ቀጥታ፡

ባሳለፍነው ሳምንት …

ከመጋቢት 6 እስከ መጋቢት 12 ቀን 2018 . ከተከናወኑ ዐበይት ጉዳዮች መካከል

  • ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (/) ያስተላለፉት ማሳሰቢያ

በመካከላኛው ምሥራቅ በተፈጠረው ቀውስ የተነሣ ነዳጅ ገዝተው የሚጠቀሙ ሀገሮች እንደልብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) አስታውቀዋል።

ስለዚህ ችግሩ ተፈትቶ ወደ መደበኛው የነዳጅ አቅርቦት ሥርዓት እስከምንመለስ የነዳጅ አከፋፋዮች፣ ማደያዎች እና ተጠቃሚዎች ነዳጅን በቁጠባ ለመሠረታዊ ነገሮች ቅድሚያ በመስጠት ሁላችንም በኃላፊነት ልንጠቀም ይገባል ሲሉ ያሳሰቡት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር።

ባሳለፍነው ሳምንት …

ከሳምንቱ ዐበይት ክንውኖች መካከል

  •  ፕሬዚዳንት ታዬ ያስጀመሩት የገቢ ማሰባሰቢያ

ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ባሳለፍነው ሳምንት የመቄዶንያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐ-ግብርን በይፋ አስጀምረዋል።

በዚሁ ወቅትም፤ ማኅበራዊ ኃላፊነት ለመንግሥት ብቻ የሚተው ተግባር አለመሆኑን ገልጸው፤ የሕይወት ምሉዕነት የሚረጋገጠው ካለው ላይ ቆርሶ በመስጠት መሆኑን አስገንዝበዋል። ለተቸገሩ መድረስና ለወገን መቆም ትልቅ የመንፈስ ዕርካታን የሚሰጥ ተግባር በመሆኑ መጠናከር እንዳለበትም አስረድተዋል።

  • ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ጋር መምከራቸው

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (/) ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ የተወያዩት ባሳለፍነው ሳምንት ነበር።

በውይይታቸውም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ ምክክር አድርገዋል።

  • የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጉብኝት

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ባሳለፍነው ሳምንት በእንዶዴ ደረቅ ወደብ ማስፋፊያ እና በኤ ኤም (AMG) - እንዶዴ የባቡር መሥመር ፕሮጀክቶች ላይ የሥራ ጉብኝት አድርገዋል።

እነዚህ በራስ ዐቅም የሚገነቡ መሠረተ ልማቶች የሎጂስቲክስ ተወዳዳሪነታችንን ከማሻሻል ባለፈ የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ያጸናሉ ሲሉም በዚሁ ወቅት በአጽንዖት ገልጸዋል።

  • ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ-መሥተዳድሮች ጋር

በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከክልል ርዕሳነ መሥተዳድሮች፣ ከከተማ አሥተዳደር ከንቲባዎች፣ ከትምህርት ዘርፍ አመራሮችና ከባለድርሻ አካላት ጋር የኢትዮጵያ ብሔራዊ የዲጂታል ፈተና ምዘና ሥርዓት እና የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ግንባታን በተመለከተ በበይነ መረብ ተወያይተዋል።

በዚሁ ወቅት 12 ክፍል ብሔራዊ ፈተናን ሙሉ በሙሉ ወደ ኦንላይን ትግበራ ለማሸጋገርና ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ፍትሐዊና ተዓማኒ የምዘና ሥርዓት ለመገንባት ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።

በአዲስ አበባ፣ በድሬዳዋ እና በሁሉም ክልሎች በተመሳሳይ ስታንዳርድ 1 ሺህ 452 ቅድመ 1 ደረጃ ትምህርት ቤቶች እስከ መጪው ነሐሴ ተጠናቀው ወደ ሥራ እንዲገቡ መግባባት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

  • 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል

በሙስሊሞች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ረመዳን ወር ተጠናቅቆ 1 ሺህ 447ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላ ሀገሪቱ በድምቀት የተከበረው ባሳለፍነው ሳምንት ነበር።

ለበዓሉ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (/) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና ሌሎች የፌደራል፣ የከተማ አሥተዳደሮች እና የክልል ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን አደረሳችሁ የመልካም ምኞት መግለጫ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል።

#ባሳለፍነው_ሣምንት #ኢዜአ 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም