ቀጥታ፡
አርእስተ ዜና
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት - አሊኮ ዳንጎቴ
Oct 2, 2025 21
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን የዳንጎቴ ግሩፕ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ ገለጹ። ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ተደራሽነት የማስፋት ፍላጎት እንዳለውም አመልክተዋል። የዳንጎቴ ግሩፕ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኢንቨስትመንትን በመሳብ በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሀገር ናት ብለዋል። መንግስት ባደረጋቸው የሪፎርም ስራዎችና የኢኮኖሚው ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መሆን ለኢንቨስትመንት እድገት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።   ኢትዮጵያ ቁልፍ ዘርፎች ለግሉ ዘርፍ ክፍት ማድረጓ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትሮችን እንድትስብ ማድረጉን አመልክተዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ እና ለኢንቨስምንት ምቹ የሆኑ ሪፎርሞች ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዝግጁ የሆነች ሀገር እንድትሆን ትልቅ ድርሻ ማበርከቱን ነው የገለጹት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች የሚደነቁና የመንግስትን የመፈጸም አቅም አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል። በቅርቡ የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መንግስት ለኢነርጂ ደህንነት መረጋገጥና የኢንዱስትሪ እድገት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ አጠቃላይ ስራዎች ኢትዮጵያ በአፍሪካ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ መግቢያ በር እንደሚያደርጋት ተናግረዋል። የዳንጎቴ ግሩፕ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትምንት ሆልዲንግ አጋርነት በአፍሪካ ኢንዱስትሪ እድገት እና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ የጋራ ራዕይ ማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያብራሩት። የዳንጎቴ ግሩፕ ያለውን ልምድ በመጠቀም የጋራ ሽርክና ስራው ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትራንፎርሜሽን እና የግብርና ምርማነት እድገት መሰረት እንዲሆን አበክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል። የማዳባሪያ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ አልፎም የጎረቤት ሀገራትን የግብርና ትራንስፎርሜሽን እንደሚያረጋግጥ ነው የገለጹት። ዳንጎቴ ግሩፕ ዛሬ በሶማሌ ክልል ከሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ በተጨማሪ የተለያዩ የማዳባሪያ አይነቶች ማምረት የሚያስችለውን ኢንቨስትመንቶች የመጀመር ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል። የማዳበሪያ ፋብሪካው የኢትዮጵያን የማዳባሪያ ፍላጎት የሚያሟላና የምርት አቅምን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል። የማዳበሪያ ፕሮጀክቱ ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ከሲሚንቶ በመጠቀል የተሰማራበት ዘርፍ መሆኑን ጠቅሰው ኩባንያው በኢትዮጵያ አሁን ያለውን የሲሚንቶ ምርት በእጥፍ የማሳደግ እቅድ እንዳለው ጠቁመዋል። ዳንጎቴ ግሩፕ የአፍሪካን ልማትና እድገት የሚያፋጥኑ ስራዎች ላይ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስ እንደሚቀጥልም አክለዋል።
ለልጆቻችን የተሻለች ሀገር መስራት የኢትዮጵያውያን የሰርክ ስራ መሆን ይኖርበታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Oct 2, 2025 32
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ማድረግና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር መስራት የዕለት ተዕለት ስራቸው ሊያደርጉት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገነዘቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀው ወደ ስራ አስገብተዋል። በተመሳሳይም በአመት 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር ፕሮጀክትም አስጀምረዋል። የዩሪያ ማዳበሪያ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ የመሰረት ድንጋይም አስቀምጠዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተመረቀ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አመርቂና የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ ስራዎች ዛሬ መጀመራቸውን አመልክተዋል። ስራዎቹን የስኬቶቻችን ማብሰሪያና የማንሰራራት መሻታችን አድርገን እንወስደዋለን ሲሉም ገልጸዋል። ለኢትዮጵያውያን ዛሬ ታላቅ ቀን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፕሮጀክቶቹ እውን መሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። ዛሬ በሶማሌ ክልል የታየው ብርሃን በመላ ኢትዮጵያ እስኪረጋገጥና እያንዳንዱን ዜጋ ካለበት የድህነት አረንቋ አውጥቶ ወደ ሚገባቸው የብልጽግናና የልማት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ በትጋት መስራትና የተጀመረውን ማጠናቀቅ ይጠበቃል ነው ያሉት። እኛ እንጀምራለን፣ እኛ ተግተን እንሰራለን እናም እኛ እንጨርሳለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስራዎቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን ብልጽግናን እናረጋግጣለን ብለዋል።   ኢትዮጵያውያን ለታላላቅ ስራዎች በመደመር የኢትዮጵያን ስም የማስጠራት፣ ከፍታዋን የማረጋገጥና ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን መስራት የሰርክ ስራቸው መሆን ይኖርበታል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ብልጽግና እና የጀመረችውን ስራ መጨረስ የማይቆም መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም አካል በቀና ልብ ለሀገር ልማትና እድገት በጋራ እንዲሰራ አሳስበዋል። በሶማሌ ክልል የተበሰሩት ፕሮጀክቶች የብልጽግና ፓርቲ ሁሉን አቃፊነት በግልጽ የሚያመላክት መሆኑንም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ማንሰራራትና ብልጽግናን እውን ለማድረግ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
በደብረማርቆስ ከተማ የሰፈነውን ሰላም በማስጠበቅ ልማትና እድገትን የሚያፋጥኑ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - የከተማ አስተዳደሩ
Oct 2, 2025 47
ደብረ ማርቆስ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፡- በደብረማርቆስ ከተማ የሰፈነውን ሰላም አስጠብቆ ልማትና እድገት በማፋጠን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ገለጸ። የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን፤ በቀረበው የአስተዳደሩ የአሻጋሪ እና ዘላቂ የልማት እቅድ ላይ ውይይት አድርጓል።   በጉባዔው መድረክ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ እንደገለጹት፤ ሕብረተሰቡን ያሳተፈ ልማት በማካሄድ ሀገር ለማሻገር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ያቀዳቸውን አሻጋሪና ዘላቂ የልማት እቅዶችን ከግብ ለማድረስ ሁሉን አቀፍ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪ፣ በትምህርት፣ በጤናና ሌሎች የልማት ዘርፎች በክልል ደረጃ የታቀደውን የ25 ዓመት እቅድ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ለማውረድ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል። በአካባቢው የሰፈነውን ሰላም አስጠብቆ በማፅናት የከተማውን ልማትና እድገት በማፋጠን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንን ለማሳካት በሚደረገው ጥረትም የምክር ቤት አባላት የተጠናከረ የድጋፍ ክትትል ማጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። የምክር ቤቱ አባል ብዙአየሁ አያሌው፤ በአስተዳደሩ የቀረበው እቅድ የሚያሰራና የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ይህ እቅድ ተግባራዊ እንዲሆንም ድጋፍና ክትትል በማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። ሌላው የምክር ቤቱ አባል ጌታቸው ህብስቱ ፤ እቅዱ የከተማዋን እድገት የሚያፋጥን በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።    
በክልሉ የሌማት ትሩፋት መርሀግብር በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ውጤት እንዲመዘገብ እያስቻለ ነው - ቢሮው
Oct 2, 2025 43
ሾኔ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲጎለብት በማድረግ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል መርሃ ግብር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ስሩር በወቅቱ እንደገለጹት መንግሥት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፉን በማሻሻልና በማዘመን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡   በክልሉ በተለይም ባለፉት አመታት ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፉን ለማሻሻልና ለማዘመን በተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። በዘርፉ ከተሰማሩ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች ባለፈ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት መጎልበት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ውጤቶች መመዝገባቸውን አመልክተዋል። በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ የተገኘው አበረታች ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው የተቀናጀ ስራ ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ከዝርያ ማሻሻል ስራው በተጓዳኝ የእንስሳት ጤና ማስጠበቅና የመኖ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።   የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ሀብታሙ ታደሰ በበኩላቸዉ፡- በዞኑ በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ትግበራ ጋር በማስተሳሰር በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፉ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በርካታ የወተት፣ የንብና የማር መንደሮችን ማደራጀት መቻሉን ጠቅሰው ዘርፉ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል። ዝርያቸው የተሻሻሉ የወተት ላሞች በማርባታቸው ከወተትና ከወተት ተዋጽኦ ንግድ የተሻለ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን የተናገሩት በሾኔ ከተማ ነዋሪ አቶ አሰፋ ደንበል ናቸው። በዝርያ ማሻሻያ መርሀ ግብር ማስጀመሪያ ላይ የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል፡፡
ኢሬቻ አብሮነትንና ትብብርን በማጠናከር ለሀገር እድገት የላቀ አበርክቶ አለው
Oct 2, 2025 36
አዲስ አበባ ፤መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፡- ኢሬቻ አብሮነትንና ትብብርን በማጠናከር ለሀገር እድገት የላቀ አበርክቶ እንዳለው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ሃላፊ ጀማል ጀምበሩ (ዶ/ር) ገለጹ። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ደረጃ በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል በተለያዩ ባህላዊ ትርኢቶች ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጀማል ጀምበሩ (ዶ/ር) የኦሮሞ ህዝብ ከገዳ ስርዓት በወረሰው የኢሬቻ በዓል በአንድነትና በአብሮነት ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ነው።   በዓሉ ለከተማዋ ትልቅ ፀጋን ይዞ የሚመጣ መሆኑን አንስተው በተለይም ቱሪስቶችን በመሳብ፣ የንግድ ተቋማትንና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ለሀገራችን እድገት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል። ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመተባበር፤ የመረዳዳትና የአንድነትና የሰላም መድረክ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት መሆኑን ጠቅሰዋል። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ታላቁ የህዳሴ ግድባችን በኢትዮጵያውያን ርብርብ በተጠናቀቀበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ደግሞ ልዩ ትርጉም ያሰጠዋል ብለዋል። በዓሉ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ አመራርና ነዋሪው ተቀናጅተው በመስራት በቂ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል። በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ እንግዶች ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የንግድ ተቋማት አቅማቸውን አጠናክረው አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ነው ያሉት። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ሞጎሴ በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል የመተባበር፣ የመረዳዳትና የአንድነት መድረክ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢሬቻ የሰላም፣ የእርቅ እና ሁሉንም ያለ ልዩነት የሚያሰባስብ በዓል ስለሆነ እሴቱን ጠብቀን ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች የተለመደውን የእንግዳ ተቀባይነት ልምዳቸውን አጠናክረው የሞቀ መስተንግዶ በማድረግ የአብሮነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።  
የሚታይ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያሉ ጸጋዎችን በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎች ይጠናከራሉ
Oct 2, 2025 48
ወላይታ ሶዶ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያሉ ጸጋዎችን በማልማት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ ገብረመስቀል ጫላ ገለጹ። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ያሉ ጸጋዎችን በማልማት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የአመራሩን አቅም ማሳደግ እንደሚገባም ገልጸዋል።   ክልሉ ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በመተባበር ለመንግስት ሥራ ኃላፊዎች ያዘጋጀው የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በወላይታ ሶዶ ከተማ እየተሰጠ ነው። አቶ ገብረመስቀል ጫላ በመድረኩ ላይ እንደገለጹት በክልሉ ያሉትን ዕምቅ ጸጋዎች በማልማት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሰሩ ሥራዎች ውጤቶች እየተመዘገቡ ነው። ለዚህም በተለይ በግብርና፣ በኢንቨስትመንት፣ በቱሪዝምና በሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፎች የተከናወኑ ተግባራት ስኬታማ መሆናቸውን በማሳያነት ጠቅሰዋል። ጸጋዎችን አልምቶ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ለማስቀጠል የክልሉ መንግስት አበክሮ እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፣ ለስኬታማነቱ የአመራሩን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ማሳደግ ይገባል ብለዋል። በክልሉ የአመራሩን ብቃት የሚያሳድጉ ስልጠናዎች እየተሰጡ መሆኑን ጠቁመው፣ ዛሬ የተጀመረው ስልጠናም የዚሁ አካል መሆኑን ተናግረዋል። በተለይ የክልሉን የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ፀጋዎች በመጠቀም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በሚደረገው ጥረት አመራሩ የነበረውን ትጋት እንዲያጠናክር ስልጠናው ያግዛል ብለዋል። በተጨማሪም ኃላፊነቱን በብቃት የሚወጣ፣ ፀጋዎችንና ዕድሎችን ለይቶ ለልማት የሚያውል እንዲሁም ፈተናዎችን ወደ ዕድል የሚቀይር አመራር በመፍጠር ውጤታማነትን ለማሳደግ ጠቀሜታ እንዳለውም አክለዋል። በክልሉ የታቀዱ ልማቶች በተያዘላቸው ጊዜና በጀት እንዲጠናቀቁ በተቀናጀ መንገድ መመራት እንዳለባቸው አንስተው፣ ለዚህም የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት መገንባት ያስፈልጋል ብለዋል። ለሥራ ሃላፊዎች ስልጠናውን እየሰጡ ያሉት የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው የማደግና የለውጥ ሂደትን በተፈለገው ፍጥነትና መጠን ለማስኬድ አስተሳሰብን ማሳደግ እንደሚገባ ገልጸዋል።   ለውጤት የእይታ ለውጥ ማድረግ ቀዳሚ ነው ያሉት አቶ ዛዲግ፣ የአዕምሮ እይታ ሲያድግ በተሰማራንበት ሁሉ ከፍ ያለ ውጤት ለማስመዝገብ የእንችላለን ስሜት ይዳብራል ብለዋል። ይህም የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ የኢትዮጵያን ልዕልና ይበልጥ ማረጋገጥ የሚያስችል አቅም እንደሚሆን አመልክተዋል። ያደጉ ሀገራት ሁሉ ለራሳቸው የነበራቸውን ዝቅተኛ አመለካከት በእንችላለን በመቀየራቸው ማደጋቸውን አስታውሰው የሁሉም ሰው የእይታ ለውጥ ለግልም ሆነ ለሀገራዊ ዕድገት አበርክቶ እንዳለው አስረድተዋል። ሰልጣኝ አመራሮችም ዕይታቸውን በማሳደግና ከክልሉ ነባራዊ ሁኔታ አሻግሮ በማየት የለውጥ ጉዞን ለማፋጠን መትጋት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ለሦስት ተከታታይ ቀናት እየተሰጠ ባለው ስልጠና የማዕከላትና የዞን እንዲሁም የሦስቱ ሪጂዮ ፖሊስ ከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ አመራሮች በመሳተፍ ላይ ናቸው።  
ከዓለም ጤና ድርጅት የተገኘው ዕውቅና ኢትዮጵያ በመድሃኒት ቁጥጥር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ያሳያል - ዶክተር መቅደስ ዳባ
Oct 2, 2025 55
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከዓለም ጤና ድርጅት ያገኘችው ዕውቅና በመድሃኒት ቁጥጥር ዘርፍ ሊደረስበት ለታሰበው ስኬት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆናችንን የሚያሳይ ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። እንደ ሀገር ተኪ ምርትን ለማሳደግ የተጀመረውን ጥረት የበለጠ የሚያግዝና የሀገር ወስጥ የመድሃኒት አምራቾችን የሚያበረታታ መሆኑንም ነው ያነሱት። ኢትዮጵያ በመድሃኒትና በህክምና መሳሪያ ቁጥጥር የደረሰችበት ስኬት ለአፍሪካ ምሳሌ እንደሚሆንም ገልጸዋል።   የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርዓት ለመፍጠር ተግባራዊ የሆኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። ሚኒስትሯ ይህንን ደረጃ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው፤ ከውጭ የሚገቡ መድሀኒቶችና ክትባቶች ዓለም አቀፍ ጥራትን፣ ብቃትንና ደህንነትን ያሟሉ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት መሰራቱ ለውጤቱ መገኘት ምክንያት ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ለኢትዮጵያ የሦስተኛ ደረጃን ሲሰጥ በመድሃኒት የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን አሰራር በአግባቡ ፈትሾ መሆኑንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ በህክምና መሳሪያ ቁጥጥር የዓለም ጤና ድርጅትን የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት በትኩረት እየሰራች ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ለሀገራት የደረጃ ሦስት ዕውቅና የሚሰጠው የተረጋጋ፣ የተቀናጀና በአግባቡ የሚመራ የቁጥጥር ስርዓት መኖሩን ሲያረጋግጥ ነው።
ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ልማት እመርታዊ ለውጥ እያስመዘገበች ነው - የዓለም ባንክ
Oct 2, 2025 46
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በጤና፣ በትምህርትና ማህበራዊ ጥበቃ ሰብዓዊ ልማት መርሃ ግብር እመርታዊ ለውጥ እያስመዘገበች መሆኑን በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ኤርትራ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ መንግሥት እና በዓለም ባንክ በጋራ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የሰው ሃብት ልማት ፎረም 2025 በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል። በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳንና ኤርትራ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ማርያም ሳሊም በዚህ ወቅት፤ የዓድዋ ድል መታሰቢያ የኢትዮጵያውያንን ጠንካራ መንፈስ፣ አንድነትና የወደፊት እጣ ፈንታ የሚወስን ታሪካዊ የድል አሻራ ነው ብለዋል። የሰብዓዊ ልማት ማሻሻያ መርሃ ግብሮች የሀገራትን ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በትምህርት፣ በጤና እና ማህበራዊ ጥበቃ መሳሪያ ሆነው ያገለግላሉ ሲሉ ገልጸዋል።   ከዚህ አኳያ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ልማት ማሻሻያ መርሃ ግብሮች ላይ እመርታዊ ለውጥ ማስመዝገቧን ተናግረዋል፡፡ የዓለም ባንክ የኢትዮጵያን ሰብዓዊ ልማት ለማሻሻል ለትምህርትና ጤና ተደራሽነት፣ ለማህበራዊ ጥበቃ ዘርፍ በሰጠው ድጋፍ ኩራት ይሰማዋል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያ በመድኃኒት ቁጥጥር ሥርዓት ደረጃ-3 ውስጥ መካተቷ አስተማማኝና ጠንካራ የጤና ስርዓትን በመዘርጋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ያደርጋል ሲሉም ተናግረዋል። የሀገር ውስጥ የህክምና አምራቾችን በማነቃቃት ለአፍሪካ ሀገራት ጭምር ትምህርት የሚሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ልማት በትምህርትና በጤና ተደራሽነት የእናቶችና ህፃነትን ሞት በመቀነስ ያስመዘገበችውን ውጤት ለማስቀጠል የዓለም ባንክ ለዘርፉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡   የዓለም ባንክ የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣና ምክትል ፕሬዝዳንት ንዲያሜ ዲዮፕ፤ ሰብዓዊ ልማትን ለማሳደግ በጤና፣ ትምህርትና ማህበራዊ ጥበቃ ዘርፍ አካታችነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ለእናቶችና ህጻናት የሚደረገው ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን በማንሳት፤ ኢትዮጵያ ላስመዘገበችው ስኬት ድጋፍ ያደረጉ አጋር አካላት ምስጋና ይገባቸዋል፤ ድጋፉም ተጠናከሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ ፎረሙ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዓለም አቀፍ የልማት አጋሮች፣ ፖሊሲ አውጪዎችና ባለሙያዎችን በማሳተፍ የኢትዮጵያን የሰው ሀብት ልማት ማሻሻል የሚያስችሉ አዳዲስ ስትራቴጂዎች ላይ መወያየት የሚያስችል ነው፡፡

Pulse Of Africa

POA English

POA English

Pulse Of Africa - English Language

Your news, current affairs and entertainment channel

Join us on

POA Arabic

POA Arabic - عربي

Pulse Of Africa - Arabic Language

قناتكم الاخبارية و الترفيهية

Join us on

ፖለቲካ
ሰላምን ለማፅናት ድጋፍና ክትትላችንን አጠናክረናል- የምክር ቤት አባላት
Oct 2, 2025 76
ሰቆጣ ፤ መስከረም 22/2018 (ኢዜአ) ፡- የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክር ቤት አባላት የአካባቢያው ሰላም ፀንቶ እንዲቀጥል ድጋፍና ክትትላቸውን ይበልጥ ማጠናከራቸውን ገለጹ። በአማራ ክልል በየደረጃው ሕዝባዊ ውይይቶች ሲካሄዱ የቆዩ ሲሆን፤ በዚህም ሕብረተሰቡ ከመንግስት ጎን በመቆም ሰላምን ለማፅናት ያለውን ቁርጠኝነት በይፋ አሳይቷል። ይህንን ቁርጠኝነት ካሳዩ የክልሉ አከባቢዎች መካከል ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ይገኝበታል። በአስተዳደሩ ምክር ቤት የደሃና ወረዳ ተወካይ አቶ ፋንታው የኋላው እንዳሉት፤ ቀደም ሲል በነበረው ችግር ሰብአዊና ቁሳዊ ሀብት ላይ ጉዳት ደርሷል። ይህንን ለመከላከል ሕዝባዊ ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየታቸውን አስታውሰው፤ በዚሀም ሕብረተሰቡ አካባቢውን ነቅቶ በመጠበቅ ሰላምን አፅንቶ እንዲቀጥል ድጋፍና ክትትላቸውን በማጠናከር ለውጥ እየመጣ መሆኑን ገልጸዋል። መንግስት በተደጋጋሚ ያቀረበውን የሰላም ጥሪ በመቀበል በርካታ የቀድሞ ታጣቂዎች ወደ ማሕበረሰቡ በመቀላቀል ሰላም እንዲሰፍን የድርሻቸውን እየተወጡ መሆኑን ተናግረዋል። ሌላው በምክር ቤቱ የአበርገሌ ወረዳ ተወካይ አቶ ሸጋው ተበጀ በበኩላቸው፤ በአስተዳደሩ ሰፍኖ ያለውን ሰላምን አፅንቶ ለማስቀጠል ድጋፍና ክትትላቸውን ማጠናከራቸውን ገልጸዋል። የጋራ ተጠቃሚነትን ለማጎልበትም ከአጎራባች ዞኖች ጋር ተቀናጅተን ለመስራት ቁርጠኛ ነን ብለዋል። በአሁኑ ወቅት የአካባቢያቸው ሰላም ፀንቶ በመቀጠሉ ለልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የተናገሩት የጋዝጊብላ ወረዳ ተወካይ ወይዘሮ አጫዋች ዘገየ ናቸው። የተገኘውን ለውጥ በቀጣይ አጠናክሮ ለማስቀጠል ሕብረተሰቡን ያሳተፈ የሰላም ግንባታ ስራዎች እንዲከናወኑ በመደገፍ እንደሚከታተሉ ገልጸዋል። የምክር ቤቱ ዋና አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ፋንታይቱ ካሴ፤በየደረጃው ያሉ ምክር ቤቶችና አባላት የሰላም ግንባታ ጉዳይ ዋነኛ አጀንዳ አድርገው እየሰሩ መሆናቸውን አንስተዋል። ሰላምን የማፅናቱ ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚጠበቅባቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል።    
የአዲስ አበባ የልማት ስራዎች የከተማዋን የዲፕሎማቲክ ማዕከልነት በተግባር የሚያረጋግጡ ናቸው-በኢትዮጵያ የቺሊ አምባሳደር
Oct 2, 2025 112
አዲስ አበባ፤መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦በአዲስ አበባ የኮሪደር ልማትን ጨምሮ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎች የከተማዋን ተወዳዳሪነት በማሳደግ የዲፕሎማቲክ ማዕከልነቷን በተግባር የሚያረጋግጡ መሆኑን በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣አፍሪካ ህብረትና በኢትዮጵያ የቺሊ አምባሳደር ሮድሪጎ ጉዝማን ገለፁ። በአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣አፍሪካ ህብረትና ኢትዮጵያ የቺሊ አምባሳደር ሮድሪጎ ጉዝማን ለኢዜአ እንዳሉት፤ቺሊና ኢትዮጵያን በርካታ የሚያመሳስሏቸው ነገሮች አሉ። ሁለቱም አገራት በአካባቢ ጥበቃ ላይ ጠንካራ አቋም ያላቸው መሆናቸውን አንስተው፤ ቺሊ በደቡብ ለደቡብ ትብብር ከአፍሪካ አገራት ጋር ትስስር ያላት መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የቀደምት ስልጣኔ ባለቤት መሆኑን ያነሱት አምባሳደሩ፤ አፍሪካ ብዝሃ ሀብት ያላት አህጉር በመሆኗ ብዝሃ ዘርፍ ትብብራችንን ለማጠናከር በትኩረት እንሰራለን ብለዋል። አምባሳደሩ ግጥምና ሙዚቃን በመሳሰሉ የኪነ ጥበብ ስራዎች የሁለቱን አገራት የባህል ትስስር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልፀዋል። የአገራቱን የባህል ትስስር በማጎልበት የአገራቱን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ይከናወናሉ ነው ያሉት። ይህም የሁለቱን አገራት ህዝቦች የበለጠ እንዲተዋወቁ ማድረግ የሚያስችል መሆኑን ነው ያስረዱት። አዲስ አበባ የአፍሪካ መዲናና የዲፕሎማቲክ ማዕከል በመሆኗ በከተማዋ የተደረገው ለውጥ ውበትና ዘመናዊነትን ያላበሳት መሆኑን ገልፀዋል። በከተማዋ እየተከናወነ ያለው የልማት ስራ መዲናዋን ዘመናዊና ምቹ በማድረግ ተወዳዳሪነቷን የሚያሳድግ መሆኑንም ነው የተናገሩት።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባትን ለመፍጠር የጀመረው ሥራ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ ደርሷል- አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ
Oct 1, 2025 169
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018(ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባትን ለመፍጠር የጀመረው ስራ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አቶ ታገሠ ጫፎ ገለጹ። በትግራይ ክልል ቀጣይ ለሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር አጀንዳ የማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ተግባራት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገልጿል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነሮች ከኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሠ ጫፎ እና ሌሎች ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተወያይተዋል።   በውይይቱም የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ፥ ባለፉት ዓመታት በምክክር ሂደቱ የተከናወኑ አጀንዳ የማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ ተግባራት አፈፃጸም ሪፖርትን አቅርበዋል። በሪፖርታቸውም ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ ሀገራዊ የምክክር ሂደት የዝግጅት ምዕራፍ ክንውኖችን፣ የአጀንዳ ማሰባሰብ እና ተሳታፊ ልየታ ተግባራትን ዳሰዋል። በዚህም በእስካሁኑ ሂደት በ11 ክልሎችና በሁለቱም ከተማ አስተዳደሮች ስኬታማ የአጀንዳ ማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ ተግባራት ማከናወን እንደተቻለ አስታውቀዋል። በተጨማሪም በሰሜን አሜሪካ ፣ በአውሮፓ፣ በአፍሪካና በመካከለኛው ምስራቅ ከሚኖሩ የዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር የገጽ ለገጽ እና የበይነመረብ (ቨርቿል) ውይይት መደረጉን አብራርተዋል። በዚህም በሰሜን አሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ፣ በካናዳ ቶሮንቶ፣ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስና ሌሎች ከተሞች አጀንዳ የማሰባሰብና የተሳታፊ ልየታ ስኬታማ የምክክር መድረኮች መካሄዳቸውን አስረድተዋል።   በአሁኑ ወቅት በስዊዲን የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ምክክር እየተካሄደ ነው ያሉት ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ፤ በቀጣይ ሳምንት ይኸው ስራ በዩናይትድ ኪንግደምና አየርላንድ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። በትግራይ ክልልም በሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ ማሰባሰብና ተሳታፊ ልየታ ማካሄድ የሚያስችሉ ቅድመ ውይይቶች መካሄዳቸውን አብራርተዋል። በዚህም በተለያዩ ጊዜያት ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ ማህበራትና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችና የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተደጋጋሚ ውይይቶች መካሄዳቸውን አንስተዋል። የኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያን አለመግባባቶችን በምክክር መፍትሔ ለመስጠት ጥልቅ ፍላጎት እንዳላቸው እስካሁን የተከናወኑ ተግባራት በተግባር ያረጋገጡ መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባትን ለመፍጠር የጀመረው ሥራ ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መድረሱንም ነው የገለጹት። በቀጣይም ኢትዮጵያዊያን በኃላፊነት መንፈስ በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ የሚያደርጉትን የነቃ ተሳትፎ በማጠናከር በዋና ዋና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መግባባትን መፍጠር እንደሚያስፈልግ መልዕክት አስተላልፈዋል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም ለኮሚሽኑ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።
‎በዋግ ኽምራ የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን  ማረጋገጥ ተችሏል- ምክር ቤቱ
Oct 1, 2025 110
ሰቆጣ ፤ መስከረም 21/2018 (ኢዜአ)፡- ‎በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የተከናወኑ የልማት ስራዎች የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማሳደጋቸውን በተደረገ ምልከታ ማረጋገጥ መቻሉን የአስተዳደሩ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፋንታይቱ ካሴ ገለጹ። ‎የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር 31ኛ መደበኛ ጉባዔ እየተካሄደ ነው።   በጉባዔው የመክፈቻ መድረክ ‎የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ ፋንታይቱ ካሴ ባደረጉት ንግግር፤ በ2017 የበጀት ዓመት ‎አስተዳደሩ ‎ከሕብረተሰቡ ጋር በመቀናጀት የአካባቢውን ሰላም በማስጠበቅ ሕዝቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ የልማት ተግባራት መከናወናቸውን በክትትል ማረጋገጣቸውን አንስተዋል። ‎‎በሕብረተሰቡ ዘንድ የልማት ጥያቄ ሆኖ የቆየው የሰቆጣ-ብልባላ- ጋሸና የአስፋልት ፕሮጀክቶች ምላሽ ያገኘበት በጀት ዓመት እንደሆነም ጠቅሰዋል። ‎‎‎የአካባቢውን እምቅ ፀጋ ለመጠቀም እቅድ መዘጋጀቱን ጠቅሰው፤ እቅዱ እውን እንዲሆን የምክር ቤት አባላት ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርጉ አብራርተዋል። አፈ ጉባኤዋ፤ የታለቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ መጠናቀቅ ከዘመናት ቁጭት የወጣንበት ከመሆኑም ባለፈ የሃገራችንን ዘላቂ እድገት መሰረት የጣለ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው ብለዋል። የግድቡ መጠናቀቅ ሌሎች ፕሮጀክቶችን ማሳካት እንደሚቻል ከፍተኛ መነሳሳት የፈጠረ እንደሆነም አመልክተው፤ የዞኑ ህዝብም ለግድቡ ግንባታ ያልተቆጠበ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።   ‎‎‎የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ሹመት ጥላሁን በበኩላቸው፤ ማዳበሪያ በወቅቱ እንዲቀርብ መደረጉ በመኸር ወቅት ምርታማነትን ለማሳደግ የሚያስችል ነው ብለዋል። ‎‎ይሕም በሀገር አቀፍ ደረጃ የምግብ ሉአላዊነትን ለማረጋገጥ የተያዘውን ግብ በአስተዳደሩ ደረጃ ለማሳካት መሰረት የጣለ መሆኑን አመልክተዋል። ‎በሰቆጣ ከተማ ዛሬ የተጀመረው የ‎ምክር ቤቱ በሁለት ቀናት ቆይታ ያለፈው በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀምና የ2018 በጀት ዓመት እቅድን መርምሮ እንደሚያፀድቅ ተመልክቷል።
በጋምቤላ ክልል የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ አመራሩ መትጋት አለበት - ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ
Oct 1, 2025 135
ጋምቤላ፤ መስከረም 21/2018 (ኢዜአ)፡- የጋምቤላ ክልልን እድገት በማፋጠን የሕዝቡን የልማት ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ አመራሩ በትጋት ሊሰራ ይገባል ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ገለጹ። የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ በብልጽግና ፓርቲ ከጋምቤላ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ሲሰጥ የቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ተጠናቋል።   በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ ርዕሰ መስተዳድር ዓለሚቱ ኡሞድ ባደረጉት ንግግር፤ የክልሉ አመራር ቅንጅታዊ አሰራርን በማጎልበት ለአካባቢው ልማት መፋጠን ይበልጥ መስራት አለበት ብለዋል። በዚህ ረገድ ቀደም ሲል የተመዘገቡ ስኬቶችን ማስቀጠል እንደሚገባም አሳስበዋል። አመራሩ የክልሉን የመልማት ጸጋዎች በመጠቀም የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በጊዜ የለኝም መንፈስ መትጋት እንዳለት አስገንዝበዋል። ለዚህም ከአቅም ግንባታ ስልጠናው የተገኘውን የአመራርነት ክህሎት ወደ ተግባር በመቀየር የሕዝብ አገልጋይነቱን ማሳደግ እንደሚገባም ርዕሰ መስተዳድሯ ገልጸዋል።   የአፍሪካ የአመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዚዳንት ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው፤ አመራሩ ያለውን እውቀትና ልምድ አስተባብሮ መስራት ከቻለ ክልሉን በአጭር ጊዜ ውስጥ ይበልጥ መለወጥ እንደሚችል ተናግረዋል። በተለይም ክልሉ ያለውን ሰፊ የመልማት አቅም ካለው የሰው ኃይል ጋር አቀናጅቶ ከተሰራ ባጠረ ጊዜ የክልሉን ልማት ማረጋገጥ ይቻላል ብለዋል። በክልሉ ለተጀመረው የልማት ስራዎች ስኬታማነት የድጋፍና የትብብር ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አስታውቀዋል። በጋምቤላ ከተማ ሲሰጥ በቆየው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል።      
በምዕራብ ጉጂ ዞን የሰፈነው ሰላም በአካባቢው የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ አስችሏል
Oct 1, 2025 139
ቡሌ ሆራ፤ መስከረም 21/2018(ኢዜአ)፦ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን የሰፈነው ሰላም በአካባቢው የልማት ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ማስቻሉን አባገዳዎችና የሀገር ሽማግሌዎች ገለጹ። በዞኑ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው መምጣታቸውን ተከትሎ በሰፈነው ሰላም የግብርና ስራን ጨምሮ በሁሉም የልማት ስራዎች ላይ ከፍተኛ መነቃቃት እየተፈጠረ መሆኑ ተገልጿል። በዞኑ ያለውን ሰላምና እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን በተመለከተ የኢዜአ ሪፖርተር አባ ገዳዎችንና የሀገር ሽማግሌዎችን አነጋግሯል። አባ ገዳዎቹና የሀገር ሽማግሌዎቹ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት ምልክት የሆነውን የኦሮሞ ገዳ ስርዓት መሰረት በማድረግ ቂምና ቁርሾን በመሻር፣ ጥላቻን በመተው ሰላም መገንባት የግድ መሆኑን ገልጸዋል። በዚህም በዞኑ ነፍጥ አንስተው በጫካ ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች እሴቱን አክብረውና የመንግስትንም የሰላም ጥሪ ተቀብለው በመምጣታቸው አመስግነዋል። በርካታ የታጠቁ ቡድኖች ትጥቃቸውን በመፍታት ወደ ሰላማዊ ህይወት መመለሳቸው በዞኑ ሰላምና መረጋጋት መፍጠሩንና የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ተናግረዋል። በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ ግጭት አሸናፊ የለውም ያሉት አባገዳ ገናሌ አጋ እና የሃገር ሽማግሌ የሆኑት ኦዳ ጎበና፤ የመንግስትን የሰላም ጥሪና የሁላችንንም የሰላም መሻት በመቀበል የመጡ ታጣቂዎችን እናመሰግናለን ብለዋል። ሌሎችም በጫካ የቀሩ ካሉ ይህን መልካም እድል በመጠቀም ትጥቃቸውን በመፍታትና ወደ ልማት በመመለስ ህዝባቸውን ለመካስ እንዲዘጋጁም መልእክት አስተላልፈዋል። የምዕራብ ጉጂ ዞን ጸጥታና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አየለ ዴባ፤ በዞኑ በርካታ ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ እና የአባገዳዎችን የሰላም ጥረት በመቀበል ትጥቃቸውን መፍታታቸውን ገልጸዋል። በዚህም በዞኑ አስተማማኝ ሰላምና መረጋጋት በመፈጠሩ በሁሉም መስኮች የልማት ስራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አረጋግጠዋል። በዞኑ በሁሉም የቀበሌ መዋቅሮች የተሟላ የመንግስት አገልግሎት እየተሰጠ መሆኑንና አርሶ አደሮችም በተሟላ አቅም የግብርና ስራቸውን እያከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል። በቀጣይም የመንግስት የሰላም በር ክፍት መሆኑን አንስተው ግጭትና ጦርነትን በመተው የሀገርን ልማትና ማንሰራራት እውን ለማድረግ በትብብር እንስራ ብለዋል።
በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክሩ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ ነው - ኮሚሽኑ
Sep 30, 2025 195
አዲስ አበባ፤ መስከረም 20/2018(ኢዜአ)፦ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክሩ የአጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ንቁ ተሳትፎ እያደረጉ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ገለጸ፡፡ ሀገራዊ ምክክር በመሰረታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለተፈጠሩ ልዩነቶችና አለመግባባቶች ምክንያት የሆኑትን ጉዳዮች በጥናትና በህዝባዊ ውይይቶች በመሰብሰብ፣ ሀገራዊ ምክክር በማካሄድና ምክረ ሃሳቦችን በማቅረብ ለተግባራዊነቱ የመከታተያ ሥርዓት በመዘርጋት ለብሔራዊ መግባባት ምቹ ሁኔታ መፍጠር የሚያስችል ነው፡፡   የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሉጌታ አጎ ለኢዜአ እንዳሉት፤ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን አጀንዳቸውን ለኮሚሽኑ በማቅረብ በሀገራቸው ጉዳይ ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በሰሜን አሜሪካ፣ ካናዳ፣ በአፍሪካና መካከለኛው ምስራቅ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር ውይይት በማካሄድ አጀንዳ የማሰባሰብ ስራ መከናወኑን ተናግረዋል። በአውሮፓ ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር አጀንዳ የማሰባሰብ ምክክር በመካሄድ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት በውጭ ከሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሎች ጋር በገጽ ለገጽና በበይነ-መረብ፤ በሀገር ውስጥ ከሚኖሩት ጋር ደግሞ በገጽ ለገጽ ገንቢ ምክክር ማካሄድ ተችሏል ብለዋል፡፡ በቀጣይም በሌሎች ክፍለ ዓለማት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሀገራዊ ምክክር ሂደቱ ላይ አጀንዳቸውን የሚያቀርቡበት ዕድል እንደሚፈጠር ገልጸው፤ ከወዲሁ አጀንዳቸውን እያቀረቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደትም በውጭ የዳያስፖራ ማህበሰረብ አባላት ምክክር ሊደረግባቸው የሚገቡ ጉዳዮችን በአጀንዳነት እያቀረቡ እንደሚገኙ አብራርተዋል። የፖለቲካ ዓላማቸውን በትጥቅ ለማሳካት በጫካ የሚንቀሳቀሱ አካላትም በሀገራዊ ምክክር አጀንዳ ማሰባሰብ ሂደት ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡   የአዲስ አበባ ዳያስፖራ ማህበር የቦርድ ሰብሳቢ አርቲስት ዘለቀ ገሰሰ፤ በውጭ የሚኖሩ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ አባላት በሀገራዊ ምክክሩ የሚሳተፉበት እድል ተፈጥሯል ብለዋል፡፡ በዚህም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዳያስፖራ አደረጃጀቶችና በቀጥታ አጀንዳቸውን ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እያቀረቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ማህበራዊ
ኢሬቻ አብሮነትንና ትብብርን በማጠናከር ለሀገር እድገት የላቀ አበርክቶ አለው
Oct 2, 2025 36
አዲስ አበባ ፤መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፡- ኢሬቻ አብሮነትንና ትብብርን በማጠናከር ለሀገር እድገት የላቀ አበርክቶ እንዳለው በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ሃላፊ ጀማል ጀምበሩ (ዶ/ር) ገለጹ። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል በጉለሌ ክፍለ ከተማ ደረጃ በጉለሌ ዕፅዋት ማዕከል በተለያዩ ባህላዊ ትርኢቶች ተከብሯል። በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት ጀማል ጀምበሩ (ዶ/ር) የኦሮሞ ህዝብ ከገዳ ስርዓት በወረሰው የኢሬቻ በዓል በአንድነትና በአብሮነት ፈጣሪውን የሚያመሰግንበት ነው።   በዓሉ ለከተማዋ ትልቅ ፀጋን ይዞ የሚመጣ መሆኑን አንስተው በተለይም ቱሪስቶችን በመሳብ፣ የንግድ ተቋማትንና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን በማነቃቃት ለሀገራችን እድገት ከፍተኛ ሚና እያበረከተ ነው ብለዋል። ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የመተባበር፤ የመረዳዳትና የአንድነትና የሰላም መድረክ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት መሆኑን ጠቅሰዋል። የዘንድሮው የኢሬቻ በዓል ታላቁ የህዳሴ ግድባችን በኢትዮጵያውያን ርብርብ በተጠናቀቀበት ማግስት የሚከበር መሆኑ ደግሞ ልዩ ትርጉም ያሰጠዋል ብለዋል። በዓሉ እሴቱን ጠብቆ በድምቀት እንዲከበር የከተማ አስተዳደሩ አመራርና ነዋሪው ተቀናጅተው በመስራት በቂ ዝግጅት መደረጉን አንስተዋል። በዓሉን ለመታደም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ እንግዶች ተገቢ አገልግሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የንግድ ተቋማት አቅማቸውን አጠናክረው አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል ነው ያሉት። የጉለሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ወልዴ ሞጎሴ በበኩላቸው የኢሬቻ በዓል የመተባበር፣ የመረዳዳትና የአንድነት መድረክ በመሆኑ የኢትዮጵያውያን የጋራ ሀብት መሆኑን ጠቅሰዋል። ኢሬቻ የሰላም፣ የእርቅ እና ሁሉንም ያለ ልዩነት የሚያሰባስብ በዓል ስለሆነ እሴቱን ጠብቀን ማስቀጠል ይገባልም ብለዋል። የከተማው ነዋሪዎች ለኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች የተለመደውን የእንግዳ ተቀባይነት ልምዳቸውን አጠናክረው የሞቀ መስተንግዶ በማድረግ የአብሮነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል።  
ኢሬቻ አብሮነት የሚገለጽበት ሀገራዊ እሴት ነው
Oct 2, 2025 38
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢሬቻ የህዝቦች አንድነትና አብሮነት የሚገለፅበት ሀገራዊ እሴት መሆኑን በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዓለምፀሐይ ሽፈራው ገለጹ። የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ በመጪው ቅዳሜና እሁድ በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ሀሳብ ይከበራል። ኢሬቻ የምስጋና በዓል፣ ከክረምት ወቅት መለያየትና መራራቅ በኋላ ሰዎች በአብሮነት ብርሃን ለማየት ያበቃቸውን ፈጣሪ የሚያመሰግኑበት በዓል ነው። የ2018 የኢሬቻ በዓል "ኢሬቻ ለሀገር ማንሰራራት" በሚል መሪ ሐሳብ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በቦሌ ክፍለ ከተማ ደረጃ ተከብሯል። በብልጽግና ፓርቲ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ምክትል እና የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ ዓለምፀሐይ ሽፈራው እንዳሉት የገዳ ስርዓት አንዱ መገለጫ የሆነው ኢሬቻ የህዝቦች ትስስር የሚጠናከርበት፣ አብሮነትና ወንድማማችነት የሚጸናበት ነው።   የምስጋና፣ የሠላም፣ የፍቅር እና የእርቅ በዓል የሆነው ኢሬቻ የአብሮነት መገለጫ የሆነ ሀገራዊ አሴት መሆኑን ተናግረዋል። መዲናዋ በአዲስ ዓመት በርካታ በዓላትና ሁነቶችን በተሳካ መልኩ ማስተናገዷን ጠቁመው የኢሬቻን በዓል በዚሁ ልክ ማክበር አለብን ብለዋል። የዘንድሮው በዓል አዲስ አበባ በኮሪደር ልማት የተዋበችበትና ታላቁ የሕዳሴ ግድብን ባጠናቀቅንበት ወቅት የሚከበር በመሆኑ ልዩ ስሜትና ደስታን ይፈጥራል ነው ያሉት። መዲናችን ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚመጡ እንግዶችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቋንም ገልፀዋል።   የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ እሸቱ ለማ(ዶ/ር) በበኩላቸው ኢሬቻ የፍቅር፣ የአንድነት እና የአብሮነት በዓል መሆኑን ጠቁመው በዓሉ በተሳካ ሁኔታ እንዲከበር ሁላችንም የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። ኢሬቻ ሁሉም ህብረተሰብ የሚሳተፍበት እንደሆነም ነው የተናገሩት። በአከባበሩ ላይ ከተገኙት መካከል ወይዘሮ ፋይዛ ሙስጠፋ ኢሬቻ ሁላችንም ያለምንም ልዩነት የምናከብረው በዓል ነው ብለዋል። አቶ ሽመልስ ተስንቱ በበኩላቸው የሁላችንም መገለጫ የሆነውን ኢሬቻን ከነትውፊቱ ጠብቀን ለቀጣይ ትውልድ ማስተላለፍ አለብን ነው ያሉት። አቶ ፀሐይ መርጋ በበኩላቸው ኢሬቻ መተሳሰብና መቀራረብ እንዲሁም አብሮነት የሚጎላበት መሆኑን ገልጸዋል። ወይዘሮ አየለች በየነም እንዲሁ ኢሬቻ ኢትዮጵያን በባህል ቱሪዝም ለዓለም የሚያስተዋውቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ከዓለም ጤና ድርጅት የተገኘው ዕውቅና ኢትዮጵያ በመድሃኒት ቁጥጥር ወሳኝ ምዕራፍ ላይ እንደምትገኝ ያሳያል - ዶክተር መቅደስ ዳባ
Oct 2, 2025 55
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ከዓለም ጤና ድርጅት ያገኘችው ዕውቅና በመድሃኒት ቁጥጥር ዘርፍ ሊደረስበት ለታሰበው ስኬት ወሳኝ ምዕራፍ ላይ መሆናችንን የሚያሳይ ነው ሲሉ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ ገለጹ። እንደ ሀገር ተኪ ምርትን ለማሳደግ የተጀመረውን ጥረት የበለጠ የሚያግዝና የሀገር ወስጥ የመድሃኒት አምራቾችን የሚያበረታታ መሆኑንም ነው ያነሱት። ኢትዮጵያ በመድሃኒትና በህክምና መሳሪያ ቁጥጥር የደረሰችበት ስኬት ለአፍሪካ ምሳሌ እንደሚሆንም ገልጸዋል።   የህብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለው ጠንካራ የጤና ቁጥጥር ስርዓት ለመፍጠር ተግባራዊ የሆኑ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል። ሚኒስትሯ ይህንን ደረጃ ለማሳካት ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ምስጋና አቅርበዋል። የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ በበኩላቸው፤ ከውጭ የሚገቡ መድሀኒቶችና ክትባቶች ዓለም አቀፍ ጥራትን፣ ብቃትንና ደህንነትን ያሟሉ እንዲሆኑ በቁርጠኝነት መሰራቱ ለውጤቱ መገኘት ምክንያት ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ለኢትዮጵያ የሦስተኛ ደረጃን ሲሰጥ በመድሃኒት የአቅርቦት ሰንሰለት ውስጥ ያለውን አሰራር በአግባቡ ፈትሾ መሆኑንም አንስተዋል። ኢትዮጵያ በህክምና መሳሪያ ቁጥጥር የዓለም ጤና ድርጅትን የብቃት ማረጋገጫ ለማግኘት በትኩረት እየሰራች ነው ብለዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ለሀገራት የደረጃ ሦስት ዕውቅና የሚሰጠው የተረጋጋ፣ የተቀናጀና በአግባቡ የሚመራ የቁጥጥር ስርዓት መኖሩን ሲያረጋግጥ ነው።
ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ልማት ላይ ያተኮሩ ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች ነው - ሚኒስትር አህመድ ሽዴ
Oct 2, 2025 58
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሰብዓዊ ልማት ላይ ያተኮሩ ውጤታማ ተግባራት እያከናወነች መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለጹ። በኢትዮጵያ መንግሥት እና በዓለም ባንክ በጋራ የተዘጋጀው የኢትዮጵያ የሰው ሃብት ልማት ፎረም 2025 የመንግሥት ከፍተኛ አመራር አባላትና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በተገኙበት በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።   "ክህሎቶችን መገንባት፣ ሥራዎችን ማቀላጠፍ፣ ልማትን ማፋጠን" በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ የሚገኘው ፎረም ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ቀናት ይቆያል። የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ በኢትዮጵያ በሰብዓዊ ልማት ላይ በትኩረት በመሰራቱ ውጤቶች ተገኝተዋል። አጠቃላይ የብልጽግና እድገት እይታው ሁለንተናዊ ብልጽግናን እውን ማድረግ መሆኑን ያመለከቱት ሚኒስትሩ፤ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ማረጋገጥ፣ ጠንካራ ሀገረ መንግስት መገንባት፣ የማህበራዊ ልማትን በተለይም የሰብዓዊ ልማትን ማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ ነው ብለዋል። ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለማህበራዊ ጥበቃ ዋስትና እና ለስራ እድል ፈጠራ ሰፊ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ እነዚህ ስራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ነው ያሉት። በከተማና በገጠር ውጤታማ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ያሉት ሚኒስትሩ በተለይም በትምህርት ልማት፣ በጤና ዘርፍ፣ የማህበራዊ ዋስትና ጥበቃን በማረጋገጥ በኩል በርካታ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑ ናቸው ብለዋል። በተጨማሪም የዜጎችን ክህሎት በማሳደግ ብቁ አምራች ለማድረግ እየተሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል። ሀገራት የሰብዓዊ ልማት ላይ ትኩረት በማድረግ ውጤታማ ስራዎችን ካከናወኑ ለኢኮኖሚ እድገታቸው ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያመለክታል ሲሉም ገልጸዋል። የሰብዓዊ ልማት ደረጃ በአደጉና በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት መካከል ልዩነት የሚፈጥር ዋና ጉዳይ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ በመከናወን ላይ ለሚገኙ ስራዎች የዓለም ባንክ በሁሉም ዘርፎች መዋዕለ ንዋይና የቴክኒክ ድጋፍ በማቅረብ ትልቁ አጋር መሆኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ የሰው ሃብት ልማት ፎረም ከዓለም ባንክ ጋር በጋራ መካሄዱ ሀገሪቱ የጀመረችውን ሁለንተናዊ ብልጽግና የበለጠ ውጤታማ የሚያደርግ ልምድ እንደሚገኝበትም አብራርተዋል።
ኢኮኖሚ
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ ናት - አሊኮ ዳንጎቴ
Oct 2, 2025 21
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ተመሯጯ የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን የዳንጎቴ ግሩፕ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ ገለጹ። ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ያለውን የኢንቨስትመንት ተደራሽነት የማስፋት ፍላጎት እንዳለውም አመልክተዋል። የዳንጎቴ ግሩፕ መስራች እና ዋና ስራ አስፈጻሚ አሊኮ ዳንጎቴ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ኢንቨስትመንትን በመሳብ በቀዳሚነት የምትጠቀስ ሀገር ናት ብለዋል። መንግስት ባደረጋቸው የሪፎርም ስራዎችና የኢኮኖሚው ለውጭ ኢንቨስትመንት ክፍት መሆን ለኢንቨስትመንት እድገት ትልቅ ድርሻ እንዳለው ገልጸዋል።   ኢትዮጵያ ቁልፍ ዘርፎች ለግሉ ዘርፍ ክፍት ማድረጓ ዓለም አቀፍ ኢንቨስትሮችን እንድትስብ ማድረጉን አመልክተዋል። የማክሮ ኢኮኖሚ እና ለኢንቨስምንት ምቹ የሆኑ ሪፎርሞች ኢትዮጵያ ለቢዝነስ ዝግጁ የሆነች ሀገር እንድትሆን ትልቅ ድርሻ ማበርከቱን ነው የገለጹት። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) መሪነት እየተከናወኑ ያሉ የመሰረተ ልማት ግንባታ ስራዎች የሚደነቁና የመንግስትን የመፈጸም አቅም አጉልቶ የሚያሳይ ነው ብለዋል። በቅርቡ የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ መንግስት ለኢነርጂ ደህንነት መረጋገጥና የኢንዱስትሪ እድገት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑንም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ አጠቃላይ ስራዎች ኢትዮጵያ በአፍሪካ በቀጣናውና በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ መግቢያ በር እንደሚያደርጋት ተናግረዋል። የዳንጎቴ ግሩፕ እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትምንት ሆልዲንግ አጋርነት በአፍሪካ ኢንዱስትሪ እድገት እና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ የጋራ ራዕይ ማሳካት የሚያስችል መሆኑን ነው ያብራሩት። የዳንጎቴ ግሩፕ ያለውን ልምድ በመጠቀም የጋራ ሽርክና ስራው ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ትራንፎርሜሽን እና የግብርና ምርማነት እድገት መሰረት እንዲሆን አበክሮ እንደሚሰራ ተናግረዋል። የማዳባሪያ ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ አልፎም የጎረቤት ሀገራትን የግብርና ትራንስፎርሜሽን እንደሚያረጋግጥ ነው የገለጹት። ዳንጎቴ ግሩፕ ዛሬ በሶማሌ ክልል ከሚገነባው የማዳበሪያ ፋብሪካ በተጨማሪ የተለያዩ የማዳባሪያ አይነቶች ማምረት የሚያስችለውን ኢንቨስትመንቶች የመጀመር ፍላጎት እንዳለው አመልክተዋል። የማዳበሪያ ፋብሪካው የኢትዮጵያን የማዳባሪያ ፍላጎት የሚያሟላና የምርት አቅምን እንደሚያሳድግ ተናግረዋል። የማዳበሪያ ፕሮጀክቱ ዳንጎቴ ግሩፕ በኢትዮጵያ ከሲሚንቶ በመጠቀል የተሰማራበት ዘርፍ መሆኑን ጠቅሰው ኩባንያው በኢትዮጵያ አሁን ያለውን የሲሚንቶ ምርት በእጥፍ የማሳደግ እቅድ እንዳለው ጠቁመዋል። ዳንጎቴ ግሩፕ የአፍሪካን ልማትና እድገት የሚያፋጥኑ ስራዎች ላይ መዋዕለ ንዋዩን ማፍሰስ እንደሚቀጥልም አክለዋል።
ለልጆቻችን የተሻለች ሀገር መስራት የኢትዮጵያውያን የሰርክ ስራ መሆን ይኖርበታል - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
Oct 2, 2025 32
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን ከፍታ እውን ማድረግና ለቀጣዩ ትውልድ የተሻለች ሀገር መስራት የዕለት ተዕለት ስራቸው ሊያደርጉት እንደሚገባ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) አስገነዘቡ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በሶማሌ ክልል ካሉብ በአመት 111 ሚሊዮን ሊትር ማምረት የሚችለውን የኦጋዴን ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት የመጀመሪያ ዙር መርቀው ወደ ስራ አስገብተዋል። በተመሳሳይም በአመት 1 ነጥብ 33 ቢሊዮን ሊትር የማምረት አቅም የሚኖረውን ሁለተኛውን ዙር ፕሮጀክትም አስጀምረዋል። የዩሪያ ማዳበሪያ እና የጎዴ ነዳጅ ማጣሪያ ፋብሪካዎች ግንባታ የመሰረት ድንጋይም አስቀምጠዋል።   ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በተመረቀ አንድ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ አመርቂና የኢትዮጵያን ብልጽግና የሚያረጋግጡ ስራዎች ዛሬ መጀመራቸውን አመልክተዋል። ስራዎቹን የስኬቶቻችን ማብሰሪያና የማንሰራራት መሻታችን አድርገን እንወስደዋለን ሲሉም ገልጸዋል። ለኢትዮጵያውያን ዛሬ ታላቅ ቀን ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፕሮጀክቶቹ እውን መሆን ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምስጋና አቅርበዋል። ዛሬ በሶማሌ ክልል የታየው ብርሃን በመላ ኢትዮጵያ እስኪረጋገጥና እያንዳንዱን ዜጋ ካለበት የድህነት አረንቋ አውጥቶ ወደ ሚገባቸው የብልጽግናና የልማት ደረጃ እስኪደርሱ ድረስ በትጋት መስራትና የተጀመረውን ማጠናቀቅ ይጠበቃል ነው ያሉት። እኛ እንጀምራለን፣ እኛ ተግተን እንሰራለን እናም እኛ እንጨርሳለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስራዎቻችን ሁሉ ኢትዮጵያን ከፍ እናደርጋለን ብልጽግናን እናረጋግጣለን ብለዋል።   ኢትዮጵያውያን ለታላላቅ ስራዎች በመደመር የኢትዮጵያን ስም የማስጠራት፣ ከፍታዋን የማረጋገጥና ለልጆቻችን የተሻለች ኢትዮጵያን መስራት የሰርክ ስራቸው መሆን ይኖርበታል ነው ያሉት። የኢትዮጵያ ብልጽግና እና የጀመረችውን ስራ መጨረስ የማይቆም መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም አካል በቀና ልብ ለሀገር ልማትና እድገት በጋራ እንዲሰራ አሳስበዋል። በሶማሌ ክልል የተበሰሩት ፕሮጀክቶች የብልጽግና ፓርቲ ሁሉን አቃፊነት በግልጽ የሚያመላክት መሆኑንም አመልክተዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የኢትዮጵያን ማንሰራራትና ብልጽግናን እውን ለማድረግ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አረጋግጠዋል።
በደብረማርቆስ ከተማ የሰፈነውን ሰላም በማስጠበቅ ልማትና እድገትን የሚያፋጥኑ ተግባራት እየተከናወኑ ነው - የከተማ አስተዳደሩ
Oct 2, 2025 47
ደብረ ማርቆስ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፡- በደብረማርቆስ ከተማ የሰፈነውን ሰላም አስጠብቆ ልማትና እድገት በማፋጠን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን የከተማው አስተዳደር ገለጸ። የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት የ2018 በጀት ዓመት 1ኛ ዙር መደበኛ ጉባዔውን ዛሬ ያካሄደ ሲሆን፤ በቀረበው የአስተዳደሩ የአሻጋሪ እና ዘላቂ የልማት እቅድ ላይ ውይይት አድርጓል።   በጉባዔው መድረክ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ እንደገለጹት፤ ሕብረተሰቡን ያሳተፈ ልማት በማካሄድ ሀገር ለማሻገር የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል። ለዚህም የከተማ አስተዳደሩ ያቀዳቸውን አሻጋሪና ዘላቂ የልማት እቅዶችን ከግብ ለማድረስ ሁሉን አቀፍ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። በግብርና፣ በቱሪዝም፣ በማዕድን፣ በኢንዱስትሪ፣ በትምህርት፣ በጤናና ሌሎች የልማት ዘርፎች በክልል ደረጃ የታቀደውን የ25 ዓመት እቅድ ወደ ከተማ አስተዳደሩ ለማውረድ እየተሰራ መሆኑንም አንስተዋል። በአካባቢው የሰፈነውን ሰላም አስጠብቆ በማፅናት የከተማውን ልማትና እድገት በማፋጠን የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል። ይህንን ለማሳካት በሚደረገው ጥረትም የምክር ቤት አባላት የተጠናከረ የድጋፍ ክትትል ማጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል። የምክር ቤቱ አባል ብዙአየሁ አያሌው፤ በአስተዳደሩ የቀረበው እቅድ የሚያሰራና የማሕበረሰቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ታሳቢ ያደረገ መሆኑን መመልከታቸውን ተናግረዋል። ይህ እቅድ ተግባራዊ እንዲሆንም ድጋፍና ክትትል በማድረግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል። ሌላው የምክር ቤቱ አባል ጌታቸው ህብስቱ ፤ እቅዱ የከተማዋን እድገት የሚያፋጥን በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ ገልጸዋል።    
በክልሉ የሌማት ትሩፋት መርሀግብር በእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፍ ውጤት እንዲመዘገብ እያስቻለ ነው - ቢሮው
Oct 2, 2025 43
ሾኔ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር በእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲጎለብት በማድረግ ውጤት እያስመዘገበ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ። በሀድያ ዞን ሾኔ ከተማ የዳልጋ ከብት ዝርያ ማሻሻል መርሃ ግብር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል፡፡ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ስሩር በወቅቱ እንደገለጹት መንግሥት የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፉን በማሻሻልና በማዘመን የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው፡፡   በክልሉ በተለይም ባለፉት አመታት ተግባራዊ እየተደረገ ባለው የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር የእንስሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ዘርፉን ለማሻሻልና ለማዘመን በተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። በዘርፉ ከተሰማሩ አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች ባለፈ ለሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት መጎልበት አስተዋጽኦ ያበረከቱ ውጤቶች መመዝገባቸውን አመልክተዋል። በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፍ የተገኘው አበረታች ውጤት ቀጣይነት እንዲኖረው የተቀናጀ ስራ ማከናወን አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው ከዝርያ ማሻሻል ስራው በተጓዳኝ የእንስሳት ጤና ማስጠበቅና የመኖ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።   የሀዲያ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶክተር ሀብታሙ ታደሰ በበኩላቸዉ፡- በዞኑ በሌማት ትሩፋት መርሀ ግብር ትግበራ ጋር በማስተሳሰር በእንስሳት ሀብት ልማት ዘርፉ እየተከናወኑ ባሉ ተግባራት ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን ተናግረዋል። በዚህም በርካታ የወተት፣ የንብና የማር መንደሮችን ማደራጀት መቻሉን ጠቅሰው ዘርፉ የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ከማረጋገጥ አንጻር ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል። ዝርያቸው የተሻሻሉ የወተት ላሞች በማርባታቸው ከወተትና ከወተት ተዋጽኦ ንግድ የተሻለ ገቢ ማግኘት መጀመራቸውን የተናገሩት በሾኔ ከተማ ነዋሪ አቶ አሰፋ ደንበል ናቸው። በዝርያ ማሻሻያ መርሀ ግብር ማስጀመሪያ ላይ የክልል፣ የዞንና የልዩ ወረዳ የግብርና መምሪያ ኃላፊዎች እንዲሁም የአካባቢው አርሶ አደሮች ተሳትፈዋል፡፡
ቪዲዮዎች
ሳይንስና ቴክኖሎጂ
አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለመዲናዋ የስማርት ሲቲ ግንባታ ጉልህ አበርክቶ ይኖረዋል
Oct 2, 2025 94
አዲስ አበባ፤ መስከረም 22/2018(ኢዜአ)፦ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በቴክኖሎጂ የታገዘ ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለመዲናዋ የስማርት ሲቲ ግንባታ ጉልህ አበርክቶ እንደሚኖረው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ገለጹ፡፡ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ለዜጎች በቴክኖሎጂ የታገዘ ፈጣን፣ ተአማኒ፣ ፍትሐዊና ተደራሽ የመንግስት አገልግሎት ለመስጠት ሚያዚያ 2017 ዓ.ም በፌደራል ደረጃ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል፡፡ ዜጎች በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ የሚገጥማቸውን እንግልትና የሚቀርቡ ቅሬታዎችን ሁሉም አካካቢ ለመፍታት አዲስ አበባን ጨምሮ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የራሳቸውን መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እያስጀመሩ ነው፡፡   የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዮናስ አለማየሁ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለዜጎች የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎትን ሥራ አስጀምሯል። የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በሥነ ምግባር የታነጹና ለሙያው በቂ ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎችን የያዘ መሆኑን ገልጸው፤ 13 የከተማ አስተዳደሩ ተቋማት በዲጂታል የታገዘ የተቀናጀ አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡ የተወሰኑ የፌደራል ተቋማትም በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን ጠቅሰዋል። ማዕከሉ ለዜጎች የተሟላ የመንግስት አገልግሎት በመስጠት የመዲናዋን ስማርት ሲቲ ግንባታ የሚያግዝና የዜጎችን ኑሮ የሚያሻሽል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በኢኮኖሚ፣ ቤቶችና ትራንስፖርት እንዲሁም መሬትና ግንባታ ዘርፎች ተከፋፍሎ የሚሰጥ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡   አገልግሎቱ በሁሉም ክፍለ ከተሞች እንዲዋቀር የሚያስችል አደረጃጀት እየተፈጠረ መሆኑን ጠቁመው፤ የቦሌ ክፍለ ከተማ የመሶብ አገልግሎት በቅርቡ ሥራ ይጀምራል ብለዋል፡፡ በአዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 107 የከተማ አስተዳደሩና የፌደራል ተቋማት አገልግሎቶች እየተሰጡ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡ ማዕከሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት የተሟላለት በመሆኑ ከሌብነትና ብልሹ አሰራር የጸዳ አገልግሎት መስጠት ያስችላል ብለዋል፡፡ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት ጳጉሜን 5 ቀን 2017 ዓ.ም ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት መደረጉ ይታወቃል።
ማዕከሉ ሰብልን በስብጥር የመዝራት የእርሻ ስነ-ዘዴን በማስተዋወቅ እንዲስፋፋ እያደረገ ነው
Oct 1, 2025 114
ሰቆጣ፤ መስከረም 21/2018 (ኢዜአ)፡- የሰቆጣ ግብርና ምርምር ማእከል ሰብልን በስብጥር የመዝራት የእርሻ ስነ-ዘዴን በማስተዋወቅ እንዲስፋፋ እያደረገ መሆኑን ገለፀ። በሰቆጣ ግብርና ምርምር ማእከል የማህበረሰብ ምጣኔ ሃብትና የግብርና ስርፀት ተመራማሪ አቶ አደመ ምህረቱ ለኢዜአ እንደገለፁት ማዕከሉ ሰብልን በስብጥር የመዝራት የእርሻ ስነ-ዘዴን በማስተዋወቅ እንዲስፋፋ እያደረገ ነው። በዚህም ሁለት ሰብሎችን በአንድ መሬት ላይ አሰባጥሮ በመዝራት የአርሶ አደሩን ተጠቃሚነት ለማጎልበት እየሰራ መሆኑን ተመራማሪው ገልፀዋል። በተለይም በመስመር በተዘራ ማሾና ቦሎቄ ሰብል ላይ እንቁ ዳጉሳን አሰባጥሮ በመዝራት ምርታማነትን ከእጥፍ በላይ ማሳደግ መቻሉን አስረድተዋል። በዚህም በአበርገሌና ዝቋላ ወረዳ በሚገኙ አምስት ቀበሌዎች ላይ 456 አርሶ አደሮች ሰብልን በስብጥር የመዝራት አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን አስረድተዋል። ቀደም ሲል አንድ አይነት ሰብል በሄክታር በመዝራት ይገኝ የነበረውን ዘጠኝ ኩንታል አማካይ ምርት አሁን ላይ ሁለቱን ሰብሎች አሰባጥሮ በመዝራት ከ20 ኩንታል በላይ ምርት ማግኘት ተችሏል ብለዋል። በተጨማሪም አካባቢው ዝናብ አጠር በመሆኑ በአንዱ ሰብል ላይ ጉዳት ሲከሰት በሌላኛው ሰብል በቂ ምርት በማስገኘት አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ያደረገ አሰራር መሆኑን አስረድተዋል። የዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አዲስ ወልዴ በበኩላቸው በያዝነው ክረምት በ70 ሄክታር መሬት ላይ በስብጥር አሰራር በኩታ ገጠም ሰብል ማልማት ተችሏል ብለዋል። በምርምር ማእከሉ በኩል እየተሰራ ያለው የስብጥር ሰብል ልማት የአርሶ አደሩን የስርዓተ ምግብ ክፍተትን በመሙላት ጤናማ ማህበረሰብን ለመፍጠር የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያስችል ነው ብለዋል። በዝቋላ ወረዳ የ02 ቀበሌ አርሶ አደር አብጨ መሰለ፤ በሰቆጣ ግብርና ምርምር የቀረበላቸው እንቁ የተሰኘውን የዳጉሳ ሰብል ከማሾ ጋር አሰባጥረው በመዝራት ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል። በወረዳው የ01 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ጅንን ገብሬ በበኩላቸው አንድ ሄክታር የእርሻ መሬታቸውን እንቁ ዳጉሳን ከማሾ ጋር በማሰባጠር መሸፈናቸውን ተናግረዋል። ባለፈው ዓመት ሰብልን በስብጥር በመዝራት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረው፤ ዘንድሮ አሰራሩን በስፋት ለመተግበር እንዲነሳሱ ማድረጉን አብራርተዋል።  
በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው
Sep 30, 2025 153
ጋምቤላ፤መስከረም 20/2018(ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ በማድረግ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ጠይባ ሀሰን ገለጹ። በጋምቤላ ክልል የሚገኙ ስደተኞችንና የአካባቢ ስደተኛ ተቀባይ ማህበረሰብ የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ የሚያደርግ መርሃ ግብር ዛሬ በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተካሂዷል።   በክልሉ በመገኘት መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ጠይባ ሀሰን፤ በኢትዮጵያ የሚገኙ ስደተኞችን የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ በተጠናከረ መልኩ ይቀጥላል ብለዋል። የአገልግሎቱ መጀመር ለስደተኞቹ አስፈላጊውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ሲሉም ገልጸዋል። የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እንደ ሀገር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተተገበረ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ዲጂታል መታወቂያውን ዜጎች በብዙ መልኩ እየተገለገሉበት ስለመሆኑ ተናግረዋል። በኢትዮጵያም በተለያዩ አካባቢዎች የተለያዩ አገራት ስደተኞች መኖራቸውን አንስተው፤ የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ በማድረግ የተሳለጠ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችላቸውን መታወቂያ የመስጠት ስራ ጀምረናል ብለዋል። በኢትዮጵያ ተጠልለው ለሚገኙ ስደተኞች የሚሰጠው የዲጂታል መታወቂያ የስደተኞችን ማንነት በሚገልጽ መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው በዛሬው እለት በጋምቤላ ክልል ኢታንግ ልዩ ወረዳ በይፋ መጀመሩን ገልጸዋል። የአገልግሎት መስሪያ ቤቱ ጋምቤላን ጨምሮ በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች የሚገኙ ስደተኞችንና የስደተኛ ተቀባይ ማህበረሰብ የዲጂታል መታወቂያ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት የሚሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ለመርሃ ግብሩ ስኬታማነት የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር እንዲጠናከርም ዋና ዳይሬክተሯ ጠይቀዋል። የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የምዝገባ ዘርፍ ኃላፊ ሄኖክ ጥላሁን፤ መንግስት በያዘው የእድገትና የለውጥ ምዕራፍ አንዱና አስቻይ ተግባር የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ መሆኑን ተናግረዋል።   በዚህም መሰረት እስካሁን ከ25 ሚሊዮን በላይ ዜጎች፣ በህጋዊ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች እና ስደተኞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቅሰዋል። በተያዘው በጀት ዓመትም የሀገሪቱን ዜጎች፣ በህጋዊ መንገድ የሚኖሩ የውጪ ዜጎችና ስደተኞችን በመመዝገብ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የማድረግ ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ብለዋል።   የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተወካይ ላክዴር ላክባክ በበኩላቸው፤ የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ዘመኑ ለሚጠይቀው የተሳለጠ አገልግሎት አበርክቶው የጎላ መሆኑን ገልጸው በክልሉ በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን ተናግረዋል።
የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎትን በማበልጸግ የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቷል
Sep 30, 2025 118
ባሕርዳር፤ መስከረም 20/2018 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል የቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎትን በማበልጸግ የተጀመረውን የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ አስታወቀ። ቢሮው በኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የወጣቶችን ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግና ለማጠናከር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ዜጎች በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልጸግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊ የዲጂታል ክህሎት እንዲኖራቸው ለማስቻል የአምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያን ኮደርስ ስልጠና በሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ማስጀመራቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም በርካታ ወጣቶች አቅማቸውን ለማሳደግ፣ ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠርና ዘመኑን የዋጀ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ክህሎትን ለማሳደግ ስልጠናውን በኦን ላይ እየወሰዱ ይገኛሉ። የአማራ ክልልም ስልጠናውን አጠናክሮ በማስቀጠል ሂደት ላይ የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትል ኃላፊ የቻለ ይግዛው ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል። በመግለጫቸውም ወጣቱን በቴክኖሎጂ እውቀትና ክህሎት በማበልጸግ የተጀመረውን የዲጅታል ኢኮኖሚ እድገት አጠናክሮ ለማስቀጠል ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል። በበጀት አመቱ ስልጠናውን አጠናክሮ ለማስቀጠልም ካለፈው በጀት ዓመት ተሞክሮ በመውሰድ 268ሺህ ወጣቶች የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ አስታውቀዋል። ስልጠናውን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 197 ወጣቶች ስልጠናውን እንዲወስዱ መደረጉን አስታውሰዋል። ይህም ክንውን ከእቅድ በላይ እንደሆነ ጠቅሰው፤ ከዕቅድ በላይ ማሳካት የተቻለው በዝግጅት ምዕራፍ ኮሚቴዎችን በማቋቋምና የማሰልጠኛ ተቋማትን በማደራጀት ወደ ስራ በመግባት እንደሆነ አስረድተዋል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠናው በዩኒቨርሲቲዎች፣ በቴክኒክና ሙያ ተቋማትና በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሰጥ የማመቻቸት ተግባር መከናወኑን አንስተዋል። ስልጠናው ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲጂታል ቴክኖሎጅ ተወዳዳሪ በማድረግ ዘላቂ እድገት ለማሳለጥ ያለመ መሆኑን አንስተዋል። ወጣቶችም ዘመኑ የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት በመቅሰም በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ የሚያደርጋቸውን ስልጠና እንዲወስዱ መልዕክት አስተላልፈዋል።    
ስፖርት
በሻምፒዮንስ ሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ ፒኤስጂ ባርሴሎናን አሸነፈ
Oct 1, 2025 117
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018 (ኢዜአ)፦ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ሁለተኛ መርሃ ግብር ፒኤስጂ ከመመራት ተነስቶ ባርሴሎናን 2 ለ 1 አሸንፏል። ማምሻውን በሉዊስ ካምፓኒስ ኦሊምፒክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌራን ቶሬስ በ19ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ባርሴሎና መሪ ሆኗል። ሴኒ ማዩሉ በ38ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈው ጎል የወቅቱን የውድድሩ አሸናፊ ፒኤስጂን አቻ አድርጓል። ጎንዛሎ ራሞስ በ90ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል የፈረንሳዩን ቡድን አሸናፊ ሆኗል። የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በጣም አዝናኝ እና ማጥቃት ላይ የተመሰረተ ነበር።   በሌሎች ጨዋታዎች አርሰናል በጋብርኤል ማርቲኔሊ እና ቡካዮ ሳካ ጎሎች ኦሎምፒያኮስን 2 ለ 0 አሸንፏል። ማንችስተር ሲቲ ከሜዳው ውጪ ከሞናኮን ጋር ሁለት አቻ ተለያይቷል። አርሊንግ ሃላንድ ሁለት ጎሎች አስቆጥሯል።   ጆርዳን ቴዜ በጨዋታ እና ኤሪክ ዳየር በፍጹም ቅጣት ለሞናኮ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። ቦሩሲያ ዶርትሙንድ አትሌቲኮ ቢልባኦን 4 ለ 1፣ ናፖሊ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 2 ለ 1 አሸንፈዋል። ቪያሪያል ከጁቬንቱስ ሁለት አቻ ሲለያዩ ባየር ሌቨርኩሰን እና ፒኤስቪ አይንድሆቨን ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል። አስቀድመው ዛሬ በተደረጉ ጨዋታዎች ኒውካስትል ዩናይትድ ዩኒየን ሴይንት ጊሎይስን 4 ለ 0፤ ካራባግ ኤፍሲ ኮፐንሃገንን 2 ለ 0 አሸንፈዋል።
ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የብስክሌት ውድድር ታስተናግዳለች 
Oct 1, 2025 99
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018(ኢዜአ)፦ዓለም አቀፍ የከተማ ተራራ ላይ የብስክሌት ውድድር (City Mountain Bike Race) በመጋቢት ወር በኢትዮጵያ እንደሚካሄድ የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን አስታወቀ። ውድድሩ ከመጋቢት 20 እስከ 22 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ይደረጋል። የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 98ኛው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና ላይ የነበራትን ተሳትፎ እና ቀጣይ ስራዎች አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።   የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የአፍሪካ ብስክሌት ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል አቶ ወንድሙ ኃይሌ ዓለም አቀፍ የከተማ ተራራ ላይ ብስክሌት ውድድሩ በአፍሪካ ሲካሄድ የመጀመሪያ መሆኑን ገልጸዋል። በውድድሩ ላይ ከ25 ሀገራት የተወጣጡ ከ110 በላይ ብስክሌተኞች እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን የሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ ሀገራት ከተሳታፊዎቹ መካከል እንደሚገኙበትም አመልክተዋል። ውድድሩ ዓለም አቀፉ የብስክሌት ህብረት (UCI) የውድድር መርሃ ግብር ውስጥ የተካተተ እና እውቅና ያለው መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ ውድድሩን ለማዘጋጀት የሚያስችል ዝግጅት መጀመሯንና መንግስት ለዝግጅቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል። ዓለም አቀፍ ውድድሩ በኢትዮጵያ መደረጉ ሀገሪቷ በአፍሪካ ደረጃ በብስክሌት ስፖርት እያስመዘገበች ያለው አመርቂ ውጤት ማሳያ እንደሆነም ነው ፕሬዝዳንቱ የገለጹት።
ኢትዮጵያ በዓለም ብስክሌት ሻምፒዮናው አፍሪካን ያኮራ ውጤት አስመዝግባለች - የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን
Oct 1, 2025 147
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና አፍሪካን ያኮራ ውጤት ማስመዝገቧን የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን አስታወቀ። ፌዴሬሽኑ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተካሄደው 98ኛው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያ የነበራትን ተሳትፎና ቀጣይ ስራዎች አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።   ከመስከረም 11 እስከ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በተካሄደው ሻምፒዮና ከ108 ሀገራት የተውጣጡ 769 ብስክሌተኞች በ13 የውድድር አይነቶች ተሳትፈዋል። ኢትዮጵያ በአምስት የውድድር አይነቶች ተሳትፋ ከአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚውን ስፍራ ይዛ አጠናቃለች። የግል ሰዓት ሙከራ፣ የጎዳና ላይ ውድድርና ድብልቅ ሪሌይ ውድድሮች ላይ ተሳትፋለች። የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ኃላፊ ፍጹም ወልደአብ 15 አባላት የያዘ ልዑክ ቡድን በብስክሌት ሻምፒዮና ላይ መሳተፉን ገልጸዋል። ለዓለም የብስክሌት ሻምፒዮና አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውንም አመልክተዋል። በኬንያ የተካሄደው የአፍሪካ ብስክሌት ሻምፒዮናና በቱር ሩዋንዳ የብስክሌት ውድድር ለዓለም ሻምፒዮናው እንደ መዘጋጃ ያገለገሉ ውድድሮች ናቸው ብለዋል። ዓለም አቀፉ የብስክሌት ማህበር(ዩሲአይ) ባዘጋጃቸው የስልጠና እድሎች ኢትዮጵያውያን ብስክሌተኞች በኬንያ፣ ፈረንሳይ እና ደቡብ አፍሪካ የስልጠና እድሎች ማግኘታቸውን ጠቁመዋል።   በመቀሌ በተካሄደው የኢትዮጵያ ብስክሌት ሻምፒዮና ላይ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ ብስክሌተኞች በሻምፒዮናው ላይ መሳተፋቸውን ነው ኃላፊው የገለጹት። ፅጌ ካህሳይ እ.አ.አ በ2028 በሎስ አንጀለስ በሚካሄደው 34ኛው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች የብስክሌት ውድድር ዝግጅት የስልጠና እድል ማግኘቷ ተጠቃሽ ነው ብለዋል። አጠቃላይ የነበረው ዝግጅት ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው የተሻለ ውጤት እንድታገኝ ማስቻሉን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ብስክሌት ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት እና የአፍሪካ ብስክሌት ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ወንድሙ ኃይሌ ኢትዮጵያ በኪጋሊ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አፍሪካን ያኮራ ውጤት ማስመዝገቧን ገልጸዋል። በዓለም ብስክሌት ሻምፒዮናው ኢትዮጵያ ሚኒማ ያሟሉ በርካታ ብስክሌተኞች ማሳተፏን አመልክተዋል።   108 ሀገራት በተሳተፉበት ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በአምስት የውድድር አይነቶች በመሳተፍ በጎዳና ላይ ውድድር ከዓለም 7ኛ ከአፍሪካ 1ኛ፤ በግል የሰዓት ሙከራ ውድድር ከዓለም 24ኛ ከአፍሪካ 1ኛ፤ በድብልቅ ሪሌይ ውድድር ከዓለም 10ኛ ከአፍሪካ 1ኛ በመሆን በአጠቃላይ ውጤት ከዓለም 7ኛ ከአፍሪካ 1ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች። በሩዋንዳ ኪጋሊ የተካሄደው 98ኛው የዓለም ብስክሌት ሻምፒዮና በአፍሪካ ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
አካባቢ ጥበቃ
ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርኩላር ኢኮኖሚን በመተግበር ለአካባቢ ተስማሚ  ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት ቁርጠኛ ናት
Oct 1, 2025 91
አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018(ኢዜአ)፦ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርኩላር ኢኮኖሚን በመተግበር ለአካባቢ ተስማሚ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት ቁርጠኛ መሆኗን የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ ገለጹ። ባለስልጣኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰርኩላር ኢኮኖሚ መድረክን አካሂዷል።   የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሌሊሴ ነሜ በዚሁ ወቅት፤ ብሔራዊ ሰርኩላር ኢኮኖሚ ለአካባቢ ምቹ የሆኑ ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት፣ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ላይ የተመሰረቱ የስራ እድሎችን ለማስፋት፣ የሴቶችና ወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማጠናከር ወሳኝ መሰረት ነው ብለዋል። ብሔራዊ ሰርኩላር ኢኮኖሚ ሀብትን በአግባቡ ጥቅም ላይ የማዋል፣ ቆሻሻን መልሶ የመጠቀም አቅምን በማጠናከር አካባቢ ላይ ጉዳት የማያስከትል የኢኮኖሚ እድገትን ለማረጋገጥና ጽዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተናግረዋል። ለስኬቱም ብሔራዊ የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ይፋ መደረጉን ጠቅሰው፥ ለፍኖተ ካርታው ትግበራ መንግስት ቁርጠኛ መሆኑን በማንሳት፥ የግሉ ዘርፍና የአጋር አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል።   በጽዱ ኢትዮጵያ ዘመቻ ባለፉት አራት ወራት ብቻ ከ30 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ያሳተፉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ንቅናቄዎች መከናወናቸውን ጠቁመው በቀጣይ ሁለት ወራት ከ50 ሚሊየን በላይ ዜጎችን ለማሳተፍ መታቀዱን ጠቁመዋል። የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ሔለን ደበበ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ሰርኩላር ኢኮኖሚ መድረክን እንድታካሂድ መመረጧ ሀገሪቱ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ግንባታ እያስመዘገበች ላለው ውጤታማነት እውቅና የሰጠ ነው ብለዋል።   የሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታው ለአካባቢ ብቻ ሳይሆን ለስትራቴጂክ ልማት እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። አዳዲስ የእሴት ሰንሰለቶችን ለመፍጠር፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶች ጥገኝነትን ለመቀነስ የከተማና የገጠር ማህበረሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ እድሎችን የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል። ለፍኖተ ካርታው ትግበራ በትኩረት እንደሚሠራ ጠቅሰው አፍሪካውያን በአንድነት የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አካታች ኢኮኖሚ መገንባት እንችላለን ነው ያሉት። በኢትዮጵያ የፊንላንድ አምባሳደር ሲኒካ አንቲላ ፊንላንድ የመጀመሪያውን ፍኖተ ካርታ ተግባራዊ ያደረገች ሀገር መሆኗን ገልጸው በዘርፉ ያላትን የበርካታ አመታት ልምድ ለማካፈል ዝግጁ ናት ብለዋል።   ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰርኩላር ኢኮኖሚን ማሳካት ብቻ ሳይሆን በዘርፉ ግንባር ቀደም በመሆን ለሌሎችም አርአያ የመሆን አቅም እንዳላት ተናግረዋል። በጀርመን የልማት ተራድኦ ደረጅት የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ ፕሮግራም ማናጀር ጀምስ ኔጅሩ ብሔራዊ ሰርኩላር ኢኮኖሚ ፍኖተ ካርታ ውጤታማ እንዲሆን በጋራ መስራት ያስፈልገናል ብለዋል።   ኢትዮጵያ ቆሻሻን መልሶ በመጠቀም ረገድ በአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ለሌሎችም አርአያ እንደምትሆን እምነታቸውን ገልጸዋል። ሰርኩላር ኢኮኖሚ ( መልሶ መጠቀም ) ለአካባቢ፣ ለኢኮኖሚ፣ ለኢንዱስትሪ እድገት ፤ ለወጣቶችና ለሴቶች ሰፊ የስራ እድል መፍጠር የሚያስችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡
የፕላስቲክ አምራቾች ከብክለት የጸዳ የአመራረት ሥርዓት እንዲከተሉ ድጋፍ ይደረጋል - የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን
Sep 25, 2025 400
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 15/2018(ኢዜአ)፦የፕላስቲክ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከብክለት የጸዳ የአመራረት ሥርዓት እንዲከተሉ የተቀናጀ ድጋፍ እንደሚደረግ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ። የኢፌዴሪ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ዙሪያ ከፕላስቲክ ከረጢት አምራች ኢንዱስትሪና ባለድርሻ አካላት ጋር የምክክር መድረክ አካሂዷል።   በዚሁ ጊዜ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ፤ የሕግ ማሻሻያን ጨምሮ ጽዱ ኢትዮጵያን እውን ማድረግ የሚያስችሉ አስቻይ ሁኔታዎች ተፈጥረዋል ብለዋል። በቅርቡም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ የጸደቀው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ የፕላስቲክ ምርቶችን ሙሉ ለሙሉ የሚከለክል እንዳልሆነ አስረድተዋል። አዋጁም ከአፈር ጋር ሳይዋሃዱ ለበርካታ ዓመታት ቆይተው ብክለትን የሚያስከትሉ የፕላስቲክ ምርቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገቡ የሚከለክል ድንጋጌ መያዙን ገልጸዋል። በዚህም የፕላስቲክ አምራቾች በተሻሻለው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ መሰረት ምርቶቻቸውን ተመልሶ ጥቅም በሚሰጡ ዕቃዎች መቀየር እንደሚኖርባቸው አስገንዝበዋል። የውይይቱ ተሳታፊ ፕላስቲክ አምራቾች በበኩላቸው፤ የተሻሻለው የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ የአካባቢ ብክለትን በመቀነስ የዜጎችን ጤንነት መጠበቅ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል። በአዋጁ የትግበራ ሂደትም አካባቢን የማይበክል የምርት ሥርዓትን በመከተል ተመልሰው ጥቅም የሚሰጡ ዕቃዎችን ለማምረት የዝግጅት ጊዜ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ንጉሱ ለማ፤ የፕላስቲክ ምርቶች የአካባቢ ብክለትን በማስከተል ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ያስከትላሉ ብለዋል።   ለዚህም በቶሎ የማይበሰብሱ ፕላስቲክ ምርቶች ላይ ዕገዳ መጣል ለአካባቢ ደኅንነት ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል። የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ፍሬነሽ መኩሪያ በበኩላቸው፤ በአዋጁ የትግበራ ሂደት ፕላስቲክ አምራቾች ለሚያጋጥማቸው ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።   የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ለሊሴ በማጠቃለያ ሃሳባቸው፤ ለአንድ ጊዜ ብቻ ጥቅም የሚሰጡ ፕላስቲክ አምራቾችን በገበያ ትስስርና ልምድ ልውውጥ ለማበረታታት ድጋፍ ይደረጋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ የአየር ጥራትን ለማሻሻል እየወሰደች ያለው እርምጃ እና ቁርጠኝነቷ የሚደነቅ ነው
Sep 25, 2025 337
አዲስ አበባ፤ መስከረም 15/2018(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ የአየር ጥራትን ለማሻሻል እየወሰደች ያለው እርምጃ እና ያላት ጠንካራ ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው ሲል ዓለም አቀፉ የምርምር ተቋም የስቶክሆልም ኢንቫይሮመንት ኢኒስቲትዩት ገለጸ። የአየር ጥራት አየር ምን ያህል ከብክለት ነጻ ነው? የሚለው የሚለካበት መንገድ ነው። ሀገራት እና ተቋማት የአየር ጥራት መለኪያዎችን በማዘጋጀት አየሩ ንጹህ ነው ወይስ ተበክሏል የሚለውን በመመዘን ጥራቱን ለማሻሻል ይሰራሉ። የአየር ጥራት መሻሻል የበሽታ ተጋላጭነት ለመቀነስ፣ ለከባቢ አየር ጥበቃ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ወሳኝ ሚና አለው። እ.አ.አ በ1989 የተመሰረተው የስቶክሆልም ኢንቫይሮመንት ኢኒስቲትዩት የአየር ንብረት፣ ከባቢ አየር እና የዘላቂ ልማት ፈተናዎች እንዲፈቱ በጥናት እና ምርምር ሳይንሳዊ ምክረ ሀሳቦችን በማቅረብ የመፍትሄ ሀሳቦችን ያቀርባል፤ የአቅም ግንባታ ድጋፍ ያደርጋል። ዓለም አቀፍ የሳይንስ ፖሊሲ ተቋሙ ከሚያደርጋቸው ድጋፎች መካከል ሀገራት የአየር ጥራት እንዲያሻሻሉ ማገዝ ነው። የስቶክሆልም ኢንቫይሮመንታል ኢኒስቲትዩት የአየር ጥራት ባለሙያ እና ተመራማሪ ንጎንጋንግ ዋንጂ ዳኑብ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ኢትዮጵያ የአየር ጥራትን ለማሻሻል ያላትን ጠንካራ ቁርጠኝነት አድንቀዋል። ኢትዮጵያ የአየር ጥራትን አስመልክቶ በየጊዜው መረጃን በማሰባሰብ ብክለትን አስቀድሞ ለመከላከል እያከናወነች ያለው ስራ አበረታች ነው ብለዋል። በተቋም ደረጃ መረጃዎችን ለፖሊሲ ግብአትነት ለማዋል ያለውን ቁርጠኝነትም አድንቀዋል። የአየር ጥራት አስተዳደር እና የጥራት መቆጣጠሪያ እቅድ ማዘጋጀት የአየር ብክለትን አስቀድሞ ለመከላከል እንደሚያስችል ተናግረዋል። ኢኒስቲትዩቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በመዲናዋ የአየር ጥራት መረጃን በማሳባሰብና የአየር ጥራት ቁጥጥር እያከናወነ ያለው ስራ እየደገፈ እንደሚገኝ ነው ባለሙያው የገለጹት። የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት የሚያበለጽጋቸውን ቴክኖሎጂዎች ጨምሮ ኢትዮጵያ በተለያዩ ተቋማት ውስጥ ያሏትን አቅሞች የአየር ጥራት መረጃዎችን በየጊዜው በመሰብሰብ ብክለትን ለመቀነስ አበክራ መስራት እንዳለባት መክረዋል። የአየር ጥራትና የአየር ንብረት መረጃዎች በተቀናጀ መልኩ በመጠቀም ብክለትን መከላከል ላይ ሁሉን አቀፍ ውጤት ለማምጣት መስራት እንደሚገባ አመልክተዋል። የስቶክሆልም ኢንቫይሮመንታል ኢኒስቲትዩት ኢትዮጵያን ጨምሮ ለአፍሪካ ሀገራት የአየር ጥራት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ነው የገለጹት። በብሄራዊ የአየር ጥራት መለኪያዎች ቀረጻ እና ትግበራ የፖሊሲና አቅም ግንባታ ድጋፍ እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰዋል። የአፍሪካ ሀገራት የአየር ጥራት መረጃዎቻቸውን ከብሄራዊ የአየር ንብረት አገልግሎቶች ማዕቀፍ ጋር በማስተሳሰር ላይ እንደሚገኙም ነው ባለሙያው ያብራሩት። ሀገራት በአየር ትንበያ ጣቢያዎቻቸው ከአየር ንብረት መረጃዎቻቸው ጋር የአየር ጥራት መረጃዎችን አጣምሮ በመጠቀም የሚፈለገውን ውጤት ለማምጣት እንዲሰሩና ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ የሚያደርጉትን ሽግግር እንዲያፋጥኑ አሳስበዋል። አፍሪካውያን የአየር ጥራት ጉዳይን በተቋማማዊ መዋቅር እና ፖሊሲ ማዕቀፍ ውስጥ ለማካተት የጀመሩትን ስራ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ልማት የሀገር በቀል የፋይናንስ ምንጮችን መጠቀሟ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው
Sep 24, 2025 431
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2018(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ለአረንጓዴ ልማት ስራዎቿ የሀገር በቀል የፋይናንስ ምንጮችን መጠቀሟ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ተግባር መሆኑን ግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት የተሰኘ ዓለም አቀፍ ተቋም አስታወቀ። ኢኒስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ አረንጓዴ እድገት የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥልም ገልጿል። ግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት እ.አ.አ በ2012 የተቋቋመ ዓለም አቀፍ የበይነ መንግስታት ተቋም ሲሆን በማደግ ላይ ለሚገኙ ሀገራት አረንጓዴ እና ዘላቂ እድገትን እንዲያረጋግጡ ድጋፍ ያደርጋል። ኢኒስቲትዩቱ በዓለም ዙሪያ 52 አባል ሀገራት ያሉት ሲሆን ኢትዮጵያን ጨምሮ 11 የአፍሪካ ሀገራትን አካቷል። የግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት የአፍሪካ ቀጣና ዳይሬክተር ካትሪና ሲንግላኪስ ኢኒስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ጋር በአረንጓዴ እድገት እና ልማት በትብብር እየሰራ እንደሚገኝ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ኢንስቲትዩቱ ለኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ ትግበራ ከ10 ዓመት በላይ ድጋፍ ማድረጉን በማሳያነት ጠቅሰዋል። በስትራቴጂው አማካኝነት በርካታ ለውጦች መምጣታቸውን ገልጸው የተራቆቱ መሬቶች መልሰው ማገገም እና በመላው ኢትዮጵያ የተካሄዱ የችግኝ ተከላ ስራዎችን ያመጡትን ውጤት በማሳያነት ጠቅሰዋል። ኢንስቲትዩቱ በስትራቴጂው ቀረጻ እና ትግበራ፣ የአቅም ግንባታ እና ስትራቴጂውን ለሚተገብሩ ተቋማት የቴክኒክ ድጋፎችን ማድረጉን አመለክተዋል። የታዳሽ ኃይል ልማት፣ በጥምር ደን ግብርና (አግሮ ፎረስትሪ) እንዲሁም የግብርና ምርታማነት ማሳደግ ስራን ከአይበገሬ አቅም ግንባታ እና የበካይ ጋዝ ቅነሳ ጋር በማስተሳሰር ለሚከናወኑ ስራዎች ድጋፍ መስጠቱን ነው ዳይሬክተሯ ያብራሩት። በሌላ በኩል ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ አማካኝነት እያከናወነች ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፤ በተለይም የፖለቲካ ቁርጠኝነት እና አመራር ሰጪነቱ ለውጤታማነቱ ወሳኝ ሚና መጫወቱን አመልክተዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ አሻራ የራሷን የፋይናንስ እና የሰው ሀብት አቅም ከአጋሮች የቴክኒክ ድጋፎች በማጣመር ያከናወነችው ስራ ተጨባጭ ውጤት ማምጣቱን ገልጸዋል። ለአረንጓዴ አሻራ ኢትዮጵያ ሀገር በቀል የፋይናንስ አማራጮችን መጠቀሟ ለሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል። ኢትዮጵያ ወደ አረንጓዴ ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የሚያስችሏትን ኢኒሼቲቮች እየተገበረች መሆኑን የገለጹት ዳይሬክተሯ ሀገር በቀል የፋይናንስ ሀብቶችን በመጠቀም አርንጓዴ እድገት ለማምጣት እያከናወነች ያለው ስራ የሚደነቅ መሆኑንም ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ልማት ስራዎች ማህበረሰቡን በንቃት ማሳተፏ የሚፈለገውን ለውጥ ለማምጣት እንደሚያስችል ነው የገለጹት። በተለይም የወጣቶች ተሳትፎ እያደገ መምጣት ለአረንጓዴ እድገት እና ዘላቂ ልማት ያለው አበርክቶ ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው የኢትዮጵያን መጪ ጊዜ የተሻለ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። ግሎባል ግሪን ግሮውዝ ኢኒስቲትዩት ኢትዮጵያን ጨምሮ አረንጓዴ ሽግግር እያደረጉ ለሚገኙ የአፍሪካ እና በማደግ ላይ የሚገኙ ሀገራት የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ዜናዎች
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አፍሪካ በዓለም መድረክ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት ድጋፉን ሊሰጥ ይገባል- አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ
Sep 24, 2025 508
አዲስ አበባ፤ መስከረም 14/2018(ኢዜአ)፦ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ አፍሪካ በዓለም መድረክ ፍትሃዊ ውክልና እንዲኖራት እያደረገችው ላለው ጥረት ድጋፍ እንዲሰጥ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ ጥሪ አቀረቡ። 80ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ በድርጅቱ ዋና መቀመጫ ኒውዮርክ እየተካሄደ ይገኛል። የጠቅላላ ጉባኤው አካል የሆነ ከፍተኛ የምክክር እና ክርክር መድረክ ዛሬ በኒው ዮርክ ተጀምሯል። “'ደህናነት በአብሮነት፤ 80 ዓመታት እና ከዚያ በላይ ለሰላም፣ ለልማት እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ” በሚል መሪ ሀሳብ ነው ጉባኤው የሚካሄደው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ሊቀ መንበር አምባሳደር ሳልማ ማሊካ ሃዳዲ “እየተለወጠ ባለው የዓለም የፖለቲካ ስርዓት ውስጥ የአፍሪካ ምልከታዎች” በሚል መሪ ሀሳብ ለጉባኤው ተሳታፊዎች የቪዲዮ መልዕክት አስተላልፈዋል። አምባሳደር ሳልማ በመልዕክታቸው አፍሪካ በተለያዩ መስኮች ራሷን ለመቻል እያከናወነቻቸው ያሉ ስራዎች ፍሬ እያፈሩ መሆናቸውን ገልጸዋል። አፍሪካ የደህንነት ጉዳዮች በራሷ ፋይናንስ በማድረግ ረገድ ለውጥ ማምጣቷን በማሳያነት ጠቅሰው የአፍሪካ የሰላም እና ደህንነት ማዕቀፍ በአፍሪካውያን ገንዘብ እና ባለቤትነት እየተመራ እንደሚገኝም አመልክተዋል። የአፍሪካ ህብረት የሰላም ፈንድ በአፍሪካውያን በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በትግበራ ላይ መሆኑን አንስተዋል። አምባሳደሯ በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ላይ ያላቸውን ሀሳብ ያጋሩ ሲሆን የንግድ ቀጣናው ዜጎች እና ገበያን ከማስተሳሰር ባለፈ ሰው ሰራሽ ድንበሮች በእኛ ላይ ከመጫናቸው በፊት የነበረውን የንግድ ትስስር እና ትብብር እንደሚመለስ ተናግረዋል። አፍሪካ በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ ያላት ድርሻ እያደገ መምጣቱን ገልጸው አህጉሪቷ በቡድን 20 ቋሚ መቀመጫ ማግኘቷ አበይት ማሳያ ነው ብለዋል። አፍሪካ በቡድን 20 ውስጥ ያገኘችው ቋሚ መቀመጫ ለዓለም ችግሮች መፍትሄ ያላትን አይተኬ ሚና በግልጽ የሚያመላክት እንደሆነም ተናግረዋል። እየተለወጠ ያለው የዓለም ስርዓት ለአፍሪካ በርካታ እድሎችን ይዞ መጥቷል ያሉት ምክትል ሊቀመንበሯ ይህን መልካም አጋጣሚ ለመጠቀም እየተሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል። አምባሳደር ማሊካ ዓለም አቀፍ አጋሮች አፍሪካ የዓለም የፋይናንስ ስርዓት እኩልነት የሰፈነበት እንዲሆን እና በተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ምክር ቤት ውክልና እንድታገኝ እያነሳች ያለው ፍትሃዊ ጥያቄ እና እውነተኛ መሻት እንዲደግፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ኢዜአ ከአፍሪካ ህብረት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። አፍሪካ ከዓለም ጋር ያላት ትብብር በጋራ መከባበር እና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረተ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸው አፍሪካ ስታድግ የዓለም ብልጽግና እና መረጋጋት ይረጋገጣል ሲሉም ተናግረዋል።
አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት አለባቸው- አንቶኒዮ ጉቴሬዝ
Sep 23, 2025 439
አዲስ አበባ፤ መስከረም 13/2018 (ኢዜአ)፡- የተባበሩት መንግሥታት አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ገለጹ። 80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ በይፋ ተከፍቷል።   በፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድንም በ80ኛው የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈ ነው። በመክፈቻ ሥነ-ሥርዓቱ ላይም የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ንግግር አድርገዋል። በንግግራቸውም፤ አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።   የተባበሩት መንግሥታትን ሥርዓትና መዋቅር ለ21ኛው ክፍለ ዘመን በሚመጥን ልክ መለወጥ እንደሚገባም በአጽንኦት ገልጸዋል። የዓለም ኀብረተሰብ ምርጫውን ሠላም፣ ፍትሕ ዘላቂ ልማት እና ሰብዓዊ ክብር ሊያደርግ እንደሚገባ አስገንዝበው፤ ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነትን እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል።
ኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት ለማጠናከር የጋራ ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ
Sep 22, 2025 452
አዲስ አበባ፤ መስከረም 12/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና የአውሮፓ ህብረት በተለያዩ መስኮች ያላቸውን አጋርነት የበለጠ ለማጎልበት እንደሚሰሩ አስታወቁ። የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ምክትል ዋና ፀሐፊ መሐመድ አብዲ ዋሬ ከአዲሱ የአውሮፓ ህብረት የትብብር ኃላፊ ጌራልድ ሃልተር ጋር በጅቡቲ ተወያይተዋል። ውይይቱ ኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት በሰላም፣ ደህንነት፣ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አቅም ግንባታ፣ የምግብ ዋስትና እና በስደተኞች ጉዳይ ላይ ያላቸውን ትብብር ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው። ሁለቱ ወገኖች አጋርነታቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ መግለጻቸውን ኢዜአ ከኢጋድ ሴክሬታሪያት ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ኢጋድ እና የአውሮፓ ህብረት እ.አ.አ 2008 አጋርነት መመስረታቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሁለቱ ተቋማት እ.አ.አ ሜይ 2025 ላይ በጅቡቲ የጋራ ምክክር ያደረጉ ሲሆን በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
አፍሪካውያን ለአህጉራቸው ሰላም እና ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም ሊያረጋግጡ ይገባል - መሐሙድ አሊ ዩሱፍ 
Sep 9, 2025 1094
አዲስ አበባ፤ ጳጉሜን 4/2017(ኢዜአ)፦ አፍሪካውያን ለአህጉራቸው ሰላም እና ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት በማጽናት የተሻለ መጻኢ ጊዜን ለመፍጠር በጋራ እንዲሰሩ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ። የአፍሪካ ህብረት ቀን ዛሬ እየተከበረ ይገኛል። ቀኑ የአፍሪካ ህብረት እ.አ.አ ሴፕቴምበር 9/1999 በሲርት ድንጋጌ አማካኝነት የተቋቋመበት ቀን የሚታወስበት ነው። የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ቀኑን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት አፍሪካውያን ቀኑን ሲዘክሩ የአህጉሪቷን ለውጦች በማክበር እና ለአንድነት፣ ሰላምና ብልጽግና ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም በማረጋገጥ ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል። የህብረቱ መመስረት ውሳኔ ለአፍሪካ ትብብር፣ ትስስር እና አጋርነት መሰረት የጣለ ነው ብለዋል። የአፍሪካ ህብረት ቀን የጋራ ጉዟችንን፣ የህዝባችንን አይበገሬነት እና ያጋመደንን የፓን አፍሪካኒዝም መንፈስ የምናከብርበት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሊቀ መንበሩ በመልዕክታቸው በአፍሪካ በተለያዩ መስኮች የተመዘገቡ ስኬቶችን አንስተዋል። በሰላምና ደህንነት፣ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና፣ የታዳሽ ኃይል ልማት፣ ዲጂታል ኢኖቬሽንና የወጣቶችን አቅም በመገንባት የተከናወኑ ስራዎች አፍሪካን በዓለም መድረክ ያላት ሚና እንዲያድግ አስተዋጽኦ ማድረጉን ነው ሊቀ መንበሩ የገለጹት። የአፍሪካ ህብረት ለአጋርነት፣ ትስስር እና ዘላቂ ልማት ያለውን ቁርጠኝነት ጠቅሰው መንግስታት፣ ሲቪክ ማህበረሰቡ፣ የግሉ ዘርፍ እና ወጣቱ ፈተናዎችን በጋራ በመሻገር አጀንዳ 2063 ይዞ የመጣችውን እድሎች እንዲጠቀም ጥሪ አቅርበዋል። ሁሉም አፍሪካውያን ክብራቸው ተጠብቆ የሚኖሩባት እና መጻኢ ጊዜያቸው ብሩህ የሆነች አህጉር እጅ ለእጅ በመያያዝ እንገንባ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።
ሐተታዎች
  "ያሆዴ"- ከተናጠል ይልቅ በትብብር የመድመቅ ተምሳሌት
Sep 28, 2025 274
(በማሙሽ ጋረደው - ከኢዜአ ሆሳዕና ቅርንጫፍ) የሀዲያ የአዲስ ዘመን መለወጫ በዓል የሆነው "ያሆዴ" የማህበራዊ መስተጋብር መሰረት ነው። ለማህበራዊ የህይወት አመራር ጉልህ አስተዋጾም ስላለውም በሀዲያዎች ዘንድ በየዓመቱ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ይከበራል፡፡ "ያሆዴ" ያለፈውን አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲስ ዘመን የሚቀበሉበት፤ የመጻኢ ተስፋ ብስራትና የልምላሜ ምልክትም ጭምር ተደርጎም ይቆጠራል፡፡ በመሆኑም በዓሉ ሲቀርብ የሀዲያ ተወላጆችና የበዓሉ ተሳታፊዎች ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ከያሉበት ወደአካባቢው በመምጣት ይሰባሰባሉ፡፡ በዘንድሮ የያሆዴ በዓልም የሀድያ ተወላጆች የተለያዩ ማህራዊና ባህላዊ ክዋኔዎችን ለመከወን እንዲመች ታስቦ በተዘጋጀ ስፍራ (ነፈራ) ተሰባስበው በዓሉን በድምቀት አክብረውታል፡፡ በበዓሉ አከባበር ያለፈው ዓመት ስኬትም ይገመገማል፤ በአዲሱ ዓመትም የተሻለ ተሰርቶ ስኬት እንዲመዘገብ በሀገር ሽማግሌዎች ምርቃት ይካሄዳል። ሊተገበር የሚችል ዕቅድም ይታቀዳል፡፡ በግልና በቤተሰብ የመጡ ስኬቶች በጋራ በመሆን ይገመገማሉ። የበረቱና ውጤት ያስመዘገቡም እንዲበረታቱ ይደረጋል። ለዚህም ነው "ያሆዴ" የማህበራዊ መስተጋብር መሰረት ነው የሚባለው። ሰዎች እንዲሰሩና ስኬት እንዲያስመዘግቡ የሚያበረታታ እሴት አለው። የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ መስፋን ቦጋለ እንደሚሉት የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል "ያሆዴ" ከተናጠል ይልቅ በትብብር የመድመቅ ተምሳሌት ነው፡፡ ከነሐሴ ወር አጋማሽ ጀምሮ የበዓሉ መቃረብን የሚያበስሩት ታዳጊ ልጆች ናቸው። ልጆቹ የዋሽንት (ገምባቡያ) ድምጽ ማሰማት ከጀመሩ በጉጉት የሚጠበቀውን የዘመን መለወጫ "ያሆዴ" በዓል መድረሱ ምልክት ነው። በዓሉ ሀድያዎች አሮጌውን ዓመት ሸኝተው አዲሱን ዓመት የሚጀምሩበት ወቅት ነው። በዓሉ የብሩህ ተስፋ፣ የሠላም፣ የፍቅር፣ የረድኤት፣ የበረከት ተምሳሌት በመሆኑም የተለየ ትርጉምና ትኩረት ይሰጠዋል፡፡ በዓሉ ሲከበር በተለያዩ ምክንያቶች ተራርቀው የሚኖሩ የቤተሰብ አባላት ከያሉበት ይሰባሰባሉ። በዓሉ በአማረ መልኩ እንዲከበርም ሁሉም የቤተሰብ አባላት የየራሳቸው የሥራ ድርሻቸውን ያከናውናሉ።   አባውራዎች ለበዓሉ ሠንጋ መግዣ የሚሆን ገንዘብ በቱታ ወይም በቅርጫ ቡድናቸው አማካኝነት እየቆጠቡ ይቆያሉ። እንዲሁም ለእንስሳት የሚሆን የግጦሽ ሳር የሚያበቅል ቦታ ከልለው ያዘጋጃሉ፡፡ ይህ የሚሆነበት ምክንያት ደግሞ በዓሉ በሚከበርበት ሰሞን የሰው ልጅ ይቅርና እንስሳትም መጥገብ አለባቸው ተብሎ ስለሚታሰብ ነው፡፡ እማውራዎች ከበዓሉ ሦስትና አራት ወራት አስቀድመው እንሰት በመፋቅ ቆጮና ቡላ ያዘጋጃሉ። በተጨማሪም ከአካባቢው እናቶች በጋራ በመሆን (ዊጆ) የተሰኘ የቅቤ እቁብ በመግባት ለበዓሉ የሚሆን ቅቤ ማጠራቀም ይጀምራሉ፡፡ ከእዚህ በተጨማሪ ለአተካናና ለሥጋ መብያ ናቀሮ ወይም ዳጣን እንዲሁም የሚጠጣ ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ የማዘጋጀት ድርሻ የእናቶች ነው፡፡ ለበዓሉ የቤት ውስጥና የውጭ ግርግዳን በቀለምና በተለያዩ ጌጣጌጦች የማስዋብ ሃላፊነት ደግሞ የልጃገረዶች ነው። ወጣት ወንዶች ከነሀሴ መግቢያ ጀምሮ አባቶቻቸው የሚያሳዩዋቸውን ግንድ በመቁረጥ ለምግብ ማብስያ እንዲውል ፈልጠው ያዘጋጃሉ። በሀዲያዎች አጠራር ለችቦ የሚሆን እንጨት ወይም ጦምቦራ ከጫካ ለቅመው አስረው እንዲደርቅም ያስቀምጣሉ፡፡ ለበዓሉ ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት የሚያደርገው ጥረት በዓሉ በስኬትና በድምቀት እንዲከበር ጠቀሜታው የጎላ ነው። በዚህም ያሆዴ ከተናጠል ይልቅ ትብብርን የሚያጠናክር ነው ማለት ይቻላል። እሴቱ በትብብር መድመቅ እንደሚቻልም የሚያሳይ ነው።   ይህን ሀሳብ የሚጋሩት አቶ መስፍን የሀዲያ የዘመን መለወጫ በዓል በምንም ሁኔታ መነጣጠል የማይቻል ትስስርን ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ይገልጻሉ። ሀገራዊ አንድነትና አብሮነትን የሚያጠናክር ዘመናትን የተሻገረና ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ባህላዊ እሴት ያለው መሆኑንም ይናገራሉ። በዓሉ ሊከበር ጥቂት ቀናት ሲቀረው አባውራዎች በቅርጫ ማህበራቸው አማካኝነት ያጠራቀሙትን ገንዘብ በመያዝ የእርድ በሬ ይገዛሉ። በዚህ ወቅት ገንዘብ ማዋጣት ያልቻሉ የቅርጫ አባላት እህል በሚደርስበት ወቅት ለመክፈል ተስማምተው በሬውን በዱቤ እንዲገዙ ይደረጋል፡፡ ይሄም የሚሆነው በያሆዴ በዓል አንዱ ሲበላ ሌላው ተመልካች መሆን ስለሌለበት ነው። እርስ በርስ መጨካከን እንዳይኖርና በዓሉን በአብሮነት ሁሉም ተደስቶ ማክበር እንዲችል ለማድረግ ነው። ከበዓሉ ዕለት በፊት ያለው የመጨረሻ ገበያም የእብድ ገበያ (መቻዕል ሜራ) የሚል ስያሜ አለው። ይሄ ሥያሜ ያገኘው በዓሉ ሲቃረብ በማህበረሰቡ ዘንድ የሚፈጠረውን ውጥረት ታሳቢ በማድርግ ነው፡፡ በዚህ የእብድ ገበያ ህብረተሰቡ መገበያየት የሚጀምረው ጠዋት ማለዳ ጀምር ሲሆን የግብይት ሂደቱ የሚጠናቀቀው ደግሞ እኩለ ቀን ላይ ነው፡፡ ለበዓሉ የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን ለመግዛትና የያሆዴ በዓል ከተከበረ በኋላ ለአንድ ወር ገበያ ስለማይቆም ይህን ታሳቢ ያደረገ ግብይት ለመፈጸም የግብይት ሂደቱ ጥድፊያ የበዛበት ሆኖ ይታያል።   ያሆዴ በዓል መከበር የሚጀምረው በአተካን ሂሞ ወይም በአተካና ምሽት ሲሆን ይህም ከበዓሉ አንድ ቀን በፊት ያለው ምሽት ነው። ስያሜውን ያገኘው "አተካና" ከተሰኘና በያሆዴዎች ዘንድ ለክብር እንግዳ እና በዘመን መለወጫ ከሚዘጋጅ ምግብ ነው። አተካና ከወተት፣ ከአይብ፣ ከቡላ፣ ከቅቤና ከሌሎች የቅመማ ቅመም ውጤቶች የሚዘጋጅ ምግብ ሲሆን በጣም ጣፋጭና የምግበ ፍላጎትን የሚጨምር ምግብ ነው፡፡ በበዓሉ ዋዜማ ይሄንን የተለየ ምግብ ተሰባስቦ በአብሮነት በመመገብ በደመቀ መልኩ በዓሉን ማክበር ይጀምራል፡፡ የአካባቢው አባቶች በወጣቶች የተዘጋጀ የማቀጣጠያ እንጨት (ሳቴ) ይዘው ትልቅ በሚባሉ አባውራ ቤት ደጃፍ ወደ ተዘጋጀው የችቦ ደመራ (ጦምቦራ) ቦታ ይመጣሉ:: የሀገር ሽማግሌች አዲሱ ዓመት የብርሃን ዓመት እንዲሆን፤ ለሀገርና ለህዝቦቿ ሰላም እንዲጸና፤ አብሮነት እንዲጠናከር፣ ሰላምና ፍቅር እንዲነግስ ፈጣሪያቸውን ከተማጸኑ በኋላ ችቦውን በእሳት ይለኩሳሉ፡፡   ችቦው ከተለኮሰ በኋላ የአካባቢው ወጣቶች ተሰባስበው ያሆዴ …ያሆዴ! …ያሆዴ! በማለት እየጨፈሩ ያነጋሉ ይጨፍራሉ:: በሀድያዎች ዘንድ "ያሆ" ማለት የአዲስ ዓመት መግባትን ተከትሎ ማብሰሪያ ጭፈራ ሲሆን "ኤዴ" ማለት ደግሞ አገናኝ ማለት ነው፡፡ በያሆዴ በዓል የእርድ ሥነ ስርዓት ለማከናወን ነዋሪዎች የሚሰበሰቡበት ስፍራ "ነፈራ" የሚል ስያሜ አለው። የተለያዩ ማህራዊና ባህላዊ ክዋኔዎችን ለመከወን እንዲመች ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ሰፋ ያለ ቦታ ሰሆን በተለያዩ የጥላ ዛፎች የተዋበና ለዚሁ ተግባር የተዘጋጀም ነው። በእለቱ ለእርድ የተዘጋጀው ሠንጋ ከቀረበ በኋላ የባህል ሽማግሌዎች የበሬውን ሻኛ በሰርዶ ሳር ለጋ ቅቤ ይቀባሉ፤ ወተትም ያፋሱበታል፡፡ ይህ ባህላዊ ሥነ ስርዓት ጋቢማ የሚባል ሲሆን (የመልካም ምኞት) መግለጫ ስነ ስርዓትም ነው፡፡ ይህም ሥነስርአት በሚከናወንበት ወቅትም "ክፉ ቀን አይምጣ፣ ርሃብ ሰቀቀን ይጥፋ፣ ጥጋብ ይስፈን፣ በአካባቢው በሀገሩ ጥጃ ይቦርቅ፣ ልጅ ይፈንጭበት፣ አገር ሰላም፣ ገበያ ጥጋብ ይሁን፣ ሰማይና ምድሩ ይታረቁን " እያሉ በአባቶች ምርቃት ከተካሄደ በኋላ የእርድ ስነ ስርዓት ይከናወናል፡፡ የእርድ ሥነ ስርዓቱ የተከናወነበት ቤት እማወራ አስቀድመው ባደረጉት ዝግጅት መሰረት ቅቤ፤ (ቦርዴ፣ ቃሪቦ፣ ጠጅ፣ ብርዝ) እንዲሁም ከታረደው የበሬ ሥጋ አርዚ ማራ (ቅምሻ) ይወሰድና ክትፎ ከተዘጋጀ በኋላ በጋራ እየበሉ እየተጫወቱ ይውላሉ፡፡ በዚህም በቅርጫ ሥጋው ላይ ከሚሳተፉት የቤተሰብ አባላት ውጪ በአካባቢው የሚገኙ አቅመ ደካሞችም ጭምር አብረው በመብላት በመጠጣት በዓሉን በአንድነት ያሳልፋሉ፡፡ ቀሪውን የቅርጫ ሥጋም አባላቱ ተከፋፍለው ወደ እየቤታቸው ይወስዱታል፡፡ በዓሉ አብሮ የመብላት፣ የመጠጣት፣ የመጠያየቅ፣ ችግርንና ግጭትን በጋራ ተወያይቶ የመፍታት፣ መፈቃቀርና መተሳሰብን የሚፈጥር፣ አቅመ ደካሞችና የተቸገሩ የሚረዱበት የአብሮነት መገለጫ በመሆኑ በተለየ መልኩ ይከበራል፡ ከእርድ ሥርዓቱ በኋላ በማግስቱ ልጆች አደይ አበባ (ዘራሮ) ይዘው ወደ ወላጆቻቸው እየጨፈሩ ይመጣሉ። የመስቀል አበባ እንደሚኖር ኑሩ ይባላሉ። ከስጋውም፣ ከቦርዴውም፣ ከአተካናውም እንዲመገቡ ያደረጋል። ይህ ስነ ስርዓትም ሚክራ ይባላል። በያሆዴ የዘመን መለወጫ በዓል ትዳር የያዙ ሴት ልጆችም ከባሎቻቸው ጋር ሆነው ወደ ወላጆቻቸው ምግብ ሰርተው፣ የሹልዳ ሥጋና አደይ አበባ ጭምር ይዘው ይሄዳሉ። በዓሉ ያላገቡ ወጣቶች የሚተጫጩበትና ለአዲስ ህይወት ጅማሬ የሚያበስሩበት በመሆኑን የተለየ ድባብ አለው፡፡ የያሆዴ በዓል ካሉት እሴቶች አንዱ የህብረተሰቡን የአካባቢ ልማት ተሳትፎ ማበረታታት ተጠቃሽ መሆኑን የገለጹት አቶ መስፍን ዕሴቱ የተጀመሩ የልማት ሥራዎች ተጠናቅቀው ለማህበረሰብ ጥቅም እንዲውሉ ጭምር አቅም እየሆነ መምጣቱን ነው የሚናገሩት።ይህ የአብሮነት ማስተሳሰሪያና የማህበራዊ መስተጋብር መጋመጃ የሆነው በዓል እሴቱን አጠናክሮ ለማስቀጠል መስራት ይገባል። እሳቸው እንዳሉት በዓሉ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዩኔስኮ ወካይ ቅርስነት እንዲመዘገብ ለማስቻል እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም መምሪያው ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ዕሴቱን የመሰነድና ምርምሮች ማካሄድን ጨምሮ እያከናወናቸው ያሉ የተለያዩ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው።  
80ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እና የኢትዮጵያ ተሳትፎ
Sep 27, 2025 414
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ግዙፉና ጉምቱው የዓለም የብዝሃወገን ዲፕሎማሲ መድረክ ነው። 80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባኤ ከጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም አንስቶ “ደህናነት በአብሮነት፤ 80 ዓመታት እና ከዚያ በላይ ለሰላም፣ ለልማት እና ለሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ይገኛል። የጠቅላላ ጉባኤው አካል የሆነ ከፍተኛ የምክክር እና ክርክር መድረክ ከመስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተደረገ ነው። ከሰላም እስከ አየር ንብረት ለውጥ፣ ከዘላቂ ልማት እስከ ዲጂታል አካታችነት፣ ከሰብዓዊነት እስከ የዓለም የኢኮኖሚ አወቃቀር፣ በዓለም መድረክ ፍትሐዊ ውክልናን ከማግኘት እስከ ዓለም በቀጣይ ምን ትሆን? ድረስ በርካታ ጉዳዮች ተነስተው ውይይቶችና ክርክሮች በማድረግ ለወደፊቱ ይበጃሉ የተባሉ ሀሳቦች በመነሳት ላይ ይገኛሉ። በጉባኤው ይፋዊ መክፈቻ ላይ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ባደረጉት ንግግር ዓለም በተለያዩ ሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች፣ ድህነት፣ ረሃብ፣ ጦርነት፣ የአየር ንብረት ለውጥ፣የኢኮኖሚ ቀውስ እየተፈተነች ባለበት ወቅት የሚከበረው የተመድ 80ኛ ዓመት አባል ሀገራት ከመቼውም ጊዜ በላይ አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለች ዓለም ለመፍጠር በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል። የተመድ ሥርዓትንና መዋቅር 21ኛው ክፍለ ዘመን በሚመጥን ልክ መለወጥ እንደሚገባ አመልክተዋል። ዋና ፀሐፊው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ምርጫውን ሰላም፣ ፍትህ ዘላቂ ልማት እና ሰብአዊ ክብር ሊያደርግ እንደሚገባና ለተግባራዊነቱም ቁርጠኝነት እንዲያሳይ ጥሪ አቅርበዋል። በፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በጠቅላላ ጉባዔው ላይ ተሳትፎ እያደረገ ነው።   ልዑካን ቡድኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራን ጨምሮ ከፍተኛ ባለስልጣናትን አካቷል። ኢትዮጵያ በጉባዔው ላይ የራሷን ብሔራዊ ጥቅሞች እና የአፍሪካን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ እንደምታደርግ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ከዋናው ጉባዔ ተሳትፎ በተጨማሪ በርካታ የሁለትዮሽና የባለብዙ ወገን የጎንዮሽ የውይይት መድረኮች ላይም ኢትዮጵያ የራሷን ብሄራዊ ጥቅሞች ቅድሚያ እየሰጠች እንደምትሳተፍም አመልክዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ጋር ተወያይተዋል። ዋና ፀሐፊው ኢትዮጵያ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አጠናቃ በመመረቋ ፣ የአየር ንብረት ጉባዔ እና ሌሎች ፕሮጀክቶችን በማስተናገድ ላስመዘገበችው ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። ሁለቱ ወገኖች በቀጣናው እና በሌሎች ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል። በተጨማሪም ፕሬዝዳንቱ ከተመድ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዝዳንት አናሌና ባርቦክ ጋር ተወያይተዋል።   ሁለቱ መሪዎች በወቅታዊ ዓለም አቀፍ ተግዳሮቶች እና በባለብዙ ወገን ግንኙነት ላይ እያሳደረ ስለሚገኘው ተጽዕኖ ሀሳቦችን ተለዋውጠዋል። ፕሬዝዳንት ታዬ የባለብዙ ወገን ግንኙነት እና የጋራ ደኀንነት መርሆዎችን ለማስጠበቅ የጋራ ጥረቶችን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል። በቅርቡ የተመረቀው የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት የተመድ ዘላቂ ልማት ግቦችን ከማሳካት ረገድ በተለይም ግብ ሰባትን ለማሳካት ግድቡ ንጹሃ የኃይል አቅርቦት ከማሳደግ አኳያ ያለውን ፋይዳ ገልጸዋል። ፕሬዝዳንት አናሌና ባርቦክ በበኩላቸው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቻርተር መርሆዎችን ማክበር እና መጠበቅ ለዓለም ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል። ሁለቱ ወገኖች በኢትዮጵያ ልማት፣ ቀጣናዊ ሰላም እና ደኀንነትን ጨምሮ በተለያዩ ቀጣናዊ የትኩረት መስኮች ላይም መክረዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከጉባኤው ጎን ለጎን ከተለያዩ ሀገራት እና ተቋማት ጋር የሁለትዮሽ ውይይቶችን እያደረጉ ይገኛል።   አምባሳደር ሃደራ ከደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መንደይ ሲማያ ኩምባ የኢትዮጵያ እና ሱዳን የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ግፍንኙነት ማጠናከር እንዲሁም በቀጣናዊ እና በባለብዙ ወገን የትብብር መድረኮች የተባበረ አቋም እንዲኖራቸው ማድረግ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ መክረዋል። ከሞዛምቢክ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማሪያ ማኑኤላ ዶስ ሳንቶስ ሉቃስ ጋርም ተወያይተዋል። ሽብርተኝነትን መከላለከል፣ አቪዬሽን እና ሕገ ወጥ የሰዎች ዝውውርን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እንደሚሰሩ ገልጸዋል። አምባሳደሩ ከአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ ባለሥልጣን አምባሳደር ጆናታን ፕራት ጋር በሀገራቱ የጋራ ፍላጎቶች ላይ ተወያይተዋል። ሁለቱ ወገኖች በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ ግንኙነት ማሻሻል የሚያስችሉ ሥራዎችን ለማከናወን ተስማምተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ከአውሮፓ ከአውሮፓ ሕብረት የውስጥ ጉዳይ እና የፍልሰት ኮሚሽነር ማግነስ ብሩነር ጋርም የተወያዩ ሲሆን ሁለቱ ወገኖች ዓለም አቀፍ ፈተና በሆኑ ከፍልሰት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ቁርጠኝነታቸውን ገልጸዋል። አምባሳደሩ ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሼክ ሻክቦት ቢን ናህያን አል ናህያን ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቱ የበለጠ በሚያጠናክሩ ዕድሎች እንዲሁም በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር የበለጠ ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል። አምባሳደር ሃደራ አበራ ከኩባ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሩኖ ሮድሪጌዝ ፓሪላ ጋር በሁለትዮሽ ትብብር ዙሪያ መክረዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ከአዘርባጃን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጄሁን ቤራሞቭ ጋር ባደረጉት የሁለትዮሽ ውይይት ኢትዮጵያና አዘርባጃን ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው አገራት መሆናቸውን በመጥቀስ ሁለቱ አገራት በተለይ በኢኮኖሚ ዘርፎች ይበልጥ ተቀናጅተው ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ገልፀዋል። ሁለቱ ወገኖች በውይይታቸው ሀገራቱ በንግድ፣ በኢንቬስትመንት፣ በቱሪዝም በግብርናና በትምህርት ዘርፎች እንዲሁም በባለብዙ ወገን መድረክ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር በጋራ ለመሥራት ተስማምተዋል። ኢትዮጵያ ከጠቅላላ ጉባኤው ጎን ለጎን ባሉ የጎንዮሽ ውይይቶች ላይ እየሳተፈች ይገኛል። ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ በተሳተፉበት መድረክ ኢትዮጵያ የአፍሪካን የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ማስፋት አላማ ያደረገው “Mission 300” ኢኒሼቲቭ ተቀላቅላለች። በዓለም ባንክ እና በአፍሪካ ልማት ባንክ የሚመራው ኢኒሼቲቭ እ.አ.አ በ2030 በአፍሪካ የሚገኙ 300 ሚሊዮን ዜጎችን በኤሌክትሪክ ኃይል የማስተሳሰር ውጥን ያለው ነው። ፕሮጀክቱ የአፍሪካ መንግስታት፣ የግሉ ዘርፍ እና የልማት አጋሮችን ያሳተፈ ሲሆን በአፍሪካ አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ፣ አካታች እና ተመጣጣኝ የኢነርጂ አቅርቦትን ተደራሽ በማድረግ የኢኮኖሚ እድገት እና ቀጣናዊ ትስስርን የማጠናከር አላማንም አንግቧል። ኢኒሼቲቩ ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀም እና ቀጣናዊ የኃይል ትስስሯን ለማሳደግ ወሳኝ ሚና እንዳለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል። ኢትዮጵያ በአፍሪካ የንጹህ ኢነርጂ ሽግግር ውስጥ ያላትን የመሪነት ሚና እንደሚያሳድግና አፍሪካ ከኢነርጂ ድህነት የማላቀቅ እና ዘላቂ ልማትን የማረጋገጥ ትልም ለማሳካት እንደሚያግዝም ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ በአፍሪካ በሽታ መከላከል እና መቆጣጠር ማዕከል (ሲዲሲ አፍሪካ) ኮሚቴ አባል የመሪዎች ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል። ሚኒስትር ዴኤታው በስብሰባው ላይ ኢትዮጵያ የጤናን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ የሀገር ውስጥ የሀብት ማሰባሰብ እና ፈጠራ የተሞላበት የፋይናንስ ግኝት እንደምትከተል አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በጠቅላላ ጉባኤው ብሔራዊ ጥቅሞች እና የአፍሪካን ጥቅሞች በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ንቁና ጠንካራ ተሳትፎ ማድረጓን እንደምትቀጥል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው ገልጸዋል። በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያን ልዑክ የመሩት ፕሬዝዳንት ታዬ አፅቀሥላሴ የጉባኤው አካል በሆነው ከፍተኛ የምክክር እና ክርክር መድረክ ላይ ንግግር አድርገዋል። ፕሬዝዳንቱ በንግግራቸው በመልክዓ ምድራዊ ሁኔታዎች ምክንያት የትኛውም ሀገር የእድገት፣ የፋይናንስ እና የቴክኖሎጂ ዕድሎች ዝግ መሆን የለበትም ሲሉ ገልጸዋል። ኢትዮጵያ ከሌሎች ሀገራት ጋር በመሆን በቀይ ባሕር እና በሕንድ ውቅያኖስ አካባቢ የሚገኙ ሁሉም ሀገሮች እኩል ልማት እና ደኀንነትን ማረጋገጥ ወደሚያስችል ሁለንተናዊ አሠራር እንዲዘረጋ ትሠራለች ብለዋል። ኢትዮጵያ ይህንን ሕጋዊ ፖሊሲዋን ለማሳካትም የዲፕሎማሲያዊ እና ሰላማዊ አማራጮችን እንደምትከተል አረጋግጠዋል። በሌላ በኩል ፕሬዝዳንቱ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትን ለማሻሻል አስቸኳይ እርምጃ እንዲወሰድ ጠይቀዋል። በማሻሻያውም ለአፍሪካ ውክልና በምክር ቤቱ በሁለቱም በኩል ቅድሚያ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርበው፤ ለአፍሪካ የረጅም ጊዜ የፍትሕ መሻት ጥያቄ አቋራጭ ወይም ግማሽ መፍትሔ እንደሌለ አስገንዝበዋል። ከታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጋር በተያያዘም፤ የናይል ወንዝ የትብብር ማዕቀፍ በፈረንጆቹ ጥቅምት 2024 ወደ ተግባር መግባቱን እና የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን ወደ መቋቋም ደረጃ መቃረቡን አስረድተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ መመረቁ፤ በኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ ላልሆኑ ኢትዮጵያውያን ንጹህ የኃይል ምንጭ እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑን አስገንዝበዋል። ግድቡ በከባድ የውኃ እጥረት ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖቻችን ንጹህ ውኃ ለማቅረብ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና አጠቃላይ ልማትን እውን ለማድረግ አቅማችንን ያሳድጋል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ። ግድቡ ለሰፋፊ ክልላዊ ትስስር ተስፋን የሚፈጥር መሆኑንም ገልጸዋል። ኢትዮጵያ እ.አ.አ 1945 የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሲመሰረት መስራች አባል ከነበሩት ሀገራት መካከል አንዷ ናት። ይህም ኢትዮጵያ የባለብዝሃ ወገን እና ዓለም አቀፍ ትብብር ያላትን የማይናወጥ አቋም እና የጸና ቁርጠኝነት በግልጽ የሚያሳይ ነው። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ጉባኤ ሰላም፣ ደህንነት፣ ዘላቂ ልማት እና የአየር ንብረት ለውጥን ጨምሮ በዓለም አንገብጋቢ ጉዳዮች ላይ ያራሷ እና የአፍሪካን ድምጽ በማሰማት የነቃ ተሳትፎ እያደረገች ትገኛለች። 80ኛው የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ መስከረም 19 ቀን 2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል።
የሐረማያ ሐይቅ የጎብኝዎች መዳረሻ ሆኗል
Sep 25, 2025 319
ሐረማያ መስከረም 15/2018 (ኢዜአ)፡- የሐረማያ ሐይቅ የጎብኝዎች መዳረሻ በመሆን በዘርፉ ለተሰማሩ አካላትም የገቢ ምንጭ ሆኗል። "ወየው ሐረማያ የሐረር ሲሳይ ባህርም እንደሰው ሞት ይሞታል ወይ? ተብሎ የተገጠመለት እና ወደ ታሪክነት ተቀይሮ የነበረው የሐረማያ ሃይቅ መልሶ ነፍስ ዘርቶ በማንሰራራት አይነተኛ የቱሪስት መስህብ ሆኗል።   የሐረማያ ሐይቅ ለ17 ዓመታት ደርቆና ነጥፎ የነበረ ቢሆንም በዙሪያው በሚገኙ ተፋሰሶች ላይ በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በተከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ሃይቁ ወደ ነበረበት የተመለሰ ሲሆን የውሃው መጠንም ከዓመት ዓመት እየጨመረ መጥቷል። በዚህም ሃይቁ የጎብኝዎች መዳረሻ እየሆነ በመምጣቱ ደግሞ በዘርፉ ተደራጅተው የተሰማሩት ሰዎች ተጠቃሚ መሆናቸውን ይናገራሉ።   ኢዜአ በስፍራው ተገኝቶ ካነጋገራቸው መካከል ወጣት እስክንድር ዩስፍ፤ የሐይቁ መመለስ ከውጪ ሀገርና ከሀገር ውስጥ ለጉብኝት የሚመጡ ሰዎች የሚጎበኝ የዓይን ማረፊያ ሆኗል። በማህበር ከተደራጁ ጓደኞቹ ጋር ቱሪስቶችን በማስጎብኘትና በአካባቢው በማዝናናት ገቢ በማግኘት ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስቶ ሐይቁን የመንከባከብ ስራም እያከናወንን እንገኛለን ብሏል። የሐረማያ ሐይቅ ወደ ነበረበት ሁኔታ መመለሱ እኔና ቤተሰቦቼን ጨምሮ ሌሎች ወጣቶች በተለያየ ዘርፍ የስራ እድል እንድናገኝ እድል ፈጥሯል ያሉት ደግሞ በሐይቁ በአስጎብኚነትና የአሳ ምግብ ቤት ከፍተው የሚሰሩት አቶ ረመዳን አሊ ናቸው።   ሐይቁ የጎብኚዎችን ቀልብ እየሳበና በበርካቶች እየተጎበኘ መሆኑን አንስተው፤ እንደ በፊቱ ሐይቁ ጉዳት እንዳይገጥመው የእንክብካቤ ስራን እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል። በኦሮሚያ ክልል የማያ ከተማ አስተዳደር የቱሪዝም ጽህፈት ቤት ተወካይ ወይዘሮ ፎዚያ መሐመድ፤ ሐይቁ ከተመለሰ ጀምሮ ወደ ስፍራው የሚመጡ ጎብኚዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን ገልጸዋል።   ይህም ለማኅብረሰቡ እና በዘርፉ የተሰማሩ ባለ ድርሻ አካላትን ተጠቃሚ ማድረጉን ጠቁመው በተለይ ሐይቁ ተመልሶ ጉዳት እንዳይጋረጥበት ህዝቡን ባሳተፈ መልኩ የእንክብካቤ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል። በከተማው የቱሪስቱን ቆይታ ለማራዘምም ሆቴሎችንና ሪዞርቶችን የማስፋፋት ስራ እየተከናወነ መሆኑን አንስተው ባለሀብቶች በኢንቨስትመንት አማራጭ እንዲሰማሩ የማስተዋወቅ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።   በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የሐረማያ ሃይቅ ተፋሰስ ልማት ፕሮጀክት አስተባባሪና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀም መምህር ዲኔ ረሺድ ለ17 ዓመታት ደርቆ የነበረው የሐረማያ ሃይቅ ዩኒቨርሲቲው በጥናት ላይ በመመስረትና ከህብረተሰቡ ጋር ባከናወነው የአፈርና ውሃ ጥበቃና አረንጓዴ አሻራ ስራዎች ሐይቁ እንዲመለስ አስችሏል። በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ስራ የተመለሰው የሐረማያ ሐይቅ በውሃ ላይ የተመሰረተ የቱሪዝም ዕድል እየፈጠረ ስለመሆኑም ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅትም ሃይቁ በደለልና ቆሻሻ እንዳይሞላ በሃይቁ ዳርቻ የተለያዩ ስትራክቸሮችን የመስራትና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ የመስጠት እንዲሁም ውሃ ቆጣቢ የመስኖ ቴክኖሎጂዎችን እንዲጠቀሙ የማድረግና የቁሳቁስ ድጋፍ ስራዎች መከናወኑን ተናግረዋል።
ከጉባ እስከ ዓለም መድረክ፤ የዓለም አይኖች ያረፉበት የሕዳሴ ግድብ 
Sep 13, 2025 1004
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጳጉሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም መመረቁ ይታወቃል። በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፣ የኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ (ዶ/ር)፣ የጂቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦመር ጊሌህ፣ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ (ዶ/ር)፣ የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት፣ የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሊ፣ የእስዋቲኒ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሴል ሚሶ ድላሚኒ፣ የአፍሪካ ሕብረት ሊቀመንበር መሀሙድ አሊ ዩሱፍ፣ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጋቴቴ ተገኝተዋል።   የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዓለምን ዓይን የሳበው የአፍሪካ ግዙፉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ በመሆኑ ብቻ አይደለም። ፕሮጀክቱ የአፍሪካን ህልሞች፣ ትብብር እና ቀጣናዊ ትስስር መልህቅ በመሆንም ጭምር ነው። የምረቃት ስነ ስርዓቱ ከአፍሪካ፣ መካከለኛው ምስራቅ፣ አውሮፓ እና በተቀረው ዓለም በሚገኙ መገናኛ ብዙሃን ሰፊ ዓለም አቀፍ ሽፋን አግኝቷል። ቢቢሲ በዘገባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ያቆመ የሀገር ኩራት ማሳያ መሆኑን ገልጾ የግድቡ ስኬት የኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች የዓመታት ጥረትና ድካም፣ በዜጎች የሀብት፣ የጉልበት እና የገንዘብ አስተዋፅኦ የተገኘ ውጤት መሆኑን አመልክቷል። ግድቡ ለሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽ በማድረግ የዜጎችን ህይወት እንደሚለውጥ ትልቅ ተስፋ እንደተጣለበትም አመልክቷል። ግድቡ የኢትዮጵያውያን ኩራት እና የቀጠናዊ ትብብር ማሳያ መሆኑን አበይት ጭብጡ አድርጎ ዘገባውን የሰራው ዶቼ ቬሌ ሙሉ በሙሉ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ የገንዘብ መዋጮ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላው ጥቁር ህዝቦች ታላቅ ስኬት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መግለጻቸውን አንስቷል። ግድቡ የተፋሰሱ ሀገራት የኢኮኖሚያዊ ውህደት እና ትብብር መሰረት መሆኑን የጠቀሰው የጀርመኑ መገናኛ ብዙሃን፤ ግድቡ፣ ኤሌክትሪክ ኃይል ለሌላቸው ኢትዮጵያውን የኢነርጂ አቅርቦትን ከማረጋገጡ ባሻገር ለጎረቤት ሀገራት የኤሌክትሪክ ኃይል በማቅረብ ቀጣናዊ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑን ገልጿል። የተርኪዬ ዜና አገልግሎት አናዶሉ የሕዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በሰራው ዘገባ የግድቡ ምረቃ ታሪካዊ ድል ሲል በዘገባው ላይ አስፍሯል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ከቅኝ ግዛት ዘመን ጀምሮ የነበረውን ኢፍትሃዊ የውሃ አጠቃቀም የቀየረ መሆኑን ጠቅሶ ኢትዮጵያ የአፍሪካን ትልቁን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድብ እውን ማድረግ መቻሏን ጠቅሷል። አልጄዚራ የኢትዮጵያውያን የዘመናት ህልምን እውን ያደረገ ስኬት ነው ሲል በሰራው ዘገባ ያለምንም አይነት የውጭ እርዳታና ድጋፍ ፣በኢትዮጵያውያን የገንዘብ መዋጮና የቦንድ ግዢ መገንባቱ የግድቡን ስኬት የተለየ እንደሚያደርገው ገልጿል። በዜጎች ዘንድ ከፍተኛ የባለቤትነት ስሜትና የጋራ ኩራት የፈጠረ ፕሮጀክት መሆኑን ያመለከተው ዘገባው፤ ኢትዮጵያውያን የገጠማቸውን ፈተና አልፈው ያጠናቀቁት ግድብ የሀገራዊ አንድነት ማሳያ እና የትውልድ ቅብብሎሽ ውጤት እንደሆነም አንስቷል። ሲኤንን የሕዳሴው ግድብ ምረቃ ሀገራዊ ኩራት ምንጭ ሆኗል ያለ ሲሆን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ትልቁን የኤሌክትሪክ ሀይል ማመነጫ ግድብ መሆኑንና ለሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን ከማረጋገጡ ባለፈ የሀገር ኩራት ምንጭ መሆኑን ገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የግድቡ አላማ ወንድም ሀገራትን መጉዳት ሳይሆን ለቀጣናው ብልጽግናን ማምጣት እንደሆነ መግለጻቸውንም በዘገባው ላይ አስፍሯል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅ ኢትዮጵያን የቀጠናው የኃይል ማዕከል ያደርጋታል ያለው ደግሞ አሶሲዬትድ ፕሬስ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካን ትልቁን የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመርቅ፣ ፕሮጀክቱ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በማሳደግ ለኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋፅኦ ከማድረጉ ባሻገር ጎረቤት ሀገራት ኃይል ለመግዛት የሚችሉበትን ሁኔታ እንደሚፈጥር ጠቅሷል። ታላቁ የሕዳሴው ግድብ መመረቅ ኢትዮጵያን የቀጣናው የኃይል ማዕከል ያደርጋታል ያለው ደግሞ አሶሲዬትድ ፕሬስ ነው። ኢትዮጵያ የአፍሪካ ትልቁን የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድብ ስትመርቅ፣ ፕሮጀክቱ የሀገሪቱን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በእጥፍ በማሳደግ ለኢኮኖሚያዊ እድገት አስተዋፅኦ ከማድረጉ ባሻገር ጎረቤት ሀገራት ከኢትዮጵያ ኃይል ለመግዛት እንደሚያስላቸው ነው በዘገባው ያመለከተው። የቻይናው ዢንዋ የሕዳሴው ግድብ ምረቃ የሀገራዊ ስኬት ማሳያ እንደሆነ ጠቅሶ ኢትዮጵያ የአፍሪካ ትልቁ የውሃ ኃይል ማመንጫ የሆነውን ታላቁን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በይፋ መርቃለች ሲል ገልጿል። በስነ ስርዓቱ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱ የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንደሚያጠናክር፣ የተረጋጋ የኃይል አቅርቦትን እንደሚያረጋግጥና የቀጠናዊ የኃይል ትስስርን እንደሚያሳድግ መግለጻቸውን ዘግቧል። በምረቃው ላይ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች መገኘት የፕሮጀክቱን ቀጣናዊ ፋይዳ የሚያሳይ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኢትዮጵያ የጎረቤቶቿን ጥቅም ሳይጎዳ በጋራ እድገት ላይ ያላትን ቁርጠኝነት በድጋሚ ማረጋገጣቸውን አውስቷል። አጠቃላይ ዘገባዎቹ የሕዳሴ ግድብ በቀጣናው፣ በአፍሪካ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የገዘፈ ተጽእኖ የሚያሳይ ነው። የሕዳሴ ግድብ ምርቃት ከመገናኛ ብዙሃን ባለፈ በዓለም ደረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን ትኩረት ስቧል። የአሜሪካ የቅድሞ ቅርጫት ኳስ ተጫዋች እና ታዋቂው የቲክቶክ የይዘት ፈጣሪ ዲላን ፔጅ የሕዳሴ ግድቡ ምርቃትን በአፍሪካ የተሰራ አዲስ ታሪክ ሲል ገልጾታል። ግድቡ በዓለም ላይ ከሚገኙ 20 ግዙፍ የኤሌትሪክ ማመንጫ ግድቦች አንዱ መሆኑንና ለወደፊት የኢትዮጵያን መጻኢ ጊዜ ብሩህ የሚያደርግ እንደሆነ ተናግሯል። ሕዳሴ የኢትዮጵያ ኢነርጂ ምርት በእጥፍ በመጨመር ሚሊዮኖች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያገኙ ያስችላል ብሏል። ግድቡ የሚያመነጨው ኃይል ለኢንዱስትሪ እና ማኑፋክቸሪንግ እድገት ትልቅ ሚና እንዳለው የገለጸው ዲላን የጎረቤት ሀገራት ኤሌክትሪክ በሽያጭ እንዲያገኙ ብር የሚከፍት እንደሆነም ጠቅሷል። ከ17 ነጥብ 3 ሚሊዮን በላይ የቲክቶክ ተከታይ ባለው የዲላን ፔጅ ገጽ የተላለፈው መልዕክት ይህ ጽሁፍ እስከጠናከረተበት ሰዓት 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሰው ቪዲዮውን በመውደድ( ላይክ በማድረግ) ድጋፉን ገልጿል። በቲክቶክ ገጹ ላይ በጤና እና መዝናኛ ቪዲዮቹ የሚታወቀው የአሜሪካ ወታደራዊ ኃይል የቀድሞ አባል ካጋን ዱንላፕ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት በኢትዮጵያ የኢነርጂ እና የመሰረተ ልማት ዘርፍ ትልቁ የሚባል ስኬት እንደሆነ ገልጿል። ግንባታው 14 ዓመታት የፈጀው ይህ ግዙፍ የሃይድሮ ፓወር ፕሮጀክት በራስ አቅም የተገነባና ይህም የብሄራዊ ጥረት ውጤትና የኢነርጂ ሉዓላዊነትን ያረጋገጠ መሆኑን አመልክቷል። ይህ የዱንላፕ ቪዲዮ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ተከታይ ባለው የቲክቶክ ገጹ ላይ እስከ አሁን ከ165 ነጥብ 6 ሺህ በላይ ተመልካች አይቶታል። ኬንያዊቷ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ ብሪላ ናታሻ በቲክቶክ ገጿ ባስላለፈችው የቪዲዮ መልዕክት አፍሪካ በሕዳሴ ግድብ ታሪክ ሰራች ስትል ገልጻለች። የአፍሪካ የነጻነት ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ያለ ምንም የውጭ እርዳታ በኢትዮጵያውያን ገንዘብ እና ትልቅ መስዋዕትነት ማሳካቷን ተናግራለች። ኢትዮጵያ ግድቡን በራሷ እቅም መገንባቷ አፍሪካ መሰል ግዙፍ ፕሮጀክቶችን የማንንም እጅ ሳትጠብቅ መስራት እንደምትችል በግልጽ ለዓለም መልዕክት ያስተላለፈችበት ነው ብላለች። የግድቡ ምርቃት አፍሪካ በራሷ አቅም የራሷን ጉዳይ ለመፈጸም የወሰደችው ትልቅ እርምጃ መሆኑን ጠቅሳ ምርቃቱ ድንቅ የሚባል ዜና እንደሆነ ተናግራለች። የቲክቶክ ገጿ ላይ 189 ሺህ 500 ተከታይ ያላት ናታሻ ግድቡን አስመለክቶ ያስተላለፈችው መልዕክት እስከ አሁን ባለው መረጃ 33 ሺህ 800 ሰዎች በመውደድ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ከዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እና ተጽኦ ፈጣሪ ግለሰቦች ሀሳብ ወጣ ስንል የግድቡ ምርቃት የአፍሪካ የአይበገሬነት እና የጽናት ምልክት፣ ራስን የመቻል እና የቀጣናዊ ዲፕሎማሲ ትብብር መገለጫ ሆኖ የታየበት ነው። የምስራቅ አፍሪካ መሪዎች በምርቃቱ ላይ መገኘት የአፍሪካ ፕሮጀክት የሆነው ሕዳሴ ግድብ ኢኮኖሚን በመቀየር፣ የኢነርጂ ዋስትናና ደህንነት በማረጋገጥ እና ድንበር ተሻጋሪ የዲፕሎማሲ ትስስር መጋመጃ መሆኑም ታይቶበታል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አፍሪካ የራሷን እጣ ፈንታ በራሷ የመወሰን አቅም እንዳላት የሚያሳይ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑን የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ በግድቡ ምርቃት ላይ ባደረጉት ንግግር ገልጸዋል። የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምርቃት ትልቅ ታሪካዊ አንድምታ አለው ያሉ ሲሆን አፍሪካውያን የራሳቸውን የብልጽግና መሻት በራሳቸው ማካሳት እንደሚችሉም የሚያመላክት መሆኑን አመልክተዋል። የሕዳሴ ግድብ ከብሄራዊ ፕሮጀክትነት ባለፈ የፓን አፍሪካ አቅምን በተግባር ያሳየና የአፍሪካ መር መሰረተ ልማት ግንባታ መገለጫ ነው ያሉት ሩቶ ግድቡ በቀጣናው ለሰላም እና ብልጽግና ያለንን የጋራ ህልም ማሳካት በእጃችን ያለ ጉዳይ መሆኑን የሚያሳይ ነው ብለዋል። በግድቡ ምርቃት ላይ የተገኙት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሃሙድ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አህጉራዊ ትብብርና ግንኙነትን የሚያጠናክር የወንድማማችነት ምልክት እንደሆነ ተናግረዋል። የላይኛውና የታችኛው ተፋሰሱ ሀገራት መበልጸግ የሚችሉት በጋራ እንደ አንድ ማህበረሰብ በመስራት መሆኑን ገልጸው፤ ውሃና ሌሎች ተፈጥሯዊ ሀብቶች በድንበር የተወሰኑ ሳይሆኑ የወደፊት እጣ ፈንታችንን የሚያስተሳስሩ ናቸው ሲሉም ገልጸዋል። የደቡብ ሱዳኑ ፕሬዝዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት የሕዳሴ ግድቡ መመረቅ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካ የኩራት ቀን ነው ያሉ ሲሆን ግድቡ የኃይል ፍላጎትን ከማሳካት ባለፈ ለልጆቻችን የምንመኘውን የበለጸገ ሀገርና አህጉር ለማስረከብ እድል የሚፈጥር ነው ብለዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያን ፕሮጀክት ነው ያሉት ደግሞ የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ ናቸው። ግድቡ የዓለምን ሕዝብ ያስደነቀ የአፍሪካ ታላቅ ፕሮጀክት መሆኑንም ገልጸዋል። የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሐሙድ አሊ ዩሱፍ ኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ገንብታ ለምረቃ ያበቃችው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከሀገሬው አልፎ ለጎረቤት ሀገራት ብርሃን ነው ሲሉ ገልጸዋል። የዚህ ፕሮጀክት ስኬት ከአኅጉራዊ አጀንዳዎች ጋር የሚጣጣም መሆኑን በመጥቀስ፤ ለአየር ንብረት የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ በመገንባት ኢትዮጵውያንን እና ቀጣናውን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ በራስ አቅም የገነባችው በመሆኑም፤ የሚደነቅና ለአኅጉራችን መነሳሳትን የሚቸር ተግባር ነው ብለዋል። 5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት የሚያመነጨው ሕዳሴ በየቤቱ ብርሃንን በመስጠት፣ ለኢንዱስትሪዎች አለኝታ በመሆንና ከምስራቅ አፍሪካ ባሻገር እድገትን ለማሳለጥ ቁልፍ ሚና ይጫወታል። የሕዳሴ ግድብ ከዲፕሎማሲ አኳያ የአፍሪካ መር ስኬትን በግልጽ የሚያመላክት ነው። ግድቡ በኢትዮጵያውያን የራስ አቅም መገንባቱ አፍሪካ የራሷን የልማት መንገድ በራሷ የመወሰን አቅም እንዳላት የሚያመላክትም ነው። ግድቡ ኢትዮጵያ እና የተፋሰሱ ሀገራት በትብብርና በውይይት አማራጭ የውሃ ሀብትን ለጋራ ልማት እና እድገት መጠቀም እንደሚቻል በግልጽ ያሳዩበት ነው። የዓለም አቀፍ መገናኘ ብዙሃንን ከፍተኛ ትኩረት የሳበው የሕዳሴ ግድብ ምርቃት የዜና ዘገባዎች ግድቡ የክፍፍል ሳይሆን የአፍሪካ አንድነት እና ለውጥ ተስፋ መሆኑ ተንጸባርቋል። ፍሪካ በአጀንዳ 2063 ሁሉን አቀፍ እድገት እና ዘላቂ ልማትን እውን ለማድረግ እየተጋች ይገኛል። ሕዳሴ ግድብ ከዚህ አህጉራዊ ማዕቀፍ አንጻር ትልቅ አህጉራዊ ስኬት ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ግድቡ መብራትን የሚያበራ ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን የመልማት አቅም የሚያስመነድግ መሆኑ የሚያጠያይቅ አይደለም። ዓለም የሕዳሴ ግድብ የራስን መቻል፣ የአይበገሬነት፣ የለውጥ እና መጻኢ ጊዜን ብሩህ የማድረግ ተምሳሌት እንደሆነ በግልጽ መስክሯል።  
ትንታኔዎች
ማድያት እና ህክምናው
Sep 29, 2025 282
ማድያትን ለማከም አስቸጋሪ መሆኑንና በታካሚዎች ላይም የሥነ ልቡና እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ ጫና ሊያመጣ የሚችል መሆኑን የቆዳ ሕክምና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ስለ ማድያት መንስዔ፣ ስለሚከሰትበት የሰውነት ክፍል፣ ማድያት ያለበት ሰው ማድረግ ስላለበት ጥንቃቄ፣ ቆዳን ስለሚያስቆጣ ሠርካዊ ልማድ እና ሕክምናውን በተመለከተ በራስ ደስታ ዳምጠው መታሰቢያ ሆስፒታል የቆዳ እና አባላዘር በሽታዎች ስፔሻሊስት ዶክተር አደራጀው ብርሃን ከኢዜአ ቆይታ አድርገዋል። በማብራሪያቸውም፤ በቆዳ ውስጥ ያሉ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) ከመጠን በላይ ቀለም ሲያመርቱ ማድያት ተከሰተ እንደሚባል ገልጸዋል። ለዚህም መንስዔው የተፈጥሮ ተጋላጭነት ከተለያዩ ቀስቃሽ ምክንያቶች ጋር የሚያደርጉት መሥተጋብር መሆኑን አስረድተዋል። 👉 የማድያት መንስዔ ምንድን ነው? 1ኛ. የሆርሞን ለውጥ፡- በእርግዝና ወቅት ወይም የወሊድ መቆጣጠሪያ ሲጠቀሙ የሚኖር የሆርሞን ለውጥ ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ያደርጋል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። 2ኛ. የፀሐይ ጨረር፡- ከልክ ያለፈ ፀሐይ ቀለም አምራች ኅዋሶች(ሴሎች) በብዛት ቀለም እንዲያመርቱ ስለሚያነቃቃ፤ የፀሐይ ጨረር ዋነኛ ቀስቃሽ እና አባባሽ ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። 3ኛ. የዘር ሐረግ፡- በቤተሰብ ውስጥ ማድያት ካለ በዘር የመተላለፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑንም ይናገራሉ። 4ኛ. የቆዳ ዓይነት፡- ጥቁሮች (ከቡናማ እስከ ጥቁር የቆዳ ቀለም ያላቸው) ንቁ ቀለም አምራች ሴሎች ስላሏቸው ለማድያት የሚኖራቸው ተጋላጭነት ከፍተኛ መሆኑን ነው የተናገሩት። 5ኛ. ሌሎች መንስዔዎች፡- ሙቀት (የሚታዩ እና የማይታዩ ጨረሮች እንዲሁም የምድጃ እሳት)፤ የተለያዩ መድኃኒቶችና የመዋቢያ ምርቶች፤ የእንቅርት ዕጢ ህመሞች እንዲሁም ጭንቀት ማድያት እንዲከሰት ወይም እንዲባባስ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል መሆናቸውንም የሕክምና ባለሙያው አስገንዝበዋል። 👉 ማድያት በየትኛው የቆዳ ክፍል ላይ ይከሰታል? ማድያት ከሚከሰትበት የቆዳ እና የሰውነት ክፍሎች አንጻር በሁለት ከፍሎ ማየት እንደሚቻል ዶክተር አደራጀው አንስተዋል። እነሱም 1ኛ. ከሚከሰትበት የቆዳ ክፍል አንጻር፡- ማድያት በውስጠኛውም ሆነ በላይኛው የቆዳ ክፍሎች ላይ ወይም በሁለቱም ላይ ሊከሰት ይችላል ብለዋል። 2ኛ. ከሚከሰትበት የሰውነት ክፍሎች አንጻር፡- የሕክምና ባለሙያው እንዳሉት 60 በመቶ ማድያት ግንባር፣ ጉንጭ፣ አፍንጫ፣ የላይኛው ከንፈር እና አገጭ ላይ ይከሰታል ብለዋል። 30 በመቶው ደግሞ ጉንጭ እና አፍንጫ ላይ እንዲሁም 10 በመቶው የአገጭ መስመርን ተከትሎ እንደሚከሰት አስረድተዋል። በሌላ በኩል አልፎ አልፎ ከፊት የሰውነት ክፍሎች በተጨማሪ በደረት፣ አንገት እና ክንድ ላይ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩንም ጠቁመዋል። 👉 የማድያት ባሕርይ ማድያት የቆዳ ቀለም ለውጥ ያመጣል፤ በግራና በቀኝ የፊት ክፍል ይወጣል። የማሳከክ ወይም የህመም ስሜት እንደሌለውም ዶክተር አደራጀው አስረድተዋል። • ማድያት በላይኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ነጣ ወይም ጠቆር ያለ ቡናማ የሆነ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አመላክተዋል። • ማድያት በውስጠኛው የቆዳ ክፍል ላይ ሲከሰት፡- ሰማያዊ ግራጫ ወይም ጠቆር ያለ ግራጫ የቆዳ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይ አንስተዋል። • ማድያት በሁለቱም የቆዳ ክፍሎች ላይ ሲከሰት፡- የተቀላቀለ የቡናማ እና ግራጫ ቀለም ለውጥ እንደሚያሳይም ባለሙያው አብራርተዋል። 👉 ማድያት ያለበት ሰው ምን ዓይነት ጥንቃቄዎችን ማድረግ ይገባዋል? 1ኛ. ወርቃማ ጥንቃቄ፡- • ተከታታይና ጥብቅ የሆነ የፀሐይ መከላከያ መጠቀም ይገባል ይላሉ የሕክምና ባለሙያው። በዚህም መሠረት ከቤት ከመውጣት ከ20 እስከ 30 ደቂቃ ቀደም ብሎ የፀሐይ መከላከያ ክሬሞችን መቀባትና በሁለት ሠዓት ልዩነት እየደረቡ መቀባት። • በሌላ በኩል ከ4 እስከ 10 ሠዓት ያለው የፀሐይ ሙቀት ለቆዳ ህመም አጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ከፀሐይ መከላከያ ክሬም በተጨማሪ ጥላና ኮፍያን መጠቀም እንደሚገባ መክረዋል። 2ኛ. ቆዳን የሚያስቆጣ የቆዳ እንክብካቤ (መስተካከል ያለበት ልማድ)• ቆዳን የሚያስቆጡ መታጠቢያዎች(ሳሙናን ጨምሮ ሌሎችም) እንዲሁም መዋቢያዎችና የሚቀቡ ነገሮች (ኮስሞቲክስን ጨምሮ ሌሎችም) አለመጠቀም ይገባል ይላሉ። • ለቆዳ ተስማሚ የሆኑ ማለስለሻዎችን በደንብ መጠቀም እንደሚገባም ይመክራሉ። 3ኛ. በሐኪም የታዘዙ መድኃኒቶችን በአግባቡ መጠቀም • በሐኪም የታዘዘ መድኃኒትን በአግባቡ(ሳያቆራርጡ) መጠቀም እንደሚመከር ያስረዱት ዶክተር አደራጀው፤ እንደ ማድያቱ እና እንደ ሰዎቹ ቆዳ ዓይነት መድኃኒቱ ለውጥ የሚያሳይበት ጊዜ ስለሚለያይና ከ8 እስከ 12 ሣምንት ሊወስድ ስለሚችል ታግሶ በደንብ ቢጠቀሙ መልካም ነው ይላሉ። 4ኛ. የተለያዩ የሕክምና አማራጮችን መጠቀም• የሕክምና ባለሙያው እንደሚመክሩት፤ በዘርፉ ያሉ የተለያዩ የሕክምና ዓይነቶችን ለምሳሌ እንደ ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ ያሉትን በሐኪም ምርመራ መሠረት መጠቀም ይገባል። 5ኛ. ከወሊድ መቆጣጠሪያ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የተከሰተ ማድያት ከሆነ ከሕክምና ባለሙያ ጋር በመመካከር ሌላ አማራጭ መጠቀም እንደሚገባም አንስተዋል። እንዲሁም ጭንቀትን መቀነስ እንደሚገባ መክረዋል። 👉 የማድያት ሕክምናን በተመለከተ የማድያት ሕክምና በጣም አስቸጋሪ ከሚባሉትና ረጂም ጊዜ ከሚወስዱ እንዲሁም በመመላለስ ከሚያስቸግሩ የቆዳ ሁኔታዎች አንዱ መሆኑን ዶክተር አደራጀው ገልጸዋል። በሕክምና ማድያቱ የጠፋላቸው ሰዎች መኖራቸውን አረጋግጠው፤ በሌላ በኩል በሕክምና ሂደት የማድያቱ ሁኔታ ከነበረበት እየቀነሰ ለውጥ የሚታይበት ሁኔታ አለ ብለዋል። ይህን ለውጥ የተለያዩ አማራጮችን በመጠቀም ማስቀጠል እንደሚገባም ይመክራሉ። እንክብካቤው ከተቋረጠ ግን ማድያቱ እንደገና የሚመለስበት ሁኔታ መኖሩን አስገንዝበዋል። 👉 የማድያት ሕክምና አማራጮች የሚቀቡ መድኃኒቶች፣ የሚዋጡ መድኃኒቶች፣ ሌሎች የሕክምና አማራጮች(ኬሚካል ፒልስ፣ የቆዳ ሕክምና እና ማይክሮ ኒድሊንግ)፣ የፀሐይ መከላከያ አማራጮችን በአግባቡ አዘውትሮ መጠቀም እንደሚገባ ይመክራሉ።
በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ  7 ቀናት የሚኖሯት ጳጉሜን…
Sep 5, 2025 1335
ጳጉሜን በሦስት ዓመታት አምስት፣ በአራት ዓመታት ውስጥ ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት ውስጥ አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት ይኖሯታል። 👉 ‘ጳጉሜን’ ማለት ምንድን ማለት ነው? ‘ጳጉሜን’ የሚለው ስያሜ “ኤፓጉሜኔ” ከሚለው የግሪክ ቃል መምጣቱን በቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የነገረ መለኮትና የሥነ-ልቡና መምህር አባ ጌዴዎን ብርሀነ ይገልጻሉ። ትርጉሙም “ተውሳክ ወይም ተረፍ” ማለት መሆኑን ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል። (አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መዝገበ መጽሐፈ ሰዋስው ወግስ ወመዝገብ ቃላት፤ ገጽ ፱፻፭) ላይም “በዓመቱ መጨረሻ ላይ አምስት ወይም ስድስት ቀን በመሆን ተጨማሪ ሆና የምትመጣ መሆኗ ተገልጿል። በዚሁ መሠረት በሦስት ዓመት አምስት፤ በአራት ዓመት (በዘመነ ዮሐንስ) ስድስት እንዲሁም በ600 ዓመታት አንድ ጊዜ ሰባት ቀናት እንደምትሆን ተመላክቷል። 👉 የጳጉሜን መሠረት? ይህን በተመለከተ መምህር አባ ጌዴዎን ሲያስረዱ፤ በየቀኑ የሚተርፉ ተረፈ ደቂቃዎችና ሰከንዶች ቀናትን እያስገኙ ተጠራቅመው ከዓመቱ በስተመጨረሻ አምስት ዕለታት ይተርፋሉ ይላሉ። በዚህም ጳጉሜን የተባሉ አምስት ዕለታት እንደሚገኙ ጠቁመው፤ አንድ ዓመት ደግሞ 365 ዕለት ከ15 ኬክሮስ ከ6 ካልኢት ይሆናል ሲሉ ይገልጻሉ። 15ቱ ኬክሮስ በአራት ዓመት ስድስት ጳጉሜንን ይወልዳል ያሉት መምህሩ፤ ስድስቱ ካልኢት ደግሞ በ600 ዓመት ሰባተኛ ጳጉሜንን ያስገኛሉ በማለት አብራርተዋል። 👉 ከጭማሬ ቀንነት በተለየ ያላት ትርጓሜ ምንድን ነው? እንደ መምህር አባ ጌዴዎን ገለጻ፤ ‘ጳጉሜን’ ከተጨማሪ ቀናትነት የተሻገረ ለኢትዮጵያውያን የማንነት ዐሻራ የእኩልነት ምልክት ናት። በዓለም ዘንድ ባለው የበላይነት እና ሌላውን አሳንሶ የማየት ዝንባሌ እንደነዚህ ያሉ የጥበብ መንገዶች የኢትዮጵያውያንን ማንነትና በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የቀዳሚነት ቦታም ከሚያሳዩ ምልክቶች መካከል አንዱ በመሆኑ የማንነት መገለጫ ናት ይላሉ። ምክንያቱም ከማንም ያልተወሰደ የራስ ማንነት መኖሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን በዓለም ዘንድ የነበራቸውን የመፈላሰፍ፣ የስልጣኔና አካባቢያቸውን በንቃት የመገንዘብ አቅም የሚያሳይ ስለሆነ ብለዋል። ጳጉሜን ኢትዮጵያን ከቀደምት ስልጡን ሀገራት መካከል ቀዳሚ የስልጣኔ ፋና የፈነጠቀባት ለመሆኗ ማሳያ ስለመሆኗም ይናገራሉ። የሰው ልጅ አካባቢውን በንቃት መገንዘብ መጀመሩ እና የሰማያዊ አካላትን የማይዋዥቁ ክስተቶች በመከታተል የማይታየውንና የማይሰፈረውን የጊዜ ርዝማኔ በብርሃናት እየሰፈረና እየለካ፤ ዕለታትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትን፣ ወቅትን፣ ዓመታትን፣ አዝማናትን እና ሌሎች ዐውዳትን መቀመሩን ጠቅሰዋል። በዚህም የጊዜ ልኬት ከሥነ-ፈለክ እና ከሐሳበ-ከዋክብት ጋር በእጅጉ የተቆራኘ እንዲሆን አድርጎታል ነው ያሉት። በአጭሩ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን ከሚያዩአቸው ተደጋጋሚ ሁነቶች በመነሳት የጊዜ አሃዶችን ወስነዋል፤ ክፍፍሎችንም በይነዋል ብለዋል መምህር አባ ጌዴዎን። በተለይም ለዕይታቸው ቅርብ የሆኑት የፀሐይ እና የጨረቃ ያለማቋረጥ መውጣት እና መግባት፣ የሚወጡበት እና የሚገቡበትም የጊዜ መጠን በአንጻራዊነት ቋሚ በመሆኑ ለቀን አቆጣጠራቸው ዋነኛ ግብዓቶች እንደሆኗቸው ተናግረዋል። በሂደትም የዑደታቸውን የጊዜ መጠን በሚገባ ተረድተው፣ የዑደታቸውን ህጸጾች ዐወቁ ይላሉ። በዚህ ብቻ ሳይገደቡ የሰማይ አሰሳን ከፀሐይ እና ጨረቃ ወደ ሌሎች አፍላካት፣ ወደ ከዋክብትም ጭምር ማስፋታቸውን ነው የሚገልጹት። በዚሁ መሠረት ኢትዮጵያ የራሳቸው የቀን መቁጠሪያ ቀመር ካላቸው ቀደምት ሀገራት መካከል አንዷ መሆን መቻሏን አስገንዝበዋል። ለዚህም በዋቢነት ከሚጠቀሱት ጥንታዊ መዛግብቶቿ መካከል መጽሐፈ ሄኖክን እና አቡሻኽርን አንስተዋል። 👉 ከነበረው ወደ ሌላኛው ዓመት መሻገሪያ እንደመሆኗ ሰዎች በዚህ ወቅት ምን አይነት ሥነ-ልቡናዊ ዝግጅት እንዲያደርጉ ይመከራል? ጊዜ የለውጥ መስፈሪያ (መለኪያ ወይም መለያ ድንበር) መሆኑን የሚገልጹት መምህር አባ ጌዴዎን፤ ለውጥ ያለጊዜ፣ ጊዜም ያለ ለውጥ አይሆኑም፤ ትርጉምም የለውም ይላሉ። ጊዜ በዚህ ዓለም የማይቋረጥ ሂደት፤ የማይቆም የለውጥ ጥያቄ መሆኑንም ያስገነዝባሉ። በዚህ የለውጥ ምክንያት የሰው ልጅ የሚኖረው ከተሰጠው ወይም ካለው እየቀነሰ እንጅ እየጨመረ እንዳልሆነም ይጠቅሳሉ። ስለዚህ ጳጉሜን የማንቂያ ደወል ናት፤ የአዲስ ዘመን ማብሰሪያ አዲስ ዘመን በለውጥ ምክንያት የተገኘ በመሆኑ ከነበረው የዕለታት ድምር ባሻገር አዲስ የሚል ቅጽል ይዞ መጥቷል ይላሉ። ስለዚህ ጳጉሜን ምን አዲስ ነገር አለ የሚል የሕይወት ጥያቄ አስከትላ የመጣች በልባችን ምኅዋር የምታቃጭል ናት ብለዋል። በጳጉሜን ብዙዎች በጽሞና ሆነው ራሳቸውን የሚያዳምጡባት ወደውስጥ በጥልቀት የሚመለከቱባት በመሆኗ ባለፉት ጊዜያት ያልተሳኩትን በቀጣይ ለማሳካት አዳዲስ ሐሳቦችን እና እቅዶችን በማዘጋጀት ለቀጣዩ ምዕራፍ የምታሻግር ናት በማለት ገልጸዋል።
የባሕር  በር የሌላቸው ሀገራት አንገብጋቢው ጉዳይ
Aug 6, 2025 2098
የባህር በር ጉዳይ በሀገራት ዘንድ በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ግዙፍ ኢኮኖሚና ሰፊ ህዝብ ላላቸው ሀገራት ሕልውና ጉዳይ ሆኗል። በቱርክሜኒስታን አዋዛ ከተማ ሶስተኛው ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራት ጉባዔ በመካሄድ ላይ ይገኛል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም በጉባኤው መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት አስተላለፈዋል። ዋና ፀሐፊው ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በተለይም መልኩ እየተለዋወጠ ባለው ዓለም፤ በአየር ንብረት ለውጥና መሰል ተጽዕኖዎች ሳቢያ መልከ ብዙ ፈተና እንደተደቀነባቸው ገልጸዋል። በተለይ ለአንዳንዶቹ ህልውናቸውን እየተፈታተነ ስለመሆኑም አጽንኦት ሰጥተዋል። የዋና ጸሐፊው ንግግርም ፦ ዛሬ ከዚህ የተሰባሰብነው ለማንክደው አንድ ዕውነት ነው። መልክዓ ምድር መዳረሻን መወሰን የለበትም። ነገር ግን በአፍሪካ፣ በኤዥያ፣ በላቲን አሜሪካና በአፍውሮፓ 32 ሀገራት ባህር በር ስለሌላቸው የማደግ ዕድላቸው ተገድቧል፤ ኢ-ፍትሃዊነትንም አስፍቷል። ሀገራችሁ አያሌ ተግዳሮቶች ተጋርጦባቸዋል። ዕድገታቸው እንዲወሰን፣ በከፍተኛ የወጪ ንግድ ትራንስፖርት እንዲበዘበዙና በዓለም ገበያ ተደራሽ እንዳይሆኑ ፈተና ገጥሟቸዋል። በርካቶች በጥሬ ዕቃ ኤክስፖርት እንዲወሰኑ፣ ለተለዋዋጭ ዓለም አቀፍ ገበያ እንዲጋለጡ ብሎም በጠባብ ኢኮኖሚያዊ መሰረት እንዲታጠሩ አድርጓቸዋል። በሌላ በኩል የዕዳ ጫና ለመልከ ብዙና ዘላቂነት ላለው ችግር ዳረጓቸዋል። አንድ ሶስተኛው የዓለማችን ባህር በር አለባ ሀገራትም ለደህንነት እንዲጋለጡና የግጭት አዙሪት ችግር እንዲገጥማቸው ተገደዋል። ምንም እንኳን 7 በመቶው የዓላማችን ህዝብ ድርሻ ቢይዙም በዓለም ኢኮኖሚ አንድ በመቶ ብቻ ድርሻ ይዘዋል። ይህም ምንጊዜም ኢ-ፍትሃዊነትና መገለል ሁነኛ ማሳያ ነው። ይህ የኢ-ፍትሃዊነት መልክ ዘላለማዊ መሆን የለበትም። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በዓለም የፋይናንስና የንግድ መዋቅር ውስጥ ለከፍተኛ ችግር የተጋለጡ ናቸው። በበይነ-ዓለም ትስስር በገሀድ በሚታይበት የዛሬው የዓለም መልክ ስርዓታዊ መድሎና መገለል በይፋ የደረሰባቸው ሀገራት ናቸው። ይህም በብዙ ምክንያቶችም የቅኝ ግዛት አሻራ ምልክት ነው። በቅርብ ጊዜ ትውስታዎች እንኳን ከኮቪድ 19 እስከ አየር ንብረት ለውጥ ቀውሶች፣ ከአቅርቦት ሰንሰለት መስተጓጎል እስከ ግጭት እንዲሁም በጂኦፖለቲካዊ ውጥረቶች ሳቢያ ባህር በር የሌላቸው ሀገራት ዘላቂ የልማት ግቦችን ዕውን ለማድረግ ተቸግረዋል። ይህ ጉባኤ ችግሮችን ከማንሳት ባሻግር መፍትሄዎች ላይ ማተኮር አለበት። የቀጣይ ዘመን የእድገት መሻት ጉዞን መቀየስ ብሎም ባህር በር አልባ ታዳጊ ሀገራትን የማልማት ዕድሎች በጋራ መግለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምክር ይገባል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅትም በዚህ ረገድ ከሀገራቱ ጎን የቆመ ነው። በቀጣይ አስርት ዓመታት በትብብር መሰራት ካለባቸው ጉዳዮች መካከል አንዱ መዋቅራዊ ሽግግርን ማሳለጥ እና ኢኮኖሚያዊ ስብጥርን ማብዛት ላይ መተኮር ይገባል። ምክንያቱም እነዚህ ሀገራት በሰው ሃይል እና በተፈጥሮ ሀብት የታደሉ ቢሆንም በፋይናንስ እጥረትና በገበያ እጦት ይህን አቅም ተጠቅመው መልማት አልቻሉም። ወሳኝ የሆኑ እሴት ጨማሪ ኢንዱስትሪዎችን መገንባት፣ ሀገር ውስጥ ፈጠራዎችን ማጎልበት እንዲሁም ለቀጣናው ለትውልድ ትሩፋት የሚያቋድስ አካታች ልማትን ዕውን ማድረግ ይሻል። የሀገራቱን የገበያና የመልክዓ ምድር ተግዳሮቶችን ለማቅለል አንዱ መፍትሄ የዲጂታላይዜሸን ሽግግር ነው። በዲጂታል ምህዳር ተደራሽነት ለማቅለልም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ስራዎች መጠንከር አለባቸው። የግል ዘርፉን ማጠናከርም ኢ-ፍትሃዊነትና ተደራሸነትን ችግርን ለማቅለል ያግዛል። ሀገራቱ በቋንቋ፣ በባህልና በጥበብ በጥልቅ የተቆራኙ ናቸው። በሀገራቱ መካከል ያለው የተቆራረጠ ሎጂስቲክስ፣ ያልተሳለጠ የድንበር ግብይት፣ የተሟላ መሰረተ ልማት አለመኖር በዓለም ገበያ ተወዳደሪና ተደራሽ ለመሆን አልቻሉም። በመሆኑም ድንበር ዘለል የሆኑ ትስስሮችን ማሳለጥ በተለይም ሀገራትን የሚያስተሳሰሩ ኮሪደሮችን መገንባት፣ የጭነት ሎጂስቲክስን ማሳለጥ፣ የሃይል እና የአየር ትራንስፖርት ትስስርን መጨመር ያስፈልጋል። ይህን መንገድ በመከተል በቀጣናውና በዓለም ገበያ መግባት ብሎም ከጥሬ ዕቃ አቅራቢነት ወደ እሴት የተጨመረባቸው ምርቶችን ማቅረብ መሸጋገር ይቻላል። በዓለም አቀፍ ደረጃ የንግድ ግብይት መልክን መለወጥ፣ የትብብርና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተቃኘ አካሄድ መከተል ይገባል። ዓለም አቀፍ የባለብዙ ወገን የፋይናንስ ተቋማትም የበይነ ሀገራት የድንበር ላይ ትስስርና የጋራ ልማት ላይ ተገቢውን የኢንቨስትመነት ልማት ፋይናንስ ማቅረብ ይገባቸዋል። ባህር በር የሌላቸው ሀገራት በቀጣናው ደረጃ ከተሰባሰቡ ልማትን ዕውን ማድረግ ያስችላልና። ባህር በር አልባ ሀገራት ምንም እንኳን ከዓለማችን ሀገራት የበካይ ጋዝ ልቀታቸው ለከ3 በመቶ ያነሱ ቢሆነም የአየር ንብረት ለውጥ ቀውስ ገፈት ቀማሾች ግን እንርሱ ናቸው። ከሰሃራ በርሃ መስፋፋት እስከ በረዶ የሚቀልጥባቸው ተራራማ ሀገራት፣ የኤስያ ሀገራት አስቸጋሪ የአየር ጸባይ ለውጥ፣ በከባድ ዝናብና አውሎንፋስ የሚመቱ የላቲን አሜሪካ ሀገራት ለዚህ ማሳያ ናቸው። የአየር ንብረት ለውጥ ባህር በር አልባ ሀገራትን እየበላቸው ነው። የአየር ንብረት ለውጥና ባህር በር አልባነት ተዳምሮ ዕድገታቸውን እንዲወሰን ለአንዳንዶቹም በህልውናቸው ላይ አደጋ ደቅኗል። በተባበሰው የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ ሳቢያ በአንድ አዳር በሚደርስ የመሰረተ ልማት ውድመት የሀገራት ዓለም አቀፍ ንግድ ተሳትፎ አደጋ ውስጥ ይወድቃል። በመሆኑም ቃል የተገቡ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖ መቋቋሚያ ፋየናንስ መተግበር፣ ተዕጽኖ የሚቋቋም መሰረተ ልማት መዘርጋት ይሻል” በማለት ነበር መልዕክታቸውን ያስተላለፉት። በአረንጓዴ ልማት፣ በፋይናንስ ማሰባሰብ፣ በብድር አቅርቦት እና ወለድ አያያዝና ትግበራ ጉዳይም ልብ መባል ያለበትን ጉዳይ ጠቅሰዋል። ባህር በር አልባ ሀገራት በጋራ ነጋቸውን ለማሳመርና ፈተናዎቻቸውን ለመሻገር በትብብር እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ የባህር በር ለማግኘት ጥያቄዋን በይፋ ከገለጸች ውላ አድራለች፤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) የባህር በር ጥያቄ የህልውና ጉዳይ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።
ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሽግግር ለምን አስፈለጋት?
Jul 19, 2025 2296
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቲኒዮ ጉቴሬዝ አነሳሽነት እ.አ.አ 2021 የተመድ የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በኒው ዮርክ በበይነ መረብ አማራጭ ተካሄዷል። “የህዝቦች ጉባኤ” እና “የመፍትሄ ጉባኤ” የሚሉ ስያሜዎች የተሰጠው ጉባኤ ላይ ከ193 ሀገራት የተወጣጡ ከ51 ሺህ በላይ ሰዎች ተሳትፈውበታል። በምግብ ስርዓት ላይ የተዘጋጀ ይህ ታሪካዊ ጉባኤ ዓለም አቀፍ ሁነት ዋንኛ ግቡ የነበረው የተመድ አባል ሀገራት የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን እንዲያመጡ እና ስርዓተ ምግብን ከዘላቂ ልማት ግቦች በተለይም ከግብ ሁለት ረሃብን ማጥፋት ጋር ማስተሳሰር ነው። ጉባኤው በአምስት ዓበይት የትኩረት ነጥቦች ላይ ያተኮረ ነበር።   ለሁሉም ዜጋ ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ ተደራሽ ማድረግ፣ ከብክነት ወደ ዘላቂ የምግብ አጠቃቀም መሸጋገር፣ ተፈጥሮን ያማከለ የምግብ ምርማነትን ማሳደግ፣ እኩልነትን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ሁኔታን ማጠናከር እና ለአደጋዎችና ጫናዎች የማይበገር ጠንካራ የምግብ ስርዓት መገንባት ጉባኤው የተወያየባቸው ጉዳዮች ናቸው። ጉባኤው በወቅቱ አባል ሀገራት ሁሉን አቀፍ የምግብ ስርዓትን በመፍጠር የዘላቂ ልማት ግቦችን እንዲያሳኩ ጥሪ አቅርቧል። የተመድ የዓለም የምግብ ደህንነት ኮሚቴ የምግብ እና የስነ ምግብ ከፍተኛ የባለሙያዎች ፓናል የስርዓተ ምግብ አካሄድ ከባቢ አየር፣ ዜጎች፣ ግብአቶች፣ ሂደቶች፣ መሰረተ ልማቶችና ተቋማትን ጨምሮ ሁሉንም ተዋንያን ያሳተፈ መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል።   ስርዓተ ምግብ ምርት፣ ማቀነባበር፣ ስርጭት፣ ማዘጋጀት፣ መመገብ እና የተረፈ ምግብ አወጋገድን አቅፎ የያዘ እና ይህም ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ከባቢ አየር ላይ ቀጥተኛ ተጽእኖ ያለው ነው። የባለሙያዎች ፓናሉ የምግብ ስርዓት ትራንስፎርሜሽን ዜጎች፣ ምድር፣ ብልጽግና፣ ሰላም እና አጋርነት ላይ ያውጠነጠነ መሆኑን ይገልጻል። ፓናሉ ይህን ከግምት ውስጥ በማስገባት በምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ያመጣል ያላቸውን ስድስት ሀልዮታዊ ማዕቀፎችን ቀርጿል። ህይወት ያላቸው እና የቁስ አካላት ባህርያት፣ ከባቢ አየር የመጀመሪያው ነው። በሁለተኛ ደረጃ የተቀመጠው ቴክኖሎጂ፣ ኢኖቬሽንና መሰረተ ልማት ሲሆን ኢኮኖሚ እና ገበያ ሶስተኛውን ስፍራ ይይዛል። ፖለቲካ እና ተቋማዊ ሁኔታ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ ጉዳዮች እንዲሁም የስነ ሕዝብ ውቃሬ ሌሎች የምግብ ስርዓት ለውጥ አምጪ ምክንያቶች እንደሆኑ ተቀምጧል። ስድስቱ የምግብ ለውጥ አሳላጭ ሁኔታዎች ተፈጻሚ እና ውጤታማ የሚያደርጉ አራት ቁልፍ መስኮች እንዳሉም የባለሙያዎች ፓናሉ ያስቀምጣል። የምግብ ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስርዓቶችን መደገፍ፣ የምግብ አቅርቦት ሰንሰለትን ማጠናከር፣ የዜጎችን የምግብ አጠቃቀም ባህሪያት ላይ ለውጥ ማምጣት እና የተመጣጠኑ ንጥረ ምግቦችን ብዝሃነት ማስፋት ቁልፍ የትኩረት ጉዳዮች ናቸው።   የተቀመጡትን ማዕቀፎች፣ ለውጥን የመፍጠሪያ መንገዶች እና አስቻይ ሁኔታዎች ከፖሊሲ እና ሁሉን አቀፍ አስተዳደር ጋር በማቆራኘት የምግብ ስርዓት ላይ ለውጥ ማምጣት እንደሚገቡ ባለሙያዎቹ ምክረ ሀሳባቸውን ያቀርባሉ። የኢትዮጵያ የስርዓት ምግብ ራዕይ (EFS) መነሾም በስርዓተ ምግብ ጉባኤው እ.አ.አ በ2030 መሳካት አለባቸው ብሎ ያስቀመጣቸውን የስርዓተ ምግብ ግቦች እውን ለማድረግ ያሉ ፈተናዎች እና እድሎች ናቸው። እ.አ.አ በ2024 የወጣው የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ በጉባኤው የተቀመጡ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እና የጉባኤውን ምክረ ሀሳቦች ለመተግበር ቁርጠኛ እንደሆነች ይገልጻል። የኢትዮጵያ መንግስት እ.አ.አ ዲሴምበር 2020 የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ የአሰራር ሂደት ይፋ ያደረገ ሲሆን ሂደቱ እ.አ.አ ጃንዋሪ 2021 ተጀምሯል። የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉ የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ራዕይን በግልጽ ያስቀመጠ ነበር። በወቅቱ ሂደቱን ለማስጀመር የቀድሞ የግብርና ሚኒስትር ኡመር ሁሴን እና የቀድሞ የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ የመሯቸው የከፍተኛ ደረጃ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ሰነዶችም ተቀርጸዋል። በስርዓት ምግብ ላይ ሁለት ብሄራዊ ምክክሮች የተደረጉ ሲሆን ምክክሮችን ተከትሎ የኢትዮጵያ ስርዓተ ምግብ ሂደት ይፋ ሆኗል። ምክክሮቹ የኢትዮጵያ ምግብ ስርዓት አሁናዊ ሁኔታ አና መጻኢ ሁኔታዎች፣ የኢትዮጵያን የምግብ ስርዓት የመለወጥ ጉዞ በሚል ርዕስ የተካሄዱ ናቸው። የስርዓተ ምግብ ሂደት ቀረጻው ላይ መንግስት፣ የግሉ ዘርፍ፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የሲቪክ ማህረሰቦች፣ የምርምር ተቋማት፣ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ተቋማት ያሉባቸው ከ120 በላይ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል። ይፋ የሆነውም የስርዓተ ምግብ ሂደት ሰነድ እ.አ.አ በ2021 በጣልያን ሮም በአካል ለመጀመሪያ ጊዜ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ ላይ ቀርቦ አዎንታዊ ምላሾችን አግኝቷል። የስርዓተ ምግብ ሂደት ማዕቀፉ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አጀንዳ፣ ከ10 ዓመት መሪ የልማት እቅድ እንዲሁም ከሌሎች የፖሊሲ እና አሰራሮች ጋር የተጋመደ ነው። የኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ሁሉን አቀፍ ሪፖርት ኢትዮጵያ የስርዓተ ምግብ ለውጥ እና ሽግግር ያስፈለገባቸውን ምክንያቶች ያስቀምጣል። የምግብ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነት በሚፈለገው ደረጃ ማረጋገጥ አለመቻል፣ ፈጣን የህዝብ እድገት፣ የክትመት መጠን መስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳት እና የአየር ንብረት ለውጥ፣ እኩል ያልሆነ የዜጎች አኗኗር፣ ደካማ የምግብ ስርዓት መሰረት፣ ግብርናን ለኢኮኖሚ ያለውን ድርሻ ማሳደግ እና የምግብ ስርዓትን ከብሄራዊና ዓለም አቀፍ ግቦችን ጋር ማሰናሰን ማስፈለጉ የስርዓተ ምግብ ለውጡ መሰረታዊ ለውጥ መነሻ ናቸው። ኢትዮጵያ በስርዓተ ምግብ ሽግግር ውስጥ ስንዴን ጨምሮ በተለያዩ ሰብሎች ምርት እና ምርታማነትን በማሳደግ፣ የንጥረ ነገሮችን ብዝሃነት በማስፋት፣ የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ተደራሽነትን በማሳደግ እና የግብርና ማቀነባበሪዎችን ቁጥር በመጨመር አመርቂ ውጤቶችን አስመዝግባለች። በዚህም በዜጎች ጤና እና ገቢ እድገት ላይ ለውጦች መምጣታቸውን ሪፖርቱ ያሳያል። ብሄራዊ የምግብ ስርዓት ማዕቀፎች፣ በምክክሮች የዘርፉ ተዋንያን የማሳተፍ ሁኔታ እያደገ መምጣት፣ በምግብ ስርዓቱ በሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ስር ለውጥ አምጪ ተብለው የተቀመጡ 24 መፍትሄዎች እና ተቋማዊ አቅም ግንባታ ሌሎች የታዩ አበረታች ለውጦች ናቸው። ሰባቱ ስትራቴጂካዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብን ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣ ጤናማ የአመጋገብ ሁኔታን መፍጠር፣ አሰራሮች እና ፖሊሲዎችን በተቀናጀ መንገድ መተግበር፣ በምግብ ስርዓቱ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮችን መተግበር፣ የገበያ ተደራሽነት ማስፋት እና መረጃ አሰጣጥን ማጠናከር፣ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ህብረተሰብ ክፍሎችን መጠበቅ እና የማይበገር አቅም መገንባት እንዲሁም መሰረተ ልማቶችን ማስፋፋት፣ ዘላቂነት ያለው የከተሜነት እድገትን መፍጠር እና ክህሎት ልማት ላይ ያተኮሩ ናቸው።   ደህንነቱ የተጠበቀ እና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በሚፈለገው መጠን ተደራሽ አለማድረግ፣ ደካማ የምግብ ደህንነት መሰረተ ልማት፣ የግብርና ሜካናይዜሽን አለመስፋፋት፣ የከባቢ አየር ጉዳቶች፣ የቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያሉ ክፍቶች እና የዜጎች የአኗኗር ሁኔታ ለይ ለውጦች ቢኖሩም አመርቂ አለመሆን፣ የፋይናንስ ውስንነት እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገሩ ቴክኖሎጂዎች ተደራሽነት በምግብ ስርዓቱ ዋና ፈተናዎች ተብለው የተቀመጡ ናቸው። የምግብ ስርዓትን አስተዳደርን እና የባለድርሻ አካላት ቅንጅትን ማጠናከር፣ የቴክኒክ ድጋፍ ሰጪ መዋቅሮችን መዘርጋት፣ የመንግስት እና የግል አጋርነትን ማጠናከር፣ አቅምን መገንባት እና የምግብ ስርዓት አጀንዳ ዘላቂነት ባለው እና በተቀናጀ ሁኔታ ለማህበረሰቡ ማስገንዘብ ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ተብለው ከተለዩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ። የገበያ ትስስርን ማጠናከር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ማጣጣሚያ እቅዶች እና ስትራቴጂዎችን ማቀናጀት እንዲሁም ወጣቶች፣ ሴቶች እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎችን ጨምሮ የስርዓተ ምግብ ትግበራው ሁሉን አካታችነት የበለጠ ማረጋገጥ ቀጣይ የቤት ስራ ተብለው የተያዙ ናቸው። በአጠቃላይ የስርዓተ ምግብ ማዕቀፉን በየጊዜው በመፈተሽ እና የሁኔታዎችን ተለዋዋጭነት ከግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ የአስተዳደር መዋቅርን በማሻሻል እ.አ.አ በ2030 የተያዙ ግቦችን ለማሳካት በትኩረት እንደሚሰራ ሁሉን አቀፍ ሪፖርቱ ያመለክታል። በአዲስ አበባ ከሐምሌ 20 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም በሚካሄደው ሁለተኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስርዓተ ምግብ ጉባኤ በስርዓተ ምግብ ላይ እያከናወነች ያለውን ስራ ለዓለም የማሳወቅ ስራ ታከናውናለች። በስርዓተ ምግብ ትራንስፎርሜሽን ያላትን ተሞክሮዎች በዋናው ጉባኤ እና በጎንዮሽ ሁነቶች ላይ ታቀርባለች። የጉባኤው ተሳታፊዎችም የኢትዮጵያን የስርዓተ ምግብ የተግባር ስራዎች እና ውጤቶች በመስክ ምልከታቸው ይቃኛሉ።
ልዩ ዘገባዎች
ባጃጅ ላይ ወድቆ የተገኘው የአደራ ገንዘብ- 82 ሺህ 265 ብር
Mar 5, 2025 5648
በአማራ ክልል ዋግኸምራ አስተዳደር የሰቆጣ ከተማ ነዋሪው ባለባጃጅ ወጣት ሠለሞን ቢምረው ተሳፋሪ ደንበኞቹን ከቦታ ቦታ በማዘዋወር ዕለታዊ ተግባሩን ይከውናል። ዛሬ ማለዳ ታዲያ በሰቆጣ ወረዳ የሰርክ ተግባሩን እያከናወነ ሳለ በድንገት ከአንድ ተሳፋሪ የተረሳ በኬሻ የተቀመጠ ንብረት ባጃጁ ውስጥ ያገኛል። ሰለሞን ቢምረው ማንነቱን ባላወቀው ተሳፋሪ የተረሳው ምንነቱን ያላወቀው በኬሻ የተቋጠረ ንብረት ገንዘብ መሆኑን ያወቀው ከደቂቃዎች በኋላ ነበር። 'ታማኝነት ለራስ ነው' የሚለው ወጣት ሰለሞን፥ ከተሳፋሪ ደንበኛ የተረሳን መጠኑን ያላወቀው ገንዘብ ለመመለስ ተጣደፈ። ተሳፋሪውን በእግር በፈረስ ማፈላለግ ይጀምራል። በሌላ በኩል የሰቆጣ ወረዳ ነዋሪዋ ወይዘር ኃይሌ በአደራ የተረከቡትን በኬሻ የተቋጠረ 82 ሺህ ብር በላይ ገንዘብ ፌርማታ ላይ ከባጃጅ ሲወርዱ መርሳታቸውን ካወቁበት ቅጽበት ጀምሮ በደንጋጤ ድባቴ ውስጥ ገብተዋል። ጉዳያቸውን ለፖሊስ አሳውቀው የአደራ ገንዘባቸውን በይገኛል ተስፋ እና ጭንቀት የባጃጅ አሽከርካሪውን ፍላጋ በየፌርማታው እየኳተኑ ነው። ተሳፋሪ እና አሳ'ፋሪ በየፊናው መፈላለጉን ተያያዙት። በዚህ መሀል የባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን ቢምረው ወደ ተሳፋሪዋ ወይዘር ኃይሌ ድንገት ከተፍ ይላል። የወይዘሮ ወይዘር ደስታ ወደር አጣ። አሳፋሪው ሰለሞንም እፎይታ ተሰማው። በተለይ የአደራ ገንዘብ መሆኑን ሲረዳ። ባጃጅ አሽከርክሪው ሰለሞን እና ተሳፋሪዋ ወይዘሮ ወይዘር በፖሊስ ፊት ንብረት ተረካከቡ። ወጣቱ ሰለሞን እንደገለጸው የተሳፋሪ ንብረት በመመለሱ ደስተኛ ነው። ለወይዘሮ ወይዘር አደራ ያስረከበችው የገንዘቡ ባለቤት ወይዘሪት ወለለ ንጉስ፤ በሰለሞን ቢምረው ነባይነት(ታማኝነት) እንዳስገረማቸው ይናገራሉ። በዚህ ወቅት ይህን ያህል ገንዘብ አግኝቶ መመለስ በዕውነቱ በነፍስም በስጋም የሚያስመሰገን በጎ ምግባር ነው ስትል አመስግናለች። የሰቆጣ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ደሳለኝ አባተ ወጣት ሰለሞን ከአሁን ቀደምም ሞባይል ጥለው የሄዱትን ለባለቤቱ በታማኝነት መመለሱን አስታውሰዋል። አሁን ደግሞ በኬሻ የተቋጠረን 82 ሽህ 265 ብር ከግል ይልቅ የህዝብን ጥቅም በማስቀደም ለግለሰቧ በታማኝነት ማስረከቡን አረጋግጠዋል። ይህን መሰል በጎ ምግባር በሁሉም የማህበረሰብ ዘንድ በአርዓያነት ሊወሰድ የሚገባው ነው ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።
"የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ"- የዕልፍ ሕጻናት አድኑ ላሌ ላቡኮ አዲስ ፍኖት
Dec 13, 2024 4269
  ሚንጊ የታዳጊዎችን ተስፋና ሕልም ብቻ ሳይሆን ሕልውና የነጠቀ ጎጂ ባህላዊ ልማዳዊ ድርጊት ነው። በደቡብ ክልል ደቡብ ኦሞ ዞን እንደ ካራ፣ ሀመርና ቤና ህዝቦች ዘንድ የሚዘወተረው ሚንጊ፤ በአካባቢው ልማድ በታችኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ቅዱስ፣ በላይኛው ድድ ጥርስ የሚያበቅሉ እንስሳት ደግሞ ርኩስ የሚል ስያሜ ይሰጣል። የላይኛው የወተት ጥርሳቸው ቀድሞ የሚበቅል ሕጻናት እንደ እርኩሳን እንስሳት ከመጥፎ መንፈስ ጋር ተቆጥሮ ለማህበረሰቡ የማይበጅ፣ አድጎም ለቤተሰቡ ጠንቅ ተቆጥሮ የመገደል ዕጣ ፈንታ ይገጥማቸዋል። በተመሳሳይ በማህበረሰቡ አባል ሴት ከትዳር በፊት ልጅ ከወለደች የተወለደው ሕጻን በ'ሚንጊ'ነት ይፈረጃል። በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናት ደግሞ መርገምት፣ ቁጣ፣ ርሀብ በሽታ… መንስዔ እንደሚሆኑ ታምኖ ከጥልቅ ወንዝ መጣል፣ ወደ ገደል መወርወር አልያም በጫካ ውስጥ የመጣል መጥፎ ዕጣ ይጠብቃቸዋል። ቤተሰባቸውን በዚህ ጎጂ ባህላዊ ድርጊት ያጡት አቶ ላሌ ላቡኮ 'ሚንጊ'ን ከመሰረቱ ለመንቀል 'የኦሞ ቻይልድ' መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት በማቋቋም ውጤታማ ስራዎች አከናውነዋል። አሁን ደግሞ የእስካሁን ጥረቶችን ተቋማዊ መልክ በመስጠት 'ሚንጊ'ን በዘላቂነት ማስቀረት የሚያስችል ተቋም አስመርቀዋል። ይህም በደቡብ ኦሞ ዞን ካራ-ዱስ ቀበሌ በዛሬው ዕለት የተመረቀው "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ነው። አካዳሚውን በምክትል ርዕሰ መሰተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር) እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ተመርቋል። ዕልፍ ህፃናትን ሕይወት የቀጠፈና ወላጆችን የወላድ መካን ያደረገውን የሚንጊ "ልብ ሰባሪ" ድርጊት ለማስቀረት እንደ ላሌ ላቡኮ ባሉ ቅን ልቦች ብርቱ ተጋድሎ መልከ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ቢሮ ኅላፊው ገልጸዋል። ያም ሆኑ ይህን ጎጂ ልማዳዊ ድርጊት በዘላቂነት ለማጥፋት የተቀናጀ ስራ እንደሚጠይቅ ይናገራሉ። በዕለቱ የተመረቀው አካዳሚም የክልሉ መንግስት በአርብቶ አደሩ አካባቢ ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህጻናት ከባህል ተፅዕኖ ተላቀው መማር እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ አብራርተዋል። በህፃናት ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ መሆናቸውን ደግሞ የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ ይገልጻሉ። ሚንጊን ለማስቀረት ከማህበረሰቡ የባህል መሪዎች ጋር በመቀናጀት በተከናወኑ ስራዎች የአስተሳሰብ ለውጥ እየመጣ መሆኑን ያነሳሉ። እናም ወትሮ በ'ሚንጊ'ነት የሚፈረጁ ሕጻናት ዛሬ ላይ "የአብራካችን ክፋይ፤ የኛ ልጆች" ተብለው በወላጆች ዕቅፍ ማደግ መጀመራቸውን ይገልጻሉ። የኦሞ ቻይለድ መስራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ ላሌ ላቡኮ፤ "ይህን መሰል ጎጂ ልማድ ድርጊት ማስወገድ በቀላሉ የሚታሰብ ሳይሆን እስከ ሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ዋጋ መክፈል ይጠይቃል" ይላሉ። ያም ሆኖ ራሳቸውን ለመስዕዋትነት ዝግጁ በማድረግ ድርጊቱ እንዲቀር ማድረግ ስለመቻላቸው ያነሳሉ። በእርሳቸው ድርጅት ብቻ ላለፉት 15 ዓመታት ከ60 በላይ በ'ሚንጊ'ነት የተፈረጁ ሕጻናትን ሕይወት እና ሕልም በመታደግ ለሀገር ኩራት እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል። "ትምህርት ባይኖር በልበ ሙሉነት ማውራት አልችልም ነበር" የሚሉት አቶ ላሌ፤ "የኦሞ ቻይልድ የወደፊት መሪዎች አካዳሚ'' ባለብሩህ አዕምሮ ሀገር ተረካቢ ሕፃናት የሚፈልቁበት ማዕከል እንደሚሆን አረጋግጠዋል።
የአርሶ አደሮችን ጓሮና ኑሮ የለወጡ ቁጥሮች- “30-40-30”
Nov 15, 2024 5785
ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ የሚሆን ሃብት የሰነቀው የ"30-40-30" ኢኒሼቲቭ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አርሶ አደሮች መንደር ተገኝቶ ስለ ’30-40-30’ አሃዞች አርሶ አደሮችን የሚጠይቅ ካለ የቁጥሮችን ትርጓሜና ስሌት በቅጡ መረዳት ይችላል። እነዚህ ቁጥሮች በገጠራማው የክልሉ አካባቢዎች አባውራዎች ዘንድ ሕይወትም፣ አስተሳስብም ለውጠዋልና። የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኅላፊ አቶ ዑስማን ሱሩር የ’30-40-30’ ኢኒሼቲቭ የተጠነሰሰው በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ ኢኒሼቲቭን በመመርኮዝ ስለመሆኑ ያስታውሳሉ። እነዚህ ቁጥሮች የተራ አሃዝ ስያሜ ሳይሆኑ በክልሉ ግብርና ወደ እመርታ ለማስፈንጠር የተቀየሱና ትውልድ ተሻጋሪ ዓላማ የሰነቁ ናቸው። በ2014 ዓ.ም ጀምሮ እያንዳንዱ የክልሉ አርሶ አደር በሶስት ዓመታት ውስጥ ቢያንስ 100 የፍራፍሬ ዛፎች አልምቶ እንዲጠቀም መሰረት የሆኑም ናቸው። በኢኒሼቲቩ የለሙ ፍራፍሬዎች የአርሶ አደሩን ኑሮ ማሻሻል ያለሙ፣ 'ለዛሬው ትውልድ ምግብ፣ ለመጪው ትውልድ ደግሞ ቅርስና ውርስ ናቸው' ይላሉ። የምግብና ስነ-ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ፣ ገቢ ምንጭ ማድረግ፣ ስራ ዕድል መፍጠር፣ ገበያ ማረጋጋት፣ ለኤክስፖርትና ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት ማቅረብን ጨምሮ ዘርፈ ብዙ ዓላማዎችም አሏቸው። በእያንዳንዱ አባውራ ጓሮ አትክልትና ፍራፍሬ እንዲለማና ተጠቃሚ እንዲሆን ለማስቻል የተወጠነ ነው። በዚህም በ'30-40-30'ን እያንዳንዱ አባወራ ጓሮውን እንደየአካባቢው ስነ-ምህዳር በሙዝ፣ በፓፓያ፣ በማንጎ፣ በቡና፣ በአቮካዶና በሌሎች ፍራፍሬ ችግኞች እንዲያለማ ተደርጓል። 'ያልተሄደበትን መንገድ በመሄዳችን በትግበራ ሂደቱ ፈተናዎች ነበሩ' የሚሉት ሃላፊው፤ ዛሬ ላይ ግን የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ ፍሬ የቀመሱትን ሁሉ አስተሳስብ ለውጧል ይላሉ። ኢኒሼቲቩ ባልተለመዱ አካባቢዎች የፍራፍሬ መንደሮች የተፈጠሩበት፣ የአርሶ አደሩ ኑሮና ጓሮ የተለወጠበት፣ የይቻላል አስተሳስብ የተፈጠረበት እንደሆነ ይናገራሉ። በክልሉ የ30-40-30 ኢኒሼቲቭ በመተግበር ከሴፍቲኔት የተላቀቁና ኑሯቸውን ያሻሻሉ አረሶ አደሮች ለዚህ ምስክር ናቸው። በስልጤ ዞን ውልባረግ ወረዳ ቶዴ ጠመዳ ነዋሪዎች አቶ ሀምዛ አሊዬ እና ባለቤታቸው አናጃ ኢሳ በሴፍትኔት ታቅፈው ሲረዱ የቆዩ ሲሆን በ30-40-30 ጓሯቸውን በቡና በማልማታቸው ዛሬ ገቢም፣ ምግብም ችለዋል። በ500 የቡና ችግኝ ድጋፍ ጀምረው በየዓመቱ እያሳደጉ ዛሬ ላይ ቡናቸውን ለቅመው በመሸጥ ገቢ ማመንጨትና ነሯቸውን መደጎም ችለዋል። ጓሯቸውን በማልማታቸውም ከሴፍትኔት መላቀቅ ብቻ ሳይሆን ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያላቸው ማህበራዊ ህይወት እንዲሻሻል ስለማድረጉም ገልጽው፤ በቀጣይነትም ሌሎች ፍራፍሬዎችን ለማልማት ተዘጋጅተዋል። በውልባረግ ወረዳ ቢላዋንጃ ባቢሶ ቀበሌ ነዋሪው አቶ ኢክማላ መሀመድ እና ልጃቸው መካ ኢክማላ ደግሞ አካባቢውን ያልተለመደ የሙዝ መንደር በማድረግ ኑሯቸውን እንዳሻሻሉ ይናገራሉ። የ30-40-30 ንቅናቄ ሲጀመር በአካባቢው "ሙዝ አይለማም" በሚል የተሳሳተ እሳቤ ቅር እያላቸው ችግኞችን ወስደው የተከሉ ቢኖሩም በርካቶች በእምቢታ ጸንተው እንደነበር አስታውሰዋል። በሂደት ውጤቱ ሲታይ ግን የልማቱ ተሳታፊዎች በዝተው በውጤትና የስኬት መንገድ ላይ መቀጠላቸውን ተናግረዋል። ከሳዑዲ አረቢያ የ10 ዓመታት የስደት ቆይታ በኋላ የተመለሰው ልጃቸው መካ ኢክማላ የስደት አስከፊነትን በማንሳት ተፈጥሮ በሰጠችን ጸጋ ሳንጠቀም በመቆየታችን ይቆጨናለ ይላል። የ30-40-30 ንቅናቄም ወጣቶች ከስደት ይልቅ በጓሯቸው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉ ዐይን የገለጠ እና የአስተሳሰብ ለውጥም ያመጣ ስለመሆኑ ይናገራል።     በሀድያ ዞን ሻሸጎ ወረዳ ዶዕሻ ጎላ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት ይቴቦ ሽጉጤ፤ ኢኒሼቲቩን በመጠቀም ከሌሎች አርሶ አደሮች ጋር የሙዝ መንደር መስርተዋል።   የክላስተር ሙዝ መንደራቸው በሶስት ዓመታት ውስጥ የቤተሰባቸው ኑሮ እንዲሻሻል ያደረገና በቀላሉ ጸጋን ተጠቅሞ መለወጥ እንደሚቻል ያረጋገጠ ስለመሆኑም ገልጸዋል። የስልጤ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና ግብርና መምሪያ ሃላፊ አቶ ሙበራ ከማል፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚል ንቅናቄ በርካቶች በተለይም በፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ልማት ተሳትፈው ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል። በአካባቢ ያሉ ጸጋዎችን በመለየት የቡና፣ የሙዝና የአቮካዶ ክላስተር በማልማት ከፍጆታ አልፈው ለማዕከላዊ ገበያ እየቀረቡ ስለመሆኑም ይናገራሉ። በሀድያ ዞን የሻሸጎ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ወንዱ መለሰ፤ የ30-40-30 የፍራፍሬ ልማት ከፍተኛ ለውጥ መምጣቱን ተናግረዋል። በሙዝ ክላስተር አርሶ አደሮች በትብብር ሰርተው እንዲለወጡ ያስቻለ መሆኑን ገልጸው፤ አርሶ አደሮችም ውጤቱን በማየት ወደተጨማሪ ልማት እየገቡ ይገኛሉ ብለዋል። የ30-40-30 ኢኒሼቲቩ 'ጥረት ካለ ስኬት እንዳለ ማሳየት የተቻለበት እና የግብርናው ዘርፍ አንኳር መሰሶዎችን ዕውን ለማድረግ ተስፋ ሰጭ ውጤት የተገኘበት መሆኑን አቶ ዑስማን ይገልጻሉ። በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች የግብዓት ፍላጎት በመጨመሩ ተደራሽነቱን ለማሳደግ ጥረት እየተደረገ ይገኛልም ብለዋል። የ30 40 30 የፍራፍሬ ልማት ፕሮጀክት አንድ አርሶ ወይም አርብቶ አደር በመጀመሪያ ዓመት 30፣ በሁለተኛው ዓመት 40 እና በሶስተኛ ዓመት 30 የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል ተጠቃሚ የሚሆንበት መርሃ ግብር መሆኑ ይታወቃል።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 53424
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 50077
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 30855
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 28343
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ በአልሸባብ ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ገለፁ
Feb 14, 2024 25351
አዲስ አበባ፤ የካቲት 6/2016 (ኢዜአ)፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አፅቀስላሴ አሸባሪው አልሸባብ ከሰሞኑ በሶማሊያ በፈፀመው የሽብር ጥቃት በደረሰው ጉዳት የተሰማቸውን ሃዘን ገለፁ። አምባሳደር ታዬ ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት በሽብር ቡድኑ ጥቃት ምክኒያት በደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እና አካል ጉዳት ጥልቅ ሃዘን እንደተሰማቸው ገልፀዋል። በኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ እንዲሁም በራሳቸው ስም የተሰማቸውን ጥልቅ ሃዘን ለሶማሊያ መንግስት እና ህዝብ የገለጹት ሚኒስትሩ ፤ በልምምድ ወቅት ወታደራዊ መኮንኖችን ኢላማ በማድረግ የተፈፀመውን ጥቃት የወንጀል ተግባር ነው ብለዋል። የወንጀል ተግባሩን ኢትዮጵያ በፅኑ እንደምታወግዘውም ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል። ጥቃቱ አልሸባብ የሽብር ቡድን በሶማሊያ እና በክፍለ አህጉሩ ደህንነት አደጋ መደቀኑን በግልፅ ያረጋገጠ መሆኑን በመግለፅ ፥ የአካባቢው ሀገራት በፀረ ሽብር የሚያደርጉትን ትብብር ሊያጠናክሩ እንደሚገባም አመልክተዋል። የሶማሊያን ሰላም እና ደህንነት በጋራ ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ ትብብሯን አጠናክራ በቁርጠኛነት እንደምትቀጥልም ባስተላለፉት የሃዘን መልዕክት ማስታወቃቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።    
በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ ይፈጸማል-ባለስልጣኑ
Apr 6, 2023 23817
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፡ በአዲስ አበባ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ገለጸ። የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ የሚፈፀምበትን የድርጊት መርሐ ግብር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በአዲስ አበባ ተወያይቷል።   የውይይቱ ዓላማ በመዲናዋ የሚገኙ ሁሉም የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በአሰራሩ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ እንዲይዙ ለማስቻል መሆኑ ተነግሯል። በዚህ ወቅት የነዳጅና ኢነርጂ ቁጥጥር ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ፤ ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል። በዚህም ቀደም ብሎ ከነዳጅ ማደያና አከፋፋይ ኩባንያዎች ጋር ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው፤ አሁን ደግሞ ለሙሉ ትግበራው ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ተደርጓል ብለዋል። በአዲስ አበባ የኤሌክትሮኒክስ የክፍያ ስርዓቱ በአማራጭነት ለሙከራ እየተተገበረ መሆኑን ጠቅሰው፤ ከሚያዚያ 16 ጀምሮ የነዳጅ ግብይት በአስገዳጅ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ እንደሚፈጸም ተናግረዋል። በመሆኑም ህብረተሰቡ ማንኛውም የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ብቻ የሚፈጸም መሆኑን ተገንዝቦ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስበዋል። የነዳጅ ግብይት በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ አተገባበር በሀገር አቀፍ ደረጃ ከሀምሌ አንድ ጀምሮ በአስገዳጅነት እንደሚተገበርም ጠቁመዋል። በኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ሞባይል መኒ ኦፊሰር ብሩክ አድሃነ፤ የነዳጅ ግብይትን በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች በማድረግ ረገድ በቴሌ ብር ውጤታማ ስራ ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል። ለዚህም ባለፉት ዘጠኝ የሙከራ ወራት በቴሌ ብር ብቻ ከ30 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ግብይት መፈጸሙን አንስተዋል። የነዳጅ ግብይቱን በአግባቡ በኤሌክትሮኒክስ የክፍያ መንገዶች ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የቴክኖሎጂ መገንባቱንም እንዲሁ። የኢትዮጵያ ነዳጅ ማደያዎች ማኅበር አባል የሆኑት አቶ ሚካኤል ገብረስላሴ እና የማህበሩ የቦርድ አባል አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ የነዳጅ ግብይት ስርዓቱ በኤሌክትሮኒክስ ክፍያ መንገዶች ብቻ መሆኑ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው ብለዋል። በተለይ ለነዳጅ አዳዮች ጥሬ ገንዘብ በመቁጠር የሚያባክኑትን ጊዜ ከመቅረፍ አንፃር እንዲሁም በማደያዎች የሚቀመጥ የግብይት ገንዘብ እንዳይኖር በማድረግ የደህንነት ስጋትን እንደሚፈታ ተናግረዋል። በተጨማሪም መንግስት የነዳጅ ምርት ከመነሻው እስከ መድረሻው ያለውን ስርጭት ሂደት መረጃ እንዲኖረው እና ነጋዴዎችም ግብርና ታክስ እንዳያጭበረብሩ በማድረግ ቴክኖሎጂው ትልቅ ሚና አለው ነው ያሉት።  
በልጆቿ የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነትን ሳትራብ ዘመናትን የተሻገረች-ኢትዮጵያ
Mar 1, 2023 23658
በቀደሰ ተክሌ (ሚዛን አማን ኢዜአ) ነፃነት የሰው ልጅ ከፈጣሪ ከተቸሩት ፀጋዎች አንዱና ዋነኛው ነው፤ በራስ ፈቃድ መወሰን፣ በራስ መሻት መከወንና በራስ ማንነት መኖር የሰው ልጅ የነፃነት አብነቶች ናቸው። ፈጣሪ ይህን ፀጋ የቸረው ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ ነው። ይሁን እንጂ ይህን ከፈጣሪ የተቸረውን ነፃነት በራሱ በወገኑ የመነጠቅ ዕጣ ፈንታ መግጠሙ አልቀረም፤ ነፃነቱን በራሱ ወገን እየተነጠቀ በራስ ፈቃድ መወሰን የማይችል እንዲሆን ተደረገ። ጥቁር ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን በነጮች ዘንድ የባርነት ግብር ተሰጣቸው። ቅኝ መግዛት ለእነሱ የኃያልነት መገለጫ አድርገው መረጡ። በዚህም አፍሪካን ተቀራምተው የራሳቸው አደረጉ። ያኔ ቅኝ ግዛት አስተዳደር ዘመናቸው በራስ እምነት መቆም፣ በራስ ባህል፣ ወግና ማንነት መኖር አይታሰብም። የሰው ልጅ ከቆዳ ቀለም ልዩነት በስተቀር በራሱ አምሳል ለተፈጠረው ሰው ተገዥ ይሆን ዘንድ አውሮፓውያን ከእኛ ውጭ ሰው ብለው በግዞት የያዟቸውን አገሮች ዜጎች የስቃይና የመከራ ህይወት እንዲያሳልፉ ፈረዱ። ከባዱን የባርነት ቅንበር በጫንቃቸው ላይ ጫኑ። ማንነታቸውን አስረስተው ያሻቸውን አደረጉ። የቅኝ አገዛዝ ገፈት ቀማሽ እንድትሆን ፅዋ የደረሳት የጥቁሮች ፈርጥ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ በቀላሉ ለቅኝ ገዥዎች እጅ አልሰጠችም። ሰውን በሰውነቱ ብቻ የምታከብረው ኢትዮጵያ የልጆቿ ነፃነት በማንም ቁጥጥር ስር እንዲወድቅ አልፈቀደችም።ኢትዮጵያን አፅንቶ ያቆማት በመከባበርና በአብሮነት ላይ የታነፀ ባህል፣ እሴት፣ ወግና ሥርዓት በባዕዳን እጅ ወድቆ ከሚከስም ''እኛ እንቅደም'' የሚል ጠንካራ የሀገር ፍቅርና ወኔ በአበራኮቿ ክፋይ ልብ ውስጥ እንደ አቶን እሳት ተንቀለቀለ። በፈጣሪያቸው እንጂ በምድራዊ ኃይል የሚመኩ አይደሉምና ቅኝ ሊገዛቸው የመጣን የውጭ ወራሪ ኃይል በጀግንነት ታግለው የኢትዮጵያን አንድነት፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት ለማስጠበቅና ለማስከበር በአንድ ልብ ወስነው ቀፎው እንደተነካበት ንብ ወደ አውደ ገባሩ ተመሙ። ኢትዮጵያዊ አንድነትን ኃይል፤ ወኔና ሞራልን ትጥቃቸው አድርገው በዓድዋ ተራራ እስከ አፍንጫው ዘመናዊ የጦር መሳሪያ የታጠቀውን የኢጣሊያ ጦር ገጠመ። ደረታቸውን ለጥይት ሰጥተው ተፋለሙ፣ ደማቸውን አፍሰው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው ለእኛ ለልጆቻቸው ነፃነትን አወረሱ፤ ለምንምና ለማንም የማይበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነትን ትጥቅና ስንቃቸው ያደረጉትን የኢትዮጵያውያንን ከብረት የጠነከረ ክንድ መቋቋም የተሳነው ወራሪ የኢጣሊያ ኃይል ገሚሱ የጎራዴ እራት ሲሆን፤ ቀሪው ቁስለኛና ምርኮኛ ሆነ፤ ሌላው ደግሞ እግሬ አውጣኝ ብሎ ህይወቱን ለማትረፍ እግሩ ወደመራው ፈረጠጠ። ጅግኖች አባቶቻችን ደማቸውን አፍሰው፣ አጠንታቸውን ከሰክሰው የኢትዮጵያ ክብርና ሉዓላዊነት አስጠብቀውና አስከብረው የፈጣሪ ልዩ ፀጋ የሆነውን "ነፃነት" ለዛሬው ትውልድ አስረከቡ። ኢትዮጵያም በትውልድ ቅበብሎሽ ሉዓላዊነቷምን አፅንታ የቆመች ነፃ አገር ሆና ቀጠለች። በዘመኑ የነበረውን ጥቁር ነጭን ማሸነፍ አይችልም የሚለውን አስተሳሰብ በሀገር ፍቅርና ወኔ ወራሪውን የፋሽሽት ኢጣሊያ ኃይል በጦር በጎራዴ አርበድብደው ድል በመንሳት ጥቁር ነጭን ማሸነፍ እንደሚች በቅኝ ገዥዎች የአገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ለነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተግባር አረጋገጡ። በደማቸው ዘመን ተሻጋሪ ደማቅ የአርነት የታሪክ ድርሳን ጻፋ። በዘመን ጅረት የማይወይብ ታሪክ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በዓድዋ ተራሮች ላይ ተጻፈ። ኢትዮጵያ በልጆቿ አንድነትና የጀግንነት ተጋድሎ ነፃነት ሳትራብ ዘመናትን ተሻገረች። የነፃነት ዓርማ ሆና ለአፍሪካውያን ታየች። የዓድዋ ድል በቅኝ አገዛዝ አስተዳደር ስር ወድቀው ይሰቃዩ የነበሩ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች በተለይም አፍሪካውያን የአርነት ትግል አድርገው የግፍ፣ የስቃይና የመከራ ቀንበርን ከጫንቃቸው ላይ አሽቀንጥረው እንዲጥሉ የፃነት ተምሳሌት ሆነ። በኢትዮጵያ የተለኮሰውን የነፃነት ችቦን አቀጣጥለው ብርቱ የአርነት ተጋድሎ አደረጉ፤ በዓድዋ ድል ከቅኝ ገዥዎች መዳፍ አፈተለኩ። የጥቁር ጭቁን ህዝቦች ነፃነት በዓድዋ የድል ገድል ለዓለም ታወጀ። አፍሪካውያን በራሳቸው ቋንቋ በነፃነት መናገር፣ በራሳቸው ባህል፣ወግና ሥርዓት እንዲሁም በራሳቸው መሪ ወደ ሚተዳደሩበት ምዕራፍ ተሸጋገሩ።የዓድዋ ድል ነገሮች አልጋ በአልጋ ሆነው በቀላሉ የተገኘ አይደለም። ኢትዮጵያውያውያ ለሀገራቸው ባላቸው ቀናሂነትና ከብረት በጠነከረ አንድነትና በጀግንነት ተጋድሎ ተጋምዶ በተደረገ እልህ አስጨራሽ ትግል እንጂ። የዓድዋ ድል ዛሬም ወደ ጀመርነው የልማት፣የዕድገትና የብልፅግና ማማ ላይ የሚያደርሰን መሰላል ነው። ይህ የሚሆነው ግን የአንድነት ኃይል ከጀግንነት ወኔ ሳይነጣጠል ፀንቶ ሲቆይ ብቻ መሆኑ እሙን ነው። ቀደምት አባቶቻቸን የዓድዋ ከፍታን በክብር መቆናጠጥ የቻሉት ዘር እየቆጠሩ ሳይሆን በኢትዮጵያዊ አብሮነትና አንድነት ተጋምደውና ተሰናስለው ነው። ያላቸውን የአንድነት ኃይል ተጠቅመው ድልን ተጎናጸፉ። በየዓመቱ ዓድዋን መዘከር ራስን ''እኔስ ምን ማድረግ እችላለሁ?'' በሚል እሳቤ ከሆነ ዓድዋ ህያው ነው፤ ወደ አለምነው የስኬትና የብልፅግና ከፍታ ላይ የአንድነታችን ኃይሉ እንደሚያደርሰን እሙን ነው። እንደ ቀደምት አባቶቻችን በተጋመደ ኅብረ ብሔራዊ አንድነታችንን በማጠናከር በኢኮኖሚው፣ ማኅበራዊ፣ በፖለቲካው ያሉ ፈተናዎችን በሀሳብ ልዕልና በማሸነፍ ለሌላ ድል መትጋት አለብን። አንድነታችንን በማፅናት በኅብረት ለኢትዮጵያ ከፍታ መትጋት ከሁላችንም ይጠበቃል።"ድር ቢያብር አንበሳ ያስር" እንዲ ሀገራዊ ብሂሉ ከተባበርን የማናልፈው ፈተና አይኖርም። አንዴ በጦርነት ሌላ ጊዜ በድርቅና በሌሎች መንስኤዎች ያጋጠሙንን ተግዳሮቶች በአብሮነት ተጋፍጠን ድል እያደረግን መጥተናል። ፈተና ሁሌም ይኖራል፤ ማሸነፍና መሸነፍ ግን በእኛ ፅናትና ጥንካሬ ይወሰናል። ለወደፊትም የሚያጋጥመንን ፈተና አንድነታችንን አፅንተን ኅብረታችን ለሀገራችን ልማት፣ ዕድገትና ብልፅግና በማዋል በርካታ ዓድዋዎችን እንሰራለን። የዓድዋ ድል ከኢትዮጵያ አልፎ ለመላው ጥቁር ጭቁን ህዝቦች የኩራት ምንጭ የነፃነት ዓርማ ነው። የዓድዋን ታሪክ መጠበቅና መደጋገም የእኛ የኢትዮጵያውን ኃላፊነትና ግዴታ ነው። ልዩነትን መስበክ ከኢትዮጵያዊ ከፍታ መሸራተት ነው። እኛነትን ረስቶ እኔ ማለት የዓድዋን ታሪክ መሸጥ ነው። ኢትዮጵያውያን አንድ ሆነን እንጂ ተከፋፍለን የሰራነው ታሪክ የለም። የትናንት መልካም ስምና ዝና ከዘመኑ ጋር አብሮ ከፍ ከፍ እያለ አብቦ ማፍራት እንጂ፤ በልዩነት አስተሳሰብና አመለካከት ሊኮሰምን አይገባም። የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የሉዓላዊነት መገለጫ፣ የዓለም ጭቁን ሕዝቦች የነፃነት ተምሳሌ-ዓድዋ ለዘላለም በክብር ሲዘከር ይኖራል‼  
ለላቀ ውጤት - የተማሪ መምህርና ወላጆች ጥምር ጥረት
Mar 27, 2023 23414
በሃብታሙ ገዜ ስልጡን የመንገድ ጠበብቶች በጥንቃቄ የከተማ ውብ ገፅታ አልበሰው ባነጿት ከዚራ አካባቢ የሚገኘው የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አዳራሽ በሰው ተሞልቷል። የተሰበሰቡት ወጣት ተማሪዎች፣ የድሬደዋ አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፍን የሚመሩ አካላትና ወላጆች በፈገግታ ተሞልተዋል። ይበልጥኑ ከወጣቶቹ ገፅታ የሚንፀባረቀው የደስታ ፈገግታ ለአዳራሹ የተለየ ብርሃን ደርቦለታል። የደስታቸው ምንጭ ደግሞ አምና የተፈተኑትን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በላቀ ውጤት አልፈው ሽልማት በመቀበል ላይ መሆናቸው ነው። የአዳራሹን የሽልማት መርሃ ግብር የሚመራው ሰው ድንገት "የዛሬው ልዩ ክስተት ከሚሸለሙት ተማሪዎቻችን መካከል ከ600 በላይ ውጤት በማምጣት ከወንድሞቿ ጋር ሦስት ሆነው ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገኘታቸው ነው" ሲል ተናገረ። ይሄኔ አዳራሹ በጭብጨባ ተናጋ፤ ሁሉም ተሰብሳቢ በአንድነት ቆሞ ጭብጨባውን አቀለጠው። ለሽልማት ወደ አደባባዩ የመጡት በደስታ ፀዳል የወረዙት የወላጅ ተወካይ እንጂ የድሉ ባለቤት የሆኑት እነዚህ ሦስት ተማሪዎቹ አይደሉም። በአዳራሹ የተሰባሰቡት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃርና የካቢኔ አባላት እንዲሁም ተሸላሚዎቹ ተማሪዎች "የዓመቱ የተለየ ክስተት የሆኑትን ተማሪዎች" ለማየት ዓይኖቻቸው ቢባዝንም አልተሳካም። ለምን ካላችሁ ተማሪዎቹ ወደ ተመደቡበት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጓዛቸው ነው። የመድረኩ የድምፅ ማጉያ ባለቤትም ሆነ ተሰብሳቢዎቹ የዓመቱ ክስተት የሆኑት ኒያ ሰላሃዲን 602፤ አሊ ሰላሃዲን 556፣ አማን ሰላሃዲን 526 ያመጡት ተማሪዎች መንትዮች መሆናቸውን ቢያውቁ ኖሮ አዳራሹ ሌላ የግርምት ደስታን ባስተናገደ ነበር። ሽልማቱን ያበረከቱት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሃር ተሸላሚዎች በጥረታቸው በትጋታቸው ባመጡት ውጤት መደሰታቸውን አብስረዋል። አገር በዜጎች አንድነትና መተባበር እንደሚፀናው፤ የተማሪዎች ውጤትም በተማሪዎችና በመምህራን ጥረት ብቻ ሳይሆን በወላጆች ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ጭምር የሚመጣ ነው። "በተለይ ከአንድ ቤተሰብ የበቀሉት ተማሪዎችና የዛሬው ሽልማት እና ውጤት ያስተማረን ይህንኑ ነው" ብለዋል ከንቲባው። በዚህ አደራሽ ውስጥ የሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ርዕሰነ-መምህራን ታድመዋል። እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ከተፈተኑት ከ3 ሺህ 700 በላይ ተማሪዎች መካከል በቀጥታ ያለፉት 250 ተማሪዎች ብቻ ናቸው። ለመጣው ውጤት ተሞጋሹም ተወቃሹም የዘርፉ አመራሮች፣ ተማሪዎች፣ መምህራንና ወላጆች ናቸው። የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሙሉካ መሐመድ "ለመጣው ዝቅተኛ ውጤት በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ያለነው በሙሉ ተጠያቂዎች ነን" ብለዋል። ኃላፊዋ ሌላውም ከዚህ ትምህርት መውሰድ እንዳለበት ነው የገለጹት። እንደ አስተዳደሩም የትምህርት አመራሮች፣ ርዕሳነ መምህራን፣ መምህራንና ወላጆች ያካተተ ኮሚቴ ተዋቅሮ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የተቀናጀ እንቅስቃሴ መጀመሩን አውስተዋል። በመንግስት የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን ከኩረጃ ነፃ ለማድረግ የተወሰደው እርምጃ ተማሪዎች በጥረታቸውና በብቃታቸው የልፋታቸውን ውጤት እንዲያገኙ ያስቻለ ነው። የፈተና አሰጣጡና ውጤቱ እንደአገር ያለንበትን አዘቀት አስተምሮ ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ፤ ብቁና በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማዋለድም ጥርጊያ መንገድ ሆኖ አልፏል ማለት ይቻላል። መንግስት የትምህርት ጥራትን ከታችኛው እርከን ጀምሮ ለማረጋገጥም በዘርፉ ሙሁራን ጥልቅ ጥናት ላይ ተመስርቶ ያዘጋጀውን የትምህርት ፍኖተ ካርታ መሠረት ያደረገ ስርዓተ ትምህርት ቀርጾ ዘንድሮ እስከ 8ተኛ ክፍል ተግባራዊ አድርጓል። ለመማር ማስተማሩ መጻህፍት ተዘጋጅተው ለመምህራን ስልጠና በመስጠትም ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል። በሚቀጥለው ዓመትም በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ ነው። በሽልማት ሥነስርዓቱ ላይ እንደታየው ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች ሚና የጎላ ነው። ወላጆች ተገቢውን ድጋፍ እና ጥብቅ ክትትል ካደረጉ የሚፈልገው ለውጥና ውጤት ማምጣት ይቻላል። ወይዘሮ ሙሉካ በአትኩሮት ከገለጹት ሃሶቦች መካከል ዋናዎቹን ሰበዞች መዝዤ፤ "ተጠያቂዎቹ እኛው ነን" የሚለውን ሃሳብ አንግቤ ለድሬዳዋና ለአገር ከፍ ሲል ለዓለም ህዝብ ጭምር በየዘርፉ ታላላቅ ሙሁራን ወደ አፈሩት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አመራሁ። ድንገት ሃሳቤን ቀለበስኩት። መነሻዬ የወላጆች ኃላፊነት እና ድጋፍ መሆኑን መርሳት ዞሮ ዞሮ የምፅፈው መዳረሻ መርሳት ይሆንብኛል ብዬ ነው። እናም ወደ ሦስቱዎቹ፤ የዓመቱ ክስተቶች አባት አመራሁ። ድሬዳዋን ለሁለት እኩሌታ የሚከፍላትን የደቻቱን ድልድይ ተሻግሬ ወደአንድ የግል የሕክምና አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ገባሁ። አምሮ በተሰናዳው ሆስፒታል ውስጥ ሙያዊ ኃላፊነታቸው እየተወጡ አገኘኋቸው፤ የማህፀንና የፅንስ ስፔሻሊስት ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍን። የውጤታማ ተማሪዎቹ ወላጅ ናቸው፤ በ1970 ዎቹ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም መዝለቅ በመርፌ ቀዳዳ የመሹለክ ያህል በሚቆጠርበት ዘመን በከፍተኛ ማዕረግ አልፈው በቀሰሙት ዕውቀትና ጥበብ የሰዎችን ሕይወት እየታደጉ ይገኛሉ። ዶክተር ሰላሃዲን ለትምህርት ጥራት መውደቅ ወደ ዩኒቨርሲቲ በስርቆትና ኩረጃ የመግባት ዝንባሌዎች እንደሆኑና ይሄም ሁሌም የሚያንገበግባቸው ጉዳይ መሆኑን አጫወቱኝ። መንግስት በተለይ የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እና ባልደረቦቻቸው በሁለተኛ ደረጃ የፈተና አሰጣጥ ላይ የወሰዱት እርምጃ አስደስቷቸዋል። "በተለይ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ከሚያሳልፉት ጊዜ በበለጠ ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው ጊዜ ይበልጣል። ከሁሉም ነገር በላይ ለትምህርት ትኩረት ማድረጋቸውን መከታተልና መደገፍ የኛ ፋንታ ነው፤ አንዴ መስመር ከያዙ የሚመልሳቸው ችግር አይኖርም" ይላሉ። ሦስቱ ልጆቻቸውን በዚህ መንገድ በመደገፍ እና ከትምህርት ቤታቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ አስችለዋል። 604 ያመጣችው ስኮላርሽፕ ሺፕ አግኝታ ወደ ውጭ ሄዳለች፤ ሁለቱ ደግሞ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ናቸው። "ለልጆቼ የፈለጉትን የማድረግ አቅም ቢኖረኝም ያለትምህርት የሚፈጠር አንዳች ነገር እንደሌለ ገብቷቸው ለውጤት በቅተዋል" ይላሉ ዶክተር ሰላሃዲን። ብዙ የመስራት እንጂ ብዙ የመናገር ዝንባሌ የማይታይባቸው እኚህ የታታሪዎች አባት ለትምህርት ጥራት መረጋገጥ እና ውጤታማ ተማሪዎችን ለማፍራት በሚደረግ ጥረት የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን ነው በአፅንኦት ያሳሰቡት። "የሽልማቱ መርሃ ግብር ወደሌላ አካባቢ በሄድኩበት አጋጣሚ በመካሄዱ ሳልገኝ ቀረሁ፤ በጣም የቆጨኝና ቅር ያለኝ ዕለት ሆኖ አልፏል" ብለዋል። እሳቸውን ጨምሮ አንቱ የተሰኙ ሙሁራን ያፈራው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ፍቃዱ ሰንበቶ፤ የማርያም ሰፈር አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ኢጀታ መኮንን ካለፈው ክፍተት በመማር ዘንድሮ የተሻለ ውጤት እንዲመጣ የተማሪዎች አመለካከት ላይ ለውጥ እና እችላለሁ የሚል መርህ የማስረጽ ሥራ ተሰርቷል ብለውኛል። ለውጤቱ ቀዳሚ ባለቤት ተማሪዎች ቢሆኑም ከወላጆቻቸው ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የተለያዩ የማካካሻና ለፈተና ዝግጁ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ነው ርዕሳነ መምህራኑ የገለጹት። ቅኝቴን በመቀጠል ሽቅብ ወደ ሳብያን ሁለተኛ እና የመሰናዶ ትምህርት ቤት አመራሁ። ይህ ትምህርት ቤት በከተማዋ ካሉት ትምህርት ቤቶች በውጤታማነት እና በብዛት ተማሪዎችን ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በማሳለፍ ረገድ ወደር አልነበረውም፤ ባለፉት ዓመታት። ከተመሠረተ 22 ዓመታትን ያስቆጠረው ይህ ትምህርት ቤት በምክትል ርዕሰ መምህርነት የሚመሩት አቶ በፍቃዱ ወልደሰማያትን አገኘኋቸው። ትምህርት ቤት በ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ካስፈተናቸው ከ800 በላይ ተማሪዎች መካከል ያለፉት 20 ናቸው። የመጣው ውጤት ያለንበትን ደረጃ ፍንትው አድጎ ያሳየን መሆኑን ተከትሎ መሠረታዊ የሆኑት ችግሮች በጋራ ተነቅሰው ለመጪው ጊዜ የተሻለ ውጤት ለማምጣት የጋራ ኮሚቴ ተዋቅሮ ወደ ሥራ ተገብቷል። አቶ በፍቃዱ እንዳሉት ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጋር የጋራ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ትምህርት ቤቱን ሞዴል ትምህርት ቤት ለማድረግ እየተሰራ ሲሆን ለዘንድሮው ተፈታኞች ልዩ የማጠናከሪያ ትምህርት እየተሰጠ ነው። እነዚህን ሥራዎች የተማሪ፣ መምህርና ወላጅ ህብረት በቅርበት እንዲከታተል ተደርጓል። ለተማሪዎች ውጤት ማማር የወላጆች የቅርብ ክትትልና ደጋፍ መሠረታዊ ጉዳይ ነው የሚሉት አቶ በፍቃዱ፣ ለዚህ ጉዳይ ትምህርት ቤቱ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው ነው የገለጹት። "በተለይ ወላጆች በትምህርት ውጤታማነት ላይ ሚናቸውን እንዲወጡ ልክ እንደ ዶክተር ሰላሃዲን አይነት ቤተሰቦች ተሞክሮ የማስፋት ሥራ ለመስራት ትምህርት ቤቱ አቅጣጫ አስቀምጧል" ብለዋል። "ፍቃደኛ ከሆኑ የመጀመሪያው እንግዳችን ዶክተር ሰላሃዲን በማድረግ ለወላጆች ህብረት ተሞክሮን እንዲያካፍሉ እናደርጋለን " ብለዋል። በድሬዳዋ ታሪክ ከፍ ሲልም እንደ አገር በ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከ1990 ዎቹ ዘመን ጀምሮ እንዲህ አይነት ዝቅተኛ ውጤት አለመምጣቱን የሚገልጹት ደግሞ የትምህርት ቤቱ አንጋፋ መምህር እዮብ ረታ ናቸው። የፊዚክስ መምህሩ እንደሚሉት የአምናው ክፍተት በሰከነ መንፈስ ታይቶ ዘንድሮ የተሻለ ሥራ ለመስራት መምህራን በጥሩ መንፈስ ጉዞ ጀምረዋል። ወላጆችም ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት መላክ ብቻ ሳይሆን የዕለት ተዕለት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ነው የገለጹት። "የተማሪዎች የትምህርት ቤት ቆይታ ለሰዓታት ብቻ የተወሰነ መሆኑን በመረዳት ወላጆች በስነ ምግባር የታነፀ በራስ የሚተማመን ዜጋ ለማፍራት የተጀመረውን ጉዞ መደገፍ አለባቸው" በትምህርት ቤቱ የዘንድሮው የ12ተኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪ ረደኤት ገነሙ በበኩሏ "እንደአገር በዩኒቨርሲቲዎች የተጀመረው የፈተና አሰጣጥ ኩረጃን የሚጠየፍ በራሱ ጥረት ውጤት ለማምጣት የሚተጋ ትውልድ ለመፍጠር ያግዛል" ብላለች። በትምህርት ቤቱ የተጀመረው ልዩ ዕገዛ መጠናከርና መቀጠል እንዳለበት የምትገልጸው ተማሪ ረድኤት ወላጆቿ ተገቢውን ድጋፍ ከማድረግ በተጨማሪ ከመምህራን ጋር የጠበቀ ግንኙነት በመፍጠር የልጆቻቸውን ትምህርት ሊከታተሉ እንደሚገባ አውግታኛለች። እኔም ሆንኩ የዘንድሮ ተፈታኞች ትምህርት ቤታችንንና ድሬዳዋን በውጤት ለማስጠራት ጠንክረን እያጠናን ነው ብላለች። ከገጠር ከተማ ተጉዞ የሚማረው የድሬዳዋ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪ አላሙዲን አልይ በበኩሉ፤ መንግሥት የፈተና ኩረጃን ለማስቀረት የጀመረውን ተግባር ይበልጥ ማጠናከር እንዳለበት ነው የገለፀው። "የዘንድሮ የመምህራን ድጋፍ የተለየ ነው፤ እኛም ልዩ የጥናት ጊዜ እንዲጀመር ጫና እየፈጠርን ነው፤ ወላጆቼም በአቅማቸው እየደገፉኝ በመሆኑ ቀሪው ሥራ የኔ ጥረትና ብርታት ይሆናል፤ ልፋቴ ውጤት እንዲያስገኝ የስርቆትና የኩረጃ ሂደት መወገድ አለበት" ብሏል ተማሪ አላሙዲን። ከሳብያን ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ግቢ ለቅቄ ስወጣ ዶክተር ሰላሃዲን ዩሱፍ ያሉኝ ትዝ አለኝ። "ለተሞክሮ የሚሆን ነገር እኔ ጋር ካለ ያለችኝን ጊዜ አብቃቅቼ ለዘንድሮው ተፈታኞች ሃሳቤን ለማካፈል ዝግጁ ነኝ" ያሉኝ በአዕምሮዬ ደጋግሞ እያቃጨለብኝ ጉዞዬን ቀጠልኩ። ለመውጫ ያህል፤ በድሬዳዋ አስተዳደር ዘንድሮ በመንግሥት እና በግል 22 ትምህርት ቤቶች ከ5 ሺህ በላይ ተፈታኞች በትምህርት ገበታ ላይ ናቸው። እነዚህ ተፈታኞች በራሳቸው ጥረት የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ በየአቅጣጫው የተቀናጀ ድጋፍ የማድረግ ጅምር ተግባራት ተስተውለዋል፤ ይሄ በቀጣይም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት። ይህን ዙሪያመለስ ድጋፍ በማጠናከር ተማሪዎቹን ለውጤት ማብቃት በሁሉም ዘንድ ለአፍታ መዘንጋት የለበትም። መድረሻውን ለማሳመር መነሻውን አድምቶ ማበጃጀት ግድ እንደሚልም እንዲሁ።
በብዛት የታዩ
ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ ታደርጋለች - አምባሳደር ስቴፋን አወር
Jun 17, 2023 53424
አዲስ አበባ ሰኔ 10/2015 (ኢዜአ) ፦ ጀርመን በኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕ ሂደት እንዲሳካ ድጋፍ እንደምታደርግ በአገሪቷ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስቴፋን አወር ገለጹ። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የሰብአዊ ድጋፍ በእጥፍ ማሳደጓንም አመልክተዋል። ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ግንኙነት ከጀመረችበት ጊዜ አንስቶ በፖለቲካው፣ በማህበራዊ እና በኢኮኖሚ የትብብር መስኮች ያላቸው አጋርነት እየተጠናከረ መምጣቱን አምባሳደር ስቴፋን ለኢዜአ ገልጸዋል። ጀርመን በአቅም ግንባታ፣ በግብርና ምርታማነት እንዲሁም በማህበራዊ ልማትና በመልካም አስተዳደር ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምታደርገው የልማት ትብብር ማደጉን አመልክተዋል። ጀርመን በተለይም በልማት ኤጀንሲዋ(ጂ አይ ዜድ) በኩል ለኢንዱስትሪው እድገት ወሳኝ የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች የአቅም ግንባታ ድጋፍ ማድረጓን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል የሰብዓዊ መብት ኮሚሽንና የብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ሙያዊ ድጋፍ እንዲሁም የግብርና ምርትና ምርታማነት እንዲጨምር ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ነው አምባሳደሩ የገለጹት። በኢትዮጵያ ለችግር የተጋለጡ ዜጎችን ለመደገፍ ሰው ተኮር የሆኑ ፕሮጀክቶችን ለአብነትም የሰብአዊና የመልሶ ማቋቋም ስራዎች ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝ ተናግረዋል። ጀርመን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን የሰብአዊ እርዳታ ወደ 82 ነጥብ 5 ሚሊዮን ዶላር ከፍ በማድረግ በእጥፍ ማሳደጓንና ይሄም "ጀርመን በኢትዮጵያ ከፍተኛ የሰብአዊ ድጋፍ በማድረግ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ያስቀምጣታል" ብለዋል። በሌላ በኩል ጀርመንና ኢትዮጵያ በንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች መኖራቸውን ጠቅሰው ይህንንም እውን ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የሁለቱን አገራት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ለአብነትም በጀርመን የባህል ተቋምና በሌሎችም ኢንስቲትዩት እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን በማሳየነት ጠቅሰዋል። በኢትዮጵያ በተለይም በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ቀጣይነት እንዲኖረው ጀርመን ፍላጎት እንዳላት ገልጸው ለዚህም ድጋፍ እያደረገች ትገኛለች ነው ያሉት አምባሳደር ስቴፋን። የኢትዮጵያ መንግሥት የሽግግር ፍትህ ለማረጋገጥ የጀመረው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የጠቆሙት አምባሳደሩ ጀርመን ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ድጋፍ ታደርጋለች ብለዋል። ጀርመን የአፍሪካ ሕብረት እንዲጠናከር በተለይም በአፍሪካ አገራት መካከልም የፖለቲካና ምጣኔ ኃብታዊ ውህደት እንዲረጋገጥ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ እንደምትቀጥል ጠቁመዋል። ኢትዮጵያና ጀርመን ግንኙነታቸውን የጀመሩት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1905 ነው።
በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ
Jun 29, 2023 50077
አዲስ አበባ ሰኔ 22/2015(ኢዜአ)፡- በኢትዮጵያና ሩስያ መካከል የዳበረውን ባህላዊና ኪነ ጥበባዊ ትስስር ይበልጥ ለማጎልበት እየተሰራ መሆኑ የሀገራቱ ተወካዮች ገለጹ። 'የሩስያ ባህል ቀን በኢትዮጵያ' በሚል መሪ ሃሳብ የሀገሪቱን ባህል የተመለከተ መርሃ ግብር በኢትዮጵያ የሩስያ ኤምባሲ አዘጋጅነት አዲስ አበባ በሚገኘው የሩስያ የሳይንስና ባህል ማዕከል/ፑሽኪን/ ተካሂዷል። የሩስያን ባህል የሚያስቃኝ የኪነ ሕንጻ ዐውደ ርዕይ በማዕከሉ የተከፈተ ሲሆን በሁለቱ ሀገራት ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶችና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።   የኢትዮጵያና ሩስያ ታሪካዊ ግንኙነት በርካታ ምዕተ ዓመታትን ቢያስቆጥርም ይፋዊ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የተጀመረው ግን በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ በዳግማዊ አጼ ምኒልክ ዘመነ መንግስት እንደሆነ ይነገራል። 125ኛው ዓመቱን ያስቆጠረው የሁለቱ ሀገራት ዘመናትን የተሻገረ ጽኑ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅነት ከፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ትብብሮች ባሻገር ባህላዊና መንፈሳዊ ትስስሮችም እንደጎለበቱ ይወሳል። በኢትዮጵያ የሩስያ አምባሳደር ኢያቭገኒ ተርኪን እንዳሉት ዘመናትን በጽኑ ወዳጅነት የዘለቀው የኢትዮ-ሩስያ ዲፕሎማሲያዊ እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር በባህላዊና መንፈሳዊ ቅርርብ ያዳበረ ነው።   በሁለቱ ሀገራት መካከል ለዘመናት የዳበሩ ባህላዊ፣ መንፈሳዊ፣ ኪነ ጥበባዊ እና ታሪካዊ ግንኙነቶችና ትብብሮች ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል። በመጭው ሕዳር ወር ዕውቅ የሩስያ ድምጻዊያንን ያካተተ ባህላዊ የሙዚቃ ቡድን ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ስራውን እንደሚያቀርብ ገልጸዋል። ከዚህም በሻጋር የኢትዮጵያ ኪነ ጥበብ ሙያተኞች ወደ ሩስያ በመሄድ የኢትዮጵያን ባህል የሚያስተዋውቁብትን ዕድል ለማመቻቸት ፍላጎት እንዳላቸውም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው የሁለቱን ወዳጅ አገሮች ባህል ልውውጥ ይበልጥ ለማጎልበት የሚያግዙ ዝግጅቶች በአዲስ አበባ ፑሽኪን ማዕከል ጋር በመተባበር እንደሚዘጋጁ ጠቁመዋል።   የኢትዮ-ሩስያ ባህላዊ ትስስር ለማጠናከር በኪነ ሕንጻ፣ በስነ ጥበብ እና በሌሎች ኪነ ጥበብ ዘርፎች ላይ በስፋት እንደሚሰራ አረጋገጠዋል። ኢትዮጵያ ባህላዊና መንፈሳዊ ቅርሶቿን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማስተዋወቅ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነች መሆኑን ገልጸዋል። ለአብነትም የላሊበላ አብያተ ክርስቲያናትን የሚዘክር የአርኪኦሎጂና የቨርቹዋል ሪያሊቲ ቋሚ ዐውደ ርዕይ በላሊበላ መከፈቱን ገልጸዋል። ”ላሊበላ በእምነት የታነፀ” በሚል መሪ ሀሳብ የተከፈተው ዐውደ ርዕይ በቀጣይ ሩስያን ጨምሮ ወደ አውሮፓ ሀገራት እና ሰሜን አሜሪካ የመውሰድ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። የሩስያ ዘመናዊ ሥነ-ጽሁፍ አባት የሚሰኘው ዕውቁ ሩስያዊ ባለቅኔ አሌክሳንደር ፑሽኪን 225ኛ ልደት በዓል በቀጣይ ዓመት በድምቀት እንደሚከበር ተገልጿል። በአሌክሳንደር ፑሽኪን ልደት ቀን የተሰየመው የሩስያ ቋንቋ ቀን በቅርቡ በአዲስ አበባ መዘከሩም ይታወሳል።
“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅ መርሐ-ግብር እየተካሄደ ነው
Mar 21, 2023 30855
አዲስ አበባ መጋቢት 12/2015(ኢዜአ)፦“የመደመር ትውልድ” መጽሐፍን በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የማስተዋወቅና የሽያጭ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በሸራተን አዲስ ሆቴል እየተካሄደ ነው። በኦሮሚያ ክልል ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።   በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ" መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።   እየተካሄደ በሚገኘው መርሐ-ግብር ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳና የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።   የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።
ባጃጅ ውስጥ ተረስቶ ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው የባጃጅ አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ነው
Mar 26, 2023 28343
አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ በድሬዳዋ ከተማ በሚያሽከረከረው ባጃጅ ውስጥ ተሳፋሪ ረስቶት ያገኘውን 150ሺህ ብር ለባለቤቱ የመለሰው አሽከርካሪ አድናቆት እየተቸረው ይገኛል። መኮንን ግርማ ኑሮውን ለማሸነፍ እና የነገውን ተሰፋ ብሩህ ለማድረግ በባጃጅ አሽከርካሪነት ተቀጥሮ የሚሰራ ወጣት ነው። ወጣቱ መጋቢት 15 ቀን 2015ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ የተለመደ ስራውን እያከናወነ ሳለ የከተማው ነዋሪ የሆኑት አቶ መሐመድ ኡስማን ከሳቢያን ኦርቢት ተብሎ ወደሚጠራው የከተማው ክፍል ለመጓዝ መሳፈራቸውን ተናግሯል። ይህ ከሆነ ከአንድ ሰዓት በኋላ “ስልክ ተደውሎ ባጃጁ ላይ ገንዘብ ወድቆ እንደሆነ እንድመለከት” ተነገረኝ ይላል ወጣቱ አሽከርካሪ መኮንን። በተነገረው መሰረት ወደ ተሳፋሪ ወንበር ላይ ዞሮ ሲመለከት በላስቲክ የተጠቀለለ 150ሺህ ብር በማግኘቱ ወዲያው ወደ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ዳይሬክቶሬት በማምራት ብሩን ለባለቤቱ መመለሱን ገልጿል። ገንዘቡን ለባለቤቱ መመለሱ እንዳስደሰተው የተናገረው ወጣቱ፤ የራስ ያልሆነ ገንዘብ ለግል መጠቀም የህሊና ቁስል በመሆኑ በራስ ወዝ ብቻ ሀብት ማፍራት እንደሚገባ መናገሩን ከድሬዳዋ ፖሊስ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ገንዘባቸው የተመለሰላቸው አቶ መሐመድ ኡስማን በበኩላቸው ገንዘባቸው በጠፋ በአንድ ሰዓት ውስጥ የተሳፈሩበትን የባጃጅ የጎን ቁጥር ለትራፊክ ፖሊስ በመናገር በፍጥነት ገንዘባቸው በመገኘቱ መደሠታቸውን ገልጸዋል። አቶ መሐመድ ለድሬዳዋ ትራፊክ ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እና ለወጣት መኮንን ግርማ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አዛዥ ኮሚሽነር ዓለሙ መግራ ስነ-ምግባር ያለው አሽከርካሪ እንዲፈጠር እየሰራን ያለው ስራ ፍሬ እያፈራ መምጣቱን ይህ ትልቅ ማሳያ ነው ብለዋል።
መጣጥፍ
በትግራይ ክልል የመስቀል በዓል አከባበር
Sep 27, 2025 349
የመስቀል በዓል በሁሉም የኢትዮጵያ አካባቢዎች በልዩ ድምቀት ከሚከበሩ በዓላት መካከል አንዱ ነው። በዓሉ እንደየአካባቢው ባህላዊና ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ጠብቆ በተለያዩ ሁነቶች ይከበራል። በትግራይ ክልልም የመስቀል በዓል እንደሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ሁሉ በናፍቆት ከሚጠበቁና በድምቀት ከሚከበሩ በዓላት ተርታ ይመደባል። ለዚህም ሲባል የተለያዩ ዝግጅቶች ከበዓሉ ዋዜማ በፊት እንዲጠናቀቁ የሚደረግ ሲሆን፥ በተለይ በየዓመቱ መስከረም 16 እና 17 ዘመድ አዝማድ ተጠራርተው የሚገናኙበት የፍቅርና የአብሮነት በዓል ሆኖ ይከበራል። የክርስቶስ ግማደ መስቀል በንግስት ኢሌኒ አማካኝነት መገኘቱን በማሰብ በየዓመቱ መስከረም አጋማሽ ላይ የሚከበረው የመስቀል በዓል የመስቀል ኃያልነት፣ እውነት በተደበቀበት ለዘላለም እንደማይቀርና ፍቅርን አብዝቶ የሚሰበክበት ከዚህ ባለፈም እርቅ የሚወርድበትና ደስታ የሚገለጽበት አጋጣሚ መሆኑም ይገለጻል። በትግራይ የበዓሉን ታላቅነትና ክብር ለማድመቅ ምእመናን ጽዱ ልብስ ለብሰውና የተለያዩ ዝማሬዎችን በማሰማት ደመራ ወደሚደመርበት ሥፍራ ችቦ ይዘው በመሄድ ደምራውን በማቀጣጠል የሚያከበሩት ሲሆን፣ በእለቱ የቤት እንስሳት ጭምር ቀንዳቸውና ጀርባቸው ላይ ቅቤ ተቀብተው እንዲያርፉ ይደረጋል። ዘመድ አዝማድ፣ ጎረቤታሞች፣ አብሮ አደጎችና የበዓሉ ታዳሚ እንግዶችም ተሰባስበው ማለዳ ላይ ገንፎ በማዘጋጀት ይመገባሉ። የእንስሳት እርድ በማከናወን ባህላዊ መጠጦችን በማዘጋጀት በዓሉን የፍቅር፣ የመሰባሰብ፣ የአንድነትና ተካፍሎ የመብላት በዓል መሆኑን በተግባር የሚያሳይበት ክስተት ሆኖ ያልፋል። "ዓኾይ ዓኾኾይ" የጎመን ምንቸት ውጣ የገንፎ ምንቸት ግባ በማለትም ችቦ ተሎኮሶ በየቤቱ በመዞር የምረቃ እና ለሚቀጥለው ዓመትም በሰላምና ደስታ እንዲሁም እድሜና ጤናን በመመኘት ይከወናል። የአደባባይ በዓል የሆነው የመስቀል በዓል በዝማሬ፣ በሆታና እልልታ የሚገለጽ ሲሆን፤ ወርሃ መስከረም እሸት አሽቶ አበቦች አብበውና ምድር ልዩ ልምላሜን ተላብሶ የሚታይ በመሆኑ ልክ በታሪኩ እንደሰፈረው የሰላም፣ የእውነትና የአንድነት በዓል መሆኑን በተግባር የሚታይበት ነው።
የሀመሯ እናት- የደስታ እንባ
Sep 11, 2025 1187
የሀመሯ እናት- የደስታ እንባ በጣፋጩ ሰለሞን (ከጂንካ) በደቡብ ኦሞ ዞን የሚገኘው ሐመር ወረዳ የሐመር ብሔረሰብ ዘመን በተሻገሩ ባህላዊ ሥርዓቶች ይታወቃል። በዚህ አካባቢ ከሚዘወተሩትና በብዛት ከሚታወቁት ባህላዊ ሥርዓቶች መካከል “ኢቫንጋዲ እና ኡኩሊ” የተባሉ ባህላዊ ጨዋታዎች ይጠቀሳሉ። “ኡኩሊ”በሐመሮች ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ባህላዊ ጨዋታ ሲሆን ለአቅመ አዳም የደረሰና ከብት ለመዝለል ዝግጁ የሆነ የሐመር ወጣት የሚጠራበት የማዕረግ ስም ነው፡፡ “ኡኩሊ” ከብት በሚዘለልበት ዕለት ሥርዓቱ በሚፈጸምበት ሥፍራ ላይ በቅርብም ይሁን በሩቅ ያሉ የወጣቱ ዘመዶች ተጠርተው የሚከናወን ባህላዊ ሥርዓት መሆኑ ይታወቃል። “ኢቫንጋዲ” ደግሞ በሐመሮች ዘንድ በስፋት የሚታወቅ ባህላዊ ጭፈራ ሲሆን ትርጉሙም “ኢቫን” ማለት “ ማታ” ሲሆን “ጋዲ” ማለት ደግሞ “ጭፈራ” ማለት መሆኑ ይነገራል። ኢቫንጋዲ በአዝመራና በደስታ ወቅት በሥራ የደከመን አእምሮና አካል ለማዝናናት ሲባል የሚከናወንና የሀመር ወጣቶች በጉጉት የሚጠብቁት ባህላዊ ጭፈራ ነው። በዚህ ባህላዊ ጨዋታ ላይ የሐመር ወጣት ወንዶችና ልጃገረዶች አምረውና ተውበው በጨረቃ ብርሃን ይጨፍራሉ። የኢቫንጋዲ ጭፈራ በሶስት ቀን አንድ ጊዜ በሐመር መንደሮች በምሽት ከጨረቃ ድምቀት ጋር አብሮ ይደምቃል። “በጨረቃ ብርሃን አየኋት በማታ ኢቫንጋዲው ቦታ” የተባለላቸው የሃመር ውብ ልጃገረዶችም ከጨረቃ ብርሃን ጋር ደምቀው የሚታዩበት ዕለት ይሆናል። በወጣትነታቸው በዚሁ ባህላዊ ሥርዓት ያለፉት የሀመሯ እናት- ወይዘሮ ባሎ ኡርጎ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ እናት ናቸው። በሐመር ወረዳ ዲመካ ከተማ የሚኖሩት ወይዘሮ ባሎ፤ በደሳሳ ጎጇቸው ሲያገኙ በልተው ሲያጡ ደግሞ ኩርምት ብለው ያሳለፉባቸው ጊዜያት እንዳሉ ያስታውሳሉ። በደሳሳ ጎጆ እየኖሩ ዝናብ ሲመጣ የጎርፍ፣ ብርድና ዶፉ ስጋት ላይ ጥሏቸው እንደኖሩ ያነሳሉ፤ በበጋ ወራት ደግሞ የሚነፍሰው ነፋስና ሀሩሩ ጸሃይ ይፈትናቸው እንደነበር ይናገራሉ። ከእለታት አንድ ቀን ወጣቶችና ጎልማሶች ጭምር ሰብሰብ ብለው መጥተው “ቤትዎን በነፃ ልናድስልዎት ነው ሲሉኝ አላመንኳቸውም ይላሉ። የእውነታችሁን ነው አልኳቸው? አዎን ቤትዎን አፍርሰን ልንሰራልዎት ነው” ብለው አረጋገጡልኝ በማለት ሁኔታውን በደስታ እንባ ታጅበው ያስታውሳሉ። በተባለው መሰረትም በክረምቱ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የቤታቸው እድሳት ተጀምሯል። የኢዜአ ሪፖርተር በስፍራው ተገኝቶ ወይዘሮ ባሎን ባነጋገራቸው ወቅት “ሰው በሚያስፈልገኝ ጊዜ ሰዎች ሁነው የተገኙ ወገኖቼ ችግሬን ለመፍታት በአካል ተገኝተዋል፤ በጣም ደስ ብሎኛል፤ የመኖርን ተስፋ እንድሰንቅ አድርገውኛል በማለት ደስታቸውን በእንባቸው ጭምር ታጅበው ገልጸዋል። የሀመሯ እናት ቤታቸው በፍጥነት ታድሶ የሚረከቡ፣ በቀጣይም አስፈላጊው እገዛና ድጋፍ የሚደረግላቸው መሆኑን የቤቱን እድሳት ያስጀመሩት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኤካል ነትር አረጋግጠዋል። እንደ ወይዘሮ ባሎ፤ ያሉ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን የማገዝና የመደገፍ ሃላፊነት አለብን ያሉት ሃላፊው፤ የመረዳዳትና የመተጋገዝ ባህል ጎልቶ እንዲቀጥል ሁላችንም የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል። የቢሮው የማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ለወገኖቻቸውያላቸውን አለኝታነት በተግባር በማሳየታቸውም አመስግነዋል። የደቡብ ኦሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ፤ የዘንድሮ የክረምት በጎ ፈቃድ ተቋማት፣ግለሰቦች፣ወጣቶችና አዛውንቶች ሳይቀር የተሳተፉበት እና የበርካቶችን ችግር መፍታት የተቻለበት መሆኑን ተናግረዋል። የክልሉ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች የወይዘሮ ባሎን ቤት ለማደስ በመምጣታቸው አመስግነው፤ ለሌሎች ተቋማትም አርአያ የሚሆን የመልካምነት ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል። በዞኑ በተያዘው የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ቤቶችን ጨምሮ የዞኑን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆኑን ተናግረዋል። በቀጣይም በዞኑ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ ወገኖችን የመደገፍና ሰው ተኮር የልማት ስራዎችን በስፋት የማከናወን ተግባር በተጠናከረ መለኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም