የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል - ኢዜአ አማርኛ
የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች ሻምፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 3/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ ከ20 ዓመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል።
ከሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአሜሪካ ኦሬጎን እየተካሄደ ባለው ሻምፒዮና ከ147 ሀገራት የተወጣጡ ከ1800 በላይ አትሌቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ኢትዮጵያም በሻምፒዮናው ላይ ተሳትፎ እያደረገች ሲሆን እስከ አሁን ሁለት የወርቅ፣ ሶስት የብር እና አንድ የነሐስ በድምሩ ስድስት ሜዳሊያዎችን በማግኘት ሶስተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አሜሪካ በስምንት ወርቅ፣ ስድስት የብር እና አራት የነሐስ በድምሩ 18 ሜዳሊያዎችን በማግኘት አንደኛ ደረጃን ይዛለች።
ጣልያን በሶስት ወርቅ እና ሁለት ነሐስ በድምሩ አምስት ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።
እስከ አሁን 35 ሀገራት የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ ገብተዋል።
ሻምፒዮናው ዛሬ ማምሻውን በሄይዋርድ ፊልድ ስታዲየም ይጠናቀቃል።