቡና በፀጥታ አካላት ቅንጅት በአካባቢው አስተማማኝ ሰላም መስፈኑን ጠቅሰዋል። የተገኘው ለውጥ እንዲቀጥል ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ትብብራችንን እናጠናክራለን ሲሉም ገልጸዋል። መድረኩን የመሩት የምዕራብ ወለጋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ተሊላ ተረፋ፤ ባለፉት ዓመታት በዞኑ አጋጥሞ የነበረው የፀጥታ ችግር የልማት ሥራዎች በሚፈለገው ፍጥነትና ጥራት እንዳይከናወኑ እንቅፋት ሆኖ መቆየቱን አስታውሰዋል። አሁን ላይ በህብረተሰቡና በፀጥታ አካላት ጥምረት ሰላም እየሰፈነ ሲሆን የልማት ስራዎችም በስፋት እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። ይህ ውጤት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ህብረተሰቡ ሰላምን በመጠበቅ ለልማት ሥራዎች ስኬታማነት የሚያደርገውን ርብርብ እንዲያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል።
ኢኮኖሚ
በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተተገበሩ የግብርና ምርታማነት ኢንሼቲቮች አስደማሚ ውጤት እያስገኙ ነው
Mar 19, 2026 38
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ተግባራዊ የተደረጉ የግብርና ምርታማነት ኢንሼቲቮች አስደማሚ ውጤት እያስገኙ መሆናቸውን በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ ምክትል የሚሲዮን መሪ ፈርጋል ራያን ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያና አየርላንድ መካከል የተገነባውን ታሪካዊ ወዳጅነት በግብርና የትብብር መስክ የበለጠ ለማጠናከር በቁርጠኝነት እየተሰራ እንደሚገኝም ተናግረዋል። ፈርጋል ራያን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያና አየርላንድ በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው ብለዋል። ይህ ዘመናትን የተሻገረ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት በግብርና ምርታማነት ትብብር ተጠናክሮ መቀጠሉንም ገልጸዋል። አየርላንድ በድንች ሃብት ልማት ያካበተችውን ልምድና ተሞክሮ ለኢትዮጵያ በማጋራት የዘርፉ ምርታማነት የሚሻሻልበትን ድጋፍ እያደረገች መሆኗን አንስተዋል። በዚህም የሀገራቱ የሁለትዮሽ ትብብር የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም የምርምር ውጤቶችን በማውጣት የአርሶ አደሩ ተጠቃሚነት እንዲሻሻል እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። በተለይም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃና ባለአነስተኛ የመሬት ይዞታ አርሶ አደሮችን የሰብል ምርታማነት አቅም በማጎልበት የምግብ ዋስትናን እያረጋገጠ እንደሚገኝ አብራርተዋል። በቀጣይም ሀገራቸው በግብርና ዘርፍ ያላትን ምርጥ ተሞክሮ በማጋራት የኢትጵያን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ጉዞ ለማፋጠን በቁርጠኝነት እንደምትሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያንና አየርላንድን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትብብር በማጠናከር የግብርና ሙያተኞችን ለማብቃት እንደሚሰራም አንስተዋል። ከበርካታ ዓመታት በፊት አየርላንድ በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ በግብርና ምርታማነት ላይ የተፈጠረባት ጫና በዜጎች የምግብ ደኅንነት ላይ ተፅዕኖ አሳድሮ እንደነበር አስታውሰዋል። በዚህም መነሻነት በግብርና ዘርፍ የተደረጉ ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት ተነሳሽነቶች ያመጡት ለውጥ የበለጸገችና እራሷን የቻለች አየርላንድን መፍጠር እንዳስቻለ አብራርተዋል። በኢትዮጵያም የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ተግባራዊ የተደረጉ የግብርና ምርታማነት ኢንሼቲቮች አስደማሚ ስኬቶችን እያስገኙ እንደሚገኝ አንስተዋል። የመንግስትና ዜጎች የግብርና ምርታማነትን የማሳደግ ቁርጠኝነትም የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ማረጋገጥ የሚያስችል ምቹ መደላድል መፍጠር እያስቻለ መሆኑን አንስተዋል።
ድሬዳዋን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሏል--ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ
Mar 19, 2026 45
ድሬዳዋ፤መጋቢት 10/ 2018 (ኢዜአ)፡-ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ አሟጦ በመሰብሰብ ድሬዳዋን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ ተናገሩ። የአስተዳደሩ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በድሬዳዋ የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ተጠናክረው በሚቀጥሉበት ሁኔታዎች ላይ ዛሬ መክረዋል። አመራሮቹ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችና መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተመልክተው በሰጡት የሥራ አቅጣጫዎች ላይ ሰፊ ምክክር አድርገዋል። መድረኩን የመሩት የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ ሀርቢ ቡህ እንዳሉት፤ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ድሬዳዋን ለኑሮ፣ ለሥራ፣ ለኢንቨስትመንትና ለንግድ ተመራጭ ለማድረግ በተከናወኑ ሥራዎች ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። የድሬዳዋን ታሪካዊ ሃብቶችና ቅርሶች በጠበቀ መንገድ በጥራት የተከናወኑ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ለከተማዋ ድምቀት ከመሆን ባለፈ ለኢንቨስትመንት እና ለቱሪዝም ዘርፍ መጎልበት ወሳኝ ሚና እያበረከቱ ነው ብለዋል። በተጨማሪም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በተሰሩ ሥራዎች በርካታ የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ወደ ማምረት በመሸጋገር በሺህ ለሚቆጠሩ ወጣቶች የሥራ ዕድል በመፍጠርና ተኪ ምርቶችን በማምረት ለድሬዳዋ እድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ መሆኑን አስረድተዋል። እነዚህን ውጤታማ ሥራዎች በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ በተቀናጀ መንገድ ለመሰብሰብ መረባረብ ይገባል ሲሉም ከንቲባው አስገንዝበዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ በበኩላቸው እንዳሉት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ ያደረጉት የሥራ ጉብኝትና የሰጡት የሥራ አቅጣጫ በየደረጃው በሚገኘው አመራርና ነዋሪ ላይ ከፍተኛ የሥራ መነሳሳት ፈጥሯል። በተለይ በአስተዳደሩ የተጀመሩ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶችን በጥራትና በፍጥነት በማጠናቀቅ ድሬዳዋን የብልጽግና ግቦች የተሳካባት ቀዳሚ ከተማ ለማድረግ የተቀናጀ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል። በኮሪደር ልማት፣ በመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና በገጠሩ ክፍል የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ተጠናክረው መቀጠላቸውም ጠቅሰዋል። በቀጣይ በየደረጃው ያለው አመራር በህዝብ ተሳትፎ የተራቆቱ ተራራማ አካባቢዎችን አረንጓዴ የማልበስና ድሬዳዋን ከተፈጥሮ አደጋ የመታደግ ጅምር ሥራዎችን ለማሳደግ በቁርጠኝነት ሊተጋ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል። በተጨማሪም ወጣቶችን የሥራ ባለቤት የማድረግ እንዲሁም ጅምር የፍራፍሬና የአትክልት ልማቶችን የማላቅ ጉዳይ ትኩረት ይሰጣቸዋል ብለዋል። በየዘርፉ ውጤታማነትን ለማስቀጠል የተለጠጠ የገቢ አሰባሰብ ዕቅድ ተዘጋጅቶ በተቀናጀ መንገድ መተግበር ቀዳሚ ጉዳይ መሆኑንም አቶ ኢብራሂም አስገንዝበዋል።
የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጠ ነው
Mar 19, 2026 55
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በከተሞች ተግባራዊ የተደረገው የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በተግባር እያረጋገጠ መሆኑን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር በከተሞች ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ብሎም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ታስቦ የተቀረጸ ስትራቴጂካዊ ፕሮግራም ነው። ከመርሃ ግብሩ ዋነኛ ዓላማዎችም መካከልም ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች መደገፍና የስራ ዕድል መፍጠር ተጠቃሾች ናቸው፡፡ በዚህም በርካታ ዜጎችን ከተረጂነት በማላቀቅ በየሶስት ዓመቱ በምርቃት ሂደት በማሳለፍ ሃብት ፈጣሪ እንዲሆኑ ማድረግ እያስቻለ ይገኛል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን ለኢዜአ እንዳሉት፤ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ከልማት መርሃ ግብር ጋር ተሰናስለው ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኝ ገልጸዋል። የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብሩም በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ ዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥና ወደ ሃብት ፈጣሪነት በማሸጋገር ዘመናዊ የከተሜነት ምኅዳር እየፈጠረ መሆኑን ተናግረዋል። የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚ ዜጎችም በከተማ ፅዳትና የአረንጓዴ ውበት የሥራ ዕድል በማመቻቸት ለከተማ ነዋሪዎች ምቹ የአኗኗር ከባቢ መፍጠር ማስቻሉንም ገልጸዋል፡፡ በዚህም የከተሞችን ውበት ማስጠበቅ፣ ዘመናዊ የከተሜነት ምኅዳር ግንባታና በከተማ ግብርና ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አስረድተዋል። የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ወዲህ 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎች ሽግግር በማድረግ መቻላቸውን ተናግረዋል፡፡ በተያዘው የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ባለፉት ወራት ውስጥ 380 ሺህ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ተጠቃሚዎችን ሽግግር ማድረጋቸውን አስረድተዋል። በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታትም በከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር የታቀፉ ዜጎችን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሙሉ በሙሉ ለማሸጋገር እንደሚሰራ አንስተዋል።
በክልሉ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በጥራትና ፍጥነት እየተገነቡ ነው
Mar 19, 2026 72
ጅግጅጋ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በክልሉ ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ፕሮጀክቶች በጥራትና ፍጥነት እየተገነቡ መሆኑን የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሁመድ ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ፤ በጅግጅጋ ከተማ እየተገነባ የሚገኘውን 1ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የታይዋን አስፋልት መንገድ የግንባታ ሂደት ጎብኝተዋል። የመንገዱ መገንባት የከተማዋን የተለያዩ አቅጣጫዎች የሚያገናኝ እና የትራንስፖርት ፍሰትን የሚያሳልጥ መሆኑን ገልጸዋል። በመሆኑም መንገዱ በተያዘለት ጊዜ በጥራትና ፍጥነት እየተከናወነ ስለመሆኑ በጉብኝታቸው ማረጋገጣቸውን ተናግረዋል። በክልሉ የተለያዩ ከተሞች የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች በጥራትና ፍጥነት እንዲጠናቀቁ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም በከተሞችም ይሁን በገጠር ህዝብን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶች ግንባታ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
በአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን በቴክኖሎጂ በማስደገፍ የሕዝብ እርካታን ለማረጋገጥ የተጀመረው ስራ ይጠናከራል
Mar 18, 2026 230
ባሕር ዳር፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ ዘመኑን በሚመጥን መልኩ በቴክኖሎጂ ታግዞ ተደራሽ እንዲሆን የተጀመሩ ስራዎች እንደሚጠናከሩ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ። ''ዲጂታል ሲቪል ሰርቪስ ለኢትዮጵያ ከፍታ'' በሚል መሪ ሀሳብ የክልሉ የመንግሥት አገልግሎት እና አስተዳደር ሪፎርም ፍኖተ ካርታ ትውውቅ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄዷል። ፍኖተ ካርታው በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማትን አገልግሎት አሰጣጥ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ መሆኑም ተመልክቷል። ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በመድረኩ ላይ እንዳሉት፤ በየጊዜው እያደገ የመጣውን የሕዝብ የመገልገል ፍላጎት መሠረት ያደረገ ቀልጣፋ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ የመንግሥት ቀዳሚ ተግባር ነው። ፍኖታ ካርታው በክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች የብቃት ምዘና ሥርዓትን በመገንባት ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥን ለማረጋገጥ ያግዛል። በተጨማሪም የመንግስት ሰራተኛውን የማስፈጸም አቅም ማሳደግ፣ ብዝሃነትንና አካታችነትን ያረጋገጠ ሲቪል ሰርቪስ መገንባት እንዲሁም ነፃ፣ ገለልተኛና ዲጂታል የሥራ አካባቢን መፍጠር ዋና ዋና የሪፎርሙ አቅጣጫዎች መሆናቸውን አስረድተዋል። ተቋማትም ፍኖተ ካርታውን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የአገልግሎት ጥራትን፣ ፍጥነትን፣ ፍትሐዊነትንና እርካታን በሚያረጋግጥ መልኩ ሊሠሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። ለዚህም ሲቪል ሰርቫንቱ የዘመኑን ቴክኖሎጂ በመታጠቅ፣ በላቀ ብቃት፣ ዕውቀትና ክህሎት ታግዞ ሪፎርሙን ሊተገብር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ሀገራዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥና ኢትዮጵያን ለማሻገር የሚያስችል የሲቪል ሰርቪስ ፖሊሲ ተቀርጾ ወደ ትግበራ መገባቱን ገልጸዋል። ፖሊሲው ሀገራዊ ዕውቀትንና ልምድን መሠረት ያደረገ በመሆኑ በፍጥነት ለውጥ ለማስመዝገብ እንደሚያስችል ጠቁመዋል። የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን በ36 ማዕከላት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መጀመሩን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ፤ ይህም ቴክኖሎጂን በመጠቀም የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት እያስቻለ መሆኑን አስረድተዋል። የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ባንችአምላክ ገብረማርያም በበኩላቸው፤ ሪፎርሙ ቀደም ሲል በተቋማት ይስተዋሉ የነበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል መሆኑን ተናግረዋል። መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተግባራዊ በተደረገባቸው ከተሞች የሕዝብ እርካታን 97 በመቶ ማድረስ መቻሉን የገለጹት ኃላፊዋ፤ ይህንን ውጤት ለማስፋት የሪፎርም ፍኖተ ካርታውን በላቀ ትብብር መተግበር እንደሚገባም አሳስበዋል። በመድረኩ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በመጀመሪያው ምዕራፍ ወደ ትግበራ ከሚገቡ የተለያዩ የክልል ተቋማት ጋር የሰነድ ርክክብ ተከናውኗል።
የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ አፍሪካን በልኳ ለዓለም የሚያስረዳ ትርክት መገንባት ያስችላል
Mar 17, 2026 179
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ አፍሪካን በልኳ ለዓለም የሚያስረዳ ትርክት መገንባት የሚያስችል መሆኑን የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ያስመዘገበቻቸው ለአፍሪካ ኩራት የሆኑ ዓለም የመሰከረላቸው ድሎችን ለማስተዋወቅ ያግዛልም ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በመጭው ሚያዚያ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ጉባዔ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ሀላፊነት የሚሰማቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር፣ ትብብርን ለመፍጠርና አዲስ አበባን የባህልና የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት፣ በመንግሥታቱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንና የሌሎች አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መገኛ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የነደፈች፣ አህጉራዊ የመተላለፊያ በር በመሆኗ አዲስ አበባ ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ተመራጭ ያደርጋታል። በዚህም በቀጣይ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም መጨረሻ በሚካሄደው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባዔ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በንቃት መሳተፍ በሚችሉባቸው ዕድሎች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል። የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካን ገንቢ ትርክት ለመገንባት በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እጅ ነው። አፍሪካ የትርክት ተጎጂ መሆኗን ገልጸው፤ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የአፍሪካ ትርክትን ለመቀየር የተቋቋመ አፍሪካዊ ሚዲያ መሆኑን ተናግረዋል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ መነሻው ኢትዮጵያ መዳረሻው አፍሪካ ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም እንደሚያስተዋውቅ ገልጸዋል። አፍሪካ የራሷን በጎ ትርክት ለመገንባት በምታደርገው ጥረት ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን በማስተባበር መሪ ተዋናይ ሆኖ ይሰራል ብለዋል፡፡ የማህበራዊ ሚዲያዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖዎች የጎላ ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ በጉባዔው ላይ ኢትዮጵያውያን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን መልካም ገጽታ እንዲገነቡና ትብብር እንዲፈጥሩ ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ በራሷ አቅም ያስመዘገበቻቸው ለአፍሪካ ኩራት የሆኑ ዓለም የመሰከረላቸው ድሎችን ለማስተዋወቅ ገንቢ ሚና እንዳለውም ገልጸዋል፡፡ በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽን መሪ ሥራ አስፈፃሚ ተሾመ ተክሉ፤ ኢትዮጵያ የቅርስ፣ የታሪክና የባህል ባለቤት መሆኗን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅና ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም ሀብት አውጥቶ ማሳየት ሳይቻል መቆየቱን ያወሱት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ሀብቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። የማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀም ከተቻለ ሀገራዊ የቱሪዝም ሀብትን ለዓለም ማሳየት የሚያስችል መድረክ ነውም ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን የቱሪዝም ሀብት ሲያስተዋውቁ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ገልጸዋል፡፡ የቱሪዝም ሚኒስቴር ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በሩ ክፍት ነው ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማየት ለሚፈልጉ ሁሉ ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል። የኤጂኤ ቴክ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገመዳ ኦላና፤ ጉባኤው የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካን ገፅታ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የእርስ በእርስ ትብብራቸውን በማጠናከር አህጉራዊ አንድነትን መፍጠር ያስችላል ብለዋል። በመድረኩ የተሳተፉ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በበኩላቸው፤ ሁነቱ የኢትዮጵያን ገፅታ ለመገንባት ብሎም የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለመገንባት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በኢትዮጵያ መዘጋጀቱ የሀገራችንን ገጽታ ለመገንባት የቱሪዝም ሃብታችንን ለማስተዋወቅ ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የጉባዔው አዘጋጆች ምስጋና ይገባቸዋል ያሉት ተሳታፊዎቹ፤ ለሁነቱ መሳካት በትብብር ለመስራትና የበኩላቸውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውንም አረጋግጠዋል፡፡
የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የአፍሪካን ትርክት በጋራ ለመቅረፅ ገንቢ ሚና አላቸው
Mar 17, 2026 228
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የአፍሪካን ትርክትና ህልም በጋራ ለመቅረፅ ገንቢ ሚና እንዳላቸው የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ ገለጹ። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ በመጭው ሚያዚያ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም በዓድዋ ድል መታሰቢያ ይካሄዳል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ /pulse of Africa/ ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው ስብሰባ "ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ" የሚል መሪ ሀሳብ ይዟል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ ሀላፊነት የሚሰማቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎችን ለማበረታታት፣ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጠናከር፣ ትብብርን ለመፍጠርና አዲስ አበባን የባህልና የዲጂታል ማዕከል ለማድረግ ያለመ ነው። የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች አፍሪካ የራሷን ትርክት መገንባት የሚያስችሉ፣ የደንበኞችን እምነት የሚያሳድጉ፣ ብራንድ ለመፍጠር ወሳኝ መሆናቸው ስብሰባውን አስፈላጊ ያደርገዋል። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት፣ በመንግሥታቱ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽንና የሌሎች አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተቋማት መገኛ የዓለም የዲፕሎማሲ ማዕከል፣ የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ የነደፈች፣ አህጉራዊ የመተላለፊያ በር በመሆኗ አዲስ አበባ ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ ተመራጭ ያደርጋታል። በዚህም በቀጣይ ሚያዚያ 2018 ዓ.ም መጨረሻ በሚካሄደው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ስብሰባ ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በንቃት መሳተፍ በሚችሉባቸው ዕድሎች ዙሪያ ከዘርፉ ተዋንያን ጋር ውይይት ተደርጓል። የፐልስ ኦፍ አፍሪካ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍጹምእሸት ሽመልስ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የአፍሪካን ገንቢ ትርክት ለመገንባት በአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እጅ ነው። አፍሪካ የትርክት ተጎጂ መሆኗን ገልጸው፤ ፐልስ ኦፍ አፍሪካ የአፍሪካ ትርክት ለመቀየር የተቋቋመ አፍሪካዊ ሚዲያ መሆኑን ተናግረዋል። ፐልስ ኦፍ አፍሪካ መነሻው ኢትዮጵያ መዳረሻው አፍሪካ ነው ያሉት ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚው፤ ከማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጋር በመተባበር የአፍሪካን ትክክለኛ ገፅታ ለዓለም እንደሚያስተዋውቅ ገልጸዋል። ማህበራዊ ሚዲያዎች አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተፅዕኖዎቹ የጎላ መሆኑን አመልክተው፤ በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያውያን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን መልካም ገጽታ እንዲገነቡና ትብብር እንዲፈጥሩ ተናግረዋል። በቱሪዝም ሚኒስቴር የቱሪዝም ፕሮሞሽን መሪ ሥራ አስፈፃሚ ተሾመ ተክሉ፤ ኢትዮጵያ የቅርስ፣ የታሪክና የባህል ባለቤት መሆኗን አንስተዋል። ኢትዮጵያ ያላትን ዕምቅና ዘርፈ ብዙ የቱሪዝም ሀብት አውጥቶ ማሳየት ሳይቻል መቆየቱን ያወሱት መሪ ስራ አስፈፃሚው፤ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለኢትዮጵያ ቱሪዝም ትልቅ ሀብቶች መሆናቸውን ገልጸዋል። የማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ዓላማ መጠቀም ከተቻለ ሀገራዊ የቱሪዝም ሀብትን ለዓለም ማሳየት የሚቻልበት መድረክ ነውም ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የሀገራቸውን የቱሪዝም ሀብት ሲያስተዋውቁ የቱሪዝም ሚኒስቴር አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርግ ገልጸዋል። የቱሪዝም ሚኒስቴር ለማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች በሩ ክፍት ነው ያሉት መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ የቱሪዝም ሀብቶችን ለማየት ለሚፈልጉ ሁሉ ምቹ ሁኔታ እንፈጥራለን ብለዋል። ኤጂኤ ቴክ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ገመዳ ኦላና በበኩላቸው፤ ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሎም የአፍሪካን ገፅታ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የእርስ በእርስ ትብብራቸውን በማጠናከር አህጉራዊ አንድነትን መፍጠር ያስችላል ብለዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን ከፍተኛ የተደማጭነት ሚና በማሳደግ የጎላ አበርክቶ እንደሚኖረው ገልጸዋል።
የድንች ምርታማነትን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እየተሰራ ነው
Mar 17, 2026 219
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 8/2018 (ኢዜአ)፦ የድንች ምርታማነትን በጥናትና ምርምር በማስደገፍ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የግብርና ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከአየርላንድ የድንች ምርምር እና ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ብሔራዊ የድንች ምርምር ልማት አውደ ጥናት አካሒዷል። ድንች በኢትዮጵያ በአነስተኛ መሬትና በአጭር ጊዜ ከፍተኛ ምርት የሚሰጥ በመሆኑ ለምግብ ዋስትና እና ለኢንዱስትሪ ግብዓትነት ቁልፍ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀዳሚ የድንች አምራች ለመሆን የሚያስችል እምቅ አቅም ያላት ሲሆን፣ በተለይም የተሻሻሉ ዝርያዎች መጨመር ምርታማነቱን በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየረው ይገኛል። የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ዶ/ር) በተወካያቸው ፕሮፌሰር አሊ መሐመድ አማካኝነት ባስተላለፉት መልዕክት፤ ግብርና ለምግብ ሉዓላዊነት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ እንዲሁም ለውጭ ምንዛሬ ግኝት ተኪ የሌለው ዘርፍ መሆኑን ጠቁመዋል። መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረትም ከፍተኛ ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን አንስተዋል። ድንች ከአገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ማግኛ አማራጭ እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው ለምርቱ እሴት በመጨመር ረገድ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ንጉሴ ደቻሳ በበኩላቸው፤ ምርታማነትን ማሳደግ የኢንስቲትዩቱ ዋነኛ ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በዚህም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ጠቅሰው ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ምርምሮች የተሻሻሉ የድንች ዝርያዎችን ቁጥር ወደ 45 ከፍ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አማካይ የድንች ምርታማነት በሄክታር 230 ኩንታል መድረሱን ተናግረው ምርቱ ሳይበላሽ ለረጅም ጊዜ የሚቆይበትን ቴክኖሎጂ ማስፋፋትና በአለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን እሴት የመጨመር ሥራ ላይ ትኩረት ይደረጋል ብለዋል። በኢትዮጵያ የአየርላንድ ኤምባሲ ምክትል የተልዕኮ ኃላፊ ፈርጋን ሪያን በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በድንች ምርታማነት ላይ እያሳየችው ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን ገልጸው፣ አገራቸው በግብርናው ዘርፍ ያላትን አጋርነት አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል።
ስፖርት
አራተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት
Mar 19, 2026 14
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ታደርጋለች። ለማጣሪያው በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ዝግጅታችውን ማድረግ ቀጥለዋል። ቡድኑ የአራተኛ ቀን ልምምዱን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ጋቶች ፓኖም (አል ዓረቢ ሳዑዲ ዓረቢያ) እና ከነዓን ማርክነህ ( አል ሻባብ ኦማን) ብሔራዊ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል። ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።
በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮን የሚሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን ፖላንድ ደርሷል
Mar 19, 2026 79
አዲስን አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ (World Athletics Indoor Championship) ከመጋቢት 11 እስከ 13 ቀን 2018 ዓ.ም በፖላንድ ቶሩን ከተማ ይካሄዳል። በሻምፒዮናው ላይ የሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑክ ቡድን ቶሩን ከተማ መድረሱን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። አትሌቶቹ በአሁኑ ሰዓት በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኙና የመጀመሪያ ልምምዳቸውን ዛሬ እንደሚያደርጉ አመልክቷል። ልዑካን ቡድኑ 6 አትሌቶች፣አንድ ቡድን መሪ፣አንድ የቴክኒክ ቡድን መሪ እና አንድ አሰልጣኝ ያካተተ ነው። ነገ በሚጀመረው ውድድር ከ118 ሀገራት የተወጣጡ 674 አትሌቶች እንደሚሳተፉ የዓለም አትሌቲክስ አስታውቋል።
ሊቨርፑል ባየር ሙኒክ እና አትሌቲኮ ማድሪድ ለሩብ ፍጻሜ አለፉ
Mar 19, 2026 133
አዲስን አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሶስት የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታዎች ማምሻውን ተደርገዋል። በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሊቨርፑል ጋላታሳራይን 4 ለ 0 ረቷል። ዶምኒክ ስቦዝላይ፣ ሁጎ ኢኪቲኬ፣ ራያን ግራቨንበርች እና መሐመድ ሳላህ ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሊቨርፑል በደርሶ መልስ ውጤት 4 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። በሌላኛው መርሐ ግብር ባየር ሙኒክ አትላንታን 4 ለ 1 አሸንፏል። በአሊያንዝ አሬና ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሃሪ ኬን በጨዋታ እና ፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ሌናርት ካርል እና ሉዊስ ዲያዝ ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ላዛር ሳማርድዚች ለአትላንታ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል። የጀርመኑ ባየር ሙኒክ በአጠቃላይ ውጤት 1ዐ ለ 2 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል። በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቶተንሃም ሆትስፐርስ አትሌቲኮ ማድሪድን 3 ለ 2 አሸንፏል። ዣቪ ሲመንስ በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ራንዳል ኮሎ ሙዋኒ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ጋር አገናኝቷል። ጁሊያን አልቫሬዝ እና ዴቪድ ሃንኮ ለአትሌቲኮ ማድሪድ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። አትሌቲኮ ማድሪድ በድምር ውጤት 7 ለ 5 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜ ገብቷል። ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ ባርሴሎና ኒውካስትል ዩናይትድን 7 ለ 2 በማሸነፍ በድምር ውጤት 8 ለ 3 በመርታት ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል። ጨዋታዎቹን ተከትሎ ሩብ ፍጻሜ የገቡ ስምንት ክለቦች ተለይተዋል። በዚሁ መሰረት ሪያል ማድሪድ ከባየር ሙኒክ፣ ባርሴሎና ከአትሌቲኮ ማድሪድ፣ ፒኤስጂ ከሊቨርፑል እና ስፖርቲንግ ሊዝበን ከአርሰናል በሩብ ፍጻሜው ይጫወታሉ። የሩብ ፍጻሜ የመጀመሪያ ዙር መጋቢት 29 እና 30 እንዲሁም ሚያዚያ 6 እና 7 ቀን 2018 ዓ.ም የመልስ ጨዋታዎች ይደረጋሉ።
ባርሴሎና ለሩብ ፍጻሜ አልፏል
Mar 18, 2026 232
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና ኒውካስል ዩናይትድን 7 ለ 2 ረምርሟል። ማምሻውን በጆሴ አልቫላዴ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራፊኒያ እና ሮበርት ሌዋንዶውስኪ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን አስቆጥረዋል። ማርክ በርናል እና ፌርሚን ሎፔዝ በጨዋታ ላሚን ያማል በፍጹም ቅጣት ምት ቀሪዎቹን ጎሎች ለባርሴሎና ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። አንቶኒ ኢላንጋ ለኒውካስል ግቦቹን አስቆጥሯል። በመጀመሪያ አጋማሽ ተመጣጣኝ ፉክክር በተደረገበት ጨዋታ ባርሴሎና በሁለተኛው አጋማሽ ፍጹም የበላይነት ወስዷል። ባርሴሎና በሁለተኛው 45 አምስት ጎሎችን አስቆጥሯል። የስፔኑ ባርሴሎና በድምር ውጤት 8 ለ 3 በማሸነፍ ለሩብ ፍጻሜ አልፏል። የአምስት ጊዜ የሊጉ አሸናፊ ቡድኑ ስምንት ውስጥ ሲገባ የአሁኑ ለ21ኛ ጊዜ ነው። በሩብ ፍጻሜው ከአትሌቲኮ ማድሪድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ አሸናፊ ጋር ይገናኛል። ኒውካስትል ዩናይትድ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ሩብ ፍጻሜ የመግባት ህልሙ ሳይሳካ ቀርቷል። በተመሳሳይ ምሽት አምስት ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከጋላታሳራይ፣ ባየር ሙኒክ ከአትላንታ እና ቶተንሃም ሆትስፐርስ ከአትሌቲኮ ማድሪድ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
አካባቢ ጥበቃ
የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በዜጎች አኗኗር እና ጤና ላይ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ ነው
Mar 19, 2026 130
ወልቂጤ፤መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በዜጎች አኗኗር እና ጤና ላይ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን የጤና ዘርፍ የስራ ሃላፊዎች ገለጹ። አዋጁ እንደ ሀገር የተጀመረውን የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ከግብ ለማድረስ ያግዛል የ"ፅዱ ኢትዮጵያ" ንቅናቄ በሀገሪቱ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን ለማሻሻል፣ የከተሞችን ውበት ለመጠበቅ እና ለዜጎች ምቹ የመኖሪያ አካባቢን ለመፍጠር ያለመ ሀገራዊ ዘመቻ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሃሳብ አመንጭነት የተጀመረው ኢንሼቲቭ በሁሉም የሀገሪቷ አካባቢዎች ተግባራዊ እየተየደረገ ያለ መሆኑ ይታወቃል። የ"ፅዱ ኢትዮጵያ" ዋነኛ ዓላማም በተለይም በከተሞች የሚታየውን የንፅህና ጉድለት በማስተካከል ለነዋሪዎችና ለጎብኝዎች ዘመናዊና ምቹ ከተሞችን የመፍጠር ነው። በዚህም መሰረት የተገነቡ መሠረተ ልማቶችን በአግባቡ መጠገንና መጠበቅ፣ የቆሻሻ አወጋገድን የማዘመን፤ የመፀዳጃ ቤቶችን የማስፋትና የማዘመን ስራ በስፋትና በጥራት ማከናወን ተችሏል። ከዚህ አንፃር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፅዱ ኢትዮጵያ ኢንሼቲቭ የተገኘውን ውጤት በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር የጤና ዘርፍ ሃላፊዎችንና ነዋሪዎችን አነጋግሯል። የጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ አየለ ፈቀደ፤ በኢንሼቲቩ በገጠርም ይሁን በከተሞች ሰፊ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው ለስኬቱ በየደረጃው ያሉ የስራ ሃላፊዎችና አጠቃላይ የማህበረሰቡ ተሳትፎ የላቀ መሆኑን ገልጸዋል። ፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ብዙ ተያያዥ የሆኑ ማህበራዊና የምጣኔ ሃብት ጥቅሞች እያስገኘ መሆኑን የገለጹት ሃላፊው በቀጣይም በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል። የአካባቢ ጽዳትና ውበትን በጋራ በመጠበቅና በመንከባከብ ምቹና ተመራጭ አካባቢ ለመፍጠር ዜጎችን በማሳተፍ ስኬት እየተመዘገበ ነው ብለዋል። በሁሉም የዞኑ አካባቢዎች ፅዱ እና ለመኖርያነት ምቹ የሆኑ መንደሮች እንዲሁም ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። እስካሁን በዞኑ ከሚገኙ 315 ቀበሌዎች መካከል 70 በመቶ ያህሉ የዚህ ኢንሼቲቭ ትግበራ ተጠቃሚዎች መሆን መቻላቸውንም ለአብነት አንስተዋል። የሃድያ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ ዶ/ር ደሳለኝ ሽጉጤ፤ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በየአካባቢው ካለው ማህበረሰብ ባለፈ ከጤና፣ ከትምህርት እና ከሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ውጤት አምጥቷል ብለዋል። የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በዞኑ ህዝብ ጤና እና አኗኗር ላይ ተጨባጭ ለውጥ እያመጣ በመሆኑ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል። የምስራቅ ጉራጌ ዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ ሰለሞን ጉግሳ፤ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በዞኑ በርካታ ቀበሌዎች እና ወረዳዎችን ጽዱ አካባቢ ማድረግ አስችሏል ብለዋል። የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ሃላፊ ሳሙኤል ዳርጌ፤ የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በክልሉ መሰረታዊ የሚባል ውጤት የመጣበት ስኬታማ ትግበራ መሆኑን ገልጸዋል። መርሃ ግብሩ የተሻሻሉ መፀዳጃ ቤት በመገንባት የሰውና እንስሳ መኖርያ በመለየት ተላላፊ በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር እያስቻለ ነው ብለዋል። በመሆኑም የፅዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ በክልሉ ዜጎች አኗኗር እና ጤና ላይ መሰረታዊ ለውጥ እያመጣ መሆኑን አንስተው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ገልጸዋል። በጉራጌ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች ነዋሪዎችም የፅዱ አካባቢ ልማት በቆሻሻ አወጋገድና አጠቃቀም ላይ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣቱን ተናግረዋል።
ለሀገራዊ የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ትግበራ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት መጠናከር አለበት
Mar 18, 2026 111
አዲስ አበባ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያን የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ስኬታማ ለማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ቅንጅት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ባለስልጣኑ የፍኖተ ካርታውን ትግበራ ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ የፌዴራል ተቋማት ጋር በጋራ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል። የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ(ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ባለስልጣኑ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል፡፡ በዚህም ፅዱ ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ለውጥ የሚያመጡ የህግና አሰራር ስርዓት ወደ ተግባር በማስገባት ለሌሎች ሀገሮች ምሳሌ የሚሆኑ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኙ ገልፀዋል። የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ግቦችን ለማሳካትና ወደ ሰርኩላር ኢኮኖሚ የሚደረገውን ሽግግር ማፋጠን የሚያስችለው ሀገራዊ ፍኖተ ካርታ በ2017 ዓ.ም ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ መገባቱን አስታውሰዋል። ፍኖተ ካርታው ፅዱ ኢትዮጵያን በመፍጠር ሂደት ቆሻሻን መልሶ ጥቅም ላይ የማዋል(Recycling) ባህልን የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረዋል። በተጨማሪም የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን በማጎልበት፣ ለተሻለ ኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን በመፍጠርና አዳዲስ የስራ እድሎችን በመክፈት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ጉልህ ሚና ይጫወታል ብለዋል። የአካባቢ ጥበቃ ስራ በአንድ ተቋም ብቻ ውጤታማ ማድረግ ስለማይቻል የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት እንደሚጠይቅ ጠቅሰዋል። በዚህም ወደ ሰርኩላር ኢኮኖሚ የሚደረገው ሽግግር እንዲፋጠን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነትና በተጠናከረ ተሳትፎ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል። ከተቋማቱ ጋር የተደረገው ስምምነት በአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ላይ ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትን ማከናወን፣ የህግና አሰራር ማሻሻያዎች፣ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ስርዓትን በቴክኖሎጂና በዕውቀት መደገፍ እንዲሁም የጋራ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን በቅንጅት መስራት ከሚከናወኑ ሥራዎች መካከል ናቸው ብለዋል፡፡ ስምምነቱን ከተፈራረሙ ተቋማት መካከል የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ፈንታ ደጀን እንደገለጹት በባለስልጣኑ የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን ውጤታማ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡ በሀገሪቱ የሚከናወኑ ግንባታዎች በመልሶ መጠቀም የተዘጋጁ የሀገር ውስጥ ግብዓቶችን እንዲጠቀሙ በትኩረት እንደሚሰራ ተናግረዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ ሃሰን መሃመድ በበኩላቸው የተዘጋጀው ፍኖተ ካርታ ከኢንዱስትሪ ዘርፉ ፖሊሲ ጋር የሚቀናጅ በመሆኑ ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል። የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር አለበል ደሴ በበኩላቸው ኢንስቲትዩቱ የፖሊሲ ፋይዳ ያላቸው ሀገራዊ ጥናቶችን በመለየት ፖሊሲ አውጪውን የማማከር ስራ የሚሰራ ተቋም እንደመሆኑ ለፍኖተ ካርታው ትግበራ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል። የኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የዋና ዳይሬክተር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሳባ ዘሪሁን በበኩላቸው በዚህ ስራ ባለድርሻ እንደመሆናችን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ዝግጁ ነን ብለዋል።
የአዲስ አበባ ኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስኬቶች ለአፍሪካ ሀገራት ከተሞች ዕድገት ትምህርት የሚሰጥ ነው
Mar 18, 2026 101
አዲስ አበባ፤መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦የአዲስ አበባ ኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስኬቶች ለአፍሪካ ሀገራት ከተሞች ዕድገት ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የዛምቢያና ኢስዋቲኒ የአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞች ገለጹ። በአዲስ አበባ የተገነቡ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራ መዲናዋን ውብ ገፅታ በማላበስ ለነዋሪዎችና ጎብኝዎች ምቹ የእንቅስቃሴ ምኅደር ፈጥረዋል። በመዲናዋ በአጭር ጊዜ የተመዘገቡ የልማት ውጤቶችም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ዕውቅናን በማስገኘት ልምድና ተሞክሮ እየተቀሰመባቸው ይገኛል። በአዲስ አበባ የተጀመረው የኮሪደር ልማትም ከተማዋን ውብ ገፅታ በማላበስ ነዋሪዎችን ምቹና የአረንጓዴ ከባቢ በማጎናጸፍ በ75 የኢትዮጵያ ከተሞች እየተተገበረ ይገኛል። የዛምቢያና የኢስዋቲኒ የአካባቢ ጥበቃ ሙያተኞች ለኢዜአ እንዳሉት፤ አዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካዊያን ማዕከልነቷን በተግባር ያረጋገጡ የልማት ውጤቶች ተገኝተዋል። በመዲናዋ በአጭር ጊዜ የተገነቡ አስደናቂ የልማት ውጤቶችም ከተማዋን ውብ ገፅታ በማላበስ ምቹ የከተሜነት ምኅዳር እንዲፈጠር ማድረጉን ገልጸዋል። በዛምቢያ የአካባቢና የገጠር ልማት ሚኒስቴር የደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ባለሙያ ብሬን ሲያካበያ፤ አዲስ አበባ ከጥቂት ዓመታት በፊት የተጎሳቆለና እርጅና የተጫጫነው ገፅታ እንደነበራት አስታውሰዋል። በአሁኑ ወቅት በአጭር ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ የተገነባው የኮሪደር ልማት ነዋሪዎች ምቹና ፅዱ የአረንጓዴ ከባቢን ያጎናጸፈ አስደናቂ ለውጥ መምጣቱን ገልጸዋል። የመዲናዋ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶችና ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውም ውብ የከተሜነት ገፅታን በመፍጠር ልዩ ድምቀት እንደፈጠሩ ተናግረዋል። በህዝብና በአመራር ቁርጠኝነት ተገንብተው የተጠናቀቁት የአዲስ አበባ የልማት ስኬቶችም ሀገራቸውን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት ከተሞች ዕድገት ትልቅ ትምህርት መሆኑን አንስተዋል። የኢስዋቲኒ የአካባቢ ጥበቃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ባለሙያ መሎሰም ቡሊ በበኩላቸው፣ ከተሜነት የአንድ ሀገር የዕድገትና ስልጣኔ መገለጫ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ በአጭር ጊዜ የተገኙ ተምሳሌታዊ የኮሪደርና የአረንጓዴ ልማት ስኬቶች ዜጎች ዘመናዊ የከተሜነት አኗኗር ሥርዓት እንዲጎናጸፉ ያደረጉ መሆናቸውን ገልጸዋል። የመዲናዋ አስደናቂ የከተማ ውበት፣የአረንጓዴና ቆሻሻ አያያዝ የልማት ስኬቶች የአፍሪካን የአየር ንብረት ለውጥና የአካባቢ መራቆት የመቀነስ ግብ ያገናዘቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ልማትም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቀነስ አህጉራዊ አጀንዳዎችን የሚያሳካና ትምህርት የሚቀሰምበት መሆኑን አንስተዋል።
በአሪ ዞን ማኅበረሰቡን ያሳተፈ የጎርፍ እና የናዳ ቅድመ መከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው
Mar 18, 2026 138
ጂንካ፤ መጋቢት 9/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ ዞን ለጎርፍ እና ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ማኅበረሰቡን በማሳተፍ አደጋን ቅድመ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የዞኑ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የዞኑ አደጋ ሥጋትና ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስራት አበበ እንደገለጹት፤ በአሪ ዞን የሚገኙ አራት ወረዳዎች በመልክዓ ምድራዊ አቀማመጣቸው ተራራማና ተዳፋት በመሆናቸው በተደጋጋሚ ለናዳ አደጋ ተጋላጭ ናቸው። በተመሳሳይ በዞኑ የሚገኙ ሦስት ከተሞች ደግሞ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ባለፈው ዓመት ወቅት በዎባ አሪ ወረዳ በተከሰተ የአፈር መንሸራተት በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ያስታወሱት ኃላፊው፤ በዘንድሮው ዓመትም በደቡብ አሪ ወረዳ ወሰት ቀበሌ መሰል አደጋ መከሰቱን ተናግረዋል። ዘንድሮ የተከሰቱት አደጋዎች ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነጻጸሩ በእጅጉ የቀነሱት ማኅበረሰቡን በማሳተፍ በተከናወኑ የመከላከል ሥራዎች መሆኑን አስረድተዋል። በአሁኑ ወቅትም የበልግ ዝናብን ተከትሎ ሊከሰት የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ አርሶ አደሮችን ለጊዜው ከአካባቢው የማውጣት ሥራ እየተሰራ ነው። በከተሞች በቆሻሻ የተደፈኑ የፍሳሽ ቦዮችን የማጽዳት ተግባር፤ ያልተጠበቀ የወንዝ ሙላት ለሰውና ለእንስሳት ሕይወት መጥፋት ምክንያት እንዳይሆን ማኅበረሰቡ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች እየሰሩ ነው ብለዋል። የደቡብ አሪ ወረዳ የወሰት ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ኃይሉ ከማይ በሰጡት አስተያየት፤ አካባቢያቸው ለናዳ ተጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረጉ መሆኑን ገልጸዋል። አደጋ እንዳይደርስባቸውም ለጊዜው ከአካባቢው በመራቅ ራሳቸውን እየጠበቁ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ሌላኛው የአስተያየት ሰጪ የባካ ዳውላ አሪ ወረዳ የሴኔጋል ቀበሌ ነዋሪ አቶ ማርቆስ አዲሱ በበኩላቸው፤ በአካባቢው በተከናወነው የተፋሰስ ልማት ሥራ ቀደም ሲል ይከሰት የነበረውን ናዳ መከላከል መቻላቸውን ገልጸዋል። ለናዳ ተጋላጭ በሆኑ ስፍራዎች ችግኞችን በመትከል አፈሩ እንዳይሸረሸር ጥበቃ እያደረግን ነው ያሉት አቶ ማርቆስ፤ በዚህም አደጋዎችን አስቀድሞ መከላከል መቻሉን አረጋግጠዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የኢጋድ እና ጃፓን ትብብር መጠናከር ለቀጣናዊ ሰላም የጎላ ሚና አለው
Mar 9, 2026 183
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018(ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና ጃፓን በቀጣናው ሰላም ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሠሩ ገለጹ። የኢጋድ ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ዳይሬክተር ሂሮኒሪ ሱዙኪ ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል። በዚሁ ወቅትም፤ በኢጋድ ቀጣና ስላለው የሰላም እና ደኅንነት ሁኔታ ሐሳቦችን ተለዋውጠዋል። በቀጣይም ትብብራቸውን በይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሠሩ ማረጋገጣቸውን ኢጋድ ሴክሬተሪያት መረጃ ጠቁሟል። ጃፓን ለኢጋድ እና አባል ሀገራት፤ በቀጣናው ሰላም፣ መረጋጋት እና ልማት መረጋገጥ ሥራ ዋና አጋር ሆና መቀጠሏም ተመላክቷል።
ሀገራት የሴቶች መብቶችን የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን መውሰድ ይገባቸዋል- መሐሙድ አሊ ዩሱፍ
Mar 9, 2026 166
አዲስ አበባ፤ የካቲት 30/2018 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ሀገራት የሴቶች መብቶች እና የሥርዓተ ጾታ እኩልነነት የሚያረጋግጡ ጠንካራ እርምጃዎችን እንዲወስዱ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ይገኛል። "መብቶች፣ ፍትሕ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሐሳብ ነው። የአፍሪካ ኀብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመልዕክታቸውም፤ ቀኑ የአፍሪካ ሴቶች እና ልጃገረድ ስኬቶችን የምናከብርበት፣ ሴቶችን ማብቃት እና ጥበቃ ላይ የገባናቸውን ቃል ኪዳኖች ዳግም የምናድስበት ነው ብለዋል። ሴቶች በአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ከአመራር ሰጪነት እስከ ቴክኒካዊ ቦታዎች ወሳኝ ሚና እየተጫወቱ እንደሚገኙም አመልክተዋል። የሥርዓተ ጾታ እኩልነት የተቋሙ ሥራ ማዕከል መሆኑንም አስረድተዋል። የአፍሪካ ኅብረትም ቀኑን እያከበረ ሲሆን፤ የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር በአፍሪካ የሴቶችን መብቶች የሚደግፉ ቁልፍ ማዕቀፎችን በዚሁ ወቅት አንስተዋል። ለአብነትም የአፍሪካ ኅብረት የሰው እና ዜጎች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች የሕግ ማዕቀፍ፣ የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል) እና የሴቶችና ልጃገረዶች ጥቃትን ማስቆም ያለመውን የኅብረቱ ን ኮንቬንሽን በማሳያነት ጠቅሰዋል። የኮንቬንሽኑ ወደ ትግበራ መግባት ትልቅ ስኬት እንደሆነ ገልጸው፤ ሀገራት በሕግ አውጪ ምክር ቤት ማዕቀፉን በማጽደቅ ወደ ትግበራ እንዲያስገቡ ጥሪ አቅርበዋል። ሊቀ መንበሩ የሥርዓተ ጾታ እኩልነት እና የልማት የትኩረት መስኮች ቁርኝት እንዳለውም አመላክተዋል። የአፍሪካ ኅብረት የ2026 ትኩረት በሆነው ውኃ እና ንጽህና ጋር በተያያዘ፤ ሀገራት የሴቶችን ጫና የሚያቃልሉ እና ተጠቃሚነታቸውን የሚያረጋግጡ ሥራዎችን እንዲያከናውኑም ጥሪ አቅርበዋል።
በቀጣናው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው -ኢጋድ
Mar 8, 2026 166
አዲስ አበባ፤ የካቲት 29/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂን ጨምሮ በቀጣናው የሴቶችን የአመራርና ውሳኔ ሰጪነት ለማሳደግ የሚያስችሉ ማዕቀፎች ተግባራዊ እየተደረጉ እንደሚገኙ አስታወቀ። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ዛሬ ለ115ኛ ጊዜ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው። "መብቶች፣ ፍትህ እና የተግባር ምላሽ፤ ለሁሉም ሴቶች እና ልጃ ገረዶች" የሴቶች ቀን የሚከበርበት መሪ ሀሳብ ነው። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሴቶችን ቀን በማስመልከት መልዕክት አስተላልፏል። ኢጋድ ለሴቶች አመራር ሰጪነት፣ አይበገሬነት እና በቀጣናው ሰላም፣ ብልጽግና እና ለውጥ ለማምጣት እያበረከቱት ላለው አስተዋጽኦ ክብር እና እውቅና እንደሚሰጥ ገልጿል። በኢጋድ ሴቶች በቀጣናው አመራር ሰጪነት ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። የኢጋድ የሰላም፣ ግብርና፣ ዲጂታል ደህንነት፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እና መሬት አስተዳደር ፎረሞች እንዲሁም የኢጋድ የስርዓተ ጾታ ስትራቴጂ ጨምሮ የተለያዩ ኢንሼቲቮች እየተገበረ መሆኑን አመልክቷል። የሴቶች ድምጽ እንዲሰማ እና መሉ ተሳትፏቸው እንዲረጋገጥ የሚያግዙ መድረኮችን መፍጠሩን ነው የኢጋድ ሴክሬተሪያት በመረጃው ያስታወቀው።
ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በሰላምና ደኅንነት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Mar 5, 2026 198
አዲስ አበባ፤ የካቲት 26/2018 (ኢዜአ)፦ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ) እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም እና ደኅንነት ያላቸውን ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የኢጋድ የሰላም እና ደኅንነት ዘርፍ ዳይሬክተር ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ከአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጋር በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ውይይት አድርገዋል። ኮማንደር አበበ ሙሉነህ ውይይቱን ያደረጉት የኢጋድ ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁን (ዶ/ር) በመወከል ነው። ውይይቱ ኢጋድ እና የአፍሪካ ኅብረት በቀጣናው ሰላም፣ ደኅንነት እና መረጋጋት ላይ ያላቸውን የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ነው። ሁለቱ ወገኖች የጋራ የተግባር ምላሽ ለመስጠት እና ስትራቴጂካዊ ትብብራቸውን ለማጎልበት ቁርጠኛ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
በኢዜአ ዐይን …!
Mar 16, 2026 2678
በዮሐንስ ደርበው ባሳለፍነው ሳምንት … የጤና ነገር … የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ ...! በየአዝማናቱ ሕዝብን በኅብረት ያሥተሣሠሩ ክስተቶች ይስተዋላሉ። ታሪክ እንደሚያሳየው ኢትዮጵያውያን በየጊዜው አንድ በሚያደርጓቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መለያየት አይሆንላቸውም። እንደውም በመሃላቸው የሚከሰቱ አለመግባባቶች ሁሉ እንደጉም ተነው በጋራ መቆም የሠርክ ተግባራቸው ነው። በዓድዋ፣ በካራማራ እና በሌሎችም ስፍራዎች ያደረጓቸውን ፀረ ባዕዳን ትግል ጨምሮ እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ባሉት የልማት ሥራዎች ያስመዘገቧቸው ድሎች በማሳያነት ሊጠቀሱ ከሚችሉት የሚካተቱ ናቸው። እነዚህ የኢትዮጵያን ኅልውና ለማስጠበቅ ሕዝቡ በአንድነት በመሰለፉ የተቀዳቻቸው ድሎች ናቸው። አንድነት ባይኖር ድሎቹ አይታሰቡም። የጀግኖች አያቶቻቸው ልጆች በዚህ ዘመንም ትልቅ ድል አስመዝግበዋል፤ በቀጣይ ደግሞ ሌላ። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት የተገለጠበት ዘርፈ-ብዙ ፀጋ ካላቸው ላይ ዕጃቸውን ያልሰበሰቡ፤ ኪሳቸውንም ያልዘጉ ኢትዮጵያውያን፤ በቁጭት፣ በደም፣ በላብ እና በጥሪታቸው ሀገራቸውን በክብር ያስጠራ ታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን የመሰለ ሜጋ ፕሮጀክት ገነቡ። ፍሬውንም ማጣጣም ከጀመሩ ሰነባበቱ። ይህ ጥቅመ-ብዙ ግድብ ከቀዳሚ ዓላማው የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት የተሻገሩ በርካታ ትሩፋቶች አሉት። አንድነትን በማጠናከር ረገድ የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት በተደፈረ ጊዜ በዓድዋ ዘመቻ ወገን በኀብረት እንደቆመው ሁሉ፤ የሕዳሴው ግድብ በግንባታ ጊዜው የሀገሬው ኅብረት ማሠሪያ ሆኗል። በዚህ ዘመንም ለአንድ ዓላማ መቆምን በማስረጽ የራሱን ዐሻራ አኑሯል። የሀገራቸውን ብልጽግና በሚሹ ታታሪዎች ርብርብ እንደመገንባቱ፤ ከምረቃ በኋላም የሚጠበቅበትን የኤሌክትሪክ ኃይል በማምረት ለሁሉም መሆኑን በተግባር አሳየ። ወዲህ ደግሞ ኢትዮጵያ ባሏት የቱሪዝም መዳረሻዎች ላይ ተደማሪ መስኅብ ሆነ። ዘርፉ በኢኮኖሚው ላይ ያለው ፍሰት እየጎመራ የሕዝቡ ተጠቃሚነት እንዲያድግ የሚደረገውን ጥረት እያገዘ ይገኛል። እንደ ዜጋ ግድቡ በቁርጠኝነትና በብልኅ አመራርነት ለስኬት መብቃቱ ደስ ያሰኛል፤ ከኃይል ማመንጨት ባሻገር የጎብኝ መዳረሻ መሆኑ ደግሞ ተጨማሪ ፀጋ። ይህን ዕድል በአግባቡ መጠቀም ይገባል፤ አንድም አካባቢውን በመጎብኘት እንዲሁም ለጎብኝ ምቹ ሁኔታዎችን በማስፋፋት። ምክንያቱም፤ የግድቡ ታሪካዊ አሠራር …ቁጭቱ…ቁርጠኝነቱ…አንድነቱ ... ራሱን የቻለ ታሪክ ነውና ይህን ሠንዶ ለጎብኝዎች በሚሆን መልክ ማንበር ያስፈልጋል። የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይስ? በሀገሪቱም በአኅጉሪቱም በዘርፉ ሜጋ የሆነውን ይህን ፕሮጀክት ለመልከ-ብዙ ፈተናዎች ሳይበገሩ በስኬት የቋጩ የዓድዋ እና ካራማራ ድሎች ባለቤት የሆኑት የብርቱዎቹ ልጆች ብርታት በቀጣይ እንደ ባሕር በር ባለቤትነት ባሉ ትላልቅ የኅልውና ጉዳዮች ላይ ሊገለጥም ይገባል። የባሕር በር ባለቤትነት የትውልድ ጥያቄ ነው። የሕዝብ ጉዳይ ነው። በዚህ ጉዳይ ቅንጣት ልዩነት አያሻም። “ድር ቢያብር አንበሳ ያሥር” ነውና ብኂሉ… ተባብሮ ኅልውናን ማስቀጠል እንጂ…. ደግሞም ይህ ታሪካዊ ስህተትን የማረቅ ሂደት ነው። በታሪክ፣ በሠነድ እና በሌሎችም ማሥረጃዎች ኢትዮጵያ ሐቅ አላትና። በጥቃቅን ነገሮች የማይጠቅም የልዩነት በርን መክፈት አያሻም። ብርቱዎቹ ለልዩነት ዕድል ያልሰጡት በዓድዋ በካራማራ በኅብረት አንጸባራቂ ድል ተጎናጽፈዋል። የአሁኑ ትውልድም ኅልውናውን ለማቆየት የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ የግድ ይለዋል። ታሪክን መዘከር ተገቢ ነው፤ ጠብቆ በማቆየት መማርም። አሁንም ዳግም ታሪክ መሥራት ይገባል። ለዚህም በቁጭት መነሳት…የባሕር በር ባለቤትነትን ማረጋገጥ። #ዓድዋ #ካራማራ #የብርቱዎቹ_ልጆች_ብርታት #ታላቁ_የኢትዮጵያ_ሕዳሴ_ግድብ #የባሕር_በር #ቀይ_ባሕር #የትውልድ_ጥያቄ #በኢዜአ_ዐይን
ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ለቀጣናው ይዞት የመጣው ተስፋ
Mar 2, 2026 305
በሙሴ መለሰ(ኢዜአ) የአየር ንብረት ቀውስ በፍጥነት እያደገ ይገኛል። ይህም በቀጣናው ግብርና እና ስርዓተ ምግብ ላይ ከፍተኛ ስጋት ደቅኗል። ኢ-ተገማች የዝናብ ሁኔታ፣ በተደጋጋሚ ጊዜ የሚከሰቱ ድርቆች እና የመሬት መራቆት የግብርና ምርታማነትን በመቀነስ፣ በዜጎች ኑሮ ላይ ተጽእኖ በማሳደር እና የስርዓተ ምግብ ላይ ፈተና መሆኑን ቀጥሏል። ግብርና በምስራቅ አፍሪካ ከ25 እስከ 40 በመቶ ዓመታዊ ጥቅል ምርት (ጂዲፒ) የሚሸፍን ነው። የግብርናውን አብዛኛውን ድርሻ የሚወስዱት አነስተኛ ይዞታ ያላቸው አርሶ አደሮች ናቸው። በነዚህ ሀገራት ግብርና ከፍተኛውን የውጭ ምንዛሬ ገቢ ድርሻ ይወስዳል። በቀጣናው ያለው ግብርና አብዛኛው ዝናብ ላይ ጥገኛ በመሆኑ በየጊዜው ለሚቀያየረው የአየር ንብረት ሁኔታ እና አደጋዎች ተጋላጭ ነው። ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋሙ ስትራቴጂዎች እና ስልቶች መቅረጽና መተግበር ላይ ውስንነቶች አሉ። ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ጠንካራ የግብርና ስርዓት ለመገንባት በአፍሪካ ደረጃ እየተተገበሩ ካሉ ተግባራት መካከል አንዱ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) ሁሉን አቀፍ እይታ ያለው የግብርና ምርታማነት አማራጭ መሆኑን የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህ የአሰራር ዘዴ የግብርና ምርታማነት ብቻ ሳይሆን ለአደጋዎች የማይበገር አቅም መገንባት እና ለአየር ንብረት ተስማሚ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል። ጽንሰ ሀሳቡ ከተለምዷዊ የግብርና አሰራር በመውጣት ሳይንስ፣ ፖሊሲ፣ ፋይናንስ እና ቴክኖሎጂን በማጣመር ግብርናን የማይበገር፣ ዘላቂ እና የኢኮኖሚ ጠቀሜታውን ማላቅ እንደሚገባ ያመለክታል። ምርታማነት እና ገቢ መጨመር፣ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አቅም መገንባት እንዲሁም የማጣጣሚያ እቅዶችን መተግበርን ጨምሮ የበካይ ጋዞችን ልቀት መቀነስ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና ቁልፍ የሚባሉ ምሰሶዎች ናቸው። በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና (Climate-smart agriculture) አማካኝነት በቆሎ፣ ስንዴ፣ ማሽላ እና ሌሎች ድርቅና ከፍተኛ ሙቀትን የሚቋቋሙ ሰብሎችን በመትከል ምርታማነትን የማሳደግ ስራ በአፍሪካ ደረጃ እየተከናወነ ይገኛል። የውሃ እና አፈር አስተዳደርን ማሻሻል፣ ውጤታማ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም እና ዲጂታል የአየር ንብረት የማማከር አገልግሎቶችን (digital climate advisory services) መስፋት ምርታማነትን በመጨመር እና አርሶ አደሮች በመረጃ ላይ የተመሰረተ ውሳኔዎችን እንዲያሳልፉ እያገዘ ይገኛል። የአፍሪካ ልማት ባንክ የአፍሪካ የግብርና ትራንስፎርሜሽን የቴክኖሎጂ ኢኒሼቲቭ ከ13 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና ኢኖቬሽን ስራዎች ተደራሽ እንዲሆኑ ያደረገ ሲሆን ምርት በ25 ሚሊዮን ቶን እንዲጨምር አስችሏል። በኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆኑ ኢኒሼቲቮችን በመተግበር ምርታማነትን ከማሳደግ ባለፈ ዜጎች ብዝሃ ህይወት እና አካባቢን እንዲጠብቁ የበኩሉን ሚና እየተጫወተ ይገኛል። አረንጓዴ አሻራ የዚሁ ስራ አንድ ማሳያ ነው። ለአየር ንብረት ተስማሚ የሆነ ግብርና (Climate-smart agriculture) በምስራቅ አፍሪካ ላለው የአየር ንብረት ቀውስ እንደ ስትራቴጂካዊ ምላሽ መስጫ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ነው። የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ዘላቂ ፈተና በሆነበት የአፍሪካ ቀንድ ይህ የግብርና አሰራር ዘዴ አማራጭ የሌለው ጉዳይ እንደሆነ ይነሳል። ድርቅን የሚቋቋሙ ሰብሎችን መጠቀም፣ የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች፣ የተቀናጀ የደን ልማት ስራ፣ የውሃ አስተዳደርን ማሻሻል፣ አርብቶ አደሮች በሚኖርባቸው አካባቢዎች የማይበገር የአደጋ መቋቋም ስርዓትን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት መረጃውን በወቅቱ ተደራሽ ማድረግ እና የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን ማጠናከር እየተከናወኑ ካሉ ስራዎች መካከል ይጠቀሳሉ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የምግብ ስርዓት የማይበገር ፕሮግራም (FSRP) ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ትኩረት ከሰጣቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ከዚሁ ጋር በተያያዘ በአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባ በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና እና የስርዓተ ምግብ ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ ስብሰባ ይደረጋል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በአፍሪካ ቀንድ ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት ላይ ያተኮረ ቀጣናዊ የምክክር ፎረም የካቲት 24 እና 25 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ያካሂዳል። የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) የሥርዓተ ምግብ አይበገሬነት ፕሮግራም ከዓለም ባንክ የአፍሪካ ቢሮ እና ከደቡባዊ አፍሪካ የግብርና ምርምር እና ልማት ማስተባበሪያ ማዕከል ጋር በመሆን ፎረሙን አዘጋጅተውታል። ምክክሩ የአየር ንብረት ለውጥ ግብርና ላይ ተጽእኖ እያሳደረ ባለበት ወቅት የሚካሄድ መሆኑ ወቅቱን የጠበቀ እንደሚያደርገው ተገልጿል። ከአደጋ ጊዜ ምላሾች ወደ ረጅም ጊዜ የማይበገር ስትራቴጂዎች እና ከሙከራ ጊዜ ኢኒሼቲቮች ወደ ቀጣናዊ መፍትሄዎች መሸጋገር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ምክክር እንደሚደረግ ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። በፎረሙ ላይ ፖሊሲ አውጪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ተመራማሪዎች እና የግሉ ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ይሳተፋሉ። በቀጣናው የሥርዓተ ምግብን ማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርናን ማስፋት የሚቻልባቸውን ተጨባጭ መፍትሄዎች እንደሚዳሠሡም ተመላክቷል። የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የማይበገር፣ አካታች እና ኢንቨስትመንትን ማዕከል ያደረገ ጠንካራ የግብርና ሥርዓቶችን ከምግብ ምርታማነት እና ኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ጎን ለጎን መገንባት የሚቻልበትን መደላድል መፍጠር ከፎረሙ የሚጠበቅ ዋና ውጤት ነው ተብሏል። ቀጣናዊ ፎረሙ ኢጋድ ተጋላጭነትን ወደ እድል ለመቀየር እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የተቀናጀ የተግባር ምላሽ ለመስጠትና ለግብርና ኢኖቬሽን ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይም አመልክቷል። በአፍሪካ ቀንድ ሚሊዮኖች የአየር ንብረት ለውጥ በፈጠራቸው ቀውሶች ገፈት ቀማሽ በሆኑበት በአሁኑ ወቅት ለአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የቴክኒክ አማራጭ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። የግብርና አሰራር ዘዴው ለዘላቂ ልማት፣ ለኢኮኖሚ አይበገሬነት እና ማህበራዊ መረጋጋት አስፈላጊ የሆነ ስትራቴጂ እንደሆነም በዘርፉ ባለሙያዎች ይነሳል። በአዲስ አበባ የሚካሄደው ቀጣናዊ ፎረም በአየር ንብረት ተስማሚ ግብርና የሀገራትን የፖለቲካ ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ድንበር ተሻጋሪ ትብብርን ለማጠናከር እና ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች ያለውን የኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚታይ መድረክ ነው። በተለይም ለአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚከናወነው ስራ የማይበገር አቅምን ለመገንባት ቁልፍ ሚና ይጫወታል። በቀጣናው የሚደረጉ ጥረቶች ከንግግር ባለፈ በተግባር ታግዘው ውጤታማ ከሆኑ ከተበታተኑና አደጋን ማዕከል ካደረጉ ምላሾች ወደ የማይበገር፣ አካታች እና መጪውን ጊዜ የዋጀ የግብርና እድገት መሸጋገር ይቻላል።
የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና !
Feb 24, 2026 355
(በፋኑኤል ዳዊት፤ ከሀዋሳ ኢዜአ ቅርንጫፍ) ሀዋሳ፤ የካቲት 17/2018 (ኢዜአ):- የባህር በር ለቀጣናዊ ሰላም፤ ለአህጉራዊ ብልፅግና ! የባህር በር የአንድ ሀገር መሬት በቀጥታ ከውቅያኖስ ወይም ከባህር ጋር የሚገናኝበት ዳርቻ ሲሆን አጠቃላይ ዓለም አቀፋዊ ግንኙቶች የሚከናወኑበት መተላለፊያም ነው። የባህር በር ከንግድና ከሌሎች የኢኮኖሚያዊ ፋይዳዎች ባሻገር የዓለም አቀፋዊ ወዳጅነትና ትስስር የቀጥታ ተሳታፊና ተጠቃሚ በማድረግ ጸጥታንና አስተማማኝ ደህንነት ለማስጠበቅ ጉልህ እንደሆነ ይገለጻል። ስለዚህም ነው የባህር በር የህልውና ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰደውና የባህር በር አልባ ሀገር መሆን እንደ ከባድ ችግር የሚታየው። የባህር በር የሌላቸው ሀገራት ከሚጋፈጧቸው በርካታ ችግሮች መካከል የሸቀጦች የምልልስ ጊዜ ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ በአለም አቀፍ ንግድ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖን ያሳድራል። በዚህም ሳቢያ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት በትራንስፖርትና በማሪታይም ንግድ በጎረቤት ሀገራት ላይ ጥገኛ ይሆናሉ። ይህም ለወደብ ኪራይ ከፍተኛ ወጪ እንዲያወጡ ስለሚያስገድድ በኢኮኖሚ እድገት ላይ ተጽዕኖው ይጎላል። ጥገኝነቱ ለጂኦፖለቲካዊ ውጥረት እና አለመረጋጋት የማጋለጥ እድሉ የሰፋ ነው። በአንዱ ሀገር የሚነሳው የፖለቲካ ትኩሳት ወይም የፖለቲካ አለመረጋጋት በተለይም የባህር በር የሌለውን ሀገር ሳይወድ በግድ ሰለባ የማድረግ ወይም ተፅዕኖ የመፍጠር ዕድሉ ሰፊ ነው። ከባህር በር ተነጥላ የማታውቀው ኢትዮጵያ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ ለዘመናት የባህር በር አልባ ሀገር የመሆን ክስተት በማስተናገዷ ከላይ በጥቂቱ የጠቀስናቸውን ችግሮች ስትጋፈጠው ቆይታ ዛሬ ላይ ደርሳለች፡፡ ኢትዮጵያ የባህር በር ያጣችበት መንገድ ሁሌም ህዝቡን ሲቆጨውና ሲያንገበግበው የቆየ ጉዳይ ሲሆን በጥቂት ግለሰቦች ይሁንታ የተቸረ ሀገርን ዝግ አድርጎ የማቆየት ሴራ ነው። ይህ ሁኔታ ውስጥ ለውስጥ ሲብላላ የቆየውን የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ገሃድ ያወጣ የትውልዱ ጥያቄ እንዲሆን አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ ይፋ በማድረግ ትውልዱ በውስጡ ይዞት የኖረውን ቁጭት ግልጽ እንዲወጣ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርቡ 65ኛ ዓመቱን ባከበረው የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ክብረ በዓል ላይ ባደረጉት ንግግር ኢትዮጵያ ከታች ከሶማሌ ጫፍ እስከ ምፅዋ ጫፍ የሚያጋጥሙ የሽብርተኝነት እንቅስቃሴዎችን ለመግታት የሚችልና ለቀጣናዊ ሰላም የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው አክለው እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከራሷ አልፋ ለጎረቤት ሀገራት ሰላም ብሎም ለአፍሪካ ብልፅግና የሚሰራ ተቋም እየገነባች መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ምላሽ ማግኘት ጠቀሜታው ለገረቤት ሃገራትና ለሌሎችም መሆኑን በግልፅ አስቀምጠዋል። በጉዳዩ ዙሪያ ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ ምሁራን እንደገለፁትም፤ ኢትዮጵያ በዘመናት ታሪኳ ተነጥላ ከማታውቀው የባህር በር ባለቤትነት በታሪክ ላለፉት 30 ዓመታት ተገልላ መቆየቷ ለጂኦ ፖለቲካዊና ጂኦ ኢኮኖሚክስ ችግሮች አጋልጧታል፡፡ በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የዲፕሎማሲ አሰልጣኝና የውጭ ፖሊሲ ተመራማሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ (ዶ/ር) በመንግስትነትና ከባህር በር ሳትነጠል ለዘመናት የኖረች ሀገር በሴራ ፖለቲካ ዝግ ሀገር እንድትሆን መደረጉ የታሪክ ስህተት መሆኑን አንስተዋል። የዓለም ሀገራት በተለያየ ምክንያት ከባህር በር እንዳይገለሉ የሚያስቀምጡት ህጎች ቢኖሩም የኢትዮጵያ በቅርብ ርቀት ከዓለም ጋር በቀጥታ እንዳትገናኝ፣ የባህር በር አልባ ሀገር እንድትሆን መደረጉ ተቀባይነት የሌለውና በትውልዱ ዘንድ ምላሽ አጥቶ የተቀመጠ ጥያቄ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ ደመቀ አጭሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ጥያቄው የትውልድ መሆኑን አንስተው ኢትዮጵያ በሴራና አግባብ ባልሆነ መንገድ የባህር በር ባለቤትነትን እንዳጣች ነው የሚናገሩት፡፡ ያለፈው ስርዓት የባህር በር ጉዳይን በግልም ይሁን በቡድን እንዲነሳ ባለመፈለጉ ውስጥ ውስጡን የቆየውን ይህ ጉዳይ አሁን ላይ መንግስት ኃላፊነትን ወስዶ እስከ መቼ ተዘግተን እንኖራለን ብሎ በይፋ ማንሳቱ ወሳኝና ወቅቱን የጠበቀ መሆኑን ምሁሩ አንሰተዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ተጠቅማ የውጭ ግንኙነቶችን፣ ንግድና እንዲሁም በዚህም በቀጠናው ተፅዕኖ የመፍጠር ሀይል እንደነበራት አውስተው ከባህር በር በተለይም ከቀይ ባህር ተነጥላ አትታይም ያሉት ደግሞ በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት መምህር ንጉስ በላይ (ዶ/ር) ናቸው። ይሁን እንጂ ከአውሮፓ ቅኝ ገዢ ሀገራት መካከል ኢጣሊያ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1890 ዎቹ ጀምሮ እስከ 1950 ዎቹ ኤርትራን በመግዛቷ ከባህር በር ለመገለል አደጋ የዳረጋት ክስተት አጋጥሟት እንደነበር እና ይህም በታሪኳ ዝግ ሀገር እንድትሆን ማድረጉን አስታውሰዋል። ይሁን እንጂ እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር ከ1952 ጀምሮ ኤርትራ ከኢትዮጵያ ጋር በፌዴሬሽን በመዋሃዷ የባህር በር ባለቤትነት መብት ድጋሚ እንድታገኝ በማድረግ እስከ 1991 ድረስ ተጠቃሚ እንደነበረች አንስተዋል። በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ የእንግሊዘኛ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ እንዳልካቸው ጀንበሬ (ዶ/ር) በታሪኳ ከቀይ ባህር ተነጥላ የማታውቀው ሀገር ኢትዮጵያ የኤርትራን የሀገርነት ጥያቄ ለመመለስ ሲባል የባህር በርን ሙሉ በሙሉ እንድታጣ መደረጉ ፈጽሞ ተገቢነት የሌለውና ፈጣን ምላሽ የሚሻ የትውልዱ የቁጭት ጥያቄ ነው ብለዋል። በተለይም ኢህአደግ ኢትዮጵያን በመራባቸው ዓመታት ይህ ጉዳይ እንደ ጥያቄ ማንሳት እንደወንጀል የሚታይ ሆኖ መዝለቁ ስርዓቱ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ ከመስጠት ባለፈ ታሪክንና የሀገሪቷን የመጻኢ ዕጣ ፈንታ ያልተመለከተ መሆኑ ጥያቄ ሲያስነሳበት እንደነበር አስታውሰዋል። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ለወደብ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን ከብሔራዊ ጥቅም ጋር በቀጥታ የተሳሰረ የህልውና ጉዳይ መሆኑን የሚገልፁት አምባሳደር ማርቆስ (ዶ/ር) በተፈጠረ የፖለቲካ ስህተት ከባህር ተዘግታ መቆየቷ አግባብ ስላልሆነ ጉዳዩ ፈጣን ምላሽን ይሻል ብለዋል። ለዚህም በፖለቲካ ስህተትና በሴራ ያጣችውን የባህር በር ባለቤትነትና ተጠቃሚነት ጥያቄ እንዲመለስላት የዓለም ማህበረሰብ ጉዳዩን በግልጽ እንዲያውቀው ለማድረግ በተሰራ ስራ በጎ ምላሽ እየተገኘበት ነው ብለዋል። ተገቢ ባልሆነ መንገድ የታጣውን የባህር በር ማግኘት የትውልዱ የዘመናት የቁጭት ጥያቄ ተገቢ ምላሽ እንዲያገኝ መንግስት በቁርጠኝነት የጀመረውን የዲፕሎማሲ ጥረት አድንቀዋል። ጥያቄው የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ለሚበራከቱበት ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ሀገራቱ ላላቸው ተያይዝ የመበልፀግ ራዕይ መሳካት ወሳኝ ድርሻ ስላለው የጎረቤት ሀገራት ለጥያቄው በጎ ምላሽ ይሰጣሉ ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል። የባህር በር ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ፣ ለወታደራዊ ሀይል ፣ ለማናቸውም የውጭ ግንኙነት እንቅስቃሴ መሳለጥ ተኪ የለሌለው እንደሆነ ያነሱት ደመቀ(ዶ/ር) ለኢትዮጵያ የመኖር እና ያለመኖር የህልውና ጥያቄ እንዲሁም የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ እንደሆነ አንስተው የተለያዩ ስልቶች በመከተል ዕድሎችን ለመጠቀም የተጀመረውን ጥረትን ማጠናከር እንደሚገባም አስገንዝበዋል። ምሁሩ አክለውም በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች የተሳሰሩ የጎረቤት ሀገራትም በጉዳዩ ዙሪያ በጎ ምላሽ በመስጠት ሊተባበሩ እንደሚገባ ጠቅሰው የኢትዮጵያ ሰላምና ብልፅግና ለቀጣናው ብሎም ለአህጉሩ የሚኖረውን ፋይዳ በመረዳት ለጥያቄው ድጋፋቸውን ሊሰጡ ይገባል ብለዋል። በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የሚገኙ ሀገራት ያላቸውን ጥያቄ በፍትሃዊነትና በአግባቡ እየመለሱ ተያይዞ የመበልፀግ ዕድልን ለመጠቀም የኢትዮጵያን የባህር በር ጥያቄ መመለስ ለሁሉም ጠቃሚ መሆኑን ሊረዱትና ሊቀበሉት ይገባል ያሉት ደግሞ ንጉስ (ዶ/ር) ናቸው። የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስተጋብር የተሳሰረና መነጣጠል የማይቻል እንደሆነ የሚገልፁት ምሁሩ ይህም ያላቸውን ዕምቅ አቅም አቀናጅተው እንዲጠቀሙና ፍላጎታቸውን እንዲያሟሉ የማድረግ ዕድልን የሚያሰፋ፤ ቀጣናውንም የተረጋጋ የሚያደርግ መሆኑን ተናግረዋል ። የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ ለማንም የምንተወው አይደለም ትውልዱ እንዲመለስ የሚፈልገው ጥያቄ ነው ያሉት እንዳልካቸው (ዶ/ር) መንግስት በይፋ መጠየቁን እና በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲፕሎማሲ የተጀመሩ ጥረቶች እያስገኟቸው ያሉ በጎ ምላሾችን ማጠናከር ይገባል ብለዋል። ምሁሩ አክለውም ያለውን አለም አቀፍ በጎ ምላሽ ከግምት በማስገባትም የአፍሪካ ቀንድም ሆኑ ሌሎች ጎረቤት ሀገራት ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ቀጣናዊ ብሎም በዚህ ውስጥ አህጉራዊ ብልፅግናን ሊያረጋግጡ እንደሚገባ ነው ያስገነዘቡት።
የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ
Feb 14, 2026 340
በሙሴ መለሰ የአፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ (Assembly of Heads of State and Government) የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ የፖሊሲ እና የውሳኔ ሰጪ አካል ነው። ይህ አካል ከሁሉም አባል ሀገራት የተውጣጡ የመንግስታት ወይም የሀገራት መሪዎችን ያቀፈ ሲሆን፣ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች የመቅረፅ እና የቀጣይ አቅጣጫዎችን የመወሰን ስልጣን ተሰጥቶታል። በአፍሪካ ህብረት ድረ-ገጽ ላይ በቀረበው መረጃ መሰረት፣ የጉባኤው ዋና ተግባራት የሚከተሉት ናቸው፦ የፖሊሲ አቅጣጫዎች፦ የህብረቱን የጋራ ፖሊሲዎች መወሰን፣ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች መለየት እና ዓመታዊ የሥራ መርሐ-ግብሮችን ያጸድቃል። ውሳኔ አሰጣጥ፦ በአህጉራዊ ሰላም፣ ጸጥታ እና ልማት ላይ የመጨረሻ ውሳኔዎችን ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ፦ የህብረቱን ፖሊሲዎች እና ውሳኔዎች አፈጻጸም መከታተል፣ እንዲሁም አባል ሀገራት ግዴታቸውን መወጣታቸውን ያረጋግጣል። ሹመቶች፦ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፣ ምክትል ሊቀመንበር እና ኮሚሽነሮችን ይሾማል። ጣልቃ ገብነት፦ በአባል ሀገራት ውስጥ የጦር ወንጀል፣ የዘር ማጥፋት ወይም በሰው ልጆች ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎች ሲያጋጥሙ ጣልቃ የመግባት ውሳኔ ያሳልፋል። ክትትልና ግምገማ: የህብረቱን አካላት እና የስራ አፈጻጸም ይገመግማል። በጀት እና መዋቅር፦ የህብረቱን በጀት ማጽደቅ፣ እንዲሁም የኮሚሽኑን አደረጃጀት እና ደንቦችን መወሰን። የጉባኤው አወቃቀር እና የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት አባልነት፦ ጉባኤው የሁሉንም 55 አባል ሀገራት መሪዎች ወይም ሕጋዊ ተወካዮቻቸውን ያቀፈ ነው። የውሳኔ አሰጣጥ፦ ውሳኔዎች የሚሳለፉት በስምምነት (Consensus) ሲሆን፣ ስምምነት ላይ መድረስ ካልተቻለ ግን በሁለት ሦስተኛ (2/3) ድምፅ ይወሰናሉ። የአሰራር ጉዳዮች ደግሞ በቀላል አብላጫ ድምፅ ይጸድቃሉ። ምልዓተ ጉባኤ (Quorum)፦ ማንኛውንም ስብሰባ ለማካሄድ ቢያንስ ሁለት ሦስተኛው የአባል ሀገራት ተወካዮች መገኘት አለባቸው። የጉባኤው ቢሮ (Bureau) ጉባኤው በየዓመቱ የሚመረጥ አንድ ሊቀመንበር እና ሌሎች አራት አባላት (ምክትል ሊቀመንበሮች) ያሉት ቢሮ አለው። ይህ ቢሮ የአህጉሪቱን አምስቱንም ቀጣናዎች (ምስራቅ፣ ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብ እና መካከለኛ አፍሪካ) ተዋጽኦ የጠበቀ መሆን ይኖርበታል። የጉባኤው አሠራር እና መደበኛ ያልሆኑ ስብሰባዎች መደበኛ ስብሰባ፦ ጉባኤው ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ መደበኛ ስብሰባ ያደርጋል። ልዩ ስብሰባ (Extraordinary Session)፦ ማንኛውም አባል ሀገር ጥያቄ አቅርቦ በሁለት ሦስተኛ አባል ሀገራት ድጋፍ ካገኘ በማንኛውም ጊዜ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል። ውሳኔዎችን ተግባራዊ ማድረግ፦ ጉባኤው ያሳለፋቸው ውሳኔዎች በአባል ሀገራት ተፈጻሚ መሆናቸውን የመከታተል እና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለበት። የህብረቱ ከፍተኛ አመራሮች የኮሚሽኑ ሊቀመንበር፦ መሐሙድ አሊ ዩሱፍ (ጅቡቲ) እ.አ.አ በየካቲት 2025 ተመርጠው በአሁኑ ወቅት የህብረቱን የዕለት ተዕለት ሥራዎች የሚመራውን ኮሚሽን እየመሩ ይገኛሉ። ምክትል ሊቀመንበር፦ አምባሳደር ሰልማ ማሊካ ሃዳዲ (አልጄሪያ) የኮሚሽኑ ምክትል ሊቀመንበር ሆነው በማገልገል ላይ ናቸው። በተለያዩ ዘርፎች የሚሰሩ ስድስት ኮሚሽነሮች በህብረቱ የስራ አስፈጻሚ ክንፍ በሆነው ኮሚሽን እየሰሩ ነው። 39ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ “ዘላቂ የውኃ አቅርቦትና ደኅንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አጠባበቅ ሥርዓቶችን ማረጋገጥ፤ ለአጀንዳ 2063 ግቦች ስኬታማነት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። ከፍተኛው የውሳኔ ሰጪ አካል የሆነው ጉባኤው በተለያዩ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
ትንታኔዎች
ባሳለፍነው ሳምንት …
Mar 14, 2026 1307
ከየካቲት 29 - መጋቢት 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል … ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በምሥራቅ ኢትዮጵያ • ባሳለፍነው ሳምንት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በድሬዳዋ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል። በዚሁ ወቅትም ድሬ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ተመልክተዋል። ማዕከሉ በውስጡ 10 ተቋማት ይዞ 73 የሚሆኑ አገልግሎቶችን ለዜጎች እየሰጠ መሆኑንም ገልፀዋል። ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል • በተመሳሳይ በድሬዳዋ የተስማሚነት ምዘና ድርጅትን ጎብኝተዋል። ድርጅቱ ዓለም አቀፍ የአሠራር ሥርዓትን በመከተል ለአምራቾች፣ ለአገልግሎት ሰጪዎች፣ ለላኪዎች፣ ለአስመጪዎች፣ ለተቆጣጣሪ መሥሪያ ቤቶች፣ ለምርምር ተቋማትና ለሸማቹ ማኅበረሰብ የምርትና አገልግሎቶች የጥራት ማረጋገጫ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግረዋል። • የድሬዳዋ የኮሪደር ልማትንም የጎበኙ ሲሆን፤ የኮሪደር ልማቱ ምቹ የሕዝብ መዝናኛ ቦታዎች፣ የተሻሻለ የአካባቢ ውበትን እና ጥራታቸውን የጠበቁ የማኅበረሰብ መሰብሰቢያ ስፍራዎች በድሬዳዋ ዕውን እንዲሆኑ ማስቻሉን አስረድተዋል። • ከድሬዳዋ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር መርሐ-ግብር ያከናወኑት ባለፈው ሳምንት ነው። • በድሬዳዋ የሚገኘውን እመርታ ቤተ-መጻሕፍትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጎብኝተዋል። ቤተ-መጻሕፍቱ በአንድ ጊዜ ለ1 ሺህ ሰው አገልግሎት መስጠት እንደሚችል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። • በሳምንቱ መጀመሪያ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሐረሪ ክልል ሶፊ ወረዳ ቡርቃ ቀበሌ የተሠራውን የገጠር ኮሪደር ሥራ ተመልክተዋል። የአካባቢው ነዋሪ በንቃት የተሳተፈበት የገጠር ኮሪደር ሥራ፤ ባሕላዊ የግንባታ ዘዴን፣ የተደራጀ ዕቅድ እና ተግባራዊ የአሠራር ውጤት ያሳየ መሆኑን አብራርተዋል። • የቁንድዶ ተራሮችንም ጎብኝተዋል። • በሐረር ከተማ የተቋቋመውን መሶብ የአንድ ማዕከልም ተመልክተዋል። ማዕከሉ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል አቀናጅቶ የማቅረብ ሀገር ዐቀፍ መርሐ-ግብር አካል መሆኑንም አስገንዝበዋል። • በምሥራቅ ሐረርጌ ዞን መልካ በሎ ወረዳ የሚገኘውን ናሲኦል ዋሻም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍነው ሳምንት ጎብኝተዋል። • ከሐረር ከተማ ነዋሪዎች ጋርም የረመዳን ኢፍጣር አካሂደዋል። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ሹመት መስጠታቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ ሌ/ጄኔራል አሥራት ደኔሮን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር፣ ረዳት ኮሚሽነር ቶፊቅ መደድን እና አቶ ኤርዚቅ ኢሳን የአዲስ አበባ ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነሮች አድርገው የሾሙት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። ✍️ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ማድረጋቸው • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከልዑካቸው ጋር በጅቡቲ የቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼኽ መሐመድ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት እስማኤል ዑማር ጊሌ በተገኙበት ውይይት አድርገዋል። • ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሥራ ጉብኝታቸውን ቀጥለውም ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ያቀኑት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በዚሁ ወቅትም ከፕሬዚዳንት ግርማዊ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸውም በሀገራቱ መካከል ለረጅም ዘመናት የቆየውን ወዳጅነት በማጎልበት፤ ትብብር እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር። ✍️ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ጋር መምከራቸው • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ባዘጋጀው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይ ታድመዋል። በዚሁ ወቅትም የሁሉም እምነት፣ ባህልና ሥርዓት የሚከበርባት ኢትዮጵያን መገንባት የመደመር መንግሥት ተልዕኮ መሆኑን ገልጸዋል። • ከዓለም አቀፉ የቴሌኮሙኒኬሽን ኅብረት ዳይሬክተር ኮስማስ ዛቫዛቫ (ዶ/ር) ጋር በዲጂታል ልማት ያለ ትብብርን ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ውይይት ያደረጉት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር። በቀጣይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂን ከግብ ለማድረስ እና ትብብራችንን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር በጀመርናቸው እና በሌሎች አዳዲስ ዘርፎች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል ሲሉም ገልጸዋል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ። • በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ አዘጋጅነት በተከናወነው የኢፍጣር መርሐ-ግብር ላይም የታደሙ ሲሆን፤ በዚሁ ወቅት “ጎረቤቱ ርቦት እርሱ ጠግቦ የሚያድር ከኛ አይደለም” የሚለው የነቢዩ መሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አስተምኅሮ፣ ለሰው ልጅ ክብር መስጠትን፣ ርኅራኄን፣ የጋራ ደስታንና አብሮነትን በተግባር መተርጎም እንዳለብን የሚያሳይ ኅያው የሕይወት ስንቅ ነው ብለዋል። ✍️ የመሬት ናዳና ጎርፍ አደጋ በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ • ባሳለፍነው ሳምንት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን በተከሰተ የመሬት ናዳ እና ጎርፍ የዜጎች ሕይወት አልፏል፤ በንብረት ላይም ውድመት ደርሷል። ይህን ተከትሎም ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎችም ከፍተኛ አመራሮች የሐዘን መግለጫ መልዕክት አስተላልፈዋል። • ከዚሁ ጋር በተያያዘ በጋሞ ዞን በመሬት ናዳ አደጋ የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍና መልሶ ለማቋቋም ከፌደራል መንግሥት ጋር በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ጥላሁን ከበደ ያስታወቁት ባሳለፍነው ሳምንት ነው። እስካሁንም በአደጋው ሳቢያ ከቀያቸው ለተፈናቀሉ ወገኖች ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስና መልሶ ለማቋቋም ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ በተቀናጀ መንገድ እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል። መላው የኢትዮጵያ ሕዝብም ለወገኑ ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል። ✍ ምክር ቤቱ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ማወጁ • የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ላካ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት ምክንያት ሕይወታቸው ያለፉትን ዜጎች በማስመልከት ብሔራዊ የሐዘን ቀን ዐውጇል። በዚህም መሠረት ትናንት የጀመረው ብሔራዊ የሐዘን ቀኑ እስከ ነገ ድረስ የሚቆይ ይሆናል። #ባሳለፍነው_ሳምንት #ዐበይት_ጉዳዮች #ኢዜአ #Ethiopian_News_Agency
ኢትዮጵያ የገነነችበት ዲፕሎማሲና የስትራቴጂካዊ እይታ ስኬት!
Feb 25, 2026 393
(በሙሴ መለስ) ባለፉት ጥቂት ወራት በኢትዮጵያ የሚደረጉ የተለያዩ ሃገራት መሪዎች፣ ታላላቅ ዲፕሎማቶች ጉብኝቶች እና የግንኙነት መድረኮች ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ያላት ተሳትፎ እየጨመረ የዲፕሎማሲ ስኬቷም የተጽዕኖ ደረጃው እያደገ ስለመምጣቱ የሚያሳዩ ናቸው። የዓለም መሪዎች ከስትራቴጂካዊ አጋርነት እስከ ቀጣናዊ ትብብር የዘለቀ ግንኙነትን ዓላማ ያደረጉ ጉብኝቶችን በአፍሪካ መዲና ኢትዮጵያ አድርገዋል። ጉብኝቶቹ የኢትዮጵያን ጂኦ ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እና የዲፕሎማሲ አቅም የሚያሳዩም ናቸው። መሪዎቹ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር ያደረጓቸው የሁለትዮሽ ውይይቶች ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነትን ማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ማጎልበት እና በአፍሪካ ቀንድ የሰላም ጥረቶች እንዲሁም የጋራ የሆኑ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፍ ፈተናዎችን በትብብር መፍታት ላይ ያተኮሩ ናቸው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ የዲፕሎማሲ የልብ ምት ናት። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ዋና መቀመጫ መሆኗ የዓለም መሪዎች ትኩረት እንዲያርፍባት አድርጓል። ጉብኝቶቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ተፈላጊነት ብቻ ሳይሆን ሰፊ በሆኑ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች ላይ እያደገ ያለውን ተሰሚነቷን አጉልተው የሚያሳዩ ናቸው። ፈተናዎች በበዙበት የአፍሪካ ቀንድ ኢትዮጵያ በሰላም ግንባታ፣ ኢኮኖሚ ትብብር እና አህጉራዊ ትስስር ገንቢ ሚና እንደምትጫወት እና አስፈላጊነቷ ወሳኝ እንደሆነ ከመሪዎቹ ንግግር መረዳት ይቻላል። ባለፉት ጥቂት ወራት ሃገራችንን ከጎበኙ የውጭ ሃገራት መሪዎች መካከል ባለፈው ሣምንት የመጡት የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይፕ ኤርዶዋን አንዱ ናቸው። ኤርዶዋን በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።ቱርኪዬ ከኢትዮጵያ ጋር ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ትልቅ ዋጋ እንደምትሰጥ እና አጋርነቷን ማጠናከር እንደምትሻ ተናግረዋል። ኤርዶዋን ኢትዮጵያ በቀጣናው ስላላት ሚና በማንሳት ዓለም ፊቱን ወደ አፍሪካ ቀንድ ባዞረበት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ ጸንቶ የቆየ የሀገረ መንግስት መዋቅር እና ተምሳሌታዊ አስተዳደር የበለጠ አስፈላጊ እየሆነ መምጣቱንም ተናግረዋል። ጉብኝቱ መልካም ውጤቶችን ይዞ እንደሚመጣና ለቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት ሙሉ እምነት አለኝ ማለታቸውም አይዘነጋም። በዓለም ከፍተኛውን የህዝብ ቁጥር የያዘችው ህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ሞዲ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ የመከሩ ሲሆን በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና በፌዴሬሽን ምክር ቤት የጋራ ስብስባ ላይ በመገኘት በጥልቅ ስሜት ባደረጉት ታሪካዊ ንግግርም ህንድ እና ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ወዳጅነት እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር እንዳላቸው አንስተዋል። የህንድ ኩባንያዎች ለኢትዮጵያ በውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ እንዳላቸው ጠቅሰው ከአምስት ቢሊዮን ዶላር በላይ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በግብርና፣ ጨርቃ ጨርቅና ማኑፋክቸሪንግን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች መሰማራታቸውን አመልክተዋል። ህንድ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ግንኙነት ወደ ስትራቴካዊ አጋርነት ምዕራፍ ለማሸጋገር መወሰኗን ገልጸው ይህም ኢኮኖሚ፣ ንግድ ፣ ኢንቨስመንት፣ ቴክኖሎጂ፣ ማዕድን፣ አረንጓዴ ኢነርጂ እና ኢኖቬሽንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ህንድን ታማኝ አጋር በማድረጓ ምስጋናቸውን ያቀረቡት ናሬንድራ ሞዲ ሀገራቸው የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ለማጠናከር አበክራ እንደምትሰራ መናገራቸው ሌላው የኢትዮጵያን የዲፕሎማሲ ተጽዕኖ የሚያመለክት ሲሆን ሞዲ ኢትዮጵያ ጥንታዊ ስልጣኔ እና ዘመናዊ ህልሞችን አጣምራ መያዟ በአይበገሬነት እና በጽናት መንፈስ እንድትቀጥል አድርጓታል ሲሉም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ስልጣኔዎች ካላቸው ሀገራት መካከል አንዷ ናት መሆኗን ያነሱት የጥንካሬ፣ የአይበገሬነት፣ የኩራት እና የለውጥ ምልክት ናት ሲሉ መግለጻቸውም አይዘነጋም። በዚሁ ዓመት ታህሳስ ወር ላይ አዲስ አበባን የጎበኙት የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጋር ባደረጉት ውይይት የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ያደነቁ ሲሆን ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር በልማቱ ዘርፍ ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እንደምትሰራም አረጋግጠዋል። ቻይና ለቀጣናዊ ሰላም፣ መረጋጋት እና ብልጽግና ከኢትዮጵያ ጋር በቅርበት እንደምትስራ በመግለጽም ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን በሁኔታዎች የማይለዋወጥ ስትራቴጂክ አጋርነት(all-weather strategic partnership) ይበልጥ ለማጎልበት በቁርጠኝነት ትሰራለች ብለዋል። የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክርስቶፈር ላንዳውና በአፍሪካ የአሜሪካ ጦር ዕዝ (አፍሪኮም) ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ጉብኝታቸው ያረጋገጡት ነገር ቢኖር የኢትዮጵያን ቀጣናዊና ዲፕሎማሲያዊ ተጽዕኖ ፈጣሪነት ነበር። በወቅቱ ክርስቶፈር ላንዳው እና ልዑካቸው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተወያዩ ሲሆን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ኤክስፖም ጎብኝቷል። ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱ አሜሪካ እና ኢትዮጵያ ለረጅም ጊዜ የቆየውን አጋርነታቸውን የበለጠ የሚያጠናክር መሆኑን በመግለጽ አሜሪካ ለአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋት ከኢትዮጵያ ጋር መስራት እንደምትፈልግም አመልክተዋል። የደቡብ ምስራቅ እስያዊቷ ሀገር ሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስትር ላውረንስ ዎንግ አዲስ አበባን የጎበኙት በህዳር ወር 2018 ዓ.ም ነበር። በወቅቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የሁለትዮሽ ውይይቶችን ያደረጉ ሲሆን በአፍሪካ የመጀመሪያቸውን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በኢትዮጵያ አዲስ አበባ በማድረጋቸው ደስታ እንደተሰማቸውም ተናግረዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሲንጋፖር በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት መወሰኗን በደስታ እንደተቀበሉት በወቅቱ ዎንግ ገልጸውም ነበር። የኤምባሲው መከፈት ሲንጋፖር ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ብቻ ሳይሆን ከአፍሪካ ህብረት እና ከመላው አፍሪካ ጋር ቁልፍ ትስስር መፍጠሪያ ሆኖ እንደሚያገለግልም አመልክተዋል። ሲንጋፖርና ኢትዮጵያ የየቀጣናቸው መግቢያ በር ናቸው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀገራቱ ያላቸውን አጋርነት የበለጠ በማጠናከር ዜጎችን በዘላቂነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ድልድይ በደቡብ ምስራቅ እስያ እና አፍሪካ መካከል እየገነቡ ነው ብለዋል። ከእስያ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ስንመለስም የኬንያውን ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በታህሳስ ወር 2018 ዓ.ም ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላትን የመሪነት ሚና በማድነቅ ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላም እና መረጋጋት ላይ ገንቢ ሚና እየተጫወተች እንደምትገኝ አንስተዋል።ኬንያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የሁለትዮሽ ትብብር የበለጠ ለማጎልበት እንደምትሻም ገልጸዋል። በአውሮፓ የጠንካራ ኢኮኖሚ ባለቤት የሆነችው የጀርመን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆአን ዋድፑልም በጥር ወር ባደረጉት የኢትዮጵያ ጉብኝት ከመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከር ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ሁሉን አቀፍ ትብብር ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት ያደነቁት ሚኒስትሩ፤ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታ ጠንካራ ኢኮኖሚ ለመገንባት ወሳኝ መሆኑን በማንሳት የጀርመን ኩባንያዎች በግንባታው ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው አመልክተዋል። የዩናይትድ ኪንግደም የውጭ፣ ኮመንዌልዝ እና የልማት ጉዳዮች ሚኒስትር ይቬት ኩፐር፣ የኖርዌይ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንድሪያስ ክራቪክ የጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒትር ዴኤታ ኩኒሚትሱ አያኖ እና የሌሎች ሃገራት መሪዎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሃላፊዎች በተደጋጋሚ ኢትዮጵያን ጎብኝተዋል። በኢትዮጵያ በቅርብ ጊዜ የተደረጉ የከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶች ጉብኝት ብቻ ሆነው ያለፉም ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ በዓለም የዲፕሎማሲ መድረክ ያላትን ተሰሚነትም የሚያሳዩ ናቸው። ህንድ እና ቱርኪዬን ጨምሮ የተለያዩ ሀገራት ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ወደ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ምዕራፍ አሸጋግረዋል። የዓለም ሀገራት መሪዎቹ ኢትዮጵያ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ፈተናዎችን በመፍታት ረገድ ያላትን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በደቡብ ደቡብ ትብብር ያላት ስትራቴጂካዊ ሚናም የተነሳ ሲሆን ይህም ኢትዮጵያ የትብብር፣ የሰላም፣ የጋራ አጋርነት እና ዘላቂ ልማት ማዕከል መሆኗን የሚያሳይ ነው። ጉብኝቶቹ እንግዳን ተቀብሎ መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ውይይቶችን ከማድረግ ባለፈ ኢትዮጵያ በቀጣናውና በዓለም የዲፕሎማሲ ውስጥ ያላትን ቦታ አጉልተው ያመላከቱ የስኬት መገለጫዎችም ናቸው።
ዘመናትን የተሻገረው የኢትዮ-እስራኤል ታሪካዊ ትስስር
Feb 24, 2026 500
(በአየለ ያረጋል) ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ያላቸው ሀገራት ናቸው፤ ኢትዮጵያና እስራኤል። የሁለቱ ሃገራት ዘመናትን የተሻገረው ግንኙነት አሁን ላይ በተለያዩ መስኮች የተጠናከረ ሆኖ ይገኛል። የሀገራቱ ግንኙነት ግን እንደየስርዓተ መንግስታቱ የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ባህሪ መልኩን እየለዋወጠ እና ውጣ ውረዶችን እያለፈ የተሻገረና ጠንካራ መሆኑም ይታወቃል። የእስራኤል ፕሬዝዳንት ኢሳክ ሄርዞግ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ እንደሚገቡ የሃገሪቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ጠቅሰው የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ፕሬዝዳንቱ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን(ዶ/ር) ጨምሮ ከተለያዩ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር እንደሚወያዩም ይጠበቃል። የኢትዮጵያ እና የእስራኤል ግንኙነት ታሪካዊ ገጽታ፦ ሃገራቱ የግንኙነታቸው ትርክት ቅድመ ልደተ ክርስቶስ በንግሥተ ሳባ እና በንጉሥ ሰለሞን ዘመነ መንግስት እንደሆነ አፈ ታሪክ ያስረዳል። ይህ አፈ-ታሪካዊ እርሾ ከኢትዮጵያ ሰለሞናዊ ስርወ መንግስት ጋርም ቀጥሏል። በመካከለኛው እና በዘመነ መሳፍንት ዘመን ሃይማኖትና ንግድ ሁለቱን ሀገራት ይበልጥ አስተሳስሯል። በተለይም ዴር ሱልጣንን ጨምሮ በኢየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማት መኖር የሁለቱን ሀገራት ባህላዊ ተጋምዶሽ አጎልብቷል። ይህ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር ከእስራኤል ሀገረ መንግስት ዳግም መመስረት በኋላም በዘመናዊት ኢትዮጰያ ታሪክም ቀጥሏል። የኢትዮ እስራኤል ፖለቲካዊ ዲፕሎማሲ፦ የዘመናዊ የኢትዮ-እስራኤል ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት የተወጠነው በአውሮፓውያኑ ዘመን ቀመር በ1956 ሲሆን በ1961 ይፋዊ የተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ተጀምሯል። በቀዳማዊ አጼ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግስት የተጀመረው የሁለቱ ሀገራት ይፋዊ የዲፕሎማሲ ወዳጅነት ስትራቴጂካዊ ጥቅምን ያማከለና የወቅቱን የቀጣናውን ነባራዊ ሁኔታ የዋጀ ግንኙነት እንዲመሰርቱ አድርጓል። በንጉሳዊ ስርዓተ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በወታደራዊ እና ሌሎች የልማት ቴክኒካል ድጋፍ የደረሰ ወዳጅነት ነበራቸው። በደርግ ዘመነ መንግስት ሁለቱ ሀገራት በእስራኤለና አረቦች ጦርነት ሳቢያ መቀዛቀዝ ተስተውሎበታል። ያም ሆኖ በግልጽም ሆነ የህቡዕ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንደነበራቸው ይወሳል። መጀመሪያ ላይ ተቋርጦ የነበረው ግንኙነት በደርግ መንግስት መጨረሻ ዓመታት (በአውሮፓውያኑ 1989) የኢትዮ-እስራኤል ይፋዊ ግንኙነት ዳግም ተጀምሯል። የ"ኦፕሬሽን ሙሴ" (1984) እና "ኦፕሬሽን ሰለሞን" (1991) የተሰኙ ቤተ እስራኤላውያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የማጓጓዝ ተልዕኮዎችም በሁለቱ ሀገራት መንግስታት ስምምነት የተካሄዱ መሆናቸውን ልብ ይሏል። በኢህአዴግ ዘመነ መንግስት (ከ1983 ዓ.ም) ጀምሮ ደግሞ የሀገራቱ ግንኙነት ወደ ተሟላ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ቀጥሏል። በፈረንጆቹ 1992 ኢትዮጵያ በእስራኤል ኤምባሲዋን ከፍታለች። በፈረንጆቹ 2003 ኢትዮጵያና እስራኤል የኢንቨስትመቶች ማስፋፊያና ጥበቃ ስምምነት ተፈራርመዋል። በ1996 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 2004) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በእስራኤል ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር አሪኤል ሻሮን ጋር ያደረጉት ታሪካዊ ውይይት የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አሳድጎታል። ጉብኝቱን ተከትሎ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲን ያጠናከሩ የተለያዩ ስምምነቶች ተደርገዋል። በተለይም በቴክኖሎጂና ግብርና ዘርፍ የሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ የልማት ትብብር ከፍ ብሏል። በአፍሪካ ቀንድ ደህንነትና ፀረ ሽብር ጉዳዮች እንዲሁም በወታደራዊ ስልጠና፣ የደህንነት መረጃ ልውውጥና የድንበር ጥበቃ ቴክኖሎጂ በትብብር ለመስራት መሰረት ጥለዋል። በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2016 ደግሞ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ በአዲስ አበባ ይፋዊ የስራ ጉብኝት አድርገዋል። ከወቅቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ጋርም መክረዋል። በተመሳሳይ በፈረንጆቹ በ2017 የወቅቱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ እስራኤልን ጎብኝተዋል። ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ ጊዜያት በየራሳቸው ብሔራዊ ጥቅሞች ዙሪያ በትብብር ቆመዋል። በዓለም አቀፍ መድረኮች አንዳቸው ለሌላው ድምጽ በመስጠት ተደጋግፈዋል። የባሕር በር ባለቤትነትን ጨምሮ ኢትዮጵያ ለብሔረታዊ ጥቅሞቿ መጠበቅ ለምታደርገው ጥረት እስራኤል አሉታዊ ምላሽ አልሰጠችም። ይልቁንም እስራኤል ኢትዮጵያን ወደ አፍሪካ እንደ መግቢያ ሁነኛ በር አድርጋ ትቆጥራለች። ከሀገራዊ ለውጡ ወዲህ የኢትዮ-አስራኤል ግንኙነት ወደ ላቀ ስትራቴካዊ አጋርነት አድጓል። በ2011 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በእስራኤል ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ደግሞ የሀገራቱ የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በአዲስ ምዕራፍ እንዲታደስ አስችሏል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ታሪካዊ የተሰኘውን ምክክር አድረገዋል። መሪዎቹ በሰጡት ገለጻም በአምስት ነጥቦች ላይ የሁለትዮሽ ትብብራቸውን ማጠናከር የሚያስችሉ ስምምነቶችን በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በውሃ፣ በመስኖ፣ በጤና እና በሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ መፈራረማቸውን አውስተው ነበር። በግብርና፣ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም በጸጥታ ዘርፎች ላይ አብሮ ለመስራት ተስማምተው እንደነበርም እንዲሁ። ባህላዊና ኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ፦ ሁለቱ ሀገራት ታሪካዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስራቸውን ወደ ልማት በመለወጥ የንግድና ኢንቨስመንት ግንኙነታቸውን ወደላቀ ደረጃ ለማድረስ ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አከናውነዋል። የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ያላቸው የኢንቨስትመንት ተሳትፎ እየጎለበተ መጥቷል። ለአብነትም የእስራኤል ኩባንያዎች በኢትዮጵያ ውስጥ በዘመናዊ ግብርና እና በሌሎች ዘርፎች ተሰማርተዋል። በማዕድን ዘርፍ (በፖታሽ)፣ በማምረቻ ዘርፍ( በጨርቃጨርቅ እና በኬሚካል ኢንዱስትሪዎች) እንዲሁም በጤናና ፋርማሲዩቲካል ዘርፍ ውጤታማ ስራዎችን እያከናወኑ ነው። በተለይም በግሪን ሃውስ፣ በግብርና ምርት ማቀነባበሪያ፣ በማምረቻ እና በፋርማሲዩቲካል (የመድኃኒት) ዘርፎች ሁነኛ ተሳትፎ አድርገዋል። በተመሳሳይ በንግድ ልውውጥ ረገድ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰሊጥና ሌሎች የቅባትና የጥራጥሬ ምርቶችን ወደ እስራኤል በስፋት ትልካለች። በአንጻሩ እስራኤል የላቁ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን፣ የግብርና ግብዓቶችን (ማዳበሪያና ኬሚካሎች)፣ የሕክምና መሣሪያዎችን እና የደህንነት ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ታቀርባለች። በዓለም አቀፍ ደረጃ በደረቅ አካባቢ ግብርና ስመጥር የሆነችው እስራኤል በዘርፉ የኢትዮጵያ ቀዳሚ የልማት አጋር ስትሆን በዘመናዊ መስኖ፣ የአቮካዶና የፍራፍሬ ልማት እንዲሁም በእንስሳት እርባታ እና የወተት ምርታማነት አጋዥ ቴክኖሎጂዎች በጎ ተሳትፎ ታደርጋለች። በሁለቱ ሀገራት ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ወዳጅነት መጠናከር ቤተ-እስራኤላውያን እንደ ድልድይ አገልግለዋል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ160 ሺህ በላይ መሰረታቸው ከኢትዮጵያ የሆኑ እስራኤላዊያን ዜጎች አሉ። እነዚህ ዜጎች ለኢኮኖሚያዊ ዲፕሎማሲ ሁነኛ ድልድይ ሆነዋል። በተለይም በእስራኤል የሰለጠኑ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በማስቻል በዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር እና በንግድ ስራ ረገድ ውጤታማ ግንኙነት እንዲፈጠር መልካም አጋጣሚ ፈጥጠሯል። ይህም የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲያቸውን ከፍ አድርጎታል። የፕሬዝዳንት ሔርዞግ ለይፋዊ ጉብኝት ወደ አዲስ አበባ መምጣት የሁለቱን ሃገራት የጸና ትብብርና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የበለጠ የሚያጎለብት እንደሚሆን ይጠበቃል። በአህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይም በጋራ የሚያከናውኑትን ስራ የሚያጠናክሩበት ምቹ ሁኔታም ይፈጥራል።
ኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ዋንጫ
Jan 2, 2026 1210
ክፍል ሁለት የቀጠለ የኢትዮጵያ ዘጠነኛ ተሳትፎ በአህጉራዊው መድረክ እ.አ.አ 1982 ኢትዮጵያ በሊቢያ አስተናጋጅነት በተካሄደው 13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ለዘጠነኛ ጊዜ ተሳትፎዋን ማድረግ ቻለች። በውድድሩ ላይ አሁንም ስምንት አገራት ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በምድብ ሁለት ከአልጄሪያ፣ዛምቢያና ናይጄሪያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን አድርጋለች። በምድብ ጨዋታዎቹ በናይጄሪያ 3 ለ 0 እንዲሁም በዛምቢያ 1 ለ 0 የተሸነፈች ሲሆን ከአልጄሪያ ጋር ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይታለች። ኢትዮጵያ በምድቧ አንድ ነጥብ ብቻ በመያዝ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች። በፍጻሜው ጨዋታ ጋና ሊቢያን በመለያ ምት በማሸነፍ ለሶስተኛ ጊዜ የአፍሪካ ዋንጫን አንስታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካው ዋንጫ የተመለሰችበት ታሪካዊ ሁነት ኢትዮጵያ ከ13ኛው የአፍሪካ ዋንጫ በኋላ በአህጉራዊው የእግር ኳስ ውድድር መድረክ ለመሳተፍ ሶስት አስርት ዓመታታን መጠበቅ ግድ ሆኖባታል። በነዚህ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ 15 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮች ተካሄደዋል። እ.አ.አ በ2013 በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ ውድድሩ ዳግም ተመለሰች። ኢትዮጵያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ያለፈችበት መንገድ ልብ አንጠልጣይ ነበር። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2012 በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከሱዳን ጋር ባደረገችው የመጨረሻ ዙር የደርሶ መልስ ጨዋታ በመጀመሪያ ዙር ኦምዱርማን ላይ 5 ለ 3 በሆነ ውጤት ተሸንፋለች። ሱዳን ጨዋታውን ያሸነፈችው በመጨረሻዎቹ ደቂቃዎች በተቆጠሩ ሁለት አጨቃጫቂ የፍጹም ቅጣት ምት በግቦች ነበር። ጥቅምት 4 2004 ዓ.ም በአዲስ አበባ ስታዲየም ለሚደረገው የመልስ ጨዋታ በስታዲየሙ ዙሪያ ከእኩለ ሌሊት ጀምሮ በርካታ ተመልካች ተሰልፎ ነበር። ጨዋታው በመጀመሪያው አጋማሽ ያለ ምንም መጠናቀቁ በስታዲየሙ የተገኘውን ተመልካች ጭንቅ ውስጥ ከቶ ነበር። ጭንቀቱ በስታዲየሙ ላሉት ብቻ ሳይሆን በቴሌቪዥን መስኮት ለሚከታተሉት በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያንም ነበር። በሁለተኛው አጋማሽ የተሻለ እንቅስቃሴ ያደረጉት ዋልያዎቹ አዳነ ግርማ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ቻሉ። ይሁንና ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው ለመሳተፍ አንድ ተጨማሪ ጎል ያስፈልጋታል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ አጥቂ ሳላዲን ሰዒድ ወሳኟን ሁለተኛ ግብ ከመረብ ላይ አሳረፈ። ግቡ ሲቆጠር በስታዲየሙ ተመልካቾች ላይ የነበረው ስሜት በከፍተኛ ደስታ የተሟላ ሲሆን ስሜታቸውንብ በእንባ የገለጹም ነበሩ። ጨዋታው በድምር ውጤት 5 ለ 5 ተጠናቆ ከሜዳ ውጪ ብዙ ባስቆጠረ በሚል ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ዳግም ወደ አፍሪካ ዋንጫ መመለስ ቻለች። ከጨዋታው በኋላ በአዲስ አበባ ስታዲየም፣በመስቀል አደባባይና በመዲናዋ የተለያዩ አውራ ጎዳናዎች፣መንደሮችና የተለያዩ አካባቢዎች እንዲሁም በመላው ኢትዮጵያ ባሉ ክፍሎች የነበረው የደስታ ስሜትና ፈንጠዝያ የሚረሳ አልነበረም። በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንም የደስታው ተቋዳሽ ነበሩ። ኢትዮጵያን ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫው እንድትመለስ ያደረጉት አሰልጣኝ ሰውነት ቢሻው ነበሩ። ደቡብ አፍሪካ ባዘጋጀችው 29ኛው የአፍሪካ ዋንጫ 16 አገራት በስድስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን አድርገዋል። ኢትዮጵያም በምድብ ሶስት ከቡርኪናፋሶ፣ናይጄሪያና ዛምቢያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። በመጀመሪያ ጨዋታዋ ኢትዮጵያ ከዛምቢያ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። አዳነ ግርማ በ65ኛው ደቂቃ ለኢትዮጵያ ግቡን አስቆጥሯል። በሁለተኛው ጨዋታ ኢትዮጵያ በቡርኪናፋሶ የ4 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዳለች። በምድቡ የመጨረሻ ጨዋታ ኢትዮጵያ በናይጄሪያ 2 ለ 0 ተሸንፋለች። ውጤቶቹን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአንድ ነጥብ የመጨረሻውን አራተኛ ደረጃ ይዛ ከምድቧ ሳታልፍ ቀርታለች። ኢትዮጵያ ከ31 ዓመት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ ብትመለስም በውድድሩ ላይ ያስመዘገበችው ውጤትና ያሳየችው ብቃት የእግር ኳስ ቤተሰቡን ያስደሰተ አልነበረም። ይሁንና ብሔራዊ ቡድኑ ከደቡብ አፍሪካ ሲመለስ በአዲስ አበባ ስታዲየም በበርካታ ደጋፊዎች አቀባበል ተደርጎለታል። በፍጻሜው ጨዋታ ናይጄሪያ ቡርኪናፋሶ 1 ለ 0 በማሸነፍ የአፍሪካን ዋንጫን ለሶስተኛ ጊዜ አንስታለች። ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ የተሳተፈችበት የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ ለመጨረሻ ጊዜ በአፍሪካ ዋንጫ የተሳተፈችው እ.አ.አ በ2021 ካሜሮን ባዘጋጀችው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ነበር። ከስምንት ዓመታት በኋላ ወደ ውድድሩ የተመለሰችው ኢትዮጵያ በምድብ አንድ ከአዘጋጅ አገር ካሜሮን፣ቡርኪናፋሶና ኬፕቨርዴ ጋር ተደልድላ ጨዋታዋን አድርጋለች። ኢትዮጵያ በመጀመሪያ የምድብ ጨዋታዋ በኬፕቨርዴ 1 ለ 0 ተሸንፋለች። በሁለተኛው ጨዋታ ዋልያዎቹ በአዘጋጇ አገር ካሜሮን 4 ለ 1 ተሸንፈዋል። በጨዋታው ኢትዮጵያ አጥቂው ዳዋ ሁቴሳ በአራተኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ መሪ መሆን ብትችልም ቪንሰንት አቡበከርና ቶኮ ኢካምቢ በተመሳሳይ ሁለት ግቦችን በማስቆጠር የማይበገሩትን አንበሶች አሸናፊ አድርገዋል። በወቅቱ በአሰልጣኝ ውበቱ የተመራው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በመጨረሻ የምድብ ጨዋታዋ ከቡርኪናፋሶ ጋር አንድ አቻ ተለያይታለች። ለብሔራዊ ቡድኑ ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጌታነህ ከበደ በፍፁም ቅጣት ምት ነበር። ኢትዮጵያ በምድቡ አንድ ነጥብ ብቻ በማግኘት ከምድቧ የመጨረሻውን ደረጃን ይዛ አጠናቃለች። የኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ በቁጥሮች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የ11 ጊዜ ተሳትፎ ኢትዮጵያ 31 ጨዋታዎችን አድርጋ 8ቱን ስታሸንፍ 19 ጊዜ ተሸንፋለች። አራት ጊዜ ደግሞ አቻ ወጥታለች። በነዚህ 31 ጨዋታዎች ኢትዮጵያ 33 ግቦችን ስታስቆጥር 67 ጎሎችን አስተናግዳለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ በሰፊ ግብ ያሸንችባቸው ጨዋታዎች ሁለት ናቸው። እ.አ.አ በ1962 ራሷ አዘጋጅታ ራሷ በወሰደችው ሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ቱኒዚያና ግብጽን በተመሳሳይ 4 ለ 2 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫው በሰፊ የግብ ልዩነት የተሸነፈችው እ.አ.አ በ1970 ሱዳን ባዘጋጀችው ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ሲሆን በወቅቱ በኮትዲቭዋር 6 ለ 1 በሆነ ውጤት ተረታለች። ሰባተኛው የአፍሪካ ዋንጫ ኢትዮጵያ በውድድሩ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግብ ያስተናገደችበት ሲሆን 12 ጎሎች ተቆጥረውባታል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎዋ ከፍተኛ ግቦችን ያስቆጠረችባቸው ውድድሮች እ.አ.አ በ1952 እና በ1968 በቅደም ተከተል ሶስተኛውንና ስድስተኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ባዘጋጅበት ወቅት ነው። በነዚህ ውድድሮች ላይ በተመሳሳይ ስምንት ግቦችን አስቆጥራለች። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ዋንጫን ሶስት ጊዜ አዘጋጅታለች። ኢትዮጵያውያኖቹ አጥቂዎች ሉቺያኖ ቫሳሎና መንግስቱ ወርቁ በአፍሪካ ዋንጫ ላይ በተመሳሳይ 8 ግቦችን በማስቆጠር በአፍሪካ ዋንጫ የምንጊዜም የከፍተኛ ግብ አግቢዎች ዝርዝር ውስጥ 21ኛ እና 22ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል። እንደ መውጫ ኢትዮጵያ ሞሮኮ እየተካሄደ በሚገኘው 35ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አትሳተፍም። የአፍሪካ እግር ኳስ መስራችና ፈር ቀዳጅ እየተባለች የምትጠራው ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ ተሳትፎዎቿ ከሰሜን፣ደቡብና ምዕራብ አፍሪካ አገራት ጋር ብርቱ ፉክክር በማድረግ መልካም የሚባል ውጤት አስመዝግባለች። ይሁንና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአፍሪካ ዋንጫ ያላት ተሳትፎ እየተቀዛቀዘ መጥቶ ብሔራዊ ቡድኑ ከምድቡ ማለፍ እየተሳነው ነው። የስፖርት ቤተሰቡና ተንታኞች ጠንካራ ብሔራዊ ቡድን መገንባት አለመቻሉ፣የእግር ኳስ እድገቱ ወደ ኋላ መቅረቱ፣ የአጥቂ መስመሩ ክፍል የአጨራረስ ድክመት፣ ለወጣት ተጫዋቾች እድል አለመስጠት፣የአሰልጣኞች በየጊዜው መለዋወጥ፣ለእገር ኳሱ የሚሰጠው ትኩረት የሚጠበቀውን ያህል አለመሆኑና እግር ኳሱ በስፖርቱ ባለፉ ሰዎች አለመመራቱን ጨምሮ በርካታ ምክንያቶች ይቀመጣሉ። ጠንካራና ተወዳዳሪ ቡድን የመገንባት ስራ ትኩረት ያሻዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2029 የሚካሄደውን 37ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ለማስተናገድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥያቄ ማቅረቧ የሚታወቅ ነው። በዚህም ውድድር ኢትዮጵያን ወክሎ የሚሳተፍ ጠንካራና አሸናፊ ብሔራዊ ቡድን መገንባት የሚያስችል "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት ተጀምሯል፡፡ “ሮድ 2029"ን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ከሁሉም አካባቢዎች 85 ብቃት ያላቸው ታዳጊዎች ተመርጠው ለዘጠኝ ወራት ስልጠና ወስደው ብቃት ያላቸው ተመርጠዋል፡፡ ከእነዚህ ታዳጊዎች መካከል 26ቱ በብቃታቸው ተመርጠው የ"ሮድ 2029" ግብን ማሳካት የሚያስችል የክፍል ውስጥ እና የሜዳ ላይ ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። ታዳጊዎቹ ኢትዮጵያ በህዳር ወር ባስተናገደችው ከ17 ዓመት በታች የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማህበር ምክር ቤት ዞን (ሴካፋ) ተሳትፎ አድርጓል። የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሄራዊ ቡድን በውድድሩ ላይ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ በሞሮኮ በሚካሄደው 16ኛው ከ17 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማለፉ ይታወቃል። "ሮድ 2029" የታዳጊዎች እግር ኳስ የስልጠና ፕሮጀክት በአሜሪካዊ እና ኢትዮጵያዊ አሰልጣኞች ጥምረት የሚካሄድ ሲሆን በኢትዮጵያ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ ሥልጠና እየተሰጠ ይገኛል። በዲጂታል አማራጮች ተደግፎ በንድፈ ሀሳብና በተግባር የሚሰጥ ሥልጠና መሆኑን በማንሳት፤ በእስካሁኑ ሂደት ተስፋ ሰጭ ውጤት ታይቶበታል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2029 የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እንድትመረጥ የቴክኒክ ጉዳዮችን ጨምሮ የተለያዩ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑንን ፌዴሬሽኑ አመልክቷል። ታዳጊዎችን እግር ኳስ ልማት፣ የስፖርት መሰረተ ልማቶች ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን እንዲያሞሉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎች እና የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች መስፋት ተስፋ ሰጪ ጅማሮዎች ነው። መንግስት የጀመራቸው ስራዎች በተጠናከረ መልኩ መቀጠል ይኖርባቸዋል። አጠቃላይ የእግር ኳሱ እደግት የስፖርት ባለድርሻ አካላትን የጋራ ትብብር ይጠይቃል። ተስፋ ሰጪ እና ብርሃን ፈንጣቂ ጅማሮዎችን ነገ ኢትዮጵያ በአፍሪካ እና በዓለም መድረክ በእግር ኳሱ ስኬታማ ለመሆን መሰረት የሚጥሉ ናቸው።
ልዩ ዘገባዎች
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 3696
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 2478
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 1/2018(ኢዜአ)፡- በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 8270
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 6756
ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
መጣጥፍ
ከዛፍ የሚታለብ ወተት
Feb 27, 2026 565
በቀደሰ ተክሌ -(ከሚዛን አማን ቅርንጫፍ) ጥበብ ከተፈጥሮ ጋር ስትገናኝ ሌላ እውነት ሌላ አዲስ ነገር ትፈጥራለች። የሰው ልጅ የመመራመርና የማወቅ ተፈጥሯዊ ባህርይው በተፈጥሮ ላይ ሁሉን የማድረግ ሥልጣንን ያስቸረ ነው። ሰው ያልነበረን አዲስ ነገር መፍጠር ባይችልም፤ ከነበረው ሌላ ውጤት ማግኘት ወይም መፍጠር ይችላል። "ጉማታ" በረከትን የመጋራት እሴት!! በዓለማችን ሰውን እና እቃን ከቦታ ወደ ቦታ የማንቀሳቀስ ትልቅ አገልግሎት ያለው ተሽከርካሪ ሕይወት ያለው መስሎ እንዲታይ የሚያደርገው የተገጠመለት ጎማ ነው። ታዲያ ይህ ጎማ ከዛፍ በተገኘ የወተት ጠብታ የሚሰራ መሆኑ አግራሞትን ከሚፈጥሩ የጥበብ ሥራ ውጤቶች መካከል እንዲሆን ያደርገዋል። የጎማ መስሪያ የሆነው ጥሬ ምርት ከዛፍ እንዴት እንደሚዘጋጅ ከስፍራው ኢዜአ የተመለከተውን ሊያስቃኛችሁ እነሆ ይላል፡- በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የጎማ ዛፍ ልማት በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ይገኛል። በምስራቅ አፍሪካ ብቸኛ የተባለው ይህ የጎማ ዛፍ ልማት በ3 ሺህ 884 ሔክታር መሬት ላይ ያረፈ ነው። አረንጓዴ ካባ የደረበውን የበበቃ ቀዬ እንደተሻገሩ ቀጥ ቀጥ ብለው የቆሙ ዛፎች ቅርንጫፋቸውን ከመሬት ከፍ አድርገው ግንዱን ለሌላ ተግባር እየተዉ አድገው በአዲስ ብርሃን ቀበሌ ደምቀው ይታያሉ። እነዚህ ዛፎች ከወገብ በታች ባለው ክፍል ብዙ ሺህ ጅራፍ እንዳረፈበት ገላ ሰምበር በሰንበር ሆነዋል። ይህም ሌሊት ሌሊት በሚፈጸም ከዛፉ ወተት ለማምረት በተደረገ ጥረት ሳቢያ የተፈጠረ ነው። ጎማን ለመሥራት የሚያስችለውና ከዛፉ የሚገኘውን ወተት ማምረትም የሰለጠኑ ባለሙያዎች ሌሊት ከ9 ሰዓት ጀምሮ የሚከውኑት ተግባር ነው። ይህን ሥራ ለማቀላጠፍም ከ500 በላይ የሚሆኑ ሰራተኞች ላይና ታች ይላሉ። ሠራተኞቹም ራሳቸውን ከማስተዳደር ባለፈ በወዝ በላባቸው ለሀገር አዎንታዊ ተጠቃሚነት የሚውለውን ምርት ያቀርባሉ። የጎማ ዛፍ በተፈጥሮ ብዙ ወተት የሚይዘው ሌሊት ነው። ቀን የሰበሰበውን ወተት ሌሊት ያለ ስስት ይለግሳል። በዚህን ሰዓት ዛፉን አድምተው ወተት ሊያልቡ የተዘጋጁ ሠራተኞች በሰለጠኑት ሙያ መሠረት የፀሐይ መውጫና መግቢያ አቅጣጫን ቀድመው ይለያሉ። የፀሐዩን አቅጣጫ ከለዩ በኋላ በዛፉ ሰሜንና ደቡብ አቅጣጫ ጎን ላይ በስለታማ ቁስ በአንድ መስመር ቀጥ አድርገው በመፈቅፈቅ ለዛፉ ወተት መውረጃ ቦይ ያበጃሉ። በመቀጠል ሁለቱን መስመሮች ከፊት ለፊት የሚያገናኝ ሌላ መስመር በማበጀት የዛፉ ወተት መሰል ፈሳሽ ከስር ወደተቀመጠው ፈሳሽ መቀበያ ባልዲ ያለ ስስት ይፈሳል። የጎማ ዛፍ ወተት ጠብታ ከእያንዳንዱ ዛፍ ስር ተሰብስቦ በብዙ ሊትር ተመዝኖ በበርሜል ይከማቻል። በአግባቡ የማጣራትና አሲድ ጨምሮ የማርጋት ሥራ ወደ ሚሰራበት ክፍል ይገባል። ወተቱ ከረጋ በኋላም ይታጠባል። ተድጦ የሚፈለገውን ያህል ቅርጽ ከያዘ በኋላ ጋቢ መስሎ ፀሐይ ላይ ይሰጣል። በፀሐይ ኃይል ጠፈፍ እንዲል የተሰጣው ምርት የተያዘለት ሰዓት ሲጠናቀቅ በባህላዊ መንገድ ወደ ተዘጋጀው ጭስ ቤት ይላካል። በዚህ ክፍል ውስጥ ለዚሁ ተግባር የሚያገለግሉ በተለያየ ደረጃ የተዘጋጁ እሳት ማንደጃ ጉድጓዶች ይገኛሉ። ከፀሐይ ላይ ተሰጥቶ ወደ ውስጥ እንዲገባ የተደረገው ምርት በዚህ ክፍል ከ5 እስከ 6 ቀናት የተለያዩ የድርቀት ደረጃዎችን እየተሸጋገረ ይቆያል። በጥሩ ሁኔታ ቀይ ሆኖ ከደረቀ በኋላ ለጎማ ኢንዱስትሪ ጥሬ ዕቃ ሆኖ ለሽያጭ ዝግጁ ይሆናል። ሁለት አስርተ ዓመታትን ያስቆጠረው የጎማ ልማትና ምርት ሥራ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገባውን የጎማ ጥሬ ዕቃ በከፊል በመሸፈን በሀገራዊ ኢኮኖሚው ላይ የራሱን አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትና ምርት ፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘማች ሳድንስ እንደሚሉት፤ የጎማ ዛፍ አንድ ጊዜ ከተተከለ በኋላ ዓመቱን ሙሉ ምርት የሚሰጥ ዛፍ ነው። የወተት ምርት ለመስጠት ችግኙ ከተተከለ በኋላ ለሦስት ዓመታት ይቆያል። በጉራፈርዳ ወረዳ ለምቶ ምርት እየሰጠ ካለው ዛፍ በወር ከ37 እስከ 40 ቶን የጎማ ዛፍ ጥሬ ምርት በመመረት ላይ ሲሆን ዘንድሮ ከ560 ቶን በላይ ምርት ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ የዘርፉን የጥሬ ምርት ፍላጎት በከፊል ለመመለስ እየተሰራ ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ከ87 ሺህ ሄክታር በላይ ለጎማ ዛፍ ምቹ መሬት እንዳላት ጥናቶች ያመለክታሉ። ይሁን እንጂ በስፋት ወደዚህ ዘርፍ በመግባት የዘርፉን ኢኮኖሚ መጠቀም አልተቻለም። የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የጎማ ዛፍ ልማትን ለማስፋፋት አቅዶ በጥናት ከተለዩ ቦታዎች መካከል በኦሮሚያ ክልል ኢሉአባቡር ዞን ከ2 ሺህ 500 ሔክታር በላይ መሬት ተረክቦ ችግኝ የማዘጋጀት ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በዚህም የሀገር ውስጥ የጥሬ ምርት ፍላጎትን በሀገር ውስጥ በመሸፈን እና የተረፈውን ኤክስፖርት በማድረግ ከዘርፉ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት የሚቻልበትን ዕድል ለመፍጠር ትኩረት መደረጉን አቶ ዘማች ጠቁመዋል። ባለሃብቶች ወደዚህ ዘርፍ ቢሰማሩ ሀገርን የሚጠቅሙ ውጤቶችን ማምጣት እንደሚቻልም አክለዋል። ኢትዮጵያ በየዘርፉ ያላት የኢኮኖሚ አቅም የዕድገት ጉዞዋ አቅሞች ናቸው። በተለይ ለም አፈሯ ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው ምርቶችን በማብቀል ለሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን ለዓለም ሀብት መፍጠር የሚያስችሉ መሆናቸውን በብዙ መንገድ ማረጋገጥ እየተቻለ ነው። ብዙም ትኩረት ያልተሰጠው የጎማ ዛፍ ልማትም ከእነዚህ አቅሞች አንዱ ነው። ያሉንን ጸጋዎች ለይቶ ለማልማትና ምርታማነትን ለመጨመር መንግሥት የሰጠውን ትኩረት መሠረት በማድረግ የጎማ ዛፍ ምቹ አጋጣሚዎችን ለይቶ መሥራት ከተቻለ ከዘርፉ በብዙ መጠቀም ይቻላል፡፡
ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት
Feb 26, 2026 521
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ ጀምረዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝት የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ ነው። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ ያደርሰዋል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩት አዘርባጃን እ.አ.አ በ1991 ነጻነቷን ማግኘቷን ተከትሎ ነው። የሀገራቱ ግንኙነት ከእ.አ.አ 1990ዎች መግቢያ አንስቶ እያደገ መጥቷል። አዘርባጃን እ.አ.አ በ2015 በኢትዮጵያ ኤምባሲ የከፈተች ሲሆን ይህም የሁለቱን ሀገራት የዲፕሎማሲ ትብብር እንዲጠናከር በር ከፍቷል። በቱርክዬ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ኢትዮጵያ ከአዘርባጃን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ስራ የሚሸፍን ሲሆን ፖለቲካ፣ ትምህርት እና ባህል ሀገራቱ ካላቸው የትብብር መስኮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው። የሁለቱ ሀገራት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እየጎለበተ መምጣቱን ከሚያመላክቱ ጉዳዮች መካከል በባለብዙ ወገን መድረክ በገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ (ናም) መድረክ በትብብር እየሰሩ መገኘታቸው ተጠቃሽ ነው። ኢትዮጵያ እ.አ.አ በ2019 በአዘርባጃን ባኩ በተካሄደው 18ኛው የገለልተኛ ሃገራት ንቅናቄ (ናም) ጉባኤ ላይ ተሳትፋለች። የገለልተኛ ሀገራት ንቅናቄ 120 አባል ሃገራትን ያቀፈና ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ቀጥሎ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የዓለም ሀገራትን በአባልነት የያዘ ስብስብ ነው። የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ወዳጅነት የደቡብ ደቡብ ትብብር ማሳያ ተደርጎም ይወሰዳል። በሀገራቱ መካከል ተከታታይ የሆኑ የባህል ልውውጥ መድረኮች ተካሄደዋል። ለዚህም እ.አ.አ በ1960ዎቹ የኢትዮጵያ ተማሪዎች በአዘርባጃን የትምህርት እድል አግኝተው ይከታተሉ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ። ከኢኮኖሚ አንጻር እ.አ.አ በ2017 በአዘርባጃን የተካሄደው የሁለቱ ሀገራት የቢዝነስ ፎረም ተጠቃሽ ነው። በወቅቱ ጨርቃጨርቅን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። በወቅቱ ሀገራቱ እርስ በእርስ ያላቸውን የንግድ ልውውጥ ምጣኔ ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ባለስልጣናት መካከል የሚደረጉ የጉብኝት ልውውጦች እያደጉ መጥተዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በግንቦት ወር 2016 ዓ.ም በአዘርባጃን ጉብኝት ማድረጋቸወ ይታወሳል። ኢትዮጵያና አዘርባጃን በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂና በሌሎች ዘርፎች ያላቸውን ትብብር የበለጠ ማሳደግና በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም እንዲሁ። ምክክሩ እጅግ ውጤታማ የነበረ ሲሆን የሁለቱን ሀገራት ህዝብ ዕድገት እና ብልፅግና በመደጋገፍና በትብብር መንፈስ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውም በወቅቱ ተገልጿል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከአዘርባጃን የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር ኮሎኔል-ጀነራል ኢይቫዞቭ ቪላያት ሱለይማን ጋር በነበራቸው ውይይት የደህንነት ጉዳዮችን ጨምሮ የኢትዮጵያን እና አዘርባጃን የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን ትብብሮችን ማጠናከር የሚያስችሉ ቀጣይ ስራዎች ላይ መክረዋል። በውይይቱም በመረጃ፣ በፀጥታና ደህንነት ዘርፎች የጋራ ትብብር አቅም ግንባታና ሌሎች ጉዳዮች ሁለቱን ሀገራት ተጠቃሚ የሚያደርጉ ፕሮጀክቶችን በጋራ ለመፈጸም መስማማታቸውን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መግለጻቸው ይታወሳል። እ.አ.አ በ2017 በወቅቱ የአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የነበሩት ኤልማር ማማድያሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸውና የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች በቋሚነት የፖለቲካ ምክክር ማድረግ የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። የአዘርባጃን የፐብሊክ ሰርቪስ እና ማኅበራዊ ፈጠራ ተቋም ሊቀ መንበር ኦልቪ ሜዲዬቭ የብሔራዊ ቤተመንግሥት እና የመሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በሰኔ ወር 2017 ዓ.ም ጎብኝተዋል። ኦልቪ ሜዲዬቭ በወቅቱ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር ተወያይተዋል። የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ያልቺን ራፊየቭ የተመራ ልዑክ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይተዋል፡፡ በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን የምትልካቸው ምርቶች ብዝኀነትን ለማሳደግና ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኗን ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡ ኢትዮጵያ ወደ አዘርባጃን ከምትልካቸው ምርቶች መካከል ሰሊጥ፣ የተቆላ ቡና፣ ተልባ፣ የፍየል እና የበግ ሥጋን ጨምሮ ሌሎች ምርቶች እንደሚገኙበት ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡ በአዘርባጃን የመከላከያ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ቩጋር ሙስታፋይ የተመራ ልዑክ በህዳር ወር 2018 ዓ.ም በኢትዮጵያ ከመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አካሂዷል፡፡ በውይይቱ ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በመከላከያ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር መስማማታቸው ይታወሳል። በኢኮኖሚ፣ በፖለቲካና ንግድ ትብብር ላይ ያተኮረው ሶስተኛ የኢትዮ-አዘርባጃን የውይይት መድረክ በጥር ወር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ከውይይቱ በኋላ ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የንግድ ግንኙነታቸውን ለማሳደግና ተጨማሪ እድሎችን መፈተሽ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ ደርሰዋል። 29ኛው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ (ኮፕ 29) በህዳር ወር 2017 ዓ.ም በአዘርባጃን መካሄዱ ይታወቃል። በጉባኤው ኢትዮጵያ በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተመራ ልዑክ ተሳትፎ አድርጋለች። በወቅቱ የኢትዮጵያ ልዑክ ከአዘርባጃን ባለስልጣናት ጋር በመወያየት ሀገራቱ በአካባቢ ጥበቃ፣ አየር ንብረት ለውጥ መከላከል እና አረንጓዴ ልማት ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በቁርጠኝነት ለመስራት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል። በሀገራቱ መካከል ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የተደረጉ ውይይቶችና የልምድ ልውውጦች የሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር እየጠነከረ መምጣቱን ያሳያል። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን በንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ግብርና፣ ዲጂታላይዜሽን፣ ትምህርት እና ባህልን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ትብብራቸውን ለማጠናከር ይሻሉ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በአዘርባጃን ሪፐብሊክ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ዛሬ ማድረግ መጀመራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የኢትዮጵያ እና የአዘርባጃን ግንኙነት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየጠነከረ መምጣቱን የገለጸው ጽህፈት ቤቱ ለዚህም ጉልህ ማሳያው በጠንካራ ትብብር የቀጠለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ጎልቶ እንደሚታይ አንስቷል። የዛሬው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጉብኝትም የዚሁ የዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት መጠናከር ማሳያ መሆኑን ጠቁሟል። ይህ ጉብኝት የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን የላቀ እና ትርጉም ያለው ደረጃ እንደሚያደርስ ይጠበቃል ሲልም ጽህፈት ቤቱ አመልክቷል። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ጉብኝት በመሪ ደረጃ የሚደረግ መሆኑ በሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ውስጥ ትልቅ ትርጉም ይሰጠዋል። ሶስት አስርት ዓመታትን የተሻገረው የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሁለትዮሽ፣ ቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ወደ ላቀ ደረጃ እንደሚሸጋገር የቅርብ ዓመታት ውይይቶች እና ጉብኝቶች ማሳያ ናቸው።