ቀጥታ፡

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ ሳዳት ጀማል ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አዲስ አበባ፤ መስከረም 21/2018(ኢዜአ)፦ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እና የተለያዩ ክለቦች ግብ ጠባቂ የነበረው ሳዳት ጀማል ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል። 

ሳዳት ጀማል በገጠመው ህመም የህክምና ርብርብ ሲደረግለት ቆይቶ የህልፈተ ህይወቱ ዜና መሰማቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። 

የቀድሞ ተጫዋች እና አሰልጣኝ ሳዳት ጀማል አስከሬን ህክምናውን ሲከታተል ከነበረበት ህንድ ሀገር ነገ ጠዋት አዲስ አበባ እንደሚገባ ተገልጿል።

ግብ ጠባቂው ከብሄራዊ ቡድን እና ክለብ ቆይታው በተጨማሪ የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን የግብ ጠባቂዎች አሰልጣኝ ነበር። 

ፌዴሬሽኑ በሳዳት ጀማል የተሰማውን እጅግ ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ለቤተሰብ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና ለእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ተመኝቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም