በደቡብ ኦሞ ዞን ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል - ኢዜአ አማርኛ
በደቡብ ኦሞ ዞን ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቷል
ሀና፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኦሞ ዞን የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማት እና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱን የዞኑ አሥተዳደር ገለጸ።
ከተለያዩ መገናኛ ብዙኃን የተውጣጡ ባለሙያዎች በሳላማጎ፣ በበና ፀማይ ወረዳዎችና በቱርሚ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ መስኅቦችን ጎብኝተዋል።
የዞኑ አሥተዳደር የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ምኅረት አሳራቱ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ የጉብኝቱ ዓላማ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ማሳደግ ነው።
በዞኑ የሚገኙ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ መስኅቦችን የማስተዋወቅ ሥራ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ጠቅሰው፤ ካለው እምቅ ዐቅም አንጻር ገና ብዙ መሥራት እንደሚገባ አመላክተዋል።
ስለዚህ የቱሪስት መዳረሻዎችን በማልማትና በማስተዋወቅ ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሠራ ነው የተናገሩት።