ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦቢኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡- - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኦቢኤን ጋር በነበራቸው ቆይታ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡-
*ምርጫን በተመለከተ:-
ለህዝባችን ቃል እንደገባነው፤አቅማችን በፈቀደ መጠን ምርጫው ዲሞክራሲያዊ እንዲሆን፤ ህዝቡ በሰላማዊ መንገድ ወጥቶ እንዲመርጥ ለማድረግ እንደ መንግስት ድርሻችንን ተወጥተናል።
ህዝቡ የፖለቲካ ሥልጣን በኃይል መያዝ መቆም አለበት ማለት፤ የፖለቲካ ሥልጣን በሰላማዊ መንገድ፤ በምርጫ፤ በህዝብ ተሳታፊነት እንጂ፤ አንድ ቡድን መጥቶ በኃይል መያዝ አይችልም ብሏል
የኢትዮጵያ ህዝብ ከዳር እስከ ዳር በአንድ ድምፅ መልዕክቱን ለእኛም ለሌሎችም አስተላልፏል።
በዲሞክራሲያዊ መንገድ መቃወም፤ መሞገት መጠየቅ ነገር ግን የሚሆነኝን መንግስት መምረጥ እችላለሁ ብሏል
ሕዝባችን ለዲሞክራሲ ያለው ቁርጠኝነት፤የዲሞክራሲ ሥርዓትን ለመገንባት ያለው ፍላጎት በግልጽ ታይቷል።
በሰላማዊ መንገድ መርጫለሁ፤ የመረጥኩት ደግሞ የገባህልኝን ቃል እንደምትፈፅም ስላመንኩ ነው ብሏል
7ኛው ምርጫ በሰላምም፤ በዲሞክራሲያዊ መንገድም በህዝብ ተሳትፎም፤ በፓርቲዎች ተሳትፎም ልዩ ታሪክ ነው።
*መደመርን በተመለከተ፦
መደመር በፖለቲካ ማሻሻያ በኢኮኖሚ ማሻሻያ በማህበራዊ ማሻሻያ ውስጥ ትልቅ ውጤት አምጥቶልናል
መደመር ከአስር በላይ በሚሆኑ ቋንቋዎች ተተርጉሟል
የመደመር ሀሳብ በተጨባጭ ችግር ፈቺ በተጨባጭ ለውጥ እያመጣ ያለ እይታ ነው
አንድ ሰው የመደመር ሀሳብ ሲያነብ የመደመር ሀሳብ ጥያቄ ሲሆንበት መመርምር ይችላል ይዘቱ ውስጥ ብዙ ታሪክ ብዙ እውቀት አለበት ብዙባህል፣ ብዙ ማንነት እንደያዘ ትልቅ ትርጉም እንዳለው ይረዳል