ቀጥታ፡

የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ ተዘጋጅተናል - የሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች

ሠመራ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በዘንድሮው ምርጫ ለመሳተፍ የሚያስችለንን ካርድ በመጠቀም የተሻለ ሐሳብ ያለውን ፓርቲ ለመምረጥ የምርጫ ቀኑን እየጠበቅን ነው ሲሉ የሎጊያ ከተማ ነዋሪዎች ገለፁ።

አስተያየታቸውን ለኢዜአ ከሰጡ ነዋሪዎች መካከል ሃስና መሐመድ እንዳሉት፤ በዘንድሮው ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች እያካሄዱ ያሉትን የምርጫ ክርክር እየተከታተሉ ነው።


 

በዚህም የተሻለ ሐሳብ እያንፀባረቀ ያለውን ፓርቲ ለመለየት መቻላቸውን አንስተዋል።

ሌሎቹ አስተያየት ሰጭዎች ዘሐራ ኢድሪስና ሃዋ ኢድሪስም፤ ለመምረጥ የሚያስችላቸውን ካርድ  መውሰዳቸውን ገልጸው ይበጀኛል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።

ካርድ ያልወሰዱ ነዋሪዎች ካርድ በማውጣት ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን እንዲጠቀሙም መክረዋል።

በመራጭነት ለመሳተፍ የመጀመሪያው መሆኑን የገለጸው አብዱ ሁሴን በበኩሉ፤ በምርጫው ለመሳተፍ የምርጫ ቀኑ እስከሚደርስ እየጠበቀ መሆኑን ተናግሯል።

እየተካሄዱ ያሉ የምርጫ ክርክሮችን እየተከታተለ መሆኑን ጠቁሞ፤ ይህም ሀገሬን ሊመራ የሚችለው ፓርቲ የትኛው ነው የሚለውን እንድለይ አስችሎኛል ብሏል።

ምርጫ ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የምንፈልገውን ፓርቲ የምንመርጥበት ልዩ ዕድል መሆኑን ተረድቼ የምርጫ ካርድ ወስጃለሁ ሉት ደግሞ ሌላኛው አስተያየት ሰጭ ሐሰን መሐመድ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም