ቀጥታ፡

አራተኛ ቀኑን የያዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅት

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 10/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዋን ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ታደርጋለች። 


 

ለማጣሪያው በአሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ከመጋቢት 7 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ዝግጅታችውን ማድረግ ቀጥለዋል።

ቡድኑ የአራተኛ ቀን ልምምዱን ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ማድረጉን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። 


 

ጋቶች ፓኖም (አል ዓረቢ ሳዑዲ ዓረቢያ) እና ከነዓን ማርክነህ ( አል ሻባብ ኦማን) ብሔራዊ ቡድኑን በመቀላቀል ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል። 

ኢትዮጵያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር የማጣሪያ ጨዋታዎቿን መጋቢት 18 እና 22 ቀን 2018 ዓ.ም ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም