ቀጥታ፡

በክልሉ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ አመራሩ በትጋት መስራት አለበት- ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)

ሆሳዕና፤ ሕዳር 17/2018 (ኢዜአ)፦በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመንግስትና በህዝብ ትብብር የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ አመራሩ በትጋት መስራት እንዳለበት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ገለፁ፡፡

በክልሉ "በመደመር መንግሥት እይታ፣ የዘርፎች እመርታ" በሚል መሪ ሀሳብ ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር)፥ አመራሩ ለተሰለፈለት ዓላማ ቅድሚያ ሰጥቶ በመስራት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መትጋት ይኖርበታል።

በክልሉ በመንግሥትና በህዝብ ትብብር የተጀመሩ የልማት ስራዎችን በማስቀጠል የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አመራሩ በትጋት መስራት አለበት ብለዋል፡፡

በክልሉ በህዝቦች መካከል አብሮነትን በማጠናከር ልማትን ለማፋጠን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አመራሩ በስልጠና ያገኘውን ተሞክሮ በማስፋት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የተጀመረውን የብልጽግና ጉዞ ለማሳካት በትጋት እንዲሰራም አሳስበዋል።

እንደ ርዕሰ መስተዳድሩ ገለጻ፥ እየተመዘገቡ የሚገኙ ስኬቶችን ማጠናከር ለሚገጥሙ ተግዳሮቶች መፍትሔ መስጠት ከአመራሩ ይጠበቃል።

ከነባር አሰራሮች በመውጣት በአዳዲስ እይታዎች ፈጠራና ፍጥነትን አክሎ በመስራት ውጤታማነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሩ አክለዋል፡፡

አመራሩ ብልሹ አሰራሮችን ከማረም ባለፈ ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ ኃላፊነቱን መወጣት እንዳለበትም አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም