ኤቨርተን ቼልሲን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ኤቨርተን ቼልሲን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት ኤቨርተን ቼልሲን 3 ለ 0 አሸንፏል።
ማምሻውን በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ቤቶ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ኢሊማን ንዳዬ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
በጨዋታው ቼልሲ የኳስ ቁጥጥር ብልጫ ቢወስድም ኤቨርተን ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ ተሽሎ ተገኝቷል።
ውጤቱን ተከትሎ በሊጉ 13ኛ ድሉን ያስመዘገበው ኤቨርተን በ46 ነጥብ ደረጃውን ከስምንተኛ ወደ ሰባተኛ ከፍ አድርጓል።
ለአውሮፓ መድረክ ተሳትፎው ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቼልሲ በ48 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።
ባለፉት ሁለት የሊግ ጨዋታዎች የተሸነፈው ቼልሲ በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ እያደረገ ባለው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥሏል።