ፉልሃም ወደ አሸናፊነት ተመልሷል - ኢዜአ አማርኛ
ፉልሃም ወደ አሸናፊነት ተመልሷል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12 /2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ31ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፉልሃም በርንሌይን 3 ለ 1 አሸንፏል።
ማምሻውን በክራቫን ኮቴጅ ስታዲየም ጆሽ ኪንግ እና ሃሪ ዊልሰን በጨዋታ ራውል ሂሚኔዝ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ዚያን ፍሌሚንግ ለበርንሌይ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ጋር አገናኝቷል።
የበርንሌይ ጆሽ ላውረንት በ94ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ከሁለት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ፉልሃም በ44 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ 13ኛ ድሉን አስመዝግቧል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 19ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው በርንሌይ በ20 ነጥብ 19ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በርንሌይ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።