ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ በ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ሁለተኛ የወርቅ ሜዳልያ አሳካች

አዲስ አበባ፤ነሐሴ 3/2018 (ኢዜአ)፦በአሜሪካ ኦሬጎን እየተካሄደ ባለው 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ኢትዮጵያ ሁለተኛ የወርቅ ሜዳልያ አሳክታለች።

ዛሬ ማለዳ በተደረገው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ የ3000 ሜትር ውድድር አትሌት ዮርዳኖስ ፅጋብ የወርቅ ሜዳሊያ አሸንፋለች።


 

አትሌቷ 8:43.65 የሆነ የግል ምርጥ ሰዓቷን በማስመዝገብ ነው ለሀገሯ የወርቅ ሜዳልያ ያስገኘቸው።

ሌላኛዋ አትሌት ሽቶ ጉሚ 8:45.06 በሆነ ሰዓት ውድድሯን ሁለተኛ ሆና በማጠናቀቅ የብር ሜዳልያ አሳክታለች። አትሌቷ በተመሳሳይ በ5000 ሜትር የብር ሜዳልያ ማግኘቷ ይታወሳል።


 

በአሜሪካ ኦሪገን እየተከናወነ የሚገኘው ከ20 ዓመት በታች የዓለም አትሌቲክስ ውድድር ዛሬ ይጠናቀቃል።

ኢትዮጵያ በውድድሩ 2 ወርቅ ፣ ሦስት ብር እና 1 ነሐስ ሜዳልያ በመሰብሰብ በሜዳልያ ሰንጠረዡ ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም