1447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም ተጠናቋል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ - ኢዜአ አማርኛ
1447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም ተጠናቋል - የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2018(ኢዜአ)፦ በመላው ሀገሪቱ የተከበረው 1,447ኛው የዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታውቋል።
በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት ጋር በመቀናጀት በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ የሰው ኃይል በማሰማራት ተገቢውን የፀጥታ ሥራ በማከናወን ኃላፊነቱን በሚገባ መወጣቱንም ገልጿል።
ከበዓሉ ዋዜማ ጀምረው በተለያዩ አካባቢዎች የተጠናከረ ጥበቃ በማከናወን በዓሉ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን በብቃት ለተወጡ የፀጥታና ደኅንነት ተቋማት አመራሮችና አባላት ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል።
በተመሳሳይ ለፀጥታና ደኅንነት አካላት አስፈላጊውን ትብብርና ድጋፍ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ላበረከተው ለመላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ለሃይማኖት አባቶች፣ ለበዓሉ አስተባባሪዎች፣ ለእምነቱ ተከታዮች እና ለወጣቶች የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አመስግኗል።