ቀጥታ፡

መገናኛ ብዙኃን ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ ማጠናከር ይጠበቅባቸዋል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፡- መገናኛ ብዙኃን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ የሚያበረክቱትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራልና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገለጹ።


 

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የልኅቀት ማዕከል የልዩ ትኩረት ዘርፍ ጋዜጠኝነት የመጀመሪያው ዙር ሠልጣኞችን እያስመረቀ ነው።

በዚሁ ወቅት አምባሳደር ሬድዋን፤ መገናኛ ብዙኃን ሀገር መገንቢያ ቁልፍ መሣሪያዎች መሆናቸውን አስገንዝበዋል።

ስለዚህ የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ የሚያበረክቱትን ከፍተኛ አስተዋጽኦ አጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት።

ለዚህ ደግሞ የሀገርን መዳረሻ ርዕይ፣ ግብና ብሔራዊ ጥቅም በቅጡ የተገነዘበ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያ ማፍራት ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።


 

የመገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የልኅቀት ማዕከል የልዩ ትኩረት ዘርፍ የጋዜጠኝነት ሥልጠናም የባለሙያዎችን ዕውቀትና ክኅሎት በማዳበር ጉልህ ፋይዳ እንደሚኖረው አመላክተዋል።

በተጨማሪም የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም የሚያስከብሩ የይዘት ሥራዎችን በማመንጨት የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና የሕዝብ አንድነት የመገናኛ ብዙኃን የትኩረት ማዕከል ሊሆን እንደሚገባ ም ነው ያሳሰቡት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም