ቀጥታ፡

በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈጠረውን ዓለም አቀፍ ጫና ለመቋቋም በኃላፊነት መሥራት ይገባል

ሐረር፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፡- በነዳጅ አቅርቦት ላይ የተፈጠረውን ዓለም አቀፍ ጫና ለመቋቋም በኃላፊነት መሥራት እንደሚገባ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ምሁር አስገነዘቡ።

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል መምህር ፍሬዘር ጥላሁን፤ በመካከለኛው ምሥራቅ የተከሰተው ውስብስብ ችግር ለነዳጅ ገዢ ሀገራት ፈተና መሆኑን አንስተዋል።



 
ስለዚህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ነዳጅ ገዝተው የሚያስገቡ ሀገራት በቁጠባ መጠቀም እንደሚጠበቅባቸው መክረዋል።

እንዲህ ዓይነት ዓለም አቀፍ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትም በኤሌክትሪክ ኃይል ልማትና ተጠቃሚነት ላይ ማተኮር እንደሚገም አመላክተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ የልማት ጥረት ትልቅ ተስፋን የሠነቀ መሆኑን ጠቁመው፤ የአረንጓዴና ታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ማተኮሯ በጥሩ ተሞከሮነት የሚጠቀስ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ጥረት እንዳለ ሆኖ ከነዳጅ ጋር በተያያዘ አሁን ያለውን ዓለም አቀፍ ችግር ለመሻገር በከፍተኛ ሀገራዊ አደራ እና የኃላፊነት ስሜት በትብብር መሥራት ይገባል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም