ENA - ኢዜአ አማርኛ
አርእስተ ዜና
የኢትዮጵያ ማንሠራራት እና የመግባባት ዴሞክራሲ ልዕልና
Sep 17, 2026 144
ኢትዮጵያ ከተለመደው የፖለቲካ የመገፋፋት አካሄድ ወጥታ፣ ሁሉንም ዜጎች የሚያካትትና በጋራ መግባባት ላይ የተመሠረተ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ላይ ትገኛለች። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ጉዞ ሀገሪቱን በፅኑ መሠረት ላይ ለማቆም እና ብሔራዊ መግባባትን በዘላቂነት ለማምጣት የሚያስችል ስኬታማ ተግባር ነው። የምክክሩ ሂደት በሃሳብ መግባባትን ማዕከል ያደረገ በመሆኑ፣ የፖለቲካ ስጋቶችን እና አለመተማመኖችን በእጅጉ ይቀንሳል። የመግባባት ዴሞክራሲ ዋነኛ መርህ ውሳኔዎች በአብላጫ ድምፅ ብቻ ሳይሆን በሁሉም ወገኖች ስምምነት ላይ እንዲመሰረቱ ማድረግ ነው። በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ሂደትም መግባባት ላይ የተደረሰባቸው አጀንዳዎች ከጥቂቶች ፍላጎት የፀዳ፣ የብዙሃኑ ድምጽና ሀሳብ ጎልቶ የወጣበት ነው። ምክክሩ ከተለመደው የፖለቲካ አካሄድ ተላቆ በምክንያት ላይ የተመሰረተ የውይይትና የመደማመጥ ባህል የዳበረበት ሲሆን ይህ መንገድ ለዘመናት የቆዩ አለመግባባቶችን በሰከነ መንፈስ ለማስተናገድ አስችሏል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክር ኮሚሽን ከአስፈጻሚው አካል ጣልቃ ገብነት ነፃ በመሆን በቀጥታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተጠሪ እንዲሆን መደረጉ፣ ተቀባይነትና ተአማኒነት እንዲያገኝ አስችሏል። በተለመደው የፖለቲካ ሥርዓት አጀንዳዎች የሚቀረጹት በጥቂት ልሂቃን ቢሆንም፣ በዚህ ምክክር ግን አጀንዳዎች ከታችኛው የህብረተሰብ ክፍል (ከወረዳ ደረጃ) በተሰበሰቡ ግብዓቶች ላይ ተመስርተው እንዲዘጋጁ መደረጉ ህዝቡ የሂደቱ ባለቤት እንዲሆን አድርጓል። የተለያዩ ማህበረሰቦች ድምፃቸው እኩል ክብደት ኖሮት ውሳኔዎች ላይ እንዲሳተፉ መደረጉ የምክክሩ አንዱ ስኬት እና የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጉዞ ማሳያ ነው ማለት ይቻላል። ከዚህ በፊት የነበረው የአሸናፊና ተሸናፊ ፖለቲካ አካሄድን ያስቀረው ሀገራዊ ምክክሩ በጠረጴዛ ዙሪያ በመቀመጥ ሁሉንም አካላት አሸናፊ የሚያደርግና የጋራ መፍትሔ ማፈላለጊያ መድረክ ሆኗል። የምክክር ጉባኤው መጠናቀቅ የሂደቱ ማብቂያ ሳይሆን ወደ ተግባራዊ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ነው። ኮሚሽኑ ያሰባሰባቸውን ከ400 በላይ ምክረ-ሀሳቦች ለተቋማት በማቅረብ እና የተገኙት ስምምነቶች መሬት ላይ መውረዳቸውን የሚከታተል የቁጥጥር ሥርዓት እያዘጋጀ ይገኛል። በምክክሩ ላይ የታየው ሰፊና ሁለንተናዊ የህዝብ ተሳትፎ ኢትዮጵያን በጠንካራ መሰረት ላይ በመገንባት፣ ብሔራዊ መግባባትን እውን ለማድረግ እና የጋራ መጻኢ ዕድልን ለመቅረጽ የሚያስችል የዚህ ዘመን የመግባባት ዴሞክራሲ ተጨባጭ ማሳያ ነው።
ግብፅ የዓባይን ጉዳይ ለውስጥ ፖለቲካ ችግሮቿ መሸፈኛ ለማድረግ እየሞከረች ነው
Sep 17, 2026 247
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ የምታደርገው የፖለቲካ ዘመቻ የራሷን ውስጣዊ ችግሮች ለመሸፈን የምትጠቀምበት ስልት መሆኑን የስትራቴጂክ ጥናትና የትስስር ኢኒሸቲቭ ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ አብዱሻኩር አብዱሰመድ ገለጹ። የግብፅ መንግስት አባይን ለፖለቲካ ፍጆታ ማዋሉ እና የተፋሰሱን ሀገራት በጠላትነት ፈርጆ ማሳየቱ በግብጻውያን ዘንድ ኢትዮጵያ ላይ የተሳሳተ ጥላቻ እንዲኖራቸው ለማድረግ መሆኑን ከፍተኛ ተመራማሪው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል። የሚዲያ ዘመቻ እና የተሳሳተ ትርክት ከውጤታማነቱ ይልቅ የግብፅን ህዝብ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን አመልክተዋል። የግብፅ መንግስት ዓባይ ብቸኛው የውሃ ምንጭ እንደሆነ በማስመሰል ለማሳመን ረዥም ረቀት መጓዟን ጠቅሰዋል። ይህ የተሳሳተ አመለካከት አንዳንድ ግብፃዊያን በሌሎች ሀገራት የሚደረጉ የልማት ስራዎች የግብፅን የውሃ ድርሻ የሚነጥቁ አድርጎ እንዲመለከቱ ምክንያት መሆኑን ተናግረዋል። የዚህ ሁሉ ዘመቻ ዋና ዓላማ በግብፅ ውስጥ የሚስተዋሉ ፖለቲካዊ እና ማሕበራዊ ቀውሶች ትኩረት እንዳያገኙ መሸፈኛ ማድረግ መሆኑን ነው ተመራማሪው ያስረዱት። አክለውም፣ ትውልዱ ይህንን የተሳሳተ ትርክት እንደ ፍጹም እውነት እንዲቀበለው ግብፅ የምትሰራው ስራ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን አንስተዋል። ግብፅ ሜዲትራኒያን እና ቀይ ባህርን ጨምሮ በርካታ የባህር ዳርቻዎች እና የከርሰ ምድር የውሃ ሀብቶች እንዳሏት ተመራማሪው ጠቁመዋል። ሆኖም በዓባይ ላይ ብቻዋን የመወሰን መብት እንዲኖራት ትፈልጋለች፣ ይህ ፍጹም ተቀባይነት የሌለው ጉዳይ ነው ብለዋል። የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) ሁሉም ሀገራት ፍትሃዊ የመጠቀም መብት እንዳላቸው በግልጽ እንደሚያስቀምጥም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን ጨምሮ ለሃይድሮ ኤሌክትሪክ ሃይል ለመጠቀም የማንንም ፈቃድ እንደማትጠይቅ እና ይህ ተፈጥሯዊ መብቷ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ነው። ሀገሪቱ ንጹህ፣ ታዳሽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ የኤሌክትሪክ ሃይል በማመንጨት ሚናዋን በሚገባ እየተወጣች ትገኛለች። ኢትዮጵያ ከጅማሮው አንስቶ ከታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ጋር በትብብር ለመስራት ተደጋጋሚ ጊዜ ጥሪ አድርጋለች። ይሁን እንጂ ግብፅ የመረጠችው አካሄድ ለጋራ ዕድገት እና ለፍትሃዊ ተጠቃሚነት ከሚያስፈልገው የትብብር አማራጭ ጋር ፍጹም የተቃረነ መሆኑን ከፍተኛ ተመራማሪው አንስተዋል። ጊዜያዊ የፖለቲካ ቅስቀሳዎች ዕድሜያቸው አጭር ነው ያሉት ተመራማሪው በህዝቦች ውስጥ የሚፈጥረው የተሳሳተ ግንዛቤ በጊዜ ሂደት እንደሚቀረፍም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።
የዓባይ ወንዝና የቀይ ባሕር ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር ማዕከላዊ አጀንዳዎች ናቸው
Sep 17, 2026 223
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ የውሃ ሀብት ተጠቃሚነትና የባሕር በር ባለቤትነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር ማዕከላዊ ስትራቴጂክ አጀንዳዎች መሆናቸውን ምሁራን ገለጹ። የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የዓባይ ወንዝና የባሕር በር ጉዳዮችን በተመለከተ የፓናል ውይይት አካሂዷል። የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁሩ ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) በፓናሉ ላይ እንዳሉት፣ የዓባይና የባሕር በር ጉዳዮች በጂኦፖለቲካዊና በልማታዊ ትስስራቸው ተነጣጥለው ሊታዩ አይገባም። የዓባይ ወንዝ ጉዳይ የልማት፣ የኢኮኖሚና የቀጣናዊ ትብብር ማዕከል በመሆኑ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ አቀራረብ ሊከተል እንደሚገባ አመልክተዋል። ሁለቱን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች በተቀናጀ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይና የልማት ስትራቴጂ መሠረት መምራት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። በዚህም የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ የውሃ ሀብት ተጠቃሚነትና የባሕር በር ባለቤትነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር ማዕከላዊ ስትራቴጂክ አጀንዳዎች መሆናቸውን አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ መሪ ተመራማሪ አቶ ሰለሞን ተፈራ በበኩላቸው፣ የባሕር በርና የዓባይ ጉዳዮች ተነጣጥለው ሳይሆን በአንድ ሀገራዊ ማዕቀፍ ውስጥ ተቀናጅተው ሊታዩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ጉዳዮቹ በምሁራን ጥናትና በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሊመሩ እንደሚገባም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና ገቨርናንስ መምህርና ተመራማሪ ተስፋዬ ጂማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የባሕር በር ጉዳይ ከሉዓላዊነት፣ ከኢኮኖሚ ዕድገትና ቀጣናዊ ሰላም የተቆራኘ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው ብለዋል። የሀገር ህልውናን፣ ደህንነትንና የዜጎችን ማኅበራዊ ልማት ከሚያሳድጉ ጉዳዮች አኳያ፣ የባሕር በርና የዓባይ ወንዝ ጉዳዮች በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ ሊታዩ እንደሚገባ አንስተዋል። ምሁራን በጥናትና ምርምር የተደገፈ የፖሊሲ ግብዓት በማቅረብ፣ እንዲሁም የሕዝብ ግንዛቤን በማሳደግ፣ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በሚደረገው ሂደት አዎንታዊ ሚና ማበርከት እንደሚችሉም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት የዚህ ትውልድ አደራ ነው
Sep 17, 2026 301
ቀይ ባሕር ለኢትዮጵያ የውሃ አካሏና በሯ ብቻ አልነበረም፤ የሺህ ዘመናት የንግድ፣ የሥልጣኔ፣ የሃይማኖትና የባህል መገለጫ፤ ከዓለም ጋር ያላትን መስተጋብር ማሳለጫ መስመር ጭምር እንጂ። የአክሱም ሥልጣኔ በቀይ ባሕር የጠረፍ ከተማዋ በኩል የከተመው የአዱሊስ ወደብ ላይ መልህቁን በመጣል ከዓረብ ልሳነ ምድር እስከ ሜዲትራኒያን፣ ከሕንድ ውቅያኖስ እስከ የአፍሪካ የባሕር ጠረፎች ድረስ የነበረው ሁለንተናዊ ትስስር የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነትና የንግድ ማዕከልነት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ገናና የታሪክ አስረጂ ነው። ኢትዮጵያ ምፅዋና አሰብ ወደቦቿን በግፍ ተነጥቃ ከቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካ ከተገለለች የጉልማሳ ዕድሜ አስቆጠረች፤ የቀጣናው የሥልጣኔ ፈር ቀዳጅ፣ የንግድ መስመር፣ የዲፕሎማሲ ማዕከል የነበረች ሀገር አምጣ በወለደቻቸው ልጆቿ ጭምር ደባ ተሰራባት ። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር የነበራት ጥብቅ ቁርኝት የዘመኑ የፖለቲካ ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ከጥንታዊ የንግድና የሥልጣኔ ታሪኳ ጋር የተሳሰረ የትውልድ የህልውና ጉዳይ የሚሆነው። ግብጽ እና ሌሎች ታሪካዊ ጠላቶች የሀገር ውስጥ ባንዳዎችን በማስተባበር በፈጸሙት ደባ ኤርትራን ከኢትዮጵያ በመገንጠል የሺህ ዘመናት ገናና የሥልጣኔ ልዕልናዋን የሚያሳጣ ክህደት ፈጽመዋል። ይኸውም ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብና ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች ያለችውን የቀጣናው ሀያል ሀገር የሎጂስቲክስ እንቅስቃሴ በማስተጓጎል በገቢና ወጪ ንግድ እና በኢንቨስትመንት ፍሰት ላይ ዕንቅፋት ደቅኗል። የዓለም ባንክ መረጃ እንደሚያመለክተው ከ95 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጵያ የገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ - ጅቡቲ ኮሪደር ብቻ የተወሰነ ነው፤ ከዚህም ባሻገር ቀይ ባህር የምስራቅ አፍሪካ ቀጣና የሰላምና የሕልውና ጉዳይ እየሆነ መጥቷል። ከቀይ ባሕር በቅርብ ርቀት የምትገኘው ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ሰፊ የሕዝብ ቁጥርን፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገትን፣ የሰላምና የደኅንነት ስጋት እንዲሁም የሕልውና ጉዳይን ሁሉ ታሳቢ ያደረገ ነው። ኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ፍትሐዊና ምክንያታዊ ነው። ህልውናን ማረጋገጥ፣ ከሌሎች ሀገራት ጋር የጋራ ጥቅምን በማስጠበቅ የኢኮኖሚ፣ የሰላምና ደኅንነት ትብብርን ማጠናከርና የጋራ ብልጽግናን የማረጋገጥ ግብም አንግቧል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጎረቤት ሀገራትን በሀይልና በመሰረተ ልማት በማስተሳሰር ኢትዮጵያ በጋራ ለመልማትና ለማደግ ያላትን ፅኑ ፍላጎት ያሳያል። ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ጂኦ ፖለቲካ እስረኛ ሆና ያሳለፈቻቸው ዓመታት በዓባይ ዘመን ትውልድ ሊያከትም ይገባል፤ ጥያቄዋም በዓለም አቀፍ የሁለትዮሽና ባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ መድረክ ቅቡልነት እያገኘ እንዴት ይፈጸም ወደሚል ወሳኝ ምዕራፍ መሸጋገሩ ይሄን እውነት ያንጸባርቃል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአንድ ወቅት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ፤ ኢትዮጵያን የባሕር በር አይገባትም የሚል ሰው የተፈጥሮን ህግ የሳተ መሆኑን አስረድተዋል። ቀይ ባሕርና ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ተነጣጥለው መኖር እንደማይችሉ፤ ይሄንንም አምኖ መቀበል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ጽናትን፣ ፈጠራ፣ ትብብርና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ሃሳብ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤም የኢትዮጵያን የዕድገትና ብልፅግና ተስፋና መፃኢ ዕድል አብራርተዋል። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ማግኘት ከምንም ነገር በላይ ቀዳሚውና ወሳኙ የኢኮኖሚ ጉዳይ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ብሔራዊ ጥቅሟንና የአፍሪካን ድምፅ ለማስተጋባት የጉዳዩን ወሳኝነት ለዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ በግልጽ ተናግረዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጂጌ (ዶ/ር) ቀደም ሲል ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያውያን በተፈጸመ የታሪክ ስህተት የትውልድን ዘላቂ ብሔራዊ ጥቅም አሳልፈን የምንሰጥ ሕዝቦች አይደለንም ብለዋል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አማካኝነት የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ በይፋ በቀረበ ማግስትም በሕዝብ ልብ ውስጥ ለጥቂት ዓመታት ተዳፍኖ የቆየው ቁጭት በአጭር ጊዜ ውስጥ ቅቡልነት ማግኘቱን ገልጸዋል። በቀጣይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅም ዙሪያ ልዩነት ሊኖረን አይገባም ያሉት ሚኒስትሩ፤ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ እንዲያገኝ ትብብርና አንድነት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር)፤ የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ቀጣናዊ ትብብርና የጋራ ብልጽግናን ማዕከል ያደረገ ነው ብለዋል። ጥያቄው ታሪካዊ፣ ተፈጥሯዊ፣ መልክዓ ምድራዊና ሕጋዊ መሰረት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትንና የሕዝብ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ ንግድና ኢንቨስትመንትን የማሳለጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። የተባበሩት መንግሥታት የባሕር ሕግ ስምምነትና ሕግጋትም ወደብ አልባ ሀገራት ወደ ባሕር የመድረስና የመጠቀም መብታቸውን የሚደግፍ ድንጋጌና ማዕቀፍ እንዳለው አስረድተዋል። በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ቀንድና የውሃ ጂኦፖለቲካ ከፍተኛ ተመራማሪ ጋሻው አይፈራም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የታሪክ ስብራትን በማረም ኢትዮጵያን ከገናና ታሪክና ሥልጣኔዋ የማስታረቅ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በማጠናከር የአፍሪካን ኢኮኖሚ ውህደት ለማሳለጥ በምታደርገው ጥረት የባሕር በር ባለቤትነት አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል። የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄው ዓለም አቀፍ ቅቡልነት እያገኘ መሆኑን በማንሳት፤ ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ ተቋማትና መገናኛ ብዙኅን የጉዳዩን አስፈላጊነት በቅጡ መገንዘባቸውን አብራርተዋል።
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት ወሳኝ የትብብር ማዕከል መሆን አለበት
Sep 17, 2026 315
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት ወሳኝ የትብብር ማዕከል መሆን እንዳለበት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢጋድ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2026 እስከ 2035 ለ10 ዓመታት የሚተገብረውን የቀጣናው የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት ዕቅድ እና የኢጋድ ቀጣና የግብርና ዘር ፖሊሲ የባለሙያዎች ግምገማ በማድረግ በሚኒስትሮች አጸድቋል። የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቋቋም በትብብር የምንቆምበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው ያለነው ብለዋል ። ኢጋድ በቀጣናው ሀገራት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ቀዳሚ መርሁ መሆኑን ገልጸዋል። የኢጋድ የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት የ10 ዓመት ዕቅድ በቀጣናው ቀጣይነት ያለውና አይበገሬ የምግብ ሥርዓት መገንባት ያስችላል ብለዋል። የኢጋድ ቀጣናዊ የግብርና ዘር ፖሊሲም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም ዘላቂ ኢኮኖሚ ማንበር እንደሚያስችል ገልጸዋል። በአፍሪካ አህጉራዊ ሽግግር ለመፍጠር የኢጋድ ኢኒሼቲቮች ጉልህ አበርክቶ እንዳላቸው ጠቁመው፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የኢጋድ ቀጣና ሀገራት ሕዝባቸውን፣ ሀብታቸውንና እውቀትን በማስተባበር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከርና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባቸው ገልጸዋል። የግብርና ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ጌታቸው ድሪባ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢጋድ ቀጣና ሀገራት በባህል፣ በታሪክና በኢኮኖሚ የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ መዋቅር ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰው፤ ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብና የግብርና ዘር ፖሊሲ ዋና አጀንዳዋ ነው ያሉት ከፍተኛ አማካሪው፤ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ገልጸዋል።
ፖለቲካ

ምክክሩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል እሳቤና ዝግጁነት የተሰነቀበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው- ምሁራን
Sep 17, 2026 304
ቦንጋ፣ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ እሳቤ የተሰነቀበትና ለሀገር ግንባታ የዜጎች ሁሉ ዝግጁነት የታየበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑን የታሪክና የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን ገለጹ። በአዲስ አበባ የተካሄደውና ከመላ ሀገሪቷ የተውጣጡ ከ4 ሺህ በላይ ጉባኤተኞች የተሳተፉበት የምክክር ጉባኤ በስኬት ተጠናቋል። የዘንድሮውን አዲስ ዓመት የተቀበልነው ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት የጋራ ቃል ኪዳን የተሰነቀበት ታሪካዊ ጉባኤ ከተጠናቀቀ በኋላ ነው። በአዲስ ዓመት አዲስ ተስፋ በመሰነቅ፤ በህብረ ብሄራዊ አብሮነት በመድመቅ የ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በመቀበል ሌላ የህይወት ምእራፍ የተጀመረበትም ነው ማለት ይቻላል። የዘንድሮው አዲስ ዓመት ኢትዮጵያዊያን በችግሮቻቸው ላይ መክረው ለመፍትሄው የጋራ አቋም የያዙበት፤ አዲስ መንግስት የሚመሰረትበትና ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባት ሂደት ተጠናክሮ የሚቀጥልበት ነው። ከዚሁ ጋር በተገናኘ ኢዜአ ያነጋገራቸው የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን፤ አዲሱ ዓመት በምክክር የተሸጋገርንበትና እንደ ዜጋም ለሀገራዊ ልማት ትልቅ ተስፋ የተሰነቀበት ነው ብለዋል። በዩኒቨርሲቲው የፖለቲካና አለም አቀፍ ግንኙነት የትምህርት ክፍል መምህር ዘሪሁን ያሬድ፤ ለሀገራዊ ችግሮች እልባት ለማበጀት ምክክርን ሁነኛ መፍትሄ ለማድረግ ወደ ምክክር መገባቱ በራሱ ዘመናዊ እሳቤ መሆኑን ገልፀዋል። በዚህም ስኬታማ መሆን የተቻለበት ታሪካዊ አጋጣሚ መፈጠሩን አንስተው በችግሮች ላይ መክረንና ለእልባቱ ተዘጋጅተን ወደ አዲስ ዓመት መሸጋገራቸው ለሁላችንም ትልቅ ተስፋ ነው ብለዋል። ሀገራዊ ምክክሩ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል የጋራ እሳቤ የተሰነቀበትና ለሀገር ግንባታ የዜጎች ሁሉ ዝግጁነት የታየበት ታሪካዊ አጋጣሚ መሆኑንም ገልጸዋል። የምክክሩ ዓላማ ሀገራዊ ችግሮችን በዘላቂነት የመፍታት ጥረት መሆኑን አንስተው ከሃይል አማራጭ ይልቅ በውይይት የሚያምን ትውልድ በመፍጠርና ሀገር በመገንባት ሂደትም ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህር ሰለሞን ማሞ፤ ሀገራዊ ምክክሩ የግጭትና የጦርነት አዙሪት የሚያበቃበትን እድል የፈጠረና ምክክር የችግሮች ሁሉ አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን ሁሉም የተረዳበት መሆኑን ገልጸዋል። በምክክሩ የታየውና ሁላችንም የተገነዘብነው የዜጎች እሳቤ ከምንም በላይ ሀገርን ያስቀደመና ለችግሮች ሁሉ ዘላቂ መፍትሄን መሻት መሆኑን ነው ብለዋል። በመሆኑም በአዲስ ዓመት፤ አዲስ ተስፋ በመሰነቅ ለተመከረባቸው አጀንዳዎች በሂደት ተፈፃሚነት በጋራ መትጋት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።
ግብፅ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን የዓባይ ተፋሰስ እውነታ መቀበል አለባት - አምባሳደር ተሾመ ቶጋ
Sep 17, 2026 496
ዓባይ ወንዝ የተፋሰሱ ሀገራት የሚጋሩትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም ከሆኑ ድንበር ተሻጋሪ የውሃ ሀብቶች ውስጥ የሚመደብ ነው። ግብፅ በወንዙ ፍሰት ላይ ምንም ዓይነት አስተዋጽኦ ሳታበረክት የታችኛው ተፋሰስ ዋና ተጠቃሚ ሆና ቆይታለች። ኢትዮጵያ ደግሞ፣ የዓባይ ወንዝ የውሃ ፍሰት 86 በመቶ ድርሻ አላት። በግብፅ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ተሾመ ቶጋ በ«ፐልስ ኦፍ አፍሪካ» (Pulse of Africa) መድረክ ላይ “Egypt Must Align Its Nile Strategies with the Realities of 21st Century” በሚል ርዕስ ባሰፈሩት ጽሑፍ፤ ግብፅ በወንዙ አጠቃቀም ላይ “ታሪካዊ መብቶች አሉኝ” በሚል አቋም ለረጅም ጊዜ መያዟን አመልክተዋል። እንደ አምባሳደሩ ገለጻ፣ ግብፅ የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ይሁንታ በሌለበት የቅኝ ግዛት ስምምነቶች ላይ የሙጥኝ ማለቷ ከዘመኑ ዓለም አቀፍ የውሃ ሕግ መርሆዎች ጋር የሚስማማ ማዕቀፍ ለመዘርጋት ትልቅ ዕንቅፋት ሆኗል። እ.አ.አ በ1959 የተፈረመው የቅኝ ግዛት ውል የዓባይን አጠቃላይ የውሃ ድርሻ የሌሎች ተፋሰስ ሀገራትን ባላሳተፈ መልኩ ለግብፅና ሱዳን ብቻ የሰጠ መሆኑን አምባሳደሩ አውስተዋል። መሰረታዊ መነሳት ያለበት ጥያቄ «ግብፅ በዓባይ ወንዝ ላይ ያላት ፍላጎት ሳይሆን፣ ያ ፍላጎት የሌሎችን የተፋሰስ ሀገራት ፍትሐዊ መብቶችና የልማት ትልሞችን በሚጎዳ መልኩ መፈጸም አለበት ወይ?» የሚለው ነው ብለዋል። የሕዝብ ቁጥር ዕድገት፣ የአየር ንብረት መዛባት፣ የምግብ ዋስትና ስጋቶች እና አዳዲስ የኢነርጂ ፍላጎቶች የዓባይ ወንዝ አስተዳደርን መሰረታዊ በሚባል ሁኔታ መቀየራቸውን አንስተዋል። የዓባይን ወንዝ በቀድሞ ታሪካዊ ውሎች ብቻ መመልከት ከእውነታው የራቀ እና ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጣ የማይችል አካሄድ መሆኑን ገልጸዋል። አምባሳደሩ በጽሑፋቸው እንዳመላከቱት፣ ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የውስጥ አቅሟን አስተባብራ የልማት ግቦቿን ማሳካት እንደምትችል ያረጋገጠ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ፕሮጀክት በወንዙ ላይ የነበረውን የኃይል ሚዛን እና ስትራቴጂካዊ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ መለወጡንም አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ተጨማሪ ልማት ማካሄድ የለባትም የሚሉ ሀሳቦች ተቀባይነት እንደሌላቸው ጠቅሰው፤ የፋይናንስ ክልከላዎችን በመጠቀም የኢትዮጵያን የልማት ፕሮጀክቶች ማስተጓጎል ፈጽሞ የማይቻል መሆኑን የሕዳሴው ግድብ በተግባር ማሳየቱን ገልጸዋል። አሁን ያለው ብቸኛው ዘላቂ መፍትሔ የሁሉንም ተፋሰስ ሀገራት ፍላጎት የሚያስተናግድ ዲፕሎማሲያዊ እና ፖለቲካዊ ማዕቀፍ መፍጠር መሆኑን አስገንዝበዋል። እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት ድንበር ተሻጋሪ ወንዞችን ከጎረቤቶቻቸው ጋር በውይይትና በድርድር እንደሚያለሙት ሁሉ፣ የዓባይ ተፋሰስ ሀገራትም ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማስተዳደር እንደሚችሉ የሌሎች ወንዞች ተሞክሮዎችን በመጥቀስ አምባሳደሩ አብራርተዋል። የተፋሰሱ ሀገራት እ.አ.አ በ2010 ይፋ ባደረጉት እና እ.አ.አ በ2024 በሕጋዊ መንገድ ጸድቆ ሥራ ላይ በዋለው አካታች የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት (CFA) አማካኝነት እያደረጉት ያለው ጥረት የላይኛው የተፋሰሱን ሀገራት ፍላጎትና ልማት መከበር እንዳለበት የሚያሳይ ነው ብለዋል። የፍትሐዊ ተጠቃሚነት ጉዳይ ከግድቡ ወይም ከኢትዮጵያና ግብፅ የሁለትዮሽ ግንኙነት የዘለለና የዘመኑን የኢኮኖሚና የውሃ አስተዳደር እውነታ ከግምት ውስጥ ያስገባ ነው። የእ.አ.አ 1993ቱ የጋራ መግባቢያ ስምምነት እና የእ.አ.አ 2015ቱ የመርሆዎች መግለጫ ስምምነት (Declaration of Principles) ኢትዮጵያ ሰላማዊ መፍትሔዎችን ለመፈለግ ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውን በጽሑፋቸው ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያውያን እና ግብፃውያን ጥልቅ ታሪካዊና ባህላዊ ትስስር እንዳላቸው አምባሳደሩ ገልጸው፤ ዓባይን እንደ ጠብ መጫሪያ ሳይሆን የሕዝቦች ማስተሳሰሪያ ድልድይ በማድረግ መጠቀም እንደሚገባ ተናግረዋል። አምባሳደሩ እንዳብራሩት፣ የኢትዮጵያ የሰላም እና የትብብር መንፈስ እንደ ድክመት ወይም መብትን አሳልፎ እንደ መስጠት ሊወሰድ አይገባም። ኢትዮጵያ ድህነትን የማስወገድ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ እና ለኢኮኖሚ የመጠቀም ሕጋዊ መብት አላት። ከዚህ ጎን ለጎንም በታችኛው ተፋሰስ ሀገራት ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ የውሃ ሀብቷን በፍትሐዊነት ለመጠቀም ትሰራለች ነው ያሉት። የዓባይ ወንዝ ተጠቃሚነት ጉዳይ በአሸናፊነትና በተሸናፊነት ላይ የተመሰረተ የውድድር መልክ መያዝ እንደሌለበትና ትክክለኛው አካሄድ በጋራ ትብብር መንፈስ መስራት መሆኑ ተገልጿል። ኢትዮጵያና ግብፅ በሃይድሮሎጂ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ፣ በድርቅና አውሎ ነፋስ አደጋዎች መከላከል፣ በግብርና ምርታማነት እና በኤሌክትሪክ ኃይል ንግድ በጋራ መስራት የሚችሉባቸው እድሎች እንዳሉ አምባሳደሩ አንስተዋል። ሀገራቱ በሃይድሮፓወር እና በውሃ ሀብት አስተዳደር በትብብር መስራት እንደሚችሉም አመልክተዋል። የኢነርጂ ንግድ፣ የኢንቨስትመንት ትስስር እና የቀጣናው ኢኮኖሚያዊ ትስስር ሁለቱ ሀገራት ወንዙን እንደ የጋራ የልማት ዕድል እንዲጠቀሙበት ትልቅ አቅም የሚፈጥር ነው ብለዋል። ግብፅ የ21ኛውን ክፍለ ዘመን የዓባይ ተፋሰስ እውነታ መቀበል እንዳለባትም ነው የተናገሩት። አሁን የሚያስፈልገው ግጭት ሳይሆን፣ በሉዓላዊ መብት፣ በፍትሐዊ አጠቃቀም፣ በጋራ መከባበር እና በጋራ ብልጽግና መርሆዎች ላይ የተመሰረተ አዲስ የፖለቲካ መግባባት መፍጠር ነው ብለዋል አምባሳደሩ። ዓባይ የአንድ አካል ብቸኛ ባለቤትነት የሚንጸባረቅበት ሊሆን አይገባም ያሉት አምባሳደሩ፤ የወደፊት የጋራ ዕጣ ፈንታ የሚገነባው በጋራ ኃላፊነት እና ትብብር ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።
በዞኑ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ
Sep 16, 2026 577
ገንዳውኃ፣ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ):- በምዕራብ ጎንደር ዞን ህብረተሰቡን በማሳተፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ። ዞኑ "አርቆ ማየት፣ አልቆ መስራት" በሚል መሪ ሀሳብ ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2018 የበጀት ዓመት የስራ እቅድ ግምገማ እና የ2019 የዕቅድ ትውውቅ መድረክ ዛሬ አጠናቋል። የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ እያሱ ይላቅ በወቅቱ እንደገለጹት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተከናወኑ የዘላቂ ሰላም ግንባታ፣ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል በቅንጅት ይሰራል። በያዝነው በጀት ዓመት የአገልግሎት አሰጣጥን በማቀላጠፍና የመሰረተ ልማት ዝርጋታዎችን በማፋጠን የሕዝቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ በበለጠ ትኩረት እንደሚሰራ አመላክተዋል። የአገልግሎት አሰጣጥን በማሻሻል ለህብረተሰቡ የተቀላጠፈ አገልግሎት ለመስጠት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን የማስፋፋት ስራ እንደሚከናወን ጠቁመዋል። ህብረተሰቡን በባለቤትነት በማሳተፍ እየተከናወኑ ያሉ የዘላቂ ሰላም ግንባታ ስራዎችም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። በብልፅግና ፓርቲ የዞኑ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንዳለው ማሩ በበኩላቸው፤ በፓርቲው አመራር ሰጪነት የዞኑን ሰላምና ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል ይበልጥ በትጋት ይሰራል ብለዋል። ዞኑ ለግብርና ልማት ያለውን ከፍተኛ አቅም በአግባቡ ለመጠቀም በቴክኖሎጂ የታገዘ አሰራርን ማስፋፋት ላይ በትኩረት ይሰራል ያሉት ደግሞ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አንዳርጌ ጌጡ ናቸው። ለዚህም የግብርና ቴክኖሎጂ፣ የምርጥ ዘርና የማዳበሪያ አቅርቦት በወቅቱ ማሰራጨት ላይ ቅንጅታዊ ተግባራት እንደሚጠናከሩ አመልክተዋል። በተጨማሪም የመስኖ ልማትን ለማስፋፋት የውሃ መሳቢያ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት ለማስተዋወቅና ለማዳረስ በትኩረት እንደሚሰራ አስታውቀዋል። በመድረኩ በተጠናቀቀው በጀት አመት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ወረዳና ከተማ አስተዳደሮች የእውቅና ሽልማት ተሰጥቷል።
የኢትዮጵያ ማንሰራራት የአፍሪካን ሕዳሴ ያበስራል - የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት
Sep 15, 2026 1062
ኢትዮጵያ አዲሱን ዓመት ብሔራዊ ጥቅሞቿን በማስቀደምና የአፍሪካውያን እውነተኛ ድምፅ በመሆን ጀምራዋለች። በዓለም አቀፍ ተለዋዋጭ የጂኦፖለቲካ ውጥረት ውስጥ ጽኑና ገለልተኛ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን በመከተል የብሪክስ አባል መሆን የቻለችው ኢትዮጵያ፣ በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ መሪዎች ጉባኤ ላይ አህጉራዊ አርአያነቷንና ስትራቴጂካዊ ተሰሚነቷን በተግባር አስመስክራለች። “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ቃል የተካሄደው ይህ ጉባኤ፣ ኢትዮጵያ ከአባልና አጋር ሀገራት ጋር ያላትን ሁለገብ ትስስር ወደ ላቀ ከፍታ ያሸጋገረና ፍትሃዊና አካታች ዓለም አቀፍ ሥርዓት እንዲገነባ ያላትን ቁርጠኝነት በግልጽ ያሳየ ምዕራፍ ሆኗል። ኢትዮጵያ በጉባኤው መድረክ ላይ ባነጸባረቀችው አቋም፣ ሀገራት ቀውሶች ከመከሰታቸው በፊት የመቋቋም አቅም ሊገነቡ እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥታለች። በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ባደረገችው ጥረት ከውጭ ለእርዳታ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ሙሉ በሙሉ መላቀቋን ይፋ ያደረገች ሲሆን የብሪክስ የሰብል ልውውጥ ማዕቀፍ (BRICS Grain Exchange) እንደ አምራችም ሆነ አቅራቢ ሆና ለመሳተፍ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣለች። በመድረኩ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂና ፈጠራ ዘርፍ የዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ዲጂታል መታወቂያ፣ የክፍያ ሥርዓቶች እና አስተማማኝ የመረጃ ልውውጥ አውታሮችን በስፋት እየገነባች መሆኗን አስገንዝባለች። ለአፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት ለመምራት የሚያስችለውን «የመደመር ሰው ሠራሽ አስተውሎት ዩኒቨርሲቲ» እያቋቋመች መሆኗን በመግለጽ፣ ከብሪክስ ተቋማት ጋር በጋራ ለመሥራት ያላትን ዝግጁነት አረጋግጣለች። አፍሪካ የበርካታ ማዕድናት ሀብት ባለቤት መሆኗን በማስታወስም፣ የማዕድን ሀብት ለኢነርጂ ሽግግር፣ ለላቀ ማኑፋክቸሪንግ እና ለዲጂታል ኢኮኖሚ ወሳኝ መሆኑን ኢትዮጵያ አንጸባርቃለች። የብሪክስ አባል ሀገራት የካፒታል፣ የቴክኖሎጂ እና የገበያ አማራጭ በመያዛቸው እነዚህን ሀብቶች አቀናጅቶ ለመጠቀምና በጥሬ ሀብቱ ላይ እሴት ለመጨመር ትልቅ እድል እንደሚፈጥር አመልክታለች። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የማምረት አቅሟን እያስፋፋች መሆኗን፣ እንዲሁም በማዕድናት፣ በታዳሽ ኢነርጂ እና እያደገ ባለው የኢንዱስትሪ አቅም ላይ አጋርነቶችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኗን አረጋግጣለች። በተጨማሪም የኢትዮጵያ አየር መንገድ አፍሪካን ከዓለም ጋር የሚያገናኝ ትልቅ ዕድል መሆኑን፣ ለጎረቤት ሀገራት የሚደረገው የኃይል አቅርቦት እና አዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ መሆኗ ለአህጉራዊና ዓለም አቀፍ ትስስር ያላትን አበርክቶ በግልጽ በማስመዝገብ መድረኩን ተጠቃማበታለች። ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ስርዓት ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም እያከናወነችና የውጭ ዕዳዋን ለማሸጋሸግ እየሰራች መሆኗን ገልጻ፤ በፈተና ውስጥ ለሚገኙ ኢኮኖሚዎች የዕዳ አከፋፈል ሂደት ፈጣን፣ ግልጽ እና ተገማች መሆን እንዳለበት አሳስባለች። እንዲሁም በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት በዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ውስጥ ያላቸው ውክልና ፍትሃዊ፣ ተደማጭነታቸውን ያረጋገጠ እና ተጨባጭ ውጤት የሚያመጣ መሆን እንዳለበት ጠንካራ ጥሪ አቅርባለች። በጉባኤው ባደረገችው ንቁ ተሳትፎም ሀገራችን የዓለም ንግድ ድርጅት አባል እንድትሆን፣ በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት (ICAO) ምክር ቤት ተጨማሪ መቀመጫ እንድታገኝ፣ እንዲሁም የዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤን (COP32) በአዲስ አበባ እንድታዘጋጅ ድጋፍ አግኝታለች፤ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ (NDB) ቢሮ በአዲስ አበባ እንዲከፈት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ወደ ስምምነት የሚቀይር «የብሪክስ አስተባባሪ» እንዲቋቋም ያቀረበቻቸው ምክረ ሀሳቦች ሰፊ ተቀባይነት አግኝተዋል። ከብሪክስ መድረክ ጎን ለጎን ከተከናወኑ ሰፊ የዲፕሎማሲ ሥራዎች መካከል ከዓለም መሪዎች ጋር የተደረጉት ውይይቶች ሀገራዊ ጥቅሞችን ከማስጠበቅና አጋርነትን ከማጠናከር አንፃር ትልቅ ስኬት የተመዘገበባቸው ነበሩ። ከሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ተደርጓል። ውይይቱ በመከላከያና ደኅንነት፣ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት፣ ቴክኖሎጂ እንዲሁም በባህልና ሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት መስኮች ያለውን ትብብር ለማሳደግ የጋራ ቁርጠኝነት የተረጋገጠበት ነበር። በተጨማሪም ለኮፕ 32 በሚደረገው ዝግጅት፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብራችንን ለማጠናከር የሚያስችል ስምምነት መፍጠር ተችሏል። ከሕንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋርም በመከላከያ ትብብር ማሳደግ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በአቅም ግንባታ እና በማዕድን ልማት ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ የዘመናት ታሪካዊ ትስስራችንን ወደተግባራዊ የኢኮኖሚና ልማት ምዕራፍ ማሸጋገር ተችሏል። በተጨማሪም ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር በኢንቨስትመንት፣ ቱሪዝም፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትና በአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎች ዙሪያ ውይይት ተደርጎ ለሀገር ውስጥ ልማት የሚሆን ትልቅ በር ተከፍቷል። ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር በብሪክስ ቅድመ-አጀንዳዎችና በሁለገብ ትብብር ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን፤ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋርም በቀይ ባሕር አካባቢ ወቅታዊ ሁነቶች እና በቀጣናው የደኅንነት መረጋጋት እንዲሁም በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረተ የንግድ፣ የኢኮኖሚና ልማት ልውውጦቻችንን ይበልጥ ለማስፋፋት በጋራ ለመሥራት ስምምነት ላይ ተደርሷል። በአጠቃላይ፣ ኢትዮጵያ በ18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ያከናወነቻቸው ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ሥራዎችና ያስመዘገበቻቸው ተጨባጭ ውጤቶች የሀገሪቱን የረጅም ጊዜ የዲፕሎማሲና የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን እውን የሚያደርጉ ወሳኝ ምሶሶዎች ናቸው። መንግሥት በዚህ ታሪካዊ መድረክ ኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነቷን በመጠቀም ስትራቴጂካዊ ጥቅሟን በድፍረት የምትጠይቅ፤ ለአፍሪካ ልማት፣ ሰላም እና ፍትሃዊ ዓለም አቀፍ ትብብር የቆመች አስተማማኝ አጋር መሆኗን በተግባር አስመስክሯል። የኢትዮጵያ ማንሰራራት የአፍሪካን ሕዳሴ ያበስራል!
በመደመር መንግሥት በሳል ዲፕሎማሲ ዓቅም የተመዘገበ የብሪክስ ድል
Sep 15, 2026 955
ኢትዮጵያ በረጅም የዲፕሎማሲ ታሪኳ የገነባችውን ልምድ ከዘመኑ ዓለም አቀፍ ለውጦች ጋር በማጣጣም፣ብሔራዊ ጥቅሟን በማስቀደምና ከተለያዩ የዓለም ኃይሎች ጋር አጋርነቷን በማስፋት በሳል የውጭ ግንኙነት አካሄድ እየተከተለች ትገኛለች። የዚህ አካሄድ ጉልህ ውጤት ማሳያ ደግሞ ኢትዮጵያ የብሪክስን ጥምረት መቀላቀሏ ነው። ይህ ስኬት ግን የጥምረቱ አባል በመሆኗ ብቻ የሚያበቃ አይደለም። ኢትዮጵያ በመድረኩ የራሷን ብሔራዊ አጀንዳ በጥምረቱ የጋራ አቋም እንዲያገኝ ማድረግ መቻሏ ዋናው የዲፕሎማሲ ውጤት ሆኗል። ይህን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ በመቅረጽና በመምራት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሚና ወሳኝ ነው። ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድንን ለመቀላቀል ፍላጎቷን በመግለጽ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ቀጥተኛ እና ታሪካዊ የዲፕሎማሲ መሪነት በነሐሴ 2015 ዓ.ም በደቡብ አፍሪካ በነበረው 15ተኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ጥያቄዋ ተቀባይነትን አግኝቶ፣ በጥር 2016 ዓ.ም በይፋ መቀላቀሏ ይታወሳል፡፡ አሁን ላይ ከ11 የብሪክስ አባል ሀገራት ውስጥ አንዷ ሆና በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ የራሷን ጉልህ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ በተለዋዋጭ የዓለም ሥርዓት ውስጥ ከአንድ የኃይል ጎራ ጋር ብቻ ሳትወግን ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የትብብር መድረኮች ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መፍጠር እንዳለባት ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት ዓለም አቀፍ የትብብርና የተፅዕኖ አድማሷን እያሰፋች ነው። የብሪክስ አባልነትም ከዚህ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የመነጨ ነው። ኢትዮጵያ በብሪክስ ውስጥ መግባቷ ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ ጥቅም የሚያመጣውን አቅም በመለየት፣ አጀንዳውን ከኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ብሔራዊ ጥቅም ጋር የተሳሰረ ስትራቴጂያዊ የዕይታ ለውጥ ውጤት ነው። ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል እንድትሆን ከዲፕሎማሲያዊ ጥረት በተጨማሪ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከቻይና፣ ከሩሲያ ከሕንድና ከሌሎች የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ባደረጉት ከፍተኛ የመሪዎች ዲፕሎማሲና ኢትዮጵያ ለዓለም ያበረከተችውን ታሪካዊ ሚና በቀጥታ ማስረዳታቸው ወሳኝ ሚና ተጫውቷል። ኢትዮጵያ በብሪክስ ያላት የነቃ ተሳትፎና የድል የጉዞ አሁንም ቀጥሏል። ከመስከረም 2 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ በህንድ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ አጀንዳዎቿን አሰምታለች። ብሔራዊ መሻቷን ገልጻለች። ድሎችን ተቀዳጅታለች። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጉባኤው ባደረጉት ንግግር ለችግሮች የማይበገር ፅኑ ሥርዓት እየገነባች መሆኗን አስረድተዋል። ኢትዮጵያ በምግብ ሉዓላዊነት በስንዴ ምርት ያስመዘገበችውን ስኬት፣ በጤና፣ በዲጂታል ሽግግርና በሰው ሰራሽ አስተውሎት ያላትን አቅም በማሳደግ ራሷን የመቻልና ለወደፊት የመዘጋጀት አቅሟን እያጠናከረች መሆኗን ጠቁመዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የኢትዮጵያን የባሕር በር ጉዳይ እያደገ ካለው ገዙፍ ኢኮኖሚዋና የህዝቧ ፍላጎት አኳያ አጣዳፊ ምላሽ የሚሻ ስትራቴጂያዊ የብሔራዊ ጥቅም አጀንዳ መሆኑን በግልጽ አቅርበዋል። ይህ ኢትዮጵያ የራሷን ወሳኝ ብሔራዊ ጥያቄዎች በምትሳተፍባቸው ዓለም አቀፍ መድረኮች ሁሉ በተቀናጀ መልኩ ለማስገንዘብና ምላሽ እንዲያገኙ የምትከተለውን የዲፕሎማሲ አቅጣጫ ፍሬያማነት ያሳያል። የመሪዎቹ ጉባኤ 140 የጋራ አቋሞችን የያዘ የኒው ዴልሂ መግለጫ በማውጣት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያም በድል ተመልሳለች። በብሪክስ ኒው ዴልሂ የአቋም መግለጫ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የንግድ ድርጅት ለመቀላቀል የምታደርገውን ጥረት ጥምረቱ በጽኑ እንደሚደግፍ በድጋሚ አረጋግጧል። በዓለም አቀፍ የሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ምክር ቤት ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሕብረት ብቸኛ እጩ በመሆን ተጨማሪ መቀመጫ እንድታገኝ የሚደረገውን ጥረት በጽኑ እንደሚደግፍም አመላክቷል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉን የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ኮፕ 32 ለማዘጋጀት የጀመረችውን ተነሳሽነትና ዝግጅት እንደሚደግፉ የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች በጋራ መግለጫቸው አረጋግጠዋል። በነገራችን ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በህነዱ የብሪክስ ጉባኤ ከአባልና አጋር ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ የሀገራቱ ትብብር ዙሪያ ፍሬያማ ውይይቶችን ያካሄዱ ሲሆን፤ በንግድና ኢንቨስትመንት፣ በመከላከያ መስኮችና በዲጂታላይዜሽን ዙሪያ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች በጥልቀት መወያየታቸው ሌላኛው ስኬት ነው። የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድልም ነው። በተያያዘም የብሪክስ አባል በመሆኗ አሁን ላይ ተሰሚነቷ ከማደጉም በላይ በፋይናንስ፣ ኢንቨስትመንት እና መሰል የዕድገት መሰረተ ልማት ትብብሮች ላይ አማራጮችን አበርክቶላታል። ለዚህም ኢትዮጵያ የኒው ዴቨሎፕመንት ባንክን በአባልነት መቀላቀሏ ለሀገራዊ የልማት ፋይናንስ፣ ለመሠረተ ልማት ድጋፍ እና ለማክሮ-ኢኮኖሚ መረጋጋት አማራጭ የገንዘብ ምንጮችን ለማግኘት የሚያስችላትና ከደቡብ ደቡብ የፋይናንስ ሥርዓቶች ጋር የሚኖራትን ትስስር የሚያጠናክር ነው። ኢትዮጵያውያን ወጣቶችም በተለያዩ የብሪክስ የወጣቶች ማዕቀፍ ውስጥ በስራ ፈጠራ፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ ሳይንስ እና መሰል መስኮች ላይ በንቃት እየተሳተፉ የሚገኝ ሲሆን፣ እየተፈጠሩ በሚገኙ የኢንቨስትመንት እድሎችም በርካታ የስራ እድሎች እየተፈጠረለቸው ይገኛል፡፡ በተጨማሪም ከአባል እና አጋር ሀገራቱ ወጣቶች ጋር ትስስር የመፍጠርና ልምድ ልውውጥ የማድረግ ዕድሎችን አስገኝቶላቸዋል፡፡ ኢትዮጵያ የባንኩ የአፍሪካ ቢሮ በአዲስ አበባ እንዲቋቋም ያላትን ዝግጁነት መግለጿም የብሪክስን አባልነት ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ትስስር ለመቀየር ያላትን ፍላጎት ያሳያል። የኢትዮጵያ የብሪክስ አባልነት ስኬታማ ጉዞ በዓለም አቀፍ ለውጥ መካከል በተለያዩ የትብብር መድረኮች በመሳተፍ ብሔራዊ ጥቅሟን ለማስገኘት በትጋትና በተፅዕኖ ፈጣሪነት እየሰራች መሆኗን ያሳያል። ብሪክስ የኢትዮጵያ ጥያቄዎች የሚሰሙበት፣ አጋርነቶችን የምትገነባበት፣ ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ዓለም አቀፍ ተፅዕኖ የምትፈጥርበት፣ አፍሪካን በመወከል አጀንዳዎቿን የምታራምድበት መድረክም ሆኗል።

ማህበራዊ
በአማራ ክልል የፍትሕ አገልግሎትን ቀልጣፋ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት ተመዝግቧል
Sep 17, 2026 276
ጎንደር ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦በአማራ ክልል የፍትሕ አገልግሎትን ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መመዝገቡን የክልሉ ፍትሕ ቢሮ አስታወቀ። በቢሮው የጎንደር ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ያለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ ዛሬ በጎንደር ከተማ አካሂዷል። የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ወንዳቸው ሰራው በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፣ ቢሮው የፍትሕ አገልግሎትን ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ዲጂታላይዝ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ይገኛል። ባለፈው በጀት ዓመትም ባከናወናቸው ተግባራት ከ22 ሺህ በላይ የወንጀል መዝገቦችን በመመርመር 99 በመቶ የሚሆኑት የፍርድ ውሳኔ እንዲያገኙ ማድረጉን ገልጸዋል። በዚህም በወንጀል የተገኘ ከ430 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብት ወደ መንግሥት ካዝና እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል። እንዲሁም ልዩ የሕግ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አቅመ ደካሞች፣ ሴቶችና ሕፃናት ከ520 ሚሊዮን ብር በላይ ሊያስወጡ የሚችሉ ጉዳዮችን ይዞ ነፃ የሕግ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ነው ያሉት። ቢሮው የመንግሥትንና የሕዝብን ጥቅም በማስጠበቅ የአገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ ተደራሽና ቀልጣፋ ለማድረግ የጀመረውን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ፍትሕ መምሪያ ኃላፊ አቶ አለልኝ ደሳለኝ በበኩላቸው፣ በዞኑ የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥና ወንጀልን በጋራ ለመከላከል እንዲቻል እየተሰራ ይገኛል። በዚህም የመንግሥትንና የሕዝብን ጥቅም ማስከበር ያስቻሉ ሥራዎች መከናወናቸውን ገልጸዋል። መምሪያው ከፖሊስ፣ ከፍርድ ቤትና ከማረሚያ ቤቶች ጋር ቅንጅታዊ አሠራርን በማጠናከር ባከናወናቸው ተግባራት በወንጀል የተሳተፉ 1 ሺህ 238 ግለሰቦችን ማስቀጣቱን ተናግረዋል። በተጨማሪም በወንጀል ድርጊት የተገኘ ሀብትን ለማስመለስ በተደረገ ጥረት ከ79 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሀብትና ንብረት በማስመለስ ለመንግሥት ገቢ እንዲሆን ተደርጓል ነው ያሉት። ባለፈው በጀት ዓመት በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር፣ በፍትኃ ብሔርና በሰነዶች ምዝገባ ከ28 ሺሕ ለሚበልጡ ሰዎች የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠቱን የገለጹት ደግሞ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ፍትሕ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ግርማ ጌታቸው ናቸው። ወንጀልን አስቀድሞ ለመከላከልም በትምህርት ቤቶችና በማኅበረሰብ አደረጃጀቶች ከ36 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች የንቃተ-ሕግ ትምህርት መስጠት መቻሉን አብራርተዋል። በመድረኩ የክልል፣ የዞንና የወረዳ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም የዓቃቤ-ሕግ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
የጊፋታ በዓል እሴቶችን ልማትን ለማሳለጥ ልንጠቀማቸው ይገባል
Sep 17, 2026 263
ሃዋሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦በአለም ቅርስነት የተመዘገበው የጊፋታ በዓል እሴቶች የህዝቦችን ትስስርና አንድነት ስለሚያጠናክሩ ልማትን ለማሳለጥ ልንጠቀማቸው ይገባል ሲሉ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ጥራቱ በየነ ገለጹ። የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል በሐዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። ከንቲባ ጥራቱ በየነ በወቅቱ እንደገለጹት፤ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የጊፋታ በዓል እሴቶች የህዝቦችን ትስስርና አንድነት ስለሚያጠናክሩ ልማትን ለማሳለጥ ልንጠቀማቸው ይገባል። በዓሉ እርቅን፣ አንድነትንና ሰላምን በማብሰር ወደ አዲስ ዕቅድና ተስፋ የሚያሸጋግር መሆኑን ጠቅሰው፤ የሕዝብ ለሕዝብ ትስስሩን በማጠናከር በአንድነት ድህነትን ማሸነፍ እንደሚገባም ገልጸዋል። የሲዳማና የወላይታ ሕዝቦች ያላቸውን ጠንካራ ትስስር በሚከናወኑ የልማት ስራዎች ማረጋገጥ እንዳለባቸው የገለጹት ከንቲባው፤ ሀዋሳን የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ማዕከል ለማድረግ የተጀመረው ጥረት በሁሉም ተሳትፎ ይጠናከራል ብለዋል። በዚህም የሀዋሳና የወላይታ ሶዶ ከተሞች ያላቸውን የቱሪዝም ሀብቶች በጋራ በማልማትና በማስተዋወቅ ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ እንደሚገባም አመልክተዋል። የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ረዳት ፕሮፌሰር ሳሙኤል ተሰማ በበኩላቸው፤ ጊፋታ የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን የመተሳሰብንና የአብሮነትን እሴትን በውስጡ የያዘ መሆኑን ገልጸዋል። በዓሉ የጠበቀ ማኅበራዊ መስተጋብር ያላቸውን የሲዳማና የወላይታ ሕዝቦች አንድነት በሚያጎላ መልኩ በሐዋሳ መከበሩ ትስስራቸውን የሚያጠናክር መሆኑንም ገልጸዋል። በመሆኑም ሁለቱ ሕዝቦች የጋራ እሴቶቻቸውን በማጠናከር ለሀገረ-መንግሥት ግንባታ ማዋልና መተጋገዝን ማስቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል። ከበዓሉ ታዳሚዎች መካከል በሐዋሳ የዳዎኤ ቡሹ ወጣቶች ቡድን አባል የሆነው ወጣት እስራኤል ገልፋቶ፤ የጊፋታ በዓል የወላይታና የሲዳማ ሕዝቦችን ወንድማማችነት በሚያጠናክር መልኩ መከበሩን ገልጿል። ሁለቱን ሕዝቦች የሚያስተሳስሯቸው እሴቶች በርካታ መሆናቸውን ጠቅሶ፤ በዓሉ በሐዋሳ መከበሩም ይህንን ያጠናክረዋል ብሏል። የሲዳማ ፊቼ ጨምበላላ እና የወላይታ ጊፋታ በዓላት በዓለም ቅርስነት በመመዝገባቸው ወጣቱ እሴቶቹን መጠበቅ እንዳለበትም አሳስቧል። በወላይታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቋንቋና ሥነ-ጥበብ ዳይሬክተርና የበዓሉ ታዳሚ አቶ ፍጹም ዛራ በበኩላቸው፤ የሰላምና የአንድነት በዓል የሆነውን ጊፋታ በጋራ ማክበር የሕዝብ ለሕዝብ ትስስርን ያጠናክራል ብለዋል። በዓሉ በዓለም ቅርስነት የተመዘገበና ጠቃሚ እሴቶችን በውስጡ የያዘ መሆኑን ጠቅሰው፤ የሁላችንንም ጥበቃ ይፈልጋል ብለዋል። በዓሉ ከሲዳማ ሕዝብ ጋር በሐዋሳ መከበሩም ባህሉን ከማስተዋወቅ ባለፈ በጋራ የልማት እንቅስቃሴዎችን የማየት እድልን የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። በመድረኩም የሀዋሳና የወላይታ ሶዶ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የወላይታና የሲዳማ ሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች የተገኙ ሲሆን፤ በጊፋታ በዓል እሴቶች ላይ ያተኮረ ጥናታዊ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል። በዓሉን የሚያንጸባርቁ የተለያዩ ኪነ-ጥበባዊ ሥራዎችም ቀርበዋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከሕገ-መንግሥታዊ ተልዕኮው ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል
Sep 17, 2026 279
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ከተሰጠው ሕገ-መንግሥታዊ ተልዕኮ ጎን ለጎን ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በተግባር እየተወጣ እንደሚገኝ የምክር ቤቱ አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በፌዴሬሽን ምክር ቤትና ተጠሪ ተቋማት በሶማሌ ክልል ጎዴ ከተማ በክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን ለተጠቃሚዎች አስረክበዋል። አፈ-ጉባኤው በርክክቡ ወቅት እንደገለጹት፤ ምክር ቤቱ አነስተኛ ገቢ ያላቸውንና አቅመ-ደካማ ዜጎችን የመደገፍና የኑሮ ደረጃቸውን የመለወጥ ተግባርን እየሠራ ይገኛል። የለውጡ መንግሥት ዋና የትኩረት አቅጣጫም ልማትን ማፋጠንና ማንንም ያላገለለ የሕብረተሰብ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሆነ ጠቁመዋል። ይህ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር በተለያዩ ክልሎች መከናወኑንና አበረታች ውጤት መመዝገቡን ጠቅሰው፤ የሶማሌ ክልልም ዘርፈ ብዙ የልማት ተግባራት የተከናወኑበትና አሁንም እየተከናወኑበት ያለ ክልል መሆኑን ገልጸዋል። በዛሬው ዕለት የተላለፉት ቤቶች ሙሉ የቤት ቁሳቁስ የተሟላላቸውና ለተጠቃሚዎችም ለአንድ ወር የሚሆን ቀለብ ጭምር የቀረበላቸው መሆኑን ገልጸዋል። ይህ የቤቶች የርክክብ መርሃ-ግብር የምክር ቤቱን ሕዝባዊ ወገንተኝነት የሚያሳይ መሆኑንና ምክር ቤቱ ከተጠሪ ተቋማት ጋር በመሆን ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች የሚያደርጉትን እገዛ በቀጣይም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አረጋግጠዋል። የሶማሌ ክልል ሴቶችና ሕፃናት ቢሮ ኃላፊ ሐሊማ ሐሰን በበኩላቸው፤ "ዛሬ የደስታ፣ የተስፋና የክብር ቀን ነው" ብለዋል። የፌዴሬሽን ምክር ቤት ያከናወነው ተግባር መንግሥት የሕዝብን ልማት ለማረጋገጥ ምን ያህል ቁርጠኛ መሆኑን የሚያሳይ ማሳያ በመሆኑ ለምክር ቤቱና ለተጠሪ ተቋማቱ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል። የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚዎች በበኩላቸው፤ ቀደም ሲል ይኖሩበት የነበረው ቤት በክረምት ለዝናብ፣ በበጋ ደግሞ ለፀሐይ ያጋልጣቸው እንደነበር አስታውሰዋል። አሁን ግን የተሰጣቸው ዘመናዊ መኖሪያ ቤት ከዚህ ሁሉ እንግልት እንደታደጋቸው ተናግረው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና ተጠሪ ተቋማት ላደረጉላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
በአማራ ክልል በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ጤናማ ሀገር ተረካቢ ዜጋን የማፍራት ቅንጅታዊ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል
Sep 17, 2026 116
ባህርዳር ፤መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ጤናማ ሀገር ተረካቢ ዜጋን የማፍራት ቅንጅታዊ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠሉን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) ገለጹ። የማኅበራዊ ክላስተር ተቋማትና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የቀዳማይ ልጅነት ልማት ፕሮግራም የልምድ ልውውጥ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በመድረኩም ሙሉነሽ ደሴ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ጤናማ ሀገር ተረካቢ ዜጋን የማፍራት ቅንጅታዊ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል። በዚህም የሕፃናትን የተሟላ እድገትና ጤንነት በማረጋገጥ የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጋን ለማፍራት እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል። ሕፃናትን ተንከባክቦ ማሳደግና በፈጠራ የዳበሩ ማድረግ ሀገርን ለመገንባት ጽኑ መሠረት ማኖር መሆኑንም ገልጸዋል። ለዚህም የክልሉ መንግሥት ከቅድመ መደበኛ ጀምሮ ትምህርት ቤቶችን ተደራሽ በማድረግ፣ የምገባ ፕሮግራምን በማጠናከር፣ በተቋማት የሕፃናት መዋያ ቦታዎችን በመገንባትና ሌሎች ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል ብለዋል። ክልሉ በ25 ዓመቱ አሻጋሪና ስትራቴጂክ ዕቅድ ሕፃናት በአካል፣ በአዕምሮ፣ በሥነ-ልቦናና ግብረ-ገብ ታንጸው እንዲያድጉ ልዩ ትኩረት መስጠቱንም አስረድተዋል። ይህንን ተግባር ከግብ ለማድረስም ማኅበረሰቡ፣ በሕፃናት ላይ የሚሠሩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት አስፈላጊውን ድጋፍና ትብብር እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል። የአፍሪካ የቀዳማይ ልጅነት ልማት ማዕከል ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ መሰረት ዘላለም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ለሕፃናት የተሟላ እድገትና ስብዕና በቀዳማይ ልጅነት ላይ የሚደረገው እንክብካቤ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። ይህም በእውቀትና ክህሎት የዳበረ ዜጋን በመፍጠር በተለይም የአፍሪካን እድገት ለማፋጠን ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አስረድተዋል። የሕፃናት ጉዳይ ለአንድ አካል ብቻ የሚተው ሳይሆን የሁሉንም ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን በመገንዘብ፤ ማዕከሉ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች በሕፃናትና በሰው ሀብት ልማት ላይ በማተኮር እየደገፈ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። የአማራ ክልል መንግሥት ለቀዳማይ ልጅነት እድገት የሰጠው ትኩረት የሚያስመሰግንና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑንም አመልክተዋል። ለሦስት ቀናት በሚካሄደው በዚህ የልምድ ልውውጥ መድረክ ላይ ከተለያዩ ክልሎች የመጡና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።
ኢኮኖሚ
የዓባይ ወንዝና የቀይ ባሕር ፍትሐዊ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር ማዕከላዊ አጀንዳዎች ናቸው
Sep 17, 2026 223
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ የውሃ ሀብት ተጠቃሚነትና የባሕር በር ባለቤትነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር ማዕከላዊ ስትራቴጂክ አጀንዳዎች መሆናቸውን ምሁራን ገለጹ። የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የዓባይ ወንዝና የባሕር በር ጉዳዮችን በተመለከተ የፓናል ውይይት አካሂዷል። የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁሩ ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) በፓናሉ ላይ እንዳሉት፣ የዓባይና የባሕር በር ጉዳዮች በጂኦፖለቲካዊና በልማታዊ ትስስራቸው ተነጣጥለው ሊታዩ አይገባም። የዓባይ ወንዝ ጉዳይ የልማት፣ የኢኮኖሚና የቀጣናዊ ትብብር ማዕከል በመሆኑ በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተ አቀራረብ ሊከተል እንደሚገባ አመልክተዋል። ሁለቱን ስትራቴጂካዊ ጉዳዮች በተቀናጀ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይና የልማት ስትራቴጂ መሠረት መምራት እንደሚያስፈልግም አንስተዋል። በዚህም የዓባይ ወንዝ ፍትሐዊ የውሃ ሀብት ተጠቃሚነትና የባሕር በር ባለቤትነትን የማረጋገጥ ጉዳይ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የማስከበር ማዕከላዊ ስትራቴጂክ አጀንዳዎች መሆናቸውን አስገንዝበዋል። የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ መሪ ተመራማሪ አቶ ሰለሞን ተፈራ በበኩላቸው፣ የባሕር በርና የዓባይ ጉዳዮች ተነጣጥለው ሳይሆን በአንድ ሀገራዊ ማዕቀፍ ውስጥ ተቀናጅተው ሊታዩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። ጉዳዮቹ በምሁራን ጥናትና በጠንካራ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ሊመሩ እንደሚገባም ተናግረዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝምና ገቨርናንስ መምህርና ተመራማሪ ተስፋዬ ጂማ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የባሕር በር ጉዳይ ከሉዓላዊነት፣ ከኢኮኖሚ ዕድገትና ቀጣናዊ ሰላም የተቆራኘ የብሔራዊ ጥቅም ጉዳይ ነው ብለዋል። የሀገር ህልውናን፣ ደህንነትንና የዜጎችን ማኅበራዊ ልማት ከሚያሳድጉ ጉዳዮች አኳያ፣ የባሕር በርና የዓባይ ወንዝ ጉዳዮች በአንድ ማዕቀፍ ውስጥ ሊታዩ እንደሚገባ አንስተዋል። ምሁራን በጥናትና ምርምር የተደገፈ የፖሊሲ ግብዓት በማቅረብ፣ እንዲሁም የሕዝብ ግንዛቤን በማሳደግ፣ ሀገራዊ ጥቅምን ለማስጠበቅ በሚደረገው ሂደት አዎንታዊ ሚና ማበርከት እንደሚችሉም ተናግረዋል።
የጋምቤላ ክልል ከተሞችን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ይጠናከራሉ
Sep 17, 2026 216
ጋምቤላ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ የጋምቤላ ክልል ከተሞችን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) ገለጹ። የክልሉ የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምና የአዲሱ በጀት ዓመት እቅድ ላይ ያዘጋጀውን የውይይት መድረክ ዛሬ አካሄዷል። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኃላፊ ጋትሉዋክ ሮን (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የክልሉ ከተሞችን ለኑሮና ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ። ከተሞችን ለነዋሪዎችና ለኢንቨስትመንት ምቹ ለማድረግ የመሠረተ ልማት ማስፋፋት ላይ የተጀመረው ጥረት እንደሚጠናከርም ገልጸዋል። ለዚህም የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የንጹህ መጠጥ ውሃ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድና ሌሎች የመሰረተ ልማት አውታሮችን ተደራሽ በማድረግ የህዝቡን የመሰረተ ልማት ጥያቄ ለመመለስ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። ህብረተሰቡ ለከተሞች የመሰረተ ልማት ግንባታ፣ ጽዳትና ውበት ስራዎች መሳካትም እያደረገ ያለውን ሁለንተናዊ ተሳትፎና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አጠናክሮ እንዲያስቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል። በበጀት ዓመቱ የተያዙ ፕሮጀክቶች በተቀመጠላቸው የጊዜ ሰሌዳ ተጠናቀው ለሕዝብ አገልግሎት እንዲበቁም የክትትልና ድጋፍ ስራዎች ይጠናከራሉ ብለዋል። የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በከተሞች የሚታዩ የመጠጥ ውሃ፣ የውስጥ ለውስጥ መንገድና የፍሳሽ ማስወገጃ መስመር ተግዳሮቶችን ለመፍታት በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመዋል። በግምገማ መድረኩ ላይ ከክልል፣ ከዞን፣ ከወረዳዎችና ከከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ኢትዮጵያ የቴምር ልማትን በማዘመን ተጨማሪ የኤክስፖርት አቅም እየገነባች ነው
Sep 17, 2026 278
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ የቴምር ልማትን በማዘመን ተጨማሪ የኤክስፖርት አቅም እየገነባች መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር ዓሊ መሃመድ ገለጹ። የግብርና ሚኒስቴር በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ ከመስከረም 10 እስከ 12 ቀን 2019 ዓ.ም የሚካሄደውን ሁለተኛውን ዓለም አቀፍ የቴምር ፌስቲቫል አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል። ፌስቲቫሉ በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት፣ በግብርና ሚኒስቴር እና በኸሊፋ ኢንተርናሽናል አዋርድ ፎር ዴት ፓልም ኤንድ አግሪካልቸራል ኢኖቬሽን በጋራ ትብብር የሚዘጋጅ ነው። የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ ፕሮፌሰር ዓሊ መሃመድ በመግለጫው እንዳሉት፣ ቴምር ለምግብነት፣ መድኃኒትነትና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ያለው ፋይዳ እጅግ ከፍተኛ ነው። መንግሥት ባህላዊና የተበታተነ አሰራር በማዘመን ምርቱን በሀገር ውስጥ ገበያ ብቻ ሳይገድብ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከ500 ሺህ እስከ 600 ሺህ ሄክታር ለቴምር ልማት የሚሆን ምቹ መሬት ያላት ቢሆንም፣ እስካሁን የለማው መሬት መጠን 6 ሺህ ሄክታር ወይም 1.2 በመቶ ብቻ ነው ብለዋል። የቴምር ልማት እየተከሰተ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥና የበረሃማነት መስፋፋት በብቃት የመቋቋም አቅም ያለው በመሆኑ ለአካባቢ ጥበቃም ሆነ ለኢኮኖሚ እድገት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው አስገንዝበዋል። ይህን አቅም እውን ለማድረግ እንደ ተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ካሉ ሀገራት የቴክኖሎጂና የእውቀት ሽግግር በማድረግ ፈጣን ለውጥ ለማምጣት መታቀዱንም ተናግረዋል። ለዚህም የፌደራል መንግሥት፣ የአፋር ክልል፣ የዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ተቋማት ባለሙያዎች ተቀናጅተው የ10 ዓመት የምርምርና የልማት ፕሮግራም አዘጋጅተው ወደ ስራ መግባታቸውንም ገልጸዋል። የአፋር ክልል ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሃሩን ዓሊ በበኩላቸው፤ በክልሉ ከ250 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረውን የቴምር ተክል ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ለማልማት ዕቅድ ተይዟል ብለዋል። በዚህም የተምር ምርታማነትን በዘመናዊ መንገድ በማሻሻል የምግብ ፍጆታንና የወጪ ንግድ አቅምን ለማጎልበት የአርሶ አደሩንና አርብቶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማሻሻል እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል። የኸሊፋ ዓለም አቀፍ የቴምርና የግብርና ፈጠራ ሽልማት ዋና ፀሐፊ ፕሮፌሰር አብደልወሃብ አልቡኻሪ ዘይድ በበኩላቸው፤ የቴምር ፌስቲቫሉ አርሶ አደሮችን፣ ተመራማሪዎችን፣ ሙያተኞችንና ውሳኔ ሰጪዎችን የሚያገናኝ ታሪካዊ መድረክ ነው ብለዋል። ይህ መድረክ በሀገሪቱ ያለውን ያልተነካ የቴምር አመራረት ዕድል ከማጎልበቱም በላይ በዘመናዊ አሠራሮች እና በወደፊት የአመራረት ዘዴዎች ላይ ያተኮረ ሳይንሳዊ ውይይት እንዲጀመር መንገድ መክፈቱን አብራርተዋል። በአፋር ክልል በሚካሄደው በዚህ የሦስት ቀናት ፌስቲቫል ላይ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት፣ አምራቾች፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ባለሀብቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይታደማሉ።
የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማረጋገጥ ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነት ጉዳይ ነው
Sep 17, 2026 153
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ማስመለስ ብሔራዊ ጥቅምን የማስጠበቅ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትን የማረጋገጥና ቀጣናዊ ሰላምን የማጠናከር ጉዳይ መሆኑን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶችና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ ገለጹ። የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ የዓባይ ወንዝና የባሕር በር ጉዳይን በተመለከተ የፓናል ውይይት እያካሄደ ይገኛል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶችና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የባሕር በር ከኢትዮጵያ የኢኮኖሚ፣ የጸጥታ፣ የኃይል አቅርቦትና የንግድ ትስስር ጋር የተቆራኘ ነው። ቀይ ባሕር ከዓለም አቀፍ የንግድና የኃይል ማጓጓዣ መስመሮች ጋር የተሳሰረ መሆኑን ገልጸው፤ ለኢትዮጵያ የንግድ ተደራሽነት፣ የሎጂስቲክስ አቅም፣ የኢኮኖሚ ተወዳዳሪነትና ጸጥታ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል። ለኢትዮጵያ የባሕር በር ብሔራዊ ጥቅም የማስጠበቅ፣ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነትና የቀጣናውን ሰላም የማረጋገጥ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አምባሳደር ዲና ሙፍቲ፤ የባሕር በር ከኢትዮጵያ ታሪክ፣ ጂኦግራፊ፣ ኢኮኖሚና የጸጥታ ሁኔታ ጋር የተያያዘ ዘላቂ ሀገራዊ አጀንዳ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ከቀይ ባሕር ጋር ያላት የጂኦግራፊ ቅርበት፣ የሕዝብ ቁጥሯና እያደገ የመጣው ኢኮኖሚ የባሕር በር አስፈላጊነት የጎላ ያደርገዋል ብለዋል። ከሀገራዊ ጥቅም ባሻገር ከጎረቤትና ከቀሪው የአፍሪካ ሀገራት ብሎም ከዓለም አቀፍ ሥርዓት ጋር የሚኖረውን የኢኮኖሚና የጸጥታ ትስስር ማጤን እንደሚገባ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ የባሕር በርን ጉዳይ በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ፣ በስምምነትና በትብብር መፍትሔ እንዲያገኝ አጥብቃ ትሻለች ብለዋል። የአዲስ አበባ አመራር አካዳሚ ፕሬዝዳንት ጣሰው ገብሬ (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ የባሕር በርና የዓባይ ጉዳዮች ከኢትዮጵያና ከአካባቢው የወደፊት የኢኮኖሚ፣ የደህንነትና የትስስር ጥቅሞች አንፃር ተመዝኖ መመራት እንዳለበት ገልጸዋል። የባሕር በርና የዓባይ ጉዳዮች በውይይት፣ በመተማመን፣ በሕጋዊ ማዕቀፎችና የሁሉንም ሕዝቦች ዘላቂ የጋራ ጥቅም ታሳቢ በማድረግ መመራት አለባቸው ብለዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
የዲጂታል ፍርድ ቤት አሰራር ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ ነው
Sep 17, 2026 234
ድሬደዋ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦የዲጂታል ፍርድ ቤት አሰራር ፍትሃዊና ግልጽ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ ምዕራፍ መሆኑን የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት አስታወቁ። በድሬደዋ አስተዳደር ፍርድ ቤቶች ከወረቀት ንክኪ የፀዳ የዲጂታላይዜሽን አገልግሎት ማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ዛሬ ተካሂዷል። አገልግሎቱ በተጀመረበት ወቅት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት፣ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር እና ሌሎች የክልልና የፌዴራል መስሪያ ቤት አመራሮች ተገኝተዋል። የኢፌዴሪ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የፍትህ ትራንስፎርሜሽን ትግበራው የፍትህ ስርዓቱን ተደራሽ፣ ግልፅና ውጤታማ በማድረግ የህዝብ እርካታን ለማረጋገጥ እያስቻለ ይገኛል። የፍርድ ቤቶች አገልግሎቶችን ዲጂታላይዝ ማድረግ ተገልጋዮች ባሉበት ቦታ ሆነው ጉዳያቸውን የሚከታተሉበትን ስርዓት ለመዘርጋት እንዳስቻለም ነው የጠቀሱት። በተለይ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ውስጥ የተጀመረውን የስማርት ኮርት ስርዓት በመላው አገሪቱ በማስፋት ፈጣንና ግልፅ የፍትህ አገልግሎት በማስፈን የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ ማስቻሉን ገልጸዋል። የፍርድ ቤቶችን መረጃ አያያዝ ለማዘመን ተግባራዊ የተደረጉ የዲጂታል አገልግሎቶችም ፈጣንና ተደራሽ ፍትህን ለማስፋት እንዳስቻሉም ነው የገለጹት። ዛሬ በድሬደዋ ተመርቆ ወደ አገልግሎት የገባው የዲጂታል አገልግሎት አሰራር በክልሎች የተጀመሩትን አበረታች ውጤቶች በላቀ ደረጃ ለማሳደግ ለተከናወኑት ተግባራት ማሳያ እንደሚሆንም አንስተዋል። የተጀመሩ የዲጂታል አገልግሎቶች የፍትህ ስርዓቱን ግልፅነትና ተጠያቂነት ከማስፈን ባሻገር፣ ተገልጋዮች ካሉበት ስፍራ ሆነው መረጃዎችን ለማግኘት እያስቻሉ መሆኑንም ጠቁመዋል። የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በበኩላቸው፤ የፍርድ ቤቶችን አሰራር ዲጂታላይዝ ማድረግ ፍትህን በእኩልነት፣ በግልፅነት እና በቅልጥፍና ተደራሽ ለማድረግ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም ፍርድ ቤቶች ከወረቀት ንክኪ የፀዳ ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋዩን እርካታ ለማረጋገጥ እየሰሩ መሆኑን ጠቁመዋል። በድሬዳዋ በተካሔደው የፍርድ ቤቶች የዲጂታላይዜሽን ይፋዊ ጅማሮ እና ጉብኝት ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አብዲ ሙክታር እና ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዝዳንቶች፣ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል ዘመናዊ አሠራር የተገልጋዮችን እንግልትና የጊዜ ብክነት አስቀርቷል
Sep 17, 2026 118
ጅማ ፤መሰከረም 7/2019 (ኢዜአ)፡- የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል አሠራሩን የዘመነ በማድረጉ ተገልጋዮች እንግልትና የጊዜ ብክነት ሳይገጥማቸው ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ገለፁ። የከተማዋ ተገልጋዮች እንደገለጹት፣ በመሶብ የአንድ ማዕከል የሚሰጡ የህዝብ አገልግሎቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከሩ፣ እየዘመኑ እና ቀልጣፋ እየሆኑ መጥተዋል። ማዕከሉ በርካታ መሥሪያ ቤቶችን በአንድ ጣሪያ ሥር በማስተሳሰሩ፣ ተገልጋዮች ከቢሮ ቢሮ ያጋጥማቸው የነበረውን እንግልት፣ አላስፈላጊ ወጪና የጊዜ ብክነት ማስቀረት ችሏል። ከነዋሪዎቹ መካከል አቶ ተስፋዬ በቀለ እንደገለጹት፣ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት የነበረው ቢሮክራሲያዊ አሰራር ለአላስፈላጊ እንግልትና የጊዜ ብክነት ይዳርግ ነበር። በአንድ ዓመት ውስጥ አንድን ጉዳይ ለማስፈጸም ከስድስት ወር በላይ ይመላለሱበት የነበረበት ወቅት እንደነበር በማስታወስ፣ የማዕከሉ መቋቋም ያንን ውጣ ውረድ በመቅረፍ ረገድ ትልቅ ለውጥ ማምጣቱን ገልጸዋል። ከዚህ በተጨማሪም፣ ቀደም ሲል ወደ ማዕከሉ ያልገቡ ተጨማሪ የመንግሥት ሴክተሮች አሁን ላይ ተካተው አገልግሎት መስጠት በመጀመራቸው፣ የማዕከሉ የአሰራር አቅምና የተቀላጠፈ አገልግሎት የመስጠት አቅም ይበልጥ መጠናከሩን ጠቁመዋል። ወይዘሮ መሬማ መሀመድ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳይ እጅግ ያስጨንቀን ነበር ብለዋል። በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚታየው ያልተገባ አሰራር ለእንግልትና ንብረት ብክነት ሲዳርገን ቆይቷል ያሉት ወይዘሮ መሬማ፤ ዛሬ ግን ወደ መሶብ አንድ ማዕከል ስንሄድ በፍፁም መተማመንና በደስታ ነው ብለዋል። የማዕከሉ ሠራተኞች ለባለጉዳይ ትልቅ ትኩረት መስጠታቸው እንዲሁም አገልግሎቱ በቴክኖሎጂ የታገዘና ፈጣን መሆኑ ከምንም በላይ አስደሳች ነው ብለዋል። አገልግሎቱ በየጊዜው እየዘመነ መጥቷል ያሉት ደግሞ የጅማ ከተማ ነዋሪዋ ወይዘሮ አለምነሽ ዲኮ ናቸው። ለሦስት የተለያዩ ጉዳዮች ወደ ማዕከሉ መምጣታቸውንና ሦስቱንም አገልግሎቶች በአንድ ስፍራ አጠናቀው መመለሳቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል። ወጣት ሚፍታ አብዱልቃድር በበኩሉ መሶብ የአንድ ማዕከል ለአቅመ ደካሞችና ለአካል ጉዳተኞች ምቹና አግባብነት ያለው አሠራር መዘርጋቱን ጠቁሞ፣ ያለምንም መጉላላት ገብቶ ተገቢውን አገልግሎት ማግኘት መቻሉን ተናግሯል። የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ሰራተኞች ሊና አብዱለዚዝ እና ሀናን አሙቲ፤ ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ ሲመጡ አገልግሎቱን አጠናቀው ለመውጣት ከ10 እስከ 15 ደቂቃ ብቻ እንደሚወስድባቸው ገልጸዋል። አሠራሩ ዲጂታላይዝ የሆነና ፈጣን በመሆኑ ተገልጋዮች ለእንግልትና ለጊዜ ብክነት እንደማይዳረጉ የጠቀሱት ሠራተኞቹ፤ እያንዳንዱ ሠራተኛ አገልግሎት የሰጠበት ደቂቃ እየተለካ የሚገመገም በመሆኑ ምንም ዓይነት የአገልግሎት ክፍተት አይፈጠርም ብለዋል። የጅማ መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አብዲ ሰለሞን፤ ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ከጀመረበት 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ አሁን ከ135 ሺህ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ማስተናገዱን ገልጸዋል። እንዲሁም በማዕከሉ ይሰጡ የነበሩት አገልግሎቶች ከ135 ወደ 139 የደረሱ ሲሆን፤ ወደ ማዕከሉ የገቡት ሴክተሮች ደግሞ ከ25 ወደ 29 ማደጋቸውን አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት የወሰደችው ስትራቴጂካዊ እርምጃ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን በተግባር የሚያረጋግጥ ነው
Sep 16, 2026 769
አዲስ አበባ፤ መስከረም 6/2019 (ኢዜአ)፦የሰው ሰራሽ አስተውሎትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የዓለምን ኢኮኖሚ በከፍተኛ ሁኔታ እየቀየረ ባለበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ ለዘርፉ የሰጠችው ከፍተኛ ትኩረትና ስትራቴጂካዊ እርምጃ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የሚያረጋግጥ መሆኑን የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ ከምትከተላቸው ብዝሃ ኢኮኖሚ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ መስክ በተከናወኑ ሰፊ ሥራዎች በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ ይገኛል። በዚህ የለውጥ ጉዞ ውስጥ ሀገሪቱ በሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ልማትና አጠቃቀም በአህጉሪቱ ቀዳሚ በመሆን ጠንካራ የመሪነት ሚና እየተወጣች ትገኛለች። ይህንን የቴክኖሎጂ አብዮት ከማፋጠን ባለፈ አህጉራዊ ተደራሽነቱን ለማስፋት በተከናወኑት ተጨባጭ ተግባራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአፍሪካ ህብረት የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ጤና ዘርፍ መሪ ሆነው መሾማቸው ይታወቃል። ይህም ኢትዮጵያ በዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እና በፈጠራ ሥራዎች ያስመዘገበችውን ድል ከማሳየቱም በላይ፣ ቀጣይነት ያለው የቴክኖሎጂ ልማት እውን እንዲሆን አርዓያነት ያለው መሰረት ጥሏል። በዚህም ሀገሪቱ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ያላት አቅም ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን በማረጋገጥ፣ ለአፍሪካ የዲጂታል ሉዓላዊነትና ብልጽግና ትልቅ ተስፋን ፈጥሯል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ዲጂታል መታወቂያን፣ የክፍያ ሥርዓቶችን እና የመረጃ ልውውጥን ያካተተ ዲጂታል የሕዝብ መሠረተ ልማት እየተገነባና የመረጃ ደህንነት ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል። በተጨማሪም የቀጣዩ ትውልድ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ አብዛኛውን የሰው ልጅ የሚያገለግል፣ በርካታ ቋንቋዎችን የሚረዳ፣ ማኅበረሰቦችን የሚያካትትና ሰፊ እውቀትን ያቀፈ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፣ በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በዋናነት በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ ነው። በተለይም ወጣቱ ትውልድ ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል አሰራር መሸጋገሩ የቴክኖሎጂ ሽግግሩ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። ከጥቂት ዓመታት በፊት በዲጂታል መንገድ ይከናወን የነበረው የገንዘብ ልውውጥ 10 በመቶ ብቻ የነበረ ቢሆንም፣ አሁን ላይ ግን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ አብዛኞቹ ባንኮች እስከ 90 በመቶ የሚሆነውን የገንዘብ እንቅስቃሴ በዲጂታል መንገድ እያከናወኑ መሆኑን በአብነት ጠቅሰዋል። ኢትዮጵያ የሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) እንደ አንድ ዋነኛ የመወዳደሪያ አቅም እና ስትራቴጂ በመውሰድ በከፍተኛ ትኩረት እየሰራችበት እንደምትገኝ አንስተዋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ለሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ትልቅ ትኩረት የሰጠች ሀገር መሆኗንም ተናግረዋል። በአትዮጵያ አብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል የቴክኖሎጂ ክህሎትን በቀላሉ መቅሰም የሚችል ወጣት የሰው ሀይል በመሆኑ፣ ኢትዮጵያን "የአፍሪካ ሲሊኮን ቫሊ" የማድረግ ትልቅ አቅም እንዳለውም ጠቁመዋል። በተለይም የ5 ሚሊዮን ኮደሮች የስልጠና ፕሮግራም ወጣቶች ወደ ሥራ ሲገቡ ለሀገሪቱ የቴክኖሎጂ መነቃቃት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክትም ተናግረዋል። በቀደመው የኢኮኖሚ አካሄድ ብቻ ውጤታማ መሆን የማይቻል በመሆኑ በቴክኖሎጂና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ላይ በባለቤትነት መሥራት ለነገዋ ኢትዮጵያ ወሳኝ እንደሆነ አብራርተዋል።
አኩቴክ ዲያግኖስቲክ የህክምና ቱሪዝም ማዕከልነት ግብ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር ነው
Sep 15, 2026 432
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ አኩቴክ ዲያግኖስቲክ ሀገሪቱን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካት ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መሆኑን የአኩቴክ ዲያግኖስቲክ ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ ታደሰ ገለጹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በቅርቡ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የሥራ እንቅስቃሴ መመልከታቸው ይታወሳል። በዚሁ ወቅት እንዳሉት፣ አኩቴክ (ACCU-TECH) ዲያግኖስቲክ ላቦራቶሪ የሀገሪቱን የጤና ዘርፍ ወደ ከፍተኛ ምዕራፍ የሚያሸጋግር እና ለዘርፉ ልዩ መለያ እና አቅም ነው። ዘመናዊው ላቦራቶሪ በአንድ ጊዜ በርካታ ናሙናዎችን በመቀበል ለተወሰነ ጊዜ ሳምፕሎችን በጥንቃቄ ማቆየት የሚያስችል አቅም እንዳለውም ተናግረዋል። የአኩቴክ ዲያግኖስቲክ ዋና ዳይሬክተር ሄኖክ ታደሰ ለኢዜአ እንዳሉት፣ ስያሜው "አኩ" ትክክለኛነትን እና "ቴክ" ቴክኖሎጂን የሚወክል ሲሆን፣ የሚጠቀማቸው ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂዎች የምርመራ ውጤቶች ጥራት እንዲኖራቸው ያስችላሉ። ይህ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ዘመናዊ ላቦራቶሪ ወደ ውጭ ሀገር ተልከው ይሠሩ የነበሩ የላቦራቶሪ ምርመራዎችን በማስቀረት ረገድ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወትም ገልጸዋል። የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ከሪቲና ፋርማሲዩቲካል ጋር በመተባበር የተቋቋመው ላቦራቶሪ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሙሉ በሙሉ አውቶሜትድ የሆነ ነው ብለዋል። ላቦራቶሪው በምርመራ ሂደቶች ላይ የሚታዩ የውጤት መዘግየቶችንና የውጭ ምንዛሬ ወጪዎችን ለማስቀረት ጉልህ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። ከዚህ ቀደም እስከ 68 በመቶ የሚደርሱ ስህተቶች ሊከሰቱ እንደሚችሉ አንስተው፣ አሁን ያለው ሲስተም ይህንን ዲጂታላይዝ በማድረግ ስህተቱን ወደ ዜሮ እንደሚያወርደው አስረድተዋል። ላቦራቶሪው በርካታ ናሙናዎችን በአንድ ጊዜ የመመርመር ብቃት ያለው ከመሆኑ ባሻገር ናሙናዎችን በጥንቃቄ የሚያቆይ መሆኑንም ተናግረዋል። ማሽኖቹ ከሰው ሰራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) ጋር የተገናኙ በመሆናቸው ሥራን በቀላሉና በፍጥነት እንዲያከናውኑ ማስቻሉን አንስተዋል። በቀጣይም አገልግሎቱን በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ በድሮን ናሙና መሰብሰብ የሚያስችል ተግባር ለማከናወን እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ላብራቶሪው ሀገሪቱን የህክምና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ግብ ለማሳካትም ተጨማሪ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል።
ስፖርት
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ይፋ ሆነ
Sep 17, 2026 120
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ የ2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የእጣ ማውጣት ስነ ስርዓት ዛሬ ተካሄዷል። በፕሪሚየር ሊጉ የሚሳተፉ 18 ክለቦች በስድስት ቋቶች ተከፍለው የእጣ የማውጣት ሂደቱ ተከናውኗል። በዚሁ መሰረት የወቅቱ የሊጉ አሸናፊ ሲዳማ ቡና በመጀመሪያ ሳምንት ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይጫወታል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ከነገሌ አርሲ፣ ኢትዮጵያ ቡና ከሸገር ከተማ፣ ሀዋሳ ከተማ ከመቻል፣ ወላይታ ድቻ ከፋሲል ከነማ፣ጋሞ ጨንቻ ከኢትዮጵያ መድን፣ ሀላባ ከተማ ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ፣ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከአዳማ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና ከባህር ዳር ከተማ ሌሎች በመጀመሪያ ሳምንት የሚደረጉ ጨዋታዎች ናቸው። በሁለተኛ ሳምንት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ቡና የሚያደርጉት የደርቢ ጨዋታ ተጠባቂ ነው። የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በሰባት የተመረጡ ስታዲየሞች ይደረጋሉ። አዲስ አበባ ስታዲየም፣ አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ስታዲየም፣ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፤ ባህርዳር አለም አቀፍ ስታዲየም፣ሀላባ ስታዲየም፣ ሆሳዕና አብዩ ኤርሳሞ ስታዲየም እና አርባምንጭ ዩንቨርሲቲ አባያ ካምፓስ ስታዲየም ውድድሩ የሚካሄድባቸው ሜዳዎች ናቸው። ፕሪሚየር ሊጉ መስከረም 29 ቀን 2019 ዓ.ም ይጀመራል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አቻ ተለያየ
Sep 17, 2026 115
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ ጋር ያለ ግብ አቻ ተለያይታለች። ጨዋታው በታንዛንያ በሚገኘው አሁሩ ስታዲየም ተካሄዷል። ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ነጥቧን አግኝታለች። ብሔራዊ ቡድኑ ሁለተኛ ጨዋታውን መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከአዘጋጇ ታንዛንያ ጋር ያደርጋል። በዚሁ ምድብ ከትናንት በስቲያ በተካሄደው ጨዋታ ታንዛንያ ሩዋንዳን 3 ለ 0 አሸንፋለች። ኢትዮጵያ ወደ ግማሽ ፍጻሜው ለማለፍ ታንዛንያን ማሸነፍ ይጠበቅበታል። ከ20 ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ከመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም አንስቶ እየተካሄደ ይገኛል። በውድድሩ ዘጠኝ ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን በማድረግ ላይ ናቸው። በማጣሪያው ለፍጻሜ የሚደርሱት ሁለት ሀገራት እ.አ.አ በ2027 በጋና ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ቀጣናውን ወክለው ይሳተፋሉ። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 15 ቀን 2019 ዓ.ም ይቆያል።
የወቅቱ የካራባኦ ካፕ አሸናፊ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ ጋር ይጫወታል
Sep 17, 2026 121
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- የእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ሶስተኛ ዙር መርሐ ግብር ዛሬ ይጠናቀቃል። ምሽት 3 ሰዓት ከ30 ላይ ማንችስተር ሲቲ ከኖርዊች ሲቲ በኢትሃድ ስታዲየም ይጫወታሉ። ባለሜዳው ማንችስተር ሲቲ የወቅቱ የዋንጫ ባለቤት ነው። በእንግሊዝ ሻምፒዮንሺፕ (ሁለተኛ የሊግ እርከን) የሚገኘው ኖርዊች ሲቲ በሁለተኛው ዙር ካርዲፍ ሲቲን 2 ለ 1 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር ተሸጋግሯል። ሁለቱም ቡድኖች ከዚህ ቀደም በካራባኦ ካፕ አምስት ጊዜ የተገናኙ ሲሆን ማንችስተር ሲቲ በሶስቱ ሲያሸንፍ በቀሪ ሁለት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል። ቡድኖቹ ለመጨረሻ ጊዜ በውድድሩ ላይ የተገናኙት እ.አ.አ በ2007 ነው። በወቅቱ በሶስተኛው ዙር ባደረጉት ጨዋታ በጆርጅ ሳማራስ ጎል ማንችስተር ሲቲ 1 ለ 0 አሸንፏል። ማንችስተር ሲቲ ዘጠኝ ጊዜ ዋንጫውን በማንሳት ከሊቨርፑል (10 ዋንጫ) በመቀጠል የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ነው። ኖርዊች ሲቲ እ.አ.አ በ1962 እና በ1985 ውድድሩን አሸንፏል። በተጨማሪም እ.አ.አ በ1973 እና 1975 ለፍጻሜ ደርሶ ሽንፈት አስተናግዷል። ማንችስተር ሲቲ ጨዋታውን የማሸነፍ ሰፊ የቅድሚያ ግምት አግኝቷል። የ28 ዓመቱ ሩበን ሪካርዶ ጨዋታውን በዋና ዳኝነት ይመሩታል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ከሩዋንዳ ጋር ይጫወታል
Sep 17, 2026 135
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከሩዋንዳ ጋር ዛሬ ታደርጋለች። ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ የሴካፋ ዞን ማጣሪያ መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በታንዛንያ አስተናጋጅነት መካሄድ ጀምሯል። በውድድሩ ላይ ዘጠኝ ሀገራት በሶስት ምድብ ተከፍለው ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ታንዛንያ እና ሩዋንዳ ጋር ተደልድሏል። ብሔራዊ ቡድኑ የመጀመሪያ የምድብ ጨዋታውን ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት ከሩዋንዳ አቻው ጋር ያደርጋል። በአሜሪካዊው አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ብሔራዊ ቡድን በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም ከተጀመረው ብሔራዊ ምልመላና ምዘና( National Camping) አንስቶ ዝግጅቱን ሲያደርግ ቆይቷል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ለታንዛንያው የሴካፋ ማጣሪያ ውድድር መጀመሪያ ላይ የ40 ተጫዋቾችን ጊዜያዊ ስም ዝርዝር ይፋ አድርጎ ነበር። በአሁኑ ወቅት አሰልጣኝ ቤንጃሚን ዚመር ስብስቡን ወደ 25 ተጫዋቾች በመቀነስ ልምምዱን ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ስፍራው አቅንቷል። በአንድሬ ካሳ ምቡንጎ የሚመራው የሩዋንዳ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም ባደረገው የመጀመሪያ ጨዋታ በአዘጋጇ ታንዛንያ 3 ለ 0 ተሸንፏል። የሩዋንዳ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበጀት እጥረት ምክንያት ቡድኑ በውድድሩ ላይ እንደማይሳተፍ አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ ከሀገሪቷ ስፖርት ሚኒስቴር ጋር በተደረገ ስምምነት ውሳኔው ተቀይሮ ውድድሩ ሊጀመር የአንድ ሳምንት እድሜ ሲቀረው መሳተፉ ተረጋግጧል። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን የማጣሪያ ጉዞውን በድል ለመጀመር ይጫወታል። በአንጻሩ የሩዋንዳ አቻው ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ ያለውን ተስፋ ለማለምለም እጅጉን ወሳኝ ነው። በቤንጃሚን ዚመር የሚመራው ታዳጊ ቡድን ሁለተኛ የምድብ ጨዋታውን መስከረም 9 ቀን 2019 ዓ.ም ከአዘጋጇ ታንዛንያ ጋር ያደርጋል። ቡድኑ ወደ ግማሽ ፍጻሜ የሚገባው ከምድቡ አንደኛ ወይም ከሶስቱ አጠቃላይ ምድቦች ምርጥ ሁለተኛ ሆኖ ካጠናቀቀ ብቻ ነው። በምድብ ሁለት ዩጋንዳ፣ ሱዳን እና ጅቡቲ እንዲሁም በምድብ ሶስት ደቡብ ሱዳን፣ ኬንያ እና ብሩንዲ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በጋና እ.አ.አ በ2027 ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በማጣሪያ ውድድሩ የፍጻሜ ተፋላሚ መሆን ይኖርበታል። ከየቀጣናው ሁለት ሀገራት ለአፍሪካ ዋንጫው ያልፋሉ። ብሔራዊ ቡድኑ በጋና በሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ብሔራዊ ቡድኑ ካለፈ እና ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ከቻለ በዛው ዓመት በአዘርባጃን እና ኡዝቤኪስታን ጣምራ አዘጋጅነት ለሚካሄደው ከ20 ዓመት በታች የፊፋ ዓለም ዋንጫ ማለፉን ያረጋግጣል። ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በ20 ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ሁለት ጊዜ ተሳትፋለች። እ.አ.አ በ1993 በሞሪሺየስ በተካሄደው እንዲሁም እ.አ.አ በ2001 ራሷ ባዘጋጀችው የአፍሪካ ዋንጫ ላይ ተሳትፋለች። የሴካፋ ዞን ማጣሪያ እስከ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።
አካባቢ ጥበቃ
የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት ወሳኝ የትብብር ማዕከል መሆን አለበት
Sep 17, 2026 315
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት ወሳኝ የትብብር ማዕከል መሆን እንዳለበት የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። ኢጋድ እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር ከ2026 እስከ 2035 ለ10 ዓመታት የሚተገብረውን የቀጣናው የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት ዕቅድ እና የኢጋድ ቀጣና የግብርና ዘር ፖሊሲ የባለሙያዎች ግምገማ በማድረግ በሚኒስትሮች አጸድቋል። የኢጋድ ዋና ጸሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና ሊከሰቱ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቋቋም በትብብር የምንቆምበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነው ያለነው ብለዋል ። ኢጋድ በቀጣናው ሀገራት የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የማይበገር ኢኮኖሚ መገንባት ቀዳሚ መርሁ መሆኑን ገልጸዋል። የኢጋድ የግብርና ምርትና የምግብ ሥርዓት ኢንቨስትመንት የ10 ዓመት ዕቅድ በቀጣናው ቀጣይነት ያለውና አይበገሬ የምግብ ሥርዓት መገንባት ያስችላል ብለዋል። የኢጋድ ቀጣናዊ የግብርና ዘር ፖሊሲም የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን የሚቋቋም ዘላቂ ኢኮኖሚ ማንበር እንደሚያስችል ገልጸዋል። በአፍሪካ አህጉራዊ ሽግግር ለመፍጠር የኢጋድ ኢኒሼቲቮች ጉልህ አበርክቶ እንዳላቸው ጠቁመው፤ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖን በመቋቋም የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የቀጣናው ሀገራት በትብብር መሥራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ለዚህ ደግሞ የኢጋድ ቀጣና ሀገራት ሕዝባቸውን፣ ሀብታቸውንና እውቀትን በማስተባበር፣ የፋይናንስ አቅምን ማጠናከርና ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባቸው ገልጸዋል። የግብርና ሚኒስትር ከፍተኛ አማካሪ ጌታቸው ድሪባ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የኢጋድ ቀጣና ሀገራት በባህል፣ በታሪክና በኢኮኖሚ የተሳሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል። የምግብ ዋስትና ማረጋገጥ በዓለም አቀፍ የሥርዓተ ምግብ መዋቅር ትኩረት የተሰጠው መሆኑን ጠቅሰው፤ ለተግባራዊነቱ መረባረብ ይገባል ብለዋል። ኢትዮጵያ ሥርዓተ ምግብና የግብርና ዘር ፖሊሲ ዋና አጀንዳዋ ነው ያሉት ከፍተኛ አማካሪው፤ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሚያስችል የትኩረት ማዕከል መሆኑንም ገልጸዋል።
የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያ መረጃዎችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የተሻለ ዝግጁነት እንዲኖር በቅንጅት እየተሰራ ነው
Sep 17, 2026 178
አዳማ፤ መስከረም 7/2019(ኢዜአ )፡-የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያ መረጃዎችን በስፋት ተደራሽ በማድረግ የተሻለ ዝግጁነትና ቅድመ ጥንቃቄ እንዲኖር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ የባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት የክረምት ወቅት የአየር ጠባይ ግምገማና የመጪው በጋ ወራት የአየር ጠባይ ሁኔታ ትንበያ መድረክ በአዳማ በማካሄድ ላይ ይገኛል። የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ፈጠነ ተሾመ(ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለፁት፤ ኢንስቲትዩቱ ለሀገሪቷ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ጠቀሜታ ያላቸውን የአጭርና የረዥም ጊዜ የአየር ፀባይ ትንበያዎችን በወቅቱ በማቅረብ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል። መረጃዎቹ በተለይም ለግብርና፣ ለውሃ ሀብት አስተዳደር፣ ለአደጋ ስጋት ቅነሳ፣ ለአቪየሽንና ትራንስፖርት፣ ለመስኖ ልማት እንዲሁም ለትምህርትና ጤና ዘርፎች እንቅስቃሴዎችን ለማከናወን ቁልፍ አጋዥ መሆናቸውን ገልጸዋል። በመሆኑም ወቅታዊና አስተማማኝ የአየር ፀባይ መረጃዎችን ለተጠቃሚው ህብረተሰብና ለባለድርሻ አካላት ተደራሽ የማድረጉ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል። ወቅቱን የጠበቀና ትክክለኛ የአየር ፀባይ መረጃ ተደራሽነትን ማረጋገጥ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ ልማትና ዕድገት ወሳኝ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ባለድርሻ አካላትም በየወቅቱ ተደራሽ የሚደረጉ የአየር ፀባይ ሁኔታዎችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ በማድረግ ሀገራችን የጀመረችው ልማትና ዕደገት እንዲፋጠን እያደረግን ያለነውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል። መድረኩ የክረምት የአየር ፀባይ ሁኔታን ከመገምገም ባለፈ በመጪው የበጋ ወቅት ሊኖር የሚችለውን የአየር ሁኔታ ትንበያ መረጃን ለተጠቃሚዎች በወቅቱ ተደራሽ በማድረግ ቀድመን ለማዘጋጀትና ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል መሆኑንም ገልጿል። የአየር ፀባይ ሁኔታ ትንበያን መሰረት በማድረግ የቅድመ ዝግጅት እርምጃዎችን መውሰድ ከባለድርሻ አካላት ይጠበቃል ያሉት ፈጠነ(ዶ/ር)፤ የአየር ፀባይ ተፅዕኖን ለመቋቋምና ቅድመ እርምጃ ለመውሰድ መድረኩ ወሳኝ ሚና አለው ብለዋል። የመጪውን የበጋ ወቅት የአየር ፀባይ ሁኔታ ትንበያ ያቀረቡት የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በመጪው የበጋ ወቅት በአርብቶ አደር አካባቢዎች ለግብርና ልማት ምቹ የሆነ የተሻለ የዝናብ ስርጭት ይኖራል ብለዋል። በተለይም ምስራቅ ሐረርጌን ጨምሮ የቦረናና ጉጂ ዞኖች፣ ሲዳማና ደቡብ ኢትዮጵያ አከባቢዎች በበጋ ወቅት የተሻለ የዝናብ ስርጭት ያገኛሉ ብለዋል። አብዛኞቹ የበጋ ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ አካባቢዎች ዓመታዊ የዝናብ ስርጭታቸውን ከ75 በመቶ በላይ የሚያገኙት በዚህ ወቅት መሆኑን ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። ይህም የአየር ፀባይ ተፅዕኖ ለመቋቋምና የውሃ ሀብትን አቅቦ ለመጠቀም ጥሩ አጋጣሚ እንደሚፈጥር ተናግረዋል። በዘንድሮው የበጋ ወቅት በኦሮሚያ ክልል በቦረና እና ጉጂ ዞኖች፣ በሶማሌ ክልል ዞኖች፣ እንዲሁም በሲዳማና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልሎች አከባቢዎች ከ75 በመቶ በላይ መደበኛና ከመደበኛ በላይ የዝናብ ስርጭት ይኖራል ተብሎ እንደሚጠበቅም ምክትል ዳይሬክተሩ ገልጸዋል። የበጋ ወቅት ዝናብ ተጠቃሚ የሆኑ አከባቢዎች ከመጪው ጥቅምት ወር ጀምሮ የዝናብ ስርጭቱን የሚያገኙ መሆናቸውንም ጨምረው ገልጸዋል።
በአፍሪካ ቀንድ ኤልኒኖ ሊያስከትል የሚችለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ለመቋቋም የቀጣናው ሀገራት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ ትንበያ እርምጃ መውሰድ አለባቸው
Sep 17, 2026 180
አዲስ አበባ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ):- በአፍሪካ ቀንድ ኢልኒኖ ሊያስከትል የሚችለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመቋቋም የቀጣናው ሀገራት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ ትንበያ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አስታወቀ። ኢጋድ በአፍሪካ ቀንድ ኤልኒኖ የሚያስከትለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ለመቋቋም የቀጣናው ሀገራት የሚያደርጉትን ዝግጅት በተመለከተ በአዲስ አበባ ምክክር እያደረገ ነው። የኢጋድ ምክትል ዋና ጸሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ በዚህ ወቅት እንዳሉት፤ የኤልኒኖ ክስተት በአፍሪካ ቀንድ በሕይወትና በንብረት ላይ አደጋ ሊያስከትል ይችላል። በአፍሪካ ቀንድ ከወትሮው የተለየ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ሊያስከትል እንደሚችል የአየር ትንበያ መረጃዎች ያሳያሉ ብለዋል። የኤልኒኖ መከሰት ተፈጥሯዊ መሆኑን በማንሳት፤ የዝናቡ መጠን በግብርና፣ በእንስሳት እርባታ እና በምግብ ዋስትና ላይ ሊያስከትል የሚችለውን ጫና መቀነስ እንደሚቻል ገልጸዋል። ለዚህ ደግሞ ኤልኒኖ በአፍሪካ ቀንድ ሊያስከትለው የሚችለውን የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ ለመቋቋም የቀጣናው ሀገራት የቅድመ ማስጠንቀቂያና ቅድመ ትንበያ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው ብለዋል። የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ከ24 ሰዓታት በፊት ማድረስ ብቻ የአደጋውን መጠን በ30 በመቶ መቀነስ እንደሚያስችል ገልጸዋል። ለቅድመ ዝግጅትና ቅድመ ትንበያ እርምጃዎች ፋይናንስ አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ፤ አደጋውን ለመከላከል ከወዲሁ የድጋፍና መልሶ ማቋቋም ወጪን ማሳደግ ይገባል ብለዋል። የኢጋድ አባል ሀገራት ዕቅዶቻቸውን ማቅረብ፣ ግብዓቶችን አስቀድመው ማከማቸትና ድንበር ተሻጋሪ የማስጠንቀቂያ መረጃዎችን ማጋራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ አጋሮች ኤልኒኖ ሊያስከትለው የሚችለውን አደጋ መከላከል የሚያስችል ድጋፍና አብሮነታቸውን እንዲያሳዩም ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ዘላቂና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕይዋን ውጤታማ በሆነ መልኩ አጠናክራ ቀጥላለች
Sep 15, 2026 337
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ):- ኢትዮጵያ ዘላቂና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕይዋን ውጤታማ በሆነ መልኩ አጠናክራ መቀጠሏን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ አለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ። ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው የኖርዲክ-አፍሪካ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪ (Nordic Africa EV Summit) ጉባኤ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ነው። ሚኒስትሩ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መሪነት አረንጓዴና የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም የልማት ስትራቴጂን በሀገራዊ የልማት ዕቅዷ ማዕከል አድርጋ እየሰራች ትገኛለች። የአረንጓዴ አሻራ፣ የታዳሽ ኃይል ማስፋፋት፣ የአረንጓዴ ከተማ ልማት እና ዝቅተኛ የካርቦን ልቀት ያለው ኢኮኖሚ የመገንባት ጥረት ኢትዮጵያ የልማት አቅጣጫዋን ለመለወጥ ያላትን ቁርጠኝነት ያሳያል ብለዋል። የሀገሪቱ የረጅም ጊዜ የአየር ንብረት ስትራቴጂ የትራንስፖርት ዘርፉን ከካርቦን ነፃ ማድረግን ዋነኛ መንገድ አድርጎ ማስቀመጡንም ጠቁመዋል። የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን፣ የሕዝብ ትራንስፖርትን፣ የአረንጓዴ ከተማ ኮሪደሮችን እና ንፁህ የትራንስፖርት ሥርዓቶችን ከታዳሽ ኃይል አቅም ጋር የማዋሃድ ሥራ እየተከናወነ መሆኑንም አብራርተዋል። ይህ ጥረት ከአካባቢ ጥበቃ ባለፈ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን፣ የኃይል ደህንነት፣ የቴክኖሎጂ ፈጠራ፣ የኢንዱስትሪ ልማት እና የዜጎችን የኑሮ ጥራት የማሻሻል አጀንዳ መሆኑን አስገንዝበዋል። የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽን፣ ግንኙነት እና መሠረተ ልማት ክፍል ዳይሬክተር ሮበርት ታማ ሊሲንጌ በበኩላቸው፤ በአፍሪካ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን የመጠቀምና የማምረት አጠቃላይ አዝማሚያ እየጨመረ መምጣቱን ገልጸዋል። አህጉሪቱ ኃይል በማመንጨት ላይ ብቻ ሳትወሰን የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ለሀገር ውስጥ ገበያ እንዲሁም ወደ አውሮፓና እስያ ለመላክም መስራት እንዳለባት ገልጸው፤ ሀገራት ተሽከርካሪዎቹን ለማስገባት የሚያስችሉ ማበረታቻዎችንና የተሟላ ስነ-ምህዳር በመፍጠር ላይ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የኖርዲክ-አፍሪካ ኢቪ ሳሚት ሮድ ቱ አፍሪካ የሀሳብ መሪ ሚከል ቤከር አከርቪክ እንደተናገሩት፤ ከተሞችን ከካርቦን ነፃና ንፁህ አየር እንዲኖር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል። በትራንስፖርት ዘርፍ የሚፈጠረው የልቀት መጠን ከፍተኛ በመሆኑ፣ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን አሰራር መተግበር በኢኮኖሚ ደረጃ ብቻ ሳይሆን ለአካባቢ ጥበቃም እውነተኛ ትራንስፎርሜሽን እንደሚያመጣ አስረድተዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
በቀጣናው ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመፍታት የሀገራት የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው - ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር)
Sep 15, 2026 537
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ)፦ በቀጣናው እያጋጠሙ የሚገኙ ፈተናዎች በዘላቂነት እንዲፈቱ የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ገለጹ። የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት 74ኛው አስቸኳይ ስብሰባውን ዛሬ በጅቡቲ አካሂዷል። በስብሰባው ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች ተሳትፈዋል። በቀጣናው ሰላም እና ጸጥታ እንዲሁም በሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ምክክር ተደርጓል። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ በቀጣናው እያጋጠሙ ያሉ ፈተናዎችን በዘላቂነት ለመቋቋም የአባል ሀገራት አብሮነትና የጋራ ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው። በኢጋድ ሴክሬታሪያት በኩል የተከናወኑ የልማትና የሰላም ሥራዎች አበረታች ውጤቶችን እያስገኙ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ተቋሙ ለቀጣናው ህዝቦች ብልጽግና መረጋገጥ የጸና አቋም እንዳለው አመልክተዋል። ምንም እንኳን የተለያዩ ጂኦፖለቲካዊ ፈተናዎች ቢኖሩም፣ የኢጋድ ሴክሬታሪያት ያለፉት ስድስት ወራት አፈጻጸም አበረታች የሚባል መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣናዊ መሠረተ ልማት እና የጤና ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችን ያነሱት ዋና ፀሐፊው፤ የቀጣናው የከርሰ ምድር ውሃ መረጃ ሥርዓት የአገልግሎት ተደራሽነት የላቀ ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመዋል። እንዲሁም የቀጣናው ዓለም አቀፍ የጤና ሽፋን መረጃ ጠቋሚ (ኢንዴክስ) ከ60 ወደ 65 በመቶ ከፍ ማለቱንና ይህም እ.አ.አ በ2027 70 በመቶ ለማድረስ የተያዘውን እቅድ ለማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያነሱት። በሌላ በኩል ሱዳን ወደ ኢጋድ ሙሉ አባልነቷ መመለሷ የቀጣናውን ትብብርና አንድነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። ዋና ፀሐፊው እ.አ.አ ጁላይ 2026 ወደ ሱዳን ባቀኑበት ወቅት የኢጋድ የሱዳን ልዑክ ቢሮ በድጋሚ በይፋ መከፈቱን አስታውሰው ይህ እርምጃ ከቀጣናው ሕዝቦች ጋር ያለውን ቀጥተኛና ዘላቂ ትስስር አጠናክሮ የሚያስቀጥል መሆኑን አመላክተዋል። ኢጋድ ከአፍሪካ ሕብረት፣ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኤጀንሲዎች እና ከሌሎች ስትራቴጂካዊ አጋሮች ጋር ያለው ግንኙነት ለቀጣናው ዘላቂ ልማት ወሳኝ ነው ብለዋል። አጋርነቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራትን አቅም በማጠናከር ረገድ የጎላ ድርሻ እንደሚያበረክትም ነው ያነሱት። በቀጣይ ሊከሰቱ የሚችሉ የአየር ንብረት ለውጥ አደጋዎችን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ስርዓትን በማጠናከር ለመቋቋም የሚያስችሉ አሰራሮች እየተቀረፁ መሆናቸውን ተናግረዋል። ሀገራት የኤልኒኖ (El Niño) የአየር ንብረት መዛባት የሚያስከትለውን ስጋት ለመቀነስ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንዳለባቸው አሳስበዋል። በሌላ በኩል ቀጣናውን ከሰው ሰራሽ አስተውሎት ጋር ለማስተሳሰርና በቴክኖሎጂ የታገዘ የልማት መሠረት ለመጣል የተጀመሩ ስራዎች ተስፋ ሰጪ መሆናቸውን ገልጸዋል። ስብሰባው የቀጣናውን ሰላም፣ ደህንነት እና ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማፋጠን በሚያስችሉ ሀገራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ በመምከርና ውሳኔዎችን በማሳለፍ መጠናቀቁን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬተሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። የኢጋድ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ከተቋሙ ቁልፍ የፖሊሲ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ ሲሆን፣ የድርጅቱን ሥራዎች በመምራትና በአባል ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና የሚጫወት ነው።
አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ ይልቁንም የሚገባትን ስፍራ በባለቤትነት እየያዘች ነው
Sep 9, 2026 510
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ):- አፍሪካ በዓለም ፊት ቦታ ለማግኘት አትማጸንም ፤ የሚገባትን ስፍራ እና ክብር በራሷ እያረጋገጠች ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን በማስመልከት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ህብረት ቀን እ.አ.አ በ1999 የቀድሞ የአፍሪካ አንድነት ድርጅት ለመተካት ይፋዊ ውሳኔ የተላለፈበት የሰርጥ ድንጋጌ (Sirte Declaration) የሚታወስበት እንደሆነ ገልጸዋል። በዚያን ወቅት የአፍሪካ መሪዎች አህጉራዊ ትስስርን ለማፋጠን እና የአፍሪካን ድምጽ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ለማድረግ የአፍሪካ ህብረትን ለመመስረት ወሳኝ እና ታሪካዊ እርምጃ የወሰዱበት ምዕራፍ ነው ብለዋል። የዘንድሮው የአፍሪካ ህብረት ቀን ለአህጉሪቱ እጅግ ልዩ ትርጉም ባለው ወቅት ላይ እየተከበረ እንደሚገኝ አውስተዋል። ከጥቂት ቀናት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ የአፍሪካን እውነተኛ ቁመና እና ትክክለኛ መጠን የሚያሳይ የዓለም ካርታ አጠቃቀምን የሚደግፍ፣ በአፍሪካ መሪነት የቀረበ የውሳኔ ሀሳብ አፅድቋል። በቶጎ ሃሳብ አመንጪነትና በአፍሪካ ህብረት ድጋፍ እውን የሆነው ይህ እርምጃ ከቀላል የካርታ ማስተካከያ በላይ ትርጉም አለው ብለዋል ሊቀ መንበሩ። አፍሪካ በዓለም ፊት እንዴት እንደምትታይ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑን እና አፍሪካ ራሷን የምትገመግምበትንና የምታሳይበትን ትርክት ራሷ መቅረጽ እንዳለባት አበክሮ የሚያስታውስ ነው። ይህ ውሳኔ አፍሪካ በዓለም ፊት በምን መልኩ መታየት እንዳለባት ከማሳየቱም በላይ፤ አፍሪካ ራሷን የምትመዝንበትንና እውነታዋን ለዓለም የምታሳይበትን ትርክት በራሷ መቅረጽ እንዳለባት በግልጽ የሚያሳይ መሆኑን ነው ያነሱት። የአፍሪካ እጣ ፈንታ የሚወሰነው በአፍሪካውያን የራሳቸው እይታ ነው። አፍሪካን በእውነተኛ ቁመናዋ፣ኃይሏ እና አቅሟ የምንመለከትበት ጊዜ አሁን ነው ብለዋል። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር አያይዘውም ካርታውን የማስተካከል እርምጃ አፍሪካ ወደ ላቀ የጋራ ራዕይ የምታደርገው አህጉራዊ ጉዞ አካል መሆኑን አንስተዋል። ይህም በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ ንግድ ቀጠና (AfCFTA) አማካኝነት የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከርን፣ ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥን፣ ዘላቂ ልማትን እውን ማድረግን እና በዓለም አቀፍ ውሳኔ ሰጪ አካላት ውስጥ የአፍሪካን ተሳትፎ ማሳደግን እንደሚያካትት በዝርዝር አስረድተዋል። የአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 የተሳሰረች፣ የበለጸገች እና ሰላማዊት አፍሪካን ለመገንባት የማዕዘን ድንጋይ ሆኖ እንደሚቀጥልም አረጋግጠዋል። ሰላም እና ፀጥታን ማረጋገጥ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን በማፋጠን እና የአፍሪካን ዓለም አቀፍ ተሰሚነት መጨመር የአፍሪካ ህብረት ቀዳሚ ትኩረቶች ናቸው ብለዋል። አፍሪካ በዓለም ፊት እውቅና ለማግኘት አትለምንም፤ ይልቁንስ በዓለም አቀፍ መድረክ የሷ የሆነውን ትክክለኛ ስፍራ በራሷ ባለቤትነት እየያዘች ነው። አሁን የሚጠበቅብን ይህንን ጠንካራ እምነት ወደ ህብረት፣ ሀብትና ብልጽግና፣ ሰላም እና ተደማጭነት መለወጥ ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ አፍሪካ የምታስመዘግበው እድገት በዓለም አቀፍ መድረኮች በሚኖራት ውክልና ብቻ ሳይሆን፣ በዜጎቿ ላይ የኑሮ ጥራት መሻሻል ጭምር መለካት እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል። በዚህም መሰረት የአፍሪካ ህብረት የ2026 ዓመት ትኩረቱን በዘላቂ የንጹህ ውሃ አቅርቦት እና ደህንነቱ የተጠበቀ የንጽህና አገልግሎት ላይ ማድረጉ፣ ህብረቱ አህጉራዊ ራዕዮችን ከዕለት ተዕለት የዜጎች ህይወት ጋር ለማያያዝ ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አመልክተዋል። በአፍሪካ ህብረት ቀን አከባበር አባል ሀገራት፣ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች፣ የአፍሪካ ተቋማት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ሴቶች እና ወጣቶች ተባብረው ይበልጥ የተሳሰረች፣ በራሷ አቅም የምትተማመን እና የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ መወሰን የምትችል አፍሪካን እንዲገነቡ ሊቀመንበሩ ጥሪ አቅርበዋል። የምንፈልጋት አፍሪካ የሚለውን አህጉራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ እና የሰርት ድንጋጌ ለቀጣዩ የአፍሪካ ትውልድ ዘላቂ የትምህርት እና የዕድገት መሰረት ሆኖ እንደሚቀጥል ገልጸዋል። የነገዋ አፍሪካ በካርታ ላይ ብቻ የተሻለ ውክልና ያላት ብቻ ሳትሆን፤ በዓለም አቀፍ መድረክ ሉዓላዊነቷ የጸና፣ ጠንካራ ውስጣዊ አንድነት ያላት፣ ለህዝቦቿም ዘላቂ ብልጽግናን የምታጎናጽፍ አህጉር መሆን ይኖርባታል ነው ያሉት። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር ለመላው አፍሪካውያን እና በውጭ ሀገር ለሚገኙ የአፍሪካ ዳያስፖራዎች ሰላማዊ እና የትብብር መንፈስ የተሞላበት የአፍሪካ ህብረት ቀን እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 4, 2026 701
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ ህብረት እና አሜሪካ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን እና ሁሉን አቀፍ ትብብራቸውን የበለጠ ለማላቅ እንደሚሰሩ አስታወቁ። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል። ውይይቱ በአፍሪካ ህብረትና አሜሪካ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት ማጠናከር እና በአህጉሪቱ ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። የኮሚሽኑ ሊቀመንበር የአፍሪካና አሜሪካን ትብብር ታሪካዊ መሆኑን አውስተው በህብረቱ፣ በአባል ሀገራት እና በአሜሪካ መካከል የሁለቱንም ወገኖች ጥቅም በሚያስጠብቅ መልኩ ጠንካራ አጋርነት መገንባት እንደሚገባ አሳስበዋል። በምስራቅ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሱዳን እየተደረጉ ላሉ አፍሪካ መር የሰላም ጥረቶች አሜሪካ እያደረገች ላለው ገንቢ አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ፍራንክ ጋርሺያ በበኩላቸው አፍሪካ አሜሪካ ቀዳሚ ትኩረት የምትሰጣት አህጉር እንደሆነች ገልጸዋል። የጋራ ፍላጎቶችንና ግቦችን ከህብረቱ ኮሚሽንና ከአባል ሀገራት ጋር በመሆን ለማሳካት ያላቸውን ጽኑ ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል። በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በዲፕሎማሲ፣ እንዲሁም በሰላምና ጸጥታ ያለውን ትብብር ማጠናከር እንደሚገባም አመልክተዋል። በውይይቱ ላይ በሱዳን ጉዳይ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ፣ የሰብአዊ እርዳታ ያለ ገደብ እንዲገባ እና በሲቪሎች የሚመራ ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር አጽንዖት ተሰጥቷል። በአፍሪካ ባለቤትነት የሚመሩ የሰላም ጥረቶች እና አሜሪካ የምትደግፋቸው የሰላም ሂደቶች በተቀናጀ መልኩ ለመተግበር ከስምምነት ላይ ተደርሷል። በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በመሰረተ ልማት እና በሰላም መስኮች የሁለቱን ወገኖች ትብብር ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ የትብብር መስኮች ተገምግመዋል። ሁለቱ ወገኖች በአፍሪካ ህብረትና በአሜሪካ ስትራቴጂክ ኢንቨስትመንት ማዕቀፍ ውስጥ የተደረጉ ስምምነቶችን ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። በሊቢያ ጉዳይ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሄ ማግኘት እንደሚያስፈልግም ተነስቷል። የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር እና ረዳት ሚኒስትሩ የሁለቱን ወገኖች ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከርና የትብብር አድማሱን ለማስፋት የጋራ ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ኢትዮጵያ 76ኛውን የዓለም ጤና ድርጅት ስብሰባ ታስተናግዳለች
Aug 5, 2026 2003
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 29/2018 (ኢዜአ)፦ 76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ ስብሰባ (RC76) ከነሐሴ 18 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይካሄዳል። ስብሰባው ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር የሚዘጋጅ ነው። በዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና መረጃ መሠረት፣ ስብስባው የቀጣናውን የጤና አጀንዳዎች ላይ መምከርና አህጉራዊ ትብብርን ማጠናከርን ያለመ ነው። የ47ቱ የአፍሪካ ቀጣና አባል አገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ጤና መሪዎች፣ የልማት አጋሮች፣ ለጋሾችና የዓለም ጤና ድርጅት ተወካዮችን ጨምሮ ከ600 በላይ ተወካዮች በስብስባው ላይ ይሳተፋሉ። የስብሰባው ተሳታፊዎች በቀጣናዊ የጤና አቅዶች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችን የሚገመግሙ ሲሆን በአዳዲስ ስትራቴጂዎችና የውሳኔ ሀሳቦች ላይ ይመክራሉ። እንዲሁም የጤና ሥርዓቶችን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ የጤና ሽፋን ተደራሽነትን ለማስፋፋት፣ የጤና ደህንነትን ለማሻሻልና የአደጋ ጊዜ ዝግጁነትን ለማሳደግ የሚረዱ የጋራ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሎ ይጠበቃል። በኢትዮጵያ፣ በአፍሪካ ህብረትና በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) የዓለም ጤና ድርጅት ተወካይ ፕሮፌሰር ፍራንሲስ ካሶሎ፤ ስብሰባው አባል አገራት የቀጣናውን የጤና አጀንዳ እንዲቀርጹ፣ አጋርነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና በመላው አፍሪካ ጤናማ፣ አስተማማኝና ጠንካራ ማህበረሰቦችን የመገንባት ሂደት ለማፋጠን ትልቅ እድል የሚሰጥ ነው ብለዋል። ተወካዩ አክለውም የኢትዮጵያ ስብሰባውን ማስተናገድ፤ ለቀጣናዊ ወንድማማችነትና ለጋራ ትብብር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን ገልጸዋል። ይህ አህጉራዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የጤና ሥርዓት ስኬቶች፣ በተለይም መሰረታዊ የጤና አገልግሎቶችን በማስፋፋትና በቅርቡ በክልል የተከሰተውን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በመቆጣጠር ረገድ የተመዘገቡ ውጤቶችን ለማሳየት ዕድል እንደሚፈጥር መረጃው አመልክቷል። ስብስባው የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ፣ የዲፕሎማሲ ማዕከልነቷን በመጠቀም ለጋራ የጤና ፈተናዎች የተቀናጀ አህጉራዊ ምላሽ ለመስጠት ስትራቴጂካዊ መድረክ እንድትሆን ያደርጋታል። በስብስባው ላይ የቴክኒክ ውይይቶች፣ አውደ ርዕዮች ፣ የሁለትዮሽ ስብሰባዎችና የሕዝብ ግንኙነት ስራዎች የሚካሄዱ ሲሆን፣ እነዚህም በአፍሪካ ተቋማት መካከል የጤናው ዘርፍ የፈጠራ ስራዎችንና የእውቀት ልውውጥን የሚያጎሉ እንደሚሆኑ ተገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ የቀጣናዊ ጽሕፈት ቤቱ የበላይ አካል ሲሆን፤ በየዓመቱ በመሰብሰብ የቀጣናውን የጤና ፖሊሲ ይወስናል፣ የድርጅቱን ሥራዎች ይገመግማል፣ እንዲሁም በመላው አህጉሪቱ ለሚከናወኑ የጤና ተግባራት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ያስቀምጣል።
ሐተታዎች
በአትሌቲክሱ ዘርፍ ታሪክ ለመጻፍ ተስፋን የሰነቁ ታዳጊ ስፖርተኞች
Sep 17, 2026 112
የኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በየዓመቱ በተለያዩ የስፖርት ዓይነቶች ታዳጊዎችን በማሰልጠን ተተኪ ስፖርተኞችን እያፈራ ይገኛል። በ2019 በጀት ዓመትም በአትሌቲክስ፣ በእግር ኳስ፣ በቅርጫት ኳስ፣ በቦክስ፣ በፓራሊምፒክ እና በሌሎች የስፖርት ዓይነቶች ታዳጊዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን ነሐሴ 2018 ዓ.ም. በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የመጀመሪያ ዙር የእጩ ታዳጊ ሰልጣኞች ምልመላ አካሂዷል። በመጀመሪያው ዙር ከተመለመሉ እጩ ሰልጣኝ ታዳጊዎች መካከል በዘንድሮ ዓመት አካዳሚውን የሚቀላቀሉ ሰልጣኞችን ለመለየት ደግሞ ከመስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም. ጀምሮ የመጨረሻ የምልመላ እያካሄደ ነው። የአካዳሚው አሰልጣኞችና ታዳጊ ሰልጣኞች ለኢዜአ እንዳሉት፤ አካዳሚው ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ታዳጊዎች ክህሎታቸውን የሚያሳድጉበት ዕድል በመፍጠር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው። ከአርሲ በቆጂ የመጣውና የአካዳሚውን የመጨረሻ ዙር ሥልጠና እየተወዳደረ የሚገኘው የ17 ዓመቱ ታዳጊ ዳግም ደጀኔ፤ ለአትሌቲክስ ባለኝ ልዩ ፍቅር ሀገሬን በዓለም አደባባይ ለማስጠራት ሕልም አለኝ ብሏል። የሥልጠና ምልመላ ሂደቱንም በስኬት ለማለፍ የቴክኒክ፣ የሥነ-ልቦናና ሌሎች ቅድመ ዝግጅቶችን በማድረግ መወዳደሩን አስታውቋል። ሌላኛዋ የ17 ዓመት ታዳጊዋ ሰሚራ ሸምሱ በበኩሏ፤ በአካዳሚው ምቹ የስፖርት መሠረተ ልማት በመሰልጠን የዕድሉ ተጠቃሚ መሆን በመቻሏ ዝግጁ መሆኗን ገልጻለች። አትሌቲክስ የሀገር ፍቅርን የምናሳይበት መድረክ በመሆኑ ይህን የስፖርት ዓይነት ልመርጥ ችያለሁ ያለው ደግሞ ከጉራጌ ዞን የመጣው የ17 ዓመቱ ታዳጊ ሰለሞን ግርማ ነው። በአትሌቲክስ መስክ የተሻለ ሳይንሳዊ ሥልጠና ወስዶ ስመጥር አትሌት ለመሆን ወደ አካዳሚው መግባት የሚያስችለውን ውድድር በማድረግ የተተኪ ስፖርተኞች አካል ለመሆን መዘጋጀቱን ተናግሯል። የ16 ዓመቷ ታዳጊ ሕንደኬ በሬ በበኩሏ በዓለም አቀፍ የስፖርት ውድድር መድረኮች የኢትዮጵያን ባንዲራ ከፍ ያደረጉ አትሌቶችን እያየች ማደጓ ለአትሌቲክስ ፍቅር እንዲኖራት እንዳስቻላት ገልጻለች። የወደፊት ሕልሟ የመሰናክል ሯጭ መሆን እንደሆነ በመግለጽ፣ ለዚህ የስፖርት ዓይነት አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ አካዳሚውን ለመቀላቀል ጥረት እያደረገች እንደምትገኝ ጠቁማለች። በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የምርምር ቤተ-ሙከራ ወርክሾፕ ኃላፊ በእምነት ተለሞስ እንዳሉት፣ አካዳሚው ታዳጊዎችን ተቀብሎ ለማሰልጠን የሰልጣኞች መመልመያ መስፈርቶችን አዘጋጅቶ እየተጠቀመ ነው። ከመስፈርቶቹ መካከልም ታዳጊዎቹ ለእያንዳንዱ የስፖርት ዓይነት የሚገኙበትን የቴክኒክና የአካል ብቃት፣ የታዳጊዎች የጤና ሁኔታና የሥነ-ልቦና ደረጃ ጉዳዮችን መካተታቸውን አብራርተዋል። በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ የአትሌቶች ትምህርትና ሥልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ ኢንስትራክተር ፍቃዱ ከበደ በበኩላቸው፣ በ2019 በዘጠኝ የስፖርት ዓይነቶች ከ16 እስከ 17 ዓመት የዕድሜ ክልል የሚገኙ 358 ታዳጊዎችን ለማሰልጠን መታቀዱን አስታውቀዋል። የሥልጠና ዓይነቶችም አትሌቲክስ፣ እግር ኳስ፣ ቅርጫት ኳስ፣ ቦክስ፣ ፓራሊምፒክ፣ ቮሊቦል፣ ብስክሌት፣ ወርልድ ቴኳንዶ እና ጠረጴዛ ቴኒስ መሆናቸውን አብራርተዋል። በዚህም በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ለመጨረሻ ዙር 638 እጩ ሰልጣኞችን በመመልመል አካዳሚውን የሚቀላቀሉ 358 ታዳጊ ስፖርተኞችን ለመምረጥ የመጨረሻ ዙር ምልመላ እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጨረሻ ዙር ምልመላ የሚያልፉ ታዳጊዎችም በተመለመሉበት የስፖርት ዓይነት ለአራት ዓመታት በአካዳሚውና በአሰላ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ አትሌቲክስ ማሰልጠኛ ማዕከል ሳይንሳዊ ሥልጠና እንደሚከታተሉ ተናግረዋል።
ጤናማ ዜጋ አምራች ሀገር፤ የመደመር መንግሥት የጤና ፖሊሲ ትሩፋት
Sep 15, 2026 337
አዲስ አበባ፤ መስከረም 5/2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ ነገን ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተገበረችው አዲስ የጤና ፖሊሲ የመደመር መንግስት ቃልን በተግባር የመተርጎም ብቃትን ከሚያመላክቱ ትሩፋቶች መካከል ተጠቃሽ ነው። የመደመር መንግስት ባለፉት ስምንት ዓመታት ትኩረት ከሰጠባቸው ዘርፎች መካከል ማህበራዊ ልማት ዘርፉ ተጠቃሽ ነው። በዚሀ ዘርፍ ከሚመደቡት መካከል ደግሞ የጤና ዘርፉ ተጠቃሽ ሲሆን የኢትዮጵያ ህዝብ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የጤና አገልግሎት ማግኘት የሚችልበትን ዕድል ለመፍጠር የፖሊሲ ማሻሻያ ማድረግን ጨምሮ የጤና መሰረተ ልማት ግንባታ እና የሰለጠነ የጤና ባለሙያ አቅም ግንባታ ላይ ውጤታማ ተግባራት አከናውኗል። ቅድሚያ መከላከል ላይ ትኩረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ በመከለስ ለአክሞ ማዳንም ትኩረት እንዲሰጥ መደረጉን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግስት ባለፉት ዓመታት በዘርፉ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ በርካታ ሆስፒታሎች ተገንብተው ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረጉንና በዚህም በዘርፉ ውጤታማ ስራዎች መሰራታቸውን መግለጻቸው ይታወሳል። የመደመር መንግስት የህብረተሰቡ ጤና በተሟላ መልኩ ሲጠበቅ ምርታማነት ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አዎንታዊ ሚና በሚገባ በመረዳት ከጤና መሰረተ ልማት ባሻገር ህብረተሰቡ አስቀድሞ ጤናውን ለሚጠብቅባቸው መሰረተ ልማቶች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል። ለዚህ ነው በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ያሉ የኮሪደር ልማትና የወንዝ ዳርቻ ልማት ላይ በትኩረት እየሰራ የሚገኘው ይህ የመንግስት ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የግል ዘርፉም የህብረተሰቡን ጤና ከመጠበቅ እና ለፖሊሲው ውጤታማነት በኩሉን ድርሻ መወጣት የሚችልበት ዕድል ተፈጥሯል። ኢትዮጵያ በጤናው ዘርፍ የተገበረችው አዲስ የጤና ፖሊሲ እና በዘርፉ የወሰደቻቸው ውጤታማ እርምጃዎች አይበገሬ የጤና ስርዓት መዘርጋት አስችሏታል። መንግስት ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ ለሀገር እድገትና ብልፅግና ወሳኝ መሆኑን በመገንዘብ ባለፉት ዓመታት ውጤታማ የፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች በመውሰዱ የጤና ቱሪዝም ተወዳዳሪነትን የሚያሳድጉ ስኬቶች ተመዝግበዋል። ከለውጡ በፊት ኢትዮጵያ ስትከተል የቆየችው በሽታ መከላከል ላይ ብቻ ያተኮረው የጤና ፖሊሲ፣ በጤና አገልግሎት አሰጣጥና የተቋማት ግንባታ እንዲሁም በዘርፉ ቴክኖሎጂ ከመጠቀም አንጻር ክፍተት ይታይበት ስለነበር ውጤታማነቱ ላይ የራሱን ተግዳሮት ደቅኖ ቆይቷል። የመደመር መንግስት የጤናው ዘርፍ ፖሊሲ ምሉዕ የሚሆነው በሽታ መከላከል ላይ ብቻ በማተኮር ሳይሆን አክሞ ማዳንንም የፖሊሲው የትኩረት ማዕከል ማድረግ ሲቻል መሆኑን በማመነ ፖሊሲው ይህንን ባካተተ መልኩ እንዲሻሻል አድርጓል። በተጨማሪም አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ማድረግ የሚያስችሉ ለጤና መሰረተ ልማት ግንባታ ለአካታች የጤና አገልግሎት ለጤና ፋይናንስ እና ለቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውጤታማነት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ በመሰራቱ በመንግስትም ሆነ በግል ዘርፉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ያካተቱ በርካታ የጤና መሰረተ ልማቶች ተገንብተው ወደ አገልግሎት እንዲገቡ ተደርጓል። ለዚህም ይመስላል በአዲስ አበባ ከተማ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን በማዘመን፣ በማስፋፋትና ጥራቱን በማሳደግ ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ መሳሪያዎችን በማስገባት የጤናውን ዘርፍ ለማዘመን እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መናገራቸው። በጤው ዘርፍ የአገልግሎትን ጥራት፣ ተደራሽነትና ፍትሐዊነትን ማረጋገጥ ቁለፍ ጉዳይ ነው። የመደመር መንግስት እነዚህን ችግሮች ለማቃለል ለአዳዲስ ሆስፒታሎች እና ጤና ጣቢያዎች ግንባታ እንዲሁም ለነባሮቹ የጤና ተቋማት የማሻሻያ እና የማዘመን ተግባራት በመከናወናቸው በአገልግሎት ጥራት ተደራሽነትና ፍትሃዊነትን ከማረጋገጥ አንጻር ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይ በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የህክምና ተቋማትን በዘመናዊ የህክምና ግብዓት ማደራጀትና አቅማቸውን ማሳደግ ፍትሃዊ እና ተደራሽ የሆነ እንዲሁም አስተማማኝ የህክምና አገልግሎት በመስጠት የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ የተያዘውን ርዕይ ለማሳካት አይነተኛ ሚና ይኖረዋል። ባለፉት ስምንት ዓመታት በጤና ዘርፍ የነበሩ ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራት መከናወናቸውን የሚገልጹት የጤና ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ በዚህም የመንግስት የጤና ተቋማት ቁጥርና የሀገር ውስጥ ምርት ድርሻ ማደጉን በመጥቀስ የማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድን ሽፋን እና የዜጎች ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉን ለዘርፉ ዕድገት ጥሩ ማሳያ ነው። ባለፉት ስምንት ዓመታት በዘርፉ በተከናወኑ ተግባራት እምርታ መመዝገቡን የመድሃኒት፣ የክትባት እና የህክምና ግብዓቶች ምርት አቅርቦት እና ቁጥጥር መጨመሩን እንዲሁም በጤና ፋይናንስ ስርዓት ላይ የተመዘገበውን ለውጥ በማሳያነት ይጠቅሳሉ። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በተለይ በጤናው ዘርፍ የተከሰቱ ዓለም አቀፍ ወረርሽኞችንና በዘርፉ የተስተዋሉ ተግዳሮቶችን ወደ ዕድል በመቀየር አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ችላለች። በዚህም የወረርሽኝ ልየታ እና ቁጥጥር፣ የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ክብካቤ፣ የጤና ባለሙያዎችን ማብቃትና ቁጥራቸውን ማሳደግ፣ የዲጂታል ጤና እና በዘርፉ የተከናወኑ ልዩ ልዩ የበጎ አድራጎት ተግባራት በጤና ዘርፉ የተመዘገቡ ስኬቶች መሆናቸውን ሚኒስትሯ መጥቀሳቸው ለተፈጠረው አቅም ጥሩ ምሳሌ ነው። የመደመር መንግስት ለማህበራዊ ልማት በተለይም ለጤናው ዘርፍ በሰጠው ትኩረት ምክንያት በርካታ ውጤታማ ተግባራት ተከናውነዋል። እነዚህ በዘርፉ የተከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ለጤና ዲፕሎማሲ ዘርፍ እመርታ አበርክቷቸው ከፍተኛ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ የገለጹ ሲሆን፤ ይህም ኢትዮጵያ የተለያዩ የዘርፉ ዓለም አቀፍ ጉባኤዎችን እንድታስተናግድ ተመራጭ እንዳደረጋት እና ከአፍሪካ በቀዳሚነት ተመርጣ ዓለም አቀፍ የጤና ድርድሮችንና ንግግሮችን እንድትመራ እንዳስቻላትም እንዲሁ።
የሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እመርታ፤ የአረጋውያን በረከት፣ የታዳጊዎች የተስፋ ማዕድ
Sep 14, 2026 433
ሀገር በታሪክ ሰሪዎችና ባለውለታዎች ጀግኖች አባቶች ገድል፣ በነገ ተስፋዎች ጽናት ትገነባለች፤ በጠንካራ ተቋማትና ተስፋን በሰነቁ ፕሮጀክቶች ትጸናለች። የመደመር መንግሥት የዜጎችን ማኅበራዊና ምጣኔ-ሀብታዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ከነደፋቸው ውጥኖች መካከል ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ይጠቀሳሉ። ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች የአቅመ ደካሞችን ቤት በማደስ፣ በተማሪዎች ምገባ እና በወጣቶች ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ብቻ የተመረኮዙ አይደሉም፤ ይልቁንስ የሀገር ባለውለታዎች ካስማ፣ የነገ ተስፋዎች ማገር ናቸው። የመደመር መንግሥት ማኅበራዊ ፍትሕ ማስፈን ቀዳሚ አጀንዳው ሲያደርግ፣ የትናንት የሀገር ጀግኖች ውለታ በመመለስ እና ለነገ ታዳጊዎች ብርሃን በመፈንጠቅ ነው። በኢትዮጵያ በከተማና ገጠር፣ በአዛውንቶችና ወጣቶች መካከል አንዳችም ልዩነት ሳይፈጠር የአካባቢያቸውን የመልማት ጸጋ አውጥቶ መጠቀም የሚያስችሉ የዜጎች ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች ተደራሽ ሆነዋል። በትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ምገባ አዲስ አበባ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተቸረው ውጤት አስመዝግባለች፤ ሌሎች ክልሎችም ብዙ ተምረውበታል። መንግሥት በመዲናዋ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ቤቶች ምገባ መርሃ ግብር 976 ሺህ 702 ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ ቁርስና ምሳ መመገብ የሚያስችል ሥርዓት በማንበር ህዝባዊነቱን በተግባር ገልጧል። ሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ኢኒሼቲቩን እንደ ትምህርት በመውሰድ የትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመጀመር የተማሪዎችን ከትምህርት ገበታ የማቋረጥ ምጣኔ ቀንሰዋል፤ የተማሪዎችን ትኩረት በመሰብሰብ ለውጤታማ መማር ማስተማር ሂደት መሰረት ጥለዋል። የደጃዝማች ወንድይራድ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ናታኒም በላይ፣ በትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር በመጀመሩ ትምህርቱን በሙሉ ትኩረት ሳያቋርጥ የሚማርበት ዕድል ማግኘቱን ገልጿል። በትምህርት ቤቶች የምገባ መርሃ ግብር መጀመሩ ለእናቶች የሥራ ዕድል በመፍጠር ገቢ ማግኘትና የአዕምሮ እርካታ እያገኙ መሆኑን የገለጹት ደግሞ በአፄ ነአኩቶ ለአብ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማሪዎች መጋቢ ወይዘሮ መሰረት እንዳለ ናቸው። በአዲስ አበባ 30 የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከላትን በማቋቋም ራሳቸውን መመገብ ለማይችሉ አቅመ ደካማ ዜጎች የተመጣጠነ ምግብ የሚያገኙበት ምቹ ምኅዳር ተፈጥሯል። የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ 30ኛውን የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሥራ ሲያስጀምሩ፣ የነዋሪዎችን ሕይወት ለመለወጥና ለኑሮ ምቹ አካባቢን መፍጠር ዋና አጀንዳቸው መሆኑን ተናግረዋል። የምገባ ማዕከላትን ማስፋፋት አቅመ ደካማ ወገኖችን ከመመገብ ባለፈ ለነዋሪዎቻችን ያለንን ክብር የምናሳይበትና ለዜጎች የሥራ ዕድል የምንፈጥርበት ነው ብለዋል። ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በመዲናዋ ማኅበራዊ ፍትሕን በማንገስ የኢትዮጵያን ብልጽግና ማረጋገጥ እንደሚያስችሉ ተናግረዋል። ሀገር ላጸኑ የሃገር ባለ ውለታዎች አባቶችና እናቶች በንጹህ፣ ጽዱና ምቹ ቤት የተደላደለ ሕይወት እንዲመሩ ተደርጓል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ታኅሣሥ 2016 የአዋሬ መንደር የጋራ መኖሪያ ህንፃ አሰርተው ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች አስተላልፈዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ሰው ተኮር የልማት ፕሮጀክቶች በአጭር ጊዜ ለውጥ የሚያመጡ፣ የዜጎችን የአኗኗር ዘይቤ የሚያሻሽሉ እና ሀገር የሚያሻግሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አዋሬን እንደ ምሳሌ በመጥቀስ፤ ዕውቀት፣ ሀብትና ጉልበት ተሰናስለው ለሀገርና ሕዝብ ካስማና ማገር የሚሆኑ ተጨባጭ ውጤቶች ማምጣት እንደሚቻል አስረድተዋል። "እንሠራለን፣ ኢትዮጵያን እንቀይራለን፣ ኢትዮጵያን እናበለጽጋለን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ውብ ኢትዮጵያን ለትውልድ ለማስረከብ ዕድሉ በኢትዮጵያውያን እጅ ላይ እንዳለ አረጋግጠዋል። የአቅመ ደካሞችን ቤት መጠገን፣ አለፍ ሲልም አዳዲስ ምቹና ዘመናዊ የመኖሪያ መንደሮችን ከተሟላ የመንገድ፣ የውሃ፣ መብራትና መሰል መሠረተ ልማት ጋር ሰርቶ ማስረከብ የመደመር መንግሥት መገለጫ ሆኗል። በመዲናዋ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ወገኖች ተሰርተው የተላለፉ ቤቶች ተጠቃሚ የሆነው ወጣት ታምራት ተመስገን የአካል ጉዳተኛ በመሆኑ በርካታ ፈተናዎችን ማስተናገዱን ገልጿል። ይሁን እንጂ አዲስ በተረከበው ቤት እንደ ልብ መንቀሳቀስና ሕይወቱን ማሻሻል የቻለበት ዕድል እንደተፈጠረለት ገልጿል። በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤታቸው የታደሰላቸው እናት ወይዘሮ ታየሁ መኮንን "ቤት ነው ለማለት እንኳን በማያስደፍር" ቤት ውስጥ ይኖሩ እንደነበር አስታውሰዋል። በሸራና በላስቲክ ከተጠጋገነ፣ የግድግዳው አፈር ከሚናድ ቤት ውስጥ መቆየታቸውን አስታውሰው፣ "ቤቴ በመታደሱ 'ቤቱ እላዬ ላይ ይደረመሳል' ከሚል ሰቀቀን ተላቅቄ፣ ያለ ሀሳብ ጎኔን ማሳረፍ ችያለሁ" ብለዋል። በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል ከጎዳና ሕይወት ወደ ለውጥ አብነት የተሸጋገሩ ወጣት ልጃገረዶች እልፍ ናቸው። ማዕከሉ በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ ሴቶች አካላዊና ሥነ ልቦናዊ ሕክምና በማድረግ፣ ዘላቂ የሕይወት ክህሎት ሥልጠና በመስጠት ሕይወታቸውን የሚያሻሽሉበት ተቋም ነው። ማዕከሉ በ2016 ዓ.ም ሥራ ከጀመረ በኋላ በአምስት ዙሮች ሦስት ሺህ 259 ሴቶችን በማሰልጠን ወጣቶች ተስፋ እንዳላቸውና ለለውጥ ቅርብ እንደሆኑ በተግባር አሳይቷል። በነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልፀጊያ ማዕከል በ2018 ዓ.ም በአምስተኛ ዙር በዶሮ እርባታ ሥልጠና ወስዳ የተመረቀችው ትዕግስት ፀጋዬ፣ ማዕከሉ ከጎዳና ሕይወት ወጥታ ጠንካራ ስብዕና መገንባት የሚያስችል አቅም እንደፈጠረላት ተናግራለች። በማዕከሉ የቤት አያያዝ ሥልጠና የወሰደችው መሰረት አበራ በበኩሏ፣ ከጎዳና ላይ ከነበረችበት አሰልቺ ሕይወት ተላቃ ጠንካራ የራስ መተማመን በመገንባት ነገን የምታልም ሴት እንዳደረጋት ገልጻለች።
የጭስ አልባው ኢንዱስትሪ ትንሳኤ፡ የመደመር እሳቤ ትሩፋት
Sep 13, 2026 612
ኢትዮጵያ ሺህ ዘመናትን የተሻገሩ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ተፈጥሯዊ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶችን በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አስመዝግባለች። በዓለም የሚዳሰስ ቅርስነት ዝርዝር ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶች መካከል የላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያናት፣ የአጼ ፋሲለደስ አብያተ መንግሥታት፣ የአክሱም ሐውልቶች፣ የሐረር ጀጎል ግንብ፣ የጢያ ትክል ድንጋይ፣ የአዋሽና የኦሞ ሸለቆዎች፣ የኮንሶ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር፣ የራስ ዳሽንና የባሌ ተራሮች ብሔራዊ ፓርኮችና ሌሎችም ይገኙበታል። በማይዳሰስ ቅርስነት ከሰፈሩ የኢትዮጵያ ቅርሶችም የመስቀል ደመራ በዓል፣ ፊቼ-ጫምባላላ፣ የገዳ ሥርዓት፣ ጥምቀት፣ ሹዋሊድ፣ የሶማሌ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት፣ የወላይታ ጊፋታና የመሳሰሉት ሕያው ሃይማኖታዊ፣ ባህላዊና ማኅበረሰባዊ ትውፊቶችን ያካትታሉ። እነዚህ ኢትዮጵያውያን ለዓለም ሕዝብ ያበረከቷቸው የመስህብ ሀብቶችም ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገጽታ ግንባታና ለአካባቢ ልማት የሚያበረክቱት ዕድል በቀላሉ የሚታይ አይደለም። የመደመር መንግሥትም ይህንን የኢትዮጵያውያንን ሰፊ የቱሪዝም አቅም በመረዳት፣ ቱሪዝምን በብዝኅ ዘርፍ የኢኮኖሚ ዕድገት ዕይታው ውስጥ ትኩረት ከሰጣቸው የልማት መስኮች አንዱ አድርጎታል። በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውም ቱሪዝም ከአምስቱ የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አንዱ እንዲሆን በመደረጉ ዘርፉ የሚያስገኘው ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ የበለጠ ትኩረት እንዲያገኝ አድርጓል። ይህም ዘርፉ ከነበረበት ተለምዷዊና አዝጋሚ ዕድገት የሚላቀቅበትን ዘመናዊ የቱሪዝም መዳረሻ መሠረተ ልማቶችን በመገንባት፣ ነባር ቅርሶች በማደስና በመጠገን ውጤታማ ሥራ ተሰርቷል። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሐሳብ አመንጪነት በገበታ ለሸገር፣ በገበታ ለሀገርና በገበታ ለትውልድ የመስህብ መዳረሻ ልማት የቱሪዝሙን ዘርፍ ማንሰራራት ያበስሩ ፕሮጀክቶች እውን ሆነዋል። ለአብነትም በገበታ ለሸገር በአዲስ አበባ የተገነቡ የወዳጅነት፣ አንድነትና የእንጦጦ ፓርኮች፤ የኮሪደርና የወንዝ ዳርቻ ልማት የመዲናዋን ዓለም አቀፍ ገጽታ መቀየር ያስቻለ ምቹ ምኅዳር ፈጥረዋል። በገበታ ለሀገርና ለትውልድ የመዳረሻ ልማት ፕሮጀክትም ጎርጎራ፣ ወንጪ፣ ኮይሻ፣ ሐላላ ኬላ፣ ደንዲ ኢኮ ሎጂ፣ አርባ ምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት፣ ሎጎ፣ ሸበሌ ሪዞርት፣ ኒን ሊ ፓልም ሎጂ እና የመሳሰሉት እንዲገነቡ አስችሏል። ይህም የመደመር መንግሥት የኢትዮጵያን የከተማና ገጠር የቱሪዝም መዳረሻ አሰናስሎ በማልማት ለሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን ገንቢ ሚና መወጣት የሚችልበትን ከፍተኛ ዕድል ከፍቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ በቱሪዝም ጉዳዮች ላይ ከኤንቢሲ ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት፤ በቱሪዝም ዘርፍ የተከናወኑ የልማት ሥራዎች የሀገሪቱን የቱሪዝም መስህብ ስፍራዎች በማስፋፋትና የመዳረሻ ብዝሃነትን በማሳደግ ተጨባጭ ውጤቶች ተመዝግበዋል። በተለይም ለዘርፉ በተሰጠው ትኩረት የኢኮኖሚ መነቃቃትን በመፍጠር በሥራ ዕድል ፈጠራም ጭምር ከአምስቱ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ማሻሻዮች መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም የጎብኚዎች ፍሰትን በመጨመርና የቆይታ ጊዜ በማራዘም የቱሪዝም ብዝኅ እመርታዊ ውጤቶች በየአካባቢው ኢኮኖሚን በማነቃቃት የገጠርና የከተማ ልማትን ለማስተሳሰር አዲስ ዕድል ፈጥረዋል ብለዋል። የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የመደመር መንግሥት የቱሪዝም መዳረሻ ልማትና የቅርስ ዕድሳት ውጤታማ ሥራ የዘርፉን ዳግም ውልደት ያበሰሩ ለውጦችን አምጥቷል ብለዋል። ይህም የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎችን የቆይታ ጊዜ በማራዘም ዘመናዊና የተሰናሰለ የከተማና ገጠር የመስህብ መዳረሻና እንቅስቃሴ እንዲፈጠር ማስቻሉን ገልጸዋል። የቱሪዝም አስጎብኚ ድርጅቶች እንደሚሉትም፤ የኢትዮጵያ መጠነ ሰፊ የመዳረሻ ልማትና የቅርስ ጥበቃ ውጤታማ ሥራ ለቱሪስቶች መዳረሻና ጉብኝት ምቹ ምኅዳርን በመፍጠር የሀገርን ገጽታ የገለጡ ናቸው። የታላቁ የኢትዮጵያ አስጎብኚ ድርጅቶች ማኅበር ምክትል ፕሬዝዳንት እንቁ ሙሉጌታ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም መሠረተ ልማት መስፋፋት የቱሪዝም ፍሰቱን በማሳደግ ተጠቃሚነትን እያሳደገ ነው። የኤደን ላንድ ቱር ኤንድ ትራቭል ባለቤት እንዳልካቸው የምሩ፤ ለቱሪዝም ልማት የተሰጠው ትኩረት አማራጭ የመዳረሻ ስፍራዎች በማስፋፋት ለመስህብ መዳረሻ ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል። የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኝዎች እንደሚሉትም፤ በኢትዮጵያ ታሪካዊ፣ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊና ተፈጥሯዊ መስህቦችን መጎብኘት የሚያስችሉ ውጤታማ የልማት ሥራዎች ተከናውነዋል። ከዓለም አቀፍ ጎብኝዎች መካከል ጀርመናዊው ሉካስ ኩፕፈርናጌል፤ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባና ሌሎች አካባቢዎች የገነባቻቸው አስደማሚ የቱሪዝም መዳረሻዎች ሀገሪቱን አፍሪካዊት ግንባር ቀደም የቱሪስት ማዕከል የሚያደርጉ ናቸው ብለዋል። ሌላኛዋ አስተያየት ሰጪ የሀገር ውስጥ ጎብኚ ምሕረት አሰፋ በበኩላቸው፤ የለሙት የቱሪዝም መዳረሻዎች የሀገርን ገጽታ የቀየሩ፣ ውብ፣ ጽዱና ዓለም አቀፍ የመስህብ ተወዳዳሪነትን የሚያጎለብቱ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያ በታሪክ፣ በሃይማኖት፣ በባህልና በተፈጥሮ የታደለችውን ሀብት ወደ ኢኮኖሚያዊ አቅም የመቀየር ሥራ በስፋት እያከናወነች ይገኛል። የመደመር መንግሥት ቱሪዝምን የብዝኅ የኢኮኖሚ አዕማድ አካል በማድረግ የገነባቸው ማራኪ የመዳረሻ ስፍራዎች የዘርፉን ማንሰራራት በማጽናት ለኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው። ቀጣዩ የዘርፉ ጉዞም የኢትዮጵያን ቅርስና ተፈጥሯዊ ጸጋ በመጠበቅ የመዳረሻ ብዝኅነትን በማስፋፋትና የአገልግሎት ጥራትን በማሳደግ ቱሪዝምን ከተስፋ ወደ ተጨባጭ የኢኮኖሚ ውጤት የሚያሻግር ይሆናል።
ትንታኔዎች
የተማሪዎች ምገባ አያሌ ትሩፋቶች
Sep 17, 2026 181
በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ466 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ህጻናት በትምህርት ቤት የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆናቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራሞች የምግብ አማራጭ ብቻ ሳይሆኑ በትምህርት፣ በጤና እና በኢኮኖሚያዊ መረጋጋት ላይ ያላቸው አዎንታዊ ተጽእኖ እጅግ የገዘፈ ነው። መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የመማር ምጣኔ በመጨመር በተቃራኒው መጠነ ማቋረጥን በእጅጉ በመቀነስ ረገድ ጉልህ ፋይዳ አለው። ፕሮግራም በተለይም በአደጋ ተጋላጭና ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ወደ ትምህርት ገበታ የሚመጡ ልጆችን ቁጥር እንዲጨምር ትልቅ አስተዋጽኦ አድርጓል። ተማሪዎች በቀን ውስጥ የሚያገኙት የተመጣጠነ ምግብ በክፍል ውስጥ ያላቸውን የንቃት፣ የማስታወስ እና የትምህርት መቀበል አቅም በማሳደግ የትምህርት ውጤታቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሻሽሏል። የኢትዮጵያ የህብረተስብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) እና የዓለም የምግብ ድርጅት መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ ምገባው ህጻናት ከስድስቱ የምግብ ምድቦች የተውጣጡ አልሚ ምግቦችን እንዲያገኙ በማድረግ የተመጣጠነ ምግብ እጥረትንና የጤና አደጋን ይቀንሳል። የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦቱ የህጻናትን አጠቃላይ አካላዊ እድገት፣ የበሽታ መከላከል አቅም (Immunity) እና የአዕምሮ ጤና በመጠበቅ ጤናማ ትውልድ እንዲፈጠር የሚያስችል ነው። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እ.አ.አ በ2030 ሁሉም ህጻናት የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ አቅዶ እየሰራ ይገኛል። በአፍሪካ ደረጃ ከ100 ሚሊዮን በላይ ህጻናት የተለያዩ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብሮች ተጠቃሚ እንደሆኑ መረጃዎች ያሳያሉ። በኢትዮጵያም የትምህርት ቤቶች ምገባ መርሃ ግብር በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናትን ተጠቃሚ እያደረገ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የተማሪዎች ምገባ መርሃ ግብር ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ አገልግሎቱን እያገኙ መሆኑን ገልጸው፤ ሀገሪቱ የምትመግበው ህጻናት ቁጥር ከአንዳንድ ሀገራት የህዝብ ቁጥር ጋር የሚስተካከል መሆኑን መግለጻቸው ይታወሳል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ታዳጊ ህፃናት ትምህርት ቤት መሄድ ሲገባቸው በዳቦ ምክንያት እንዳይስተጓጎሉ ማድረግ ሊተኮርበት የሚገባ ዋነኛ የሀገር ግንባታ ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደረጃ የምገባ ኤጀንሲ በማቋቋም ተማሪዎችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የማድረግ ዘላቂ ተግባር በስኬት በመከናወን ላይ ይገኛል። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በመዲናዋ በሚገኙ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከቅድመ-አንደኛ እስከ መካከለኛ ደረጃ ለሚማሩ አንድ ሚሊየን የሚጠጉ ተማሪዎች በቀን ሁለት ጊዜ (ቁርስ እና ምሳ) በነፃ ይመገባሉ። ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሞክሮ በመነሳት ይህ ስራ በፈረንሳይ ፓሪስ እና በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተከናወኑ ዓለም አቀፍ መድረኮች ላይ ተወዳድረው አሸናፊ በመሆን የሜላን ፓክት ሽልማት (Milan Pact Award) ተቀዳጅቷል። እ.አ.አ በ2022 በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተካሄደው 8ኛው የዓለም አቀፍ የከተሞች የምግብ ፖሊሲ ስምምነት ጉባኤ ላይ የተበረከተው ይህ ታሪካዊ የሜላን ፓክት ሽልማት፣ አዲስ አበባ መርሃ ግብሩን በዘላቂነትና በተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ዘርፍ እጅግ ውጤታማ በሆነ መንገድ በመምራቷ የተሰጠ ነው። በተጨማሪም እ.አ.አ በ2021 በጣሊያን ሮም በተካሄደው የዓለም ሥነ ምግብ ኮንፈረንስ እና በሚላን የምገባ ፎረም ላይ መዲናዋ የምገባ ፎርም ምርጥ ተሞክሮ በሚል እውቅና አግኝታለች። እነዚህ ዓለም አቀፍ ሽልማቶች የተሰጡት መርሃ ግብሩ የተማሪዎችን የምገባ ችግር ከመቅረፍ ባለፈ፣ ከተማዋ የምግብ ስርዓትን በዘላቂነት በመምራትና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት በማደራጀት ማህበራዊ ፍትህና የኢኮኖሚ ነፃነት እውን እንዲሆን በማድረጓ ነው። የአዲስ አበባ አርአያነት ያለው ተግባር አሁን ላይ ወደ ክልሎች እና ከተሞች በስፋት እየተዳረሰ ይገኛል፤ እንደ ኬንያ ያሉ የአፍሪካ ሀገራት የልዑካን ቡድኖችም መዲናዋን በመጎብኘት ልምድ እየቀሰሙ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት (EPHI) የተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን የተመለከተ አዲስ የስነ ምግብ መጽሐፍ አዘጋጅቶ ተግባራዊ አድርጓል። ከንቲባ አዳነች አቤቤ መርሃ ግብሩ ተማሪዎች በኢኮኖሚ አቅም ማነስ ምክንያት ይሰማቸው የነበረውን የስነ-ልቦና ጫናና የድፍረት ማጣት ሙሉ በሙሉ በመቅረፍ ማህበራዊ ፍትህ ማረጋገጡን በአንድ ወቅት ገልጸዋል። ምግብ በማብሰልና በማቅረብ ሂደት ላይ ከ25 ሺህ በላይ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው እናቶች በህብረት ስራ ማህበራት ተደራጅተው ቋሚ የገቢ ምንጭ እንዲያገኙ በማድረግ የሴቶችን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አቅም ገንብቷል። የትምህርት ሚኒስቴር መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በሀገር አቀፍ የተማሪዎች የምገባ መርሃ ግብሩ አብዛኛው በጀት በሀገር ውስጥ አቅም እና በመንግስት የሚሸፈን ነው። መርሃ ግብሩ ከተጀመረ ወዲህ በተለይም ድርቅና የአየር ንብረት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የተማሪዎች ምዝገባ በ10 በመቶ እንዲጨምር እና የትምህርት ማቋረጥ ምጣኔ በእጅጉ እንዲቀንስ አድርጓል። ትምህርት ቤቶች የወጪ ጫናቸውን እንዲቀንሱ በትምህርት ቤቶች ግቢ ውስጥ የጓሮ አትክልት ልማት፣ የዶሮ እና የወተት ከብቶች እርባታ እንዲጀመር ተደርጓል። ኢትዮጵያ ይሄን መርሃ ግብር የምግብ አቅርቦትን ተደራሽ ማድረግ ብቻ ሳይሆን የሀገርን የረጅም ጊዜ የሰው ሀብት (Human Capital) መገንቢያ ስትራቴጂ አድርጋ እየሰራች ይገኛል። የምገባ ፕሮግራሙ ከትምህርት ተደራሽነትና ውጤታማነት ባሻገር ህጻናት በጤናማ አካልና አእምሮ እንዲያድጉ በማድረግ ለሀገር አቀፍ የጤና ጥበቃ ስራዎች ትልቅ አበርክቶ እያበረከተ ይገኛል። በምገባ ማዕከላት ዙሪያ የሚደረጉ የንፅህና አጠባበቅና የደህንነት ትምህርቶች ተማሪዎች በለጋ እድሜያቸው ጤናማ የኑሮ ዘይቤዎችን እንዲላመዱና የግል ንፅህናቸውን እንዲጠብቁ አቅም እየፈጠረ ይገኛል። በአጠቃላይ የምገባ ፕሮግራም በትምህርት ላይ እያሳረፈ ካለው በጎ አሻራ ባለፈ ምርታማ ትውልድ ለመፍጠር እና ለአንድ ሀገር እድገት እና ልማት ያለው አስተዋጽኦ ጉልህ ነው። በዚህ ረገድም ኢትዮጵያ በስኬት ጎዳና እና ለሌሎች አርአያ በሚሆን ተምሳሌታዊ ተግባር በግንባር ቀደምትነት የምትነሳ ሀገር ናት።
የቱሪዝም ትንሳኤን ያበሰረው የመደመር እሳቤ
Sep 16, 2026 446
ኢትዮጵያ አስደማሚ የተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ የቱሪዝም ሀብቶች ባለቤት ናት ። የጎብኚዎችን ቀልብ የሚስቡ ደጋግመው ቢያዩዋቸው ፣ ቢታደሙባቸው የማይሰለቹ ተጠንተውም የማያልቁ ፀጋዎች ቢኖሯትም ለዘመናት በወጉ ሳትገልጣቸው የሚጠበቀውን ያክልም ሳይጎበኙ ሳይተዋወቁም ቆይተዋል። ይህን ባለማድረጓ ደግሞ ከዕልፍ የቱሪዝም ጸዋጋዎቿ ሳትቋደስ ዘመናትን ተሻግራለች። “በታሪክም ሆነ በተፈጥሮ ጸጋዎች ከኛ ጋር ሊወዳደሩ የማይችሉ ብዙ ሀገራት ከኢንዱስትሪው ብዙ አትርፈዋል። እኛ ግን እንቁዎቻችንን ደብቀን ታሪካችንን አቧራ አልብሰን ለዘመናት ቆይተናል።” የመደመር መንግሥት መጽሐፍ ገጽ 259 ዛሬ ግን ይህ ታሪክ እየተቀየረ ነው። ከመደመር መንግሥት አምስት ወሳኝ የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ በሆነው ቱሪዝም ቅርሶችንና ወሳኝ ፀጋዎችን ከቁስ ወደ ቁርስ እየለወጠ፣ ኢትዮጵያን እየገለጠ እንዲመጣ እየተደረገ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በአራት ኪሎ ቤተመንግስት “ሀ” ተብሎ የተጀመረው አዳዲስ የቱሪስት መዳረሻ ልማት በገበታ ፕሮጀክቶች አማካኝነት ወደ ሁሉም የሃገራችን ክፍሎች ተዳርሷል። በኢትዮጵያ ትኩረት ተነፍጓቸው የነበሩት የሀገራችን የቱሪዝም ሀብቶች በመደመር መንግሥት ቅድሚያ ተሰጥቷቸው ትንሳኤያቸው ተበስሯል። ለዘመናት አቧራ ለብሰው የኖሩ ዕንቁ የቱሪዝም ሀብቶች አቧሯቸው እየተራገፈ ነው። ከዳሎል እስከ ስሜን ተራሮች ማራኪ ተፈጥሯዊ መስህቦች ይበልጥ ለዓለም እየተዋወቁ ነው። አዳዲስ ተፈጥሯዊ ፀጋዎችም በቱሪዝም ልማት ኢኒሼቲቮች የመገለጥና የመታወቅ ዕድል አግኝተዋል። የመደመር እሳቤ የምናብ ከፍታና የመፈጸም ልክ አንዱ ጉልህ ማሳያ የቱሪዝሙ ዘርፍ ፕሮጀክቶች ናቸው። ከነዚህ ኢኒሼቲቮችም መካከል አንዱ ከቤተ መንግስት እደሳት ጀምሮ አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ያደረጋት የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት ነው። የገበታ ለሸገር ፕሮጀክት የቱሪዝም አብዮትን በመቀስቀስ የአንድነት ፓርክን፣ እንጦጦና ወዳጅነት ፓርክና ሌሎች ተያያዥ ፕሮጀክቶችን ዕውን አድርጓል። ዛሬ ላይ አዲስ አበባን አዲስ መልክ አጎናጽፎ፤ የነተቡ ሰፈሮች ወደ ውብ መልኮች ተቀይረው የሚሊዮኖች ጎብኚዎች መዳረሻ ሆነዋል። ከገበታ ለሸገር በመቀጠል የኢትዮጵያን አዳዲስ መልኮች የገለጠው ኢኒሸቲቭ ደግሞ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ነው። ገበታ ለሀገር ከኦሮሚያ ክልል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ወንጪን፣ ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳውሮና ኮንታን የሸፈነው ኮይሻን፣ከአማራ ክልል የጣናን ምዕራባዊ ዳርቻ የተንተራሰችውን ጎርጎራን ውብ አድርጓል። እነዚህ ፕሮጀክቶች የኢትዮጵያን አይነተ ብዙ ታሪክ፣ ተፈጥሮንና ባህል በመግለጥ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሞገስና ድምቀት ሆነዋል። ከገበታ ለሀገር ቀጥሎ ገቢራዊ የተደረገው የገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት አድማሱ በሶማሌ ክልል ሸበሌ ሪዞርትን፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የደንቢ ኢኮ ሎጅን፣ በአማራ ክልል የሐይቅ ሎጎ ሪዞርትን፣ በአፋር ክልል የኒዒን ሌ ፓልም ሎጅ እንዲሁም የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርትን እውን አድርጓል። ከገበታ ለሸገር እስከ ገበታ ለትውልድ ፕሮጀክቶች ባሻገር የመደመር መንግስት ታሪካዊ ቅርሶችን የመጠበቅ፣ እሴት ጨምሮ የመግለጥ አኩሪ ስራዎችንም አከናውኗል። ለዚህ ደግሞ ከብሔራዊ ቤተ መንግስት ጀምሮ ጥንታዊ አብያተ መንግስታት፣ ታሪካዊ፣ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች ተጠግነዋል። የባለፉት ጥቂት ዓመታት የቱሪዝም ዘርፍ ለውጦች የኢትዮጵያን ገጽታ ያስተዋወቁ፤ በየአካባቢው ተስፋና ልማትን የፈነጠቁ፣ ዘመን ተሻጋሪ ስራዎች ናቸው። እነዚህ ፕሮጀክቶች በኢትዮጵያ የዕድገትና የብልጽግና ታሪክ ውስጥ በደማቁ የሚጻፉ አንቀጾች ሆነው ለትውልድ የተኖሩ ዓሻራዎች ናቸው።
የኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ የከፍታ ጉዞ ማሳያ - ብሪክስ
Sep 13, 2026 894
''የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው" በማለት ነው የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ18ኛው የብሪክስ ጉባዔ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር። 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የጥምረቱ አባል ሀገራት መሪዎች በተገኙበት “ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርንና ዘላቂነትን መገንባት” በሚል መሪ ሀሳብ በህንድ ኒውዴልሂ እየተካሄደ ነው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እና የልዑክ ቡድናቸው በዚሁ ዓለም አቀፍ ተጽዕኖ በሚፈጥረው ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ ይገኛሉ። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው። ብሪክስ ለአፍሪካ ቀጣና እና በተለይም ለኢትዮጵያ በርካታ የኢኮኖሚ፣ የፖለቲካ እና የጂኦ-ፖለቲካዊ ጥቅሞችን የሚያስገኝ አዲስ የዓለም ስርዓት እየተፈጠረበት የሚገኝ ጥምረት ነው። የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በዚህም እንደ ቻይና፣ ህንድ እና ሩሲያ ካሉ ታላላቅ ሀገራት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጣውን የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት በተለይም በማኑፋክቸሪንግ፣ በግብርና እና በኢነርጂ ዘርፍ በማሳደግ በኩል አይነተኛ አማራጭ የኢንቨስትመንት መንገድ ነው። ጥምረቱ ለኢትዮጵያ ከሚያስገኘው ትሩፋት አንጻር ሲታይ የውጭ ምንዛሬ እጥረትን በመቅረፍ፤ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር በሚደረጉ የንግድ ልውውጦች የሀገር ውስጥ ገንዘብን የመጠቀም ዕድልን ስለሚፈጥር፣ የውጭ ምንዛሬ ግኝት እጥረትን ከመቀነስ አኳያም እንዲሁ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው። ኢትዮጵያ በሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዕቅዷ ኢኮኖሚዋን በመሠረታዊነት ለሚያሳድጉ መሠረተ ልማት ግንባታ እና ማስፋፊያ እንዲሁም ለቴክኖሎጂ ሽግግር ልዩ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች ትገኛለች። ከዚህ አኳያ ብሪክስ የመንገድ፣ የባቡር፣ የኃይል ማመንጫዎችና ዲጂታል ቴክኖሎጂ እና መሰል የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የሚሆን የፋይናንስ ድጋፍ በማመቻቸት በኩል ኢትዮጵያ ለያዘችው ግብ ስኬት ከፍተኛ ጠቀሜታ የሚያስገኝ ጥምረት ነው። ባለፉት ዓመታት ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲው ዘርፍ ላሳካቻቸው ውጤቶች የዓለም አቀፍ ግንኙነቷን የቃኘችበት አዲስ አካሄድ ተጠቃሽ ነው። ከእነዚህ ስኬቶች መካከል ደግሞ በብሪክስ ጥምረት ውስጥ አባል የሆነችበት መንገድ አንዱ ሲሆን፤ ይህ የብሪክስ ጥምረት ለኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ተፅዕኖ ፈጣሪነት የራሱን ሚና በመጫወት ኢትዮጵያ በቀጣናው እና በአህጉሪቷ ያላትን መሪነትና ዲፕሎማሲያዊ የበላይነት በማጠናከር በዓለም አቀፍ መድረክ ያላትን ድምፅ እንድታጎላ እና ተጽዕኖ ፈጣሪነቷ እንዲያድግ እያስቻለ መሆኑም በተጨባጭ ታይቷል። የብሪክስ ጥምረት በአፍሪካ አለፍ ሲልም በጥምረቱ አባል ሀገራት መካከል ተመጣጣኝ ልማት እንዲኖር እና ሀገራቱ የኢኮኖሚ እና የፖለቲካ ትብብራቸውን እንዲያጠናክሩ አስቻይ ምህዳር እየፈጠረም ይገኛል። በተለይ አፍሪካ ያላትን የተፈጥሮ ሀብት በማልማት የኢኮኖሚ ዕድገቷን እንድታፋጥን አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ መሆን የሚያስችለውን አደረጃጀት እና አሰራር እየዘረጋም ይገኛል። ይህ የጥምረቱ አዳዲስ አደረጃጀት እና አሰራር አዲሱ የልማት ባንክ እንዲወለድ አስችሏል። በዚህ ባንክ አማካኝነት የአፍሪካ ሀገራት ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት እና ከዓለም ባንክ ጥብቅ መስፈርቶች ነፃ በሆነ መንገድ ለተለያዩ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አማራጭ የፋይናንስ ምንጭ ወይም ብድር እንዲያገኙ ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል። በጥምረቱ አማካኝነት የተፈጠረው አዲሱ የልማት ባንክ የአፍሪካ ሀገራት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘብ እና ከአሜሪካ ዶላር ተጽእኖ ውጪ ከታላላቅ የብሪክስ ሀገራት ጋር የንግድ ልውውጥ እንዲያከናውኑ በር እየከፈተ ይገኛል። በተጨማሪም አፍሪካ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ የውሳኔ መድረኮች ላይ ያላትን ተፅዕኖ ፈጣሪነት በማሳደግ፣ ፍትሐዊ የሆነ የዓለም አቀፍ ስርዓት እንዲፈጠር እያስቻለ መሆኑም የአደባባይ ምስጢር ከሆነ ሰነባብቷል። ይህ የብሪክስ ጥምረት መመስረት፣ መስፋፋትና መጠናከር በዓለም የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ስርዓት ላይ በርካታ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጦችንና አንድምታዎችን እያስከተለ ይገኛል። የብሪክስ ጥምረት ተመስርቶ እየፈጠረ ያለው ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ተጽዕኖ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ የምዕራባውያን ሀገራት በዓለም ፖለቲካ ላይ የነበራቸውን የበላይነት በመገዳደር፣ ሥልጣንና ውሳኔ ሰጪነት ለተለያዩ የአህጉራት ኃይሎች እንዲከፋፈል፣ በዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያ ጥያቄዎች ጎልተው እንዲሰሙ የማድረግ አቅም እየፈጠረ ነው። በተጨማሪም የብሪክስ ጥምረት አባል ሀገራት በንግድ ልውውጣቸው ወቅት በራሳቸው ሀገራዊ ገንዘቦች የመጠቀም ዝንባሌያቸው በመጨመሩ፣ የአሜሪካ ዶላር በዓለም ንግድና መጠባበቂያ ክምችት ላይ ያለውን ፍጹም የበላይነት በማዳከም፤ አዲሱ ልማት ባንክ የብሪክስ የድንገተኛ የገንዘብ ድጋፍ ማዕቀፍ የምዕራባውያኑን ጥብቅ የፖለቲካ መስፈርቶች ሳይከተሉ ለታዳጊ ሀገራት ፕሮጀክቶች ፋይናንስ እንዲያቀርቡ ብሎም የብሪክስ አባል ሀገራት የዓለምን ከፍተኛ የነዳጅ፣ የጋዝ፣ የብረታ ብረት እና የግብርና ምርቶች አቅርቦት የሚቆጣጠሩ በመሆናቸው፣ በዓለም አቀፍ የንግድ መስመሮች እና የዋጋ ውሳኔዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንዲያሳድሩ የውሳኔ ሰጪነት አቅማቸውን እያሳደገ መጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያም ሆነች አፍሪካ ያላቸውን የመልማት አቅም ለመጠቀም አማራጭ የልማት ፋይናንስ እጅግ አስፈላጊ መሆኑን አፅንኦት ሰጥተዋል። ለዚህ ደግሞ የብሪክስ ጥምረት ይዞት የመጣውን ዕድል በውል አንስተዋል። ለዚህም ነው በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው ሲሉ ያመላከቱት። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ መሆኗን ያረጋገጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ከጥምረቱ የሚጠበቅ መሆኑንም ነው ያነሱት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የብሪክስ ጉባዔ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው። የጥምረቱ አቅም ከተናጠል አካሄድ ይልቅ ትብብርና ለጋራ እሴት መጎልበት ያለውን ዕድል ያመላክታል። ኢትዮጵያ ለኮቪድ እና ኤልኒኖን ጨምሮ ለዓለም የኢኮኖሚ እና የንግድ ስርዓት መመሰቃቀል እጅ ሳትሰጥ፤ ይልቁንም መሰል ቀጣናዊ፣ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ችግሮችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ ለችግሮች የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት ባከናወነቻቸው ተግባራት ጽናትን ገንዘቧ እያደረገች ትገኛለች። ለዚህም ነው "አካታች ዓለም አቀፍ አስተዳደር እና ባለ ብዙ ወገን ትብብርን ማጠናከር” በሚል አጀንዳ ላይ ትኩረት ባደረገው የጉባኤው የመጀመሪያ ቀን ውሎ ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ችግሮች ከመፈጠራቸው አስቀድሞ ጽናትን ማጠናከር እና የአስተዳደር ስርዓት አካል የማድረግን መሠረታዊ ጠቀሜታ የገለጹት። ይህ ጽኑ ስርዓት ግንባታ ኢትዮጵያ በፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ እንድትበረታ ማስቻሉን ለማሳያነት አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ከውጭ ከሚገባ የስንዴ ጥገኝነት ተላቃ በምግብ ራሷን መቻሏን አንስተዋል። በጤና ቅድመ መከላከል ፖሊሲ አካል ሆኖ የሕክምና ቁሳቁሶችና መድኃኒቶች ማምረትን፣ የዲጂታል ስርዓት ሽግግርንና ደኅንነቱ የተጠበቀ አጠቃቀም የማስፈን አበይት ተግባራት መከናወናቸውን ነው አጽንኦት የሰጡት። በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ የጀመረችው የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ አፍሪካ የነገውን የቴክኖሎጂ ዘመን በባለቤትነት እንድትመራ ትልቅ ሚና የሚጫወት መሆኑን የገለጹት። በእነዚህና መሰል የልማት ትብብሮች ከጥምረቱ አባል ሀገራት ጋር አብሮ ለመስራት ዝግጁ መሆኗንም ነው ያረጋገጡት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ጥምረቱ የተቋቋመበትን ዓላማ እና መርህ በተጨባጭ እውን እያደረገች እንደምትገኝ በመጠቆም፤ ኢትዮጵያ በሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የዲጂታል ስርዓት ማሻሻያ ባከናወነቻቸው አመርቂ ትግበራዎች፣ በታዳሽ ኃይል መስፋፋት እና የኢንዱስትሪ መሠረት ልማቶቿ፣ በግብርና ስርዓት ማሻሻያ እየተመዘገቡ ያሉ የምግብ ሉዓላዊነት መረጋገጥ ብሎም ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ግዙፍ የአየር መንገድ ግንባታ የአኅጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ንግድ ትሥሥርን ለማስፋፋት በምታደርገው ጥረት በጥምረቱ ለሚነሱ ተያያዥ የውይይት አጀንዳዎች መሪ ተዋናይ መሆን እንደሚያስችላትም አንስተዋል። ይህ የጠቅላይ ሚኒስትሩ እና የልዑክ ቡድናቸው የብሪክስ ጉባኤ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለአፍሪካ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው መሆኑ እሙን ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጉባኤው እያደረጉት ካለው ተሳትፎ ጎን ለጎን ቀጣናዊና ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ከተለያዩ የብሪክስ ስብስብ አባል ሀገራት መሪዎች ጋር ውጤታማ የሁለትዮሽ ውይይቶችን አድርገዋል። በዚህም ከህንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ፣ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ፣ ከቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግ፣ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያ፣ ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያ እንዲሁም ከሌሎች መሪዎች ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን በሚያጠናክሩ አጀንዳዎች ላይ ውጤታማ ውይይቶችን አካሂደዋል። የውይይቶቹ ማጠንጠኛም የጥምረቱን አባል ሀገራት የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያበረታቱ እንደ ኢንቨስትመንት፣ ቀጣናዊ ጉዳዮች፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታና ክህሎት፣ ቱሪዝም፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ሊኖሩ ስለሚችሉ ትብብሮች ላይ ያተኮሩ እንደነበሩ ተመላክቷል።
ከታሪክ ዘካሪነት ወደ ታሪክ ሰሪነት፤ የአዲሱ ትውልድ የሜጋ ፕሮጀክቶች ግንባታ አብዮት
Sep 13, 2026 589
የአንድ ሕዝብ የነፃነት ድል የሚያበቃው በድል ማግስት በሚተረክ የታሪክ መዛግብት ብቻ አይደለም። በሌላ የታሪክ ገጽ ላይ አዲስ ድል መጎናፀፍ ሲቻል የቀደመውን ድል ትርጉምና ምልዑነት የበለጠ ያጎላዋል። ዓድዋ የክንደ ብርቱ ቅድመ አያቶች የሀገርን ሉዓላዊ ነፃነት የማስጠበቅ አኩሪ የድል ምልክት ነው። የድል ምልክትነቱም ለጭቁኑ የዓለም ጥቁር ሕዝቦች ፅናትና የነፃነት ጎህን በመቅደድ፣ ለአሁኑ ትውልድ ደግሞ የይቻላል መንፈስን አጎናፅፏል። ጀግንነትንና አልበገር ባይነትን ከቅድመ አያቶቹ የወረሰው የአሁኑ ትውልድም በሌላ የታሪክ ገጽ በጉባ ተራሮች ግርጌ በዓባይ የዘመናት ዥረት ላይ ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመገንባት የራሱን ታሪክ ጽፏል። የሕዳሴ ምረቃ የተበሰረባት ጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ዕለትም የኢትዮጵያን አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌትነት የሚበይኑ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች የተበሰሩባት ድርብ ታሪካዊት ዕለት ሆና ተመዝግባለች። በሕዳሴ የይቻላል መንፈስን የተጎናፀፈችው ኢትዮጵያም በኃይል፣ በግብርና፣ በአቪዬሽን፣ በጋዝ፣ በማዕድንና በሌሎች ዘርፎች ወደ ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ ተሸጋግራለች። የጉባ ብስራቶችም የአንድ ፕሮጀክት ወይም ዘርፍ ስኬት ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያ ሀብቷን በራሷ አቅም በማልማት የብልፅግና ጉዞዋን ለማስፋት የምታደርገው የልማት ጉዞ ሕያው ምልክት ናቸው። የመደመር መንግሥት አፍሪካዊት የብልፅግና ተምሳሌት ኢትዮጵያን በራሷ ልጆች የመቅረጽ ራዕይም ከዓድዋ ነፃነትን፣ ከሕዳሴ የልማት ድልን፣ ከጉባ ተራሮች ግርጌ ብስራትን በመሰነቅ ታሪክን ከመዘከር ወደ አዲስ ታሪክ መጻፍ ተሸጋግሯል። ይህም ሕዳሴ ግድብ በአንድ የታሪክ ምዕራፍ ብቻ ተከትቦ የሚቀር የትውልድ ዓርማ ሳይሆን ለሚቀጥሉት ትውልዶች የመፈጸም አቅምና የይቻላል መንፈስ የሚያስተላልፍ ቅርስ መሆኑን ያሳያል። የአንድ ግዙፍ የትውልዱ ብሔራዊ ፕሮጀክት ምረቃም የሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶችን ውልደት በማብሰር ኢትዮጵያ በአዲስ የስኬት ምዕራፍ እየተስፈነጠረች መሆኗን ያመላክታል። የጉባ ብስራት የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ እንዲሁም የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ አብነቶች ናቸው። ኃይልን ከግብርና፣ ኢንዱስትሪን ከአቬየሽን ያሰናሰሉት የጉባ ብስራት ግዙፍ ፕሮጀክቶችም በዚህ የልማት ጉዞ ቀጣዩን ምዕራፍ መጻፍ ጀምረዋል። ይህም ኢትዮጵያ ሜጋ ፕሮጀክቶችን የምታልም ሀገር ብቻ ሳትሆን የመፈጸም አቅም ያላት መሆኗን የሚያሳይ አዲስ የልማት ምዕራፍ ነው። በመደመር መንግሥት ውልደት ማግስት ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና በፖለቲካዊ ዘርፎች ያስመዘገበቻቸው እመርታዎች ሀገርን ከመዋቅራዊ ስብራት ወደ ማንሰራራት ያሸጋገሩ ድሎች ናቸው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በጳጉሜ 4 ቀን 2017 ዓ.ም ታሪካዊቷ ዕለት እንዳሉት፤ ሕዳሴ ያስገኘው ወኔና ተስፋ የነገዋን ኢትዮጵያ ብሩህ አድማስ የሚያበስሩ ፕሮጀክቶችን ለማስፈጸም መንገድ ከፍቷል። በዚህም በጥቂት ዓመታት ውስጥ ለሰላማዊ ዓላማ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት፣ የጋዝ፣ የነዳጅ ማጣሪያና የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካዎች፣ እንዲሁም 1 ነጥብ 5 ሚሊዮን የመኖሪያ ቤቶች እንደሚገነቡ ማብሰራቸው ይታወሳል። እነዚህ ግዙፍ የልማት ዕቅዶች በቁጥር የሚገለጹ ፕሮጀክቶች ብቻ አይደሉም። ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን ከራሷ የመፈጸም አቅም ጋር በማሰናሰል የነገን ሀገራዊ ተስፋ የሚያመላክቱ የልማት አቅጣጫዎች ናቸው። የመደመር መንግሥት ግዙፍ ሀገራዊ የልማት ትልሞችም የኢትዮጵያን ሁሉን አቀፍ የማንሰራራት ምዕራፍ በማብሰር፣ የሀገርን ብልፅግና የሚቀርጹ እመርታዎች የተገኙባቸው ናቸው። ከእነዚህ መካከል የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ የፕሮጀክት ግንባታ ብስራት አንዱ ነው። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅም ኢትዮጵያ በአቪዬሽን ዘርፍ ያላትን አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በማጎልበት፣ በኢኮኖሚ፣ በቱሪዝምና በዲፕሎማሲ ዘርፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚከፍት ቁልፍ መሠረተ ልማት ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፕሮጀክቱን ግንባታ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት፣ የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲጠናቀቅ የኢትዮጵያን ዓለም አቀፍ የአቪዬሽን ዘርፍ ተወዳዳሪነት የሚያሳድግ ነው። በዚህ መነፅር ሲታይም የቢሾፍቱ ዓለም አቀፍ የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት የአቪዬሽን ፕሮጀክት ብቻ አይሆንም። ኢትዮጵያ በአፍሪካ ያላትን የአቪዬሽን መሪነት በማላቅ፣ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትን የሚያጎለብት ስትራቴጂካዊ ኢንቨስትመንት ይሆናል። የቢሾፍቱ አየር ማረፊያ ግዝፈትና ዝማኔ ኢትዮጵያን የአቪዬሽን፣ የቱሪዝምና የዲፕሎማሲ ማዕከል የማድረግ ከፍተኛ አቅም አለው ያሉት ደግሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው ናቸው። ይህም ሕዳሴ ግድብ ያስተዋወቀው የታላቅ ሀገር ግዙፍ ፕሮጀክትን የመፈጸም ባህል ከኃይል ዘርፍ ወደ አቪዬሽንና ሌሎች ስትራቴጂካዊ የልማት መስኮች እየተስፋፋ መሆኑን ያመላክታል። ሌላኛው የኢትዮጵያን የማንሰራራት አቅጣጫ የሚበይነው ግዙፍ ፕሮጀክትም የተፈጥሮ ጋዝና የአፈር ማዳበሪያን በሀገር ውስጥ የማምረት ትልም ነው። የኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብት ከመሬት ሥር ተደብቆ የሚቀር ሳይሆን፣ የምርት፣ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ልማት መሠረት የማድረግ አዲስ የዕድገት አቅጣጫ ሆኗል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክትን ባስጀመሩበት ወቅት፣ የኢትዮጵያ የጋዝ ምርት ፕሮጀክት የኃይል አቅርቦትን ከግብርና ምርታማነት ጋር ያሰናሰለ ነው ብለዋል። ይህም የኦጋዴን የተፈጥሮ ጋዝ የኃይል አቅርቦትን ከማሟላት ባሻገር፣ የኢትዮጵያን የምግብ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ በሚደረገው ጉዞ በስፍራው ለሚገነባው የአፈር ማዳበሪያ ፋብሪካ ግብዓትነት ያገለግላል። በዚህ አተያይም ጋዝን ማልማት የኃይል ፍላጎትን ከማሟላት ባሻገር፣ የግብርና ምርታማነትን፣ የኢንዱስትሪ ምርትንና የሀገር ውስጥ ግብዓት አቅርቦትን የሚያጠናክር የተሰናሰለ ስልታዊ የልማት አቅም ይፈጥራል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለብዝኅ ክፍለ ኢኮኖሚ ዕድገት የሰጠው ትኩረትም ኢትዮጵያን በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ ቱሪዝምና ዲጂታል ዘርፎች በስኬት ምሕዋር እንድትገባ አድርጓታል። ይህም የኢትዮጵያን ማዕድን ከጥሬ ዕቃ ላኪነት ወደ እሴት የታከለበትና ፈጠራ ያለበት የምርት ሰንሰለት የሚሸጋገርበትን ወሳኝ ዕድል ፈጥሯል። የማዕድን ሚኒስትር ኢንጂነር ሃብታሙ ተገኘ፣ የካሉብ ፋብሪካ የተፈጥሮ ጋዝ ማጣራትና ወደ ፈሳሽነት የመቀየር የማዕድን ልማት ለተሽከርካሪና ፋብሪካ አማራጭ የኃይል ምንጭ ማቅረብ የሚያስችል ነው ብለዋል። ይህ ተፈጥሮ ሀብትን በጥሬ ዕቃነት ከመሸጥ ይልቅ በማቀነባበርና በማልማት የበለጠ እሴት ለማስገኘት የተያዘውን አቅጣጫ ያመላክታል። የመደመር መንግሥት ሀገር በቀል የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያም የግሉን ዘርፍ በማሳተፍና ዓለም አቀፍ ባለሀብቶችን በመሳብ፣ አዳዲስ የልማትና የኢንቨስትመንት ዕድሎችን ከፍቷል። ለዚህም ነው የዳንጎቴ ግሩፕ ባለቤትና መሥራች አሊኮ ዳንጎቴ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሪፎርም በኢኮኖሚው ውስጥ ጤናማ ውድድርና ቀልጣፋ አሠራር እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል። ከሕዳሴ ግድብ እስከ አቪዬሽን፣ ከተፈጥሮ ጋዝ እስከ ማዳበሪያ ድረስ ገሃድ የገለጠው የኢትዮጵያ ማንሰራራትም ከማለም ወደ መፈጸም፣ ከመፈጸምም ወደ ዘላቂ የልማት አቅም ለመሸጋገር የሚደረገውን ጉዞ ያመላክታል። የዓድዋ ድል የኢትዮጵያውያንን አንድነትና የጋራ አቅም ለዓለም ታሪክ ያሳየ ድል እንደነበር ሁሉ፣ ሕዳሴ ግድብም ያንኑ የጋራ አቅም በዘመናዊ ልማት ላይ የገለጠ አዲስ ታሪካዊ ክስተት ሆኗል። የኢትዮጵያውያን አንድነት የዓድዋን ድል ካቀዳጀ፣ ያው በሕብር የተሸመነ አንድነትም ሕዳሴን እውን አድርጓል። ሕዳሴ የተስፋ ብርሃን ካበራ፣ ያ ተስፋም በሌሎች የልማት ሜጋ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ ሆኖ እየቀጠለ ነው። ይህ የይቻላል መንፈስ ከፕሮጀክት ወደ ፕሮጀክት የሚጓዝ ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያን ስለነገ ሀገራቸው ያላቸውን እምነት የሚያድስ የልማት ብስራት ነው። ሕዳሴ ግድብ የተጀመረውን የተስፋ ጉዞ አዲስ አቅጣጫ አስይዞታል። የሚቀጥለው ታላቅ ተግባር ደግሞ ይህን የመፈጸም አቅም ወደ ዘላቂ ምርታማነት፣ የሥራ ዕድል፣ የዜጎች ተጠቃሚነትና የተሻለ ኑሮ መቀየር ነው። እናም የሕዳሴ ግድብ ብስራት በግድቡ የውሃ ሙሌት ብቻ የሚያበቃ ሳይሆን፣ በኢትዮጵያውያን የጋራ ህልም፣ በሀገራዊ አንድነትና በመፈጸም አቅም የሚቀጥል የልማት ብስራትን ፈንጥቋል።
ልዩ ዘገባዎች
በታዳጊው የተሰራችው መኪና
Jun 17, 2026 13400
ለአዳዲስ ፈጠራ የማይታክተው ልጅዓለም ንጉሱ ትውልድና እድገቱ በአማራ ክልል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ሰቆጣ ወረዳ ፀመራ ቀበሌ ነው። ከሕጻንነቱ ጀምሮ ፈትቶ መግጠምና አፍርሶ መስራትን እየተለማመደ የመጣው ልጅዓለም፤ ከቤት እስከ ትምህርት ቤት ያልተቋረጠ ፈጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ከዚህ ቀደም ለሚማርበት ፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከወዳደቁ ቁሶች የተለያዩ ቅርፃ ቅርፆችን በመስራት የፈጠራ አሻራውን አኑሯል። በትምህርትና በፈጠራ ሥራው ገፍቶበት አሁን ላይ የ8ኛ ክፍል ተማሪ የሆነው ልጅዓለም እንጨት ገጣጥሞ መኪና በመስራት ያለውን የጥበብና ፈጠራ ክህሎት አሳይቷል። በታዳጊው የተሰራችውና በፔዳል የምትነዳው መኪና ሁለት ሰዎችን የማያዝ አቅም አላት። በቀጣይ ተጨማሪ ቁሶችን በማቅረብና በተለያየ መንገድ የሚያግዘው ካገኘ መኪናዋ በዲናሞ እንድትንቀሳቀስ ለማድረግ መዘጋጀቱን ተናግሯል። የተሽከርካሪውን አካል የገጣጠመው በአካባቢው አጠራር "እንቋ" የተሰኘ ዛፍ እንጨትን በመጠቀም ሲሆን የተሽከርካሪውን እግር ለማዘጋጀት ደግሞ የዋርካ ዛፍ ተጠቅሟል። በዚህም መሰረት የልጅዓለም መኪና የመብራትና የመሪ ስራዋ ተጠናቆ ሁለት ሰዎችን ጭና መንቀሳቀስ እንደምትችል በተግባር አሳይቷል። "በቀጣይ የሚያግዘኝና የሚደግፈኝ ካገኘሁ በዲናሞ የሚሰራ ተሽከርካሪ ለመስራት ዝግጁ ነኝ" ያለው ጥበበኛው ተማሪ ወደ ፊት ለሀገሬ ብዙ የመፍጠር ህልም አለኝ ብሏል። የፀመራ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ግርማ ጌቴ፤ ከዚህ በፊት ተማሪ ልጅዓለም በትምህርት ቤቱ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎች እንዳሉት አስታውሰው ትምህርቱንም ፈጠራውንም አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል። የፈጠራ ክህሎቱን፣ ተሰጥኦውንና ፍላጎቱን ከ5ኛ ክፍል ጀምሮ ተከታትያለሁ ያሉት መምህሩ የሳይንስ ትምህርቱንና የግል ክህሎቱን ደምሮ ለአዳዲስ ሥራዎች እየተጋ መሆኑን አንስተው፣ የመኪና ፈጠራውም ይህንኑ በተግባር ያሳየበት ነው ብለዋል። የግብዓት አቅርቦት ድጋፍ ከተደረገለት የተሻለና ውጤታማ ሥራ መስራት እንደሚችል ገልጸው ለሚፈጥሩ ወጣቶች በጥሩ ምሳሌነት የሚጠቀስ መሆኑን ተናግረዋል። በእንጨት የተገጣጠመችው መኪና በሁላችንም ድጋፍ የዲናሞ፣ የብረትና ሌሎች አስፈላጊ ቁሶች ከተሟሉላት በታዳጊው ጥበብ የተሻለች መኪና ሆና ልትሰራ ትችላለች ሲለም እምነታቸውን ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ስንት ዓይነት የአዕዋፍ ዝርያዎች አሉ?
Oct 13, 2025 22523
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2018 (ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአዕዋፍ ኑሮ ምቹ እና ተስማሚ ሁኔታዎች ካሉባቸው ሀገራት አንዷ ናት። በፈረንጆቹ 2024 እና 2025 የተደረጉ የጥናት ውጤቶች እንዳመላከቱት፤ በኢትዮጵያ ከ881 እስከ 926 የሚደርሱ የአዕዋፍ ዝርያዎች ይገኛሉ። ይህ አሃዝ ነዋሪ እና ፍልሰተኛ የአዕዋፍ ዝርያዎችን እንደሚያካትት በኢትዮጵያ ዱር እንስሣት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ለአዕዋፋት ኑሮ ምቹና አስፈላጊ ከሆኑ ሀገራት መካከል እንደምትመደብም ጠቅሰዋል። 639 ነዋሪዎችን እና 224 ወቅታዊ ፍልሰተኞችን ጨምሮ 926 የአዕዋፍ ዝርያዎች በኢትዮጵያ እንደሚገኙ ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ላይ የተደረገ ጥናት ውጤት አመላክቷል ነው ያሉት። ከእነዚህ መካከል በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኙት የአዕዋፍ ዝርያዎች ቁጥራቸው ከ18 እስከ 20 እንደሚደርስ ጠቁመዋል። አማካኝ የወፎች ዕድሜ እንደ ዝርያ፣ መጠን እና አካባቢ ስለሚለያይ ለሁሉም ወፎች አንድ አማካይ ዕድሜ አለመኖሩንም አንስተዋል። ትንሽ ዕድሜ የሚኖሩት የድንቢጥ ዝርያዎች መሆናቸውን ጠቅሰው አማካኝ ዕድሜያቸውም ሦስት ዓመት መሆኑን ተናግረዋል። እንደ አልባትሮስ (Albatrosses and Some Parrots) ያሉ ትላልቅ የአዕዋፍ ዝርያዎች እና አንዳንድ በቀቀኖች ለብዙ አሥርተ ዓመታት ሊኖሩ እንደሚችሉ አመላክተዋል። መጠን፣ ዝርያ እና የመኖሪያ አካባቢ በአዕዋፍ የሕይወት ዘመን ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩም አስገንዝበዋል። በዚህም መሠረት ትልልቅ ወፎች ከትንንሽ ወፎች የበለጠ ረጅም ዕድሜ ይኖራሉ ብለዋል። እንደ ዝርያቸው የሚወሰን ቢሆንም አዕዋፋት ከቀዝቃዛ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸው አካባቢዎች ላይ መኖር እንደሚችሉም አንስተዋል። አንድ ተመራጭ የአየር ንብረት የላቸውም፤ አብዛኞቹ የአዕዋፍ ዝርያዎች የተረጋጋ፣ አስተማማኝ የምግብ አቅርቦት ለማግኘት እና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ ሁኔታዎችን የሚቸር የአየር ሁኔታን ይመርጣሉ ነው ያሉት። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁ 11 ሺህ 100 የሚጠጉ የአዕዋፍ ዝርያዎች እንዳሉም ነው ያስረዱት።
በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ
Oct 11, 2025 15545
በዮሐንስ ደርበው በየዓመቱ በሚሊየን የሚቆጠሩ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን አስታውቋል። የዓለም የስደተኛ ወፎች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ20ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ15ኛ ጊዜ "ምቹ የመኖሪያ ቦታ፤ ለአዕዋፋት አኗኗር ምቹ የሆኑ ከተምች እና ማኅበረሰብ" በሚል መሪ ሐሳብ ዛሬ በመላው ዓለም እየተከበረ ነው። በኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ጥበቃ ባለሥልጣን የጥበቃ ቦታዎችና የብሔራዊ ፓርኮች ዋርደን ፋንታዬ ነጋሽ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የዓለም የፍልሰተኛ ወፎች ቀን የሚከበረው ስለ ፍልሰተኛ ወፎች ያለ የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለማሳደግ እና በእንቅስቃሴያቸው ወቅት ተገቢ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጎልበት ነው። ለምግብና ለመራባት በይበልጥ ምቹ ሁኔታ በመፈለግ ብሎም ከወቅታዊ ተፈጥሯዊ ሁኔታዎች (ቅዝቃዜና ሙቀት ) ለማምለጥ ወፎች ምቹ ወደሚሉት አካባቢ እንደሚፈልሱ አንስተዋል። በዚህም መሠረት ከአውሮፓ፣ እስያ፣ ከተለያዩ የአፍሪካ እና ባልካን ሀገራት በየዓመቱ በተለያዩ ወቅቶች በሚሊየን የሚቆጠሩ ወፎች በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ጠቁመዋል። አንዳንድ ፍልሰቶች አጭር መሆናቸውን ገልጸው፤ አኅጉራትን፣ በረሃዎችን እና ውቅያኖሶችን ማቋረጥ የግድ የሚሆንባቸው ረጅም ርቀት የሚሸፍኑ ፍልሰቶች እንዳሉም አስገንዝበዋል። ትክክለኛ ዓመታዊ ቆጠራ ላይ የተመሠረተ አሀዛዊ መረጃ ማግኘት ቢያዳግትም፤ በተለይም በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ መስመር አማካኝነት በየዓመቱ በርካታ ፍልሰተኛ ወፎች ወደ ኢትዮጵያን ይመጣሉ ብለዋል። በዚህም መሠረት ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን የሚልቁ ፍልሰተኛ ወፎች በኢትዮጵያ በኩል የሚያልፈውን የስምጥ ሸለቆ መስመር ይጠቀማሉ ነው ያሉት። በተጨማሪም 199 ገደማ ዝርያዎች ከአውሮፓና እስያ እንዲሁም 47 ዓይነት ዝርያዎች ከአፍሪካ የተለያዩ ሀገራት በፍልሰት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ እና ከወራት ቆይታ በኋላ ወደተለያዩ አቅጣጫዎች ተመልሰው እንደሚሄዱም አንስተዋል። እንደዝርያቸው ቢወሰንም ከቅዝቃዜ እስከ ሞቃታማ የአየር ንብረት ያላቸውን አካባቢዎች በማካለል የሚኖሩት እነዚህ ፍልሰተኛ ወፎች ቋሚ የመኖሪያ ሥፍራ እና ወጥ የአየር ንብረት የላቸውም ብለዋል። ነገር ግን አብዛኞቹ የወፍ ዝርያዎች ለአስተማማኝ የምግብ አቅርቦትና ልጆቻቸውን ለመንከባከብ ተስማሚ የአየር ንብረት ወዳላቸው አካባቢዎች ርቀው በመሄድ አስቸጋሪ ወቅቶች እስከሚያልፉ ይጠብቃሉ ነው ያሉት።
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 21294
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
መጣጥፍ
ጊፋታ እና ኮርማ ጪሻ
Sep 17, 2026 202
"ጊፋታና ኮርማ ጪሻ" (በማስረሻ ሐብታሙ ከኢዜአ ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ) የወላይታ ዘመን መለወጫ "ጊፋታ" በዓል ሲደርስ ሜዳና ጋራው በአበቦች ይደምቃል። የአበቦቹ መዓዛ አካባቢውን ያውዳል። ሕዝቡም የወደፊቱን ብሩህ ተስፋ በዐይነ-ሕሊናው እያሰበ ዕለቱን በናፍቆት ይጠብቃል። ከአበቦች መካከልም ከሁሉ ቀድሞ የሚፈካው "ኮርማ ጪሻ" ወይም "የጊፋታ አበባ" በሰፊው መስክ ላይ ሌላ ውበትና ድምቀት ይፈጥራል። ''ኮርማ ጪሻ'' በወላይታዎች ዘንድ የጊፋታ በዓል ዋዜማና የመምጫ ወቅት መጠቆሚያ ከሆኑት የተፈጥሮ ምልክቶች አንዱ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ''ኮርማ ጪሻ'' ከአደይ አበባ የሚለይ ሲሆን፤ ነጭ ቀለም እና ትናንሽ ቅጠሎች ያሉት የአበባ ዓይነት ነው። በወላይታ ዘመን አቆጣጠር መሠረት "ኩሻ አጊና" ወይም ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ በጊፋታ ወር መባቻ ላይ በአካባቢው በስፋት በማበብ ለእይታ ድምቀት የሚሰጥና የወላይታ አዲስ ዓመት መቃረቡን የሚያበስር ድንቅ የተፈጥሮ ስጦታ ነው "ኮርማ ጪሻ" ወይም "የጊፋታ አበባ"። በጉዳዩ ላይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የወላይታ ታሪክ ተመራማሪ አቶ አዳነ አይዛ እንደሚያስረዱት፤ ቀደምት የወላይታ ሥነ-ፈለግ አዋቂዎች ዘመንን ለመቁጠር ከፀሐይ፣ ጨረቃ እና ከዋክብት እንቅስቃሴ በተጨማሪ፣ የተፈጥሮ ለውጦችን ከመልክዓ-ምድሩ ውበትና ከተፈጥሯዊ ምልክቶች ጋር አጣምረው ይጠቀሙ እንደነበር አውስተው፤ ይህ ''ኮርማ ጪሻ'' ትልቁ ማረጋገጫ ስለመሆኑም ይገልጻሉ። "ጊፋታ" ሲቃረብ የወላይታ ሕዝብ ለበዓሉ ሙሉ ዝግጅት የሚያደርግበት አያሌ የተፈጥሮ ምልክቶች እንዳሉት ተመራማሪው ይናገራሉ። ወላይታዎች የዝናብና የአየር ንብረት ለውጥን መሠረት በማድረግ ጊዜን የሚቆጥሩ ሲሆን፤ የክረምቱ ከባድ ዝናብና ጨለማ ወቅት አልፎ ሙሉ የፀሐይ ብርሃን መተካት ''ቦቃልሳ'' ማለትም ''ኦፊንታ'' (የፀደይ ወቅት) ሊጀምር ሲል ለጊፋታ በዓል ጥቂት ቀናት ብቻ መቅረቱን በማጥናት አንዱ ከአንዱ መረጃ መለዋወጥ ይጀምራሉ ብለዋል። የወንዞች ሙላትና መጉደልም እንደ አንድ ምልክት የሚወሰድ ሲሆን፤ ለሦስት ወራት ምድርን አጨልሞ የነበረው ጭጋግና የጉም ወቅት አልፎ በክረምቱ ጎርፍ ሞልተው የነበሩ ወንዞች ጊፋታ ሲቃረብ እየጎደሉ ይመጣሉ። ጨረቃም በአዲስ መልክ ለመውጣት በአሮጌው ዓመት በጨለማ ውስጥ ለቀናት ቆይታ ''ጤሩዋ'' ወይም መውጫ ጊዜዋ ሲደርስ በ''ግሩዋ'' (በሥነ-ፈለግ አዋቂዎች) ዓይን ከታየች፤ አዲስ ዓመት መቃረቡን በአዋጅ ሳይነገራቸው እንዲሁ በተፈጥሮ ምልክት ብቻ ዝግጅት ማድረግ ይጀምራሉ። ይህ ብቻ አይደለም፤ የጊፋታ መምጣትን ጠቋሚ የሆነው የነጭ ቢራቢሮ መንጋ የወላይታን ምድር በመውረር ከአንድ አቅጣጫ ወደ ሌላኛው አቅጣጫ መብረር ሲጀምርም ጊፋታ መቃረቡን አመልካች መሆኑን አቶ አዳነ ይገልጻሉ። በዚህ ወቅት ልጆች የቢራቢሮ መንጋ ለማደን ወደ መስክ ወጥተው የሚያደርጉት ጨዋታ የጊፋታ መምጫን ልዩ ያደርገዋል፤ የበዓሉ መቃረብ ደወል ተደርጎም ይወሰዳል። በዚህ ትይዩ ወቅት የሚያብበው ''ኮርማ ጪሻ'' የክረምቱ ጨለማና ያ ከባዱ ዝናብና ጉም አልፎ ወደ ፀደይ ብርሃን በሚሸጋገርበት ወቅት የፀሐይን መውጣት ተከትሎ የሚመጣ ጊዜ ወይም ''ቦቃልሳ'' የሚባለው ወቅት ሊገባ ሲል መሆኑንም የዘርፉ ሊቃውንት ይናገራሉ። በወላይታ ባህል "ኮርማ ጪሻ" ሲያብብ ኅብረተሰቡ የጊፋታ በዓል ዝግጅቱን በይፋ የሚያጧጧፍበት ልዩ የተፈጥሮ ጥሪ ተደርጎ የሚወሰድ መሆኑን ተናግረው፤ ሳይሸራረፍ ዘመናትን እየተሻገረ ይኸው ለዛሬው ትውልድ መድረሱን የገለጹት ደግሞ በወላይታ ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ የባህል፣ የታሪክና ቅርስ ተመራማሪ አቶ ግርማ ገነነ ናቸው። "ኮርማ ጪሻ" በወላይታዎች ዘንድ ለጊፋታ በዓል "እንኳን አደረሰህ / አደረሳችሁ!" ተብሎ የሚበረከት የመልካም ምኞት መግለጫ የአበባ ስጦታ መሆኑንም አመልክተዋል። ''ኮርማ ጪሻ'' በወላይታ የዘመን አቆጣጠር እና ተፈጥሯዊ ቀመር ውስጥ ትልቅ ሥፍራ የሚሰጠው ምስጢራዊ አበባ መሆኑን የገለጹት አቶ ግርማ፤ ወደ አዲስ ዘመን መሻገሪያ ምልክት፣ የተስፋ እንዲሁም ከጨለማ ወደ ብርሃን መሸጋገርን የሚያበስርና ለመንፈስ እርካታን የሚሰጥ ነው ብለዋል። የወላይታ የዘመን አቆጣጠር ሥርዓት በጨረቃ እና በፀሐይ ዑደት ላይ የተመሠረተ ሆኖ በዓሉ የሚከበርበትን ትክክለኛ ቀን፤ "አዋቂዎች" ከሚያደርጉት ስሌት ጎን ለጎን፣ የተፈጥሮ ጸጋ የሆነው ኮርማ ጪሻ ወይም የጊፋታ አበባ ፍንትው አድርጎ ያሳያል። አበባው የወቅቱን መለወጥና የአዲሱን ዓመት መባቻ በተፈጥሯዊ ቋንቋ የሚነግር ነው። የዚህን አበባ ምስጢር ታላቅነት የሚያብራሩት ከሀገር ሽማግሌዎች አንዱ የሆኑት አቶ ኢያሱ ጋጃቦ በበኩላቸው፤ ይህ አበባ ለ"ጊፋታ" ወይም ለአዲስ ዘመን በዓል መግቢያ አንድ ወር ጊዜ ብቻ ሲቀረው የሚበቅልና ቀናት ሲቀሩት የሚያብብ ድንቅ የተፈጥሮ ፀጋ መሆኑን ይናገራሉ። ኮርማ ጪሻን ከጊፋታ በዓል መምጫ ወቅት ውጭ በዓመት ውስጥ ፈልጎ ማግኘት እንደማይቻል ገልጸው፤ ይህንን ተፈጥሮ በመተርጎም ረገድ የቀደምት አባቶች አእምሯዊ ጥበብ ማሳያ እንደሆነ ተናግረዋል። ''ኮርማ ጪሻ'' ወይም የጊፋታ አበባ ከጊፋታ በዓል ማግስት ባለው ማክሰኞ ዕለት ወደ አማች ቤት ወይም ወደ አበልጅ ቤት "ዮዮ ጊፋታ" በማለት ይዞ በመሄድ ለአባዎራው ይሰጣል። በዚህ ጊዜ አባወራው "ዮዮ ዮዮ" በማለት ተቀብሎ ከምሰሶ ጋር አስሮ ያስቀምጣል። ይህም የቤቱ መሶብ፣ በረከትና አዲሱ ዘመን እንደ ምሰሶው ጸንቶ እንዲኖር የሚደረግበት የአዲሱ ዓመት መቀበያ ምልክትና ምርቃት ነው፡፡ በዚህም ወቅት አባዎራው ''ጊፋታይ እንተና ቆዶፖ፤ እንቴ ጊፋታ ቆዲቴ'' ወይም "ዘመን እናንተን አይቁጠራችሁ፤ እናንተ ዘመናትን እየቆጠራችሁ ኑሩ" በማለት ይመርቃል። "ኮርማ ጪሻ" የወላይታ ነባር የሥነ-ፈለግ እውቀት የሚገለጥበት ተፈጥሯዊ እውቀት መሆኑንም ተናግረዋል። በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው የወላይታ የዘመን መለወጫ በዓል "ጊፋታ" ዘንድሮ በ"ጊፋታ አጊና" ወይም መስከረም 10 ቀን 2019 ዓ.ም ተወላጆችና የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።
የአፍሪካ የልማት መሰረትና የሰላም ማስከበር አውራ - ኢትዮጵያ
Sep 16, 2026 206
ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስከብራ የኖረች ሀገር ከመሆኗ ባሻገር፣ ለአህጉሩ ሀገራት የነፃነት፣ የልማትና የሰላም ማስከበር ጥረቶች ታሪካዊና መዋቅራዊ መሰረት በመጣል ግንባር ቀደም ሚና ስትጫወት ቆይታለች። ሀገሪቱ ለአፍሪካ አንድነት፣ ለቀጣናዊ ትስስርና ለሰላም ማስከበር ያበረከተችው አስተዋጽኦም የላቀ ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ገቢር ነበብ ሆኖ፣ ለጎረቤት አገራት ቅድሚያ በመስጠት፣ በጋራ ልማትና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ የሚመራ ነው። አገሪቱ በአፍሪካ አህጉር በሚከናወኑ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የመሠረተ ልማት ትስስር፣ የሰላም ማስከበርና ተዛማጅ ሁለንተናዊ መስኮች የምትጫወተው የፊት አውራነትና የመሪነት ሚና በተጠናከረ ሁኔታ ቀጥሏል። የኢነርጂ እጥረት የአፍሪካ አገራት የኢኮኖሚ ዕድገት ዋነኛ ማነቆ መሆኑን የተረዳችው ኢትዮጵያ፣ ግዙፍ የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመገንባትና ጥቅም ላይ በማዋል አህጉራዊ አርአያነቷን እያስመሰከረች ትገኛለች። በዚህ ረገድ የላቀ ምሳሌ የሚሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ፣ የአገሪቱን የኃይል ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ ለጎረቤት አገራትም አስተማማኝ የኃይል ምንጭ በመሆን ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትስስርን በጥብቅ መሠረት ላይ ጥሏል። ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ለሱዳን፣ ለጅቡቲ እና ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ የቀጣናውን የኢነርጂ ፍላጎት ከመሙላት ባለፈ፣ ዘላቂ የኃይል ልማት ትስስርን በተግባር እያረጋገጠች ትገኛለች። በተጨማሪም ከታንዛኒያ፣ ከሩዋንዳ፣ እንዲሁም ከሌሎች የምስራቅ አፍሪካና የአፍሪካ ቀንድ አገራት ጋር የኃይል መስመሮችን ለመዘርጋትና ትስስሩን የበለጠ ለማስፋፋት በትጋት እየሰራች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የኃይል ልማት ፖሊሲ ያጋራ ተጠቃሚነትንና አብሮ ማደግን መሰረት ያደረገ በመሆኑ ጎረቤት አገራት የታዳሽ ሃይል ተጠቃሚ እንዲሆኑ የድርሻዋን ማበርከቷን ቀጥላለች። ኢትዮጵያ የቀጣናው የሎጅስቲክስና የትራንስፖርት ዋና ማዕከል በመሆንም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ትስስርን እያጠናከረች ትገኛለች። የሀገሪቱ ተቋማዊ አምባሳደር የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ አፍሪካን ከእስያ፣ አውሮፓ፣ አሜሪካ እና መካከለኛው ምስራቅ ጋር በማያያዝ ረገድ የማይተካ ሚና የሚጫወት ወሳኝ የትራንስፖርት አውታር ሆኗል። በተጨማሪም ከጂቡቲ፣ ኬንያ እና ሱዳን ጋር የተዘረጉት የትራንስፖርትና የሎጀስቲክስ መሰረተ ልማቶች፣ ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿና ከቀጣናው አገራት ጋር ያላትን የንግድና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በጥራትና በፍጥነት ለማሳለጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ይገኛሉ። የኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ ልማትም ከሀገራዊና ቀጣናዊ ወሰኖች የተሻገረ ግብ በመሰነቅ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም እና የተፈጥሮ ሀብትን ለመታደግ ያለመ ግዙፍ ስትራቴጂካዊ እርምጃ ነው። ይህ ታላቅ የልማት ኢንሼቲቭ ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ መከላከል ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት በተግባር ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፓሪስ የአየር ንብረት ስምምነትንና የተባበሩት መንግሥታት የዘላቂ ልማት ግቦችን (SDGs) ከማሳካት አንጻር በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እውቅናና አድናቆት ተችሮታል። የአባይ ወንዝ መነሻ የሆነችው ኢትዮጵያ፣ በአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብሯ አማካኝነት የታችኞቹ የተፋሰሱ አገራት በጎርፍና በደለል እንዳይጠቁ ከመጠበቋም በላይ፣ የጋራ የውሃ ሀብትን በዘላቂነት ለመንከባከብና ለመጠበቅ በትጋት እየሠራች ትገኛለች። ይህ ጥረት የወንዙን ዓመታዊ የውሃ ፍሰት በመጠበቅና የአፈር መሸርሸርን በመቀነስ ለቀጣናው አገራት ዘላቂ ጥቅም የሚያረጋግጥ ተግባራዊ እርምጃ ነው። ኢትዮጵያ በቀጣናዊና አህጉራዊ የሰላም ማስከበር ስራዎች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ አሁንም በግንባር ቀደምትነት እየሠራች ትገኛለች። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ሥር በሶማሊያ (AMISOM/ATMIS)፣ በደቡብ ሱዳን፣ በኮንጎና በሌሎችም የአህጉሪቱ የግጭት ቀጣናዎች የሰላም አስከባሪ ኃይሎችን በማሰማራት ረገድ የኢትዮጵያን ያህል ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈለና አስተዋጽኦ ያደረገ አገር የለም ለማለት ይቻላል። ኢትዮጵያ በተለይም በሶማሊያ የሚንቀሳቀሰውን አል-ሸባብን የመሳሰሉ ሽብርተኛ ቡድኖች ላይ ጠንካራ ወታደራዊ እርምጃ በመውሰድ ሽብርተኝነትን በግንባር ቀደምትነት እየታገለች ትገኛለች። የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት አባላት የሶማሊያ መንግሥት ተቋማት እንዲጠናከሩና ቀጣናው ሙሉ በሙሉ ከሽብር ስጋት ነፃ እንዲሆን በጀግንነት፣ በውጤታማነትና በላቀ ቁርጠኝነት የተጣለባቸውን አገራዊና አህጉራዊ ኃላፊነት እየተወጡ ይገኛሉ። የአፍሪካን አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ስምምነት በማጽደቅና በተግባር ላይ በማዋል ረገድም ኢትዮጵያ የጎላ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። አህጉራዊ የንግድ ውሎችና ግዴታዎች ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆኑ፣ እንዲሁም የጉምሩክ አሠራሮች የተቀላጠፉና ዘመናዊ እንዲሆኑ በትጋት እየሠራች ነው። ለፓን-አፍሪካኒዝም እሴቶች መጠናከር፣ ለአህጉሪቱ የኢኮኖሚ ነፃነትና ሉዓላዊነት መረጋገጥ የኢትዮጵያ የታሪክና የፖሊሲ ካፒታል ጠንካራ መሠረት ሆኗል። በአጠቃላይ፣ አገሪቱ የአፍሪካ የልማት ምሰሶና የሰላም ማስከበር ግንባር ቀደም መሪ በመሆን ታሪካዊና አህጉራዊ ኃላፊነቷን በተጠናከረ ሁኔታ እየተወጣች ትገኛለች። በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረትና የተባበሩት መንግስታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን (UNECA) መቀመጫ በመሆን የአህጉሪቱን እውነተኛ ትረካዎችና የመረጃ ልውውጥ በግንባር ቀደምትነት የምታስተጋባ "የአፍሪካ ድምፅ" ስትሆን፣ እንደ ታላቁ የህዳሴ ግድብ ባሉ የታዳሽ ኃይል ፕሮጀክቶቿና ለጎረቤት ሀገራት በምታቀርበው ንጹህ ኤሌክትሪክ የቀጣናውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ሽግግርና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ ትደግፋለች። በተጨማሪም በባቡር፣ በአውራ ጎዳናዎች፣ በቴሌኮም፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢጋድ (IGAD) በኩል አህጉራዊ የመሰረተ ልማትና የንግድ ትስስርን በማጠናከር፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና (AfCFTA) ስምምነትን ከመደገፍ ባሻገር በሰላም ማስከበርና በቀጣናዊ ድርድሮች ረገድ የምትጫወተው ሚና ለዘላቂ ልማትና ሰላም ትልቅ ዋስትና ሆኗል።