ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
የመደመር እሳቤ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብር ጠንካራ የፖለቲካ ባህል እያጎለበተ ነው 
Oct 8, 2026 52
አዲስ አበባ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የመደመር እሳቤ ለኢትዮጵያ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ የከፈተና አገራዊ ጥቅምን በሚያስተማምን ሁኔታ የሚያስከብር ጠንካራ የፖለቲካ ባሀል እያጎለበተ መምጣቱን ምሁራን ገለጹ። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሰይመዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ባደረጉት ንግግር፤ ገዥው ፓርቲና ተፎካካሪዎች በአንድ መንግሥት ውስጥ ለብሔራዊ ጥቅም በጋራ መስራት እንደሚቻል በተግባር መረጋገጡንና ይህም የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውን እያጠናከረው መምጣቱን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ሄኖክ ስዩም (ዶ/ር) እንዳሉት፤ የመንግሥት ምሥረታ ሂደቱ የዴሞክራሲ ባህልና የሕብረ ብሔራዊ አንድነት ፍሬ ማፍራት መጀመሩን የሚያሳይ ነው። መንግሥት በግብርና፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንዱስትሪና ታዳሽ ኃይል ላይ ትኩረት በማድረግ የኢኮኖሚ እድገቱን እያፋጠነ ይገኛል ብለዋል። በተጨማሪም የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የባህር በር መብት እንዲሁም ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክር አቋም መያዙ ሀገራዊ አንድነትን ያጎለበተ መሆኑን ጠቁመዋል። ፖለቲካዊ ልዩነቶችን በውይይት የመፍታት አቅጣጫ መቀመጡም ለሰላም ስኬት ትልቅ ዕድል መፍጠሩን አብራርተዋል። በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የልማት ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ዶክተር አብዱበሽር ሰይድ በበኩላቸው፤ የዓለም አቀፍ ሁኔታዎችን ያገናዘቡ የፖሊሲ አቅጣጫዎች መቀመጣቸው የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም ለማስጠበቅ የሚረዱ አዎንታዊ እርምጃዎች መሆናቸውን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት የተጀመሩ የልማትና የሰላም ስኬቶች ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገሩ ምሁራን በምርምር የተደገፉ የመፍትሔ ሃሳቦችን በማቅረብ፣ መገናኛ ብዙሃን ሚዛናዊ መረጃ በማሰራጨት እንዲሁም ህዝቡ ልማትና ሰላምን በመንከባከብ የተቀናጀ ድርሻቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል::
የመደመር መንግሥት የማይታለፍ ቀይ መስመር - ሙስና ሌብነትና የወገንተኝነት አሰራር!!
Oct 8, 2026 65
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ሙስና፣ ሌብነትና ወገንተኝነት የሀገርን ዕድገትና ብልፅግና ያኮሰምናል። የዜጎችን ፍትሐዊና ግልጸኝነት የሰፈነበት የአስተዳደር ሥርዓት መሻት የሚገዳደር የልማት ጠንቅም ነው። ለዚህም ነው የመደመር መንግሥት ጠንካራ አቋም የያዘው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ዳግም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሰየሙበት ወቅት፤ ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርንና ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መራር እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስምረውበታዋል። ይህ የመደመር መንግሥት ግልጽ አቋም ሌብነትና ሙስና የማይታለፍ ቀይ መስመር መሆኑን ያሳያል። መልዕክቱም የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶችን በማዘመን ብልሹ አሰራርን ለመግታትና ለሙስና መንስኤ የሆኑ ክፍተቶችን ለመዝጋት ትኩረት እንደሚሰጡ ያመላክታል። ይህም ለዜጎች ተስፋ፣ ለሙሰኞች ደግሞ መርዶን የሚያሰማ ጥብቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። አንድ ዜጋ የመንግሥት አገልግሎት ሲፈልግ ከቢሮ ቢሮ መዞር፣ ረጅም ወረፋ መጠበቅ፣ የግለሰብ ግንኙነትን ማማተርም ሆነ ተገቢ ያልሆነ ክፍያ መጠየቅ የለበትም። የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ እንዝህላልነት ሙስናን፣ ወገንተኝነትንና የዘመድ አዝማድ አሰራርን ያበረታታሉ። የፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያወጣው የሦስተኛው ብሔራዊ የሙስና ግንዛቤ ጥናትም በሙስና፣ በሌብነትና በብልሹ አሰራር ላይ ተከታታይና መራር እርምጃ የመውሰድ አስፈላጊነትን ያመላክታል። የመደመር መንግሥት ይህን ክፍተት ለመዝጋት የዲጂታል አብዮትን እንደ ዋና መሣሪያ የሚጠቀም ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር እየፈጠረ ይገኛል። ለዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥርዓት ተጨባጭ አብነት ነው። የተቋማት አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል መቅረባቸው ዜጎች ከቢሮ ቢሮ መዞር ሳይጠበቅባቸው የአገልግሎት ሂደቱን ግልጽና ፈጣን ያደርገዋል። በፌዴራል ደረጃ የተጀመረው የመሶብ አንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎት ምኅዳርም አሁን ላይ የተደራሽነት አድማሱን አስፍቷል። ለአብነትም በአዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ብቻ በ11 ክፍለ ከተሞች የመሶብ የዲጂታል አገልግሎት ማዕከላት ወደሥራ ገብተዋል። አሁን ይህ ሥርዓት ወደ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ ይገኛል። ከዚህም በላይ በተንቀሳቃሽና በእጅ ስልክ መተግበሪያ የተቀናጀ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ዜጎች በቤታቸውና በአቅራቢያቸው እንዲገለገሉ አስችሏል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያም የዚህ ጉዞ ወሳኙ አካል ሆኗል። አንድ ሰው አንድ ነው በሚል የተጀመረው መርሃ ግብሩም የግለሰብን የዲጂታል መለያ በማረጋገጥ የሐሰት ሰነድና የማጭበርበር ዕድልን በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። የተቀናጀና የተናበበ አገልግሎትን ለዜጎች በመስጠትም ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ማስገኘቱን ቀጥሏል። የዲጂታላይዜሽን ጉዞው የመንግሥት አገልግሎትን ከግለሰብ ተጽዕኖ ነፃ እንዲሆን አድርጓል። የዲጂታል አገልግሎቶች ግልጽነትን በማስፈን ተጠያቂነትን እያረጋግጡ ነው። የዲጂታል ግብይትና ክፍያ ሥርዓት መስፋፋቱም ተመሳሳይ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት ምኅዳር ዕድልን ፈጥሯል። የገንዘብ ዝውውርና እንቅስቃሴ የግብይት ሥርዓት ከእጅ ንክኪ በጸዳ ቁጥር የሙሰኞችን ሸምቀቆ በማጥበቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ያስችላል። ይህም የመደመር መንግሥት የዲጂታል አብዮት አንዱ ተጨባጭ እመርታ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ለማዘመን ትኩረት ይሰጣል። ብቃት ላይ የተመሠረተ የሥራ መመዘኛና የአፈጻጸም ክትትልም ሙስና፣ ሌብነት፣ የዘመድ አሰራርና ወገንተኝነትን የሚያከስም ሁነኛ መሠረት ነው። እነዚህ እርምጃዎችም የመደመር መንግሥት ሙስናን ከወንጀለኛ መቅጣት ባሻገር ሌብነት እንዳይፈጠር የሚያደርግ ሥርዓት ለመገንባት የሚያከናውነውን ተከታታይ ተግባር ያመላክታል። ይህን ቁርጠኝነት ወደ ተግባር ለመቀየርም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ተከታታይ ሥራ እየሰራ ይገኛል። ኮሚቴው የሙስና፣ የሌብነትና የወገንተኝነት ትግልን በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ በመምራት በሌብነት ላይ የሚወሰደውን መራር እርምጃ በሥርዓት እያስፈጸመ ነው። መራር እርምጃው ቃል ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ለውጥ መሆን አለበት። የፀረ-ሙስና ተቋማት አቅም፣ የሲቪል ሰርቪስ ብቃት፣ የዲጂታል አገልግሎት ስፋት፣ የመንግሥት ግዥ ግልጽነትና የፕሮጀክት ክትትል በአንድ ላይ ሲሰናሰሉ የሚለካ ውጤት ይመጣል። የመደመር መንግሥት ጽኑ ፍላጎትም ለዜጎች ያለአንዳች እጅ መንሻና ብልሹ አሰራር የመንግሥት አገልግሎት ማስገኘት ነው። ዜጎች በየቀኑ በመንግሥት ተቋማት የሚያገኙት ፍትሐዊና ግልጽ አገልግሎትም ሌብነትን የሚያደርቅ እውነተኛ መለኪያ ይሆናል። ትልቅ ሀገርና ትልቅ ሕዝብን የሚመጥን ታላቅ ርዕይ ለሰነቀችው ኢትዮጵያ ርዕይን በተግባር የሚያስፈጽም ታማኝ፣ ብቁ፣ ግልጽና ተጠያቂ ተቋም እየተገነባ ነው። የመደመር መንግሥት ሙስና፣ ሌብነትና ወገንተኝነትን የማይታለፍ ቀይ መስመር አድርጎ መበየኑም የሀገርንና የሕዝብን ሀብት ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል ካለው ቁርጠኛ አቋም ይመነጫል። የፍትሐዊ የመንግሥት አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትም ለዜጎች ተስፋን፣ ለሌቦች ደግሞ መርዶን የሚያውጅ ጥብቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ሆኗል። የሌብነት ቀይ መስመርነትም የሕዝብና መንግስትን መተማመን በማጎልበት የኢትዮጵያን መሻት በማላቅ ዕድገትና ብልፅግና ለማሳለጥ ተስፋን የፈነጠቀ ቀጣይነት ያለው ሥራ ሆኗል።
የአፈር ለምነትና ጤንነትን ለመመለስ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሻሻሉ ነው 
Oct 8, 2026 57
አዲስ አበባ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የአፈር ለምነትና ጤንነትን በመመለስ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ማሻሻላቸውን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ፈቃዱ ጉርሙ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከኮሪያ ዓለም አቀፍ የግብርና ፕሮጀክት (KOPIA) ጋር በመተባበር የአፈርን ለምነትና ጤንነት በመጠበቅ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ የሦስት ዓመት ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዛሬው ዕለት ፕሮጀክቱ እየተተገበረ በሚገኝበት በቢሾፍቱ አካባቢ ደንካካ ቀበሌ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችና የለሙ ሰብሎች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።   የኢንስቲትዩቱ የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ፈቃዱ ጉርሙ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ በየጊዜው የሚያወጣቸው ልዩ ልዩ የሰብል ዝርያዎች የግብርና ምርታማነትን በከፍተኛ መጠን እያሳደጉ ይገኛሉ። ቀደም ሲል ከ KOPIA ጋር በሰብል ማልማትና በዝርያ ማሻሻል ላይ ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ትኩረቱን አፈር ላይ ያደረገ ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። አፈር አስፈላጊውን ንጥረ ነገር አግኝቶ ጤንነቱ ሲጠበቅ ከፍተኛ ምርትና ምርታማነትን ይሰጣል ብለዋል። አፈር ታመመ የሚባለው ሰብል ሊሰጠው የሚገባውን ንጥረ ነገር መስጠት ሲያቅተው፣ የንጥረ ነገር ይዘቱ ሲቀንስ፣ አሲዳማና ጨዋማ ሲሆን፣ እንዲሁም ውሃ አፈሩ ላይ በመተኛቱ ምክንያት ሰብሎች ተስፋፍተው እንዳይበቅሉ ሲያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የአፈርን ለምነት በመመለስ የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሻሻሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።   በሌላ በኩል የኮሪያ ዓለም አቀፍ የግብርና ፕሮጀክት (KOPIA) የኢትዮጵያ ማዕከል ዳይሬክተር ሶንግ ዮንግ፤ ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ያላቸውን ታሪካዊ ወዳጅነት አሁን ላይ በግብርና ትራንስፎርሜሽን እና በቴክኖሎጂ ሽግግር በማጠናከር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የአፈርን ኦርጋኒክ ይዘት በመገንባት፣ የውሃ ፍሳሽ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን በማስፋፋት እንዲሁም የመኖ ሰብሎችን በማልማት የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና የሰብል ምርታማነትን ያቀናጀ አሰራር እንደሚተገበር ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ ከቢሾፍቱ ምርምር ማዕከል እና ከኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት የምርምር ውጤቶችን በቀጥታ ለአርሶ አደሩ የማድረስ ሥራ እንደሚሠራም አስረድተዋል። የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፤ በአፈር ለምነትና ጤንነት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ምርትና ምርታማነታቸውን እንዳሳደገላቸው አረጋግጠዋል።
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ፈጠራን ከምርታማነት ጋር ለማስተሳሰር እየሰራ ነው
Oct 8, 2026 60
ባህር ዳር፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ችግር በምርምር ለመፍታትና ፈጠራን ከምርታማነት ጋር ለማስተሳሰር በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው 3ኛውን ዓመታዊ የማህበረሰብ ተሳትፎና የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር አውደ ጥናት ዛሬ አካሂዷል።   በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እንየው አድጎ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማርና ከምርምር ሥራው ባሻገር ለማህበረሰብ አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። የፈጠራና ምርምር ሥራ የሚያከናውኑ ኢንዱስትሪዎችና ተመራማሪዎችን በመደገፍ የማምረትና የአገልግሎት አሰጣጥ አቅምን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። በዚህም የፈጠራ ባለሙያዎችን ለማብዛት፣ የኢንዱስትሪ አጋርነት፣ የምክር አገልግሎትና የፋይናንስ ተደራሽነት ላይ ይበልጥ አተኩሮ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የዛሬው አውደጥናትም ከልምድ ልውውጥ ባሻገር ምርምርን ወደ ቁሳዊ ሀብትና አገልግሎት ለማሸጋገር የሚያስችሉ የጋራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ አስረድተዋል።   የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፣ በተለያዩ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ ችግሩን መሰረት ያደረገ የምርምር ሥራ ማከናወን ወሳኝ ነው። በዚህ ረገድ ዩኒቨርሲቲው ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት የጀመረው የምርምር ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል። ይህም ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል በመቀየር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።   የአማጋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መጣአለም አማረ እንደገለጹት፤ ወጣት ተመራማሪዎች የሚያካሂዱት የምርምር ሥራ በፋብሪካው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማቃለል የሚያስችል ነው። በአውደጥናቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የክልልና የፌዴራል የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የሚታይ
ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ
Oct 8, 2026 119
መስከረም 28/2019 (ኢዜአ) ፡-የመደመር መንግስት፤ ሀገርን የማላቅ አዲስ ምዕራፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዛሬው እለት እጩ የካቢኔ አባላትን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበው ሹመታቸውን አጸድቀዋል። የካቢኔ አባላቱ ሹመት ህዝብን የማገልገል አቅምና ፍላጎት፤ የትምህርት ዝግጁነት፣ የስራ ልምድና አጠቃላይ ውጤታማነትን መሰረት ያደረገ ነው። እንደ አጠቃላይ ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የከፍታ ምዕራፍ የማሸጋገር አደራና ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል። በቀጣይ በላቀ የስራ አፈፃፀም የሀገርን እድገት የማስቀጠልና በዜጎች የዕለት ተዕለት ሕይወት በሚታይ ለውጥ ለማምጣት መትጋትም ይጠበቅባቸዋል። በተቋማት ቀጣይነት፣ በሥርዓት ግንባታና በሕዝብ አገልግሎት ውጤታማነት ላይ በመመሥረት የሀገር ግንባታን ሂደት ማስቀጠል የመደመር መንግስት አበይት ትኩረቱ አድርጎ እንደሚሰራም ይጠበቃል። የተቋማት ስኬት የሚለካው ለሕዝብ በሚሰጡት ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሁም ውጤታማ አገልግሎት በመሆኑ ሚኒስትሮቹ በዚሁ ልክ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል። የዜጎችን ተጠቃሚነት የማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን የሚተጉ መሆን ይኖርባቸዋል። የመደመር መንግስት የካቢኔ አባላት እጩዎችም የመፈጸም አቅምና ፍላጎት፣ የሥራ ልምድና የትምህርት ዝግጅት እንደ መሠረታዊ መስፈርቶች ተወስደው የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የህዝብ እውነተኛ አገልጋይ ለመሆን በመዘጋጀት መሆኑን እንዳለበት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አስገንዝበዋል። የመንግስት ሹመት “የሚዝናኑበት ሳይሆን የሚሰሩበት” ከፍተኛ የሕዝብ አደራ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ የካቢኔ አባላት ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ለማገልገል እንዲተጉም አሳስበዋል። የመደመር መንግስት ሀገር የመምራት እድልም የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የማስቀጠል፣ የተቋማትን ግንባታ የማጠናከር፣ የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ፣ የዜጎችን ተጠቃሚነት የማስቀጠል ይሆናል።  

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ

የኦሮሚያ ክልል አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው
Oct 8, 2026 97
ነገሌ ቦረና፣ መስከረም 28/2019(ኢዜአ)፡- የኦሮሚያ ክልል አዲሱ የዞኖች አደረጃጀት ህብረተሰቡን የልማት ተጠቃሚነት የበለጠ የሚያረጋግጥ ነው ሲሉ የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ። የደቡብ ኦሮሚያ ዞኖች አደረጃጀትን በተመለከተ የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪዎች አስተያየታቸውን ለኢዜአ ሰጥተዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ አቶ ሽምብራ ጋረደው አደረጃጀቱ የህብረተሰቡን አብሮነት በማጠናከር የሰላምና የልማት ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ያግዛል ብለዋል፡፡ ይህም የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን በህዝብ ተሳትፎ ለመስራትና በጋራ ለመልማት ተደማሪ አቅም እንደሚሆን ገልጸዋል፡፡ አዲሱ አደረጃጀት ሀብትንና የሰው ሀይልን በማቀናጀት ልማቶች የሚፋጠኑበትንና ማህበራዊ አገልግሎትን ለማስፋት እንደሚያስችል የገለጹት ደግሞ ሌላው የከተማው ነዋሪ አቶ ባጫ ጅማ ናቸው። አደረጃጀቱ የህብረተሰቡ የአብሮነትና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚኒት ይበልጥ እንዲረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ለስኬታማነቱ ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡ የከተማው ነዋሪ አቶ ሀይሉ ተሬ በበኩላቸው አደረጃጀቱ ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች ውጤታማነት የተሻለ አቅም ይፈጥራል የሚል ተስፋ ማድርጋቸውን ገልጸዋል። በተለይም ፍትሀዊ ተጠቃሚነትና ብልጽግናን ለማረጋገጥ የመተጋገዝ ባህላዊ እሴቶችን የሚያሳድግ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
የመደመር መንግስት ያስቀመጣቸው የልማት ዕቅዶች ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ መሠረት የሚጥሉ ናቸው 
Oct 8, 2026 166
አሶሳ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ የመደመር መንግስት ያስቀመጣቸው የልማት ዕቅዶች ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ መሠረት የሚጥሉ ናቸው ሲሉ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ተናገሩ። አዲስ የተመሠረተው የመደመር መንግሥት ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ መሰየሙ ይታወቃል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ የመደመር መንግሥት በአምስት ዓመታት ውስጥ የሚያከናውናቸውን የልማትና ግዙፍ ሀገራዊ ትልሞች ለምክር ቤቱ አብራርተዋል። በማብራሪያቸውም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያረጋግጡና የዜጎችን ሕይወት የሚቀይሩ የልማት ሥራዎች እንደሚከናወኑ ጠቅሰዋል። በዚሁ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚገኙ የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ የመደመር መንግሥት ያስቀመጣቸው የአምስት ዓመታት የልማት ዕቅዶች ኢትዮጵያ ለጀመረችው የብልጽግና ጉዞ መሠረት የሚጥሉ ናቸው ብለዋል። የቤኒሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ ሊቀመንበር አቶ አብዱሰላም ሸንገል፤ መንግሥት ያቀዳቸው የልማት ሥራዎች አሻጋሪና የሕዝብን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ናቸው ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የተነሱት ሀሳቦች ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ መሠረት የሚጥሉ መሆናቸውን የገለጹት አቶ አብዱሰላም፣ ለዚህም በአሳታፊነት ላይ ይበልጥ መሥራት እንደሚገባ አመልክተዋል። የመደመር መንግሥት በሀገሪቱ ሰላም እንዲፀና፣ የልማት ሥራዎች ተደራሽነት እንዲስፋፋና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መፍታት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት እንዳለበት ተናግረዋል። መንግሥት ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሀገር ልማት ላይ ተቀራርቦ የመሥራት ልምዱ ለሀገር እድገት የራሱ ድርሻ እንዳለው ገልጸው፣ ፓርቲያቸውም ለዚሁ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመዋል። የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ለሜሳ ኔኖ በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት በሀገሪቱ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠልና በሕብረተሰቡ የሚነሱ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የሚያስችሉ አቅጣጫዎችን ማስቀመጡን መገንዘባቸውን ገልጸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስቀመጧቸው የአምስት ዓመት የትኩረት አቅጣጫዎች ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩና ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማስመዝገብ ተጨማሪ አቅም የሚሆኑ ናቸው ብለዋል። ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ስኬታማነት በሁሉም መስክ ድልን መቀዳጀት ወሳኝ መሆኑን ጠቁመው፣ በተለይም የሀገርን ኢኮኖሚ በማሳደግ በሁሉም ዘርፍ ሉዓላዊነትን ማስጠበቅ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ማህበራዊ
በመልካ አቴቴ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ባህልና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በቂ ዝግጅት ተደርጓል
Oct 8, 2026 66
ሸገር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ በሸገር ከተማ መልካ አቴቴ የሚከበረው የኢሬቻ በዓል ባህልና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ። በሸገር ከተማ በቡራዩ ክፍለ ከተማ በሚገኘው የመልካ አቴቴ ስፍራ “ኢሬቻ ለብሔራዊ መግባባት” በሚል መሪ ሐሳብ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓል በማስመልከት ከወጣቶችና ሴቶች ጋር ዛሬ ውይይት ተደርጓል።   የቡራዩ ክፍለ ከተማ አስተዳዳሪ አቶ አባታ አስራት በወቅቱ እንደገለጹት፤ በዓሉን ለመታደም ለሚመጡ እንግዶች ደማቅ አቀባበል ለማድረግ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውነዋል። የመልካ አቴቴ ኢሬቻ በዓል የኦሮሞ ሕዝብ ማንነትና ባህል ማሳያ ከሆኑት እሴቶች አንዱ መሆኑን ያነሱት አቶ አባታ፣ በዓሉ የሰላምና የአንድነት ምልክት መሆኑንም ገልጸዋል። በዓሉ የሰላም፣ የአንድነትና የማኅበራዊ መግባባት መገለጫ በመሆኑ ባህላዊ ሥርዓቱንና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል። ከአባ ገዳዎች፣ ከወጣቶችና ከከተማው ነዋሪዎች ጋር በመቀናጀት በዓሉ የሚከበርበትን አካባቢ የማጽዳት፣ ለሚመጡ እንግዶች ምቹ የማድረግ እንዲሁም የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን የማስፋፋትና የማስዋብ ሥራ መሠራቱን ገልጸዋል። በተለይ የከተማው ወጣቶች ከጎቤና ሺኖዬ በዓላት ጀምሮ እስከ ኢሬቻ መልካ አቴቴ በዓል ድረስ በተለያዩ ተግባራት መሳተፋቸውን ጠቁመው፣ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል። ለበዓሉ የሚታደሙ የሀገራችንን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ጨምሮ ሌሎች እንግዶችን ተቀብሎ ለማስተናገድ የጸጥታ አካላት በትኩረት እየሠሩ መሆኑን ገልጸው፤ ወጣቶችም የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።   የክፍለ ከተማው የወጣቶች አስተባባሪ ወጣት ሲሳይ ሞአ በበኩሉ፤ ወጣቶችን በማደራጀት ለበዓሉ ለሚመጡ እንግዶች አቀባበል ለማድረግ ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጿል። በተለይም ወጣቱ ከጸጥታ አካላትና ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋር በመቀናጀት በዓሉ በድምቀት እንዲከበር በቅንጅት እየሠሩ መሆናቸውን ተናግሯል። በውይይቱ ላይ የተሳተፈችው ወጣት አዲሴ በቀለ በበኩሏ፤ በዓሉ ባህሉንና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመደራጀት የበኩላቸውን ኃላፊነት እየተወጡ መሆኑን ተናግራለች።   የእሬቻ መልካ አቴቴ በዓል ሰላምን፣ አንድነትንና ማህበራዊ መግባባትን በማጠናከር እንዲሁም የኦሮሞን ባህልና ማንነት ለተከታታይ ትውልድ ለማስተላለፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው በውይይቱ ላይ ተመልክቷል። የሆራ ፊንፊኔ እና የሆራ ሀርሰዲ የእሬቻ በዓል ባሳለፍነው መስከረም 23 እና 24 ቀን 2019 ዓ.ም በድምቀት መከበሩ ይታወሳል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በተቋማት ላይ አመኔታ እንዲኖራቸው አስችሏል
Oct 8, 2026 85
ሮቤ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በቅልጥፍና እንዲስተናገዱ ዕድልን ከመፍጠር ባሻገር በተቋማት ላይ አመኔታ እንዲኖራቸው አስችሏል ሲሉ የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የደቡብ ምሥራቅ ኦሮሚያ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ኢድሪስ ተናገሩ። በደሎ መና ከተማ የተገነባው መሶብ የአንድ መዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከል ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ አስተዳዳሪው እንደተናገሩት፤ የክልሉ መንግሥት ዜጎች ከመንግሥት የሚያገኙትን መሠረታዊ አገልግሎቶች የማዘመን ሥራ ላይ በትኩረት እየሠራ ይገኛል።   በተቋማት የሚታየውን የአገልግሎት አሰጣጥና የቅልጥፍና ችግር ለመፍታት «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት አንዱ መፍትሔ መሆኑንም ተናግረዋል። «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዜጎች በክብርና በቅልጥፍና እንዲስተናገዱ እንዲሁም በተቋማት ላይ አመኔታ እንዲኖራቸው የሚያደርግ መሆኑን ገልጸዋል። የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ ፍትሐዊና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን፣ ከንክኪ የጸዳና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል እንደሆነም ተናግረዋል። በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች የአንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋፋት የተቀላጠፈ የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥን ለመፍጠር እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።   «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለተያዘው የዲጂታል ኢትዮጵያ ጉዞ አጋዥ እንደሆነ አቶ አሕመድ ጠቁመው አገልግሎቱ ዜጎችን ከአላስፈላጊ ወጪ የሚታደግና እርካታን የሚፈጥር መሆኑን አመልክተዋል። የክልሉ መንግሥት አዲስ አደረጃጀትን በመዘርጋት መንግሥታዊ አገልግሎቶችን ወደ ሕዝቡ ለማቅረብ ያካሄደው የሪፎርም ሥራ የዚሁ ጥረት አካል መሆኑን አስታውሰዋል።   የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ ዑመር መሐመድ በበኩላቸው፤ የአንድ ማዕከል አገልግሎቱ 82 አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል የሚሰጥ መሆኑን ገልጸዋል። «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሁሉም ዜጎች በእኩል የሚስተናገዱበት አካታች ሥርዓት መሆኑንም ተናግረዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች በበኩላቸው፤ ቀልጣፋ አገልግሎትን በአንድ ማዕከል ማግኘት ቀደም ሲል ይደርስባቸው የነበረውን እንግልት እንደሚያስቀርም ገልጸዋል።
በበጎ ፈቃደኝነት በሚለገስ የሚተካ ደም የማይተካውን የሰዎች ህይወት እንታደግ
Oct 7, 2026 340
ደሴ፣ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፡-በበጎ ፈቃደኝነት በሚለገስ የሚተካ ደም የማይተካውን የወገኖቻችንን ህይወት እንታደግ ሲሉ ለበርካታ ጊዜያት ደም የለገሱ የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ። አገልግሎቱ ከበጎ ፈቃደኞች ተጨማሪ ደም ለመሰብሰብ የሚያስችለውን የግንዛቤ ማሳደጊያ የውይይት መድረክ ዛሬ አካሄዷል። በውይይቱ ላይ የተገኙት መምህር ኑሩ ይመርና ወጣት ሰሚራ ሰይድ፤ በበጎ ፈቃደኝነት በሚሰጥ የሚተካ ደም የማይተካውን የወገኖቻችንን ህይወት እንታደግ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል። መምህር ኑሩ ለ92 ጊዜያት ደም በመለገስ፣ በደም እጦት ለሞት አደጋ የተጋለጡ ወገኖችን መታደግ በመቻላቸው ሁልጊዜም የሕሊና እርካታና ደስታ እንደሚሰማቸው ገልጸዋል።   መምህር ኑሩ አክለውም ሦስት ልጆቻቸው አርአያነታቸውን በመከተል ቋሚ ደም ለጋሽ ሆነው በርካታ ወገኖችን በደም እጦት ምክንያት ከመሞት እየታደጉ እንደሚገኙ ተናግረዋል። ደም መለገስ የሚያስከትለው ምንም ዓይነት ጉዳት ስለሌለው በደም እጦት ለአደጋ የተጋለጡ ዜጎችን ሕይወት መታደግ አለብን ያለችው ደግሞ ወጣት ሰሚራ ሰይድ ናት። እርሷም በቋሚነት ደም እየለገሰች መሆኑን ጠቁማ፣ ጓደኞቿን በማስተባበር በየሦስት ወሩ በቋሚነት ደም እንዲለግሱ የማድረግ ተግባሯን አጠናክራ እንደምትቀጥልም አረጋግጣለች።   የደሴ ደምና ሕብረ-ሕዋስ ባንክ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ታደሰ ሲሳይ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፣ በቀላሉ የሚተካውን ደም በመለገስ የማይተካውን ክቡር የሰው ሕይወት እንደመታደግ ትልቅ ነገር የለም። እስካሁን በጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር በሚሰበሰበው ደም የበርካታ ዜጎችን ሕይወት ማዳን መቻሉንም ተናግረዋል። ባለፈው በጀት ዓመት ብቻ የተሰበሰበውን 11 ሺህ 778 ዩኒት ደም ለ36 የጤና ተቋማት በማሰራጨት፣ በአደጋና በወሊድ ጊዜ ደም ፈሷቸው ለሕይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የደረሱ ዜጎችን ሕይወት መታደግ መቻሉን ገልጸዋል። በጎ ፈቃደኞች በለገሱት ደም የበርካታ ዜጎች ሕይወት መታደግ መቻሉን የጠቀሱት ኃላፊው፣ አሁንም በጎ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጥሪ አቅርበዋል። በዘንድሮው በጀት ዓመት ለመሰብሰብ ከታቀደው 15 ሺህ 515 ዩኒት ደም ውስጥ እስካሁን ከ5 ሺህ ዩኒት በላይ መሰብሰቡን ተናግረዋል።   የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱ መሐመድ በበኩላቸው በትራፊክ አደጋ፣ በወሊድና በሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች ደም ፈሷቸው በደም እጦት የሚሞቱ ዜጎችን ለመታደግ ከስጦታ ሁሉ የሚበልጠውን ደም በመለገስ ሁሉም ማኅበራዊና ሰብዓዊ ኃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ብለዋል። በዞኑ በተለያዩ ተቋማት አማካይነት ሕብረተሰቡን በማስተባበር ደም እንዲለግስ ለማድረግ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑንም አክለው ገልጸዋል። በመድረኩም ከደቡብ ወሎ ዞን፣ ከደሴ ከተማ፣ ከወረዳዎችና ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች፣ ደም ለጋሾችና ሌሎች አጋር አካላት ተሳትፈዋል።
በክልሉ የህክምና አገልግሎትን ፍትሃዊነትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በቅንጅት የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ ናቸው
Oct 7, 2026 310
ደብረ ብርሃን፤ መስከረም 27/ 2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የሕክምና አገልግሎትን ፍትሐዊነትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሠራሮች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ፡፡ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሐኪም ግዛው ሆስፒታል የሲቲ ስካን (CT Scan) እና የፍሎሮስኮፒ (Fluoroscopy) ሕክምና ቴክኖሎጂዎች ዛሬ ሥራ ጀምረዋል። የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ገስጥ ጥላሁን በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ በክልሉ የሕክምና አገልግሎት ፍትሐዊነትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ ናቸው።   በተለይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመሩ ቅንጅታዊ አሠራሮች ውጤት እያስመዘገቡ መሆኑን አስረድተዋል። የዩኒቨርሲቲው ሆስፒታል በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ታግዞ ለማኅበረሰቡ የጤና አገልግሎት ለመስጠት የጀመራቸው ተግባራት በተለይ አክሞ ከማዳን አንፃር ውጤታማ መሆናቸውን ገልፀዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው፤ የጤና አገልግሎት ሥርዓቱን ለማሻሻል የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል።   በዘርፉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጥቅም ላይ መዋላቸው የተሻለ የሕክምና አገልግሎት ፍለጋ ወደ አዲስ አበባ ይደረግ የነበረውን እንግልትና ወጪ ለመቀነስ እንደሚያስችልም ጠቅሰዋል። ይሕም የአካባቢውን ሕዝብ ጨምሮ ከአፋርና ከኦሮሚያ አጎራባች ዞኖች ለሚመጡ ዜጎች የሚሰጠውን አገልግሎት ለማስፋፋት እንደሚያግዝ አስታውቀዋል። ከተማ አስተዳደሩ አዳዲስ የሕክምና አገልግሎቶችን ለሕዝቡ ተደራሽ ለማድረግ ለሚመጡ ባለሀብቶች ምቹ ሁኔታዎችና ማበረታቻዎች እንደሚያቀርብም አመልክተዋል። የሆስፒታሉን አገልግሎት ለማስፋፋት በሚደረገው ጥረት ውስጥ አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው ያረጋገጡት።   የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት አስማረ መለስ በበኩላቸው፤ በሆስፒታሉ ደረጃውን የጠበቀ የጤና አገልግሎት ለማዳረስ አልሞ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል። በቀጣይም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስገባት አገልግሎቱ ምቹ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አመልክተዋል።  
ኢኮኖሚ
የአፈር ለምነትና ጤንነትን ለመመለስ እየተከናወኑ የሚገኙ ሥራዎች የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሻሻሉ ነው 
Oct 8, 2026 57
አዲስ አበባ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦የአፈር ለምነትና ጤንነትን በመመለስ ረገድ የተከናወኑ ተግባራት የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ማሻሻላቸውን በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ፈቃዱ ጉርሙ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ከኮሪያ ዓለም አቀፍ የግብርና ፕሮጀክት (KOPIA) ጋር በመተባበር የአፈርን ለምነትና ጤንነት በመጠበቅ የሰብል ምርታማነትን ለማሳደግ ያለመ የሦስት ዓመት ፕሮጀክት እየተገበረ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በዛሬው ዕለት ፕሮጀክቱ እየተተገበረ በሚገኝበት በቢሾፍቱ አካባቢ ደንካካ ቀበሌ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችና የለሙ ሰብሎች የመስክ ምልከታ ተካሂዷል።   የኢንስቲትዩቱ የሰብል ምርምር ዳይሬክተር ፈቃዱ ጉርሙ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ኢንስቲትዩቱ በየጊዜው የሚያወጣቸው ልዩ ልዩ የሰብል ዝርያዎች የግብርና ምርታማነትን በከፍተኛ መጠን እያሳደጉ ይገኛሉ። ቀደም ሲል ከ KOPIA ጋር በሰብል ማልማትና በዝርያ ማሻሻል ላይ ሲሰሩ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ትኩረቱን አፈር ላይ ያደረገ ፕሮጀክት ተቀርጾ ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። አፈር አስፈላጊውን ንጥረ ነገር አግኝቶ ጤንነቱ ሲጠበቅ ከፍተኛ ምርትና ምርታማነትን ይሰጣል ብለዋል። አፈር ታመመ የሚባለው ሰብል ሊሰጠው የሚገባውን ንጥረ ነገር መስጠት ሲያቅተው፣ የንጥረ ነገር ይዘቱ ሲቀንስ፣ አሲዳማና ጨዋማ ሲሆን፣ እንዲሁም ውሃ አፈሩ ላይ በመተኛቱ ምክንያት ሰብሎች ተስፋፍተው እንዳይበቅሉ ሲያደርግ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ አሁን ላይ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች የአፈርን ለምነት በመመለስ የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሻሻሉ እንደሚገኙ ተናግረዋል።   በሌላ በኩል የኮሪያ ዓለም አቀፍ የግብርና ፕሮጀክት (KOPIA) የኢትዮጵያ ማዕከል ዳይሬክተር ሶንግ ዮንግ፤ ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ያላቸውን ታሪካዊ ወዳጅነት አሁን ላይ በግብርና ትራንስፎርሜሽን እና በቴክኖሎጂ ሽግግር በማጠናከር ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል። በሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የአፈርን ኦርጋኒክ ይዘት በመገንባት፣ የውሃ ፍሳሽ ቴክኖሎጂዎችን በመተግበር፣ የተፈጥሮ ማዳበሪያዎችን በማስፋፋት እንዲሁም የመኖ ሰብሎችን በማልማት የእንስሳት መኖ አቅርቦትንና የሰብል ምርታማነትን ያቀናጀ አሰራር እንደሚተገበር ጠቅሰዋል። ፕሮጀክቱ ከኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት፣ ከቢሾፍቱ ምርምር ማዕከል እና ከኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት የምርምር ውጤቶችን በቀጥታ ለአርሶ አደሩ የማድረስ ሥራ እንደሚሠራም አስረድተዋል። የፕሮጀክቱ ተጠቃሚ አርሶ አደሮች በበኩላቸው በሰጡት አስተያየት፤ በአፈር ለምነትና ጤንነት ላይ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ምርትና ምርታማነታቸውን እንዳሳደገላቸው አረጋግጠዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ግቦችን ለማሳካት የህዝብ ተሳትፎ ሊጠናከር ይገባል 
Oct 8, 2026 58
አርባ ምንጭ፤መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለማከናወን የተያዙ የልማት ግቦች እንዲሳኩ ህዝቡ ድጋፉን ማጠናከር እንዳለበት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር) እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በአርባ ምንጭ ከተማ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል።   ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ለሀገረ መንግስት ግንባታ ሀገር በቀል ዕውቀት፣ ጥበብና ፍልስፍናን ማዕከል በማድረግ እየተሰራ ነው። የጋሞዎች የሰላም እሴትም ለሀገረ መንግስት ግንባታ ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጸው፣ እሴቶቹን በማጎልበት ልንጠቀማቸው ይገባል ሲሉ ተናግረዋል። ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ሥራዎች የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና የጎደሉትን ለመሙላት የክልሉ መንግስት ከህዝቡ ጋር በትብብር ይሰራል ብለዋል።   በጋሞ ዞን ለተደረገላቸው ደማቅ አቀባበል ምስጋና ያቀረቡት ርዕሰ መስተዳድሩ ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)፣ አርባ ምንጭ ከተማን ጨምሮ በክልሉ የተጀመሩ የልማት ግቦች እንዲሳኩ የመንግስትና የህዝብን አቅም በማስተባበር ይሰራል ብለዋል። በመደመር መንግስት የዲጂታል ሥርአትን በማጎልበት ከዓለም ጋር ዕኩል ለመጓዝ ያለእረፈት ይሰራል ብለዋል። በተለይ ህዝቡ ሰላምና አንድነቱን በመጠበቅ ክልሉን የሰላም፣ የመቻቻልና የብልጽግና ተምሳሌት ለማድረግ የተጀመሩ ተግባራትን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል፡፡
በከተማው የመስኖ ልማቱን በማዘመን ለገበያ የሚሆን ምርት ለማምረት ትኩረት ተደርጓል
Oct 8, 2026 81
ደብረ ብርሃን ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ በደብረ ብርሃን ከተማ የመስኖ ልማቱን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለገበያ የሚሆን ምርት ለማምረት ትኩረት መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ገለጸ። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ የበጋ መስኖ ልማት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ አካሄዷል።   በወቅቱም ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ እንደገለጹት፤ የመስኖ ልማቱን በማዘመን የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ ባለፈ ለገበያ የሚሆን ምርት ለማምረት በትኩረት ይሠራል። በዘርፉ የሚሰማሩ አርሶ አደሮች ጥራትና ብዛት ያለው ምርት በማምረት በከተማዋ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ግብዓት ለማቅረብ መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል። ለዚህም የኩታ ገጠም የአስተራረስ ዘዴን መጠቀም፣ ግብዓትን በአግባቡና በወቅቱ ማቅረብ እንዲሁም አዳዲስ አሠራሮችና ቴክኖሎጂዎችን መተግበር እንደሚገባ አስረድተዋል። የበጋ መስኖ ልማትን ከከተማ ግብርና ጋር አስተሳስሮ በማልማት የምርታማነት እድገትን ለማረጋገጥ በሚደረገው ጥረት አስተዳደሩ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።   የከተማ አስተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ መርሻ አይሳነው በበኩላቸው፤ የግብርናውን ዘርፍ ከምርታማነት ባሻገር ለወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማዋል እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። በያዝነው በጋ በከተማ አስተዳደሩ 6 ሺህ 661 ሄክታር መሬት በበጋ መስኖ ለማልማት ወደ ሥራ መገባቱን ጠቁመው፣ ከዚህ ውስጥ 2 ሺህ ሄክታሩ አዲስ የተካተተ መሬት መሆኑን ተናግረዋል። ከአጠቃላይ መሬቱ ውስጥ 5 ሺህ 680 ሄክታር የሚሆነው በበጋ ስንዴ የሚሸፈን መሆኑን ጠቁመው፣ ለዚህም 882 የውኃ መሳቢያ ጄኔሬተሮችና 23 የእርሻ ትራክተሮች ጥቅም ላይ እንደሚውሉም ገልጸዋል።   ከጽጌሬዳ ቀበሌ የመጡት አርሶ አደር ቄስ ታደሰ በቀለ በበኩላቸው፤ ባለፈው ዓመት አንድ ሄክታር ማሳቸውን በኩታ ገጠም በስንዴ በማልማት 39 ኩንታል ምርት ማግኘታቸውን ተናግረዋል። በያዝነው በጋም ሁለት ሄክታር መሬታቸውን በስንዴ በመሸፈን ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት አቅደው ሥራ መጀመራቸውን አስረድተዋል። ከጨፈና ቀበሌ አርሶ አደር አድማሱ ገመቹ በበኩላቸው፤ በተያዘው የበጋ ወራት አንድ ሄክታር መሬታቸውን በበጋ ስንዴ ለማልማት ዝግጅት ማድረጋቸውን ገልጸዋል።
በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ወደ ስራ ተገብቷል
Oct 8, 2026 74
ጎንደር ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል በመካናይዜሽን የታገዘ ዘመናዊ ግብርና ለማስፋፋት ትኩረት መሰጠቱን በምክትል ርእስ መስተዳድር ማእረግ የክልሉ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ገለፁ። የክልሉ ግብርና፣ እንስሳትና አሳ ሀብት ልማት ቢሮ "ዘመናዊ ግብርና ለሁለንተናዊ ልዕልና" በሚል መሪ ሃሳብ በጎንደር ከተማ የውይይት መድረክ እያካሔደ ይገኛል።   ​የዘርፍ አስተባባሪው ድረስ ሳህሉ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ የግብርናውን ዘርፍ በቴክኖሎጂና በአዳዲስ አሰራር የዳበረ በማድረግ ምርታማነትን የማሳደግ ስራ እየተከናወነ ይገኛል። ዘርፉን በቴክኖሎጂና በአዳዲስ አሰራር የዳበረ በማድረግ ሳይንሳዊ የአመራረት ዘይቤን በመከተል የተከናወኑ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እንደተመዘገበባቸው አንስተዋል። "የመደመር መንግስት ትኩረት ከሰጣቸው አገር በቀል የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ ግብርና ዋነኛው ነው" ያሉት ዶክተር ድረስ ዘርፉን በማዘመን ለኢንዱስትሪ ግብአትና ለውጭ ንግድ ማዋል እንደሚገባ ገልጸዋል። ​እንደ ሰሊጥ፣ አኩሪ አተርና ጥጥ ያሉ ገበያ ተኮር ምርቶች ላይ በማተኮርም እድገትን ለማፋጠን የዘርፉ አመራሮችና ባለሙያዎች የግብርና ትራንስፎርሜሽንን ማረጋገጥ እንደሚገባቸው ነው ያሳሰቡት።   የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ መስፍን አበጀ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በ2018/19 የምርት ዘመን አዳዲስ የግብርና አሰራሮችና ቴክኖሎጂ በመተግበር 205 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለማግኘት ወደ ስራ ተገብቷል ነው ያሉት። የሚጠበቀውን ምርት ለማግኘትም አርሶ አደሩ በቂ የግብርና ኤክስቴንሽን ድጋፍ እንዲያገኝ እየተደረገ መሆኑንም አብራርተዋል። በተጨማሪም ከሰባት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ዘመናዊ ማዳበሪያ በወቅቱ ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በመደረጉ በምርት እድገት ላይ አዎንታዊ ሚና መጫወቱን ተናግረዋል። ዘመናዊ እርሻን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረትም የእርሻ ትራክተሮችን ቁጥር ወደ ስድስት ሺህ ማሳደግ በመቻሉ በዘመናዊ መንገድ የሚታረስ መሬት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመር መምጣቱን አስረድተዋል። ለሁለት ቀናት በሚካሄደው በዚሁ መድረክ ላይ የክልል ቢሮዎች፣ የዞን መምሪያ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ፈጠራን ከምርታማነት ጋር ለማስተሳሰር እየሰራ ነው
Oct 8, 2026 60
ባህር ዳር፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ችግር በምርምር ለመፍታትና ፈጠራን ከምርታማነት ጋር ለማስተሳሰር በትኩረት እየሰራ መሆኑን አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው 3ኛውን ዓመታዊ የማህበረሰብ ተሳትፎና የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር አውደ ጥናት ዛሬ አካሂዷል።   በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ ተሳትፎ ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር እንየው አድጎ እንደገለጹት፣ ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማርና ከምርምር ሥራው ባሻገር ለማህበረሰብ አገልግሎት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። የፈጠራና ምርምር ሥራ የሚያከናውኑ ኢንዱስትሪዎችና ተመራማሪዎችን በመደገፍ የማምረትና የአገልግሎት አሰጣጥ አቅምን ለማሳደግ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል። በዚህም የፈጠራ ባለሙያዎችን ለማብዛት፣ የኢንዱስትሪ አጋርነት፣ የምክር አገልግሎትና የፋይናንስ ተደራሽነት ላይ ይበልጥ አተኩሮ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። የዛሬው አውደጥናትም ከልምድ ልውውጥ ባሻገር ምርምርን ወደ ቁሳዊ ሀብትና አገልግሎት ለማሸጋገር የሚያስችሉ የጋራ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ያለመ መሆኑ አስረድተዋል።   የአማራ ክልል መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አባተ ጌታሁን (ዶ/ር) በበኩላቸው እንዳሉት፣ በተለያዩ ምክንያት ጉዳት የደረሰባቸው አካባቢዎች መልሰው እንዲያገግሙ ችግሩን መሰረት ያደረገ የምርምር ሥራ ማከናወን ወሳኝ ነው። በዚህ ረገድ ዩኒቨርሲቲው ለችግሩ መፍትሄ ለማምጣት የጀመረው የምርምር ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ገልጸዋል። ይህም ችግሮችን ወደ መልካም ዕድል በመቀየር የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችል በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።   የአማጋ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ መጣአለም አማረ እንደገለጹት፤ ወጣት ተመራማሪዎች የሚያካሂዱት የምርምር ሥራ በፋብሪካው የሚስተዋሉ ችግሮችን ለማቃለል የሚያስችል ነው። በአውደጥናቱ ላይ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ ተመራማሪዎች፣ የክልልና የፌዴራል የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።
የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ማዕከላት ጋር በመቀናጀት የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሳደገ ነው
Oct 8, 2026 59
ነቀምቴ፤ መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፡- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ማዕከላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሳደገ መሆኑን አስታወቀ። የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ሥርፀት ኦፊሰር ተመራማሪ ጋዲሳ ተሾመ ከመማር ማስተማር በተጓዳኝ ከባኮ ብሔራዊ የበቆሎ ምርምር ማዕከል ጋር በመተባበር BH-520 የተሰኘ የተሻሻለ የበቆሎ ዝርያን በማባዛት የአርሶ አደሩን ምርታማነት እያሳደገ ነው። ይህም የአርሶ አደሩን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት ከማገዝ ባለፈ ኢኮኖሚያዊ አቅሙን እያጠናከረ መምጣቱን ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው የግብርና ምርታማነትን ለማሳደግ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችን በማባዛት ለ300 የአርሶ አደር ማሰራጨቱንም ተመራማሪው ገልጸዋል። የከተማ ግብርናን ለማስፋፋት የሚያግዙ የአትክልት ዘር ማቅረብና ተጠቃሚዎችም ውጤታማ እንዲሆኑ ሙያዊ ድጋፍ ማድረጉን አንስተዋል። በቀጣይም የግብርናን ውጤታማነት በማሳደግ አርሶ አደሮችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ የጀመረውን የሥልጠናና የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደሚያጠናክር ገልፀዋል። ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመቀናጀት ለአርሶ አደሩ የሚያቀርቡት የግብርና ቴክኖሎጂ የአርሶ አደሮችን ምርታማነትን ማሳደጉን የገለጹት ደግሞ የዋዩ ቱቃ ወረዳ ግብርና ባለሙያ አቶ ሚልኬሳ ነመራ ናቸው። ይህም የአርሶ አደሩን የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎችንና የግብርና ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ባህል እያዳበረው መምጣቱን ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው የሚያቀርበው የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች ከአካባቢው የአየርና የአፈር ሁኔታ ጋር የሚስማሙ መሆናቸው ለምርታማነት ማሳደግ ከፍተኛ ድርሻ ማበርከታቸውን አስረድተዋል። የዋዩ ቱቃ ወረ ባቦ ቀበሌ አርሶ አደር አቶ መልካሙ ሀነቢሳ በበኩላቸው እንደገለጹት፣ ከዩኒቨርሲቲው ያገኙትን የተሻሻለ የበቆሎ ዘር ተጠቅመው ምርታማነታቸውን ማሳደጋቸውን ተናግረዋል። በዚህም የቤተሰባቸውን የምግብ ፍላጎት ከማሟላት ባለፈ ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት እንዳገዛቸው ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው ያቀረበላቸው የተሻሻለ የሰብል ዝርያና የግብርና ቴክኖሎጂ ድጋፍ ምርታማነታቸውን ለማሳደግ እንዳገዛቸው የጠቆሙት ደግሞ ሌላው ተጠቃሚ አርሶ አደር ጀቤሳ ቱፍ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው ውጤታማ እንዲሆኑ ያበረከተላቸው አስተዋጽኦ በኑሮዋቸው ላይ ተጨባጭ ለውጥ በማምጣቱ ተሞክሯቸውን ለሌሎች አርሶ አደሮች እያካፈሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።  
በከተማው አገልግሎትን በተሻለ ቅርበትና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተደራሽ የማድረጉ ተግባር ይጠናከራል
Oct 8, 2026 57
ጊምቢ ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ በጊምቢ ከተማ አገልግሎትን በተሻለ ቅርበትና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ተደራሽ የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የከተማው አስተዳደር ከንቲባ ፈዬራ አቦማ ገለጹ። በከተማው «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት በዛሬው ዕለት ወደ ሥራ ገብቷል።   ከንቲባ ፈዬራ አቦማ በምረቃው ወቅት እንዳሉት፤ በከተማ አስተዳደሩ «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት ወደ ሥራ መግባቱ ለማኅበረሰቡ ፈጣንና ጥራት ያለው አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ይኖረዋል።   «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተገልጋዩ ማኅበረሰብ የተለያዩ አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ፣ በአጭር ጊዜና በቅርበት እንዲያገኝ በማድረግ ረገድ ጉልህ ሚና አለው ብለዋል። ይህም በከተማ አስተዳደሩ በተለያዩ ጊዜያት የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የቆዩ አሰራሮችን በማስቀረት ማኅበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኝ ያስችላል ብለዋል። በከተማ አስተዳደሩ አገልግሎትን በማስፋፋት፣ በተሻለ ቅርበትና በቴክኖሎጂ በመታገዝ ለማኅበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አቶ ፈዬራ አረጋግጠዋል።   በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የምዕራብ ኦሮሚያ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተሊላ ተረፋ በበኩላቸው፤ መንግሥት ለማኅበረሰቡ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ዘርፈ ብዙ አማራጮችን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል። ዛሬ ወደ ተግባር የገባው የጊምቢ በ«መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን በአንድ ቦታ ለመስጠት እንደሚያስችልም አብራርተዋል። ይህም የጊምቢ ከተማና የአካባቢው ማኅበረሰብ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የሚያስቀር መሆኑን አመልክተዋል። የጊምቢ «መሶብ» የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለከተማዋ ነዋሪዎች ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ሁነኛ መፍትሔ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ገልጸዋል።
ዓለም አቀፍ አድናቆት የተቸረው የኢትዮጵያ የዲጂታል ሽግግር
Oct 8, 2026 208
አዲስ አበባ፣መስከረም 28/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) እና ሳይንስ ዘርፍ በአፍሪካ ፋና ወጊ ስኬቶችን ማስመዝገቧ የሚደነቅ ነው ሲሉ የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ (ጃይካ) አማካሪ ታካሺ ኦኢካዋ ገለጹ። የኢትዮጵያ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለአፍሪካ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የማድረግ አቅም እንዳለውም አማካሪው ተናግረዋል። የጃፓን ዓለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ የፕሮጀክት ዋና አማካሪ እና የቦስተን ኮንሳልቲንግ ግሩፕ (BCG) ምስራቅ አፍሪካ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ታካሺ ኦኢካዋ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በኢትዮጵያ በዲጂታል ሽግግር ዙሪያ ከመንግሥት እና ጀማሪ የቴክኖሎጂ ስታርትአፖች በቅርበት ለመሥራት መቻላቸውን ተናግረዋል። ይህም በኢትዮጵያ በቴክኖሎጂው ዘርፍ መሰረተ ሰፊ ለውጥ እየመጣ መሆኑን እንዲረዱ እንዳስቻላቸውም አንስተዋል። በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደገ የመጣው የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ስብስብ እና ለመስኩ እየተደረገ ያለው የመንግሥት ድጋፍ ሀገሪቱ ለአጠቃላይ በአፍሪካ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ውስጥ የጎላ አስተዋጽኦ እንድታደርግ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርላትም አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ወጣትና ሊሰለጥን የሚችል እንዲሁም የቴክኖሎጂ እውቀትና ዝንባሌ ያለው የሰው ኃይል መኖሩ ለዘርፉ ዕድገት ቁልፍ ጉዳይ መሆኑንም አማካሪው አንስተዋል። መንግሥት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ዲጂታል ሽግግር እያሳየ ያለው ቁርጠኝነት አቅም ካለው የሰው ኃይል ጋር ተዳምሮ በቀጣይ ኢትዮጵያ በዲጂታል መስክ ተጠቃሽ ሀገር የሚያደርጋት መሰረት እየጣለ መሆኑን መገንዘባቸውንም ጠቅሰዋል። "ይህ የወጣቶች አቅም እና የመንግሥት ድጋፍ ሲቀናጅ የኢትዮጵያ ዲጂታል ሽግግር በአስተማማኝ ምህዋር ውስጥ እንዲጓዝ የሚያደርግ ነው ሲሉም ተናግረዋል። የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በአዲሱ የስታርትአፕ አዋጅ አማካኝነት ለአዳዲስ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚያደርገውን ማበረታቻ፣ ድጋፍ እና ስልጠና በአርአያነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል። የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂው ዘርፍ ዕድገት ለአፍሪካ ዲጂታል ሽግግር መሳለጥ ትልቅ አቅም የሚሆን ነው ያሉት አማካሪው ከራሷ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የዲጀታል አገልግሎቶችን የማቅረብ አቅም እየገነባች ነው ብለዋል። "የኢትዮጵያ ማደግ ማለት የአፍሪካ ማደግ ማለት ነው" ያሉት አማካሪው፤ የኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የበለጠ ተዛማጅነት እና ተስማሚነት ያላቸውን አገልግሎቶች በማቅረብ፣ ሀገሪቱ የአገልግሎት ወጪ ንግዷን እንድታስፋፋ ትልቅ እድል እንደሚፈጥርም ጠቁመዋል። ኢትዮጵያ የፓን-አፍሪካ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ማዕከል ለመሆን የምታደርገው ጥረት የሚደነቅ ነው ያሉት ኦኢካዋ፤የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ተቋቁሞ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ሥራዎችን በተሳለጠ አግባብ እንዲመራ መደረጉ ትልቅ እርምጃ መሆኑን አንስተዋል። ሰው ሰራሽ አስተውሎት የሚያመጣቸውን ዕድሎች በተጓዳኝ ስጋቶችንም የሚያስወግዱ ሥራዎችም አብረው ሊሰሩ እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል። በጃፓን እና በኢትዮጵያ መካከል በተለይም በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና በሮቦቲክስ ዘርፍ ጠንካራ የቴክኖሎጂ ትብብር ለማድረግ የሚያስችሉ ሰፊ እድሎች እንዳሉ ጠቁመዋል። ጃፓን በሰው ሰራሽ አስትውሎትና በሮቦቲክስ ሰፊ ልምድ ያላት ሀገር መሆኑን ገልጸው፤እነዚህን ዘርፎች በማቀናጀት የላቀ ውጤት ለማምጣት ሀገራቱ ትብብራቸውን ይበልጥ ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ ጀማሪ ስታርትአፖችን የሚያበረታታ ፖሊሲዎችና አሰራሮችን እየዘረጋች መሆኑን ጠቅሰው፤ይህም በመሆኑን ወደ ፊት በመስኩ ትልቅ ውጤት ለማምጣት መሰረት የሚጥል ነው ብለዋል።      
ስፖርት
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ይጫወታል
Oct 7, 2026 201
አዲስ አበባ፤ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በኦሊምፒክ ጨዋታዎች ማጣሪያ ሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል። ጨዋታው ምሽት አንድ ሰዓት ላይ በኪጋሊ ፔሌ ስታዲየም ይካሄዳል። ብሔራዊ ቡድኑ እ.አ.አ በ2028 በሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ከመስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ ዝግጅቱን አድርጓል። በለሜቻ ግርማ የሚሰለጥነው ቡድን ከሲሸልስ አቻው ጋር ሁለት ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታዎች አከናውኗል። በዚህም ሉሲዎቹ 16 ለ 0 እና 10 ለ 0 አሸንፈዋል። በነዚህ ጨዋታዎች 26 ጎሎቹን በማስቆጠር ቡድኑ ፍጹም የበላይነቱን ይዟል። ቻለው ለሜቻ በሁለት ዓመት ውል የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ሆነው የተሾሙት ከሁለት ሳምንታት ገደማ በፊት ነው። በአንድሬ ካሳ ሙቡንጎ የሚመራው የሩዋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ላለፉት 10 ቀናት ዝግጅቱን በኪጋሊ ሲያደርግ ቆይቷል። ሙቡንጎ በመጀመሪያ ዙር ለ29 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገው በሂደት አራት ተጫዋቾችን ቀንሰው ለጨዋታው ተዘጋጅተዋል። ኢትዮጵያ እና ሩዋንዳ የመልስ ጨዋታቸውን ጥቅምት 3 2019 ዓ.ም በአበበ በቂላ ስታዲየም ያከናውናሉ። በደርሶ መልስ ውጤት ሉሲዎቹ ካሸነፉ ሶስተኛውን ዙር ይቀላቀላሉ። ብሔራዊ ቡድኑ በፊፋ የሴቶች የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ እና ከዚህ ቀደም በነበሩ ማጣሪያዎች በነበረው የተሻለ ብቃት የቅድመ ማጣሪያ ሳያደርግ ወደ ሁለተኛ ዙር ቀጥታ ገብቷል። በአምስት ዙሮች በሚካሄደው ማጣሪያ ሁለት ሀገራት አፍሪካን ወክለው በኦሊምፒክ ውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ። በአጠቃላይ በኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ 12 ሀገራት የሚሳተፉ ይሆናል። የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የዚኛውን ሳይጨምር ከዚህ ቀደም በአራት የኦሊምፒክ ማጣሪያዎች ላይ ተሳትፈዋል። እ.አ.አ በ2012 በለንደን በተካሄደው 30ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ላይ ለመሳተፍ ባደረገው የማጣሪያ ተሳትፎ መጨረሻ ዙር የደረሰበት ትልቁ ውጤቱ ነው። በወቅቱ በደቡብ አፍሪካ በድምር ውጤት 3 ለ 1 ተሸንፎ ለኦሊምፒኩ ማለፍ አልቻለም።
የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ሲሸልስን በድጋሚ በሰፊ የግብ ልዩነት አሸነፈ
Oct 3, 2026 360
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ) ፦ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሲሸልስ ጋር ባደረገው ሁለተኛ ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ጨዋታ ሲሸልስን 10 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት አሸንፏል። በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳግማዊ ሰለሞን ሁለት በጨዋታ እና አንድ በፍጹም ቅጣት ምት በአጠቃላይ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሰርታለች። እሙሽ ዳንኤል ሁለት ጎሎችን ከመረብ ላይ ስታገናኝ ቱሪስት ለማ፣ ቤተልሄም መንተሎ፣ ቤተልሄም በቀለ፣ ረድኤት አስረሳኸኝ እና የሲሸልሷ አሻንታ ማሪ በራሷ ላይ ቀሪዎቹን ጎሎች ለሉሲዎቹ አስቆጥረዋል። ሀገራቱ ከቀናት በፊት ባደረጉት የመጀመሪያ የወዳጅነት ጨዋታ ኢትዮጵያ 16 ለ 0 ማሸነፏ የሚታወስ ነው። በቻለው ለሜቻ የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሁለቱ ጨዋታዎች 26 ጎሎችን በማስቆጠር የበላይነቱን አሳይቷል። ብሔራዊ ቡድኑ በ2028 ኦሊምፒክ ሴቶች እግር ኳስ ማጣሪያ ከሩዋንዳ ጋር ለሚያደርጉት ጨዋታ ዝግጅት ላይ ይገኛል። የወዳጅነት ጨዋታዎቹም የዚህ ዝግጅት አካል ናቸው። ኢትዮጵያ የሁለተኛ ዙር የ2026 የሎጅ አንጀለስ ኦሊምፒክ የማጣሪያ ጨዋታዎቿን ከሩዋንዳ ጋር መስከረም መጨረሻ እና ጥቅምት ወር መግቢያ ላይ ታደርጋለች።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት ምሳሌ ሆኗል
Oct 7, 2026 135
አዲስ አበባ፤መስከረም 27/2019(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት ለሌሎች ሀገራት አርዓያ የሆነ ታላቅ ተግባር መሆኑን የዘርፉ ሙያተኞች ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፣ ታላቅ ርዕይን አንግባ በትኩረት እየሰራችባቸው ከሚገኙ ውጤታማ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች መካከል አረንጓዴ ዐሻራ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን ለመከላከል፣ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባለፉት ዓመታት በአርንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ተክላለች። የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ 1ኛ መደበኛ ስብሰባውን መካሄዱ ይታወቃል። በዚህ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ከጀመረችበት ጊዜ ጀምሮ እስካሁን 56 ቢሊዮን ችግኞችን በመትከል የተራቆቱ መሬቶችን አረንጓዴ ማልበስ ተችሏል። በተጨማሪም ይህ መርሀ ግብር የመሬት መሸርሸርን እንዲቀንስ፣ ስነ ምህዳራን መጠበቅ እንዳስቻለም መግለጻቸው ይታወሳል። በተባበሩት መንግስታት የደን ፎረም ሴክሬታሪያት ዳይሬክተር ዶክተር ጁሊያት ቢያኦ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ የደን ሽፋንን ለመጨመር የሚከናወኑ ተግባራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ጉልህ ሚና እንደሚያበረክቱም ገልጸዋል። የደን መራቆትን ለመቅረፍና የመሬት ገጽታ ለመጠበቅ መንግስት ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የዘርፉን ተዋንያን ርብርብ የሚጠይቅ መሆኑን አብራርተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብርን ነድፎ ባለፉት ዓመታት በመተግበር የአረንጓዴ ሽፋንን ለማሳደግ ያከናወነው ተግባር ውጤት ማስመዝገቡንም አክለዋል።   የአፍሪካ የደን ፎረም የደን ተመራማሪ የሆኑት ዶሪስ ሙታ (ዶ/ር) በበኩላቸው የአካባቢ ስነ ምህዳርን ለመጠበቅና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራት የመንግስትን ቁርጠኝነት የሚጠይቅ መሆኑን አንስተዋል። በመሆኑም ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ያከናወነቻቸው ውጤታማ ተግባራት ከደን ሽፋን መመናመን ጋር ተያይዞ የሚከሰት የአየር ንብረት ለውጥ መዛባትን በመከላከል በኩል ጉልህ ሚና አለው ብለዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር ያስመዘገበችው ውጤት በዘርፉ በትኩረት ከተሰራ ታሪክ መቀየር እንደሚቻል ለዓለም ጥሩ ምሳሌ እንደሚሆን ተናግረዋል። እንደ አረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር አይነት ፕሮጀክት ነድፎ መተግበር ፋይዳው አካባቢን በደን ከመሸፈን በላይ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በመሆኑም መሰል ምሳሌ የሚሆን ተግባር ሰዎች በምቹ ስነ ምህዳር እንዲኖሩ ዕድል የሚፈጥርና ምርታማነትን የሚያሳድግ አርዓያነት ያለው ተግባር እንደሆነም ነው ዶሪስ ሙታ ( ዶ/ር) የገለጹት።    
በአማራ ክልል የግሪሳ ወፍ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ነው
Oct 7, 2026 132
ባህር ዳር፤ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ በአማራ ክልል የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ ለመከላከል የኬሚካል ርጭት እየተካሔደ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው የሰብል ልማትና ጥበቃ ዳይሬክተር ማንደፍሮ አስላከ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ከነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም መጨረሻ ጀምሮ የተከሰተውን የግሪሳ ወፍ መንጋ በዘመናዊና ባህላዊ መንገድ የመከላከል ሥራ እየተሠራ ይገኛል።   በደቡብና ሰሜን ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞኖች በሚገኙ 15 ወረዳዎች የተከሰተው የግሪሳ ወፍ መንጋ በደረሰ ሰብል ላይ ጉዳት እንዳያደርስ በተቀናጀ አግባብ የመከላከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። መንጋው የማሽላ፣ የጤፍ፣ የስንዴ፣ የገብስ፣ የዳጉሳ፣ የሩዝ እና የመሳሰሉ ሰብሎችን በእሸትነት ደረጃ ፍሬውን በመብላትና በማራገፍ ጥፋት የሚያስከትል ነው። በዚህም 74 የግሪሳ ወፍ መንጋ ማደሪያ ቦታዎችን በመለየት ከመስከረም 4 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት በማከናወን አብዛኛውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ ተችሏል።   በተቀናጀ መንገድ በተካሄደ የመከላከል ሥራ ሰብሉን ሙሉ በሙሉ ከግሪሳ ወፍ ጉዳት መታደግ እንደተቻለ ነው ዳይሬክተሩ ያስገነዘቡት። አርሶ አደሩ በየእለቱ ሰብሉን አሰሳ በማድረግ ከግሪሳ ወፍ ጉዳት የመከላከል ሥራውን አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል። የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ደጀኔ ከበደ በበኩላቸው፤ መንጋው የተከሰተው በከሚሴ ከተማ አስተዳደር፣ በዳዋ ጨፋ፣ በአርጡማ ፉርሲ፣ በጅሌ እና ባቲ ወረዳዎች መሆኑን ተናግረዋል። መንጋውን በአውሮፕላን የኬሚካል ርጭት ፈጥኖ በማከናወን የመከላከል ሥራ በመሠራቱ ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነውን የግሪሳ ወፍ ማስወገድ መቻሉን ገልጸዋል። አሁንም መንጋውን የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አመልክተው፤ አርሶ አደሩም በባህላዊ መንገድ ድምፅ በማሰማት መንጋው በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት እንዳያደርስ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
አረንጓዴ ዐሻራ ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ሳቢ በማድረግ ረገድ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው
Oct 3, 2026 255
አዲስ አበባ ፤መስከረም 23/2019 (ኢዜአ)፦የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር የሀገሪቱን የአረንጓዴ ልማት ግቦች ከማሳካት ባለፈ፣ ከተሞችን ለኑሮ ምቹ እና ተስማሚ እያደረገ እንደሚገኝ የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ገለጸ። ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመገንባት በ2011 ዓ.ም በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት የጀመረችው ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ መርኃ ግብር ለአፍሪካም ሆነ ለዓለም ትልቅ አርአያ መሆን ችሏል። በዚህ ግዙፍ ሀገራዊ ተነሳሽነት አማካኝነት ባለፉት 8 ዓመታት ውስጥ 56 ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ተችሏል። በመርሃ ግብሩ የተተከሉ ችግኞች ስነ-ምህዳርን ከማስጠበቅና ከተሞችን አረንጓዴ ከማላበስ ባለፈ ለምግብነት እና ለቱሪስት መዳረሻነት ምቹ ሁኔታን ፈጥረዋል። ይህ ሁሉን አቀፍ ጥረት ሀገሪቱ የተፈጥሮ ጸጋዎቿን ጠብቃ የምግብ ሉዓላዊነቷን ለማረጋገጥ ለምታደርገው ብሩህ ጉዞ ጠንካራ እና አዲስ መሰረት ጥሏል። በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ አማን አሰፋ (ዶ/ር) ለኢዜአ እንደገለጹት፣ በከተሞች የሚካሄዱ የአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ስራዎች ከተሞች ለኑሮ ምቹ፣ ዘመናዊና ማራኪ አድርጓቸዋል። በከተሞች አካበቢ ከፍተኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መኖር እና የኢንዱስትሪ ማዕከል መሆናቸው ለከፍተኛ ካርቦን ልቀትና ብክለት ተጋላጭ ናቸው ብለዋል። በመሆኑም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ይህንን ችግር በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን አንስተዋል። በዚህም የሙቀት መጠንን በመቀነስ፣ የአካባቢ ስነ-ምህዳርን በመጠበቅ እና በከተሞች አካባቢ ጎርፍ እንዳይከሰት በመከላከል ለአየር ንብረት ለውጥ ትልቅ አዎንታዊ ድርሻ እያበረከተ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለአረንጓዴ ዐሻራ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት አዳዲስ የከተማ ፕላን አሠራር ላይ ማሻሻያ ማድረጉንም ተናግረዋል። በዚህም አዲስ የሚዘጋጁ የከተማ ፕላኖች 30 በመቶ ለአረንጓዴ ልማት፣ 30 በመቶ ለመሠረተ ልማት እና 40 በመቶው ደግሞ ለመኖሪያነት እንዲውሉ የሚያስችል ሞዳሊቲ እንዲከተሉ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በዚህ መሰረት የሚከናወኑ የከተማ ፕላን ዝግጅቶች የሀገሪቱን አረንጓዴ የልማት ግቦች ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖራቸው ተገልጿል።      
የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን እያጎለበተ ነው
Oct 1, 2026 262
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2019 (ኢዜአ) ፦የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄ የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋት ትግበራ ውጤታማነትን በማጎልበት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ገለጸ። የባለሥልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የጽዱ ኢትዮጵያ ንቅናቄ ተጨባጭ ውጤት አምጥቷል። በተለይም የከተሞችን ሁለንተናዊ ጽዳትና ውበት ከማሻሻል ባሻገር ለአካባቢ ጥበቃና ሥነ-ምኅዳር ድኅንነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም የጽዱ ኢትዮጵያ ተነሳሽነት ከተሞችን ለነዋሪዎቻቸው ዘመናዊ ምኅዳርን በማጎናጸፍ የኮሪደር፣ የወንዝ ዳርቻና መሰል ውጤታማ የልማት ሥራዎችን የሚያፋጥን አስቻይ ምኅዳር መፍጠሩን ተናግረዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣንም የሕብረተሰብ ተሳትፎን በማሳደግ የጽዱ ኢትዮጵያን ግብ የሚያሳካ የአካባቢ ጥበቃ፣ የጽዳትና ውበት ባህልን የሚያጎለብት ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እያካሄደ መሆኑን አመልክተዋል። በዚህም በመጀመሪያው ዙር "ውበት ይንቃ፤ ብክለት ይብቃ" በሚል መሪ ሀሳብ ለስድስት ወራት የብክለት ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መከናወኑን አስታውሰዋል። በሁለተኛው ዙር ደግሞ "ጽዱ ኢትዮጵያን ባህል እናድርግ" በሚል መሪ ሀሳብ የጽዳት ባህልን ማጠናከር የሚያስችል መሰረት መጣል እንደተቻለ አንስተዋል። በአሁኑ ወቅት ከሰኔ እስከ መስከረም ለ3 ወራት የሚቆይ 3ኛ ዙር ''የጽዱ ኢትዮጵያ ለትውልድ'' ሀገር አቀፍ ንቅናቄ እየተካሄደ መሆኑን አንስተዋል። በየዓመቱ የሚካሄዱት የጽዱ ኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ ንቅናቄም የማኅበረሰቡን የአካባቢ ጥበቃ ግንዛቤ በማጎልበት ተቋማት በብክለት መከላከል ላይ የድርሻቸውን እንዲወጡ እያደረገ ነው ብለዋል። መርሐ ግብሩም የአካባቢ ጥበቃ ሕግጋትና መመሪያዎችን ሙሉ በሙሉ በውጤታማነት በማስፈጸም ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን ጠቁመዋል። የተገኘውን ውጤት ይበልጥ ለማጠናከር በቀጣይም ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃን ለማረጋገጥና ብክለትን ለመከላከል የተቀናጁ የአካባቢ የጽዳትና ውበት ጥበቃ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል።    
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ያላቸውን የጋራ ውጥኖች በቁርጠኝነት ለመተግበር እንደሚሰሩ ገለጹ  
Sep 21, 2026 1015
አዲስ አበባ፤ መስከረም 10/2019 (ኢዜአ)፦ የአፍሪካ ህብረት እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሰላም፣ ኢኮኖሚና ፍትሃዊ ዓለምን ለማስፈን በጋራ እያከናወኑ የሚገኘውን ስራ ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚሰሩ አስታወቁ። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከመስከረም 8 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ በኒው ዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። “መተማመንን ዳግም መገንባት እና አዳዲስ ለውጦችን በአግባቡ መምራት፣ ለሁሉም የሚሰራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅትን መፍጠር” የጉባኤው መሪ ሀሳብ ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ለመታደም ኒው ዮርክ ይገኛሉ። ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ስትራቴጂካዊ ትብብር ማጎልበት፣ የሰላምና ደህንነት ማዕቀፎችን ማጠናከርና አፍሪካን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ሪፎርሞች ላይ ያተኮረ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄዷል። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ እና የተባበበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ መድረኩን በጋራ መርተውታል። ስብስባው ሁለቱ ተቋማት አፍሪካ መዋቅራዊ ፈተናዎችን ለመፍታት እያደረገች ያለቻቸውን ጥረቶች ለመደገፍና ፍትሃዊ የዓለም ስርዓትን ለመፍጠር ያላቸውን የጋራ ቁርጠኝነት ይበልጥ ያረጋገጠ መሆኑን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። የዓለም አቀፍ የፋይናንስ አወቃቀርን ማሻሻል፣ ዘላቂ የእዳ አስተዳደር እና የአፍሪካ ሀገራት ከቁልፍ የማዕድን ሀብቶች ይበልጥ ተጠቃሚ ማድረግ ውይይት ከተደረገባቸው አጀንዳዎች መካከል ይጠቀሳሉ። ሁለቱ ወገኖች በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ህብረት እና የተመድን ትብብር ያለውን ስትራቴጂካዊ ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተዋል። የተቋማቱ ሶስት ነባር የትብብር ማዕቀፎች በአዲስ መልክ ለማደስ እና እ.አ.አ በ2026 ትግበራው የሚጠናቀቀውን የጋራ ፍኖተ ካርታ የተፈጻሚነት ገደብ ለማራዘም መስራት እንደሚገባ ተመላክቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአፍሪካ ያሉ የሰላም እና የደህንነት ተግዳሮቶችን ለመፍታት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የአፍሪካ ህብረት ቁልፍ አጋር ሆኖ እንደሚቀጥል ዳግም አረጋግጧል። የአፍሪካን የሰላምና ደህንነት መዋቅር ማጠናከር፣ ግጭትን አስቀድሞ የመከላከል ዲፕሎማሲና የእርቅ ሂደትን በሚገባ መተግበርና ለአፍሪካ ፈተናዎች አፍሪካዊ መፍትሄዎችን ማረጋገጥ የሚያስችል በቂ አቅም መገንባት እንደሚያስፈልግ በስብሰባው ላይ ተነስቷል። በውይይቱ በሳሄል ቀጠና፣ በሊቢያ፣ በሱዳን፣ በደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ያሉ ወቅታዊ ጉዳዮችና የሰላም ጥረቶች ተገምግመዋል። በስብስባው ላይ ግጭቶች፣ በዓለም አቀፍ የአቅርቦት ሰንሰለት ላይ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች እና የባህር በር መስመሮችን መዝጋትን ጨምሮ ሌሎች ውጫዊ ሁኔታዎች በአፍሪካ ኢኮኖሚ እና ምግብ ዋስትና ላይ ተጨማሪ ጫና እየፈጠሩ መሆኑ ተነስቷል። የአየር ንብረት ለውጥ እያደረሰ ያለው ጉዳትም ምክክር ተደርጎበታል። ሁለቱ ወገኖች በውይይቶች ጠንካራ የጋራ ግብረ መልስ መስጫ ማዕቀፍ ለመፍጠር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአፍሪካ ህብረት እና ተመድ ፍኖተ ካርታ ዝግጅን ለማጠናቀቅ፣ በአፍሪካ ሀገራት የሰላም ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር፣ የምግብ ዋስትና ተግዳሮቶችን ለመፍታትና ለድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የአሰራር ማዕቀፎችን ለመቅረጽ በቅርበት እንደሚሰሩ መግለጻቸውን የአፍሪካ ህብረት መረጃ ያመለክታል። 81ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እስከ መስከረም 18 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 1092
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው።   በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 988
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 1167
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሐተታዎች
የኢትዮጵያን መሻት የሚያሳካ- የመደመር መንግሥት  
Oct 8, 2026 54
በሰውነት ጀምበሩ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ኢትዮጵያ በዘመናት መካከል በተለያዩ የመንግሥት አስተዳደር ሥርዓቶች ያለፈች ጥንታዊት ሀገር ነች። ይህ የመንግሥት ሥርዓተ ታሪክ የመሪዎችን ርዕይ፣ የሕዝቦችን አብሮነት፣ የሥልጣን ፍላጎትና የሀገር ግንባታ ሕልምን አጣምሮ የያዘ ሕያውና የዘመናት ጉዞ ነው። የኢትዮጵያ ታሪክ ከንጉሠ ነገሥቱ ፍጹማዊ ማዕከላዊነት ጀምሮ እስከ ደርግ ሶሻሊስታዊ ሙከራ፣ ከኢሕአዴግ የብሔር ፌዴራሊዝም እስከ አሁኑ ሀገር በቀል የመደመር ፍልስፍና ያለው ሂደት እያንዳንዱ ሥርዓት በሀገሪቷና በሕዝቦች ላይ የራሱን ዐሻራ አሳርፏል፤ እያሳረፈም ይገኛል። የንጉሠ ነገሥቱ ዘመን በዘመናዊ ተቋማት ግንባታና በማዕከላዊ ጠንካራ መንግሥት ምስረታ የሚታወስ ቢሆንም የሰፊውን ሕዝብ መሠረታዊ የነፃነት፣ የመሬት ባለቤትነት እና የማንነት ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ባለመቻሉ በለውጥ ማዕበል ተናግቶ በደርግ ወታደራዊ ሥርዓት ተተካ። ደርግ "መሬት ላራሹ" አዋጅን የመሳሰሉ ጅምሮችን ቢያደርግም፣ ዴሞክራሲያዊ መብቶችን በመርገጡ እና የቀይ ሽብርን አሰቃቂ ጭፍጨፋ በማካሄዱ ኢትዮጵያን ረጅም የእርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ከቷታል። ደርግ የ1987 ዓ.ም ሕገ-መንግሥት ሀገሪቱን በብሔር፣ በቋንቋና በመልክዓ ምድር ላይ በተመሠረቱ 9 ክልሎችና 2 የከተማ አስተዳደሮች በመክፈል አስተዳደራዊ መዋቅሩን ዘረጋ። ይሁን እንጂ ጠንካራ የሕዝብ አገልግሎት ፍላጎት የሚያረካ፣ ለልማትና ለዕድገት ቅድሚያ የሚሰጥ ተቋም መገንባት ተስኖት ቆይቷል። በእርግጥ የኢሕአዴግ በሕገ-መንግሥት አስተዳደር ለዘመናት ታፍነው የነበሩ ብሔሮችና ብሔረሰቦች ቋንቋቸውን እንዲያደራጁ፣ ባህላቸውን እንዲያሳድጉና አካባቢያቸውን በራሳቸው የሚያስተዳድሩበትን ዕድል ለመፍጠር ጥረት አድርጓል። ነገር ግን የፖለቲካ ምኅዳሩን አንዱን አጋር ሌላውን እህት በሚል አግላይና ከፋፋይ ስልት አስተዳደር የዘረጋው ሕወሓት መራሹ ሥርዓት በሀገሪቷ ላይ ፈላጭ ቆራጭ በመሆን ሥልጣነ መንበሩን ተቆናጦ ቆይቷል። ይህም አብዮታዊ ዴሞክራሲ ሥርዓት ሰዎችን ከሀገራዊ ዜግነታቸው ይልቅ በብሔር አጥር ውስጥ ብቻ እንዲወሰኑ አድርጎ ቆይቷል። የፖለቲካ ምኅዳሩን በመዝጋት፣ የዜጎችን መሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶች በመጨቆንና በየአካባቢው የብሔር ግጭቶች እንዲባባሱ በማድረጉ ተቃውሞ ገጠመው። አልቻለም እንጂ የሕዝብን ተቃውሞ በማፈን ለጥቂት ጊዜ ለመራመድም ሙከራ አድርጎ ነበር። ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ማዕበሉም በአራቱም አቅጣጫ ገደፉን አልፎ ኢትዮጵያ በ2010 ዓ.ም ለውጥን አምጣ ወልዳለች። ይህ ለውጥ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የሚመራውን የመደመር መንግሥትን እንዲተዋወቅ አድርጓል። ይህ በሀገር በቀል ዕውቀት የሚመራው የመደመር መንግሥት ስብራቶችን የመጠገንና አዲስ አቅጣጫ የመቀየስ ባሕሪ የነበሩ ጭቆናዎችን በማስቀረት፣ የፖለቲካ ምኅዳሩን በመቀየር አጋርና ዋና የሚለውን ሥርዓት በማስቀረት ሁሉም ዜጋ በሀገሩ ላይ የመወሰንና የመጠቀም መብትን የሚያጎናጽፍ ሥርዓት ፈጥሯል። ዛሬ "መደመር" የሚለውን ሀገራዊ ፍልስፍና መሪ ፍኖት አድርጎ በመውሰድ የመደመር ዕይታ እያሰረጸ መልካም ነገሮችን ማስቀጠል፣ የተበላሹትን ማረምና አዳዲስ የጎደሉ ነገሮችን ማሟላትን እንደ ዋና መርህ አድርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የመደመርን አስተሳሰብ ሲያብራሩ "መደመር ማለት ያለንን መልካም ነገር አቀናጅተን፣ የጎደለንን ሞልተን፣ የተበላሸውን አርመን ወደፊት መራመድ ነው። በጽንፈኝነትና በከፋፋይ ፖለቲካ ሀገር አትገነባም። ኢትዮጵያ ሁላችንንም አቅፋ የምትይዝ ሀገር ናት" ብለዋል። መጋቢት 24 ቀን 2010 ዓ.ም የለውጥ መንግሥት ኢትዮጵያን ከተረከበ ወዲህ ባለፉት ስምንት ዓመታት በኢትዮጵያ በርካታ ማሻሻያዎችን በማድረግ ሁሉን አቀፍ ለውጦች አስመዝግቧል። ለአብነት ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያዎችን በማድረግ ኢኮኖሚው ከነበረበት ስብራት የሚያገግምበትን ዕድል ፈጥሯል። ይህም ግብርና መር የነበረውን የኢኮኖሚ ሥርዓት ወደ ብዝኅ የኢኮኖሚ ልማት አቅጣጫን በመቀየስ በርካታ ለውጦችን አስመዝግቧል። ባለፉት ዓመታት በርካታ ሀገራዊ ንቅናቄዎች በመተግበር በየዘርፉ እመርታዊ ውጤቶች የሚመዘገብበትን መንገድ ቀይሷል። ይህም ከገበታ ለሸገር ጀምሮ ገበታ ለሀገር፣ ገበታ ለትውልድ በሚል የተፈጠሩ ንቅናቄዎች የቱሪስት መስህቦችና መዳረሻዎችን በማስፋፋትና በማደስ ኢትዮጵያን የቱሪዝም ማዕከል እያደረጋት ይገኛል። ዜጎች የተትረፈረፈና የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ የሚያስችል የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር ተግባራዊ በማድረግ ብዙዎች ተጠቃሚ ሆነዋል። ከራሳቸው አልፎም ለገበያ በማቅረብ ትሩፋታቸውን አጋርተዋል። በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል፣ በዲጂታል ኢትዮጵያ፣ በመሶብ የአንድ ማዕከልና ሌሎችም የተጀመሩ ንቅናቄዎች በርካታ ለውጦችን መመዝገብ ችለዋል። ለውጡ ኢኮኖሚያዊ ለውጦችን ብቻ ሳይሆን የፖለቲካ ፓርቲዎችን ስም ከተቃዋሚነት ወደ ተፎካካሪነት በመቀየር በፖለቲካው መስክ ሁሉም እኩል እንዲሳተፍ በማድረግ የፖለቲካ ምኅዳሩን አስፍቷል። በዚህም ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በሀገር ጉዳይ ላይ እኩል የሚሳተፉበትን አውድ ፈጥሯል። ለዚህም ነው በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ በርካታ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ሰላማዊና የተረጋጋ ተሳትፎ ያደረጉት። ሕዝብ የሰጣቸውን ድምፅ ተቀብለው ለሀገር መጽናት በአብላጫ ድምፅ ካገኘው ፓርቲ ጋር በጋራ ለመሥራት ጽኑ አቋማቸውን በመግለጽ በኢትዮጵያ ታሪክ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ አርዓያ የሚሆን ገድል የፈጸሙት። በሀገር ደረጃ የተመዘገቡትን ድንቅ ለውጦች በጥሞና የተመለከተው ሕዝብ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለብልፅግና ፓርቲ ድምፅ በመስጠት አድናቆቱን ገልጿል፤ ተግባሩንም እንዲቀጥል አደራ ሰጥቷል። በሰባተኛው ሀገራዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ የሕዝብ ተወካዮችን ምክር ቤት 428 ወንበሮችን በማሸነፍ ቀሪዎችን ደግሞ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ድምፅ አግኝተው ምክር ቤት ገብተዋል። ከአብላጫው ሕዝብ ድምፅ ያገኘውና አደራውን የተቀበለው ብልፅግና በጠንካራ መንፈስ፣ በጸና አደራ የመደመር መንግሥትን መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም በይፋ መስርቷል። ምክር ቤቱም በአካሄደው ስብሰባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን (ዶ/ር) ለሁለተኛ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ለሁለተኛ ጊዜ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሰየሙበት ወቅት እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ሥርዓትን የመገንባት ሙከራዎች የቁጭት ችግር ባይኖርባቸውም የእፎይታና የስክነት ችግር ይስተዋልባቸው ነበር። ባለፉት ዓመታት የሌሎችን ተሞክሮ ከራሳችን ጋር ስናስማማ ቆይተናል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር)፤ መደመር የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማሰቢያ ቋንቋ መሆን እንደሚችል አረጋግጠናል ብለዋል። አዲሱ የመደመር መንግሥት መጪውን ዘመን ታሳቢ ያደረገ የፌዴራል መንግሥት አስፈጻሚ አካላት ስያሜ፣ አደረጃጀት፣ ሥልጣንና ተግባር በመቀየር በምክር ቤቱ አዋጅ እንዲጸድቅ አድርጓል። የአዋጁ መውጣትና ተግባራዊ መሆን የተቋማትን የማስፈጸም አቅም ያጎለብታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመደመር መንግሥት የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን አቅርበው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያሾሙ እንደገለጹት፤ ትምህርት ብቻውን የመፈጸም አቅምን ሊተካ ስለማይችል፣ የተማሩ ነገር ግን ተግባር ላይ ውጤት የማስመዝገብ፣ የመከታተልና ከፍተኛ ዲሲፕሊን ያላቸውን ግለሰቦች ማጣጣም ላይ ትኩረት ተደርጓል ብለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደገለጹት የአሁኑ ሹመት ከመቼውም ጊዜ በተለየ መልክ ከባድ ኃላፊነት ነው። ሌት ተቀን በመሥራት የሕዝብን ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ለውጡ በእያንዳንዱ ሰው ዘንድ ጥቅም የሚያስከትል መሆኑን የማረጋገጥ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል። ይህ ሲታይ የመደመር መንግሥት ተሿሚዎቹ ኃላፊነቱን ለመወጣት እንደሚችሉ በተሰማሩበት የሥራ መስክ የተሻለ አፈጻጸምና ውጤት ያስመዘገቡ አካላት በሥራ ልምዳቸው ተመዝነዋል። የመደመር መንግሥት ተሿሚዎችም በመጪዎቹ አምስት ዓመታት በርካታ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ከፍተኛ ጥረትና ሩጫ የሚጠይቅ በመሆኑ ያንን ኃላፊነት ለመወጣት የሚያስችል አቅም ያላቸው መሆኑ በሚገባ ተፈትሿል። በዚህም በምርጫው ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፅ በመስጠት የሰጡትን ታላቅ አደራና የመንግሥትን ቁመና የማጠናከር ፍላጎት ለመሸከም ዝግጁ የሆኑ ሙስናን የሚጸየፉና ሕዝብን ማገልገል እንደ ታላቅ ጸጋ የሚቆጥሩ መሆናቸው በጠቅላይ ሚኒስትሩም በምክር ቤት አባላትም ታምኖባቸዋል። ይህ አዲስ አደረጃጀትም የኢትዮጵያን የማንሰራራት ጉዞ እውን ለማድረግ የሚረዳ ፍኖት ነው። ነገር ግን ይህ የመንግሥት አደረጃጀት እንደ ሀገር የታሰበውን ሀገራዊ ዓላማ ማሳካት እንዲችል ሁሉም የማኅበረሰብ አካል በየተሰማራበት መስክ መትጋት ይገባል። ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ የመንግሥትን የትኩረት አቅጣጫ ለሁለቱም ምክር ቤቶች ባቀረቡበት ወቅት፤ የኢትዮጵያን ሰላም ለማጽናትና ልማትን ለማረጋገጥ ሁሉም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። እናም የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገትና ብልፅግና ለማረጋገጥ በሚደረገው ሀገራዊ ጥረት የበኩላችንን ኃላፊነት እንወጣ- መልዕክታችን ነው።
ገቢር-ነበብ ዲፕሎማሲ፤ የመደመር መንግሥት ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ መርህ
Oct 8, 2026 56
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ ፣ ታላቅ ርዕይ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲዋ አንድ ጉልህ ለውጥ- ዲፕሎማሲው ከምላሽ ሰጪ አቀራረብ ወደ ገቢር ነበብነት፣ ተሳታፊና ሀገራዊ ጥቅምን በግልጽ ወደሚያስቀምጥ አቅጣጫ ተሸጋግሯል። የመደመር መንግሥት የውጭ ግንኙነት አቀራረብ የሀገሪቱን ጥቅም ከጎረቤት ሀገራት ጥቅም፣ ከቀጣናዊ ሰላም፣ ከአህጉራዊ ትብብርና ከዓለም አቀፍ አጋርነት ጋር በማስተሳሰር የሚጓዝ ነው። ይህም ሀገራዊ ጥቅምን መተው ሳይሆን፣ የራስን ጥቅም ከሌሎች ጋር በሚያጣጥም መንገድ ማሳካትን የሚያስችል የጋራ ተጠቃሚነት አስተሳሰብ ነው። 👉ቅድሚያ ለጎረቤት፤ የጋራ ጥቅም የዲፕሎማሲው መሠረት የኢትዮጵያ የውጭ ፖሊሲ ግንኙነት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት በቀዳሚነት ማስቀመጡ የዲፕሎማሲው አንዱ ጉልህ መገለጫ ነው። በአፍሪካ ቀንድ ያለው የሰላምና ደህንነት ሁኔታ፣ የንግድ ትስስር፣ የህዝብ እንቅስቃሴ፣ የውሃና የኃይል ሀብት፣ የመሠረተ ልማት ትስስርና የባህር መዳረሻ ጉዳዮች በአንድ ሀገር ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ አይደሉም። ስለዚህም ነው የመደመር መንግሥት የጎረቤት ፖሊሲ ሀገራዊ ጥቅምን ከቀጠናዊ ጥቅም ጋር በማጣመር እያስኬደው የሚገኘው። ይህም የጎረቤት ሀገር መረጋጋት ለኢትዮጵያ መረጋጋት፣ የጎረቤት ኢኮኖሚ መጠናከርም ለኢትዮጵያ ንግድና ኢኮኖሚ እድል ነው ከሚለው አስተሳሰብ ይነሳል። ይህንኑ አቅጣጫ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመጀመሪያ ዓመት የሥራ ዘመን መጀመሪያ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሲናገሩ ኢትዮጵያ በሁለትዮሽና በባለብዙ ወገን ግንኙነቶች ብሔራዊ ጥቅሟን መሠረት አድርጋ እንደምትሰራ ነው የገለጹት። በዚህም ጎረቤት ሀገራት በተፈጥሮ የተገናኙ ወዳጆች መሆናቸውን ጠቅሰው፣ ከሁሉም ጋር በሰላም፣ በጋራ ጥቅምና በትብብር የመስራት መርህን እንደሚያስቀጥሉ ነው የገለጹት። 👉የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይ፤ ሀገራዊ ጥቅም በዲፕሎማሲያዊ መንገድ የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት ጥያቄ ጉዳይ የሀገሪቷ የውጭ ፖሊሲ ከሚያተኩርባቸው ዋነኛ አጀንዳዎች አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ያላት ሀገር እንደመሆኗ፣ ከዓለም ገበያ ጋር ያላትን የንግድ ትስስር ለማስፋትና የሎጂስቲክስ ወጪዎችን ለመቀነስ የባህር መዳረሻ የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ጥቅም በማድረግ በትኩረት እየሰራችበት ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እንደሚገልጹት የመደመር መንግስት የኢትዮጵያ ስልጣኔ ያለ ባህር በር እውን ሊሆን እንደማይችል እና በሰጥቶ መቀበል መርህ ሀገሪቷ ወጥቶ መግቢያ በር እንዲኖራት እየሰራ ይገኛል። ይህም ጉዳዩን ከጎረቤት ሀገራት ሉዓላዊነትና ከቀጣናዊ ሰላም ጋር በማጣጣም በድርድርና በጋራ ጥቅም መርህ መፍትሔ ለመፈለግ ያለውን አቅጣጫ ያሳያል። የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ቁመና በሁለትዮሽ ግንኙነት ብቻ የሚወሰን አይደለም። አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ በአህጉራዊ የፖለቲካ፣ የሰላም፣ የደህንነትና የልማት አጀንዳዎች ላይ ለኢትዮጵያ ልዩ የዲፕሎማሲ ቦታ ይሰጣታል። በአፍሪካ ህብረት ያላት ተሳትፎም አህጉራዊ ትብብርን ከሀገራዊ ጥቅም ጋር ለማጣመር የሚያስችል መድረክ ነው። ይህም የመደመር እሳቤን ከሀገራዊ ድንበር አልፎ አፍሪካዊ ትብብርን እንደ የጋራ ልማትና ተጠቃሚነት መሠረት የሚመለከት መሆኑን ያሳያል። ኢትዮጵያ ከጃንዩወሪ 1 ቀን 2024 ጀምሮ የብሪክስ ሙሉ አባል መሆኗ በውጭ ግንኙነቷ የተጨመረ አዲስ የዲፕሎማሲ መድረክ ነው። አባልነቱ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ፣ ከእስያ፣ ከገልፍና ከሌሎች የግሎባል ሳውዝ ሀገራት ጋር ያላትን ትብብር ለማጠናከርና የዲፕሎማሲ አማራጮቿን ለማስፋት ዕድል ፈጥሯል። ብሪክስ ከኢኮኖሚና ከፋይናንስ ትብብር ባሻገር በዓለም አቀፍ ተቋማት ማሻሻያ፣ በደቡብ ደቡብ ትስስር ድምፅ መጠናከርና በብዙ ወገን ትብብር ዙሪያ የሚካሄዱ ውይይቶች መድረክ በመሆኑ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ አማራጭ ይፈጥራል። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ከጎረቤትና ከአፍሪካ ደረጃ ባሻገር ከቻይና፣ ከህንድ፣ ከሩሲያ፣ ከቱርክ፣ ከገልፍ ሀገራት፣ ከአውሮፓና ከሌሎች የዓለም ሀገራት ጋር ያላትን ግንኙነት እያሰፋች ትገኛለች። ግንኙነቱም በፖለቲካዊ ውይይት ብቻ ሳይወሰን ኢንቨስትመንት፣ ንግድ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኃይል፣ መሠረተ ልማትና የሰው ኃይል ልማትን ያካትታል። ይህ አቀራረብ ዲፕሎማሲው የውጭ ፖሊሲ ግቦችን ብቻ ሳይሆን የልማት ፍላጎቶችንም የሚያገለግል መሣሪያ እየሆነ መምጣቱን የሚያሳይ ነው። በዚህም የዲፕሎማሲ ስኬት በተፈረሙ ስምምነቶች ብዛት ብቻ ሳይሆን፣ በሚፈጠሩ የኢኮኖሚ እድሎች፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ፍሰት፣ የቴክኖሎጂ ሽግግርና የልማት ትብብር የሚመዘን ነው። በአጠቃላይ የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ጉዞ ሀገሪቱ የውጭ ግንኙነቷን ከሀገራዊ ጥቅም ጋር አጥብቃ በማስተሳሰር የዲፕሎማሲ አማራጮቿን እያሰፋች መምጣቷን ያሳያል። ከጎረቤት ሀገራት ጋር የጋራ ጥቅምን መሠረት ማድረግ፣ የባህር በር ባለቤትነት ጉዳይን በድርድር ለመፍታት መስመር መክፈት፣ በአፍሪካ ህብረት ተሳትፎን ማጠናከር፣ በብሪክስ መሳተፍና ከተለያዩ የዓለም ኃይሎች ጋር ግንኙነትን ማስፋት የዚህ አቅጣጫ ዋና መገለጫዎች ናቸው። የዛሬው የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ቁመና ከጎረቤት ግንኙነት ወደ ቀጣናዊ ፖለቲካል ኢኮኖሚ ትብብር፣ ከአህጉራዊ ተሳትፎ ወደ ዓለም አቀፍ የባለ ብዙ ወገን መድረኮች የሚዘልቅ ሰፊ አውታር እየገነባች መምጣቷ እውን ነው። የዚህ ጉዞ ዋና ገፅታም ሀገራዊ ጥቅምን በግልጽ ማስቀመጥ፣ የጎረቤቶችን ጥቅምና ሉዓላዊነት ማክበር፣ የቀጣናውን ሰላም ከሀገራዊ ጥቅም ጋር ማስተሳሰርና በተለያዩ የዓለም ዲፕሎማሲ መድረኮች ተሳትፎን ማስፋት ነው። በዚህ አንፃር የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ቁመና በገቢር ነበብ ዲፕሎማሲ እንዲሁም ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም እያስቀመጠች ከጎረቤት፣ ከአህጉርና ከዓለም ጋር የጋራ ጥቅም የሚፈጥር የዲፕሎማሲ መስመር እየገነባች መሆኗን የሚያሳይ አቅጣጫ ሆኗል።
የሀገር ሃብትን መግለጥ - ልማትን ማሳለጥ
Oct 8, 2026 66
የአባይ መነሻ፣ የዓለም የዲፕሎማሲ መናገሻ የሆነችው ታላቋ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ፣ የታሪክ፣ የባህልና ቅርስ ሃብታም ሀገር ነች። ኢትዮጵያ ገና ብዙ ተገልጠው ያላለቁ እምቅ ሃብቶች ያሏት በመሆኑ ሃብቷን የመለየትና የማወቅ፣ የመጠበቅ፣ የማልማትና ለህዝብ ጥቅም የማዋል ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል። እምቅ የሀገር ሀብቶችን አልምቶ ከመጠቀም ባሻገር የልማት አቅሞችን በመለየት ወደ ኢኮኖሚ ዕድል የመቀየር ሂደትም ቀጥሏል። የሀገርን እምቅ ሃብቶች በመግለጥ በተደመረ አቅም በማልማት ረገድ የመደመር መንግሥት ባለፉት ዓመታት አስደናቂ ተግባራትን ፈፅሞ ውጤትም ማምጣቱ ይታወቃል። በህዝብ ይሁንታ ሌላ የመምራት እድል የተሰጠው የመደመር መንግሥት የማልማትና ህዝብን ተጠቃሚ የማድረግ ጥረቱ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል። የተፈጥሮ ሀብቶች፣ የታሪክና የሥልጣኔ አሻራዎች፣ የባህልና የሃይማኖት ቅርሶችና ሌሎችም የኢትዮጵያ የቱሪዝም አቅሞች ሆነው የሚቀጥሉ ይሆናል። ከባሌ ተራሮች እስከ ኤርታሌ፣ ከአዋሽ እስከ አልጣሽ ብሔራዊ ፓርኮች፣ የጣና ሀይቅን ጨምሮ ሌሎችንም ባክነውና ተደብቀው የቆዩ ሃብቶችን በማልማት ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህን ሀብቶች ማልማት ማለት ቱሪስቶችን ብቻ መሳብ አይደለም። መንገድን ማሻሻል፣ መሠረተ ልማትን ማስፋፋት፣ የመስተንግዶ አቅምን ማሳደግ፣ ለአካባቢው ማህበረሰብ የሥራና የገቢ ዕድል መፍጠር እና የተፈጥሮና የባህል ሀብቶችን መጠበቅ ጭምር ነው። በመሆኑም የቱሪዝም ልማት ሀገርን ለዓለም ከማስተዋወቅ ባሻገር የሃብት ምንጭ ሆኖ እያገለገለ ይገኛል። የሀገርን እምቅ አቅም በመግለጥ ከተሞችና ገጠርን በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር ህዝቡ እንዲጠቀም እየተደረገ ነው። ይህ ደግሞ በአንድ በኩል ሀገርን ይበልጥ ያስተሳስራል፤ በሌላ በኩል ደግሞ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴን የሚያፋጥን ይሆናል። በመሆኑም የመደመር መንግስት እነዚህን መልካም ጅምሮች አጠናክሮ በመቀጠል የሀገርን ልማት እድገትና ማንሰራራት ማስቀጠል ይጠበቅበታል። የመደመር መንግሥት አቅዶ መሥራት፣ ጀምሮ ማጠናቀቅና ለህዝብ አገልግሎት ማብቃት የሚለውን የሥራ ባህል ይበልጥ ማጠናከርም ይኖርበታል። በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለኢትዮጵያ ያልተገለጡ አቅሞችን የማሳየት፣ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን የማላቅና የማጠናቀቅ ዘመን እንደሚሆንም ይጠበቃል። የሀገሪቱ የልማት ፍላጎት ሰፊ በመሆኑ አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በመጀመር በጥራትና በፍጥነት የማከናወን እንዲሁም ቀደም ሲል የተጀመሩትን በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ማብቃት ይገባል። የመንግሥት የሥራ አፈጻጸም ከ“ምን ታቀደ?” ወደ “ምን ተጠናቀቀ?” እና “ለህዝብ ምን ጥቅም አመጣ?” በሚል የውጤት መለኪያ መሰረት መቀጠል አለበት። ኢትዮጵያ ብዙ ያልተገለጠ ሀብት ያላት ሀገር ናት፤ አሁን ላይ ሃብት አለን ወይ? የሚለው ሳይሆን፣ ያለንን ሃብት በምን ፍጥነት፣ በምን ጥራትና በምን ዓይነት ልማት የጋራ ጥቅም ላይ እናውለው? የሚለው ነው፤ ለዚህም የመደመር መንግሥት በጠንካራና ቀጣይነት ባለው ልማት ምላሽ መስጠቱን የሚቀጥል ይሆናል።
የወል ትርክት ግንባታ ለጠንካራና ህብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግስት መሰረት
Oct 8, 2026 67
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ ወቅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፡ ለሕብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ የሆነው የወል ትርክት ተገቢው ትኩረት እንደሚሰጠው ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም፣ ወንድማማችነት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ለማድረግ ጠንካራ ሕብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት መገንባት ወሳኝ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ለዚህ ደግሞ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎችን የሚያስተሳስርና የጋራ እሴቶችን የሚያጎላ የወል ትርክት የመገንባት ሥራ ቀዳሚው እና ዋነኛው መሠረት ነው። የመደመር መንግሥት አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር፣ የሀገራዊ ምክክር ሂደትን እውን ለማድረግ እንዲሁም አዲስ የፖለቲካ ባህል ለመገንባት የወሰዳቸው እርምጃዎች የወል ትርክትን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም ያለሙ ናቸው። ይህም የሕዝቦችን የጋራ ፍላጎት በማቀናጀትና የፍትሐዊ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የሰላም ግንባታ ዕድሎችን ለማስፋፋት የላቀ ድርሻ እያበረከተ ይገኛል። በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተካሄደው ሀገራዊ ምክክሩ የመላው የኢትዮጵያ ዜጎችን ሐሳብና ድምፅ በአንድነት ያሰባሰበ መድረክ በመሆኑ፣ በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የባለቤትነትና "የያገባኛል" መንፈስ እንዲጎለብት ማስቻሉን መመልከት ተችሏል። ሁሉም የማኅበረሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት በዚህ ሂደት፣ የጋራ እሴቶችን በማጎልበት ረገድ አዎንታዊ ምዕራፍ ተከፍቷል። ከዚሁ ጎን ለጎን፣ አሳታፊና አካታች የፖለቲካ ምኅዳር ለመፍጠር የተወሰዱት አዎንታዊ እርምጃዎች የጋራ አስተሳሰብንና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታን የሚያጠናክሩ ናቸው። ይህም የኢትዮጵያን የነገ ጉዞ በተስተካከለ መንገድ ለመምራትና የጋራ የወል ትርክትን በጽኑ መሠረት ላይ ለመገንባት የሚያስችል አቅም ፈጥሯል። የወል ትርክት ግንባታ በባዶ መሬት ላይ የሚከናወን ሳይሆን፣ ኢትዮጵያውያን በታሪካቸው ያበለጸጉዋቸውን አሰባሳቢ እሴቶች መሠረት ያደረገ ነው። የሕዝቦችን አብሮነት የሚያጠናክሩ የአደባባይ፣ ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ በዓላት፤ እንዲሁም በየዓመቱ የሚከበረው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በዓል ማኅበረሰቡን አብሮነት በማጠናከር ረገድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸው። በተጨማሪም በሀገሪቱ ታሪክ ውስጥ የጋራ ኩራትና የነፃነት ምልክት የሆነው የዓድዋ ድል፣ መላው የኢትዮጵያ ሕዝቦች በአንድነት ቆመው ያሸነፉበትና የጋራ ማንነታቸውን ያረጋገጡበት አሰባሳቢ ትርክት ነው። በዘመናዊው ምዕራፍ ደግሞ የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት የሁሉም ኢትዮጵያውያን ንቁ ተሳትፎ፣ ሀብትና ዕውቀት የፈሰሰበት ታላቅ የጋራ ስኬት በመሆኑ የወል ትርክት ግንባታ ሌላው ማሳያና መሠረት ሆኖ ያገለግላል። እነዚህ እሴቶችና ስኬቶች የሕብረተሰቡን አብሮነት በማጠናከር ለሕብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ የሚኖራቸውን አዎንታዊ ሚና ማጎልበት ተችሏል። መንግሥት ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ ከኢኮኖሚ ማጠናከር ባለፈ ለወል ትርክት ግንባታ መጠናከር ጉልህ አስተዋፅኦ እንዲኖረው ታስቦ የተቃኘ ነው። የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ስኬታማነት ለኢትዮጵያ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ እና ታላቅ ርዕይ እውን መሆን የላቀ ሚና ይጫወታል። በገንዘብ ፖሊሲዎች ማሻሻያ አማካኝነት የዕዳ ጫናን መቀነስ፣ የዋጋ ንረትን ማረጋጋትና ገቢን ማሳደግ መቻሉ የዜጎችን እኩል የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ያረጋግጣል። በተለይም በግብርናው ዘርፍ በተካሄደው የልማት እመርታ፣ በበጋ መስኖ ስንዴ አምራችነት ራስን የመቻል ስኬት እና የሰብል ክላስተር እርሻዎች የምግብ ሉዓላዊነትን በማረጋገጥ የሕዝብን ድህነት የመቀነስና የሀገር አቅምን የማሳደግ ሕልምን እውን አድርገዋል። ዜጎች በልማት ሂደቱ እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ ሲሆኑ ለሀገራዊ እድገት የሚያደርጉት አስተዋፅኦ እያደገ የሚሄድ በመሆኑ፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያው የወል ትርክትን በተግባር ለማጠናከር አስተማማኝ መንገድ ሆኗል። በአጠቃላይ የወል ትርክትን ማጎልበትና ማጠናከር ለጠንካራ ሕብረ ብሔራዊ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ምሦሶ ነው። አሰባሳቢ ታሪካዊ እሴቶችን ከመፍጠር ባሻገር፣ አካታች የፖለቲካ ምኅዳርን ማስፋፋት፣ የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ማጠናከር እና የሕዝብን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የኢኮኖሚ ሪፎርሞችን ማስቀጠል የወል ትርክትን እውን የማድረጉ ሂደት አካላት ናቸው። በመሆኑም የወል ትርክት ግንባታን ማጎልበት የሀገርን ዘላቂ ሰላም፣ አንድነትና ብልጽግና የሚያረጋግጥ ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ ሂደት ነው።
ትንታኔዎች
የመደመር መንግሥት የማይታለፍ ቀይ መስመር - ሙስና ሌብነትና የወገንተኝነት አሰራር!!
Oct 8, 2026 65
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ ሙስና፣ ሌብነትና ወገንተኝነት የሀገርን ዕድገትና ብልፅግና ያኮሰምናል። የዜጎችን ፍትሐዊና ግልጸኝነት የሰፈነበት የአስተዳደር ሥርዓት መሻት የሚገዳደር የልማት ጠንቅም ነው። ለዚህም ነው የመደመር መንግሥት ጠንካራ አቋም የያዘው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ7ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ላይ ዳግም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በተሰየሙበት ወቅት፤ ሙስናን፣ ሌብነትን፣ የዘመድ አሰራርንና ወገንተኝነትን ለማስወገድ መንግሥት መራር እርምጃዎችን እንደሚወስድ አስምረውበታዋል። ይህ የመደመር መንግሥት ግልጽ አቋም ሌብነትና ሙስና የማይታለፍ ቀይ መስመር መሆኑን ያሳያል። መልዕክቱም የመንግሥት ተቋማት አገልግሎቶችን በማዘመን ብልሹ አሰራርን ለመግታትና ለሙስና መንስኤ የሆኑ ክፍተቶችን ለመዝጋት ትኩረት እንደሚሰጡ ያመላክታል። ይህም ለዜጎች ተስፋ፣ ለሙሰኞች ደግሞ መርዶን የሚያሰማ ጥብቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ነው። አንድ ዜጋ የመንግሥት አገልግሎት ሲፈልግ ከቢሮ ቢሮ መዞር፣ ረጅም ወረፋ መጠበቅ፣ የግለሰብ ግንኙነትን ማማተርም ሆነ ተገቢ ያልሆነ ክፍያ መጠየቅ የለበትም። የመንግሥት አገልግሎት አሰጣጥ እንዝህላልነት ሙስናን፣ ወገንተኝነትንና የዘመድ አዝማድ አሰራርን ያበረታታሉ። የፌዴራል ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ያወጣው የሦስተኛው ብሔራዊ የሙስና ግንዛቤ ጥናትም በሙስና፣ በሌብነትና በብልሹ አሰራር ላይ ተከታታይና መራር እርምጃ የመውሰድ አስፈላጊነትን ያመላክታል። የመደመር መንግሥት ይህን ክፍተት ለመዝጋት የዲጂታል አብዮትን እንደ ዋና መሣሪያ የሚጠቀም ዘመናዊ የአገልግሎት ምኅዳር እየፈጠረ ይገኛል። ለዚህም መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ሥርዓት ተጨባጭ አብነት ነው። የተቋማት አገልግሎቶች በአንድ ማዕከል መቅረባቸው ዜጎች ከቢሮ ቢሮ መዞር ሳይጠበቅባቸው የአገልግሎት ሂደቱን ግልጽና ፈጣን ያደርገዋል። በፌዴራል ደረጃ የተጀመረው የመሶብ አንድ ማዕከል የዲጂታል አገልግሎት ምኅዳርም አሁን ላይ የተደራሽነት አድማሱን አስፍቷል። ለአብነትም በአዲስ አበባ በ2018 ዓ.ም ብቻ በ11 ክፍለ ከተሞች የመሶብ የዲጂታል አገልግሎት ማዕከላት ወደሥራ ገብተዋል። አሁን ይህ ሥርዓት ወደ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች እየተስፋፋ ይገኛል። ከዚህም በላይ በተንቀሳቃሽና በእጅ ስልክ መተግበሪያ የተቀናጀ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ዜጎች በቤታቸውና በአቅራቢያቸው እንዲገለገሉ አስችሏል። የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያም የዚህ ጉዞ ወሳኙ አካል ሆኗል። አንድ ሰው አንድ ነው በሚል የተጀመረው መርሃ ግብሩም የግለሰብን የዲጂታል መለያ በማረጋገጥ የሐሰት ሰነድና የማጭበርበር ዕድልን በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። የተቀናጀና የተናበበ አገልግሎትን ለዜጎች በመስጠትም ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ማስገኘቱን ቀጥሏል። የዲጂታላይዜሽን ጉዞው የመንግሥት አገልግሎትን ከግለሰብ ተጽዕኖ ነፃ እንዲሆን አድርጓል። የዲጂታል አገልግሎቶች ግልጽነትን በማስፈን ተጠያቂነትን እያረጋግጡ ነው። የዲጂታል ግብይትና ክፍያ ሥርዓት መስፋፋቱም ተመሳሳይ፣ ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት ምኅዳር ዕድልን ፈጥሯል። የገንዘብ ዝውውርና እንቅስቃሴ የግብይት ሥርዓት ከእጅ ንክኪ በጸዳ ቁጥር የሙሰኞችን ሸምቀቆ በማጥበቅ ተጋላጭነትን መቀነስ ያስችላል። ይህም የመደመር መንግሥት የዲጂታል አብዮት አንዱ ተጨባጭ እመርታ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መክፈቻ ሥነ-ስርዓት ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት፤ የተጀመረውን የሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም በማጠናከር የአገልግሎት አሰጣጥን የበለጠ ለማዘመን ትኩረት ይሰጣል። ብቃት ላይ የተመሠረተ የሥራ መመዘኛና የአፈጻጸም ክትትልም ሙስና፣ ሌብነት፣ የዘመድ አሰራርና ወገንተኝነትን የሚያከስም ሁነኛ መሠረት ነው። እነዚህ እርምጃዎችም የመደመር መንግሥት ሙስናን ከወንጀለኛ መቅጣት ባሻገር ሌብነት እንዳይፈጠር የሚያደርግ ሥርዓት ለመገንባት የሚያከናውነውን ተከታታይ ተግባር ያመላክታል። ይህን ቁርጠኝነት ወደ ተግባር ለመቀየርም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር የሚመራ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ተከታታይ ሥራ እየሰራ ይገኛል። ኮሚቴው የሙስና፣ የሌብነትና የወገንተኝነት ትግልን በተቀናጀና በተጠናከረ መልኩ በመምራት በሌብነት ላይ የሚወሰደውን መራር እርምጃ በሥርዓት እያስፈጸመ ነው። መራር እርምጃው ቃል ብቻ ሳይሆን ተቋማዊ ለውጥ መሆን አለበት። የፀረ-ሙስና ተቋማት አቅም፣ የሲቪል ሰርቪስ ብቃት፣ የዲጂታል አገልግሎት ስፋት፣ የመንግሥት ግዥ ግልጽነትና የፕሮጀክት ክትትል በአንድ ላይ ሲሰናሰሉ የሚለካ ውጤት ይመጣል። የመደመር መንግሥት ጽኑ ፍላጎትም ለዜጎች ያለአንዳች እጅ መንሻና ብልሹ አሰራር የመንግሥት አገልግሎት ማስገኘት ነው። ዜጎች በየቀኑ በመንግሥት ተቋማት የሚያገኙት ፍትሐዊና ግልጽ አገልግሎትም ሌብነትን የሚያደርቅ እውነተኛ መለኪያ ይሆናል። ትልቅ ሀገርና ትልቅ ሕዝብን የሚመጥን ታላቅ ርዕይ ለሰነቀችው ኢትዮጵያ ርዕይን በተግባር የሚያስፈጽም ታማኝ፣ ብቁ፣ ግልጽና ተጠያቂ ተቋም እየተገነባ ነው። የመደመር መንግሥት ሙስና፣ ሌብነትና ወገንተኝነትን የማይታለፍ ቀይ መስመር አድርጎ መበየኑም የሀገርንና የሕዝብን ሀብት ለተፈለገው ዓላማ ለማዋል ካለው ቁርጠኛ አቋም ይመነጫል። የፍትሐዊ የመንግሥት አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትም ለዜጎች ተስፋን፣ ለሌቦች ደግሞ መርዶን የሚያውጅ ጥብቅ የማስጠንቀቂያ ደወል ሆኗል። የሌብነት ቀይ መስመርነትም የሕዝብና መንግስትን መተማመን በማጎልበት የኢትዮጵያን መሻት በማላቅ ዕድገትና ብልፅግና ለማሳለጥ ተስፋን የፈነጠቀ ቀጣይነት ያለው ሥራ ሆኗል።
የትምህርት ጥራት - የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ችቦ የትውልድ ብሩህ ፋና
Oct 8, 2026 47
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሰባተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአንደኛ ዓመት የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ መመሥረቻ አንደኛ መደበኛ ስብሰባውን ባካሄደበት ወቅት፤ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በድጋሚ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር በማድረግ ሰይሟል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የትምህርት ጥራት የበለጠ በማስቀጠል የኢትዮጵያን ስልጣኔ የሚገነባውን ትውልድ ለመፍጠር አበክረን እንሰራለን፤ ህብረተሰቡ በሞራል፣ በእሴት፣ በክህሎት እንዲሁም በሀገራት ስሜት የሚታነጽበት መንገድ እንከተላለን ብለዋል። የትምህርት ሥርዓት የትኛውም ሀገር የወደፊት ዕጣ ፈንታ የሚቀረጽበት፣ የሥልጣኔ ቀጣይነት የሚረጋገጥበትና የትውልድ አቅም የሚገነባበት ታላቁ የሀገር ግንባታ መሣሪያ ነው። መንግሥትና ሕዝብ ተባብረው መንገድና ድልድይ ሊገነቡ፣ ታላላቅ የኃይል ማመንጫዎችን ሊገነቡ ወይንም ግዙፍ ፋብሪካዎችን ሊያቆሙ ይችላሉ። ነገር ግን እነዚህ ሁሉ መሠረተ ልማቶች ቀጣይነት ሊኖራቸው የሚችለውና ፍሬ የሚያፈሩት የሚንከባከባቸው፣ የሚያሻሽላቸውና አዲስ ዕውቀት የሚያመነጭ ብቁና ንቁ ትውልድ ሲኖር ብቻ ነው። በመሆኑም የመደመር መንግሥት በትምህርት ዘርፍ የሚያደርገው ኢንቨስትመንት በሀገር የወደፊት ጽኑ ሕልውናና ዘላቂ አቅም ላይ የሚደረግ ታላቅ መዋዕለ ነዋይ ነው። ይህ የተቀናጀ የለውጥ አጀንዳ ከአንድ ነጠላ ፕሮጀክት ወይም ከአንድ የትምህርት ደረጃ ብቻ የሚጀምር ሳይሆን፣ ከተማሪው ዕለታዊ ሕይወት እስከ ሀገራዊ የዕውቀት አቅም ድረስ የተዘረጋ ሰፊ ርዕይ ነው፡ 👉የተማሪዎች ምገባ (የሰው ሀብት ልማት ፖሊሲ)፡- በረሃብ የሚሰቃይ ተማሪ በትምህርቱ ላይ ትኩረት ሊያደርግ አይችልም። ረሃብ የመማር ፍላጎትን ከመቀነሱም በላይ ልጆችን ከትምህርት ገበታ ያርቃል። ይህንን እውነታ በመረዳት መንግሥት የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም እንደ አንድ ትልቅ የሰው ሀብት ልማት ፖሊሲ ተወስዷል። ይህም ተማሪዎች በትምህርታቸው እንዲቀጥሉ ከማድረጉ ባሻገር፣ ሁሉም በአንድ ማዕድ እኩል ተቀምጠው እንዲመገቡ በማድረግ በልጆች ዘንድ የእኩልነት፣ የአብሮነትና የማኅበራዊ መተሳሰብ ስሜትን አጎልብቷል። 👉የመምህራን ብቃትና ሙያዊ ማሻሻያ፡- ጥራት ያለው ትምህርት በብቁ መምህራን ይረጋገጣል። መንግሥት መሠረተ ልማቶችን ከማሟላት ጎን ለጎን በመምህራን ሙያዊ ብቃትና ዘመናዊ የማስተማር ክህሎት ላይ አድርጓል። መምህራን እውቀት አጋሪ፣ መሪና አዳዲስ እሳቤዎችን የሚቀርጹ የትውልድ ሞዴል እንዲሆኑ በማስቻል፣ የትምህርት ጥራት ትርጉም ባለው መልኩ ወደ ተማሪዎች እንዲሸጋገር ተደርጓል። 👉መሠረተ ልማትና የልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ግንባታ፡- ቁጥርን ከጥራት ጋር ያገናኙ በርካታ አዳዲስ ትምህርት ቤቶችና ደረጃቸውን ያሻሻሉ ተቋማት ተገንብተዋል። በተለይም የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡና ልዩ ተሰጥኦ ያላቸውን ተማሪዎች አፈላልጎ በመቀበል፣ በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ የታገዘ ትውልድ ለማፍራት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። 👉የንባብ ባህልና የቴክኖሎጂ ምጥቀት፡- ትምህርት በክፍል ውስጥ ብቻ የሚገደብ ባለመሆኑ፣ እንደ አብርሆት ያሉ ታላላቅ ቤተ-መጻሕፍት ተገንብተዋል። ይህም በንባብ የሚገነባ፣ ጥያቄ የሚጠይቅና የሀገርን የዕድገት አቅጣጫ በአዎንታዊ መልኩ መቀየር የሚችል ትውልድ ይፈጥራል። በተጨማሪም፣ የዲጂታል ቴክኖሎጂንና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሥልጠናዎችን በማስፋፋት ተማሪዎች የዓለምን የቴክኖሎጂ ምጥቀት እንዲቀስሙና አዳዲስ የፈጠራ ሥራዎችን እንዲያመነጩ መንገድ ተከፍቷል። 👉ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን የምርምር ማዕከል ማድረግ፡- ዩኒቨርሲቲዎችን ከዲግሪ ማደያነት አውጥቶ በዘመናዊ ቤተ-ሙከራዎችና የምርምር አቅም በማጠናከር የሀገሪቱን ችግሮች በሳይንሳዊ መንገድ የሚፈቱና በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያን ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የማዕከል ቦታዎች እንዲሆኑ ተደርጓል። በዚህም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በተልዕኮ የመለየት ሥራዎች የተሰሩ ሲሆን የምርምር፣ የተግባር ሳይንስ ፣ አጠቃላይ ወይንም ሁለንተናዊ እንዲሁም ልዩ ትኩረት የሚሹ ዩኒቨርሲቲዎች በሚል ተከፋፍለው ትውልድን በማብቃት ላይ ይገኛሉ፡፡ በሌላ መልኩም ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ እንዲሆኑ እየተደረገ ሲሆን፣ ይህም ተቋማቱ በራሳቸው አስተዳደራዊና አካዳሚያዊ ነፃነት በመመራት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጡ፣ የላቀ የምርምር አቅም እንዲገነቡና ሀገራዊ ችግሮችን መፍታት የሚችሉ ተወዳዳሪ ተቋማት እንዲሆኑ ያስችላቸዋል።
የነገዋን ኢትዮጵያ የሚረከብ ትውልድ እየተገነባ ነው
Oct 7, 2026 158
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአዲሱ የመደመር መንግሥት ምሥረታ ወቅት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት፡ አዲሱ ትውልድ በእውቀት፣ በክህሎት፣ በሥነ-ምግባርና በሀገር ፍቅር ታንጾ አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳለበት በአጽንኦት አሳስበዋል። ይህ ጥሪ የትውልድ ግንባታን የሀገሪቱ የወደፊት አቅም፣ ህልውና እና ሉዑላዊነት መሠረት አድርጎ የሚያስቀምጥ ስትራቴጂካዊ አቅጣጫ ነው። ይህ መልዕክት የነገ ተስፋን በቃልና በምኞት ብቻ ማቅረብ ሳይሆን፣ ዛሬ በፅኑ መሠረት ላይ የሚገነባው የሰው ኃይል ነገ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ፣ ቴክኖሎጂ፣ ሳይንስና ፖለቲካዊ አቅም ሙሉ በሙሉ የሚወስን መሆኑን የሚያመላክት እይታ ነው። የነገዋን ኢትዮጵያ በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት በሚደረገው በዚህ ታሪካዊ ጉዞ፣ ወጣቶች የለውጥ ተከታዮችና ተመልካቾች ብቻ ሳይሆኑ የፊተኛው መስመር መሪዎች፣ የፈጠራ ባለቤቶች እና ዋና ውሳኔ ሰጪዎች መሆን አለባቸው። በዛሬው ፈጣን፣ ውስብስብና ተለዋዋጭ ዓለም ወጣቶች ወደ ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ አመራር ግንባር ቀደምትነት መምጣት የሚገባቸው በዋናነት በሚከተሉት ቁልፍ ምክንያቶችና ምሰሶዎች ምክንያት ነው፡፡ በአሁኑ ወቅት ዓለም የምትመራውና የኃይል ሚዛኗ የሚወሰነው በኢኮኖሚና በቴክኖሎጂ የበላይነት ፉክክር ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity)፣ የዳታ ሳይንስ (Data Science) እና ዲጂታል ኢኮኖሚ የዓለምን የፖለቲካና የሀብት አሰላለፍ ሙሉ በሙሉ እየቀየሩት ይገኛሉ። ስለሆነም የነገው የኢትዮጵያ ትውልድ በነዚህ ዘመናዊ የዕውቀት መስኮች ማለትም በኢንጂነሪንግና በቴክኖሎጂ፣ በዘመናዊ የግብርና ቴክኖሎጂና ምግብ ዋስትና፣ በጤና ጥበቃና ህክምና ሳይንስ፣ በኢንዱስትሪ፣ በግንባታና በማኑፋክቸሪንግ፣ በታዳሽ ኃይልና ማሽነሪ፣ በዲጂታል አገልግሎትና ሶፍትዌር ልማት፣ እና በሌሎች በርካታ ስትራቴጂካዊ ሙያዎች ላይ በከፍተኛ ደረጃ የመምጠቅና የማደግ ግዴታ አለበት። ወጣቱ ትውልድ የዲጂታል ዘመን ተወላጅ (Digital Native) በመሆኑ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በፍጥነት የመረዳት፣ የመተግበርና ወደ አዲስ የፈጠራ ውጤት የመቀየር ተፈጥሮአዊ ዝንባሌና ዝግጁነት አለው። በዛሬው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ ውድድር ውስጥ ተወዳዳሪ ሆኖ መቆም የሚቻለው በባህላዊና ያረጁ አሰራሮች ሳይሆን በየዕለቱ ተሻሽሎ፣ ጠንክሮና በርትቶ በመገኘት ብቻ ነው። ወጣቶች በሀገሪቱ የውሳኔ ሰጪነትና የመሪነት ቦታ ላይ ሲቀመጡ የሀገሪቱን የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን (Digital Transformation) በከፍተኛ ፍጥነት ማፋጠን ይችላሉ። ይህንን እውን ለማድረግም ወጣቶችን በፕሮግራሚንግና በዲጂታል ክህሎት ለማብቃት የተጀመረው የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ኮደሮች (5 Million Coders) ፕሮጀክት፣ የሀገሪቱን የሰው ኃይል አቅም ከአዲሱ ዲጂታል ኢኮኖሚ ጋር ለማጣጣም የተቀመጠውን ግልጽ አቅጣጫ ያሳያል። በተጨማሪም የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት፣ ዩኒቨርሲቲዎችና ሌሎች የሳይንስና ቴክኖሎጂ ተኮር ተቋማት በሰፊው እየተገነቡና እየተስፋፉ መሆናቸው፣ ኢትዮጵያ ከቴክኖሎጂ ተጠቃሚነትና ተካፋይነት አልፋ ወደ ቴክኖሎጂ ፈጣሪነትና ምንጭነት ለመሸጋገር ያላትን ጽኑ ፍላጎት ያመላክታል። በአሁኑ ወቅት የዓለም ፖለቲካ ሁኔታ በየዕለቱ የሚቀያየር፣ ያልተረጋገጠ እና እጅግ ውስብስብ መስመር የሚይዝ ነው። በዚህ ዘመን የሀገር ሉዓላዊነት እና የህዝብ ክብር የሚጠበቀው በወታደራዊ ኃይል ብቻ ሳይሆን በኢኮኖሚ ጥንካሬ፣ በዲጂታል ደህንነት እና በፖለቲካዊ/ዲፕሎማሲያዊ ብልህነት ነው። ዓለም ወዴት እየሄደች እንደሆነ በቅርበት የሚከታተል፣ መረጃዎችንና ሁነቶችን በጥራት በመተንተን ሀገራዊ ጥቅምን የሚያስከብር፣ እንዲሁም ፈጣንና ስትራቴጂካዊ ውሳኔ መስጠት የሚችል የወጣት መሪዎች ስብስብ ካልኖረ ሀገር ለውጫዊ ተፅዕኖ፣ ጫና እና ጥቃቶች ተጋላጭ ትሆናለች። ስለሆነም ሉዓላዊነቷ የተከበረ፣ የኢኮኖሚ ነፃነቷ የተረጋገጠ እና የማትደፈር ኢትዮጵያን ለማቆም የዓለምን የኃይል አሰላለፍ በሚገባ መረዳትና መምራት የሚችሉ ብስል ወጣት መሪዎች ወሳኝ ናቸው። ኢትዮጵያ በፅኑ የምትፈልገው በመረጃና ማስረጃ ላይ ተመስርተው የሚከራከሩ፣ ልዩነቶችን በሰለጠነ ውይይት የሚያቀርቡ፣ የሌላውን ሀሳብ በትዕግስት የሚያዳምጡና ለጋራ ጥቅም የሚቆሙ ወጣቶችን ነው። ወጣቶች ወደ አመራር መድረክ ሲመጡ አዳዲስና ተለዋዋጭ የፖለቲካ ባህሎችን በማስተዋወቅ ሀገሪቱን ከኋላቀር የፖለቲካ አዙሪት ወደ ልማት፣ ዕድገትና ህብረት መምራት ይችላሉ። አንድ ሀገር ጠንካራና ዘላቂ መሠረት የሚኖራት የትውልድ ሽግግሩ በሥርዓት፣ በሰላም፣ በስልጠናና በበቂ ዝግጅት ሲካሄድ ብቻ ነው። ወጣቶች ዛሬውኑ በውሳኔ ሰጪ ቦታዎች ላይ መሳተፍ ካልጀመሩና ተግባራዊ ልምድ ካላካበቱ፣ የነገዋን ሀገር የመረከብና የመምራት ብቃታቸው አጠራጣሪ ይሆናል። ወጣቶች የቴክኖሎጂና የሳይንስ ዕውቀት ብቻ ሳይሆን የሀገር ፍቅር፣ የኃላፊነት ስሜት፣ ታማኝነትና የላቀ ሥነ-ምግባር ያላቸው መሪዎች ሆነው ሲወጡ ሀገርን ከማንኛውም ውጫዊና ውስጣዊ ጫናዎች በፅናት መከላከል ይችላሉ። የጠቅላይ ሚኒስትሩ "አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመረከብ አዲሱ ትውልድ መዘጋጀት አለበት" የሚለው ጥሪና መልዕክት፣ ትውልዱን ለነገ ተስፋ ብቻ ሳይሆን ለዛሬው የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥም ንቁና ግንባር ቀደም ሚና ሊኖረው እንደሚገባ ያሳስባል። የነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋና ህልውና ያለው በወጣቶቿ እጅ ውስጥ ነው፤ ይህንን ተስፋ ደግሞ ወደ ተጨባጭ እውነታ የመቀየር ሀገራዊ ኃላፊነት የሚጀምረው ከዛሬው የትውልድ ግንባታ ሥራ ነው።
የመደመር እሳቤ-ለግዙፍ ሀገራዊ ውጥኖች ስኬት
Oct 7, 2026 345
የመደመር መንግሥት እና እሳቤ የተበታተነ አቅምን በማሰባሰብ፣ሀገር በቀል እውቀቶችን መሠረት በማድረግ እና የሕዝብ ተሳትፎን በማስተባበር ግዙፍና ስትራቴጂካዊ ሀገራዊ ውጥኖችን ማሳካት እንደሚቻል በተግባር ያሳየ ፍልስፍና ነው። ይህ እሳቤ ወረቀት ላይ ብቻ የቀረ ሳይሆን፣ ውስን ሀገራዊ ሃብትን በአንድ ላይ በማቀናጀት አዳዲስ የሥራ ባህሎችንና ተጨባጭ ውጤቶችን ማምጣት የቻለ እሳቤ መሆኑን በተለያዩ ዘርፎች የተመዘገቡ ስኬቶች ያረጋግጣሉ። የመደመር እሳቤ ዋና ግብ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ማረጋገጥ ሲሆን፣ ባለፉት ዓመታት የተከናወኑት ተግባራት የሀገሪቱን የልማት ምዕራፍ ወደ ላቀ ደረጃ አሸጋግረዋል። በኢኮኖሚ እና በመሠረተ-ልማት ዘርፎች የታዩት ተጨባጭ ማሳያዎች የመደመር እሳቤ ያለውን ትልቅ የማስፈጸም አቅም በግልጽ ያሳያሉ።በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ከውጭ የሚገባውን ስንዴ ሙሉ በሙሉ በማስቀረት ኢትዮጵያን የአፍሪካ ትልቁ የስንዴ አምራች ያደረገው የስንዴ ልማት እመርታ እና በሕዝብና መንግሥት ትብብር ግንባታው የተከናወነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የዚሁ እሳቤ ፍሬዎች ናቸው። በተጨማሪም ከ56 ቢሊዮን በላይ ችግኞች የተተከሉበት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ የከተሞችን ገጽታ የቀየረው የኮሪደር ልማት እንዲሁም በአጭር ጊዜ ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ መዳረሻዎችን የገነቡት የ“ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” ፕሮጀክቶች የመደመር ስልታዊ አካሄድ ግዙፍ ውጥኖችን በአጭር ጊዜ ማጠናቀቅ እንደሚችል ማረጋገጫዎች ናቸው።በመደመር መንግሥት ምስረታ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ይህንን እሳቤ ይበልጥ የሚያጠናክሩ ቁልፍ ሐሳቦችን አንስተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምንጩን የሚረሳ ወንዝ እንደሚደርቅ ሁሉ፣ መሠረቱንና ሀገራዊ እሳቤውን በመጣል የሚጀመር የሥልጣኔ ጉዞ ሩቅ ሊጓዝ እንደማይችል ገልጸው፤ ባለፉት ዓመታት የኢትዮጵያዊነት መሠረት የሆነውን የመደመር እሳቤን በተሟላ ሁኔታ ወደ ሥራ ማስገባት መቻሉን አብራርተዋል። አዲሱ የመደመር መንግሥት የሀገር ውስጥ እሴቶችን ከውጭው ጠቃሚና ተራማጅ ዕውቀት ጋር በማዋሃድ አዲስ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ለመገንባት እንደሚሠራ አስምረውበታል። በተጨማሪም በትናንቱ ንግግራቸው የመደመር ፖለቲካዊ ባህሪ ልዩነቶችን አቀናጅቶ የጋራ ውጤት መፍጠር መሆኑን በመጥቀስ፣በምርጫ ውድድር ውስጥ የፓርቲዎች ማሸነፍና መሸነፍ ቢኖርም እንኳ ውጤቱ ሲደመር ኢትዮጵያ አሸናፊ እንጂ ተሸናፊ ልጆች የሌሏት ሀገር መሆኗን ማሳየት ነው ብለዋል። ባለፉት ዓመታት ከተናጠል ዘርፍ ወደ ብዙሃ ዘርፍ በመሸጋገር በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በኮሪደርና ቱሪዝም ልማት የተመዘገቡት አስደናቂ ውጤቶች ሁሉ የተናጠል አቅሞችን በማቀናጀት (Synergy) የመጡ መሆናቸውን አስገንዝበዋል። በአጠቃላይ የመደመር መንግሥት አዳዲስ ዕድሎችን ወደ ውጤት በመቀየር እና የጀመራቸውን ግዙፍ ስራዎች በተከታታይነት በማስቀጠል ታላቅ ሀገር የመገንባት ርዕዩን አፅንቶ የሚቀጥል ነው።
ልዩ ዘገባዎች
ከአዲሱ መንግስት ምን ይጠበቃል?
Oct 5, 2026 272
ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ አዲስ የሚመሰረተው መንግስት በሀገሪቷ የተጀመሩ የልማት ስራዎችን የማስቀጠል፤ በተለይም የተጀመሩ ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለስኬት ማብቃት ትልቁ የቤት ስራ ነው የሚሆነው። በከተሞች እየተከናወነ ያለውን የኮሪደር ልማትና የስማርት ሲቲ ግንባታ፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን የማስፋት፣ የአረንጓዴ አሻራ ልማትን ማስቀጠል ሌላኛው ሀገራዊ ሃላፊነት ነው የሚሆነው። የኢትዮጵያ ልማት በከተሞች ጋር ብቻ የሚወሰን ባለመሆኑ በገጠር አካባቢዎች የተጀመሩ የገጠር ትራንስፎርሜሽን የልማት ስራዎችንም ማስቀጠል የግድ ይላል። የገጠር ትራንስፎርሜሽን ዋነኛ ዓላማም የገጠሩን ህዝብ አኗኗር ማዘመን፣ የመሠረተ ልማትና የመሰረታዊ አገልግሎት ተደራሽነትን ማሻሻል፣ የገጠር ኢኮኖሚን ማጠናከርና የገጠር ነዋሪዎችን ከዘመናዊ የምርትና የገበያ ሥርዓት ጋር ማስተሳሰር መሆን አለበት። ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በባህልና በሃይማኖት የበለፀገች ሀገር በመሆኗ አዳዲስ የቱሪዝም መዳረሻዎችን መፍጠር፣ ያሉትን የመጠበቅና የማልማት እንዲሁም ታሪካዊና ተፈጥሯዊ ሀብቶችን መጠበቅ፣ የቱሪስት ቆይታን ማራዘምና ከቱሪዝም ጋር የተሳሰሩ የስራ እድሎችን የማስፋት ጉዳይ የአዲሱ መንግስት ዋነኛ ትኩረት ሆኖ ይቀጥላል። በግብርናው ዘርፍም በምርትና ምርታማነት፣ በመስኖ ልማት፣ በስንዴ፣ በሌማት ትሩፋት፣ በቡና፣ በሆርቲካልቸርና በሌሎችም የግብርና ዘርፎች የተጀመሩ ስራዎች በዘላቂነት እንዲቀጥሉ ማድረግ ይጠበቃል። ከምርት መጨመር ባሻገር የግብርና ምርቶችን ማቀነባበር፣ የገበያ ትስስርን ማሻሻል፣ የማከማቻና የመጓጓዣ ስርዓትን ማዘመን እና የአርሶ አደሩን ገቢ የማሳደግ ጉዳይ ትኩረት ይፈልጋል። የምርትና ምርታማነት መጨመር በመጨረሻም ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት፣ የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥና የሀገሪቱን የውጭ ምንዛሬ አቅም በማሳደግ ከተረጅነት ለመውጣት የሚደረገውን ጥረት ማሳካት ይጠበቅበታል። የማዕድን ልማት፣ ዲጂታላይዜሽንና የመንግስት አገልግሎት አሰጣጥን የማዘመን ጉዳይም ልዩ ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል። የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር የምርትና የገበያ አቅርቦትን ማሳደግ፣ የአቅርቦት ሰንሰለትን ማሻሻል፣ ህገወጥ የገበያ አሰራሮችን መቆጣጠርና የዜጎችን የመግዛት አቅም ማሻሻል ይጠበቃል። የኑሮ ውድነት ችግር በአንድ መፍትሄ የሚፈታ ባለመሆኑ የገቢ፣ የምርት፣ የገበያና የፋይናንስ ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መልኩ ማስኬድ ያስፈልጋል።
የአካታች ሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት
Oct 5, 2026 174
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):- አዲሱ የመንግስት ምስረታ - አካታች የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ በምክር ቤት አብላጫ መቀመጫ ያገኘው ብልጽግና ፓርቲ መንግስት የመመስረት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ በዛሬው እለት ይሄው የሚከናወን ይሆናል። በፓርላማው የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መቀመጫ ያገኙ በመሆኑ የፖለቲካ ክርክሮችና የሃሳብ ብዝሃነት የሚስተናገዱበት እንደሚሆንም ይጠበቃል። በኢትዮጵያ አካታችና አሳታፊ የፖለቲካ ስርአት ግንባታ መሰረት ያኖረው አዲሱ የመንግስት ምስረታ ሂደት የክልሎች ተጠናቆ በዛሬው እለት የፌዴራል መንግስት ምስረታ እውን ይሆናል። ባለፉት ዓመታት የተመዘገበው የአካታችነት ስኬት የመንግሥት ከፍተኛ የአመራር እርከኖች፣ የሚኒስትሮች ምክር ቤትና የፍትህ ተቋማት አመራሮች ላይ የተፎካካሪ ፓርቲ ተወካዮችን፣ የሴቶችንና የወጣቶችን ፍትሃዊ ስብጥር በተግባር ማሳየት ያስቻለ ነው። ከባለፉት አምስት አመታት ተሞክሮ በመነሳትም የዘንድሮው ምርጫ በብዙ መስፈርቶች ዴሞክራሲያዊ፣ አሳታፊ እና አካታች መሆኑን በተግባር ያሳየና የሀገረ መንግስት ግንባታ ሂደት ፅኑ መሰረት ያኖረ ሆኗል። በተቋማዊ አካታችነትና ሀገራዊ መግባባትን ለመፍጠር በተወሰዱ እርምጃዎችም ጉልህ ውጤቶች ተመዝግበዋል። ሁሉንም የፖለቲካና የኅብረተሰብ ክፍሎች ያቀፈው ሀገራዊ የምክክር ሂደት በሀገሪቷ የቆዩ ልዩነቶችን በምክክር ለመፍታት አዲስ ምእራፍ የከፈተ ሆኗል። ከዚህ ጎን ለጎን የጽንሰ-ሐሳብ፣ የቋንቋና የባህል ስብጥሮችን ያከበሩ የትምህርትና የባህል ፖሊሲዎች መተግበራቸው፣ ዜጎች በቋንቋቸው የመማርና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው እንዲሰፋ በማድረግ ረገድም ትልቅ ስኬት ታይቷል። በመሆኑም በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ አብላጫ ድምፅ ያገኘው የብልፅግና ፓርቲ የሚያቋቁመው አዲሱ መንግስት በቀጣይ ሁለንተናዊ አካታችነትን በማረጋገጥ ረገድ ብዙ እንደሚሰራ ይጠበቃል። ገዢው ፓርቲ መወዳደር የሚችልባቸውን አካባቢዎች በመተው ለተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች እድሉን መስጠቱ በምክር ቤቱ የተለያዩ ድምፆች እንዲስተጋቡ ምቹ ሁኔታ የፈጠረ ሆኗል። በመሆኑም ጠቅላላ ምርጫው የፖለቲካ ተሳታፊነትንና ውክልናን በማስፋት ረገድ ጉልህ ውጤቶች የተመዘገቡበት ነበር ማለት ይቻላል። በተጨማሪም በውሳኔ ሰጪነትና በፖለቲካ ውድድር ውስጥ የሴቶች፣ የወጣቶችና የልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፎ እንዲያድግ በመደረጉ ህዝባዊ ወካይነት ያለው የምርጫ ሂደትን ለማከናወን አስችሏል። ምርጫ አስተዳደሩንና አሰራሩን አሳታፊና ፍትሃዊ በማድረግ ረገድ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኩል የታዩት እርምጃዎች ሌላው የአካታችነት ማሳያዎች ናቸው። የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ተዳራሽ ማድረግ፣ ለአካል ጉዳተኞች ምቹ የሆኑ የምርጫ ግብዓቶችን ማዘጋጀት እና በምርጫ ታዛቢነት የሲቪክ ማህበራትን፣ የሀገር ውስጥና የውጪ ምርጫ ታዛቢዎችን ማሳተፍ ተችሏል። ይህም የህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ያለምንም ገደብ የመምረጥ መብታቸውን እንዲጠቀሙና በሂደቱ ላይ ያላቸው እምነት እንዲጎለብት አድርጓል። በመሆኑም በዛሬው እለት የሚመሰረተው መንግሥት ልዩ ልዩ የፖለቲካና የማህበረሰብ ክፍሎችን ድምፅ በማስተናገድና ሀገራዊ መግባባትን በመፍጠር ጠንካራ የሀገረ መንግስት ግንባታ መሰረት የሚያኖር እንደሚሆን ይጠበቃል።
የመደመር መንግሥት-የብሔራዊ ጥቅም ዘብ
Oct 5, 2026 178
ኢትዮጵያ ዛሬ አዲስ መንግሥት ትመሠርታለች።ይህ መንግሥት የዛሬውን ትውልድ ብቻ ሳይሆን፤የመጪውንም ትውልድ ፍላጎት በጽኑ መሠረት ላይ የሚያቆም ሥራ የሚሠራ ነው። አዲሱ መንግሥት ትልቅ የሕዝብ አደራ የሚቀበልና የነገዋን ኢትዮጵያ በከፍታ ላይ የሚያስቀምጥ እንደሚሆን እሙን ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ እጅግ ውስብስብ የሆኑ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኅበራዊ ፈተናዎች አልፋ ዛሬ አዲስ የምዕራፍ ላይ ትገኛለች። አዲሱ መንግስት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን፣ ሉዓላዊነቷን እና የሕዝቦቿን የጋራ እድገት ለማረጋገጥ ባደረገችው ያላሰለሰ ጥረት ውስጥ ቀጣይ ጉዞዋን በተሻለ መልኩ የሚያስቀጥል መንግሥት ይሆናል። ይህ ታሪካዊ ጉዞ በቀላሉ የተገኘ አልነበረም። ሕዝቡ የወደፊት ዕጣ ፈንታውን በቃላት ሳይሆን በተግባር ለመወሰን፣ መብቱን በድምፁ በመጠቀም ታሪካዊ አደራውን ለመወጣት ውስብስብ ፈተናዎችን አልፏል። በፈተና ውስጥ አልፎ የሰጠው ድምፅ ተራ የምርጫ ሂደት ሳይሆን፤ የሀገርን ሕልውና የማስከበር፣የብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ እና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር የማስረከብ ጽኑ ፍላጎት መግለጫ ነበር። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት የዚሁ የሕዝብ አደራና የጽናት ውጤት ነው።ይህ የመደመር መንግሥት የሀገሪቱን ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ እና ቀጣናዊ ጥቅሞች ያስከብራል፤ የኢትዮጵያን የሉዓላዊ ድንበር እና የወደፊት ሕልውና በጠንካራ ዲፕሎማሲና በውስጥ አንድነት ይጠብቃል። የዛሬዎቹን አጣዳፊ ጥያቄዎች ለመመለስ ብቻ ሳይሆን፣ መጪው ትውልድ የሚተማመንባት፣ በኢኮኖሚ የበለጸገች እና ብሔራዊ ጥቅሟን የምታስጠብቅ ሀገር መንግስት ይመሰርታል። ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን በሁለት ውኃዎች ላይ አድርጋ በጽናት እየተንቀሳቀሰች ትገኛለች። የአባይን ውኃ ለሁለንተናዊ እድገቷ መጠቀም ጀምራለች፤ ሕዳሴንም ጨርሳ የማድረግ አቅሟን አረጋግጣለች።ይህ ጉዞ ቀላል አልነበረም፤ሀገሪቱ በውስጥና በውጭ በርካታ ፈተናዎችን፣ ተፅዕኖዎችንና ጫናዎችን አልፋ ነው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰችው። ዛሬ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅሟን የበለጠ የሚያስከብርላትን የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ አንሥታ ጉዳዩን ዓለም አቀፍ አጀንዳ አድርጋዋለች። የመደመር መንግሥት ኢትዮጵያ ኢ-ፍትሐዊና ባልተገባ መልኩ ያጣችውን የባሕር በሯን እንድታገኝ በትክክለኛው መንገድ ይጓዛል፤ ግቡንም ያሳካል። ዛሬ የሚመሠረተው አዲስ መንግሥት ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ መደላደል የሚፈጥር ነው፤ የሀገሪቱን የባሕር በር ፍላጎት፣የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ ተጠቃሚነት፣የውስጥ ደኅንነትና የኢኮኖሚ ነፃነት አፅንኦት ሰጥቶ ማስጠበቅ ነው።ልዩነቶችን በማቀናጀትና አቅሞችን በመደመር የሀገርን ሕልውና አስተማማኝ ማድረግም ሌላው ከመደመር መንግስት የሚጠበቅ ነው። ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የበርካታ ዘመናት ታሪካዊ ጠላቶቿንና ተላላኪዎቻቸውን እኩይ ሴራ ትበጣጥሳለች።የውስጥና የውጭ ጫናዎችን በህዝቦቿ ጽናት፣የአንድነት መንፈስና የማይናወጥ ሀገራዊ ወኔ እያሸነፈች ትቀጥላለች።ለነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ሳትበገር በማንኛውም ጊዜና ሁኔታ ወደ ላቀ የልማት፣ የብልፅግናና የዕድገት ከፍታ ወደ ፊት መገስገሷን ትቀጥላለች። ዛሬ የሚመሰረተው አዲሱ የመደመር መንግሥትም የሕዝቡን ተስፋና እምነት ወደ መሬት በማውረድ፣የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም አክብሮና አስከብሮ ለመጪው ትውልድ የምትመችና በጽኑ መሠረት ላይ የተገነባች ሀገርን የማስረከብ ታሪካዊ ኃላፊነት አለበት።
የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ
Oct 5, 2026 193
መስከረም 25/2019 (ኢዜአ):-የኢትዮጵያ ፖለቲካ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ትልቅ ሀገር- ትልቅ ህዝብ- ታላቅ ርእይ የዛሬው እለት ኢትዮጵያ በፖለቲካዊ ታሪኳ ሌላ አዲስ ምዕራፍ የምትከፍትበት ታሪካዊ እለት ነው። በግንቦት ወር የተካሄደው ምርጫ፣ የሕዝብ ድምፅና ውሳኔ ወደ ተጨባጭ የመንግሥት ምስረታ የተሸጋገረበት ወቅት ላይ ይገኛል። የሕዝብ ድምፅ ድምር ውጤት መንግስት የሚመሰረትበትና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ሂደት ጽኑ መሰረት የያዘበት አዲስ የታሪክ ምእራፍ ተከፍቷል። የምርጫ ሂደት በራሱ የሚጠናቀቀው የምርጫ ውጤት በመገለጹ ብቻ ባለመሆኑ የሕዝብ ውሳኔ በተቋማት በኩል ተግባራዊ ሲሆንና የሕዝብን የልማትና የአገልግሎት ፍላጎት ማስተናገድና ምላሽ መስጠት የሚችል መንግስት ሲመሰረት ነው። በዚሁ መሰረትም ባሳለፍነው ሳምንት ድሬዳዋና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ ክልሎች የመንግሥት ምስረታ ሂደታቸውን አጠናቀው ወደ ስራ ገብተዋል። በዛሬው እለት ደግሞ የፌዴራል መንግስት የሚመሰረትበት፤ አዲሱ ፓርላማ ሥራውን በይፋ የሚጀምርበትና አዲስ የፌዴራል መንግሥት የሚመሠረትበት ታሪካዊ እለት ነው። ኢትዮጵያ በታሪኳ የተለያዩ የፖለቲካ ሥርዓቶችንና የለውጥ ወቅቶችን አሳልፋለች። በእያንዳንዱ ዘመን የሀገሪቱ ፖለቲካ በሕዝቡ ፍላጎት፣ በሀገራዊ ጥቅምና በዘመኑ ተግዳሮቶች ተፅዕኖ ሥር ወድቆ የታየበት አጋጣሚ የበዛ ነበር ማለት ይቻላል። የዛሬው የመንግስት ምስረታ ግን ከ54 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ድምፃቸውን በነፃነት የሰጡበት ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ድምር ውጤት ነው። በመሆኑም አዲስ የሚመሰረተው መንግስት የቆዩ የፖለቲካ ስብራቶችን በማከም የኢትዮጵያን የወደፊት ብሩህ ተስፋ የሚተልምና ቀጣይ መዳረሻዋን የሚወስን ይሆናል። ታላቋን ኢትዮጵያ ለመምራት ትልቅ ርዕይ የሰነቀ መንግስት የግድ በመሆኑ እንደ ሀገር የተያዙ እቅዶችን በተደመረ አቅም በማሳካት እድገትና ማንሰራራቷን ማስቀጠል ይገባል። በመሆኑም አዲሱ መንግሥት በምርጫ ወቅት ለህዝብ የገባውን ቃል በማክበር ለተግባራዊነቱ መትጋት ይጠበቅበታል። የህዝብን አደራ በአግባቡ በመወጣት ቃልን በተግባር መፈፀም የግድ ይላል። የዜጎች የሥራ ዕድል፣ የኑሮ ውድነት፣ የሰላምና ደህንነት ጉዳይ፣ የልማት ፍላጎት፣ የፍትሕ አገልግሎትና የመንግሥት ተጠያቂነት የአዲሱ መንግስት የቤት ስራዎች ናቸው። ፓርላማውም ሕግ ከማውጣት ባሻገር የመንግሥትን አፈጻጸም መከታተል፣ ተጠያቂነትን ማረጋገጥና የዜጎችን ድምፅ ወደ ፖሊሲና የሕግ አቅጣጫ መቀየር ይጠበቅበታል። በዚህ መልኩ የሚቀጥለው ፓርላማ የዴሞክራሲ ሥርዓቱን በማጠናከር የህዝብ የልማት መሰረቶች ተጠናክረው የተሻለ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚሰራ ይሆናል። የሕዝብ ድምፅ የሥልጣን ምንጭና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ መሰረት የሚያኖር መሆኑ ይታወቃል። በህዝብ ድምጽ የተሰጠ ሃላፊነት ደግሞ ተጠያቂነት ጭምር ያለበት አደራ ነው። በመሆኑም አዲሱ መንግስት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ለዘላቂ ሰላምና ልማት፣ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታና የህግ የበላይነት መስራት ይጠበቅበታል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108601
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81782
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59948
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57555
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 40836
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 40769
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 40186
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 38682
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 108601
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 81782
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 59948
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 57555
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ
Oct 7, 2026 188
ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ሕዝብ፣ ታላቅ ርዕይ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ አዲስ ምዕራፍ ተከፍቷል።የመደመር መንግሥት ከትናንት በስትያ በይፋ በተመሠረተበት ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በፓርላማ ያቀረቡት ንግግር የመንግሥቱን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያን የወደፊት ራዕይ በግልጽ የሚያሳይ ነው። የንግግራቸው ማዕከላዊ ጭብጥም ኢትዮጵያ ዘላቂ ችግሮቿን የምትፈታው በራሷ የሥልጣኔ መንገድ ስትጓዝ ብቻ መሆኑን አጽንኦት ሰጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው ኢትዮጵያ የብዝሃ ሥልጣኔ ሀገር መሆኗን አንስተዋል። ለዘመናት የታሪክ፣ የባህል፣ የእምነት እና የማንነት መገናኛ ሆና ቆይታለች። ለብዙ ሕዝቦች መነሻ፣ ለብዙ ትውልዶች መነቃቃት ምንጭ የሆኑ ታሪኮችን በውስጧ ይዛለች። ሆኖም ይህን ታላቅ ቅርስ ወደ ዘላቂ ልማትና ዕድገት በመቀየር ረገድ ፈተናዎች በተደጋጋሚ ያጋጥማሉ። የጀመርነውን ማስቀጠል፣ የተገነባውን ማስጠበቅ እና በትውልድ መካከል ቀጣይነትን ማረጋገጥ ትልቁ ፈተና መሆኑንም አስገንዝበዋል።አንድ ትውልድ የገነባውን ሌላው ትውልድ እያፈረሰ የሚሄድበት ሁኔታ ሥልጣኔን እንደማይፈጥር ፣ ሀገርንም እንደማያበለጽግ አብራርተዋል። በዚህ ምክንያት ኢትዮጵያ በብዙ ዘርፎች ያላትን አቅም ሙሉ በሙሉ መጠቀም አልቻለችም። ሀሳብን በውይይት ከመፍታት ይልቅ በኃይል ለማስፈጸም የተደረጉ ጥረቶች ሀገሪቱን ወደ ኋላ ጎትተዋል። በመሆኑም የመደመር መንግሥት መልዕክት ግልጽ ነው፤ የኢትዮጵያ ችግሮች መፍትሔ የሚገኘው በግጭት ሳይሆን በመግባባት፣ በመደመር እና በጋራ ግብ ዙሪያ በመሰባሰብ ነው። አዲሱ የኢትዮጵያ ሥልጣኔ ማለት የመከባበር ባህልን መገንባት፣ ሕግን ማክበር፣ ልዩነቶችን እንደ ጥንካሬ መቀበል እና የጋራ ሀገራዊ ራዕይ መፍጠር ነው። ይህ ደግሞ ስሜትን በማሸነፍ፣ ጥላቻን በመተው እና አቅምን በጋራ በማሰባሰብ የሚሳካ ታላቅ ሀገራዊ ርዕይ ነው። በዚህ አዲስ ምዕራፍ ውስጥ ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር የመንግሥት ቀዳሚው አጀንዳው ነው። ከሁሉም የዓለም ሀገራት ጋር የሚደረገው ግንኙነት የኢትዮጵያን ጥቅም እና ተጽዕኖ የሚያሳድግ መሆን አለበት ብለዋል። ይህ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በሌሎች ፍላጎት የምትመራ ሳይሆን በራሷ ብሔራዊ ጥቅም ላይ ተመስርታ የምትወስን ጠንካራ ሀገር መሆኗን ነው። በቀጣናውም ኢትዮጵያ የመረጋጋት እና የትብብር ማዕከል ሆና ትቀጥላለች። ጎረቤቶቿ በተፈጥሮ ያገኘቻቸው አጋሮቿ በመሆናቸው የጋራ ጥቅም፣ የሰላም እና የትብብር መርሆዎች የውጭ ግንኙነቷ መሠረት እንደሚቀጥሉ አጽንዖት ሰጥተዋል። በዚህም ኢትዮጵያ የራሷን ጥቅም በማስከበር እና በጋራ ጥቅም መርህ ላይ ተመስርታ የቀጣናው ተፅዕኖ ፈጣሪ ሀገር ለመሆን ትሰራለች። በመሆኑም የመደመር መንግሥት ምሥረታ የአስተሳሰብ ለውጥ፣ የሥልጣኔ ግንባታ ጥሪ እና ብሔራዊ ጥቅምን ማዕከል ያደረገ አዲስ ሀገራዊ የከፍታ ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ስኬታማ የሚሆነው ደግሞ መንግሥት፣ ፓርላማ፣ ተቋማት እና ሕዝብ በአንድ ራዕይ ሲተባበሩ ብቻ ነው። ኢትዮጵያ ያላትን ታሪካዊ ቅርስ ወደ ዘመናዊ ሥልጣኔ በመቀየር፣ ብሔራዊ ጥቅሟን በማስከበር እና በቀጣናው የሰላም አርበኛ ሆና በመቆም አዲስ ታሪክ ለመጻፍ ተዘጋጅታለች። የኢትዮጵያ ዘላቂ ብልጽግና፣ የሕዝቦቿ አንድነት እና የቀጣናው ደህንነት የሚረጋገጠው አዲስ ኢትዮጵያዊ ሥልጣኔ በሚገነባበት መጠን ነው።
"የነጭ ወርቅ" ጸጋና በረከት
Oct 7, 2026 261
ገንዳውኃ፤ መስከረም 27/2019 (ኢዜአ)፦ "የነጭ ወርቅ" ጸጋና በረከት፤ የኢኮኖሚ ምንጭና የስልጣኔ መገለጫ በአለም ላይ የኢንዱስትሪ አብዮት የተጀመረው በጨርቃ ጨርቅና ሱፍ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት መሆኑን የታሪክ መዛግብት ያወሳሉ። በ18ኛው እና 19ኛው ክፍለ ዘመን አውሮፓ ውስጥ የተቀሰቀሰው የኢንዱስትሪ አብዮት ዋነኛ አንቀሳቃሽ ኃይል የጥጥ ማቀናበሪያ ማሽኖችና የጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች መከፈት ነበር። በእንግሊዝ የተቀጣጠለው የጨርቃጨርቅና የሱፍ ኢንዱስትሪ አብዮት የሰብል ልማት የሚካሄድበትን መሬት ወደ በግ ፣ግጦሽና ጥጥ ልማት በመቀየሩ "በጎች ሰዎችን እየበሉ ነው" ብሎ በመጻፍ ታዋቂው ጸሃፊ ቶማስ ሙር መቃወሙ ይታወሳል።   በአገራችን ኢትዮጵያም እንደ አፋር፣ የአማራ ክልል ሰሜን ምእራብና ምእራብ ቆላማ አካባቢዎች የጥጥ ምርት በስፋት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው ግብአት በመዋል የአገራችን እድገት እንዲፋጠን በማስቻል የሚታወቁ ናቸው። በምእራብ ጎንደር ዞን በኢትዮጵያ የጥጥ ምርት ታሪክ ቀደምትና የጥጥ ምርት መገኛ ዋና ማዕከል በመሆኑ ከሚያስገኘው ጥቅም በመነሳት የአካባቢው ህዝብ ጥጥን “ነጩ ወርቅ” እያሉ ይጠሩታል። ዞኑ ለሰሊጥ፣ አኩሪ አተር፣ ማሽላ፣ ቦሎቄና ሌሎች የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙና ለኢንዱስትሪዎች ግብአት የሚውል ተኪ ምርቶችን በስፋት በማምረት ለአገራችን ልማት የጀርባ አጥንት ነው። ለገበያ ተኮር ምርቶች ሰፊ የእርሻ መሬት፣ ምቹ ስነ ምህዳርና የአየር ንብረት፣ እምቅ የውሃ ሃብት ያለው በመሆኑ ለመካናይዜሽን የግብርና ልማት የተመቸ ነው። ምንም እንኳ ዞኑ ለተኪ ምርትና ለወጭ ንግድ የሚሆኑ ምርቶች ያለው ጸጋ ከፍተኛ ቢሆንም የዛሬው የጽሁፍ መነሻ “6ኛውን የዓለም የጥጥ ቀን (World Cotton Day)” አስመልክቶ በጥጥ ልማት ላይ ያጠነጠነ መሆኑ አልቀረም። ያለውን የጥጥ ልማት ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የዞኑ አርሶ አደሮችና ከአገራችን የተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ባለሃብቶች የጥጥ ልማትን በስፋት እያካሄዱ እንደሚገኙ ይታወቃል።   በዞኑ ከ300 በላይ ባለሃብቶች እና ከ10 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ በየዓመቱ ከ24 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በጥጥ በማልማት ከ400 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት ተሰብስቦ ለገበያ ያቀርባል። ከእርሻ እስከ ጥጥ መዳመጫና ጨርቃጨርቅ ፋብሪካዎች፣ ከማከማቸት፣ ማጓጓዝና ወደ ውጭ መላክ ያለው የንግድና የእሴት ሰንሰለት ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ለአገር በሚያስገኘው የውጭ ምንዛሬና ለህብረተሰቡ በሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጥቅም “ነጩ ወርቅ” ተብሎ ለመጠራት በቅቷል። በዞኑ የጥጥ መዳመጫ ፋብሪካዎችና የምርጥ ዘር አቅርቦት መስፋፋት በዘርፉ የሚሳተፉ አርሶ አደሮችና ባለሃብቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ እንዲመጣ አስችሏል።   የጥጥ ምርት የኢኮኖሚ መሠረት ብቻ ሳይሆን የአገራት የጥበብ፣ የባህልና የስልጣኔ መገለጫና ማስተሳሰሪያም ጭምር መሆኑን የኢትዮጵያን የሸማ፣ የጥበብና የባህል አልባሳት በዓለም ደረጃ ያለውን ተወዳጅነት ማየት በቂ ነው። በጥጥ የተሰሩ ባህላዊ አልባሳት የህብረተሰቡን ውበት፣ ታሪክና ጥበብ የሚያንፀባርቁ በመሆናቸው የማንነት መግለጫም ጭምር ነው። በኢትዮጵያውያን እናቶች ውብ እጆች ተፈትሎ፤ ድርና ማግ ተሰናስሎ በመሸመን በባህላዊ እንዱስትሪ የሚመረተው የባህል አልባሳት ዛሬ የአገራችን መገለጫ ለመሆን በቅቷል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም