ሊቨርፑል በብራይተን ተሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
ሊቨርፑል በብራይተን ተሸነፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት ብራይተን ሊቨርፑልን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአሜክስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ዳኒ ዌልቤክ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።
ሚሎስ ኬርኬዝ የሊቨርፑልን ብቸኛ ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር የተደረገበት ሲሆን ለግብ የቀረቡ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል።
በሊጉ 11ኛ ድሉን ያስመዘገበው ብራይተን በ43 ነጥብ ደረጃውን ከ12ኛ ወደ 8ኛ ከፍ አድርጓል።
ብራይተን በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ተስፋውን ያለመለመ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል።
በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሊቨርፑል በ49 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።
ቀያዮቹ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት በሚያደርጉት ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ጥለዋል።