ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር በታህሳስ ወር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ ሕዳር 18/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ዋንጫ ሶስተኛ ዙር ታህሳስ 4 እና 5 ቀን 2018 ዓ.ም በሃዋሳ እና በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

የሶስተኛ ዙር ዕጣ ማውጣት ዛሬ ተካሂዷል።

በዚሁ መሰረት አቃቂ ክፍለ ከተማ ከነጌሌ አርሲ፣ መቻል ከድሬዳዋ ከተማ፣ ባህር ዳር ከተማ ከቦዲቲ ከተማ፣ ኢትዮጵያ መድን ከቢሾፍቱ ከተማ ይጫወታሉ።

ደብረብርሃን ከተማ ከቤንች ማጂ ቡና፣ሲዳማ ቡና ከአርባምንጭ ከተማ፣ ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ ከንብ እግር ኳስ ክለብ እና ኢትዮጵያ ቡና ከመቀሌ 70 እንደርታ ሌሎች መርሃ ግብሮች ናቸው።

የወቅቱ የውድድሩ አሸናፊ ወላይታ ድቻ በሁለተኛው ዙር መሰናበቱ የሚታወስ ነው።

የኢትዮጵያ ዋንጫን የሚያሸንፈው ቡድን በቀጣዩ ዓመት ኢትዮጵያን ወክሎ በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ይሳተፋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም