የቡና ልማትን ማጠናከር የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይረዳል - ኢዜአ አማርኛ
የቡና ልማትን ማጠናከር የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ይረዳል
ሰቆጣ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የቡና ልማትን በማጠናከር የአርሶ አደሩን ዘላቂ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተሠራ ነው።
በአሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ የመስኖ አትክልትና ፍራፍሬ ልማት ቡድን መሪ ደሳለኝ አዳነ እንዳሉት፤ እስካሁን በተደረገ ጥረት ከ2 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በማሳተፍ በ36 ሔክታር ላይ የቡና ልማት ተከናውኗል።
በዘንድሮው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብርም በ11 ሔክታር ላይ በኩታ ገጠም ለማልማት የሚያስችል 16 ሺህ 854 የቡና ችግኝ መዘጋጀቱን ለኢዜአ አረጋግጠዋል።
ለዚህም ለቡና ልማት ተስማሚ የዓየር ንብረትና ሥነ-ምኅዳር ያላቸውን አካባቢዎች የመለየትና አርሶ አደሮቹን የማዘጋጀት ሥራ እየተከናወነ እንደሚገኝም አመላክተዋል።
በዚህም 1 ሺህ 324 አርሶ አደሮች እንደሚሳተፉ ጠቁመው፤ የቡና ልማቱም በኩታ ገጠም የእርሻ ሥነ-ዘዴ ይከናወናል ብለዋል።