ቀጥታ፡

ከ18 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ዜጎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል - ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2018(ኢዜአ)፦ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ከ18 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

ምርጫ ቦርድ የ7ኛው ጠቅላላ ምርጫን የመራጮች ምዝገባ በጊዜ ሠሌዳው መሠረት ከየካቲት 28 እስከ መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም በማከናወን ላይ እንደሚገኝ አመልክቷል።

በዚህም ቦርዱ ከየካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በማንዋልና በዲጂታል አማራጭ ባከናወነው የመራጮች ምዝገባ በድምሩ 18 ሚሊየን 556 ሺህ 337 መራጮች መመዝገባቸውን አስታውቋል።

ከጾታ ስብጥር አንጻርም 10 ሚሊየን 133 ሺህ 639 ወንድ እና 8 ሚሊየን 422 ሺህ 698 ሴት የምርጫ ካርድ መውሰዳቸውን ነው የገለጸው።

በተያያዘም ቦርዱ ለመራጮች ምዝገባ አወዳድሮና ገለልተኝነታቸውን በፖለቲካ ፓርቲዎች አስተችቶ ያሠለጠናቸውን 187 ሺህ 28 የምርጫ አስፈጻሚዎች ማሰማራቱንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም