በ3000 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት ባለሽኝ ባወቀ እና አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አራተኛና ስድስተኛ ወጥተዋል - ኢዜአ አማርኛ
በ3000 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት ባለሽኝ ባወቀ እና አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ አራተኛና ስድስተኛ ወጥተዋል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በ21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ማምሻውን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ተደርገዋል።
በ3000 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት ባለሽኝ ባወቀ 9 ደቂቃ ከ00 ሴኮንድ ከ26 ማይክሮ ሴኮንድ አራተኛ ወጥታለች።
በውድድሩ ላይ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊ አትሌት አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ 9 ደቂቃ ከ02 ሴኮንድ ከ41 ማይክሮ ሴኮንድ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።
ጣልያናዊቷ አትሌት ናዲያ ባቶክሌቲ 8 ደቂቃ ከ57 ሴኮንድ ከ64 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
አሜሪካዊቷ ኤሚሊ ማክካይ ሁለተኛ እና አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ሁል ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በወንዶች የ3000 ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት አዲሱ ይሁኔ 7 ደቂቃ ከ38 ሴኮንድ ከ60 ማይክሮ ሴኮንድ ስምንተኛ ወጥቷል።
ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጌትነት ዋለ 7 ደቂቃ ከ40 ሴኮንድ ከ21 ማይክሮ ሴኮንድ 12ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ጆሽ ኬር 7 ደቂቃ ከ35 ሴኮንድ ከ56 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝቷል።
አሜሪካዊው ኮል ሆከር ሁለተኛ ሲወጣ ፈረንሳዊው ያን ሽሩብ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።
በፖላንድ ቶሩን ከተማ እየተካሄደ የሚገኘው 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።
ሻምፒዮናው ነገ ይጠናቀቃል።