በሐረሪ ክልል ሰባት ሺህ 500 ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት ወስደዋል - ኢዜአ አማርኛ
በሐረሪ ክልል ሰባት ሺህ 500 ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት ወስደዋል
ሐረር፤ ህዳር 16/2018 (ኢዜአ):- በሐረሪ ክልል እስካሁን ሰባት ሺህ 500 ዜጎች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናን በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ አስታወቀ።
የኤጀንሲው ኃላፊ አቶ ጀማል ኢብራሂም ለኢዜአ እንደገለፁት በክልሉ በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እስካሁን 16 ሺህ ዜጎች ስልጠናውን ወስደዋል።
ስልጠናውን ከወሰዱት መካከል እስካሁን ሰባት ሺህ 500 ዜጎች በብቃት በማጠናቀቅ የምስክር ወረቀት መውሰዳቸውን ተናግረዋል።
በክልሉ በተያዘው በጀት ዓመት ከ15 ሺህ በላይ ወጣቶችን የስልጠናው ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን የገለጹት አቶ ጀማል፤ ባለፉት አራት ወራት ከ6 ሺህ 500 በላይ ወጣቶችን በዘርፉ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በመርሃ ግብሩ ፕሮግራሚንግ፣ ዳታ ሳይንስ፣ አንድሮይድ፣ ሰው ሰራሽ አስተውሎትና ተያያዥነት ያላቸው ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሚገኙም ገልጸዋል።
ሥልጠናው ወጣቶችን የክህሎት ባለቤት ከማድረግ ባለፈ ብቁ፣ ተወዳዳሪና ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ እያስቻለ መሆኑንም አክለዋል።
የአምስት ሚሊዮን የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና መርሃ ግብር በክልሉ በታቀደው መሰረት እየተከናወነ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡
በክልሉ ስልጠናውን ያልወሰዱ ወጣቶች በቀጣይ ጊዜያት ተመዝግበው እንዲሰለጥኑና የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑም ኃላፊው ጥሪ አስተላልፈዋል።
የአምስት ሚሊዮን ኮደርስ ስልጠና ወጣቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እያደረገ መሆኑም ይታወቃል።