የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት በመሆን ተመደቡ - ኢዜአ አማርኛ
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት በመሆን ተመደቡ
አዲስ አበባ፤ ሕዳር 17/2018(ኢዜአ)፦ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)ን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መድቧል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ጸህፈት ቤት እንዳስታወቀው፤ በተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማእቀፍ ኮንቬንሽን መሠረት ኢትዮጵያ የኮፕ 32 አስተናጋጅ ሀገር መሆኗን ተከትሎ የኢትዮጵያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑትን ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)ን የኮፕ 32 ተወካይ ፕሬዝደንት አድርጎ መድቧል።
ዶክተር ጌዲዮን ከሀገር ውስጥ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከተባበሩት መንግሥታት አካላት እና አለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመተባበር የኮፕ 32 ዝግጅትን እንደሚመሩም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ማእቀፍ ኮንቬንሽን አባል ሀገራት ለኢትዮጵያ የማዘጋጀት ኃላፊነት በመስጠታቸው ምስጋናውን አቅርቧል፡፡
በዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ አስተባባሪነት ከአለም የአየር ንብረት ጥበቃ ማኅበረሰብ ጋር በቅርበት ለመሥራት ዝግጁ መሆኑንም ገልጿል፡፡