ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ እና ኳታር ያላቸውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከርና ለጋራ ጥቅም ትብብሮችን ማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፤ ህዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ እና ኳታር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ይበልጥ ማጠናከርና ለጋራ ጥቅም ትብብሮችን ማሳደግ በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

የመከላከያ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሃመድ ከኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ሼክ ሳኡድ ቢን አብዱራህማን ቢን ሀሰን አል ታኒ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።


 

የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስትር ኢኒጂነር አይሻ መሀመድ ለሶስት ቀናት የስራ ጉብኝት በኳታር ዶሃ እንደሚገኙ መከላከያ ይገኛሉ።

ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በዛሬው ዕለት የኳታር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የመከላከያ ሚኒስትር ሼክ ሳኡድ ቢን አብዱራህማን ቢን ሀሰን አል ታኒ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡


 

በውይይታቸውም በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከርና ለጋራ ጥቅም ትብብሮችን ለማሳደግ ፍላጎት እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡

በተለይም በመከላከያ ልዩ ልዩ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር ለማሳደግና ለማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።

በተጨማሪም በተለያዩ ኢንቨስትመንትና የአቅም ግንባታ መስኮችም ትብብራቸውን ለማሳደግ ፅኑ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን ኢዜአ ከመከላከያ ሰራዊት ኦንላይን ሚዲያ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም